input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
የሴት ልጅ ግርዛት አዉሮጳን ማስጋቱ የሴት ልጅ ግርዛት በተለያዩ ሃገራት ተግባራዊ እንደሚሆን ሲነገር የቆየ ጉዳይ ነዉ። |
አሁን አሁን ግን በሰዎች ከሀገር ወደሀገር መዟዟር ምክንያት ቀድሞ በማይታወቅበት አካባቢ ሁሉ እየተዳረሰ መሆኑ እየተነገረ ነዉ። |
አዉሮጳ ዉስጥ በልማድም ሆነ በባህል ያልነበረዉ ይህ ድርጊት ዛሬ የበርካቶች ስጋት ከሆነ ሰነባበተ። |
መረጃዎች እንደሚያመለክቱ አዉሮጳ ዉስጥ በየዓመቱ ታዳጊ ሴቶች ለግርዛት ይጋለጣሉ። |
ይህን ጎጂ ልማድ ለመግታት የሚንቀሳቀሱ ተቋማትም የአዉሮጳ ኅብረት የተጠናከረ ርምጃ እንዲወስድ ግፊት እያደረጉ ነዉ። |
አዉሮጳ ዉስጥ ስዊድን ናት በመጀመሪያ ሴት ልጆች ግርዛት እንዳይፈጸምባቸዉ በህግ የደነገገች አገር። |
በጎርጎሪዮሳዊዉ ዓ ም በመሠረቱት ጎበዝ በተሰኘዉ ተቋም አማካኝነትም የባህል ልዉዉጥና ማኅበራዊ እንዲሁም ጤና ነክ ጉዳዮችን የሚመለከቱ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋሉ። |
ጎበዝ የተሰኘዉ ተቋም በተለይ የሴቶችን ጤንነት በሚመለከት የሴት ልጅ ግርዛት እንዲቆም የበኩሉን ጥረት እንደሚያደርግ ነዉ የተረዳነዉ። |
የኔዘርላንድ መንግስት ግን መረጃ ማዳረሱንና ለቤተሰቦችም ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ገፍቶበታል በነገራችን ላይ በዚህ አገልግሎት ከሚሳተፉ ሶስቱ የኔዘርላንድ ዜጎች ናቸዉ። |
የሚያስከትለዉ ስቃይም በወቅቱ ሲፈጸም ብቻ ሳይሆን ለአንዳንዶች የእድሜ ልክ መሆኑንም የደረሰባቸዉን በእማኝነት የሚጠቅሱ መረጃዎች ሞልተዋል። |
ጠቅላይ ምኒስትር አብይ አሕመድ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በተለያዩ እርከኖች በሚገኙ የመንግሥት መዋቅሮች ስቅየት ይፈጸም እንደነበር ተናግረዋል። |
ምንም ይሁን ማን ሕገ መንግሥትን ማክበር አለበት የሚል እሳቤ መያዝ ያስፈልጋል። |
ኃላፊነትን የሚሰማን መንግሥት ስንሆን ደግሞ የዚህ ጉዳይ መዛነፍ ኃላፊነት መውሰድ ያለብን እኛ ነን ብለዋል። |
ሕገ መንግሥቱ የደኅንነት ተቋማት መከላከያውን ጨምሮ ከፓርቲ ገለልተኛ ሆነው ሕግ እና አገር የሚጠብቁ መሆን አለባቸው ብሎ ያስገድዳል። |
ሲሉ የጠየቁት ጠቅላይ ምኒስትሩ እንደዛ ካላደራጀንው ኢ ሕገ መንግሥታዊ በሆነ መንገድ ተቋም ፈጥረናል ማለት ነው ሲሉ ተደምጠዋል። |
ሕገ መንግሥቱ በፍርድ ቤት የታሰረ ሰው ግረፉ ጭለማ ቤት አስቀምጡ ይላል እንዴ |
ይኼን ሕገመንግሥታዊ ያልሆነ ድርጊት በእያንዳንዱ ቀበሌ በእያንዳንዱ ወረዳ በእያንዳንዱ ዞን ሲፈጸም ቆይቷል። |
ጠቅላይ ምኒስትሩ ነፍጥ አንግበው መንግሥታቸውን ለመጣል ኤርትራ የገቡ ተቃዋሚዎች እንዲመለሱ ጥሪ አቅርበዋል። |
ጠቅላይ ምኒስትሩ በንግግራቸውም ሆነ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በቀረቡላቸው ጥያቄዎች ኢትዮጵያ የገጠሟትን አንገብጋቢ ጉዳዮች አንስተዋል። |
የአገራቸው ኤኮኖሚ የገጠመውን ፈተና የፖለቲካውን ውጥንቅጥ የፍትኅ ሥርዓቱን ችግሮች ስለ ሙስናና በተለያዩ አካባቢዎች ስለሚታዩ ግጭቶች ማብራሪያ አቅርበዋል። |
ጠቅላይ ምኒስትሩ እንዳሉት በ ዓ ም የመጀመሪያ ስድስት ወራት ብቻ ኢትዮጵያ ሚሊዮን ዶላር ለዕዳ ስትከፍል ቢሊዮን ዶላር ተበድራለች። |
አጠቃላይ የአገሪቱ የብድር መጠን ደግሞ ወደ ቢሊዮን ዶላር አሻቅቧል። |
የሁለቱ ሐገራት ባለሥልጣናት ግን የሥምምነቱ ይዘት በተደጋጋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ መብራራቱ እና በዓምደ መረብ መሰራጨቱን ይናገራሉ። |
አፍሪቃ የአንጎላ ምርጫ ዘመቻ አንጎላ ከ ቀናት በኋላ አዲስ ምክር ቤት እና አዲስ ፕሬዚደንት ትመርጣለች። |
በጎርጎሮሳዊው ዓ ም ስልጣን ላይ ሲመጡ አንጎላ ከፖርቱጋል ቅኝ አገዛዝ ተላቃ ነፃነቷን ካገኘች ገና አራት ዓመቷ ነበር። |
በአንጎላ የርስበርሱ ጦርነት ከ ዓመታት በኋላ ምርጫው በ ዓም ተካሂዷል። |
የያኔው ምርጫ በሀገሪቱ ከዚያን ጊዜ በኋላ እንደተካሄዱት ምርጫዎች ሁሉ ፕሬዚደንት ዶሽ ሳንቶሽን እና ፓርቲያቸው አሸናፊዎች ሆነዋል። |
የተቃዋሚ ወገኖች ምርጫቹን እኩል እድል ያላገኙባቸው እና የመንግሥት የማጭበርበር ተግባር የታየባቸው ነው በሚል በጥብቅ ይነቅፋሉ። |
ይሁንና ምርጫውን የታዘቡ ዓለም አቀፍ ቡድኖች የምርጫውን ውጤት ሲቀበሉ ነው የታዩት። |
በዘንድሮው የአንጎላ ምርጫ በመዲናይቱ ሉዋንዳ ለሚገኙት የምክር ቤት መንበሮች ስድስት ፓርቲዎች በተፎካካሪነት ቀርበዋል። |
በምርጫው ውጤት የአብላጫውን ድምፅ በሚያገኘው ፓርቲ የእጩዎች ስም ዝርዝር ላይ ስሙ በአንደኛነት የሚቀርበው እጩ የሀገሪቱ ርዕሰ ብሔር ይሆናል። |
በዘንድሮው ምርጫ አንድ በግልጽ የሚታወቅ ጉዳይ ቢኖር ፕሬዚደንት ኤድዋርዶ ዶሽ ሳንቶሽ የሀገሪቱ መሪ እንደማይሆኑ ነው። |
በምርጫው እንደማይወዳደሩ ቀደም ሲል ካስታወቁ በኋላ ፓርቲው በመጨረሻ ባካሄደው ጉባዔው ዦዋዎ ሉሬንቾን ቀዳሚው እጩ አድርጎ ሰይሟል። |
ከምርጫው በኋላ ሉሬንቾ ቀጣዩ የአንጎላ ፕሬዚደንት መሆናቸው እንደማይቀር ማንም አልተጠራጠረም። |
የተቃዋሚ ወገን በአሁኑ ጊዜም ቢሆን በቂ የማሸነፍ እድል የለውም። |
እርግጥ በወቅቱ በሚታየው ከፍተኛ የህዝብ ብሶት የተነሳ የተቃዋሚ ወገን ከገዢው ፓርቲ የተወሰነ ድምፅ መንጠቁ አይቀርም። |
ይሁን እንጂ የተቃዋሚ ፓርቲዎች የተከፋፈሉ እና ጠንካራ መሪም የሌላቸው ናቸው። |
ምን ለመስራት እንደሚፈልጉም መልዕክታቸውን ለህዝብ በሚገባ መልኩ ማስተላለፍ አልቻሉም። |
እስካሁን እንደሚታየው በሀገሪቱ ያሉት ፓርቲዎች እኩል የመፎካከር እድል አላቸው ሊባል አይችልም። |
እርግጥ ሁሉም ፓርቲዎች በመንግሥት ራድዮ እና ቴሌቪዥን ማስታወቂያዎቻቸውን ማስተላለፍ ይችላሉ። |
ይህ ግን ብቸኛው ምሳሌ ነው ከዚህ በተረፈ ግን ፓርቲዎች በጠቅላላ በአንድ ዓይን ታይተው እኩል እድል ይሰጣቸዋል ብሎ ማሰቡ ስህተት ነው። |
ምክንያቱም ይላሉ የፓርቲው የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ንቱ ሁሌም ሲደረግ እንደቆየው ገዢው ፓርቲ ከሌሎቹ በተለየ ለራሱ ሰፊ እድል ሰጥቶዋል። |
ቴካ ንቱ ካለፉት ዓመታት ወዲህ በጀርመን የኤሰን ከተማ ሲሆን የሚኖሩት ለምርጫው ዘመቻ እረፍት ወስደው ወደ አንጎላ ሄደዋል። |
ባለፉት ምርጫዎች የተቃዋሚው ወገን በጠቅላላ ከ የምክር ቤት መንበሮች መካከል ዎቹን እንኳን አለማግኘቱ በጣም የሚያሳዝን ነው። |
ብዙ የፖለቲካ ታዛቢዎች እንደሚገምቱት በምርጫ ዘመቻ ወቅት ብዙም የማይታዩት የአንጎላ ፕሬዚደንት ዶሽ ሳንቶሽ በጠና ሳይታመሙ አልቀሩም። |
የፖርቱጋል ሳምንታዊ መጽሄት ኤስፕሬሶ ታማኝ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው እየተበላሸ የሄደው የፕሬዚደንቱ ጤንነት የአንጎላ አመራር አባላትን እጅግ አሳስቧል። |
ርዕሰ ብሔሩ ፕሬዚደንቱ አንድ ነገር ቢሆኑ ይህ ለ ኤምፒኤልኤ ድንገተኛ አይሆንበትም የዶሽ ሳንቶሽን ተተኪ በማዘጋጀት ዦአዎ ሉሬንሶን መርጧል። |
በመሆኑም ፕሬዚደንቱ ድንገት በምርጫ ዘመቻ ወቅት እንኳን ቢሞቱ ፓርቲው ችግር አያጋጥመውም። |
ከፍተኛ የመንግሥት ቦታዎችን ለመያዝ የስልጣን ሽኩቻ ሊነሳ ይችላል ባይ ናቸው። |
ምክንያቱም ኾዜ ኤድዋርዶ ዶሽ ሳንቶሽ ዋና ዋና የሚባሉትን የመንግሥት ስልጣን ቦታዎችን ለርሳቸው ታማኝ ለሆኑ ሰዎች ሰጥተዋል። |
ለምሳሌ ልጃቸው ኢዛቤል ዶሽ ሳንቶሽ የሀገሪቱን የነዳጅ ዘይት ተቋም ሶናንጎልን ወንድ ልጃቸው የመንግሥቱን የነዳጅ ዘይት መስሪያ ቤትን በኃላፊነት ይመራሉ። |
የፖሊስ የጦር ኃይሉ እና የስለላ ድርጅቱም በዶሽ ሳንቶሽ ታማኞች ነው የተያዘው። |
እነዚህ ባለስልጣናት ዶሽ ሳንቶሽ ስልጣናቸውን በሚለቁበትም ጊዜ ይህንኑ ስልጣናቸውን እንደያዙ መቆየት ይችላሉ። |
የአንጎላ ምክር ቤት በመጨረሻው ጉባዔው ወቅት ተሰናባቹ ፕሬዚደንት የሾሟቸው ባለስልጣናት እንዳይነኩ የሚያዝ አንድ ህግ በከፍተኛ ድምፅ አፅድቋል። |
ህጉን በምክር ቤት የሚወከሉት ሁለቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዩኒታ እና ካዛ ሲኤ ቢቃወሙትም ከ የምክር ቤት መንበሮች ብቻ በመያዛቸው ሕጉ አልፏል። |
የሕጉ ማለፍ በጣም አነጋጋሪ እንደነበር ዜጠኛ ኾዜ አዳልቤርቶ አስታውሷል። |
ኤድዋርዶ ዶሽ ሳንቶሽ ፕሬዚደንቱ ትተውልን የሚሄዱት ሕግ ብዙ ክርክር አስነስቶ ነበር። |
እና ለጦር ኃይሉ ለፖሊሱ እና ለስለላው ተቋም የሚፈልጓቸውን ሰዎች መሾም ይፈልጋሉ ብዬ ነው የማስበው። |
የአፍሪቃ ዋንጫ አስተናጋጅ ለሳምንታት የዘለቀ ደም አፋሳሽ አመፅ መካከለኛው አፍሪቃ የምትገኘው ሀገር ብሩንዲን አጨናንቋል። |
የሀገሪቱ ጦር ከአማፂያን ጋር እየተታኮሰ በርካታ ሰዎች መሞታቸውም ተረጋግጧል። |
ከዚህም በተጨማሪ ማንነታቸው ያልታወቁ እና የወታደር የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች በርካታ የመንግሥት ፓርቲ አባሎችን መግደላቸው ተሰምቷል። |
በሚመጣው ግንቦት እና ሰኔ ወር ብሩንዲ ውስጥ ምክር ቤታዊ እና ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይካሄዳል። |
የገዢው ፓርቲ መሪ ፒር ንኩሩንዚዛ ለሶስተኛ ዙር በፕሬዘደንትነት እቀርባለው ማለት ግጭቱን ይበልጥ አፋፍሞታል። |
የብሩንዲ ህገ መንግሥት ለአንድ መሪ የስልጣን ዘመን ቢበዛ የምርጫ ዙር ነው ያስቀመጠው። |
ጥቃቶች ሲፈፀሙ የሚታየው ልክ በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ግጭት ሲነሳ ነው። |
እንደ ቦኒምፓ ተቃዋሚዎች ገዢው መንግሥት የምርጫ ምዝገባውን እያጭበረበረ ነው ብለው ያምናሉ ይላሉ። |
የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቦኒምፓ ሲቪል ማሕበረሰቡም ቢሆን በምርጫው የምዝገባ አሠራር ደስተኛ እንዳልሆነ ነው የሚናገሩት። |
ሆን ተብሎ ተቃዋሚዎችን ለማስፈራራት እና ለማሸማቀቅ ሲባል ፍተሻ ይካሄድ ነበር። |
የመብት ተሟጋቹ ቦኒምፓ መንግሥትን የሚቃወም አስተያየት በመስጠታቸው ታስረው እንደነበር ይናገራሉ። |
ጋዜጠኞችም ቢሆኑ ነፃነት እንደሌላቸው እና ለህይወታቸው እንደሚሰጉ ነው የሚናገሩት። |
የተባለው የተቃዋሚዎች የሬዲዮ ጣቢያ ባልደረባ የሆነ አንድ ጋዜጠኛ ለዶይቸ ቬለ እንደተናገረው በቅርቡ ከተጣለበት ጥቃት ለጥቂት ነው የተረፈው። |
የመካከለኛው አፍሪቃ የግንኙነት መረብ ባልደረባ ጌዚነ አሜስ ለተቃዋሚዎች እና የመብት ተሟጋቾች የመፈናፈኛው እድል እጅግ ውስን ነው። |
ይህም ማለት ሀሳብ የመስጠት እና የመሰብሰብ መብታቸው የቀነሰ ነው። |
መንግሥት ደግሞ በሲቪል ማህበረሰብ እና የመብት ተሟጋቾች ላይ ጭቆናውን ቀጥሏል። |
በዛ ላይ መንግሥት እና ተቃዋሚዎች አንድ ዓይነት ህግ የላቸውም ይላሉ። |
ይህም ግልፅ የሚሆነው ለምሳሌ ተቃዋሚዎች ልክ ከምርጫዎቹ ሁለት ሳምንታት አስቀድመው ብቻ ነው የመሰብሰብ እና የምርጫ ዘመቻ የማካሄድ መብት ያላቸው። |
ይልቁንስ ተቃዋሚዎች የምርጫ ሂደቱን ሊያበላሹ ብሎም መንግሥትን ሊገለብጡ ነው የተነሳሱት። |
ይህም በዚህ ላይ የሚደረገው አፀፋ አመፅ ማስነሳቱን ለማየት ነው። |
እንደ ጌዚነ አሜስ ብሩንዳዊያኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ መንግሥት ቃል የሚገባውን እንደማይወጣው ተገንዝበዋል። |
አሜስ ህዝቡ ምርጫ አድክሞታል ይህ ግን የግድ በመንግሥት ምክንያት ብቻ አይደለም ይላሉ። |
እና የአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሀገሪቱን ከመቶ ማስተዳደሪያ እንደሚሸፍን ለማስታወስ እወዳለሁ። |
ጌዚነ አሜስ ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት አንድ አይነት ርምጃ ያስፈልገዋል ባይ ናቸው። |
የብሩንዲን ወቅታዊ ልማት ወጥ ለማድረግ የአውሮፓ ህብረት አንድ አይነት ውሳኔ ያስፈልጋል በግልፅ የፕረስ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ እና የመሰብሰብን ነፃነት የሚጠይቅ። |
በተለይ የሀገሪቱ መንግሥት ዝግጅቱን ከጥሩ ገፅታው ብቻ ለማሳያ እየተጠቀመበት እንደሆነ የመብት ተሟጋቾች ይናገራሉ። |
ተረኛ የነበረችው ሞሮኮ ባለፈው ህዳር ወር ነበር በምዕራብ አፍሪቃ የተዛመተውን ገዳዩን የኤቦላ ቫይረስ ፍራቻ ውድድርን እንደማታዘጋጅ ያስታወቀችው። |
በአለም አቀፍ ዘንድ ገፅታውን ለመቀየር ሲሞክር ይህ የመጀመሪያው ጊዜ አይደለም ይላሉ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል ቪክቶር ኖጉሪያ ። |
እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል ያሉ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለዓመታት የኤኳቶሪያል ጊኒን መንግሥት የሰብአዊ መብትን አያከብርም ሲሉ ተችተዋል። |
ልዩ ለግድያ የተዘጋጀ ቦታ አለ ከዚህም በተጨማሪ የፕረስም ሆነ ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት የተጨቆነ ነው። |
አምንስቲ ኢንተርናሽናል ባለፉት አመታት የፖለቲካ ተቃዋሚዎች ክስ ሳይመሰረትባቸው በዘፍቃድ እየታሰሩ እና እየተገረፉ ነው ሲል ዘግቧል። |
እንደዚሁ ድርጅት ዘገባ ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ቢያንስ አራት እስረኞች ተገድለዋል። |
ኤኳቶሪያል ጊኒ ለሁለት ሳምንታት ያክል ብቻ ነው የሞት ብይኗን ያቋረጠችው። |
ይህም የፖርቹጋል ቋንቋ ተናጋሪ ሀገራት ማህበረሰን ለመቀላቀል መስፈርቶችን ማሟላት ስለነበረባት እንደሆነ ይነገራል። |
የተፈጥሮ ሀብትን በተመለከተ ኤኳቶሪያል ጊኒ በዘይት እና በጋዝ ከአፍሪቃ ሀብታም ከሆኑት ሀገራት ተርታ ትመደባለች። |
የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከጥሬ ሀብት የውጭ ገበያ የሚገኘውን ገንዘብ ለራሳቸው በግል ባንካቸው እንደሚያስገቡ ይተቻሉ። |
ሀገሪቱ የዘይት ሀብት ስላላት የህዝቡ የነፍስ ወከፍ ገቢ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት ጋር ሲነፃጸር በአማከይ ከፍተኛ ነው። |
ይላሉ ከሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኖጉሪያ እኢአ ከ ዓም ጀምሮ ፕሬዚዳንት ቴውድሮ ኦቢያንግ ንጉማ ሀገሪቱን ይመራሉ። |
የመብት ተሟጋቹ እንደሚሉት ፕሬዚዳንቱ ይህንን አጋጣሚ ለጥሩ ስም እየተጠቀሙበት ነው። |
ነገር ግን በሌላ በኩል ስላለው የሀገሪቱም ገፅታ ትኩረት እንዲሰጥ ይጠቅማል። |
ነገር ግን ጋዜጠኞች በዚህ ጉዳይ ላይ ፍላጎቱ ካላቸው በሀገሪቱ ትኩረት ስላላገኘው ነገር ሊዘግቡ ይችላሉ። |
በርግጥ የዘንድሮው የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ሀገር ኤኳቶሪያል ጊኒ ከዚሁ ዝግጅት በምን እንደምትጠቀም በቀጣዩ ሳምንታት የሚታይ ይሆናል። |