input
stringlengths 1
130k
⌀ |
---|
በ እና ዓም በብዙ አፍሪቃውያት ሀገራት ውስጥ ተቃውሞ ተካሂዷል። |
በዚምባብዌ እና በዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ ወጣቶች በተጠሉት ፕሬዚደንቶቻቸው አንፃር በተደጋጋሚ ተቃውሞ አድርገዋል ። |
በሴኔጋል እና በቡርኪና ፋሶም ተቃዋሚዎች አምባገነን መሪዎቻቸውን ከስልጣን አባረዋል። |
በሌሎች አፍሪቃውያትሀገራት ግን ተቃውሞዎቹ ያን ያህል አልተሳኩም ይላሉ ፕሮፌሰር ዛካሪያ ማምፒሌ። |
በዚህ ፈንታ ድምፃቸውን ለማሰማት ሌላ አማራጭ ያፈላልጋሉ ማለት ነው። |
ትልቁ አደጋ ግን ተቃውሞው እንዴት እንደሚካሄድ እና ምን እንደሚያስከትል መተንበይ አለመቻሉ ነው። |
እቅዱ በአፍሪቃ የወጣቶች ሰነድ የተቀመጡትን ዓላማዎች ከግብ የማድረስ እና የወጣቱንም አቅም በፖለቲካው እና በልማቱ ዘርፍ የማጎልበት ዓላማ ይዞ ተነስቷል። |
ይሁን እንጂ የዚምባብዌ ተወላጇ የመብት ተሟጋች ሊንዳ ማዜሪሬ በሰነዱ ስለተቀመጡት አማላይ ቃላት መስማት አትፈልግም። |
ኮሚሽነር ዘይኑ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ፖሊስ ኢንጅንየሩ በሞቱበት ቦታ የነበሩ ማስረጃዎች እና መረጃዎችን የሚሰጡ ሰዎችን ይዞ እየመረመረ ነው ብለዋል። |
የአሟሟታቸውን ሁኔታ የሚያሳይ የምርመራ ውጤት ፈጥነን ለማቅረብ ርብርብ እያደረግን ነው። |
ዉይይቱ ሲያበቃ ዛሬ ከቀትር በኋላ የነበረዉን ጋዜጣዊ መግለጫ የተከታተለዉን የብራስልስ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴን በስልክ አነጋግሬዋለሁ። |
የገበያ ማዕከሉ አሁን በሚገኝበት መብራት ኃይል በተባለው ቦታ እንኳ ቃጠሎ ሲገጥመው ሁለተኛ ጊዜው ነው ፡፡ |
የገበያ ማዕከሉ አሁን በሚገኝበት መብራት ኃይል በተባለው ቦታ እንኳ ቃጠሎ ሲገጥመው ሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡ |
መልካም እንደልሆነ አጋጣሚ ደግሞ በሁለቱም የአደጋ ክስተት ንብረታቸው ተቃጥሎ የተጎዱ ወገኖች አሉ ፡፡ |
በሌላ በኩል ነጋዴዎቹ መደበኛ ስራቸውን ለመጀመር የብድር ገንዘብ እየተመቻቸ ስለመሆኑ መስማታቸውን ገልፀዋል ፡፡ |
ምንም እንኳን እስካሁን ተግባራዊ ባይደረግም ብድር ከችግሩ አገግሞ ወደ ስራ ለመግባት አያስችልም የሚሉት ነጋዴዎች መንግሥት የተለየ ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል፡፡ |
ብድር ጫና ይፈጥራል የሚል ቅሬታ ስለመነሳቱ ያነሳሁላቸው ኃላፊው አብዛኞቹ ቀደም ሲል ከተቋሙ የወሰዱትን ብድር የመለሱ መሆናቸውን አረጋግጠናል ብለዋል ፡፡ |
የገበያ ማዕከሉ መልሶ ግንባታ እየተካሄደ በሚገኝበት ቦታ ተገኝቼ እንደተመለከትኩት እንዳንዶቹ ሱቆች በር በመግጠም ሥራ ለመጀመር ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ተመልክቻለሁ ፡፡ |
ባህል ሪታ ፓንክኸርስት የኢትዮጵያ ባለውለታ አዲስ አበባ ላይ ትዳር የመሰረቱት የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪዎች በትዳር ከ ዓመታት በላይ ዘልቀዋል። |
ወ ሮ ሪታ ፓንክኸርስት በቤተ መፅሕፍት ባለሙያነታቸው በብሔራዊ ቤተ መፅሕፍት አገልግለዋል። |
በኢትዮጵያዉያን ዘንድ ሕያዉ ሆነዉ ሲታወሱ ይኖራሉ ሀገራችን ሀገሯ ህዝባችን ህዝቧ ኑሯችን ኑሮዋ ሆኖ ስታገለግለን እድሜዋን ጨርሳ ከእኛው ዘንድ አረፈች። |
ደህና ሁኚ ይላል ጋዜጠኛ የትነበርክ ታደለ በፌስቡክ ድረገፁ ያስቀመጠዉ ጽሑፍ። |
ባለቤታቸዉ አጋፋዉ የኢትዮጵያ የታሪክ ተመራማሪ የፕሮፊሰር ሪቻርድ ፓንክኸርስት ከሁለት ዓመት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸዉ ይታወሳል። |
በዚህ ዝግጅታችን የሪታ ፓንክኸርስትን የሕይወት ታሪክና በኢትዮጵያ ሳሉ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ እንቃኛለን። |
በጎርጎረሳዉያኑ ዓ ም በሩሜንያ የተወለዱት ወ ሮ ሪታ ፓንክኸርስት በ ዓመታቸዉ ከወላጆቻቸዉ ጋር ወደ እንጊሊዝ ተሰደዱ። |
ታዳጊዋ ሪታ በእንጊሊዝ ሃገር ካምብሪጅ ከተማ በሚገኝ የልጃገረዶች ት ቤት የአንደኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል። |
የከፍተኛ ትምህርታቸዉን በኦክስፎድ ዩንቨርስቲ ፈረንሳይኛና ሩስያንኛን በሚያካትተዉ የዘመናዊ ቋንቋች ጥናት በማስተርስ ዲግሪ ተመርቀዋል። |
ሪታ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን እንዳጠናቀቁ በመጀመርያ የተቀጠሩት ቻተም ሃዉስ በሚገኘዉ ፕሬስ ቤተ መፅሕፍት ዉስጥ ነዉ። |
ከዝያም ሪታ የዝያን ግዜ የፍቅር ጓደኛቸዉ ሪቻርድን እና የሪቻርድን እናት ሲልቪያ ፓንክኸርስትን ተከትለዉ ወደ ኢትዮጵያ በጎርጎረሳዉያኑ ዓ ም ይመጣሉ። |
የሪታ ፓንክኸርስት ልጅ አሉላ ፓንክኸርስት ስለእናቱ ማንነት እንዲነግረን ቀጠሮ ልንይዝ የደወልነት በለቅሶ ላይ ሳለ ነበር። |
እንድያም ሆኖ ለነገ ቀጠረንና ግንቦት የእናቱ ግባዕተ መሬት ከተፈፀመ ከአንድ ቀን በኋላ በስልክ ስለናቱ አጫወተን። |
እናቱ ሪታ በብሪታንያ የከፍተኛ ትምህርታቸዉን አጠናቀዉ በመፀሐፍ ትርጉም በቋንቋ አስተማሪነት እንዲሁም በቤተ መፅሐፍ ዉስጥ ሲሰሩ ሳለ ሪቻርድን ይተዋወቃሉ። |
ሪታ እናቴ አባቴን እንደ አጋጣሚ ለንደን ከተማ ላይ ተዋዉቃዉ ነበር። |
አባቴ ከእናቴጋር ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ መወሰኑን ነግሮ አብራ እንድትመጣ ጋበዛት እስዋም ወድያዉኑ ከሱ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ወሰነች። |
እናት እና አባትዋ ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ መወሰንዋን ሲሰሙ በጣም ሰግተዉ ነበር። |
በዚሁ ዓመት እናትና አባቴ እዚሁ አዲስ አበባ ጋብቻቸዉን ፈፀሙ። |
ሚዜዎቻቸዉ ሜትር አርቴስት አፈወርቅ ተክሌ እና መንግስቱ ለማ ነበሩ። |
አዲስ አበባ ላይ ትዳር የመሰረቱት የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪዎች በትዳር ከ ዓመታት በላይ ዘልቀዋል። |
በረጅም ዓመታት የስራ ዘመናቸው ወ ሮ ሪታ የኢትዮጵያን ባሕል የኢትዮጵያውያን ሴቶች ታሪክን እንዲሁም በኢትዮጵያ የቤተ መፅሕፍት ታሪክና ዕድገትን መርምረዋል ዘክረዋል። |
ወደ ለንደን የተሰደዱት በወቅቱ በሃገሪቱ በነበረዉ አስከፊ ሁኔታ ልጆቻችንን ለማሳደግ ከባድነ ነበር የሚል ስጋት አድሮባቸዉ ስለነበረ ነዉ። |
እግረ መንገድዋን አባቴ ሪቻርድ በሚያዘጋጀዉ ኢትዮጵያን ኦብዘርቬሽን በተባለዉ መጽሔት ላይ በጽሑፍ ታግዘዉ ነበር። |
በቤተ መጻሕፍት በተለይ የአጼ ቴድሮስ በብራና ላይ የተፃፉ ደብዳቤዎችን እና ጽሑፎችን በተመለከተ የተለያዩ ጽሑፎችን በማቅረብ አስተዋዉቃለች። |
አቶ አሉላ በቀይ ሽብር ጊዜ ወላጆቼ እኛን ይዘዉ ወደ ብሪታንያ ተሰደዉ ነበር ብለኸኛል እስቴ ስለ ስደት ታሪክ ንገረን |
ኑሮዋቸዉ ሙሉ በሙሉ እዚሁ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ዉስጥ ነበር። |
ደርግ ወደ ስልጣን በመጣ ጊዜ መጀመርያ ሁኔታዉ ተቀይሮ ብሩህ ተስፋ ይመስል ነበር ። |
አማን አብዶ የአባቴ ተማሪ ነበር በጣም ጎበዝ ተማሪ በጣም የሚያደንቀዉ ተማሪ ነበር። |
አካባቢዉ ላይ ታንኮች ገብተዉ አማን አብዶ በተገደለ ጊዜ እና ሁኔታዉ አሳሳቢ እየሆነ ሄደ። |
አባቴ እንግሊዝ ለንደን እንደገባ ስራ አልነበረዉም ከዝያም ለንደን በሚገኝ ዩንቨርስቲ የአፍሪቃ ጥናት ተቋም ዉስጥ ለማስተማር የአንድ ዓመት ኮንትራት አገኘ። |
እናቴም በቤተ መፅሐፍት ጉዳይ ሞያ በለንደን በአንድ ዩንቨርስቲ ዉስጥ ስራን ጀመረች። |
እንድያም ሆኖ ወላጆቼ ለንደን ይኑሩ እንጂ ሃሳባቸዉ ወደ ኢትዮጵያ ነበር። |
በዝያዉ በለንደን ሲኖሩ የመጀመርያዉ የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ የዓለም አቀፍ ጉባኤ ለንደን ላይ እንዲጀመር አብረዉ ነበር ስራን የሰሩት። |
ከዝያም አባቴ ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ እድልን ሲያገኝ ለመመለስ ፈለገ። |
ከዝያም አባቴ ተመልሶ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ በኢትዮጵያ ጥናት ተቋም ማገልገል ጀመረ። |
እናቴም እንዲሁ የተለያዩ የጥናት ጽሑፎችን እንዲሁም የተማሪዎች የመመረቅያ ጽሑፎችን አርትዓይ በማድረግ ሥራን መስራት እገዛን ጀመረች። |
ለምሳሌ ለኢትዮጵያዉያን ወጣት ተማሪዎች በየዉጭ ትምህርት እድል እንዲያገኙ በአንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ዉስጥ በመስራት ትልቅ እገዛን አድርጋለች። |
በተለይ ግቢዋ ዉስጥ የምትተክላቸዉን የተለያዩ ተክሎች አበቦች በጣም ትወድ ነበር። |
በዚህም ወጣት አታክልተኞችን ለማበረታታት በሚደረገዉ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስተዋጾን አበርክታለች። |
በሃገሪቱ በሚካሄድ የአትክልት ትርኢት ዉድድር ላይ በዳኝነት ወንበር ላይ ትቀመጥ ነበር። |
ወ ሮ ሪታ ፓንክኸርስት ባለፉት ስድስት አምስት ዓመታት ከባለቤታቸዉ ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ታሪካቸዉን መፃፍ ጀምረዉ ነበር። |
ኢትዮጵያን ወዳጅዋ ሲቭሊያ ፓንክኸርስት ለኢትዮጵያ ሰርተዉ እዉቀት ፍቅርን አስተላልፈዉ አልፈዋል። |
የፓንክኸርስት ቤተሰቦች ለኢትዮጵያዉያ ያበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅዖ ትዉልድ ሲማርበት እንዲሁም በስራቸዉ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ ሕያዉ ሆነዉ ሲታወሱ ይኖራሉ። |
አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከገዢው ፓርቲ የተለመደ ይትባህል ወጣ ባለ መልኩ ያቀረቡት ንግግር ብዙዎች ተስፋ እንዲሰንቁ አድርጓቸዋል፡፡ |
ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በቶሎ ማሻሻያዎችን እንዲተገብሩ የሚጠይቁ ደጋግመው የሚያነሱት አንድ ጉዳይ አለ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፡፡ |
ባለፈው የካቲት ወር የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ድንጋጌ ለስድስት ወር እንደሚቆይ ቢቀመጥም ጠያቂዎቹ ግን አሁኑኑ ይነሳ ባይ ናቸው፡፡ |
ይህንን አቋማቸው በይፋ ካሳወቁት መካከል የኢትዮጵያ መንግስት ሁነኛ አጋር የሚባሉት አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ይገኙበታል፡፡ |
የአሜሪካንን ፈለግ የተከተለ የሚመስለው የአውሮፓ ህብረትም አዋጁ በቶሎ እንዲነሳ ፍላጎቱን ገልጿል፡፡ |
ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ ቀናት ያህል ታስሮ ባለፈው ሳምንት ተለቅቋል፡፡ |
በእስር በቆየበት የፖሊስ መምሪያ ውስጥ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ጥሳችኋል በሚል ወደ ገደማ ተጠርጣሪዎች ታስረው መመልከቱን ይናገራል፡፡ |
አብዛኞቹ የተከሰሱበትን ጉዳይ ግን እንኳ በቅጡ እንደማያውቁ እና ሲያዙም ድብደባ እንደተፈጸመባቸው እንደነገሩት ይገልጻል፡፡ |
የፉሪ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር አየለ ደበላ እና የፉሪ የትራፊክ ፖሊስ ኃላፊ አለ፡፡ |
አብዛኞቹ የመጡት ከአዲስ አበባ እና ከአዲስ አበባ ዙሪያ ነው፡፡ |
ለምሳሌ አንድ አማረ የሚባል መካኒሳ ጋር የተያዘ ፌስ ቡኩን እያየ የኮሎኔል ደመቀን ፎቶ አጋርተሃል ተብሎ ነው የመጣው፡፡ |
በሙሉ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተይዘው እኛ የነበርንበት ፖሊስ ጣቢያ ያሉ ከቤታቸው ከስራ ቦታቸው እና ከመንገድ ላይ የተያዙ ናቸው፡፡ |
እነርሱ አሁን ከእኛ የተለየ የሚያደርጋቸው ከፍተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል በተያዙበት የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ቀን ላይ፡፡ |
አሁን ሲያዩን አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከመውጣቱ በፊት በአመጽ ወቅት ላይ ተሳትፎ ነበራችሁ ነው፡፡ |
ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ባህር ዳርም ተርጣሪዎች የተያዙበት ሁኔታ ተመሳሳይ እንደሆነ የዓይን እማኞች ይናገራሉ፡፡ |
የባህር ዳር ዩኒቨርስቲው መምህር እና ጓደኞቻቸው በቆዩበት ፖሊስ ጣቢያ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የታሰሩ ቁጥራቸው ወደ የሚጠጉ ሰዎች እንዳጋጠሟቸው ይናገራሉ፡፡ |
ባህር ዳር ከነማ ከደሴ ከነማ ጋር በነበረው ጨዋታ ዕለት ረብሻ ፈጥራችኋል ተብለው ተይዘው የነበሩ ወደ ወይም ልጆች ነበሩ፡፡ |
እንዲዚህ አይነት በትንንሽ ጉዳዩች ጽሁፍ በኪሳችሁ ይዛችሁ ስቴድየም ተገኝታችኋል ተብሎ የታሰሩ ልጆች ነበሩ፡፡ |
እንደዚህ አይነት ልጆች ዘጠነኛ ፖሊስ ጣቢያ ብዙ እስረኛ ነው የነበረው፡፡ |
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማስፈጸሚያ መመሪያ በመላው ሀገሪቱ የሚተገብሩ ብሎ ክልከላዎችን የዘረዘረ ሲሆን ለተወሰኑ ቦታዎች ደግሞ አራት ክልከላዎችን አስቀምጧል፡፡ |
አዋጁን እና መመሪያውን የፈተሹ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ክልከላዎቹ አሻሚ ትርጉም ያላቸው እና ግልጽነት የሚጎድላቸው ናቸው ሲሉ ይተቻሉ፡፡ |
መመሪያ ተብሎ የወጣውን የኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ስታየው ህግ በሚያረቅቁ ሰዎች ተጽፏል ብሎ ለመናገር በጣም ነው የሚያሳፍረው፡፡ |
ስለ አመክኖያዊ ትስስራቸው መሬት ላይ ሲተገበሩ ስለሚያመጡት ውጤት ምን ያህል ተጨባጭ ናቸው |
ምን ያህል ከሰው እና ከማህበረሰብ የቀን ተቀን መስተጋብር ጋር አብረው ይሄዳሉ ስለሚለው ጉዳይ ብዙም ትኩረት የተሰጠ አይመስለኝም፡፡ |
ለህግ ደንቦች አረቃቀቅ ምንም ክብር በሌለው ሁኔታ የተረቀቀ አይነት ነው፡፡ |
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ ያሉ ድንጋጌዎች በስፋት የተቀመጡ እና አሻሚዎች የሆኑ ናቸው፡፡ |
ምርመራ ለምን ያህል ጊዜ ያህል ይካሄዳል የሚሉት እንደዚሁ የሉም፡፡ |
ታሳሪዎቹ አላግባብ መታሰራቸውን የት አቤት ማለት እንደሚችሉ ለማወቅ ተቸግረዋል። |
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወቅት የሚወሰዱ እንደዚህ አይነት እርምጃዎችን የመከታተል እና የመቆጣጠር ተግባር ያለው መርማሪ ቦርድ ግን ስራየን እያከናወነንኩ ነው ይላል። |
መርማሪ ቦርዱ በአዋጁ የሚወሰዱ እርምጃዎች ኢ ሰብዓዊ መሆናቸውን ካመነ እርምጃውን እንዲያስተካክል ለኮማንድ ፖስቱ ሀሳብ እንደሚሰጥ ተደንግጓል፡፡ |
ቦርዱ ከተሰጠው ስልጣን እና ተግባር አንዱ በአዋጁ ምክንያት የታሰሩ ግለሰቦችን እና የታሰሩበትን ምክንያት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ይፋ ማድረግ ነው፡፡ |
አራማጆች አክቲቪስቶች ግን በየአካባቢው የታሰሩ ሰዎች በቦርዱ ከተጠቀሰው በጣሙኑ እንደሚልቅ ይሟገታሉ። |
የቦርዱ ሰብሳቢ በባለፈው ሳምንት መግለጫቸው ከህብረተሰቡ ከሚደርሷቸው ጥቆማዎች ብዙዎቹ ሰዎች እየታሰሩ ያሉት በቂም በቀል ነው የሚል እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ |
ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በስልጣን ላይ በቆየባቸው ዓመታት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያውጅ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜው ነው፡፡ |
ባለፈው ዓመት ታውጆ የነበረው ተመሳሳይ ድንጋጌ ለ ወር ከቆየ በኋላ እንዲነሳ ተደርጓል፡፡ |
በሚኒስትሮች ምክር ቤት አማካኝነት በየካቲት የታወጀው የአሁኑ ድንጋጌ ሕገ መንግስቱን እና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከአደጋ ለመከላከል በሚል እንደነበር ይታወሳል፡፡ |
የአምቦው ዩኒቨርስቲ መምህር ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ነባራዊ ሁኔታ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም ባይ ናቸው። |
መቀመጫቸውን ዋሽንግተን ዲሲ ያደረጉት የሰብዓዊ መብቶች ህግ ባለሙያው አቶ ዩሴፍ ተመሳሳይ አስተያየት አላቸው፡፡ |
በዓረብኛ ፊደል የተገኙ የኢትዮጵያ የፅሁፍ ቅርሶች መግቢያ ለርስዎ የምናቀርበውን አገልግሎታችንን ለማሻሻል በማሰብ ኩኪዎችን እንጠቀማለን። |