label
class label 4
classes | headline
stringlengths 17
80
| text
stringlengths 1
16.8k
| headline_text
stringlengths 28
16.8k
| url
stringlengths 36
49
|
---|---|---|---|---|
3politics
| "ህይወቴን እንዳጣ የሚደረግ ሙከራ ነው" አቶ ልደቱ አያሌው | ለሦስተኛ ጊዜ ህክምና ለማግኘት ወደውጪ አገር እንዳይሄዱ የተከለከሉት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ድርጊቱ በህክምና እጦት "ህይወቴን እንዳጣ የሚደረግ ሙከራ ነው" አሉ። አቶ ልደቱ አያሌው ለቢቢሲ ይህንን የተናገሩት ለህክምና ወደ ውጪ አገር ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ ለሦስተኛ ጊዜ ከተስተጓጎለና ፓስፖርታቸው ከተወሰደ በኋላ ነው። ያለባቸው የጤና ችግር በአገር ውስጥ ሊታከም የማይችል "የልብ ጉዳይ ነው። ከልብም የደም ቧንቧ መዘጋት [አርተሪ ብሎኬጅ] ነው። ስለዚህ ተገቢውን ህክምና ካላገኘሁ ለህይወቴ የሚያሰጋ ነው" ነው ሲሉ ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ከዓመት ከስምንት ወር በፊት ተመሳሳይ ህክምና ማግኘታቸውን ገልጸው፤ በአሁኑ ጉዟቸው የተደረገላቸው ህክምና በትክክል ስለመስራቱ ለማረጋገጥና ተጨማሪ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ነበር። የጤና ችግራቸው ያለህክምና የሚድን ስላልሆነ እንዲሁም የሚያስፈልጋቸው ህክምና ደግሞ በአገር ውስጥ ስለሌለ ያሉበት ሁኔታ "ለህይወቴ አስጊ" ነው ብለዋል። በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለወራት በእስር ላይ የቆዩት አቶ ልደቱ አያሌው ባለባቸው የጤና ችግር ምክንያት እራሳቸውን ከዚህ በፊት ሲያደርጉት ከነበረው ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ማግለላቸውን በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል። የተደረገባቸውን ተደጋጋሚ የጉዞ ክልከላ በተመለከተ "ምን ያህል ያለአግባብ ህይወቴን እንዳጣ እየተሞከረ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። እኔም ከዚህ የተለየ ትርጉም ልሰጠው አልችልም" ብለዋል። አቶ ልደቱ ካለባቸው የልብ ህመም ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት የተደረገላቸው ህክምና ያለበት ሁኔታን ለማወቅና ተጨማሪ ተከታይ ህክምና ለማግኘት ነበር ወደ አሜሪካ ሊጓዙ የነበረው። ሐሙስ ዕለት ወደ አሜሪካ ለመሄድ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያቀኑት አቶ ልደቱ ሻንጣቸውን አስረክበው ወደ አውሮፕላን ለመሳፈር የመጨረሻ ፓስፖርት በሚያሳዩበት ጊዜ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ እንዳለባቸው በመግለጽ እንደመለሷቸው ተናግረዋል። በዚህ ጊዜ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የተጻፈ ደብዳቤን ቢያሳዩም "የፍርድ ቤት እገዳ ስላለብህ መውጣት አይችሉም" እንደተባሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ከአገር እንዳይወጡ በኢሚግሬሽን ሠራተኞች ተከልክለው እንደነበር መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሁለቱንም ጊዜ ጉዞ እንዳያደርጉ የተከለከሉት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሆኑን ገልጸዋል። ከአገር እንዳይወጡ በተከለከሉበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቤቱታ አቅርበው የነበሩት አቶ ልደቱ፤ ክልከላው በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አለመፈጸሙን መግለጹ ይታወሳል። የደኅንነት መሥሪያ ቤቱን ምላሽ ተከትሎም የነበረው ችግር ተፈትቷል በሚል ጉዞ ለማድረግ መነሳታቸውን የሚጠቅሱት አቶ ልደቱ፤ ነገር ግን ውጤቱ ቀደም ካሉት ጉዞዎች ጋር ተመሳሳይ ሆኗል ብለዋል። ሐሙስ ዕለት ጉዞ ማድረግ እንደማይችሉ በተነገራቸው ጊዜም ለኮሚሽኑ ዋና ኃላፊ ለዶክተር ዳንኤል በቀለ በስልክ እንዳሳወቁና እሳቸውም የኢሚግሬሽን ባለስልጣናትን ለማነጋገር መሞከራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶ/ር ዳንኤልም ያገኙት መልስ "መውጣት አይችልም፤ የፍርድ ቤት እገዳ አለበት " የሚል ነበር ያሉት አቶ ልደቱ ከዚህ በኋላ ለጉዞ አስረክበው የነበረውን ሻንጣቸውን በመቀበል መመለሳቸውን ገልጸዋል። ቀደም ባለው የጉዞ ክልከላ ወቅት "የመለሱኝ ብሔራዊ ደህንነቶች ናቸው። ሁለቱንም ጊዜ ሲመልሱኝ የፍርድ ቤት እገዳ አለብህ፤ መውጣት አትችልም እያሉ ነው። የት ነው የፍርድ ቤት እገዳ ያለብኝ ስላቸው የሚነግሩኝ ነገር የለም።" ብለዋል። ለሦስተኛ ጊዜ ለህክምና የሚያደርጉት ጉዞ በማያውቁት ምክንያት መስተጓጎሉን የሚናገሩት አቶ ልደቱ፤ "ሁለት ጊዜ ከአገር እንዳልወጣ የከለከለኝ ብሔራዊ ደኅንነት ነበር" ብለዋል። ቢቢሲ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት እንዲሁም ከኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለአሁን አልተሳካም። በአንደበተ ርቱዕነታቸው የሚታወቁት አቶ ልደቱ አያሌው ለረጅም ዓመታት በተቃውሞው ፖለቲካ ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በተለይ በአወዛጋቢው የ1997 ምርጫ ወቅት በነበራቸው ሚና ከፍ ያለ እውቅና አግኝተዋል። አቶ ልደቱ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ የተለያዩ ክሶች ቀርበውባቸው በኦሮሚያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ለበርካታ ወራት የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ከቀረቡባቸው ክሶች ነጻ ተብለው መለቀቃቸው ይታወሳል። | "ህይወቴን እንዳጣ የሚደረግ ሙከራ ነው" አቶ ልደቱ አያሌው ለሦስተኛ ጊዜ ህክምና ለማግኘት ወደውጪ አገር እንዳይሄዱ የተከለከሉት ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌው ድርጊቱ በህክምና እጦት "ህይወቴን እንዳጣ የሚደረግ ሙከራ ነው" አሉ። አቶ ልደቱ አያሌው ለቢቢሲ ይህንን የተናገሩት ለህክምና ወደ ውጪ አገር ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ ለሦስተኛ ጊዜ ከተስተጓጎለና ፓስፖርታቸው ከተወሰደ በኋላ ነው። ያለባቸው የጤና ችግር በአገር ውስጥ ሊታከም የማይችል "የልብ ጉዳይ ነው። ከልብም የደም ቧንቧ መዘጋት [አርተሪ ብሎኬጅ] ነው። ስለዚህ ተገቢውን ህክምና ካላገኘሁ ለህይወቴ የሚያሰጋ ነው" ነው ሲሉ ጨምረው ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ከዓመት ከስምንት ወር በፊት ተመሳሳይ ህክምና ማግኘታቸውን ገልጸው፤ በአሁኑ ጉዟቸው የተደረገላቸው ህክምና በትክክል ስለመስራቱ ለማረጋገጥና ተጨማሪ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ነበር። የጤና ችግራቸው ያለህክምና የሚድን ስላልሆነ እንዲሁም የሚያስፈልጋቸው ህክምና ደግሞ በአገር ውስጥ ስለሌለ ያሉበት ሁኔታ "ለህይወቴ አስጊ" ነው ብለዋል። በተለያዩ የወንጀል ድርጊቶች ተጠርጥረው ለወራት በእስር ላይ የቆዩት አቶ ልደቱ አያሌው ባለባቸው የጤና ችግር ምክንያት እራሳቸውን ከዚህ በፊት ሲያደርጉት ከነበረው ንቁ የፖለቲካ ተሳትፎ ማግለላቸውን በቅርቡ መግለጻቸው ይታወሳል። የተደረገባቸውን ተደጋጋሚ የጉዞ ክልከላ በተመለከተ "ምን ያህል ያለአግባብ ህይወቴን እንዳጣ እየተሞከረ እንደሆነ የሚያሳይ ነው። እኔም ከዚህ የተለየ ትርጉም ልሰጠው አልችልም" ብለዋል። አቶ ልደቱ ካለባቸው የልብ ህመም ጋር በተያያዘ ከዚህ በፊት የተደረገላቸው ህክምና ያለበት ሁኔታን ለማወቅና ተጨማሪ ተከታይ ህክምና ለማግኘት ነበር ወደ አሜሪካ ሊጓዙ የነበረው። ሐሙስ ዕለት ወደ አሜሪካ ለመሄድ ወደ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ያቀኑት አቶ ልደቱ ሻንጣቸውን አስረክበው ወደ አውሮፕላን ለመሳፈር የመጨረሻ ፓስፖርት በሚያሳዩበት ጊዜ ከአገር እንዳይወጡ እገዳ እንዳለባቸው በመግለጽ እንደመለሷቸው ተናግረዋል። በዚህ ጊዜ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት የተጻፈ ደብዳቤን ቢያሳዩም "የፍርድ ቤት እገዳ ስላለብህ መውጣት አይችሉም" እንደተባሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አቶ ልደቱ ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ከአገር እንዳይወጡ በኢሚግሬሽን ሠራተኞች ተከልክለው እንደነበር መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ሁለቱንም ጊዜ ጉዞ እንዳያደርጉ የተከለከሉት በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት መሆኑን ገልጸዋል። ከአገር እንዳይወጡ በተከለከሉበት ጊዜ ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቤቱታ አቅርበው የነበሩት አቶ ልደቱ፤ ክልከላው በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አለመፈጸሙን መግለጹ ይታወሳል። የደኅንነት መሥሪያ ቤቱን ምላሽ ተከትሎም የነበረው ችግር ተፈትቷል በሚል ጉዞ ለማድረግ መነሳታቸውን የሚጠቅሱት አቶ ልደቱ፤ ነገር ግን ውጤቱ ቀደም ካሉት ጉዞዎች ጋር ተመሳሳይ ሆኗል ብለዋል። ሐሙስ ዕለት ጉዞ ማድረግ እንደማይችሉ በተነገራቸው ጊዜም ለኮሚሽኑ ዋና ኃላፊ ለዶክተር ዳንኤል በቀለ በስልክ እንዳሳወቁና እሳቸውም የኢሚግሬሽን ባለስልጣናትን ለማነጋገር መሞከራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዶ/ር ዳንኤልም ያገኙት መልስ "መውጣት አይችልም፤ የፍርድ ቤት እገዳ አለበት " የሚል ነበር ያሉት አቶ ልደቱ ከዚህ በኋላ ለጉዞ አስረክበው የነበረውን ሻንጣቸውን በመቀበል መመለሳቸውን ገልጸዋል። ቀደም ባለው የጉዞ ክልከላ ወቅት "የመለሱኝ ብሔራዊ ደህንነቶች ናቸው። ሁለቱንም ጊዜ ሲመልሱኝ የፍርድ ቤት እገዳ አለብህ፤ መውጣት አትችልም እያሉ ነው። የት ነው የፍርድ ቤት እገዳ ያለብኝ ስላቸው የሚነግሩኝ ነገር የለም።" ብለዋል። ለሦስተኛ ጊዜ ለህክምና የሚያደርጉት ጉዞ በማያውቁት ምክንያት መስተጓጎሉን የሚናገሩት አቶ ልደቱ፤ "ሁለት ጊዜ ከአገር እንዳልወጣ የከለከለኝ ብሔራዊ ደኅንነት ነበር" ብለዋል። ቢቢሲ ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት እንዲሁም ከኢሚግሬሽን መሥሪያ ቤት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ለአሁን አልተሳካም። በአንደበተ ርቱዕነታቸው የሚታወቁት አቶ ልደቱ አያሌው ለረጅም ዓመታት በተቃውሞው ፖለቲካ ውስጥ በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ በተለይ በአወዛጋቢው የ1997 ምርጫ ወቅት በነበራቸው ሚና ከፍ ያለ እውቅና አግኝተዋል። አቶ ልደቱ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ የተለያዩ ክሶች ቀርበውባቸው በኦሮሚያ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ለበርካታ ወራት የቆዩ ሲሆን በመጨረሻም ከቀረቡባቸው ክሶች ነጻ ተብለው መለቀቃቸው ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56778226 |
2health
| ሕንድ በኮቪድ-19 ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ ልትከፍል ነው | የሕንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግሥት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ ሰዎች ቤተሰቦች እከፍለዋለው ያለውን ካሳ ማጽደቁ ተሰምቷል። ለእያንዳንዱ ሟች የሚከፈለው የካሳ መጠን ደግሞ 50 ሺ ሩፒ ወይም 647 ዶላር መሆኑ ተገልጿል። በሕንድ እስካሁን ባለው ይፋዊ መረጃ መሰረት 447 ሺ ዜጎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ባለሙያዎች እንደሚሉት የሟቾች ቁጥር መንግስት ከሚለው በአስር አጥፍ ሊበልጥ ይችላል። የሕንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃላፊው ኤምአር ሻህ ሰኝ ዕለት ''የሟቾች ወራሽ አልያም የቅርብ ዘመድ ካሳውን ያገኛል'' ብለዋል። ፍርድ ቤቱ አክሎም የሟቾች ቤተሰቦች ተገቢውን ማስረጃና ሰነድ ለመንግሥት ካስገቡ በኋላ በሚቀጥሉት 30 ቀናት ውስጥ የካሳ ክፍያውን ከመንግስት ማግኘት ይችላሉ ብሏል። ባለፈው ሰኔ ወር ጠበቆችና የመብት ተቆርቋሪዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ እንዲሳተፍና በኮቪድ-19 ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰዎች ካሳ እንዲከፈል ፊርማ አሰባስበው ነበር። በወቅቱም የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ብሄራዊ አደጋ ተብሎ ከታወጀ ለተጎጂዎች መንግሥት ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት የብሄራዊ አደጋ አመራር መመሪያን በመጥቀስ ተከራክረዋል። መመሪያው እንደሚለው በማንኛው ብሄራዊ አደጋ ወቅት ተጎጂዎች ከመንግስት እስከ 400 ሺ ሩፒ የሚደርስ ካሳ ሊከፈላቸው እንደሚገባ ተጠቅሷል። "መንግስት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ገንዘብ እንዳወጣ እናውቃለን። ነገር ግን በመመሪያው መሰረት መንግስት 400 ሺ ሩፒ ለተጎጂዎች መክፈል ነበረበት። ወይም ደግሞ ለደሃ ማህበረሶች ከፍተኛውን የገንዘብ መጠን መስጠትና ደህና ኑሮ ላላቸው ደግሞ ዝቅተኛውን መስጠት ይቻል ነበር" ብለዋል ፊርማውን ሲያሰባስቡ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ጋወራቭ ባንሳል። የፌደራል መንግስት እንደሚለው የካሳ ክፍያው የሚፈጸመው በኮቪድ-19 ምክንያት የቤተሰብ አባል ለሞተባቸው ሰዎች ሲሆን ግለሰቡ አልያም ግለሰቧ በቫይረሱ ምክንያት ስለመሞታቸው ደግሞ ተገቢው ማስረጃ መቅረብ አለበት። የካሳ ክፍያውን የሚፈጽሙት ደግሞ የግዛት መንግስታት ናቸው ተብሏል። ኬራላ እና ራጃስታን የተባሉት ግዛቶች ደግሞ የካሳ ክፍያው ከፍተኛ ጫና እንደሚያደርስባቸው በመግለጽ የፌደራሉ መንግስት ክፍያውን እንዲፈጽም ጠይቀዋል። እንደ ካርናታካ ያሉት ግዛቶች ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች እስከ 100 ሺ ሩፒ የሚደርስ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። እስካሁን 16 ቤተሰቦች የካሳ ክፍያውን እንዳገኙ የአካባቢው ገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። | ሕንድ በኮቪድ-19 ለሞቱ ሰዎች ቤተሰቦች ካሳ ልትከፍል ነው የሕንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መንግሥት በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ ሰዎች ቤተሰቦች እከፍለዋለው ያለውን ካሳ ማጽደቁ ተሰምቷል። ለእያንዳንዱ ሟች የሚከፈለው የካሳ መጠን ደግሞ 50 ሺ ሩፒ ወይም 647 ዶላር መሆኑ ተገልጿል። በሕንድ እስካሁን ባለው ይፋዊ መረጃ መሰረት 447 ሺ ዜጎች በኮሮናቫይረስ ምክንያት ሕይወታቸው አልፏል። ነገር ግን ባለሙያዎች እንደሚሉት የሟቾች ቁጥር መንግስት ከሚለው በአስር አጥፍ ሊበልጥ ይችላል። የሕንድ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኃላፊው ኤምአር ሻህ ሰኝ ዕለት ''የሟቾች ወራሽ አልያም የቅርብ ዘመድ ካሳውን ያገኛል'' ብለዋል። ፍርድ ቤቱ አክሎም የሟቾች ቤተሰቦች ተገቢውን ማስረጃና ሰነድ ለመንግሥት ካስገቡ በኋላ በሚቀጥሉት 30 ቀናት ውስጥ የካሳ ክፍያውን ከመንግስት ማግኘት ይችላሉ ብሏል። ባለፈው ሰኔ ወር ጠበቆችና የመብት ተቆርቋሪዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ በጉዳዩ ላይ እንዲሳተፍና በኮቪድ-19 ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ሰዎች ካሳ እንዲከፈል ፊርማ አሰባስበው ነበር። በወቅቱም የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ብሄራዊ አደጋ ተብሎ ከታወጀ ለተጎጂዎች መንግሥት ካሳ የመክፈል ግዴታ እንዳለበት የብሄራዊ አደጋ አመራር መመሪያን በመጥቀስ ተከራክረዋል። መመሪያው እንደሚለው በማንኛው ብሄራዊ አደጋ ወቅት ተጎጂዎች ከመንግስት እስከ 400 ሺ ሩፒ የሚደርስ ካሳ ሊከፈላቸው እንደሚገባ ተጠቅሷል። "መንግስት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ገንዘብ እንዳወጣ እናውቃለን። ነገር ግን በመመሪያው መሰረት መንግስት 400 ሺ ሩፒ ለተጎጂዎች መክፈል ነበረበት። ወይም ደግሞ ለደሃ ማህበረሶች ከፍተኛውን የገንዘብ መጠን መስጠትና ደህና ኑሮ ላላቸው ደግሞ ዝቅተኛውን መስጠት ይቻል ነበር" ብለዋል ፊርማውን ሲያሰባስቡ ከነበሩት ሰዎች መካከል አንዱ የሆኑት ጋወራቭ ባንሳል። የፌደራል መንግስት እንደሚለው የካሳ ክፍያው የሚፈጸመው በኮቪድ-19 ምክንያት የቤተሰብ አባል ለሞተባቸው ሰዎች ሲሆን ግለሰቡ አልያም ግለሰቧ በቫይረሱ ምክንያት ስለመሞታቸው ደግሞ ተገቢው ማስረጃ መቅረብ አለበት። የካሳ ክፍያውን የሚፈጽሙት ደግሞ የግዛት መንግስታት ናቸው ተብሏል። ኬራላ እና ራጃስታን የተባሉት ግዛቶች ደግሞ የካሳ ክፍያው ከፍተኛ ጫና እንደሚያደርስባቸው በመግለጽ የፌደራሉ መንግስት ክፍያውን እንዲፈጽም ጠይቀዋል። እንደ ካርናታካ ያሉት ግዛቶች ደግሞ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ቤተሰቦች እስከ 100 ሺ ሩፒ የሚደርስ የካሳ ክፍያ ለመፈጸም መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። እስካሁን 16 ቤተሰቦች የካሳ ክፍያውን እንዳገኙ የአካባቢው ገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58799031 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ 'በጦርነት አድጌ በወረርሽኝ አልሞትም" | "በጦርነት ነው ያደግኩት፤ በወረርሸኙ አልሞትም።" ማርጋሬት አልኮክ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ጀርመን በእንግሊዝ ላይ ያደረሰችው "ዘ ብሊትዝ" ተብሎ የሚጠራው የቦምብ ጥቃት በመጠለያ ውስጥ ሆነው ያን ፈታኝ ጊዜ አልፈውታል ። ከዚያም ባሕር፣ ውቅያኖስ ተሻግረው ወደ አውስትራሊያ ተወሰዱ። ላኪ ማርቲን እባላለሁ፤ የ89 ዓመቷ ማርጋሬት አያቴ (ናና) ናት ያንን የጦርነት ጊዜ በጨለምተኝነት አታወሳውም፤ በተቻለ መጠን ሳቅና ቀልድ በተሞላበት መልኩ ነው ጦርነትን የመሰለ አስከፊ ነገር የምታወራው። ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝም እንዲሁ በቀልድ ነው የምታወራው። "አንዳንዴ በምን ተአምር ነው እንዲያው እዚህ ወረርሽኝ ላይ የጣለኝ፤ እንዴት በህይወት እያለሁ ይሄን አየሁ" ትለኛለች ስደውልላት። ከዚያም ትቀጥልና "የከፋ ነገር ስላየሁ ወረርሽኙ ብዙም አያስጨንቀኝም" ትለኛለች። በጥር ወር ላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአውስትራሊያ ሲያጋጥም አያቶቼ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል በመሆናቸው ወላጆቼም ሆነ እኔ ከበሽታው እንደሚጠበቁና ምንም እንደማይነካቸው እርግጠኛ ነበርን። ነገር ግን ግምታችን የተሳሳተ ነበር በአምስት ወራት ውስጥ በአውስትራሊያ ከተከሰተው 247 ሞቶች መካከል 156ቱ በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በርካታ አረጋውያንም ሊያልቁ የቻሉበት ምክንያትም የጤና ሥርዓቱ እነዚህን ተጋላጭ የኅብረተሰቡ ክፍሎችን ችላ በማለቱ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው። በተለያየ የስልጣን እርከን ደረጃ ላይ የሚገኙ ኃላፊዎችም ለዚህ ክፍተት መፈጠር ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው ነው። በአውስትራሊያ ውስጥ 180 ሺህ ያህል አረጋውያን በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ይኖራሉ። እነዚህ ማዕከላት በእርዳታ ድርጅቶች፣ በግል ኩባንያዎችና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚተዳደሩ ናቸው። የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ እነዚህም ማዕከላት በፍጥነት ነው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያስገቧቸው። አንዳንዶቹም መንግሥት ካስተላለፈው መመሪያም በማፈንገጥ እንግዶች እንዳይጎበኙ አረጋውያኑም በክፍላቸው ብቻ እንዲቆዩና ሌሎች እንቅስቃሴዎችንም እንዳያደርጉ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ማርጋሬት ያሉበት ማዕከል ለተወሰነ ጊዜ ጎብኚዎችን ቢከለክሉም በግቢው ውስጥ እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱና መውጣትም ስለፈቀዱላቸው እድለኛ ናቸው። ሌላኛዋ የ87 ዓመቷ አያቴ፤ የእሷም ስም በሚገርም ሁኔታ ማርጋሬት ነው፤ ከመጋቢት ጀምሮ በክፍሏ ውስጥ ናት። ማዕከሉ በሜልቦርን የሚገኝ ሲሆን፤ ይህች ከተማም የወረርሽኙ ማዕከል ሆናለች። አያቴ በክፍሏ ተወስና ነው ያለችው፤ የሚፈቀድላት በኮሪደሩ ላይ እንድትራመድ ብቻ ነው። ለወራትም ያለ ጎብኚ ብቻዋን ትበላለች፤ ወንበሯ ላይ ቁጭ ብላ ነው የምታሳልፈው። እንዲያም ሆኖ በዚህ አስጨናቂ ሰዓት በማዕከሉ እያገለገሉ ላሉ ሠራተኞች ምስጋናዋ ከፍ ያለ ነው። "እንዲህ ተዘግቶ መቀመጥ ከባድ ቢሆንም ተቀብየዋለሁ፤ ከሁሉ በላይ ለእኔ ደኅንነትም ነው" ትለናለች። "ብዙም አልጨነቅም። ቤተሰቦቼን አለማየቴ ከባድ ቢሆንም እዚህ አይደሉም ማለት ግን አይወዱኝም ማለት አይደለምም" በማለት ስሜታችንን ትነካዋለች። እሷ ያለችበትን ማዕከል የሚያስተዳድረው ኩባንያ በሁሉም ነገር ዝግጁ እንደሆነ አሳውቆናል። ጥብቅ የሆነ የጽዳት ቁጥጥርን ጨምሮ፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በከፍተኛ መጠን አከማችቷል። ነገር ግን በተለያዩ ሁለት ግዛቶች የሚገኙ ማዕከላት የቫይረሱን መዛመት መቆጣጠር አቅቷቸው በርካታ አረጋውያን ረግፈዋል፤ ይህም ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው ልብ ሰባሪ ሆኗል። እነዚህ አረጋውያን በቫይረሱ በቀላሉ እንደሚጠቁና፣ ተጋላጭም እንደሆኑ ማወቅ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። በርካታዎቹ አረጋውያን ሌላ ተደራራቢ ህመሞች ያሉባቸው ሲሆኑ በማዕከላቱም ውስጥ ያለው የህክምና አገልግሎት የተወሰነ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የማዕከሉ ሠራተኞችም በተለያዩ ቦታዎች ከመስራታቸውም አንፃር ቫይረሱን በቀላሉ ያዛምታሉ። በየካቲት ወር ላይ በአውሮፓ በሚገኙ ማዕከላት ውስጥ ያሉ አረጋውያን በሚያሰቅቅ ሁኔታ እንደ ቅጠል እየረገፉ እንደሆነ ታሪኮች መውጣት ጀመሩ። ይህም ሁኔታ በአውስትራሊያ ሊያጋጥም እንደሚችል አገሪቷ ማወቅ ነበረባት የሚሉት በሞናሽ ዩኒቨርስቲ የጤና ሕግ ክፍል ኃላፊ ጆ ኢብራሂም ናቸው። "የአውስትራሊያ ምላሽ በቂ አልነበረም። ለሚመጣው ነገር በሙሉ ዝግጁ አልነበረችም እናም አሁን የተፈጠረው ክስተት ሊያስደንቀን አይገባም" ይላሉ ። "ብዙ ሰዎች ይህ መሆኑ አይቀሬ ነበር ሲሉ ይሰማል። ይሄ ግን ትክክለኛ አይደለም፤ ምክንያቱም ምንም ማድረግ አንችልም ነበር የሚለውን ትርጉም ስለሚሰጥ ነው። የኮሮናቫይረስ በአረጋውያን ላይ ምን ያህል አደጋ እንደደቀነ ከግምት ውስጥም አላስገባነውም። በሌሎች አገሮች ላይ እያለቁ የነበሩትንም አረጋውያን መረጃዎች አላጤንነውም" ይላሉ። በመጋቢት ወር ላይ በሲድኒ የሚገኝ ዶሮቲ ሄንደርሰን ሎጅ የተባለ የአረጋውያን ማዕከል ሠራተኛ በኮሮናቫይረስ መያዟ ተረጋገጠ፤ በግንቦት ወርም 21 በማዕከሉ የሚኖሩ አረጋውያንና ሠራተኞችም ተያዙ። ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ ሞቱ። ሌላ እንዲሁ በሲድኒ ውስጥ የሚገኝ ኒውማርች የተባለ ማዕከልም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ህሙማንን ወደ ጤና ማዕከል ከመላክ ይልቅ ክፍላቸው ውስጥ እንዲዘጉ አደረገ። ማዕከሉ የሠራተኞች ዕጥረት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችም በበቂ ሁኔታ አልነበሩትም። ይህንንም ተከትሎ 19 አረጋውያን ሲሞቱ በርካቶችም በቫይረሱ ተያዙ። የአረጋውያኑ መሞት በርካታ ጥያቄዎችን ቢያጭርም ይህ ለምን እንደተከሰተ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አካል አልተገኘም። አሁንም ከክስተቱ ያልተማረችው አውስትራሊያ አረጋውያኗን በኮሮናቫይረስ እያጣች ነው። የቪክቶሪያ ግዛት እንደ አዲስ ወረርሽኙ እያገረሸባት ሲሆን ከማህበረሰቡ ስርጭት በተጨማሪ የአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቁ ነው። በአሁኑ ወቅትም 1 ሺህ 200 የሚሆኑ አረጋውያን በ97 ማዕከላት ውስጥ መያዛቸው ተረጋግጧል። ፕሮፌሰር ኢብራሂም እንደሚሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ብቻቸውን ቫይረሱን መግታት አይችሉም። "በሽታው ቢያጋጥም ምን ማድረግ አለብን የሚለው ላይ የተቀመጠ ግልጽ ያለ ፖሊሲም ሆነ ይህንንም መቆጣጠር የሚችል መዋቅር አልተዘረጋም" ይላሉ። የአረጋውያኑን የእንክብካቤ ማዕከላት በቀጥታ የሚመለከተው የፌደራል መንግሥቱን ቢሆንም ወረርሽኙን ደግሞ በየግዛቱ ያሉ የኅብረተሰብ ጤና ኃላፊዎች በበላይነት ይቆጣጠሩታል። "በዚህም ምክንያቱ ኃላፊነቱ የማን ነው በሚል መወዛገብ ተፈጠረ። ይሄ ብቻ አይደለም የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህክምናው መሰጠት ያለበት ሆስፒታል ወይስ ቤታቸው ውስጥ የሚለውም ላይ ውሳኔ ሳያገኝ እንዲሁ እያወዛገበ ነበርም" በማለት ያስረዳሉ። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኔዝ በዚህ ሳምንት ሰፋ ያለ ምርመራና ኃላፊነት ሊወስዱ የሚባቸውም አካላት እንዲጠየቁ ተናግረዋል። "በኒውማርች እንክብካቤ ማዕከል ካጋጠመን ክስተት ለምን አልተማርንም? ይህ የተከሰተው ከወራት በፊት ነበር" በማለትም ይጠይቃሉ። በሜልቦርን የግዛቲቷና የፌደራል ኤጀንሲዎች ተጣምረውም በቪክቶሪያ የተከሰተውን የወረርሽኝ ቀውስ ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው። ለፕሮፌሰር ኢብራሂም ግን ዋናው ነገር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በአውስትራሊያ የሚገኙ የእንክብካቤ ማዕከላት ሁኔታ ሊገመገም እንዲሁም ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ይላሉ። "በዚህም መንገድ ነው የትኞቹ ማዕከላት አደጋ ውስጥ እንዳሉ የምንረዳው" የሚሉት ፕሮፌሰሩ አክለውም "ከዚያ በመቀጠልም ያለምንም ማንገራገር ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድ ይገባል" በማለትም ምክራቸውን ለግሰዋል። በእንክብካቤ ማዕከላቱ የተፈጠረውንም ሁኔታ የሚያጣራ የመንግሥት ቡድንም ተቋቁሟል። ከተለያዩ ቦታዎች የተገኙ መረጃዎች እንደሚያስረዱትም ለእነዚህ አረጋውያን መሞት ዋነኛ ምክንያቶች በማዕከላቱ የሚገኙ ሠራተኞች እጥረት እና በቂ ስልጠና አለማግኘት የሚጠቀሱ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረትና የጤና ኃላፊዎች ምላሽ መዘግየት ይገኙበታል። የአውስትራሊያ ህክምና ማኅበር በበኩሉ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል፤ ጥብቅ ምርመራም ያስፈልጋል እያለ ነው። በቪክቶሪያ የሚገኘው ቅርንጫፉ ፕሬዚዳንት ጁሊያን ራይት ለናይን ጋዜጣ እንደተናገሩት ቀውሱ "የተገመተውን አሳዛኝ ክስተት ጥሎ አልፏል" እንዳሉ አስነብቧል። በቪክቶሪያ የሚገኙ በርካታ አረጋውያን በኮሮናቫይረስ መሞታቸው አይቀሬ እንደሆነ የአውስትራሊያ ጤና ቢሮ ፀሐፊ ብሬንዳን መርፊ ከሰሞኑ ተናግረዋል። ውድ አያቶቼ በእነዚህ ማዕከላት አለመገኘታቸው እድለኛ ነኝ። አሁንም የሚገኙባቸው የእንክብካቤ ማዕከላት ከኮሮናቫይረስ ነፃ ናቸው። አንደኛዋ አያቴ ማርጋሬት ጎብኚም አያያትም፤ ሌላኛዋ አያቴ ማርጋሬትን ግን በሳምንት አንዴ እንድናያት ተፈቅዶልናል፤ እናቴም ቅዳሜ እለት ሄዳ ነበር። ለረዥም ጊዜያት ሳቁ፣ ተቃቀፉ፣ ቀልድም ጣል እያደረጉ ኮሮናቫይረስ እንዳለ ዘነጉት። አያቴ ናና ቫይረሱ ከያዛት መሞቻዬ ነው ብትልም እንዲህ በቀላሉ እጅ አልሰጥም ትላለች። "ህፃን እያለሁ ዳክዬዎች አባረሩኝ ግን አልደረሱብኝም፤ አሁንም ኮሮናቫይረስ ይይዘኛል የሚል ግምት የለኝም" ብላ አስቃናለች። | ኮሮናቫይረስ ፡ 'በጦርነት አድጌ በወረርሽኝ አልሞትም" "በጦርነት ነው ያደግኩት፤ በወረርሸኙ አልሞትም።" ማርጋሬት አልኮክ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ ጀርመን በእንግሊዝ ላይ ያደረሰችው "ዘ ብሊትዝ" ተብሎ የሚጠራው የቦምብ ጥቃት በመጠለያ ውስጥ ሆነው ያን ፈታኝ ጊዜ አልፈውታል ። ከዚያም ባሕር፣ ውቅያኖስ ተሻግረው ወደ አውስትራሊያ ተወሰዱ። ላኪ ማርቲን እባላለሁ፤ የ89 ዓመቷ ማርጋሬት አያቴ (ናና) ናት ያንን የጦርነት ጊዜ በጨለምተኝነት አታወሳውም፤ በተቻለ መጠን ሳቅና ቀልድ በተሞላበት መልኩ ነው ጦርነትን የመሰለ አስከፊ ነገር የምታወራው። ስለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝም እንዲሁ በቀልድ ነው የምታወራው። "አንዳንዴ በምን ተአምር ነው እንዲያው እዚህ ወረርሽኝ ላይ የጣለኝ፤ እንዴት በህይወት እያለሁ ይሄን አየሁ" ትለኛለች ስደውልላት። ከዚያም ትቀጥልና "የከፋ ነገር ስላየሁ ወረርሽኙ ብዙም አያስጨንቀኝም" ትለኛለች። በጥር ወር ላይ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአውስትራሊያ ሲያጋጥም አያቶቼ የአረጋውያን መንከባከቢያ ማዕከል በመሆናቸው ወላጆቼም ሆነ እኔ ከበሽታው እንደሚጠበቁና ምንም እንደማይነካቸው እርግጠኛ ነበርን። ነገር ግን ግምታችን የተሳሳተ ነበር በአምስት ወራት ውስጥ በአውስትራሊያ ከተከሰተው 247 ሞቶች መካከል 156ቱ በአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ውስጥ የሚገኙ ናቸው። በርካታ አረጋውያንም ሊያልቁ የቻሉበት ምክንያትም የጤና ሥርዓቱ እነዚህን ተጋላጭ የኅብረተሰቡ ክፍሎችን ችላ በማለቱ ነው ተብሎ እየተተቸ ነው። በተለያየ የስልጣን እርከን ደረጃ ላይ የሚገኙ ኃላፊዎችም ለዚህ ክፍተት መፈጠር ጥያቄዎች እየቀረቡላቸው ነው። በአውስትራሊያ ውስጥ 180 ሺህ ያህል አረጋውያን በእንክብካቤ ማዕከል ውስጥ ይኖራሉ። እነዚህ ማዕከላት በእርዳታ ድርጅቶች፣ በግል ኩባንያዎችና በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የሚተዳደሩ ናቸው። የወረርሽኙን መከሰት ተከትሎ እነዚህም ማዕከላት በፍጥነት ነው ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያስገቧቸው። አንዳንዶቹም መንግሥት ካስተላለፈው መመሪያም በማፈንገጥ እንግዶች እንዳይጎበኙ አረጋውያኑም በክፍላቸው ብቻ እንዲቆዩና ሌሎች እንቅስቃሴዎችንም እንዳያደርጉ ሲከለክሉ ቆይተዋል። ማርጋሬት ያሉበት ማዕከል ለተወሰነ ጊዜ ጎብኚዎችን ቢከለክሉም በግቢው ውስጥ እንደፈለጉ እንዲንቀሳቀሱና መውጣትም ስለፈቀዱላቸው እድለኛ ናቸው። ሌላኛዋ የ87 ዓመቷ አያቴ፤ የእሷም ስም በሚገርም ሁኔታ ማርጋሬት ነው፤ ከመጋቢት ጀምሮ በክፍሏ ውስጥ ናት። ማዕከሉ በሜልቦርን የሚገኝ ሲሆን፤ ይህች ከተማም የወረርሽኙ ማዕከል ሆናለች። አያቴ በክፍሏ ተወስና ነው ያለችው፤ የሚፈቀድላት በኮሪደሩ ላይ እንድትራመድ ብቻ ነው። ለወራትም ያለ ጎብኚ ብቻዋን ትበላለች፤ ወንበሯ ላይ ቁጭ ብላ ነው የምታሳልፈው። እንዲያም ሆኖ በዚህ አስጨናቂ ሰዓት በማዕከሉ እያገለገሉ ላሉ ሠራተኞች ምስጋናዋ ከፍ ያለ ነው። "እንዲህ ተዘግቶ መቀመጥ ከባድ ቢሆንም ተቀብየዋለሁ፤ ከሁሉ በላይ ለእኔ ደኅንነትም ነው" ትለናለች። "ብዙም አልጨነቅም። ቤተሰቦቼን አለማየቴ ከባድ ቢሆንም እዚህ አይደሉም ማለት ግን አይወዱኝም ማለት አይደለምም" በማለት ስሜታችንን ትነካዋለች። እሷ ያለችበትን ማዕከል የሚያስተዳድረው ኩባንያ በሁሉም ነገር ዝግጁ እንደሆነ አሳውቆናል። ጥብቅ የሆነ የጽዳት ቁጥጥርን ጨምሮ፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በከፍተኛ መጠን አከማችቷል። ነገር ግን በተለያዩ ሁለት ግዛቶች የሚገኙ ማዕከላት የቫይረሱን መዛመት መቆጣጠር አቅቷቸው በርካታ አረጋውያን ረግፈዋል፤ ይህም ሁኔታ ለቤተሰቦቻቸው ልብ ሰባሪ ሆኗል። እነዚህ አረጋውያን በቫይረሱ በቀላሉ እንደሚጠቁና፣ ተጋላጭም እንደሆኑ ማወቅ የሮኬት ሳይንስ አይደለም። በርካታዎቹ አረጋውያን ሌላ ተደራራቢ ህመሞች ያሉባቸው ሲሆኑ በማዕከላቱም ውስጥ ያለው የህክምና አገልግሎት የተወሰነ ነው። ከዚህም በተጨማሪ የማዕከሉ ሠራተኞችም በተለያዩ ቦታዎች ከመስራታቸውም አንፃር ቫይረሱን በቀላሉ ያዛምታሉ። በየካቲት ወር ላይ በአውሮፓ በሚገኙ ማዕከላት ውስጥ ያሉ አረጋውያን በሚያሰቅቅ ሁኔታ እንደ ቅጠል እየረገፉ እንደሆነ ታሪኮች መውጣት ጀመሩ። ይህም ሁኔታ በአውስትራሊያ ሊያጋጥም እንደሚችል አገሪቷ ማወቅ ነበረባት የሚሉት በሞናሽ ዩኒቨርስቲ የጤና ሕግ ክፍል ኃላፊ ጆ ኢብራሂም ናቸው። "የአውስትራሊያ ምላሽ በቂ አልነበረም። ለሚመጣው ነገር በሙሉ ዝግጁ አልነበረችም እናም አሁን የተፈጠረው ክስተት ሊያስደንቀን አይገባም" ይላሉ ። "ብዙ ሰዎች ይህ መሆኑ አይቀሬ ነበር ሲሉ ይሰማል። ይሄ ግን ትክክለኛ አይደለም፤ ምክንያቱም ምንም ማድረግ አንችልም ነበር የሚለውን ትርጉም ስለሚሰጥ ነው። የኮሮናቫይረስ በአረጋውያን ላይ ምን ያህል አደጋ እንደደቀነ ከግምት ውስጥም አላስገባነውም። በሌሎች አገሮች ላይ እያለቁ የነበሩትንም አረጋውያን መረጃዎች አላጤንነውም" ይላሉ። በመጋቢት ወር ላይ በሲድኒ የሚገኝ ዶሮቲ ሄንደርሰን ሎጅ የተባለ የአረጋውያን ማዕከል ሠራተኛ በኮሮናቫይረስ መያዟ ተረጋገጠ፤ በግንቦት ወርም 21 በማዕከሉ የሚኖሩ አረጋውያንና ሠራተኞችም ተያዙ። ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ ሞቱ። ሌላ እንዲሁ በሲድኒ ውስጥ የሚገኝ ኒውማርች የተባለ ማዕከልም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ህሙማንን ወደ ጤና ማዕከል ከመላክ ይልቅ ክፍላቸው ውስጥ እንዲዘጉ አደረገ። ማዕከሉ የሠራተኞች ዕጥረት እንዲሁም የኮሮናቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችም በበቂ ሁኔታ አልነበሩትም። ይህንንም ተከትሎ 19 አረጋውያን ሲሞቱ በርካቶችም በቫይረሱ ተያዙ። የአረጋውያኑ መሞት በርካታ ጥያቄዎችን ቢያጭርም ይህ ለምን እንደተከሰተ አጥጋቢ ምላሽ የሚሰጥ አካል አልተገኘም። አሁንም ከክስተቱ ያልተማረችው አውስትራሊያ አረጋውያኗን በኮሮናቫይረስ እያጣች ነው። የቪክቶሪያ ግዛት እንደ አዲስ ወረርሽኙ እያገረሸባት ሲሆን ከማህበረሰቡ ስርጭት በተጨማሪ የአረጋውያኑ የእንክብካቤ ማዕከላት በከፍተኛ ሁኔታ እየተጠቁ ነው። በአሁኑ ወቅትም 1 ሺህ 200 የሚሆኑ አረጋውያን በ97 ማዕከላት ውስጥ መያዛቸው ተረጋግጧል። ፕሮፌሰር ኢብራሂም እንደሚሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ብቻቸውን ቫይረሱን መግታት አይችሉም። "በሽታው ቢያጋጥም ምን ማድረግ አለብን የሚለው ላይ የተቀመጠ ግልጽ ያለ ፖሊሲም ሆነ ይህንንም መቆጣጠር የሚችል መዋቅር አልተዘረጋም" ይላሉ። የአረጋውያኑን የእንክብካቤ ማዕከላት በቀጥታ የሚመለከተው የፌደራል መንግሥቱን ቢሆንም ወረርሽኙን ደግሞ በየግዛቱ ያሉ የኅብረተሰብ ጤና ኃላፊዎች በበላይነት ይቆጣጠሩታል። "በዚህም ምክንያቱ ኃላፊነቱ የማን ነው በሚል መወዛገብ ተፈጠረ። ይሄ ብቻ አይደለም የኮሮናቫይረስ ህሙማን ህክምናው መሰጠት ያለበት ሆስፒታል ወይስ ቤታቸው ውስጥ የሚለውም ላይ ውሳኔ ሳያገኝ እንዲሁ እያወዛገበ ነበርም" በማለት ያስረዳሉ። የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንቶኒ አልባኔዝ በዚህ ሳምንት ሰፋ ያለ ምርመራና ኃላፊነት ሊወስዱ የሚባቸውም አካላት እንዲጠየቁ ተናግረዋል። "በኒውማርች እንክብካቤ ማዕከል ካጋጠመን ክስተት ለምን አልተማርንም? ይህ የተከሰተው ከወራት በፊት ነበር" በማለትም ይጠይቃሉ። በሜልቦርን የግዛቲቷና የፌደራል ኤጀንሲዎች ተጣምረውም በቪክቶሪያ የተከሰተውን የወረርሽኝ ቀውስ ለመቆጣጠር ጥረት እያደረጉ ነው። ለፕሮፌሰር ኢብራሂም ግን ዋናው ነገር ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ በአውስትራሊያ የሚገኙ የእንክብካቤ ማዕከላት ሁኔታ ሊገመገም እንዲሁም ቁጥጥር ሊደረግበት ይገባል ይላሉ። "በዚህም መንገድ ነው የትኞቹ ማዕከላት አደጋ ውስጥ እንዳሉ የምንረዳው" የሚሉት ፕሮፌሰሩ አክለውም "ከዚያ በመቀጠልም ያለምንም ማንገራገር ፈጣንና የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድ ይገባል" በማለትም ምክራቸውን ለግሰዋል። በእንክብካቤ ማዕከላቱ የተፈጠረውንም ሁኔታ የሚያጣራ የመንግሥት ቡድንም ተቋቁሟል። ከተለያዩ ቦታዎች የተገኙ መረጃዎች እንደሚያስረዱትም ለእነዚህ አረጋውያን መሞት ዋነኛ ምክንያቶች በማዕከላቱ የሚገኙ ሠራተኞች እጥረት እና በቂ ስልጠና አለማግኘት የሚጠቀሱ ናቸው። ከዚህም በተጨማሪ የኮሮናቫይረስ የመከላከያ ቁሳቁሶች እጥረትና የጤና ኃላፊዎች ምላሽ መዘግየት ይገኙበታል። የአውስትራሊያ ህክምና ማኅበር በበኩሉ መንግሥትን ተጠያቂ አድርጓል፤ ጥብቅ ምርመራም ያስፈልጋል እያለ ነው። በቪክቶሪያ የሚገኘው ቅርንጫፉ ፕሬዚዳንት ጁሊያን ራይት ለናይን ጋዜጣ እንደተናገሩት ቀውሱ "የተገመተውን አሳዛኝ ክስተት ጥሎ አልፏል" እንዳሉ አስነብቧል። በቪክቶሪያ የሚገኙ በርካታ አረጋውያን በኮሮናቫይረስ መሞታቸው አይቀሬ እንደሆነ የአውስትራሊያ ጤና ቢሮ ፀሐፊ ብሬንዳን መርፊ ከሰሞኑ ተናግረዋል። ውድ አያቶቼ በእነዚህ ማዕከላት አለመገኘታቸው እድለኛ ነኝ። አሁንም የሚገኙባቸው የእንክብካቤ ማዕከላት ከኮሮናቫይረስ ነፃ ናቸው። አንደኛዋ አያቴ ማርጋሬት ጎብኚም አያያትም፤ ሌላኛዋ አያቴ ማርጋሬትን ግን በሳምንት አንዴ እንድናያት ተፈቅዶልናል፤ እናቴም ቅዳሜ እለት ሄዳ ነበር። ለረዥም ጊዜያት ሳቁ፣ ተቃቀፉ፣ ቀልድም ጣል እያደረጉ ኮሮናቫይረስ እንዳለ ዘነጉት። አያቴ ናና ቫይረሱ ከያዛት መሞቻዬ ነው ብትልም እንዲህ በቀላሉ እጅ አልሰጥም ትላለች። "ህፃን እያለሁ ዳክዬዎች አባረሩኝ ግን አልደረሱብኝም፤ አሁንም ኮሮናቫይረስ ይይዘኛል የሚል ግምት የለኝም" ብላ አስቃናለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-53680615 |
5sports
| ሞሮኮ ለዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ በመድረስ ታሪክ ሰራች | ሞሮኮ ፖርቹጋልን በመርታት ለዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዊት አፍሪካዊት ጋር በመሆን ታሪክ ሰራች። ሰሜናዊ አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሮኮ ትናንት ታህሳስ 1፣ 2015 ዓ.ም ፖርቹጋልን በኳታር የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ 1ለ0ም በመርታት ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈችው። በዚህም ጨዋታ ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቷት የነበረውን ፖርቹጋልን እንዲሁም መሪ ተጨዋቿን ክርስቲያኖ ሮናልዶን ግስጋሴ ገትታለች። የሞሮኮው አጥቂ ዩሴፍ ኤን ኔሲሪ በመጀመሪያው አጋማሽ የማሸነፊያውን ጎል በማስቆጠር የአል ቱማማ ስታዲየምን ታዳሚዎች እንዲሁም የአረቡን አለምና አፍሪካውያንን አስፈንጥዟል። የአትላስ አናብስቱ ደጋፊዎች ስታዲየሙን ሞልተውት የነበረ ሲሆን በዓለም አቀፉ የስፖርት መድረክ ሞሮኮን ከፍ ያደረጋትንም ድል በከፍተኛ ደስታ ገልጸውታል። በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጨዋታዎች 196 ጊዜ በመጫወት ክብረ ወሰኑን የተቆጣጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ50ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ቢገባም ጎል ሊቀናው አልቻለም። አገሩንም ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሊያሳልፋት አልቻለም። በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይን የምትፋለመው ሞሮኮ ከእረፍት በፊት ኤን ኔሲሪ፣ ያህያ አቲያት አላህ ያሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ጎል አስቆጥሯል። የፖርቹጋሉ አጥቂ ብሩኖ ፈርናዴዝ ከደቂቃዎች በኋላ አስደናቂ ጎል ለማስቆጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የጎሉ ብረት መልሶበት አገሩን እኩል የማድረግ እድሉ ለጥቂት ከሽፏል። በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታ ሞሮኮ ተጨዋቾች ቢጎዱባትም እንዲሁም እንዲሁም አጥቂዋ ዋሊድ ቼዲራ በስምንት ደቂቃ ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን ቢጫ ካርድ በማየቱ ከጨዋታው ቢሰናበትም ፖርቹጋል ጎል ማስቆጠር አልቻለችም። ሶስት የአፍሪካ ሃገራት ከዚህ ቀደም በነበሩ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ሩብ ፍጻሜ ደረጃ ላይ ቢደርሱም አንዳቸውም ቢሆን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም ነበር። ድንቅ ጨዋታን ላሳዩት የሞሮኮ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ኤን ኔሲሪ በቴስታ ያስቆጠራት ግብ ሃገሪቱን በታሪክ መዝገብ እንድትሰፍር በማድረግ ደስታቸውን ሌላ ደረጃ ላይ አድርሶታል። | ሞሮኮ ለዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ በመድረስ ታሪክ ሰራች ሞሮኮ ፖርቹጋልን በመርታት ለዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ የደረሰች የመጀመሪያዊት አፍሪካዊት ጋር በመሆን ታሪክ ሰራች። ሰሜናዊ አፍሪካዊቷ ሃገር ሞሮኮ ትናንት ታህሳስ 1፣ 2015 ዓ.ም ፖርቹጋልን በኳታር የዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ 1ለ0ም በመርታት ነው ወደ ቀጣዩ ዙር ያለፈችው። በዚህም ጨዋታ ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቷት የነበረውን ፖርቹጋልን እንዲሁም መሪ ተጨዋቿን ክርስቲያኖ ሮናልዶን ግስጋሴ ገትታለች። የሞሮኮው አጥቂ ዩሴፍ ኤን ኔሲሪ በመጀመሪያው አጋማሽ የማሸነፊያውን ጎል በማስቆጠር የአል ቱማማ ስታዲየምን ታዳሚዎች እንዲሁም የአረቡን አለምና አፍሪካውያንን አስፈንጥዟል። የአትላስ አናብስቱ ደጋፊዎች ስታዲየሙን ሞልተውት የነበረ ሲሆን በዓለም አቀፉ የስፖርት መድረክ ሞሮኮን ከፍ ያደረጋትንም ድል በከፍተኛ ደስታ ገልጸውታል። በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ጨዋታዎች 196 ጊዜ በመጫወት ክብረ ወሰኑን የተቆጣጠረው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ50ኛው ደቂቃ ተቀይሮ ቢገባም ጎል ሊቀናው አልቻለም። አገሩንም ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሊያሳልፋት አልቻለም። በግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ፈረንሳይን የምትፋለመው ሞሮኮ ከእረፍት በፊት ኤን ኔሲሪ፣ ያህያ አቲያት አላህ ያሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት ጎል አስቆጥሯል። የፖርቹጋሉ አጥቂ ብሩኖ ፈርናዴዝ ከደቂቃዎች በኋላ አስደናቂ ጎል ለማስቆጠር ተቃርቦ የነበረ ቢሆንም የጎሉ ብረት መልሶበት አገሩን እኩል የማድረግ እድሉ ለጥቂት ከሽፏል። በሁለተኛው አጋማሽ ጨዋታ ሞሮኮ ተጨዋቾች ቢጎዱባትም እንዲሁም እንዲሁም አጥቂዋ ዋሊድ ቼዲራ በስምንት ደቂቃ ተጨማሪ ጊዜ ውስጥ ሁለተኛውን ቢጫ ካርድ በማየቱ ከጨዋታው ቢሰናበትም ፖርቹጋል ጎል ማስቆጠር አልቻለችም። ሶስት የአፍሪካ ሃገራት ከዚህ ቀደም በነበሩ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች ላይ ሩብ ፍጻሜ ደረጃ ላይ ቢደርሱም አንዳቸውም ቢሆን ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፍ አልቻሉም ነበር። ድንቅ ጨዋታን ላሳዩት የሞሮኮ ተጨዋቾች እና ደጋፊዎች ኤን ኔሲሪ በቴስታ ያስቆጠራት ግብ ሃገሪቱን በታሪክ መዝገብ እንድትሰፍር በማድረግ ደስታቸውን ሌላ ደረጃ ላይ አድርሶታል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/czq32x0wl8eo |
5sports
| የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች መለያ በስማቸው ምትክ የጥቁሮች ፍትህ ጥያቄ ሊሰፍርበት ነው | የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ቀሪዎቹን 12 ጨዋታዎች ሲያደርጉ ከመለያቸው ጀርባ ላይ በስማቸው ፈንታ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' [የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው] የሚለውን ጽሁፍ እንደሚያሰፍሩ ተገለጸ። ከዚህ በተጨማሪም ፕሪምየር ሊጉ ከጨዋታ በፊትም ሆነ በኋላ የጥቁሮች የፍትህ ጥያቄ መለያ በሆነው ተንበርክኮ ድጋፋቸውን ለመግለጽና መልዕክት ማስተላለፍ የሚፈልጉ ተጫዋቾች አይከለከሉም ብሏል። ቀድሞ በተጀመረው የጀርመን ቡንደስሊጋ የሚጫወቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ የጆርጅ ፍሎይድን ሞት አስመልከቶ ሜዳ ውስጥ ቀድመው መልዕክት ያስተላለፉት። የፕሪምየር ሊጉ 20 ቡድኖች ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ "እኛ እንደ እግር ኳስ ተጫዋች በህብረት በመቆም የዘር መድሎን ለማስወገድ አብረን እንቆማለን" ብለዋል። አክለውም ሁሉንም ያካተተ፣ መከባበር ያለበትና በቀልም እንዲሁም በጾታ ሳይለይ ሁሉም እኩል እድል የሚያገኝበት ዓለም አቀፋዊ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ የሚለውን መልዕክት የዘንድሮው የውድድር ዓመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ተጫዋቾች በጀርባቸው ላይ የሚያደርጉ ሲሆን በተጨማሪም በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን የሚያመሰግን መልዕክትም ያስተላልፋሉ። በርካታ የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች በስልጠና ሜዳዎች ላይ በመንበርከክ ዘረኝነትን ያወገዙበትን ምስል ቀደም ሲል በማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ አጋርተዋል። ባለፈው ወር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳል ህይወቱ ባለፈቸው የ46 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ምክንያት ዘረኝነት ይቁም በማለት ሜዳ ውስጥ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ አራት የጀርመን ቡንደስሊጋ ተጫዋቾች በእግር ኳስ ማኅበሩ ምርመራ ተደርጎባቸው ነበር። በመጨረሻ ግን የትኛውም ተጫዋች ቅጣት እንዳልተጣለበትና ተጫዋቾች በሚቀጥሉት ሳምንታት ዘረኝነትን በመቃወም መልዕክታቸውን ማስተላለፍ እንደሚችሉ የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር አስታውቋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከሦስት ወራት በኋላ በዝግ ስታዲየሞች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ የሚጀመር ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በርካታ ጥንቃቄዎች ይደረጋሉ ተብሏል። የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና የኒውካስል እንዲሁም የቶተንሀም አማካይ ጀርሜይን ጄናስ ለቀሪዎቹ 12 ጨዋታዎች የሚተላለፈው መልዕክት በዘላቂነት ቢታሰብበት ጥሩ ነው ብሏል። "ሁሉም ክለቦችና ተጫዋቾች በዚህ ጉዳይ ላይ ተስማምተው ዘረኝነትን ለመዋጋት ማሰባቸው በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው። ቀላል ለማይባሉ ሰዎች መልዕክቱ እንደሚደርስም እርግጠኛ ነኝ። ፕሪምየር ሊጉ በመላው ዓለም በርካታ ተከታታዯች ያሉት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ጠንከር ያሉ መልዕክቶች ለወደፊቱም ቢቀጥሉ ጥሩ ነው" ብሏል ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ። አክሎም "በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጥቁር አሰልጣኞች እንደሌሉ በስፋት ይነገራል፤ አሰልጣኞችና ሌሎች አባላት ሲመለመሉ ብዝሃነትን ባማከለ መልኩ መደረግ ያለባቸው ይመስለኛል’’ ብሏል። | የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች መለያ በስማቸው ምትክ የጥቁሮች ፍትህ ጥያቄ ሊሰፍርበት ነው የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች ቀሪዎቹን 12 ጨዋታዎች ሲያደርጉ ከመለያቸው ጀርባ ላይ በስማቸው ፈንታ 'ብላክ ላይቭስ ማተር' [የጥቁሮች ህይወት ዋጋ አለው] የሚለውን ጽሁፍ እንደሚያሰፍሩ ተገለጸ። ከዚህ በተጨማሪም ፕሪምየር ሊጉ ከጨዋታ በፊትም ሆነ በኋላ የጥቁሮች የፍትህ ጥያቄ መለያ በሆነው ተንበርክኮ ድጋፋቸውን ለመግለጽና መልዕክት ማስተላለፍ የሚፈልጉ ተጫዋቾች አይከለከሉም ብሏል። ቀድሞ በተጀመረው የጀርመን ቡንደስሊጋ የሚጫወቱ እግር ኳስ ተጫዋቾች ነበሩ የጆርጅ ፍሎይድን ሞት አስመልከቶ ሜዳ ውስጥ ቀድመው መልዕክት ያስተላለፉት። የፕሪምየር ሊጉ 20 ቡድኖች ባወጡት የአቋም መግለጫ ላይ "እኛ እንደ እግር ኳስ ተጫዋች በህብረት በመቆም የዘር መድሎን ለማስወገድ አብረን እንቆማለን" ብለዋል። አክለውም ሁሉንም ያካተተ፣ መከባበር ያለበትና በቀልም እንዲሁም በጾታ ሳይለይ ሁሉም እኩል እድል የሚያገኝበት ዓለም አቀፋዊ ማኅበረሰብ ለመፍጠር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ‘ብላክ ላይቭስ ማተር’ የሚለውን መልዕክት የዘንድሮው የውድድር ዓመት እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሁሉም ተጫዋቾች በጀርባቸው ላይ የሚያደርጉ ሲሆን በተጨማሪም በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን የሚያመሰግን መልዕክትም ያስተላልፋሉ። በርካታ የፕሪምየር ሊግ ተጫዋቾች በስልጠና ሜዳዎች ላይ በመንበርከክ ዘረኝነትን ያወገዙበትን ምስል ቀደም ሲል በማኅበራዊ መገናኛ መድረክ ላይ አጋርተዋል። ባለፈው ወር በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሳል ህይወቱ ባለፈቸው የ46 ዓመቱ ጥቁር አሜሪካዊ ጆርጅ ፍሎይድ ሞት ምክንያት ዘረኝነት ይቁም በማለት ሜዳ ውስጥ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ አራት የጀርመን ቡንደስሊጋ ተጫዋቾች በእግር ኳስ ማኅበሩ ምርመራ ተደርጎባቸው ነበር። በመጨረሻ ግን የትኛውም ተጫዋች ቅጣት እንዳልተጣለበትና ተጫዋቾች በሚቀጥሉት ሳምንታት ዘረኝነትን በመቃወም መልዕክታቸውን ማስተላለፍ እንደሚችሉ የጀርመን እግር ኳስ ማኅበር አስታውቋል። የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ከሦስት ወራት በኋላ በዝግ ስታዲየሞች በሚቀጥለው ሳምንት ረቡዕ የሚጀመር ሲሆን የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በርካታ ጥንቃቄዎች ይደረጋሉ ተብሏል። የቀድሞው የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንና የኒውካስል እንዲሁም የቶተንሀም አማካይ ጀርሜይን ጄናስ ለቀሪዎቹ 12 ጨዋታዎች የሚተላለፈው መልዕክት በዘላቂነት ቢታሰብበት ጥሩ ነው ብሏል። "ሁሉም ክለቦችና ተጫዋቾች በዚህ ጉዳይ ላይ ተስማምተው ዘረኝነትን ለመዋጋት ማሰባቸው በጣም ደስ የሚል ሀሳብ ነው። ቀላል ለማይባሉ ሰዎች መልዕክቱ እንደሚደርስም እርግጠኛ ነኝ። ፕሪምየር ሊጉ በመላው ዓለም በርካታ ተከታታዯች ያሉት እንደመሆኑ እንዲህ አይነት ጠንከር ያሉ መልዕክቶች ለወደፊቱም ቢቀጥሉ ጥሩ ነው" ብሏል ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ። አክሎም "በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጥቁር አሰልጣኞች እንደሌሉ በስፋት ይነገራል፤ አሰልጣኞችና ሌሎች አባላት ሲመለመሉ ብዝሃነትን ባማከለ መልኩ መደረግ ያለባቸው ይመስለኛል’’ ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53033059 |
3politics
| ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፖሊስ ድብደባ እንደተፈጸመበት ጠበቃው እና ወንድሙ ተናገሩ | በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ድበደባ እንደተፈጸመበት ጠበቃው እና ወንድሙ ለቢቢሲ ተናገሩ። የጋዜጠኛው ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ በተመስገን ላይ ድብደባው የተፈጸመው ሐሙስ ረፋድ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም. ታስሮ በሚገኘበት 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን ገልጿል። ታሪኩ ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ሄዶ በመካከላቸው ባለው ርቀት ምክንያት ሲነጋገሩ መደማመጥ ባለመቻላቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ወደ እርሱ ለመጠጋት መሞከሩን ተከትሎ፣ ከጠባቂ የፖሊስ አባላት ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ድብደባ እንደተፈጸመበት አስረድቷል። “በጠያቂ እና በተጠያቂ መካከል ያለው ርቀት ሰፊ ነው። በአንድ ጊዜ ከ10 ሰው በላይ ነው የሚያወራው። መጯጯህ ነው። ከዚህ በፊት በእስር ላይ ሳለ ጆሮው ላይ ጉዳት አጋጥሞት ነበር። በዚህ ሁኔታ መደማመጥ ይከብደዋል” የሚለው ታሪኩ፤ ለመጠጋት ጥያቄ ካቀረበ በኋላ ድበደባ እንደተፈጸመት ተናግሯል። “ዓይናችን እያየ በጫማ ጥፊ እና በቦክስ መቱት። . . . ከዚያ ወደ እስረኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ክፍል ይዘውት ሄዱ። ‘ካላየነው’ ብለን አስቸገርን። ይሄ ከሆነ ከ40 ደቂቃ በኋላ ለሁለት ደቂቃ ያክል አሳዩን። ከግራ ዓይኑ በታች አብጧል። ለብሶት ያለው ካናቴራ ተቀዷል። ምንም ነገር ማድረግ አልቻልንም። ለጠበቃው ተናግረን ወጣን” ብሏል የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዳ። በተመሳሳይ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ጋዜጠኛው በመንግሥት ፀጥታ ኃይል አባላት ድበደባ እንደተፈጸመበት ከቤተሰብ አባላት መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠበቃ ሄኖክ ከቀናት በፊት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደነበሩ አስታውሰው፣ ተመስገንን ባያገኙትም ስለደረሰበት ጉዳት ከቤተሰብ አባላት ሰምቻለሁ ብለዋል። ታናሽ ወንድሙ ሊጠይቀው ሄዶ መደማመጥ ባለመቻላቸው ለጠጋት በሚሞክርበት ጊዜ አለመግባባት ተፈጥሮ “በጥበቃ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ተመስገንን ጎትተው በማውጣት በጥፊ እና በእርግጫ ድብደባ ፈጸሙበታል” ሲሉ ጠበቃ ሄኖክ ተናግረዋል። “ይህ ሰው ፊት የተፈጸመ ድርጊት ነው። ኋላ ደግሞ ወደ ውስጥ አስገብተው ድብደባ ፈጽመውበታል። ቆይቶ ቤተሰብ ተመስገንን ሲያገኘው ልብሱ ተቀዳዶ እና ብዙ ጉዳት ደርሶበታል” ብለዋል። ጠበቃ ሄኖክ እንደሚሉት ጋዜጠኛ ተመስገን በመንግሥት ቁጥጥር ስር ሳለ ድበደባ ቢፈጸምበትም ለፍርድ ቤትም ሆነ ለሚመለከተው አካል ቅሬታ ማቅረብ ስላልፈለገ የቅሬታ ማመልከቻ አላስገባንም ብለዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ተጠርጥሮ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል። በዕለቱ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገንን ገንዘብ ተከፍሎት በተለያዩ ሚዲያዎች እየቀረበ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት መጠርጠሩን ተናግሯል። ጠበቃ ሄኖክ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን እና መስከረም አበራ ጉዳያቸው ቀርቦበት ለነበረው ፍርድ ቤት ክሱ መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንጂ በመደበኛ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መሆን የለበትም ብለው ያቀረቡት ክርክር በፍርድ ቤቱ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም. ከሥራ ቦታው በሁለት መኪና ተጭነው በመጡ የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መወሰዱ ይታወሳል። የጋዜጠኛው ቤት እንዲሁም ቢሮው በፖሊስ የተፈተሸ ሲሆን፣ በተለያየ ጊዜ የታተሙ የፍትህ መጽሔቶች፣ ሃርድ ዲስኮችና ሌሎች ፖሊስ ለምርመራ ያስፈልገኛል የሚላቸውን ሰነዶች መውሰዳቸውን ጠበቃ ሄኖክ አስረድተዋል። | ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በፖሊስ ድብደባ እንደተፈጸመበት ጠበቃው እና ወንድሙ ተናገሩ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ድበደባ እንደተፈጸመበት ጠበቃው እና ወንድሙ ለቢቢሲ ተናገሩ። የጋዜጠኛው ታናሽ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ በተመስገን ላይ ድብደባው የተፈጸመው ሐሙስ ረፋድ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም. ታስሮ በሚገኘበት 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን ገልጿል። ታሪኩ ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ሄዶ በመካከላቸው ባለው ርቀት ምክንያት ሲነጋገሩ መደማመጥ ባለመቻላቸው ጋዜጠኛ ተመስገን ወደ እርሱ ለመጠጋት መሞከሩን ተከትሎ፣ ከጠባቂ የፖሊስ አባላት ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ ድብደባ እንደተፈጸመበት አስረድቷል። “በጠያቂ እና በተጠያቂ መካከል ያለው ርቀት ሰፊ ነው። በአንድ ጊዜ ከ10 ሰው በላይ ነው የሚያወራው። መጯጯህ ነው። ከዚህ በፊት በእስር ላይ ሳለ ጆሮው ላይ ጉዳት አጋጥሞት ነበር። በዚህ ሁኔታ መደማመጥ ይከብደዋል” የሚለው ታሪኩ፤ ለመጠጋት ጥያቄ ካቀረበ በኋላ ድበደባ እንደተፈጸመት ተናግሯል። “ዓይናችን እያየ በጫማ ጥፊ እና በቦክስ መቱት። . . . ከዚያ ወደ እስረኛ ክፍል ሳይሆን ወደ ሌላ ክፍል ይዘውት ሄዱ። ‘ካላየነው’ ብለን አስቸገርን። ይሄ ከሆነ ከ40 ደቂቃ በኋላ ለሁለት ደቂቃ ያክል አሳዩን። ከግራ ዓይኑ በታች አብጧል። ለብሶት ያለው ካናቴራ ተቀዷል። ምንም ነገር ማድረግ አልቻልንም። ለጠበቃው ተናግረን ወጣን” ብሏል የነበረውን ሁኔታ ሲያስረዳ። በተመሳሳይ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ አቶ ሄኖክ አክሊሉ ጋዜጠኛው በመንግሥት ፀጥታ ኃይል አባላት ድበደባ እንደተፈጸመበት ከቤተሰብ አባላት መስማታቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ጠበቃ ሄኖክ ከቀናት በፊት ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ ላይ ይግባኝ ለማቅረብ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት እንደነበሩ አስታውሰው፣ ተመስገንን ባያገኙትም ስለደረሰበት ጉዳት ከቤተሰብ አባላት ሰምቻለሁ ብለዋል። ታናሽ ወንድሙ ሊጠይቀው ሄዶ መደማመጥ ባለመቻላቸው ለጠጋት በሚሞክርበት ጊዜ አለመግባባት ተፈጥሮ “በጥበቃ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት ተመስገንን ጎትተው በማውጣት በጥፊ እና በእርግጫ ድብደባ ፈጸሙበታል” ሲሉ ጠበቃ ሄኖክ ተናግረዋል። “ይህ ሰው ፊት የተፈጸመ ድርጊት ነው። ኋላ ደግሞ ወደ ውስጥ አስገብተው ድብደባ ፈጽመውበታል። ቆይቶ ቤተሰብ ተመስገንን ሲያገኘው ልብሱ ተቀዳዶ እና ብዙ ጉዳት ደርሶበታል” ብለዋል። ጠበቃ ሄኖክ እንደሚሉት ጋዜጠኛ ተመስገን በመንግሥት ቁጥጥር ስር ሳለ ድበደባ ቢፈጸምበትም ለፍርድ ቤትም ሆነ ለሚመለከተው አካል ቅሬታ ማቅረብ ስላልፈለገ የቅሬታ ማመልከቻ አላስገባንም ብለዋል። ከአንድ ሳምንት በፊት በቁጥጥር ሥር የዋለው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት ተጠርጥሮ ግንቦት 19/2014 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ እንደነበር ይታወሳል። በዕለቱ ፖሊስ ጋዜጠኛ ተመስገንን ገንዘብ ተከፍሎት በተለያዩ ሚዲያዎች እየቀረበ ሁከትና ብጥብጥ በማነሳሳት መጠርጠሩን ተናግሯል። ጠበቃ ሄኖክ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን እና መስከረም አበራ ጉዳያቸው ቀርቦበት ለነበረው ፍርድ ቤት ክሱ መታየት ያለበት በመገናኛ ብዙኃን አዋጅ እንጂ በመደበኛ የወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ መሆን የለበትም ብለው ያቀረቡት ክርክር በፍርድ ቤቱ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ዛሬ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። የፍትህ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር የሆነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ግንቦት 18/2014 ዓ.ም. ከሥራ ቦታው በሁለት መኪና ተጭነው በመጡ የፀጥታ ኃይሎች ተይዞ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መወሰዱ ይታወሳል። የጋዜጠኛው ቤት እንዲሁም ቢሮው በፖሊስ የተፈተሸ ሲሆን፣ በተለያየ ጊዜ የታተሙ የፍትህ መጽሔቶች፣ ሃርድ ዲስኮችና ሌሎች ፖሊስ ለምርመራ ያስፈልገኛል የሚላቸውን ሰነዶች መውሰዳቸውን ጠበቃ ሄኖክ አስረድተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c90qeld9lzjo |
3politics
| ኬንያዊው ፖለቲከኛ ለአዲስ ተጋቢዎች ብድር ለመስጠት ቃል ገቡ | ከወራት በኋላ በሚደረገው የኬንያ ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ፖለቲከኛ፤ ከተመረጡ ከ4,400 እስከ 8,800 ዶላር የሚደርስ ብድር ለአዲስ ተጋቢዎች ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ፕሬዝዳንታዊ ማኒፌስቷቸውን እሑድ ይፋ ያደረጉት ማቻኮስ የተባለው ግዛት አገረ ገዢ አልፍሬድ ሙቱዋ፤ በ20 ዓመት የሚከፈልና ዝቅተኛ ወለድ ያለው ብድር ጥንዶች "ሕይወታቸው በክብር እንዲጀምሩ" ይረዳል ብለዋል። "የዚህ ሁሉ ውጤት ምንድን ነው?" ብለው በመጠየቅ የጀመሩት ሙቱዋ "ለሁላችንም ክብር ነው። የኑሮ ደረጃን ከማሻሻል እና በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የመኖሪያ ቤቶችን ጥራት ከማሳደግ ባለፈ የጭቃ ቤቶችን ያስቀራል" ብለዋል። ችግኝ ተከላ እንደ ጥሎሽ እንዲቆጠር መንግሥታቸው እንደሚያበረታታም ተናግረዋል። በቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ በተላለፈው የማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ ዝግጅት ላይ "ጥሎሽ ለመክፈል ስትሄዱ ምን ያህል ዛፎች እንደተከላችሁ መናገር አለባችሁ" ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ የፖለቲከኛው ሃሳብ ግን ከሁሉም ዘንድ አውንታዊ ምላሽ አላገኘው፣ ከአንዳንድ የማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ተጠቃሚ ኬንያውያን በኩል የሰላ ትችት እና ፌዝ አስተናግዷል። የ10 ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው መገባደጃ ወራት ላይ የሚገኙትን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ለመተካት 10 የሚጠጉ ፖለቲከኞች በዕጩነት ለመቅረብ ከወዲሁ ዘመቻ ጀምረዋል። ነሐሴ 2022 በሚካሄደው ምርጫ ዋና ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱት አንጋፋው የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ እና የአሁኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ይገኙበታል። ምጣኔ ሀብት፣ የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ሙስናን መዋጋት የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ በሚሹ ሰዎች ቁልፍ አጀንዳዎች ሆነው ብቅ ብለዋል። ያለፉት ምርጫዎች የሚያሳዩት ግን ኬንያውያን ከፖሊሲ ጉዳዮች ይልቅ በጎሳ ወይም ሕብረት ፈጥረው ለሚመጡ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ታይቷል። | ኬንያዊው ፖለቲከኛ ለአዲስ ተጋቢዎች ብድር ለመስጠት ቃል ገቡ ከወራት በኋላ በሚደረገው የኬንያ ምርጫ ለፕሬዝዳንትነት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት ፖለቲከኛ፤ ከተመረጡ ከ4,400 እስከ 8,800 ዶላር የሚደርስ ብድር ለአዲስ ተጋቢዎች ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ፕሬዝዳንታዊ ማኒፌስቷቸውን እሑድ ይፋ ያደረጉት ማቻኮስ የተባለው ግዛት አገረ ገዢ አልፍሬድ ሙቱዋ፤ በ20 ዓመት የሚከፈልና ዝቅተኛ ወለድ ያለው ብድር ጥንዶች "ሕይወታቸው በክብር እንዲጀምሩ" ይረዳል ብለዋል። "የዚህ ሁሉ ውጤት ምንድን ነው?" ብለው በመጠየቅ የጀመሩት ሙቱዋ "ለሁላችንም ክብር ነው። የኑሮ ደረጃን ከማሻሻል እና በአገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የመኖሪያ ቤቶችን ጥራት ከማሳደግ ባለፈ የጭቃ ቤቶችን ያስቀራል" ብለዋል። ችግኝ ተከላ እንደ ጥሎሽ እንዲቆጠር መንግሥታቸው እንደሚያበረታታም ተናግረዋል። በቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ በተላለፈው የማኒፌስቶ ማስተዋወቂያ ዝግጅት ላይ "ጥሎሽ ለመክፈል ስትሄዱ ምን ያህል ዛፎች እንደተከላችሁ መናገር አለባችሁ" ሲሉ ተደምጠዋል። ይህ የፖለቲከኛው ሃሳብ ግን ከሁሉም ዘንድ አውንታዊ ምላሽ አላገኘው፣ ከአንዳንድ የማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ተጠቃሚ ኬንያውያን በኩል የሰላ ትችት እና ፌዝ አስተናግዷል። የ10 ዓመታት የሥልጣን ዘመናቸው መገባደጃ ወራት ላይ የሚገኙትን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ለመተካት 10 የሚጠጉ ፖለቲከኞች በዕጩነት ለመቅረብ ከወዲሁ ዘመቻ ጀምረዋል። ነሐሴ 2022 በሚካሄደው ምርጫ ዋና ተፎካካሪ ይሆናሉ ተብለው ከተገመቱት አንጋፋው የተቃዋሚ መሪ ራይላ ኦዲንጋ እና የአሁኑ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ይገኙበታል። ምጣኔ ሀብት፣ የወጣቶች ሥራ አጥነት እና ሙስናን መዋጋት የፕሬዝዳንትነቱን ቦታ በሚሹ ሰዎች ቁልፍ አጀንዳዎች ሆነው ብቅ ብለዋል። ያለፉት ምርጫዎች የሚያሳዩት ግን ኬንያውያን ከፖሊሲ ጉዳዮች ይልቅ በጎሳ ወይም ሕብረት ፈጥረው ለሚመጡ ድምጻቸውን እንደሚሰጡ ታይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59549852 |
0business
| ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከቀናት በኋላ ልትጀምር ነው | ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገር ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ኅዳር 5/2015 ዓ.ም ልትጀምር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኤሌክትሪክ የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም በስኬት መከናወኑን ተከትሎም ወደ ኬንያ የሚደረገው የኤሌክትሪክ ኃይል የወጪ ንግድ ሊጀመር እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ መለስ ዓለም ገልጸዋል። አገራቱን በሚያገናኘው 500 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ላይ የኃይል ማስተላለፍ የሙከራ ሥራ በይፋ መጀመሩን ያስታወቁት የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ አያሌው ናቸው። ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ ሙከራው በስኬት መከናወኑን ያስታወቁት ሥራ አስኪያጁ ይህም በቅርቡ አገሪቱ የምታደርገው የኃይል ሽያጭ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚሄድ አመላካች ነው ማለታቸውን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኤሌክትሮ ሜካኒካል መሳሪያዎች ፍተሻዎች እንዲሁም ከቀናት በፊት የመገናኛ ሲግናል በመላክ ከኬንያ ኔትወርክ ጋር ማገናኘት መቻሉን ሥራ አስኪያጁ ማስታወቃቸው ተጠቅሷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፉ በይፋ ሲጀመርም በሕብረተሰቡ ላይ አደጋ እንዳይደርስ መስመሩ ከሚያልፍባቸው ዞኖች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መካሄዱም ተገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የኃይል ማስተላለፍ ሙከራው በሚከወንበትም ወቅት ምንም አደጋ አለመድረሱንም አቶ ቴዎድሮስ መናገራቸው ተጠቁሟል። የግንባታ ሥራው በ2008 የተጀመረው የኢትዮ- ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር 334.5 ሚሊዮን ዶላር እንደፈጀ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ የግንባታ ሥራ ከአራት ዓመት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል። ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ በኩል የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ግንባታ እና የፍተሻ እንዲሁም የሙከራ ሥራዎች ቢጠናቀቁም በኬንያ በኩል ቀሪ የዝርጋታ እና የግንባታ ሥራዎች እንዳሉ እየተነገረ መጀመር ከነበረበት ወቅት እየተጓተተ ረዘም ያሉ ወራት ተቆጥረዋል። የማስተላለፊያ መስመር የግንባታ ሥራው ሲኢቲ በተሰኘ የቻይና ኩባንያ ሲከናወን የኮንቨርተር ጣቢያውና ሌሎች ተግባራት ደግሞ ሲመንስ በተሰኘ ኩባንያ መከናወኑ ተገልጿል። ለምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ከፍተኛ ስፍራ ያለው ይህ ፕሮጀክት 1.3 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል። አገራቱን የሚያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር 500 ኪሎ ቮልትና ከኢትዮጵያ በኩል 440 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ በአጠቃላይ ከ1 ሺህ ሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው ነው። ወጪውም ከዓለም ባንክ በተገኘው ብድር 684 ሚሊዮን ዶላር፣ ለኢትዮጵያ 441 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 27.4 ቢሊዮን ዶላር የተሸፈነ ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክም ይህንኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ ጋር የሚያገናኘውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ድጋፍ ለኢትዮጵያ 232 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 116 ሚሊዮን ዶላር አጽድቋል። ለኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እና ለሌሎች ሥራዎች በብድር ከተገኘው በተጨማሪ አገራቱም ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ለመስራት የራሳቸውን ወጪ አድርገዋል። ፕሮጀክቱ በምሥራቅ አፍሪካ ባሉ አገራት መካከል ድንበር ዘለል የኃይል ንግድ እንዲሁም ትስስርን ለማስተባበር በአውሮፓውያኑ 2005 የተቋቋመው ቀጠናዊ ተቋም ኢስተርን አፍሪካ ፓወር ፑል አካል ነው። በአጠቃላይ የኃይል ልማት እና ተግባር የማስተባበር ሥልጣን የተሰጠው ተቋም ዋና ጽህፈቱ በአዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን፣ አስራ አንድ አባል አገራት አሉት። እነሱም ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ እና ሊቢያ። ኮንጎ (ዲአርሲ)፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ናቸው። ፕሮጀክቱ እነዚህንም አገራት በኃይል የማስተሳሰርና የማዋሃድ አቅም እንዳለው ይነገራል። በሁለቱ አገራት የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርም እስከ 2000 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ያለው ነው። | ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከቀናት በኋላ ልትጀምር ነው ኢትዮጵያ ለጎረቤት አገር ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ኅዳር 5/2015 ዓ.ም ልትጀምር መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። የኤሌክትሪክ የማስተላለፍ የሙከራ ሥራ ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም በስኬት መከናወኑን ተከትሎም ወደ ኬንያ የሚደረገው የኤሌክትሪክ ኃይል የወጪ ንግድ ሊጀመር እንደሆነ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃለ አቀባይ መለስ ዓለም ገልጸዋል። አገራቱን በሚያገናኘው 500 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል መስመር ላይ የኃይል ማስተላለፍ የሙከራ ሥራ በይፋ መጀመሩን ያስታወቁት የፕሮጀክቱ የሳይት ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ አያሌው ናቸው። ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ ሙከራው በስኬት መከናወኑን ያስታወቁት ሥራ አስኪያጁ ይህም በቅርቡ አገሪቱ የምታደርገው የኃይል ሽያጭ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደሚሄድ አመላካች ነው ማለታቸውን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ከዚህ ቀደም የተለያዩ የኤሌክትሮ ሜካኒካል መሳሪያዎች ፍተሻዎች እንዲሁም ከቀናት በፊት የመገናኛ ሲግናል በመላክ ከኬንያ ኔትወርክ ጋር ማገናኘት መቻሉን ሥራ አስኪያጁ ማስታወቃቸው ተጠቅሷል። የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፉ በይፋ ሲጀመርም በሕብረተሰቡ ላይ አደጋ እንዳይደርስ መስመሩ ከሚያልፍባቸው ዞኖች ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መካሄዱም ተገልጿል። ከዚህም ጋር ተያይዞ የኃይል ማስተላለፍ ሙከራው በሚከወንበትም ወቅት ምንም አደጋ አለመድረሱንም አቶ ቴዎድሮስ መናገራቸው ተጠቁሟል። የግንባታ ሥራው በ2008 የተጀመረው የኢትዮ- ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር 334.5 ሚሊዮን ዶላር እንደፈጀ ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ የግንባታ ሥራ ከአራት ዓመት በፊት መጠናቀቁ ይታወሳል። ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ በኩል የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ግንባታ እና የፍተሻ እንዲሁም የሙከራ ሥራዎች ቢጠናቀቁም በኬንያ በኩል ቀሪ የዝርጋታ እና የግንባታ ሥራዎች እንዳሉ እየተነገረ መጀመር ከነበረበት ወቅት እየተጓተተ ረዘም ያሉ ወራት ተቆጥረዋል። የማስተላለፊያ መስመር የግንባታ ሥራው ሲኢቲ በተሰኘ የቻይና ኩባንያ ሲከናወን የኮንቨርተር ጣቢያውና ሌሎች ተግባራት ደግሞ ሲመንስ በተሰኘ ኩባንያ መከናወኑ ተገልጿል። ለምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ትስስር ከፍተኛ ስፍራ ያለው ይህ ፕሮጀክት 1.3 ቢሊዮን ዶላር ፈጅቷል። አገራቱን የሚያገናኘው የኤሌክትሪክ መስመር 500 ኪሎ ቮልትና ከኢትዮጵያ በኩል 440 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ በአጠቃላይ ከ1 ሺህ ሜትር በላይ ርዝማኔ ያለው ነው። ወጪውም ከዓለም ባንክ በተገኘው ብድር 684 ሚሊዮን ዶላር፣ ለኢትዮጵያ 441 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 27.4 ቢሊዮን ዶላር የተሸፈነ ነው። የአፍሪካ ልማት ባንክም ይህንኑ በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የግልገል ጊቤ ሦስት ግድብ ጋር የሚያገናኘውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ድጋፍ ለኢትዮጵያ 232 ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ለኬንያ 116 ሚሊዮን ዶላር አጽድቋል። ለኃይል ማስተላለፊያ መስመር ዝርጋታ እና ለሌሎች ሥራዎች በብድር ከተገኘው በተጨማሪ አገራቱም ይህንን ትልቅ ፕሮጀክት ለመስራት የራሳቸውን ወጪ አድርገዋል። ፕሮጀክቱ በምሥራቅ አፍሪካ ባሉ አገራት መካከል ድንበር ዘለል የኃይል ንግድ እንዲሁም ትስስርን ለማስተባበር በአውሮፓውያኑ 2005 የተቋቋመው ቀጠናዊ ተቋም ኢስተርን አፍሪካ ፓወር ፑል አካል ነው። በአጠቃላይ የኃይል ልማት እና ተግባር የማስተባበር ሥልጣን የተሰጠው ተቋም ዋና ጽህፈቱ በአዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን፣ አስራ አንድ አባል አገራት አሉት። እነሱም ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ እና ሊቢያ። ኮንጎ (ዲአርሲ)፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ናቸው። ፕሮጀክቱ እነዚህንም አገራት በኃይል የማስተሳሰርና የማዋሃድ አቅም እንዳለው ይነገራል። በሁለቱ አገራት የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመርም እስከ 2000 ሜጋ ዋት የመሸከም አቅም ያለው ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c4nr1py1j72o |
0business
| በለንደን በሕግ ዘርፍ የተሰማራ ኩባንያ ሠራተኞች በደመወዝ ቅናሽ በቋሚነት ከቤት እንዲሠሩ ፈቀደ | በለንደን የሚገኝ እና በሕግ ዘርፍ የሚሰራ አንድ ኩባንያ ሠራተኞች በቋሚነት ከቤት የሚሰሩበትን አማራጭ ይፋ አድርጓል። ሆኖም ይህንን አማራጭ የሚወስዱ ሠራተኞች ሙሉ ደመወዛቸውን አያገኙም። በለንደን የሚገኘው ስቴፈንሰን ሃርውድ የተባለው በሕግ የሥራ ዘርፍ ላይ የታወቀ ስም ያለው ድርጅት ያስቀመጠውን በቋሚነት ከቤት የመስራት አማራጭ የሚፈልጉ ሰዎች ከደመወዛቸው 20 በመቶው ይቆረጣል። የኮሮና ወረርሽኝ ይዟቸው ከመጡ ጉዳዮች አንዱ ከቤት መስራትን ነው። ሆኖም ከቤት መስራት ማንን ይጠቀማል? ማንን ይጎዳል? በሚል ሲያከራክር ቆይቷል። ከቤት በመስራት አሰሪም፣ ሠረተኛም እየተጠቀሙ ነው። ሠራተኞች ገንዘብ እና ጊዜያቸውን እንዲቆጥቡ ሲያግዝ አሰሪዎችን ደግሞ ለቢሮ ቦታ እና ሥራ ማስኬጂያ የሚያወጡትን ወጪ ቀንሷል። ሆኖም ሠራተኞች ከቤት ሲሰሩ የሚሰሩበት መጠን ወይም ምርታማነታቸው ዝቅ ይላል በሚል የሚከራከሩም አሉ። ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ሰዎች ወደ ሥራ ቦታቸው ለመሄድ የሚያጠፉትን ጊዜ በመቆጠብ በምሽት እና በእረፍት ሰዓት ብዙም ሳይረበሹ እንዲሰሩ ያስችላል የሚሉም አሉ። በቅርቡ በዩኬ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊ የሆኑት ጃኮብ ሪስሞግ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ከቤት መስራቱን ያቁም ማለታቸውን ተከትሎ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። በጉዳዩ ላይ በትምህርት ተቋማት የተደረጉ ጥናቶች ከቤት መስራት የሠራተኞችን ውጤታማነት ከፍ እንደሚያደረግ ያሳያሉ። በርካታ የግል ኩባንያዎች ደግሞ ከቤት እና ከቢሮ እያቀያየሩ ማሰራት ሰፋ ያለ የሥራ ቦታ እንዲኖር እንደሚያስችል እና ሠራተኞችንም እያስደሰተ መሆኑን ጠቁመዋል። ስቴፈን ሃርውድ የኮሮና ወርሽኝ በተከሰተበት ጊዜ ከቤት የሚሰሩ እና ከለንደን ውጪ ያሉ ሠራተኞችን በዝቅተኛ ደመወዝ መቅጠር መቻሉን ለቢቢሲ ገልጿል። ሆኖም እነዚህ ሠራተኞች ከቢሮ መስራት ቢፈልጉ የመጓጓዣ ወጪ መጠየቅ እንደሚችሉ ተናግሯል። የስቴፈን የሕግ ኩባንያ አሁን ያቀረበው አማራጭ ያላቸው ሠራተኞች ከቤት ለመስራት ማመልከት እንደሚችሉ ያስታወቀ ሲሆን ከቤት እና ከቢሮ የሚሰሩ ሰዎች በሁለት ዓይነት የደመወዝ ማዕቀፍ የሚሰሩበትን አሰራርም ዘርግቷል። በአጋርነት ከሚሰሩት ውጪ ሁሉም ሠራተኞች ቢሮ መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት የመስራት አማራጭ ተሰጥቷቸዋል። ኩባንያው ብዙ ሠራተኞች ከቤት የመስራት አማራጭን ይወስዳሉ ብሎ እንደማይጠብቅም ገልጿል። በዚህ አሰራር መሰረት ለድርጅቱ የተቀጠረን አንድ ሠራተኛ እንደ ምሳሌ ብንወስድ ደመወዙ 90 ሺህ ፓውንድ ቢሆን ከቤት ለመስራት ቢወስን ደመወዙ ወደ 72 ሺህ ፓውንድ ዝቅ ይላል ማለት ነው። አሁን ላይ ሠራተኞች በሳምንት እስከ ሁለት ቀን መስራት የሚችሉበት አማራጭ የተዘረጋ ሲሆን ይህ ቤት ከቤት እና ቢሮ እየቀያየሩ የመስራት አሰራር በድርጅቱ ሥር ላሉ በለንደን ፣ ፓሪስ ፣ ግሪክ ፣ ሆንግኮንግ ፣ ሲንጋፖር እና ደቡብ ኮሪያ ለሚገኙ 1 ሺህ 100 ሠራተኞች እየተተገበረ ነው። "ለአብዛኛው ሠራተኞቻችን ይህ ፖሊሲያችን በአግባቡ እየሰራ ነው" ሲሉም የድርጅቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ኒኮላስ ብሉም ከኮሮና ወርርሽኝ ማክተም በኋላ 10 በመቶ የሚሆነው ሠራተኛ ከቤቱ ይሰራል የሚል ግምት አስቀምጠዋል። እንደሳቸው ገለጻ ከሆነ ከቤት መስራት የሠራተኞችን ውጤታማነት ለመጨመር፤ እኩልነትን መሰረት ያላደረገን አሰራር ለማጥበብ እና ከበድ ያለ ሥራ የሚሰሩ ሰዎች በተሻለ ነጻነት እንዲሰሩ ያግዛል። የተወሰኑ ተቋማት ሠራተኞች በተቀየጠው አሰራርም ቢሆን ወደ ቢሮ መመለስን እየተቃወሙ ይገኛሉ። አፕል በሳምንት ሦስት ቀን ከቢሮ ለመስራት ያቀደ ሲሆን ይህ አሰራሩ ተቋሙን "የወጣቶች፣ የነጮች እና የወንዶች የበላይነት" የሚታይበት ያደርገዋል የሚል አስተያየት ቀርቦበታል። | በለንደን በሕግ ዘርፍ የተሰማራ ኩባንያ ሠራተኞች በደመወዝ ቅናሽ በቋሚነት ከቤት እንዲሠሩ ፈቀደ በለንደን የሚገኝ እና በሕግ ዘርፍ የሚሰራ አንድ ኩባንያ ሠራተኞች በቋሚነት ከቤት የሚሰሩበትን አማራጭ ይፋ አድርጓል። ሆኖም ይህንን አማራጭ የሚወስዱ ሠራተኞች ሙሉ ደመወዛቸውን አያገኙም። በለንደን የሚገኘው ስቴፈንሰን ሃርውድ የተባለው በሕግ የሥራ ዘርፍ ላይ የታወቀ ስም ያለው ድርጅት ያስቀመጠውን በቋሚነት ከቤት የመስራት አማራጭ የሚፈልጉ ሰዎች ከደመወዛቸው 20 በመቶው ይቆረጣል። የኮሮና ወረርሽኝ ይዟቸው ከመጡ ጉዳዮች አንዱ ከቤት መስራትን ነው። ሆኖም ከቤት መስራት ማንን ይጠቀማል? ማንን ይጎዳል? በሚል ሲያከራክር ቆይቷል። ከቤት በመስራት አሰሪም፣ ሠረተኛም እየተጠቀሙ ነው። ሠራተኞች ገንዘብ እና ጊዜያቸውን እንዲቆጥቡ ሲያግዝ አሰሪዎችን ደግሞ ለቢሮ ቦታ እና ሥራ ማስኬጂያ የሚያወጡትን ወጪ ቀንሷል። ሆኖም ሠራተኞች ከቤት ሲሰሩ የሚሰሩበት መጠን ወይም ምርታማነታቸው ዝቅ ይላል በሚል የሚከራከሩም አሉ። ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ሰዎች ወደ ሥራ ቦታቸው ለመሄድ የሚያጠፉትን ጊዜ በመቆጠብ በምሽት እና በእረፍት ሰዓት ብዙም ሳይረበሹ እንዲሰሩ ያስችላል የሚሉም አሉ። በቅርቡ በዩኬ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊ የሆኑት ጃኮብ ሪስሞግ ሁሉም የመንግሥት ሠራተኛ ከቤት መስራቱን ያቁም ማለታቸውን ተከትሎ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር። በጉዳዩ ላይ በትምህርት ተቋማት የተደረጉ ጥናቶች ከቤት መስራት የሠራተኞችን ውጤታማነት ከፍ እንደሚያደረግ ያሳያሉ። በርካታ የግል ኩባንያዎች ደግሞ ከቤት እና ከቢሮ እያቀያየሩ ማሰራት ሰፋ ያለ የሥራ ቦታ እንዲኖር እንደሚያስችል እና ሠራተኞችንም እያስደሰተ መሆኑን ጠቁመዋል። ስቴፈን ሃርውድ የኮሮና ወርሽኝ በተከሰተበት ጊዜ ከቤት የሚሰሩ እና ከለንደን ውጪ ያሉ ሠራተኞችን በዝቅተኛ ደመወዝ መቅጠር መቻሉን ለቢቢሲ ገልጿል። ሆኖም እነዚህ ሠራተኞች ከቢሮ መስራት ቢፈልጉ የመጓጓዣ ወጪ መጠየቅ እንደሚችሉ ተናግሯል። የስቴፈን የሕግ ኩባንያ አሁን ያቀረበው አማራጭ ያላቸው ሠራተኞች ከቤት ለመስራት ማመልከት እንደሚችሉ ያስታወቀ ሲሆን ከቤት እና ከቢሮ የሚሰሩ ሰዎች በሁለት ዓይነት የደመወዝ ማዕቀፍ የሚሰሩበትን አሰራርም ዘርግቷል። በአጋርነት ከሚሰሩት ውጪ ሁሉም ሠራተኞች ቢሮ መምጣት ሳይጠበቅባቸው ካሉበት የመስራት አማራጭ ተሰጥቷቸዋል። ኩባንያው ብዙ ሠራተኞች ከቤት የመስራት አማራጭን ይወስዳሉ ብሎ እንደማይጠብቅም ገልጿል። በዚህ አሰራር መሰረት ለድርጅቱ የተቀጠረን አንድ ሠራተኛ እንደ ምሳሌ ብንወስድ ደመወዙ 90 ሺህ ፓውንድ ቢሆን ከቤት ለመስራት ቢወስን ደመወዙ ወደ 72 ሺህ ፓውንድ ዝቅ ይላል ማለት ነው። አሁን ላይ ሠራተኞች በሳምንት እስከ ሁለት ቀን መስራት የሚችሉበት አማራጭ የተዘረጋ ሲሆን ይህ ቤት ከቤት እና ቢሮ እየቀያየሩ የመስራት አሰራር በድርጅቱ ሥር ላሉ በለንደን ፣ ፓሪስ ፣ ግሪክ ፣ ሆንግኮንግ ፣ ሲንጋፖር እና ደቡብ ኮሪያ ለሚገኙ 1 ሺህ 100 ሠራተኞች እየተተገበረ ነው። "ለአብዛኛው ሠራተኞቻችን ይህ ፖሊሲያችን በአግባቡ እየሰራ ነው" ሲሉም የድርጅቱ ቃል አቀባይ ተናግረዋል። በስታንፎርድ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ኒኮላስ ብሉም ከኮሮና ወርርሽኝ ማክተም በኋላ 10 በመቶ የሚሆነው ሠራተኛ ከቤቱ ይሰራል የሚል ግምት አስቀምጠዋል። እንደሳቸው ገለጻ ከሆነ ከቤት መስራት የሠራተኞችን ውጤታማነት ለመጨመር፤ እኩልነትን መሰረት ያላደረገን አሰራር ለማጥበብ እና ከበድ ያለ ሥራ የሚሰሩ ሰዎች በተሻለ ነጻነት እንዲሰሩ ያግዛል። የተወሰኑ ተቋማት ሠራተኞች በተቀየጠው አሰራርም ቢሆን ወደ ቢሮ መመለስን እየተቃወሙ ይገኛሉ። አፕል በሳምንት ሦስት ቀን ከቢሮ ለመስራት ያቀደ ሲሆን ይህ አሰራሩ ተቋሙን "የወጣቶች፣ የነጮች እና የወንዶች የበላይነት" የሚታይበት ያደርገዋል የሚል አስተያየት ቀርቦበታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61277155 |
5sports
| እግር ኳስ፡ ዛሬ የሚጀምረውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማን ያሸንፍ ይሆን? | በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2020/21 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ፉልሃም ከአርሰናል በሚያደርጉት ጨዋታ 8፡30 ሲል ይጀምራል። ዛሬ ከሚደረጉ 4 ጨዋታዎች መካከል፣ ያለፈው ዓመት የውድድር ዘመን አሸናፊዎቹ ሊቨርፑሎች፣ ፕሪምየር ሊጉ ከተቀላቀሉት ሊድስ ዩናይትድ ጋር በአንፊልድ የሚያደርጉት ጨዋታ አንዱ ነው። ማንችስተር ሲቲ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲና ዎልቭስ ፕሪምየር ሊጉ ከተጠናቀቀ በኋላ በአውሮፓ የውድድር መድረኮች ሲሳተፉ ስለነበር ጨዋታቸውን የሚጀምሩት በሚቀጥለው ሳምንት ነው። በዘንድሮ ፕሪሚየር ሊግድ ውድድር ፉልሃም፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ዌስት ብሮም አልቢን አዲስ ተሳታፊ ቡድኖች ናቸው። ሊድስ ዩናይትድ ከ16 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን ሲያረጋግጥ፣ ዌስት ብሮም ደግሞ በቻምፒየንሺፕ ውድድር እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ ጠብቆ ወደ ፕሪምየር ሊግ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ፉልሀም ደግሞ በመጨረሻው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ብርንትፎርድን በዌምብሌይ ስታዲየም በማሸነፍ በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ መሳተፍ የሚያስችላቸው ዕድል አግኝተዋል። ኖርዊች፣ ዋትፎርድና ቦርንማውዝ ወደ ቻምፒየንሺፑ በመውረድ ከላይ ለተጠቀሱት ሶስት ክለቦች ቦታቸውን የለቀቁ ቡድኖች መሆናቸው ይታወሳል። ደጋፊዎች ወደ ስታዲም መቼ ይመለሱ ይሆን? የዘንድሮው የውድድር ዓመት በዝግ ስታዲየሞች የሚጀመር ሲሆን የኮሮናቫይረስ ስርጭትና ሁኔታዎች እየታየ ተመልካቾች ቀስ በቀስ ወደ ስታዲየሞች መግባት እንደሚጀምሩም ተስፋ ተደርጓል። ምናልባትም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም የሚካሄዱት እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ብቻ ሊሆን ይችላል። አርሰናል ከሼፊልድ በኢሚሬትስ በሚያደርጉት ጨዋታ ታዳሚዎች በአነስተኛ ቁጥር ወደ ስታዲየም ሊመለሱ ይችላሉ የሚል ቅድመ ዝግጅት አለ። እንደውም አንዳንድ ቡድኖች በሙከራ ደረጃ የቅድመ ውድድር ጨዋታዎችና የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታዎች በተመልካቾች ፊት እንዲካሄድና ሁኔታዎች እየታዩ ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ሀሳብ አቅርበው ነበር። አዲስ ፈራሚዎች በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ከፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች እንደ ቼልሲ ድንቅ ተጫዋቾችን የሰበሰበ የለም። ፍራንክ ላምፓርድ እስካሁንም ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት ቸልሲዎች ደፋ ቀና እያሉ ነው። የተከላካይ መስመር ተጫዋቹን ቲያጎ ሲልቫ ከፈረንሳዩ ፒኤስጂ፣ የግራ መስመር ተመላላሹ ቢን ቺልዌልን ከሌስተር ሲቲ፣ የአያክሱን የክንፍ መስመር አጥቂ ሃኪም ዚዬክ፣ የአርፒ ሌፕሲዥ የጎል አነፍናፊው ቲሞ ቨርነር፣ የባየር ሊቨርኩሰን የጨዋታ አቀጣጣዩ ኪያ ሃርቭዝ እንዲሁም ወጣቱን ተከላካዩ ማላንግ ሳር ከኒስ አስፈርመዋል። በዘንድሮው የዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ደግሞ ኤቨርተኖች ናቸው። በካርሎ አንቸሎቲ የሚመሩት ኤቨርተኖች አብዱላዬ ዱኩሬን ከዋትፎርድ፣ ሃመስ ሮድሪጌዝን ከሪያል ማድሪድ እንዲሁም አላንን ከናፖሊ አስፈርመዋል። አርሰናል እስካሁን የሊሉን ተከላካይ ጋብሪኤል ማጋሊያስ እንዲሁም የቼልሲውን ዊሊያን ያስፈረመ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትዶች ደግሞ የአያክሱን የመሃል ሜዳ ተጫዋች ቫን ደ ቢክን አስፈርመዋል። ማን በበላይነት ያጠናቅቃል? የዘንድሮውን የውድድር ዓመት የትኛው ቡድን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል የሚለው ጥያቄ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያዎችን ለሁለት ከፍሏል። አንደኛው ጎራ ሊቨርፑሎች በድጋሚ ሻምፒዮን ይሆናሉ ሲል በሌላኛው ጎራ ደግሞ ዘንድሮ ማንቸስትር ሲቲዎች የሚያቆማቸው የለም ይላሉ። በርካታ አቋማሪ ድርጅቶች ግን ዘንድሮ ማንቸስተር ሲቲ እንደሚያሸንፍ ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ነገር ግን የሲቲዎች ደካማ የተከላካይ መስመር ብዙ ጎሎችን የሚያስተናግድ ከሆነ አሁንም ለሊቨርፑል ዋንጫውን አሳለፈው ሊሰጡ እንደሚችሉ ተገምቷል። ሊቨርፑሎችም ቢሆኑ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ቡድኑን ሊቀይር የሚችል ተጫዋች እስካሁን አለማስፈረማቸው ጨዋታዎቻቸውን ከባድ ሊያደርግባቸው እንደሚችል ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም ቡድኖች ከዚህ በኋላ ለሊቨርፑል የሚሆን አይነት አጨዋወት ይዘው እንደሚመጡ መገመት አይከብድም። ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ደግሞ ቡድናቸውን በማጠናከር ስራ ላይ እንደመሆናቸው መጠን ከአንድ እስከ አራት ውስጥ ይጨርሳሉ አይጨርሱም የሚለው እንጂ የሊጉ ሻምፒዮን እንደማይሆኑ ግልጽ ነው ብለዋል አቋማሪዎቹ ድርጅቶች። አርሰናል፣ ቶተንሃም፣ ሌስተር ሲቲና ኤቨርተን ደግሞ ከአምስተኛ በታች ያለውን ቦታ ይዘው እንደሚጨርሱ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። | እግር ኳስ፡ ዛሬ የሚጀምረውን የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ማን ያሸንፍ ይሆን? በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2020/21 እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ፉልሃም ከአርሰናል በሚያደርጉት ጨዋታ 8፡30 ሲል ይጀምራል። ዛሬ ከሚደረጉ 4 ጨዋታዎች መካከል፣ ያለፈው ዓመት የውድድር ዘመን አሸናፊዎቹ ሊቨርፑሎች፣ ፕሪምየር ሊጉ ከተቀላቀሉት ሊድስ ዩናይትድ ጋር በአንፊልድ የሚያደርጉት ጨዋታ አንዱ ነው። ማንችስተር ሲቲ፣ ማንችስተር ዩናይትድ፣ ቼልሲና ዎልቭስ ፕሪምየር ሊጉ ከተጠናቀቀ በኋላ በአውሮፓ የውድድር መድረኮች ሲሳተፉ ስለነበር ጨዋታቸውን የሚጀምሩት በሚቀጥለው ሳምንት ነው። በዘንድሮ ፕሪሚየር ሊግድ ውድድር ፉልሃም፣ ሊድስ ዩናይትድ እና ዌስት ብሮም አልቢን አዲስ ተሳታፊ ቡድኖች ናቸው። ሊድስ ዩናይትድ ከ16 ዓመታት ጥበቃ በኋላ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መመለሱን ሲያረጋግጥ፣ ዌስት ብሮም ደግሞ በቻምፒየንሺፕ ውድድር እስከመጨረሻው ጨዋታ ድረስ ጠብቆ ወደ ፕሪምየር ሊግ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። ፉልሀም ደግሞ በመጨረሻው የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ብርንትፎርድን በዌምብሌይ ስታዲየም በማሸነፍ በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ መሳተፍ የሚያስችላቸው ዕድል አግኝተዋል። ኖርዊች፣ ዋትፎርድና ቦርንማውዝ ወደ ቻምፒየንሺፑ በመውረድ ከላይ ለተጠቀሱት ሶስት ክለቦች ቦታቸውን የለቀቁ ቡድኖች መሆናቸው ይታወሳል። ደጋፊዎች ወደ ስታዲም መቼ ይመለሱ ይሆን? የዘንድሮው የውድድር ዓመት በዝግ ስታዲየሞች የሚጀመር ሲሆን የኮሮናቫይረስ ስርጭትና ሁኔታዎች እየታየ ተመልካቾች ቀስ በቀስ ወደ ስታዲየሞች መግባት እንደሚጀምሩም ተስፋ ተደርጓል። ምናልባትም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች በዝግ ስታዲየም የሚካሄዱት እስከ ጥቅምት ወር ድረስ ብቻ ሊሆን ይችላል። አርሰናል ከሼፊልድ በኢሚሬትስ በሚያደርጉት ጨዋታ ታዳሚዎች በአነስተኛ ቁጥር ወደ ስታዲየም ሊመለሱ ይችላሉ የሚል ቅድመ ዝግጅት አለ። እንደውም አንዳንድ ቡድኖች በሙከራ ደረጃ የቅድመ ውድድር ጨዋታዎችና የሊጉ የመክፈቻ ጨዋታዎች በተመልካቾች ፊት እንዲካሄድና ሁኔታዎች እየታዩ ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ሀሳብ አቅርበው ነበር። አዲስ ፈራሚዎች በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ከፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች እንደ ቼልሲ ድንቅ ተጫዋቾችን የሰበሰበ የለም። ፍራንክ ላምፓርድ እስካሁንም ስድስት ተጫዋቾችን ያስፈረመ ሲሆን ተጨማሪ ተጫዋቾችን ወደ ስታንፎርድ ብሪጅ ለማምጣት ቸልሲዎች ደፋ ቀና እያሉ ነው። የተከላካይ መስመር ተጫዋቹን ቲያጎ ሲልቫ ከፈረንሳዩ ፒኤስጂ፣ የግራ መስመር ተመላላሹ ቢን ቺልዌልን ከሌስተር ሲቲ፣ የአያክሱን የክንፍ መስመር አጥቂ ሃኪም ዚዬክ፣ የአርፒ ሌፕሲዥ የጎል አነፍናፊው ቲሞ ቨርነር፣ የባየር ሊቨርኩሰን የጨዋታ አቀጣጣዩ ኪያ ሃርቭዝ እንዲሁም ወጣቱን ተከላካዩ ማላንግ ሳር ከኒስ አስፈርመዋል። በዘንድሮው የዝውውር መስኮት በንቃት እየተሳተፉ የሚገኙት ደግሞ ኤቨርተኖች ናቸው። በካርሎ አንቸሎቲ የሚመሩት ኤቨርተኖች አብዱላዬ ዱኩሬን ከዋትፎርድ፣ ሃመስ ሮድሪጌዝን ከሪያል ማድሪድ እንዲሁም አላንን ከናፖሊ አስፈርመዋል። አርሰናል እስካሁን የሊሉን ተከላካይ ጋብሪኤል ማጋሊያስ እንዲሁም የቼልሲውን ዊሊያን ያስፈረመ ሲሆን ማንቸስተር ዩናይትዶች ደግሞ የአያክሱን የመሃል ሜዳ ተጫዋች ቫን ደ ቢክን አስፈርመዋል። ማን በበላይነት ያጠናቅቃል? የዘንድሮውን የውድድር ዓመት የትኛው ቡድን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል የሚለው ጥያቄ ደግሞ የዘርፉ ባለሙያዎችን ለሁለት ከፍሏል። አንደኛው ጎራ ሊቨርፑሎች በድጋሚ ሻምፒዮን ይሆናሉ ሲል በሌላኛው ጎራ ደግሞ ዘንድሮ ማንቸስትር ሲቲዎች የሚያቆማቸው የለም ይላሉ። በርካታ አቋማሪ ድርጅቶች ግን ዘንድሮ ማንቸስተር ሲቲ እንደሚያሸንፍ ግምታቸውን እያስቀመጡ ነው። ነገር ግን የሲቲዎች ደካማ የተከላካይ መስመር ብዙ ጎሎችን የሚያስተናግድ ከሆነ አሁንም ለሊቨርፑል ዋንጫውን አሳለፈው ሊሰጡ እንደሚችሉ ተገምቷል። ሊቨርፑሎችም ቢሆኑ በዘንድሮው የዝውውር መስኮት ቡድኑን ሊቀይር የሚችል ተጫዋች እስካሁን አለማስፈረማቸው ጨዋታዎቻቸውን ከባድ ሊያደርግባቸው እንደሚችል ባለሙያዎቹ አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም ቡድኖች ከዚህ በኋላ ለሊቨርፑል የሚሆን አይነት አጨዋወት ይዘው እንደሚመጡ መገመት አይከብድም። ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ደግሞ ቡድናቸውን በማጠናከር ስራ ላይ እንደመሆናቸው መጠን ከአንድ እስከ አራት ውስጥ ይጨርሳሉ አይጨርሱም የሚለው እንጂ የሊጉ ሻምፒዮን እንደማይሆኑ ግልጽ ነው ብለዋል አቋማሪዎቹ ድርጅቶች። አርሰናል፣ ቶተንሃም፣ ሌስተር ሲቲና ኤቨርተን ደግሞ ከአምስተኛ በታች ያለውን ቦታ ይዘው እንደሚጨርሱ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54115494 |
0business
| በሊባኖስ የኢኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ ተቃውሞዎች እየተባባሱ ነው | ሊባኖስ ያጋጠማትን የመገበያያ ገንዘቧ መድከምን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የሊባኖስ መገበያያ ገንዘብ ዋጋ በታሪኳ ዝቅተኛ ወደሚባል ደረጃ በመውረዱና 70 በመቶ የሚሆነውን አቅሙን በማጣቱ ከጥቅምት ወር ጀምሮ አገሪቷ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች ነው፡፡ ቁጣዎችም ተባብሰዋል፡፡ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተርም የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ ውይይት ለማድረግ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ ተቃውሞዎቹ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ እንደገና ተጀምሯል፡፡ የሊባኖስ ፓውንድ ዋጋ መውደቅ አገሪቷን በአስርት ዓመታት ውስጥ አስከፊ ወደ ሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ከቷታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ምንዛሬ ላይ የተሰማሩ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለድህነት ተዳርገዋል፡፡ በወረርሽኙ ወቅትም ችግራቸው ተባብሷል፡፡ በሊባኖሷ ከተማ ቤሩት የቢቢሲ ዘጋቢ ሊና ሲንጃብ እንደገለጸችው፤ ሐሙስ ዕለት ምሽት በከተማዋ እንብርት ላይ ተሰባስበው የነበሩ ተቃዋሚዎች እሳት በማቀጣጠል እና መንገዶችን በመዝጋት ቁጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን የአኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ በመጀመሪያዎቹ ወራት በነበሩት ተቃውሞዎች ፖለቲካዊ ለውጥ ለመጠየቅ የተደረጉ ቢሆንም የአሁኑ ግን መነሻው ርሃብ ነው፡፡ በአገሪቷ የሥራ አጦች ቁጥር ከፍተኛ ሆኗል፡፡ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለሰሩበት የሚከፈላቸው ዋጋው በወደቀው የአገሪቷ ገንዘብ ነው፡፡ በመሆኑም ለአብዛኞቹ ቤተሰቦች ምግብና መሰረታዊ ፍላጎትን ማሟላት ፈታኝ ሆኗል፡፡ ከተቃዋሚዎቹ መካከል አንዷ "ሊባኖስ ሁል ጊዜ በተቃውሞ ውስጥ ነው ያለችው ፤ ይህ ማለት ጥረታችን እና ጩኸታችን ለውጥ ማምጣት አልቻለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በበለጠ ተቃውሞ ማሰማት አለብን" ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ አብዛኞቹ አሁን እየታየ ያለው ችግር እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ 1975 ሊባኖስ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደሚያስታውሳቸው እና ተቃውሞው በዚህ ሁኔታ እየቀጠለ ከሄደ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል አሳስቧቸዋል፡፡ ሌላኛው ተቃዋሚም "ዛሬ የአንድ ዶላር ምንዛሬ 7ሺህ የሊባኖስ ፓውንድ ደርሷል፡፡ የቤት ኪራይ ለመክፈልም ሆነ ምግብ ለመመገብ አልቻልንም ፤ በመሆኑም የዶላር ምንዛሬው ዝቅ ካላላ በስተቀር እና ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ እዚሁ እንቆያለን ፤ ያገኘነው ጠቅላይ ሚኒስተርም ከዚህ ቀደም ከነበረው የባሰ ነው" ብለዋል፡፡ ከቤሩት ውጭ ያሉ በርካታ መንገዶች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው፡፡ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽን ቀድሞም ሌባኖስ በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቅ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡ ይህም ባለፈው ዓመት ጸረ መንግሥት ተቃውሞዎችን አስነስቷል፡፡ ምንም እንኳን የአገሪቷ መንግሥት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሰጠው ምላሽ ቢመሰገንም ግማሽ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው ከድህነት ወለል በታች ነው፡፡ የመገበያያ ገንዘብ ዋጋው መውደቅም የዋጋ ግሽበት በማስከተሉ የገቢ ንግድ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የንግድ ተቋማት ኪሳራ አጋጥሟቸዋል፡፡ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ህዝቧም ሥራ አጥ ሆኗል፡፡ | በሊባኖስ የኢኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ ተቃውሞዎች እየተባባሱ ነው ሊባኖስ ያጋጠማትን የመገበያያ ገንዘቧ መድከምን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል፡፡ የሊባኖስ መገበያያ ገንዘብ ዋጋ በታሪኳ ዝቅተኛ ወደሚባል ደረጃ በመውረዱና 70 በመቶ የሚሆነውን አቅሙን በማጣቱ ከጥቅምት ወር ጀምሮ አገሪቷ ተቃውሞዎችን እያስተናገደች ነው፡፡ ቁጣዎችም ተባብሰዋል፡፡ የአገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስተርም የኢኮኖሚ ቀውስ ላይ ውይይት ለማድረግ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ ጠርተዋል፡፡ ተቃውሞዎቹ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በተጣለው የእንቅስቃሴ ገደብ ሳቢያ ጋብ ብሎ የነበረ ቢሆንም በቅርቡ እንደገና ተጀምሯል፡፡ የሊባኖስ ፓውንድ ዋጋ መውደቅ አገሪቷን በአስርት ዓመታት ውስጥ አስከፊ ወደ ሆነ የኢኮኖሚ ቀውስ ከቷታል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ምንዛሬ ላይ የተሰማሩ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለድህነት ተዳርገዋል፡፡ በወረርሽኙ ወቅትም ችግራቸው ተባብሷል፡፡ በሊባኖሷ ከተማ ቤሩት የቢቢሲ ዘጋቢ ሊና ሲንጃብ እንደገለጸችው፤ ሐሙስ ዕለት ምሽት በከተማዋ እንብርት ላይ ተሰባስበው የነበሩ ተቃዋሚዎች እሳት በማቀጣጠል እና መንገዶችን በመዝጋት ቁጣቸውን ገልጸዋል፡፡ ምንም እንኳን የአኮኖሚ ቀውሱን ተከትሎ በመጀመሪያዎቹ ወራት በነበሩት ተቃውሞዎች ፖለቲካዊ ለውጥ ለመጠየቅ የተደረጉ ቢሆንም የአሁኑ ግን መነሻው ርሃብ ነው፡፡ በአገሪቷ የሥራ አጦች ቁጥር ከፍተኛ ሆኗል፡፡ አብዛኞቹ ሊባኖሳዊያንም ለሰሩበት የሚከፈላቸው ዋጋው በወደቀው የአገሪቷ ገንዘብ ነው፡፡ በመሆኑም ለአብዛኞቹ ቤተሰቦች ምግብና መሰረታዊ ፍላጎትን ማሟላት ፈታኝ ሆኗል፡፡ ከተቃዋሚዎቹ መካከል አንዷ "ሊባኖስ ሁል ጊዜ በተቃውሞ ውስጥ ነው ያለችው ፤ ይህ ማለት ጥረታችን እና ጩኸታችን ለውጥ ማምጣት አልቻለም ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ በበለጠ ተቃውሞ ማሰማት አለብን" ብለዋል፡፡ ይሁን እንጅ አብዛኞቹ አሁን እየታየ ያለው ችግር እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ 1975 ሊባኖስ ወደ እርስ በርስ ጦርነት ቀድሞ የነበረውን ጊዜ እንደሚያስታውሳቸው እና ተቃውሞው በዚህ ሁኔታ እየቀጠለ ከሄደ ወዴት ሊያመራ እንደሚችል አሳስቧቸዋል፡፡ ሌላኛው ተቃዋሚም "ዛሬ የአንድ ዶላር ምንዛሬ 7ሺህ የሊባኖስ ፓውንድ ደርሷል፡፡ የቤት ኪራይ ለመክፈልም ሆነ ምግብ ለመመገብ አልቻልንም ፤ በመሆኑም የዶላር ምንዛሬው ዝቅ ካላላ በስተቀር እና ጥያቄዎቻችን ካልተመለሱ እዚሁ እንቆያለን ፤ ያገኘነው ጠቅላይ ሚኒስተርም ከዚህ ቀደም ከነበረው የባሰ ነው" ብለዋል፡፡ ከቤሩት ውጭ ያሉ በርካታ መንገዶች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው፡፡ ከኮሮናቫይረስ ወረርሽን ቀድሞም ሌባኖስ በታሪኳ አጋጥሟት የማያውቅ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ገብታለች፡፡ ይህም ባለፈው ዓመት ጸረ መንግሥት ተቃውሞዎችን አስነስቷል፡፡ ምንም እንኳን የአገሪቷ መንግሥት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሰጠው ምላሽ ቢመሰገንም ግማሽ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው ከድህነት ወለል በታች ነው፡፡ የመገበያያ ገንዘብ ዋጋው መውደቅም የዋጋ ግሽበት በማስከተሉ የገቢ ንግድ ላይ ተጽዕኖ አሳድሯል፡፡ በሺህዎች የሚቆጠሩ የንግድ ተቋማት ኪሳራ አጋጥሟቸዋል፡፡ አንድ ሦስተኛ የሚሆነው ህዝቧም ሥራ አጥ ሆኗል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-53025567 |
5sports
| ትናንት ፍጹም ቅጣት ምት በሳቱት ጥቁር እንግሊዛውያን ላይ የዘረኝነት ጥቃት ደርሷል ተባለ | ትናንት ጣሊያን እንግሊዝን በፍጹም ቅጣት ምት አሸንፋ ሻምፒዮን ስትሆን ሦስት ፍጹም ቅጣት ምት በሳቱት ጥቁር እንግሊዛውያን ላይ የዘረኝነት ጥቃት መድረሱ ተነገረ። ጣሊያ እና እንግሊዝ በመደበኛው እና በተጨማሪ ሰዓት 1ለ1 በማጠናቀቃቸው አሸናፊውን ለመለየት ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት ተሸጋግረው ነበር። ይሁን እንጂ ማርከስ ራሽፎርድ የመታት ፍጹም ቅጣት ምት በግቡ ብረት ሲመለስ ጄደን ሳንቾ እና ቡካዮ ሳካ የመቷቸው ኳሶች በጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ተመልሰዋል። ይህን ተከትሎ በሦስቱ ተጫዋቾች ላይ በማህበራዊ ድር አምባ የዘረኝነት ጥቃት ደርሶባቸዋል። በጉዳዩ ላይ የእንግሊዝ እገር ኳስ ማህበር ያተገቢ ያልሆነ ሲል ፖሊስ ደግሞ ምርመራ ጀምሬያለሁ ብሏል። እንግሊዝ ለትልቅ ክብር ለመብቃት ከ55 ዓመት በላይ ያደረገች ጥበቃ ሳይሳካለት ቀርቷል። የማንቸስትር ዩናይትዱ ሉክ ሾው በሁለተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል እንግሊዝ ባለ ክብር ለመሆን በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሆነች አስመስሎ ነበር። በ33 ጨዋታዎች ያልተሸነፈችው ጣሊያን ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ በ67ኛው ደቂቃ በተከላካዩ ሊዮናርዶ ቦኑቺ ጎል አቻ ለመሆን በቃች። ጨዋተው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ቢያመራም ጎል መቆጠር ሳይችል ቀርቷል። ጨዋተው በፍጹም ቅጣት ምት ሲጠናቀቅ ሦስት እንግሊዝ ተጨቻዋቾች ዕድሎቻቸውን ሳይጠቀሙ ቀርተዋል። አምበሉ ሃሪ ኬን እና ተከላካዪ ሃሪ ማጓየር ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር የቻሉ የእንግሊዝ ተጫዋቾች ናቸው። የእንግሊዙ ግብ ጠባቂ ፒክፎርድ በበኩሉ የአንድሪያ ቤሎቲ እና የጆርጂንሆን ኳሶች በማዳን የቡድኑን ተስፋ ማለምለም ችሎ ነበር። ዶሜኒኮ ቤራዲ፣ ሊዮናርዶ ቦኑቺ እና ፌደሪኮ በርናርዴስኪ ደግሞ ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ጎልነት የቀየሩ ተጫዋቾች ናቸው። ራሽፎርድ እና ሳንቾ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ተቀይረው የገቡ ሲሆን የአንግሊዙ አሰልጠኝ ጋሬት ሳውዝጌት ለፍጹም ቅጣት ምት ብለው ቀይረው እንዳስገቧቸው ቢገመትም ሳይሳካለቸው ቀርቷል። ጣሊያኖችም ያለመሸነፍ ክብራቸው ወደ 34 ጨዋታዎች ባሳደጉበት ምሽት የዩሮ 2020 ክብርን ለመጎናጸፍ በቅተዋል። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ በዕድሜ የገፉ ተጫዋቾችን ከወጣቶች ጋር በማቀናጀት ምርጥ የሚባል ውድድር ለማሳለፍ ችለዋል። ቡድናቸው በውድድሩ ላይ እንደ ቤልጂም እና ስፔን ያሉ ቡድኖችን በማሸነፍ ነው ለፍጻሜ የበቃው። ለ2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ተስኗት ለነበረችው ጣሊያን ድሉ የማንቺኒ እና የቡድኑ ጠንካራ ሥራ ውጤት ተደርጎ ተወስዷል። ጣሊያን በትላንት ምሽቱ ጨዋታ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ በጎል ሙከራ ከእንግሊዝ የተሻለች ሆና አምሽታለች። "ሽንፈቱ የሚያሳምም ነው" ሽንፈቱን "የሚያሳምም"? ያሉት አሰልጣኝ ሳውዝጌት ተጫዋቾቻቸው "ማድረግ የሚችሉትን በሙሉ ማድረጋቸውን" ተናግረዋል። "ሁላችንም በህብረት ቆመን ነበር። ተጫዋቾቹ ለሃገራቸው የማይታመን አስደሳች ጊዜን ሰጥተው ነበር" ብለዋል። የ22 ዓመቱ ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል። ስፔናዊው የ18 ዓመቱ አማካይ ፕድሪ የውድድሩ ወጣት ኮከብ ተጫዋች ለመባል በቅቷል። ፑርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት ጎሎች እና አንድ ለጎል አመቻችቶ ኳስ በማቀበሉ የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ አጠናቋል። | ትናንት ፍጹም ቅጣት ምት በሳቱት ጥቁር እንግሊዛውያን ላይ የዘረኝነት ጥቃት ደርሷል ተባለ ትናንት ጣሊያን እንግሊዝን በፍጹም ቅጣት ምት አሸንፋ ሻምፒዮን ስትሆን ሦስት ፍጹም ቅጣት ምት በሳቱት ጥቁር እንግሊዛውያን ላይ የዘረኝነት ጥቃት መድረሱ ተነገረ። ጣሊያ እና እንግሊዝ በመደበኛው እና በተጨማሪ ሰዓት 1ለ1 በማጠናቀቃቸው አሸናፊውን ለመለየት ቡድኖቹ ወደ መለያ ምት ተሸጋግረው ነበር። ይሁን እንጂ ማርከስ ራሽፎርድ የመታት ፍጹም ቅጣት ምት በግቡ ብረት ሲመለስ ጄደን ሳንቾ እና ቡካዮ ሳካ የመቷቸው ኳሶች በጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ ተመልሰዋል። ይህን ተከትሎ በሦስቱ ተጫዋቾች ላይ በማህበራዊ ድር አምባ የዘረኝነት ጥቃት ደርሶባቸዋል። በጉዳዩ ላይ የእንግሊዝ እገር ኳስ ማህበር ያተገቢ ያልሆነ ሲል ፖሊስ ደግሞ ምርመራ ጀምሬያለሁ ብሏል። እንግሊዝ ለትልቅ ክብር ለመብቃት ከ55 ዓመት በላይ ያደረገች ጥበቃ ሳይሳካለት ቀርቷል። የማንቸስትር ዩናይትዱ ሉክ ሾው በሁለተኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል እንግሊዝ ባለ ክብር ለመሆን በትክክለኛው መንገድ ላይ እንደሆነች አስመስሎ ነበር። በ33 ጨዋታዎች ያልተሸነፈችው ጣሊያን ቀስ በቀስ ወደ ጨዋታው በመመለስ በ67ኛው ደቂቃ በተከላካዩ ሊዮናርዶ ቦኑቺ ጎል አቻ ለመሆን በቃች። ጨዋተው ወደ ተጨማሪ ሰዓት ቢያመራም ጎል መቆጠር ሳይችል ቀርቷል። ጨዋተው በፍጹም ቅጣት ምት ሲጠናቀቅ ሦስት እንግሊዝ ተጨቻዋቾች ዕድሎቻቸውን ሳይጠቀሙ ቀርተዋል። አምበሉ ሃሪ ኬን እና ተከላካዪ ሃሪ ማጓየር ከፍጹም ቅጣት ምት ማስቆጠር የቻሉ የእንግሊዝ ተጫዋቾች ናቸው። የእንግሊዙ ግብ ጠባቂ ፒክፎርድ በበኩሉ የአንድሪያ ቤሎቲ እና የጆርጂንሆን ኳሶች በማዳን የቡድኑን ተስፋ ማለምለም ችሎ ነበር። ዶሜኒኮ ቤራዲ፣ ሊዮናርዶ ቦኑቺ እና ፌደሪኮ በርናርዴስኪ ደግሞ ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ጎልነት የቀየሩ ተጫዋቾች ናቸው። ራሽፎርድ እና ሳንቾ በጨዋታው መገባደጃ ላይ ተቀይረው የገቡ ሲሆን የአንግሊዙ አሰልጠኝ ጋሬት ሳውዝጌት ለፍጹም ቅጣት ምት ብለው ቀይረው እንዳስገቧቸው ቢገመትም ሳይሳካለቸው ቀርቷል። ጣሊያኖችም ያለመሸነፍ ክብራቸው ወደ 34 ጨዋታዎች ባሳደጉበት ምሽት የዩሮ 2020 ክብርን ለመጎናጸፍ በቅተዋል። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ በዕድሜ የገፉ ተጫዋቾችን ከወጣቶች ጋር በማቀናጀት ምርጥ የሚባል ውድድር ለማሳለፍ ችለዋል። ቡድናቸው በውድድሩ ላይ እንደ ቤልጂም እና ስፔን ያሉ ቡድኖችን በማሸነፍ ነው ለፍጻሜ የበቃው። ለ2018ቱ የሩሲያ የዓለም ዋንጫ ማለፍ ተስኗት ለነበረችው ጣሊያን ድሉ የማንቺኒ እና የቡድኑ ጠንካራ ሥራ ውጤት ተደርጎ ተወስዷል። ጣሊያን በትላንት ምሽቱ ጨዋታ በኳስ ቁጥጥርም ሆነ በጎል ሙከራ ከእንግሊዝ የተሻለች ሆና አምሽታለች። "ሽንፈቱ የሚያሳምም ነው" ሽንፈቱን "የሚያሳምም"? ያሉት አሰልጣኝ ሳውዝጌት ተጫዋቾቻቸው "ማድረግ የሚችሉትን በሙሉ ማድረጋቸውን" ተናግረዋል። "ሁላችንም በህብረት ቆመን ነበር። ተጫዋቾቹ ለሃገራቸው የማይታመን አስደሳች ጊዜን ሰጥተው ነበር" ብለዋል። የ22 ዓመቱ ጣሊያናዊው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ የውድድሩ ኮከብ ተጫዋች ተብሎ ተመርጧል። ስፔናዊው የ18 ዓመቱ አማካይ ፕድሪ የውድድሩ ወጣት ኮከብ ተጫዋች ለመባል በቅቷል። ፑርቹጋላዊው ክርስቲያኖ ሮናልዶ በአምስት ጎሎች እና አንድ ለጎል አመቻችቶ ኳስ በማቀበሉ የውድድሩ ኮከብ ጎል አግቢ ሆኖ አጠናቋል። | https://www.bbc.com/amharic/57774763 |
0business
| ሩሲያ ወደ አውሮፓ ጋዝ የሚያስተላልፈውን ዋና መስመር እንደገና ዘጋች | ሩሲያ ለጥገና በሚል ወደ አውሮፓ የሚሄደውን ኖርድ ስትሪም 1 የተሰኘውን የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧን እንደገና ዘጋች። በዚህም ለአውሮፓ የሚደርሰው የጋዝ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ቆሟል። በሩሲያ መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳዳረው ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ጋዝፕሮም ኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ላይ የተጣለው ገደብ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት ይቆያል ብሏል። ሩሲያ ቀደም ሲልም በቧንቧው በኩል ወደ ውጪ የሚላከውን ጋዝ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሳለች። በምዕራባውያን አገራት ላይ የኃይል አቅርቦትን እንደ መሳሪያ ተጠቅማለች የሚለውን ክስም ውድቅ አድርጋለች። የኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ከሩሲያ ባሕር ዳርቻ ሴንት ፒተርስበርግ ተነስቶ በባልቲክ ባሕር ስር 1 ሺህ 200 ኪሎሜትር ሸፍኖ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ጀርመን ድረስ የሚዘልቅ ነው። በአውሮፓውያኑ 2011 አገልግሎት መስጠት የጀመረው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው በቀን ከፍተኛውን 170 ሚሊዮን ኪዪቡክ ሜትር ጋዝ ከሩሲያ ወደ ጀርመንም መላክ ይችላል። ከዚህ ቀደም ሩሲያ በየዓመቱ ለምታካሂደው የጥገና ሥራ ለአስር ቀናት ዘግታው የነበረ ሲሆን፣ ከተከፈተ በኋላም በ20 በመቶ አቅም ብቻ እየሰራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ሩሲያ ችግር ያለባቸው መሳሪያዎች ስላሉ ነው ብላለች። የጀርመን የኔትወርክ ተቆጣጣሪ ፕሬዝዳንት ሩሲያ በሚቀጥሉት ቀናት አቅርቦት ከጀመረች አገሪቱ ባላት ክምችት መቋቋም እንደምትችል ተናግረዋል። "ችግሩን ለመቋቋም እንደምንችል እገምታለሁ፤ ሩሲያ በመጪው ቅዳሜ ወደ 20 በመቶ መላክ እንደምትጀምር አምናለሁ፤ ነገር ግን ማንም በትክክል ይህንን በእርግጠኛነት መናገር አይችልም" በማለት ክላውስ ሙለር ለሮይተርስ ተናግረዋል። ነገር ግን የጀርመኑ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሮበርት ሃቤክ ለፋይናንሺያል ታይምስ እንደተናገሩት እርምጃው ከወዲሁ አንዳንድ የጀርመን ኩባንያዎች ምርታቸውን እንዲያቆሙ አስገድዷቸዋል፣ በአሁኑ ወቅት የተፈጠረው ጉዳይ "አሳዛኝ ነው" ብለዋል። | ሩሲያ ወደ አውሮፓ ጋዝ የሚያስተላልፈውን ዋና መስመር እንደገና ዘጋች ሩሲያ ለጥገና በሚል ወደ አውሮፓ የሚሄደውን ኖርድ ስትሪም 1 የተሰኘውን የጋዝ ማስተላለፊያ ቧንቧን እንደገና ዘጋች። በዚህም ለአውሮፓ የሚደርሰው የጋዝ አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ቆሟል። በሩሲያ መንግሥት ባለቤትነት የሚተዳዳረው ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ጋዝፕሮም ኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ላይ የተጣለው ገደብ ለሚቀጥሉት ሦስት ቀናት ይቆያል ብሏል። ሩሲያ ቀደም ሲልም በቧንቧው በኩል ወደ ውጪ የሚላከውን ጋዝ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሳለች። በምዕራባውያን አገራት ላይ የኃይል አቅርቦትን እንደ መሳሪያ ተጠቅማለች የሚለውን ክስም ውድቅ አድርጋለች። የኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ ከሩሲያ ባሕር ዳርቻ ሴንት ፒተርስበርግ ተነስቶ በባልቲክ ባሕር ስር 1 ሺህ 200 ኪሎሜትር ሸፍኖ እስከ ሰሜን ምሥራቅ ጀርመን ድረስ የሚዘልቅ ነው። በአውሮፓውያኑ 2011 አገልግሎት መስጠት የጀመረው የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው በቀን ከፍተኛውን 170 ሚሊዮን ኪዪቡክ ሜትር ጋዝ ከሩሲያ ወደ ጀርመንም መላክ ይችላል። ከዚህ ቀደም ሩሲያ በየዓመቱ ለምታካሂደው የጥገና ሥራ ለአስር ቀናት ዘግታው የነበረ ሲሆን፣ ከተከፈተ በኋላም በ20 በመቶ አቅም ብቻ እየሰራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ ሩሲያ ችግር ያለባቸው መሳሪያዎች ስላሉ ነው ብላለች። የጀርመን የኔትወርክ ተቆጣጣሪ ፕሬዝዳንት ሩሲያ በሚቀጥሉት ቀናት አቅርቦት ከጀመረች አገሪቱ ባላት ክምችት መቋቋም እንደምትችል ተናግረዋል። "ችግሩን ለመቋቋም እንደምንችል እገምታለሁ፤ ሩሲያ በመጪው ቅዳሜ ወደ 20 በመቶ መላክ እንደምትጀምር አምናለሁ፤ ነገር ግን ማንም በትክክል ይህንን በእርግጠኛነት መናገር አይችልም" በማለት ክላውስ ሙለር ለሮይተርስ ተናግረዋል። ነገር ግን የጀርመኑ ኢኮኖሚ ሚኒስትር ሮበርት ሃቤክ ለፋይናንሺያል ታይምስ እንደተናገሩት እርምጃው ከወዲሁ አንዳንድ የጀርመን ኩባንያዎች ምርታቸውን እንዲያቆሙ አስገድዷቸዋል፣ በአሁኑ ወቅት የተፈጠረው ጉዳይ "አሳዛኝ ነው" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw9d8x9lz9do |
2health
| ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ መመሪያ አዘጋጀች | ኢትዮጵያ በአገር አፍ ደረጃ በበሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ማዘጋጀቷን ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል። በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሞት መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ለማዘጋጅት መነሻ የሆነው የኮሮኖቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑም ተገልጿል። መመሪያወው በማህበረሰቡ ውስጥ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን ጭምር ማካተት እንደሚኖርበት ታምኖ የአገሪቱን የሞት መጠን የሚያሳውቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል። በተለይም እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሞቱን መጠን በትክክል ለማወቅ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሞት መጠን ለመገምገም፣ በሽታው የትኛውን የማህበረሰብ ክፍል በፆታ፣ በእድሜና ሌሎች መስፈርቶች አስመልክቶ የትኛውን አካል ነው እያጠቃ ነው የሚለውን በተመለከተ መመሪያው ምላሽ ይሰጣል ተብሏል። መመሪያው ይፋ የተደረገው ግንቦት 11፣ 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ነው። መመሪያው ይፋ መሆኑን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የጤና ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ መስጠት ዳይሬክቶሬት የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ዳሰሳ እና ምላሽ መስጠት ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ሮዚና ታሪኩ ከመረጃዎች አሰባሰብና መለኪያ ጋርም ተያይዞ ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች በመመሪያው መካተታቸውን አስታውቀዋል። መመሪያው መጠናቀቁን አስመልክቶ አዳማ በነበረው ዝግጅት ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደተናገሩት መመሪያው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጉዳት ሳያደርሱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል። መመሪያውን በማዘጋጀቱ በኩል የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የክልሎች የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር እና የአጋር ድርጅት ተወካይ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውም ከመረጃው መረዳት ተችሏል። | ኢትዮጵያ በአገር አቀፍ ደረጃ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ መመሪያ አዘጋጀች ኢትዮጵያ በአገር አፍ ደረጃ በበሽታ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎችን መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ማዘጋጀቷን ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ካገኘው መረጃ መረዳት ችሏል። በአገሪቱ ውስጥ ያለውን የሞት መጠን ለማወቅ የሚያስችል የቅኝት መመሪያ ለማዘጋጅት መነሻ የሆነው የኮሮኖቫይረስ ወረርሽኝ መሆኑም ተገልጿል። መመሪያወው በማህበረሰቡ ውስጥ በበሽታ የሚሞቱ ሰዎችን ጭምር ማካተት እንደሚኖርበት ታምኖ የአገሪቱን የሞት መጠን የሚያሳውቅ መመሪያ ተዘጋጅቷል ተብሏል። በተለይም እንዲህ አይነት ወረርሽኞች ሲከሰቱ የሞቱን መጠን በትክክል ለማወቅ፣ ከዚህ ቀደም የነበረውን የሞት መጠን ለመገምገም፣ በሽታው የትኛውን የማህበረሰብ ክፍል በፆታ፣ በእድሜና ሌሎች መስፈርቶች አስመልክቶ የትኛውን አካል ነው እያጠቃ ነው የሚለውን በተመለከተ መመሪያው ምላሽ ይሰጣል ተብሏል። መመሪያው ይፋ የተደረገው ግንቦት 11፣ 2013 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ነው። መመሪያው ይፋ መሆኑን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጡት የጤና ክስተቶች ቅኝትና ምላሽ መስጠት ዳይሬክቶሬት የእናቶችና ጨቅላ ህጻናት ሞት ዳሰሳ እና ምላሽ መስጠት ቡድን አስተባባሪ ወ/ሮ ሮዚና ታሪኩ ከመረጃዎች አሰባሰብና መለኪያ ጋርም ተያይዞ ወሳኝ የሚባሉ ጉዳዮች በመመሪያው መካተታቸውን አስታውቀዋል። መመሪያው መጠናቀቁን አስመልክቶ አዳማ በነበረው ዝግጅት ላይ የኢንስቲትዩቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ አስቻለው አባይነህ እንደተናገሩት መመሪያው የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች ጉዳት ሳያደርሱ ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊ ነው ብለዋል። መመሪያውን በማዘጋጀቱ በኩል የጤና ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ የክልሎች የህብረተሰብ ጤና አደጋ ቁጥጥር እና የአጋር ድርጅት ተወካይ ባለሙያዎች ተሳትፎ ማድረጋቸውም ከመረጃው መረዳት ተችሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57188529 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ውጤትን በ30 ደቂቃ ውስጥ ማወቅ ሊቻል ነው | ኮቪድ-19ን በደቂቃዎች ውስጥ የሚለይ ምርመራ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመለየት ስራን በእጅጉ ያሳድጋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ። አምስት ዶላር ብቻ የሚያስወጣው ይህ ምርመራ ሃብታም ባልሆኑ እና የጤና ባለሙያዎችና የላብራቶሪ እጥረት ባለባቸው አገራት የኮቪድ-19 ሕሙማንን ለመለየት በእጅጉ ይረዳል ተብሏል። መመርመሪያውን ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር የተደረገ ስምምነት በስድስት ወር ውስጥ 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ያስችላል። ይህንን እርምጃ የጤና ድርጅቱ የበላይ ኃላፊዎች "ጉልህ ሚና የሚጫወት" ብለውታል። በበርካታ አገራት ምርመራ ከተደረገ በኋላ ውጤት ለማወቅ የሚፈጀው ጊዜ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚያርጉትን ትግል ጎድቶት ቆይቷል። እንደ ሕንድና ሜክሲኮ ባሉ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ በተሰራጨባቸው አገራት በፍጥነት መርምሮ ውጤቱን ማወቅ አለመቻል የወረርሽኙን የመስፋፋት ፍጥነት ትክክለኛ ምስል ማሳየት አልቻለም ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ አዲሱ "ተንቀሳቃሽ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ" መመርመሪያ ውጤትን ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰኞ እለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ግን የኮሮናቫይረስን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት ካልሆነም ቀናት እንደሚፈጅ ይታወቃል። አቦት እና ኤስዲ ባዮሴንሰር የተባሉ መድሃኒት አምራቾች ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ስምምነት መድረሳቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረው ገልፀዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት የሚመረቱ መመርመሪያዎች በቫይረሱ በጣም የተጎዱ የላቲን አሜሪካ አገራትን ጨምሮ ለ133 አገራት ይሰጣል ተብሏል። "ይህ በተለይ ከፍተኛ ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች የመመርመር አቅም ላይ ትልቅ እመርታ የሚፈጥር ነው" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። አክለውም "ላቦራቶሪ በሌላቸውና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ወይንም ምርመራውን ለማካሄድ በቂ የሰለጠነ ባለሙያ በሌለበት አካባቢ የመመርመር አቅምን ያሰፋል።'' | ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ውጤትን በ30 ደቂቃ ውስጥ ማወቅ ሊቻል ነው ኮቪድ-19ን በደቂቃዎች ውስጥ የሚለይ ምርመራ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት ውስጥ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመለየት ስራን በእጅጉ ያሳድጋል ሲል የዓለም ጤና ድርጅት ተናገረ። አምስት ዶላር ብቻ የሚያስወጣው ይህ ምርመራ ሃብታም ባልሆኑ እና የጤና ባለሙያዎችና የላብራቶሪ እጥረት ባለባቸው አገራት የኮቪድ-19 ሕሙማንን ለመለየት በእጅጉ ይረዳል ተብሏል። መመርመሪያውን ከሚያመርቱ ድርጅቶች ጋር የተደረገ ስምምነት በስድስት ወር ውስጥ 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ያስችላል። ይህንን እርምጃ የጤና ድርጅቱ የበላይ ኃላፊዎች "ጉልህ ሚና የሚጫወት" ብለውታል። በበርካታ አገራት ምርመራ ከተደረገ በኋላ ውጤት ለማወቅ የሚፈጀው ጊዜ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር የሚያርጉትን ትግል ጎድቶት ቆይቷል። እንደ ሕንድና ሜክሲኮ ባሉ ቫይረሱ በከፍተኛ ሁኔታ በተሰራጨባቸው አገራት በፍጥነት መርምሮ ውጤቱን ማወቅ አለመቻል የወረርሽኙን የመስፋፋት ፍጥነት ትክክለኛ ምስል ማሳየት አልቻለም ሲሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ይህ አዲሱ "ተንቀሳቃሽ እና ለአጠቃቀም ምቹ የሆነ" መመርመሪያ ውጤትን ከ15 እስከ 30 ደቂቃ ባለው ጊዜ ውስጥ እንደሚሰጥ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ሰኞ እለት በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ግን የኮሮናቫይረስን ውጤት ለማወቅ ሰዓታት ካልሆነም ቀናት እንደሚፈጅ ይታወቃል። አቦት እና ኤስዲ ባዮሴንሰር የተባሉ መድሃኒት አምራቾች ከቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን 120 ሚሊዮን መመርመሪያዎችን ለማምረት ስምምነት መድረሳቸውን ዶ/ር ቴድሮስ ጨምረው ገልፀዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት የሚመረቱ መመርመሪያዎች በቫይረሱ በጣም የተጎዱ የላቲን አሜሪካ አገራትን ጨምሮ ለ133 አገራት ይሰጣል ተብሏል። "ይህ በተለይ ከፍተኛ ስርጭት ባለባቸው አካባቢዎች የመመርመር አቅም ላይ ትልቅ እመርታ የሚፈጥር ነው" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ። አክለውም "ላቦራቶሪ በሌላቸውና ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ አካባቢዎች ወይንም ምርመራውን ለማካሄድ በቂ የሰለጠነ ባለሙያ በሌለበት አካባቢ የመመርመር አቅምን ያሰፋል።'' | https://www.bbc.com/amharic/54336434 |
2health
| በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ | በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ። በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። ሮይተር በበኩሉ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር ማገርሸቱ ከተመዘገበው ቁጥር ውስጥ ሩብ ለሚሆነው ድርሻ አለው ሲል ዘግቧል፡፡ ቀደም ሲል የቫይረሱ ስርጭት ማዕከል የነበረችው አውሮፓ 12.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት 305,700 ደግሞ ህይወታቸው አልፎፋባት በድጋሚ የቫይረሱ ስርጭቱ ማዕከል ሆናለች፡፡ በአሜሪካ 10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በቀን ከ125,000 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የችግሩን መጠን ከማሳነስ ባለፈ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ እና አካላዊ ርቀት ማስጠበቅን ባይቀበሉም ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሙሉ ሃይላቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ባይደን በጥቂት ቀናት ከፍተኛ የሳይንስ ሊቃውንትን ያካተተ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል ለማቋቋም ቃል ገብተዋል። ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ እና ሁሉም አሜሪካዊያን ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ሲሆኑ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል እንዲያደርጉ ለመጠየቅ አቅደዋል። ባይደን ወረርሽኙ በአገሪቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ኃላፊነታቸውን ሊረከቡ ይችላሉ ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር ዶ/ር ስኮት ጎትሊብ ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር ጎትሊብ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ጥር መጨረሻ ድረስ መቀነስ ይጀምራል። "ብቸኛው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ውስጥ ስንት ሰዎች ይሞታሉ እና ምን ያህል ሰዎች ይያዛሉ የሚለው ነው" ብለዋል፡፡ በአውሮፓ ፈረንሳይ እሁድ 38,619 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ቅዳሜ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው የ86,852 ቁጥር ግን በጣም ያነሰ ነው፡፡ ሆኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ መረጃ የመሰብሰብ ችግሮች እንደነበሩበት በመግለጽ ሰኞ እርማት እንደሚያደረግ ገልጿል ፡፡ ህንድ እና ብራዚልም እንዲሁ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ | በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አለፈ። በበርካታ አገራት በኮቪድ-19 የሚያዙ ከፍተኛ ቁጥር መመዝገቡን ተከለትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሚሊዮን አልፏል። እንደጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ ከሆነ ከ1.25 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። በብዙ አገራት በቂ ምርመራ ባለመደረጉ እንጂ ይህን አሃዝ ከፍ ያለ ነው ተብሎ ይገመታል። ሮይተር በበኩሉ ቫይረሱ ሁለተኛ ዙር ማገርሸቱ ከተመዘገበው ቁጥር ውስጥ ሩብ ለሚሆነው ድርሻ አለው ሲል ዘግቧል፡፡ ቀደም ሲል የቫይረሱ ስርጭት ማዕከል የነበረችው አውሮፓ 12.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙባት 305,700 ደግሞ ህይወታቸው አልፎፋባት በድጋሚ የቫይረሱ ስርጭቱ ማዕከል ሆናለች፡፡ በአሜሪካ 10 ሚሊዮን ገደማ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በቀን ከ125,000 በላይ ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የችግሩን መጠን ከማሳነስ ባለፈ የአፍና የአፍንጫ ጭምብል ማድረግ እና አካላዊ ርቀት ማስጠበቅን ባይቀበሉም ተመራጩ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሙሉ ሃይላቸው እንደሚሠሩ ቃል ገብተዋል። ባይደን በጥቂት ቀናት ከፍተኛ የሳይንስ ሊቃውንትን ያካተተ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል ለማቋቋም ቃል ገብተዋል። ተጨማሪ ምርመራዎችን ለማድረግ እና ሁሉም አሜሪካዊያን ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ሲሆኑ የአፍና የአፍንጫ ጭንብል እንዲያደርጉ ለመጠየቅ አቅደዋል። ባይደን ወረርሽኙ በአገሪቱ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርስ ኃላፊነታቸውን ሊረከቡ ይችላሉ ሲሉ የቀድሞው የአሜሪካ የምግብ እና የመድኃኒት አስተዳደር ኮሚሽነር ዶ/ር ስኮት ጎትሊብ ገልጸዋል። እንደ ዶ/ር ጎትሊብ ከሆነ የቫይረሱ ስርጭት ጥር መጨረሻ ድረስ መቀነስ ይጀምራል። "ብቸኛው ጥያቄ በዚህ ጊዜ ውስጥ ስንት ሰዎች ይሞታሉ እና ምን ያህል ሰዎች ይያዛሉ የሚለው ነው" ብለዋል፡፡ በአውሮፓ ፈረንሳይ እሁድ 38,619 አዲስ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን መዝግባለች። ቅዳሜ ከፍተኛ ሆኖ ከተመዘገበው የ86,852 ቁጥር ግን በጣም ያነሰ ነው፡፡ ሆኖም የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ መረጃ የመሰብሰብ ችግሮች እንደነበሩበት በመግለጽ ሰኞ እርማት እንደሚያደረግ ገልጿል ፡፡ ህንድ እና ብራዚልም እንዲሁ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/54869295 |
2health
| መፀዳጃ ቤት ስንጠቀም በምናያቸው ምልክቶች የምንለየው የካንሰር ዓይነት | በአንጀት ካንሰር የሞተችው የአርባ ዓመቷ ጎልማሳ ዴሚ ዴብራ ጄምስ በሽታውን ቀድሞ ለማወቅ ሁሉም ሰው ሰገራው ላይ ያሉ ለውጦችን ትኩረት እንዲሰጥ ስትመክር ቆይታለች። ታዲያ እንዴት የአንጀት ካንሰርን ልንለይ እንችላለን? ከዚህ የጤና ችግር ጋር በተያያዘ ሦስት ነገሮችን ልብ ማለት ይኖርብናል፡ እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ በአንጀት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚከተሉት አይነት ሌሎች ምልክቶችም ሊኖሩት ይችላሉ። የክብደት መቀነስ፣ መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ በደንብ ያልተጻዳዱ ያህል መሰማት፣ ከተለመደው በተለየ የሰውነት መድከምና የመዛል ስሜት ያጋጥማል። እነዚህ ምልክቶች ታዩ ማለት ግን የአንጀት ካንሰር አለ ማለት ላይሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ለሦስት ሳምንታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከታዩ እንዲሁም የሚሰማን ነገር ትክክል ካልሆነ ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል። በዚህም ተገቢው ምርመራ በፍጥነት ተደርጎ ካንሰር ከሆነ እና በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ከተደረሰበት ለማከም ቀላል ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ የአንጀት ካንሰር ሰገራ በተገቢው መስመር እንዳይወገድ በማድረግ መዘጋትን ሊፈጥርና ይህም ከባድ የሆድ ቁርጠት፣ ድርቀት እና ህመምን ሊያስከትል ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥምም ችላ ሳይሉ ወደ ሐኪም ዘንድ በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው። መፀዳጃ ቤት በሚጠቀሙ ጊዜ የሚወጣውን ሰገራ ይመልከቱ፣ የተለየ ነገር ሲያጋጥምዎት የሕክምና ባለሙያ ለማማከር በወደ ኋላ አይበሉ። በተለይ ሰገራ ላይ የደም ምልክትና መፀዳጃ ቤት ሲጠቀሙ የመድማት ሁኔታ ካጋጠመ በቀላሉ መታለፍ የለበትም። አንዳንድ ጊዜ በሰገራ መተላለፊያ አካል ላይ ባሉ የደም ስሮች እብጠት ሳቢያ ቀይ ደም ሊወጣ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ በአንጀት ካንሰር ሳቢያ የተከሰተ ሊሆን ይችላል። ጠቆር ያለ ደም ወይም ጥቁር ደም ሰገራ ላይ ከታየ ይህ የተከሰተው በአንጀት ወይም በጨጓራ ላይ ባጋጠመ የጤና ችግር ስለሚሆን አሳሳቢ ሊሆንም ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ቀጠን ያለ ሰገራ መኖር ወይም ከወትሮው በተለየ ቶሎ ቶሎ መፀዳዳት ሊኖር ይችላል። ወይም ደግሞ አንጀት ውስጥ የተከማቸው ሰገራ ያልወጣ መስሎ መሰማት አሊያም በበቂ ሁኔታ አለመፀዳዳት ያጋጥማል። በዩናይትድ ኪንግደም ስለ አንጀት ካንሰር መረጃ የሚሰጠው ድረ ገጽ ወደ ሐኪም ዘንድ ከመሄድ በፊት በየዕለቱ የሚታዩ ምልክቶችን በመከታተል መመዝገብ እንደሚገባ ይመክራል። ይህንንም ለሐኪምዎ መናገር ያለብዎትን ሳይዘነጉ አንድ ባንድ መናገር እንዲችሉ ይረዳል። ሐኪሞች በተለያዩ የአንጀት ጤና እክሎች ያሉባቸው በርካታ ሰዎችን ስለሚመለከቱ በእራሳችሁ ላይ ያያችሁትን ለውጥ ወይም መድማት ካለ መናገራችሁ የበሽታውን መንስዔ ማወቅ እንዲችሉ ያግዛል። በአብዛኛው የአንጀት ካንሰር በዘር አይተላለፍም። ይሁን እንጂ የቅርብ የቤተሰብ አባል ከአምሳ ዓመት ዕድሜ በፊት በበሽታው ተይዘው ሕክምና አድርገው የሚያውቁ ከሆነ፣ ይህንን ለሐኪም መናገር አስፈላጊ ነው። እንደ ሊንቺ ሲንድረም ያሉ አንዳንድ በዘር የሚተላለፉ ካንሰሮች ለአንጀት ካንሰር የመጋለጥ እድል እንዲሰፋ ያደርጋል። ስለዚህ ሁኔታ ሐኪም ማወቅ ከቻለ በሽታውን ቀድሞ ለመከላከል ያስችላል። ከሚከሰቱት የአንጀት ካንሰሮች ግማሽ ያህሉ ጤናማ የሕይወት ዘይቤን በመከተል ቀድመን ልንከላከላቸው የምንችላቸው እንደሆኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ በብዛት አሰር ያላቸውን ምግቦችን በመመገብ እና ስብን በመቀነስ እንዲሁም በቀን ውስጥ ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃ በመጠጣት የአንጀት ካንሰርን ቀድሞ መከላከል ይቻላል። ነገር ግን የሚያሳስብ ምልክት ከተከሰተ የጤና ባለሙያን ማማከር እና የካንሰር ምርመራ ማድረግ ይመከራል። የአንጀት ካንሰር ምልክቶች ከታዩ ፈጠን ብሎ ሐኪም ማማከር በሽታውን ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው። ምርመራውም ቱቦ በመጠቀም ሁሉንም የአንጀት ክፍሎች በካሜራ በሚያሳይ መሣሪያ (ኮሎኖስኮፒ) ይደረጋል። ወይም ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለማየት በሚያስችል መሣሪያ (ሲግሞዶስኮፒ) በተባለ ተጣጣፊ መሣሪያ ምርመራው ይካሄዳል። በመጀመሪያው የአንጀት ካንሰር ደረጃ ላይ ምርመራ ያደረጉ ሰዎች በሽታውን በቶሎ በመለየት አስፈላጊው ሕክምናን በወቅቱ ማግኘት ስለሚችሉ የሚከሰተውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። የካንሰር በሽታ በብዛት የሚከሰተውና ገዳይ የሚሆነው እድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ በመሆኑ ልክ እንደ ሌሎች የካንሰር በሽታዎች ሁሉ በአንጀት ካንሰር የተያዙ ከ15 እስከ 40 ባለው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በሕይወት የመቆየታቸው ዕድል ሰፊ ነው። ሆኖም አጠቃላይ በሕይወት የመቆየት እድል ከሌሎች የአውሮፓ አገራት ጋር ሲነጻጸር በዩኬ ያለው ጥሩ የሚባል አይደለም። የአንጀት ካንሰር በተለይ ቀድሞ ሕክምና ማድረግ ከተቻለ የሚድን በሽታ ነው። በሽታውን ቀድሞ ለመከላከል ያለው ሕክምና በአብዛኛው በግል የሚከናወን ሲሆን፣ የዘረ መል ምርመራ ቀድሞ ማድረግ የተከሰተውን ካንሰር ለማከም ያስችላል። ይህ ዘዴ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ተጨማሪ ዓመታትን በሕይወት እንዲቆዩ ይረዳል። በየትኛውም የዕድሜ ክልል በበሽታው ለተያዘ ሰው ሕክምናው ይሰጣል። ሕክምናው ቀዶ ሕክምና፣ ኬሞቴራፒ፣ ራዲዮቴራፒ ወይም ደግሞ እንደየግለሰቡ የካንሰር ሁኔታ ሌሎች ሕክምናዎች ሊሰጡ ይችላሉ። | መፀዳጃ ቤት ስንጠቀም በምናያቸው ምልክቶች የምንለየው የካንሰር ዓይነት በአንጀት ካንሰር የሞተችው የአርባ ዓመቷ ጎልማሳ ዴሚ ዴብራ ጄምስ በሽታውን ቀድሞ ለማወቅ ሁሉም ሰው ሰገራው ላይ ያሉ ለውጦችን ትኩረት እንዲሰጥ ስትመክር ቆይታለች። ታዲያ እንዴት የአንጀት ካንሰርን ልንለይ እንችላለን? ከዚህ የጤና ችግር ጋር በተያያዘ ሦስት ነገሮችን ልብ ማለት ይኖርብናል፡ እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ በአንጀት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚከተሉት አይነት ሌሎች ምልክቶችም ሊኖሩት ይችላሉ። የክብደት መቀነስ፣ መፀዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ በደንብ ያልተጻዳዱ ያህል መሰማት፣ ከተለመደው በተለየ የሰውነት መድከምና የመዛል ስሜት ያጋጥማል። እነዚህ ምልክቶች ታዩ ማለት ግን የአንጀት ካንሰር አለ ማለት ላይሆን ይችላል። ነገር ግን እነዚህ ምልክቶች ለሦስት ሳምንታትና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ከታዩ እንዲሁም የሚሰማን ነገር ትክክል ካልሆነ ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል። በዚህም ተገቢው ምርመራ በፍጥነት ተደርጎ ካንሰር ከሆነ እና በመጀመሪያው ደረጃ ላይ ከተደረሰበት ለማከም ቀላል ይሆናል። አንዳንድ ጊዜ የአንጀት ካንሰር ሰገራ በተገቢው መስመር እንዳይወገድ በማድረግ መዘጋትን ሊፈጥርና ይህም ከባድ የሆድ ቁርጠት፣ ድርቀት እና ህመምን ሊያስከትል ይችላል። እንዲህ አይነት ችግር ሲያጋጥምም ችላ ሳይሉ ወደ ሐኪም ዘንድ በመሄድ አስፈላጊውን ምርመራ ማድረግ ተገቢ ነው። መፀዳጃ ቤት በሚጠቀሙ ጊዜ የሚወጣውን ሰገራ ይመልከቱ፣ የተለየ ነገር ሲያጋጥምዎት የሕክምና ባለሙያ ለማማከር በወደ ኋላ አይበሉ። በተለይ ሰገራ ላይ የደም ምልክትና መፀዳጃ ቤት ሲጠቀሙ የመድማት ሁኔታ ካጋጠመ በቀላሉ መታለፍ የለበትም። አንዳንድ ጊዜ በሰገራ መተላለፊያ አካል ላይ ባሉ የደም ስሮች እብጠት ሳቢያ ቀይ ደም ሊወጣ ይችላል፤ ነገር ግን ይህ በአንጀት ካንሰር ሳቢያ የተከሰተ ሊሆን ይችላል። ጠቆር ያለ ደም ወይም ጥቁር ደም ሰገራ ላይ ከታየ ይህ የተከሰተው በአንጀት ወይም በጨጓራ ላይ ባጋጠመ የጤና ችግር ስለሚሆን አሳሳቢ ሊሆንም ይችላል። ከዚህም በተጨማሪ ቀጠን ያለ ሰገራ መኖር ወይም ከወትሮው በተለየ ቶሎ ቶሎ መፀዳዳት ሊኖር ይችላል። ወይም ደግሞ አንጀት ውስጥ የተከማቸው ሰገራ ያልወጣ መስሎ መሰማት አሊያም በበቂ ሁኔታ አለመፀዳዳት ያጋጥማል። በዩናይትድ ኪንግደም ስለ አንጀት ካንሰር መረጃ የሚሰጠው ድረ ገጽ ወደ ሐኪም ዘንድ ከመሄድ በፊት በየዕለቱ የሚታዩ ምልክቶችን በመከታተል መመዝገብ እንደሚገባ ይመክራል። ይህንንም ለሐኪምዎ መናገር ያለብዎትን ሳይዘነጉ አንድ ባንድ መናገር እንዲችሉ ይረዳል። ሐኪሞች በተለያዩ የአንጀት ጤና እክሎች ያሉባቸው በርካታ ሰዎችን ስለሚመለከቱ በእራሳችሁ ላይ ያያችሁትን ለውጥ ወይም መድማት ካለ መናገራችሁ የበሽታውን መንስዔ ማወቅ እንዲችሉ ያግዛል። በአብዛኛው የአንጀት ካንሰር በዘር አይተላለፍም። ይሁን እንጂ የቅርብ የቤተሰብ አባል ከአምሳ ዓመት ዕድሜ በፊት በበሽታው ተይዘው ሕክምና አድርገው የሚያውቁ ከሆነ፣ ይህንን ለሐኪም መናገር አስፈላጊ ነው። እንደ ሊንቺ ሲንድረም ያሉ አንዳንድ በዘር የሚተላለፉ ካንሰሮች ለአንጀት ካንሰር የመጋለጥ እድል እንዲሰፋ ያደርጋል። ስለዚህ ሁኔታ ሐኪም ማወቅ ከቻለ በሽታውን ቀድሞ ለመከላከል ያስችላል። ከሚከሰቱት የአንጀት ካንሰሮች ግማሽ ያህሉ ጤናማ የሕይወት ዘይቤን በመከተል ቀድመን ልንከላከላቸው የምንችላቸው እንደሆኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ። በቂ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ፣ በብዛት አሰር ያላቸውን ምግቦችን በመመገብ እና ስብን በመቀነስ እንዲሁም በቀን ውስጥ ከስድስት እስከ ስምንት ብርጭቆ ውሃ በመጠጣት የአንጀት ካንሰርን ቀድሞ መከላከል ይቻላል። ነገር ግን የሚያሳስብ ምልክት ከተከሰተ የጤና ባለሙያን ማማከር እና የካንሰር ምርመራ ማድረግ ይመከራል። የአንጀት ካንሰር ምልክቶች ከታዩ ፈጠን ብሎ ሐኪም ማማከር በሽታውን ለመቆጣጠር ወሳኝ ነው። ምርመራውም ቱቦ በመጠቀም ሁሉንም የአንጀት ክፍሎች በካሜራ በሚያሳይ መሣሪያ (ኮሎኖስኮፒ) ይደረጋል። ወይም ደግሞ የተወሰነውን ክፍል ለማየት በሚያስችል መሣሪያ (ሲግሞዶስኮፒ) በተባለ ተጣጣፊ መሣሪያ ምርመራው ይካሄዳል። በመጀመሪያው የአንጀት ካንሰር ደረጃ ላይ ምርመራ ያደረጉ ሰዎች በሽታውን በቶሎ በመለየት አስፈላጊው ሕክምናን በወቅቱ ማግኘት ስለሚችሉ የሚከሰተውን ጉዳት በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ይቻላል። የካንሰር በሽታ በብዛት የሚከሰተውና ገዳይ የሚሆነው እድሜያቸው በገፉ ሰዎች ላይ በመሆኑ ልክ እንደ ሌሎች የካንሰር በሽታዎች ሁሉ በአንጀት ካንሰር የተያዙ ከ15 እስከ 40 ባለው የዕድሜ ክልል የሚገኙ ሰዎች በሕይወት የመቆየታቸው ዕድል ሰፊ ነው። ሆኖም አጠቃላይ በሕይወት የመቆየት እድል ከሌሎች የአውሮፓ አገራት ጋር ሲነጻጸር በዩኬ ያለው ጥሩ የሚባል አይደለም። የአንጀት ካንሰር በተለይ ቀድሞ ሕክምና ማድረግ ከተቻለ የሚድን በሽታ ነው። በሽታውን ቀድሞ ለመከላከል ያለው ሕክምና በአብዛኛው በግል የሚከናወን ሲሆን፣ የዘረ መል ምርመራ ቀድሞ ማድረግ የተከሰተውን ካንሰር ለማከም ያስችላል። ይህ ዘዴ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ተጨማሪ ዓመታትን በሕይወት እንዲቆዩ ይረዳል። በየትኛውም የዕድሜ ክልል በበሽታው ለተያዘ ሰው ሕክምናው ይሰጣል። ሕክምናው ቀዶ ሕክምና፣ ኬሞቴራፒ፣ ራዲዮቴራፒ ወይም ደግሞ እንደየግለሰቡ የካንሰር ሁኔታ ሌሎች ሕክምናዎች ሊሰጡ ይችላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c885exp9rexo |
2health
| ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች | ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው። ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። "በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ" ነበር ብለዋል፡፡ የእስራኤል ትልቁ የጤና ፈንድ ክላሊት በተመሳሰይ ዕድሜ እና የጤና ሁኔታ በሚገኙ 600,000 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን፣ ክትባት ካልወሰዱ ሰዎች አንጻር እንደታየባቸው አመልክቷል፡፡ ክትባቱን በወሰዱት ዘንድ 94% ያነሰ ኢንፌክሽኖችን አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ክትባቱ ሁሉንም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከባድ ህመሞችን ተከላክሏል፡፡ ውጤቱ ከ70 ዎቹ በላይ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ቡድኖች ውስጥ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ "እንደ እንግሊዝ ላሉት ሌሎች ሀገሮች" ስለ ክትባቱ ጠቃሚ መልዕክት ከማስተላለፉም በተጨማሪ፣ በቫይረሱ በጣም ሊታመሙ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች "በከፍተኛ" ሁኔታ ክትባቱን እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል ፕሮፌሰር ሌቪን፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ከማላላት በፊት ምን ያህል ቁጥር መከተብ እንደሚያስፈልግ መናገር አልችልም ብለዋል፡፡ "በመተላለፍ ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም" ብለዋል፡፡ ሆኖም ቢያንስ "ክትባቱ ግለሰብን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው" ሲሉም አክለዋል፡፡ የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃን በመተንተን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ኤራን ሴጋል በበኩላቸው ክትባቱ በኮቪድ -19 ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት ሃገሪቱ ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ ከሆኑት መካከል 80 በመቶውን መከተብ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ እስራኤል የክትባት መርሃግብሩ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመመልከት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ብትሆንም፣ ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ህዝብን ማዳረስ እና በርካታ ሳምንታትን ሊፈጅባት ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ክትባት በተወሰዱ እና ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ በሆናቸው እና ከዚያ ቀደም ነዋሪዎቻቸውን ባስከተቡ ከተሞች ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ታይቷል። ይህም ቀደም ባሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ወቅት ያልታየ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ከእገዳው ይልቅ ክትባቱ ለቁጥሩ መቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ ፕሮፌሰር ሴጋል እንደሚያስጠነቀቁት ከሆነ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ በዝግታ የቀነሰ ሲሆን ምናልባትም በእስራኤል ውስጥ ዋነኛው የቫይረሱ ዝርያ በሆነው እና በብሪታንያ በተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ "በጣም ፈጣን" በሆነው በእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር እንኳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊከላከሉት የማይችሉ ሲሆን በበሽታው ከተያዙም በጠና ሊታመሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ "አሁንም ቢሆን ከእንቅስቃሴ እገዳው ለመውጣት በጥንቃቄ መውጣት አለብን" ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሆስፒታል መተኛት ሊገደዱ ይችላሉ ይላሉ፡ እስራኤል ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ማዕበል እያጋጠማት እና በጥብቅ እገዳዎች ውስጥ ብትቆይም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ የመከተብ መብት ስላላቸው ትምህርት ቤቶች የመከፈት ተስፋ አላቸው ተብሏል፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ክትባቱን ማን መስጠት አለበት በሚለው ጥያቄ ሃገሪቱ ትችት ደርሶባታል፡፡ ለጤና ሠራተኞች እንዲደርስ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጋዛ ላሉት ፍልስጤሞች የተወሰነ መጠን ያለው ክትባት ማሳለፍ የጀመረችው ገና አሁን ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከነዋሪዎቿ ለሩብ ያህሉ ሁለቱንም ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡ | ኮሮናቫይረስ: እስራኤል የፋይዘር ክትባት ውጤታማ ሆኖ ማግኘቷን ገለፀች ከእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር የተገኙ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የፋይዘር ክትባት የኮሮናቫይረስ ምልክቶችን 94 በመቶ የመከላከል አቅም አለው። ይህም ክትባቱ በክሊኒክ ውስጥ በተደረጉለት ሙከራዎች ወቅት የነበረውን ያህል ከፍተኛ ቁጥር ባለው ህዝብ ውስጥም ውጤታማ መሆኑን ያሳያል፡፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ሰዎች ከፍተኛ ውጤታማነት እያስገኘ መሆኑን የማህበረሰብ ጤና ሐኪሙ ፕሮፌሰር ሀጋይ ሌቪን ተናግረዋል። "በጣም ተጋላጭ ለሆኑት ቡድኖች ከፍተኛ የክትባት ሽፋን መስጠት ወሳኝ" ነበር ብለዋል፡፡ የእስራኤል ትልቁ የጤና ፈንድ ክላሊት በተመሳሰይ ዕድሜ እና የጤና ሁኔታ በሚገኙ 600,000 ክትባት በወሰዱ ሰዎች ላይ መልካም የሚባል ውጤት መገኘቱን፣ ክትባት ካልወሰዱ ሰዎች አንጻር እንደታየባቸው አመልክቷል፡፡ ክትባቱን በወሰዱት ዘንድ 94% ያነሰ ኢንፌክሽኖችን አግኝቷል፡፡ በተጨማሪም ክትባቱ ሁሉንም ማለት በሚቻል ሁኔታ ከባድ ህመሞችን ተከላክሏል፡፡ ውጤቱ ከ70 ዎቹ በላይ የሆኑትን ጨምሮ በሁሉም የዕድሜ ቡድኖች ውስጥ ተመሳሳይ ነበር፡፡ ይህ "እንደ እንግሊዝ ላሉት ሌሎች ሀገሮች" ስለ ክትባቱ ጠቃሚ መልዕክት ከማስተላለፉም በተጨማሪ፣ በቫይረሱ በጣም ሊታመሙ የሚችሉትን የህብረተሰብ ክፍሎች "በከፍተኛ" ሁኔታ ክትባቱን እንዲያገኙ ያግዛል ብለዋል ፕሮፌሰር ሌቪን፡፡ ፕሮፌሰሩ አክለውም የእንቅስቃሴ ገደቦችን ከማላላት በፊት ምን ያህል ቁጥር መከተብ እንደሚያስፈልግ መናገር አልችልም ብለዋል፡፡ "በመተላለፍ ላይ ያለው ተጽዕኖ ምን እንደሆነ እስካሁን አናውቅም" ብለዋል፡፡ ሆኖም ቢያንስ "ክትባቱ ግለሰብን ለመጠበቅ ጠቃሚ ነው" ሲሉም አክለዋል፡፡ የእስራኤል ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መረጃን በመተንተን ላይ የሚገኙት ፕሮፌሰር ኤራን ሴጋል በበኩላቸው ክትባቱ በኮቪድ -19 ጉዳዮች ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመረዳት ሃገሪቱ ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ ከሆኑት መካከል 80 በመቶውን መከተብ እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ እስራኤል የክትባት መርሃግብሩ የሚያስከትለውን ተጽዕኖ ለመመልከት በዓለም ላይ የመጀመሪያዋ ሀገር ብትሆንም፣ ወደዚህ ደረጃ ለመድረስ ከፍተኛ የሆነ ህዝብን ማዳረስ እና በርካታ ሳምንታትን ሊፈጅባት ይችላል፡፡ በመጀመሪያ ክትባት በተወሰዱ እና ዕድሜያቸው ከ60ዎቹ በላይ በሆናቸው እና ከዚያ ቀደም ነዋሪዎቻቸውን ባስከተቡ ከተሞች ውስጥ የቫይረሱ ስርጭት ሲቀንስ ታይቷል። ይህም ቀደም ባሉት የእንቅስቃሴ ገደቦች ወቅት ያልታየ ነው ተብሏል፡፡ ይህም ከእገዳው ይልቅ ክትባቱ ለቁጥሩ መቀነስ ትልቅ ሚና እንዳለው ጠንካራ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ ፕሮፌሰር ሴጋል እንደሚያስጠነቀቁት ከሆነ ቁጥሩ ከሚጠበቀው በላይ በዝግታ የቀነሰ ሲሆን ምናልባትም በእስራኤል ውስጥ ዋነኛው የቫይረሱ ዝርያ በሆነው እና በብሪታንያ በተገኘው የኮሮናቫይረስ ዝርያ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ "በጣም ፈጣን" በሆነው በእስራኤል የክትባት መርሃ ግብር እንኳን በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሊከላከሉት የማይችሉ ሲሆን በበሽታው ከተያዙም በጠና ሊታመሙ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል፡፡ "አሁንም ቢሆን ከእንቅስቃሴ እገዳው ለመውጣት በጥንቃቄ መውጣት አለብን" ወይም ብዙ ቁጥር ያላቸው ሰዎች ሆስፒታል መተኛት ሊገደዱ ይችላሉ ይላሉ፡ እስራኤል ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ማዕበል እያጋጠማት እና በጥብቅ እገዳዎች ውስጥ ብትቆይም ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ሁሉ የመከተብ መብት ስላላቸው ትምህርት ቤቶች የመከፈት ተስፋ አላቸው ተብሏል፡፡ በፍልስጤም ግዛቶች ክትባቱን ማን መስጠት አለበት በሚለው ጥያቄ ሃገሪቱ ትችት ደርሶባታል፡፡ ለጤና ሠራተኞች እንዲደርስ እስራኤል በዌስት ባንክ እና በጋዛ ላሉት ፍልስጤሞች የተወሰነ መጠን ያለው ክትባት ማሳለፍ የጀመረችው ገና አሁን ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ከነዋሪዎቿ ለሩብ ያህሉ ሁለቱንም ዙር ክትባት ሰጥታለች፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-56073530 |
5sports
| "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ | የኢትዮጵያ የማራቶን ውድድር ሯጮች ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ እንዳልተላለፈ ከአትሌቶቹ ጋር ካታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ ተናገሩ። በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል። • ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው ብለዋል ዱቤ ጅሎ። አትሌቶች የሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ በዓለም አቀፍ የውድድር ሕግና ደንብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውና በሌሎችም ሃገራት የሚሰራበት እንደሆነ አመልክተዋል። ለሦስት ወራት ከውድድር እርቆ የሚወሰደው እረፍት ሁሉንም በማራቶን ውድድር የተሳተፉ አትሌቶችን የሚመለከት መሆኑን የጠቀሱት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ፤ በተለይ በዶሃ ያለው ከባድ ሙቀት ላይ ለተወዳደሩ አትሌቶች እረፍቱ በጣም አስፈላጊያቸው ነው ብለዋል ለቢቢሲ። ባለፈው አርብ ሌሊት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ሯጮች በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ውድድሩን አቋርጠው መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በርካቶችም ለማቋረጥ ተገደው ነበር። • ''በኳታር የኢትዮጵያ ቡድን በሙቀቱ ተቸግሯል'' የቡድኑ መሪ • የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ከአትሌቲክስ ታገዱ ስለዚህም የማራቶን ሯጮቹ ከነበሩበት ከባድ ሁኔታ እንዲያገግሙ በፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት ለሦስት ወራት ልምምድ እየሰሩ እረፍት እንዲያደርጉና ከውድድር እንዲርቁ መደረጉን አመልክተዋል። በሴቶቹ የማራቶን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩትና አቋርጠው ለመውጣት የተገደዱት ሯጮች የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ዱቤ ጅሎን ጠይቆ ባገኘው መረጃ መሰረት አንዷ ከገጠማት ቀላል ችግር በስተቀር ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋዋል። በዶሃ ባለው ከባድ ሙቀት ምክንያት በእኩለ ሌሊት ጎዳና ላይ በሚደረጉት የማራቶንና የእርምጃ ውድድሮች ተሳታፊዎች ላይ ከባድ ጫናን የሚያሳድር እንደሆነ የተናገሩት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ስታዲየም ውስጥ የሚደረገው ግን ብዙም አስቸጋሪ እንዳልሆነ ገልጸዋል። | "የማራቶን ሯጮቹ ላይ የተላለፈው እገዳ አይደለም" ዱቤ ጂሎ የኢትዮጵያ የማራቶን ውድድር ሯጮች ላይ ምንም አይነት የእገዳ ውሳኔ እንዳልተላለፈ ከአትሌቶቹ ጋር ካታር የሚገኙት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክትር ዱቤ ጂሎ ለቢቢሲ ተናገሩ። በካታር ዶሃ እየተካሄደ ባለው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን ውድድር ላይ የተሳተፉት አትሌቶች ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት እረፍት አድርገው እንዲያገግሙ እንጂ እገዳ አለመሆኑን ገልጸዋል። • ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ • በዶሃ የሴቶች ማራቶን ሦስት ኢትዮጵያውያን ሯጮች አቋርጠው ወጡ ውሳኔው ከ42 ኪሎሜትሮች በላይ በሚሮጥበት ከባድ በሚባለው የማራቶን ውድድር ላይ የሚሳተፉ ሯጮችን ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ የሚወሰድ ተቀባይነት ያለው እረፍት ነው ብለዋል ዱቤ ጅሎ። አትሌቶች የሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ እንዲያገኙ ማድረግ በዓለም አቀፍ የውድድር ሕግና ደንብ ውስጥ ተቀባይነት ያለውና በሌሎችም ሃገራት የሚሰራበት እንደሆነ አመልክተዋል። ለሦስት ወራት ከውድድር እርቆ የሚወሰደው እረፍት ሁሉንም በማራቶን ውድድር የተሳተፉ አትሌቶችን የሚመለከት መሆኑን የጠቀሱት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ፤ በተለይ በዶሃ ያለው ከባድ ሙቀት ላይ ለተወዳደሩ አትሌቶች እረፍቱ በጣም አስፈላጊያቸው ነው ብለዋል ለቢቢሲ። ባለፈው አርብ ሌሊት በተካሄደው የሴቶች ማራቶን ላይ ተሳታፊ የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ሯጮች በነበረው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት ውድድሩን አቋርጠው መውጣታቸው የሚታወስ ሲሆን እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በርካቶችም ለማቋረጥ ተገደው ነበር። • ''በኳታር የኢትዮጵያ ቡድን በሙቀቱ ተቸግሯል'' የቡድኑ መሪ • የሞ ፋራህ የቀድሞ አሠልጣኝ ከአትሌቲክስ ታገዱ ስለዚህም የማራቶን ሯጮቹ ከነበሩበት ከባድ ሁኔታ እንዲያገግሙ በፌዴሬሽኑ ደንብ መሰረት ለሦስት ወራት ልምምድ እየሰሩ እረፍት እንዲያደርጉና ከውድድር እንዲርቁ መደረጉን አመልክተዋል። በሴቶቹ የማራቶን ውድድር ላይ ተሳታፊ የነበሩትና አቋርጠው ለመውጣት የተገደዱት ሯጮች የጤንነት ሁኔታን በተመለከተ በስፍራው የሚገኘው የቢቢሲ ዘጋቢ ዱቤ ጅሎን ጠይቆ ባገኘው መረጃ መሰረት አንዷ ከገጠማት ቀላል ችግር በስተቀር ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋዋል። በዶሃ ባለው ከባድ ሙቀት ምክንያት በእኩለ ሌሊት ጎዳና ላይ በሚደረጉት የማራቶንና የእርምጃ ውድድሮች ተሳታፊዎች ላይ ከባድ ጫናን የሚያሳድር እንደሆነ የተናገሩት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ ስታዲየም ውስጥ የሚደረገው ግን ብዙም አስቸጋሪ እንዳልሆነ ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/49897069 |
5sports
| የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ ኳታር ከምድብ ጨዋታ ባሻገር መሄድ ሳትችል መሰናበቷ ተረጋገጠ | ኳታር ከሴኔጋል ጋር በነበራት ጨዋታ በገጠማት ሽንፈት ሳቢያ እያስተናገደችው ካለው የዓለም ዋንጫ ውድድር ከምድብ ጨዋታው ባሻገር ሳትሄድ መሰናበት የግድ ሆኖባታል። ኳታር በውድድሩ የመክፈቻ ዕለት ከኢኳዶር ጋር በነበራት ጨዋታ ሁለት ለዜሮ በሆነ ውጤት ተሸንፋ ነበር ውድድሩን የጀመረችው፣ ትናንት አርብ ደግሞ ከአፍሪካዊቷ ሴኔጋል ጋር ገጥማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረትታለች። በዚህም ሳቢያ ኳታር ማድረግ ካለባት ሦስት የምድብ ግጥሚያዎች ሁለቱን በመሸነፏ ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሏን በሌሎች ቡድኖች ጨዋታ ላይ የተንጠለጠለ አድርጎት ነበር። ነገር ግን የምድኑ ኃያላን ኢኳዶር እና ኔዘርላንድ ነጥብ ተጋርተው በመውጣታቸው ኳታር የሚቀራትን የመጨረሻ ጨዋታ አድርጋ ውጤቱ ምንም ቢሆን ከውድድሩ ለመሰናበት ተገዳለች። ኳታር የምድብ ጨዋታ መረሃ ግብሯን ብቻ ለማሟላት የአውሮፓ የእግር ኳስ አንጋፋ ከሆነችው መካከል አንዷ ከሆነችው ከኔዘርላንድስ ጋር በሚቀጥለው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዋን አድርጋ ትሰናበታለች። ኳታር በሴኔጋል ከተሸነፈች በኋላ በውድድሩ ውስጥ ለመቆየት በመጀመሪያ ጨዋታዋ ካሸነፈቻች ኢኳዶር አስቸጋሪ ውለታን ማግኘት ነበረባት። ነገር ግን ከኔዘርላንድ ጋር የገጠመችው የደቡብ አሜሪካዋ አገር ኢኳዶር አንድ አቻ በመውጣቷ፣ ኳታር ከምድብ ውድድሩ ለመሻገር ሳትችል ቀርታለች። በዚህ ምድብ በመጀመሪያ ጨዋታቸው በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 የተሸነፉት የአፍሪካ ሻምፒዮኖቹ ሴኔጋሎች፣ ከሽንፈታቸው አገግመው ኳታርን በማሸነፍ በምድብ ውድድሩ ውስጥ ተፎካካሪነታቸውን አጠናክረዋል። ኳታር አረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫን ከማስተናገዷ በተጨማሪ ብሔራዊ ቡድኗም በዓለም ዋንጫ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው። ከውድድሩ የመክፈቻ ዕለት አንሰቶ ባሉት ስድስት ቀናት ውስጥ ሁለት ጨዋታዎችን ያደረገችው ኳታር፣ አምስት ግቦች ተቆጥረውባት አንድ ግብ አስቆጥራ በጨዋታዎቹ ተሸንፋለች። ቀሪ ጨዋታዋን በመጪው ማክሰኞ ከኔዘርላንድስ ጋር የምታደርግ ሲሆን፣ ቀላል ይሆንላታል ተብሎ አይጠበቅም። ኳታር ቢሊዮኖችን አፍስሳ ዘመናዊ ስታዲየሞችን በመገንባት ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ዓለም አቀፉን እግር ኳስ ውድድር በማስተናገድ ታሪክ አስምዝገባለች። ነገር ግን በውድድሩ ላይ ብሔራዊ ቡድኗ በተከታታይ ጨዋታዎቹ ሽንፈት ስለገጠመው በዙር ውድድሩ ላይ በመሰናበቷ ከሆነ፣ የዓለም ዋንጫን አስተናግዳ በምድብ ጨዋታ ከውድድሩ ውጪ በመሆን ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። ከሁለት ጨዋታዎች ተመሳሳይ አራት ነጥብና ሁለት የግብ ልዩነቶች ይዘው የምድቡን የመሪነት ስፍራ የያዙት ኢኳዶር እና ኔዘርላንድስ በአንደኝነት ወደ ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ውድድር ለመግባት ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል። በዚህም መሠረት በአውሮፓ ሊጎች ውስጥ በሚሰለፉ ተጫዋቾች ከተገነባችው ሴኔጋል ጋር የምትገጥመው ኢኳዶር ከባድ ፈተና የሚጠብቃት ሲሆን፣ ከወዲሁ ከውድድሩ መውጣቷን ካረጋገጠችው ከኳታር ጋር የምትገጥመው ኔዘርላንድስ ግን በአሸናፊነት የምድቡን የበላይነት ትይዛለች ተብሎ ይጠበቃል። | የዓለም ዋንጫ አስተናጋጅ ኳታር ከምድብ ጨዋታ ባሻገር መሄድ ሳትችል መሰናበቷ ተረጋገጠ ኳታር ከሴኔጋል ጋር በነበራት ጨዋታ በገጠማት ሽንፈት ሳቢያ እያስተናገደችው ካለው የዓለም ዋንጫ ውድድር ከምድብ ጨዋታው ባሻገር ሳትሄድ መሰናበት የግድ ሆኖባታል። ኳታር በውድድሩ የመክፈቻ ዕለት ከኢኳዶር ጋር በነበራት ጨዋታ ሁለት ለዜሮ በሆነ ውጤት ተሸንፋ ነበር ውድድሩን የጀመረችው፣ ትናንት አርብ ደግሞ ከአፍሪካዊቷ ሴኔጋል ጋር ገጥማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረትታለች። በዚህም ሳቢያ ኳታር ማድረግ ካለባት ሦስት የምድብ ግጥሚያዎች ሁለቱን በመሸነፏ ወደ ቀጣይ ዙር የማለፍ እድሏን በሌሎች ቡድኖች ጨዋታ ላይ የተንጠለጠለ አድርጎት ነበር። ነገር ግን የምድኑ ኃያላን ኢኳዶር እና ኔዘርላንድ ነጥብ ተጋርተው በመውጣታቸው ኳታር የሚቀራትን የመጨረሻ ጨዋታ አድርጋ ውጤቱ ምንም ቢሆን ከውድድሩ ለመሰናበት ተገዳለች። ኳታር የምድብ ጨዋታ መረሃ ግብሯን ብቻ ለማሟላት የአውሮፓ የእግር ኳስ አንጋፋ ከሆነችው መካከል አንዷ ከሆነችው ከኔዘርላንድስ ጋር በሚቀጥለው ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታዋን አድርጋ ትሰናበታለች። ኳታር በሴኔጋል ከተሸነፈች በኋላ በውድድሩ ውስጥ ለመቆየት በመጀመሪያ ጨዋታዋ ካሸነፈቻች ኢኳዶር አስቸጋሪ ውለታን ማግኘት ነበረባት። ነገር ግን ከኔዘርላንድ ጋር የገጠመችው የደቡብ አሜሪካዋ አገር ኢኳዶር አንድ አቻ በመውጣቷ፣ ኳታር ከምድብ ውድድሩ ለመሻገር ሳትችል ቀርታለች። በዚህ ምድብ በመጀመሪያ ጨዋታቸው በኔዘርላንድስ 2 ለ 0 የተሸነፉት የአፍሪካ ሻምፒዮኖቹ ሴኔጋሎች፣ ከሽንፈታቸው አገግመው ኳታርን በማሸነፍ በምድብ ውድድሩ ውስጥ ተፎካካሪነታቸውን አጠናክረዋል። ኳታር አረቡ ዓለም የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫን ከማስተናገዷ በተጨማሪ ብሔራዊ ቡድኗም በዓለም ዋንጫ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያው ነው። ከውድድሩ የመክፈቻ ዕለት አንሰቶ ባሉት ስድስት ቀናት ውስጥ ሁለት ጨዋታዎችን ያደረገችው ኳታር፣ አምስት ግቦች ተቆጥረውባት አንድ ግብ አስቆጥራ በጨዋታዎቹ ተሸንፋለች። ቀሪ ጨዋታዋን በመጪው ማክሰኞ ከኔዘርላንድስ ጋር የምታደርግ ሲሆን፣ ቀላል ይሆንላታል ተብሎ አይጠበቅም። ኳታር ቢሊዮኖችን አፍስሳ ዘመናዊ ስታዲየሞችን በመገንባት ለአረቡ ዓለም የመጀመሪያ የሆነውን ዓለም አቀፉን እግር ኳስ ውድድር በማስተናገድ ታሪክ አስምዝገባለች። ነገር ግን በውድድሩ ላይ ብሔራዊ ቡድኗ በተከታታይ ጨዋታዎቹ ሽንፈት ስለገጠመው በዙር ውድድሩ ላይ በመሰናበቷ ከሆነ፣ የዓለም ዋንጫን አስተናግዳ በምድብ ጨዋታ ከውድድሩ ውጪ በመሆን ከደቡብ አፍሪካ ቀጥላ ሁለተኛዋ አገር ሆናለች። ከሁለት ጨዋታዎች ተመሳሳይ አራት ነጥብና ሁለት የግብ ልዩነቶች ይዘው የምድቡን የመሪነት ስፍራ የያዙት ኢኳዶር እና ኔዘርላንድስ በአንደኝነት ወደ ቀጣይ የጥሎ ማለፍ ውድድር ለመግባት ተጋጣሚዎቻቸውን ማሸነፍ ይጠበቅባቸዋል። በዚህም መሠረት በአውሮፓ ሊጎች ውስጥ በሚሰለፉ ተጫዋቾች ከተገነባችው ሴኔጋል ጋር የምትገጥመው ኢኳዶር ከባድ ፈተና የሚጠብቃት ሲሆን፣ ከወዲሁ ከውድድሩ መውጣቷን ካረጋገጠችው ከኳታር ጋር የምትገጥመው ኔዘርላንድስ ግን በአሸናፊነት የምድቡን የበላይነት ትይዛለች ተብሎ ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c2e99pgn9j2o |
3politics
| አሜሪካዊቷን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ለማስለቀቅ የተደረገው የእስረኞች ልውውጥ እንዴት ተካሄደ? | ሩሲያ ውስጥ ለወራት ታስራ የነበረችውን አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነርን እንዲያስፈቱ እና ወደ አገሯ እንዲመልሱ የሕዝብ ግፊት በርትቶባቸው የነበሩት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጨረሻ ተሳክቶላቸዋል። እንደ ጀግና የምትታየው ስፖርተኛዋ ተፈትታ ወደ አገሯ እንድትመለስ ደከመች ሰለቸኝ ሳትል ከፊት ሆና ዘመቻውን ስትመራም የነበረችው የትዳር አጋሯም ቼሪል እፎይ ብላለች። “ደህና ናት። በአውሮፕላን ውስጥ ናት። ወደ አገሯ፣ ወደ ቤቷ እየመጣች ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ባይደን ለሕዝባቸው ንግግር አድርገዋል። ግሪነር በሩሲያ የቆየችበትንም ሰቆቃ የተሞላበት ወቅት “የገሃነም ወራት” ሲሉ ጠርተውታል። አጋሯ ቼሬልም ፈገግ ብላ የታየች ሲሆን ለጋዜጠኞች “በከፍተኛ ስሜት ላይ ነኝ። [ፕሬዝዳንቱ] ሳቄን መልሰውልኛል” ብላለች። በእስረኛ ልውውጥ የተፈታችውን ብሪትኒን ለመመለስ ዘጠኝ ወራት ወስዷል። ምንም እንኳን በርካቶች ደስታቸውን ቢገልጹም የባይደን አስተዳደር በእስር ላይ ያለውን ሌላኛውን የአሜሪካ ዜጋ ፖል ዊላን ማስፈታት አለመቻሉ ደስታውን ሙሉ አላደረገውም። ብሪትኒ በቁጥጥር ስር የዋለችው ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በሞስኮ አየር ማረፊያ ላይ ነበር። ትንሽ መጠን ያለው የካናቢስ (ዕጸ ፋርስ) ዘይት በሻንጣዋ ውስጥ መገኘቱ ነበር ለእስር የዳረጋት። ብሪትኒ ጥፋተኛ መሆኗን ብታምንም፣ ሆን ብላ ያደረገችው እንዳልሆነ ገልጻለች። የባይደን አስተዳደር በስህተት እንደታሰረች በተደጋጋሚ ሲገልጽም ቆይቷል። እነዚህን እስረኞች እንደታገቱባት ስትገልጽ የቆየችው አሜሪካ ቅድሚያ እነዚህን ታጋቾች ለማስለቀቅም ልዩ ልዑክ እስከማቋቋም ደርሳለች። ሆኖም የብሪትኒ የመለቀቅ ጉዳይ ውስብብ ሁኔታዎችን ያስተናገደ ነበር። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት አሜሪካ ዩክሬንን እያስታጠቀች እና ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገችበት ባለበት ወቅት መሆኑ ነው። ሆኖም የአሜሪካ መንግሥት በሩሲያ በእስር ላይ የነበረውን አሜሪካዊ የባሕል ኃይል አባል ትሬቨር ሪድን በሚያዝያ ወር ማስለቀቅ ችሏል። ሁለቱ አገራት ፖለቲካዊ ውጥረታቸውን ወደ ጎን ማድረግ እንደሚችሉ ባሳየ ድርድር በአሜሪካ በኮኬይን ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል ታስሮ በነበረውን ሩሲያዊ አብራሪ መቀያየር ቻሉ። የትሬቨር መለቀቅ እንዲሁም የብሪትኒ እስር የዓለምን ቀልብ መሳብ ሌሎች የታሰሩባቸውም ቤተሰቦች በአንድነት እንዲቆሙና በዋይት ሐውስ ላይ ጫና እንዲያሳድሩ አድርጓቸዋል። ሐምሌ ወር ላይ ብሪትኒ በሩሲያ ላልተወሰነ ጊዜ ልታሰር እችላለሁ የሚል ፍራቻ እንዳላት እና እንዳይረሷትም በመለመን ለፕሬዝዳንት ባይደን በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ላከች። ከቀናት በኋላ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን የሩሲያ አቻዎቻቸው በእስረኞች ልውውጥ እያቀረቡ ያሏቸውን ተጨባጭ ነገሮች ሊቀበሉ እንዳልቻሉ በመግለጽ ብስጭታቸውን በአደባባይ ገለጹ። የብሊንከን በይፋ እንዲህ መናገር በዲፕሎማሲው ዓለም ያልተለመደ ነው ተብሏል። የታጋቾቹም ሆነ የእስረኞች ልውውጥ ምስጢራዊ በሆነ ሁኔታ ነበር የሚካሄደው። ሩሲያውያን ነውጠኛውን የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ እና በአሜሪካ 25 ዓመት እስር የተፈረደበትን ቪክቶር ቦውት እንደሚፈልጉ ግልጽ ሆነ። ግለሰቡ ሩሲያ አደገኛ በሆኑ የአየር ጉዞዎች አደጋ ወደተሞላባቸው ስፍራዎች የሚሄድ ነጋዴ ነው የሚል ስም አትርፏል። ቪክቶር ከሩሲያ የስለላ ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበረው ግልጽ ባይሆንም፣ የሩሲያ እና የአሜሪካ ተንታኞች የሚስማሙበት ጉዳይ በደኅንነት መረጃ የካበተ ስለመሆኑ ነው። ለዚህም ነው ሩሲያ አጥብቃ እንዲመለስላት ስትሟገት የቆየችው። ይህም ለአሜሪካ ፈታኝ ጥያቄ በመሆኑ፣ ለዚህም ነበር አስተዳደሩ በድርድሩ ውስጥ ለአራት ዓመታት ያህል በእስር ላይ የሚገኘውን የኮርፖሬት ደኅንነት ሥራ አስፈጻሚ ዊላንን ለማካተት አጥብቆ የጠየቀው። ግለሰቡ በስለላ ወንጀል ተከሶ የ16 ዓመት እስራት ተፈርዶበት በሩሲያ እስር ላይ ይገኛል። ድርድሮቹም ለተወሰነ ወራት ፍሬ ሊያፈሩ ያልቻሉ ሲሆን፣ ብሪትኒም የዘጠኝ ዓመት አስር ተፈረደባት። የጠየቀችውም ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ ራቅ ወዳለ እስር ቤትም ተላከች። ለቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ሁኔታዎች ጨለሙባት። ድንገትም ነው የእስረኛ ልውውጡ ዜና ይፋ የሆነው። በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ሁለቱም የሩሲያ እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ተስፋ እንዳለ ቢጠቁሙም የእስረኛ ልውውጡ ጉዳይ ድንገት ነው የተነገረው። አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ስምምነቱ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ መደረሱን ነው። ዋነኛው የስምምነቱ ነጥብም ሁለት እስረኞችን በአንድ መለወጥ የሚል ቢሆንም፣ ሩሲያ ብሪትኒን ብቻ እንደምትለቅ አስታወቀች። “ይህ ስምምነት የትኛው አሜሪካዊ ነው ወደ አገሩ መምጣት ያለበት የሚል ምርጫ አልነበረም” በማለት የተናገሩት አንቶኒ ብሊንከን “ምርጫው አንድ ወይም ምንም ነበር” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን በጣም አሳዛኝ ውሳኔን መቀበል ነበረባቸው፤ ይህም ብሪትኒን በቦውት መለወጥ። በዚህም ሁለቱ እስረኞችም አቡ ዳቢ አውሮፕላን ማረፊያ መንደርደሪያ ላይ እንዲተላለፉ በማድረግ ልውውጡ ተካሄደ። ብዙም ሳይቆይ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ የጋራ ሽምግልና ጥረታቸው ብሪታትኒ እንድትፈታ ረድቷል ሲሉ መግለጫ አወጡ። ፕሬዝዳንት ባይደን ለልውውጡ የሚሆን ቦታ ስላቀረበች የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ቢያመሰግኑም፣ ነገር ግን ዋይት ሐውስ መደበኛ አደራዳሪ የሚለውን ሚና ሀሳብ ዝቅ አድርጎታል። የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ዣን ፒየር ሳዑዲ አረቢያ ጉዳዩን ከሞስኮ ጋር በማንሳት ቢያመሰግኑም ድርድሩ በአሜሪካ እና በሩሲያ ብቻ የተካሄደ ነው ብለዋል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ዊላን በስምምነቱ ውስጥ አለመካተቱ እንዳሳዘናቸው እና ከእስር እንዲፈታ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። ከዊላን ጋር ተያይዞ ያለው ዋነኛ ችግሮች “ሐሰተኛ የስለላ ወንጀል ክስ” ነው ሲሉ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ተናግረዋል። በግልጽ እንደሚታየው ለሩሲያውያን ከሰላይ ይልቅ የስፖርት ኮከብን መለወጥ እንደ ትልቅ ጉዳይ አይተውታል ብለዋል። ብሪትኒ ታዋቂ በመሆኗ እስሯ የሚዲያ ቀልብን የሳበ ቢሆንም ከዘጠኝ ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩ ሌሎች አሜሪካውያንም እንዳሉ ማስታወስ ይገባል ተብሏል። በተጨማሪም አሜሪካ እንደ ልዕለ ኃያል አገርነቷ ሳይሆን ልታሳካ የምትችለው ጉዳይ ውስንነትና ከፍተኛ ዋጋ መክፈል እንደነበረባት አስታዋሽ ነው ተብሏል። “ሌላኛው ወገን ሁልጊዜም ተጠቃሚ ይሆናል” ሲሉም የአሜሪካ እስረኞች ተወካይ ሮጀር ካርስተንስ በቅርቡ ተናግረዋል። በአሁኑ ስምምነት አሜሪካ “የሞት ነጋዴ” በመባል የሚታወቀውን የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ከአንድ ግራም ያነሰ የካናቢስ ዘይት ይዛ በተገኘችው የስፖርት ኮከብ ለመለወጥ ተገደደች። ሁለቱ አገራት ያካሄዱት የእስረኞች ልውውጥ በዚህ ዓመት ሁለተኛው ነው። ሆኖም ይህ የእስረኞች ልውውጥ ሩሲያ እና አሜሪካ ግንኙነታቸው እንደሸከረ፣ ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ ድርድሮች እና ንግግሮችን እንደሚቀጥሉ ያሳያል። | አሜሪካዊቷን ቅርጫት ኳስ ተጫዋች ለማስለቀቅ የተደረገው የእስረኞች ልውውጥ እንዴት ተካሄደ? ሩሲያ ውስጥ ለወራት ታስራ የነበረችውን አሜሪካዊቷ የቅርጫት ኳስ ተጫዋች ብሪትኒ ግሪነርን እንዲያስፈቱ እና ወደ አገሯ እንዲመልሱ የሕዝብ ግፊት በርትቶባቸው የነበሩት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በመጨረሻ ተሳክቶላቸዋል። እንደ ጀግና የምትታየው ስፖርተኛዋ ተፈትታ ወደ አገሯ እንድትመለስ ደከመች ሰለቸኝ ሳትል ከፊት ሆና ዘመቻውን ስትመራም የነበረችው የትዳር አጋሯም ቼሪል እፎይ ብላለች። “ደህና ናት። በአውሮፕላን ውስጥ ናት። ወደ አገሯ፣ ወደ ቤቷ እየመጣች ነው” ሲሉ ፕሬዝዳንት ባይደን ለሕዝባቸው ንግግር አድርገዋል። ግሪነር በሩሲያ የቆየችበትንም ሰቆቃ የተሞላበት ወቅት “የገሃነም ወራት” ሲሉ ጠርተውታል። አጋሯ ቼሬልም ፈገግ ብላ የታየች ሲሆን ለጋዜጠኞች “በከፍተኛ ስሜት ላይ ነኝ። [ፕሬዝዳንቱ] ሳቄን መልሰውልኛል” ብላለች። በእስረኛ ልውውጥ የተፈታችውን ብሪትኒን ለመመለስ ዘጠኝ ወራት ወስዷል። ምንም እንኳን በርካቶች ደስታቸውን ቢገልጹም የባይደን አስተዳደር በእስር ላይ ያለውን ሌላኛውን የአሜሪካ ዜጋ ፖል ዊላን ማስፈታት አለመቻሉ ደስታውን ሙሉ አላደረገውም። ብሪትኒ በቁጥጥር ስር የዋለችው ሩሲያ ዩክሬንን ከመውረሯ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ በሞስኮ አየር ማረፊያ ላይ ነበር። ትንሽ መጠን ያለው የካናቢስ (ዕጸ ፋርስ) ዘይት በሻንጣዋ ውስጥ መገኘቱ ነበር ለእስር የዳረጋት። ብሪትኒ ጥፋተኛ መሆኗን ብታምንም፣ ሆን ብላ ያደረገችው እንዳልሆነ ገልጻለች። የባይደን አስተዳደር በስህተት እንደታሰረች በተደጋጋሚ ሲገልጽም ቆይቷል። እነዚህን እስረኞች እንደታገቱባት ስትገልጽ የቆየችው አሜሪካ ቅድሚያ እነዚህን ታጋቾች ለማስለቀቅም ልዩ ልዑክ እስከማቋቋም ደርሳለች። ሆኖም የብሪትኒ የመለቀቅ ጉዳይ ውስብብ ሁኔታዎችን ያስተናገደ ነበር። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት አሜሪካ ዩክሬንን እያስታጠቀች እና ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገችበት ባለበት ወቅት መሆኑ ነው። ሆኖም የአሜሪካ መንግሥት በሩሲያ በእስር ላይ የነበረውን አሜሪካዊ የባሕል ኃይል አባል ትሬቨር ሪድን በሚያዝያ ወር ማስለቀቅ ችሏል። ሁለቱ አገራት ፖለቲካዊ ውጥረታቸውን ወደ ጎን ማድረግ እንደሚችሉ ባሳየ ድርድር በአሜሪካ በኮኬይን ዕፅ ማዘዋወር ወንጀል ታስሮ በነበረውን ሩሲያዊ አብራሪ መቀያየር ቻሉ። የትሬቨር መለቀቅ እንዲሁም የብሪትኒ እስር የዓለምን ቀልብ መሳብ ሌሎች የታሰሩባቸውም ቤተሰቦች በአንድነት እንዲቆሙና በዋይት ሐውስ ላይ ጫና እንዲያሳድሩ አድርጓቸዋል። ሐምሌ ወር ላይ ብሪትኒ በሩሲያ ላልተወሰነ ጊዜ ልታሰር እችላለሁ የሚል ፍራቻ እንዳላት እና እንዳይረሷትም በመለመን ለፕሬዝዳንት ባይደን በእጅ የተጻፈ ደብዳቤ ላከች። ከቀናት በኋላ፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ኃላፊ አንቶኒ ብሊንከን የሩሲያ አቻዎቻቸው በእስረኞች ልውውጥ እያቀረቡ ያሏቸውን ተጨባጭ ነገሮች ሊቀበሉ እንዳልቻሉ በመግለጽ ብስጭታቸውን በአደባባይ ገለጹ። የብሊንከን በይፋ እንዲህ መናገር በዲፕሎማሲው ዓለም ያልተለመደ ነው ተብሏል። የታጋቾቹም ሆነ የእስረኞች ልውውጥ ምስጢራዊ በሆነ ሁኔታ ነበር የሚካሄደው። ሩሲያውያን ነውጠኛውን የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ እና በአሜሪካ 25 ዓመት እስር የተፈረደበትን ቪክቶር ቦውት እንደሚፈልጉ ግልጽ ሆነ። ግለሰቡ ሩሲያ አደገኛ በሆኑ የአየር ጉዞዎች አደጋ ወደተሞላባቸው ስፍራዎች የሚሄድ ነጋዴ ነው የሚል ስም አትርፏል። ቪክቶር ከሩሲያ የስለላ ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደነበረው ግልጽ ባይሆንም፣ የሩሲያ እና የአሜሪካ ተንታኞች የሚስማሙበት ጉዳይ በደኅንነት መረጃ የካበተ ስለመሆኑ ነው። ለዚህም ነው ሩሲያ አጥብቃ እንዲመለስላት ስትሟገት የቆየችው። ይህም ለአሜሪካ ፈታኝ ጥያቄ በመሆኑ፣ ለዚህም ነበር አስተዳደሩ በድርድሩ ውስጥ ለአራት ዓመታት ያህል በእስር ላይ የሚገኘውን የኮርፖሬት ደኅንነት ሥራ አስፈጻሚ ዊላንን ለማካተት አጥብቆ የጠየቀው። ግለሰቡ በስለላ ወንጀል ተከሶ የ16 ዓመት እስራት ተፈርዶበት በሩሲያ እስር ላይ ይገኛል። ድርድሮቹም ለተወሰነ ወራት ፍሬ ሊያፈሩ ያልቻሉ ሲሆን፣ ብሪትኒም የዘጠኝ ዓመት አስር ተፈረደባት። የጠየቀችውም ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ ራቅ ወዳለ እስር ቤትም ተላከች። ለቅርጫት ኳስ ተጫዋቿ ሁኔታዎች ጨለሙባት። ድንገትም ነው የእስረኛ ልውውጡ ዜና ይፋ የሆነው። በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ሁለቱም የሩሲያ እና የአሜሪካ ባለሥልጣናት ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ተስፋ እንዳለ ቢጠቁሙም የእስረኛ ልውውጡ ጉዳይ ድንገት ነው የተነገረው። አንድ ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን እንደተናገሩት ስምምነቱ ባለፉት 48 ሰዓታት ውስጥ መደረሱን ነው። ዋነኛው የስምምነቱ ነጥብም ሁለት እስረኞችን በአንድ መለወጥ የሚል ቢሆንም፣ ሩሲያ ብሪትኒን ብቻ እንደምትለቅ አስታወቀች። “ይህ ስምምነት የትኛው አሜሪካዊ ነው ወደ አገሩ መምጣት ያለበት የሚል ምርጫ አልነበረም” በማለት የተናገሩት አንቶኒ ብሊንከን “ምርጫው አንድ ወይም ምንም ነበር” ብለዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን በጣም አሳዛኝ ውሳኔን መቀበል ነበረባቸው፤ ይህም ብሪትኒን በቦውት መለወጥ። በዚህም ሁለቱ እስረኞችም አቡ ዳቢ አውሮፕላን ማረፊያ መንደርደሪያ ላይ እንዲተላለፉ በማድረግ ልውውጡ ተካሄደ። ብዙም ሳይቆይ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ሳዑዲ አረቢያ የጋራ ሽምግልና ጥረታቸው ብሪታትኒ እንድትፈታ ረድቷል ሲሉ መግለጫ አወጡ። ፕሬዝዳንት ባይደን ለልውውጡ የሚሆን ቦታ ስላቀረበች የተባበሩት አረብ ኤምሬትስን ቢያመሰግኑም፣ ነገር ግን ዋይት ሐውስ መደበኛ አደራዳሪ የሚለውን ሚና ሀሳብ ዝቅ አድርጎታል። የዋይት ሐውስ የፕሬስ ሴክሬታሪ ካሪን ዣን ፒየር ሳዑዲ አረቢያ ጉዳዩን ከሞስኮ ጋር በማንሳት ቢያመሰግኑም ድርድሩ በአሜሪካ እና በሩሲያ ብቻ የተካሄደ ነው ብለዋል። የአሜሪካ ባለሥልጣናት ዊላን በስምምነቱ ውስጥ አለመካተቱ እንዳሳዘናቸው እና ከእስር እንዲፈታ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። ከዊላን ጋር ተያይዞ ያለው ዋነኛ ችግሮች “ሐሰተኛ የስለላ ወንጀል ክስ” ነው ሲሉ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን ተናግረዋል። በግልጽ እንደሚታየው ለሩሲያውያን ከሰላይ ይልቅ የስፖርት ኮከብን መለወጥ እንደ ትልቅ ጉዳይ አይተውታል ብለዋል። ብሪትኒ ታዋቂ በመሆኗ እስሯ የሚዲያ ቀልብን የሳበ ቢሆንም ከዘጠኝ ወራት በላይ በእስር ላይ የቆዩ ሌሎች አሜሪካውያንም እንዳሉ ማስታወስ ይገባል ተብሏል። በተጨማሪም አሜሪካ እንደ ልዕለ ኃያል አገርነቷ ሳይሆን ልታሳካ የምትችለው ጉዳይ ውስንነትና ከፍተኛ ዋጋ መክፈል እንደነበረባት አስታዋሽ ነው ተብሏል። “ሌላኛው ወገን ሁልጊዜም ተጠቃሚ ይሆናል” ሲሉም የአሜሪካ እስረኞች ተወካይ ሮጀር ካርስተንስ በቅርቡ ተናግረዋል። በአሁኑ ስምምነት አሜሪካ “የሞት ነጋዴ” በመባል የሚታወቀውን የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪ ከአንድ ግራም ያነሰ የካናቢስ ዘይት ይዛ በተገኘችው የስፖርት ኮከብ ለመለወጥ ተገደደች። ሁለቱ አገራት ያካሄዱት የእስረኞች ልውውጥ በዚህ ዓመት ሁለተኛው ነው። ሆኖም ይህ የእስረኞች ልውውጥ ሩሲያ እና አሜሪካ ግንኙነታቸው እንደሸከረ፣ ከመጋረጃ ጀርባ ያሉ ድርድሮች እና ንግግሮችን እንደሚቀጥሉ ያሳያል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cd1vkyy6v93o |
5sports
| ኮሮናቫይረስ፡ የሜዳ ቴኒሱ ኮከብ ሰርቢያዊው ጆኮቪች በኮቪድ-19 ተያዘ | ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ጆኮቪች 33 ዓመቱ ሲሆን በቤልግሬድ አንድ የቴኒስ ውድድር አሰናድቶ ነበር ሰሞኑን፡፡ ውድድሩ የተሰናዳው ሁለት ዓላማ አንግቦ ነበር፡፡ አንደኛው በደቡም ምሥራቅ አውሮጳ የሚገኙ ቴኒስ ተጫዋቾች ከውድድር ርቀው ስለነበር ለቀጣይ ውድድር እንዲዘጋጁ ለማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የሚገኘው ገቢ ከኮሮና ጋር በተያያዘ የሚውል ለበጎ አድራጎት እንዲሰጥ ነበር፡፡ ይህ ውድድር ገና ከመጀመሩ ታዲያ አሳዛኝ ዜና አጋጥሞታል፡፡ ቢያንስ አራት የሚሆኑ ዕውቅ የቴኒስ ተጫዋቾች በኮሮና መያዛቸው ታውቋል፡፡ ከነዚህም መሐል ክሮሺያዊው ቦርና ኮሪክ እና ሰርቢያዊው ቪክተር ትሮይኪ እንዲሁም ቡልጋሪያዊው ግሪጎር ዲሚትሮቭ ይገኙበታል። • ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች • የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ተቆልፎባቸው እንዲሰሩ የተገደዱ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገለፀ • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው ‹‹ይህንን የቴኒስ ውድድር ያሰናዳሁት ከቅን ልቦና ተነስቼ ነበር፡፡ ሁሉንም የጤና መመርያዎች ለመከተል ሞክረናል፡፡ ይህ አሳዛኝ ዜና በመምጣቱ ከልብ አዝናለሁ›› ብሏል ቾኮቪች፡፡ የእንግሊዙ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች አንዲ ሙሬይ በበኩሉ ‹‹ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው›› ሲል ትዊተር ሰሌዳው ጽፏል፡፡ ይህንን ውድድር በዚህ ወቅት ማሰናዳት አደጋ ሊኖረው ይችላል የሚል ሐሳብ ቀድሞውንም ሲንጸባረቅ ነበር፡፡ የቴኒስ ውድድሩ በጆኮቪች ሐሳብ አመንጪነት ሲሰናዳ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች ራሳቸውን ከውድድር በማራቃቸው እንደ ማነቃቂያ ሊሆናቸው ይችላል፤ በዚያውም የበጎ አድራጎት ሥራ ይሆናል በሚል ነበር፡፡ ጆኮቪች በድረገጹ እንደጻፈው መጀመርያ ቤልግሬድ እንደደረሰ በኮሮና መያዙ ይፋ የተደረገው ኖቫክና ቤተሰቡ ነበር፡፡ ሆኖም ምንም ምልክት አያሳይም ነበር፡፡ ይህ በሰርቢያ የተሰናዳው ውድድር 4ሺህ ሰዎች ታድመውታል፡፡ ሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾችም ከውድድር በኋላ መሸታ ቤት ሲደንሱ የሚያሳይ ፎቶ ወጥቷል፡፡ በመጀመርያው ቀን ውድድር የቡልጋሪያው ዲሚትሮቭ ከክሮሺያው ኮሪክ ጋር ቅዳሜ እለት ተጫውተው ነበር፡፡ ጆኮቪች ከዚህ ቀደም የኮሮናቫይረስ ክትባት ቢኖር እንኳ ክትባቱን ለመወጋት ፍቃደኛ እንደማይሆን በትዊተር ገጹ በመጻፉ የሴራ ንድፈሐሳብ አራማጆች ክትባቱ በቢልጌትስ የተቀነባበረ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማስረጃ የርሱን ጽሑፍ ሲያጋሩ ነበር፡፡ ሚስቱ ጄሌና ከዚህ ቀደም ኮሮናቫይረስ የመጣው በ5ጂ ቴክኖሎጂ ነው የሚል ይዘት ያለው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቷ ሲታይ ቤተሰቡ በወረርሽኙ ምንነት ላይ ጥርጣሬ እንደነበረው እንዲገመት በር ከፍቷል። | ኮሮናቫይረስ፡ የሜዳ ቴኒሱ ኮከብ ሰርቢያዊው ጆኮቪች በኮቪድ-19 ተያዘ ሰርቢያዊው የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች ጆኮቪች 33 ዓመቱ ሲሆን በቤልግሬድ አንድ የቴኒስ ውድድር አሰናድቶ ነበር ሰሞኑን፡፡ ውድድሩ የተሰናዳው ሁለት ዓላማ አንግቦ ነበር፡፡ አንደኛው በደቡም ምሥራቅ አውሮጳ የሚገኙ ቴኒስ ተጫዋቾች ከውድድር ርቀው ስለነበር ለቀጣይ ውድድር እንዲዘጋጁ ለማድረግ ሲሆን ሁለተኛው የሚገኘው ገቢ ከኮሮና ጋር በተያያዘ የሚውል ለበጎ አድራጎት እንዲሰጥ ነበር፡፡ ይህ ውድድር ገና ከመጀመሩ ታዲያ አሳዛኝ ዜና አጋጥሞታል፡፡ ቢያንስ አራት የሚሆኑ ዕውቅ የቴኒስ ተጫዋቾች በኮሮና መያዛቸው ታውቋል፡፡ ከነዚህም መሐል ክሮሺያዊው ቦርና ኮሪክ እና ሰርቢያዊው ቪክተር ትሮይኪ እንዲሁም ቡልጋሪያዊው ግሪጎር ዲሚትሮቭ ይገኙበታል። • ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች • የናይጄሪያ ፖሊስ በሩዝ ፋብሪካ ተቆልፎባቸው እንዲሰሩ የተገደዱ 300 ሰራተኞችን ነፃ ማውጣቱን ገለፀ • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው ‹‹ይህንን የቴኒስ ውድድር ያሰናዳሁት ከቅን ልቦና ተነስቼ ነበር፡፡ ሁሉንም የጤና መመርያዎች ለመከተል ሞክረናል፡፡ ይህ አሳዛኝ ዜና በመምጣቱ ከልብ አዝናለሁ›› ብሏል ቾኮቪች፡፡ የእንግሊዙ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋች አንዲ ሙሬይ በበኩሉ ‹‹ይህ ለኛ ትልቅ ትምህርት ነው›› ሲል ትዊተር ሰሌዳው ጽፏል፡፡ ይህንን ውድድር በዚህ ወቅት ማሰናዳት አደጋ ሊኖረው ይችላል የሚል ሐሳብ ቀድሞውንም ሲንጸባረቅ ነበር፡፡ የቴኒስ ውድድሩ በጆኮቪች ሐሳብ አመንጪነት ሲሰናዳ እውቅ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾች ራሳቸውን ከውድድር በማራቃቸው እንደ ማነቃቂያ ሊሆናቸው ይችላል፤ በዚያውም የበጎ አድራጎት ሥራ ይሆናል በሚል ነበር፡፡ ጆኮቪች በድረገጹ እንደጻፈው መጀመርያ ቤልግሬድ እንደደረሰ በኮሮና መያዙ ይፋ የተደረገው ኖቫክና ቤተሰቡ ነበር፡፡ ሆኖም ምንም ምልክት አያሳይም ነበር፡፡ ይህ በሰርቢያ የተሰናዳው ውድድር 4ሺህ ሰዎች ታድመውታል፡፡ ሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾችም ከውድድር በኋላ መሸታ ቤት ሲደንሱ የሚያሳይ ፎቶ ወጥቷል፡፡ በመጀመርያው ቀን ውድድር የቡልጋሪያው ዲሚትሮቭ ከክሮሺያው ኮሪክ ጋር ቅዳሜ እለት ተጫውተው ነበር፡፡ ጆኮቪች ከዚህ ቀደም የኮሮናቫይረስ ክትባት ቢኖር እንኳ ክትባቱን ለመወጋት ፍቃደኛ እንደማይሆን በትዊተር ገጹ በመጻፉ የሴራ ንድፈሐሳብ አራማጆች ክትባቱ በቢልጌትስ የተቀነባበረ ስለመሆኑ እንደ አንድ ማስረጃ የርሱን ጽሑፍ ሲያጋሩ ነበር፡፡ ሚስቱ ጄሌና ከዚህ ቀደም ኮሮናቫይረስ የመጣው በ5ጂ ቴክኖሎጂ ነው የሚል ይዘት ያለው ቪዲዮ በማህበራዊ ሚዲያ ማጋራቷ ሲታይ ቤተሰቡ በወረርሽኙ ምንነት ላይ ጥርጣሬ እንደነበረው እንዲገመት በር ከፍቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-53160664 |
2health
| ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን ሊሰናበቱ የፈለጉ አራት ልጆች ለለይቶ ማቆያ 600 ሺህ ብር ክፈሉ ተባሉ | በአውስትራሊያ በህይወትና በሞት መካከል ያለ አባታቸውን ሊሰናበቱ ከሌላ ከተማ ሊመጡ የፈለጉ አራት ልጆች ለሚያርፉበት ለይቶ ማቆያ ሆቴል አስራ ስድስት ሺህ ዶላር (600 ሺህ ብር) መክፈል አለባችሁ ተብለዋል። የ39 አመት አባታቸው በካንሰር ህመም በፀና የታመመ ሲሆን ኩዊንስላንድ በምትባለው ከተማ ቤቱ ውስጥ ይገኛል። አራቱ ልጆቹ ደግሞ በሌላኛዋ ከተማ ሲድኒ ናቸው ያሉት። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አውስትራሊያ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ የጣለች ሲሆን የኩዊንስላንድ ባለስልጣናትም ለዚህ ሲሉ ህጉን እንዲያላሉት ብዙዎች ተማፅነዋቸዋል። ሁኔታው ቁጣን በመቀስቀሱም ከ200 ሺህ ዶላር በላይም ገንዘብ ተዋጥቷል። መጀመሪያ ላይ ህመምተኛው ማርክ ኪንስ አንድ ልጅ ብቻ ሊያየው እንደሚችልና ከልጆቹም መምረጥ እንዳለበት ተነግሮት ነበር። በኋላም የግዛቲቷ አስተዳደር ሁኔታውን አሻሽለው ሁሉም ልጆቹ መጥተው እንዲያዩትና እንዲሰናበቱት ፈቀዱ። ሆኖም ልጆቹ ለሁለት ሳምንታት ያህል በራሳቸው ወጪ በሆቴል ለይቶ ማቆያ እንዲገቡም እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀመጠላቸው። ከዚህም በተጨማሪም ልጆቹ አባታቸውን በሚጎበኙበት ወቅት ሰውነታቸው በሙሉ በመከላከያ መሸፈን አለበት። "ባለቤቴ እሱን ለማየት ይህን ያህል ክፍያ ክፈሉ እያላችሁን ነው? ለመቅበርስ ምን ያህል ሊያስወጣን ነው? አለችኝ" በማለት የልጆቹ አያት ብሩስ ላንግቦርን ለ7 ኒውስ ተናግረዋል። ልጆቹን አባታቸውን እንዲያዩና እንዲሰናበቱም ለማስቻል በጎ ፈንድ ሚ ገንዘብ እየተሰባሰበ ነው። መጀመሪያ ታቅዶ የነበረው 30 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ ቢሆንም ባልተጠበቀ ሁኔታም 200 ሺህ ዶላር ተዋጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም አንድ ሺህ ዶላር አዋጥተዋል። በገንዘብ ማሰባሰቢያው ድረገፅም በርካቶች ቤተሰቦቹን ያፅናኑ ሲሆን፤ የኩዊንስላንድ አስተዳደርም ከፍተኛ ትችትን እያስተናገደ ነው። በርካቶችም "ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን እንዳያዩ እንዴት ይከለከላሉ? እንዲህ አይነት ገንዘብ ክፈሉ ማለትም አሳፋሪና ጨካኝነት ነው"ብለውታል። የኩዊንስላንድ የጤና ኃላፊዎች በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት አለም አቀፍ ወረርሽኝ እየታገሉ ከመሆናቸው አንፃር ህዝቡን በተለይ ተጋላጭ ማህበረሰቡን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስምረዋል። | ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን ሊሰናበቱ የፈለጉ አራት ልጆች ለለይቶ ማቆያ 600 ሺህ ብር ክፈሉ ተባሉ በአውስትራሊያ በህይወትና በሞት መካከል ያለ አባታቸውን ሊሰናበቱ ከሌላ ከተማ ሊመጡ የፈለጉ አራት ልጆች ለሚያርፉበት ለይቶ ማቆያ ሆቴል አስራ ስድስት ሺህ ዶላር (600 ሺህ ብር) መክፈል አለባችሁ ተብለዋል። የ39 አመት አባታቸው በካንሰር ህመም በፀና የታመመ ሲሆን ኩዊንስላንድ በምትባለው ከተማ ቤቱ ውስጥ ይገኛል። አራቱ ልጆቹ ደግሞ በሌላኛዋ ከተማ ሲድኒ ናቸው ያሉት። የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት አውስትራሊያ ከከተማ ወደ ከተማ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ የጣለች ሲሆን የኩዊንስላንድ ባለስልጣናትም ለዚህ ሲሉ ህጉን እንዲያላሉት ብዙዎች ተማፅነዋቸዋል። ሁኔታው ቁጣን በመቀስቀሱም ከ200 ሺህ ዶላር በላይም ገንዘብ ተዋጥቷል። መጀመሪያ ላይ ህመምተኛው ማርክ ኪንስ አንድ ልጅ ብቻ ሊያየው እንደሚችልና ከልጆቹም መምረጥ እንዳለበት ተነግሮት ነበር። በኋላም የግዛቲቷ አስተዳደር ሁኔታውን አሻሽለው ሁሉም ልጆቹ መጥተው እንዲያዩትና እንዲሰናበቱት ፈቀዱ። ሆኖም ልጆቹ ለሁለት ሳምንታት ያህል በራሳቸው ወጪ በሆቴል ለይቶ ማቆያ እንዲገቡም እንደ ቅድመ ሁኔታ ተቀመጠላቸው። ከዚህም በተጨማሪም ልጆቹ አባታቸውን በሚጎበኙበት ወቅት ሰውነታቸው በሙሉ በመከላከያ መሸፈን አለበት። "ባለቤቴ እሱን ለማየት ይህን ያህል ክፍያ ክፈሉ እያላችሁን ነው? ለመቅበርስ ምን ያህል ሊያስወጣን ነው? አለችኝ" በማለት የልጆቹ አያት ብሩስ ላንግቦርን ለ7 ኒውስ ተናግረዋል። ልጆቹን አባታቸውን እንዲያዩና እንዲሰናበቱም ለማስቻል በጎ ፈንድ ሚ ገንዘብ እየተሰባሰበ ነው። መጀመሪያ ታቅዶ የነበረው 30 ሺህ ዶላር ለመሰብሰብ ቢሆንም ባልተጠበቀ ሁኔታም 200 ሺህ ዶላር ተዋጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰንም አንድ ሺህ ዶላር አዋጥተዋል። በገንዘብ ማሰባሰቢያው ድረገፅም በርካቶች ቤተሰቦቹን ያፅናኑ ሲሆን፤ የኩዊንስላንድ አስተዳደርም ከፍተኛ ትችትን እያስተናገደ ነው። በርካቶችም "ሊሞት የተቃረበ አባታቸውን እንዳያዩ እንዴት ይከለከላሉ? እንዲህ አይነት ገንዘብ ክፈሉ ማለትም አሳፋሪና ጨካኝነት ነው"ብለውታል። የኩዊንስላንድ የጤና ኃላፊዎች በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት አለም አቀፍ ወረርሽኝ እየታገሉ ከመሆናቸው አንፃር ህዝቡን በተለይ ተጋላጭ ማህበረሰቡን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ አስምረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54119251 |
0business
| በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ሰዎችን ገደለ | በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ሲያወጡ የነበሩ ሰዎች የመደርመስ አደጋ ደርሶባቸው ሕይወታቸውን አጡ። የአገሪቱ ሄራልድ ጋዜጣ እንዳስነበበው ከሆነ በደረሰው የመሬት መደርመስ ምክንያት ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። 20 የሚሆኑት ደግሞ በተደረመሰው አፈር ተቀብረው እስካሁን መውጣት አልቻሉም። ማዕድን አውጪዎቹ ከመዲናዋ ሐረሬ በስተምዕራብ በኩል 120 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቃ በምትገኘው ክዌክዌ ከተማ ነው ማዕድን ሲያወጡ የነበረው። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንን ውሳኔን ተከትሎ የማዕድን ማውጫ ስፍራው በ2007 እ.አ.አ እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ሰዎች በሕገ ወጥ መልኩ ወደቦታው በማምራት በምሽት ማዕድን ሲያወጡ ቆይተዋል። "ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ እየሰራን እያለ በሌላኛው የማዕድን ማውጫ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የጩኸት ድምጽ ሰማን፤ ከዚያ ወጥተን ስንመለከት የተደረመሰ ድንጋይ ጓደኞቻችን ላይ እየተጫነ መሆኑን አየን" በማለት በቦታው የነበረ አንድ የማዕድን ሠራተኛ ምስክርነቱን ሰጥቷል። "አንዱን ጓደኛችንን ተረባርበን በሕይወት ማትረፍ ብንችልም ሁለቱ ግን ወዲያው ነበር የሞቱት። ከተቀበሩበት ለማውጣት ብንሞክርም የተጫናቸው አለት ከባድ በመሆኑ እርሱን ማንሳት አልቻልንም። ከሟቾቹና በሕይወት ከተረፉት ተጎጂዎች በተጨማሪ 20 የማዕድን ሠራተኞች ከመሬት በታች መውጫ አጥተዋል" ብሏል። ከአደጋው የተረፉት ተጎጂዎች ወደ አካባቢው ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ባለፈው ዓመት 22 የማዕድን ሠራተኞች በተመሳሳይ አደጋ በዚምባብዌ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአገሪቱ መንግሥትም በአሁኑ ወቅት በሕገ ወጥ ማዕድን ማውጣት ሥራ ተሰማርተዋል ያላቸውን ግለሰቦች በብዛት እያፈሰ በማሰር ላይ ይገኛል። | በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ማውጫ ተደርምሶ ሰዎችን ገደለ በዚምባብዌ የወርቅ ማዕድን ሲያወጡ የነበሩ ሰዎች የመደርመስ አደጋ ደርሶባቸው ሕይወታቸውን አጡ። የአገሪቱ ሄራልድ ጋዜጣ እንዳስነበበው ከሆነ በደረሰው የመሬት መደርመስ ምክንያት ሁለት ሰዎች ወዲያውኑ ሕይወታቸው አልፏል። 20 የሚሆኑት ደግሞ በተደረመሰው አፈር ተቀብረው እስካሁን መውጣት አልቻሉም። ማዕድን አውጪዎቹ ከመዲናዋ ሐረሬ በስተምዕራብ በኩል 120 ኪሎ ሜትር አካባቢ ርቃ በምትገኘው ክዌክዌ ከተማ ነው ማዕድን ሲያወጡ የነበረው። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣንን ውሳኔን ተከትሎ የማዕድን ማውጫ ስፍራው በ2007 እ.አ.አ እንዲዘጋ ተደርጎ ነበር። ነገር ግን ሰዎች በሕገ ወጥ መልኩ ወደቦታው በማምራት በምሽት ማዕድን ሲያወጡ ቆይተዋል። "ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ እየሰራን እያለ በሌላኛው የማዕድን ማውጫ አካባቢ ከፍተኛ የሆነ የጩኸት ድምጽ ሰማን፤ ከዚያ ወጥተን ስንመለከት የተደረመሰ ድንጋይ ጓደኞቻችን ላይ እየተጫነ መሆኑን አየን" በማለት በቦታው የነበረ አንድ የማዕድን ሠራተኛ ምስክርነቱን ሰጥቷል። "አንዱን ጓደኛችንን ተረባርበን በሕይወት ማትረፍ ብንችልም ሁለቱ ግን ወዲያው ነበር የሞቱት። ከተቀበሩበት ለማውጣት ብንሞክርም የተጫናቸው አለት ከባድ በመሆኑ እርሱን ማንሳት አልቻልንም። ከሟቾቹና በሕይወት ከተረፉት ተጎጂዎች በተጨማሪ 20 የማዕድን ሠራተኞች ከመሬት በታች መውጫ አጥተዋል" ብሏል። ከአደጋው የተረፉት ተጎጂዎች ወደ አካባቢው ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተደረገላቸው ነው። ባለፈው ዓመት 22 የማዕድን ሠራተኞች በተመሳሳይ አደጋ በዚምባብዌ ሕይወታቸውን አጥተዋል። የአገሪቱ መንግሥትም በአሁኑ ወቅት በሕገ ወጥ ማዕድን ማውጣት ሥራ ተሰማርተዋል ያላቸውን ግለሰቦች በብዛት እያፈሰ በማሰር ላይ ይገኛል። | https://www.bbc.com/amharic/news-51410600 |
0business
| ኩባ በህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ለአነስተኛ እና መካከለኛ የግል ንግዶች ፍቃድ ሰጠች | ግለሰቦች ለሚያስተዳድሯቸው አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች ለአመታት ፍቃድ ከልክላ የነበረችው ኩባ ባለፈው ወር በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ይህንን ህግ ሽራለች። የኩባ ኮሚኒስት መንግሥት ሕዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ አነስተኛና መካከለኛ የግል ንግዶችን ሕጋዊ እንዲሆኑ አድርጓል። በአዲሱ ህግ መሰረት እስከ 100 ሰራተኞች ያሉት የንግድ ድርጅቶችን ግለሰቦች እንዲያቋቁሙ ተፈቅዷል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚጌል ዲአዝ-ካኔል ኩባ የኢኮኖሚ ሞዴሏን ለማዘመን ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው ብለዋል። ሆኖም ሺዎች የኢኮኖሚውን ሁኔታ በተመለከተ አደባባይ መውጣታቸው መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ በፍጥነት እንዲደርስ ምክንያት ነው የሚሉ አስተያየቶች ተደምጠዋል። ሰልፈኞቹ የሀገሪቱ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የያዘበትን መንገድ ያወገዙ ሲሆን የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ሀገሪቱ በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ባለችበት ጊዜ በተነሳው በዚህ ተቃውሞው ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ በርካቶች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ባስከተለው አለመረጋጋት ቢያንስ አንድ ሰው መሞቱ ተዘግቧል። ታዲያ ባለፈው አርብ አነስተኛና መካከለኛ ንግድን በተመለከተ መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ በሀገሪቱ የተደረገ ትልቅ የፖሊሲ ለውጥ ነው ተብሏል። ኢኮኖሚዋ እየላሸቀ ነው የምትባለው ኩባ በሐምሌ ወር ባለሥልጣናቱ ወደ አገሪቱ የሚመጡ ተጓዦች ግብር መክፈል ሳይጠበቅባቸው ምግብ ፣ መድኃኒት እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያመጡ ፍቅዳለች። በሀገሪቱ አለ የሚባለውን የመድኃኒት እና የምግብ እጥረትን ለማቃለል አንዳንድ ኩባንያዎች ከውጭ የሚያስገቡበትን ግብር እስከመሻር ደርሳለች። ለኩባ ኢኮኖሚ ወሳኝ ከሆኑት ዘርፎች አንዱ የሆነው ቱሪዝም በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በዓለም አቀፍ የጉዞ ገደቦች ምክንያት ክፉኛ ተጎድተውባታል። የስኳር ምርትን ወደ ውጭ መላክ ሌላኛው የኩባ ቁልፍ ገቢ ነው። ሆኖም የዘንድሮው ምርት ግን ከተጠበቀው እጅግ የወረደ ሆኗል። የዚህም ድምር የመንግስት የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲሞጠጥ ምክንያት በመሆኑ እጥረትን ለማሟላት ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን መግዛት ለሀገሪቱ ፈተና ሆኗል። ኩባ በቅርቡ ለተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞው እና ለሰፊ ችግሮቿ አሜሪካን እና የጣለችባትን የኢኮኖሚ ማዕቀቦ ዋነኛ ምክንያት አድርጋ ትከሳለች። | ኩባ በህዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ለአነስተኛ እና መካከለኛ የግል ንግዶች ፍቃድ ሰጠች ግለሰቦች ለሚያስተዳድሯቸው አነስተኛና መካከለኛ ንግዶች ለአመታት ፍቃድ ከልክላ የነበረችው ኩባ ባለፈው ወር በተካሄደው ሕዝባዊ ተቃውሞ ምክንያት ይህንን ህግ ሽራለች። የኩባ ኮሚኒስት መንግሥት ሕዝባዊ ተቃውሞን ተከትሎ አነስተኛና መካከለኛ የግል ንግዶችን ሕጋዊ እንዲሆኑ አድርጓል። በአዲሱ ህግ መሰረት እስከ 100 ሰራተኞች ያሉት የንግድ ድርጅቶችን ግለሰቦች እንዲያቋቁሙ ተፈቅዷል። የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ሚጌል ዲአዝ-ካኔል ኩባ የኢኮኖሚ ሞዴሏን ለማዘመን ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደች ነው ብለዋል። ሆኖም ሺዎች የኢኮኖሚውን ሁኔታ በተመለከተ አደባባይ መውጣታቸው መንግስት እዚህ ውሳኔ ላይ በፍጥነት እንዲደርስ ምክንያት ነው የሚሉ አስተያየቶች ተደምጠዋል። ሰልፈኞቹ የሀገሪቱ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን የያዘበትን መንገድ ያወገዙ ሲሆን የፖለቲካ ለውጥ እንዲደረግ ጠይቀዋል። ሀገሪቱ በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ባለችበት ጊዜ በተነሳው በዚህ ተቃውሞው ምክንያት በአገር አቀፍ ደረጃ በርካቶች ለእስር የተዳረጉ ሲሆን ባስከተለው አለመረጋጋት ቢያንስ አንድ ሰው መሞቱ ተዘግቧል። ታዲያ ባለፈው አርብ አነስተኛና መካከለኛ ንግድን በተመለከተ መንግስት ያሳለፈው ውሳኔ በሀገሪቱ የተደረገ ትልቅ የፖሊሲ ለውጥ ነው ተብሏል። ኢኮኖሚዋ እየላሸቀ ነው የምትባለው ኩባ በሐምሌ ወር ባለሥልጣናቱ ወደ አገሪቱ የሚመጡ ተጓዦች ግብር መክፈል ሳይጠበቅባቸው ምግብ ፣ መድኃኒት እና ሌሎች አስፈላጊ ነገሮችን እንዲያመጡ ፍቅዳለች። በሀገሪቱ አለ የሚባለውን የመድኃኒት እና የምግብ እጥረትን ለማቃለል አንዳንድ ኩባንያዎች ከውጭ የሚያስገቡበትን ግብር እስከመሻር ደርሳለች። ለኩባ ኢኮኖሚ ወሳኝ ከሆኑት ዘርፎች አንዱ የሆነው ቱሪዝም በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት በዓለም አቀፍ የጉዞ ገደቦች ምክንያት ክፉኛ ተጎድተውባታል። የስኳር ምርትን ወደ ውጭ መላክ ሌላኛው የኩባ ቁልፍ ገቢ ነው። ሆኖም የዘንድሮው ምርት ግን ከተጠበቀው እጅግ የወረደ ሆኗል። የዚህም ድምር የመንግስት የውጭ ምንዛሪ ክምችት እንዲሞጠጥ ምክንያት በመሆኑ እጥረትን ለማሟላት ከውጭ የሚገቡ ዕቃዎችን መግዛት ለሀገሪቱ ፈተና ሆኗል። ኩባ በቅርቡ ለተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃውሞው እና ለሰፊ ችግሮቿ አሜሪካን እና የጣለችባትን የኢኮኖሚ ማዕቀቦ ዋነኛ ምክንያት አድርጋ ትከሳለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-58135227 |
5sports
| ሴኔጋላዊያን የብሬክ ዳንሰኞች የኦሎምፒክ ተሳታፊ ለመሆን ተስፋ ሰንቀዋል | ሴኔጋላዊያን የብሬክ ዳንሰኞች የኦሎምፒክ ተሳታፊ ለመሆን ተስፋ ሰንቀዋል | ሴኔጋላዊያን የብሬክ ዳንሰኞች የኦሎምፒክ ተሳታፊ ለመሆን ተስፋ ሰንቀዋል ሴኔጋላዊያን የብሬክ ዳንሰኞች የኦሎምፒክ ተሳታፊ ለመሆን ተስፋ ሰንቀዋል | https://www.bbc.com/amharic/sport-50210682 |
5sports
| 'ፌክ' ፓስፖርት ይዞ ተገኝቷል የተባለው ሮናልዲንሆ ፍርድ ቤት ቀረበ | ብራዚላዊ የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅመዋል ተብለው በመጠርጠራቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ። አቃቤ ሕግ፤ ወንድማማቾቹ ባለፈው ረቡዕ የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን ሲደርሱ ሃሰተኛ ሰንዶች ተሰጥቷቸዋል ሲል ይከሳል። አቃቤ ሕግ ወንድማማቾቹ ቀለል ያለ ቅጣት ይቀጡ የሚል ሃሳብ ቢያቀርብም ዳኛው ግን የኋሊት ጠፍራችሁ አምጡልኝ ሲሉ አዘዋል። ሮናልዲንሆና ወንድሙ አርብ ዕለት ነው የካቴና ሲሳይ የሆኑት። አቃቤ ሕግ ሮናልዲንሆና ወንድሙ በቀጣፊዎች ተታለዋል ይላል። ወንድማማቾቹም 'እኛ የምናውቀው ነገር የለም' ይላሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ያረፉበትን ሆቴል ከበረበረ በኋላ ምርመራ አድርጎባቸዋል። ሮናልዲሆንና ወንድሙ 'ፖስፖርቱ ሲሰጠን የክብር መገለጫ መስሎን ነበር' ይላሉ። ፓርጓዊው ዳኛ ሮናልዲንሆም ሆነ ወንድሙ ፍርድ እስኪሰጣቸው ድረስ ማቆያ እንዲሰነብቱ አዘዋል። ዓለም ካየቻቸው ድንቅ እግር ኳሰኞች አንዱ የሚባለው ሮናልዲንሆ ባለፈው ሐምሌ ግብር አልከፈለም ተብሎ የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን መነጠቁ አይዘነጋም። አልፎም ብራዚል ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈጥሮ ሃብት መጠበቂያ ሥፍራ ገንብቷል ተብሎ ክስ ቀርቦበት ነበር። «ቃዋቂ እግር ኳሰኛ ነው። አከብረዋለሁ። ነገር ግን ሕግ ሕግ ነው» ሲሉ የፓራጓይ ሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ለሃገራቸው ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አዲስ የታተመ መፅሐፉን ለማስተዋወቅና እርዳታ ለሚሹ ሕፃናት ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው። ሁለት ጊዜ የዓለም ኮከብ ተብሎ የተሸለመው ሮናልዶ የ2002 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ ነው። አልፎም ከባርሴሎና ጋር ስኬታማ ጊዜ አሳልፏል። ብራዚላዊው የኳስ ቀማሪ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የተጣራ ሃብት እንዳለው ይገመታል። | 'ፌክ' ፓስፖርት ይዞ ተገኝቷል የተባለው ሮናልዲንሆ ፍርድ ቤት ቀረበ ብራዚላዊ የእግር ኳስ ጠቢብ ሮናልዲንሆና ወንድሙ ፓራጓይ ለመግባት ሃሰተኛ ፓስፖርት ተጠቅመዋል ተብለው በመጠርጠራቸው ፍርድ ቤት ቀረቡ። አቃቤ ሕግ፤ ወንድማማቾቹ ባለፈው ረቡዕ የፓራጓይ ዋና ከተማ አሱንሲዮን ሲደርሱ ሃሰተኛ ሰንዶች ተሰጥቷቸዋል ሲል ይከሳል። አቃቤ ሕግ ወንድማማቾቹ ቀለል ያለ ቅጣት ይቀጡ የሚል ሃሳብ ቢያቀርብም ዳኛው ግን የኋሊት ጠፍራችሁ አምጡልኝ ሲሉ አዘዋል። ሮናልዲንሆና ወንድሙ አርብ ዕለት ነው የካቴና ሲሳይ የሆኑት። አቃቤ ሕግ ሮናልዲንሆና ወንድሙ በቀጣፊዎች ተታለዋል ይላል። ወንድማማቾቹም 'እኛ የምናውቀው ነገር የለም' ይላሉ። ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ ያረፉበትን ሆቴል ከበረበረ በኋላ ምርመራ አድርጎባቸዋል። ሮናልዲሆንና ወንድሙ 'ፖስፖርቱ ሲሰጠን የክብር መገለጫ መስሎን ነበር' ይላሉ። ፓርጓዊው ዳኛ ሮናልዲንሆም ሆነ ወንድሙ ፍርድ እስኪሰጣቸው ድረስ ማቆያ እንዲሰነብቱ አዘዋል። ዓለም ካየቻቸው ድንቅ እግር ኳሰኞች አንዱ የሚባለው ሮናልዲንሆ ባለፈው ሐምሌ ግብር አልከፈለም ተብሎ የብራዚልና የስፔን ፓስፖርቱን መነጠቁ አይዘነጋም። አልፎም ብራዚል ውስጥ በሕገ-ወጥ መንገድ የተፈጥሮ ሃብት መጠበቂያ ሥፍራ ገንብቷል ተብሎ ክስ ቀርቦበት ነበር። «ቃዋቂ እግር ኳሰኛ ነው። አከብረዋለሁ። ነገር ግን ሕግ ሕግ ነው» ሲሉ የፓራጓይ ሃገር ውስጥ ሚኒስቴር ለሃገራቸው ጋዜጠኞች ተናግረዋል። የ39 ዓመቱ ሮናልዲንሆ ወደ ፓራጓይ ያቀናው አዲስ የታተመ መፅሐፉን ለማስተዋወቅና እርዳታ ለሚሹ ሕፃናት ድጋፍ ለማሰባሰብ ነው። ሁለት ጊዜ የዓለም ኮከብ ተብሎ የተሸለመው ሮናልዶ የ2002 ዓለም ዋንጫ አሸናፊ ነው። አልፎም ከባርሴሎና ጋር ስኬታማ ጊዜ አሳልፏል። ብራዚላዊው የኳስ ቀማሪ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የተጣራ ሃብት እንዳለው ይገመታል። | https://www.bbc.com/amharic/51789011 |
2health
| ትግራይ ውስጥ ከባድ የጤና ስጋት የፈጠሩ 3 ተላላፊ በሽታዎች | በትግራይ ክልል ወባ፣ ኮሌራ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ እንዲሁም አባ ሠንጋ በወረርሽኝ መልክ መከሰታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ። የክልሉ ጤና ቢሮ እንደሚለው ከሆነ ከእነዚህ በሽታዎች መካከል ውስጥ ሶስቱ በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ሆነዋል። ቢሮው ለቢቢሲ በላከው መረጃ መሰረት የእብድ ውሻ በሽታ፣ አባ ሠንጋ እንዲሁም ወባ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረ የመድሃኒት እጥረት፣ የጤና ተቋማት መዳከም እንዲሁም የመገናኛ መንገዶች መቋረጥና የአቅርቦት እጥረት ከተያያዥ ችግሮች ጋር ተደማምረው ለበሽታዎቹ መስፋፋት ዋና ምክንያቶች ሆነዋል። ትግራይ ውስጥ የተከሰቱ ሶስት ከባድ የጤና ስጋቶች የትኞቹ ናቸው? አባ ሠንጋ ትግራይ ውስጥ ‘መገረም’ በሚል የሚታወቅ ሲሆን በቀላሉ ማወቅና ለጤና ባለሙያዎች ማሳወቅ ከሚቻሉ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው። በዚህ ዓመት (2022) ማእከላዊ ዞን ናዕዴር ዓዴት ወረዳ ውስጥ 10 ሰዎች መያዛቸውን የሚያመላክት ሪፖርት ቀርቧል። ከዚያ ወዲህ ወደ ክልሉ ጤና ቢሮ ሪፖርት የላኩ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በበሽታው የተጠቁ በርካታ ሰዎች መኖራቸው ታውቋል። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ " ሰኔ10/2022 ዓ.ም በታሕታይ ቆራሮ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ የዓዲ-ገሽቲን ዓዲ-ሓበሳይን ጣብያዎች እንዲሁም ሰሜን ምዕራብና ምስራቅ ዞኖች ውስጥ ሞት ሲያጋጥም ሰዎችና እንስሳት መያዛቸው የሚያሳይ መረጃ አለኝ" ብሏል። ይህን ተከትሎ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO)፣ ከእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ፣ እንዲሁም ከጤና ቢሮ የተውጣጣ ቡድን ሰኔ 22 2022 ሁኔታውን መርምሮ የመከላከል ስራ እንዲሰራ ተልኳል። ቡድኑ ከእንስሳት ጋር ንክኪ ከነበራቸውና ስጋ ከበሉ 120 ሰዎች መካከል 34 በበሽታው እንደተያዙ እና ሁለት ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ አረጋግጧል። በበሽታው መያዛቸውከተጠረጠሩ 30 የቤት እንስሳት (ከብቶት፣ ፍየሎችና አህዮች) ውስጥ 23 ሞት እንዳጋጠመ ተገንዝቧል። "በዳሰሳቸው 12 ወረዳዎችን ለማዳረስ የሞከሩ ሲሆን በመንገዳቸው ላይ 13 በአባ ሠንጋ የተያዙ ሰባት [አንድ ላዕላይ ማይጨው 12 ደግሞ ቆላ ተምቤን ውስጥ] አግኝተዋል" ይላል የክልሉ ጤና ቢሮ ለቢቢሲ የላከው መረጃ። ክልሉ አክሎም በመገናኛ እጥረት ሳብያ ግን የህዝብ ጤና ስጋት አስተዳደር [Public health Emergency Management (PHEM)] ቡድን ከሁሉም ወረዳዎች የጤና ተቋማት ሙሉ መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ከመጋቢት 2022 መጨረሻ ጀምሮ በማእከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ዞኖች ውስጥ በጠቅላላ በአባ ሠንጋ መያዛቸው የተጠረጠሩ 116 ሰዎችና 7 ሞት እንደተመዘገበ የጤና ቢሮ ሪፖርት ያመለክታል። ከጦርነቱ በፊት የእብድ ውሻ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ስራ በማህበረሰቡ፣ በመጀመርያ ደረጃ የጤና ክትትል ቡድን እንዲሁም ሆስፒታሎች ይሰራ ነበር። በወቅቱ በርካታ የጤና ተቋማት በበሽታው ስለተጠረጠሩና ስላጋጠመ ሞት የሚያሳይ ሪፖርት ያቀርቡ ነበር። የውሾች ክትባት፣ ባለቤት የሌላቸው ውሾች አስተዳደር፣ በበሽታው ለተያዙ ሰዎች የሚደረግ ህክምና እንዲሁም የህዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይነት ስኬታማ በሆነ መልኩ ይካሄዱ ነበር። እስከ 2030 በእብድ ውሻ በሽታ የሚያጋጥም ሞት ዜሮ ለማድረስ እየተሰራ እንደነበር የትግራይ ክልል የጤና ቢሮ ያመለክታል። "ይሁን እንጂ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስና ከበባ በአሁኑ ወቅት በውሻ መነከስንና በበሽታው መያዝን የሚመለከት ሪፖርት ከ12 በመቶ በታች በሆኑ የጤና ተቋማት ብቻ ተገድቦ እንደሚገኝ" የትግራይ ክልል የላከው ሪፖርት ያሳያል። "በአሁኑ ወቅት በውሻ መነከስና ያጋጠመ ሞትን የሚመለከቱ ይፋ የሆኑና ያልሆኑ ሪፖርቶች ወደ ቢሮው እየመጡ ነው” የሚለው የትግራይ የጤና ቢሮ፣ በጦርነቱ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት ለውሾች የሚሆን ክትባት፣ ባለቤት የሌላቸው ውሾችን ለማስወገድ የሚውል ‘ስትሪክኒን’ የሚባል ኬሚካል እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚረዳ የመድሃኒት አቅርቦት እንደሌለ አስረድቷል። በዚህም ምክንያት በ11 የትግራይ ወረዳዎች 41 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። እንዲሁም በበሽታው የታመሙ ሰዎች ለማከም የሚረዳ መድሃኒት ባለመኖሩ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቤታቸው በባህላዊ መንገድ አልያም ወደ ባህላዊ ሐኪም በመሄድ መፍትሔ ለማግኘት እንዲጥሩ እያስገደዳቸው ነው። በትግራይ ክልል የወባ ወረርሽኝ ከመስከረም -እስከ ታሕሳስ ባለው ወቅት እጅግ ስፋት ባለው ሁኔታ የሚታይ ሲሆን፤ በሚያዝያ እና ግንቦት ወራትም ያጋጥማል። በክልሉ ለመጨረሻ ጊዜ ወረርሽኝ የተከሰተው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ ሲሆን አካባቢውም አሕፈሮም የሚባል ወረዳ ነበረ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የወባ በሽታ የመከላከል እና የቁጥጥር ስትራቴጂዎች በተገቢው መንገድ በመተግበራቸው የበሽታው ወረርሽኝ አጋጥሞ አያውቅም። አሁን ላይ በጦርነቱ ሳቢያ ተገቢ የህክምና አገልግሎት፣ የህክምና አቅርቦቶች እና መደበኛ ክትትል ባለመኖሩ የበሽታው መስፋፋትና በበሽታው ምክንያት የሚያጋጥም ሞት እየተመዘገበ መሆኑ የክልሉ ቢሮ ለቢቢሲ ገልጿል። ወረርሽኙን ለመከላከል እና ህይወትን ለማዳን ቀድሞ ስለበሽታው መስፋፋት ማወቅ እና የታካሚ መረጃ ማግኘት ወሳኝ መሆኑን የጤና ቢሮው ይገልጻል። ነገር ግን በትግራይ የመገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት በመቋረጡ እና ከየአካባቢው የሚቀርቡ መረጃዎች ያልተሟሉ በመሆናቸው የበሽታው መስፋፋት በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት እንዳዳገተው ገልጿል። ወባ ከሰኔ 2020 ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ በወረርሽኝ መልክ እየተዛመተ መሆኑን የትግራይ ጤና ቢሮ ያስረዳል። የበሽታውን ሁኔታ የሚያጠና የባለሙያዎች ቡድን ወደ ተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እንደተላኩ የሚገልፀው ጤና ቢሮው "ለቡድኑ ጉዞ የቀረበ የነዳጅ እና የገንዘብ ድጋፍ መቀለ በሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ፅህፈት ቤት የተሸፈነ ነው። ሆኖም ግን በነዳጅ እና በጊዜ እጥረት የበሽታውን ዋና መንስኤ መለየት አልቻሉም” ብሏል። እ.ኤ.አ. እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2022 ባለው ጊዜ በትግራይ ውስጥ ከ10 በላይ ወረዳዎች የወባ በሽታ መስፋፋት ታይቷል። በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀረ ወባ መድሐኒት እና ሌሎች የህክምና አቅርቦቶች ባለመኖሩም ሁኔታው ተባብሷል። ወረርሽኙን በጊዜ መቆጣጠር ካልተቻለ ወደ ብዙ የትግራይ አካባቢዎች ሊዛመት እንደሚችል ነው የትግራይ ጤና ቢሮ ያስጠነቀቀው። | ትግራይ ውስጥ ከባድ የጤና ስጋት የፈጠሩ 3 ተላላፊ በሽታዎች በትግራይ ክልል ወባ፣ ኮሌራ፣ የእብድ ውሻ በሽታ፣ እንዲሁም አባ ሠንጋ በወረርሽኝ መልክ መከሰታቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ። የክልሉ ጤና ቢሮ እንደሚለው ከሆነ ከእነዚህ በሽታዎች መካከል ውስጥ ሶስቱ በከፍተኛ ደረጃ ስጋት ሆነዋል። ቢሮው ለቢቢሲ በላከው መረጃ መሰረት የእብድ ውሻ በሽታ፣ አባ ሠንጋ እንዲሁም ወባ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረ የመድሃኒት እጥረት፣ የጤና ተቋማት መዳከም እንዲሁም የመገናኛ መንገዶች መቋረጥና የአቅርቦት እጥረት ከተያያዥ ችግሮች ጋር ተደማምረው ለበሽታዎቹ መስፋፋት ዋና ምክንያቶች ሆነዋል። ትግራይ ውስጥ የተከሰቱ ሶስት ከባድ የጤና ስጋቶች የትኞቹ ናቸው? አባ ሠንጋ ትግራይ ውስጥ ‘መገረም’ በሚል የሚታወቅ ሲሆን በቀላሉ ማወቅና ለጤና ባለሙያዎች ማሳወቅ ከሚቻሉ በሽታዎች መካከል አንዱ ነው። በዚህ ዓመት (2022) ማእከላዊ ዞን ናዕዴር ዓዴት ወረዳ ውስጥ 10 ሰዎች መያዛቸውን የሚያመላክት ሪፖርት ቀርቧል። ከዚያ ወዲህ ወደ ክልሉ ጤና ቢሮ ሪፖርት የላኩ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በበሽታው የተጠቁ በርካታ ሰዎች መኖራቸው ታውቋል። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ " ሰኔ10/2022 ዓ.ም በታሕታይ ቆራሮ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ የዓዲ-ገሽቲን ዓዲ-ሓበሳይን ጣብያዎች እንዲሁም ሰሜን ምዕራብና ምስራቅ ዞኖች ውስጥ ሞት ሲያጋጥም ሰዎችና እንስሳት መያዛቸው የሚያሳይ መረጃ አለኝ" ብሏል። ይህን ተከትሎ ከዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO)፣ ከእርሻና ገጠር ልማት ቢሮ፣ እንዲሁም ከጤና ቢሮ የተውጣጣ ቡድን ሰኔ 22 2022 ሁኔታውን መርምሮ የመከላከል ስራ እንዲሰራ ተልኳል። ቡድኑ ከእንስሳት ጋር ንክኪ ከነበራቸውና ስጋ ከበሉ 120 ሰዎች መካከል 34 በበሽታው እንደተያዙ እና ሁለት ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ አረጋግጧል። በበሽታው መያዛቸውከተጠረጠሩ 30 የቤት እንስሳት (ከብቶት፣ ፍየሎችና አህዮች) ውስጥ 23 ሞት እንዳጋጠመ ተገንዝቧል። "በዳሰሳቸው 12 ወረዳዎችን ለማዳረስ የሞከሩ ሲሆን በመንገዳቸው ላይ 13 በአባ ሠንጋ የተያዙ ሰባት [አንድ ላዕላይ ማይጨው 12 ደግሞ ቆላ ተምቤን ውስጥ] አግኝተዋል" ይላል የክልሉ ጤና ቢሮ ለቢቢሲ የላከው መረጃ። ክልሉ አክሎም በመገናኛ እጥረት ሳብያ ግን የህዝብ ጤና ስጋት አስተዳደር [Public health Emergency Management (PHEM)] ቡድን ከሁሉም ወረዳዎች የጤና ተቋማት ሙሉ መረጃ ማግኘት እንዳልቻለ ገልጿል። ከመጋቢት 2022 መጨረሻ ጀምሮ በማእከላዊ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ ደቡብ ምስራቅና ምስራቅ ዞኖች ውስጥ በጠቅላላ በአባ ሠንጋ መያዛቸው የተጠረጠሩ 116 ሰዎችና 7 ሞት እንደተመዘገበ የጤና ቢሮ ሪፖርት ያመለክታል። ከጦርነቱ በፊት የእብድ ውሻ በሽታ ቁጥጥርና መከላከል ስራ በማህበረሰቡ፣ በመጀመርያ ደረጃ የጤና ክትትል ቡድን እንዲሁም ሆስፒታሎች ይሰራ ነበር። በወቅቱ በርካታ የጤና ተቋማት በበሽታው ስለተጠረጠሩና ስላጋጠመ ሞት የሚያሳይ ሪፖርት ያቀርቡ ነበር። የውሾች ክትባት፣ ባለቤት የሌላቸው ውሾች አስተዳደር፣ በበሽታው ለተያዙ ሰዎች የሚደረግ ህክምና እንዲሁም የህዝብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች በቀጣይነት ስኬታማ በሆነ መልኩ ይካሄዱ ነበር። እስከ 2030 በእብድ ውሻ በሽታ የሚያጋጥም ሞት ዜሮ ለማድረስ እየተሰራ እንደነበር የትግራይ ክልል የጤና ቢሮ ያመለክታል። "ይሁን እንጂ ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠረው ቀውስና ከበባ በአሁኑ ወቅት በውሻ መነከስንና በበሽታው መያዝን የሚመለከት ሪፖርት ከ12 በመቶ በታች በሆኑ የጤና ተቋማት ብቻ ተገድቦ እንደሚገኝ" የትግራይ ክልል የላከው ሪፖርት ያሳያል። "በአሁኑ ወቅት በውሻ መነከስና ያጋጠመ ሞትን የሚመለከቱ ይፋ የሆኑና ያልሆኑ ሪፖርቶች ወደ ቢሮው እየመጡ ነው” የሚለው የትግራይ የጤና ቢሮ፣ በጦርነቱ ምክንያት ባለፉት ሁለት ዓመታት ለውሾች የሚሆን ክትባት፣ ባለቤት የሌላቸው ውሾችን ለማስወገድ የሚውል ‘ስትሪክኒን’ የሚባል ኬሚካል እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚረዳ የመድሃኒት አቅርቦት እንደሌለ አስረድቷል። በዚህም ምክንያት በ11 የትግራይ ወረዳዎች 41 ሰዎች በእብድ ውሻ በሽታ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል። እንዲሁም በበሽታው የታመሙ ሰዎች ለማከም የሚረዳ መድሃኒት ባለመኖሩ በበሽታው የተያዙ ሰዎች በቤታቸው በባህላዊ መንገድ አልያም ወደ ባህላዊ ሐኪም በመሄድ መፍትሔ ለማግኘት እንዲጥሩ እያስገደዳቸው ነው። በትግራይ ክልል የወባ ወረርሽኝ ከመስከረም -እስከ ታሕሳስ ባለው ወቅት እጅግ ስፋት ባለው ሁኔታ የሚታይ ሲሆን፤ በሚያዝያ እና ግንቦት ወራትም ያጋጥማል። በክልሉ ለመጨረሻ ጊዜ ወረርሽኝ የተከሰተው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ከመጋቢት እስከ ሚያዝያ ሲሆን አካባቢውም አሕፈሮም የሚባል ወረዳ ነበረ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የወባ በሽታ የመከላከል እና የቁጥጥር ስትራቴጂዎች በተገቢው መንገድ በመተግበራቸው የበሽታው ወረርሽኝ አጋጥሞ አያውቅም። አሁን ላይ በጦርነቱ ሳቢያ ተገቢ የህክምና አገልግሎት፣ የህክምና አቅርቦቶች እና መደበኛ ክትትል ባለመኖሩ የበሽታው መስፋፋትና በበሽታው ምክንያት የሚያጋጥም ሞት እየተመዘገበ መሆኑ የክልሉ ቢሮ ለቢቢሲ ገልጿል። ወረርሽኙን ለመከላከል እና ህይወትን ለማዳን ቀድሞ ስለበሽታው መስፋፋት ማወቅ እና የታካሚ መረጃ ማግኘት ወሳኝ መሆኑን የጤና ቢሮው ይገልጻል። ነገር ግን በትግራይ የመገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት በመቋረጡ እና ከየአካባቢው የሚቀርቡ መረጃዎች ያልተሟሉ በመሆናቸው የበሽታው መስፋፋት በተመለከተ ትክክለኛ መረጃ ለማግኘት እንዳዳገተው ገልጿል። ወባ ከሰኔ 2020 ሁለተኛ ሳምንት ጀምሮ በወረርሽኝ መልክ እየተዛመተ መሆኑን የትግራይ ጤና ቢሮ ያስረዳል። የበሽታውን ሁኔታ የሚያጠና የባለሙያዎች ቡድን ወደ ተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች እንደተላኩ የሚገልፀው ጤና ቢሮው "ለቡድኑ ጉዞ የቀረበ የነዳጅ እና የገንዘብ ድጋፍ መቀለ በሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ፅህፈት ቤት የተሸፈነ ነው። ሆኖም ግን በነዳጅ እና በጊዜ እጥረት የበሽታውን ዋና መንስኤ መለየት አልቻሉም” ብሏል። እ.ኤ.አ. እስከ ሐምሌ 23 ቀን 2022 ባለው ጊዜ በትግራይ ውስጥ ከ10 በላይ ወረዳዎች የወባ በሽታ መስፋፋት ታይቷል። በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የፀረ ወባ መድሐኒት እና ሌሎች የህክምና አቅርቦቶች ባለመኖሩም ሁኔታው ተባብሷል። ወረርሽኙን በጊዜ መቆጣጠር ካልተቻለ ወደ ብዙ የትግራይ አካባቢዎች ሊዛመት እንደሚችል ነው የትግራይ ጤና ቢሮ ያስጠነቀቀው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c72wzeg612do |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ዋይት ሀውስ በዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ንግግር ተቆጣ | ዋይት ሀውስ፤ ከፍተኛ የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ፤ ስለ ኮሮናቫይረስ ያደረጉት ንግግር ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ሲል ከሰሰ። ዶ/ር ፋውቺ ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ አሜሪካ “ከፍተኛ ጉዳት ገጥሟታል” ብለዋል። አሜሪካ ከየትኛው አገር በበለጠ በወረርሽኙ ሳቢያ ዜጎቿን አጥታለች። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት ከ230,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ደግሞ በቫይረሱ ተይዟል። ዶ/ር ፋውቺ በቃለ ምልልሱ ላይ “ወደቀዝቃዛው ወቅት ስንገባ ነገሮች ይባባሳሉ” ብለዋል። በተያያዥም ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ስለ ወረርሽኙ ያላቸውን አቋም ገምግመዋል። ባይደን ለቫይረሱ ተገቢውን ትኩረት እንደሰጡት “ከሕብረተሰብ ጤና እና ከምጣኔ ሀብት አንጻርም በቁምነገር እየተከታተሉት ነው” በማለት ገልጸዋል። አሜሪካ የሕብረተሰብ ጤናን በተመለከተ ለውጥ ማምጣት እንዳለባት አሳስበዋል። በዚህ የዶ/ር ፋውቺ አስተያየት ዋይት ሀውስ ደስተኛ አልሆነም። ባይደን ምርጫውን እንዲያሸንፉ የሚገፋ ምላሽ ነው በማለትም ዶክተሩን ተችተዋል። ቃል አቀባዩ ጁድ ደሬ፤ “አስተያየቱ ተቀባይነት የለውም። ከመርህ ውጪ ነው። ዶ/ር ፋውቺ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል አባል እንደመሆናቸው ለለውጥ መገፋፋት ነበር የሚጠበቅባቸው። እሳቸው ግን ፕሬዘዳንቱን በመተቸት ለተቀናቃኛቸው ወገንተኝነት አሳይተዋል” ብሏል። የወረርሽኙ ጉዳይ በትራምፕ እና በባይደን መካከል ዋነኛ ከሆኑት መከራከሪያ ነጥቦች አንዱ ነው።ባይደን “ውሳኔያችን ሳይንስን የተመረኮዘ መሆን አለበት” ብለው፤ ምርጫውን ካሸነፉ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ትራምፕ በበኩላቸው፤ ባይደን እንቅስቃሴ ላይ ገደብ በመጣል አሜሪካውያንን የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ይከታሉ ብለዋል። “ባይደንን ከመራጥችሁ ትምህርት ቤት አይከፈትም። ተማሪዎች አይመረቁም። ሠርግ አይኖርም። ገና አይከበርም” ብለዋል። ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጡ መርሆችን ተከትለው ነው። በሌላ በኩል ትራምፕ አካላዊ ርቀት ሳይጠበቅ በርካታ ዜጎች የተገኙባቸው የምረጡኝ ቅስቀሳዎች አካሂደዋል። | ኮሮናቫይረስ፡ ዋይት ሀውስ በዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ንግግር ተቆጣ ዋይት ሀውስ፤ ከፍተኛ የተላላፊ በሽታዎች ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ፤ ስለ ኮሮናቫይረስ ያደረጉት ንግግር ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ሲል ከሰሰ። ዶ/ር ፋውቺ ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ አሜሪካ “ከፍተኛ ጉዳት ገጥሟታል” ብለዋል። አሜሪካ ከየትኛው አገር በበለጠ በወረርሽኙ ሳቢያ ዜጎቿን አጥታለች። በጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መረጃ መሠረት ከ230,000 በላይ ሰዎች ሞተዋል። ከዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ደግሞ በቫይረሱ ተይዟል። ዶ/ር ፋውቺ በቃለ ምልልሱ ላይ “ወደቀዝቃዛው ወቅት ስንገባ ነገሮች ይባባሳሉ” ብለዋል። በተያያዥም ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና ተቀናቃኛቸው ጆ ባይደን ስለ ወረርሽኙ ያላቸውን አቋም ገምግመዋል። ባይደን ለቫይረሱ ተገቢውን ትኩረት እንደሰጡት “ከሕብረተሰብ ጤና እና ከምጣኔ ሀብት አንጻርም በቁምነገር እየተከታተሉት ነው” በማለት ገልጸዋል። አሜሪካ የሕብረተሰብ ጤናን በተመለከተ ለውጥ ማምጣት እንዳለባት አሳስበዋል። በዚህ የዶ/ር ፋውቺ አስተያየት ዋይት ሀውስ ደስተኛ አልሆነም። ባይደን ምርጫውን እንዲያሸንፉ የሚገፋ ምላሽ ነው በማለትም ዶክተሩን ተችተዋል። ቃል አቀባዩ ጁድ ደሬ፤ “አስተያየቱ ተቀባይነት የለውም። ከመርህ ውጪ ነው። ዶ/ር ፋውቺ የኮሮናቫይረስ ግብረ ኃይል አባል እንደመሆናቸው ለለውጥ መገፋፋት ነበር የሚጠበቅባቸው። እሳቸው ግን ፕሬዘዳንቱን በመተቸት ለተቀናቃኛቸው ወገንተኝነት አሳይተዋል” ብሏል። የወረርሽኙ ጉዳይ በትራምፕ እና በባይደን መካከል ዋነኛ ከሆኑት መከራከሪያ ነጥቦች አንዱ ነው።ባይደን “ውሳኔያችን ሳይንስን የተመረኮዘ መሆን አለበት” ብለው፤ ምርጫውን ካሸነፉ እንቅስቃሴ ላይ ገደብ ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል። ትራምፕ በበኩላቸው፤ ባይደን እንቅስቃሴ ላይ ገደብ በመጣል አሜሪካውያንን የምጣኔ ሀብት ቀውስ ውስጥ ይከታሉ ብለዋል። “ባይደንን ከመራጥችሁ ትምህርት ቤት አይከፈትም። ተማሪዎች አይመረቁም። ሠርግ አይኖርም። ገና አይከበርም” ብለዋል። ባይደን የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ ኮሮናቫይረስን ለመከላከል የወጡ መርሆችን ተከትለው ነው። በሌላ በኩል ትራምፕ አካላዊ ርቀት ሳይጠበቅ በርካታ ዜጎች የተገኙባቸው የምረጡኝ ቅስቀሳዎች አካሂደዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54776092 |
0business
| መንግሥት ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመሸጥ ጨረታ አወጣ | የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን በጨረታ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች መሸጥ እንደሚፈልግ አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የጨረታ ጥሪ ላይ እንደተመለከተው የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በስኳር ፋብሪካዎቹ ግዢ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። በመንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙት እና ለሽያጭ የቀረቡት ስኳር ፋብሪካዎች፡ ኦሞ ኩራዝ 1፣ 2፣ 3 እና 5፣ አርጆ ደዴሳ፣ ከሰመ፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስቴር ጨረታውን ያወጣው በዘርፉ ተወዳዳሪነትን ከፍ ለማድረግ እና የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ለማሟላት ያለመ መሆኑን አስታውቋል። ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ፍጆታን ለመሸፈን በከፍታኛ የውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ አገራት እንደምታስገባ ያመላከተው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ስምንቱ ፋብሪካዎች ወደ ግል ይዞታ መሸጋገራቸው ተወዳዳሪነትን እና ምርትን ይጨምራል ብሏል። የስኳር ምርት ዘርፍ ማደግ የስኳር ሸንኮራ አገዳ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ላሉ የማኅብረሰብ ክፍሎች ሕይወት እና ገቢ መሸሻል ያስገኛሉም ተብሏል። የአገር ውስጥ የውጪ ባለሃብቶች ወደ ስኳር ዘርፉ መግባታቸው ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ስኳር ከማምረት በተጨማሪ የተለያዩ የስኳር አይነቶችን ወደ ውጪ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ ብሏል የገንዘብ ሚኒስቴር። የገንዘብ ሚኒስቴር ለጨረታ ያቀረብኳቸው የስኳር ፋብሪካዎች በቅርቡ የተገነቡ እና የሚገኙባቸው ስፍራዎችም ለሸንኮራ አገዳ ምርት ምቹ፣ ከፍተኛ የውሃ ሃብት ያለበት፣ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው መሆናቸውን ገልጿል። ይህንን ፋብሪካዎቹን ወደ ግል የማዞር ሂደት ኧርነስት ኤንድ ያንግ ያተባለውን አማካሪ ተቋም በአማካሪነት ሂደቱ ግልጽ እና የተሳካ እንዲሆን ሥራውን እንደሚያካናውን ተገልጿል። የስኳር ፋብሪካዎቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው የአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ወይም ጥምር ተቋማት ፍላጎታቸውን የሚገልጽ ሰንድ እንዲያቀርቡ የገንዘብ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። ከአራት ዓመት በፊት የውቅቱ ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢህአዴግ ግምገማ አድርጎ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል፣ ለአስርታት በመንግሥት ብቸኛ ቁጥጥር ስር የነበሩ እና በግንባታ ላይ ያሉ ማምረቻ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ባለቤትነት እንዲዘዋወሩ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትም ሆነ በግንባታ ላይ የሚገኙ የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ እንዲተላለፉ ተወስኖ ነበር። ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል የማዞር ሃሰብ እንዲሰረዝ ሲደረግ፣ ይህ የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል የማዞሩ ጥሪ ውሳኔው ከተላለፈ ከዓመታት በኋላ የቀረበ ነው። | መንግሥት ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን ለመሸጥ ጨረታ አወጣ የኢትዮጵያ መንግሥት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ ስምንት የስኳር ፋብሪካዎችን በጨረታ ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች መሸጥ እንደሚፈልግ አስታወቀ። የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የጨረታ ጥሪ ላይ እንደተመለከተው የአገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ባለሃብቶች በስኳር ፋብሪካዎቹ ግዢ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርቧል። በመንግሥት ይዞታ ስር የሚገኙት እና ለሽያጭ የቀረቡት ስኳር ፋብሪካዎች፡ ኦሞ ኩራዝ 1፣ 2፣ 3 እና 5፣ አርጆ ደዴሳ፣ ከሰመ፣ ጣና በለስ እና ተንዳሆ ናቸው። የገንዘብ ሚኒስቴር ጨረታውን ያወጣው በዘርፉ ተወዳዳሪነትን ከፍ ለማድረግ እና የአገር ውስጥ የስኳር ፍላጎትን ለማሟላት ያለመ መሆኑን አስታውቋል። ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ፍጆታን ለመሸፈን በከፍታኛ የውጭ ምንዛሪ ስኳር ከውጪ አገራት እንደምታስገባ ያመላከተው የገንዘብ ሚኒስቴር፤ ስምንቱ ፋብሪካዎች ወደ ግል ይዞታ መሸጋገራቸው ተወዳዳሪነትን እና ምርትን ይጨምራል ብሏል። የስኳር ምርት ዘርፍ ማደግ የስኳር ሸንኮራ አገዳ አብቃይ በሆኑ አካባቢዎች ላሉ የማኅብረሰብ ክፍሎች ሕይወት እና ገቢ መሸሻል ያስገኛሉም ተብሏል። የአገር ውስጥ የውጪ ባለሃብቶች ወደ ስኳር ዘርፉ መግባታቸው ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውል ስኳር ከማምረት በተጨማሪ የተለያዩ የስኳር አይነቶችን ወደ ውጪ በመላክ የውጭ ምንዛሪ ያስገኛሉ ብሏል የገንዘብ ሚኒስቴር። የገንዘብ ሚኒስቴር ለጨረታ ያቀረብኳቸው የስኳር ፋብሪካዎች በቅርቡ የተገነቡ እና የሚገኙባቸው ስፍራዎችም ለሸንኮራ አገዳ ምርት ምቹ፣ ከፍተኛ የውሃ ሃብት ያለበት፣ መሠረተ ልማት የተሟላላቸው መሆናቸውን ገልጿል። ይህንን ፋብሪካዎቹን ወደ ግል የማዞር ሂደት ኧርነስት ኤንድ ያንግ ያተባለውን አማካሪ ተቋም በአማካሪነት ሂደቱ ግልጽ እና የተሳካ እንዲሆን ሥራውን እንደሚያካናውን ተገልጿል። የስኳር ፋብሪካዎቹን ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው የአገር ውስጥ፣ ዓለም አቀፍ ወይም ጥምር ተቋማት ፍላጎታቸውን የሚገልጽ ሰንድ እንዲያቀርቡ የገንዘብ ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል። ከአራት ዓመት በፊት የውቅቱ ገዢ ፓርቲ የነበረው ኢህአዴግ ግምገማ አድርጎ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ካሳለፋቸው ውሳኔዎች መካከል፣ ለአስርታት በመንግሥት ብቸኛ ቁጥጥር ስር የነበሩ እና በግንባታ ላይ ያሉ ማምረቻ እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ባለቤትነት እንዲዘዋወሩ መወሰኑ ይታወሳል። በዚህም መሠረት በመንግሥት ይዞታ ሥር ያሉ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙትም ሆነ በግንባታ ላይ የሚገኙ የባቡር፣ የስኳር ልማት፣ የኢንዱስትሪ ፓርክ፣ የሆቴልና የተለያዩ የማኑፋክቸሪንግ ድርጅቶች ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል በአክሲዮን ሽያጭ ወደ ግል ዘርፍ እንዲተላለፉ ተወስኖ ነበር። ከእነዚህም መካከል የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም በከፊል ወደ ግል የማዞር ሃሰብ እንዲሰረዝ ሲደረግ፣ ይህ የስኳር ፋብሪካዎችን ወደ ግል የማዞሩ ጥሪ ውሳኔው ከተላለፈ ከዓመታት በኋላ የቀረበ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c6p6qr2p579o |
3politics
| በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት የተከሰሰው ኬንያዊ ጠበቃ ሞቶ ተገኘ | በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በምስክሮች ጣልቃ ገብነት ክስ ቀርቦበት የነበረው ኬንያዊው ጠበቃ ፖል ጊቼሩ ሞቶ ተገኘ። ፖሊስ እንዳስታወቀው ጠበቃው ፖል ጊቼሩ ሰኞ ምሽት በመዲናዋ ናይሮቢ በሚገኘው ቤቱ ሞቶ መገኘቱን አረጋግጧል። ጠበቃው በአውሮፓውያኑ 2007 ምርጫ ማግስት ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ ለምስክሮች ጉቦ በመስጠት ነው ክስ የቀረበበት። ምስክሮቹ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአይሲሲ ተከሰው በነበረበት ወቅት ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች እንደነበሩም ተገልጿል። በዚህ ሁከት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።ጠበቃው የቀረበበትን ክስ አስተባብሏል። ጠበቃው የአይሲሲ የእስር ማዘዣ ካወጣበት ከአምስት ዓመት በኋላም በአውሮፓውያኑ 2020 ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል። አቃብያነ ህግ እንደሚሉት ጠበቃው ፈጸመው በተባለው ተግባር ምክንያት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በፍርድ ቤቱ የቀረቡባባቸውን ክሶች ውሃ እንዳይቋጥር አድርጎታል ብለዋል። ዊሊያም ሩቶ በኬንያ ምርጫ ማግስት በተቀሰቀው ሁከት በተፈጸሙ ግድያዎች፣ ስወራ እና ማፈናቀል በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ተከሰው ነበር። ዊሊያም ሩቶ እነዚህን ወንጀሎች አልፈጸምኩም በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል። አይሲሲ በዊሊያም ሩቶ ላይ በቂ ማስረጃ ባለማግኘቱ ክሱን አቋርጧል። በጠበቃው አሟሟት ላይ አንዳንድ ዝርዝር መረጃዎች እየወጡ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአሟሟቱ ላይ ፖሊስ ፈጣን እና የተረጋጋጠ ምርመራ እንዲያደርግ የኬንያ የመብት ተቋማት ጠይቀዋል። | በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት የተከሰሰው ኬንያዊ ጠበቃ ሞቶ ተገኘ በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት (አይሲሲ) በምስክሮች ጣልቃ ገብነት ክስ ቀርቦበት የነበረው ኬንያዊው ጠበቃ ፖል ጊቼሩ ሞቶ ተገኘ። ፖሊስ እንዳስታወቀው ጠበቃው ፖል ጊቼሩ ሰኞ ምሽት በመዲናዋ ናይሮቢ በሚገኘው ቤቱ ሞቶ መገኘቱን አረጋግጧል። ጠበቃው በአውሮፓውያኑ 2007 ምርጫ ማግስት ከተፈጠረው ሁከት ጋር በተያያዘ ለምስክሮች ጉቦ በመስጠት ነው ክስ የቀረበበት። ምስክሮቹ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በአይሲሲ ተከሰው በነበረበት ወቅት ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች ምስክርነት የሚሰጡ ግለሰቦች እንደነበሩም ተገልጿል። በዚህ ሁከት ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።ጠበቃው የቀረበበትን ክስ አስተባብሏል። ጠበቃው የአይሲሲ የእስር ማዘዣ ካወጣበት ከአምስት ዓመት በኋላም በአውሮፓውያኑ 2020 ራሱን አሳልፎ ሰጥቷል። አቃብያነ ህግ እንደሚሉት ጠበቃው ፈጸመው በተባለው ተግባር ምክንያት ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በፍርድ ቤቱ የቀረቡባባቸውን ክሶች ውሃ እንዳይቋጥር አድርጎታል ብለዋል። ዊሊያም ሩቶ በኬንያ ምርጫ ማግስት በተቀሰቀው ሁከት በተፈጸሙ ግድያዎች፣ ስወራ እና ማፈናቀል በአለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት ተከሰው ነበር። ዊሊያም ሩቶ እነዚህን ወንጀሎች አልፈጸምኩም በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል። አይሲሲ በዊሊያም ሩቶ ላይ በቂ ማስረጃ ባለማግኘቱ ክሱን አቋርጧል። በጠበቃው አሟሟት ላይ አንዳንድ ዝርዝር መረጃዎች እየወጡ ባለበት በአሁኑ ወቅት በአሟሟቱ ላይ ፖሊስ ፈጣን እና የተረጋጋጠ ምርመራ እንዲያደርግ የኬንያ የመብት ተቋማት ጠይቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c97e8q53xewo |
0business
| የሱዊዝ መተላለፊያ ለመርከቦች እንቅስቃሴ ክፍት ሆነ | ለሳምንት ያህል የስዊዝ ቦይን ዘግታ የነበረችው መርከብ ከቦታው ላይ መነሳቷንና መስመሩም ለእንቅስቃሴ ክፍት መደረጉን የግብጽ ባለሥልጣናት ተናገሩ። ከማክሰኞ ጀምሮ በአንዲት መርከብ የተዘጋው የሱዊዝ መተላለፊ መስመር ለመክፈት የተደረገው ጥረት ውጤት አስገኝቶ መርከቧ ከመተላለፊያው ላይ እንድትንቀሳቀስ ተደረጓል። ባለስልጣናት ለቀናት የተዘጋው የሱዊዝ ቦይ ቅዳሜ ወይም እሁድ ይከፈታል በማለት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት መስመሩን ለማስከፈት ችለዋል። በዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎልን ያስከተለው የመተላለፊያው መዘጋት ለተጨማሪ በርካታ ቀናት ሊቆይ ይችላል ተብሎ ቢሰጋም በተደረገው ጥረት ግዙፏ የጭነት መርከብ እንድትንቀሳቀስ ተደርጎ መተላለፊያው ሊከፈት ችሏል። ከማክሰኞ ጀምሮ የባሕር መተላለፊያ መስመሩን በአግድሞሽ ዘግታ የቆመችውን ግዙፏን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ጥረት ሲደረግ ነበር። በዚህም ሳቢያ በመተላለፊያው የሰሜንና የደቡብ መግቢያ መስመር ላይ የሱዊዝ ቦይ መከፈትን በሚጠብቁ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው መርከቦች መጨናነቅ መፈጠሩ ተገልጿል። ጆ ሬይኖልድስ የታዋቂው የመርከብ እቃ አመላላሽ ድርጅት ሚርስክ ዋና ኢንጂነር ናቸው። ለቢቢሲ ሲገልጹ ''በቦዩ ደቡባዊ መግቢያ በኩል መንገዱ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ነው። ይህ ደግሞ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ፈጥሯል'' ብለዋል። ''በመላው ዓለም የተዘረጋው የመርከቦች የጉዞ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል'' ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ማክሰኞ ጠዋት አካባቢ 400 ሜትር ርዝማኔና 59 ሜትር ስፋት ያለው መርከብ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አሁንም ድረስ መንገድ እንደዘጋ ይገኛል። የሱዊዝ ቦይ በመባል የሚታወቀው የግብፅ መተላለፊያ ሜድትራኒያን እና ቀይ ባሕርን በማገናኘት በእስያና አውሮፓ መካከል አጭሩ የሚባለውን የውቅያኖስ መንገድ ይፈጥራል። በታይዋኑ ኤቨርግሪን ማሪን ሥር ያለው ኤቨር ጊቭን መርከብ በዓለም ትልቁ ኮንቴነር ጫኝ ሲሆን፤ 200,000 ቶን የሚመዝን እንዲሁም 20,000 ኮንቴነር ማጓጓዝ የሚችል ነው። ኤቨር ግሪን የተሰኘው ግዙፍ መርከብ ከቻይና ተነስቶ ወደ ኔዘርላንድስ እያቀና ነበር። የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት መርከቡ ባጋጠመው ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ነው መሀል ላይ ቆሞ የቀረው። በፈረንጆቹ 2018 የተሠራው ይህ የፖናማ መርከብ ኤቨርግሪን ማሪን በተሰኘው የትራንስፖርት ኩባንያ ባለቤትነት ነው የሚንቀሳቀሰው። በእንደዚህ አይነት ችግሮች ብዙ ልምድ አላቸው የተባሉ ድርጅቶች የሱዊዝ ቦይ ትራፊክ መጨናነቅን ለመፍታት ቢጥሩም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም። የግብፅ ፕሬዝዳንት አማካሪ ችግሩ በቀናት ውስጥ እንደሚፈታ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ባለሙያዎቹ ትልቋን መርከብ ለማንቀሳቀስና ወደቀደመው እንቅስቃሴ ለመመለስ ሳምንታት ሊፈጅ እንደሚችል ሲሉ ቆይተዋል። መተላለፊያው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ምርቶች የሚተላለፉበት ሲሆን፤ የጦፈ ንግድ የሚካሄድበት መስመር ነው። ከመላው ዓለም የባሕር ንግድም 12 በመቶው የሚያልፈውም በዚሁ የግብፅ የባሕር ላይ ማቋረጫ መስመር በኩል ነው። በሱዊዝ ቦይ ምትክ እንደ አማራጭ የቀረበው የኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ መንገድ ደግሞ ከሱዊዝ ቦይ ጋር ሲነጻጸር ተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ይፈጃል። ይህ ደግሞ ለበርካታ የመርከብ ድርጅቶች አዋጪ አይደለም። የግብፅ ሱዊዝ ቦይ በመዘጋቱ ምክንያት እስካሁን በየቀኑ 9.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መተላለፍ አልቻሉም። ሎይድስ ሊስት የተባለው የመርከብ ጉዞ ድርጅት እንደሚለው፤ በቀን ውስጥ ከምዕራብ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩ 5.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መጓጓዝ አልቻሉም። ከምሥራቅ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩና የተስተጓጎሉ ምርቶች ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው። ሎይድስ ሊስት ባወጣው አሃዝ መሠረት፤ በአሁኑ ጊዜ 160 መርከቦች በሱዊዝ ቦይ በኩል ለማለፍ እየጠበቁ ነው። ከእነዚህ መካከል 41 የሚሆኑት የተለያዩ ምርቶች ሲይዙ 24 ደግሞ ነዳጅ ጫኝ ናቸው። ቢአይኤምሲኦ የተባለው ዓለም አቀፍ የመርከበኞች ማኅበር እንደሚለው መተላለፊያው ተዘግቶ ከቆየ የምርት አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። በተጨማሪም በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ የተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት "ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ" ላይ መሆናቸውን ገልጿል። | የሱዊዝ መተላለፊያ ለመርከቦች እንቅስቃሴ ክፍት ሆነ ለሳምንት ያህል የስዊዝ ቦይን ዘግታ የነበረችው መርከብ ከቦታው ላይ መነሳቷንና መስመሩም ለእንቅስቃሴ ክፍት መደረጉን የግብጽ ባለሥልጣናት ተናገሩ። ከማክሰኞ ጀምሮ በአንዲት መርከብ የተዘጋው የሱዊዝ መተላለፊ መስመር ለመክፈት የተደረገው ጥረት ውጤት አስገኝቶ መርከቧ ከመተላለፊያው ላይ እንድትንቀሳቀስ ተደረጓል። ባለስልጣናት ለቀናት የተዘጋው የሱዊዝ ቦይ ቅዳሜ ወይም እሁድ ይከፈታል በማለት ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ ቆይቶ ዛሬ ጠዋት መስመሩን ለማስከፈት ችለዋል። በዓለም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ መስተጓጎልን ያስከተለው የመተላለፊያው መዘጋት ለተጨማሪ በርካታ ቀናት ሊቆይ ይችላል ተብሎ ቢሰጋም በተደረገው ጥረት ግዙፏ የጭነት መርከብ እንድትንቀሳቀስ ተደርጎ መተላለፊያው ሊከፈት ችሏል። ከማክሰኞ ጀምሮ የባሕር መተላለፊያ መስመሩን በአግድሞሽ ዘግታ የቆመችውን ግዙፏን የጭነት መርከብ ለማንቀሳቀስ ጥረት ሲደረግ ነበር። በዚህም ሳቢያ በመተላለፊያው የሰሜንና የደቡብ መግቢያ መስመር ላይ የሱዊዝ ቦይ መከፈትን በሚጠብቁ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው መርከቦች መጨናነቅ መፈጠሩ ተገልጿል። ጆ ሬይኖልድስ የታዋቂው የመርከብ እቃ አመላላሽ ድርጅት ሚርስክ ዋና ኢንጂነር ናቸው። ለቢቢሲ ሲገልጹ ''በቦዩ ደቡባዊ መግቢያ በኩል መንገዱ በመዘጋቱ በርካታ መርከቦች ለማለፍ እየተጠባበቁ ነው። ይህ ደግሞ ከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ፈጥሯል'' ብለዋል። ''በመላው ዓለም የተዘረጋው የመርከቦች የጉዞ ሥርዓት ላይ ከፍተኛ ጫና ያሳድራል'' ሲሉም አስጠንቅቀዋል። ማክሰኞ ጠዋት አካባቢ 400 ሜትር ርዝማኔና 59 ሜትር ስፋት ያለው መርከብ ባጋጠመው የቴክኒክ ችግር ምክንያት አሁንም ድረስ መንገድ እንደዘጋ ይገኛል። የሱዊዝ ቦይ በመባል የሚታወቀው የግብፅ መተላለፊያ ሜድትራኒያን እና ቀይ ባሕርን በማገናኘት በእስያና አውሮፓ መካከል አጭሩ የሚባለውን የውቅያኖስ መንገድ ይፈጥራል። በታይዋኑ ኤቨርግሪን ማሪን ሥር ያለው ኤቨር ጊቭን መርከብ በዓለም ትልቁ ኮንቴነር ጫኝ ሲሆን፤ 200,000 ቶን የሚመዝን እንዲሁም 20,000 ኮንቴነር ማጓጓዝ የሚችል ነው። ኤቨር ግሪን የተሰኘው ግዙፍ መርከብ ከቻይና ተነስቶ ወደ ኔዘርላንድስ እያቀና ነበር። የግብፅ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት መርከቡ ባጋጠመው ቴክኒካዊ ችግር ምክንያት ነው መሀል ላይ ቆሞ የቀረው። በፈረንጆቹ 2018 የተሠራው ይህ የፖናማ መርከብ ኤቨርግሪን ማሪን በተሰኘው የትራንስፖርት ኩባንያ ባለቤትነት ነው የሚንቀሳቀሰው። በእንደዚህ አይነት ችግሮች ብዙ ልምድ አላቸው የተባሉ ድርጅቶች የሱዊዝ ቦይ ትራፊክ መጨናነቅን ለመፍታት ቢጥሩም እስካሁን መፍትሄ አልተገኘም። የግብፅ ፕሬዝዳንት አማካሪ ችግሩ በቀናት ውስጥ እንደሚፈታ ገልጸው ነበር። ነገር ግን ባለሙያዎቹ ትልቋን መርከብ ለማንቀሳቀስና ወደቀደመው እንቅስቃሴ ለመመለስ ሳምንታት ሊፈጅ እንደሚችል ሲሉ ቆይተዋል። መተላለፊያው በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ምርቶች የሚተላለፉበት ሲሆን፤ የጦፈ ንግድ የሚካሄድበት መስመር ነው። ከመላው ዓለም የባሕር ንግድም 12 በመቶው የሚያልፈውም በዚሁ የግብፅ የባሕር ላይ ማቋረጫ መስመር በኩል ነው። በሱዊዝ ቦይ ምትክ እንደ አማራጭ የቀረበው የኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ መንገድ ደግሞ ከሱዊዝ ቦይ ጋር ሲነጻጸር ተጨማሪ ሁለት ሳምንታት ይፈጃል። ይህ ደግሞ ለበርካታ የመርከብ ድርጅቶች አዋጪ አይደለም። የግብፅ ሱዊዝ ቦይ በመዘጋቱ ምክንያት እስካሁን በየቀኑ 9.6 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መተላለፍ አልቻሉም። ሎይድስ ሊስት የተባለው የመርከብ ጉዞ ድርጅት እንደሚለው፤ በቀን ውስጥ ከምዕራብ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩ 5.1 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች መጓጓዝ አልቻሉም። ከምሥራቅ አቅጣጫ ይመጡ የነበሩና የተስተጓጎሉ ምርቶች ደግሞ 4.5 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ናቸው። ሎይድስ ሊስት ባወጣው አሃዝ መሠረት፤ በአሁኑ ጊዜ 160 መርከቦች በሱዊዝ ቦይ በኩል ለማለፍ እየጠበቁ ነው። ከእነዚህ መካከል 41 የሚሆኑት የተለያዩ ምርቶች ሲይዙ 24 ደግሞ ነዳጅ ጫኝ ናቸው። ቢአይኤምሲኦ የተባለው ዓለም አቀፍ የመርከበኞች ማኅበር እንደሚለው መተላለፊያው ተዘግቶ ከቆየ የምርት አቅርቦት ላይ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም። በተጨማሪም በሱዊዝ የመተላለፊያ መስመር ላይ ቆማ የባሕር ላይ ጉዞን ባስተጓጎለችው መርከብ የተነሳ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ጭማሪ ታይቷል። በመተላለፊያ መስመሩ መዘጋት ሰበብ የድፍድፍ ነዳጅ አቅርቦት ሊስተጓጎል ይችላል በሚል ስጋት ነው ረቡዕ ዕለት የዓለም የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ የታየበት። በሰሜናዊ ምሥራቅ አፍሪካ የሚገኘውን ወሳኝ የባሕር ላይ መተላለፊያን ዘግታ የምትገኘው የጭነት መርከብ ባለቤት የሆነው ጃፓናዊ በመርከቧ ምክንያት በዓለም የንግድ ልውውጥ ላይ ለተፈጠረው መስተጓጎል ይቅርታ መጠየቁ ተነግሯል። በከባድ ንፋስ ምክንያት መስመሯን ስታ መተላለፊያውን የዘጋችውን መርከብ ለማንቀሳቀስ በጣም አስቸጋሪ እንደሆነ የገለጸው የመርከቧ ባለቤት "ነገር ግን የተቻላቸውን ጥረት በማድረግ" ላይ መሆናቸውን ገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56547974 |
3politics
| የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ሳርኮዚ ለምርጫ ቅስቀሳ ባወጡት ወጪ አንድ ዓመት ተፈረደባቸው | የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ዳግም ለመመረጥ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ ለምርጫ ቅስቀሳ ገንዘብ ወጪ አድርገዋል ተብለው የአንድ ዓመት እስር ተፈረደባቸው። ሳርኮዚ እአአ 2012 ላይ ፈረንሳይን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዳግም ቢወዳደሩም በምርጫው ሳይሳካላቸው መቅረቱ ይታወሳል። የ66 ዓመቱ የቀድሞው ፕሬዝደንት ለምርጫ ቅሰቀሳ ከሚፈቀደው በላይ ወጪ አድርገዋል ሲል ፓሪስ የሚገኝ ፍርድ ቤት ዛሬ ብይን ሰጥቷል። ሳርኮዚ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ ወጪ አድርገዋል ብሏል ፍርድ ቤቱ። ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስር ቢፈረድባቸውም ፍርዳቸውን በእስር ቤት ሆነ መጨረስ አይጠበቅባቸውም። የሳርኮዚን እንቅስቃሴ መከታተያ በቀድሞው ፕሬዝደንት እግር ላይ ከታሰረ በኋላ ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስራቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ማሳለፍ ይችላሉ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ምንም ጥፋት የለብኝም የሚሉ ሲሆን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ይላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሳርኮዚ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ሲባሉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ሳርኮዚ ኅዳር ወር ላይ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ነበር። ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስር በተፈረደባቸው ክስ ላይ ፓርቲያቸው ለምርጫ ቅስቀሳ ከሚፈቀው 22.5 ሚሊዮን ዩሮ እጥፍ ለምርጫ ቅስቀሳ ወጪ አድርጓል ተብሏል። ፓርቲያቸው ለምርጫ ቅስቀሳ ያወጣውን ወጪ ለመደበቅ የሕዝብ ግንኙነት ተቋም ቀጥሮ ለምርጫ ቅስቀሳ የወጣውን ገንዘብ ለድርጅቱ ክፍያ የተፈጸም አስመስሏል። የፓሪሱ ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው ብይን ላይ ምንም እንኳ የቀድሞ ፕሬዝደንት በፓርቲው የተፈጸመውን ማጭበርበር በዝርዝር ሊያውቁ ባይችሉም፤ ለምርጫ ቅስቀሳ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ ወጪ ስለመሆኑ እያወቁ ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም ብሏል። ሳርኮዚ በቀድሞ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦላንዴ እስከተተኩበት ጊዜ ድረስ ከእአአ 2007 እስከ 2012 ድረስ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት በመሆን ለአንድ የስልጣን ዘመን አገልግለዋል። | የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ሳርኮዚ ለምርጫ ቅስቀሳ ባወጡት ወጪ አንድ ዓመት ተፈረደባቸው የቀድሞ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት ኒኮላስ ሳርኮዚ ዳግም ለመመረጥ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ ለምርጫ ቅስቀሳ ገንዘብ ወጪ አድርገዋል ተብለው የአንድ ዓመት እስር ተፈረደባቸው። ሳርኮዚ እአአ 2012 ላይ ፈረንሳይን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዳግም ቢወዳደሩም በምርጫው ሳይሳካላቸው መቅረቱ ይታወሳል። የ66 ዓመቱ የቀድሞው ፕሬዝደንት ለምርጫ ቅሰቀሳ ከሚፈቀደው በላይ ወጪ አድርገዋል ሲል ፓሪስ የሚገኝ ፍርድ ቤት ዛሬ ብይን ሰጥቷል። ሳርኮዚ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ ወጪ አድርገዋል ብሏል ፍርድ ቤቱ። ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስር ቢፈረድባቸውም ፍርዳቸውን በእስር ቤት ሆነ መጨረስ አይጠበቅባቸውም። የሳርኮዚን እንቅስቃሴ መከታተያ በቀድሞው ፕሬዝደንት እግር ላይ ከታሰረ በኋላ ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስራቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ማሳለፍ ይችላሉ ሲል ፍርድ ቤቱ ወስኗል። የቀድሞ ፕሬዝደንት ምንም ጥፋት የለብኝም የሚሉ ሲሆን የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ይላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሳርኮዚ በተከሰሱበት ወንጀል ጥፋተኛ ሲባሉ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። ሳርኮዚ ኅዳር ወር ላይ በሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ተብለው ነበር። ሳርኮዚ የአንድ ዓመት እስር በተፈረደባቸው ክስ ላይ ፓርቲያቸው ለምርጫ ቅስቀሳ ከሚፈቀው 22.5 ሚሊዮን ዩሮ እጥፍ ለምርጫ ቅስቀሳ ወጪ አድርጓል ተብሏል። ፓርቲያቸው ለምርጫ ቅስቀሳ ያወጣውን ወጪ ለመደበቅ የሕዝብ ግንኙነት ተቋም ቀጥሮ ለምርጫ ቅስቀሳ የወጣውን ገንዘብ ለድርጅቱ ክፍያ የተፈጸም አስመስሏል። የፓሪሱ ፍርድ ቤት ዛሬ በሰጠው ብይን ላይ ምንም እንኳ የቀድሞ ፕሬዝደንት በፓርቲው የተፈጸመውን ማጭበርበር በዝርዝር ሊያውቁ ባይችሉም፤ ለምርጫ ቅስቀሳ በሕግ ከሚፈቀደው በላይ ወጪ ስለመሆኑ እያወቁ ምንም አይነት እርምጃ አልወሰዱም ብሏል። ሳርኮዚ በቀድሞ ፕሬዝደንት ፍራንሷ ኦላንዴ እስከተተኩበት ጊዜ ድረስ ከእአአ 2007 እስከ 2012 ድረስ የፈረንሳይ ፕሬዝደንት በመሆን ለአንድ የስልጣን ዘመን አገልግለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-58751353 |
5sports
| ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሴቶች እና ወንዶች የተለያየ ሰዓትን መምረጥ እንዳለባቸው ጥናት አመለከተ | አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለጤና ጠቃሚ እንደሆነ አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን ከምንሰራቸው አካላዊ እንቅስቃሴዎች ተገቢውን ጥቅም እንድናገኝ የምንሰራበትን ሰዓት ከግምት ውስጥ ማስገባት ወሳኝ ነው። አንድ በቅርቡ የተካሄደ ጥናት፤ ወንዶችና ሴቶች አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ሰዓት የበለጠ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል አመላክቷል። እንደ ጥናቱ ከሆነ ሴቶች ጠዋት ላይ አካላዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘውን የስብ ክምችት በፍጥነት ማጥፋት የሚችሉ ሲሆን፣ ወንዶችን ደግሞ የበለጠ ውጤታማ የሚያደርገው ምሽት ላይ ስፖርት መስራታቸው ነው። በሁለቱም ጾታ ውስጥ የሆርሞን መለያየት፣ የእንቅልፍ ሰዓት እና ተፈጥሯዊ አወቃቀር በጠቅላላው ልዩነት የሚያመጣ መሆኑ በጥናቱ ላይ ተገልጿል። ዕድሜያቸው ከ25 እስከ 55 የሆኑና በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ 30 ወንዶችና 26 ሴቶችን ያሳተፈው ይህ ጥናት፤ ለ12 ሳምንታት ነው የተካሄደው። በእነዚህ ሳምንታት የጥናቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ አይነት የማሳሳብ፣ የፍጥነት፣ የጥንካሬ እንዲሁም የዝላይ አቅማቸውን ከፍ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ነበር። የሴቶቹ ቡድን ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል ጀምሮ እነዚህን አካላዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን፤ የወንዶቹ ቡድን ደግሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት እንቅስቃሴዎቹን እንዲሰሩ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ምግቦችን እንዲመገቡ ተደርጓል። ተሳታፊዎቹ በዚህ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ውስጥ ለ12 ሳምንታት የሰነበቱ ሲሆን ተመራማሪዎቹ ደግሞ የደም ዝውውራቸውን፣ በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የስብ መጠን፣ አካላዊ ብቃት እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ሲመዘግቡና ሲያወዳድሩ ቆይተዋል። መጀመሪያ ላይ ተመራማሪዎቹ ይፋ ያደረጉት ውጤት ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች በተለያየ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴያቸውን ቢያደርጉም ሁሉም በጣም ጥሩ የሚባል አካላዊ ለውጥ አሳይተዋል። "አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሰዓት መምረጥ ላያስፈልግ ይችላል። ነገር ግን ከሴቶችና ወንዶች አንጻር ስናየው ግን አካላዊ እንቅስቃሴ የምንሰራበት ሰዓት በምናገኘው ጥቅም ፍጥነትና ውጤታማነት ላይ ልዩነት አለው’’ ይላሉ የጥናቱ መሪ የሆኑት ዶ/ር ፖል አርሴሮ። በጥናቱ መሠረት በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የስብ መጠን መቀነስና የደም ግፊታቸውን ለማውረድ የሚፈልጉ ሴቶች ጠዋት ላይ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ የበለጠ ጥቅም እንደሚያገኙ ዶ/ር ፖል ያስረዳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አካላዊ ጡንቻቸውን ማሳደግና ጥንካሬያቸውን መጨመር የሚፈልጉ ሴቶች ወደ ማታ አካባቢ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ እንደሚመረጥ ጥናቱ ጠቁሟል። ወንዶች ደግሞ በጥናቱ መሰረት ጠዋትም ሆነ ማታ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ አጠቃላይ አካላዊ ብቃታቸውን መጨመር የሚችሉ ሲሆን፤ የልባቸውን ጤንነት መጠበቅና ማሻሻል እንዲሁም የአእምሮ ጤና ማሻሻል የሚፈልጉ ከሆነ ግን ማታ አካባቢ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ ጥሩ ነው። ወንዶች እና ሴቶች በተለያዩ ሰዓታት አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረጋቸው ለምን ልዩነት እንደሚያመጣ ተመራማሪዎቹ እስካሁን አልደረሱበትም። ነገር ግን ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልጉ ጠቁመዋል። | ለስፖርታዊ እንቅስቃሴ ሴቶች እና ወንዶች የተለያየ ሰዓትን መምረጥ እንዳለባቸው ጥናት አመለከተ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ለጤና ጠቃሚ እንደሆነ አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን ከምንሰራቸው አካላዊ እንቅስቃሴዎች ተገቢውን ጥቅም እንድናገኝ የምንሰራበትን ሰዓት ከግምት ውስጥ ማስገባት ወሳኝ ነው። አንድ በቅርቡ የተካሄደ ጥናት፤ ወንዶችና ሴቶች አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉበት ሰዓት የበለጠ ውጤታማ ሊያደርጋቸው እንደሚችል አመላክቷል። እንደ ጥናቱ ከሆነ ሴቶች ጠዋት ላይ አካላዊ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ በሰውነታቸው ውስጥ የሚገኘውን የስብ ክምችት በፍጥነት ማጥፋት የሚችሉ ሲሆን፣ ወንዶችን ደግሞ የበለጠ ውጤታማ የሚያደርገው ምሽት ላይ ስፖርት መስራታቸው ነው። በሁለቱም ጾታ ውስጥ የሆርሞን መለያየት፣ የእንቅልፍ ሰዓት እና ተፈጥሯዊ አወቃቀር በጠቅላላው ልዩነት የሚያመጣ መሆኑ በጥናቱ ላይ ተገልጿል። ዕድሜያቸው ከ25 እስከ 55 የሆኑና በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ 30 ወንዶችና 26 ሴቶችን ያሳተፈው ይህ ጥናት፤ ለ12 ሳምንታት ነው የተካሄደው። በእነዚህ ሳምንታት የጥናቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ አይነት የማሳሳብ፣ የፍጥነት፣ የጥንካሬ እንዲሁም የዝላይ አቅማቸውን ከፍ የሚያደርጉ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርጉ ነበር። የሴቶቹ ቡድን ከጠዋቱ 2 ሰዓት ተኩል ጀምሮ እነዚህን አካላዊ እንቅስቃሴዎች እንዲሰሩ የተደረገ ሲሆን፤ የወንዶቹ ቡድን ደግሞ ከምሽቱ 12 ሰዓት እስከ ሁለት ሰዓት እንቅስቃሴዎቹን እንዲሰሩ ተደርጓል። ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ምግቦችን እንዲመገቡ ተደርጓል። ተሳታፊዎቹ በዚህ ተመሳሳይ እንቅስቃሴ ውስጥ ለ12 ሳምንታት የሰነበቱ ሲሆን ተመራማሪዎቹ ደግሞ የደም ዝውውራቸውን፣ በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የስብ መጠን፣ አካላዊ ብቃት እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን ሲመዘግቡና ሲያወዳድሩ ቆይተዋል። መጀመሪያ ላይ ተመራማሪዎቹ ይፋ ያደረጉት ውጤት ሁሉም የጥናቱ ተሳታፊዎች በተለያየ ሰዓት አካላዊ እንቅስቃሴያቸውን ቢያደርጉም ሁሉም በጣም ጥሩ የሚባል አካላዊ ለውጥ አሳይተዋል። "አካላዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሰዓት መምረጥ ላያስፈልግ ይችላል። ነገር ግን ከሴቶችና ወንዶች አንጻር ስናየው ግን አካላዊ እንቅስቃሴ የምንሰራበት ሰዓት በምናገኘው ጥቅም ፍጥነትና ውጤታማነት ላይ ልዩነት አለው’’ ይላሉ የጥናቱ መሪ የሆኑት ዶ/ር ፖል አርሴሮ። በጥናቱ መሠረት በሰውነታቸው ውስጥ ያለውን የስብ መጠን መቀነስና የደም ግፊታቸውን ለማውረድ የሚፈልጉ ሴቶች ጠዋት ላይ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ የበለጠ ጥቅም እንደሚያገኙ ዶ/ር ፖል ያስረዳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ አካላዊ ጡንቻቸውን ማሳደግና ጥንካሬያቸውን መጨመር የሚፈልጉ ሴቶች ወደ ማታ አካባቢ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ እንደሚመረጥ ጥናቱ ጠቁሟል። ወንዶች ደግሞ በጥናቱ መሰረት ጠዋትም ሆነ ማታ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ አጠቃላይ አካላዊ ብቃታቸውን መጨመር የሚችሉ ሲሆን፤ የልባቸውን ጤንነት መጠበቅና ማሻሻል እንዲሁም የአእምሮ ጤና ማሻሻል የሚፈልጉ ከሆነ ግን ማታ አካባቢ አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርጉ ጥሩ ነው። ወንዶች እና ሴቶች በተለያዩ ሰዓታት አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረጋቸው ለምን ልዩነት እንደሚያመጣ ተመራማሪዎቹ እስካሁን አልደረሱበትም። ነገር ግን ተጨማሪ ጥናቶች እንደሚያስፈልጉ ጠቁመዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cy6ne5zdx93o |
3politics
| ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በዕጩነት የተለዩ የ42 ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ ሆነ | ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከሕዝብ ከተጠቆሙ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ግለሰቦች መካከል በዕጩነት የተለዩ የ42ቱን የስም ዝርዝር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋ አደረገ። በቀጣይ ሂደትም ከ42ቱ መካከል ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት የሚሰየሙትን ለመለየት በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ለማቋቋም ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከል ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ በተቀመጡት መስፈርቶች አማካኝነት 42ቱን መለየታቸውን ከሳምንት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታውቀው ነበር። ከተጠቆሙት 632 ዕጩዎች ውስጥ የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የትምህርት ሁኔታና የሥራ ልምድ ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር ከተደረገበት በኋላ ለሕዝብ ቀርበው አስተያየት እንደሚሰበሰብ ተገልጾ ነበር። በዚህም መሠረት አብዛኞቹ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በማስተማርና በምርምር ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ምሁራን የተካተቱበት የ42 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን ሕዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸውም ተጠይቋል። በቀረበው ጥሪ መሠረት ከተለያዩ ወገኖች ከተጠቆሙት ዕጩዎች መካከል የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የሚከተሉት ናቸው፡ 1. ሎሬት ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ 2. ፕሮፌሰር አፈወርቅ በቀለ ስመኝ 3. ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ 4. ፕሮፌሰር ባዬ ይማም 5. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ 6. ፕሮፌሰር ያእቆብ አርሳኖ 7. ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሃኑ ዓለሙ 8. ፕሮፌሰር ህዝቅያስ አሰፋ 9. ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ 10. ፕሮፌሰር ዶክተር ዳንኤል ቅጣው 11. ፕሮፌሰር ዘካሪያስ ቀነአ ተስገራ 12. ፕሮፌሰር ክፍሌ ወ/ሚካኤል ሐጀቶ 13. ዶክተር በድሉ ዋቅጅታ 14. ዶክተር ሰሚር የሱፍ 15. ዶክተር አብዲሳ ዘርዓይ በማኖ 16. ዶክተር ሀብታሙ ወንድሙ 17. ዶክተር ታከለ ሰቦቃ 18. ዶክተር ዮናስ አዳዬ 19. ዶክተር ወዳጆ ወ/ጊዮርጊስ 20. ዶክተር ሙሉጌታ አረጋዊ 21. ዶክተር ነጋልኝ ብርሃኑ ባዬ 22. ዶክተር አበራ ዴሬሳ 23. ዶክተር አይሮሪት መ/ድያሲን 24. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌጡ መንገሻ 25. ዶክተር ዳዊት ዮሐንስ 26. ዶክተር ተካለ ሰቦቃ 27. ኢንጂኒየር ጌታሁን ሁሴን ሽኩር 28. አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካኤል 29. አምባሳደር ምዑዝ ገብረ ሕይወት ወልደ ሥላሴ 30. አምባሳደር ማህሙድ ድሪር 31. አቶ ዘገየ አስፋው አብዲ 32. ወ/ሮ ዘነብወርቅ ታደሰ ማርቆስ 33. አቶ ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ እሸቴ 34. አቶ መላኩ ወልደማሪያም 35. አቶ አንዳርጋቸው አሰግድ 36. አቶ ገመቹ ዱቢሶ ጉደና 37. አቶ ሳሙኤል ጣሰው ተፈራ 38. አቶ አህመድ ሁሴን መሐመድ 39. ወ/ሮ ሂሮት ገ/ሥላሴ ኦዳ 40. አቶ ንጉሡ አክሊሉ 41. አቶ ተስፋዬ ሐቢሶ 42. አቶ አባተ ኪሾ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተጠቆሙትን 42ቱን ግለሰቦች ዝርዝር ከአጭር የትምህርትና የሥራ መግለጫ ጋር በድረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን ሕዝቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው ጥያቄ አቅርቧል። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሹመት እንደሚቀርቡ ተገልጿል። | ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በዕጩነት የተለዩ የ42 ግለሰቦች ዝርዝር ይፋ ሆነ ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከሕዝብ ከተጠቆሙ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ግለሰቦች መካከል በዕጩነት የተለዩ የ42ቱን የስም ዝርዝር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይፋ አደረገ። በቀጣይ ሂደትም ከ42ቱ መካከል ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን በኮሚሽነርነት የሚሰየሙትን ለመለየት በቀረቡት ዕጩዎች ላይ ሕዝብ አስተያየት እንዲሰጥ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል። ኢትዮጵያ ውስጥ ባሉ መሠረታዊ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር በማድረግና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ሂደትን የሚመራና የሚያስተባብር አካል በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አማካይነት ለማቋቋም ጥቆማ መካሄዱ ይታወሳል። ለሕዝብ በቀረበ ጥሪ መሠረት 632 ዕጩዎች በተለያዩ ወገኖች ተጠቁመው ከእነዚህ መካከል ኮሚሽኑን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ በተቀመጡት መስፈርቶች አማካኝነት 42ቱን መለየታቸውን ከሳምንት በፊት የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ አስታውቀው ነበር። ከተጠቆሙት 632 ዕጩዎች ውስጥ የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የትምህርት ሁኔታና የሥራ ልምድ ላይ ከአማካሪዎች ጋር ምክክር ከተደረገበት በኋላ ለሕዝብ ቀርበው አስተያየት እንደሚሰበሰብ ተገልጾ ነበር። በዚህም መሠረት አብዛኞቹ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በማስተማርና በምርምር ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ምሁራን የተካተቱበት የ42 ሰዎች ስም ዝርዝር ይፋ የተደረገ ሲሆን ሕዝቡ አስተያየት እንዲሰጥባቸውም ተጠይቋል። በቀረበው ጥሪ መሠረት ከተለያዩ ወገኖች ከተጠቆሙት ዕጩዎች መካከል የተለዩት 42ቱ ዕጩ ተጠቋሚዎች የሚከተሉት ናቸው፡ 1. ሎሬት ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈራ 2. ፕሮፌሰር አፈወርቅ በቀለ ስመኝ 3. ፕሮፌሰር ጥላሁን ተሾመ 4. ፕሮፌሰር ባዬ ይማም 5. ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ 6. ፕሮፌሰር ያእቆብ አርሳኖ 7. ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሃኑ ዓለሙ 8. ፕሮፌሰር ህዝቅያስ አሰፋ 9. ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጀቤሳ 10. ፕሮፌሰር ዶክተር ዳንኤል ቅጣው 11. ፕሮፌሰር ዘካሪያስ ቀነአ ተስገራ 12. ፕሮፌሰር ክፍሌ ወ/ሚካኤል ሐጀቶ 13. ዶክተር በድሉ ዋቅጅታ 14. ዶክተር ሰሚር የሱፍ 15. ዶክተር አብዲሳ ዘርዓይ በማኖ 16. ዶክተር ሀብታሙ ወንድሙ 17. ዶክተር ታከለ ሰቦቃ 18. ዶክተር ዮናስ አዳዬ 19. ዶክተር ወዳጆ ወ/ጊዮርጊስ 20. ዶክተር ሙሉጌታ አረጋዊ 21. ዶክተር ነጋልኝ ብርሃኑ ባዬ 22. ዶክተር አበራ ዴሬሳ 23. ዶክተር አይሮሪት መ/ድያሲን 24. ዶክተር ተገኘወርቅ ጌጡ መንገሻ 25. ዶክተር ዳዊት ዮሐንስ 26. ዶክተር ተካለ ሰቦቃ 27. ኢንጂኒየር ጌታሁን ሁሴን ሽኩር 28. አምባሳደር ታደለች ኃይለሚካኤል 29. አምባሳደር ምዑዝ ገብረ ሕይወት ወልደ ሥላሴ 30. አምባሳደር ማህሙድ ድሪር 31. አቶ ዘገየ አስፋው አብዲ 32. ወ/ሮ ዘነብወርቅ ታደሰ ማርቆስ 33. አቶ ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ እሸቴ 34. አቶ መላኩ ወልደማሪያም 35. አቶ አንዳርጋቸው አሰግድ 36. አቶ ገመቹ ዱቢሶ ጉደና 37. አቶ ሳሙኤል ጣሰው ተፈራ 38. አቶ አህመድ ሁሴን መሐመድ 39. ወ/ሮ ሂሮት ገ/ሥላሴ ኦዳ 40. አቶ ንጉሡ አክሊሉ 41. አቶ ተስፋዬ ሐቢሶ 42. አቶ አባተ ኪሾ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለአገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት የተጠቆሙትን 42ቱን ግለሰቦች ዝርዝር ከአጭር የትምህርትና የሥራ መግለጫ ጋር በድረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገ ሲሆን ሕዝቡም አስተያየት እንዲሰጥባቸው ጥያቄ አቅርቧል። ከዚህ ሂደት በኋላም በተጠቋሚ ዕጩዎቹ ላይ ከሕዝብ የሚቀርበው አስተያየት ተገምግሞ የመጨረሻዎቹ 11 ዕጩ ኮሚሽነሮች ተለይተው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሹመት እንደሚቀርቡ ተገልጿል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60260831 |
2health
| የኮሮናቫይረስ ክትባት መገኘት ተስፋ የዓለም ገበያን እያነቃቃው ነው | ኮቪድ-19ን ለመከላከል ይረዳሉ የተባሉ ክትባቶች ወደመጨረሻ ደረጃቸው ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የዓለም ገበያ እንደ አዲስ እየተነቃቃ መሆኑ ተዘግቧል። ፋይዘር የተባለው መድሀኒት አምራች ኩባንያ ኮሮናቫይረስን የመከላከል አቅሙ 90 በመቶ ነው ያለውን ክትባት ይፋ ካደረገ በኋላ የድርጅቱ ድርሻ በዓለም ገበያ በ9 መቶ ከፍ ማለቱ ተስተውሏል። በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊው ጆ ባይደን መሆናቸው ከተነገረ ወዲህ መነቃቃት እያሳየ የነበረው ዓለም ገበያ አሁን ደግሞ ክትባቱን ተከትሎ ሌላ እሽቅድድምን ፈጥሯል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ የ2008 የዓለም የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መቀነሱ የሚታወስ ነው። በሞዛምቢክ ከ50 በላይ ሰዎች በጽንፈኞች 'አንገታቸው ተቀላ' አርሜኒያ "እጅግ በጣም የሚያም" ያለችውን የሰላም ስምምነት ከአዘርባጃን ጋር ለመፈረም ተገደደች 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ተሰራ በአሜሪካ የሚገኙ ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋቸው ከ1.1 በመቶ እስከ 5.6 በመቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍ ያለ ሲሆን በእሲያና አውሮፓ የሚገኙ ድርጅቶችም ድርሻቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል። ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘርና ባዮኤንቴክ ክትባቱን በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ይህ ክትባት ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው። ከዚህ ቀደም የተደረገው ሙከራ ክትባቱ ሰውነታችን ከበሽታው ጋር እንዲለማመድና አንቲቦዲዎችን እንዲያዳብር መርዳቱ የተስተዋለ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቲ-ሴል በመባል የሚታወቀው የመከላከል አቅምን የኮሮናቫይረስን መዋጋት እንዲችል አድርጎታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኘው 'ኤፍቲኤስኢ 100' የወረርሽኙ ዜና ከተሰማበት መጋቢት ወር ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በዓለም አቀፍ ገበያ ድርሻው ላይ የ82 ቢሊየን ፓውንድ ጭማሪ አግኝቷል። የተለያዩ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች እየሞከሯቸው ባሉት የክትባት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያገኙ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ መግለጻቸውን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ገበያው ከዚህም በበለጠ ሊያድግ እንደሚችል ተጠቁሟል። | የኮሮናቫይረስ ክትባት መገኘት ተስፋ የዓለም ገበያን እያነቃቃው ነው ኮቪድ-19ን ለመከላከል ይረዳሉ የተባሉ ክትባቶች ወደመጨረሻ ደረጃቸው ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ የዓለም ገበያ እንደ አዲስ እየተነቃቃ መሆኑ ተዘግቧል። ፋይዘር የተባለው መድሀኒት አምራች ኩባንያ ኮሮናቫይረስን የመከላከል አቅሙ 90 በመቶ ነው ያለውን ክትባት ይፋ ካደረገ በኋላ የድርጅቱ ድርሻ በዓለም ገበያ በ9 መቶ ከፍ ማለቱ ተስተውሏል። በአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አሸናፊው ጆ ባይደን መሆናቸው ከተነገረ ወዲህ መነቃቃት እያሳየ የነበረው ዓለም ገበያ አሁን ደግሞ ክትባቱን ተከትሎ ሌላ እሽቅድድምን ፈጥሯል። የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአክስዮን ገበያ ከአውሮፓውያኑ የ2008 የዓለም የገንዘብ ቀውስ ወዲህ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ መቀነሱ የሚታወስ ነው። በሞዛምቢክ ከ50 በላይ ሰዎች በጽንፈኞች 'አንገታቸው ተቀላ' አርሜኒያ "እጅግ በጣም የሚያም" ያለችውን የሰላም ስምምነት ከአዘርባጃን ጋር ለመፈረም ተገደደች 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ተሰራ በአሜሪካ የሚገኙ ድርጅቶች የአክሲዮን ዋጋቸው ከ1.1 በመቶ እስከ 5.6 በመቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍ ያለ ሲሆን በእሲያና አውሮፓ የሚገኙ ድርጅቶችም ድርሻቸው በከፍተኛ ሁኔታ ጭማሪ አሳይቷል። ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘርና ባዮኤንቴክ ክትባቱን በሶስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል። በቁጥር የበዙ ክትባቶች የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የተነገረ ሲሆን ይህ ክትባት ተስፋ ከተጣለባቸው ውስጥ ቀዳሚው ነው። ከዚህ ቀደም የተደረገው ሙከራ ክትባቱ ሰውነታችን ከበሽታው ጋር እንዲለማመድና አንቲቦዲዎችን እንዲያዳብር መርዳቱ የተስተዋለ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቲ-ሴል በመባል የሚታወቀው የመከላከል አቅምን የኮሮናቫይረስን መዋጋት እንዲችል አድርጎታል ተብሏል። በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኘው 'ኤፍቲኤስኢ 100' የወረርሽኙ ዜና ከተሰማበት መጋቢት ወር ጀምሮ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በዓለም አቀፍ ገበያ ድርሻው ላይ የ82 ቢሊየን ፓውንድ ጭማሪ አግኝቷል። የተለያዩ መድሃኒት አምራች ኩባንያዎች እየሞከሯቸው ባሉት የክትባት ስራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያገኙ ስለመሆኑ በተደጋጋሚ መግለጻቸውን ተከትሎ የዓለም አቀፍ ገበያው ከዚህም በበለጠ ሊያድግ እንደሚችል ተጠቁሟል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54884202 |
3politics
| በማህተማ ጋንዲ ገዳይ ዙሪያ ያለው ምስጢር | ጥር 30/1948 ምሽት ማህተማ ጋንዲ ወይም በሙሉ ስማቸው ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ በሕንድ መዲና ደልሂ ከፀሎት ሲወጡ በሽጉጥ ተገደሉ። ከቅርብ ርቀት ሽጉጥ ተኩሶ የገደላቸውም ናታሁራም ቪናያክ ጎድሴ ይባላል። የ38 ዓመቱ ገዳይ ሂንዱ ማሃሳብሃ ተብሎ የሚጠራው የአክራሪው ቀኝ ክንፍ ፓርቲ አባል ነው። ጋንዲ ሙስሊሞችን ይደግፋሉ እንዲሁም ለፓኪስታን ገር የሆነ ልብ በማሳየት ሂንዲዎችን ክደዋልም ሲል ከሷቸዋል። ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣታቸውን ተከትሎ በአንድ ግዛት ስር የነበሩት ሕንድና ፓኪስታን በሚል ለሁለት በመከፈል በ1947 ለተፈጠረው ደም መፋሰስም ጋንዲን ተጠያቂ አድርገዋቸዋል። ማህተማ ጋንዲ ከተገደሉ ከዓመት በኋላ ጎድሴ የሞት ቅጣት ተፈረደበት። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን ካረጋገጠ በኋላ በኅዳር 1949 ዓ.ም ግለሰቡ በስቅላት ተቀጣ። በግድያው ተባባሪ የነበረው ናራያን አፕቴም በሞት ሲቀጣ፣ ሌሎች እጃቸው አለበት የተባሉ ስድስት ግለሰቦች ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። የጎድሴን የኋላ ታሪክ ስናይ የሂንዱ ማሃሳብሃን ከመቀላቀሉ በፊት የሕንድ ገዢ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ (ቢጄፒ) ርዕዮተ ዓለም መስረት የሆነው የራሽትሪያ ስዋያምሴቫክ ሳንግ (ብሔራዊ የበጎ ፈቃደኞች ድርጅት) አባል ነበር። አገሪቱን በአሁኑ ወቅት እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም ቢሆኑ በሕንድ ውስጥ በሂንዱ ብሄርተኝነቱ ፈር ቀዳጅ የሆነው የ95 ዓመቱ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲን (ቢጄፒ) የተቀላቀሉት ከረጅም ዓመታት በፊት ነው። የራሽትሪያ ስዋያምሴቫክ ሳንግ (አርኤስኤስ) በሕንድ ባለው አገዛዝ እንዲሁም በውጭው ዓለም ከፍተኛ ሚናን በመጫወት የሚጠቀስ ነው። ለአስርት ዓመታትም አርኤስኤስ "የሕንዳውያን አባት" ተብለው የሚጠሩትንና በድንቅነታቸው ታሪክ የሚዘክራቸውን ማህተማ ጋንዲ ገዳይን ጎድሴን ሲያወግዝ ይሰማ ነበር። ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሂንዱ ቀኝ አክራሪ ቡድን ጎድሴን በጀግንነት በማወደስና የጋንዲን መገደል በይፋ አክብረዋል። በባለፈው ዓመትም የገዢው ፓርቲ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑ ግለሰብ ጎድሴን "አርበኛ" ሲሉ አሞካሽተውታል። እነዚህ ክስተተች በርካታ ሕንዳውያንን ቢያበሳጩም አርኤስኤስ ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ በፊት ከድርጅት አባልነቱ ተሰናብቷል በሚል አቋሙ እንደጸና ነው። ነገር ግን በቅርቡ የወጣ መጽሐፍ የአርኤስኤስን አለኝ የሚለውን እውነት የሚያፈርስ ነው። ጎድሴ ዓይነ አፋር፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያቋረጠና ማሃሳብሃን ከመቀላቀሉ በፊትም በልብስ ስፌትና ፍራፍሬ በመሸጥ ይተዳደር ነበር። ማሃሳብሃን ከተቀላቀለ በኋላ የጋዜጣ አርትዖት ሥራ ተሰማራ። በፍርድ ሂደቱ ወቅት 150 አንቀፆች ያሉትን መግለጫ ይዞ የቀረበ ሲሆን ለአምስት ሰዓት ያህልም አንብቧል። ጋንዲን ለመግደል ምንም አይነት የተቀነባበረ ሴራ የለም በማለትም ተባባሪዎቹን ከቅጣት ለማዳንም ሞክሯል። የሂንዱትቫ ወይም የሕንዳዊነት ማንነትን እሳቤ በወለደው በመሪያቸው ቪናያክ ዳሞዳር ሳቫርካር መሪነት ተቀነባብሮ የተፈጸመ ግድያ ነው የሚለውን ክስም ውድቅ አደረገው። መሪው ሳቫርካር ከሁሉም ክሶች ነፃ ቢወጣም ተቺዎች ጋንዲን የሚጠላው የአክራሪው ቀኝ ክንፍ ከግድያው ጀርባ እጁ አለበት ብለው ያምናሉ። ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ ከረጅም ጊዜ በፊት ከአርኤስኤስ ጋር መቆራረጡን ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። የጋንዲ ገዳይ መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት ድሪንደርድራ ጃሃ ጎሴ በበኩላቸው ከፖስታ ሠራተኛ አባትና ከቤት እመቤት እናት የተወለደው ጎድሴ በአርኤስኤስ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሠራተኛ እንደነበርም አስፍረዋል። በተጨማሪም ከአርኤስኤስ ስለመባረሩ ምንም አይነት መረጃ የለም ይላሉ። ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ቃሉን በሚሰጥበት ወቅትም የሂንዱ ማሃሳብሃ አባል ከሆነ በኋላ ከአርኤስኤስ ስለመውጣቱ ያለው ነገር የለም። ሆኖም ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት አርኤስኤስን ከተሰናበተ በኋላ የሂንዱ ማሃሳብሃ አባል እንደሆነ ቢናገርም መቼ ከድርጅቱ እንደወጣም ሊያስረዳ አልቻለም። ከዚህም ጋር ተያይዞ የጎድሴ ህይወት አከራካሪ ሆኖ መቀጠሉንም ጃሃ ይናገራሉ። የአርኤስኤስ ደጋፊ ጸሐፊዎች ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ ከአስር ዓመት በፊት ድርጅቱን እንደተሰናበተና ከዚያም ሂንዱ ማሃሳብሃን ተቀላቅሏል የሚል አጀንዳን ለመግፋት ተጠቅመውበታል ይላሉ ጃሃ። አሜሪካዊው ተመራማሪ ጄኤ ኩራን ጁኒየር ጎድሴ አርኤስኤስን በ1930 እንደተቀላቀለ እና ከአራት ዓመት በኋላ መሰናበቱን ያስረዳል፣ ነገር ግን ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ጎድሴ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ለፖሊስ በሰጠው ለሁለቱም ድርጅቶች ይሰራ እንደነበር አምኗል ሲሉ ጃሃ ጽፈዋል። የጎድሴ የቤተሰብ አባላት የዚህ ክርክር አካል ሆነዋል። በ2005 የሞተው የናቱራም ጎድሴ ወንድም ጎፓል ጎድሴ በበኩሉ አርኤስኤስን እንዳልተሰናበተ ተናግሯል። የጎድሴ ታላቅ ወንድም ልጅ በ2015 ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ቆይታ ጎድሴ አርኤስኤስን በ1932 እንደተቀላቀለና ከድርጅቱም እንዳልተባረረ ራሱም እንዳልወጣ ተናግሯል። የተለያዩ መዛግብትን ያገላበጡት ጃሃ ሁለቱ የሂንዱ ድርጅቶች ግንኙነት እንደነበራቸው ያስረዳሉ። የሂንዱ ማሃሳብሃ እና አርኤስኤስ ተመሳሳይ ግብና ለየት ያለ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ሲንቀሳቀሱ የነበሩት በተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም ነው ሲሉ ጽፈዋል። ሁለቱም ድርጅቶች ጋንዲ እስከሚገደሉበት ጊዜ ድረስ የቅርብ ጊዜ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን የሁለቱም ድርጅቶች አባል የሆኑ ግለሰቦች ነበሯቸው። ጋንዲ ከተገደሉ በኋላ አርኤስኤስ ከአንድ ዓመት በላይ ታግዷል። አርኤስኤስ ጎድሴ በፍርድ ቤት የተናገረውን ድርጅቱን በ1930ዎቹ አጋማሽ ለቅቆ መውጣቱን በመጥቀስ እንዲሁም የፍርድ ቤት ውሳኔውን ከአርኤስኤስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ማሳያ ነው ሲልም ይከራከራል። የአርኤስኤስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ራም ማድሃቭ ጎድሴ በግድያው ወቅት "የአርኤስኤስ አባል ነበር ማለት ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት የተፈጠረ ውሸት ነው" ብለዋል። በአርኤስኤስ በጣም ተደማጭነት ካላቸው መሪዎች አንዱ የሆኑት ኤም ኤስ ጎልዋልከር የጋንዲን ግድያ "ወደር የለሽ አሳዛኝ ሁኔታ" ሲሉ በመግለጽ በጣም አስደንጋጭ የሚያደርገውም ግድያውን ያቀነባበረው የአገሪቱ ዜጋና ሂንዱ መሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በቅርብ ጊዜም እንደ ኤምጂ ቫይድያ ያሉ የአርኤስኤስ አመራሮች "የሕንድን ታላቅ ሰው በመግደል የሂንዱትቫን ፅንሰ ሃሳብ ያንቋሸሸ ነፍሰ ገዳይ" ሲሉ ጎድሴን ጠርተውታል። እንደ ቪክራም ሳምፓት ያሉ ደራሲዎች በበኩላቸው አርኤስኤስ እና የሂንዱ ማሃሳብሃ የሚሞቅና የሚቀዘቅዝ ግንኙነት እንደነበራቸው ያምናሉ። የሳቫርካርን የህይወት ታሪክ በሁለት ጥራዝ የፃፉት ቪክራም ሳምፓት "የሂንዱዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ" በሚል የሂንዱ ማሃሳብሃ የበጎ ፈቃደኞች ቡድንን ከ"አብዮታዊ ምስጢራዊ ማኅበር" ጋር በማዋቀር ያደረገው ውሳኔ አሳዝኖታል፣ ከአርኤስኤስ ጋር የነበረውንም ግንኙነት አሻክሮታል። ሳምፖት እንዳሉት "በጀግንነት አምልኮ የተጠመደ እና የተጋነነ አድናቆት "እሳቤን " ከሚከተለው ከማሃሳብሃ መሪ ሳቫርካር በመለየትም አርኤስኤስ ግለሰቦችን ጣኦት ከማድረግ ተቆጥቧል። አርኤስኤስ 'ኤ ቪው ቱ ዘ ኢንሳይድን' የጻፉት ዋልተር ኬ አንደርሰን እና ሽሪድሃር ዲ ዳም በመጽሐፋቸው የቀድሞው አባል ናቱራም ጎድሴ በጋንዲ ግድያ ላይ መሳተፉ ድርጅቱን በከፍተኛ ሁኔታ አጠልሽቶታል፤ ጎድቶታልም ብለዋል። ድርጅቱ የፋሽስት፣ አምባገነን፣ አጭበርባሪዎችን ከመደገፍ ጋር መያያዙ ስሙ ጠፍቷል። ነገር ግን ጎድሴ የአርኤስኤስ አካል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥርጣሬዎች መቼም ደብዝዘው አያውቁም። ጎድሴ በኅዳር 15/1949 ወደ መሰቀያው ስፍራ ከመወሰዱ በፊት የአርኤስኤስ ፀሎት የመጀመሪያዎቹን አራት ዓረፍተ ነገሮች ሲያነበንብ ነበር። "ይህም የድርጅቱ ንቁ አባል እንደነበረ በድጋሚ ያሳያል" ሲሉ ጃሃ ያስረዳል። "አርኤስኤስን ከጋንዲ ገዳይ ማግለል የታሪክ ፈጠራ ነው" ይላሉ ጃሃ። ማስታወሻ፦ በፅሁፉ የተጠቀሱት የቀን አቆጣጠሮች በሙሉ በአውሮፓውያኑ ነው | በማህተማ ጋንዲ ገዳይ ዙሪያ ያለው ምስጢር ጥር 30/1948 ምሽት ማህተማ ጋንዲ ወይም በሙሉ ስማቸው ሞሃንዳስ ካራምቻንድ ጋንዲ በሕንድ መዲና ደልሂ ከፀሎት ሲወጡ በሽጉጥ ተገደሉ። ከቅርብ ርቀት ሽጉጥ ተኩሶ የገደላቸውም ናታሁራም ቪናያክ ጎድሴ ይባላል። የ38 ዓመቱ ገዳይ ሂንዱ ማሃሳብሃ ተብሎ የሚጠራው የአክራሪው ቀኝ ክንፍ ፓርቲ አባል ነው። ጋንዲ ሙስሊሞችን ይደግፋሉ እንዲሁም ለፓኪስታን ገር የሆነ ልብ በማሳየት ሂንዲዎችን ክደዋልም ሲል ከሷቸዋል። ከብሪታንያ ቅኝ ግዛት ነፃ መውጣታቸውን ተከትሎ በአንድ ግዛት ስር የነበሩት ሕንድና ፓኪስታን በሚል ለሁለት በመከፈል በ1947 ለተፈጠረው ደም መፋሰስም ጋንዲን ተጠያቂ አድርገዋቸዋል። ማህተማ ጋንዲ ከተገደሉ ከዓመት በኋላ ጎድሴ የሞት ቅጣት ተፈረደበት። ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን ካረጋገጠ በኋላ በኅዳር 1949 ዓ.ም ግለሰቡ በስቅላት ተቀጣ። በግድያው ተባባሪ የነበረው ናራያን አፕቴም በሞት ሲቀጣ፣ ሌሎች እጃቸው አለበት የተባሉ ስድስት ግለሰቦች ደግሞ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል። የጎድሴን የኋላ ታሪክ ስናይ የሂንዱ ማሃሳብሃን ከመቀላቀሉ በፊት የሕንድ ገዢ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ (ቢጄፒ) ርዕዮተ ዓለም መስረት የሆነው የራሽትሪያ ስዋያምሴቫክ ሳንግ (ብሔራዊ የበጎ ፈቃደኞች ድርጅት) አባል ነበር። አገሪቱን በአሁኑ ወቅት እየመሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲም ቢሆኑ በሕንድ ውስጥ በሂንዱ ብሄርተኝነቱ ፈር ቀዳጅ የሆነው የ95 ዓመቱ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲን (ቢጄፒ) የተቀላቀሉት ከረጅም ዓመታት በፊት ነው። የራሽትሪያ ስዋያምሴቫክ ሳንግ (አርኤስኤስ) በሕንድ ባለው አገዛዝ እንዲሁም በውጭው ዓለም ከፍተኛ ሚናን በመጫወት የሚጠቀስ ነው። ለአስርት ዓመታትም አርኤስኤስ "የሕንዳውያን አባት" ተብለው የሚጠሩትንና በድንቅነታቸው ታሪክ የሚዘክራቸውን ማህተማ ጋንዲ ገዳይን ጎድሴን ሲያወግዝ ይሰማ ነበር። ሆኖም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሂንዱ ቀኝ አክራሪ ቡድን ጎድሴን በጀግንነት በማወደስና የጋንዲን መገደል በይፋ አክብረዋል። በባለፈው ዓመትም የገዢው ፓርቲ ባሃራቲያ ጃናታ ፓርቲ የፓርላማ አባል የሆኑ ግለሰብ ጎድሴን "አርበኛ" ሲሉ አሞካሽተውታል። እነዚህ ክስተተች በርካታ ሕንዳውያንን ቢያበሳጩም አርኤስኤስ ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ በፊት ከድርጅት አባልነቱ ተሰናብቷል በሚል አቋሙ እንደጸና ነው። ነገር ግን በቅርቡ የወጣ መጽሐፍ የአርኤስኤስን አለኝ የሚለውን እውነት የሚያፈርስ ነው። ጎድሴ ዓይነ አፋር፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያቋረጠና ማሃሳብሃን ከመቀላቀሉ በፊትም በልብስ ስፌትና ፍራፍሬ በመሸጥ ይተዳደር ነበር። ማሃሳብሃን ከተቀላቀለ በኋላ የጋዜጣ አርትዖት ሥራ ተሰማራ። በፍርድ ሂደቱ ወቅት 150 አንቀፆች ያሉትን መግለጫ ይዞ የቀረበ ሲሆን ለአምስት ሰዓት ያህልም አንብቧል። ጋንዲን ለመግደል ምንም አይነት የተቀነባበረ ሴራ የለም በማለትም ተባባሪዎቹን ከቅጣት ለማዳንም ሞክሯል። የሂንዱትቫ ወይም የሕንዳዊነት ማንነትን እሳቤ በወለደው በመሪያቸው ቪናያክ ዳሞዳር ሳቫርካር መሪነት ተቀነባብሮ የተፈጸመ ግድያ ነው የሚለውን ክስም ውድቅ አደረገው። መሪው ሳቫርካር ከሁሉም ክሶች ነፃ ቢወጣም ተቺዎች ጋንዲን የሚጠላው የአክራሪው ቀኝ ክንፍ ከግድያው ጀርባ እጁ አለበት ብለው ያምናሉ። ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ ከረጅም ጊዜ በፊት ከአርኤስኤስ ጋር መቆራረጡን ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል። የጋንዲ ገዳይ መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት ድሪንደርድራ ጃሃ ጎሴ በበኩላቸው ከፖስታ ሠራተኛ አባትና ከቤት እመቤት እናት የተወለደው ጎድሴ በአርኤስኤስ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ሠራተኛ እንደነበርም አስፍረዋል። በተጨማሪም ከአርኤስኤስ ስለመባረሩ ምንም አይነት መረጃ የለም ይላሉ። ፍርድ ቤት ከመቅረቡ በፊት ቃሉን በሚሰጥበት ወቅትም የሂንዱ ማሃሳብሃ አባል ከሆነ በኋላ ከአርኤስኤስ ስለመውጣቱ ያለው ነገር የለም። ሆኖም ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት አርኤስኤስን ከተሰናበተ በኋላ የሂንዱ ማሃሳብሃ አባል እንደሆነ ቢናገርም መቼ ከድርጅቱ እንደወጣም ሊያስረዳ አልቻለም። ከዚህም ጋር ተያይዞ የጎድሴ ህይወት አከራካሪ ሆኖ መቀጠሉንም ጃሃ ይናገራሉ። የአርኤስኤስ ደጋፊ ጸሐፊዎች ጎድሴ ጋንዲን ከመግደሉ ከአስር ዓመት በፊት ድርጅቱን እንደተሰናበተና ከዚያም ሂንዱ ማሃሳብሃን ተቀላቅሏል የሚል አጀንዳን ለመግፋት ተጠቅመውበታል ይላሉ ጃሃ። አሜሪካዊው ተመራማሪ ጄኤ ኩራን ጁኒየር ጎድሴ አርኤስኤስን በ1930 እንደተቀላቀለ እና ከአራት ዓመት በኋላ መሰናበቱን ያስረዳል፣ ነገር ግን ለዚህ ማስረጃ ማቅረብ አልቻለም። ጎድሴ የፍርድ ሂደቱ ከመጀመሩ በፊት ለፖሊስ በሰጠው ለሁለቱም ድርጅቶች ይሰራ እንደነበር አምኗል ሲሉ ጃሃ ጽፈዋል። የጎድሴ የቤተሰብ አባላት የዚህ ክርክር አካል ሆነዋል። በ2005 የሞተው የናቱራም ጎድሴ ወንድም ጎፓል ጎድሴ በበኩሉ አርኤስኤስን እንዳልተሰናበተ ተናግሯል። የጎድሴ ታላቅ ወንድም ልጅ በ2015 ከጋዜጠኞች ጋር ባደረገው ቆይታ ጎድሴ አርኤስኤስን በ1932 እንደተቀላቀለና ከድርጅቱም እንዳልተባረረ ራሱም እንዳልወጣ ተናግሯል። የተለያዩ መዛግብትን ያገላበጡት ጃሃ ሁለቱ የሂንዱ ድርጅቶች ግንኙነት እንደነበራቸው ያስረዳሉ። የሂንዱ ማሃሳብሃ እና አርኤስኤስ ተመሳሳይ ግብና ለየት ያለ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን ሲንቀሳቀሱ የነበሩት በተመሳሳይ ርዕዮተ ዓለም ነው ሲሉ ጽፈዋል። ሁለቱም ድርጅቶች ጋንዲ እስከሚገደሉበት ጊዜ ድረስ የቅርብ ጊዜ ግንኙነት የነበራቸው ሲሆን የሁለቱም ድርጅቶች አባል የሆኑ ግለሰቦች ነበሯቸው። ጋንዲ ከተገደሉ በኋላ አርኤስኤስ ከአንድ ዓመት በላይ ታግዷል። አርኤስኤስ ጎድሴ በፍርድ ቤት የተናገረውን ድርጅቱን በ1930ዎቹ አጋማሽ ለቅቆ መውጣቱን በመጥቀስ እንዲሁም የፍርድ ቤት ውሳኔውን ከአርኤስኤስ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ማሳያ ነው ሲልም ይከራከራል። የአርኤስኤስ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ራም ማድሃቭ ጎድሴ በግድያው ወቅት "የአርኤስኤስ አባል ነበር ማለት ፖለቲካዊ ጥቅም ለማግኘት የተፈጠረ ውሸት ነው" ብለዋል። በአርኤስኤስ በጣም ተደማጭነት ካላቸው መሪዎች አንዱ የሆኑት ኤም ኤስ ጎልዋልከር የጋንዲን ግድያ "ወደር የለሽ አሳዛኝ ሁኔታ" ሲሉ በመግለጽ በጣም አስደንጋጭ የሚያደርገውም ግድያውን ያቀነባበረው የአገሪቱ ዜጋና ሂንዱ መሆኑ ነው ሲሉ ተናግረዋል። በቅርብ ጊዜም እንደ ኤምጂ ቫይድያ ያሉ የአርኤስኤስ አመራሮች "የሕንድን ታላቅ ሰው በመግደል የሂንዱትቫን ፅንሰ ሃሳብ ያንቋሸሸ ነፍሰ ገዳይ" ሲሉ ጎድሴን ጠርተውታል። እንደ ቪክራም ሳምፓት ያሉ ደራሲዎች በበኩላቸው አርኤስኤስ እና የሂንዱ ማሃሳብሃ የሚሞቅና የሚቀዘቅዝ ግንኙነት እንደነበራቸው ያምናሉ። የሳቫርካርን የህይወት ታሪክ በሁለት ጥራዝ የፃፉት ቪክራም ሳምፓት "የሂንዱዎችን ጥቅም ለማስጠበቅ" በሚል የሂንዱ ማሃሳብሃ የበጎ ፈቃደኞች ቡድንን ከ"አብዮታዊ ምስጢራዊ ማኅበር" ጋር በማዋቀር ያደረገው ውሳኔ አሳዝኖታል፣ ከአርኤስኤስ ጋር የነበረውንም ግንኙነት አሻክሮታል። ሳምፖት እንዳሉት "በጀግንነት አምልኮ የተጠመደ እና የተጋነነ አድናቆት "እሳቤን " ከሚከተለው ከማሃሳብሃ መሪ ሳቫርካር በመለየትም አርኤስኤስ ግለሰቦችን ጣኦት ከማድረግ ተቆጥቧል። አርኤስኤስ 'ኤ ቪው ቱ ዘ ኢንሳይድን' የጻፉት ዋልተር ኬ አንደርሰን እና ሽሪድሃር ዲ ዳም በመጽሐፋቸው የቀድሞው አባል ናቱራም ጎድሴ በጋንዲ ግድያ ላይ መሳተፉ ድርጅቱን በከፍተኛ ሁኔታ አጠልሽቶታል፤ ጎድቶታልም ብለዋል። ድርጅቱ የፋሽስት፣ አምባገነን፣ አጭበርባሪዎችን ከመደገፍ ጋር መያያዙ ስሙ ጠፍቷል። ነገር ግን ጎድሴ የአርኤስኤስ አካል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚነሱ ጥርጣሬዎች መቼም ደብዝዘው አያውቁም። ጎድሴ በኅዳር 15/1949 ወደ መሰቀያው ስፍራ ከመወሰዱ በፊት የአርኤስኤስ ፀሎት የመጀመሪያዎቹን አራት ዓረፍተ ነገሮች ሲያነበንብ ነበር። "ይህም የድርጅቱ ንቁ አባል እንደነበረ በድጋሚ ያሳያል" ሲሉ ጃሃ ያስረዳል። "አርኤስኤስን ከጋንዲ ገዳይ ማግለል የታሪክ ፈጠራ ነው" ይላሉ ጃሃ። ማስታወሻ፦ በፅሁፉ የተጠቀሱት የቀን አቆጣጠሮች በሙሉ በአውሮፓውያኑ ነው | https://www.bbc.com/amharic/news-60172567 |
2health
| ተጨማሪ ዘጠኝ የኮቪድ-19 ምልክቶች ይፋ ሆኑ | ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ላይ ተጨማሪ ዘጠኝ ምልክቶች ተጨመሩ። እነዚህ ምልክቶች ከዚህ በፊት የነበሩትን የሚያሰፉና ተጨማሪ ነገሮችን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ናቸው። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው አዲስ መመሪያ ውስጥ የጉሮሮ ህመም፣ የጡንቻ ህመም እና 'ተቅማጥ' ከተካተቱት አዳዲስ የኮሮረናቫይረስ ምልክቶች መካከል ናቸው። ይህ መመሪያ የወጣው ወረርሽኙ ከተከሰተ ሁለት ዓመታት ካለፈው በኋላ ሲሆን እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ይደረግ የነበረው የነጻ ምርመራ ከተቋረጠ ከቀናት በኋላ ነው። ነገር ግን የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልእክት አዳዲሶቹ ምልክቶች ከጉንፋን ብዙም ያልተለዩ መሆናቸውን አሳስቧል። ከዚህ በፊት የሚታወቁት የኮቪድ-19 ምልክቶች ትኩሳት፣ የማያቆም ሳል፣ የሽታ እና የመቅመስ ስሜቶቻችን መጥፋት እንዲሁም ድካም የሚጠቀሱ ናቸው። ወረርሽኙ ባጋጠመበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ወቅት የስርጭቱን አካሄድ መረዳትና ምልክቶቹን መለየት ከባድ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ዓለም ስለቫይረሱ ማወቅ ከሚገባው አብዛኛውን ነገር አውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ቢሆን ከረጅም ጊዜ በፊት ምልክቶች ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በርካታ ናቸው። ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ትክክለኛ ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው እንዲሁም ምን አይነት ምልክቶችን የሚያሳይ ሰው ነው ምርመራ ማድረግ ያለበት የሚሉት ጥያቄዎች መከራከሪያ ሆነው ቆይተዋል። ለምሳሌ ራስ ምታት የኮሮናቫይረስ ምልክት ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል ቢሆንም ራሱን ያመመው ሰው በሙሉ ግን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አይችልም። ምክንያቱም ራስ ምታት ከኮሮናቫይረስ ውጪ በበርካታ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ትኩሳት፣ ሳል፣ ማሽተት ማቆም አልያም ጣእም ማጣት በርካቶችን የማያከራክሩ ምልክቶች ሲሆኑ አሁን ላይ ደግሞ ዘጠኝ ተጨማሪ ምልክቶች እንዲጨመሩ ተደርጓል። እነዚህም ትንፋሽ ማጠር፣ ድካም፣ የሰውነት መላሸቅ፣ ራስ ምታት፣ የጉሮሮ ሕመም፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ [ንፍጥ]፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ተቅማጥ እና አጠቃላይ የጤንነት ስሜት ማጣት ናቸው። ዩኬ ውስጥ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4.9 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን መንግስት በነጻ ሲያከናውነው የነበረው ምርመራም ባሳለፍነው ሳምንት ተጠናቋል። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ እንደሚለው ሰዎች አሁንም ቢሆን በተቻላቸው መጠን ከቤታቸው ላለመውጣት መሞከርና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውንም ንክኪ መቀነስ አለባቸው። በተለይ ደግሞ እነዚህን ምልክቶች የሚያሳይ ሰው ምርመራ ማድረግና እራሱን ከሰዎች መለየት እንዳለበት ኤጀንሲው አሳስቧል። | ተጨማሪ ዘጠኝ የኮቪድ-19 ምልክቶች ይፋ ሆኑ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ በኮሮናቫይረስ የተያዘ ሰው የሚያሳያቸው ምልክቶች ላይ ተጨማሪ ዘጠኝ ምልክቶች ተጨመሩ። እነዚህ ምልክቶች ከዚህ በፊት የነበሩትን የሚያሰፉና ተጨማሪ ነገሮችን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ ናቸው። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባዘጋጀው አዲስ መመሪያ ውስጥ የጉሮሮ ህመም፣ የጡንቻ ህመም እና 'ተቅማጥ' ከተካተቱት አዳዲስ የኮሮረናቫይረስ ምልክቶች መካከል ናቸው። ይህ መመሪያ የወጣው ወረርሽኙ ከተከሰተ ሁለት ዓመታት ካለፈው በኋላ ሲሆን እንግሊዝ ውስጥ ደግሞ ይደረግ የነበረው የነጻ ምርመራ ከተቋረጠ ከቀናት በኋላ ነው። ነገር ግን የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልእክት አዳዲሶቹ ምልክቶች ከጉንፋን ብዙም ያልተለዩ መሆናቸውን አሳስቧል። ከዚህ በፊት የሚታወቁት የኮቪድ-19 ምልክቶች ትኩሳት፣ የማያቆም ሳል፣ የሽታ እና የመቅመስ ስሜቶቻችን መጥፋት እንዲሁም ድካም የሚጠቀሱ ናቸው። ወረርሽኙ ባጋጠመበት የመጀመሪያዎቹ ወራት ወቅት የስርጭቱን አካሄድ መረዳትና ምልክቶቹን መለየት ከባድ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ግን ዓለም ስለቫይረሱ ማወቅ ከሚገባው አብዛኛውን ነገር አውቋል። የዓለም ጤና ድርጅትም ቢሆን ከረጅም ጊዜ በፊት ምልክቶች ብሎ ያስቀመጣቸው ነገሮች በርካታ ናቸው። ነገር ግን ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ትክክለኛ ምልክቶቹ የትኞቹ ናቸው እንዲሁም ምን አይነት ምልክቶችን የሚያሳይ ሰው ነው ምርመራ ማድረግ ያለበት የሚሉት ጥያቄዎች መከራከሪያ ሆነው ቆይተዋል። ለምሳሌ ራስ ምታት የኮሮናቫይረስ ምልክት ተደርጎ ሊቆጠር የሚችል ቢሆንም ራሱን ያመመው ሰው በሙሉ ግን የኮሮናቫይረስ ምርመራ ማድረግ አይችልም። ምክንያቱም ራስ ምታት ከኮሮናቫይረስ ውጪ በበርካታ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል። ትኩሳት፣ ሳል፣ ማሽተት ማቆም አልያም ጣእም ማጣት በርካቶችን የማያከራክሩ ምልክቶች ሲሆኑ አሁን ላይ ደግሞ ዘጠኝ ተጨማሪ ምልክቶች እንዲጨመሩ ተደርጓል። እነዚህም ትንፋሽ ማጠር፣ ድካም፣ የሰውነት መላሸቅ፣ ራስ ምታት፣ የጉሮሮ ሕመም፣ ከአፍንጫ የሚወጣ ፈሳሽ [ንፍጥ]፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ ተቅማጥ እና አጠቃላይ የጤንነት ስሜት ማጣት ናቸው። ዩኬ ውስጥ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 4.9 ሚሊየን የደረሰ ሲሆን መንግስት በነጻ ሲያከናውነው የነበረው ምርመራም ባሳለፍነው ሳምንት ተጠናቋል። የዩኬ የጤና ደህንነት ኤጀንሲ እንደሚለው ሰዎች አሁንም ቢሆን በተቻላቸው መጠን ከቤታቸው ላለመውጣት መሞከርና ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸውንም ንክኪ መቀነስ አለባቸው። በተለይ ደግሞ እነዚህን ምልክቶች የሚያሳይ ሰው ምርመራ ማድረግና እራሱን ከሰዎች መለየት እንዳለበት ኤጀንሲው አሳስቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60992822 |
5sports
| ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? | በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ዱቤ ጅሎ ለኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ ነው የተባለውን ሽልማት ሊያገኙ ነው። የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (አይኤኤፍ) 'ቬተራን ፒን' የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሽልማት ዜና ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ከጥቂት ቀናት በፊት እንደደረሳቸው አቶ ዱቤ ለቢቢሲ ገልፀዋል። •"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ •በታላቁ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው ይህንን ሽልማት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊ አግኝቶት እንደማያውቅም አቶ ዱቤና ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ገልፀዋል። ሽልማቱ ከዚህ ቀደም አትሌት የነበሩና ለስፖርቱ ዕድገትና ልማት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም በፊት ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት ተሸልሟል። የአፍሪካው አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን መርጦ ወደ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመላክ የሽልማቱ ሂደት ይከናወናል። ሽልማቱ መስከረም ወር ላይ ዶሃ በሚዘጋጀው የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፒዮን በመስከረም ወር የሚሰጥ ይሆናል። •ታይላንዳዊው ቦክሰኛ በውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ ሽልማቱን ያገኙበት ምክንያት ሽልማቱ ዕውቅና መስጠት ነው የሚሉት አቶ ዱቤ "ከአስር አመታት በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት አስተዋፅኦ ላደረግኩት የሚበረከት ነው። "በወቅቱም ውጤታማ አፈፃፀሞች ላሳየሁባቸው እውቅና መስጠት ነው" ብለዋል። በሽልማቱ መደሰታቸውን ገልፀው የበለጠ ለስራ እንደሚያነሳሳቸው ይናገራሉ። "ከዚህም ቀደም ቬተራን (የአንጋፋነት) ፒን የሚባል ሽልማት የተሸለመ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ" የሚናገሩት አቶ ዱቤ ለአመታት የአትሌቶች ተወካይና ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆነው ማገልገላቸው ለዚህ እንዳበቃቸው ገልፀዋል። ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ጆን ሪድጌዎን የተላከላቸው ደብዳቤም 'ለረዥም ጊዜ ለሽልማት የሚገባ ስራ በአትሌቲክሱ ስለሰሩ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል' የሚል ነው። አቶ ስለሺ ብስራት በበኩላቸው "የተሸለሙት ፈጣን የሆነ ኮሚዩኒኬሽን ስላላቸው ነው" ብለዋል። "በጥሩ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ የተመረጠች ሲሆን" ይህንን ደግሞ የሚመሩት አቶ ዱቤ ጅሎ መሆናቸውን አቶ ስለሺ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሁለቱም ኃላፊዎች ሽልማቱ ትልቅ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ዱቤ በአሁኑ ወቅት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የአትሌቲክስ ጥናት ውድድርና የአትሌቲክስ ልማት ይመራሉ። አቶ ዱቤ ጅሎ ማናቸው? | ስለ አቶ ዱቤ ጅሎ ሽልማት ምን እናውቃለን? በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቴክኒካል ዳይሬክተርነት እያገለገሉ የሚገኙት አቶ ዱቤ ጅሎ ለኢትዮጵያዊ የመጀመሪያ ነው የተባለውን ሽልማት ሊያገኙ ነው። የአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (አይኤኤፍ) 'ቬተራን ፒን' የሚል ስያሜ ያለው ይህ ሽልማት ዜና ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ከጥቂት ቀናት በፊት እንደደረሳቸው አቶ ዱቤ ለቢቢሲ ገልፀዋል። •"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ •በታላቁ ሩጫ ላይ የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ላይ የአበረታች መድኃኒት ምርመራ ሊካሄድ ነው ይህንን ሽልማት ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያዊ አግኝቶት እንደማያውቅም አቶ ዱቤና ሌላ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተጠባባቂ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ብስራት ገልፀዋል። ሽልማቱ ከዚህ ቀደም አትሌት የነበሩና ለስፖርቱ ዕድገትና ልማት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የሚሰጥ ሲሆን ከዚህም በፊት ኬንያዊው አትሌት ፖል ቴርጋት ተሸልሟል። የአፍሪካው አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን መርጦ ወደ ዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በመላክ የሽልማቱ ሂደት ይከናወናል። ሽልማቱ መስከረም ወር ላይ ዶሃ በሚዘጋጀው የአለም አቀፍ አትሌቲክስ ሻምፒዮን በመስከረም ወር የሚሰጥ ይሆናል። •ታይላንዳዊው ቦክሰኛ በውድድር ሳቢያ ሕይወቱ አለፈ ሽልማቱን ያገኙበት ምክንያት ሽልማቱ ዕውቅና መስጠት ነው የሚሉት አቶ ዱቤ "ከአስር አመታት በላይ ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ እድገት አስተዋፅኦ ላደረግኩት የሚበረከት ነው። "በወቅቱም ውጤታማ አፈፃፀሞች ላሳየሁባቸው እውቅና መስጠት ነው" ብለዋል። በሽልማቱ መደሰታቸውን ገልፀው የበለጠ ለስራ እንደሚያነሳሳቸው ይናገራሉ። "ከዚህም ቀደም ቬተራን (የአንጋፋነት) ፒን የሚባል ሽልማት የተሸለመ ኢትዮጵያዊ እንደሌለ" የሚናገሩት አቶ ዱቤ ለአመታት የአትሌቶች ተወካይና ቴክኒካል ዳይሬክተር ሆነው ማገልገላቸው ለዚህ እንዳበቃቸው ገልፀዋል። ከአይኤኤፍ ፕሬዝዳንት ጆን ሪድጌዎን የተላከላቸው ደብዳቤም 'ለረዥም ጊዜ ለሽልማት የሚገባ ስራ በአትሌቲክሱ ስለሰሩ ሽልማቱ ተበርክቶላቸዋል' የሚል ነው። አቶ ስለሺ ብስራት በበኩላቸው "የተሸለሙት ፈጣን የሆነ ኮሚዩኒኬሽን ስላላቸው ነው" ብለዋል። "በጥሩ ዲፕሎማሲ ኢትዮጵያ የተመረጠች ሲሆን" ይህንን ደግሞ የሚመሩት አቶ ዱቤ ጅሎ መሆናቸውን አቶ ስለሺ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሁለቱም ኃላፊዎች ሽልማቱ ትልቅ እንደሆነ ይናገራሉ። አቶ ዱቤ በአሁኑ ወቅት በአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ውስጥ የአትሌቲክስ ጥናት ውድድርና የአትሌቲክስ ልማት ይመራሉ። አቶ ዱቤ ጅሎ ማናቸው? | https://www.bbc.com/amharic/news-49102031 |
2health
| በሳይንስ የበለፀገ የአሳማ ልብ ተገጥሞለት የነበረው ግለሰብ ሕይወቱ አለፈ | በሳይንሳዊ መንገድ የበለፀገ የአሳማ ልብ ቀዶ ጥገና የተደረገለት የዓለማች የመጀመሪያው ግለሰብ የተባለው ሰው ሕይወቱ አለፈ። ዴቪድ ቤኔት የልብ በሽተኛ ነበር። የአሳማ ልብ ከተገጠመለት በኋላ ለሁለት ወራት ቆይቶ ነው የሞተው። ግለሰቡ ጤናው መቃወስ የጀመረው ከጥቂት ቀናት በፊት እንደነበር ዶክተሩ ተናግረዋል። ዴቪድ በዶክተሮች ጥብቅ ክትትል ሲደርግለት ቆይቶ በፈረንጆቹ ማርች 8 ይህችን ዓለም ተሰናብቷል። ሰውዬው የመጀመሪያው የአሳማ ልብ በቀዶ ጥገና እንዲገጠምለት የፈቀደው ሂደቱ ለሞት ሊዳርገው እንደሚችል በመረዳት ነው። በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የጤና ማዕከል ያሉ ዶክተሮች ቀዶ ጥገናውን እንዲያደርጉ ከአሜሪካ መንግሥት ሰዎች ፈቃድ አግኝተዋል። ዴቪድ የሰው ልብ በቀዶ ጥገና ሊገጥምለት ስለማይችል ነው የአሳማ ልብ የሞከረው። ከቀዶ ጥገናው በፊት ለስድስት ሳምንታት በማሽን እርዳታ ነበር ሲተነፍስ የከረመው። ታኅሣሥ 29 ቀን ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ዓለም አጀብ ካለ በኋላ የቀሩትን ቀናት ከቤተሰቡና ወዳጆቹ ጋር አሳልፏል። ነገር ግን እየቆየ ጤናው ይቃወስ መጣ። ዶክተሮቹም ተደናገጡ። "በጣም ጀግና እና ልዩ የሆነ ሰው ነው። እስከ መጨረሻው ነው የተፋለመው" ይላል የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ባርትሊ ግሪፊዝ። የሰውዬው ልጅ የሆነው ዴቪድ ጁኒዬር የአባቱ ቀዶ ጥገና ለሌሎች የተስፋ ጭላንጭል እንዲሆን ይመኝ እንደነበር ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ዶክተር ግሪፊዝ ከዚህ ቀደም ቀዶ ጥገናው መሳካቱ የሚለገስ የሰውነት አካል አጥተው ለሚሞቱ ሰዎች ተስፋ ሰጭ ነው ብለው ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ ውጥ የሚለገስ የሰውነት አካል በማጣት በየቀኑ 17 ሰዎች ይሞታል። 100 ሺህ ገደማ ሰዎች ደግሞ መጠባበቂያ መዝገብ ላይ ስማቸው ሰፍሯል። የአሳማ ልብን ለሰው ልጅ በቀዶ ጥገና መግጠም የሚለው ሐሳብ ለረዥም ጊዜ ጥናት ሲደርግበትና ሲብላላ የቆየ ጉዳይ ነው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ኒው ዮርክ የሚገኙ ዶክተሮች የአሳማ ኩላሊት በተሳካ ሁኔታ ለሰው እንደገጠሙ ተናግረው ነበር። ምንም እንኳ ያኔ ይህ ቀዶ ጥገና አዲስ ነገር ቢሆንም ቀዶ ጥገና የተደረገለት ግለሰብ አእምሮው መሥራት ያቆመና የመዳን ተስፋው የመነመነ ነበር። ከዚያ በኋላ የተሰማው የአሳማ ልብ ቀዶ ጥገና በሕክምናው ዘርፍ ትልቁ ዜና ሆኖ ቆይቷል። የእንስሳትን አካል ለሰው መግጠምን አስቸጋሪ የሚያደርገው "ሃይፐርኪዩት ሪጄክሽን" የተባለ ሂደት ነው። ሰውነታችን ከሌላ ዝርያ አካል ሲገጥምለት ባዕድ ነገር እንደመጣበት አውቆ የተገጠመውን አካል በደቂቃዎች ውስጥ ይገድለዋል። ነገር ግን ለአሳማው የሰውነት አካል አስር ጊዜ በሳይንሳዊ መንገድ በልፅጎ ሰውነታችን እንዲቀበለው ማድረግ ተችሎ ነበር። ቢሆንም ይህንን ሰው ላይ ሞክሮ ሰውነት የተለገሰውን አካል ይገድለዋል አይገድለውም የሚለውን መጠባበቅ ለዶክተሮች በጣም አስጨናቂ ሂደር ነበር። የልብ ቀዶ ጥገናውን ያደረጉት ዶክተሮች ልቡን ከገጠሙ ከአንድ ወር በኋላም ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑን ተናግረው ነበር። ሰውዬው የሞተበት ትክክለኛው ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም። | በሳይንስ የበለፀገ የአሳማ ልብ ተገጥሞለት የነበረው ግለሰብ ሕይወቱ አለፈ በሳይንሳዊ መንገድ የበለፀገ የአሳማ ልብ ቀዶ ጥገና የተደረገለት የዓለማች የመጀመሪያው ግለሰብ የተባለው ሰው ሕይወቱ አለፈ። ዴቪድ ቤኔት የልብ በሽተኛ ነበር። የአሳማ ልብ ከተገጠመለት በኋላ ለሁለት ወራት ቆይቶ ነው የሞተው። ግለሰቡ ጤናው መቃወስ የጀመረው ከጥቂት ቀናት በፊት እንደነበር ዶክተሩ ተናግረዋል። ዴቪድ በዶክተሮች ጥብቅ ክትትል ሲደርግለት ቆይቶ በፈረንጆቹ ማርች 8 ይህችን ዓለም ተሰናብቷል። ሰውዬው የመጀመሪያው የአሳማ ልብ በቀዶ ጥገና እንዲገጠምለት የፈቀደው ሂደቱ ለሞት ሊዳርገው እንደሚችል በመረዳት ነው። በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ የጤና ማዕከል ያሉ ዶክተሮች ቀዶ ጥገናውን እንዲያደርጉ ከአሜሪካ መንግሥት ሰዎች ፈቃድ አግኝተዋል። ዴቪድ የሰው ልብ በቀዶ ጥገና ሊገጥምለት ስለማይችል ነው የአሳማ ልብ የሞከረው። ከቀዶ ጥገናው በፊት ለስድስት ሳምንታት በማሽን እርዳታ ነበር ሲተነፍስ የከረመው። ታኅሣሥ 29 ቀን ቀዶ ጥገና ተደርጎለት ዓለም አጀብ ካለ በኋላ የቀሩትን ቀናት ከቤተሰቡና ወዳጆቹ ጋር አሳልፏል። ነገር ግን እየቆየ ጤናው ይቃወስ መጣ። ዶክተሮቹም ተደናገጡ። "በጣም ጀግና እና ልዩ የሆነ ሰው ነው። እስከ መጨረሻው ነው የተፋለመው" ይላል የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ባርትሊ ግሪፊዝ። የሰውዬው ልጅ የሆነው ዴቪድ ጁኒዬር የአባቱ ቀዶ ጥገና ለሌሎች የተስፋ ጭላንጭል እንዲሆን ይመኝ እንደነበር ኤፒ የዜና ወኪል ዘግቧል። ዶክተር ግሪፊዝ ከዚህ ቀደም ቀዶ ጥገናው መሳካቱ የሚለገስ የሰውነት አካል አጥተው ለሚሞቱ ሰዎች ተስፋ ሰጭ ነው ብለው ነበር። ዩናይትድ ስቴትስ ውጥ የሚለገስ የሰውነት አካል በማጣት በየቀኑ 17 ሰዎች ይሞታል። 100 ሺህ ገደማ ሰዎች ደግሞ መጠባበቂያ መዝገብ ላይ ስማቸው ሰፍሯል። የአሳማ ልብን ለሰው ልጅ በቀዶ ጥገና መግጠም የሚለው ሐሳብ ለረዥም ጊዜ ጥናት ሲደርግበትና ሲብላላ የቆየ ጉዳይ ነው። ባለፈው ዓመት ጥቅምት ኒው ዮርክ የሚገኙ ዶክተሮች የአሳማ ኩላሊት በተሳካ ሁኔታ ለሰው እንደገጠሙ ተናግረው ነበር። ምንም እንኳ ያኔ ይህ ቀዶ ጥገና አዲስ ነገር ቢሆንም ቀዶ ጥገና የተደረገለት ግለሰብ አእምሮው መሥራት ያቆመና የመዳን ተስፋው የመነመነ ነበር። ከዚያ በኋላ የተሰማው የአሳማ ልብ ቀዶ ጥገና በሕክምናው ዘርፍ ትልቁ ዜና ሆኖ ቆይቷል። የእንስሳትን አካል ለሰው መግጠምን አስቸጋሪ የሚያደርገው "ሃይፐርኪዩት ሪጄክሽን" የተባለ ሂደት ነው። ሰውነታችን ከሌላ ዝርያ አካል ሲገጥምለት ባዕድ ነገር እንደመጣበት አውቆ የተገጠመውን አካል በደቂቃዎች ውስጥ ይገድለዋል። ነገር ግን ለአሳማው የሰውነት አካል አስር ጊዜ በሳይንሳዊ መንገድ በልፅጎ ሰውነታችን እንዲቀበለው ማድረግ ተችሎ ነበር። ቢሆንም ይህንን ሰው ላይ ሞክሮ ሰውነት የተለገሰውን አካል ይገድለዋል አይገድለውም የሚለውን መጠባበቅ ለዶክተሮች በጣም አስጨናቂ ሂደር ነበር። የልብ ቀዶ ጥገናውን ያደረጉት ዶክተሮች ልቡን ከገጠሙ ከአንድ ወር በኋላም ሁሉም ነገር ሰላም መሆኑን ተናግረው ነበር። ሰውዬው የሞተበት ትክክለኛው ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን ግልፅ አይደለም። | https://www.bbc.com/amharic/news-60687786 |
3politics
| ሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ በሕዳሴው ግድብ ድርድርና በሰሜኑ ጦርነት ላይ ምን ተፅዕኖ ይኖረዋል? | ሲንገዳገድ የቆየው የሱዳን የሽግግር አስተዳደር ለይቶለት በጦር ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶበት ከኃላፊነቱ ተወግዶ የሽግግሩ መንግሥት አባል የነበሩት ጄነራል አል ቡርሐን መሪነቱን ጠቅልለው ይዘዋል። የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም መፈንቅለ መንግሥቱን ያወገዙ ሲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማትም ለሱዳን የሚሰጡትን እርዳታ ከማገድ በተጨማሪ የመንግሥት ግልበጣውን ላደረጉት መሪዎች እውቅና ከመስጠት ተቆጥበዋል። ኦማር ሐሰን አልባሽር ከስልጣን መባረር በኋላ በአገሪቱ ጦር ሠራዊትና በሲቪል ፖለቲከኞች መካከል የነበረው ውዝግብ ሰላም ነስቷት የቆየችው ሱዳን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ሰላም የማግኘቷ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። የመንግሥት ግልበጣ ዜናው ከተነገረበት ሰዓት አንስቶ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር የሚፈልገው ሕዝቧ፣ የሙያ ማኅበራትና ፖለቲከኞች በየእለቱ አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩና በአገሪቱ የተከሰተው አከመረጋጋት በታላቁ ሕዳሴ ግድብና በድንበር ይገባኛል ምክንያት እየተወዛገበቻት ካለችው ኢትዮጵያ አንጻር ምን ውጤት ይኖረዋል? የሱዳንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩት ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን የሱዳኑ አልሲሲ ይሆናሉ የሚል ስጋት አለ። ጄነራሉ ከግብፁ መሪ አልሲሲ ጋርም መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል። መቀመጫቸውን ለንደን ያደረጉት የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አጥኚ አብዱራህማን ሰኢድ አቡሃሽም የጄነራል አል ቡርሐን የሱዳን መንግሥትን ሥልጣን መጠቅለል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይናገራሉ። "ባለፉት ሁለት ዓመታት የአልቡርሐን መንግሥት ከግብፅ ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርሞ በአባይ ጉዳይ ላይ አንድ ዓይነት ፖሊሲ ሲያራምዱ ቆይተዋል" ይላሉ አቡሃሽም። በዚህም የተነሳ የድንበር ውዝግቦችን እያስነሱ ኢትዮጵያን ሲተናኮሱና ወደ ጦርነት እንድትገባ ሲገፋፉ መቆየታቸውን አጥኚው ጠቅሰዋል። "ይህም በኢትዮጵያ መንግሥት ትዕግስት ነው የታለፈው" ይላሉ። አቡሃሽም እንደሚሉት የሱዳን መንግሥት ሲቪል አባላት ጄነራል አል ቡርሐን በሚያደርጓቸው ትንኮሳዎች አይስማሙም ነበር። ሱዳናውያንም ቢሆኑ ኢትዮጵያን እንደ ባለውለታና ወንድም ሕዝብ ስለሚያዩ ውዝግቡን አይደግፉትም። በመሆኑም ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረና በአገሪቱ ዲሞክራሲ ከጠፋ ጄነራል አልቡርሐን ለሥልጣናቸው ሲሉ ወደ አሉታዊ አማራጮች ሊያዘነብሉ እንደሚችሉ አቡሃሽም አስረድተዋል። "ይህ ከሆነም በቀጥታ ወደ ጦርነት ሊያመራ ስለሚችል ኢትዮጵያን ያሰጋታል" በማለት፤ ይህ ካልሆነም አልቡርሐን ከግብፅ ጋር በሚኖራቸው ቅርበት የተነሳ ኢትዮጵያን ለጦርነት ሊገፋፉ እንደሚችሉ ይናገራሉ። የሱዳኑ ቀውስ በሰሜኑ ጦርነት ላይ የሚኖረው አንድምታ እንደ ፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽም ከሆነ የአልቡርሐን ኃይል አይሎ በቀጥታ ወደ ጦርነት ካልገባ በስተቀር የሱዳን ቀውስ በሰሜኑ ጦርነት ላይ ብዙ ለውጥ አያመጣም። ምክንያታቸው የሱዳን ኃይል የህወሓት ኃይሎችን ለመደገፍ ሲሞክር በመቆየቱ አዲስ ነገር አይፈጠርም የሚል ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን በሚገኝ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ የህወሓት ኃይሎች እንደተደራጁ እና ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክሩ እንደቆዩ ክስ ሲያቀርብ እንደነበርም ተንታኙ አስታውሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሱዳን መንግሥታት ስትራቴጂያዊ የሆነ አቋም ስለሌለው በኢትዮጵያ ላይ ተቃዋሚ ኃይሎች በሚመጡበት ጊዜ እንደየ ሁኔታው አቋማቸውን ሊለዋውጡ እንደሚችሉ አቡሃሺም ያስረዳሉ። በመሆኑም "ህወሓትን እንደ አንድ ስትራቴጂያዊ ተባባሪ አድርጎ ሲሸነፍ የሚያግዘው፤ ሲወድቅ የሚያነሳው ሊሆንለት የሚችል አይመስለኝም" ብለዋል አጥኚው። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ግንባታውና በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ መካከል የሚካሄደው ድርድር አስር ዓመታትን ቢያስቆጥርም ከስምምነት ሳይደርሱ አስካሁን ቆይቷል። ጉዳዩ ወደ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ድረስ አምርቶም ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ ምክር ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ በሕዳሴው ግድብ ላይ መክሮ ጉዳዩ በአፍሪካ ሕብረት አመቻችነት መፍትሔ እንዲያገኝ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ድርድሩ ሳይጀመር በሱዳን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶ የአገሪቱ ካቢኔ መበተኑ የሕዳሴው ግድብ ድርድርን ወዴት ይወስደው ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል። የምሥራቅ ናይል ቴክኒካዊ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ በኢትዮጵያ የተፈጠረው ሁኔታ፤ በተለይ ደግሞ ሱዳን ውስጥ የተፈጠረው ቀውስ ተፅእኖ በመፍጠሩ ድርድሩ እስካሁን አለመጀመሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፀጥታው ምክር ቤት በሁለተኛው ስብሰባው አገራቱ በተወሰነ የጊዜ ገደብ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ውሳኔ አስቀምጦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ይህንን ግን ማድረግ አልተቻለም ብለዋል። ድርድሩን ለማመቻቸት ኃላፊነት የወሰደው የአፍሪካ ሕብረትም ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እስክትመለስ ድረስ ከአባልነት ማገዱን አስታውቋል። ጄነራል ቡርሐን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ካቢኔውን ሲበትኑ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ላይ የሱዳን ተደራዳሪ የሚባሉት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውሃና መስኖ ሚኒስትርም እንቅስቃሴያቸው ታግዷል። በመሆኑም "የተደራዳሪዎቹ የወደፊት እጣ ፋንታ ባልታወቀበት ሁኔታ ስለድርድር ማውራት አስቸጋሪ ነው" ይላሉ አቶ ፈቅ አሕመድ። "የፖሊሲ ለውጦችም ይኖራሉ፤ ሱዳን በአሁኑ ሰዓት የምትከተለው ፖሊሲም ምን እንደሆነ አልታወቀም። የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ ላይም ሱዳን አትሳተፍም። በመሆኑም የሕዳሴው ግድብ ድርድር ተንጠልጥሎ የሚቆይ ይመስለኛል" ብለዋል። የሱዳን ወታደራዊ ኃይልና የግብፅ መንግሥት ግንኙነት በሕዳሴው ግድብ ላይ አልባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ወታደራዊውና ሲቪል መሪዎች ሥልጣን ተጋርተው አገሪቱን ሲመሩ ቢቆዩም በይበልጥ ሥልጣኑን የያዘው ወታደራዊው ኃይል እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ወታደራዊው ኃይል ከካይሮ ጋር እንዳበረ ተናግረዋል። በመሆኑም ወታደራዊው መንግሥት ሥልጣን ላይ ቢቆይም ባይቆይም እስከ አሁን የነበራቸውን አቋም ይለውጣል የሚል እምነት የላቸውም። "ብቸኛው አማራጭ ድርድር በመሆኑም ድርድሩ ይቀጥላል። ይህንንም እነርሱም ጠንቅቀው ያውቁታል" ብለዋል። አቶ ፈቅ አሕመድ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ አሜሪካ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ላይ እየፈጠሩ ያሉት ጫና ውጤት እያሳየ መሆኑን ይናገራሉ። በቁጥጥር ስር የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውንም ለዚህ እንደ አብነት ጠቅሰዋል። ጫናው ከበረታበት ወታደራዊ ኃይል የሲቪል መንግሥቱን ወደ ሥራው ይመልሳል አሊያም በአጭር ጊዜ ምርጫ አካሂዶ ሌላ የሲቪል አስተዳደር ያቋቁማል የሚል ግምት እንዳለ የተናገሩት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ይህ ከሆነ ቶሎ ወደ ድርድር የመመለስ ሁኔታ ይኖራል ብለዋል። ካልሆነስ? "ይህ የማይሆን ከሆነ አገራቱ ሌላ አማራጭ የሚፈልጉ ይመስለኛል" ይላሉ አቶ ፈቅ አሕመድ። የሱዳን መንግሥት ተዳራዳሪዎቹን [የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውሃና መስኖ ሚኒስትር] ወደ ሥራ መልሶ ወደ ድርድሩን እንዲመለሱ ማድረግ ባለሙያው ያስቀመጡት አንደኛው አማራጭ ነው። ከዚህም ባሻገር ሌላ ጊዜያዊ ተደራዳሪ በመሰየም ሦስቱ አገራት የሚደራደሩበትን ሁኔታ መፍጠር እንደሚቻልም ተናግረዋል። በወሰን ተሻጋሪ ወንዞች የሚወዛገቡ አገራት ድርድር የሦስተኛ አገር ጣልቃ ገብነት ባይደገፍም፤ የተሻለ፣ የተለየ ፍላጎት እና ወገንተኝነት የሌለው ሦስተኛ አካል በማስገባት መደራደርም ሌላኛው አማራጭ ነው ብለዋል። አቶ ፈቅ አሕመድ እንደሚሉት የአፍሪካ ሕብረት በድርድሩ አልቀጥልም ቢል እንኳን አገራቱ ፍላጎት ካላቸው ተነጋግረው ልዩነቶቻቸውን መፍታት ይችላሉ። ግብፅ ከሕዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አማራጮችን ስትሞክር እንደቆየች የሚናገሩት አቶ ፈቅ አሕመድ "ሙርሲ ፕሬዝዳንት እያሉ ለውዝግቡ ስድስት የመፍትሔ ሃሳቦችን አቅርበው ነበር። ከስድስቱ ተግባራዊ ያልተደረገው 'ቀጥተኛ ጦርነት መክፈት' የሚለው ብቻ ነው" ይላሉ። ይሁን እንጂ ወደ ቀጥታ ጦርነት መግባት ራሳቸውንም ሰለባ ስለሚያደርጋቸው አሁን ባሉበት ይቀጥላሉ የሚል እምነት እንዳላቸው አቶ ፈቅ አሕመድ አክለዋል። የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽምም ይህንኑ ሃሳብ ይጋሩታል። "የአባይ ጉዳይ በይበልጥ ሊፈታ የሚችለው በኢትዮጵያና በግብፅ ነው" ያሉት አቡሃሽም፤ ግብፆችም ሆኑ ሱዳኖች የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ኃይሎች ለመደገፍ ወይም ላለመደገፍ የሚወስኑት ለአባይ ሲሉ ነው ብለዋል። ነገር ግን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ80 በመቶ በላይ ተገንብቶ ያለቀ በመሆኑና የሚቀለበስ ጉዳይ ባለመሆኑ በተለይ ግብፆቹ ምን ዓይነት መፍትሔ ነው የሚፈልጉት የሚለው ጉዳይ እስካሁን ግልጽ አለመሆኑን አቡሃሽም ተናግረዋል። "ግብፅ ግድቡን አፈርሳለሁ ብትል እንኳን በራሷ ላይ ይዞት የሚመጣው መዘዝ ከባድ በመሆኑ፤ ይህም ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም" ብለዋል። በኢትዮጵያ በኩል በድርድር መቀጠሉ ጥሩ ነው የሚሉት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስጠበቅ የሌሎችንም ጥቅም ሳትነካ፤ በአሜሪካ ተጀምሮ የነበረውን የስምምነት መርሆዎችና ይዘቶችን በመተው በአዲስ ስልት ድርድር በማካሄድ ወደ ተሻለ ስምምነት መምጣት እንደምትችል ተናግረዋል። ቀጠናው ውስብስብ ችግር ውስጥ ይገባ ይሆን? በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የሰሜኑ ጦርነት፣ የአልፋሽቃ ድንበር ውዝግብ፣ የግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ውዝግብ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ፍላጎቶች፣ የአረብ አገራት ሚና ቀጠናውን ወደ ውስብስብ ችግር ያመሩታል የሚል ስጋት አለ። የፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽም ግን ይህ የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ወይም በወታደራዊ መንገድ በቶሎ መጠናቀቁ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአካባቢው ጠቃሚ ነው ይላሉ። "የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነቱን የውስጥ ጉዳዩ አድርጎ ሊጨርሰው እየሞከረ ነው" የሚሉት ተንታኙ ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ አለመጠናቀቁ ለሌሎች አገራት ጣልቃ መግባት በር ሊከፍት ይችላል ብለው ያምናሉ። ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ እየተተራመሰች የአባይና የግድቡ ጉዳዮችን የሚያዘናጉ እና የሚያደናቅፉ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ለግብፆች አመቺ ይሆናል ይላሉ። በሌላ በኩል ኤርትራ ህወሓትን እንደ ጠላት እንደምታይ የጠቀሱት ተንታኙ፤ የህወሓት ጥንካሬ እያየለ ከሄደ ኤርትራ በቀጥታ ጦርነቱ ውስጥ ልትገባ የምትችልበት ዕድል እንዳለ ይጠቅሳሉ። | ሱዳን መፈንቅለ መንግሥት፡ የሱዳን ፖለቲካዊ ቀውስ በሕዳሴው ግድብ ድርድርና በሰሜኑ ጦርነት ላይ ምን ተፅዕኖ ይኖረዋል? ሲንገዳገድ የቆየው የሱዳን የሽግግር አስተዳደር ለይቶለት በጦር ሠራዊቱ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶበት ከኃላፊነቱ ተወግዶ የሽግግሩ መንግሥት አባል የነበሩት ጄነራል አል ቡርሐን መሪነቱን ጠቅልለው ይዘዋል። የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም መፈንቅለ መንግሥቱን ያወገዙ ሲሆን ዓለም አቀፍ ተቋማትም ለሱዳን የሚሰጡትን እርዳታ ከማገድ በተጨማሪ የመንግሥት ግልበጣውን ላደረጉት መሪዎች እውቅና ከመስጠት ተቆጥበዋል። ኦማር ሐሰን አልባሽር ከስልጣን መባረር በኋላ በአገሪቱ ጦር ሠራዊትና በሲቪል ፖለቲከኞች መካከል የነበረው ውዝግብ ሰላም ነስቷት የቆየችው ሱዳን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ሰላም የማግኘቷ ነገር አጠራጣሪ ሆኗል። የመንግሥት ግልበጣ ዜናው ከተነገረበት ሰዓት አንስቶ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንድትሸጋገር የሚፈልገው ሕዝቧ፣ የሙያ ማኅበራትና ፖለቲከኞች በየእለቱ አደባባይ በመውጣት ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው። በሱዳን ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣን መቆጣጠሩና በአገሪቱ የተከሰተው አከመረጋጋት በታላቁ ሕዳሴ ግድብና በድንበር ይገባኛል ምክንያት እየተወዛገበቻት ካለችው ኢትዮጵያ አንጻር ምን ውጤት ይኖረዋል? የሱዳንን መፈንቅለ መንግሥት የመሩት ጄነራል አብደል ፋታህ አል ቡርሐን የሱዳኑ አልሲሲ ይሆናሉ የሚል ስጋት አለ። ጄነራሉ ከግብፁ መሪ አልሲሲ ጋርም መልካም ግንኙነት እንዳላቸው ይነገራል። መቀመጫቸውን ለንደን ያደረጉት የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አጥኚ አብዱራህማን ሰኢድ አቡሃሽም የጄነራል አል ቡርሐን የሱዳን መንግሥትን ሥልጣን መጠቅለል በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ይናገራሉ። "ባለፉት ሁለት ዓመታት የአልቡርሐን መንግሥት ከግብፅ ጋር የጋራ ስምምነት ተፈራርሞ በአባይ ጉዳይ ላይ አንድ ዓይነት ፖሊሲ ሲያራምዱ ቆይተዋል" ይላሉ አቡሃሽም። በዚህም የተነሳ የድንበር ውዝግቦችን እያስነሱ ኢትዮጵያን ሲተናኮሱና ወደ ጦርነት እንድትገባ ሲገፋፉ መቆየታቸውን አጥኚው ጠቅሰዋል። "ይህም በኢትዮጵያ መንግሥት ትዕግስት ነው የታለፈው" ይላሉ። አቡሃሽም እንደሚሉት የሱዳን መንግሥት ሲቪል አባላት ጄነራል አል ቡርሐን በሚያደርጓቸው ትንኮሳዎች አይስማሙም ነበር። ሱዳናውያንም ቢሆኑ ኢትዮጵያን እንደ ባለውለታና ወንድም ሕዝብ ስለሚያዩ ውዝግቡን አይደግፉትም። በመሆኑም ወታደራዊ ኃይሉ ሥልጣኑን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረና በአገሪቱ ዲሞክራሲ ከጠፋ ጄነራል አልቡርሐን ለሥልጣናቸው ሲሉ ወደ አሉታዊ አማራጮች ሊያዘነብሉ እንደሚችሉ አቡሃሽም አስረድተዋል። "ይህ ከሆነም በቀጥታ ወደ ጦርነት ሊያመራ ስለሚችል ኢትዮጵያን ያሰጋታል" በማለት፤ ይህ ካልሆነም አልቡርሐን ከግብፅ ጋር በሚኖራቸው ቅርበት የተነሳ ኢትዮጵያን ለጦርነት ሊገፋፉ እንደሚችሉ ይናገራሉ። የሱዳኑ ቀውስ በሰሜኑ ጦርነት ላይ የሚኖረው አንድምታ እንደ ፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽም ከሆነ የአልቡርሐን ኃይል አይሎ በቀጥታ ወደ ጦርነት ካልገባ በስተቀር የሱዳን ቀውስ በሰሜኑ ጦርነት ላይ ብዙ ለውጥ አያመጣም። ምክንያታቸው የሱዳን ኃይል የህወሓት ኃይሎችን ለመደገፍ ሲሞክር በመቆየቱ አዲስ ነገር አይፈጠርም የሚል ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት ሱዳን በሚገኝ ስደተኞች ካምፕ ውስጥ ወደ 20 ሺህ የሚጠጉ የህወሓት ኃይሎች እንደተደራጁ እና ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት ሲሞክሩ እንደቆዩ ክስ ሲያቀርብ እንደነበርም ተንታኙ አስታውሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሱዳን መንግሥታት ስትራቴጂያዊ የሆነ አቋም ስለሌለው በኢትዮጵያ ላይ ተቃዋሚ ኃይሎች በሚመጡበት ጊዜ እንደየ ሁኔታው አቋማቸውን ሊለዋውጡ እንደሚችሉ አቡሃሺም ያስረዳሉ። በመሆኑም "ህወሓትን እንደ አንድ ስትራቴጂያዊ ተባባሪ አድርጎ ሲሸነፍ የሚያግዘው፤ ሲወድቅ የሚያነሳው ሊሆንለት የሚችል አይመስለኝም" ብለዋል አጥኚው። የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ግንባታውና በኢትዮጵያ፣ በሱዳንና በግብፅ መካከል የሚካሄደው ድርድር አስር ዓመታትን ቢያስቆጥርም ከስምምነት ሳይደርሱ አስካሁን ቆይቷል። ጉዳዩ ወደ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ድረስ አምርቶም ባለፈው ሐምሌ ወር ላይ ምክር ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ በሕዳሴው ግድብ ላይ መክሮ ጉዳዩ በአፍሪካ ሕብረት አመቻችነት መፍትሔ እንዲያገኝ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ድርድሩ ሳይጀመር በሱዳን ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ተካሂዶ የአገሪቱ ካቢኔ መበተኑ የሕዳሴው ግድብ ድርድርን ወዴት ይወስደው ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ሆኗል። የምሥራቅ ናይል ቴክኒካዊ አህጉራዊ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ፈቅ አሕመድ ነጋሽ በኢትዮጵያ የተፈጠረው ሁኔታ፤ በተለይ ደግሞ ሱዳን ውስጥ የተፈጠረው ቀውስ ተፅእኖ በመፍጠሩ ድርድሩ እስካሁን አለመጀመሩን ለቢቢሲ ገልጸዋል። የፀጥታው ምክር ቤት በሁለተኛው ስብሰባው አገራቱ በተወሰነ የጊዜ ገደብ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ እንዳለባቸው ውሳኔ አስቀምጦ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ይህንን ግን ማድረግ አልተቻለም ብለዋል። ድርድሩን ለማመቻቸት ኃላፊነት የወሰደው የአፍሪካ ሕብረትም ሱዳን ወደ ሲቪል አስተዳደር እስክትመለስ ድረስ ከአባልነት ማገዱን አስታውቋል። ጄነራል ቡርሐን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ ካቢኔውን ሲበትኑ በሕዳሴው ግድብ ጉዳይ ላይ የሱዳን ተደራዳሪ የሚባሉት የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውሃና መስኖ ሚኒስትርም እንቅስቃሴያቸው ታግዷል። በመሆኑም "የተደራዳሪዎቹ የወደፊት እጣ ፋንታ ባልታወቀበት ሁኔታ ስለድርድር ማውራት አስቸጋሪ ነው" ይላሉ አቶ ፈቅ አሕመድ። "የፖሊሲ ለውጦችም ይኖራሉ፤ ሱዳን በአሁኑ ሰዓት የምትከተለው ፖሊሲም ምን እንደሆነ አልታወቀም። የአፍሪካ ሕብረት ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ ላይም ሱዳን አትሳተፍም። በመሆኑም የሕዳሴው ግድብ ድርድር ተንጠልጥሎ የሚቆይ ይመስለኛል" ብለዋል። የሱዳን ወታደራዊ ኃይልና የግብፅ መንግሥት ግንኙነት በሕዳሴው ግድብ ላይ አልባሽር ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ ወታደራዊውና ሲቪል መሪዎች ሥልጣን ተጋርተው አገሪቱን ሲመሩ ቢቆዩም በይበልጥ ሥልጣኑን የያዘው ወታደራዊው ኃይል እንደነበር ያስታወሱት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ወታደራዊው ኃይል ከካይሮ ጋር እንዳበረ ተናግረዋል። በመሆኑም ወታደራዊው መንግሥት ሥልጣን ላይ ቢቆይም ባይቆይም እስከ አሁን የነበራቸውን አቋም ይለውጣል የሚል እምነት የላቸውም። "ብቸኛው አማራጭ ድርድር በመሆኑም ድርድሩ ይቀጥላል። ይህንንም እነርሱም ጠንቅቀው ያውቁታል" ብለዋል። አቶ ፈቅ አሕመድ የዓለም ባንክ፣ የአፍሪካ ሕብረት፣ የአውሮፓ ሕብረት፣ አሜሪካ እና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሱዳን ወታደራዊ መንግሥት ላይ እየፈጠሩ ያሉት ጫና ውጤት እያሳየ መሆኑን ይናገራሉ። በቁጥጥር ስር የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ ወደ ቤታቸው መመለሳቸውንም ለዚህ እንደ አብነት ጠቅሰዋል። ጫናው ከበረታበት ወታደራዊ ኃይል የሲቪል መንግሥቱን ወደ ሥራው ይመልሳል አሊያም በአጭር ጊዜ ምርጫ አካሂዶ ሌላ የሲቪል አስተዳደር ያቋቁማል የሚል ግምት እንዳለ የተናገሩት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ይህ ከሆነ ቶሎ ወደ ድርድር የመመለስ ሁኔታ ይኖራል ብለዋል። ካልሆነስ? "ይህ የማይሆን ከሆነ አገራቱ ሌላ አማራጭ የሚፈልጉ ይመስለኛል" ይላሉ አቶ ፈቅ አሕመድ። የሱዳን መንግሥት ተዳራዳሪዎቹን [የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የውሃና መስኖ ሚኒስትር] ወደ ሥራ መልሶ ወደ ድርድሩን እንዲመለሱ ማድረግ ባለሙያው ያስቀመጡት አንደኛው አማራጭ ነው። ከዚህም ባሻገር ሌላ ጊዜያዊ ተደራዳሪ በመሰየም ሦስቱ አገራት የሚደራደሩበትን ሁኔታ መፍጠር እንደሚቻልም ተናግረዋል። በወሰን ተሻጋሪ ወንዞች የሚወዛገቡ አገራት ድርድር የሦስተኛ አገር ጣልቃ ገብነት ባይደገፍም፤ የተሻለ፣ የተለየ ፍላጎት እና ወገንተኝነት የሌለው ሦስተኛ አካል በማስገባት መደራደርም ሌላኛው አማራጭ ነው ብለዋል። አቶ ፈቅ አሕመድ እንደሚሉት የአፍሪካ ሕብረት በድርድሩ አልቀጥልም ቢል እንኳን አገራቱ ፍላጎት ካላቸው ተነጋግረው ልዩነቶቻቸውን መፍታት ይችላሉ። ግብፅ ከሕዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ የተለያዩ አማራጮችን ስትሞክር እንደቆየች የሚናገሩት አቶ ፈቅ አሕመድ "ሙርሲ ፕሬዝዳንት እያሉ ለውዝግቡ ስድስት የመፍትሔ ሃሳቦችን አቅርበው ነበር። ከስድስቱ ተግባራዊ ያልተደረገው 'ቀጥተኛ ጦርነት መክፈት' የሚለው ብቻ ነው" ይላሉ። ይሁን እንጂ ወደ ቀጥታ ጦርነት መግባት ራሳቸውንም ሰለባ ስለሚያደርጋቸው አሁን ባሉበት ይቀጥላሉ የሚል እምነት እንዳላቸው አቶ ፈቅ አሕመድ አክለዋል። የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽምም ይህንኑ ሃሳብ ይጋሩታል። "የአባይ ጉዳይ በይበልጥ ሊፈታ የሚችለው በኢትዮጵያና በግብፅ ነው" ያሉት አቡሃሽም፤ ግብፆችም ሆኑ ሱዳኖች የኢትዮጵያን ተቃዋሚ ኃይሎች ለመደገፍ ወይም ላለመደገፍ የሚወስኑት ለአባይ ሲሉ ነው ብለዋል። ነገር ግን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ከ80 በመቶ በላይ ተገንብቶ ያለቀ በመሆኑና የሚቀለበስ ጉዳይ ባለመሆኑ በተለይ ግብፆቹ ምን ዓይነት መፍትሔ ነው የሚፈልጉት የሚለው ጉዳይ እስካሁን ግልጽ አለመሆኑን አቡሃሽም ተናግረዋል። "ግብፅ ግድቡን አፈርሳለሁ ብትል እንኳን በራሷ ላይ ይዞት የሚመጣው መዘዝ ከባድ በመሆኑ፤ ይህም ዘላቂ መፍትሄ አይሆንም" ብለዋል። በኢትዮጵያ በኩል በድርድር መቀጠሉ ጥሩ ነው የሚሉት አቶ ፈቅ አሕመድ፤ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስጠበቅ የሌሎችንም ጥቅም ሳትነካ፤ በአሜሪካ ተጀምሮ የነበረውን የስምምነት መርሆዎችና ይዘቶችን በመተው በአዲስ ስልት ድርድር በማካሄድ ወደ ተሻለ ስምምነት መምጣት እንደምትችል ተናግረዋል። ቀጠናው ውስብስብ ችግር ውስጥ ይገባ ይሆን? በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የሰሜኑ ጦርነት፣ የአልፋሽቃ ድንበር ውዝግብ፣ የግብፅ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ውዝግብ፣ የኢትዮጵያና የኤርትራ ፍላጎቶች፣ የአረብ አገራት ሚና ቀጠናውን ወደ ውስብስብ ችግር ያመሩታል የሚል ስጋት አለ። የፖለቲካ ተንታኙ አቡሃሽም ግን ይህ የሰሜኑ ጦርነት በሰላም ወይም በወታደራዊ መንገድ በቶሎ መጠናቀቁ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአካባቢው ጠቃሚ ነው ይላሉ። "የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርነቱን የውስጥ ጉዳዩ አድርጎ ሊጨርሰው እየሞከረ ነው" የሚሉት ተንታኙ ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ አለመጠናቀቁ ለሌሎች አገራት ጣልቃ መግባት በር ሊከፍት ይችላል ብለው ያምናሉ። ይሁን እንጅ ኢትዮጵያ በውስጥ ጉዳይዋ እየተተራመሰች የአባይና የግድቡ ጉዳዮችን የሚያዘናጉ እና የሚያደናቅፉ ሁኔታዎች ከተፈጠሩ ለግብፆች አመቺ ይሆናል ይላሉ። በሌላ በኩል ኤርትራ ህወሓትን እንደ ጠላት እንደምታይ የጠቀሱት ተንታኙ፤ የህወሓት ጥንካሬ እያየለ ከሄደ ኤርትራ በቀጥታ ጦርነቱ ውስጥ ልትገባ የምትችልበት ዕድል እንዳለ ይጠቅሳሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-59066437 |
0business
| በኢትዮጵያ ለሚታየው የነዳጅ እጥረት ምክንያቱ ምንድን ነው? | በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት ለሰዓታት ረጅም ሰልፍ ለመጠበቅ ከተገደዱ ቀናት ተቆጥረዋል። በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ተከትሎ መንግሥት ለዓመታት ለነዳጅ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ቀስ በቀስ ለማቋረጥ ወስኖ ተግባራዊ ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። ኢትዮጵያ ለነዳጅ የምታደርገው ድጎማ ነዳጅ ለሁሉም ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ አስችሎ ቆይቷል፤ ነገር ግን ይህ ድጎማ ከዚህ በኋላ ዘላቂ እንደማይሆን በነዳጅና ፔትሮሊየም ባለሥልጣን ውስጥ የሚሰሩ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ስታንዳርድ ጥናት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ እንደሚሉት መንግሥት ለነዳጅ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪ ያደርጋል። በግንቦትና በሰኔ መካከል ባሉ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ብቻ መንግሥት 16 ቢሊዮን ብር ወይም 268 ሚሊዮን ዶላር ነዳጅን ለመደጎም ሲል ወጪ ማድረጉን አቶ ለሜሳ ተናግረዋል። ከዋጋ ጭማሪው ባሻገር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚከሰቱት ግጭቶች የትራንስፖርት መስመሮችን በማስተጓጎል በቅርብ ወራት ውስጥ የነዳጅ አቅርቦት ችግር በአገሪቱ ውስጥ እንዲከሰት ምክንያት እየሆኑ ነው። ነገር ግን አሁን ለተከሰተው የነዳጅ እጥረት መባባስ ከጂቡቲ ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን ነዳጅ መድረስ ካለባቸው ቦታ ውጪ መውሰድና የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ትራንስፖርት መዘግየት ምክንያት እንደሆነ አቶ ለሜሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንዳንድ አከፋፋዮችም መንግሥት በተወሰነ ደረጃ ድጎማውን በማንሳት አዲስ የነዳጅ ታሪፍ ይፋ በሚያደርግበት ጊዜ በተጨማሪ ዋጋ ለመሸጥ ሲሉ ነዳጅ ያከማቻሉ ሲሉም ባለሥልጣኑ ይከሳሉ። ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ነዳጅ ጭነው ተደብቀው የነበሩ 15 ቦቴዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር። የተሽከርካሪዎችን መዘግየት ለማስቀረትም ከአዋሽ ጀምሮ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች መመደባቸው ተገልጿል። አንዳንድ ሪፖርቶች ወደ አገሪቱ ከሚገባው ነዳጅ ውስጥ የተወሰኑት ቦቴዎች በጦርነት ምክንያት ዝግ ወደ ሆነችው ትግራይ ክልል እንዲገባ እንደሚደረግ ቢያመለክቱም፣ ባለሥልጣኑ ግን ይህንን የሚያረጋግጥ በቂ መረጃ እንደሌለ ይናገራሉ። “እስካሁን የምናውቀው አንዳንድ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ይዘው ከሚጠበቁበት ቦታ ላይ አለመድረሳቸውን ነው” ሲሉ አቶ ቱሉ ስላልታወቁት ቦቴዎች ተናግረዋል። ስለዚህም በአገሪቱ ውስጥ ለሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት፣ በተለያዩ ጊዜያት በነዳጅ ማመላለሻ መስመሮች አካባቢ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች፣ ተሽከርካሪዎች አቅርቦታቸውን በሚፈለጉበት ቦታ ዘግይተው ማድረስ፣ ነዳጅ መድረስ ካለባቸው ቦታዎች ውጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች መሸጋገር እንዲሁም አከፋፋዮች ነዳጅን ደብቆ ማስቀመጥ ምክንያት ናቸው ብለዋል። በተለይ ነዳጅ ለመቅዳት ተሽከርካሪዎች የታሪፍ ክለሳ ከሚደረግባቸው የወራት መጨረሻ ቀናት ቀደም ብሎ መኪናቸውን ሙሉ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ሰልፎች እንዲበራከቱ ያደርጋሉ። ከቀጣዩ ሐምሌ ወር ጀምሮ መንግሥት በነዳጅ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ለማንሳት ለሚወስደው እርምጃ የመጀመሪያው ደረጃ በመሆኑ ካሉት ተደራራቢ ችግሮች በተጨማሪ የነዳጅ ሰልፉን እንዳባበሰው አሽከርካሪዎች ይናገራሉ። የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች የነዳጅ ድጎማ መነሳቱ ላይ የተለያየ ሃሳቦችን ያንጸባርቃሉ። አንዳንዶች የተቀናጀ ቁጥጥር እና በቂ ግንዛቤ ለሕብረተሰቡ ከደረሰ የከፋ ጫና አያስከትልም ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ባለው የኑሮ ውድነት ላይ መሠረታዊ የሆነውን የነዳጅ ድጎማን ማንሳት “ እየነደደ ባለ እሳት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው” ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመውታል። | በኢትዮጵያ ለሚታየው የነዳጅ እጥረት ምክንያቱ ምንድን ነው? በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ አሽከርካሪዎች ነዳጅ ለመቅዳት ለሰዓታት ረጅም ሰልፍ ለመጠበቅ ከተገደዱ ቀናት ተቆጥረዋል። በዓለም ገበያ የነዳጅ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩን ተከትሎ መንግሥት ለዓመታት ለነዳጅ ሲያደርግ የነበረውን ድጎማ ቀስ በቀስ ለማቋረጥ ወስኖ ተግባራዊ ለማድረግ እየተዘጋጀ ነው። ኢትዮጵያ ለነዳጅ የምታደርገው ድጎማ ነዳጅ ለሁሉም ተጠቃሚዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ አስችሎ ቆይቷል፤ ነገር ግን ይህ ድጎማ ከዚህ በኋላ ዘላቂ እንደማይሆን በነዳጅና ፔትሮሊየም ባለሥልጣን ውስጥ የሚሰሩ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናግረዋል። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ስታንዳርድ ጥናት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ እንደሚሉት መንግሥት ለነዳጅ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪ ያደርጋል። በግንቦትና በሰኔ መካከል ባሉ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ብቻ መንግሥት 16 ቢሊዮን ብር ወይም 268 ሚሊዮን ዶላር ነዳጅን ለመደጎም ሲል ወጪ ማድረጉን አቶ ለሜሳ ተናግረዋል። ከዋጋ ጭማሪው ባሻገር በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚከሰቱት ግጭቶች የትራንስፖርት መስመሮችን በማስተጓጎል በቅርብ ወራት ውስጥ የነዳጅ አቅርቦት ችግር በአገሪቱ ውስጥ እንዲከሰት ምክንያት እየሆኑ ነው። ነገር ግን አሁን ለተከሰተው የነዳጅ እጥረት መባባስ ከጂቡቲ ወደ አገር ውስጥ የሚገባውን ነዳጅ መድረስ ካለባቸው ቦታ ውጪ መውሰድና የነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ትራንስፖርት መዘግየት ምክንያት እንደሆነ አቶ ለሜሳ ለቢቢሲ ተናግረዋል። አንዳንድ አከፋፋዮችም መንግሥት በተወሰነ ደረጃ ድጎማውን በማንሳት አዲስ የነዳጅ ታሪፍ ይፋ በሚያደርግበት ጊዜ በተጨማሪ ዋጋ ለመሸጥ ሲሉ ነዳጅ ያከማቻሉ ሲሉም ባለሥልጣኑ ይከሳሉ። ባለፈው ሳምንት በአፋር ክልል ነዳጅ ጭነው ተደብቀው የነበሩ 15 ቦቴዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር። የተሽከርካሪዎችን መዘግየት ለማስቀረትም ከአዋሽ ጀምሮ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች መመደባቸው ተገልጿል። አንዳንድ ሪፖርቶች ወደ አገሪቱ ከሚገባው ነዳጅ ውስጥ የተወሰኑት ቦቴዎች በጦርነት ምክንያት ዝግ ወደ ሆነችው ትግራይ ክልል እንዲገባ እንደሚደረግ ቢያመለክቱም፣ ባለሥልጣኑ ግን ይህንን የሚያረጋግጥ በቂ መረጃ እንደሌለ ይናገራሉ። “እስካሁን የምናውቀው አንዳንድ ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ነዳጅ ይዘው ከሚጠበቁበት ቦታ ላይ አለመድረሳቸውን ነው” ሲሉ አቶ ቱሉ ስላልታወቁት ቦቴዎች ተናግረዋል። ስለዚህም በአገሪቱ ውስጥ ለሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት፣ በተለያዩ ጊዜያት በነዳጅ ማመላለሻ መስመሮች አካባቢ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች፣ ተሽከርካሪዎች አቅርቦታቸውን በሚፈለጉበት ቦታ ዘግይተው ማድረስ፣ ነዳጅ መድረስ ካለባቸው ቦታዎች ውጪ ወደ ሌሎች ቦታዎች መሸጋገር እንዲሁም አከፋፋዮች ነዳጅን ደብቆ ማስቀመጥ ምክንያት ናቸው ብለዋል። በተለይ ነዳጅ ለመቅዳት ተሽከርካሪዎች የታሪፍ ክለሳ ከሚደረግባቸው የወራት መጨረሻ ቀናት ቀደም ብሎ መኪናቸውን ሙሉ ለማድረግ የሚያደርጉት ጥረት ሰልፎች እንዲበራከቱ ያደርጋሉ። ከቀጣዩ ሐምሌ ወር ጀምሮ መንግሥት በነዳጅ ላይ የሚያደርገውን ድጎማ ለማንሳት ለሚወስደው እርምጃ የመጀመሪያው ደረጃ በመሆኑ ካሉት ተደራራቢ ችግሮች በተጨማሪ የነዳጅ ሰልፉን እንዳባበሰው አሽከርካሪዎች ይናገራሉ። የምጣኔ ሐብት ባለሙያዎች የነዳጅ ድጎማ መነሳቱ ላይ የተለያየ ሃሳቦችን ያንጸባርቃሉ። አንዳንዶች የተቀናጀ ቁጥጥር እና በቂ ግንዛቤ ለሕብረተሰቡ ከደረሰ የከፋ ጫና አያስከትልም ይላሉ። ሌሎች ደግሞ ባለው የኑሮ ውድነት ላይ መሠረታዊ የሆነውን የነዳጅ ድጎማን ማንሳት “ እየነደደ ባለ እሳት ላይ ነዳጅ ማርከፍከፍ ነው” ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመውታል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c726xp15vy6o |
5sports
| ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተደረጉ የእግር ኳስ ጨዋታዎች እነማን አሸነፉ? | በአውሮፓ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን በስፋት መሰራጨት መጀመሩን ተከትሎ በርካታ የእግር ኳስ ጨዋታዎች እየተስተጓጎሉ ነው፤ ነገር ግን ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ በጣልያን ሴሪ እንዲሁም በስፔናን ላሊ ጋ በርካታ ጨዋታዎች ተካሂደዋል። በእንግሊዝ ፕሪምየር ምንም እንኳን ጥቂት የማይባሉ ወሳኝ ጨዋታዎች በኦሚክሮን ስርጭት ምክንያት ለሌላ ጊዜ ቢተላለፉም በሊጉ ከአንድ እስከ ሦስት የሚገኙት ቡድኖች ግን ጨዋታቸውን አድርገዋል። ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስልን አራት ለዜሮ በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን ያረጋገጠ ሲሆን ቼልሲዎች ደግሞ ከዎልቭስ ያደረጉትን ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ጨርሰዋል። ቼልሲዎች በአራት ጨዋታ ለሦስተኛ ጊዜ ነው አቻ የወጡት። ትናንት ምሽት ደግሞ ሊቨርፑል በአዲሱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የሚመሩት ቶተንሀሞችን ገጥሟል። ጨዋታው ምንም እንኳን በሙከራዎችና በግቦች የታጀበ ቢሆንም ውጤቱ ግን አቻ ነበር። ጨዋታውም 2 ለ 2 ተጠናቋል። ይህንን ተከትሎ ማንቸስተር ሲቲዎች በ18 ጨዋታዎች ሊጉን በ44 ነጥብ መምራት የጀመሩ ሲሆን ሊቨርፑል ደግሞ በ41 ነጥብ የሁለተኛውን ቦታ ይዟል። ቼልሲ በ38 ነጥብ ሦስተኝነቱን አሁንም ማስጠበቅ ያለ ሲሆን አርሰናል፣ ዌስት ሀም፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም ለአራተኛው ቦታ እየተፎካከሩ ይገኛሉ። በርንሌይ ኒውካስል እና ኖርዊች ሲቲተ ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ናቸው። በጣልያን ሴሪ አ የሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን ከሳሌኒታና ያደረገውን ጨዋታ 5 ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ በ48 ነጥብ መሪነቱን ማረጋገጥ ችሏል። በጉጉት የተጠበቀው የናፖሊ እና የሚላን ጨዋታ ደግሞ በናፖሊ አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። ይህን ተከትሎ ናፖሊ በ39 ነጥብ ከኢንተር ሚላን በመቀጠል ሁለተኝነቱን ያረጋገጠ ሲሆን ኤሲ ሚላኖች ደግሞ ምንም እንኳን ቢሸነፉም በተመሳሳይ 39 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጠው ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ጁቬንቱሶች ደግሞ ቅዳሜ ዕለት ቦሎኛን ሁለት ለምንም በማሸነፍ በ25 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በስፔን ላሊጋ ቅዳሜ ዕለት የቀድሞ ተጫዋቻቸውን በአሰልጣኝነት የቀጠሩት ባርሴሎናዎች ከኤልቼ ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። ከቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ማለፍ ያቃታቸው ባርሴሎናዎች በሊጉም ቢሆን ወደ ቀድሞ ቦታቸው ለመመለስ ብዙ ይቀራቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በ28 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት። ያለፈው ዓመት የላሊጋው አሸናፊ አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ በሲቪያ ሁለት ለአንድ መሸነፉን ተከትሎ በ29 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሲቪያ ደግሞ አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው በ37 ነጥብ ሁለተኛ ነው። የሊጉ መሪ ሪያል ማድሪድ ትናንት ምሽት የነጥብ ልዩነቱን ማስፋት የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል። እሁድ ምሽት ከካዲዝ የተገናኙት ሪያል ማድሪዶች ጨዋታውን ያለምንም ግብ ዜሮ ለዜሮ በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። | ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በተደረጉ የእግር ኳስ ጨዋታዎች እነማን አሸነፉ? በአውሮፓ አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ ኦሚክሮን በስፋት መሰራጨት መጀመሩን ተከትሎ በርካታ የእግር ኳስ ጨዋታዎች እየተስተጓጎሉ ነው፤ ነገር ግን ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ፣ በጣልያን ሴሪ እንዲሁም በስፔናን ላሊ ጋ በርካታ ጨዋታዎች ተካሂደዋል። በእንግሊዝ ፕሪምየር ምንም እንኳን ጥቂት የማይባሉ ወሳኝ ጨዋታዎች በኦሚክሮን ስርጭት ምክንያት ለሌላ ጊዜ ቢተላለፉም በሊጉ ከአንድ እስከ ሦስት የሚገኙት ቡድኖች ግን ጨዋታቸውን አድርገዋል። ማንቸስተር ሲቲ ኒውካስልን አራት ለዜሮ በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን ያረጋገጠ ሲሆን ቼልሲዎች ደግሞ ከዎልቭስ ያደረጉትን ጨዋታ ያለምንም ግብ አቻ ጨርሰዋል። ቼልሲዎች በአራት ጨዋታ ለሦስተኛ ጊዜ ነው አቻ የወጡት። ትናንት ምሽት ደግሞ ሊቨርፑል በአዲሱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ የሚመሩት ቶተንሀሞችን ገጥሟል። ጨዋታው ምንም እንኳን በሙከራዎችና በግቦች የታጀበ ቢሆንም ውጤቱ ግን አቻ ነበር። ጨዋታውም 2 ለ 2 ተጠናቋል። ይህንን ተከትሎ ማንቸስተር ሲቲዎች በ18 ጨዋታዎች ሊጉን በ44 ነጥብ መምራት የጀመሩ ሲሆን ሊቨርፑል ደግሞ በ41 ነጥብ የሁለተኛውን ቦታ ይዟል። ቼልሲ በ38 ነጥብ ሦስተኝነቱን አሁንም ማስጠበቅ ያለ ሲሆን አርሰናል፣ ዌስት ሀም፣ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሀም ለአራተኛው ቦታ እየተፎካከሩ ይገኛሉ። በርንሌይ ኒውካስል እና ኖርዊች ሲቲተ ደግሞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ናቸው። በጣልያን ሴሪ አ የሊጉ መሪ ኢንተር ሚላን ከሳሌኒታና ያደረገውን ጨዋታ 5 ለባዶ በሆነ ውጤት በማሸነፍ በ48 ነጥብ መሪነቱን ማረጋገጥ ችሏል። በጉጉት የተጠበቀው የናፖሊ እና የሚላን ጨዋታ ደግሞ በናፖሊ አንድ ለባዶ አሸናፊነት ተጠናቋል። ይህን ተከትሎ ናፖሊ በ39 ነጥብ ከኢንተር ሚላን በመቀጠል ሁለተኝነቱን ያረጋገጠ ሲሆን ኤሲ ሚላኖች ደግሞ ምንም እንኳን ቢሸነፉም በተመሳሳይ 39 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጠው ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። የውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኙት ጁቬንቱሶች ደግሞ ቅዳሜ ዕለት ቦሎኛን ሁለት ለምንም በማሸነፍ በ25 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። በስፔን ላሊጋ ቅዳሜ ዕለት የቀድሞ ተጫዋቻቸውን በአሰልጣኝነት የቀጠሩት ባርሴሎናዎች ከኤልቼ ያደረጉትን ጨዋታ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። ከቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ማለፍ ያቃታቸው ባርሴሎናዎች በሊጉም ቢሆን ወደ ቀድሞ ቦታቸው ለመመለስ ብዙ ይቀራቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በ28 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ነው የሚገኙት። ያለፈው ዓመት የላሊጋው አሸናፊ አትሌቲኮ ማድሪድ ደግሞ በሲቪያ ሁለት ለአንድ መሸነፉን ተከትሎ በ29 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ሲቪያ ደግሞ አንድ ቀሪ ጨዋታ እየቀረው በ37 ነጥብ ሁለተኛ ነው። የሊጉ መሪ ሪያል ማድሪድ ትናንት ምሽት የነጥብ ልዩነቱን ማስፋት የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል። እሁድ ምሽት ከካዲዝ የተገናኙት ሪያል ማድሪዶች ጨዋታውን ያለምንም ግብ ዜሮ ለዜሮ በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59708923 |
0business
| ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶከረንሲዎች በኢትዮጵያ ዕውቅና የላቸውም አለ | የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎች በአገሪቱ ውስጥ ለግብይት መጠቀም ዕውቅና አልተሰጣቸውም በማለት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከለከለ። ብሔራዊ ባንክ በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አማካይነት ባወጣው መግለጫ፤ በክሪፕቶከረንሲዎች ግብይት መፈጸም ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ ኅብረተሰቡ እራሱን ከመሰል ተግባራት ይጠብቅ ብሏል። ክሪፕቶከረንሲ በአጭር ቋንቋ የማይዳሰስ ዲጂታል ገንዘብ ማለት ነው። ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ፣ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ነው ሲል ይገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ። በስፋት ከሚታወቁት መካከል ቢትኮይን፣ ኤቴሪያም፣ ካርዳኖ እና ዶጅኮይን ተጠቃሽ ናቸው። ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሰዎች እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችን በመጠቀም ለምርት እና አገልግሎት ክፍያ እየፈጸሙ እንደሆነ ጠቁሟል። ምንም እንኳን ባንኩ ይህን ይበል እንጂ በኢትዮጵያ ለሚሰጡት ምርት እና አገልግሎት ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ የሚቀበሉ ድርጅቶች ስለመኖራቸው ግልጽ አይደለም። እንዲህ ዓይነቶቹ የዲጂታል መገበያያ ዘዴዎች በአገሪቱ እየተስፋፉ መምጣታቸውን በመግለጽ በአገሪቱ ተቀባይነት የሌለው ሕገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገራት ሰዎች ለሚያገኟቸው ምርት እና አገልግሎቶች በክሪፕቶከረንሲዎች አማካይነት ክፍያ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል። ማይክሮሶፍት፣ ፔይፓል፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያ ይፋዊ መገበያያ ገንዘብ ብር መሆኑን አስታውሶ፤ “በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም” ብሏል። በክሪፕቶከረንሲ ግብይት ላይ መንግሥታት ቁጥጥር ለማድረግ ያዳግታቸዋል። በክሪፕቶከረንሲ በሚደረጉ ግብይቶች ላይም የሻጭ እና ገዢ ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት ማድረግ ይቻላል። በዚህም ምክንያት ሕገ ወጥ ቡድኖች/ግለሰቦች የተከለከሉ ቁሶች ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ። በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርገው ሊጠቀሙም ይችላሉ። ይህም ለአገራት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል። ብሔራዊ ባንክም በዛሬው መግለጫው ክሪፕቶከረንሲዎች “በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል” ብሏል። “ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል” ካለ በኋላ ኅብረተሰቡም በዚህ “ሕገ ወጥ ተግባር” ላይ የተሰማሩትን አካላትን ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁም ጥሪውን አስተላልፏል። ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እንዱሁም ኤል ሳልቫዶር በቅርቡ ቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያ አድርገዋል። ይህ ማለት ሰዎች በእነዚህ አገራት ለሚያገኙት አገልግሎት ክፍያ በቢትኮይን መፈጸም ይችላሉ። በተቀሩት አገራት በተለይ ደግሞ በምዕራባውያን አገራት ሕገ ወጥ ነው ማለት ግን አይደለም። አንደ ቦሊቪያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ኮሎምቢያ ያሉ አገራት ግን ቢትኮይን ላይ ክልከላ ጥለዋል ወይም ሕገ ወጥ አድርገውታል። | ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶከረንሲዎች በኢትዮጵያ ዕውቅና የላቸውም አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎች በአገሪቱ ውስጥ ለግብይት መጠቀም ዕውቅና አልተሰጣቸውም በማለት ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከለከለ። ብሔራዊ ባንክ በአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አማካይነት ባወጣው መግለጫ፤ በክሪፕቶከረንሲዎች ግብይት መፈጸም ሕገ ወጥ ተግባር በመሆኑ ኅብረተሰቡ እራሱን ከመሰል ተግባራት ይጠብቅ ብሏል። ክሪፕቶከረንሲ በአጭር ቋንቋ የማይዳሰስ ዲጂታል ገንዘብ ማለት ነው። ኦክስፎርድ መዝገበ ቃላት ክሪፕቶከረንሲን፤ የገንዘብ ልውውጦችን ደኅንነት የሚያረጋግጥ፣ የተጨማሪ አሃዶችን መፈጠርን የሚቆጣጠር እና ገንዘብ መተላለፉን የሚያረጋግጥ፣ ጠንካራ ክራፕቶግራፊ የሚጠቀም መገበያያ እንዲሆን ተደርጎ የተቀረጸ ዲጂታል ገንዘብ ነው ሲል ይገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በርካታ ዓይነት ክሪፕቶካረንሲዎች አሉ። በስፋት ከሚታወቁት መካከል ቢትኮይን፣ ኤቴሪያም፣ ካርዳኖ እና ዶጅኮይን ተጠቃሽ ናቸው። ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ሰዎች እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶከረንሲዎችን በመጠቀም ለምርት እና አገልግሎት ክፍያ እየፈጸሙ እንደሆነ ጠቁሟል። ምንም እንኳን ባንኩ ይህን ይበል እንጂ በኢትዮጵያ ለሚሰጡት ምርት እና አገልግሎት ክፍያ በክሪፕቶከረንሲ የሚቀበሉ ድርጅቶች ስለመኖራቸው ግልጽ አይደለም። እንዲህ ዓይነቶቹ የዲጂታል መገበያያ ዘዴዎች በአገሪቱ እየተስፋፉ መምጣታቸውን በመግለጽ በአገሪቱ ተቀባይነት የሌለው ሕገ ወጥ ድርጊት መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል። በአሁኑ ወቅት በበርካታ አገራት ሰዎች ለሚያገኟቸው ምርት እና አገልግሎቶች በክሪፕቶከረንሲዎች አማካይነት ክፍያ መፈጸም እየተለመደ መጥቷል። ማይክሮሶፍት፣ ፔይፓል፣ የጉዞ ወኪሉ ኤክስፔዲያን ከመሳሰሉ ባለብዙ ሚሊዮን ገንዘብ ኩባንያዎችን አንስቶ እስከ ሆቴሎች እና ካፊቴሪያዎች ቢትኮይንን በክፍያ መልክ ይቀበላሉ። ብሔራዊ ባንክ የኢትዮጵያ ይፋዊ መገበያያ ገንዘብ ብር መሆኑን አስታውሶ፤ “በየትኛውም የክፍያ መፈጸሚያ ሰነድም ሆነ ሥርዓት ያለ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ የገንዘብ ዝውውርም ሆነ ገንዘብ ነክ አገልግሎት መስጠት አይቻልም” ብሏል። በክሪፕቶከረንሲ ግብይት ላይ መንግሥታት ቁጥጥር ለማድረግ ያዳግታቸዋል። በክሪፕቶከረንሲ በሚደረጉ ግብይቶች ላይም የሻጭ እና ገዢ ማንነት ይፋ ሳይደረግ ግብይት ማድረግ ይቻላል። በዚህም ምክንያት ሕገ ወጥ ቡድኖች/ግለሰቦች የተከለከሉ ቁሶች ሊገዙ እና ሊሽጡ ይቻላሉ። በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አድርገው ሊጠቀሙም ይችላሉ። ይህም ለአገራት ስጋት ሆኖ ቀጥሏል። ብሔራዊ ባንክም በዛሬው መግለጫው ክሪፕቶከረንሲዎች “በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ለማሸሽ ምቹ ሁኔታን እየፈጠረ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል” ብሏል። “ይህን ፈጽመው በሚገኙ አካላት ላይ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል” ካለ በኋላ ኅብረተሰቡም በዚህ “ሕገ ወጥ ተግባር” ላይ የተሰማሩትን አካላትን ለብሔራዊ ባንክ እና ለሚመለከታቸው ሕግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁም ጥሪውን አስተላልፏል። ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እንዱሁም ኤል ሳልቫዶር በቅርቡ ቢትኮይንን ሕጋዊ መገበያያ አድርገዋል። ይህ ማለት ሰዎች በእነዚህ አገራት ለሚያገኙት አገልግሎት ክፍያ በቢትኮይን መፈጸም ይችላሉ። በተቀሩት አገራት በተለይ ደግሞ በምዕራባውያን አገራት ሕገ ወጥ ነው ማለት ግን አይደለም። አንደ ቦሊቪያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ኮሎምቢያ ያሉ አገራት ግን ቢትኮይን ላይ ክልከላ ጥለዋል ወይም ሕገ ወጥ አድርገውታል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0g085dpwno |
0business
| በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ ዋጋ ከአንዳንድ የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር | ምንም እንኳን በዓለም ገበያ ላይ ዋጋው ቢጨምርም ለወራት ባለበት የቆየው የኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል። በዚህም መሠረት በመላው አገሪቱ በታኅሣሥ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም በተለያዩ የነዳጅ እምርቶች ላይ ቀላል የማይባል ጭማሪ ታይቷል። በዚህ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል፤ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መኖሩና ከጎረቤት አገራት ጋር ሲነጻጸር በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ ዋጋ ዝቅተኛ በመሆኑ የነዳጅ ምርቶች ለከፍተኛ ኮንትሮባንድ መጋለጡ ተጠቅሷል። የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎ የነዳጅ ፍላጎት ዝቅ በማለቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቶ የቆየ ቢሆንም፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ዋጋው ቀስበቀስ እየጨመረ አሁን ካለበት ላይ ደርሷል። ባለፉት ወራት ጭማሪው ያለመቋረጥ የቀጠለ ሲሆን፣ በወረርሽኙ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የዓለም ምጣኔ ሀብት ለማንሰራራትና ወደነበረበት ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የነዳጅ ፍጆታ ከፍ እያለ መሆኑ ለዚህ ተጠቃሽ ነው። በኢትዮጵያ የተደረገው የዋጋ ክለሳ ለወራት በሊትር 25 ብር ከ85 ሳንቲም ይሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ አሁን በተደረገው የዋጋ ማስተካከያ አንድ ሊትር ቤንዚን 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። ይህም ከስደስት ብር በላይ ጭማሪን በአንድ ሊትር ላይ ያስከተለ ሲሆን፣ ጭማሪው በሌሎችም ሸቀጦችና አገልግሎቶች ላይ ሊንጸባረቅ እንደሚችል ከዚህ ቀደም የታዩት ልምዶች ያመለክታሉ። ነጭ ናፍጣ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ73 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 58 ብር ከ77 ሳንቲም በሊትር ከኅዳር 30 ቀን 2014 ጀምሮ እንደሚሸጥ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት አገራት ሲነጻጸር በየጊዜው እየተደረገ ካለው የዋጋ ጭማሪ ጋር ቢሆንም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ አገራት ነዳጅ በአነስተኛ ዋጋ ከሚሸጥባቸው አገራት መካከል ተጠቃሽ ነች። በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ የነዳጅ መሸጫ ዋጋን እንደሚያቀርበው 'ስታቲስታ' መረጃ ከሆነ ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች ከሆኑት አንጎላ፣ ናይጄሪያ እና አልጄሪያ በመቀጠል በአፍሪካ ውስጥ በአስተኛ ዋጋ የነዳጅ ምርቶች ለሕዝቧ የምታቀርብ አገር ናት። የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነችው ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ በቀጠናው ካሉ አገራት ነዳጅ በውድ የምታቀርብ አገር እንደሆነች ይነገራል። በስታቲስቲክስታይምስ መረጃ መሠረት በኬንያ 1 ሊትር ነዳጅ 1.19 ዶላር ይሸጣል። ከኬንያ በመከተል በአካባቢው ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ያላቸው አገራት ሱዳን እና ኡጋንዳ ሲሆኑ፤ ነዳጅ የምታመርተው ሱፋን በሊትር 1.03 ዶላር ስታስከፍል፣ በቅርቡ የነዳጅ ዘይት ያገኘችው ኡጋንዳ ደግሞ አንድ ሊትር በ1.09 የአሜሪካ ዶላር ታቀርባለች። በዓለም ላይ ዜጎቿን አነስተኛ የነዳጅ ዋጋ የምታስከፍለው ነዳጅ አምራች የሆነችው እና ምጣኔ ሀብቷ ክፉኛ የተጎሳቆለባት ቬንዙዌላ ነች። እንደ ግሎባል ፔተሮል ፕራይስ ከሆነ በቬንዙዌላ በ1 የኢትዮጵየ ብር (0.02 የአሜሪካ ዶላር) አንድ ሊትር ነዳጅ መሸመት ይቻላል። በአፍሪካ ነዳጅ በከፍተኛ ዋጋ ከሚሸጡባቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ናት። በመረጃው መሠረት በደቡብ አፍሪካ አንድ ሊትር ነዳጅ የሚሸጠው በ1.25 ዶላር ነው። የበለጸጉት እንደ ኔዘርላንስ፣ ኖርዌይ፣ ጣሊያ እና ሆንግ ኮንግ ለአንድ ሊትር ነዳጅ ከ2 የአሜሪካ ዶላር በላይ (ወደ 95 ብር ገደማ) ይጠይቃሉ። ነዳጅ የማታመርተው ኢትዮጵያ፤ ነዳጅ አምራች ከሆኑ አገራት በላይ በአነሰ ዋጋ ነዳጅ ለዜጎች ታቀርባለች። ይህ የሆነውም መንግሥት ለዘረፉ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት ነው። አገሪቱ ከዓመታዊ በጀቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መድባ ነዳጅ ታቀርባለች። ኢትዮጵያ ነዳጅ የምታስገባው ከየት ነው? ኢትዮጵያ ለፍጆታዋ የሚውለውን ነዳጅ ከተለያዩ ነዳጅ አምራች አገራት የምታስገባ ሲሆን፣ በዋናነት ከመካከለኛው ምሥራቅና የባሕረ ሰላጤው አገራት ታገኛለች። በዚህም መሠረት በአሁኑ ጊዜ አገሪቱ የሚያስፈልጋትን የነዳጅ ዘይት ከሳዑዲ አረቢያ እና ከኩዌት በማስመጣት ላይ እንደምትገኝ የነዳጅ ድርጅት መረጃ ያመለክታል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንደሚለው በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚገባበት ብቸኛው መንገድ በጂቡቲ ወደብ በኩል ባለው መስመር ነው። ከአራት ወራት በፊት ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ባገኘው መረጃ መሠረት ለአገሪቱ ፍጆታ በየዕለቱ 2.5 ሚሊዮን ሊትር ቤንዚን እና 8 ሚሊየን ሊትር ናፍጣ ይቀርባል ። ይህንንም ለማሟላት በየዓመቱ ለአገሪቱ ፍጆታ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን፣ ኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዓመት ምን ያህል የነዳጅ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ የተለያዩ መረጃዎችን በመመርኮዝ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ያቅዳል። ። ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸው የነዳጅ ምርቶች አምስት ዓይነት ናቸው። እነዚህም ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ዓይነት ናፋጣዎች ናቸው። በዚህም መሠረት ቤንዚን በዓመት እስከ 700 ሺህ ሜትሪክ ቶን፣ 2.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ናፍጣ፣ 600 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅና እስከ 70 ሺህ ሜትሪክ ቶን የተለያየ አይነት የኢንዱስትሪ ናፍጣ በየዓመቱ እንደሚገባ ታደሰ ኃይለማርያም ተናግረው ነበር። | በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ ዋጋ ከአንዳንድ የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነጻጸር ምንም እንኳን በዓለም ገበያ ላይ ዋጋው ቢጨምርም ለወራት ባለበት የቆየው የኢትዮጵያ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቋል። በዚህም መሠረት በመላው አገሪቱ በታኅሣሥ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ የተደረገ ሲሆን፤ በዚህም በተለያዩ የነዳጅ እምርቶች ላይ ቀላል የማይባል ጭማሪ ታይቷል። በዚህ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረግ ካስፈለገባቸው ምክንያቶች መካከል፤ የዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ መኖሩና ከጎረቤት አገራት ጋር ሲነጻጸር በኢትዮጵያ ያለው የነዳጅ ዋጋ ዝቅተኛ በመሆኑ የነዳጅ ምርቶች ለከፍተኛ ኮንትሮባንድ መጋለጡ ተጠቅሷል። የኮሮናቫይረስ ክስተትን ተከትሎ የነዳጅ ፍላጎት ዝቅ በማለቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ከፍተኛ ቅናሽ አሳይቶ የቆየ ቢሆንም፣ ከአንድ ዓመት በኋላ ዋጋው ቀስበቀስ እየጨመረ አሁን ካለበት ላይ ደርሷል። ባለፉት ወራት ጭማሪው ያለመቋረጥ የቀጠለ ሲሆን፣ በወረርሽኙ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የዓለም ምጣኔ ሀብት ለማንሰራራትና ወደነበረበት ለመመለስ በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የነዳጅ ፍጆታ ከፍ እያለ መሆኑ ለዚህ ተጠቃሽ ነው። በኢትዮጵያ የተደረገው የዋጋ ክለሳ ለወራት በሊትር 25 ብር ከ85 ሳንቲም ይሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ አሁን በተደረገው የዋጋ ማስተካከያ አንድ ሊትር ቤንዚን 31 ብር ከ74 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል። ይህም ከስደስት ብር በላይ ጭማሪን በአንድ ሊትር ላይ ያስከተለ ሲሆን፣ ጭማሪው በሌሎችም ሸቀጦችና አገልግሎቶች ላይ ሊንጸባረቅ እንደሚችል ከዚህ ቀደም የታዩት ልምዶች ያመለክታሉ። ነጭ ናፍጣ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ 28 ብር ከ94 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 23 ብር ከ73 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 58 ብር ከ77 ሳንቲም በሊትር ከኅዳር 30 ቀን 2014 ጀምሮ እንደሚሸጥ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴሩ አስታውቋል። የኢትዮጵያ የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት አገራት ሲነጻጸር በየጊዜው እየተደረገ ካለው የዋጋ ጭማሪ ጋር ቢሆንም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከሚገኙ አገራት ነዳጅ በአነስተኛ ዋጋ ከሚሸጥባቸው አገራት መካከል ተጠቃሽ ነች። በዓለም ዙሪያ ባሉ አገራት ውስጥ የነዳጅ መሸጫ ዋጋን እንደሚያቀርበው 'ስታቲስታ' መረጃ ከሆነ ኢትዮጵያ ነዳጅ አምራች ከሆኑት አንጎላ፣ ናይጄሪያ እና አልጄሪያ በመቀጠል በአፍሪካ ውስጥ በአስተኛ ዋጋ የነዳጅ ምርቶች ለሕዝቧ የምታቀርብ አገር ናት። የኢትዮጵያ ጎረቤት የሆነችው ምሥራቅ አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ በቀጠናው ካሉ አገራት ነዳጅ በውድ የምታቀርብ አገር እንደሆነች ይነገራል። በስታቲስቲክስታይምስ መረጃ መሠረት በኬንያ 1 ሊትር ነዳጅ 1.19 ዶላር ይሸጣል። ከኬንያ በመከተል በአካባቢው ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ያላቸው አገራት ሱዳን እና ኡጋንዳ ሲሆኑ፤ ነዳጅ የምታመርተው ሱፋን በሊትር 1.03 ዶላር ስታስከፍል፣ በቅርቡ የነዳጅ ዘይት ያገኘችው ኡጋንዳ ደግሞ አንድ ሊትር በ1.09 የአሜሪካ ዶላር ታቀርባለች። በዓለም ላይ ዜጎቿን አነስተኛ የነዳጅ ዋጋ የምታስከፍለው ነዳጅ አምራች የሆነችው እና ምጣኔ ሀብቷ ክፉኛ የተጎሳቆለባት ቬንዙዌላ ነች። እንደ ግሎባል ፔተሮል ፕራይስ ከሆነ በቬንዙዌላ በ1 የኢትዮጵየ ብር (0.02 የአሜሪካ ዶላር) አንድ ሊትር ነዳጅ መሸመት ይቻላል። በአፍሪካ ነዳጅ በከፍተኛ ዋጋ ከሚሸጡባቸው አገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ ተጠቃሽ ናት። በመረጃው መሠረት በደቡብ አፍሪካ አንድ ሊትር ነዳጅ የሚሸጠው በ1.25 ዶላር ነው። የበለጸጉት እንደ ኔዘርላንስ፣ ኖርዌይ፣ ጣሊያ እና ሆንግ ኮንግ ለአንድ ሊትር ነዳጅ ከ2 የአሜሪካ ዶላር በላይ (ወደ 95 ብር ገደማ) ይጠይቃሉ። ነዳጅ የማታመርተው ኢትዮጵያ፤ ነዳጅ አምራች ከሆኑ አገራት በላይ በአነሰ ዋጋ ነዳጅ ለዜጎች ታቀርባለች። ይህ የሆነውም መንግሥት ለዘረፉ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት ነው። አገሪቱ ከዓመታዊ በጀቷ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ መድባ ነዳጅ ታቀርባለች። ኢትዮጵያ ነዳጅ የምታስገባው ከየት ነው? ኢትዮጵያ ለፍጆታዋ የሚውለውን ነዳጅ ከተለያዩ ነዳጅ አምራች አገራት የምታስገባ ሲሆን፣ በዋናነት ከመካከለኛው ምሥራቅና የባሕረ ሰላጤው አገራት ታገኛለች። በዚህም መሠረት በአሁኑ ጊዜ አገሪቱ የሚያስፈልጋትን የነዳጅ ዘይት ከሳዑዲ አረቢያ እና ከኩዌት በማስመጣት ላይ እንደምትገኝ የነዳጅ ድርጅት መረጃ ያመለክታል። የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት እንደሚለው በአሁኑ ወቅት የነዳጅ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የሚገባበት ብቸኛው መንገድ በጂቡቲ ወደብ በኩል ባለው መስመር ነው። ከአራት ወራት በፊት ቢቢሲ ከኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ባገኘው መረጃ መሠረት ለአገሪቱ ፍጆታ በየዕለቱ 2.5 ሚሊዮን ሊትር ቤንዚን እና 8 ሚሊየን ሊትር ናፍጣ ይቀርባል ። ይህንንም ለማሟላት በየዓመቱ ለአገሪቱ ፍጆታ የሚያስፈልገውን የነዳጅ መጠን ከተለያዩ ተቋማት ጋር በመሆን፣ ኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በዓመት ምን ያህል የነዳጅ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ የተለያዩ መረጃዎችን በመመርኮዝ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት ያቅዳል። ። ኢትዮጵያ ከውጭ የምታስገባቸው የነዳጅ ምርቶች አምስት ዓይነት ናቸው። እነዚህም ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ሁለት ዓይነት ናፋጣዎች ናቸው። በዚህም መሠረት ቤንዚን በዓመት እስከ 700 ሺህ ሜትሪክ ቶን፣ 2.8 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን ናፍጣ፣ 600 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅና እስከ 70 ሺህ ሜትሪክ ቶን የተለያየ አይነት የኢንዱስትሪ ናፍጣ በየዓመቱ እንደሚገባ ታደሰ ኃይለማርያም ተናግረው ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-59594066 |
3politics
| ፖሊስ ኢትዮ-እስራኤላውያንን ጨምሮ ዜጎችን ሰልሏል መባሉን እስራኤል ልታጣራ ነው | የእስራኤል ፖሊስ ከኢትዮጵያ የሄዱ ቤተ እስራኤላውያንን ጨምሮ የታዋቂ ዜጎችን ስልክ ያለሕጋዊ ፈቃድ ጠልፏል የሚለውን ክስ የሚያጣራ ኮሚሽን በእስራኤል መንግሥት እንደሚቋቋም ተገለጸ። የስልክ ግንኙነትን የሚፈትሽ መተግበሪያ (ስፓይዌር) ያለ ፈቃድ በመጠቀም የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ልጅን ጨምሮ የባለሥልጣናትን፣ ተቃዋሚዎችን እና የጋዜጠኞችን ስልክ መሰለሉ 'ካልካስት' በተባለ ጋዜጣ ተዘግቧል። የኔታንያሁ የሙስና ክስ ውስጥ የተካተተ ምስክር ስልክም እንደተጠለፈ ተገልጿል። የኔታንያሁ ልጅ እና በሙስና ክስ ላይ ምስክር የሆኑም ስልካቸው መጠለፉ ቢገለጽም፤ በስለላ የተገኘው መረጃ በፍርድ ቤት እንደማስረጃ ስለመቅረቡ አልታወቀም። ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት "ይህ ዘገባ እውነት ከሆነ ከባድ ጥፋት ነው የተፈጸመው" ብለዋል። ጋዜጠኞች እንደሚሉት የእስራኤል ፖሊሶች ፔጋሰስ የተባለውን የስለላ መተግበሪያ ነው የተጠቀሙት። በእስራኤሉ ጋዜጣ በወጣው ዘገባ መሠረት የበርካታ እስራኤላውያን ስልክ በፖሊስ ያለ ፈቃዳቸው ተጠልፏል። ሕጋዊ ምርመራ ባልተከፈተባቸው ሰዎች እንዲሁም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለላው መከናወኑም ተጠቁሟል። ስለላ ሲካሄድባቸው ነበር ከተባሉት መካከል የአገሪቱ የትራንስፖርት፣ የገንዘብና የፍትሕ ሚኒስትሮች ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን-እስራኤላውያን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋቾችም እንደተሰለሉ ተገልጿል። በእስራኤል ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ብሎም የኔታንያ፣ መቫስረት ዛየን፣ ኪርያት አታ እና ሆሎን ከንቲባዎችም ያለ ፈቃዳቸው እየተሰለሉ ነበር ተብሏል። ፔጋሰስ መተግበሪያን ያመረተው የእስራኤሉ ኤንኤስኦ ሲሆን፤ ተቋሙ በመላው ዓለም ለአምባገነን መሪዎች የስለላ መተግበሪያ በመሸጥ ይወነጀላል። ድርጅቱ በበኩሉ መተግበሪያውን አንዴ ከሸጠ በኋላ ክትትል እንደማያደርግና የእስራኤል ዜጎችን ለመሰለል እንደማይውል ገልጿል። የእስራኤል ፖሊስ ያለ ዜጎች ፈቃድ ሰልሏል የሚለውን ዘገባ በተመለከተ ግን እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ፔጋሰስ የተባለው መተግበሪያ ከግለሰቦች ስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት፣ ምስል፣ ኢሜል፣ የተቀረጸ ድምጽ እና የስልክ ንግግር መጥለፍ ያስችላል። "ፔጋሰስ ሽብርና ሌሎች ወንጀሎችን ለመዋጋት ከሚያስችሉ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። ነገር ግን መተግበሪያው የእስራኤል ዜጎችንና ባለሥልጣናትን እንዲሰልል አልተሠራም" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት። ምክትል ዐቃቤ ሕግ አሚት ሜሪ ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሚገኙና ለሕዝቡ ምላሽ እንደሚሰጥም አክለዋል። ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ "ዴሞክራሲያችንን ልናጣ አይገባም። ፖሊሳችንን ልናጣ አይገናም። ሕዝባችንም በፖሊስ ላይ እምነት እንዲያጣ አንፈልግም" ብለዋል። የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስትር ኦማር ባርሊዝ፤ ጉዳዩን የሚመረምረው ኮሚሽን ጡረታ በወጡ ዳኛ እንደሚመራና ማንኛውንም ሰው ለምስክርነት የመጥራት መብት እንዳለው አስረድተዋል። | ፖሊስ ኢትዮ-እስራኤላውያንን ጨምሮ ዜጎችን ሰልሏል መባሉን እስራኤል ልታጣራ ነው የእስራኤል ፖሊስ ከኢትዮጵያ የሄዱ ቤተ እስራኤላውያንን ጨምሮ የታዋቂ ዜጎችን ስልክ ያለሕጋዊ ፈቃድ ጠልፏል የሚለውን ክስ የሚያጣራ ኮሚሽን በእስራኤል መንግሥት እንደሚቋቋም ተገለጸ። የስልክ ግንኙነትን የሚፈትሽ መተግበሪያ (ስፓይዌር) ያለ ፈቃድ በመጠቀም የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ልጅን ጨምሮ የባለሥልጣናትን፣ ተቃዋሚዎችን እና የጋዜጠኞችን ስልክ መሰለሉ 'ካልካስት' በተባለ ጋዜጣ ተዘግቧል። የኔታንያሁ የሙስና ክስ ውስጥ የተካተተ ምስክር ስልክም እንደተጠለፈ ተገልጿል። የኔታንያሁ ልጅ እና በሙስና ክስ ላይ ምስክር የሆኑም ስልካቸው መጠለፉ ቢገለጽም፤ በስለላ የተገኘው መረጃ በፍርድ ቤት እንደማስረጃ ስለመቅረቡ አልታወቀም። ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት "ይህ ዘገባ እውነት ከሆነ ከባድ ጥፋት ነው የተፈጸመው" ብለዋል። ጋዜጠኞች እንደሚሉት የእስራኤል ፖሊሶች ፔጋሰስ የተባለውን የስለላ መተግበሪያ ነው የተጠቀሙት። በእስራኤሉ ጋዜጣ በወጣው ዘገባ መሠረት የበርካታ እስራኤላውያን ስልክ በፖሊስ ያለ ፈቃዳቸው ተጠልፏል። ሕጋዊ ምርመራ ባልተከፈተባቸው ሰዎች እንዲሁም ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ስለላው መከናወኑም ተጠቁሟል። ስለላ ሲካሄድባቸው ነበር ከተባሉት መካከል የአገሪቱ የትራንስፖርት፣ የገንዘብና የፍትሕ ሚኒስትሮች ይጠቀሳሉ። በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን-እስራኤላውያን እንዲሁም የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋቾችም እንደተሰለሉ ተገልጿል። በእስራኤል ውስጥ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ብሎም የኔታንያ፣ መቫስረት ዛየን፣ ኪርያት አታ እና ሆሎን ከንቲባዎችም ያለ ፈቃዳቸው እየተሰለሉ ነበር ተብሏል። ፔጋሰስ መተግበሪያን ያመረተው የእስራኤሉ ኤንኤስኦ ሲሆን፤ ተቋሙ በመላው ዓለም ለአምባገነን መሪዎች የስለላ መተግበሪያ በመሸጥ ይወነጀላል። ድርጅቱ በበኩሉ መተግበሪያውን አንዴ ከሸጠ በኋላ ክትትል እንደማያደርግና የእስራኤል ዜጎችን ለመሰለል እንደማይውል ገልጿል። የእስራኤል ፖሊስ ያለ ዜጎች ፈቃድ ሰልሏል የሚለውን ዘገባ በተመለከተ ግን እስካሁን ምላሽ አልሰጠም። ፔጋሰስ የተባለው መተግበሪያ ከግለሰቦች ስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት፣ ምስል፣ ኢሜል፣ የተቀረጸ ድምጽ እና የስልክ ንግግር መጥለፍ ያስችላል። "ፔጋሰስ ሽብርና ሌሎች ወንጀሎችን ለመዋጋት ከሚያስችሉ መተግበሪያዎች አንዱ ነው። ነገር ግን መተግበሪያው የእስራኤል ዜጎችንና ባለሥልጣናትን እንዲሰልል አልተሠራም" ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ናፍታሊ ቤኔት። ምክትል ዐቃቤ ሕግ አሚት ሜሪ ጉዳዩን እየተከታተሉት እንደሚገኙና ለሕዝቡ ምላሽ እንደሚሰጥም አክለዋል። ፕሬዝዳንት አይዛክ ሄርዞግ "ዴሞክራሲያችንን ልናጣ አይገባም። ፖሊሳችንን ልናጣ አይገናም። ሕዝባችንም በፖሊስ ላይ እምነት እንዲያጣ አንፈልግም" ብለዋል። የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስትር ኦማር ባርሊዝ፤ ጉዳዩን የሚመረምረው ኮሚሽን ጡረታ በወጡ ዳኛ እንደሚመራና ማንኛውንም ሰው ለምስክርነት የመጥራት መብት እንዳለው አስረድተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/60291117 |
2health
| የምግብ ፍላጎት የሚቀንሰው መድኃኒት ከመጠን በላይ ውፍረትን እንደሚቀንስ ተነገረ | የምግብ ፍላጎትን የሚቀንሰው መድኃኒት አንዳንድ ሰዎች ከአንድ አምስተኛ በላይ የሰውነት ክብደታቸውን እንዲቀንሱ አድርጓቸዋል ሲል አንድ ዓለም አቀፍ ጥናት አስታወቀ፡፡ ሴማግሉታይድ የተሰኘው እና በየሳምንቱ የሚሰጠው መድኃኒት ከአመጋገብ እና ከአካል ብቃት ምክሮች ጎን ለጎን ተሰጥቷል፡፡ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሰዎች ላይ በተደረገው ጥናት በአማካይ 15 ኪሎ ግራም ክብደት በ15 ወር የሙከራ ጊዜ መቀነሱ ታይቷል፡፡ ባለሙያዎች ውጤቱ ከመጠን በላይ ውፍረትን ለማከም "የአዲስ ምዕራፍ" ምልክት ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ከኬንት የመጣችው ጃን ከሰውነት ክብደቷ ከአንድ አምስተኛው በላይ የሚሆነውን 28 ኪሎ ግራም ቀንሳለች፡፡ "መድኃኒቱ ሕይወቴን የቀየረ ሲሆን ለምግብ ያለኝን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ቀይሯል" ብላለች፡፡ ምግብ መቀነስ ለጉዳት እንደዳረጋት ተናግራ፤ ረሃብ ስለማይሰማት መድኃኒቱን መውሰድ "ፍፁም የተለየ ነበር" ስትል ገልጻለች፡፡ 'ጥረት የማይፈልግ' ጃን አሁን ከሙከራው ስለወጣች የምግብ ፍላጎቷ ተመልሶ ክብደቷ እየጨመረ ይገኛል። "በሙከራው ጊዜ ክብደት መቀነስ ምንም ጥረት እንደማይፈልግ ቢሰማኝም አሁን ግን ከምግብ ጋር የማያቋርጥ ወደሚመስል ውጊያ እንደመመለስ ነው" ብላለች፡፡ ሴማግሉታይድ ለሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ሕክምና ይውል ስለነበር በአንዳንድ ሰዎች ቀድሞውኑ ቢታወቅም በዚህ ሙከራ ግን በከፍተኛ መጠን መሰጠቱ ተመልክቷል፡፡ መድኃኒቱ የሚሠራው የሰውነትን የምግብ ፍላጎት በመቀነስ እና ምግብ ከተመገቡ በኋላ ሆድ መሙላቱን የሚያሳውቀውን ሆርሞን የሚለቅበትን ሂደት በማስመሰል ነው፡፡ በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜዲስን ይፋ በተደረጉት ውጤቶች መሠረት በሴማግሉታይድ የታገዙት ሰዎች በአማካይ 15 ኪሎ ግራም ክብደት የቀንሰዋል፡፡ 'አዲስ ዘመን' ከተመራማሪዎቹ አንዷ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቼል ባተርሃም ለቢቢሲ እንደተናገሩት "የሚያስከትለው የክብደት መቀነስ መጠን በዘርፉ ለውጥ ያመጣል።" "ላለፉት 20 ዓመታት ከመጠን ባለፈ ውፍረት ዙሪያ ጥናት ሳካሂድ ቆይቻለሁ። እስከ አሁን ከቀዶ ህክምና ውጭ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ለመከላከል ውጤታማ ህክምና አላገኘንም" ብለዋል። ክብደትን መቀነስ የልብ ህመም፣ የስኳር እና የኮቪድ -19 ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ ሴማግሉታይድ ለመድኃኒት ተቆጣጣሪዎች እየቀረበ ስለሆነም በመደበኛነት ሊታዘዝ አይችልም፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ባተርሃም ከሆነ መድኃኒቱ መጀመሪያ ላይ በስፋት ለገበያ ከመቅረቡ በፊት በልዩ ባለሙያ ክብደት መቀነስ ላይ በሚሠሩ ክሊኒኮች ጥቅም ላይ እንደሚውል ይጠበቃል፡፡ በሕክምናው ላይ ማቅለሽለሽ፣ ተቅማጥ፣ ማስታወክ እና የሆድ ድርቀት የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ነበሩ፡፡ በተጨማሪም ክብደት መቀነሱ በረዥም ጊዜ ውስጥ ሊቆይ የሚችል መሆኑን ለመመልከትም የአምስት ዓመት ጥናቶች አሉ፡፡ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ስቴፈን ኦራሂሊይ እንደተናገሩት "የተገኘው የክብደት መቀነስ መጠን ፈቃድ ከተሰጠው የፀረ ውፍረት መድኃኒት አንጻር ውጤቱ ትልቅ ነው" ብለዋል፡፡ "ወደፊት የጎንዮሽ ጉዳቶቹ ያነሱ የክብደት መቀነስ ደረጃዎችን ለማሳካት የአዲስ ዘመን ጅማሬ ነው" ሲሉ ገልጸዋቀል፡፡ የሥነ ምግብ ባለሙያው እና የአስቶን ሜዲካል ትምህርት ቤቱ ዶ/ር ዱአን ሜሎር "ሰዎች ክብደታቸውን እንዲቀንሱ የሚያግዝ አማራጭ መኖሩ ጠቃሚ ነው። ክብደትን ለመቀነስ አሁንም ግን የአኗኗር ለውጥ ይፈልጋል። ማንኛውም መድኃኒት ወይም የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል" ብለዋል። "ስለዚህ ክብደት ለመቀነስ ከመሞከርዎ በፊት ከጤና ባለሙያ ጋር መነጋገሩ ሁል ጊዜም ብልህነት ነው" ሲሉም አስረድተዋል፡፡ | የምግብ ፍላጎት የሚቀንሰው መድኃኒት ከመጠን በላይ ውፍረትን እንደሚቀንስ ተነገረ የምግብ ፍላጎትን የሚቀንሰው መድኃኒት አንዳንድ ሰዎች ከአንድ አምስተኛ በላይ የሰውነት ክብደታቸውን እንዲቀንሱ አድርጓቸዋል ሲል አንድ ዓለም አቀፍ ጥናት አስታወቀ፡፡ ሴማግሉታይድ የተሰኘው እና በየሳምንቱ የሚሰጠው መድኃኒት ከአመጋገብ እና ከአካል ብቃት ምክሮች ጎን ለጎን ተሰጥቷል፡፡ ወደ 2,000 የሚጠጉ ሰዎች ላይ በተደረገው ጥናት በአማካይ 15 ኪሎ ግራም ክብደት በ15 ወር የሙከራ ጊዜ መቀነሱ ታይቷል፡፡ ባለሙያዎች ውጤቱ ከመጠን በላይ ውፍረትን ለማከም "የአዲስ ምዕራፍ" ምልክት ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡ ከኬንት የመጣችው ጃን ከሰውነት ክብደቷ ከአንድ አምስተኛው በላይ የሚሆነውን 28 ኪሎ ግራም ቀንሳለች፡፡ "መድኃኒቱ ሕይወቴን የቀየረ ሲሆን ለምግብ ያለኝን ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ቀይሯል" ብላለች፡፡ ምግብ መቀነስ ለጉዳት እንደዳረጋት ተናግራ፤ ረሃብ ስለማይሰማት መድኃኒቱን መውሰድ "ፍፁም የተለየ ነበር" ስትል ገልጻለች፡፡ 'ጥረት የማይፈልግ' ጃን አሁን ከሙከራው ስለወጣች የምግብ ፍላጎቷ ተመልሶ ክብደቷ እየጨመረ ይገኛል። "በሙከራው ጊዜ ክብደት መቀነስ ምንም ጥረት እንደማይፈልግ ቢሰማኝም አሁን ግን ከምግብ ጋር የማያቋርጥ ወደሚመስል ውጊያ እንደመመለስ ነው" ብላለች፡፡ ሴማግሉታይድ ለሁለተኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ሕክምና ይውል ስለነበር በአንዳንድ ሰዎች ቀድሞውኑ ቢታወቅም በዚህ ሙከራ ግን በከፍተኛ መጠን መሰጠቱ ተመልክቷል፡፡ መድኃኒቱ የሚሠራው የሰውነትን የምግብ ፍላጎት በመቀነስ እና ምግብ ከተመገቡ በኋላ ሆድ መሙላቱን የሚያሳውቀውን ሆርሞን የሚለቅበትን ሂደት በማስመሰል ነው፡፡ በኒው ኢንግላንድ ጆርናል ኦፍ ሜዲስን ይፋ በተደረጉት ውጤቶች መሠረት በሴማግሉታይድ የታገዙት ሰዎች በአማካይ 15 ኪሎ ግራም ክብደት የቀንሰዋል፡፡ 'አዲስ ዘመን' ከተመራማሪዎቹ አንዷ የሆኑት ፕሮፌሰር ሪቼል ባተርሃም ለቢቢሲ እንደተናገሩት "የሚያስከትለው የክብደት መቀነስ መጠን በዘርፉ ለውጥ ያመጣል።" "ላለፉት 20 ዓመታት ከመጠን ባለፈ ውፍረት ዙሪያ ጥናት ሳካሂድ ቆይቻለሁ። እስከ አሁን ከቀዶ ህክምና ውጭ ከመጠን ያለፈ ውፍረትን ለመከላከል ውጤታማ ህክምና አላገኘንም" ብለዋል። ክብደትን መቀነስ የልብ ህመም፣ የስኳር እና የኮቪድ -19 ተጋላጭነትን እንደሚቀንስ ተናግረዋል፡፡ ሴማግሉታይድ ለመድኃኒት ተቆጣጣሪዎች እየቀረበ ስለሆነም በመደበኛነት ሊታዘዝ አይችልም፡፡ እንደ ፕሮፌሰር ባተርሃም ከሆነ መድኃኒቱ መጀመሪያ ላይ በስፋት ለገበያ ከመቅረቡ በፊት በልዩ ባለሙያ ክብደት መቀነስ ላይ በሚሠሩ ክሊኒኮች ጥቅም ላይ እንደሚውል ይጠበቃል፡፡ በሕክምናው ላይ ማቅለሽለሽ፣ ተቅማጥ፣ ማስታወክ እና የሆድ ድርቀት የመሳሰሉ የጎንዮሽ ጉዳቶች ነበሩ፡፡ በተጨማሪም ክብደት መቀነሱ በረዥም ጊዜ ውስጥ ሊቆይ የሚችል መሆኑን ለመመልከትም የአምስት ዓመት ጥናቶች አሉ፡፡ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ስቴፈን ኦራሂሊይ እንደተናገሩት "የተገኘው የክብደት መቀነስ መጠን ፈቃድ ከተሰጠው የፀረ ውፍረት መድኃኒት አንጻር ውጤቱ ትልቅ ነው" ብለዋል፡፡ "ወደፊት የጎንዮሽ ጉዳቶቹ ያነሱ የክብደት መቀነስ ደረጃዎችን ለማሳካት የአዲስ ዘመን ጅማሬ ነው" ሲሉ ገልጸዋቀል፡፡ የሥነ ምግብ ባለሙያው እና የአስቶን ሜዲካል ትምህርት ቤቱ ዶ/ር ዱአን ሜሎር "ሰዎች ክብደታቸውን እንዲቀንሱ የሚያግዝ አማራጭ መኖሩ ጠቃሚ ነው። ክብደትን ለመቀነስ አሁንም ግን የአኗኗር ለውጥ ይፈልጋል። ማንኛውም መድኃኒት ወይም የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን እና የጎንዮሽ ጉዳቶችን ሊያመጣ ይችላል" ብለዋል። "ስለዚህ ክብደት ለመቀነስ ከመሞከርዎ በፊት ከጤና ባለሙያ ጋር መነጋገሩ ሁል ጊዜም ብልህነት ነው" ሲሉም አስረድተዋል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/56027723 |
3politics
| የጣሊያኗ ጆርጂያ ሜሎኒ የቀኝ አክራሪ መንግሥት ሊመሠርቱ ነው | የጣሊያን ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ጆርጂያ ሜሎኒ መንግሥት ለመመሥረት በይፋ ፍቃደኝነታቸውን ገለጹ። አንድ ቀኝ አክራሪ ብሔርተኛ ፓርቲ በጣሊያን መንግሥት ሲመሠርት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ፕሬዝዳንት ሰርጊዮ ማታሬላ ጆርጂያ ሜሎኒ መንግሥት እንዲመሠርቱ የጠየቁት ፓርቲያቸው ‘ብራዘለርስ ኦፍ ኢታሊ’ ምርጫ ማሸነፉነት ተከትሎ ነው። ጆርጂያ ሜሎኒ የመጀመርያዋ የጣሊያን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በይፋ ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት በመጪው ቅዳሜ ነው። ሥልጣን የሚረከቡት ደግሞ ጣሊያንን በአስቸጋሪው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ ከመሯት ማሪዮ ድራጊ ነው። የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል የሆነችው ጣሊያን በአውሮፓ ኅብረት አባላት ሦስተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ናት። ጆርጂያ ሜሎኒ በውጭ ፖሊሲ ረገድ ምንም ለውጥ እንደማያደርጉ ቃል ገብተዋል። ሜሎኒ በነጭ ፊያት መኪና ወደ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ተጉዘው ለአንድ ሰዓት ያህል ከፕሬዝዳንቱ ጋር ከተወያዩ በኋላ ከቤተ መንግሥት ወጥተው ካቢኔያቸውን አሳውቀዋል። በካቢኔዋ ውስጥ የማቴዎ ሳልቪኒ ቀኝ አክራሪ ሊግ ፓርቲ እና የ86 ዓመቱ ሲልቪዮ በርለስኮኒ ፓርቲ ፎርዛ ኢታሊያ ተካቶበታል። አወዛጋቢው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጋዳፊ ወዳጅ የነበሩት ሲልቪዮ በርልስኮኒ የፑቲን ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የተናገሩበት የድምጽ ቅጂ ሾልኮ ከወጣ በኋላ በጣሊያን ጆርጂያ ሜሎኒ ሊመሠረቱት የነበረው መንግሥት መጠነኛ መንገጫገጭ ተፈጥሮበት ነበር። የፓርቲዎቹ መሪዎች ከፕሬዝዳንት ማታሬላ ጋር አርብ ለ11 ደቂቃዎች ያህል ከተወያዩ በኋላ ጆርጂያ በሰጡት መግለጫ ጣሊያናዊያን በአዲሱ መንግሥት ሊተማመኑ ይገባል ብለዋል። ጨምረውም፣ "አዲሱ መንግሥት በብቃት ችግሮችን የሚጋፈጥና መፍትሄ የሚሰጥ ይሆናል" ብለዋል። ጆርጂያ ካዋቀሩት ካቢኔ ከ24 ሚኒስትሮች ውስጥ ስድስቱ ብቻ ሴቶች ናቸው። ከነዚህም መሀል የቤተሰብና የወሊድ ምጣኔ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ኡጌንያ ሮሴላ ይገኙበታል። እኚህ ሴት ጽንስ ማቋረጥን የሚቃወሙ ናቸው። አዲሱ የአካባቢ ጉዳዮች ሚኒስትር ሮቤርቶ ካልዴሮሊ በዘረኛ ንግግራቸው የሚታወቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም የመጀመርያ ጥቁር የካቢኔ አባል የነበሩን ሰው ‘ዝንጀሮ’ ብለው የተሳደቡ ናቸው። ሲልቪዮ በርልስኮኒ ምንም እንኳ በካቢኔው ባይካተቱም ይህን ጥምር መንግሥት ችግር ውስጥ ከተውት ቆይተዋል። ይህም የሆነው የፑቲን ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የተናገሩበት ድምጽ ቅጂ ሾልኮ መውጣቱን ተከትሎ ነው። የ86 ዓመቱ በርልስኮኒ ቪላድሚር ፑቲን "20 ጠርሙስ ምን የመሰለ ቮድካ ለልደቴ ልኮልኛል" ካሉ በኋላ "እኔ ከፑቲን አምስት ምርጥ ወዳጆቹ አንዱ ነኝ" ሲሉ ተሰምቷል። ከዚህም ሌላ በርልስኮኒ የዩክሬንን ፕሬዝዳንት ሲያወግዙ፤ ምዕራባዊያንን ሲያንቋሽሹና ፑቲንን ሲያንቆለጳጵሱ በሾለከው የድምጽ ቅጂ ይሰማል። ሆኖም በርልስኮኒ ነገሩ ከአውድ ውጭ ተወስዶብኛል፤ ጣሊያንና ምዕራቡ በዩክሬን ጉዳይ የያዘውን አቋም እደግፋለሁ ሲሉ አስተባብለዋል። ሌላው በጆርጂያ ሜሎኒ ካቢኔ ውስጥ የተካተቱት ማቴዎ ሳልቪኒም የረዥም ጊዜ የፑቲን አድናቂ ናቸው። ሆኖም ጆርጂያ ሜሎኒ ጥምር መንግሥት ለመመሥረት የግድ እርሳቸውን ማካተት ነበረባቸው። ጆርጂያ ሜሎኒ የ45 ዓመት ሴት ሲሆኑ በጸረ ስደተኛ አቋማቸው የሚታወቁ ናቸው። የመጀመርያ ሥራቸው የሚሆነው ጣሊያናዊያን የኃይል ወጪያቸውን ዝቅ ማድረግ ነው። ከሊቢያ ወደ ጣሊያን የሚገቡ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ለማቆም በሜዲትራኒያን የባሕር ኃይል አዘምታለሁ ብለዋል ሜሎኒ። የሜሎኒ ፓርቲ መሥራችና አዲስ የሴኔቱ አፈ ጉባኤ የሆኑት ሰው፣ የፋሺስት ቤኒቶ ሞሶሎኒ ከፍተኛ አፍቃሪ ናቸው። የጆርጂያ ሜሎኒ ፓርቲ፣ ብራዘርስ ኦፍ ኢታሊ ራሱ ከፋሽስቱ ሞሶሎኒ ዘመን የሚመዘዝ ታሪክ አለው። | የጣሊያኗ ጆርጂያ ሜሎኒ የቀኝ አክራሪ መንግሥት ሊመሠርቱ ነው የጣሊያን ቀኝ አክራሪ ፓርቲ መሪ ጆርጂያ ሜሎኒ መንግሥት ለመመሥረት በይፋ ፍቃደኝነታቸውን ገለጹ። አንድ ቀኝ አክራሪ ብሔርተኛ ፓርቲ በጣሊያን መንግሥት ሲመሠርት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለመጀመርያ ጊዜ ነው። ፕሬዝዳንት ሰርጊዮ ማታሬላ ጆርጂያ ሜሎኒ መንግሥት እንዲመሠርቱ የጠየቁት ፓርቲያቸው ‘ብራዘለርስ ኦፍ ኢታሊ’ ምርጫ ማሸነፉነት ተከትሎ ነው። ጆርጂያ ሜሎኒ የመጀመርያዋ የጣሊያን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በይፋ ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት በመጪው ቅዳሜ ነው። ሥልጣን የሚረከቡት ደግሞ ጣሊያንን በአስቸጋሪው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጊዜ ከመሯት ማሪዮ ድራጊ ነው። የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) አባል የሆነችው ጣሊያን በአውሮፓ ኅብረት አባላት ሦስተኛዋ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባለቤት ናት። ጆርጂያ ሜሎኒ በውጭ ፖሊሲ ረገድ ምንም ለውጥ እንደማያደርጉ ቃል ገብተዋል። ሜሎኒ በነጭ ፊያት መኪና ወደ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ተጉዘው ለአንድ ሰዓት ያህል ከፕሬዝዳንቱ ጋር ከተወያዩ በኋላ ከቤተ መንግሥት ወጥተው ካቢኔያቸውን አሳውቀዋል። በካቢኔዋ ውስጥ የማቴዎ ሳልቪኒ ቀኝ አክራሪ ሊግ ፓርቲ እና የ86 ዓመቱ ሲልቪዮ በርለስኮኒ ፓርቲ ፎርዛ ኢታሊያ ተካቶበታል። አወዛጋቢው የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጋዳፊ ወዳጅ የነበሩት ሲልቪዮ በርልስኮኒ የፑቲን ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የተናገሩበት የድምጽ ቅጂ ሾልኮ ከወጣ በኋላ በጣሊያን ጆርጂያ ሜሎኒ ሊመሠረቱት የነበረው መንግሥት መጠነኛ መንገጫገጭ ተፈጥሮበት ነበር። የፓርቲዎቹ መሪዎች ከፕሬዝዳንት ማታሬላ ጋር አርብ ለ11 ደቂቃዎች ያህል ከተወያዩ በኋላ ጆርጂያ በሰጡት መግለጫ ጣሊያናዊያን በአዲሱ መንግሥት ሊተማመኑ ይገባል ብለዋል። ጨምረውም፣ "አዲሱ መንግሥት በብቃት ችግሮችን የሚጋፈጥና መፍትሄ የሚሰጥ ይሆናል" ብለዋል። ጆርጂያ ካዋቀሩት ካቢኔ ከ24 ሚኒስትሮች ውስጥ ስድስቱ ብቻ ሴቶች ናቸው። ከነዚህም መሀል የቤተሰብና የወሊድ ምጣኔ ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ኡጌንያ ሮሴላ ይገኙበታል። እኚህ ሴት ጽንስ ማቋረጥን የሚቃወሙ ናቸው። አዲሱ የአካባቢ ጉዳዮች ሚኒስትር ሮቤርቶ ካልዴሮሊ በዘረኛ ንግግራቸው የሚታወቁ ሲሆን ከዚህ ቀደም የመጀመርያ ጥቁር የካቢኔ አባል የነበሩን ሰው ‘ዝንጀሮ’ ብለው የተሳደቡ ናቸው። ሲልቪዮ በርልስኮኒ ምንም እንኳ በካቢኔው ባይካተቱም ይህን ጥምር መንግሥት ችግር ውስጥ ከተውት ቆይተዋል። ይህም የሆነው የፑቲን ቀንደኛ ደጋፊ መሆናቸውን የተናገሩበት ድምጽ ቅጂ ሾልኮ መውጣቱን ተከትሎ ነው። የ86 ዓመቱ በርልስኮኒ ቪላድሚር ፑቲን "20 ጠርሙስ ምን የመሰለ ቮድካ ለልደቴ ልኮልኛል" ካሉ በኋላ "እኔ ከፑቲን አምስት ምርጥ ወዳጆቹ አንዱ ነኝ" ሲሉ ተሰምቷል። ከዚህም ሌላ በርልስኮኒ የዩክሬንን ፕሬዝዳንት ሲያወግዙ፤ ምዕራባዊያንን ሲያንቋሽሹና ፑቲንን ሲያንቆለጳጵሱ በሾለከው የድምጽ ቅጂ ይሰማል። ሆኖም በርልስኮኒ ነገሩ ከአውድ ውጭ ተወስዶብኛል፤ ጣሊያንና ምዕራቡ በዩክሬን ጉዳይ የያዘውን አቋም እደግፋለሁ ሲሉ አስተባብለዋል። ሌላው በጆርጂያ ሜሎኒ ካቢኔ ውስጥ የተካተቱት ማቴዎ ሳልቪኒም የረዥም ጊዜ የፑቲን አድናቂ ናቸው። ሆኖም ጆርጂያ ሜሎኒ ጥምር መንግሥት ለመመሥረት የግድ እርሳቸውን ማካተት ነበረባቸው። ጆርጂያ ሜሎኒ የ45 ዓመት ሴት ሲሆኑ በጸረ ስደተኛ አቋማቸው የሚታወቁ ናቸው። የመጀመርያ ሥራቸው የሚሆነው ጣሊያናዊያን የኃይል ወጪያቸውን ዝቅ ማድረግ ነው። ከሊቢያ ወደ ጣሊያን የሚገቡ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ለማቆም በሜዲትራኒያን የባሕር ኃይል አዘምታለሁ ብለዋል ሜሎኒ። የሜሎኒ ፓርቲ መሥራችና አዲስ የሴኔቱ አፈ ጉባኤ የሆኑት ሰው፣ የፋሺስት ቤኒቶ ሞሶሎኒ ከፍተኛ አፍቃሪ ናቸው። የጆርጂያ ሜሎኒ ፓርቲ፣ ብራዘርስ ኦፍ ኢታሊ ራሱ ከፋሽስቱ ሞሶሎኒ ዘመን የሚመዘዝ ታሪክ አለው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c16xn3wrk44o |
5sports
| ጋና ከኢትዮጵያ ጋር አቻ በመለያየቷ ለዓለም ዋንጫ የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ | ጋና ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያካሄደችውን ጨዋታ አንድ አቻ መለያየቷን ተከትሎ ኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ውድድር የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። የጋና ብሔራዊ ቡድን አምበል አንደሬ አዩ በመጀመሪያው አጋማሽ ከቅጣት ምት አስደናቂ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን በሁለተኛ አጋማሽ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አምበል ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያን አቻ ማድረግ ችሏል። በመድቡ 4 ነጥብ ብቻ ያላቸው ዋሊያዎቹ ቀድሞውኑ ከውድድሩ ውጪ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ 9 ነጥብ የነበራት ጋና ግን ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ጨዋታ አሸንፋ ለዓለም ዋንጫ ውድድር ተሳታፊነት ግስጋሴዋን የምታቀናበት ጨዋታ ይሆናል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ስታዲየም የላትም ተብላ በደቡብ አፍሪካ ለመጫወት የተገደደችው ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ነጥብ ተጋርታለች። ጋና እና ኢትዮጵያ በሚገኙበት ምድብ ደቡብ አፍሪካ አንድ ጨዋታ እየቀራት 10 ነጥብ ያላት ሲሆን፤ ዚምባብዌ በተመሳሳይ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለት በ1 ነጥብ መጨረሻ ላይ ተቀምጣለች። ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ዚምባብዌን በሜዳዋ የምታስተናግድ ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ ይህን ጨዋታ የምታሸንፍ ከሆነ ምድቡን በአንድኛነት ትጨርሳለች። የአፍሪካ አገራት በ10 ምድብ ሲጫወቱ የቆዩ ሲሆን፤ ከየምድቡ አንደኛ ሆነው የሚጨርሱት ከአራት ወራት በኋላ በደርሶ መልስ ተለይተው አምስት አገራት ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ አፍሪካን ወክለው ይቀርባሉ። እስካሁን ድረስ ማሊ፣ ግብፅ፣ ሴኔጋል እና ሞሮኮ ከምድባቸው በአንደኛነት ማለፋቸውን ያረጋገጡ አገራት ናቸው። | ጋና ከኢትዮጵያ ጋር አቻ በመለያየቷ ለዓለም ዋንጫ የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገባ ጋና ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያካሄደችውን ጨዋታ አንድ አቻ መለያየቷን ተከትሎ ኳታር ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ውድድር የማለፍ እድሏ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። የጋና ብሔራዊ ቡድን አምበል አንደሬ አዩ በመጀመሪያው አጋማሽ ከቅጣት ምት አስደናቂ ጎል ያስቆጠረ ሲሆን በሁለተኛ አጋማሽ ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ አምበል ጌታነህ ከበደ ኢትዮጵያን አቻ ማድረግ ችሏል። በመድቡ 4 ነጥብ ብቻ ያላቸው ዋሊያዎቹ ቀድሞውኑ ከውድድሩ ውጪ መሆናቸው የተረጋገጠ ሲሆን፤ 9 ነጥብ የነበራት ጋና ግን ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን ጨዋታ አሸንፋ ለዓለም ዋንጫ ውድድር ተሳታፊነት ግስጋሴዋን የምታቀናበት ጨዋታ ይሆናል ተብሎ ተጠብቆ ነበር። ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀ ስታዲየም የላትም ተብላ በደቡብ አፍሪካ ለመጫወት የተገደደችው ኢትዮጵያ ከጋና ጋር ነጥብ ተጋርታለች። ጋና እና ኢትዮጵያ በሚገኙበት ምድብ ደቡብ አፍሪካ አንድ ጨዋታ እየቀራት 10 ነጥብ ያላት ሲሆን፤ ዚምባብዌ በተመሳሳይ አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለት በ1 ነጥብ መጨረሻ ላይ ተቀምጣለች። ደቡብ አፍሪካ ዛሬ ምሽት አራት ሰዓት ላይ ዚምባብዌን በሜዳዋ የምታስተናግድ ሲሆን፤ ደቡብ አፍሪካ ይህን ጨዋታ የምታሸንፍ ከሆነ ምድቡን በአንድኛነት ትጨርሳለች። የአፍሪካ አገራት በ10 ምድብ ሲጫወቱ የቆዩ ሲሆን፤ ከየምድቡ አንደኛ ሆነው የሚጨርሱት ከአራት ወራት በኋላ በደርሶ መልስ ተለይተው አምስት አገራት ኳታር ለምታዘጋጀው የዓለም ዋንጫ አፍሪካን ወክለው ይቀርባሉ። እስካሁን ድረስ ማሊ፣ ግብፅ፣ ሴኔጋል እና ሞሮኮ ከምድባቸው በአንደኛነት ማለፋቸውን ያረጋገጡ አገራት ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/news-59249766 |
2health
| የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስን ዳግም ዕጩ አድርጎ አቀረበ | የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ዳግም ለቀጣይ አምስት ዓመታት በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ዕጩ አደረገ። ድርጅቱን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዶ/ር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ውጤትም ግንቦት 2014 ዓ.ም. ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ኃላፊነታቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ከመረከባቸው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የጤና ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ዶ/ር ቴድሮስ ከአምስት ዓመታት በፊት ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የኢትዮጵያ ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። ይሁን እንጂ የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነታቸውን ተጠቅመው ለህወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ ሲል በተደጋጋሚ ከሷቸዋል። የዓለም ጤና ደርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በጄኔቭ ለስበሰባ ከመቀመጡ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ ገለልተኝነት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቦርዱ በዳይሬክተሩ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የቀረበውን የኢትዮጵያ ጥያቄ ወደ ጎን በመግፋት ሳይመለከተው ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅትን ለመምራት ዕጩ በሆኑበት ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተጠራ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት አቤቱታውን ያልተመለከቱበትን ምክንያት ገልጸዋል። "ይህ ጉዳይ በጣም የተወሳሰበና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው፤ ከዚህ ኮሚቴ የአስራር ማዕቀፍ ውጪ ነው" አሞት ያሉ ሲሆን፤ የቦርዱ 34 አባላት በሙሉ የምርመራ ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በጉዳዩ ላይ በተወያየበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ የአገራቸውን አቤቱታ ለማብራራት በመከሩበት ጊዜ እንዲያቋርጡ ተደርገው ነበር። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ውሳኔው የዓለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አለመሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቃል አቀባዩ የዓለም ጤና ድርጅት በዶ/ር ቴድሮስ ላይ ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ይጠይቃልም ሲሉ ለሮይተርስ ጨምረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የድርጅቱን ነፃነት፣ ገለልተኝነት መርህ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት በመጠየቅ ምርመራ እንዲደረግ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በትግራይ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓመታት አባልና አመራር የነበሩበትን ህወሓት የሚደግፉ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ሲሉ ሲከሱ ቆይተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እና የዓለም ጤና ድርጅት የቢቢሲ የጄኔቭ ዘጋቢ ኦሞጂን ፉክስ እንዳለችው የትኛውም የከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር እንደ ዶ/ር ቴድሮስ አልተፈተነም። የኮቪድ-19 ወረርሸኝ፣ ቻይና ስለ ወረርሽኑ መረጃ እንድታጋራ ጫና ማድረግ፣ ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፈጠረው እሰጣገባ፣ የአሜሪካ ድጋፍ ማቆም እና ከድርጅቱ አባልነት መውጣት በቀዳሚነት የሚወጠቀሱ ሲሆን። ለአንድ ዓመት የዘለቀው የትግራዩ ጦርነት በግል ያደረሰባቸው ጫና እና ከትውልድ አገራቸው መንግሥት ጋር የገቡት ቅሬታ የዶ/ር ቴድሮስ ፈተናዎች ከነበሩት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዝርያውን እየቀረ ዓለም ማሸበሩን አላቆመም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሁንም የኮቪድ ክትባትን አልወሰዱም። የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ፈጽመውታል በተባለው የጾታ ጥቃት የድርጅቱን የከበረ ስም አጉዱፏል። በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የትራምፕን ውሳኔ በመቀልበስ አሜሪካን ወደ የዓለም ጤና ድርጅት አባልነት መልሰዋል። አሜሪካ ለድርጅቱ የምታደርገው ከፍተኛ ድጋፍም ቀጥሏል። በውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፉት ዶ/ር ቴድሮስ ግዙፉን የጤና ድርጅት ለሌላ አምስት ዓመታት የመምራት ጽኑ ፍላጎት አላቸው ተብሏል። | የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስን ዳግም ዕጩ አድርጎ አቀረበ የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ድርጅቱን ዳግም ለቀጣይ አምስት ዓመታት በዳይሬክተርነት እንዲመሩ ዕጩ አደረገ። ድርጅቱን ለሁለተኛ ዙር ለመምራት ዶ/ር ቴድሮስ ያለተፎካካሪ ብቸኛ ዕጩ ሆነው የቀረቡ ሲሆን የመጨረሻው ውጤትም ግንቦት 2014 ዓ.ም. ላይ ይፋ ይደረጋል ተብሏል። ዶ/ር ቴድሮስ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ኃላፊነታቸውን ከአምስት ዓመት በፊት ከመረከባቸው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የጤና ሚኒስትር ሆነው ማገልገላቸው ይታወሳል። ዶ/ር ቴድሮስ ከአምስት ዓመታት በፊት ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ የኢትዮጵያ ድጋፍ አልተለያቸውም ነበር። ይሁን እንጂ የትግራዩን ጦርነት ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ኃላፊነታቸውን ተጠቅመው ለህወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ ሲል በተደጋጋሚ ከሷቸዋል። የዓለም ጤና ደርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ በጄኔቭ ለስበሰባ ከመቀመጡ በፊት የኢትዮጵያ መንግሥት በዶ/ር ቴድሮስ ገለልተኝነት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጥያቄ ማቅረቡ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ቦርዱ በዳይሬክተሩ ላይ ምርመራ እንዲደረግ የቀረበውን የኢትዮጵያ ጥያቄ ወደ ጎን በመግፋት ሳይመለከተው ቀርቷል። ዶ/ር ቴድሮስ ለሁለተኛ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅትን ለመምራት ዕጩ በሆኑበት ጉዳይ ላይ ለመወያየት በተጠራ የሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ ፓትሪክ አሞት አቤቱታውን ያልተመለከቱበትን ምክንያት ገልጸዋል። "ይህ ጉዳይ በጣም የተወሳሰበና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው፤ ከዚህ ኮሚቴ የአስራር ማዕቀፍ ውጪ ነው" አሞት ያሉ ሲሆን፤ የቦርዱ 34 አባላት በሙሉ የምርመራ ጥያቄውን ሳይቀበሉት ቀርተዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በጉዳዩ ላይ በተወያየበት ጊዜ የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ የአገራቸውን አቤቱታ ለማብራራት በመከሩበት ጊዜ እንዲያቋርጡ ተደርገው ነበር። ይህንንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም ጤና ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ በድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ንግግር እንዳያደርጉ መከልከሉ ተቀባይነት የሌለው ነው ሲል ተቃውሞውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ለገሰ ቱሉ ውሳኔው የዓለም ጤና ድርጅት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛ አለመሆኑን ማሳያ ነው ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ቃል አቀባዩ የዓለም ጤና ድርጅት በዶ/ር ቴድሮስ ላይ ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ይጠይቃልም ሲሉ ለሮይተርስ ጨምረው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት የድርጅቱን ነፃነት፣ ገለልተኝነት መርህ ጥያቄ ውስጥ እንደከተቱት በመጠየቅ ምርመራ እንዲደረግ አቤቱታ አቅርቦ ነበር። በትግራይ ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሲቪልና ወታደራዊ ባለሥልጣናት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ለዓመታት አባልና አመራር የነበሩበትን ህወሓት የሚደግፉ ተግባራት ላይ ተሳትፈዋል ሲሉ ሲከሱ ቆይተዋል። ዶ/ር ቴድሮስ እና የዓለም ጤና ድርጅት የቢቢሲ የጄኔቭ ዘጋቢ ኦሞጂን ፉክስ እንዳለችው የትኛውም የከዚህ ቀደም የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር እንደ ዶ/ር ቴድሮስ አልተፈተነም። የኮቪድ-19 ወረርሸኝ፣ ቻይና ስለ ወረርሽኑ መረጃ እንድታጋራ ጫና ማድረግ፣ ከቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር የተፈጠረው እሰጣገባ፣ የአሜሪካ ድጋፍ ማቆም እና ከድርጅቱ አባልነት መውጣት በቀዳሚነት የሚወጠቀሱ ሲሆን። ለአንድ ዓመት የዘለቀው የትግራዩ ጦርነት በግል ያደረሰባቸው ጫና እና ከትውልድ አገራቸው መንግሥት ጋር የገቡት ቅሬታ የዶ/ር ቴድሮስ ፈተናዎች ከነበሩት መካከል ተጠቃሽ ናቸው። አሁንም ቢሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዝርያውን እየቀረ ዓለም ማሸበሩን አላቆመም፤ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አሁንም የኮቪድ ክትባትን አልወሰዱም። የዓለም ጤና ድርጅት ሠራተኞች በዲሞክራቲክ ኮንጎ ፈጽመውታል በተባለው የጾታ ጥቃት የድርጅቱን የከበረ ስም አጉዱፏል። በሌላ በኩል ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የትራምፕን ውሳኔ በመቀልበስ አሜሪካን ወደ የዓለም ጤና ድርጅት አባልነት መልሰዋል። አሜሪካ ለድርጅቱ የምታደርገው ከፍተኛ ድጋፍም ቀጥሏል። በውጣ ውረዶች ውስጥ ያለፉት ዶ/ር ቴድሮስ ግዙፉን የጤና ድርጅት ለሌላ አምስት ዓመታት የመምራት ጽኑ ፍላጎት አላቸው ተብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60133588 |
5sports
| ኢትዮጵያ የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታሪኳ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት አስመዘገበች | በኮሎምቢያ ካሊ ለስድስት ቀናት ከሐምሌ 25- ሐምሌ 30 2014 ዓ.ም በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ሶስተኛ ሆና አጠናቀቀች። ኢትዮጵያ በስድስት ወርቅ፣ በአምስት ብር እና አንድ ነሃስ ሜዳሊያ በአጠቃላይ በ12 ሜዳሊያዎች አሜሪካንና ጃማይካንም ተከትላ ነው በሶስተኛነት ያጠናቀቀችው። ይህም ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ የተመዘገበ ውጤት ከፍተኛው እንደሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። “ዘንድሮ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛው ሲሆን ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው” ብሏል ፌዴሬሽኑ በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው በዚህ ውድድር አሜሪካ በሰባት ወርቅ፣ በአራት ብርና በአራት ነሐስ ሜዳሊያ በ15 ሜዳሊያዎች በአንደኛነት አጠናቃለች። እሷንም ተከትላ ጃማይካ በስድስት ወርቅ፣ በሰባት ብርና በሶስት ነሃስ በአጠቃላይ 16 ሜዳሊያዎች በማግኘት ከፍተኛውን የሜዳሊያ ቁጥር ብትይዝም በአሜሪካ በወርቅ ተበልጣ በሁለተኛነት አጠናቃለች። አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ ሶስት ወርቅ፣ ሶስት ብርና አራት ነሐስ በማግኘት በአጠቃላይ በአስር ሜዳሊያዎች በአራተኛነት ውድድሩን ማጠናቀቋን ከአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል። በዚህ በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ የሻምፒዮና ውድድር ላይ ኤርምያስ ግርማ በ800 ሜትር ወርቅ በማግኘት እንዲሁም በ1500 ሜትር ብር በማግኘት የጥምር ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆኗል። በአንድ ሺህ ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር ብርቄ ሃየሎም የሻምፒዮኑንሺፕ ክብረ ወሰን በማሻሻል በአንደኛነት ወርቅ አስመዝግባለች። ሴት አትሌቶች በደመቁበትና በቅርቡ በተደረገው የኦሪጎን አትሌቲክሽ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአስር ሜዳሊያዎች በታሪኳ ከፍተኛውን ሜዳሊያ ማስመዝገቧ ይታወሳል። ኢትዮጵያ በ4ወርቅ፣ በ4ብርና በ2 ነሃስ ከአዘጋጇ አሜሪካ በመቀጠል ከዓለም 2ኛ ደረጃ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል። የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወይም የአለም ጁኒየር የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ20 አመት በታች ባሉ አትሌቶች የሚደረግ አለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ነው። ባለፈው አመት በነበረው ውድድር ኬንያ በስምንት ወርቅ በአጠቃላይ በአስራ ስድስት ሜዳሊያ በአንደኛነት ነበር ያጠናቀቀችው፣ ኢትዮጵያ በወቅቱ ሶስት ወርቅ፣ ሰባት ብር፣ ሁለት ነሐስ በአጠቃላይ 12 ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን በአራተኝነት ነበር ማጠናቀቋ ይታወሳል። በዘንድሮው አመት በ5000 ሜትር ብር ያስገኘችው መልክናት ውድ ባለፈው አመት ሁለት ሜዳልያዎችን አስገኝታ ነበር። ከ20 አመት በታች ለተደረገው የሻምፒዮንሺፕ ውድድር ኢትዮጵያ 19 አትሌቶችን መላኳን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን በሁለቱም ጾታዎች በአስር አይነት ውድድሮች ተሳትፈዋል። ለስድስት ቀናት በካሉሊ ኮሎምቢያ በተደረገው ውድድር በአጠቃላይ 41 ሃገራት ቢያንስ አንድ ሜዳሊያ ሲያሸንፉ 24 ሃገራት ደግሞ ቢያንስ አንድ ወርቅ ማግኘታቸውን ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። | ኢትዮጵያ የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና በታሪኳ ከፍተኛ የተባለውን ውጤት አስመዘገበች በኮሎምቢያ ካሊ ለስድስት ቀናት ከሐምሌ 25- ሐምሌ 30 2014 ዓ.ም በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ12 ሜዳሊያዎች ከአፍሪካ አንደኛ ከአለም ሶስተኛ ሆና አጠናቀቀች። ኢትዮጵያ በስድስት ወርቅ፣ በአምስት ብር እና አንድ ነሃስ ሜዳሊያ በአጠቃላይ በ12 ሜዳሊያዎች አሜሪካንና ጃማይካንም ተከትላ ነው በሶስተኛነት ያጠናቀቀችው። ይህም ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ታሪክ የተመዘገበ ውጤት ከፍተኛው እንደሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። “ዘንድሮ የተመዘገበው ውጤት ከፍተኛው ሲሆን ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው” ብሏል ፌዴሬሽኑ በትናንትናው ዕለት በተጠናቀቀው በዚህ ውድድር አሜሪካ በሰባት ወርቅ፣ በአራት ብርና በአራት ነሐስ ሜዳሊያ በ15 ሜዳሊያዎች በአንደኛነት አጠናቃለች። እሷንም ተከትላ ጃማይካ በስድስት ወርቅ፣ በሰባት ብርና በሶስት ነሃስ በአጠቃላይ 16 ሜዳሊያዎች በማግኘት ከፍተኛውን የሜዳሊያ ቁጥር ብትይዝም በአሜሪካ በወርቅ ተበልጣ በሁለተኛነት አጠናቃለች። አፍሪካዊቷ አገር ኬንያ ሶስት ወርቅ፣ ሶስት ብርና አራት ነሐስ በማግኘት በአጠቃላይ በአስር ሜዳሊያዎች በአራተኛነት ውድድሩን ማጠናቀቋን ከአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘው መረጃ ያሳያል። በዚህ በተካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ የሻምፒዮና ውድድር ላይ ኤርምያስ ግርማ በ800 ሜትር ወርቅ በማግኘት እንዲሁም በ1500 ሜትር ብር በማግኘት የጥምር ሜዳሊያዎች ባለቤት ሆኗል። በአንድ ሺህ ሜትር የሴቶች ፍጻሜ ውድድር ብርቄ ሃየሎም የሻምፒዮኑንሺፕ ክብረ ወሰን በማሻሻል በአንደኛነት ወርቅ አስመዝግባለች። ሴት አትሌቶች በደመቁበትና በቅርቡ በተደረገው የኦሪጎን አትሌቲክሽ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአስር ሜዳሊያዎች በታሪኳ ከፍተኛውን ሜዳሊያ ማስመዝገቧ ይታወሳል። ኢትዮጵያ በ4ወርቅ፣ በ4ብርና በ2 ነሃስ ከአዘጋጇ አሜሪካ በመቀጠል ከዓለም 2ኛ ደረጃ ከአፍሪካ አንደኛ ደረጃ በመያዝ ማጠናቀቋ ይታወሳል። የዓለም ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወይም የአለም ጁኒየር የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ከ20 አመት በታች ባሉ አትሌቶች የሚደረግ አለም አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ነው። ባለፈው አመት በነበረው ውድድር ኬንያ በስምንት ወርቅ በአጠቃላይ በአስራ ስድስት ሜዳሊያ በአንደኛነት ነበር ያጠናቀቀችው፣ ኢትዮጵያ በወቅቱ ሶስት ወርቅ፣ ሰባት ብር፣ ሁለት ነሐስ በአጠቃላይ 12 ሜዳሊያ በማግኘት ውድድሩን በአራተኝነት ነበር ማጠናቀቋ ይታወሳል። በዘንድሮው አመት በ5000 ሜትር ብር ያስገኘችው መልክናት ውድ ባለፈው አመት ሁለት ሜዳልያዎችን አስገኝታ ነበር። ከ20 አመት በታች ለተደረገው የሻምፒዮንሺፕ ውድድር ኢትዮጵያ 19 አትሌቶችን መላኳን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የተገኘው መረጃ የሚያስረዳ ሲሆን በሁለቱም ጾታዎች በአስር አይነት ውድድሮች ተሳትፈዋል። ለስድስት ቀናት በካሉሊ ኮሎምቢያ በተደረገው ውድድር በአጠቃላይ 41 ሃገራት ቢያንስ አንድ ሜዳሊያ ሲያሸንፉ 24 ሃገራት ደግሞ ቢያንስ አንድ ወርቅ ማግኘታቸውን ከአለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያስረዳል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cyrgemvd2y3o |
5sports
| የኦስካር ሽልማት፡ ዊል ስሚዝ በታላቁ የሽልማት መድረክ ላይ ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ | ተዋናይ ዊል ስሚዝ ኦስካርስ በተሰኘው የፊልም ጥበብ የሽልማት መድረክ የሚስቱን ስም አንስቶ ያብጠለጠለውን ታዋቂውን ኮሜዲያን ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ። ክሪስ ሮክ፤ የዊል ስሚዝ ሚስት ጄዳ ፒንኬት ስሚዝን የፀጉር ቁርጥ በቀልድ ወረፍ ካደረገ በኋላ ነው ይህ የተከሰተው። ዊል ስሚዝ ከመቀመጫው በመነሳት ወደ መድረኩ አቅንቶ ክሪስ ሮክን በጥፊ አጋጭቶ ሲመለስ ብዙዎች ጉዳዩ ቀልድ ነው ብለው አስበው ነበር። ነገር ግን ወደ ወንበሩ ከተመለሰ በኋላ "የሚስቴን ስም በ. . . አፍህ አታንሳ" ብሎ ሲጮህ ነው ብዙዎች ተዋናዩ ማምረሩን የተረዱት። ስሚዝ ከዚህ ብዙዎችን ካስበረገገ ድርጊት በኋላ የኦስካር ሽልማቱን ሲያነሳ ለድርጊቴ ይቅርታ በሉኝ ብሏል። "አካዳሚውን [ኦስካር ሸላሚው ኮሚቴ] እንዲሁም ለሽልማት የታጩ የተውኔት አጋሮቼን ይቅርታ መጠየቅ እሻለሁ" ሲል ተማፅኗል። ዊል ስሚዝ፤ ኪንግ ሪቻርድ በተሰኘው ፊልም ላይ የቴኒስ ከዋክብቱን ቬነስና ሰሪና ዊሊያምስ አባት ሆኖ በመተወኑ ነው በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስም የከበደውን የኦስካር ሽልማት ያገኘው። "ጥበብ የሕይወት ቅጂ ናት። ልክ እንደ ተወንኩት ሪቻርል ዊሊያምስ የእብደት ሥራ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ፍቅር የእብድ ሥራ እንድትሠሩ ያደርጋችኋል።" ባለቤቱ ፒንኬት ስሚዝ ከዚህ በፊት የፀጉር መነቀል የሚያስከትል 'አላፒሺያ' የተሰኘ በሽታ እንዳለባት ተናግራ ነበር። የዊል ስሚዝ ጥፊ ሰላባ የሆነው ክሪስ ሮክ በሁኔታው እጅግ ተደናግጦ "በቴሌቪዥን ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ክስተት ታድመናል" ሲል ተደምጧል። ክሪስ ሮክ ወደ መድረክ የወጣው በምርጥ የዘገባ ፊልም ዘርፍ አሸናፊ ለሆነው ግለሰብ ሽልማት ለመስጠት ነበር። ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ዶልቢ ቲያትር በተባለው ግዙፍ መድረክ ላይ ዊል ስሚዝ የፈፀመው ድርጊት ብዙዎችን አጀብ አሰኝቷል። ብዙዎች ዊል ስሚዝ የሙያ አጋሩን በጥፊ ያጋጨው እየቀለደ እንዳልሆነ የገባቸው ወደ መቀመጫው ተመልሶ አፀያፊ ቃል ከተጠቀመ በኋላ ነው። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን በቴሌቪዥን ሲያሰራጭ የነበረው ኤቢሲ የተሰኘው ጣቢያ ይህን የዊል ስሚዝ ንግግር ከማስተላለፍ ተቆጥቧል። ፒንኬት ስሚዝ ፌስቡክ ላይ በምታሰራጨው ሬድ ቴብል ቶክ በተሰኘው ዝግጅት ላይ ፀጉር የሚያሳጣ በሽታ እንዳለባት ይፋ ያደረገችው ከአራት ዓመታት በፊት ነበር። "ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጉሬን እየታጠብኩ ተነቅሎ ሲወድቅ በጣም ደንግጬ ነበር። ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ ፀጉሬን የምላጨው።" ዊል ስሚዝ የባለቤቱ ስም ተነስቶ ሲብጠለጠል ሊዋጥለት ባለመቻሉ ከኦስካርስ ሽልማት ታሪክ የማይፋቅ ድርጊት ፈፅሟል። ከዚህ ድርጊት ለጥቆ ደግሞ በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦስካር ሽልማት በማንሳት ሌላ ታሪክ ፅፏል። ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረኩ ድጋሚ ካቀና በኋላ የይቅርታ ቃሉን አሰምቶ ንግግር ሲያደርግ አምላኩን አመሰግኗል። "በዚህ ቢዝነስ [የፊልም ዓለም] ውስጥ እስካለን ድረስ ሰዎች ስለኛ የማይሆን ነገር ሲያወሩ ሰምቶ እንዳልሰሙ ማለፍን መቀበል እንዳለብኝ አውቃለሁ። ሰዎች እኛን የሚያንቋሽሽ ነገር ሲያደርጉ ፈገግ ብለን ማለፍ እንዳለብን እረዳለሁ" ብላል ስሚዝ። "መቼም በቀጣይ ዓመትም እንደምትጋብዙኝ ተስፋ አለኝ" በማለት ነው ዊል ስሚዝ ንግግሩን የቋጨው። | የኦስካር ሽልማት፡ ዊል ስሚዝ በታላቁ የሽልማት መድረክ ላይ ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ ተዋናይ ዊል ስሚዝ ኦስካርስ በተሰኘው የፊልም ጥበብ የሽልማት መድረክ የሚስቱን ስም አንስቶ ያብጠለጠለውን ታዋቂውን ኮሜዲያን ክሪስ ሮክን በጥፊ ተማታ። ክሪስ ሮክ፤ የዊል ስሚዝ ሚስት ጄዳ ፒንኬት ስሚዝን የፀጉር ቁርጥ በቀልድ ወረፍ ካደረገ በኋላ ነው ይህ የተከሰተው። ዊል ስሚዝ ከመቀመጫው በመነሳት ወደ መድረኩ አቅንቶ ክሪስ ሮክን በጥፊ አጋጭቶ ሲመለስ ብዙዎች ጉዳዩ ቀልድ ነው ብለው አስበው ነበር። ነገር ግን ወደ ወንበሩ ከተመለሰ በኋላ "የሚስቴን ስም በ. . . አፍህ አታንሳ" ብሎ ሲጮህ ነው ብዙዎች ተዋናዩ ማምረሩን የተረዱት። ስሚዝ ከዚህ ብዙዎችን ካስበረገገ ድርጊት በኋላ የኦስካር ሽልማቱን ሲያነሳ ለድርጊቴ ይቅርታ በሉኝ ብሏል። "አካዳሚውን [ኦስካር ሸላሚው ኮሚቴ] እንዲሁም ለሽልማት የታጩ የተውኔት አጋሮቼን ይቅርታ መጠየቅ እሻለሁ" ሲል ተማፅኗል። ዊል ስሚዝ፤ ኪንግ ሪቻርድ በተሰኘው ፊልም ላይ የቴኒስ ከዋክብቱን ቬነስና ሰሪና ዊሊያምስ አባት ሆኖ በመተወኑ ነው በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለስም የከበደውን የኦስካር ሽልማት ያገኘው። "ጥበብ የሕይወት ቅጂ ናት። ልክ እንደ ተወንኩት ሪቻርል ዊሊያምስ የእብደት ሥራ ሠርቻለሁ። ነገር ግን ፍቅር የእብድ ሥራ እንድትሠሩ ያደርጋችኋል።" ባለቤቱ ፒንኬት ስሚዝ ከዚህ በፊት የፀጉር መነቀል የሚያስከትል 'አላፒሺያ' የተሰኘ በሽታ እንዳለባት ተናግራ ነበር። የዊል ስሚዝ ጥፊ ሰላባ የሆነው ክሪስ ሮክ በሁኔታው እጅግ ተደናግጦ "በቴሌቪዥን ታሪክ እጅግ አስደናቂውን ክስተት ታድመናል" ሲል ተደምጧል። ክሪስ ሮክ ወደ መድረክ የወጣው በምርጥ የዘገባ ፊልም ዘርፍ አሸናፊ ለሆነው ግለሰብ ሽልማት ለመስጠት ነበር። ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ዶልቢ ቲያትር በተባለው ግዙፍ መድረክ ላይ ዊል ስሚዝ የፈፀመው ድርጊት ብዙዎችን አጀብ አሰኝቷል። ብዙዎች ዊል ስሚዝ የሙያ አጋሩን በጥፊ ያጋጨው እየቀለደ እንዳልሆነ የገባቸው ወደ መቀመጫው ተመልሶ አፀያፊ ቃል ከተጠቀመ በኋላ ነው። የሽልማት ሥነ ሥርዓቱን በቴሌቪዥን ሲያሰራጭ የነበረው ኤቢሲ የተሰኘው ጣቢያ ይህን የዊል ስሚዝ ንግግር ከማስተላለፍ ተቆጥቧል። ፒንኬት ስሚዝ ፌስቡክ ላይ በምታሰራጨው ሬድ ቴብል ቶክ በተሰኘው ዝግጅት ላይ ፀጉር የሚያሳጣ በሽታ እንዳለባት ይፋ ያደረገችው ከአራት ዓመታት በፊት ነበር። "ለመጀመሪያ ጊዜ ፀጉሬን እየታጠብኩ ተነቅሎ ሲወድቅ በጣም ደንግጬ ነበር። ለዚህ ነው ብዙውን ጊዜ ፀጉሬን የምላጨው።" ዊል ስሚዝ የባለቤቱ ስም ተነስቶ ሲብጠለጠል ሊዋጥለት ባለመቻሉ ከኦስካርስ ሽልማት ታሪክ የማይፋቅ ድርጊት ፈፅሟል። ከዚህ ድርጊት ለጥቆ ደግሞ በሕይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የኦስካር ሽልማት በማንሳት ሌላ ታሪክ ፅፏል። ሽልማቱን ለመቀበል ወደ መድረኩ ድጋሚ ካቀና በኋላ የይቅርታ ቃሉን አሰምቶ ንግግር ሲያደርግ አምላኩን አመሰግኗል። "በዚህ ቢዝነስ [የፊልም ዓለም] ውስጥ እስካለን ድረስ ሰዎች ስለኛ የማይሆን ነገር ሲያወሩ ሰምቶ እንዳልሰሙ ማለፍን መቀበል እንዳለብኝ አውቃለሁ። ሰዎች እኛን የሚያንቋሽሽ ነገር ሲያደርጉ ፈገግ ብለን ማለፍ እንዳለብን እረዳለሁ" ብላል ስሚዝ። "መቼም በቀጣይ ዓመትም እንደምትጋብዙኝ ተስፋ አለኝ" በማለት ነው ዊል ስሚዝ ንግግሩን የቋጨው። | https://www.bbc.com/amharic/news-60897684 |
5sports
| ኢትዮጵያ፡ የቴኳንዶ ሦስተኛ ዳን ባለቤቱ የአካል ጉዳተኛ ከማል ቃሲም | ነዋሪነቱ በባሕርዳር ከተማ የሆነው ከማል ቃሲም አንድ እግሩን ያጣው በልጅነቱ ከቆመ ታንክ ላይ ሲጫወት ነበር። በአንድ ወቅት ጓደኞቹ ቴኳንዶ ሲሰሩ አይቶ ምነው እንደ እነሱ ሁለት እግር ኖሮኝ ስፖርቱን ሙያዬ ባደረግኩት ብሎ ተመኘ። ቅን አሳቢ ጓደኞቹ ግን በአንድ እግርም ህልሙን እውን ማድረግ እንደሚችል ነገሩት። ለመሞከር አላመነታም። ያኔ እንደዋዛ የጀመረው የቴኳንዶ ስፖርት ዛሬ ሦስተኛ ዳን እንዲደርስ አስችሎታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችንም አሰልጥኗል። | ኢትዮጵያ፡ የቴኳንዶ ሦስተኛ ዳን ባለቤቱ የአካል ጉዳተኛ ከማል ቃሲም ነዋሪነቱ በባሕርዳር ከተማ የሆነው ከማል ቃሲም አንድ እግሩን ያጣው በልጅነቱ ከቆመ ታንክ ላይ ሲጫወት ነበር። በአንድ ወቅት ጓደኞቹ ቴኳንዶ ሲሰሩ አይቶ ምነው እንደ እነሱ ሁለት እግር ኖሮኝ ስፖርቱን ሙያዬ ባደረግኩት ብሎ ተመኘ። ቅን አሳቢ ጓደኞቹ ግን በአንድ እግርም ህልሙን እውን ማድረግ እንደሚችል ነገሩት። ለመሞከር አላመነታም። ያኔ እንደዋዛ የጀመረው የቴኳንዶ ስፖርት ዛሬ ሦስተኛ ዳን እንዲደርስ አስችሎታል። በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችንም አሰልጥኗል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54325094 |
0business
| ኬንያ በጥራት ስጋት ምክንያት ታዋቂ የምግብ ዘይት ምርቶችን አገደች | ኬንያ ከጤናና ጥራት ጋር በተያያዘ ስጋት ምክንያት 10 ታዋቂ የምግብ ዘይት ምርቶች ገበያ ላይ እንዳይውሉ እገዳ ጣለች። የኬንያ ደረጃዎች ተቆጣጣሪ ኬብስ በችርቻሮ ለሚሸጡ ሱቆች እና መገበያያ መደብሮች በጸፈው ደብዳቤ ላይ እነዚህ ምርቶች መደበኛ የጥራት ፈተናዎችን ማለፍ አልቻሉም ብሏል። እነዚህ ምርቶች ከሽያጭ መደርደሪያዎች በአስቸኳይ እንዲወርዱ ትዕዛዝ ተላልፏል። ተቋሙ የተላለፈው ትዕዛዝ ሙሉ እገዳ ሳይሆን አምራቾቹ የተወሰኑ የጥራት መስፈርቶችን እስካሟሉ ድረስ ጊዜያዊ እገዳ መሆኑን አብራርቷል። ትልልቅ የመገበያያ መደብሮችንና ትላልቅ ቸርቻሪዎችን ላቀፈው የኬንያ የችርቻሮ ነጋዴዎች ማህበር ተቋሙ በጻፈው ደብዳቤ የተጠቀሱት የምግብ ዘይት ምርቶች ወደ ገበያ ከመመለሳቸው በፊት የጥራት ማረጋገጫ ማግኘታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባም አሳስቧል። እነዚህ 10 የምግብ ዘይት ምርቶች የሚመረቱ በኬንያ የሚጠቀሱ አራት ትልልቅ የምግብ ዘይት ኩባንያዎች ሲሆኑ እነሱም ቢድኮ አፍሪካ፣ ፕዋኒ የዘይት አምራች፣ ካቻ የዘይት ማጣሪያ እና ሜኔንጋይ የዘይት ማጣሪያ ናቸው። ቢቢሲ ሁለቱን ኩባንያዎች ምላሽ የጠየቃቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ ምላሽ አልሰጡም። ጉዳዩን ለመፍታት ተቋሙ እና ዘይት አምራቾቹ በዛሬው ዕለት አርብ እንደሚገናኙም የኢንዱስትሪ ምንጮች ገልጸዋል። | ኬንያ በጥራት ስጋት ምክንያት ታዋቂ የምግብ ዘይት ምርቶችን አገደች ኬንያ ከጤናና ጥራት ጋር በተያያዘ ስጋት ምክንያት 10 ታዋቂ የምግብ ዘይት ምርቶች ገበያ ላይ እንዳይውሉ እገዳ ጣለች። የኬንያ ደረጃዎች ተቆጣጣሪ ኬብስ በችርቻሮ ለሚሸጡ ሱቆች እና መገበያያ መደብሮች በጸፈው ደብዳቤ ላይ እነዚህ ምርቶች መደበኛ የጥራት ፈተናዎችን ማለፍ አልቻሉም ብሏል። እነዚህ ምርቶች ከሽያጭ መደርደሪያዎች በአስቸኳይ እንዲወርዱ ትዕዛዝ ተላልፏል። ተቋሙ የተላለፈው ትዕዛዝ ሙሉ እገዳ ሳይሆን አምራቾቹ የተወሰኑ የጥራት መስፈርቶችን እስካሟሉ ድረስ ጊዜያዊ እገዳ መሆኑን አብራርቷል። ትልልቅ የመገበያያ መደብሮችንና ትላልቅ ቸርቻሪዎችን ላቀፈው የኬንያ የችርቻሮ ነጋዴዎች ማህበር ተቋሙ በጻፈው ደብዳቤ የተጠቀሱት የምግብ ዘይት ምርቶች ወደ ገበያ ከመመለሳቸው በፊት የጥራት ማረጋገጫ ማግኘታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባም አሳስቧል። እነዚህ 10 የምግብ ዘይት ምርቶች የሚመረቱ በኬንያ የሚጠቀሱ አራት ትልልቅ የምግብ ዘይት ኩባንያዎች ሲሆኑ እነሱም ቢድኮ አፍሪካ፣ ፕዋኒ የዘይት አምራች፣ ካቻ የዘይት ማጣሪያ እና ሜኔንጋይ የዘይት ማጣሪያ ናቸው። ቢቢሲ ሁለቱን ኩባንያዎች ምላሽ የጠየቃቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ ምላሽ አልሰጡም። ጉዳዩን ለመፍታት ተቋሙ እና ዘይት አምራቾቹ በዛሬው ዕለት አርብ እንደሚገናኙም የኢንዱስትሪ ምንጮች ገልጸዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw4g29l2ey7o |
0business
| መንግሥት ያጋጠመውን ተጨማሪ ወጪ ለመሸፈን የ122 ቢሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ አቀረበ | የገንዘብ ሚኒስቴር በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጥያቄ አቀረበ። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ገንዘብ በማስፈለጉ እና መንግሥት በሚሰበስበው ገቢ ያለውን የክፍያ ጥያቄ መመለስ አዳጋች በመሆኑ እንዲሁም ያለውን የተጨማሪ ወጪ በበጀት ሽግሽግ መሸፈን ባለመቻሉ ተጨማሪ በጀት ማዘጋጀት አስፈልጓል። ይህ ተጨማሪ በጀት ለአገር ደኅንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግሥት ሥራዎች ማስፈጸሚያነት የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል። ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ አንድ ዓመት በላይ የሆነው ጦርነት ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመስፋፋት ከፍተኛ ውድመትን ያስከተለ ሲሆን መንግሥትን ከፍተኛ ወጪ በማስወጣት በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ ይነገራል። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ወጪዎችን ለመሸፈን ባለፈው ዓመትም 26.4 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መጽደቁ ይታወሳል። በወቅቱ እንደተገጸው በ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት ያስፈለገው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ጦርነት ጋር ተያይዞ ላጋጠሙ ወጪዎች፣ በድርቅ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ እና ለተመላሾች የእለት እርዳታ አቅርቦት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ለማዳበሪያ አቅርቦት ድጎማ፣ ለጎርፍ መከላከል ነበር። በዚህ ዓመት በገንዘብ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የቀረበው የተጨማሪ በጀት ጥያቄ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከአራት እጥፍ በላይ ጨምሮ 122 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ይህ የተጨማሪ በጀት ጥያቄው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ ለሕህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርብ ሲሆን፣ ተቀባይነት ካገኘ በቀጥታ ሥራ ላይ እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ባለፈው ዓመት፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2014 ዓ.ም ከፍተኛውን ዓመታዊ በጀትን ማጽደቋ ይታወሳል። የአገሪቱ ዓመታዊ በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሄድ ላይ ሲሆን የዚህ ዓመት በጀት ግን 561 ቢሊዮን ብር ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤትና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል። ይህም በጀት ከ2013 ዓ.ም በ85 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሎ በአገሪቱ መንግሥት የበጀት ታሪክ ከፍተኛው ለመሆን ችሏል። አሁን የተጠየቀው ተጨማሪ በጀት ሲታከልበት ደግሞ አጠቃላይ የዓመቱ በጀት ከ680 ቢሊዮን ብር በላይ ይሆናል። | መንግሥት ያጋጠመውን ተጨማሪ ወጪ ለመሸፈን የ122 ቢሊዮን ብር የበጀት ጥያቄ አቀረበ የገንዘብ ሚኒስቴር በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ወጪ በማስፈለጉ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት የ122 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት ጥያቄ አቀረበ። ሚኒስቴሩ እንዳስታወቀው በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ተጨማሪ ገንዘብ በማስፈለጉ እና መንግሥት በሚሰበስበው ገቢ ያለውን የክፍያ ጥያቄ መመለስ አዳጋች በመሆኑ እንዲሁም ያለውን የተጨማሪ ወጪ በበጀት ሽግሽግ መሸፈን ባለመቻሉ ተጨማሪ በጀት ማዘጋጀት አስፈልጓል። ይህ ተጨማሪ በጀት ለአገር ደኅንነት ማስጠበቂያ፣ ለሰብአዊ እርዳታ፣ በጦርነትና ግጭቶች ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ማቋቋሚያ እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ የመንግሥት ሥራዎች ማስፈጸሚያነት የሚውል መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አመልክቷል። ትግራይ ውስጥ ተቀስቅሶ አንድ ዓመት በላይ የሆነው ጦርነት ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመስፋፋት ከፍተኛ ውድመትን ያስከተለ ሲሆን መንግሥትን ከፍተኛ ወጪ በማስወጣት በአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ላይ ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ ይነገራል። ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ ያጋጠሙ ወጪዎችን ለመሸፈን ባለፈው ዓመትም 26.4 ቢሊዮን ብር ተጨማሪ በጀት መጽደቁ ይታወሳል። በወቅቱ እንደተገጸው በ2013 ዓ.ም ተጨማሪ በጀት ያስፈለገው በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ከተከሰተው ጦርነት ጋር ተያይዞ ላጋጠሙ ወጪዎች፣ በድርቅ ለተጎዱ፣ ለተፈናቀሉ እና ለተመላሾች የእለት እርዳታ አቅርቦት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል፣ ለማዳበሪያ አቅርቦት ድጎማ፣ ለጎርፍ መከላከል ነበር። በዚህ ዓመት በገንዘብ ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ የቀረበው የተጨማሪ በጀት ጥያቄ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከአራት እጥፍ በላይ ጨምሮ 122 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ይህ የተጨማሪ በጀት ጥያቄው በሚኒስትሮች ምክር ቤት ታይቶ ለሕህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚቀርብ ሲሆን፣ ተቀባይነት ካገኘ በቀጥታ ሥራ ላይ እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል። ባለፈው ዓመት፣ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለ2014 ዓ.ም ከፍተኛውን ዓመታዊ በጀትን ማጽደቋ ይታወሳል። የአገሪቱ ዓመታዊ በጀት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ በመሄድ ላይ ሲሆን የዚህ ዓመት በጀት ግን 561 ቢሊዮን ብር ሆኖ በሚኒስትሮች ምክር ቤትና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀድቋል። ይህም በጀት ከ2013 ዓ.ም በ85 ቢሊዮን ብር ከፍ ብሎ በአገሪቱ መንግሥት የበጀት ታሪክ ከፍተኛው ለመሆን ችሏል። አሁን የተጠየቀው ተጨማሪ በጀት ሲታከልበት ደግሞ አጠቃላይ የዓመቱ በጀት ከ680 ቢሊዮን ብር በላይ ይሆናል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59827779 |
3politics
| “ጃል አብዲ ረጋሳ ከአገር ሳልወጣ ያየሁትን እንዳልናገር አስጠንቅቆኛል” ታምራት ነገራ | ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከታዩት የህትመት ሚዲያዎች መካከል ከፍ ያለ ተነባቢነት እና ዝናን አትርፋ የነበረችው የ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ ባልደረቦች ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ታምራት ነገራ ዳግም ለስደት ተዳርጓል። ታምራት ነገራ እና የአዲስ ነገር ባልደረቦች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ይመራ ከነበረው መንግሥት በገጠማቸው ጫናና ስጋት ከአገር ተሰደው ለዓመታት መቆየታቸው ይታወሳል። ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ ባካሄዱት ለውጦች ተበረታተው ወደ አገር ቤት ከተመለሱት የጋዜጣዋ ባልደረቦች መካከል ታምራት ነገራ አንዱ ነው። ለዓመታት ከቆየባት አሜሪካ የተመለሰው ታምራት ባለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን በመስጠት እና በመንግሥት ላይ ጠንካራ ትችቶችን በመሰንዘር ይታወቃል። ኋላ ላይም “ተራራ ኔትወርክ” የተባለውን የራሱን የዩቲዩብ ቻናል በመጀመር ዜና እና ትንታኔዎችን ሲያርብ ቆይቷል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ታኅሣሥ መጀመሪያ ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከቤቱ ተወስዶ ለአራት ወራት ያህል በእስር ከቆየ በኋላ በዋስ መፈታቱ ይታወሳል። ታምራት መጋቢት ወር ማብቂያ ላይ ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ ሥራው ሳይመለስ ለወራት ድምጹ ሳይሰማ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ከባለቤቱ ጋር ዳግም ወደ ስደት ተመልሷል። ታምራት አሁን እንዳይጠቀስ ከፈለገው በስደት ካለበት ስፍራ ስለእስሩ፣ በዝምታ ስለቆየበት ምክንያት፣ ስለወደፊት ዕቅዱና ስለሌሎች ጉዳዮች በተለይ ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቢቢሲ፡ መሰደድህን የሚገልጥ ዜና ባሳለፍነው ሳምንት ተመልክተናል። በርግጥም ስደትን መርጠሃል? ለምን? ታምራት ነገራ፡ አዎ መሰደዴን የሚገልጸው ዜና እውነት ነው። ለመሰደድ የወሰንኩባቸው ምክንያቶች ግልጽ ናቸው። የታሰርኩበት ሁኔታ፣ ከታሰርኩ በኋላ ብሎም በዋስ ከተለቀቅሁ በኋላ ወደ ጋዜጠኝነት ለመመለስ የሚያስፈልጉ ነገሮች አልተሟሉም። እንዲያውም አደጋዎች እየጨመሩ መጡ። የኦሮሚያ ፖሊስ ስታስር የወሰዳቸው ከ32 በላይ የስቱዲዮ እቃዎችን አልመለሰልኝም። ይሄ የእኔ ብቻ ሳይሆን የተራራ ኔትወርክ ሠራተኞች ንብረት የሆኑም ይገኙበታል። ባለቤቴ ሰላም በላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ “ታምራት ላይ ክስ ትመሰርታላችሁ ወይ፣ ምርመራ ጨርሰናል ብላችኋል፣ ንብረታችንን ትመልሳላችሁ ወይ?” የሚሉ ጥያቄዎችን በማመልከቻ ጭምር አቅርባ ነበር። ያገኘችው ምላሽ ግን “አይበቃችሁም ወይ?”፣ ወደ ሥራም ለመመለስ ታስባላችሁ ወይ?” በሚል ማስፈራሪያው ከእኔ አልፎ ቤተሰቤ ላይ እና ሠራተኞች ላይ መምጣቱ ሌላው የመሰደዴ ምክንያት ነው። ማስፈራሪያው እየጨመረ መጥቶ ለቅሶ ቤት፣ ሠርግ ወይም በአደባባይ ከተገኘሁ “ለምን ዐይንህን እናያለን?” የሚሉ የደኅንነት እና የፖሊስ ኃይሎች እየታዩ ስለመጡ አገር ውስጥ መኖር አሳሳቢ እየሆነ መጣ። ከእኔ ባሻገር ግን ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው እስር እና እንግልት ብሎም በአጠቃላይ ሚዲያ ላይ የሚደረገው አፈና እየበረታ መምጣቱ በቀጣይነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የሚዲያ ሥራ መስራት ይቻላል የሚለውን እምነቴን ሙሉ ሉሙሉ ስለዘጋው፣ የሚዲያ ሥራውንም ለመስራት ብሎም በሰላም ለመኖር ከአገር መውጣት አስገዳጅ ሆኖ ስላገኘነው እኔ እና ባለቤቴ ወጥተናል። ባለፉት ወራት ታስሬ በነበረበት ብሎም ከተፈታሁ በኋላ ከፍርድ ቤት፣ ከዐቃቤ ሕግ፣ ከፖሊስ ብሎም ተራራ ኔትወርክን ማስተዳደርን ጨምሮ ይህንን የሕይወት ጉዞ ያለ ባለቤቴ ሰላም በላይ እገዛ እና አብሮነት ላልፈው አልችልም ነበር። ብዙዎች ከሚያውቁት በላይ ነው የሰላም ሚና። ተራራ እንዲቋቋም ብሎም በእግሩ እንዲቆም ያደረገችው። አንደኛው እንድሰደድ ምክንያት የሆነኝም ባለቤቴን ወደ እነዚያ 7 ቀናት [ፍርድ ቤት ሳይቀርብ፣ ያለበት ሳይታወቅ የቆየባቸው] መልሶ ለመውሰድ የሚያስችል ጭካኔ ስለሌለኝ ነው። ከብዙ የቤተሰብ እና የግል የኑሮ ጫና ጋር በፖሊስ፣ በፌደራል ብሎም በክልል ዐቃቤ ሕግ፣ በፍርድ ቤት ምን አይነት እንግልት እንደደረሰባት ለመናገር አልችልም። ስለዚህ አንዱ ለመሰደድ እንድመርጥ ያደረገኝ በእሷ ትከሻ ላይ የነበረው ጫና ነው። አብረን እንድንሰደድ ያደረገው አንዱ ምክንያትም እሱ ነው። ቢቢሲ፡ በቁጥጥር ስር ከዋልክ በኋላ ያለህበትን ለማወቅ እና ፍርድ ቤት እስከምትቀርብ ድረስ 7 ቀናት ጠይቋል። የት ነበር የተወሰድከው? እዚያ የነበረህ ቆይታ ምን ይመል ነበር? ታምራት ነገራ፡ በቁጥጥር ስር ከዋልኩ በኋላ ለ7 ቀናት ፍርድ ቤት አልቀረብኩም፣ ቤተሰብም የት እንዳለሁ ማወቅ አልቻለም ነበር። በወቅቱ ወደ ገላን ከተማ ተወስጄ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ነበር የቆየሁት። ካምፕ መሆኑን ያወቅሁት በቁጥጥር ስር ያዋሉኝ ፖሊሶች ዩኒፎርማቸውን በማየት ነው። ይህ ካምፕ የኢትዮጵያ መንግሥት ብሎም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የግድያ እና የስቅይት ካምፕ ነው። ለሰባት ቀናትም ለብቻዬ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር በማልገናኝበት ክፍል ውስጥ ነበር የታሰርኩት። በእነዚህ ቀናት ለእኔ የጮሁ ሰዎችን በሙሉ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ማመስገን እፈልጋለሁ። ይህ ጫና ባይኖር ኖሮ ምን አልባትም በሕይወት ላልኖር እችል ነበር። ቢቢሲ፡ ከተፈታህ በኋላ ዝምታን መርጠህ ነበር። ለምን? ከዚያ ስለምን ተመልሰህ ወደ ሚዲያህ አልመጣህም? ታምራት ነገራ፡ ዝምታን የመርጥኩበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንደኛው እንደተፈታሁ ለመናገር ያሰብኳቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። በተለይም እስር ቤት ውስጥ ያገኘኋቸው በፖለቲካም፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም ሆነ የፖለቲካ አቅጣጫ ላይ የማልስማማቸው ብዙ ሰዎችን አግኝቻለሁ። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች አጽንተው የተናገሩት እዚህ እስር ቤት ያየኽውን ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነህ እንድትናገር አንፈቅድልህም ነው ያሉኝ። ከቤተሰቤም በፊት ማለት ነው። በተለይም ጃል አብዲ ረጋሳ [የኦነግ ከፍተኛ አመራር እና በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኛ] በዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በግሉም ሆነ በቤተሰቡ ላይ ብዙ መከራ፣ ስቃይ ብሎም ከፍተኛ የሚባለውን ግፍ ካዩ ሰዎች አንዱ ይመስለኛል። እርሱ አጥብቆ ያስጠነቀቀኝ ነገር፣ “ከኢትዮጵያ ሳትወጣ የምንነግርህንም ሆነ ያየህውን ነገር እንዳትናገር” ብሎ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ በተቀበሩ የጨለማ እስር ቤቶች ውስጥ የሚፈጽመውንና ያየሁትን ሳልናገር ወደ ሚዲያ ሥራው መመለስ አልችልም። እንደ ጋዜጠኛም ሆነ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ይህንን ሳልናገር ሚዲያ መስራት አልችልም። ይህንን የምናገርበት ቀን ይመጣል። ብዙ መረጃዎች የያዘዝኩት አለ። ይህንንም በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁ። ያንን እንዳላደርግ የእነ ጃል አብዲ ማስጠንቀቂያ ብሎም ቤተሰብ አለ። ሦስተኛው ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታ ለሚዲያ የሚመች አይደለም። ስለዚህ የምናገር ከሆነ፣ የምናገረው እውነት መሆን አለበት። እውነትን ለመናገር ደግሞ እውነትን ለመናገር የሚቻልበት ቦታ ላይ መሆን ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት እውነትን ለመናገር የሚቻልበት ቦታ ናት ብዬ አላምንም። ሁኔታዎች ከተቀየሩ ብዬ 7 ወር ያህል ቆየሁኝ። ያለው ነገር ይበልጥ እየባሰ መጣ። ቢቢሲ፡ በስደት ከምትኖርበት አሜሪካ ስትመለስ ይዘህ የመጣህውን ተስፋ እና አሁን ለዳግም ስደት ስትዳረግ ያለህን ስሜት አነጻጽረህ ንገረኝ እስቲ? ታምራት ነገራ፡ የዛሬ አራት ዓመት ከስደት ተመልሼ ስመጣ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎቻችን ተስፋ ነበረን። አሁን ተስፋ አስቆራጭ ነገር አለ። ተስፋ የቆረጥኩት አሁን ባለው መንግሥት እና አገዛዝ እንጂ በኢትዮጵያ አይደለም። ሥርዓቱ ተስፋ የሚቆረጥበት ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ ላይ ተስፋ አልቆርጥም። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚዲያ ሥራ ለመስራት አስቸጋሪ ነው። ሚዲያ አንዱ ጎኑ ንግድ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የትኛውንም ንግድ ለማንቀሳቀስ ያለው ሕገ መንግሥት፣ ብሔርተኝነት እና ዘረኝነት እየታየ ሥራ ለመስራት የሚቻልበት ሆኖ አይታይም። ስለዚህ ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲታይ አሁን ያለው ነገር ተስፋ ያስቆርጣል፤ ተስፋ የምንቆርጠው ግን በገዢዎቹ ላይ እንጂ በኢትዮጵያ ላይ አይደለም። ቢቢሲ፡ ከዚህ በኋላ ወደ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ትመለሳለህ? ታምራት ነገራ፡ የመገናኛ ብዙኃን ሥራ በውስጤ ስለሆነ የትም ብሄድ፣ ምንም ቋንቋ ብናገር ከውስጤ የማይቀር ሥራ ስለሆነ አይቀርም። ስለዚህ ወደ መገናኛ ብዙኃን ሥራ እመለሳለሁ። እመለሳለሁ ብቻ ሳይሆን የተራራ ኔትወርክ የኢትዮጵያዊነት ድምጽ መሆኑን ይቀጥላል። ተጠናክረን እና ከባለፈውም በበለጠ ነጻ በሆነ ሁኔታ ይቀጥላል። ስለኢትዮጵያ ተስፋ መስጠታችንን፣ ማስተማራችን እና ድምጽ መሆናችን አይቀርም። ቢቢሲ፡ በቆይታህ ካከናወንከው ውስጥ ማድረግ አልነበረብኝም እና ሳላደርግ የቀረሁት የምትለው? ታምራት ነገራ፡ ከመታሰሬ አንድ ቀን በፊት ሦስት አዲስ ተመራቂ ልጆችን ቀጥረን ጨርሰን ነበር። ሙሉ ሂደቱን ጨርሰን ነበር። እና በጣም የሚቆጨኝ ወጣቶችን እና የሚቀጥለውን ትውልድ አገሬ ውስጥ ሆኜ ያለችኝን መጠነኛም ብትሆን የጋዜጠኝነት እውቀት ላሳያቸው እፈልግ ነበር። የዲጂታል ጋዜጠኝነትን በአዲስ መልኩ መስራት ፈልጌ ነበር። የተራራ ኔትወርክን ለመደገፍ በተሰበሰበ ገንዘብ የተገዙ የስቱዲዮ እቃዎች በመንግሥት እጅ ውስጥ ወድቀዋል። ነገር ግን እሱ አይደለም የሚያሳስበኝ። የሚያሳስበኝ ለወጣት ጋዜጠኞች በአገሬ ውስጥ ሆኜ ጋዜጠኝነትን ለማሳየት ባለመቻሌ ነው። ቢቢሲ፡ ወደ ኢትዮጵያ መቼ እመለሳለሁ ብለህ ታስባለህ? ኢትዮጵያ እንዴት ሆና እንድትጠብቅህ ትፈልጋለህ? ታምራት ነገራ፡ ወደ ኢትዮጵያ ልመለስ እችላለሁ፤ ሁኔታዎች ከተቀየሩ። ዋናው የሚያሳስበኝ ግን መመለስ ያለመመለስ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ውጪ ላለው የምትሆን አገር እንዴት ነው ማድረግ የሚቻለው የሚለው ጥያቄ ነው የሚያሳስበኝ። ይሄ ደግሞ የእኔ ብቻ ጥያቄ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው። በዚህ ላይ ያለኝን አስተዋጽኦን ከውጪም ሆኜ ቢሆን አበረክታለሁ ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያውያን የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ እስከምናይ ድረስ አናቆምም። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ለማንም የምትሆን አይደለችም። ሁልጊዜ እንደምለው እስራኤላዊያን እስራኤል ከፈረሰች ከሁለት ሺህ ዓመት በኋላ መልሰው ገንብተዋታል። ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ እንዳለባት ሁላችንም እናውቃለን። ኢትዮጵያ እንድትቆም የምንፈልገው ሰዎች ብንችል በዘመናችን እናቆማታለን፤ ባንችል በቃል አቁመናት ያ ቃል ነገ ከሺህ ዓመታትም በኋላ ይሁን ኢትዮጵያን መልሶ የሚሰራ እንዲሆን ማድረግ ግዴታ አለብን ባይ ነኝ። ቢቢሲ፡ በቅርቡ ከኢሠፓ መልሶ ምሥረታ ጋር ስምህ በተደጋጋሚ ተነስቶ ነበር። በዚህ ዙሪያ ምን ምላሽ አለህ? ታምራት ነገራ፡ ከኢሠፓ ምሥረታ ጋር ስሜ መነሳቱ ለእኔም ዜና ነው። ምንም የማውቀው ነገር የለም። እኔ የኢሠፓ አባልም ደጋፊም አይደለሁም። በወቅቱ ግን ይህንን ማስተባበል አስፈላጊ ስላልነበረ አላስተባበልኩም። ከዚህ በተጨማሪ ግን ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ግንኙነት እንዲኖረኝ አልፈልግም። በወጣትነት ዘመኔ ከቅንጅት ጋር ተሳትፌያለሁ፤ ተመራጭ ነበርኩ። ፖለቲካ ፓርቲን ከምሥረታው በቅርብ ርቀት አይቼዋለሁ። ቅንጅትን ያፈረሱትም ሆነ ለማሰቀጠል የሞከሩት አመራሮች ጋር በቅርበት ሰርቼ የፖለቲካ ፓርቲን አሰራር ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እንደሆነ አይቼዋለሁ። እኔ የፖለቲካ ፓርቲ ኢትዮጵያን ያድናል የሚል እምነትም የለኝም። ለዚህም ነው ወደ ሚዲያ ሥራ የማተኩረው። | “ጃል አብዲ ረጋሳ ከአገር ሳልወጣ ያየሁትን እንዳልናገር አስጠንቅቆኛል” ታምራት ነገራ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከታዩት የህትመት ሚዲያዎች መካከል ከፍ ያለ ተነባቢነት እና ዝናን አትርፋ የነበረችው የ“አዲስ ነገር” ጋዜጣ ባልደረቦች ከነበሩት መካከል አንዱ የሆነው ታምራት ነገራ ዳግም ለስደት ተዳርጓል። ታምራት ነገራ እና የአዲስ ነገር ባልደረቦች በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ይመራ ከነበረው መንግሥት በገጠማቸው ጫናና ስጋት ከአገር ተሰደው ለዓመታት መቆየታቸው ይታወሳል። ነገር ግን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎ ባካሄዱት ለውጦች ተበረታተው ወደ አገር ቤት ከተመለሱት የጋዜጣዋ ባልደረቦች መካከል ታምራት ነገራ አንዱ ነው። ለዓመታት ከቆየባት አሜሪካ የተመለሰው ታምራት ባለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን ላይ ወቅታዊ ፖለቲካዊ ትንታኔዎችን በመስጠት እና በመንግሥት ላይ ጠንካራ ትችቶችን በመሰንዘር ይታወቃል። ኋላ ላይም “ተራራ ኔትወርክ” የተባለውን የራሱን የዩቲዩብ ቻናል በመጀመር ዜና እና ትንታኔዎችን ሲያርብ ቆይቷል። ነገር ግን ባለፈው ዓመት ታኅሣሥ መጀመሪያ ላይ በፀጥታ ኃይሎች ከቤቱ ተወስዶ ለአራት ወራት ያህል በእስር ከቆየ በኋላ በዋስ መፈታቱ ይታወሳል። ታምራት መጋቢት ወር ማብቂያ ላይ ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ ሥራው ሳይመለስ ለወራት ድምጹ ሳይሰማ ቆይቶ ባለፈው ሳምንት ከባለቤቱ ጋር ዳግም ወደ ስደት ተመልሷል። ታምራት አሁን እንዳይጠቀስ ከፈለገው በስደት ካለበት ስፍራ ስለእስሩ፣ በዝምታ ስለቆየበት ምክንያት፣ ስለወደፊት ዕቅዱና ስለሌሎች ጉዳዮች በተለይ ከቢቢሲ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ቢቢሲ፡ መሰደድህን የሚገልጥ ዜና ባሳለፍነው ሳምንት ተመልክተናል። በርግጥም ስደትን መርጠሃል? ለምን? ታምራት ነገራ፡ አዎ መሰደዴን የሚገልጸው ዜና እውነት ነው። ለመሰደድ የወሰንኩባቸው ምክንያቶች ግልጽ ናቸው። የታሰርኩበት ሁኔታ፣ ከታሰርኩ በኋላ ብሎም በዋስ ከተለቀቅሁ በኋላ ወደ ጋዜጠኝነት ለመመለስ የሚያስፈልጉ ነገሮች አልተሟሉም። እንዲያውም አደጋዎች እየጨመሩ መጡ። የኦሮሚያ ፖሊስ ስታስር የወሰዳቸው ከ32 በላይ የስቱዲዮ እቃዎችን አልመለሰልኝም። ይሄ የእኔ ብቻ ሳይሆን የተራራ ኔትወርክ ሠራተኞች ንብረት የሆኑም ይገኙበታል። ባለቤቴ ሰላም በላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ ኮሚሽን በመሄድ “ታምራት ላይ ክስ ትመሰርታላችሁ ወይ፣ ምርመራ ጨርሰናል ብላችኋል፣ ንብረታችንን ትመልሳላችሁ ወይ?” የሚሉ ጥያቄዎችን በማመልከቻ ጭምር አቅርባ ነበር። ያገኘችው ምላሽ ግን “አይበቃችሁም ወይ?”፣ ወደ ሥራም ለመመለስ ታስባላችሁ ወይ?” በሚል ማስፈራሪያው ከእኔ አልፎ ቤተሰቤ ላይ እና ሠራተኞች ላይ መምጣቱ ሌላው የመሰደዴ ምክንያት ነው። ማስፈራሪያው እየጨመረ መጥቶ ለቅሶ ቤት፣ ሠርግ ወይም በአደባባይ ከተገኘሁ “ለምን ዐይንህን እናያለን?” የሚሉ የደኅንነት እና የፖሊስ ኃይሎች እየታዩ ስለመጡ አገር ውስጥ መኖር አሳሳቢ እየሆነ መጣ። ከእኔ ባሻገር ግን ሌሎች ጋዜጠኞች ላይ የሚደረገው እስር እና እንግልት ብሎም በአጠቃላይ ሚዲያ ላይ የሚደረገው አፈና እየበረታ መምጣቱ በቀጣይነት ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የሚዲያ ሥራ መስራት ይቻላል የሚለውን እምነቴን ሙሉ ሉሙሉ ስለዘጋው፣ የሚዲያ ሥራውንም ለመስራት ብሎም በሰላም ለመኖር ከአገር መውጣት አስገዳጅ ሆኖ ስላገኘነው እኔ እና ባለቤቴ ወጥተናል። ባለፉት ወራት ታስሬ በነበረበት ብሎም ከተፈታሁ በኋላ ከፍርድ ቤት፣ ከዐቃቤ ሕግ፣ ከፖሊስ ብሎም ተራራ ኔትወርክን ማስተዳደርን ጨምሮ ይህንን የሕይወት ጉዞ ያለ ባለቤቴ ሰላም በላይ እገዛ እና አብሮነት ላልፈው አልችልም ነበር። ብዙዎች ከሚያውቁት በላይ ነው የሰላም ሚና። ተራራ እንዲቋቋም ብሎም በእግሩ እንዲቆም ያደረገችው። አንደኛው እንድሰደድ ምክንያት የሆነኝም ባለቤቴን ወደ እነዚያ 7 ቀናት [ፍርድ ቤት ሳይቀርብ፣ ያለበት ሳይታወቅ የቆየባቸው] መልሶ ለመውሰድ የሚያስችል ጭካኔ ስለሌለኝ ነው። ከብዙ የቤተሰብ እና የግል የኑሮ ጫና ጋር በፖሊስ፣ በፌደራል ብሎም በክልል ዐቃቤ ሕግ፣ በፍርድ ቤት ምን አይነት እንግልት እንደደረሰባት ለመናገር አልችልም። ስለዚህ አንዱ ለመሰደድ እንድመርጥ ያደረገኝ በእሷ ትከሻ ላይ የነበረው ጫና ነው። አብረን እንድንሰደድ ያደረገው አንዱ ምክንያትም እሱ ነው። ቢቢሲ፡ በቁጥጥር ስር ከዋልክ በኋላ ያለህበትን ለማወቅ እና ፍርድ ቤት እስከምትቀርብ ድረስ 7 ቀናት ጠይቋል። የት ነበር የተወሰድከው? እዚያ የነበረህ ቆይታ ምን ይመል ነበር? ታምራት ነገራ፡ በቁጥጥር ስር ከዋልኩ በኋላ ለ7 ቀናት ፍርድ ቤት አልቀረብኩም፣ ቤተሰብም የት እንዳለሁ ማወቅ አልቻለም ነበር። በወቅቱ ወደ ገላን ከተማ ተወስጄ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ማሰልጠኛ ካምፕ ውስጥ ነበር የቆየሁት። ካምፕ መሆኑን ያወቅሁት በቁጥጥር ስር ያዋሉኝ ፖሊሶች ዩኒፎርማቸውን በማየት ነው። ይህ ካምፕ የኢትዮጵያ መንግሥት ብሎም የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የግድያ እና የስቅይት ካምፕ ነው። ለሰባት ቀናትም ለብቻዬ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር በማልገናኝበት ክፍል ውስጥ ነበር የታሰርኩት። በእነዚህ ቀናት ለእኔ የጮሁ ሰዎችን በሙሉ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ማመስገን እፈልጋለሁ። ይህ ጫና ባይኖር ኖሮ ምን አልባትም በሕይወት ላልኖር እችል ነበር። ቢቢሲ፡ ከተፈታህ በኋላ ዝምታን መርጠህ ነበር። ለምን? ከዚያ ስለምን ተመልሰህ ወደ ሚዲያህ አልመጣህም? ታምራት ነገራ፡ ዝምታን የመርጥኩበት ብዙ ምክንያቶች አሉ። አንደኛው እንደተፈታሁ ለመናገር ያሰብኳቸው ብዙ ነገሮች ነበሩ። በተለይም እስር ቤት ውስጥ ያገኘኋቸው በፖለቲካም፣ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥትም ሆነ የፖለቲካ አቅጣጫ ላይ የማልስማማቸው ብዙ ሰዎችን አግኝቻለሁ። ነገር ግን እነዚህ ሰዎች አጽንተው የተናገሩት እዚህ እስር ቤት ያየኽውን ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነህ እንድትናገር አንፈቅድልህም ነው ያሉኝ። ከቤተሰቤም በፊት ማለት ነው። በተለይም ጃል አብዲ ረጋሳ [የኦነግ ከፍተኛ አመራር እና በእስር ላይ ያሉ ፖለቲከኛ] በዐቢይ አሕመድ አስተዳደር በግሉም ሆነ በቤተሰቡ ላይ ብዙ መከራ፣ ስቃይ ብሎም ከፍተኛ የሚባለውን ግፍ ካዩ ሰዎች አንዱ ይመስለኛል። እርሱ አጥብቆ ያስጠነቀቀኝ ነገር፣ “ከኢትዮጵያ ሳትወጣ የምንነግርህንም ሆነ ያየህውን ነገር እንዳትናገር” ብሎ ነው። ሁለተኛው የኢትዮጵያ መንግሥት በተለይም በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ በተቀበሩ የጨለማ እስር ቤቶች ውስጥ የሚፈጽመውንና ያየሁትን ሳልናገር ወደ ሚዲያ ሥራው መመለስ አልችልም። እንደ ጋዜጠኛም ሆነ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ይህንን ሳልናገር ሚዲያ መስራት አልችልም። ይህንን የምናገርበት ቀን ይመጣል። ብዙ መረጃዎች የያዘዝኩት አለ። ይህንንም በቅርቡ ይፋ አደርጋለሁ። ያንን እንዳላደርግ የእነ ጃል አብዲ ማስጠንቀቂያ ብሎም ቤተሰብ አለ። ሦስተኛው ደግሞ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው እውነታ ለሚዲያ የሚመች አይደለም። ስለዚህ የምናገር ከሆነ፣ የምናገረው እውነት መሆን አለበት። እውነትን ለመናገር ደግሞ እውነትን ለመናገር የሚቻልበት ቦታ ላይ መሆን ያስፈልጋል። ኢትዮጵያ በአሁን ሰዓት እውነትን ለመናገር የሚቻልበት ቦታ ናት ብዬ አላምንም። ሁኔታዎች ከተቀየሩ ብዬ 7 ወር ያህል ቆየሁኝ። ያለው ነገር ይበልጥ እየባሰ መጣ። ቢቢሲ፡ በስደት ከምትኖርበት አሜሪካ ስትመለስ ይዘህ የመጣህውን ተስፋ እና አሁን ለዳግም ስደት ስትዳረግ ያለህን ስሜት አነጻጽረህ ንገረኝ እስቲ? ታምራት ነገራ፡ የዛሬ አራት ዓመት ከስደት ተመልሼ ስመጣ እኔ ብቻ ሳልሆን ብዙዎቻችን ተስፋ ነበረን። አሁን ተስፋ አስቆራጭ ነገር አለ። ተስፋ የቆረጥኩት አሁን ባለው መንግሥት እና አገዛዝ እንጂ በኢትዮጵያ አይደለም። ሥርዓቱ ተስፋ የሚቆረጥበት ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያ ላይ ተስፋ አልቆርጥም። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚዲያ ሥራ ለመስራት አስቸጋሪ ነው። ሚዲያ አንዱ ጎኑ ንግድ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት የትኛውንም ንግድ ለማንቀሳቀስ ያለው ሕገ መንግሥት፣ ብሔርተኝነት እና ዘረኝነት እየታየ ሥራ ለመስራት የሚቻልበት ሆኖ አይታይም። ስለዚህ ከአራት ዓመት በፊት ከነበረው ጋር ሲታይ አሁን ያለው ነገር ተስፋ ያስቆርጣል፤ ተስፋ የምንቆርጠው ግን በገዢዎቹ ላይ እንጂ በኢትዮጵያ ላይ አይደለም። ቢቢሲ፡ ከዚህ በኋላ ወደ መገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ትመለሳለህ? ታምራት ነገራ፡ የመገናኛ ብዙኃን ሥራ በውስጤ ስለሆነ የትም ብሄድ፣ ምንም ቋንቋ ብናገር ከውስጤ የማይቀር ሥራ ስለሆነ አይቀርም። ስለዚህ ወደ መገናኛ ብዙኃን ሥራ እመለሳለሁ። እመለሳለሁ ብቻ ሳይሆን የተራራ ኔትወርክ የኢትዮጵያዊነት ድምጽ መሆኑን ይቀጥላል። ተጠናክረን እና ከባለፈውም በበለጠ ነጻ በሆነ ሁኔታ ይቀጥላል። ስለኢትዮጵያ ተስፋ መስጠታችንን፣ ማስተማራችን እና ድምጽ መሆናችን አይቀርም። ቢቢሲ፡ በቆይታህ ካከናወንከው ውስጥ ማድረግ አልነበረብኝም እና ሳላደርግ የቀረሁት የምትለው? ታምራት ነገራ፡ ከመታሰሬ አንድ ቀን በፊት ሦስት አዲስ ተመራቂ ልጆችን ቀጥረን ጨርሰን ነበር። ሙሉ ሂደቱን ጨርሰን ነበር። እና በጣም የሚቆጨኝ ወጣቶችን እና የሚቀጥለውን ትውልድ አገሬ ውስጥ ሆኜ ያለችኝን መጠነኛም ብትሆን የጋዜጠኝነት እውቀት ላሳያቸው እፈልግ ነበር። የዲጂታል ጋዜጠኝነትን በአዲስ መልኩ መስራት ፈልጌ ነበር። የተራራ ኔትወርክን ለመደገፍ በተሰበሰበ ገንዘብ የተገዙ የስቱዲዮ እቃዎች በመንግሥት እጅ ውስጥ ወድቀዋል። ነገር ግን እሱ አይደለም የሚያሳስበኝ። የሚያሳስበኝ ለወጣት ጋዜጠኞች በአገሬ ውስጥ ሆኜ ጋዜጠኝነትን ለማሳየት ባለመቻሌ ነው። ቢቢሲ፡ ወደ ኢትዮጵያ መቼ እመለሳለሁ ብለህ ታስባለህ? ኢትዮጵያ እንዴት ሆና እንድትጠብቅህ ትፈልጋለህ? ታምራት ነገራ፡ ወደ ኢትዮጵያ ልመለስ እችላለሁ፤ ሁኔታዎች ከተቀየሩ። ዋናው የሚያሳስበኝ ግን መመለስ ያለመመለስ አይደለም። ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ውጪ ላለው የምትሆን አገር እንዴት ነው ማድረግ የሚቻለው የሚለው ጥያቄ ነው የሚያሳስበኝ። ይሄ ደግሞ የእኔ ብቻ ጥያቄ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥያቄ ነው። በዚህ ላይ ያለኝን አስተዋጽኦን ከውጪም ሆኜ ቢሆን አበረክታለሁ ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያውያን የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ እስከምናይ ድረስ አናቆምም። አሁን ያለችው ኢትዮጵያ ለማንም የምትሆን አይደለችም። ሁልጊዜ እንደምለው እስራኤላዊያን እስራኤል ከፈረሰች ከሁለት ሺህ ዓመት በኋላ መልሰው ገንብተዋታል። ኢትዮጵያ የመፍረስ አደጋ እንዳለባት ሁላችንም እናውቃለን። ኢትዮጵያ እንድትቆም የምንፈልገው ሰዎች ብንችል በዘመናችን እናቆማታለን፤ ባንችል በቃል አቁመናት ያ ቃል ነገ ከሺህ ዓመታትም በኋላ ይሁን ኢትዮጵያን መልሶ የሚሰራ እንዲሆን ማድረግ ግዴታ አለብን ባይ ነኝ። ቢቢሲ፡ በቅርቡ ከኢሠፓ መልሶ ምሥረታ ጋር ስምህ በተደጋጋሚ ተነስቶ ነበር። በዚህ ዙሪያ ምን ምላሽ አለህ? ታምራት ነገራ፡ ከኢሠፓ ምሥረታ ጋር ስሜ መነሳቱ ለእኔም ዜና ነው። ምንም የማውቀው ነገር የለም። እኔ የኢሠፓ አባልም ደጋፊም አይደለሁም። በወቅቱ ግን ይህንን ማስተባበል አስፈላጊ ስላልነበረ አላስተባበልኩም። ከዚህ በተጨማሪ ግን ከማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ ጋር ግንኙነት እንዲኖረኝ አልፈልግም። በወጣትነት ዘመኔ ከቅንጅት ጋር ተሳትፌያለሁ፤ ተመራጭ ነበርኩ። ፖለቲካ ፓርቲን ከምሥረታው በቅርብ ርቀት አይቼዋለሁ። ቅንጅትን ያፈረሱትም ሆነ ለማሰቀጠል የሞከሩት አመራሮች ጋር በቅርበት ሰርቼ የፖለቲካ ፓርቲን አሰራር ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እንደሆነ አይቼዋለሁ። እኔ የፖለቲካ ፓርቲ ኢትዮጵያን ያድናል የሚል እምነትም የለኝም። ለዚህም ነው ወደ ሚዲያ ሥራ የማተኩረው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c165znkrl12o |
2health
| እስራኤል 5 ሺህ አዕዋፋትን የገደለውን 'የአቪያን ፍሉ' ወረርሽኝ ለመቆጣጠር እየጣረች ነው | በእስራኤል ከባዱና የአዕዋፋት ዝርያን የሚያጠቃው የአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ መቀስቀሱን ተከተሎ አገሪቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተርኪ የተባሉ የዶሮ ዝርያዎችን እያስወገደች ነው። የአገሪቱ አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ታማር ዛንድበርግ፤ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ "በዱር እንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት" ሲሉ በገለጹት ወረርሽኝ ሳቢያ በሁላ የተፈጥሮ ጥብቅ ስፍራ ከ5,000 በላይ የሚሆኑ እና የሚፈልሱ 'ክሬንስ' ተብለው የሚታወቁ የአዕዋፋት ዝርያዎች ሞተዋል። የአገሪቱ አርሶ አደሮችም ወረርሽኙን ለመከላከል በሚል ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ተርኪ ዶሮዎችን እንዲያስወግዱ እየተገደዱ ሲሆን፤ ይህም በእስራኤል የእንቁላል እጥረት ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። እስካሁን ይህ አዕዋፋቱን የሚያጠቃው ቫይረስ ወደ ሰው ስለመተላለፉ አልተረጋገጠም። ሆኖም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናታሊ ቤኔት በሽታው ወደ ሰዎች እንዳይተላለፍ በሚደረገው ጥረት ዙሪያ ለመወያየት ሰኞ ዕለት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪያቸውን እና ሌሎች ባለሙያዎችን ማነጋገራቸው ተሰምቷል። በበሽታው ከተያዙ አዕዋፋት ጋር የቅርብ ግንኙነት ወይም ንክኪ የነበራቸው ሰዎች የመከላከያ ሕክምና እየተደረገላቸው ነው። አቪያን ፍሉ ከአዕዋፋት ወደ ሰው የመተላለፍ ዕድሉ ጠባብ ቢሆንም እንደ አውሮፓውያኑ ከ2003 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ 456 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አሳውቋል። ከእስራኤል ተፈጥሮ እና ፓርኮች ባለሥልጣን የወጡ ምስሎች፣ ሌሎች የዱር እንስሳት በወረርሽኙ እንዳይያዙ ለመጠበቅ ከሁላ ሐይቅ የሞቱ ክሬኖችን ለማንሳት የተሰማሩ ባለሙያዎችን ያሳያል። ሁላ በተሰኘው ጥብቅ ስፋራ ዙሪያ ባለው ሸለቆ ውስጥ የ250 ክሬኖች ቅሪቶች መታየታቸውን እና 30ዎቹ ደግሞ ታመው በአገሪቱ ሌላ ስፍራ መታየታቸውንም ባለሥልጣኑ ገልጿል። ከአውሮፓ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እነዚህ አዕዋፋት በሁላ የተፈጥሮ ጥበቅ ስፍራ ላይ ሲከርሙ ማየት ብዙውን ጊዜ ለወፍ አድናቂዎች አስደሳች ክስተት ነው። ነገር ግን ጣቢያው ባለፈው ሳምንት ለጎብኝዎች ዝግ የተደረገ ሲሆን ምክንያቱ ድግሞ ከባድ እንደሆነ የተገለጸው በአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ ነው። ምልክቶች የማይታዩበት አቪያን ፍሉ በባሕርያቸው ከቦታ ቦታ በሚፈልሱ ወፎች ላይ የሚከሰት ነው። በአገር ውስጥ ያሉ ወፎች ለዚህ ወረርሽኝ ያላቸው ተጋላጭነት ዝቅተኛ ቢሆንም ቫይረሱ ለሽያጭ በቀረቡ ወይም በቤተሰብ ውስጥ በሚራቡ የአዕዋፍ ዝርያዎች ላይ ከተገኘ ግን ሁሉንም በፍጥነት ማስወገድ ይመከራል። በሰሜን እስራኤል 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሞሻቭ ማርጋዮት በተሰኘው የጋራ ማርቢያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ እንቁላል የሚጥሉ ዶሮዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና በሰዎች ላይ ያለውን አደጋ ለመቀነስ እየተገለሉ መሆኑን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሞሻቭ በእስራኤል ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉ እንቁላሎች 7 በመቶውን ያቀርባል። ታይምስ ኦፍ እስራኤል የተሰኘው ሚዲያ እንደዘገበው በእስራኤል የመጀመሪያው የአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ እንደ አውሮፓውያኑ ጥቅምት 18 ተመዝግቧል። | እስራኤል 5 ሺህ አዕዋፋትን የገደለውን 'የአቪያን ፍሉ' ወረርሽኝ ለመቆጣጠር እየጣረች ነው በእስራኤል ከባዱና የአዕዋፋት ዝርያን የሚያጠቃው የአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ መቀስቀሱን ተከተሎ አገሪቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተርኪ የተባሉ የዶሮ ዝርያዎችን እያስወገደች ነው። የአገሪቱ አካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ታማር ዛንድበርግ፤ በእስራኤል ታሪክ ውስጥ "በዱር እንስሳት ላይ የከፋ ጉዳት" ሲሉ በገለጹት ወረርሽኝ ሳቢያ በሁላ የተፈጥሮ ጥብቅ ስፍራ ከ5,000 በላይ የሚሆኑ እና የሚፈልሱ 'ክሬንስ' ተብለው የሚታወቁ የአዕዋፋት ዝርያዎች ሞተዋል። የአገሪቱ አርሶ አደሮችም ወረርሽኙን ለመከላከል በሚል ግማሽ ሚሊዮን የሚሆኑ ተርኪ ዶሮዎችን እንዲያስወግዱ እየተገደዱ ሲሆን፤ ይህም በእስራኤል የእንቁላል እጥረት ሊያስከትል ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። እስካሁን ይህ አዕዋፋቱን የሚያጠቃው ቫይረስ ወደ ሰው ስለመተላለፉ አልተረጋገጠም። ሆኖም የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ናታሊ ቤኔት በሽታው ወደ ሰዎች እንዳይተላለፍ በሚደረገው ጥረት ዙሪያ ለመወያየት ሰኞ ዕለት የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪያቸውን እና ሌሎች ባለሙያዎችን ማነጋገራቸው ተሰምቷል። በበሽታው ከተያዙ አዕዋፋት ጋር የቅርብ ግንኙነት ወይም ንክኪ የነበራቸው ሰዎች የመከላከያ ሕክምና እየተደረገላቸው ነው። አቪያን ፍሉ ከአዕዋፋት ወደ ሰው የመተላለፍ ዕድሉ ጠባብ ቢሆንም እንደ አውሮፓውያኑ ከ2003 ጀምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ 456 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መሞታቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አሳውቋል። ከእስራኤል ተፈጥሮ እና ፓርኮች ባለሥልጣን የወጡ ምስሎች፣ ሌሎች የዱር እንስሳት በወረርሽኙ እንዳይያዙ ለመጠበቅ ከሁላ ሐይቅ የሞቱ ክሬኖችን ለማንሳት የተሰማሩ ባለሙያዎችን ያሳያል። ሁላ በተሰኘው ጥብቅ ስፋራ ዙሪያ ባለው ሸለቆ ውስጥ የ250 ክሬኖች ቅሪቶች መታየታቸውን እና 30ዎቹ ደግሞ ታመው በአገሪቱ ሌላ ስፍራ መታየታቸውንም ባለሥልጣኑ ገልጿል። ከአውሮፓ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ እነዚህ አዕዋፋት በሁላ የተፈጥሮ ጥበቅ ስፍራ ላይ ሲከርሙ ማየት ብዙውን ጊዜ ለወፍ አድናቂዎች አስደሳች ክስተት ነው። ነገር ግን ጣቢያው ባለፈው ሳምንት ለጎብኝዎች ዝግ የተደረገ ሲሆን ምክንያቱ ድግሞ ከባድ እንደሆነ የተገለጸው በአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ ነው። ምልክቶች የማይታዩበት አቪያን ፍሉ በባሕርያቸው ከቦታ ቦታ በሚፈልሱ ወፎች ላይ የሚከሰት ነው። በአገር ውስጥ ያሉ ወፎች ለዚህ ወረርሽኝ ያላቸው ተጋላጭነት ዝቅተኛ ቢሆንም ቫይረሱ ለሽያጭ በቀረቡ ወይም በቤተሰብ ውስጥ በሚራቡ የአዕዋፍ ዝርያዎች ላይ ከተገኘ ግን ሁሉንም በፍጥነት ማስወገድ ይመከራል። በሰሜን እስራኤል 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ሞሻቭ ማርጋዮት በተሰኘው የጋራ ማርቢያ ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን የሚበልጡ እንቁላል የሚጥሉ ዶሮዎች ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና በሰዎች ላይ ያለውን አደጋ ለመቀነስ እየተገለሉ መሆኑን የእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። ሞሻቭ በእስራኤል ውስጥ ጥቅም ላይ ከሚውሉ እንቁላሎች 7 በመቶውን ያቀርባል። ታይምስ ኦፍ እስራኤል የተሰኘው ሚዲያ እንደዘገበው በእስራኤል የመጀመሪያው የአቪያን ፍሉ ወረርሽኝ እንደ አውሮፓውያኑ ጥቅምት 18 ተመዝግቧል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59815430 |
5sports
| ማንቸስተር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አደጋ? | እጅግ ድንቅ ፉክክር የታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያለፈው ወድድር ዘመን እነሆ በአዲሱ ተተክቷል። አውሮፓ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የዓለማችን ልጥጥ ክለቦች የሚገኙበት ቢሆንም አደጋ የተጋረጠበት ይመስላል። አደጋው ደግሞ የባለፈው ውድድር ዘመን ቻምፒዮና - ማንቸስተር ሲቲ፤ ይላል የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ቤን ሱዘርላንድ። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» •"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተወዳጅ እንዲሆን ካደረጉት ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ልብ-አንጠልጣይ ፉክክር የሚታይበት መሆኑ ነው። ፈጣን፣ ፈታኝ እና የማይጠበቁ ውጤቶች የሚመዘገቡበት ሊግ ነው። ቢሆንም ይህ ምስል አደጋ ላይ ይመስላል። በዓመታት ሂደት ሊጉ ስድስት ኃያላን ክለቦች ተብለው የሚታወቁትን አምርቷል። ዩናይትድና ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አርሴናል እና የከተማ ተቀናቃኙ ቶተንሃም እንዲሁም የምዕራብ ለንደኖቹ ቼልሲ። አደጋው እዚህ ጋ ነው። በሂደት ስድስቱ ኃያላን ቀርቶ አንድ ኃያል እንዳይሆን የሚል ስጋት። ያለፈው ውድድር ዘመን እጅግ ተወዳጅ ያደረገው ሊቨርፑል የሲቲን እግር እየተከተለ ዋንጫ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ነበር። ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች የቋመጡለትን ዋንጫ ተቀያይረው አግኝተዋል። ፕሪሚዬር ሊግን የቋመጠው ሊቨርፑል ቻምፒዮንስ ሊግ ሲያነሳ፤ ቻምፒዮንስ ሊግን ለማንሳት የሻተው ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ወስዷል። •ታዳጊዎችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ተከሶ የነበረው ቱጃር አሟሟት ጥያቄን ፈጥሯል ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሶስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል፤ በአቡ ዳቢ ቱጃሮች የተያዘው ሲቲ ደግሞ ቻምፒዮንስ ሊግ አንስቶ አያውቅም። ሲቲ ዘንድሮ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ከቻለ ሌላ ታሪክ ይፅፋል። በአንድ ውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማስቆጠር እና በርካታ ነጥቦች በማምጣት ሲቲ ሪከርዱን ይዟል። በኤፍ ኤ ዋንጫ ዋትፈርድን 6-0 በመርታት ተመልካችን አጀብ አሰኝተዋል። ይህን ያዩ የኳስ ተንታኞች 'እግር ኳስ ከስማለች' እስከማለት ደርሰዋል። የፈርናንዲሆ ምትክ ያስፈልጋቸዋል እየተባሉ ሲታሙ የነበሩት ሲቲዎች ባለተሰጥዖው ሮድሪን አስፈርመዋል። በዘመናዊ እግር ኳስ ምርጡ አሰልጣኝ የሚል ስያሜ የተሰጠው ፔፕ ጉዋርዲዮላን የያዙት ሲቲዎች ወደፊትም ተፅዕኖዋቸው እንደሚቀጥል ይገመታል። የተሻለ የእረፍት ጊዜ ያሳለፉት ሲቲዎች በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ሊቨርፑልን መርታት ችለዋል። በአቋምም ሆነ በስነልቡና ጥንካሬ ከሊቨርፑል የተሻሉ ሆነው ነበር የታዩት። በሌላ በኩል ሌሎች ኃያላን ሲቲን ተቋቁመው የሊጉን ዋንጫ ያነሳሉ ማለት ከባድ ነው። አርሴናሎች ፔፔን ቢያስፈርሙም፤ ተከላካይ መስመሩ አሁንም ጥገና የሚያሻው ይመስላል። ኪዬራን ቲየርኒን ከሴልቲክ፣ ዴቪድ ልዊዝን ደግሞ ከቼልሲ ማስፈረማቸው ሳይዘነጋ። አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ቼልሲዎች ኤደን ሃዛርድን ለቼልሲ ቢሸጡም በተጣለባቸው ቅጣት ምክንያት ተጫዋች መግዛት አልቻሉም። ይህ ደግሞ ለአዲሱ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ሁኔታዎችን የሚያከብድበት ይመስላል። የዩናይትዱ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድኑን የተቀበለ ሰሞን ድንቅ አቋም ቢያሳይም ወደ መጨረሻ ከበድ ያለ ጊዜ አይቷል። ዩናይትዶች ሊጉን ያሸንፋሉ ተብሎ የተሰጣቸው ግምት ከእስከዛሬው እጅግ ዝቅ ያለ ነው። •ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ ታድያ የእነዚህ ኃያላን ቡድኖች እንደ ሲቲ ዝግጁ አለመሆን ለሊጉ አደጋ መሆኑ አይቀርም። እንደ ጣልያን [ጁቬንቱስ ለ8 ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳበት]፤ እንዲሁም ጀርመን [ባየርንሚዩኒክ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት] ሊጎች አጓጊነቱ የወረደ እንዳይሆን ነው ዋነኛው ስጋት። በየወሩ ክፍያ እየከፈሉ የሚመለከቱ ተመልካቾች ክፍያቸውን ሊያቋርጡ ይችላሉ፤ በተለይ ደግሞ እንግሊዝ የሚገኙቱ የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ማሽቆልቆል ከማሳየቱ ጋር በተያያዘ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን ፉክክር የማይታይበት ሊግን ለማዬት ተመልካቾች ብዙም ጉጉት ላያሳዩ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ጣልያን እና ጀርመን የአፍሪቃ እና እስያ ተመልካቾችን ለመመለስ ብዙ ትግል እያደረጉ እንዳለ ልብ ይሏል። አውሮፓ ሱፐር ሊግ እውን ከሆነ አደጋው ለፕሪሚዬር ሊግም ጭምር ነው። ሲቲ በገንዘቡ ነው ዋንጫ እየገዛ ያለው የሚለው ትላልቅ የሊጉ ክለቦች ጭምር ሊቀላቀሉ ይችላሉ። 500 ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ የሱፐር ሊግ ዓመታዊ ገቢ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ምንም እንኳ የሱፐር ሊግ ሃሳብ ከ98 የአውሮፓ ክለቦች በ94ቱ ተቃውሞ ቢገጥመውም። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ግን ዕቅዱ እንዳለ ነው። ማን ያውቃል ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊዎች ቁጥር እየጨመረ ሊመጣ ይችል ይሆናል። ቶተንሃም፣ ቼልሲ እና አርሴናል ባለፈው ዓመት አንድ ወቅት ላይ ለሊጉ ለዋንጫ ያሰፈሰፉ ቡድኖች ነበሩ። ቢሆንም ከተስፋ ውጭ ምንም የተጨበጠ አልነበረም። ይህ ደግሞ ደጋፊዎቻቸው በጊዜ ሂደት እየሸሹ እንዲመጡ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። ደጋፊዎች ሁሉንም የቀጥታ ሥርጭት ጨዋታዎች ከፍለው መመልከት አይችሉም። አውሮፕ ሊግ ጨዋታዎች ግን ክፍያቸው እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያነሰ ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ አደጋ ነው። ማንቸስተር ሲቲ መቆም ካልቻለ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዕጣ ፈንታ ከሴሪ ኤ፣ ቡንደስሊጋ እና የስኮቲሽ ፕሪሚዬርሺፕ የተለየ የሚሆን አይመስልም፤ የአንድ ቡድን ፍፁም ተፅዕኖ የሚታይበት ሊግ። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አሁን ላይ አጓጊና እና ኃያል ይመስላል፤ በዚህ ከቀጠለ ግን አወዳደቁ የሚያምር አይሆንም። | ማንቸስተር ሲቲ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አደጋ? እጅግ ድንቅ ፉክክር የታየበት የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያለፈው ወድድር ዘመን እነሆ በአዲሱ ተተክቷል። አውሮፓ ውስጥ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ የዓለማችን ልጥጥ ክለቦች የሚገኙበት ቢሆንም አደጋ የተጋረጠበት ይመስላል። አደጋው ደግሞ የባለፈው ውድድር ዘመን ቻምፒዮና - ማንቸስተር ሲቲ፤ ይላል የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ቤን ሱዘርላንድ። •ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን መረጃ የለም» •"የት ይቀርልሃል!? አፈር ድሜ ትበላለህ...!" ጋሽ አበራ ሞላ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ተወዳጅ እንዲሆን ካደረጉት ጉዳዮች መካከል ዋነኛው ልብ-አንጠልጣይ ፉክክር የሚታይበት መሆኑ ነው። ፈጣን፣ ፈታኝ እና የማይጠበቁ ውጤቶች የሚመዘገቡበት ሊግ ነው። ቢሆንም ይህ ምስል አደጋ ላይ ይመስላል። በዓመታት ሂደት ሊጉ ስድስት ኃያላን ክለቦች ተብለው የሚታወቁትን አምርቷል። ዩናይትድና ሲቲ፣ ሊቨርፑል፣ አርሴናል እና የከተማ ተቀናቃኙ ቶተንሃም እንዲሁም የምዕራብ ለንደኖቹ ቼልሲ። አደጋው እዚህ ጋ ነው። በሂደት ስድስቱ ኃያላን ቀርቶ አንድ ኃያል እንዳይሆን የሚል ስጋት። ያለፈው ውድድር ዘመን እጅግ ተወዳጅ ያደረገው ሊቨርፑል የሲቲን እግር እየተከተለ ዋንጫ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ነበር። ነገር ግን ሁለቱም ክለቦች የቋመጡለትን ዋንጫ ተቀያይረው አግኝተዋል። ፕሪሚዬር ሊግን የቋመጠው ሊቨርፑል ቻምፒዮንስ ሊግ ሲያነሳ፤ ቻምፒዮንስ ሊግን ለማንሳት የሻተው ሲቲ የሊጉን ዋንጫ ወስዷል። •ታዳጊዎችን በወሲብ ንግድ በማሰማራት ተከሶ የነበረው ቱጃር አሟሟት ጥያቄን ፈጥሯል ሊቨርፑል የሊጉን ዋንጫ ካነሳ ሶስት አስርት ዓመታት ተቆጥረዋል፤ በአቡ ዳቢ ቱጃሮች የተያዘው ሲቲ ደግሞ ቻምፒዮንስ ሊግ አንስቶ አያውቅም። ሲቲ ዘንድሮ የሊጉን ዋንጫ ማንሳት ከቻለ ሌላ ታሪክ ይፅፋል። በአንድ ውድድር ዘመን በርካታ ጎሎች በማስቆጠር እና በርካታ ነጥቦች በማምጣት ሲቲ ሪከርዱን ይዟል። በኤፍ ኤ ዋንጫ ዋትፈርድን 6-0 በመርታት ተመልካችን አጀብ አሰኝተዋል። ይህን ያዩ የኳስ ተንታኞች 'እግር ኳስ ከስማለች' እስከማለት ደርሰዋል። የፈርናንዲሆ ምትክ ያስፈልጋቸዋል እየተባሉ ሲታሙ የነበሩት ሲቲዎች ባለተሰጥዖው ሮድሪን አስፈርመዋል። በዘመናዊ እግር ኳስ ምርጡ አሰልጣኝ የሚል ስያሜ የተሰጠው ፔፕ ጉዋርዲዮላን የያዙት ሲቲዎች ወደፊትም ተፅዕኖዋቸው እንደሚቀጥል ይገመታል። የተሻለ የእረፍት ጊዜ ያሳለፉት ሲቲዎች በኮሚኒቲ ሺልድ ጨዋታ ሊቨርፑልን መርታት ችለዋል። በአቋምም ሆነ በስነልቡና ጥንካሬ ከሊቨርፑል የተሻሉ ሆነው ነበር የታዩት። በሌላ በኩል ሌሎች ኃያላን ሲቲን ተቋቁመው የሊጉን ዋንጫ ያነሳሉ ማለት ከባድ ነው። አርሴናሎች ፔፔን ቢያስፈርሙም፤ ተከላካይ መስመሩ አሁንም ጥገና የሚያሻው ይመስላል። ኪዬራን ቲየርኒን ከሴልቲክ፣ ዴቪድ ልዊዝን ደግሞ ከቼልሲ ማስፈረማቸው ሳይዘነጋ። አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት ቼልሲዎች ኤደን ሃዛርድን ለቼልሲ ቢሸጡም በተጣለባቸው ቅጣት ምክንያት ተጫዋች መግዛት አልቻሉም። ይህ ደግሞ ለአዲሱ አሰልጣኝ ፍራንክ ላምፓርድ ሁኔታዎችን የሚያከብድበት ይመስላል። የዩናይትዱ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድኑን የተቀበለ ሰሞን ድንቅ አቋም ቢያሳይም ወደ መጨረሻ ከበድ ያለ ጊዜ አይቷል። ዩናይትዶች ሊጉን ያሸንፋሉ ተብሎ የተሰጣቸው ግምት ከእስከዛሬው እጅግ ዝቅ ያለ ነው። •ዘሩባቤል ሞላና በአነቃቂ መንፈስ የታሸው 'እንፋሎት' አልበሙ ታድያ የእነዚህ ኃያላን ቡድኖች እንደ ሲቲ ዝግጁ አለመሆን ለሊጉ አደጋ መሆኑ አይቀርም። እንደ ጣልያን [ጁቬንቱስ ለ8 ተከታታይ ዓመታት ዋንጫ ያነሳበት]፤ እንዲሁም ጀርመን [ባየርንሚዩኒክ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት] ሊጎች አጓጊነቱ የወረደ እንዳይሆን ነው ዋነኛው ስጋት። በየወሩ ክፍያ እየከፈሉ የሚመለከቱ ተመልካቾች ክፍያቸውን ሊያቋርጡ ይችላሉ፤ በተለይ ደግሞ እንግሊዝ የሚገኙቱ የሃገሪቱ ምጣኔ ሃብት ማሽቆልቆል ከማሳየቱ ጋር በተያያዘ። በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን ፉክክር የማይታይበት ሊግን ለማዬት ተመልካቾች ብዙም ጉጉት ላያሳዩ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ። ጣልያን እና ጀርመን የአፍሪቃ እና እስያ ተመልካቾችን ለመመለስ ብዙ ትግል እያደረጉ እንዳለ ልብ ይሏል። አውሮፓ ሱፐር ሊግ እውን ከሆነ አደጋው ለፕሪሚዬር ሊግም ጭምር ነው። ሲቲ በገንዘቡ ነው ዋንጫ እየገዛ ያለው የሚለው ትላልቅ የሊጉ ክለቦች ጭምር ሊቀላቀሉ ይችላሉ። 500 ሚሊዮን ዩሮ ደግሞ የሱፐር ሊግ ዓመታዊ ገቢ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው። ምንም እንኳ የሱፐር ሊግ ሃሳብ ከ98 የአውሮፓ ክለቦች በ94ቱ ተቃውሞ ቢገጥመውም። •በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን ፌስቲቫል፡ ሙዚቃ፣ ኳስ፣ ፍቅርና ቡጢ.. ግን ዕቅዱ እንዳለ ነው። ማን ያውቃል ከጊዜ ወደ ጊዜ የደጋፊዎች ቁጥር እየጨመረ ሊመጣ ይችል ይሆናል። ቶተንሃም፣ ቼልሲ እና አርሴናል ባለፈው ዓመት አንድ ወቅት ላይ ለሊጉ ለዋንጫ ያሰፈሰፉ ቡድኖች ነበሩ። ቢሆንም ከተስፋ ውጭ ምንም የተጨበጠ አልነበረም። ይህ ደግሞ ደጋፊዎቻቸው በጊዜ ሂደት እየሸሹ እንዲመጡ ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነው። ደጋፊዎች ሁሉንም የቀጥታ ሥርጭት ጨዋታዎች ከፍለው መመልከት አይችሉም። አውሮፕ ሊግ ጨዋታዎች ግን ክፍያቸው እንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ያነሰ ነው። ይህ ደግሞ ትልቅ አደጋ ነው። ማንቸስተር ሲቲ መቆም ካልቻለ የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዕጣ ፈንታ ከሴሪ ኤ፣ ቡንደስሊጋ እና የስኮቲሽ ፕሪሚዬርሺፕ የተለየ የሚሆን አይመስልም፤ የአንድ ቡድን ፍፁም ተፅዕኖ የሚታይበት ሊግ። የእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አሁን ላይ አጓጊና እና ኃያል ይመስላል፤ በዚህ ከቀጠለ ግን አወዳደቁ የሚያምር አይሆንም። | https://www.bbc.com/amharic/news-49310398 |
0business
| የቱርክ የዋጋ ግሽበት በ24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ | በቱርክ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለለት የዋጋ ግሽበት አጋጠመ። በአገሪቱ ያለው የዋጋ ግሸበት 83 በመቶ መድረሱ ተገልጿል። ትራንስፖርት፣ ምግብ እና የቤት ዘርፎች ደግሞ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። ኢንፍሌሽን ሪሰርች ግሩፕ የሚባለው ገለልተኛ የአጥኚዎች ቡድን ዓመታዊውን የዋጋ ግሽበት 186.7 በመቶ ያደርሰዋል። ባለፈው ዓመት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በሚል ባልተለመደ ሁኔታ የወለድ ምጣኔውን ቀንሰው ነበር። በርካታ ባንኮች ደግሞ የዋጋ ግሽበቱን ለመከላከል የወለድ መጠናቸውን ከፍ አድርገው ነበር። የትራንስፖርት ዘርፉ 117.66 በመቶ የዋጋ ግሽበት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው። ምግብ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ መጠጦች በ93 በመቶ ይከተላሉ። የምጣኔ ሃብት ፖሊሲያቸው በውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ጣልቃ መግባትን የሚያካትተው ኤርዶሃን፤ የወለድ ምጣኔን “የሁሉም ሴጣኖች እናት እና አባት ነው” ሲሉ ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት የወለድ ምጣኔ ከ19 በመቶ ወደ 14 በመቶ መቀነሱ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሊራን ዋጋ ቀንሶታል። ይህም አገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸው ዕቃዎችን በከፍተኛ ዋጋ እንድትገዛ ያስገድዳታል። ሊራ ከዶላር አንጻር ያለው ልዩነት ክብረወሰን በሆነ ደረጃ ቀንሶ 1 የኤሜሪካ ዶላር በ18.56 ሊራ እየተመነዘረ ነው። የአሜሪካው ባንክ ጂፒ ሞርጋን እንዳለው የቱርክ የዋጋ ግሽበት “የፖሊሲ ለውጥ ካልተደረገ ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ ይሆናል።” ሰኞ ምሽት ቴሌቭዥን ፊት የቀረቡት ፕሬዝዳንት አርዶሃን “ይህንን የዋጋ ግሽበት ችግር አራግፈን በጋራ ጠንካራዋን ቱርክ እንገነባለን” ብለዋል። ይህ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ጭማሪ የተከሰተው ከሁለተኛው የዓለም ጦርንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲሉ የቀድሞው የቱርክ ማዕከላዊ ባንክ ዋና ኢኮኖሚስት ሃካን ካራ ተናግረዋል። ከሚቀጥለው ሃገራዊ ምርጫ በፊት የዋጋ ግሽበት እና የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ የኤርዶሃንን ፓርቲ ፈተና ይሆናል ተብሏል። ከኮቪድ-19 ስርጭት ጋር በተያያዘ በተከሰተ የአቅርቦት መስተጓጎል በመፈጠሩ እና የነዳጅ እና የምግብ ዋጋን ካናረው የዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ጭማሪ እየተከሰተ ነው። | የቱርክ የዋጋ ግሽበት በ24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ በቱርክ ባለፉት 24 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለለት የዋጋ ግሽበት አጋጠመ። በአገሪቱ ያለው የዋጋ ግሸበት 83 በመቶ መድረሱ ተገልጿል። ትራንስፖርት፣ ምግብ እና የቤት ዘርፎች ደግሞ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል። ኢንፍሌሽን ሪሰርች ግሩፕ የሚባለው ገለልተኛ የአጥኚዎች ቡድን ዓመታዊውን የዋጋ ግሽበት 186.7 በመቶ ያደርሰዋል። ባለፈው ዓመት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት በሚል ባልተለመደ ሁኔታ የወለድ ምጣኔውን ቀንሰው ነበር። በርካታ ባንኮች ደግሞ የዋጋ ግሽበቱን ለመከላከል የወለድ መጠናቸውን ከፍ አድርገው ነበር። የትራንስፖርት ዘርፉ 117.66 በመቶ የዋጋ ግሽበት በማስመዝገብ ቀዳሚ ነው። ምግብ እና ከአልኮል ነጻ የሆኑ መጠጦች በ93 በመቶ ይከተላሉ። የምጣኔ ሃብት ፖሊሲያቸው በውጭ ምንዛሪ ገበያ ውስጥ ጣልቃ መግባትን የሚያካትተው ኤርዶሃን፤ የወለድ ምጣኔን “የሁሉም ሴጣኖች እናት እና አባት ነው” ሲሉ ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት የወለድ ምጣኔ ከ19 በመቶ ወደ 14 በመቶ መቀነሱ የአገሪቱን መገበያያ ገንዘብ ሊራን ዋጋ ቀንሶታል። ይህም አገሪቱ ከውጭ የምታስገባቸው ዕቃዎችን በከፍተኛ ዋጋ እንድትገዛ ያስገድዳታል። ሊራ ከዶላር አንጻር ያለው ልዩነት ክብረወሰን በሆነ ደረጃ ቀንሶ 1 የኤሜሪካ ዶላር በ18.56 ሊራ እየተመነዘረ ነው። የአሜሪካው ባንክ ጂፒ ሞርጋን እንዳለው የቱርክ የዋጋ ግሽበት “የፖሊሲ ለውጥ ካልተደረገ ባልተለመደ መልኩ ከፍተኛ ይሆናል።” ሰኞ ምሽት ቴሌቭዥን ፊት የቀረቡት ፕሬዝዳንት አርዶሃን “ይህንን የዋጋ ግሽበት ችግር አራግፈን በጋራ ጠንካራዋን ቱርክ እንገነባለን” ብለዋል። ይህ ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ጭማሪ የተከሰተው ከሁለተኛው የዓለም ጦርንት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ሲሉ የቀድሞው የቱርክ ማዕከላዊ ባንክ ዋና ኢኮኖሚስት ሃካን ካራ ተናግረዋል። ከሚቀጥለው ሃገራዊ ምርጫ በፊት የዋጋ ግሽበት እና የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ የኤርዶሃንን ፓርቲ ፈተና ይሆናል ተብሏል። ከኮቪድ-19 ስርጭት ጋር በተያያዘ በተከሰተ የአቅርቦት መስተጓጎል በመፈጠሩ እና የነዳጅ እና የምግብ ዋጋን ካናረው የዩክሬን ጦርነት ጋር ተያይዞ በዓለም አቀፍ ደረጃ የዋጋ ጭማሪ እየተከሰተ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cpey3qdzd08o |
3politics
| በኢራቅ የሺዓ መሪው ራሳቸውን ከፖለቲካ ማግለላቸውን ተከትሎ በተነሳ ብጥብጥ 15 ሰዎች ተገደሉ | በኢራቅ የሺዓ መሪው ሙክታዳ አል ሳድር ከፖለቲካ ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በተነሳ ግርግር አስራ አምስት ሰዎች ተገደሉ። በኢራቋ መዲና ባግዳድ የተነሳው ሁከት በጸጥታ ኃይሎችና በፖለቲከኛው ደጋፊዎች መካከል በተነሳው ግጭት ነው። የኢራቅ ባለስልጣናት እንደሚሉት የሙክታዳ አል ሳድር ደጋፊዎች ተቃውሟቸውን ለማሰማት የፕሬዚዳንቱን ቤተ መንግሥት ጥሰው ከገቡ በኋላ በርካቶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። አለመረጋጋቱ የተቀሰቀው ሙክታዳ አል ሳድር ከፖለቲካው አለም ራሳቸውን ማግለላቸውን ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው። የኢራቅ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚንስትር መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ ያደረጉ ሲሆን በሌሎች ከተሞች በተፈጠረውም አለመረጋጋት ጦሩ ብሔራዊ የሰዓት እላፊ አውጇል። የኢራቅ ጎዳናዎች በተዋጊዎች የተኩስ ልውውጥ የተሞሉ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከታየውም አስከፊው ነው ተብሏል። እነዚህ ውጊያዎች የተካሄዱት በከተማው አረንጓዴ ዞን ተብሎ በሚጠራውና የመንግሥት ህንፃዎች ችና የውጭ ኤምባሲዎች በሚገኙበት አካባቢ ነው። ግጭቱ የተፈጠረው ለሙክታዳ አል ሳድር ታማኝ በሆኑት ፒስ ብርጌድስ በተሰኘው ሚሊሻ እና በኢራቅ ጦር አባላት መካከል እንደሆነ የኢራቅ ደህንነት ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋሩ ቪዲዮዎች አንዳንድ ተዋጊዎች በሮኬት የሚንቀሳቀሱ የእጅ ቦምቦችን ጨምሮ የከባድ መሳሪያ ልውውጥ እንደነበር ያሳያሉ። ይህንንም ተከትሎ ኢራን ከኢራቅ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር የዘጋች ሲሆን ኩዌት ዜጎቿ አገሪቷን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት 15 የሙክታዳ አል ሳድር ደጋፊዎች በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ሲያልፍ ወደ 350 የሚጠጉት ተቃዋሚዎች ቆስለዋል ሲል ኤኤፍኢ ዘግቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃለ አቀባይ በኢራቅ የተከሰቱት ሁነቶች አስደንጋጭ መሆናቸውን ገልጻው “ሁከቱን ለማረጋጋት አፋጣኝ እርምጃዎች እንዲወሰዱ” ጥሪ አቅርበዋል ። ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሙክታዳ አል ሳድር አጋር የሆኑት ሙስጠፋ አል ካዲሚ የካቢኔ ስብሰባዎች እንዲታገዱ ውሳኔ አሳልፈው ተጽዕኖ ፈጣሪ የሃይማኖት አባቶች ጣልቃ እንዲገቡ እና ብጥብጡን እንዲያቆሙ ተማጽነዋል። የሙክታዳ አል ሳድር ከፍተኛ ረዳት ለኢራቅ መንግስት የዜና ወኪል ኢ ኤን ኤ እንደተናገሩት ሁከቱ እና የጦር ውጊያው እስኪቆም ድረስ የረሃብ አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሙክታዳ አል ሳድር ራሳቸውን ከፖለቲካ ህይወት ለማግለል ውሳኔ ያስተላለፉትተቀናቃኝ የሺአ መሪዎች እና ፓርቲዎች የኢራቅን የፖለቲካ ስርዓት ለማሻሻል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው። በጥቅምት ወር፣ ለሙክታዳ አል ሳድር ታማኝ የሆኑ እጩዎች በኢራቅ ፓርላማ ብዙ መቀመጫዎችን ቢያሸንፉም ነገር ግን መንግስት ለመመስረት በቂ መቀመጫዎችን ማግኘት አልቻሉም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኢራን ከሚደገፉ የሺዓ ቡድኖች ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ ባለመሆናቸውም ለአንድ አመት ያህል የፖለቲካ አለመረጋጋት አስከትሏል። ሙክታዳ አል ሳድር የኢራቅ ፖለቲከኛ እና የሚሊሺያ መሪ ሲሆኑ የሳድሪስት ንቅናቄ መሪ እንዲሁም ቀደም ሲል የአሜሪካ ጦር ኢራቅ ውስጥ በነበረበት ወቅት ይመሩት የነበረው ሚሊሻ ማህዲ ጦር ተተኪ የሆነው የሰላም ኩባንያዎች መሪ ናቸው። | በኢራቅ የሺዓ መሪው ራሳቸውን ከፖለቲካ ማግለላቸውን ተከትሎ በተነሳ ብጥብጥ 15 ሰዎች ተገደሉ በኢራቅ የሺዓ መሪው ሙክታዳ አል ሳድር ከፖለቲካ ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በተነሳ ግርግር አስራ አምስት ሰዎች ተገደሉ። በኢራቋ መዲና ባግዳድ የተነሳው ሁከት በጸጥታ ኃይሎችና በፖለቲከኛው ደጋፊዎች መካከል በተነሳው ግጭት ነው። የኢራቅ ባለስልጣናት እንደሚሉት የሙክታዳ አል ሳድር ደጋፊዎች ተቃውሟቸውን ለማሰማት የፕሬዚዳንቱን ቤተ መንግሥት ጥሰው ከገቡ በኋላ በርካቶች መቁሰላቸውን ተናግረዋል። አለመረጋጋቱ የተቀሰቀው ሙክታዳ አል ሳድር ከፖለቲካው አለም ራሳቸውን ማግለላቸውን ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው። የኢራቅ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚንስትር መረጋጋት እንዲሰፍን ጥሪ ያደረጉ ሲሆን በሌሎች ከተሞች በተፈጠረውም አለመረጋጋት ጦሩ ብሔራዊ የሰዓት እላፊ አውጇል። የኢራቅ ጎዳናዎች በተዋጊዎች የተኩስ ልውውጥ የተሞሉ ሲሆን በቅርብ ዓመታት ውስጥ ከታየውም አስከፊው ነው ተብሏል። እነዚህ ውጊያዎች የተካሄዱት በከተማው አረንጓዴ ዞን ተብሎ በሚጠራውና የመንግሥት ህንፃዎች ችና የውጭ ኤምባሲዎች በሚገኙበት አካባቢ ነው። ግጭቱ የተፈጠረው ለሙክታዳ አል ሳድር ታማኝ በሆኑት ፒስ ብርጌድስ በተሰኘው ሚሊሻ እና በኢራቅ ጦር አባላት መካከል እንደሆነ የኢራቅ ደህንነት ባለስልጣናት አስታውቀዋል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋሩ ቪዲዮዎች አንዳንድ ተዋጊዎች በሮኬት የሚንቀሳቀሱ የእጅ ቦምቦችን ጨምሮ የከባድ መሳሪያ ልውውጥ እንደነበር ያሳያሉ። ይህንንም ተከትሎ ኢራን ከኢራቅ ጋር የሚያዋስናትን ድንበር የዘጋች ሲሆን ኩዌት ዜጎቿ አገሪቷን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ አሳስባለች። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት 15 የሙክታዳ አል ሳድር ደጋፊዎች በጥይት ተመትተው ህይወታቸው ሲያልፍ ወደ 350 የሚጠጉት ተቃዋሚዎች ቆስለዋል ሲል ኤኤፍኢ ዘግቧል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ቃለ አቀባይ በኢራቅ የተከሰቱት ሁነቶች አስደንጋጭ መሆናቸውን ገልጻው “ሁከቱን ለማረጋጋት አፋጣኝ እርምጃዎች እንዲወሰዱ” ጥሪ አቅርበዋል ። ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሙክታዳ አል ሳድር አጋር የሆኑት ሙስጠፋ አል ካዲሚ የካቢኔ ስብሰባዎች እንዲታገዱ ውሳኔ አሳልፈው ተጽዕኖ ፈጣሪ የሃይማኖት አባቶች ጣልቃ እንዲገቡ እና ብጥብጡን እንዲያቆሙ ተማጽነዋል። የሙክታዳ አል ሳድር ከፍተኛ ረዳት ለኢራቅ መንግስት የዜና ወኪል ኢ ኤን ኤ እንደተናገሩት ሁከቱ እና የጦር ውጊያው እስኪቆም ድረስ የረሃብ አድማ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል። ሙክታዳ አል ሳድር ራሳቸውን ከፖለቲካ ህይወት ለማግለል ውሳኔ ያስተላለፉትተቀናቃኝ የሺአ መሪዎች እና ፓርቲዎች የኢራቅን የፖለቲካ ስርዓት ለማሻሻል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ነው። በጥቅምት ወር፣ ለሙክታዳ አል ሳድር ታማኝ የሆኑ እጩዎች በኢራቅ ፓርላማ ብዙ መቀመጫዎችን ቢያሸንፉም ነገር ግን መንግስት ለመመስረት በቂ መቀመጫዎችን ማግኘት አልቻሉም። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በኢራን ከሚደገፉ የሺዓ ቡድኖች ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ ባለመሆናቸውም ለአንድ አመት ያህል የፖለቲካ አለመረጋጋት አስከትሏል። ሙክታዳ አል ሳድር የኢራቅ ፖለቲከኛ እና የሚሊሺያ መሪ ሲሆኑ የሳድሪስት ንቅናቄ መሪ እንዲሁም ቀደም ሲል የአሜሪካ ጦር ኢራቅ ውስጥ በነበረበት ወቅት ይመሩት የነበረው ሚሊሻ ማህዲ ጦር ተተኪ የሆነው የሰላም ኩባንያዎች መሪ ናቸው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cw0gevzxzqwo |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማቅረብ የሃብታምና ድሃ አገራት ፍጥጫ | ስለ ኮቪድ-19 ክትባት ስናወራ አንድ ጥያቄ ብዙዎቻችንን ሰቅዞ መያዙ አያጠራጥርም - መቼ ይሆን እኔ የምከተበው? የሚለው። ጥቂት አገራት የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የማሕበረሰብ ክፍሎች ብለው ለይተዋል። የዓለማችንን ሰዎች ፀረ-ኮሮናቫይረስ መከተብ የሞትና የሕይወት ጉዳይ ነው። ነገር ግን እንዲህ ቀላል አይደለም። ጉዳዩ በርካታ ግዙፍና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት፣ መንግሥታት የማይፈፅሙትን ቃል የሚገቡበት፣ በቢሮክራሲ የታጠረና ቁጥጥር የበረታበት ነው። ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት የተሰኘው ተቋም ባልደረባ የሆኑት አጋተ ዳማራይስ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ሠርተዋል። ተቋሙ ዓለማችን ምን ያክል ክትባት ማምረት እንደምትችልና ያለው የጤና መሠረተ ልማት ምን ያህል በቂ ነው? የሚለውን አጥንቷል። የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ፍጥጫው የሃብታምና የድሃ ነው። ዩናይትድ ኪንግደምና ዩናይትድ ስቴትስ በአሁኑ ወቅት በቂ የሆነ የክትባት አቅርቦት አላቸው። ምክንያቱም ክትባቱን መግዛት የሚያስችል ገንዘብ አላቸውና። ሌሎች እንደ ካናዳና የአውሮፓ ሕብረት አባላት ያሉ አገራት የመግዛት አቅሙ ቢኖራቸውም ክትባት ላይ ብዙ እየተሯሯጡ ያሉ አይመስሉም። ካናዳ ሕዝቧ ከሚያስፈልገው የክትባት መጠን አምስት እጥፍ ከፍ ያለ ክትባት ብታዝም ክትባቱ በታሰበው ጊዜ የደረሰላት አይመስልም። ካናዳ ክትባቱ በፈለገችው ሰዓት ያልደረሰላት ምናልባት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የውጭ ገበያን እንዳይከለክል በመፍራት ፊቱን ወደ አውሮፓውያን ክትባት አምራቾች በማዞሯ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ሳትሆን የአውሮፓ ሕብረት ነው ክትባት ወደ ውጭ መላክ የለበትም የሚል አቋም እያንፀባረቀ ያለው። አብዛኛዎቹ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ አገራት ገና ዜጎቻቸውን መከተብ አልጀመሩም። ነገር ግን በተለይ መሃል ላይ አንዳንድ ሃገራት አስደናቂ ውጤት እያስመዘገቡ ነው። ለምሳሌ ሰርቢያ በአሁኑ ወቅት ከሕዝቧ በመቶኛ ሲቆጠር በርካታ ሰው በማስከተብ ከዓለም ስምንተኛ ናት። እርግጥ ሰርቢያ ከቻይናና ሩስያ ብዙ ተጠቅማለች። ሁለቱ ሃያላን አገራት በምስራቅ አውሮፓ ያላቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሰርቢያን ወዳጅ አድርገው ይዘዋል። የሩስያ ስፓትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትና የቻይናው ሲኖፋርም ሰርቢያ ውስጥ እንደልብ ይገኛሉ። ምንም እንኳ ሰርቢያዊያን የክትባት ቅፅ ሲሞሉ ከፋይዘር፣ ስፓትኒክ አሊያም ሲኖፋርም ምረጡ ቢባሉም በርካቶች ሲኖፋርም ነው የሚሰጣቸው። ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስም ሲኖፋርም በተሰኘው የቻይና ክትባት ላይ ጥገኛ ናት። አገሪቱ ለዜጎቿ እየሰጠችው ካለው ክትባት 80 በመቶው ሲኖፋርም ነው። አልፎም በአገሯ የሲኖፋርም ማምረቻ ፋብሪካ እየገነባች ትገኛለች። አንድ አገር የዓለማችን ከፍተኛ የክትባት አምራች ሆነች ማለት ዜጎቿን በሙሉ ቀድማ ትከትባለች ማለት አይደለም። አይኢዩ የተሰኘው ተቋም ሠራሁት ባለው ጥናት መሠረት የዓለማችን ከፍተኛ ክትባት አምራች የሚባሉት ቻይናና ሕንድ እስከ ፈረንጆቹ 2022 ድረስ ዜጎቻቸውን በበቂ ሁኔታ ላይከትቡ ይችላሉ። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አገራቱ ያላቸው የሕዝብ ብዛትና የጤና ሠራተኞች ቁጥጥር አለመመጣጠኑ ነው። ሕንድ የዓለማችን ከፍተኛው የክትባት አምራች ኩባንያ የሆነችው በአንድ ሰው ምክንያት ነው። አንዳር ፑንዋላ። የዚህ ሰው ኩባንያ የሆነው ሴረም በዓለማችን ከፍተኛው የክትባት አምራች ድርጅት ነው። ነገር ግን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት አጋማሽ ቤተሰቦቹ ሰውዬው አብዷል እስኪሉ ድረስ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች እየመዠረጠ ለክትባት ምርምር ያውል ነበር። ቢሆንም ቁማሩ ተሳክቶለት ክትባቶቹ ውጤታማ መሆን ችለዋል። አሁን የዚህ ሃብታም ኩባንያ በቀን 2.4 ሚሊዮን ክትባቶች ያመርታል። የፑንዋላ ኩባንያ ለሕንድ፣ ብራዚል፣ ሞሮኮ፣ ባንግላዴሽ እና ደቡብ አፍሪካ ክትባት በዋናነት በማቅረብ ላይ ይገኛል። የዚህ ሰው ኩባንያዎች ከሌሎች የሚለያቸው የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት የጀመሩት ቀድመው መሆኑ ነው። ለምሳሌ የኮቪድ-19 ክትባት አሁን ማምረት የጀመሩ ፋብሪካዎች ክትባቱ ታሽጎ እስኪወጣ ወራት ሊፈጅባቸው ይችላል። ፑናዋላ መጀመሪያ የምሰጠው ለሕንድ ነው ይላል። ቀጥሎ ደግሞ ለአፍሪካ። ይህ የሚሆነው በኮቫክስ አማካይነት ነው። ኮቫክስ በዓለም ጤና ድርጅት አማካይነት የተቋቋመ ፕሮግራም ሲሆን ለዓለማችን አገራት ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ክትባት ለማቅረብ ያልማል። ክትባት የመግዛት አቅም የሌላቸው አገራት ደግሞ በነፃ እንዲያገኙ ይመቻችላቸዋል። የኮቫክስ ፕሮግራም በሚቀጥለው ወር ለአገራት ክትባት ማድረስ ለመጀመር አቅዷል። ነገር ግን የመግዛት አቅም የሌላቸው አገራት በጎን በኩል ከኃያላኑ ጋር ውል ለመፈፀም ደፋ ቀና ማለታቸው የዚህን ፕሮግራም ተፈፃሚነት አጠራጣሪ አድርጎታል። ፑናዋላ እንደሚለው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እርሱን በአንድ በሌላም መንገድ አግኝተውት ክትባት እንዲሰጣቸው ጠይቀውታል። ባለፈው ሳምንት ዩጋንዳ ከሴረም ኩባንያ 18 ሚሊዮን ክትባት በ7 ዶላር ሒሳብ ማግኘቷን አሳውቃለች። 4 ዶላር የሚችለው ኮቫክስ ነው። ሴረም የተሰኘው ተቋም ከዩጋንዳ ጋር ንግግር ላይ እንደሆነ ቢያሳውቅም ስምምነት ላይ ግን አልደረስንም ብሏል። የፑናዋላ ተቋም ከዓለም ጤና ድርጅት ፈቃድ ካገኘ 200 ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶችን ለኮቫክስ ፕሮግራም ለማቅረብ ዝግጁ ነው። ሃብታሙ ሕንዳዊ ለኮቫክስ ፕሮግራም 900 ሚሊዮን ተጨማሪ ክትባቶች ለማቅረብ ቃል ገብቷል። ጥናቱን የሠራው ተቋም አንዳንድ አገራት በፈረንጆቹ 2023 እንኳ ሙሉ በመሉ ክትባት ላያገኙ ይችላሉ ሲል ይተነብያል። በተለይ ደግሞ በርካታው የሕዝብ ክፍል ወጣት የሆነባቸውና የቫይረሱ ተፅዕኖ ጎልቶ ያልወጣባቸው አገራት ክትባቱ በጊዜ ላይደርሳቸው ይችላል ይላል ግምቱ። እርግጥ ነው ክትባቶች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መጠን እየተመረቱ ነው። ነገር ግን እኛስ መች ይደርሰናል? የሚል ጥያቄ ምላሽ በብዙ ኹነቶች ላይ የተመሠረተ ነው። | ኮሮናቫይረስ፡ የኮቪድ-19 ክትባትን ለማቅረብ የሃብታምና ድሃ አገራት ፍጥጫ ስለ ኮቪድ-19 ክትባት ስናወራ አንድ ጥያቄ ብዙዎቻችንን ሰቅዞ መያዙ አያጠራጥርም - መቼ ይሆን እኔ የምከተበው? የሚለው። ጥቂት አገራት የኮቪድ-19 ክትባት ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የማሕበረሰብ ክፍሎች ብለው ለይተዋል። የዓለማችንን ሰዎች ፀረ-ኮሮናቫይረስ መከተብ የሞትና የሕይወት ጉዳይ ነው። ነገር ግን እንዲህ ቀላል አይደለም። ጉዳዩ በርካታ ግዙፍና ዓለም አቀፍ ኩባንያዎች የሚሳተፉበት፣ መንግሥታት የማይፈፅሙትን ቃል የሚገቡበት፣ በቢሮክራሲ የታጠረና ቁጥጥር የበረታበት ነው። ኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት የተሰኘው ተቋም ባልደረባ የሆኑት አጋተ ዳማራይስ በዚህ ጉዳይ ላይ ሰፋ ያለ ጥናት ሠርተዋል። ተቋሙ ዓለማችን ምን ያክል ክትባት ማምረት እንደምትችልና ያለው የጤና መሠረተ ልማት ምን ያህል በቂ ነው? የሚለውን አጥንቷል። የጥናቱ ውጤት እንደሚያሳየው ፍጥጫው የሃብታምና የድሃ ነው። ዩናይትድ ኪንግደምና ዩናይትድ ስቴትስ በአሁኑ ወቅት በቂ የሆነ የክትባት አቅርቦት አላቸው። ምክንያቱም ክትባቱን መግዛት የሚያስችል ገንዘብ አላቸውና። ሌሎች እንደ ካናዳና የአውሮፓ ሕብረት አባላት ያሉ አገራት የመግዛት አቅሙ ቢኖራቸውም ክትባት ላይ ብዙ እየተሯሯጡ ያሉ አይመስሉም። ካናዳ ሕዝቧ ከሚያስፈልገው የክትባት መጠን አምስት እጥፍ ከፍ ያለ ክትባት ብታዝም ክትባቱ በታሰበው ጊዜ የደረሰላት አይመስልም። ካናዳ ክትባቱ በፈለገችው ሰዓት ያልደረሰላት ምናልባት የዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የውጭ ገበያን እንዳይከለክል በመፍራት ፊቱን ወደ አውሮፓውያን ክትባት አምራቾች በማዞሯ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ወቅት አሜሪካ ሳትሆን የአውሮፓ ሕብረት ነው ክትባት ወደ ውጭ መላክ የለበትም የሚል አቋም እያንፀባረቀ ያለው። አብዛኛዎቹ ገቢያቸው አነስተኛ የሆኑ አገራት ገና ዜጎቻቸውን መከተብ አልጀመሩም። ነገር ግን በተለይ መሃል ላይ አንዳንድ ሃገራት አስደናቂ ውጤት እያስመዘገቡ ነው። ለምሳሌ ሰርቢያ በአሁኑ ወቅት ከሕዝቧ በመቶኛ ሲቆጠር በርካታ ሰው በማስከተብ ከዓለም ስምንተኛ ናት። እርግጥ ሰርቢያ ከቻይናና ሩስያ ብዙ ተጠቅማለች። ሁለቱ ሃያላን አገራት በምስራቅ አውሮፓ ያላቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ሰርቢያን ወዳጅ አድርገው ይዘዋል። የሩስያ ስፓትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትና የቻይናው ሲኖፋርም ሰርቢያ ውስጥ እንደልብ ይገኛሉ። ምንም እንኳ ሰርቢያዊያን የክትባት ቅፅ ሲሞሉ ከፋይዘር፣ ስፓትኒክ አሊያም ሲኖፋርም ምረጡ ቢባሉም በርካቶች ሲኖፋርም ነው የሚሰጣቸው። ዩናይትድ አራብ ኤሜሬትስም ሲኖፋርም በተሰኘው የቻይና ክትባት ላይ ጥገኛ ናት። አገሪቱ ለዜጎቿ እየሰጠችው ካለው ክትባት 80 በመቶው ሲኖፋርም ነው። አልፎም በአገሯ የሲኖፋርም ማምረቻ ፋብሪካ እየገነባች ትገኛለች። አንድ አገር የዓለማችን ከፍተኛ የክትባት አምራች ሆነች ማለት ዜጎቿን በሙሉ ቀድማ ትከትባለች ማለት አይደለም። አይኢዩ የተሰኘው ተቋም ሠራሁት ባለው ጥናት መሠረት የዓለማችን ከፍተኛ ክትባት አምራች የሚባሉት ቻይናና ሕንድ እስከ ፈረንጆቹ 2022 ድረስ ዜጎቻቸውን በበቂ ሁኔታ ላይከትቡ ይችላሉ። ለዚህ ደግሞ ዋነኛው ምክንያት አገራቱ ያላቸው የሕዝብ ብዛትና የጤና ሠራተኞች ቁጥጥር አለመመጣጠኑ ነው። ሕንድ የዓለማችን ከፍተኛው የክትባት አምራች ኩባንያ የሆነችው በአንድ ሰው ምክንያት ነው። አንዳር ፑንዋላ። የዚህ ሰው ኩባንያ የሆነው ሴረም በዓለማችን ከፍተኛው የክትባት አምራች ድርጅት ነው። ነገር ግን ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት አጋማሽ ቤተሰቦቹ ሰውዬው አብዷል እስኪሉ ድረስ በመቶ ሚሊዮን ዶላሮች እየመዠረጠ ለክትባት ምርምር ያውል ነበር። ቢሆንም ቁማሩ ተሳክቶለት ክትባቶቹ ውጤታማ መሆን ችለዋል። አሁን የዚህ ሃብታም ኩባንያ በቀን 2.4 ሚሊዮን ክትባቶች ያመርታል። የፑንዋላ ኩባንያ ለሕንድ፣ ብራዚል፣ ሞሮኮ፣ ባንግላዴሽ እና ደቡብ አፍሪካ ክትባት በዋናነት በማቅረብ ላይ ይገኛል። የዚህ ሰው ኩባንያዎች ከሌሎች የሚለያቸው የኮቪድ-19 ክትባት ማምረት የጀመሩት ቀድመው መሆኑ ነው። ለምሳሌ የኮቪድ-19 ክትባት አሁን ማምረት የጀመሩ ፋብሪካዎች ክትባቱ ታሽጎ እስኪወጣ ወራት ሊፈጅባቸው ይችላል። ፑናዋላ መጀመሪያ የምሰጠው ለሕንድ ነው ይላል። ቀጥሎ ደግሞ ለአፍሪካ። ይህ የሚሆነው በኮቫክስ አማካይነት ነው። ኮቫክስ በዓለም ጤና ድርጅት አማካይነት የተቋቋመ ፕሮግራም ሲሆን ለዓለማችን አገራት ዋጋው ተመጣጣኝ የሆነ ክትባት ለማቅረብ ያልማል። ክትባት የመግዛት አቅም የሌላቸው አገራት ደግሞ በነፃ እንዲያገኙ ይመቻችላቸዋል። የኮቫክስ ፕሮግራም በሚቀጥለው ወር ለአገራት ክትባት ማድረስ ለመጀመር አቅዷል። ነገር ግን የመግዛት አቅም የሌላቸው አገራት በጎን በኩል ከኃያላኑ ጋር ውል ለመፈፀም ደፋ ቀና ማለታቸው የዚህን ፕሮግራም ተፈፃሚነት አጠራጣሪ አድርጎታል። ፑናዋላ እንደሚለው አብዛኛዎቹ የአፍሪካ አገራት መሪዎች እርሱን በአንድ በሌላም መንገድ አግኝተውት ክትባት እንዲሰጣቸው ጠይቀውታል። ባለፈው ሳምንት ዩጋንዳ ከሴረም ኩባንያ 18 ሚሊዮን ክትባት በ7 ዶላር ሒሳብ ማግኘቷን አሳውቃለች። 4 ዶላር የሚችለው ኮቫክስ ነው። ሴረም የተሰኘው ተቋም ከዩጋንዳ ጋር ንግግር ላይ እንደሆነ ቢያሳውቅም ስምምነት ላይ ግን አልደረስንም ብሏል። የፑናዋላ ተቋም ከዓለም ጤና ድርጅት ፈቃድ ካገኘ 200 ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶችን ለኮቫክስ ፕሮግራም ለማቅረብ ዝግጁ ነው። ሃብታሙ ሕንዳዊ ለኮቫክስ ፕሮግራም 900 ሚሊዮን ተጨማሪ ክትባቶች ለማቅረብ ቃል ገብቷል። ጥናቱን የሠራው ተቋም አንዳንድ አገራት በፈረንጆቹ 2023 እንኳ ሙሉ በመሉ ክትባት ላያገኙ ይችላሉ ሲል ይተነብያል። በተለይ ደግሞ በርካታው የሕዝብ ክፍል ወጣት የሆነባቸውና የቫይረሱ ተፅዕኖ ጎልቶ ያልወጣባቸው አገራት ክትባቱ በጊዜ ላይደርሳቸው ይችላል ይላል ግምቱ። እርግጥ ነው ክትባቶች ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ መጠን እየተመረቱ ነው። ነገር ግን እኛስ መች ይደርሰናል? የሚል ጥያቄ ምላሽ በብዙ ኹነቶች ላይ የተመሠረተ ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-56096274 |
3politics
| ባይደን ከኢራን ጋር ለመነጋገር ብለው ማዕቀብ እንደማያነሱ ገለጹ | የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ኢራን እአአ በ2015 የተፈረመውን የኒውክሌር ስምምነት ካልተገበረች ማዕቀብ እንደማያነሱላት ተናገሩ። አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ከኢራን ጋር ለመነጋገር ስትል እንደማታነሳ ከሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። የኢራኑ መሪ አያቶላ አሊ ካምኒ በበኩላቸው ኢራን ስምምነቱን የምታከብረው አሜሪካ ማዕቀቡን ስታነሳላት ነው ብለዋል። 2015 ላይ የኢራንን የኒውክሌር ምርት የሚገድብ ስምምነት ተፈርሞ ነበር። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን በ2018 ከስምምነቱ አስወጥተዋል። ስምምነቱ ሲፈረም ላልተው የነበሩ ማዕቀቦችን ትራምፕ በድጋሚ አጥብቀውም ነበር። ኢራን ማዕቀቦቹ እንደ አዲስ መጣላቸውን ተከትሎ ከስምምቱ ውጪ የሆኑ ድርጊቶች መፈጸም ጀምራለች። ኒውክሌርን ለሰላማዊ ተግባር ነው የማውለው የምትለው ኢራን የተጣራ ዩናንየም ምርቷን እያሳደገች ነው። የተጣራ ዩናንየም የኒውክሌር ቦምብ ለመሥራት ይውላል። ስምምነቱ ለምን ፈረሰ? ኢራን፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሩስያ እና ዩናይትድ ኪንግደም በ2015 የኒውክሌር ስምምነት ፈርመው ነበር። በስምምነቱ መሠረት ቴህራን የምታበለጽገውን ዩራንየም እንደምትቀንስና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የምርት ሂደቱን እንዲከታተሉ እንደምትፈቅድ ተገልጿል። ኢራን እነዚህን እርምጃዎች ከወሰደች በምላሹ ማዕቀቦች እንደሚነሱላት ቃል ተገብቶም ነበር። ሆኖም ግን ትራምፕ አሜሪካን ከስምምነቱ አስወጥተው ኢራን አዲስ ስምምነት እንድትፈርም ጫና ለማሳደር ሞክረዋል። ኢራን በአዲሱ የትራምፕ እቅድ አልስማማም ብላ ዩራንየምን በ20% ጥራት ወደ ማምረት እንደምትመለስ አስታውቃለች። የጦር መሣሪያ መሥራት የሚቻለው 90% የምርት ጥራት ላይ ሲደረስ ነው። ባይደን ኢራንን ወደቀደመው ስምምነት ለመመለስ ሲሉ ምጣኔ ሀብታዊ ማዕቀቦችን ያነሱ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ "በፍጹም ማዕቀብ አላነሳም" ብለው ምላሽ ሰጥተዋል። ኢራን ግን ወደቀደመው ስምምነት ለመመለስ ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ የማዕቀቦችን መነሳት ያካትታል። የኢራኑ መሪ በብሔራዊ ቴሌቭዥን "ሁሉንም ማዕቀቦች ያንሱ። ከዚያ ወደ ስምምነቱ እንደመለሳለን" ሲሉ ተደምጠዋል። | ባይደን ከኢራን ጋር ለመነጋገር ብለው ማዕቀብ እንደማያነሱ ገለጹ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን ኢራን እአአ በ2015 የተፈረመውን የኒውክሌር ስምምነት ካልተገበረች ማዕቀብ እንደማያነሱላት ተናገሩ። አሜሪካ ኢራን ላይ የጣለቻቸውን ማዕቀቦች ከኢራን ጋር ለመነጋገር ስትል እንደማታነሳ ከሲቢኤስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። የኢራኑ መሪ አያቶላ አሊ ካምኒ በበኩላቸው ኢራን ስምምነቱን የምታከብረው አሜሪካ ማዕቀቡን ስታነሳላት ነው ብለዋል። 2015 ላይ የኢራንን የኒውክሌር ምርት የሚገድብ ስምምነት ተፈርሞ ነበር። የቀድሞው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካንን በ2018 ከስምምነቱ አስወጥተዋል። ስምምነቱ ሲፈረም ላልተው የነበሩ ማዕቀቦችን ትራምፕ በድጋሚ አጥብቀውም ነበር። ኢራን ማዕቀቦቹ እንደ አዲስ መጣላቸውን ተከትሎ ከስምምቱ ውጪ የሆኑ ድርጊቶች መፈጸም ጀምራለች። ኒውክሌርን ለሰላማዊ ተግባር ነው የማውለው የምትለው ኢራን የተጣራ ዩናንየም ምርቷን እያሳደገች ነው። የተጣራ ዩናንየም የኒውክሌር ቦምብ ለመሥራት ይውላል። ስምምነቱ ለምን ፈረሰ? ኢራን፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ሩስያ እና ዩናይትድ ኪንግደም በ2015 የኒውክሌር ስምምነት ፈርመው ነበር። በስምምነቱ መሠረት ቴህራን የምታበለጽገውን ዩራንየም እንደምትቀንስና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የምርት ሂደቱን እንዲከታተሉ እንደምትፈቅድ ተገልጿል። ኢራን እነዚህን እርምጃዎች ከወሰደች በምላሹ ማዕቀቦች እንደሚነሱላት ቃል ተገብቶም ነበር። ሆኖም ግን ትራምፕ አሜሪካን ከስምምነቱ አስወጥተው ኢራን አዲስ ስምምነት እንድትፈርም ጫና ለማሳደር ሞክረዋል። ኢራን በአዲሱ የትራምፕ እቅድ አልስማማም ብላ ዩራንየምን በ20% ጥራት ወደ ማምረት እንደምትመለስ አስታውቃለች። የጦር መሣሪያ መሥራት የሚቻለው 90% የምርት ጥራት ላይ ሲደረስ ነው። ባይደን ኢራንን ወደቀደመው ስምምነት ለመመለስ ሲሉ ምጣኔ ሀብታዊ ማዕቀቦችን ያነሱ እንደሆነ ለቀረበላቸው ጥያቄ "በፍጹም ማዕቀብ አላነሳም" ብለው ምላሽ ሰጥተዋል። ኢራን ግን ወደቀደመው ስምምነት ለመመለስ ያስቀመጠችው ቅድመ ሁኔታ የማዕቀቦችን መነሳት ያካትታል። የኢራኑ መሪ በብሔራዊ ቴሌቭዥን "ሁሉንም ማዕቀቦች ያንሱ። ከዚያ ወደ ስምምነቱ እንደመለሳለን" ሲሉ ተደምጠዋል። | https://www.bbc.com/amharic/55976536 |
0business
| ኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት ከሚያሳዩ አገራት መካከል ተካተተች | የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጪው 30 ዓመታት የዓለምን ግማሽ የሕዝብ ቁጥር ይይዛሉ ያላቸውን ስምንት አገራት ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ እና ታንዛኒያ ከአፍሪካ አገራት በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል። እንዲሁም በሚቀጥለው ዓመት ቻይናን በመብለጥ በዓለም ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት አገር የምትሆነው ሕንድ እንዲሁም ፓኪስታን ከስምንቱ አገራት መካከል ናቸው። ሕንድ 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ በመያዝ ነው በሕዝብ ብዛቷ ለዓመታት የዓለም ቁንጮ ሆና የቆየችውን ቻይናን የምትበልጠው። በቀጣይ ዓመት ኅዳር ወር ውስጥም የዓለም ሕዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን የሚደርስ ቢሆንም፣ የዓለም የሕዝብ ቁጥር እድገት ቁጥር እስከ ዛሬ ከነበረው የእድገት መጠን ያነሰ እንደሆነም የመንግሥታቱ ድርጅት ይፋ አድርጓል። በስልሳ ዓመታት ውስጥም ዝቅተኛ የተባለው የሕዝብ ቁጥር እድገት መመዝገቡን ይፋ ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት፣ ከ40 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ከፍተኛ እድገት ላይ ሊደርስ እንደሚችል እና ቁጥሩም 10.4 ቢሊዮን እንደሚደርስ ትንበያው ያሳያል። እ.ኤ.አ. በ2050፣ 61 አገራት የሕዝብ ቁጥራቸው ቢያንስ በአንድ በመቶ መቀነስ ያሳያል ተብሎ ይገመታል። በአሁኑ ወቅትም በተወሰኑ ታዳጊ አገራት ውስጥ እድገቱ በአንድ ሴት 2.1 በመቶ አካባቢ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ ምጣኔ ያለውን የሕብ ብዛት ቁጥር የመተካት እንጂ እድገት እንዳልሆነ ተመድ አስታውቋል። ቻይና 1.15 ልጅ በአንድ ሴት በማስመዝገብ በዓለም ዝቅተኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት ካስመዘገቡ አገራት መካከል ስትሆን፣ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ደግሞ የሕዝብ ቁጥሯ መቀነስ እንደሚጀምር አስታውቃለች። ቻይና ጥንዶች ከአንድ ልጅ በላይ መውለድ እንዳይችሉ የሚከለክለውን ሕጓን በማንሳት ብሎም ሁለት እና ከዚያ በላይ ለሚወልዱ ዜጎቿ ማበረታቻዎችን መስጠት ብትጀምርም እድገቱን ከመቀነስ አላስቆመውም። ምንም እንኳን አንድ ሴት የምትወልደው ልጅ ቁጥር ቢቀንስም የሕዝብ ቁጥር እድገት በተለይም ከሕክምና ሳይንስ መሻሻል ጋር ተያይዞ የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር በመቀነስ፣ እንዲያድጉ በማስቻሉ ምክንያት እድገቱ ቀጥሏል። | ኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት ከሚያሳዩ አገራት መካከል ተካተተች የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በመጪው 30 ዓመታት የዓለምን ግማሽ የሕዝብ ቁጥር ይይዛሉ ያላቸውን ስምንት አገራት ይፋ ያደረገ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ግብፅ፣ ኮንጎ፣ ናይጄሪያ እና ታንዛኒያ ከአፍሪካ አገራት በዝርዝሩ ውስጥ ተካተዋል። እንዲሁም በሚቀጥለው ዓመት ቻይናን በመብለጥ በዓለም ብዙ ሕዝብ የሚኖርባት አገር የምትሆነው ሕንድ እንዲሁም ፓኪስታን ከስምንቱ አገራት መካከል ናቸው። ሕንድ 1.4 ቢሊዮን ሕዝብ በመያዝ ነው በሕዝብ ብዛቷ ለዓመታት የዓለም ቁንጮ ሆና የቆየችውን ቻይናን የምትበልጠው። በቀጣይ ዓመት ኅዳር ወር ውስጥም የዓለም ሕዝብ ቁጥር 8 ቢሊዮን የሚደርስ ቢሆንም፣ የዓለም የሕዝብ ቁጥር እድገት ቁጥር እስከ ዛሬ ከነበረው የእድገት መጠን ያነሰ እንደሆነም የመንግሥታቱ ድርጅት ይፋ አድርጓል። በስልሳ ዓመታት ውስጥም ዝቅተኛ የተባለው የሕዝብ ቁጥር እድገት መመዝገቡን ይፋ ያደረገው የተባበሩት መንግሥታት፣ ከ40 ዓመታት በኋላ በድጋሚ ከፍተኛ እድገት ላይ ሊደርስ እንደሚችል እና ቁጥሩም 10.4 ቢሊዮን እንደሚደርስ ትንበያው ያሳያል። እ.ኤ.አ. በ2050፣ 61 አገራት የሕዝብ ቁጥራቸው ቢያንስ በአንድ በመቶ መቀነስ ያሳያል ተብሎ ይገመታል። በአሁኑ ወቅትም በተወሰኑ ታዳጊ አገራት ውስጥ እድገቱ በአንድ ሴት 2.1 በመቶ አካባቢ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህ ምጣኔ ያለውን የሕብ ብዛት ቁጥር የመተካት እንጂ እድገት እንዳልሆነ ተመድ አስታውቋል። ቻይና 1.15 ልጅ በአንድ ሴት በማስመዝገብ በዓለም ዝቅተኛ የሕዝብ ቁጥር እድገት ካስመዘገቡ አገራት መካከል ስትሆን፣ ከመጪው ዓመት ጀምሮ ደግሞ የሕዝብ ቁጥሯ መቀነስ እንደሚጀምር አስታውቃለች። ቻይና ጥንዶች ከአንድ ልጅ በላይ መውለድ እንዳይችሉ የሚከለክለውን ሕጓን በማንሳት ብሎም ሁለት እና ከዚያ በላይ ለሚወልዱ ዜጎቿ ማበረታቻዎችን መስጠት ብትጀምርም እድገቱን ከመቀነስ አላስቆመውም። ምንም እንኳን አንድ ሴት የምትወልደው ልጅ ቁጥር ቢቀንስም የሕዝብ ቁጥር እድገት በተለይም ከሕክምና ሳይንስ መሻሻል ጋር ተያይዞ የሚሞቱ ሕጻናት ቁጥር በመቀነስ፣ እንዲያድጉ በማስቻሉ ምክንያት እድገቱ ቀጥሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/ce4l8rdzp0no |
0business
| አንድ ኪሎ ቡና ከ47 ሺህ ብር በላይ የሸጠው ኢትዮጵያዊ | ለገሠ በጦሳ 2014 ዕድል ፊቷን ካዞረችላቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ ሆኗል። ነዋሪነቱ አዲስ በተቋቋመው ሲዳማ ክልል ነው። ሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ ቡርሳ ቀበሌ። ቡርሳ ከክልሉ ዋና መዲና ሐዋሳ 80 ኪሎ ሜትር ያህል ትርቃለች። እድገቱና ውልደቱም በዚያ ነው። በሠላሳዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው ለገሠ የሚተዳደረው በግብርና ነው። “ከቀድሞ ጀምሮ በግብርና ነው የምተዳደረው” የሚለው ለገሠ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ እና የመሳሰሉትን እያመረትኩ ነበር የምንኖረው” ሲል ያክላል። እንሰት ከጓሮው እና እንስሳት ከደጁ አይጠፉም። የእሱ፣ የባለቤቱ እና የአራት ልጆቻቸው መተዳደሪያም ይህ ነው። በቅርቡ ግን ፊቱን ወደ ሌላ ዘርፍ አዞረ፤ ቡና ወደ ማብቀሉ። ቡና አዲሱ መተዳደሪያው ከሆነ አምስት ዓመት ሆነው። በፊት ለምን ቡና አታመርቱም ነበር ሲባል “ቀዬው ቡና እንደሚያመርት አናውቅም ነበር” ይላል። እውነትም አካባቢው ለቡና ምቹ መሆኑን ሳያውቁ ቆይተዋል። አሁንም በአካባቢው ቡና በስፋት እየተመረተ አይደለም። ጥቂቶች ናቸው ቡና የሚያመርቱት። ለገሠ ፊቱን ወደ ቡና ሲያዞርም ከሌላው ይልቅ ቡና ውጤታማ ሆነለት። “ከሌላው እርሻ የቡናው በገቢ የተሻለ ነው” ሲል ለገሠ ይገልጻል። ግማሽ ሔክታር መሬት ላይ ከአንድ ሺህ ኪሎ በላይ ቡና በየዓመቱ ይሰበስባል። የሚያመርተውን ቡና በአካባቢው ለሚገኙ ቡና ነጋዴዎች ይሸጣል። በዓመት ‘ከ70 እስከ 100 ሺህ ብር’ ያገኝ ነበር። በዚህ መካከል ደግሞ ቡና ለዓለም አቀፍ ገበያ በውድድር እንደሚቀርብ ይሰማል። ሌሎች ከእነሱ አካባቢ ያመረቱትን እና የገዙትን ቡና 'ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ' አቅርበው በዓለም አቀፍ ገበያ እንደሚሸጥ ሰምቷል። ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ የቡና የጥራት ውድድር ነው። ባለፉት 20 ዓመታት የጥራት ውድድር በዋና ዋና የቡና አብቃይ አገራት ውስጥ ይካሄድ ነበር። በኢትዮጵያ ውድድሩ የተጀመረው ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ዓላማው ከቡናዎች መካከል የተሻለውን መርጦ በዓለም አቀፍ ጨረታ ለታላላቅ ገዢዎች መሸጥ ነው። በተጨማሪም ገበሬዎችን እንዲሁም ልዩ ጣዕም ያላቸውን ቡናዎች እና አምራቾችን ማስተዋወቅም ሌላኛው ዓላማው ነው። በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ሻጮች ቡናቸው በከፍተኛ ዋጋ ይቸበቸባል። ለገሠ ይህንን ሰምቶ ‘እኔስ ለምን በግሌ አልወዳደርም?’ አለ። በአካባቢያቸው ለሚገኙ ነጋዴዎች ቡናውን ማስረከብ አቆመ። “የማውቃቸው ሰዎች ከዚህ ቀደም [በውድድሩ] ቡናቸው እየሸጡ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሲወጡ ተመልክቻለሁ” ይላል። ለገሠ ለውድድሩ አንድ ሺህ ኪሎ ያህል አቀረበ። ውድድሩ አዘጋጅ ከቀረበለት ቡና የተሻለውን መምረጥ እና ቀንሶ ለውድድሩ የማቅረብ መብት አለው። ከዚህ ውስጥ ተጣርቶ 480 ኪሎ ያህሉ ለውድድሩ ፍጻሜ ቀረበ። ውድድሩ ላይ እስከ 40 ባለው ደረጃ ውስጥ ብገባ ሲል ለገሠ ተመኘ። ውጤቱ ሲመጣ ግን ከተመኘውም በላይ ሆነ። ቡናው አንደኛ ወጣ። የአምስት ዓመት ልፋቱ ፍሬ አፈራ። ያውም ጥሩ ፍሬ። የለገሠ አንድ ኪሎ ቡና በውድድሩ ከፍተኛ በሚባል 884.10 ዶላር ተሸጠ። 47 ሺህ 236 ብር ገደማ ማለት ነው። አንድ ኪሎ ቡና 47 ሺህ 236 ብር። ይህም በኢትዮጵያ የቡና ታሪክ በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠ ሆኖ ተመዘገበ። ያቀረበው ቡና አጠቃላይ ዋጋ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አስገኘለት። ውጤቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ ነበር የሰማው። “መረጃውን በወንድሜ በኩል ነው የሰማሁት። በጣም ነው ደስ ያለኝ” ብሏል ዜናውን የሰማበትን አጋጣሚ ሲገልጽ። “ቡናው አንደኛ ይወጣል ብዬ አልጠበቅኩም። ግን ተመረጠ። ሌሎች ሲወዳደሩ እና ሲያሸንፉ አይቼ ቡናውን አጥቤ በሚፈለገው መንገድ ለውድድሩ አቀረብኩ። እስከ 40 ባለው ደረጃ ውስጥ ቢገባ ብዬ ነበር ያሰብኩት” ብሏል። ለመሆኑ ይህ ቡና ምን ቢሆን ነው እንደዚህ ውድ በሆነ ዋጋ የተሸጠው? አካባቢው ደጋማ ነው። ቡና ማምረት ያልተለመደበት አካባቢ። “የቡናው ጥራቱ ለመሬቱ አዲስ በመሆኑ ይመስለናል። መሬቱ ኦርጋኒክ [ተፈጥሯዊ] ሲሆን ከቡና ጋር በተያያዘ ብዙም አልተጠቀምንበትም። ለብዙ ዓመታት ቢታረስም ቡና ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው የተተከለበት። ስለዚህ ቦታው ኦርጋኒክ ስለሆነ ቡና የሚፈልገውን ነገር ከመሬቱ ያገኘ ይመስለኛል” ሲል ይመልሳል። ከዚህ ውጪ ይህ ነው ብሎ የሚያቀርበው ሌላ ምክንያትም አለ። “አማኝ ነን” የሚለው ለገሠ “አማኝ ነን። ቡናውን ምርጥ ያደረገልኝ ፈጣሪ ነው” ይላል። “እኔ ወደ ቡና ሥራ እንደገባሁ የተሳካላቸው እንዴት እንደሚሠሩ እከታተል ነበር። እኔም ቡናውን አድርቄ ነው የሸጥኩት። 40 ውስጥም እገባለሁ ብዬ አላሳብኩም። እግዚአብሔር ረዳኝ።” ለገሠ ቡናውን ከመትከል ጀምሮ እስከ መንከባከብ ድረስ ይሳተፋል። “(አንዳንዴ) ሠራተኛ ቀጥሬ አሠራለሁ። እኔም እየገባሁ እሠራለሁ። ሙሽራው ቡና ሲመጣ ስሩ ማዕድን ይዞ ስለሚመጣ እንዳይነካ እያደረኩ እየኮተኮትኩ እንከባከበዋለሁ። ከማሳዬ አልጠፋም።” ለገሠ አሁን ሚሊየነር ሆኗል። ብሩ እስካሁን እጁ ባይገባም፤ ከአሁኑ ግን ዕቅድ ተጀምሯል። “ቡና ውስጥ ያልገመትኩት ነው የገጠመኝ። ሐዋሳ ከተማ ቤት ገዝቼ ለመግባት አስባለሁ። ሥራውን ማስፋፋትም እፈልጋለሁ። ቡና ዓለም ውስጥ በስፋት እገባለሁ” ይላል። ጎረቤት፣ ዘመድ . . . በለገሠ ውጤት ማን ያልተደሰተ አለ? በፊት ‘አቅም ያላቸው ናቸው የሚወዳደሩት’ በሚል ወደ ኋላ ያሉትንም እንዳነቃቃ ለገሠ ያስባል። “አሁን ሌሎችም ለመወዳደር ፍላጎት አላቸው” ሲል በአካባቢው የፈጠረውን መነሳሳት ይገልጻል። አልፎ አልፎ የግብርና ባለሙያዎች እየመጡ ‘እንዲህ ብታደርጉ እንዲህ ቢሆን ይህ ቢጨመር ይህ ቢቀነስ ይሏቸዋል።’ በውጤቱም ደስተኞች ሆነዋል። መሬቱ ‘ለቡና’ አዲስ ስለሆነ ‘በደንብ ሥሩ’ ሲሉ ሌሎችንም እየመከሩ ነው። አቶ ለገሠ በፊት እርጥብ ቡና ነበር ለገበያ የሚያቀርበው። አሁን አድርቆ መሸጥ ችሏል። የሚሸጠውም በአካባቢው ላሉ ነጋዴዎች ነበር። አሁን በዓለም አቀፍ መድረክ መሸጥ ችሏል። በዓመት እስከ መቶ ሺህ ብር ብቻ ያገኝ ነበር። በአሁኑ ወቅት ሚሊዮኖችን ማግኘት ችሏል። አሁን ጉዞውን ጀምሯል። ዓይኑንም በቀጣዩ ውድድር ላይ ጥሏል። “ከዚህ በሚበልጥ ሁኔታ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ተዘጋጅቼ ለውድድር እቀርባለሁ” ሲል ያጠናቅቃል። ይህ የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር ስፔሻሊቲ (ባለ ልዩ ጣዕም ቡና) ብቻ ሳይሆን ለየት ያለ ቡና ገዢዎች የሚገዙበት ነው። ቡናውም ከመሸጡ በፊት በተለያየ ደረጃ እና አገራት ተቀምሶ፣ ደረጃ ወጥሎት ነው ለሽያጭ የሚቀርበው። በውድድሩ ማሸነፍ እውቅና ይዞ ይመጣል። ለገሠ ከዚህ በኋላ በተመሳሳይ ዋጋ ባይሸጥ እንኳን ቡናው ከሌሎች አምራቾች እኩል ዋጋ አይሰጠውም። ከውድድሩ የሚገዛው ቡናም በተለየ ቡና መሸጫ በድንቅ ባለሙያ ተዘጋጅቶ በውድ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል። ሦስተኛው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ከአሊያንስ ኮፊ ኤክሰለንስ እና ዩኤስኤይድ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በዘንድሮው ውድድር የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ከፍተኛ በሚባል ዋጋ ተሽጧል። የለገሠን አንድ ኪሎ ቡና በ884.10 ዶላር (47236 ብር) የገዛው የቻይናው ኤልኤንኬ ኮፊ ትሬዲንግ ነው። ቀሪው ቡና ደግሞ ሳዛ ኮፊ ለሚባል ድርጅት ተሽጧል። ዋጋው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ሽያጭ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። በዘንድሮው ውድድር ከ23 አገራት የተወጣጡ 170 ገዢዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ከውድድሩ በኋላ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ “አርሶ አደሮቻችን አገራቸውን አኩርተዋል። የዘንድሮው ውድድር በብዙ ስኬት እና አስደናቂ ክብረ ወሰን ተጠናቋል” ብለዋል። የዩኤስኤይድ ዳይሬክተር ሴን ጆንስ በበኩላቸው “በዚህ በዩኤስኤይድ ድጋፍ በሚካሄደው ውድድር በተለይም የቡናው ዘርፍ እንዲቀየር በማገዛችን ኩራት ይሰማናል። አነስተኛ ቡና አምራቾችን ከቡና ገዢዎች ጋር በማገናኘት አምራቾች ገቢያቸው እንዲያድግ ማድረግ ችለናል” ብለዋል። | አንድ ኪሎ ቡና ከ47 ሺህ ብር በላይ የሸጠው ኢትዮጵያዊ ለገሠ በጦሳ 2014 ዕድል ፊቷን ካዞረችላቸው ኢትዮጵያውያን አንዱ ሆኗል። ነዋሪነቱ አዲስ በተቋቋመው ሲዳማ ክልል ነው። ሲዳማ ክልል አርቤጎና ወረዳ ቡርሳ ቀበሌ። ቡርሳ ከክልሉ ዋና መዲና ሐዋሳ 80 ኪሎ ሜትር ያህል ትርቃለች። እድገቱና ውልደቱም በዚያ ነው። በሠላሳዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኘው ለገሠ የሚተዳደረው በግብርና ነው። “ከቀድሞ ጀምሮ በግብርና ነው የምተዳደረው” የሚለው ለገሠ በቆሎ፣ ስንዴ፣ ገብስ እና የመሳሰሉትን እያመረትኩ ነበር የምንኖረው” ሲል ያክላል። እንሰት ከጓሮው እና እንስሳት ከደጁ አይጠፉም። የእሱ፣ የባለቤቱ እና የአራት ልጆቻቸው መተዳደሪያም ይህ ነው። በቅርቡ ግን ፊቱን ወደ ሌላ ዘርፍ አዞረ፤ ቡና ወደ ማብቀሉ። ቡና አዲሱ መተዳደሪያው ከሆነ አምስት ዓመት ሆነው። በፊት ለምን ቡና አታመርቱም ነበር ሲባል “ቀዬው ቡና እንደሚያመርት አናውቅም ነበር” ይላል። እውነትም አካባቢው ለቡና ምቹ መሆኑን ሳያውቁ ቆይተዋል። አሁንም በአካባቢው ቡና በስፋት እየተመረተ አይደለም። ጥቂቶች ናቸው ቡና የሚያመርቱት። ለገሠ ፊቱን ወደ ቡና ሲያዞርም ከሌላው ይልቅ ቡና ውጤታማ ሆነለት። “ከሌላው እርሻ የቡናው በገቢ የተሻለ ነው” ሲል ለገሠ ይገልጻል። ግማሽ ሔክታር መሬት ላይ ከአንድ ሺህ ኪሎ በላይ ቡና በየዓመቱ ይሰበስባል። የሚያመርተውን ቡና በአካባቢው ለሚገኙ ቡና ነጋዴዎች ይሸጣል። በዓመት ‘ከ70 እስከ 100 ሺህ ብር’ ያገኝ ነበር። በዚህ መካከል ደግሞ ቡና ለዓለም አቀፍ ገበያ በውድድር እንደሚቀርብ ይሰማል። ሌሎች ከእነሱ አካባቢ ያመረቱትን እና የገዙትን ቡና 'ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ' አቅርበው በዓለም አቀፍ ገበያ እንደሚሸጥ ሰምቷል። ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ የቡና የጥራት ውድድር ነው። ባለፉት 20 ዓመታት የጥራት ውድድር በዋና ዋና የቡና አብቃይ አገራት ውስጥ ይካሄድ ነበር። በኢትዮጵያ ውድድሩ የተጀመረው ከሁለት ዓመት በፊት ነው። ዓላማው ከቡናዎች መካከል የተሻለውን መርጦ በዓለም አቀፍ ጨረታ ለታላላቅ ገዢዎች መሸጥ ነው። በተጨማሪም ገበሬዎችን እንዲሁም ልዩ ጣዕም ያላቸውን ቡናዎች እና አምራቾችን ማስተዋወቅም ሌላኛው ዓላማው ነው። በዚህ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ሻጮች ቡናቸው በከፍተኛ ዋጋ ይቸበቸባል። ለገሠ ይህንን ሰምቶ ‘እኔስ ለምን በግሌ አልወዳደርም?’ አለ። በአካባቢያቸው ለሚገኙ ነጋዴዎች ቡናውን ማስረከብ አቆመ። “የማውቃቸው ሰዎች ከዚህ ቀደም [በውድድሩ] ቡናቸው እየሸጡ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ሲወጡ ተመልክቻለሁ” ይላል። ለገሠ ለውድድሩ አንድ ሺህ ኪሎ ያህል አቀረበ። ውድድሩ አዘጋጅ ከቀረበለት ቡና የተሻለውን መምረጥ እና ቀንሶ ለውድድሩ የማቅረብ መብት አለው። ከዚህ ውስጥ ተጣርቶ 480 ኪሎ ያህሉ ለውድድሩ ፍጻሜ ቀረበ። ውድድሩ ላይ እስከ 40 ባለው ደረጃ ውስጥ ብገባ ሲል ለገሠ ተመኘ። ውጤቱ ሲመጣ ግን ከተመኘውም በላይ ሆነ። ቡናው አንደኛ ወጣ። የአምስት ዓመት ልፋቱ ፍሬ አፈራ። ያውም ጥሩ ፍሬ። የለገሠ አንድ ኪሎ ቡና በውድድሩ ከፍተኛ በሚባል 884.10 ዶላር ተሸጠ። 47 ሺህ 236 ብር ገደማ ማለት ነው። አንድ ኪሎ ቡና 47 ሺህ 236 ብር። ይህም በኢትዮጵያ የቡና ታሪክ በከፍተኛ ዋጋ የተሸጠ ሆኖ ተመዘገበ። ያቀረበው ቡና አጠቃላይ ዋጋ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ አስገኘለት። ውጤቱን ከሁለት ሳምንት በፊት ገደማ ነበር የሰማው። “መረጃውን በወንድሜ በኩል ነው የሰማሁት። በጣም ነው ደስ ያለኝ” ብሏል ዜናውን የሰማበትን አጋጣሚ ሲገልጽ። “ቡናው አንደኛ ይወጣል ብዬ አልጠበቅኩም። ግን ተመረጠ። ሌሎች ሲወዳደሩ እና ሲያሸንፉ አይቼ ቡናውን አጥቤ በሚፈለገው መንገድ ለውድድሩ አቀረብኩ። እስከ 40 ባለው ደረጃ ውስጥ ቢገባ ብዬ ነበር ያሰብኩት” ብሏል። ለመሆኑ ይህ ቡና ምን ቢሆን ነው እንደዚህ ውድ በሆነ ዋጋ የተሸጠው? አካባቢው ደጋማ ነው። ቡና ማምረት ያልተለመደበት አካባቢ። “የቡናው ጥራቱ ለመሬቱ አዲስ በመሆኑ ይመስለናል። መሬቱ ኦርጋኒክ [ተፈጥሯዊ] ሲሆን ከቡና ጋር በተያያዘ ብዙም አልተጠቀምንበትም። ለብዙ ዓመታት ቢታረስም ቡና ግን ባለፉት ጥቂት ዓመታት ነው የተተከለበት። ስለዚህ ቦታው ኦርጋኒክ ስለሆነ ቡና የሚፈልገውን ነገር ከመሬቱ ያገኘ ይመስለኛል” ሲል ይመልሳል። ከዚህ ውጪ ይህ ነው ብሎ የሚያቀርበው ሌላ ምክንያትም አለ። “አማኝ ነን” የሚለው ለገሠ “አማኝ ነን። ቡናውን ምርጥ ያደረገልኝ ፈጣሪ ነው” ይላል። “እኔ ወደ ቡና ሥራ እንደገባሁ የተሳካላቸው እንዴት እንደሚሠሩ እከታተል ነበር። እኔም ቡናውን አድርቄ ነው የሸጥኩት። 40 ውስጥም እገባለሁ ብዬ አላሳብኩም። እግዚአብሔር ረዳኝ።” ለገሠ ቡናውን ከመትከል ጀምሮ እስከ መንከባከብ ድረስ ይሳተፋል። “(አንዳንዴ) ሠራተኛ ቀጥሬ አሠራለሁ። እኔም እየገባሁ እሠራለሁ። ሙሽራው ቡና ሲመጣ ስሩ ማዕድን ይዞ ስለሚመጣ እንዳይነካ እያደረኩ እየኮተኮትኩ እንከባከበዋለሁ። ከማሳዬ አልጠፋም።” ለገሠ አሁን ሚሊየነር ሆኗል። ብሩ እስካሁን እጁ ባይገባም፤ ከአሁኑ ግን ዕቅድ ተጀምሯል። “ቡና ውስጥ ያልገመትኩት ነው የገጠመኝ። ሐዋሳ ከተማ ቤት ገዝቼ ለመግባት አስባለሁ። ሥራውን ማስፋፋትም እፈልጋለሁ። ቡና ዓለም ውስጥ በስፋት እገባለሁ” ይላል። ጎረቤት፣ ዘመድ . . . በለገሠ ውጤት ማን ያልተደሰተ አለ? በፊት ‘አቅም ያላቸው ናቸው የሚወዳደሩት’ በሚል ወደ ኋላ ያሉትንም እንዳነቃቃ ለገሠ ያስባል። “አሁን ሌሎችም ለመወዳደር ፍላጎት አላቸው” ሲል በአካባቢው የፈጠረውን መነሳሳት ይገልጻል። አልፎ አልፎ የግብርና ባለሙያዎች እየመጡ ‘እንዲህ ብታደርጉ እንዲህ ቢሆን ይህ ቢጨመር ይህ ቢቀነስ ይሏቸዋል።’ በውጤቱም ደስተኞች ሆነዋል። መሬቱ ‘ለቡና’ አዲስ ስለሆነ ‘በደንብ ሥሩ’ ሲሉ ሌሎችንም እየመከሩ ነው። አቶ ለገሠ በፊት እርጥብ ቡና ነበር ለገበያ የሚያቀርበው። አሁን አድርቆ መሸጥ ችሏል። የሚሸጠውም በአካባቢው ላሉ ነጋዴዎች ነበር። አሁን በዓለም አቀፍ መድረክ መሸጥ ችሏል። በዓመት እስከ መቶ ሺህ ብር ብቻ ያገኝ ነበር። በአሁኑ ወቅት ሚሊዮኖችን ማግኘት ችሏል። አሁን ጉዞውን ጀምሯል። ዓይኑንም በቀጣዩ ውድድር ላይ ጥሏል። “ከዚህ በሚበልጥ ሁኔታ ከዚህ በተሻለ ሁኔታ ተዘጋጅቼ ለውድድር እቀርባለሁ” ሲል ያጠናቅቃል። ይህ የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር ስፔሻሊቲ (ባለ ልዩ ጣዕም ቡና) ብቻ ሳይሆን ለየት ያለ ቡና ገዢዎች የሚገዙበት ነው። ቡናውም ከመሸጡ በፊት በተለያየ ደረጃ እና አገራት ተቀምሶ፣ ደረጃ ወጥሎት ነው ለሽያጭ የሚቀርበው። በውድድሩ ማሸነፍ እውቅና ይዞ ይመጣል። ለገሠ ከዚህ በኋላ በተመሳሳይ ዋጋ ባይሸጥ እንኳን ቡናው ከሌሎች አምራቾች እኩል ዋጋ አይሰጠውም። ከውድድሩ የሚገዛው ቡናም በተለየ ቡና መሸጫ በድንቅ ባለሙያ ተዘጋጅቶ በውድ ዋጋ ለገበያ ይቀርባል። ሦስተኛው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ውድድር የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን ከአሊያንስ ኮፊ ኤክሰለንስ እና ዩኤስኤይድ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው። በዘንድሮው ውድድር የኢትዮጵያ ቡና በታሪኩ ከፍተኛ በሚባል ዋጋ ተሽጧል። የለገሠን አንድ ኪሎ ቡና በ884.10 ዶላር (47236 ብር) የገዛው የቻይናው ኤልኤንኬ ኮፊ ትሬዲንግ ነው። ቀሪው ቡና ደግሞ ሳዛ ኮፊ ለሚባል ድርጅት ተሽጧል። ዋጋው የካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ ሽያጭ ክብረ ወሰን ሆኖ ተመዝግቧል። በዘንድሮው ውድድር ከ23 አገራት የተወጣጡ 170 ገዢዎች ተሳታፊ ሆነዋል። ከውድድሩ በኋላ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዱኛ ደበላ “አርሶ አደሮቻችን አገራቸውን አኩርተዋል። የዘንድሮው ውድድር በብዙ ስኬት እና አስደናቂ ክብረ ወሰን ተጠናቋል” ብለዋል። የዩኤስኤይድ ዳይሬክተር ሴን ጆንስ በበኩላቸው “በዚህ በዩኤስኤይድ ድጋፍ በሚካሄደው ውድድር በተለይም የቡናው ዘርፍ እንዲቀየር በማገዛችን ኩራት ይሰማናል። አነስተኛ ቡና አምራቾችን ከቡና ገዢዎች ጋር በማገናኘት አምራቾች ገቢያቸው እንዲያድግ ማድረግ ችለናል” ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cpwe404n806o |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ ክትባቱን ቀድሞ የሚያገኘው ማን ይሆን? እንዴትስ ይከፋፈላል? | ተመራማሪዎች ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት ማግኘት ሲችሉ በፍጥነት ለመላው ዓለም በሚበቃ መልኩ ማዘጋጀት አዳጋች ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። የምርምር ላብራቶሪዎችና ትልልቅ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ከዚህ በፊት አንድን ክትባት ለማዘጋጀት፣ ለመፈተሽ፣ ለማምረትና ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ የሚወስደውን ጊዜ በመሻር በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ክትባቱ በእርግጠኝነት ሲገኝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማከፋፈልም የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን በሀብታም አገራት መካከል ክትባቱን ለማግኘት በሚደረገው እሽቅድድም ተጋላጭ የሆኑት የዓለማችን ማኅበረሰቦቸ ተጎጂ ይሆናሉ። ክትባቱን ማነው ቀድሞ የሚያገኘው? ምን ያህል ያስወጣ ይሆን? የእንቅስቃሴ ገደቦች ተጥለው በሚገኙበት በዚህ ወቅት ክትባቱን እንዴት በፍጥነት በሁሉም ቦታ ማዳረስ ይቻላል? የሚሉት ወሳኝ ጥያቄዎች አልተመለሱም። ከዚህ ቀደም በነበረው ተሞክሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ ክትባቶችን ለማዘጋጀት፣ ለመሞከርና ለማሰራጨት ዓመታትን ይወስድ ነበር። እንደዚያም ሆኖ ክትባቶች ስኬታማ የማይሆኑበት አጋጣሚዎች አሉ። የሰው ልጅ የፈንጣጣ በሽታን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት 200 ዓመታት ወስዶበታል። ምንም እንኳን ክትባት ቢገኝላቸውም እንደ ፖሊዮ፣ ቲታነስ፣ ቲቢ እና የመሳሰሉ በሽታዎች ደግሞ አሁንም ድረስ አብረውን ይኖራሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያሳትፉ የሙከራ ሥራዎች በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በሚገኙ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተከናወኑ ይገኛሉ። በደህናው ዘመን ከአምስት እስከ አስር ዓመታት ይወስድ የነበረው ፍቱን ክትባት የማግኘቱ ሥራ አዋጪ እንደማይሆን የተገነዘቡት አንዳንድ አገራት፤ ደርሰንበታል ያሉት የክትባት አይነትን በብዛት ለማምረት በዝግጅት ላይ ናቸው። አምራቾችም ለክትባቱ የሚረዳ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ ለማድረግ ተዘጋጅተው እየጠበቁ ነው። ባሳለፍነው ወር ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ማግኘቱን ተናግረው ነበር። በአገራቸው ላለፉት ሁለት ወራት በሰዎች ላይ ሙከራ እየተደረገበት የነበረው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መፈቀዱን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል። ክትባቱ አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት ማለፉን የገለጹት ፑቲን፤ ልጃቸው ክትባቱን እየወሰደች እንደምትገኝም ተናግረዋል። ጥቅምት ወይም ኅዳር ላይ ክትባቱን በጅምላ የመስጠት እቅድ እንዳለ የአገሪቱ አመራሮች ቢናገሩም፤ ባለሙያዎች የሩሲያ የክትባት ምርምር እየሄደ ያለበት ፍጥነት ላይ ጥያቄ አንስቷል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ሩሲያ ክትባት ስታመርት ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንድትከተል ማሳሰቡም አይዘነጋም። የሩሲያ ክትባት ድርጅቱ በሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ይገኛሉ ብሎ ከዘረዘራቸው ክትባቶች መካከል አደይለም። እነዚህ ክትባቶች በሰዎች ላይ ተሞክረው ተጨማሪ ምርምር መካሄድ አለበት። ፕሬዘዳንት ፑቲን ግን፤ በሞስኮው ጋማሊያ ተቋም ውስጥ የተሠራው ክትባት ቫይረሱን “በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል” ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር "አንዳንዴ በግላቸው ምርምር የሚያካሂዱ ሰዎች ውጤታም እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህም እጅግ መልካም ዜና ነው" ብለዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ ውጤታማ ክትባት በማግኘት እና በምርምር ደረጃዎች በማለፍ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለም አስምረውበታል። በመላው ዓለም ክትባቱን ለማግኘት ሙከራ በማድረግ ላይ የሚገኙት ቀሪዎቹ ተቋማት ደግሞ ክትባታቸው በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ፈቃድ እንደሚገኝ ተስፋ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ግን እስከ ፈረንጆቹ 2021 አጋማሽ ድረስ በርከት ያሉ ለኮቪድ-19 የሚሆኑ ክትባቶችን ላንመለከት እንችላለን ሲል ተደምጧል። የእንግሊዙ ግዙፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ አስትራዜኔካ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየበለጸገ የሚገኘውን ክትባት ለማምረት ፈቃድ ያገኘ ሲሆን ለዩናይትድ ኪንግደም 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማምረት ተስማምቷል። ለተቀረው ዓለም ደግሞ 2 ቢሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ለማከፋፈል አቅሙ እንዳለው አስታውቋል። ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተባሉት ሌሎች ግዙፍ ኩባንያዎች ደግሞ ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት እስካሁን ድረስ 1 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጋቸውን በመግለጽ በያዝነው ዓመት የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ላይ የማምረት ፈቃድ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። ፈቃድ የሚያገኙ ከሆነ ደግሞ የፈረንጆቹ 2020 ከማለቁ በፊት ቢያንስ 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን እንዲሁም ከዚያ በኋላ ደግሞ በ2021 ተጨማሪ 1.3 ቢሊየን ብልቃጦችን ማምረት አለባቸው። ከእነዚህ ትልልቅ ድርጅቶች በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ 20 የሚሆኑ መድኃኒት አምራቾች ክሊኒካል ሙከራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁሉም ስኬታማ እንደማይሆኑ ይታወቃል፤ ብዙ ጊዜ ክትባት ለመስራት ላይ ታች ከሚሉት ድርጅቶች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ተሳክቶላቸው ማምረት የሚጀምሩት። የእንግሊዙ አስትራዜኒካ በቅልጥፍና ያመርተዋል የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድኃኒት በዋናነት እንዲደርስ የታሰበው ደግሞ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ነው። አስትራዜኒካ በበኩሉ ለፍጥነት እንዲረዳው ከሌሎች ሁለት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት አድርጓል። ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያው የሕህንዱ ሴሩም ኢንዲያ አንዱ ሲሆን፤ ይህ መድኃኒት አምራች በዓለም ላይ መድኃኒትን በከፍተኛ መጠን በማምረት አቅሙ ተስተካካይ የለውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባስተላለፉት መልዕክት ''እየጠበቅን ያለው ክትባት ለሁሉም የሰው ልጆች በእኩል የሚደርስ የሕዝብ ክትባትን ነው'' ካሉ በኋላ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየአቅሙ ርብርብ እንዲያደርግም ተማጽነዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለጊዜው ስማቸው ካልተጠቀስ ስድስት መድኃኒት አምራቾች ጋር ስምምነት መፈረሙ ተሰምቷል። አሜሪካም ብትሆን እስከ ጥር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 300 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማግኘት እየሰራች ነው። ነገር ግን ሁሉም የዓለማችን አገራት በዚህ ፍጥነት ክትባቶቹን ማግኘት አይችሉም። ከዚህ ቀደም ከትባቶችን በማከፋፈል የሚታወቁት እንደ 'ሜድሲንስ ሳንስ ፍሮንቲርስ' ያሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ደግሞ አገራት ከመድኃኒት አምራች ድርጅቶቹ ጋር የሚያደርጉት ድርድር የክትባት ፉክክር እንዳይፈጥር ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። በዚህም ድርጅቶቹ የሚያመርቱትን ክትባት በሙሉ ሃብታም አገራት የሚቀራመቱት ከሆነ ደሃዎቹ አገራት ሊዘነጉ ነው ማለት ነው። ከዚህ በፊት በነበሩ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የሕይወት አድን ክትባቶች ስርጭት ጉዳይ በርካታ አገራት ህጻናትን ከተላላፊ በሽታዎች መከላከል እንዳይችሉና ለሚሊየኖች ሞት ምክንያት ሆኗል። አንዲት ብልቃጥ ክትባት ምን ያክል ይጠየቅባት ይሆን? በአሁኑ ጊዜ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ክትባት ለማግኘት እና ለማምረት ፈሰስ እየተደረገ ነው። ለዚህም ወጪውን ከሞላ ጎደል እየሸፈኑ የሚገኙት ባለጸጋ አገራት ናቸው። እያደጉ ያሉ አገራት ክትባቱን በርካሽም ሆነ በነጻ ለማግኘት ድርድር ላይ ናቸው። የክትባቶች ዋጋ አገራት በሚያዙት መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ ሞደርና የተባለው መድኃኒት አምራች ኩባንያ ለኮቪድ-19 ይሆናል ያለውን ክትባት በብልቃጥ ከ32 እስከ 37 ዶላር ድረስ እንደሚሸጥ ገልጿል። አስትራዜኒካ ደግሞ ክትባቱን ባመረተበት ዋጋ እንደሚሸጠው አልያም እጅግ በጣም በረከሰ ዋጋ እንደሚያከፋፍለው አስቃውቋል። በሕንድ የሚገኘው በዓለማችን ትልቁ የክትባት አምራች ኩባንያ ሴረም ኢንስቲትዩት ደግሞ ከጋቪ እና ከቢልና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን የ150 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያገኘ ሲሆን እስከ 100 ሚሊየን ክትባቶችን ለዝቅተኛ ገቢ አገራት ለማቅረብ ተስማምቷል። የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍ እና ሌሎች ድርጅቶች ክትባቱ ከተገኘ በአግባቡ ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ቀደም ብለው ዘርግተዋል። ማቀዝቀዣ ያላቸው መኪኖች፣ በፀሐይ የሚሰሩ ማቀዝቀዣዎች እና ማከማቻ መጋዘኖች ከዚህ በፊት ለነበሩ ክትባቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ ነበር። እነዚሁ መገልገያዎችም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይጠበቃል። | ኮሮናቫይረስ ፡ ክትባቱን ቀድሞ የሚያገኘው ማን ይሆን? እንዴትስ ይከፋፈላል? ተመራማሪዎች ለኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት ማግኘት ሲችሉ በፍጥነት ለመላው ዓለም በሚበቃ መልኩ ማዘጋጀት አዳጋች ሊሆን እንደሚችል መገመት አይከብድም። የምርምር ላብራቶሪዎችና ትልልቅ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች ከዚህ በፊት አንድን ክትባት ለማዘጋጀት፣ ለመፈተሽ፣ ለማምረትና ውጤታማነቱን ለማረጋገጥ የሚወስደውን ጊዜ በመሻር በፍጥነት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። ክትባቱ በእርግጠኝነት ሲገኝም በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማከፋፈልም የሚደረገው ጥረት እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን በሀብታም አገራት መካከል ክትባቱን ለማግኘት በሚደረገው እሽቅድድም ተጋላጭ የሆኑት የዓለማችን ማኅበረሰቦቸ ተጎጂ ይሆናሉ። ክትባቱን ማነው ቀድሞ የሚያገኘው? ምን ያህል ያስወጣ ይሆን? የእንቅስቃሴ ገደቦች ተጥለው በሚገኙበት በዚህ ወቅት ክትባቱን እንዴት በፍጥነት በሁሉም ቦታ ማዳረስ ይቻላል? የሚሉት ወሳኝ ጥያቄዎች አልተመለሱም። ከዚህ ቀደም በነበረው ተሞክሮ ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል ጥቅም ላይ የሚውሉ ክትባቶችን ለማዘጋጀት፣ ለመሞከርና ለማሰራጨት ዓመታትን ይወስድ ነበር። እንደዚያም ሆኖ ክትባቶች ስኬታማ የማይሆኑበት አጋጣሚዎች አሉ። የሰው ልጅ የፈንጣጣ በሽታን ከምድረ-ገጽ ለማጥፋት 200 ዓመታት ወስዶበታል። ምንም እንኳን ክትባት ቢገኝላቸውም እንደ ፖሊዮ፣ ቲታነስ፣ ቲቢ እና የመሳሰሉ በሽታዎች ደግሞ አሁንም ድረስ አብረውን ይኖራሉ። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያሳትፉ የሙከራ ሥራዎች በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በሚገኙ የምርምር ተቋማትና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተከናወኑ ይገኛሉ። በደህናው ዘመን ከአምስት እስከ አስር ዓመታት ይወስድ የነበረው ፍቱን ክትባት የማግኘቱ ሥራ አዋጪ እንደማይሆን የተገነዘቡት አንዳንድ አገራት፤ ደርሰንበታል ያሉት የክትባት አይነትን በብዛት ለማምረት በዝግጅት ላይ ናቸው። አምራቾችም ለክትባቱ የሚረዳ በቢሊየኖች የሚቆጠር ዶላር ፈሰስ ለማድረግ ተዘጋጅተው እየጠበቁ ነው። ባሳለፍነው ወር ደግሞ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን የኮቪድ-19 ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ፍቃድ ማግኘቱን ተናግረው ነበር። በአገራቸው ላለፉት ሁለት ወራት በሰዎች ላይ ሙከራ እየተደረገበት የነበረው ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል መፈቀዱን ፕሬዝዳንቱ አስታውቀዋል። ክትባቱ አስፈላጊውን የምርመራ ሂደት ማለፉን የገለጹት ፑቲን፤ ልጃቸው ክትባቱን እየወሰደች እንደምትገኝም ተናግረዋል። ጥቅምት ወይም ኅዳር ላይ ክትባቱን በጅምላ የመስጠት እቅድ እንዳለ የአገሪቱ አመራሮች ቢናገሩም፤ ባለሙያዎች የሩሲያ የክትባት ምርምር እየሄደ ያለበት ፍጥነት ላይ ጥያቄ አንስቷል። የዓለም ጤና ድርጅት በበኩሉ ሩሲያ ክትባት ስታመርት ዓለም አቀፍ ሕግጋትን እንድትከተል ማሳሰቡም አይዘነጋም። የሩሲያ ክትባት ድርጅቱ በሦስተኛ ደረጃ ሙከራ ላይ ይገኛሉ ብሎ ከዘረዘራቸው ክትባቶች መካከል አደይለም። እነዚህ ክትባቶች በሰዎች ላይ ተሞክረው ተጨማሪ ምርምር መካሄድ አለበት። ፕሬዘዳንት ፑቲን ግን፤ በሞስኮው ጋማሊያ ተቋም ውስጥ የተሠራው ክትባት ቫይረሱን “በዘላቂነት ለመከላከል የሚያስችል” ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ቃል አቀባይ ክርስቲያን ሊንድሜር "አንዳንዴ በግላቸው ምርምር የሚያካሂዱ ሰዎች ውጤታም እንደሆኑ ይናገራሉ። ይህም እጅግ መልካም ዜና ነው" ብለዋል። ቃል አቀባዩ አያይዘውም፤ ውጤታማ ክትባት በማግኘት እና በምርምር ደረጃዎች በማለፍ መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለም አስምረውበታል። በመላው ዓለም ክትባቱን ለማግኘት ሙከራ በማድረግ ላይ የሚገኙት ቀሪዎቹ ተቋማት ደግሞ ክትባታቸው በያዝነው የአውሮፓውያኑ ዓመት ፈቃድ እንደሚገኝ ተስፋ አድርገዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ግን እስከ ፈረንጆቹ 2021 አጋማሽ ድረስ በርከት ያሉ ለኮቪድ-19 የሚሆኑ ክትባቶችን ላንመለከት እንችላለን ሲል ተደምጧል። የእንግሊዙ ግዙፍ የመድኃኒት አምራች ኩባንያ አስትራዜኔካ በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እየበለጸገ የሚገኘውን ክትባት ለማምረት ፈቃድ ያገኘ ሲሆን ለዩናይትድ ኪንግደም 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማምረት ተስማምቷል። ለተቀረው ዓለም ደግሞ 2 ቢሊየን የክትባት ብልቃጦችን አምርቶ ለማከፋፈል አቅሙ እንዳለው አስታውቋል። ፋይዘር እና ባዮንቴክ የተባሉት ሌሎች ግዙፍ ኩባንያዎች ደግሞ ለኮቪድ-19 ክትባት ለማግኘት እስካሁን ድረስ 1 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጋቸውን በመግለጽ በያዝነው ዓመት የፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ላይ የማምረት ፈቃድ እንደሚያገኙ ተስፋ አድርገዋል። ፈቃድ የሚያገኙ ከሆነ ደግሞ የፈረንጆቹ 2020 ከማለቁ በፊት ቢያንስ 100 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን እንዲሁም ከዚያ በኋላ ደግሞ በ2021 ተጨማሪ 1.3 ቢሊየን ብልቃጦችን ማምረት አለባቸው። ከእነዚህ ትልልቅ ድርጅቶች በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ 20 የሚሆኑ መድኃኒት አምራቾች ክሊኒካል ሙከራቸውን በማከናወን ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን ሁሉም ስኬታማ እንደማይሆኑ ይታወቃል፤ ብዙ ጊዜ ክትባት ለመስራት ላይ ታች ከሚሉት ድርጅቶች መካከል 10 በመቶ የሚሆኑት ብቻ ናቸው ተሳክቶላቸው ማምረት የሚጀምሩት። የእንግሊዙ አስትራዜኒካ በቅልጥፍና ያመርተዋል የተባለው ይህ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድኃኒት በዋናነት እንዲደርስ የታሰበው ደግሞ መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው አገሮች ነው። አስትራዜኒካ በበኩሉ ለፍጥነት እንዲረዳው ከሌሎች ሁለት ኩባንያዎች ጋር ስምምነት አድርጓል። ከእነዚህ መካከል የመጀመሪያው የሕህንዱ ሴሩም ኢንዲያ አንዱ ሲሆን፤ ይህ መድኃኒት አምራች በዓለም ላይ መድኃኒትን በከፍተኛ መጠን በማምረት አቅሙ ተስተካካይ የለውም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባስተላለፉት መልዕክት ''እየጠበቅን ያለው ክትባት ለሁሉም የሰው ልጆች በእኩል የሚደርስ የሕዝብ ክትባትን ነው'' ካሉ በኋላ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በየአቅሙ ርብርብ እንዲያደርግም ተማጽነዋል። የዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት ለጊዜው ስማቸው ካልተጠቀስ ስድስት መድኃኒት አምራቾች ጋር ስምምነት መፈረሙ ተሰምቷል። አሜሪካም ብትሆን እስከ ጥር ወር ባለው ጊዜ ውስጥ 300 ሚሊየን የክትባት ብልቃጦችን ለማግኘት እየሰራች ነው። ነገር ግን ሁሉም የዓለማችን አገራት በዚህ ፍጥነት ክትባቶቹን ማግኘት አይችሉም። ከዚህ ቀደም ከትባቶችን በማከፋፈል የሚታወቁት እንደ 'ሜድሲንስ ሳንስ ፍሮንቲርስ' ያሉ በጎ አድራጎት ድርጅቶች ደግሞ አገራት ከመድኃኒት አምራች ድርጅቶቹ ጋር የሚያደርጉት ድርድር የክትባት ፉክክር እንዳይፈጥር ስጋታቸውን እየገለጹ ነው። በዚህም ድርጅቶቹ የሚያመርቱትን ክትባት በሙሉ ሃብታም አገራት የሚቀራመቱት ከሆነ ደሃዎቹ አገራት ሊዘነጉ ነው ማለት ነው። ከዚህ በፊት በነበሩ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት የሕይወት አድን ክትባቶች ስርጭት ጉዳይ በርካታ አገራት ህጻናትን ከተላላፊ በሽታዎች መከላከል እንዳይችሉና ለሚሊየኖች ሞት ምክንያት ሆኗል። አንዲት ብልቃጥ ክትባት ምን ያክል ይጠየቅባት ይሆን? በአሁኑ ጊዜ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ክትባት ለማግኘት እና ለማምረት ፈሰስ እየተደረገ ነው። ለዚህም ወጪውን ከሞላ ጎደል እየሸፈኑ የሚገኙት ባለጸጋ አገራት ናቸው። እያደጉ ያሉ አገራት ክትባቱን በርካሽም ሆነ በነጻ ለማግኘት ድርድር ላይ ናቸው። የክትባቶች ዋጋ አገራት በሚያዙት መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። ለምሳሌ ሞደርና የተባለው መድኃኒት አምራች ኩባንያ ለኮቪድ-19 ይሆናል ያለውን ክትባት በብልቃጥ ከ32 እስከ 37 ዶላር ድረስ እንደሚሸጥ ገልጿል። አስትራዜኒካ ደግሞ ክትባቱን ባመረተበት ዋጋ እንደሚሸጠው አልያም እጅግ በጣም በረከሰ ዋጋ እንደሚያከፋፍለው አስቃውቋል። በሕንድ የሚገኘው በዓለማችን ትልቁ የክትባት አምራች ኩባንያ ሴረም ኢንስቲትዩት ደግሞ ከጋቪ እና ከቢልና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን የ150 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ያገኘ ሲሆን እስከ 100 ሚሊየን ክትባቶችን ለዝቅተኛ ገቢ አገራት ለማቅረብ ተስማምቷል። የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዩኒሴፍ እና ሌሎች ድርጅቶች ክትባቱ ከተገኘ በአግባቡ ማሰራጨት የሚያስችል ሥርዓት ቀደም ብለው ዘርግተዋል። ማቀዝቀዣ ያላቸው መኪኖች፣ በፀሐይ የሚሰሩ ማቀዝቀዣዎች እና ማከማቻ መጋዘኖች ከዚህ በፊት ለነበሩ ክትባቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ ነበር። እነዚሁ መገልገያዎችም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ይጠበቃል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54114328 |
2health
| ኮሮናቫይረስ ፡ ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ተይዞ ሆስፒታል ገባ | ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ ኮሮናቫይረስ እንዳለበት በመረጋገጡ ሎስአንጀለስ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ለላሪ ኪንግ ቤተሰብ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለኤቢሲ ኒውስና ቀድሞ ይሰራበት ለነበረው ሲኤንኤን ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ላሪ ሆስፒታል ከገባ ከሳምንት በላይ ሆኖታል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የልብ ህመምን ጨምሮ በርካታ የጤና እክሎች ሲያጋጥሙት የነበረው ላሪ፤ ከ60 ዓመት በላይ በዘለቀው የቴሌቪዥን አቅራቢነት ሙያው በርካታ ሽልማቶችናና እውቅናዎችን አግኝቷል። የ87 ዓመቱ ላሪ ተወካዮች እስካሁን በይፋ ወጥተው ሆስፒታል ስለመግባቱና አሁን ስላለበት ሁኔታ ምንም አይነት መግለጫ ስላልሰጡ ዝርዝር መረጃ የለም። ላሪ ኪንግ መጀመሪያ ላይ እውቅናን ያገኘው በ1970ዎቹ በሬዲዮ ያቀርበው በነበረ ዝግጅቱ ነበር። ከዚያም ከ1985 እስከ 2010 (እአአ) በሲኤንኤን ቴሌቪዥን ላይ በተለያዩ መስኮች የዓለማችን ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር በሚያደርገው ቃለ ምልልስ እውቅናን አትርፏል። ላሪ ኪንግ ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን ሙያው በተጨማሪ በአሜሪካ ታዋቂ ለሆነው 'ዩኤስኤ ቲዴይ' ለተባለው ጋዜጣ ለ20 ዓመታት አምደኛ ሆኖ ጽሁፎችን ሲያርብ ቆይቷል። በቅርቡም በሩሲያ መንግሥት በሚተዳደረው የስርጭት ተቋም ስር ለሚቀርቡት 'ሁሉ' እና 'አርቲ' ለተባሉት ቴሌቪዥኖች 'ላሪ ኪንግ ናው' የተሰኘ ዝግጅትን ያቀርብ ነበር። ታዋቂው ቃለ መጠይቅ አድራጊ ላሪ ኪንግ ሙያውን እያከናወነ ባለበት ዘመን ውስጥ የስኳር፣ የልብ ህመምና የሳምባ ካንሰርን ጨምሮ በርካታ ከባድ የጤና ችግሮች ገጥመውት ነበር። በተጨማሪም ካሉት አምስት ልጆች ውስጥ ሁለቱ በልብ ህመምና በሳንባ ካንሰር በሳምንት ልዩነት ውስጥ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ሞተውበታል። ላሪ ኪንግ ከ30 ዓመት በፊት የልብ ህሙማን ሆነው የገንዘብ አቅምም ሆነ የጤና መድን የሌላቸውን ሰዎች የሚረዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት በስሙ በማቋቋም ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። | ኮሮናቫይረስ ፡ ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ በኮቪድ-19 ተይዞ ሆስፒታል ገባ ታዋቂው የቴሌቪዥን አቅራቢ ላሪ ኪንግ ኮሮናቫይረስ እንዳለበት በመረጋገጡ ሎስአንጀለስ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተደረገለት መሆኑን የአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ለላሪ ኪንግ ቤተሰብ ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለኤቢሲ ኒውስና ቀድሞ ይሰራበት ለነበረው ሲኤንኤን ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ላሪ ሆስፒታል ከገባ ከሳምንት በላይ ሆኖታል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የልብ ህመምን ጨምሮ በርካታ የጤና እክሎች ሲያጋጥሙት የነበረው ላሪ፤ ከ60 ዓመት በላይ በዘለቀው የቴሌቪዥን አቅራቢነት ሙያው በርካታ ሽልማቶችናና እውቅናዎችን አግኝቷል። የ87 ዓመቱ ላሪ ተወካዮች እስካሁን በይፋ ወጥተው ሆስፒታል ስለመግባቱና አሁን ስላለበት ሁኔታ ምንም አይነት መግለጫ ስላልሰጡ ዝርዝር መረጃ የለም። ላሪ ኪንግ መጀመሪያ ላይ እውቅናን ያገኘው በ1970ዎቹ በሬዲዮ ያቀርበው በነበረ ዝግጅቱ ነበር። ከዚያም ከ1985 እስከ 2010 (እአአ) በሲኤንኤን ቴሌቪዥን ላይ በተለያዩ መስኮች የዓለማችን ተጽእኖ ፈጣሪ ከሆኑ ታዋቂ ግለሰቦች ጋር በሚያደርገው ቃለ ምልልስ እውቅናን አትርፏል። ላሪ ኪንግ ከሬዲዮና ከቴሌቪዥን ሙያው በተጨማሪ በአሜሪካ ታዋቂ ለሆነው 'ዩኤስኤ ቲዴይ' ለተባለው ጋዜጣ ለ20 ዓመታት አምደኛ ሆኖ ጽሁፎችን ሲያርብ ቆይቷል። በቅርቡም በሩሲያ መንግሥት በሚተዳደረው የስርጭት ተቋም ስር ለሚቀርቡት 'ሁሉ' እና 'አርቲ' ለተባሉት ቴሌቪዥኖች 'ላሪ ኪንግ ናው' የተሰኘ ዝግጅትን ያቀርብ ነበር። ታዋቂው ቃለ መጠይቅ አድራጊ ላሪ ኪንግ ሙያውን እያከናወነ ባለበት ዘመን ውስጥ የስኳር፣ የልብ ህመምና የሳምባ ካንሰርን ጨምሮ በርካታ ከባድ የጤና ችግሮች ገጥመውት ነበር። በተጨማሪም ካሉት አምስት ልጆች ውስጥ ሁለቱ በልብ ህመምና በሳንባ ካንሰር በሳምንት ልዩነት ውስጥ ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ሞተውበታል። ላሪ ኪንግ ከ30 ዓመት በፊት የልብ ህሙማን ሆነው የገንዘብ አቅምም ሆነ የጤና መድን የሌላቸውን ሰዎች የሚረዳ የበጎ አድራጎት ድርጅት በስሙ በማቋቋም ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55516800 |
2health
| በሺዎች የሚቆጠሩ ሀሰተኛ የበይነ መረብ መድሃኒት መደብሮች ተዘጉ | በግንቦት ወር በዓለም ዙሪያ ባሉ ሀሰተኛ የ'ኦንላይን' (በይነ መረብ) መድሃኒት መደብሮች ላይ የተወሰደው ይህ እርምጃ እስካሁን ከነበሩት ከፍተኛው ነው ተብሏል። ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም [ኢንተር ፖል] እያደረገ ያለው ዘመቻ አካል በሆነው በዚህ እርምጃ በበይነ መረብ አማካኝነት ህገ ወጥ መድሃኒቶች የሚሸጡ ከ100 ሺህ በላይ የ'ኦንላየን' (በይነ መረብ) ገበያዎች እንዲወገዱ ተደርገዋል። በዚህ ዘመቻ በዩኬ 13 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህገ ወጥ መድሃኒት በቁጥጥር ስር ውሏል። እንድ አውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2008 ዘመቸው ከተጀመረ በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት ሲሆን እርምጃው ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ህገ ወጥ የ'ኦንላየን' የመድሃኒት ግብይት በተጦጦፈበት ጊዜ የተወሰደ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በዘመቻው ከግምቦት 18 እስከ 25 ድረስ በነበሩት ቀናት በ92 ሀገራት 277 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 20 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህጋዊ ያልሆነ መድሃኒትና ከህክምና ጋር የተያያዙ መሰራያዎች በመንግስታቱ ተወርሷል። በቁጥጥር ከዋሉት ቁሶች አብዘኞቹ ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚውል ሀሰተኛና ትክክለኝነታቸው ያልተረጋገጠ ኪቶች መሆናቸም ተዘግቦል። በዩኬ ከ3 ሺህ በላይ ህገ ወጥና ፍቃድ የሌላቸው የህክምና ምርቶችን የሚያስተዋውቁ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች የተወገዱ ሲሆን 43 ድረ ገጾች ደግሞ ተዘግተዋል። | በሺዎች የሚቆጠሩ ሀሰተኛ የበይነ መረብ መድሃኒት መደብሮች ተዘጉ በግንቦት ወር በዓለም ዙሪያ ባሉ ሀሰተኛ የ'ኦንላይን' (በይነ መረብ) መድሃኒት መደብሮች ላይ የተወሰደው ይህ እርምጃ እስካሁን ከነበሩት ከፍተኛው ነው ተብሏል። ዓለም አቀፉ የፖሊስ ተቋም [ኢንተር ፖል] እያደረገ ያለው ዘመቻ አካል በሆነው በዚህ እርምጃ በበይነ መረብ አማካኝነት ህገ ወጥ መድሃኒቶች የሚሸጡ ከ100 ሺህ በላይ የ'ኦንላየን' (በይነ መረብ) ገበያዎች እንዲወገዱ ተደርገዋል። በዚህ ዘመቻ በዩኬ 13 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህገ ወጥ መድሃኒት በቁጥጥር ስር ውሏል። እንድ አውሮፓውያኑ የዘመን ስሌት በ2008 ዘመቸው ከተጀመረ በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት ሲሆን እርምጃው ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ ህገ ወጥ የ'ኦንላየን' የመድሃኒት ግብይት በተጦጦፈበት ጊዜ የተወሰደ ነው። እንደ አውሮፓውያኑ በዘመቻው ከግምቦት 18 እስከ 25 ድረስ በነበሩት ቀናት በ92 ሀገራት 277 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን 20 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ህጋዊ ያልሆነ መድሃኒትና ከህክምና ጋር የተያያዙ መሰራያዎች በመንግስታቱ ተወርሷል። በቁጥጥር ከዋሉት ቁሶች አብዘኞቹ ለኮሮና ቫይረስ ምርመራ የሚውል ሀሰተኛና ትክክለኝነታቸው ያልተረጋገጠ ኪቶች መሆናቸም ተዘግቦል። በዩኬ ከ3 ሺህ በላይ ህገ ወጥና ፍቃድ የሌላቸው የህክምና ምርቶችን የሚያስተዋውቁ የኢንተርኔት ማስታወቂያዎች የተወገዱ ሲሆን 43 ድረ ገጾች ደግሞ ተዘግተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57417538 |
0business
| በደቡብ አፍሪካው ዝርፊያ ከአርባ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ | ደቡብ አፍሪካውያን ሥራችንን ወስደበውናል ያሏቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ላይ ጥቃት አድረሰዋል። አመፀኞቹ የውጭ ሃገር ዜጎች ሱቆችንና ንብረቶችን በመዝረፍ እና በማቃጠል ላይ እንዳሉ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህንን ተከትሎም ከአርባ በላይ ደቡብ አፍሪካውያን ትናንት ማምሻውን ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፖሊስ አመጸኞቹን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ መሆን ሲጀምሩ ደግሞ የጎማ ጥይቶችንም ጭምር ተጠቅሞ ነበር ተብሏል። • በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ • ደቡብ አፍሪካ በወሮበሎች ላይ የጦር ሠራዊቷን አዘመተች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጂፒ በተሰኘው የደቡብ አፍሪቃ ግዛት የሬስቶራንት ባለቤት የሆነው አቶ ተከስተ ሹምዬ ስለሁኔታው ጠይቀነው ነበር። ''የሌላ ሃገር ዜጎች የሆኑ አፍሪካውያን ላይ ነው ጥቃቱ የተሰነዘረው። በተለይ ደግሞ የመኪና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ናይጄሪያውያን ላይ ከእሁድ ጀምሮ ጥቃት ተፈጽሟል። እስካሁን በሰማሁት ዜና ከ50 በላይ መኪና ተቃጥሏል''በማለት ሁኔታውን ያስረዳል። እሁድ ጠዋት ላይ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ህንጻ እንደተቃጠለ ሁኔታው እስካሁን እንዳልተረጋጋ ተከስተ ይናገራል። ተከስተ እንደሚለው በግምት ከአስር ቀናት በፊት ፕሪቶሪያ በተባለችው ከተማ የሃገሬው ታክሲ ሾፌሮች ከናይጄሪያውያን ሾፌሮች ጋር ተጋጭተው በናይጄሪያውያን በተተኮሰ ጥይት አንድ ደቡብ አፍሪካዊ መሞቱን ተከትሎ ትልቅ ብጥብጥ ተነስቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ላለፉት ቀናት ናይጄሪያውያንን ጨምሮ ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን ንብረት መዝረፍና ማቃጠል ተበራክቶ እንደነበር ተከስተ ይናገራል። ''ይህ ዝርፊያና አመጽ ወደ ጆሃንስበርግ ተዛምቶ መጥቷል። እሁድ ዕለት ዝርፊያና ማቃጠሉ ተጀመረ። ቀደም ብሎ ግን ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን እናስወጣለን የሚል ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ደርሶን ነበር''። • ትሬቨር ኖዋ የዓለማችን አራተኛው ቱጃር ቀልደኛ ሆነ ብዙ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ጂፒ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኢትዮጵያን ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ወይ? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ተከስተ ሲመልስ፤ '' ጂፒ አካባቢ እስካሁን ምንም የደረሰ ነገር የለም። ግን ፕሪቶሪያ ውስጥ ሱቆች ሲቃጠሉ የአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሱቆችም አብረው ወድመዋል። ግን እዚህ ጆሃንስበርግ የፖሊስ ቁጥሩ ከፍ ስላለ ብዙ ደፍረው አልመጡም'' ብሏል። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎች ስራችንን ቀምተውናል በሚል መነሻ እራሳቸውን በማደራጀት ሱቆች ላይ የመዝመት ሁኔታ ታይቷል ይላሉ። ''ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜጎቻችን በስነልቦናም ይሁን ከዝርፊያው ጋር በተገናኘ የሚያጋጥማቸው ችግር አለ፤ ይህንንም ለመፍታት ከሃገሪቱ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የሚቻለውን ሁሉ እየተደረገ ነው''። አክለውም ''በእኛ ማህበረሰብ በኩል በቂ የሆነ ከለላ በማድረግ ላይ እና የዜጎች ንብረት እንዳይዘረፍ በመከላከል በኩል የተሟላ አይደለም በሚል ቅሬታ አለ'' ብለዋል። • ደቡብ አፍሪቃዊቷን የቦክስ ቻምፒዮን የገደለው ተያዘ ብዙ ናይጄሪያውን እና የናይጄሪያውያን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የናይጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆፍሪ ኦንዬማ ''ማሰብ የተሳናቸው ወንጀለኞች'' የፈጸሙት ተግባር ነው በማለት መሰል ተግባራት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል። የውጭ ሃገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ሱቆች መዘረፍና ማቃጠል የደቡብ አፍሪካ የዕለት ተዕለት አጋጣሚ እየሆነ መጥቷል። በቅርቡም መፍትሄ የሚያገኝ አይመስልም። ብዙዎችም እንዴት ደቡብ አፍሪካውያን የሌላ አፍሪካ ሃገር ዜጎች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ? ብለው ቢጠይቁም ጉዳዩ በቀላሉ ምላሽ የሚያገኝ ነገር አይደለም። ምናልባት ስራ አጥ የሆነው የደቡብ አፍሪካ 28 በመቶ የሚሆነው ወጣት ስራ ቢያገኝ ይሄ ሁሉ ነገር በአንዴ ይቆም ነበር የሚሉም አልጠፉም። | በደቡብ አፍሪካው ዝርፊያ ከአርባ በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ ደቡብ አፍሪካውያን ሥራችንን ወስደበውናል ያሏቸውን ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ዜጎች ላይ ጥቃት አድረሰዋል። አመፀኞቹ የውጭ ሃገር ዜጎች ሱቆችንና ንብረቶችን በመዝረፍ እና በማቃጠል ላይ እንዳሉ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ይህንን ተከትሎም ከአርባ በላይ ደቡብ አፍሪካውያን ትናንት ማምሻውን ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውለዋል። ፖሊስ አመጸኞቹን ለመቆጣጠር አስለቃሽ ጭስ የተጠቀመ ሲሆን ነገሮች ከቁጥጥር ውጪ መሆን ሲጀምሩ ደግሞ የጎማ ጥይቶችንም ጭምር ተጠቅሞ ነበር ተብሏል። • በደቡብ አፍሪካ እስር ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ተለቀቁ • ደቡብ አፍሪካ በወሮበሎች ላይ የጦር ሠራዊቷን አዘመተች ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጂፒ በተሰኘው የደቡብ አፍሪቃ ግዛት የሬስቶራንት ባለቤት የሆነው አቶ ተከስተ ሹምዬ ስለሁኔታው ጠይቀነው ነበር። ''የሌላ ሃገር ዜጎች የሆኑ አፍሪካውያን ላይ ነው ጥቃቱ የተሰነዘረው። በተለይ ደግሞ የመኪና ሽያጭ ላይ የተሰማሩ ናይጄሪያውያን ላይ ከእሁድ ጀምሮ ጥቃት ተፈጽሟል። እስካሁን በሰማሁት ዜና ከ50 በላይ መኪና ተቃጥሏል''በማለት ሁኔታውን ያስረዳል። እሁድ ጠዋት ላይ ሶስት ሰዎች መገደላቸውን እና አንድ ህንጻ እንደተቃጠለ ሁኔታው እስካሁን እንዳልተረጋጋ ተከስተ ይናገራል። ተከስተ እንደሚለው በግምት ከአስር ቀናት በፊት ፕሪቶሪያ በተባለችው ከተማ የሃገሬው ታክሲ ሾፌሮች ከናይጄሪያውያን ሾፌሮች ጋር ተጋጭተው በናይጄሪያውያን በተተኮሰ ጥይት አንድ ደቡብ አፍሪካዊ መሞቱን ተከትሎ ትልቅ ብጥብጥ ተነስቶ ነበር። በዚህም ምክንያት ላለፉት ቀናት ናይጄሪያውያንን ጨምሮ ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን ንብረት መዝረፍና ማቃጠል ተበራክቶ እንደነበር ተከስተ ይናገራል። ''ይህ ዝርፊያና አመጽ ወደ ጆሃንስበርግ ተዛምቶ መጥቷል። እሁድ ዕለት ዝርፊያና ማቃጠሉ ተጀመረ። ቀደም ብሎ ግን ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎችን እናስወጣለን የሚል ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ደርሶን ነበር''። • ትሬቨር ኖዋ የዓለማችን አራተኛው ቱጃር ቀልደኛ ሆነ ብዙ ኢትዮጵያውያን በሚገኙበት ጂፒ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በኢትዮጵያን ላይ የደረሰ ጉዳት አለ ወይ? ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ተከስተ ሲመልስ፤ '' ጂፒ አካባቢ እስካሁን ምንም የደረሰ ነገር የለም። ግን ፕሪቶሪያ ውስጥ ሱቆች ሲቃጠሉ የአንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሱቆችም አብረው ወድመዋል። ግን እዚህ ጆሃንስበርግ የፖሊስ ቁጥሩ ከፍ ስላለ ብዙ ደፍረው አልመጡም'' ብሏል። በደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም በበኩላቸው ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች ከሌላ ሃገራት የመጡ ዜጎች ስራችንን ቀምተውናል በሚል መነሻ እራሳቸውን በማደራጀት ሱቆች ላይ የመዝመት ሁኔታ ታይቷል ይላሉ። ''ከዚህ ጋር በተያያዘ ዜጎቻችን በስነልቦናም ይሁን ከዝርፊያው ጋር በተገናኘ የሚያጋጥማቸው ችግር አለ፤ ይህንንም ለመፍታት ከሃገሪቱ የጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር የሚቻለውን ሁሉ እየተደረገ ነው''። አክለውም ''በእኛ ማህበረሰብ በኩል በቂ የሆነ ከለላ በማድረግ ላይ እና የዜጎች ንብረት እንዳይዘረፍ በመከላከል በኩል የተሟላ አይደለም በሚል ቅሬታ አለ'' ብለዋል። • ደቡብ አፍሪቃዊቷን የቦክስ ቻምፒዮን የገደለው ተያዘ ብዙ ናይጄሪያውን እና የናይጄሪያውያን ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ የናይጄሪያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆፍሪ ኦንዬማ ''ማሰብ የተሳናቸው ወንጀለኞች'' የፈጸሙት ተግባር ነው በማለት መሰል ተግባራት በአስቸኳይ እንዲቆም አሳስበዋል። የውጭ ሃገር ዜጎች ንብረት የሆኑ ሱቆች መዘረፍና ማቃጠል የደቡብ አፍሪካ የዕለት ተዕለት አጋጣሚ እየሆነ መጥቷል። በቅርቡም መፍትሄ የሚያገኝ አይመስልም። ብዙዎችም እንዴት ደቡብ አፍሪካውያን የሌላ አፍሪካ ሃገር ዜጎች ላይ ጥቃት ያደርሳሉ? ብለው ቢጠይቁም ጉዳዩ በቀላሉ ምላሽ የሚያገኝ ነገር አይደለም። ምናልባት ስራ አጥ የሆነው የደቡብ አፍሪካ 28 በመቶ የሚሆነው ወጣት ስራ ቢያገኝ ይሄ ሁሉ ነገር በአንዴ ይቆም ነበር የሚሉም አልጠፉም። | https://www.bbc.com/amharic/49561141 |
3politics
| “ለተራቡ ቤተሰቦቼ ገንዘብ መላክ አልቻልኩም” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም | የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም፣ ትግራይ ለሚገኙ “የተራቡ ቤተሰቦቻቸው” ገንዘብ መላክ እንዳልቻሉ ተናገሩ። “ቤተሰቦቼ ትግራይ ናቸው። ብር ልልክላቸው እፈልጋለሁ። ግን ገንዘብ ልልክላቸው አልቻልኩም” ብለዋል ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባደረጉት ንግግር። ዶ/ር ቴድሮስ አክለውም “ማን እንደሞተ ማን በሕይወት እንዳለ አላውቅም” ሲሉ ተደምጠዋል። ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ትግራይ እንደ ባንክ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ መብራት ያሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች ተቆራርጣ ቆይታለች። ለወራት ጋብ ብሎ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም. ዳግም አገርሽቷል። ግጭቱን በመጀመር አንደኛው ወገን ሌላኛውን እየከሰሰ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና መንግሥታት የፌደራል መንግሥቱ እና የህወሓት ኃይሎች ግጭቱን አቁመው ለድርድር እንዲቀመጡ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት ሦስተኛ ቀኑን ይዟል። እስካሁን ግን በአካባቢው ስላለው ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚወጣ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ ዕቀባ በማድረግ ይከሰሳል። የፌደራል መንግሥቱ በምላሹ ጦርነቱንና የትግራይ ኃይሎችን እንደ ምክንያት ያቀርባል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች በጦርነቱ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚጠብቁ ሲሆን፣ ለረሃብ መጋለጣቸውንም ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከትግራይ ሕዝብ ግማሽ ያህሉ “አሳሳቢ የምግብ እጥረት” ገጥሞታል ብሏል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትርና የአሁኑ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ ጦርነቱ ስላሳደረባቸው የከፋ ተጽዕኖ ሲናገሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ባለፈው ሳምንት፣ በትግራይ ያለው ሁኔታ “ከዩክሬን የባሰ ነው። ዓለም ለዩክሬን እና ትግራይ በእኩል መጠን ምላሽ የማይሰጠው፣ እርዳታም በበቂ ደረጃ ለትግራይ የማይቀርበው ዘረኝነት ስለሰፈነ ነው” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። “ያለ ምንም ማጋነን የትግራይ ሰብአዊ ቀውስ ከዩክሬን የባሰ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ። ከወራት በፊትም ይሄንን ተናግሬዋለሁ። የትግራይ ሕዝብ የቆዳ ቀለሙ ነው [ትኩረት ለመነፈጉ] ምክንያቱ” ብለዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ለትግራይ ኃይሎች መሣሪያ በማቀበል ተባብረዋል ሲል ቢከስም፣ ዋና ኃላፊው ክሱን አጣጥለዋል። “ወገንተኝነት እንዳሳየሁ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች ሐሰተኛ ናቸው” ብለዋል። ዛሬ አርብ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም. ሦስተኛ ቀኑን የያዘውን ጦርነት በመቀስቀስ አንደኛው ወገን ሌላኛውን እየከሰሰ ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ስላለው ሁኔታ የትኛውም ወገን መግለጫ አልሰጠም። ረቡዕ ዕለት ጥቃት እንደተከፈተባቸው በትግራይ ቴሌቪዥን ያሳወቁት የትግራይ ኃይሎች፤ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የአገር መከላከያ ሠራዊት ጥምር ኃይል በትግራይ ደቡብ አቅጣጫ መጠነ ሰፊ ጥቃት ጀምረዋል ብሎ ነበር። ህወሓት ለጦርነት ሲዘጋጅና ከሰላም ድርድሩ ለመራቅ ሰበብ ሲፈልግ ቆይቶ ነበር ያለው መንግሥት ደግሞ፣ ረቡዕ ማለዳ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ሲል ከሷል። የህወሓት ከፍተኛ አመራሩ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ አሁንም ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነና የትግራይ ሕዝብ እየተሰቃየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። “አዲስ አበባ ባሉት አመራሮች በተጣለው ዕቀባ ምክንያት ሰዎች እየተራቡ ነው። ሰብአዊ እርዳታ በአፋጣኝ ሕዝቡ ያስፈልገዋል። ሕዝባችን ሰብአዊ እርዳታ እያስገለገው ጦርነት ብንጀምር ሞኝነት ይሆንብናል” ብለዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምላሽ ለማግኘት ቢቢሲ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ከሚዋሰኑበት እንዲሁም በፌደራሉ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት እየተካሄደባቸው እንደሆነ ከሚነገሩት አካባቢዎች 20 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ቆቦ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች ረቡዕ ጀምሮ የከባድ መሣሪያ ተኩስ ድምፅ እንሚሰማ ሐሙስ አመሻሽ ላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ሲሆን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። አንዲት ነዋሪ “የከባድ መሣሪያ ተኩስ እየሰማን ነው። አሁንም ድረስ ተኩሱ አልተቋረጠም። ጦርነቱ ተባብሷል። ተጨማሪ ኃይልም ወደ አካባቢው እየገባ ነው” ስትል ያለውን ሁኔታ ለቢቢሲ ገልጻለች። አንድ ሌላ ነዋሪ የከባድ መሣሪያ ተኩስ መሰማቱ እንደቀጠለና ይህም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ግራ መጋባትን እንደፈጠረ ገልጿል። አንዳንዶችም "በአቅራቢያ ወደሚገኝ ከተማ” መሄዳቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። በትግራይ ተነስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በሺዎች ሕይወታቸውን ያጡበት፣ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉበት እንዲሁም በአሜሪካ ባለሥልጣናት አሐዝ መሠረት 700,000 ዜጎች “ለረሃብ” የተጋለጡበት ነው። | “ለተራቡ ቤተሰቦቼ ገንዘብ መላክ አልቻልኩም” ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ አድኃኖም፣ ትግራይ ለሚገኙ “የተራቡ ቤተሰቦቻቸው” ገንዘብ መላክ እንዳልቻሉ ተናገሩ። “ቤተሰቦቼ ትግራይ ናቸው። ብር ልልክላቸው እፈልጋለሁ። ግን ገንዘብ ልልክላቸው አልቻልኩም” ብለዋል ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ባደረጉት ንግግር። ዶ/ር ቴድሮስ አክለውም “ማን እንደሞተ ማን በሕይወት እንዳለ አላውቅም” ሲሉ ተደምጠዋል። ጦርነቱ ከተነሳ ወዲህ ትግራይ እንደ ባንክ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ መብራት ያሉ መሠረታዊ አገልግሎቶች ተቆራርጣ ቆይታለች። ለወራት ጋብ ብሎ የነበረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ነሐሴ 18/2014 ዓ.ም. ዳግም አገርሽቷል። ግጭቱን በመጀመር አንደኛው ወገን ሌላኛውን እየከሰሰ ሲሆን፣ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና መንግሥታት የፌደራል መንግሥቱ እና የህወሓት ኃይሎች ግጭቱን አቁመው ለድርድር እንዲቀመጡ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ግጭት ሦስተኛ ቀኑን ይዟል። እስካሁን ግን በአካባቢው ስላለው ጦርነት ከሁለቱም ወገን የሚወጣ መረጃ የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዳይገባ ዕቀባ በማድረግ ይከሰሳል። የፌደራል መንግሥቱ በምላሹ ጦርነቱንና የትግራይ ኃይሎችን እንደ ምክንያት ያቀርባል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ንጹሀን ዜጎች በጦርነቱ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፋጣኝ የምግብ እርዳታ የሚጠብቁ ሲሆን፣ ለረሃብ መጋለጣቸውንም ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ያወጧቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከትግራይ ሕዝብ ግማሽ ያህሉ “አሳሳቢ የምግብ እጥረት” ገጥሞታል ብሏል። የቀድሞው የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትርና የአሁኑ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ኃላፊ ዶ/ር ቴድሮስ ጦርነቱ ስላሳደረባቸው የከፋ ተጽዕኖ ሲናገሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም። ባለፈው ሳምንት፣ በትግራይ ያለው ሁኔታ “ከዩክሬን የባሰ ነው። ዓለም ለዩክሬን እና ትግራይ በእኩል መጠን ምላሽ የማይሰጠው፣ እርዳታም በበቂ ደረጃ ለትግራይ የማይቀርበው ዘረኝነት ስለሰፈነ ነው” ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል። “ያለ ምንም ማጋነን የትግራይ ሰብአዊ ቀውስ ከዩክሬን የባሰ እንደሆነ ልነግራችሁ እወዳለሁ። ከወራት በፊትም ይሄንን ተናግሬዋለሁ። የትግራይ ሕዝብ የቆዳ ቀለሙ ነው [ትኩረት ለመነፈጉ] ምክንያቱ” ብለዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት ዶ/ር ቴድሮስ ለትግራይ ኃይሎች መሣሪያ በማቀበል ተባብረዋል ሲል ቢከስም፣ ዋና ኃላፊው ክሱን አጣጥለዋል። “ወገንተኝነት እንዳሳየሁ የሚጠቁሙ ሪፖርቶች ሐሰተኛ ናቸው” ብለዋል። ዛሬ አርብ ነሐሴ 20/2014 ዓ.ም. ሦስተኛ ቀኑን የያዘውን ጦርነት በመቀስቀስ አንደኛው ወገን ሌላኛውን እየከሰሰ ሲሆን፣ ባለፉት ሁለት ቀናት ስላለው ሁኔታ የትኛውም ወገን መግለጫ አልሰጠም። ረቡዕ ዕለት ጥቃት እንደተከፈተባቸው በትግራይ ቴሌቪዥን ያሳወቁት የትግራይ ኃይሎች፤ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖ እና የአገር መከላከያ ሠራዊት ጥምር ኃይል በትግራይ ደቡብ አቅጣጫ መጠነ ሰፊ ጥቃት ጀምረዋል ብሎ ነበር። ህወሓት ለጦርነት ሲዘጋጅና ከሰላም ድርድሩ ለመራቅ ሰበብ ሲፈልግ ቆይቶ ነበር ያለው መንግሥት ደግሞ፣ ረቡዕ ማለዳ ላይ ጥቃት ፈጽሟል ሲል ከሷል። የህወሓት ከፍተኛ አመራሩ አቶ ጌታቸው ረዳ፣ ከቢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ አሁንም ከፍተኛ ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነና የትግራይ ሕዝብ እየተሰቃየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። “አዲስ አበባ ባሉት አመራሮች በተጣለው ዕቀባ ምክንያት ሰዎች እየተራቡ ነው። ሰብአዊ እርዳታ በአፋጣኝ ሕዝቡ ያስፈልገዋል። ሕዝባችን ሰብአዊ እርዳታ እያስገለገው ጦርነት ብንጀምር ሞኝነት ይሆንብናል” ብለዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ምላሽ ለማግኘት ቢቢሲ ያደረገው ጥረት አልተሳካም። የአማራ ክልል እና የትግራይ ክልል ከሚዋሰኑበት እንዲሁም በፌደራሉ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል ግጭት እየተካሄደባቸው እንደሆነ ከሚነገሩት አካባቢዎች 20 ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው ቆቦ ከተማ ያሉ ነዋሪዎች ረቡዕ ጀምሮ የከባድ መሣሪያ ተኩስ ድምፅ እንሚሰማ ሐሙስ አመሻሽ ላይ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ሲሆን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የሚሰማው የተኩስ ድምፅ ስጋት እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። አንዲት ነዋሪ “የከባድ መሣሪያ ተኩስ እየሰማን ነው። አሁንም ድረስ ተኩሱ አልተቋረጠም። ጦርነቱ ተባብሷል። ተጨማሪ ኃይልም ወደ አካባቢው እየገባ ነው” ስትል ያለውን ሁኔታ ለቢቢሲ ገልጻለች። አንድ ሌላ ነዋሪ የከባድ መሣሪያ ተኩስ መሰማቱ እንደቀጠለና ይህም በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ግራ መጋባትን እንደፈጠረ ገልጿል። አንዳንዶችም "በአቅራቢያ ወደሚገኝ ከተማ” መሄዳቸውን ለቢቢሲ ተናግሯል። በትግራይ ተነስቶ ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት በሺዎች ሕይወታቸውን ያጡበት፣ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉበት እንዲሁም በአሜሪካ ባለሥልጣናት አሐዝ መሠረት 700,000 ዜጎች “ለረሃብ” የተጋለጡበት ነው። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cnl10pdgrrro |
0business
| ቤንዚን በሊትር 11 ብር ጨምሮ 48 ብር ገደማ ሊሸጥ ነው | መንግሥት ለነዳጅ የሚያውለውን ድጎማ ሂደት ለማንሳት በያዘው ዕቅድ መሠረት በመጀመሪያው ዙር የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ክለሳ ከፍተኛ ጭማሪ ተደረገ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነገ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም. ድረስ የሚያገለግል አዲስ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ 10 ብር ከ96 ሳንቲም ጨማሪ በማሳየት ከነገ ጀምሮ በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም ይሸጣል። ነጭ ናፍጣ ደግሞ ባለፉት ጥቂት ወራት 14 ብር ገደማ ጭማሪ አሳይቷል። ከሚያዚያ 30/2014 ጀምሮ በሊትር 35.43 ብር ሲሸጥ የነበረው ነጭ ናፍጣ በአንድ ግዜ 13.59 ብር ጨምሮ ከነገ ጀምሮ በሊትር 49.02 ብር ለገበያ ይቀርባል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ክለሳ አስመልክቶ ማከስኞ ምሽት ባወጣው የዋጋ ዝርዝር መሠረት ከነገ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ነጭ ናፍጣ 49.02፣ ኬሮሲን 49.02፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 53.10፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 52.37 እና የአውሮፕላን ነዳጅ 98.83 በሊትር ዋጋ እንደተቆረጠላቸው አስታውቋል፡፡ በአሁኑ በነዳጅ ምርቶች ላይ የተደረገው ጭማሪ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ጭማሪዎች ሁሉ ከፍተኛው ቢሆንም፣ አሁንም መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል። ምንም እንኳን መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች በአጠቃላይ ድጎማ ሲያደርግ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በተባለ ሥርዓት አማካይነት ለሕዝብ የትራንስፖርት መገልገያዎች ድጎማ ይደረጋል ተብሏል። ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ መንግሥት በነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ተከታታይ ጭማሪን አድርጓል። ለማሳያም ከሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ በተደረገው ለውጥ ቤንዚን የ15 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ከ31.74 ወደ 36.87 ብር ከፍ እንዲል ተደርጎ ነበር። ለዚህ ከፍተኛ ጭማሪ የሚነሱት ምክንያቶች ደግሞ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርት ዋጋ መጨመር እና መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች እያደረገ ባለው ድጎማ ምክንያት በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ወጪ ማድረጉ ጫና እየፈጠረበት በመሆኑ ነው። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ስታንዳርድ ጥናት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ እንደሚሉት መንግሥት ለነዳጅ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪ ያደርጋል። በግንቦትና በሰኔ መካከል ባሉ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ብቻ መንግሥት 16 ቢሊዮን ብር ወይም 268 ሚሊዮን ዶላር ነዳጅን ለመደጎም ሲል ወጪ ማድረጉን አቶ ለሜሳ ተናግረዋል። የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ጭማሪ ሲደረግ እንደሚስተዋለው በሌሎች ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በስከተል የኑሮ ውድነቱን ያባብሰዋል የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ አስከትሏል። | ቤንዚን በሊትር 11 ብር ጨምሮ 48 ብር ገደማ ሊሸጥ ነው መንግሥት ለነዳጅ የሚያውለውን ድጎማ ሂደት ለማንሳት በያዘው ዕቅድ መሠረት በመጀመሪያው ዙር የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ክለሳ ከፍተኛ ጭማሪ ተደረገ። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከነገ ረቡዕ ሰኔ 29/2014 እስከ ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም. ድረስ የሚያገለግል አዲስ የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ዝርዝር ይፋ አድርጓል። በዚህም መሠረት በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ሲሸጥ የነበረው ቤንዚን፤ 10 ብር ከ96 ሳንቲም ጨማሪ በማሳየት ከነገ ጀምሮ በሊትር 47 ብር ከ83 ሳንቲም ይሸጣል። ነጭ ናፍጣ ደግሞ ባለፉት ጥቂት ወራት 14 ብር ገደማ ጭማሪ አሳይቷል። ከሚያዚያ 30/2014 ጀምሮ በሊትር 35.43 ብር ሲሸጥ የነበረው ነጭ ናፍጣ በአንድ ግዜ 13.59 ብር ጨምሮ ከነገ ጀምሮ በሊትር 49.02 ብር ለገበያ ይቀርባል። የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ባወጣው የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ክለሳ አስመልክቶ ማከስኞ ምሽት ባወጣው የዋጋ ዝርዝር መሠረት ከነገ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም. ጀምሮ ነጭ ናፍጣ 49.02፣ ኬሮሲን 49.02፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 53.10፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 52.37 እና የአውሮፕላን ነዳጅ 98.83 በሊትር ዋጋ እንደተቆረጠላቸው አስታውቋል፡፡ በአሁኑ በነዳጅ ምርቶች ላይ የተደረገው ጭማሪ ከዚህ ቀደም ከነበሩት ጭማሪዎች ሁሉ ከፍተኛው ቢሆንም፣ አሁንም መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች ከፍተኛ ድጎማ እያደረገ መሆኑ ተገልጿል። ምንም እንኳን መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች በአጠቃላይ ድጎማ ሲያደርግ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በተባለ ሥርዓት አማካይነት ለሕዝብ የትራንስፖርት መገልገያዎች ድጎማ ይደረጋል ተብሏል። ባለፉት ጥቂት ወራት የኢትዮጵያ መንግሥት በነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ ላይ ተከታታይ ጭማሪን አድርጓል። ለማሳያም ከሚያዝያ 30/2014 ዓ.ም. ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ በተደረገው ለውጥ ቤንዚን የ15 በመቶ ጭማሪ በማድረግ ከ31.74 ወደ 36.87 ብር ከፍ እንዲል ተደርጎ ነበር። ለዚህ ከፍተኛ ጭማሪ የሚነሱት ምክንያቶች ደግሞ ዓለም አቀፍ የነዳጅ ምርት ዋጋ መጨመር እና መንግሥት ለነዳጅ ምርቶች እያደረገ ባለው ድጎማ ምክንያት በቢሊዮን የሚቆጠር ብር ወጪ ማድረጉ ጫና እየፈጠረበት በመሆኑ ነው። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ስታንዳርድ ጥናት ዳይሬክተር አቶ ለሜሳ ቱሉ እንደሚሉት መንግሥት ለነዳጅ በሚያደርገው ድጎማ ምክንያት በየዓመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ወጪ ያደርጋል። በግንቦትና በሰኔ መካከል ባሉ ሰላሳ ቀናት ውስጥ ብቻ መንግሥት 16 ቢሊዮን ብር ወይም 268 ሚሊዮን ዶላር ነዳጅን ለመደጎም ሲል ወጪ ማድረጉን አቶ ለሜሳ ተናግረዋል። የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ላይ ጭማሪ ሲደረግ እንደሚስተዋለው በሌሎች ምርቶችና አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ በስከተል የኑሮ ውድነቱን ያባብሰዋል የሚል ስጋት በበርካቶች ዘንድ አስከትሏል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cxen371z51eo |
3politics
| የካፒቶል ሂል ሁከት፡ የአሜሪካ ፍርድ ቤት የትራምፕን ጥያቄ ውድቅ አደረገ | የዩናይትድ ስቴትስ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካፒቶል ሁከት መርማሪዎች የዋይት ሃውስ መዝገቦቻቸውን እንዳይመለከቱ ለማገድ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገው። ትራምፕ በዋይት ሃውስ መዝገቦቻቸው የፕሬዝደንቶችን ማህደር በሚስጥር እንዲቀመጥ በሚፈቅደው መብት ሊጠበቅ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰነዶቹ ላይ የነበረውን መብት አንስተዋል። ትራምፕ ጥር 6 ስለተፈጠረው የካፒቶል ሂል ሁከት አስቀድመው ያውቁ እንደሆነ ለማወቅ ምርማሪዎች በምርመራ ላይ ይገኛሉ። የአሜሪካ ኮንግረስ የጆ ባይደንን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ለማረጋገጥ በስብሰባ ላይ ባለበት ወቅት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ህንጻን መውረራቸው ይታወሳል። ትራምፕ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ መጨበርበር ነበር በሚል በባይደን መሸነፋቸውን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የሐሙሱን ውሳኔን በመቃወም ይግባኝ ያቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉዳዩም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያመራል። ውሳኔውን ያሳወቁት የኮሎምቢያ አካባቢ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞች የባይደንን ትዕዛዝ በመሻር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ያቀረቡትን ጥያቄ የሚያስቀብል "ምንም ምክንያት" አላቀረቡም ብለዋል። አክለውም ሁለቱም የመንግሥት አካላት ከጥቃቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው መዝገቦች ልዩ የህግ ፍላጎት እንዳለው ተስማምተዋል ብለዋል። ጥያቄው በፕሬዝዳንት ባይደን ፓርቲ በሆነው ዴሞክራቶች የበላይነት በተያዘው በተወካዮች ምክር ቤት በተቋቋመ ኮሚቴ የተካሄደ ነው። ኮሚቴው በኮንግረሱ ላይ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ስለነበረው ሁኔታ ፍንጭ ይሰጠኛል በሚል የስልክ ልውውጦችን፣ የጎብኝዎች መዝገቦችን እና ሌሎች የዋይት ሃውስ ሰነዶችን ለማየት ይፈልጋል። "በቀድሞው እና በአሁኑ ፕሬዝዳንቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሙሉ በሙሉ የመደመጥ ሕገ መንግሥታዊ እና ህጋዊ መብታቸው በመከልከልከሉ ሊጠገን የማይችል ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል" ሲሉ የትራምፕ ጠበቆች ደንበኛቸው ቀደም ሲል ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቤት ብለዋል። የካፒቶሉን ግርግር ተከትሎ አመጽ አነሳስተዋል በሚል ትራምፕ በኮንግረሱ የታችኛው ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳ ቢሆንም በወቅቱ ሪፐብሊካን በበላይነት በተቆጣጠሩት የላይኛው ምክር ቤት (ሴኔት) ውድቅ ሆኗል። ከካፒቶል ሂልን አመጽ ጋር በተያያዘ ከ670 በላይ ሰዎች ታስረዋል። | የካፒቶል ሂል ሁከት፡ የአሜሪካ ፍርድ ቤት የትራምፕን ጥያቄ ውድቅ አደረገ የዩናይትድ ስቴትስ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የካፒቶል ሁከት መርማሪዎች የዋይት ሃውስ መዝገቦቻቸውን እንዳይመለከቱ ለማገድ ያቀረቡትን ጥያቄ ውድቅ አደረገው። ትራምፕ በዋይት ሃውስ መዝገቦቻቸው የፕሬዝደንቶችን ማህደር በሚስጥር እንዲቀመጥ በሚፈቅደው መብት ሊጠበቅ ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል። ሆኖም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በሰነዶቹ ላይ የነበረውን መብት አንስተዋል። ትራምፕ ጥር 6 ስለተፈጠረው የካፒቶል ሂል ሁከት አስቀድመው ያውቁ እንደሆነ ለማወቅ ምርማሪዎች በምርመራ ላይ ይገኛሉ። የአሜሪካ ኮንግረስ የጆ ባይደንን ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ለማረጋገጥ በስብሰባ ላይ ባለበት ወቅት የትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ህንጻን መውረራቸው ይታወሳል። ትራምፕ ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ምንም ማስረጃ ሳያቀርቡ መጨበርበር ነበር በሚል በባይደን መሸነፋቸውን ለመቀበል ፍቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የሐሙሱን ውሳኔን በመቃወም ይግባኝ ያቀርባሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ጉዳዩም ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያመራል። ውሳኔውን ያሳወቁት የኮሎምቢያ አካባቢ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ዳኞች የባይደንን ትዕዛዝ በመሻር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ያቀረቡትን ጥያቄ የሚያስቀብል "ምንም ምክንያት" አላቀረቡም ብለዋል። አክለውም ሁለቱም የመንግሥት አካላት ከጥቃቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው መዝገቦች ልዩ የህግ ፍላጎት እንዳለው ተስማምተዋል ብለዋል። ጥያቄው በፕሬዝዳንት ባይደን ፓርቲ በሆነው ዴሞክራቶች የበላይነት በተያዘው በተወካዮች ምክር ቤት በተቋቋመ ኮሚቴ የተካሄደ ነው። ኮሚቴው በኮንግረሱ ላይ ጥቃት ከመሰንዘሩ በፊት ስለነበረው ሁኔታ ፍንጭ ይሰጠኛል በሚል የስልክ ልውውጦችን፣ የጎብኝዎች መዝገቦችን እና ሌሎች የዋይት ሃውስ ሰነዶችን ለማየት ይፈልጋል። "በቀድሞው እና በአሁኑ ፕሬዝዳንቶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ሙሉ በሙሉ የመደመጥ ሕገ መንግሥታዊ እና ህጋዊ መብታቸው በመከልከልከሉ ሊጠገን የማይችል ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል" ሲሉ የትራምፕ ጠበቆች ደንበኛቸው ቀደም ሲል ለይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አቤት ብለዋል። የካፒቶሉን ግርግር ተከትሎ አመጽ አነሳስተዋል በሚል ትራምፕ በኮንግረሱ የታችኛው ምክር ቤት ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳ ቢሆንም በወቅቱ ሪፐብሊካን በበላይነት በተቆጣጠሩት የላይኛው ምክር ቤት (ሴኔት) ውድቅ ሆኗል። ከካፒቶል ሂልን አመጽ ጋር በተያያዘ ከ670 በላይ ሰዎች ታስረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59594067 |
5sports
| ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ይቆያል፡ ፔፕ ጋርዲዮላ | በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ሰሞኑን አንድ ነገር ላይ ስምምነት ነበራቸው። የስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ሰሞኑን የፈጠረው ቅራኔ መዳረሻውን ማንችስተር ሲቲ ያደርጋል የሚል። "ሜሲ የእግር ኳስ ዘመኑን በባርሳ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል፤ የማምነውም እንደዚያ እንደሚሆን ነው" በማለት የማንቺስትር ሲቲው አለቃና የቀድሞው የሜሲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ግን የበርካቶችን ግምት ከግምት እንዳያልፍ አድርጎታል። የ32 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የኮከብ የእግር ኳስ ሕይወቱን ያሳለፈው ከባርሴሎና ጋር ነው። ነገር ግን በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ክለቡን በነጻ ዝውውር መልቀቅ የሚያስችል ስምምነት አለው። የአሁኑ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከ2008 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 2012 ድረስ ለአራት ዓመታት ያክል ሜሲን አሰልጥኖታል። በአራት ዓመት ጊዜውም ሦስት የላሊጋና ሁለት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በአንድ ወቅትም "እኔ በጣም እድለኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ቢያንስ የዓለማችንን ምርጡን ተጫዋች ሌዮኔል ሜሲን አሰልጥኜዋለሁ" በማለት ጋርዲዮላ ለሜሲ ያለውን አድናቆት ገልጿል። ይህ ወደጅነታቸውም አሁን እንደገና ሊያገናኛቸው ይችላል የሚለውን ግምት በበርካቶች ዘንድ አሳድሯል። ነገር ግን ጋርዲዮላ የማይታሰብ ነው ብሏል። "እዚያው [ባርሴሎና] ይቆያል፤ የእኔ ፍላጎት ይህ ነው" በማለት። ጋርዲዮላ ባርሴሎናን ለቆ ወደ ባየር ሙኒክ ሲያመራ ባርሴሎናን በዋንጫ አንበሽብሾት ነበር። የክለቡም በጣም ስኬታማው አሰልጣኝ የነበረ ሲሆን በአራት ዓመት ቆይታው 14 ዋንጫዎችን ለስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ገቢ አድርጓል። ከዚያም ወደ ጀርመን አቅንቶ ጋርዲዮላ ከባየር ሙኒክ ጋር ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የቡንደስ ሊጋውን ዋንጫ ማሸነፍ ችሏዋል። ወደ እንግሊዝ በማምራትም ማንችስተር ሲቲን በማሰልጠን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ የውድድር ጊዜያት በበላይነት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሸፏል። በዚህኛው የውድድር ዘመን ግን ጋርዲዮላ የሚደግመው አይመስልም፤ አንድም ጨዋታ ያልተሸነፈው ሊቨርፑል 13 ጨዋታዎች ብቻ እየቀሩት ማንችስተር ሲቲን በ22 ነጥብ ርቆ ሊጉን እየመራ ይገኛል። የባርሴሎናው የምንጊዜም ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ በመሆን የምድራችን ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን በባርሳ ቆይታው 10 የላሊጋና አራት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፏል። እስከ ፈረንጆቹ 2021 በባርሳ የሚያቆየው ኮንትራትም አለው። ነገር ግን የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤሪክ አቢዳል ተጫዋቾች በቀድሞው የክለቡ አሰልጣኝ ኧርኔስቶ ቫልቨርዴ ጊዜ "ጠንክረው አይሰሩም ነበር" የሚል ክስ ማንሳቱን ተከትሎ ሜሲ የአጸፋ መልስ ሰጥቷል። በእንደዚህ አይነት ጠንካራ ንግግሩ ለዓመታት የማይታወቀው ሜሲ አሁን መልስ መስጠቱ ክለቡ ጋር መለያየትን ስለመረጠ ሊሆን ይችላል በማለት ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። አሁን በአቢዳልና በሜሲ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ጋርዲዮላ ማራገብ አልፈለገም። ሁለቱንም በአንድ ወቅት ባርሳ ውስጥ ያሰለጠኑት ጋርዲዮላ "ስለሌላ ክለብ ተጫዋቾች ማውራት አልፈልግም፤ ሜሲ ግን የእግር ኳስ ዘመኑን እዚያው ባርሴሎና ውስጥ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል" ብሏል። | ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ይቆያል፡ ፔፕ ጋርዲዮላ በርካታ የስፖርቱ ቤተሰቦች ሰሞኑን አንድ ነገር ላይ ስምምነት ነበራቸው። የስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሊዮኔል ሜሲ ከባርሴሎና ጋር ሰሞኑን የፈጠረው ቅራኔ መዳረሻውን ማንችስተር ሲቲ ያደርጋል የሚል። "ሜሲ የእግር ኳስ ዘመኑን በባርሳ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል፤ የማምነውም እንደዚያ እንደሚሆን ነው" በማለት የማንቺስትር ሲቲው አለቃና የቀድሞው የሜሲ አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ግን የበርካቶችን ግምት ከግምት እንዳያልፍ አድርጎታል። የ32 ዓመቱ አርጀንቲናዊ የኮከብ የእግር ኳስ ሕይወቱን ያሳለፈው ከባርሴሎና ጋር ነው። ነገር ግን በዚህ የውድድር ዘመን መጨረሻ ክለቡን በነጻ ዝውውር መልቀቅ የሚያስችል ስምምነት አለው። የአሁኑ የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ከ2008 እ.አ.አ ጀምሮ እስከ 2012 ድረስ ለአራት ዓመታት ያክል ሜሲን አሰልጥኖታል። በአራት ዓመት ጊዜውም ሦስት የላሊጋና ሁለት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አንስቷል። በአንድ ወቅትም "እኔ በጣም እድለኛ ነኝ፤ ምክንያቱም ቢያንስ የዓለማችንን ምርጡን ተጫዋች ሌዮኔል ሜሲን አሰልጥኜዋለሁ" በማለት ጋርዲዮላ ለሜሲ ያለውን አድናቆት ገልጿል። ይህ ወደጅነታቸውም አሁን እንደገና ሊያገናኛቸው ይችላል የሚለውን ግምት በበርካቶች ዘንድ አሳድሯል። ነገር ግን ጋርዲዮላ የማይታሰብ ነው ብሏል። "እዚያው [ባርሴሎና] ይቆያል፤ የእኔ ፍላጎት ይህ ነው" በማለት። ጋርዲዮላ ባርሴሎናን ለቆ ወደ ባየር ሙኒክ ሲያመራ ባርሴሎናን በዋንጫ አንበሽብሾት ነበር። የክለቡም በጣም ስኬታማው አሰልጣኝ የነበረ ሲሆን በአራት ዓመት ቆይታው 14 ዋንጫዎችን ለስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ገቢ አድርጓል። ከዚያም ወደ ጀርመን አቅንቶ ጋርዲዮላ ከባየር ሙኒክ ጋር ለሦስት ተከታታይ ዓመታት የቡንደስ ሊጋውን ዋንጫ ማሸነፍ ችሏዋል። ወደ እንግሊዝ በማምራትም ማንችስተር ሲቲን በማሰልጠን ያለፉትን ሁለት ተከታታይ የውድድር ጊዜያት በበላይነት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ አሸፏል። በዚህኛው የውድድር ዘመን ግን ጋርዲዮላ የሚደግመው አይመስልም፤ አንድም ጨዋታ ያልተሸነፈው ሊቨርፑል 13 ጨዋታዎች ብቻ እየቀሩት ማንችስተር ሲቲን በ22 ነጥብ ርቆ ሊጉን እየመራ ይገኛል። የባርሴሎናው የምንጊዜም ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ስድስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ በመሆን የምድራችን ብቸኛ ተጫዋች ሲሆን በባርሳ ቆይታው 10 የላሊጋና አራት የቻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን አሸንፏል። እስከ ፈረንጆቹ 2021 በባርሳ የሚያቆየው ኮንትራትም አለው። ነገር ግን የባርሴሎናው ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ኤሪክ አቢዳል ተጫዋቾች በቀድሞው የክለቡ አሰልጣኝ ኧርኔስቶ ቫልቨርዴ ጊዜ "ጠንክረው አይሰሩም ነበር" የሚል ክስ ማንሳቱን ተከትሎ ሜሲ የአጸፋ መልስ ሰጥቷል። በእንደዚህ አይነት ጠንካራ ንግግሩ ለዓመታት የማይታወቀው ሜሲ አሁን መልስ መስጠቱ ክለቡ ጋር መለያየትን ስለመረጠ ሊሆን ይችላል በማለት ተንታኞች ግምታቸውን አስቀምጠዋል። አሁን በአቢዳልና በሜሲ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ጋርዲዮላ ማራገብ አልፈለገም። ሁለቱንም በአንድ ወቅት ባርሳ ውስጥ ያሰለጠኑት ጋርዲዮላ "ስለሌላ ክለብ ተጫዋቾች ማውራት አልፈልግም፤ ሜሲ ግን የእግር ኳስ ዘመኑን እዚያው ባርሴሎና ውስጥ የሚያጠናቅቅ ይመስለኛል" ብሏል። | https://www.bbc.com/amharic/sport-51425052 |
3politics
| የአዲሱ ካቢኔ አምስቱ ቁልፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች | ስድስተኛውን ዙር ብሔራዊ ምርጫን ተከትሎ ብልጽግና ፓርቲ አብዛኛውን የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መቀመጫዎች ካሸነፈ በኋላ ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲስ መንግሥት መስርቷል። በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ቀን ስበሰባ የብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበርና ባለፉት ሦስት ዓመታት አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ዐቢይ አሕመድ፣ ለቀጣይ አምስት ዓመት በመሪነት መንበር ላይ እንዲቆዩ መርጧቸዋል። የአስተዳደራቸውን ሥራ አስፈጻሚ ከፍተኛ ባለሥልጣንትን ይፋ ማድረግ ደግሞ ቀጣዩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራ ነው። በዚህም በእሳቸው በሚመራውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ አባል የሚሆኑና በቁልፍ የሚኒስትርነት ቦታዎች ላይ የሚሰየሙ ግለሰቦችን በመምረጥ ለምክር ቤቱ አቅርበው እንዲሾሙ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፓርቲያቸው ቀደም ሲል እንደገለጹት በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ከብልጽግና ፓርቲ ባሻገር ከተፎካካሪ ፓርቲ አባላት መካከል እንዲካተቱ አድርገዋል። እስካሁን በነበሩት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ላይ የአወቃቀርና የስያሜ ለውጥ የተደረገባቸው ያሉ ሲሆን ነባርና አዳዲስ ሚኒስትሮች ተካተዋል። አዲሱ መንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚኖሩት ሁሉም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በሚመደቡባቸው መስኮች የየራሳቸው ቁልፍ ሚና ቢኖራቸውም አንዳንዶቹ ግን የሚኖራቸው ኃላፊነትና ተጽዕኗቸው የጎላ ነው። አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ይኖራቸዋል ከሚባለው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አኳያ አምስት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ቃኝተናል። • የገንዘብ ሚኒስቴር፡ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሓት አማጺያን ጋር አገሪቱ የገባችበትን ጦርነት ተከትሎ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ክፉኛ እየተፈተነ ይገኛል። ይህ ጦርነት በርካታ የምጣኔ ሀብት አውታሮች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመትን አድርሷል። ይህንን ጦርነት ተከትሎ ዋነኛ የአገሪቱ ድጋፍ ሰጪ ምዕራባውያን እጃቸውን የመሰብሰብ አዝማሚያ እያሳዩ ነው። በተጨማሪም በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በተከታታይ እየጨመረ በመሄዱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የምንዛሪ ገበያ ያለው የምንዛሪ ተመን ልዩነቱ እጅጉን የሰፋ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ባለፉት ወራት በመናሩ የሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምዕራባውያን አገራትና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለአገሪቱ በሚያቀርቡት ድጋፍ ላይ ለውጥ የሚኖር ከሆነ አሁን ባለው የዶላር እጥረት፣ የመሠረታዊ ፍጆታ እቃዎች ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት ሊፈትነው ይችላል ተብሎ ያሰጋል። • ሰላም ሚኒስቴር፡ በአገሪቱ ሠሜናዊ ክፍል ያለው ጦርነት፣ በምዕራብ እና ደቡብ ያለው አለመረጋጋት የአገሪቱን ሰላም እና ደኅንነትን አደጋ ውስጥ ከከተቱት ጉዳዮች መካከል ናቸው። ለውጥ ይደረግባቸዋል ከሚባሉት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አንዱ የሆነው ይህ ተቋም ያጋጠሙ የሰላም መደፍረሶችን ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት መሥራት እንዳለበት፣ ይህም የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት እንደሚካሄድ ተናግረዋል። • የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡ ትግራይ ውስጥ ከተከሰተው ግጭትና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ሥራ ይጠብቃታል። በትግራይ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። በትግራይ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ትግራይ ባለው የሰብአዊ ቀውስ እንዲሁም በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ርዕስ በማድረግ ውይይት አድርጓል። በቅርቡ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ የተደረጉት የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊዎች ጉዳይ ከመንግሥታቱ ድርጅት፣ ከምዕራባውያን በኩል ተቃውሞን አስከትሏል። ይህም ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ባላት ግንኙነት ላይ አሉታዊ ውጤት ሊኖረው የሚችል ሲሆን በዚህ በኩልም አገሪቱ ዋነኛ ሥራ ይጠብቃታል። በዚህ መካከል ኢትዮጵያ በመላው ዓለም ካሏት ከ60 በላይ ቆንስላዎች እና ኤምባሲዎች ገሚሱን ለመቀነስ ያላትን እቅድ ይፋ አድርጋ ወደ እርምጃ ገብታለች። • ዐቃቤ ሕግ፡ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በሚነሱ ብሔር ተኮር ግጭቶች፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች የተነሳ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ግለሰቦች በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ሲያማርሩ ይሰማል። በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ያለው የፍትህ አካል ገለልተኛ፣ ታማኝ እና ብቁ አይደለም የሚል የሰላ ትችት ሲቀርብ ይደመጣል። ከዚህ በተጨማሪም የተፋጠነ ፍትህ የሚሹ በርካታ ዜጎች ፍትህ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ከዚህ አንጻር የስያሜ ለውጥ ሊደረግበት ይችላል የተባለው የአገሪቱ ዋነኛ የፍትህ ተቋም ዐቃቤ ሕግ በርካታ ሥራዎች ይጠበቁበታል። • ገቢዎች ሚኒስቴር፡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም በመንሰራፋቱ ምክንያት የተከሰተው የንግድ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ገቢ ላይ ቀላል የማይባል ተጽእኖን አሳድሯል። የአወቃቀር ለውጥ እንደሚደረግባቸው ከተነገረካቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው የገቢዎች ሚኒስቴር በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። አገሪቱ ለተለያዩ ሥራዎቿ የምታውለውን መዋዕለ ነዋይ ከልዩ ልዩ ምንጮች የሚያሰባስበው ይህ ተቋም በተለያዩ ምክንያቶች ጫና ውስጥ ለወደቀው የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። የአገሪቱን የታክስና የገቢ መሠረት የማስፋቱ ሥራን የሚያከናውነው ይህተ ተቋም በምጣኔ ሀብቱ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጫና ለመቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት ተጥሎበታል። በተለያዩ ወቅቶች በአገሪቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ብዛት፣ መዋቅርና ስያሜዎች ላይ በየጊዜው ለውጦች ሲካሄዱ የነበረ ሲሆን፤ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የካቢኔ ሚኒስቴሮች ዝርዝር ላይም ይኸው ለውጥ እንደሚኖር በስፋት እየተነገረ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችንም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚመሩ ዕጩዎችን በማቅረብ እንዲሾሙላቸው ይጠይቃሉ። | የአዲሱ ካቢኔ አምስቱ ቁልፍ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ስድስተኛውን ዙር ብሔራዊ ምርጫን ተከትሎ ብልጽግና ፓርቲ አብዛኛውን የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን መቀመጫዎች ካሸነፈ በኋላ ሰኞ መስከረም 24/2014 ዓ.ም አዲስ መንግሥት መስርቷል። በምክር ቤቱ የመጀመሪያ ቀን ስበሰባ የብልጽግና ፓርቲ ሊቀመንበርና ባለፉት ሦስት ዓመታት አገሪቱን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የመሩት ዐቢይ አሕመድ፣ ለቀጣይ አምስት ዓመት በመሪነት መንበር ላይ እንዲቆዩ መርጧቸዋል። የአስተዳደራቸውን ሥራ አስፈጻሚ ከፍተኛ ባለሥልጣንትን ይፋ ማድረግ ደግሞ ቀጣዩ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሥራ ነው። በዚህም በእሳቸው በሚመራውን የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውስጥ አባል የሚሆኑና በቁልፍ የሚኒስትርነት ቦታዎች ላይ የሚሰየሙ ግለሰቦችን በመምረጥ ለምክር ቤቱ አቅርበው እንዲሾሙ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩና ፓርቲያቸው ቀደም ሲል እንደገለጹት በተለያዩ የመንግሥት ኃላፊነት ቦታዎች ከብልጽግና ፓርቲ ባሻገር ከተፎካካሪ ፓርቲ አባላት መካከል እንዲካተቱ አድርገዋል። እስካሁን በነበሩት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች ላይ የአወቃቀርና የስያሜ ለውጥ የተደረገባቸው ያሉ ሲሆን ነባርና አዳዲስ ሚኒስትሮች ተካተዋል። አዲሱ መንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚኖሩት ሁሉም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች በሚመደቡባቸው መስኮች የየራሳቸው ቁልፍ ሚና ቢኖራቸውም አንዳንዶቹ ግን የሚኖራቸው ኃላፊነትና ተጽዕኗቸው የጎላ ነው። አገሪቱ ካለችበት ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር ይኖራቸዋል ከሚባለው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊነት አኳያ አምስት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶችን ቃኝተናል። • የገንዘብ ሚኒስቴር፡ ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሓት አማጺያን ጋር አገሪቱ የገባችበትን ጦርነት ተከትሎ የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ክፉኛ እየተፈተነ ይገኛል። ይህ ጦርነት በርካታ የምጣኔ ሀብት አውታሮች እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመትን አድርሷል። ይህንን ጦርነት ተከትሎ ዋነኛ የአገሪቱ ድጋፍ ሰጪ ምዕራባውያን እጃቸውን የመሰብሰብ አዝማሚያ እያሳዩ ነው። በተጨማሪም በአገሪቱ ያለው የውጭ ምንዛሪ ዋጋ በተከታታይ እየጨመረ በመሄዱ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጥቁር ገበያውና በመደበኛው የምንዛሪ ገበያ ያለው የምንዛሪ ተመን ልዩነቱ እጅጉን የሰፋ ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪም በአገሪቱ ያለው የኑሮ ውድነት ባለፉት ወራት በመናሩ የሸቀጦችና አገልግሎቶች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። የምዕራባውያን አገራትና የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ለአገሪቱ በሚያቀርቡት ድጋፍ ላይ ለውጥ የሚኖር ከሆነ አሁን ባለው የዶላር እጥረት፣ የመሠረታዊ ፍጆታ እቃዎች ዋጋ መናር ጋር ተያይዞ የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት ሊፈትነው ይችላል ተብሎ ያሰጋል። • ሰላም ሚኒስቴር፡ በአገሪቱ ሠሜናዊ ክፍል ያለው ጦርነት፣ በምዕራብ እና ደቡብ ያለው አለመረጋጋት የአገሪቱን ሰላም እና ደኅንነትን አደጋ ውስጥ ከከተቱት ጉዳዮች መካከል ናቸው። ለውጥ ይደረግባቸዋል ከሚባሉት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች አንዱ የሆነው ይህ ተቋም ያጋጠሙ የሰላም መደፍረሶችን ለመፍታት እና ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት መሥራት እንዳለበት፣ ይህም የአዲሱ መንግሥት ቁልፍ አጀንዳ ሊሆን እንደሚገባ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው የአዲስ መንግሥት ምስረታና በዓለ ሲመት ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል መግባባትን ለመፍጠር ሁሉን አካታች ውይይት እንደሚካሄድ ተናግረዋል። • የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፡ ትግራይ ውስጥ ከተከሰተው ግጭትና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ አገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ግንኙነትና የዲፕሎማሲ ሥራ ይጠብቃታል። በትግራይ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። በትግራይ ያለውን ጦርነት ተከትሎ ምዕራባውያንና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ግፊቶችን እያደረጉ ይገኛሉ። የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ትግራይ ባለው የሰብአዊ ቀውስ እንዲሁም በሕዳሴው ግድብ ዙሪያ ኢትዮጵያን ርዕስ በማድረግ ውይይት አድርጓል። በቅርቡ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል በሚል ከኢትዮጵያ ለቀው እንዲወጡ የተደረጉት የተባበሩት መንግሥታት ኃላፊዎች ጉዳይ ከመንግሥታቱ ድርጅት፣ ከምዕራባውያን በኩል ተቃውሞን አስከትሏል። ይህም ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግሥታት ጋር ባላት ግንኙነት ላይ አሉታዊ ውጤት ሊኖረው የሚችል ሲሆን በዚህ በኩልም አገሪቱ ዋነኛ ሥራ ይጠብቃታል። በዚህ መካከል ኢትዮጵያ በመላው ዓለም ካሏት ከ60 በላይ ቆንስላዎች እና ኤምባሲዎች ገሚሱን ለመቀነስ ያላትን እቅድ ይፋ አድርጋ ወደ እርምጃ ገብታለች። • ዐቃቤ ሕግ፡ በኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በሚነሱ ብሔር ተኮር ግጭቶች፣ ፖለቲካዊ ተቃውሞዎች የተነሳ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ግለሰቦች በፍትህ ሥርዓቱ ላይ ሲያማርሩ ይሰማል። በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ያለው የፍትህ አካል ገለልተኛ፣ ታማኝ እና ብቁ አይደለም የሚል የሰላ ትችት ሲቀርብ ይደመጣል። ከዚህ በተጨማሪም የተፋጠነ ፍትህ የሚሹ በርካታ ዜጎች ፍትህ እየተጠባበቁ ይገኛሉ። ከዚህ አንጻር የስያሜ ለውጥ ሊደረግበት ይችላል የተባለው የአገሪቱ ዋነኛ የፍትህ ተቋም ዐቃቤ ሕግ በርካታ ሥራዎች ይጠበቁበታል። • ገቢዎች ሚኒስቴር፡ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም በመንሰራፋቱ ምክንያት የተከሰተው የንግድ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ገቢ ላይ ቀላል የማይባል ተጽእኖን አሳድሯል። የአወቃቀር ለውጥ እንደሚደረግባቸው ከተነገረካቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው የገቢዎች ሚኒስቴር በአገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ሚና ካላቸው ተቋማት መካከል አንዱ ነው። አገሪቱ ለተለያዩ ሥራዎቿ የምታውለውን መዋዕለ ነዋይ ከልዩ ልዩ ምንጮች የሚያሰባስበው ይህ ተቋም በተለያዩ ምክንያቶች ጫና ውስጥ ለወደቀው የአገሪቱ ምጣኔ ሀብት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል። የአገሪቱን የታክስና የገቢ መሠረት የማስፋቱ ሥራን የሚያከናውነው ይህተ ተቋም በምጣኔ ሀብቱ ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጫና ለመቋቋም የሚያስችሉ ተግባራትን የማከናወን ኃላፊነት ተጥሎበታል። በተለያዩ ወቅቶች በአገሪቱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ብዛት፣ መዋቅርና ስያሜዎች ላይ በየጊዜው ለውጦች ሲካሄዱ የነበረ ሲሆን፤ ይፋ ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው የካቢኔ ሚኒስቴሮች ዝርዝር ላይም ይኸው ለውጥ እንደሚኖር በስፋት እየተነገረ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከላይ የተጠቀሱትንና ሌሎችንም የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች የሚመሩ ዕጩዎችን በማቅረብ እንዲሾሙላቸው ይጠይቃሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-58794356 |
5sports
| በአምላክ ተሰማ የዓለምን ቀልብ የገዙበት የአፍሪካ ዋንጫ ፍልሚያ | ኢትዮጵያዊው አርቢትር በአምላክ ተሰማ ትላንት ምሽት የስፖርቱ ዓለም መነጋገሪያ ሆነው አምሽተዋል። ለምን? ካሜሩን እያስተናገደችው የምትገኘው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ፍፃሜውን ቀጣይ እሑድ ሲያገኝ ሴኔጋል የዋንጫ ተፋላሚ መሆኗን አውቃለች። ረቡዕ ምሽት ከቡርኪና ፋሶ ፍፃሜ የተጫወተችው ሴኔጋል በኮከብ አጥቂዋ ሳዲዮ ማኔ ታግዛ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ፍልሚያውን ረታለች። ቢሆንም ከዚህ እልህ አስጨራሽ ጨዋታና ውጤት ትይዩ ኢትዮጵያዊው የመሃል ዳኛ በአምላክ ተሰማ መነጋገሪያ ሆነው አምሽተዋል። በአምላክ ተሰማ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሦስተኛ ጨዋታቸውን ረቡዕ ምሽት ዳኝተዋል። በአምላክ ከዚህ ቀደም ሴኔጋል ከጊኒ እንዲሁም አዘጋጇ ካሜሩን ከኮሞሮስ ያደረጉትን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ግብፅ ከናይጄሪያ እንዲሁም ከሱዳን ያደረገችውን ጨዋታ ደግሞ በአጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል [ቪኤአር] ዳኝነት መርተዋል። ነገር ግን ሴኔጋል ከቡርኪና ፋሶ ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ፍልሚያ የመሩት 'ኢንተርናሽናል' አልቢትር የመገናኛ ብዙኃንና የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነዋል። በጨዋታው ምን ተፈጠረ? በደማቅ ፈገግታቸው የሚታወቁት በአምላክ ተሰማ ከተጫዋቾች ጋር እሰጥ አገባ መግባት የሚፈልጉ ዳኛ አይደሉም። የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ አንዳንዴም ቀይ ካርድ ሲሰጡ በፈገግታ ታጅበው ነው። የወደቀ ተጫዋች ለማንሳት የሚቀድማቸውም የለም። በረቡዕ ምሽቱ ጨዋታ የሰኔጋሉ ኩያቴ ከቡርኪና ፋሶው ግብ ጠባቂ ኮፊ ጋር የተጋጨበትን ክስተት የተመለከቱት በአምላክ ለሴኔጋል ፍጹም ቅጣት ምት ይሰጣሉ። ሁለቱ ተጫዋቾች ክፉኛ በመጎዳታቸው ምክንያት ሕክምና እስኪያገኙ የጠበቁት ዳኛው ወደ ቪኤአር መስኮት በማቅናት ተሳስቻለሁ ፍጹም ቅጣት ምት አይደለም ሲሉ ይወስናሉ። የመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ገደማ ደግሞ የቡርኪናቤው ተከላካይ ኤድሞን ታፕሶባ ኳስ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ነክቷል በማለት ዳኛው ለሴኔጋል 'ሪጎሬ' ይሸልማሉ። አልፎም ተጫዋቹ ለፈፀመው ቅጣት ማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ይሰጡታል። ነገር ግን ውሳኔያቸውን ከማጽደቃቸው በፊት አጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል እንዲመለከቱ ረዳቶታቸው ይጠቁሟቸዋል። ከሜዳው ጠርዝ ወደቆመው የቪኤአር መስኮት ያቀኑት በአምላክ ፍጹም ቅጣት ምቱን ሽረው ወደ ታፕሶባ አቅንተው ቢጫ ካርድህ ተሰርዞልሃል ብለው ይቅርታ ሲጠይቁት በቴሌቪዥን መስኮት ታይተዋል። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ያለምንም ግብ ቢጠናቀቅም የስፖርት ቤተሰቡ የበአምላክን ስም እያነሳ ሲያወድሳቸው ተስተውሏል። ሁለቱም የፍጹም ቅጣት ምቶች አሳማኝ አይደሉም ያሉ በርካታ የስፖርት ወዳጆች ዳኛው ቪኤአርን በአግባቡ መጠቀማቸውን ሳያደንቁ አላለፉም። ቁጥራቸው የበዛ አፍሪካዊያን የስፖርት ጋዜጠኞች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የበአምላክን ስም እያነሱ ሲያንቆለጳጵሷቸው ታይተዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የትዊተር ተከታዮች ያሉት ጋናዊው እውቅ የስፖርት ጋዜጠኛ ሳዲቅ አዳምስ "ድንቅ ውሳኔ" ብሎ ሲያሞግሳቸው ኬንያዊቷ ታዋቂ የስፖርት ጋዜጠኛ ካታሚ ሚሼል ደግሞ "ሁሉም ውሳኔዎቹ አግባብ ናቸው" ስትል ለዳኛው አድናቆቷን ገልፋለች። ደቡብ አፍሪካዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ሊሬንዝ ኮለርም ለበአምላክ አድናቆታቸውን ከቸሩ ሰዎች መካከል ነው። ጎል ዶት ኮም የተሰኘው የእግርኳስ ድረ-ገፅ እስቲ ስለ በአምላክ ያላችሁን አስተያየን አጋሩን ብሎ በትዊተር ገፁ ከለጠፈው መልዕክት ሥር በርካታ የስፖርት ወዳጆች ለዳኛው አድናቆታቸውን ሲያጎርፉ ነበር። አልፎም በርካታ ኢትዮጵያውያንም የዳኛውን ብቃት በማድነቅ 'ኮርተንብሃል' ሲሉ ለዳኛ በአምላክ ያላቸውን ክብር አሳይተዋል። 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በበርካታ ክስተቶች የታጀበ፤ በዳኞች ቢጫና ቀይ ካርድ የተከበበ መሆኑን ተከትሎ በአምላክ ይህን ፈታኝ ጨዋታ በብቃት መዳኘታቸው ከበሬታ አጎናፅፏቸዋል። ጨዋታውን ሴኔጋል በሳዲዮ ማኔ፣ በአብዱ ዲያሎና በኢድሪስ ጉዬ ጎሎች በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች። ዛሬ ሐሙስ ምሽት ደግሞ ግብፅ አዘጋጇ ካሜሩንን ትገጥማለች። | በአምላክ ተሰማ የዓለምን ቀልብ የገዙበት የአፍሪካ ዋንጫ ፍልሚያ ኢትዮጵያዊው አርቢትር በአምላክ ተሰማ ትላንት ምሽት የስፖርቱ ዓለም መነጋገሪያ ሆነው አምሽተዋል። ለምን? ካሜሩን እያስተናገደችው የምትገኘው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ጨዋታ ፍፃሜውን ቀጣይ እሑድ ሲያገኝ ሴኔጋል የዋንጫ ተፋላሚ መሆኗን አውቃለች። ረቡዕ ምሽት ከቡርኪና ፋሶ ፍፃሜ የተጫወተችው ሴኔጋል በኮከብ አጥቂዋ ሳዲዮ ማኔ ታግዛ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ፍልሚያውን ረታለች። ቢሆንም ከዚህ እልህ አስጨራሽ ጨዋታና ውጤት ትይዩ ኢትዮጵያዊው የመሃል ዳኛ በአምላክ ተሰማ መነጋገሪያ ሆነው አምሽተዋል። በአምላክ ተሰማ በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ሦስተኛ ጨዋታቸውን ረቡዕ ምሽት ዳኝተዋል። በአምላክ ከዚህ ቀደም ሴኔጋል ከጊኒ እንዲሁም አዘጋጇ ካሜሩን ከኮሞሮስ ያደረጉትን ጨዋታ በመሃል ዳኝነት ግብፅ ከናይጄሪያ እንዲሁም ከሱዳን ያደረገችውን ጨዋታ ደግሞ በአጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል [ቪኤአር] ዳኝነት መርተዋል። ነገር ግን ሴኔጋል ከቡርኪና ፋሶ ለዋንጫ ለማለፍ ያደረጉትን ፍልሚያ የመሩት 'ኢንተርናሽናል' አልቢትር የመገናኛ ብዙኃንና የማኅበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነዋል። በጨዋታው ምን ተፈጠረ? በደማቅ ፈገግታቸው የሚታወቁት በአምላክ ተሰማ ከተጫዋቾች ጋር እሰጥ አገባ መግባት የሚፈልጉ ዳኛ አይደሉም። የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ አንዳንዴም ቀይ ካርድ ሲሰጡ በፈገግታ ታጅበው ነው። የወደቀ ተጫዋች ለማንሳት የሚቀድማቸውም የለም። በረቡዕ ምሽቱ ጨዋታ የሰኔጋሉ ኩያቴ ከቡርኪና ፋሶው ግብ ጠባቂ ኮፊ ጋር የተጋጨበትን ክስተት የተመለከቱት በአምላክ ለሴኔጋል ፍጹም ቅጣት ምት ይሰጣሉ። ሁለቱ ተጫዋቾች ክፉኛ በመጎዳታቸው ምክንያት ሕክምና እስኪያገኙ የጠበቁት ዳኛው ወደ ቪኤአር መስኮት በማቅናት ተሳስቻለሁ ፍጹም ቅጣት ምት አይደለም ሲሉ ይወስናሉ። የመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ገደማ ደግሞ የቡርኪናቤው ተከላካይ ኤድሞን ታፕሶባ ኳስ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ ነክቷል በማለት ዳኛው ለሴኔጋል 'ሪጎሬ' ይሸልማሉ። አልፎም ተጫዋቹ ለፈፀመው ቅጣት ማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ ይሰጡታል። ነገር ግን ውሳኔያቸውን ከማጽደቃቸው በፊት አጋዥ ተንቀሳቃሽ ምስል እንዲመለከቱ ረዳቶታቸው ይጠቁሟቸዋል። ከሜዳው ጠርዝ ወደቆመው የቪኤአር መስኮት ያቀኑት በአምላክ ፍጹም ቅጣት ምቱን ሽረው ወደ ታፕሶባ አቅንተው ቢጫ ካርድህ ተሰርዞልሃል ብለው ይቅርታ ሲጠይቁት በቴሌቪዥን መስኮት ታይተዋል። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ ያለምንም ግብ ቢጠናቀቅም የስፖርት ቤተሰቡ የበአምላክን ስም እያነሳ ሲያወድሳቸው ተስተውሏል። ሁለቱም የፍጹም ቅጣት ምቶች አሳማኝ አይደሉም ያሉ በርካታ የስፖርት ወዳጆች ዳኛው ቪኤአርን በአግባቡ መጠቀማቸውን ሳያደንቁ አላለፉም። ቁጥራቸው የበዛ አፍሪካዊያን የስፖርት ጋዜጠኞች በማኅበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የበአምላክን ስም እያነሱ ሲያንቆለጳጵሷቸው ታይተዋል። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ የትዊተር ተከታዮች ያሉት ጋናዊው እውቅ የስፖርት ጋዜጠኛ ሳዲቅ አዳምስ "ድንቅ ውሳኔ" ብሎ ሲያሞግሳቸው ኬንያዊቷ ታዋቂ የስፖርት ጋዜጠኛ ካታሚ ሚሼል ደግሞ "ሁሉም ውሳኔዎቹ አግባብ ናቸው" ስትል ለዳኛው አድናቆቷን ገልፋለች። ደቡብ አፍሪካዊ የስፖርት ጋዜጠኛ ሊሬንዝ ኮለርም ለበአምላክ አድናቆታቸውን ከቸሩ ሰዎች መካከል ነው። ጎል ዶት ኮም የተሰኘው የእግርኳስ ድረ-ገፅ እስቲ ስለ በአምላክ ያላችሁን አስተያየን አጋሩን ብሎ በትዊተር ገፁ ከለጠፈው መልዕክት ሥር በርካታ የስፖርት ወዳጆች ለዳኛው አድናቆታቸውን ሲያጎርፉ ነበር። አልፎም በርካታ ኢትዮጵያውያንም የዳኛውን ብቃት በማድነቅ 'ኮርተንብሃል' ሲሉ ለዳኛ በአምላክ ያላቸውን ክብር አሳይተዋል። 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በበርካታ ክስተቶች የታጀበ፤ በዳኞች ቢጫና ቀይ ካርድ የተከበበ መሆኑን ተከትሎ በአምላክ ይህን ፈታኝ ጨዋታ በብቃት መዳኘታቸው ከበሬታ አጎናፅፏቸዋል። ጨዋታውን ሴኔጋል በሳዲዮ ማኔ፣ በአብዱ ዲያሎና በኢድሪስ ጉዬ ጎሎች በማሸነፍ ለሁለተኛ ተከታታይ ጊዜ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች። ዛሬ ሐሙስ ምሽት ደግሞ ግብፅ አዘጋጇ ካሜሩንን ትገጥማለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-60241093 |
2health
| የአፍሪካ ሕብረት በኦሚክሮን ምክንያት በአባል አገራቱ ላይ የጉዞ እቀባ መደረጉን አወገዘ | የአፍሪካ ሕብረት ምዕራባዊያን አገራት በአዲሱ የኮቪድ ዝርያ ኦሚክሮን ምክንያት በአፍሪካ አገራት ላይ የጣሉትን እቀባ ተቃወመ። ኦሚክሮን የሚል ስም የተሰጠው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደበብ አፍሪካ መገኘቱን ተከትሎ ምዕራብ አገራት በአባል አገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እቀባ ተቀባይነት እንደሌለው ሕብረቱ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ደቡብ አፍሪካ አዲሱን ቫይረስ ማግኘቷና በተገቢው ፍጥነት ለዓለም ማሳወቋ የሚደነቅ ነው ያለው የሕብረቱ መግለጫ፤ ነገር ግን ደቡብ አፍሪካ ይህን በምታደርግበት ጊዜ ቫይረሱ በሌሎች የአውሮፓ አገራት እንደነበረ ፍንጮች መኖራቸውን ገልጧል። ያም ሆኖ ደቡብ አፍሪካ ተህዋሲው መኖሩን በማጋለጧ መቀጣት አይገባትም ይላል መግለጫው። እንደ ዩናይትድ ኪንደግም፣ አሜሪካ እና ካናዳ ያሉ አገራት የኦሚክሮንን መገኘት ተከትሎ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ሌሎች የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ላይ ጉዞ እቀባ ጥለዋል። ምዕራባዊያን በደቡብ አፍሪካ አገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እቀባ የምጣኔ ሀብት ፈተና እንደሚፈጥርም ሕብረቱ በመግለጫው ጠቅሷል። ኦሚክሮን እና የሚሰራጭበት ፍጥነትና ጠቅላላ ባህሪያቱ ገና በመጠናት ላይ ያለ ሆኖ ሳለ ሥርጭቱ አደገኛ ነው በሚል አባል አገራቱ ላይ እቀባ መጣል ተቀባይነት ስለሌለው በአስቸኳይ የጉዞ እገዳ ይነሳላቸው ሲል የአፍሪካ ሕብረት አሳስቧል። አሁን በአባል አገራት የተጣሉ የጉዞ ክልከላዎች ከምጣኔ ሀብት ተግዳሮቶች ባሻገር የሕክምና ቁሳቁሶች ወደ አፍሪካ እንዳይገቡ ሌላ ፈተና ይደቅናልም ብሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች ለምርምር የሚያስፈልጓቸውን ቁሳቁሶች እንዳያገኙም ያደርጋቸዋል። በዚህና ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ የአፍሪካ አገራትን መርጦ የጉዞ እቀባ ማድረግ ተቀባይነት የሌለውና አሳፋሪም ነው ሲል መግለጫው ይቋጫል። የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት በተመሳሳይ ይህን በአፍሪካ አገራት የተጣለውን እቀባ መኮነናቸው ይታወሳል። | የአፍሪካ ሕብረት በኦሚክሮን ምክንያት በአባል አገራቱ ላይ የጉዞ እቀባ መደረጉን አወገዘ የአፍሪካ ሕብረት ምዕራባዊያን አገራት በአዲሱ የኮቪድ ዝርያ ኦሚክሮን ምክንያት በአፍሪካ አገራት ላይ የጣሉትን እቀባ ተቃወመ። ኦሚክሮን የሚል ስም የተሰጠው አዲሱ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በደበብ አፍሪካ መገኘቱን ተከትሎ ምዕራብ አገራት በአባል አገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እቀባ ተቀባይነት እንደሌለው ሕብረቱ ባወጣው መግለጫ ጠቅሷል። ደቡብ አፍሪካ አዲሱን ቫይረስ ማግኘቷና በተገቢው ፍጥነት ለዓለም ማሳወቋ የሚደነቅ ነው ያለው የሕብረቱ መግለጫ፤ ነገር ግን ደቡብ አፍሪካ ይህን በምታደርግበት ጊዜ ቫይረሱ በሌሎች የአውሮፓ አገራት እንደነበረ ፍንጮች መኖራቸውን ገልጧል። ያም ሆኖ ደቡብ አፍሪካ ተህዋሲው መኖሩን በማጋለጧ መቀጣት አይገባትም ይላል መግለጫው። እንደ ዩናይትድ ኪንደግም፣ አሜሪካ እና ካናዳ ያሉ አገራት የኦሚክሮንን መገኘት ተከትሎ ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ ሌሎች የደቡባዊ አፍሪካ አገራት ላይ ጉዞ እቀባ ጥለዋል። ምዕራባዊያን በደቡብ አፍሪካ አገራት ላይ የጣሉት የጉዞ እቀባ የምጣኔ ሀብት ፈተና እንደሚፈጥርም ሕብረቱ በመግለጫው ጠቅሷል። ኦሚክሮን እና የሚሰራጭበት ፍጥነትና ጠቅላላ ባህሪያቱ ገና በመጠናት ላይ ያለ ሆኖ ሳለ ሥርጭቱ አደገኛ ነው በሚል አባል አገራቱ ላይ እቀባ መጣል ተቀባይነት ስለሌለው በአስቸኳይ የጉዞ እገዳ ይነሳላቸው ሲል የአፍሪካ ሕብረት አሳስቧል። አሁን በአባል አገራት የተጣሉ የጉዞ ክልከላዎች ከምጣኔ ሀብት ተግዳሮቶች ባሻገር የሕክምና ቁሳቁሶች ወደ አፍሪካ እንዳይገቡ ሌላ ፈተና ይደቅናልም ብሏል። ይህም ብቻ ሳይሆን የደቡብ አፍሪካ ተመራማሪዎች ለምርምር የሚያስፈልጓቸውን ቁሳቁሶች እንዳያገኙም ያደርጋቸዋል። በዚህና ሌሎች ምክንያቶች የተነሳ የአፍሪካ አገራትን መርጦ የጉዞ እቀባ ማድረግ ተቀባይነት የሌለውና አሳፋሪም ነው ሲል መግለጫው ይቋጫል። የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት በተመሳሳይ ይህን በአፍሪካ አገራት የተጣለውን እቀባ መኮነናቸው ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59574507 |
5sports
| ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን አልተመለሱም ስለተባሉ ኤርትራውያን እስካሁን የሚታወቀው | በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ኦሪገን ተጉዘው ጠፍተዋል ከተባሉ 5 ኤርትራውያን አትሌቶች መካከል ሦስቱ ለውድድር ወደ ሌሎች አገራት መሄዳቸውን ተነገረ። በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ከሄዱት የኤርትራ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት መካከል ወደ አገራቸው ያልተመለሱ ስለመኖራቸው ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ተዘግቧል። ቀደም ሲል የኦሪገን ግዛት ፖሊስ የአምስት የአትሌቲክሱ ቡድን አባላት ስም ዝርዝርን በማውጣት የደረሱበት አልታወቀም ብሎ አሳውቆ ነበር። ይሁን እንጂ ኬፒቲቪ፣ ሪጅስታር-ጋርድ እና ኬዚ የተሰኙ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ጠፍተዋል ተብለው የነበሩ አትሌቶች ተገኝተዋል ሲል የኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ ገልጿል በማለት ዘግበዋል። እንደ የአካባቢው ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ፤ የአትሌቶቹን አድራሻ አግቻለሁ ብሎ ለኦሪገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ ያስታወቀው የኤርትራ ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው። ዘገባዎቹ ይህን ይበሉ እንጂ አሁንም የአምስቱ ኤርትራውያን ስም በኦሬገን ግዛት ፖሊስ ድረ ገጽ ላይ አድራሻቸው በጠፉ ግለሰቦች ዝርዝር ላይ ይገኛል። በግዛቷ ፖሊስ ድረ ገጽ ላይ አድራሻቸው አይታወቅም ተብሎ ስማቸው የተዘረዘሩት ኤርትራውያን በሙሉ ጾታቸው ወንድ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል አንዱ አስልጣኝ ነው። የ44 ዓመቱ አሰልጣኝ በርሄ አስገዶም፣ ፊልሞን አንደ፣ ሃብቶም ሳሙኤል፣ መርሃዊ መብርሃቱ እና የማነ ኃይለሥላሴ በድረ ገጹ ላይ ጠፍተው እየተፈለጉ ካሉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተው ይገኛሉ። አድራሻቸው አይታወቅም ተብሎ ስማቸው ከረዘረዘሩት ኤርትራውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ፤ ማለትም መርሃዊ መብርሃቱ እና ሃብቶም ሳሙኤል ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ኮሎምቢያ ማቅናታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። የ18 ዓመት ወጣት የሆኑት ሁለቱ አትሌቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ትሻምፒዮና ላይ በ3 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ውድድሮች እንደሚሳተፉ በይፋዊ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ሰነድ ላይ ስማቸው ተዘርዝሯል። ጠፍተዋል ከተባሉ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው የማነ ኃይለሥላሴ ደግሞ ለሌላ ውድድር ወደ ስዊትዘርላንድ ማቅናቱን ለቢቢሲ ተናግሯል። ቢቢሲም የአትሌቱ የጉዞ ሰነድና ቪዛን ተመልክቷል። የዳይመንድ ሊግ አካል በሆነው እና በስዊትዘርላንድ ሎውዛን ከተማ በሚደረገው ውድድር ላይ ለመሳትፍ ወደ ስፍራው እንደሚያቀናም አትሌት የማነ ተናግሯል። ቀደም ሲል የኦሬገን ፖሊስ አድራሻቸው ጠፍቷል ካላቸው ልዑካን ቡድን አባላት መካከል የአሰልጣኝ በርሄ አስገዶም እና ፊሊሞን አንደ ያሉበት አልታወቀም። ኤርትራ 10 አትሌቶች በአራት ውድድሮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደተጠናቀቀው 18ኛው ኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ልካ ነበር። በውድድሩ ላይ የማነ ኃይለሥላሴ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል 7ኛ ሆኖ አጠናቋል። መርሃዊ መብራቱ በ5ሺህ ሜትር ማጣሪያውን ሳያልፍ የቀረ ሲሆን ሃብቶም ሳሙኤል በ10 ሺህ ሜትር 17ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ፊልሞን አንደ ደግሞ በማራቶን ለለመወዳደር ተመዝግቦ ነበር። | ከዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን አልተመለሱም ስለተባሉ ኤርትራውያን እስካሁን የሚታወቀው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ኦሪገን ተጉዘው ጠፍተዋል ከተባሉ 5 ኤርትራውያን አትሌቶች መካከል ሦስቱ ለውድድር ወደ ሌሎች አገራት መሄዳቸውን ተነገረ። በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለመሳተፍ ወደ አሜሪካ ከሄዱት የኤርትራ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት መካከል ወደ አገራቸው ያልተመለሱ ስለመኖራቸው ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ተዘግቧል። ቀደም ሲል የኦሪገን ግዛት ፖሊስ የአምስት የአትሌቲክሱ ቡድን አባላት ስም ዝርዝርን በማውጣት የደረሱበት አልታወቀም ብሎ አሳውቆ ነበር። ይሁን እንጂ ኬፒቲቪ፣ ሪጅስታር-ጋርድ እና ኬዚ የተሰኙ የአካባቢው መገናኛ ብዙኃን ጠፍተዋል ተብለው የነበሩ አትሌቶች ተገኝተዋል ሲል የኦሬገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ ገልጿል በማለት ዘግበዋል። እንደ የአካባቢው ሚዲያዎች ዘገባ ከሆነ፤ የአትሌቶቹን አድራሻ አግቻለሁ ብሎ ለኦሪገን ዩኒቨርሲቲ ፖሊስ ያስታወቀው የኤርትራ ብሔራዊ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው። ዘገባዎቹ ይህን ይበሉ እንጂ አሁንም የአምስቱ ኤርትራውያን ስም በኦሬገን ግዛት ፖሊስ ድረ ገጽ ላይ አድራሻቸው በጠፉ ግለሰቦች ዝርዝር ላይ ይገኛል። በግዛቷ ፖሊስ ድረ ገጽ ላይ አድራሻቸው አይታወቅም ተብሎ ስማቸው የተዘረዘሩት ኤርትራውያን በሙሉ ጾታቸው ወንድ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል አንዱ አስልጣኝ ነው። የ44 ዓመቱ አሰልጣኝ በርሄ አስገዶም፣ ፊልሞን አንደ፣ ሃብቶም ሳሙኤል፣ መርሃዊ መብርሃቱ እና የማነ ኃይለሥላሴ በድረ ገጹ ላይ ጠፍተው እየተፈለጉ ካሉ ሰዎች ዝርዝር ውስጥ ተካተው ይገኛሉ። አድራሻቸው አይታወቅም ተብሎ ስማቸው ከረዘረዘሩት ኤርትራውያን አትሌቶች መካከል ሁለቱ፤ ማለትም መርሃዊ መብርሃቱ እና ሃብቶም ሳሙኤል ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ኮሎምቢያ ማቅናታቸውን ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። የ18 ዓመት ወጣት የሆኑት ሁለቱ አትሌቶች ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ትሻምፒዮና ላይ በ3 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር ውድድሮች እንደሚሳተፉ በይፋዊ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ሰነድ ላይ ስማቸው ተዘርዝሯል። ጠፍተዋል ከተባሉ አትሌቶች መካከል አንዱ የሆነው የማነ ኃይለሥላሴ ደግሞ ለሌላ ውድድር ወደ ስዊትዘርላንድ ማቅናቱን ለቢቢሲ ተናግሯል። ቢቢሲም የአትሌቱ የጉዞ ሰነድና ቪዛን ተመልክቷል። የዳይመንድ ሊግ አካል በሆነው እና በስዊትዘርላንድ ሎውዛን ከተማ በሚደረገው ውድድር ላይ ለመሳትፍ ወደ ስፍራው እንደሚያቀናም አትሌት የማነ ተናግሯል። ቀደም ሲል የኦሬገን ፖሊስ አድራሻቸው ጠፍቷል ካላቸው ልዑካን ቡድን አባላት መካከል የአሰልጣኝ በርሄ አስገዶም እና ፊሊሞን አንደ ያሉበት አልታወቀም። ኤርትራ 10 አትሌቶች በአራት ውድድሮች ተሳታፊ እንዲሆኑ ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ላይ ወደተጠናቀቀው 18ኛው ኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ልካ ነበር። በውድድሩ ላይ የማነ ኃይለሥላሴ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል 7ኛ ሆኖ አጠናቋል። መርሃዊ መብራቱ በ5ሺህ ሜትር ማጣሪያውን ሳያልፍ የቀረ ሲሆን ሃብቶም ሳሙኤል በ10 ሺህ ሜትር 17ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ፊልሞን አንደ ደግሞ በማራቶን ለለመወዳደር ተመዝግቦ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/articles/c9rq4l3yz36o |
3politics
| 'ምዕራባዊያን ሩሲያን እንዳያስቆጡ እመክራለሁ' በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር | በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ምዕራባዊያን ሩሲያን እንዳያስቆጡ አሳሰቡ፡፡ አምባሳደሩ አሁን የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ የዲፕሎማሲ ዕድል እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ሁኔታዎችን በጥንቃቄና በብስለት ዲፕሎማሲን ተጠቅሞ ማርገብ እንጂ ሩሲያን ማስቆጣት አደጋው የከፋ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ ከተቆጣች ደግሞ የዲፕሎማሲ ሐሳቧን እርግፍ አድርጋ ልትተወው ትችላለችም ብለዋል፡፡ ባለፉት ቀናት በሩሲያና በምዕራብ አገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ሰኞና ማክሰኞ ዕለት ኪያቭና ሞስኮ በመመላለስ ከዚያም ደግሞ ወደ በርሊን በመብረር ሁኔታዎችን ለማርገብ ሲተጉ ሰንብተዋል፡፡ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር 6 ሰዓታት የወሰደ ንግግርና ምክክር በማድረግም ወረራ እንደማይደረግ ፑቲን ቃል ገብተውልኛል ሲሉ ተስፋን ለዓለም ማብሰራቸው አይዘነጋም፡፡ አሜሪካ በበኩሏ ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ድንበር ላይ 100ሺህ ወታደር ማሰለፏን በመጥቀስ ወረራው በማንኛውም ቅጽበት ሊደረግ ይችላል ስትል ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣናቷም ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር ከሚያስፈልጋቸው የወታደር ኃይል 70 በመቶው በድንበር ሰፍሮ እንደሚገኝ ሲናገሩ ነበር፡፡ የደኅንነት ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሩሲያ ወረራውን ተአማኒና ቅቡል ለማድረግ ሐሰተኛ ፊልም እየቀረጸች እንደሆነ መረጃ እንደደረሳቸው ለዓለም ይፋ ያደረጉት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ጆ ባይደን በበኩላቸው ሰኞ ዕለት አዲሱን የጀርመን መራሒ መንግሥት በዋሺንግተን ተቀብለው ያስተናገዱ ሲሆን ሩሲያ ወረራ ከቃጣት ምን ዓይነት ቅጣቶች ሊጣሉባት እንደሚችሉ መክረዋል፡፡ በተለይም ሩሲያን ክፉኛ ያሽመደምዳታል ብለው የገመቱትን የኖርዲክስ ስትሪም2 የጋዝ ማስተላለፊያ ለመዝጋት እንደማያመነቱ ሁለቱ መሪዎች ቃል ሰጥተው ነበር፡፡ ሩሲያ የዛሬ 8 ዓመት ግድም ነበር የዩክሬንን ደቡባዊ ክፍል፣ የክሬሚያ ባሕረ ገብን በወረራ የያዘቸው፡፡ ከሰኞ ወዲህ የዲፕሎማሲ ጥረቱ ተስፋ ሰጪ እየኾነ የመጣ ቢመስልም ዛሬ ሐሙስ ሩስያ ከሰሜናዊት ጎረቤቷ ቤላሩስ ጋር ወታደራዊ ልምምድ እንደምትጀምር አስታውቃለች፡፡ በዚህ ልምምድ 30ሺህ የሚኾኑ ወታደሮቿ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡ ቤላሩስ የፑቲን ቀኝ እጅ ናት፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ግን የሩሲያ ወታደሮች ከቤላሩስ ጋር ልምምድ ካደረጉ በኋላ ወደ አገራቸው ቋሚ የጦር ሰፈር እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ ይህ ወታደራዊ ልምምድ ሁኔታዎችን ለማርገብ የሚደረግን ጥረት የማንኳሰስ ያህል ነው ስትል ተችተዋለች፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀመሩት የዲፕሎማሲ ጥረት ፍሬ ማፍራት እንደሚጀምር እየተጠበቀ ሲሆን በተለይ የሚኒስክ ስምምነት አሁን ለተፈጠረው ውጥረት እንደ መፍትሄ ሊወሰድ እንደሚችል ፍንጮች አሉ፡፡ ይህ ስምምነት በ2014 ሩሲያ ክሪሚያን ከተቆጣጠረች በኋላ የተደረሰ አዲስ ስምምነት ሲሆን የደቡባዊ ዩክሬን አካባቢ በሩሲያ በሚደገፉ አማጺያን እንዲተዳደር ያደረገ ስምምነት ነው፡፡ ይህን ስምምነት ፈረንሳይና ጀርመን ያሸማገሉትና የፈረሙበት ስምምነት ነው፡፡ የአሁኑ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ይህ ስምምነት ለሩሲያ ያደላ ነበር ሲሉ እምብዛምም አይቀበሉትም፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደር ቺዞፍ የዲፕሎማሲ ጥረቱ እንዳለ ሆኖ ሩሲያ ግን ለጊዜው ወታደሮቿን ከድንበር ፈቀቅ የማድረግ ፍላጎት እንደሌላት አረጋግጠዋል፡፡ "ሁሉም ሚዲያ የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ድንበር ስለመጠጋታቸው ያወራል፡፡ ወደ ሩሲያ ፊታቸውን ስላዞሩ የዩክሬን ወታደሮችስ ለምን አይወራም?" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ሩሲያ ለምዕራብ አገራት ሰላም እንዲሰፍን በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠች ሲሆን ከነዚህ መሀል ዋነኞቹ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወደ ምሥራቅ አውሮጳ መስፋፋቱን እንዲያቆም፣ በተለይ ደግሞ በፍጹም ዩክሬንን በአባልነት እንዳይቀበል የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ይህን የሩሲያን ጥያቄ ምዕራብ አገራት ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆየታ የነበራቸው በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ይህ ጥያቄ ቁልፍ ጉዳይ ነው፤ ሩሲያ በኔቶ ላይ ያላትን ጥያቄ ከማንሳት አትቦዝንም ብለዋል፡፡ | 'ምዕራባዊያን ሩሲያን እንዳያስቆጡ እመክራለሁ' በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ምዕራባዊያን ሩሲያን እንዳያስቆጡ አሳሰቡ፡፡ አምባሳደሩ አሁን የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ የዲፕሎማሲ ዕድል እንዳለም ጠቁመዋል፡፡ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት ሁኔታዎችን በጥንቃቄና በብስለት ዲፕሎማሲን ተጠቅሞ ማርገብ እንጂ ሩሲያን ማስቆጣት አደጋው የከፋ እንደሚሆን አስጠንቅቀዋል። ሩሲያ ከተቆጣች ደግሞ የዲፕሎማሲ ሐሳቧን እርግፍ አድርጋ ልትተወው ትችላለችም ብለዋል፡፡ ባለፉት ቀናት በሩሲያና በምዕራብ አገራት መካከል ከፍተኛ ውጥረት እንደነበረ አይዘነጋም፡፡ የፈረንሳዩ ኢማኑኤል ማክሮን ሰኞና ማክሰኞ ዕለት ኪያቭና ሞስኮ በመመላለስ ከዚያም ደግሞ ወደ በርሊን በመብረር ሁኔታዎችን ለማርገብ ሲተጉ ሰንብተዋል፡፡ ከቭላድሚር ፑቲን ጋር 6 ሰዓታት የወሰደ ንግግርና ምክክር በማድረግም ወረራ እንደማይደረግ ፑቲን ቃል ገብተውልኛል ሲሉ ተስፋን ለዓለም ማብሰራቸው አይዘነጋም፡፡ አሜሪካ በበኩሏ ሩሲያ ዩክሬንን ለመውረር ድንበር ላይ 100ሺህ ወታደር ማሰለፏን በመጥቀስ ወረራው በማንኛውም ቅጽበት ሊደረግ ይችላል ስትል ማስጠንቀቋ ይታወሳል፡፡ ባለሥልጣናቷም ፑቲን ዩክሬንን ለመውረር ከሚያስፈልጋቸው የወታደር ኃይል 70 በመቶው በድንበር ሰፍሮ እንደሚገኝ ሲናገሩ ነበር፡፡ የደኅንነት ባለሥልጣናት በበኩላቸው ሩሲያ ወረራውን ተአማኒና ቅቡል ለማድረግ ሐሰተኛ ፊልም እየቀረጸች እንደሆነ መረጃ እንደደረሳቸው ለዓለም ይፋ ያደረጉት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ጆ ባይደን በበኩላቸው ሰኞ ዕለት አዲሱን የጀርመን መራሒ መንግሥት በዋሺንግተን ተቀብለው ያስተናገዱ ሲሆን ሩሲያ ወረራ ከቃጣት ምን ዓይነት ቅጣቶች ሊጣሉባት እንደሚችሉ መክረዋል፡፡ በተለይም ሩሲያን ክፉኛ ያሽመደምዳታል ብለው የገመቱትን የኖርዲክስ ስትሪም2 የጋዝ ማስተላለፊያ ለመዝጋት እንደማያመነቱ ሁለቱ መሪዎች ቃል ሰጥተው ነበር፡፡ ሩሲያ የዛሬ 8 ዓመት ግድም ነበር የዩክሬንን ደቡባዊ ክፍል፣ የክሬሚያ ባሕረ ገብን በወረራ የያዘቸው፡፡ ከሰኞ ወዲህ የዲፕሎማሲ ጥረቱ ተስፋ ሰጪ እየኾነ የመጣ ቢመስልም ዛሬ ሐሙስ ሩስያ ከሰሜናዊት ጎረቤቷ ቤላሩስ ጋር ወታደራዊ ልምምድ እንደምትጀምር አስታውቃለች፡፡ በዚህ ልምምድ 30ሺህ የሚኾኑ ወታደሮቿ እንደሚሳተፉ ተነግሯል፡፡ ቤላሩስ የፑቲን ቀኝ እጅ ናት፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ቭላድሚር ቺዞፍ ግን የሩሲያ ወታደሮች ከቤላሩስ ጋር ልምምድ ካደረጉ በኋላ ወደ አገራቸው ቋሚ የጦር ሰፈር እንደሚመለሱ ተናግረዋል፡፡ አሜሪካ ይህ ወታደራዊ ልምምድ ሁኔታዎችን ለማርገብ የሚደረግን ጥረት የማንኳሰስ ያህል ነው ስትል ተችተዋለች፡፡ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የጀመሩት የዲፕሎማሲ ጥረት ፍሬ ማፍራት እንደሚጀምር እየተጠበቀ ሲሆን በተለይ የሚኒስክ ስምምነት አሁን ለተፈጠረው ውጥረት እንደ መፍትሄ ሊወሰድ እንደሚችል ፍንጮች አሉ፡፡ ይህ ስምምነት በ2014 ሩሲያ ክሪሚያን ከተቆጣጠረች በኋላ የተደረሰ አዲስ ስምምነት ሲሆን የደቡባዊ ዩክሬን አካባቢ በሩሲያ በሚደገፉ አማጺያን እንዲተዳደር ያደረገ ስምምነት ነው፡፡ ይህን ስምምነት ፈረንሳይና ጀርመን ያሸማገሉትና የፈረሙበት ስምምነት ነው፡፡ የአሁኑ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ይህ ስምምነት ለሩሲያ ያደላ ነበር ሲሉ እምብዛምም አይቀበሉትም፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉት አምባሳደር ቺዞፍ የዲፕሎማሲ ጥረቱ እንዳለ ሆኖ ሩሲያ ግን ለጊዜው ወታደሮቿን ከድንበር ፈቀቅ የማድረግ ፍላጎት እንደሌላት አረጋግጠዋል፡፡ "ሁሉም ሚዲያ የሩሲያ ወታደሮች ወደ ዩክሬን ድንበር ስለመጠጋታቸው ያወራል፡፡ ወደ ሩሲያ ፊታቸውን ስላዞሩ የዩክሬን ወታደሮችስ ለምን አይወራም?" ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ሩሲያ ለምዕራብ አገራት ሰላም እንዲሰፍን በርካታ ቅድመ ሁኔታዎችን ያስቀመጠች ሲሆን ከነዚህ መሀል ዋነኞቹ የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ወደ ምሥራቅ አውሮጳ መስፋፋቱን እንዲያቆም፣ በተለይ ደግሞ በፍጹም ዩክሬንን በአባልነት እንዳይቀበል የሚሉ ይገኙበታል፡፡ ይህን የሩሲያን ጥያቄ ምዕራብ አገራት ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡ ከቢቢሲ ጋር ቆየታ የነበራቸው በአውሮጳ የሩሲያ አምባሳደር ይህ ጥያቄ ቁልፍ ጉዳይ ነው፤ ሩሲያ በኔቶ ላይ ያላትን ጥያቄ ከማንሳት አትቦዝንም ብለዋል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-60329209 |
3politics
| የሩሲያ እና ዩክሬን ፍጥጫ በመባባሱ የነዳጅ ዋጋ እያሻቀበ ነው | የዩክሬን እና ሩሲያ ቀውስ በዓለም ዙሪያ የነዳጅ አቅርቦትን ያደናቅፋል በሚል ስጋት የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ነው። የዓለም አቀፍ የገበያ መለኪያ በሆነው የብሬንት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ዛሬ ማክሰኞ በበርሜል 97.76 ዶላር ደርሷል። ይህም በሰባት ዓመት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን በአማፅያን ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ሁለት ክልሎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ወታደሮቿ ወደ አካባቢዎቹ እንዲገቡ ፈቅዳለች። የእስያ የአክሲዮን ገበያዎች ዝቅተኛ ሲሆኑ የአሜሪካ እና የአውሮፓ የአክሲዮን ሽያጮች ለኪሳራ ተጋልጠዋል። ከሳዑዲ አረቢያ ቀጥላ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ በሆነችው ሩሲያ ላይ ዩናይትድ ኪንግደም እና በርካታ የምዕራባውያን አገሮች ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ እየዛቱ ነው። ሩሲያ በተፈጥሮ ጋዝን ምርት ደግሞ ቀዳሚ ናት። ሩሲያ ወታደሮቿ ራሳቸውን የዶኔስክ እና ሉሃንስክ ሕዝቦች ሪፐብሊኮች ብለው ባወጁት አካባቢዎች "የሠላም ማስከበር" እንደሚሰማሩ አስታውቃለች። አሜሪካ ደግሞ የሠላም አስከባሪ መባላቸውን "ከንቱ" ስትል ገልጻ፣ ሩሲያ ለጦርነት ሰበብ እየፈጠረች ነው ስትል ተናግራለች። የማኑላይፍ ኢንቬስትሜንት ማኔጅመንት ባልደረባ የሆኑት ሱ ትሪን የዩክሬን እና የሩሲያ ቀውስ በነዳጅ ዋጋ ላይ "ከፍተኛ እንድምታ" አለው ብለዋል። ሩሲያ አነስተኛ ድፍድፍ ወይም የተፈጥሮ ጋዝ እንድታቀርብ የሚያስገድድ ማዕቀብ "በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ይኖረዋል" ሲሉ አክለዋል። በፊደልቲ ኢንተርናሽናል የኢንቨስትመንት ዳይሬክተር የሆኑት ማይኪ ከሪ በበኩላቸው በዩክሬን ቀውስ፣ በአሜሪካ ያለው ቀዝቃዛ ክረምት እና በዓለም ዙሪያ በነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦቶች ላይ ባለው የኢንቨስትመንት እጥረት ምክንያት ነዳጅ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሊወጣ ይችላል ብለዋል። "ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ ከሚውለው 10 በርሜል ነዳጅ ዘይት አንዱን ታቀርባለች። በመሆኑም በነዳጅ ዋጋ ላይ ዋና ተዋናይ በመሆኗ የነዳጅ ተጠቃሚዎችን ይጎዳል" ይላሉ። አሜሪካ እና አውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ ጥለውት ለዓመታት የዘለቁት ማዕቀቦች በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድረዋል። በገንዘብ ተቋማት፣ በቴክኖሎጂዎች እና በግለሰቦች ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች "ሊጠናከሩ" እንደሚችሉ ከሪ ተናግረዋል። | የሩሲያ እና ዩክሬን ፍጥጫ በመባባሱ የነዳጅ ዋጋ እያሻቀበ ነው የዩክሬን እና ሩሲያ ቀውስ በዓለም ዙሪያ የነዳጅ አቅርቦትን ያደናቅፋል በሚል ስጋት የነዳጅ ዋጋ እየጨመረ ነው። የዓለም አቀፍ የገበያ መለኪያ በሆነው የብሬንት የድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ዛሬ ማክሰኞ በበርሜል 97.76 ዶላር ደርሷል። ይህም በሰባት ዓመት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል። ሩሲያ በምሥራቅ ዩክሬን በአማፅያን ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ሁለት ክልሎች እውቅና ከመስጠት ባለፈ ወታደሮቿ ወደ አካባቢዎቹ እንዲገቡ ፈቅዳለች። የእስያ የአክሲዮን ገበያዎች ዝቅተኛ ሲሆኑ የአሜሪካ እና የአውሮፓ የአክሲዮን ሽያጮች ለኪሳራ ተጋልጠዋል። ከሳዑዲ አረቢያ ቀጥላ ሁለተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ በሆነችው ሩሲያ ላይ ዩናይትድ ኪንግደም እና በርካታ የምዕራባውያን አገሮች ማዕቀብ ሊጥሉ እንደሚችሉ እየዛቱ ነው። ሩሲያ በተፈጥሮ ጋዝን ምርት ደግሞ ቀዳሚ ናት። ሩሲያ ወታደሮቿ ራሳቸውን የዶኔስክ እና ሉሃንስክ ሕዝቦች ሪፐብሊኮች ብለው ባወጁት አካባቢዎች "የሠላም ማስከበር" እንደሚሰማሩ አስታውቃለች። አሜሪካ ደግሞ የሠላም አስከባሪ መባላቸውን "ከንቱ" ስትል ገልጻ፣ ሩሲያ ለጦርነት ሰበብ እየፈጠረች ነው ስትል ተናግራለች። የማኑላይፍ ኢንቬስትሜንት ማኔጅመንት ባልደረባ የሆኑት ሱ ትሪን የዩክሬን እና የሩሲያ ቀውስ በነዳጅ ዋጋ ላይ "ከፍተኛ እንድምታ" አለው ብለዋል። ሩሲያ አነስተኛ ድፍድፍ ወይም የተፈጥሮ ጋዝ እንድታቀርብ የሚያስገድድ ማዕቀብ "በዓለም ኢኮኖሚ ላይ ጉልህ ተጽዕኖ ይኖረዋል" ሲሉ አክለዋል። በፊደልቲ ኢንተርናሽናል የኢንቨስትመንት ዳይሬክተር የሆኑት ማይኪ ከሪ በበኩላቸው በዩክሬን ቀውስ፣ በአሜሪካ ያለው ቀዝቃዛ ክረምት እና በዓለም ዙሪያ በነዳጅ እና ጋዝ አቅርቦቶች ላይ ባለው የኢንቨስትመንት እጥረት ምክንያት ነዳጅ በበርሜል ከ100 ዶላር በላይ ሊወጣ ይችላል ብለዋል። "ሩሲያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥቅም ላይ ከሚውለው 10 በርሜል ነዳጅ ዘይት አንዱን ታቀርባለች። በመሆኑም በነዳጅ ዋጋ ላይ ዋና ተዋናይ በመሆኗ የነዳጅ ተጠቃሚዎችን ይጎዳል" ይላሉ። አሜሪካ እና አውሮፓ ሕብረት ሩሲያ ላይ ጥለውት ለዓመታት የዘለቁት ማዕቀቦች በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ትልቅ ተጽዕኖ አሳድረዋል። በገንዘብ ተቋማት፣ በቴክኖሎጂዎች እና በግለሰቦች ላይ የሚጣሉ ማዕቀቦች "ሊጠናከሩ" እንደሚችሉ ከሪ ተናግረዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60476512 |
0business
| የወደፊቱ መገበያያ ይሆናል የሚባለው ቢትኮይን ምንድን ነው? | በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አገራት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብን [ቢትኮይን] ብዙ አገራት በከፊልና ሙሉ በሙሉ እየተጠቀሙበት ይገኛል። አንዳንዶቹ ምናልባትም ቢትኮይን የወደፊቱ የመገበያያ አማራጭ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ለመሆኑ ቢትኮይን ምንድን ነው? | የወደፊቱ መገበያያ ይሆናል የሚባለው ቢትኮይን ምንድን ነው? በአሁኑ ወቅት በተለያዩ አገራት የዲጂታል መገበያያ ገንዘብን [ቢትኮይን] ብዙ አገራት በከፊልና ሙሉ በሙሉ እየተጠቀሙበት ይገኛል። አንዳንዶቹ ምናልባትም ቢትኮይን የወደፊቱ የመገበያያ አማራጭ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ለመሆኑ ቢትኮይን ምንድን ነው? | https://www.bbc.com/amharic/news-59459630 |
3politics
| የአሜሪካ ማዕቀብ በቀጣናው ስትራቴጂያዊ ለውጥን ያስከትል ይሆን? | ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ግንቦት 15/2013 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ካለው ግጭት ጋር እየተፈፀሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ጥቃቶች አገራቸው በተደጋጋሚ ስጋቷን ብታሰማም ትርጉም ያለው ምላሽ ባለመኖሩ አገራቸው የጉዞ እቀባ መጣሏን አስታውቀዋል። በዚህም በኢትዮጵያና በኤርትራ የቀድሞ እና የአሁን ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ እና ደኅንነት ኃላፊዎች እንዲሁም የአማራ ክልል መደበኛና ኢ-መደበኛ የጸጥታ አባላትና ግለሰቦች፣ ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ባደናቀፉ የህወሓት አባላት ላይ የቪዛ እቀባ አሜሪካ ጥላለች። ይህ በግጭቱ ላይ እጃቸው ያለበት ወይም ተባባሪ የሆኑትን የሚመለከት ሲሆን እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር እቀባው ተግባራዊ ሊሆንባቸው እንደሚችል የወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ከጉዞ እቀባው በተጨማሪ አሜሪካ የምታደርገውን የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት እገዛ እንዲቋረጡና ግጭቱ ካልቆመና መሻሻሎች ካልታዩ፤ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደምትወስድም አስጠንቅቃለች። ሌሎችም አገራት የአሜሪካን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አድርጋለች። ይህ የማዕቀብ ሁኔታ አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው ያልተገባ ጫና አካል ነው በሚልም ኢትዮጵያን አሳዝኗል። ምንም እንኳን አሜሪካ ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት ትርጉም ያለው እርምጃ ሊወሰድ አልተቻለም ብትልም ኢትዮጵያ በበኩሏ ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር ገንቢ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ እየሰራች ነበር ብላለች። ኢትዮጵያ በትግራይ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በጥምረት ሆነው ለመመርመር እየሰሩ መሆናቸውንና ተጠያቂ የሚሆኑበትንም ስራ እያከናወነች እንደሆነ አስታውቃለች። እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ በአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ በመጥቀስ ቀውሱን ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች። አሜሪካ ያሳለፈቻቸው እርምጃዎች የሁለቱንም አገራት የዘመናት ግንኙነት የሚጎዳ ነው ትላለች ኢትዮጵያ። የአሜሪካንን እርምጃዎች በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነት ነው የምትለው ኢትዮጵያ፤ አሜሪካ በዚሁ የምትቀጥል ከሆነ ግንኙነታቸውን የምታጤነው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የማዕቀቡ አንድምታ፤ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ይሆን? ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ውስጥ እየተደረጉ ስላሉ እርምጃዎች ተመሳሳይ አረዳድ የላቸውም። በቀጣናው ከአልሻባብ መግነን ጋር ተያይዞ ሸብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል የአሜሪካ ቀኝ እጅ የነበረችው ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ባለው ቀውስ ምክንያት ግንኙነታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ለአስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአሜሪካ የደኅንነት አጋር ነበረች የሚሉት የአሜሪካ የቀድሞ ዲፕሎማትና በአትላንቲክ ካውንስል የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት ካሜሮን ሀድሰን ናቸው። ለረጅም ጊዜያት ፖለቲካዊ ድርድሮችንና ሽምግልናዎችን በዋነኝነት በመምራት፣ በሰላም በማስከበር ስምሪት እንዲሁም በአጠቃላይ መረጋጋት በሌለባቸው የቀጣናው አካባቢዎች መረጋጋትን በማምጣት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና መጫወቷን ካሜሮን ይናገራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ራሷ መረጋጋት የሌለባት አገር ናት የሚሉት ዲፕሎማቱ፤ አሜሪካም ይሄንን ለመቆጣጠር የራሷን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባት ይላሉ። በተለይም ከማዕቀቡ ጋር ተያይዞ በሁለትዮሽ ግንኙነቱ ላይ አዲስ የሆነ ግንኙነትን የሚያሳይ ነው፤ እንዲሁም አሜሪካ ስትራቴጂያዊ ለውጥን ማድረጓን ጠቋሚ ነው ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም ዳይሬክተርና መምህር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው በዲፕሎማቱ ሃሳብ አይስማሙም፤ የአሁኑን ማዕቀብ በአገራቱ መካከል መሰረታዊ የሚባል የርዕዮተ ዓለም ልዩነት የሌለበት ስለሆነ "ጊዜያዊ ነው" በማለት። ኢትዮጵያ ካላት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻር ስትራቴጂክ ቦታ ላይ ከመሆኗም ጋር ተያይዞ አሁንም በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በቀጣናው ካሉ አገራት ከኢትዮጵያ የተሻለ ወዳጅ ለአሜሪካ ማግኘት ያስቸግራል ብለው እንደሚያምኑ ምሁሩ ይናገራሉ። ለዚህም እንደ ዋቢ የሚጠቅሱት የሶማሊያ በአልሻበብ ቁጥጥር ስር መውደቅ፣ የሶማሌላንድና የፑንትላንድ ዕውቅና አለማግኘት፣ በኬንያና በሶማሊያ መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት፣ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ትርምስ ውስጥ መሆኑ ኢትዮጵያ አሁንም ለቀጣናው የተሻለች የአሜሪካ አጋር ናት እንዲሉ አስችሏቸዋል። በተለይም አሜሪካ የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት ድጋፍ እቀባ ማድረጓን ተከትሎ አገራቱ ሽብርተኝነትን በጋራ እንዋጋለን የሚሉትን ፕሮጀክት እንዲቆም አያደርገውም ወይ? ብለው በርካቶች ጥያቄ ያነሳሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ በኩልም በሰጠው መግለጫ እርምጃው ቀጣናውን ችግር ላይ የሚጥል እንዲሁም ኢትዮጵያ በፀረ-አልሻባብ የሽብር መከላከል እና በሰላም ጥበቃ ላይ ያላትን ሚና በጉልህ የሚጎዳ ሲሉ ተችተውታል። ዶክተር ዮናስም በተመሳሳይ መልኩ "ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ለአሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ቀኝ እጅ ነበረች አሁንም ናት" ብለው ያምናሉ። የዲፕሎማቱ ካሜሮን ሀድሰን እይታ ግን ከውጭ ጉዳይ መግለጫም ሆነ ከምሁሩ አስተያየት ለየት ይላል። አገሪቱ በአሁኑ ወቅት በውስጧ ካለው ቀውስ የተነሳ ለዓመታት የሚጠበቅባትን በቀጣናው የተጫወተችውን ሚና በአሁኑ ወቅት መጫወት አትችልም ይላሉ። "ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሕዝቡ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማካሄድ አዳዲስ የደኅንነት አጋሮችን እንደነ ሩሲያ፣ ቻይናና የባሕረ ሰላጤው አገራትን አገራትን አጋርነትን እየተመለከተች ነው። ሁኔታዎች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ እነዚህን የመሳሰሉ የደኅንነት ግንኙነቶች በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የምዕራባውያን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ያስከትላል" ይላሉ። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከፀረ-ሽብር ጋር በተገናኘ ለኢትዮጵያ ስልጠናዎችን፣ እንዲሁም የደኅንነት መረጃዎችን በመለዋወጥ ይሰሩ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የቀድሞው የሲአይኤ አባል የነበሩት ዲፕሎማት ሀድሰን እንደሚሉት አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መሳሪያም አቀባይ ነበረች። በቅርቡ ያወጣችው የጉዞ እቀባና 'ዲፌንስ ትሬድ ኮንትሮል ፖሊሲ' ያለችውን ተግባራዊ እንደምታደርግም አሜሪካ አስታውቃለች። ይህ ፖሊሲ ምንን ያካትታል? ለዲፕሎማቱ ቢቢሲ ያቀረበላቸው ጥያቄ ነው። እሳቸውም በምላሹ የትኛውም እርምጃ በሕዝብ ላይ ጥፋት የሚፈፀምበት የቴክኖሎጂ ግብአት ላይ ከሚደረግ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይናገራሉ። ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ይህ ፖሊሲ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን ጨምሮ፣ ሶፍትዌሮች፣ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቁሳቁሶችና ረቀቅ ያሉ ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ያካትታል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተለገሱ በአሜሪካ የተሰሩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መጠገን አስፈልጎ መለዋወጫ ቢያስፈልግ በዚህ እቀባ መሰረት ኢትዮጵያ ይሄንን ማካሄድ አትችልም ይላሉ። የሁለቱ አገራት ግንኙነት መበላሸት ኢትዮጵያና አሜሪካ ከመቶ ዓመታት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በሊግ ኦፍ ኔሽንም ሆነ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምስረታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚሉት ዶክተር ዮናስ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት ከአሜሪካ ጋር ትስስር አላቸው ይላሉ። የሁለትዮሽ አጋርነታቸውም ነፀብራቅ የሚባሉት በትምህርት ተቋማት እንዲሁም የአሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበራትን ሚና እንደ ምሳሌ በማንሳት አሜሪካ ለዘመናት የኢትዮጵያ የልማት አጋር ሆና ቀጥላለች ይላሉ። ለዚያም ነው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማዕቀቡን የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥንና የመቶ ሃያ ዓመታቱንም ግንኙነት "በዜሮ ያባዛው" ያለው። በአገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ዳራ በምንመለከትበት ወቅት ሻክሮ የነበረው ደርግ ኢትዮጵያን ያስተዳድር በነበረ ወቅት ነበር። ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን ግንኙነታቸው ጠንካራ የሚባል እንደሆነ ይነገራል። ዲፕሎማቱም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ ወስዳ አታውቅም ይላሉ። በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የተወሰነ ውጥረት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ በአሜሪካ የቀረበው የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በሁለቱ አገራት መጣሉን ተከትሎ እንደሆነ ያወሳሉ። አሜሪካ በማንኛውም በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን አጋርነት አልተወችም የሚሉት ዶክተር ዮናስ ይህ እቀባ "ማስደንገጥ የለበትም" ይላሉ። ለምሳሌ ያህልም ኢህአዴግ በ2002 ምርጫ መቶ በመቶ አሸንፌያለሁ ብሎ የፓርላማ ወንበሩን ከተቆጣጠረ በኋላ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው ብለው ማፅደቃቸውን በማውሳት ነው። "ይህ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ ነበር" ይላሉ። በአፍሪካ ውስጥ "ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፖለቲካ መዲና ናት" የሚሉት ዶክተር ዮናስ "ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት እቀባም አሜሪካንም ሆነ ኢትዮጵያን ይጎዳል" ይላሉ። በተለይም ኢትዮጵያ የራሷን አፀፋዊ እርምጃዎች የምትወስድ ከሆነ ሁኔታዎች ሊጋጋሉና ቀጣናው የአሸባሪዎች መፈንጫ ሊሆን እንደሚችል ምሁራዊ እይታቸውን ይሰጣሉ። በተለይም በቀጣናው የደኅንነት ስጋት ቢፈጠር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድም ሆነ ወደ ሌሎች አካካቢዎች አንደሚዛመትና ጉዳቱም ሰፋ ያለ መልክ ሊኖረው እንደሚችል በአፅንኦት ያስረዳሉ። "በነገራችን ላይ የደኅንነትና የሰላም ጥናት ድንበር አይከፋፍልም። አንድ አካባቢ ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከተጎዳ መላው ዓለም ነው የሚጎዳው። ለምሳሌ ከዓመታት በፊት በአሜሪካ ላይ ተፈጸመው የመስከረም 11ዱን ጥቃት ብንወስድ፤ ባደጉም ይሁን ባላደጉ አገራት ውስጥ ከፍተኛ ትርምስ ነው የፈጠረው" የሚሉት ዶክተር ዮናስ የአንድ አገር ደኅንነት ወይም ሰላም የሚባል የለም በማለት የአገራቱ እጣ ፈንታ በከፍተኛ ሁኔታ የተሳሰረ እንደሆነ ይተነትናሉ። ዲፕሎማቱም በበኩላቸው ማዕቀቡ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር በነበራትን ግንኙነት ላይ ስትራቴጂያዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠቁመው፤ ይህም ሁኔታ አሜሪካ በቀጣናው ላይ ያላትን ስትራቴጂያዊ ፍላጎቶችም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚያደርስ አልደበቁም። በተለይም ኢትዮጵያ በውስጧ ሰላም ካልሰፈነባትና አጋርነቷ ከቀረ አሜሪካ በቀይ ባሕር ዙሪያ ደኅንነትንም ሆነ መረጋጋት ለማምጣትም እንዲሁም ተፅእኖ ለመፍጠር ፈተና እንደሚሆንባት ያስረዳሉ። የአሜሪካ ስጋት ምንድን ነው? በትግራይ ካለው ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ጥቃትና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ችግር በተጨማሪ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል እንዲሁም በአገሪቱ ላይ የተጋረጡት የሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ አንድነትና የግዛት ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል ይላል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎች እርዳታ እንዳይደርስ እክል መፍጠር፣ በክልሉ ውስጥ ያሉ ግድያዎች፣ በአስገዳጅ ሁኔታ መፈናቀል፣ መዋቅራዊ የሆነ ወሲባዊ ጥቃት፣ ሆስፒታሎችና የህክምና ተቋማት መውደም አሜሪካ እንዳሳሰባት ትገልጻለች። እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ቀጥለዋል የምትለው አሜሪካ ተደጋጋሚ ጉትጎታዎችን ባደርግም ለቀውሱ ፖለቲካዊም ሆነ ሰላማዊ መፍትሄ መምጣት አልተቻለም ትላለች። በዚህም ምክንያት የወሰደችው እርምጃ አስፈላጊ ነው ትላለች። ዶክተር ዮናስ በበኩላቸው ሁለቱንም አገራት ይጎዳል ያሉት ይህን ማዕቀብ በተሳሳተና በደንብ ባልተጠና መረጃ ላይ ተመስርቶ የተወሰደ ነው ይላሉ። ምሁሩ በአውሮፓውያኑ 2003 አሜሪካ ኢራቅን መውረሯን እንደ ምሳሌ በማንሳትም በወቅቱ አሜሪካ ምክንያት ያደረገችው ኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አላት የበሚል ነበር። ነገር ግን መሳሪያው አለመኖሩ የታወቀው ኢራቅ ከፈራረሰችና ከዘገዬ በኋላ መሆኑን ታሪክን ያጣቅሳሉ። በተመሳሳይም አፍጋኒስታንን በማንሳት ከቀደመ ስህተት መማርና ማገናዘብ እንደሚገባ ያወሳሉ። "በስሜት የሚደረጉ ነገሮች የሚያሳዝኑ ይሆናሉ። በዚህ ትብብር ወቅት ኢትዮጵያን በግድ አንበረክካታለሁ ብሎ ማሰቡ በተለይም በጣም ካደጉ አገራት የሚጠበቅም አልነበረም። በተለይም የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ከመሆኑ አንፃር። ይሄንን በድጋሚ ያጤኑታል ብዬ አስባለሁ" ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግሥትም በተለይም አሜሪካ ከምታወጣቸው መግለጫዎች ጋር በተያያዘ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተው ጫና ለመሞከር የሚሞክሩ መንግሥታት ተቀባይነት አይኖረውም ሲል መደመጡ ይታወሳል፟። ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ ክልል ቀውስና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ምዕራባውያን እንዲሁም አሜሪካ ከፍተኛ ጫና እያሳደረች ነው ያሉ ተቃውሟቸውን በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች አገራት በበይነ መረብ አሰምተዋል። የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የሕግ እና የውሃ ጉዳይ የቴክኒክ ባለሞያዎች በዋሽንግተን ዲሲ ሲደራደሩ በነበረበት ወቅት፤ በዓመታት የተራዘመ ድርቅ እንዲሁም በተራዘመ ዓመታት አነስተኛ የውሃ ፍሰት ላይም መሰረታዊ መግባባት ተደርሷል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ያለምንም ውጤት መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረውንም ድርድር ያቋረጠችበት ምክንያት በግብጽ ፍላጎት ታዛቢ እንዲሆኑ የገቡት አሜሪካና የዓለም ባንክ ለግብጽ ከመወገን አልፈው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ላይ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል በማለት ኢትዮጵያ መውቀሷ የሚታወስ ነው። አሜሪካ፣ የዓለም ባንክ ከግብጽ ጎን ቆመው ነበር በተባለው በዚህ ድርድር ላይ ከመጀመሪያው ሙሌት በኋላ ኢትዮጵያ ለምትጠቀመው ውሃ ለግብጽ የተጠራቀመ የውሃ ጉድለት ማካካሻ እንድትሰጥ የሚያስገድድ እንደሆነም ተገልጾ ነበር። ከዚህም ጋር በተያያዘ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሕዳሴ ግድቡ ድርድር ምክንያት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደማይሰጥ ገልፀው ነበር። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአሜሪካ የአሁኑ ማዕቀብ የትግራይ ግጭት ብቻ አይደለም የሕዳሴ ግድብም ነው የሚሉ አልታጡም። ነገር ግን የአትላንቲክ ካውንስሉ ካሜሩን ሀድሰን በበኩላቸው "የአሜሪካ ዋነኛ ስጋት በትግራይ ያለው ጦርነት እንዲሁም በአገሪቱ ያለው አለመረጋጋት አገሪቷን አንዳይበታትናት የሚል ፍራቻ ነው" ይላሉ። ምንም እንኳን የተጣለው ማዕቀብ አገሪቱን የበለጠ እንዳያዳክማት አሜሪካ ብትሰጋም "በትግራይ ውስት እየተፈፀመ ካለው የመብት ጥሰት ክብደት አንፃር ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆና አግኝታዋለች" ይላሉ። እቀባው ጣልቃ ገብነት ወይስ? ዲፕሎማቱ ጠንከር ያለ እርምጃ ቢሉም ለዶክተር ዮናስ በአገራት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባትና በጉልበት ለመፍታት መሞከር "ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ አካሄድ ነው" ይላሉ። "ሁላችንም እንደ መረብ የተያያዝን ዓለም ላይ ስለምንኖር አንዱ ሌላውን ገፍትሮ፣ አንዱ የሌላው የበላይ፣ አዛዥና ናዛዥ ሆኖ፤ ሌላኛው ታዛዥ ሎሌ ወይም ባርያ ሆኖ ለመኖር ጊዜው አልፏል" የሚሉት ዶክተር ዮናስ "21ኛው ክፍለ ዘመን አገራት ችግሮቻቸውን በአንድነት ተባብረው የሚፈቱበት ዘመን እንጂ አንዱ ሌላኛውን አስፈራርቶ ችግር ሊፈታ አይችልም" ይላሉ። ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዘመናት የቆየው ግንኙነት እንዳይበላሽና ዘላቂው ጥቅም እንዲጠበቅ ውሳኔው መጤን አለበት በማለትም ምክር ይለግሳሉ። "አሜሪካ ለራሷም ጥቅም ለራሷም ክብር ሲባል የወሰደችውን አቋም እንደገና ማጤንና መገምገም አለባት" በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ለመሆኑ አሜሪካ ኢትዮጵያ እቀባውን የጣለችውም ሆነ ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ አገሪቷ ምን እንድታደርግ የሚጠይቅ ነው? ጥሰቶችን በገለልተኛ አካላት ተጣርተው ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲጠበቁ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም እክል እንዲደርሱ እንዲሁም የኤርትራ መንግሥትም ሠራዊቱን በአስቸኳይ ከክልሉ እንዲያስወጣና ዓለም አቀፍ እውቅና ወዳለው የኤርትራ ግዛት እንዲመለሱ የሚጠይቅ ነው። ግጭቱ እስካልቆመና ሰብዓዊ እርዳታዎችን ማቅረብ ካልተቻለ ያለው የምግብ ደኅንነት ስጋት ወደ ረሃብ ይቀየራል ይላል። የትግራይን ቀውስ ማስቆም የማይችሉ ከሆነ ከአሜሪካም ሆነ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሌሎች እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል የሚለው የአሜሪካ ሐሳብ በኢትዮጵያ ላለው ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመጣ አገራቸው እንደምትሰራ ዘርዝሯል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በክልሉ ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመመርመር ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራች እንደሆነና በተመሳሳይም የሰብዓዊ እርዳታም ባልተገደበ ሁኔታ እርዳታ እንዲቀርብ እየሰራሁ ነው ብላለች። ነገር ግን ያላት አቅም ውስን መሆኑንም አስታውቃለች። ኢትዮጵያ ባወጣችው በዚሁ መግለጫ ላይ አሜሪካ በዋነኝነት ስለምትጠቅሰው የኤርትራ ሠራዊት መውጣት ጉዳይ የተጠቀሰ የለም። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች በቅርቡ እንደሚወጡ አስታውቆ ነበር። አሜሪካ የምታወጣው መግለጫዎችን በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው እያለ ሲወቅስ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት እቀባውን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ በኩል በሰጠው መግለጫ "የኢትዮጵያ ነፃነትና ሉዓላዊነት በገንዘብ የማይቀየር ቀይ መስመር ነው" ብሎታል። በተለይም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ኃይሎች ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው የሚለው ጥረት በመንግሥት በኩል ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ተገልጿል። እቀባውንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ሽብርተኛ ተብሎ ከተሰየመው ህወሓት ጋር ድርድር ማድረግ እንደማይቻል ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል" በማለት ቡድኑ መልሶ እንዲያንሰራራ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ አሉታዊ ውጤት የሚኖረውና የማይሳካ መሆኑ ተጠቅሷል። ዶክተር ዮናስም በበኩላቸው ከህወሓት ጋር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በተለያዩ አካላት ወደ ድርድር ለማምጣት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አስታውሰው በወቅቱ አሜሪካም የራሷን ድርሻ መጫወት ትችል ነበር ይላሉ። "የኢትዮጵያ ምክር ቤት ተሰብስቦ ህወሓትን በሽብርተኝነት ከፈረጀው በኋላ እንደገና ህወሓትን ከዚያ ውስጥ ለማውጣትና እንደ መንግሥት ሁለቱን እኩል አድርጎ ለድርድር ግቡ ማለት ቅንነት ያለው አይመስለኝም" ብለዋል። የአሜሪካ መንግሥት በአገሪቱ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ሽብርተኛ ቡድን" ተብሎ የተሰየመውን ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በእኩል የመመልከት ዝንባሌ እንዳስቀየመው አስፍሯል። | የአሜሪካ ማዕቀብ በቀጣናው ስትራቴጂያዊ ለውጥን ያስከትል ይሆን? ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ግንቦት 15/2013 የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን በትግራይ ካለው ግጭት ጋር እየተፈፀሙ ያሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ጥቃቶች አገራቸው በተደጋጋሚ ስጋቷን ብታሰማም ትርጉም ያለው ምላሽ ባለመኖሩ አገራቸው የጉዞ እቀባ መጣሏን አስታውቀዋል። በዚህም በኢትዮጵያና በኤርትራ የቀድሞ እና የአሁን ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ እና ደኅንነት ኃላፊዎች እንዲሁም የአማራ ክልል መደበኛና ኢ-መደበኛ የጸጥታ አባላትና ግለሰቦች፣ ሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦትን ባደናቀፉ የህወሓት አባላት ላይ የቪዛ እቀባ አሜሪካ ጥላለች። ይህ በግጭቱ ላይ እጃቸው ያለበት ወይም ተባባሪ የሆኑትን የሚመለከት ሲሆን እንዲሁም የቅርብ ቤተሰቦቻቸውም ጭምር እቀባው ተግባራዊ ሊሆንባቸው እንደሚችል የወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ከጉዞ እቀባው በተጨማሪ አሜሪካ የምታደርገውን የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት እገዛ እንዲቋረጡና ግጭቱ ካልቆመና መሻሻሎች ካልታዩ፤ ተጨማሪ እርምጃዎችን እንደምትወስድም አስጠንቅቃለች። ሌሎችም አገራት የአሜሪካን ፈለግ እንዲከተሉ ጥሪ አድርጋለች። ይህ የማዕቀብ ሁኔታ አሜሪካ በኢትዮጵያ የምታደርገው ያልተገባ ጫና አካል ነው በሚልም ኢትዮጵያን አሳዝኗል። ምንም እንኳን አሜሪካ ለግጭቱ መፍትሄ ለማምጣት ትርጉም ያለው እርምጃ ሊወሰድ አልተቻለም ብትልም ኢትዮጵያ በበኩሏ ከአሜሪካ አስተዳደር ጋር ገንቢ ግንኙነት በመፍጠር በጋራ እየሰራች ነበር ብላለች። ኢትዮጵያ በትግራይ የተፈፀሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተመለከተ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር በጥምረት ሆነው ለመመርመር እየሰሩ መሆናቸውንና ተጠያቂ የሚሆኑበትንም ስራ እያከናወነች እንደሆነ አስታውቃለች። እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት ግብዣ በአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ምርመራ እያካሄደ እንደሆነ በመጥቀስ ቀውሱን ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች። አሜሪካ ያሳለፈቻቸው እርምጃዎች የሁለቱንም አገራት የዘመናት ግንኙነት የሚጎዳ ነው ትላለች ኢትዮጵያ። የአሜሪካንን እርምጃዎች በውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብነት ነው የምትለው ኢትዮጵያ፤ አሜሪካ በዚሁ የምትቀጥል ከሆነ ግንኙነታቸውን የምታጤነው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሳስቧል። የማዕቀቡ አንድምታ፤ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ይሆን? ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ቀውስ ውስጥ እየተደረጉ ስላሉ እርምጃዎች ተመሳሳይ አረዳድ የላቸውም። በቀጣናው ከአልሻባብ መግነን ጋር ተያይዞ ሸብርተኝነትን ለመዋጋት በሚል የአሜሪካ ቀኝ እጅ የነበረችው ኢትዮጵያና አሜሪካ በትግራይ ባለው ቀውስ ምክንያት ግንኙነታቸው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ለአስርት ዓመታት ኢትዮጵያ የአሜሪካ የደኅንነት አጋር ነበረች የሚሉት የአሜሪካ የቀድሞ ዲፕሎማትና በአትላንቲክ ካውንስል የደኅንነት ኃላፊ የሆኑት ካሜሮን ሀድሰን ናቸው። ለረጅም ጊዜያት ፖለቲካዊ ድርድሮችንና ሽምግልናዎችን በዋነኝነት በመምራት፣ በሰላም በማስከበር ስምሪት እንዲሁም በአጠቃላይ መረጋጋት በሌለባቸው የቀጣናው አካባቢዎች መረጋጋትን በማምጣት ኢትዮጵያ ከፍተኛ ሚና መጫወቷን ካሜሮን ይናገራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት ሁኔታ ራሷ መረጋጋት የሌለባት አገር ናት የሚሉት ዲፕሎማቱ፤ አሜሪካም ይሄንን ለመቆጣጠር የራሷን አስተዋፅኦ ማበርከት አለባት ይላሉ። በተለይም ከማዕቀቡ ጋር ተያይዞ በሁለትዮሽ ግንኙነቱ ላይ አዲስ የሆነ ግንኙነትን የሚያሳይ ነው፤ እንዲሁም አሜሪካ ስትራቴጂያዊ ለውጥን ማድረጓን ጠቋሚ ነው ይላሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ጥናት ተቋም ዳይሬክተርና መምህር ዶክተር ዮናስ አዳዬ በበኩላቸው በዲፕሎማቱ ሃሳብ አይስማሙም፤ የአሁኑን ማዕቀብ በአገራቱ መካከል መሰረታዊ የሚባል የርዕዮተ ዓለም ልዩነት የሌለበት ስለሆነ "ጊዜያዊ ነው" በማለት። ኢትዮጵያ ካላት መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ አንጻር ስትራቴጂክ ቦታ ላይ ከመሆኗም ጋር ተያይዞ አሁንም በምሥራቅ አፍሪካም ሆነ በቀጣናው ካሉ አገራት ከኢትዮጵያ የተሻለ ወዳጅ ለአሜሪካ ማግኘት ያስቸግራል ብለው እንደሚያምኑ ምሁሩ ይናገራሉ። ለዚህም እንደ ዋቢ የሚጠቅሱት የሶማሊያ በአልሻበብ ቁጥጥር ስር መውደቅ፣ የሶማሌላንድና የፑንትላንድ ዕውቅና አለማግኘት፣ በኬንያና በሶማሊያ መካከል ያለው የሻከረ ግንኙነት፣ የሱዳን የሽግግር መንግሥት ትርምስ ውስጥ መሆኑ ኢትዮጵያ አሁንም ለቀጣናው የተሻለች የአሜሪካ አጋር ናት እንዲሉ አስችሏቸዋል። በተለይም አሜሪካ የምጣኔ ሀብትና የደኅንነት ድጋፍ እቀባ ማድረጓን ተከትሎ አገራቱ ሽብርተኝነትን በጋራ እንዋጋለን የሚሉትን ፕሮጀክት እንዲቆም አያደርገውም ወይ? ብለው በርካቶች ጥያቄ ያነሳሉ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ ዲና ሙፍቲ በኩልም በሰጠው መግለጫ እርምጃው ቀጣናውን ችግር ላይ የሚጥል እንዲሁም ኢትዮጵያ በፀረ-አልሻባብ የሽብር መከላከል እና በሰላም ጥበቃ ላይ ያላትን ሚና በጉልህ የሚጎዳ ሲሉ ተችተውታል። ዶክተር ዮናስም በተመሳሳይ መልኩ "ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ለአሜሪካ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ቀኝ እጅ ነበረች አሁንም ናት" ብለው ያምናሉ። የዲፕሎማቱ ካሜሮን ሀድሰን እይታ ግን ከውጭ ጉዳይ መግለጫም ሆነ ከምሁሩ አስተያየት ለየት ይላል። አገሪቱ በአሁኑ ወቅት በውስጧ ካለው ቀውስ የተነሳ ለዓመታት የሚጠበቅባትን በቀጣናው የተጫወተችውን ሚና በአሁኑ ወቅት መጫወት አትችልም ይላሉ። "ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሕዝቡ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማካሄድ አዳዲስ የደኅንነት አጋሮችን እንደነ ሩሲያ፣ ቻይናና የባሕረ ሰላጤው አገራትን አገራትን አጋርነትን እየተመለከተች ነው። ሁኔታዎች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ እነዚህን የመሳሰሉ የደኅንነት ግንኙነቶች በአፍሪካ ቀንድ ያለውን የምዕራባውያን ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ ስትራቴጂያዊ ለውጥ ያስከትላል" ይላሉ። አሜሪካ ከዚህ ቀደም ከፀረ-ሽብር ጋር በተገናኘ ለኢትዮጵያ ስልጠናዎችን፣ እንዲሁም የደኅንነት መረጃዎችን በመለዋወጥ ይሰሩ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የቀድሞው የሲአይኤ አባል የነበሩት ዲፕሎማት ሀድሰን እንደሚሉት አሜሪካ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የጦር መሳሪያም አቀባይ ነበረች። በቅርቡ ያወጣችው የጉዞ እቀባና 'ዲፌንስ ትሬድ ኮንትሮል ፖሊሲ' ያለችውን ተግባራዊ እንደምታደርግም አሜሪካ አስታውቃለች። ይህ ፖሊሲ ምንን ያካትታል? ለዲፕሎማቱ ቢቢሲ ያቀረበላቸው ጥያቄ ነው። እሳቸውም በምላሹ የትኛውም እርምጃ በሕዝብ ላይ ጥፋት የሚፈፀምበት የቴክኖሎጂ ግብአት ላይ ከሚደረግ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይናገራሉ። ሰፋ ያለ ይዘት ያለው ይህ ፖሊሲ የኮምፒውተር ቴክኖሎጂን ጨምሮ፣ ሶፍትዌሮች፣ ክትትልና ቁጥጥር የሚደረግባቸው ቁሳቁሶችና ረቀቅ ያሉ ወታደራዊ ቴክኖሎጂን ያካትታል። በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የተለገሱ በአሜሪካ የተሰሩ ወታደራዊ ቁሳቁሶችን መጠገን አስፈልጎ መለዋወጫ ቢያስፈልግ በዚህ እቀባ መሰረት ኢትዮጵያ ይሄንን ማካሄድ አትችልም ይላሉ። የሁለቱ አገራት ግንኙነት መበላሸት ኢትዮጵያና አሜሪካ ከመቶ ዓመታት በላይ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በሊግ ኦፍ ኔሽንም ሆነ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምስረታ ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል የሚሉት ዶክተር ዮናስ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ኢንዱስትሪዎችና ተቋማት ከአሜሪካ ጋር ትስስር አላቸው ይላሉ። የሁለትዮሽ አጋርነታቸውም ነፀብራቅ የሚባሉት በትምህርት ተቋማት እንዲሁም የአሜሪካ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የነበራትን ሚና እንደ ምሳሌ በማንሳት አሜሪካ ለዘመናት የኢትዮጵያ የልማት አጋር ሆና ቀጥላለች ይላሉ። ለዚያም ነው የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማዕቀቡን የሁለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት የማይመጥንና የመቶ ሃያ ዓመታቱንም ግንኙነት "በዜሮ ያባዛው" ያለው። በአገራቱ መካከል ያለውን ታሪካዊ ዳራ በምንመለከትበት ወቅት ሻክሮ የነበረው ደርግ ኢትዮጵያን ያስተዳድር በነበረ ወቅት ነበር። ኢህአዴግ ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ግን ግንኙነታቸው ጠንካራ የሚባል እንደሆነ ይነገራል። ዲፕሎማቱም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ እንዲህ አይነት እርምጃ ወስዳ አታውቅም ይላሉ። በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል የተወሰነ ውጥረት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራን ጦርነት ተከትሎ በአሜሪካ የቀረበው የተባበሩት መንግሥታት የጦር መሳሪያ ማዕቀብ በሁለቱ አገራት መጣሉን ተከትሎ እንደሆነ ያወሳሉ። አሜሪካ በማንኛውም በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የነበራትን አጋርነት አልተወችም የሚሉት ዶክተር ዮናስ ይህ እቀባ "ማስደንገጥ የለበትም" ይላሉ። ለምሳሌ ያህልም ኢህአዴግ በ2002 ምርጫ መቶ በመቶ አሸንፌያለሁ ብሎ የፓርላማ ወንበሩን ከተቆጣጠረ በኋላ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው ብለው ማፅደቃቸውን በማውሳት ነው። "ይህ ሁኔታ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ያሳዘነ ነበር" ይላሉ። በአፍሪካ ውስጥ "ኢትዮጵያ የአፍሪካ ፖለቲካ መዲና ናት" የሚሉት ዶክተር ዮናስ "ኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉት እቀባም አሜሪካንም ሆነ ኢትዮጵያን ይጎዳል" ይላሉ። በተለይም ኢትዮጵያ የራሷን አፀፋዊ እርምጃዎች የምትወስድ ከሆነ ሁኔታዎች ሊጋጋሉና ቀጣናው የአሸባሪዎች መፈንጫ ሊሆን እንደሚችል ምሁራዊ እይታቸውን ይሰጣሉ። በተለይም በቀጣናው የደኅንነት ስጋት ቢፈጠር ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የአፍሪካ ቀንድም ሆነ ወደ ሌሎች አካካቢዎች አንደሚዛመትና ጉዳቱም ሰፋ ያለ መልክ ሊኖረው እንደሚችል በአፅንኦት ያስረዳሉ። "በነገራችን ላይ የደኅንነትና የሰላም ጥናት ድንበር አይከፋፍልም። አንድ አካባቢ ያለው የደኅንነት ሁኔታ ከተጎዳ መላው ዓለም ነው የሚጎዳው። ለምሳሌ ከዓመታት በፊት በአሜሪካ ላይ ተፈጸመው የመስከረም 11ዱን ጥቃት ብንወስድ፤ ባደጉም ይሁን ባላደጉ አገራት ውስጥ ከፍተኛ ትርምስ ነው የፈጠረው" የሚሉት ዶክተር ዮናስ የአንድ አገር ደኅንነት ወይም ሰላም የሚባል የለም በማለት የአገራቱ እጣ ፈንታ በከፍተኛ ሁኔታ የተሳሰረ እንደሆነ ይተነትናሉ። ዲፕሎማቱም በበኩላቸው ማዕቀቡ ኢትዮጵያ ከምዕራቡ ዓለም ጋር በነበራትን ግንኙነት ላይ ስትራቴጂያዊ ለውጥ እንደሚያመጣ ጠቁመው፤ ይህም ሁኔታ አሜሪካ በቀጣናው ላይ ያላትን ስትራቴጂያዊ ፍላጎቶችም ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደሚያደርስ አልደበቁም። በተለይም ኢትዮጵያ በውስጧ ሰላም ካልሰፈነባትና አጋርነቷ ከቀረ አሜሪካ በቀይ ባሕር ዙሪያ ደኅንነትንም ሆነ መረጋጋት ለማምጣትም እንዲሁም ተፅእኖ ለመፍጠር ፈተና እንደሚሆንባት ያስረዳሉ። የአሜሪካ ስጋት ምንድን ነው? በትግራይ ካለው ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ጥቃትና አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ ችግር በተጨማሪ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ባወጣው መግለጫ፤ በትግራይ ክልል እንዲሁም በአገሪቱ ላይ የተጋረጡት የሉዓላዊነት፣ ብሔራዊ አንድነትና የግዛት ጉዳይ ከፍተኛ ስጋት አሳድሮብኛል ይላል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ወታደሮች ጨምሮ ሌሎች ታጣቂዎች እርዳታ እንዳይደርስ እክል መፍጠር፣ በክልሉ ውስጥ ያሉ ግድያዎች፣ በአስገዳጅ ሁኔታ መፈናቀል፣ መዋቅራዊ የሆነ ወሲባዊ ጥቃት፣ ሆስፒታሎችና የህክምና ተቋማት መውደም አሜሪካ እንዳሳሰባት ትገልጻለች። እንዲሁም የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች ቀጥለዋል የምትለው አሜሪካ ተደጋጋሚ ጉትጎታዎችን ባደርግም ለቀውሱ ፖለቲካዊም ሆነ ሰላማዊ መፍትሄ መምጣት አልተቻለም ትላለች። በዚህም ምክንያት የወሰደችው እርምጃ አስፈላጊ ነው ትላለች። ዶክተር ዮናስ በበኩላቸው ሁለቱንም አገራት ይጎዳል ያሉት ይህን ማዕቀብ በተሳሳተና በደንብ ባልተጠና መረጃ ላይ ተመስርቶ የተወሰደ ነው ይላሉ። ምሁሩ በአውሮፓውያኑ 2003 አሜሪካ ኢራቅን መውረሯን እንደ ምሳሌ በማንሳትም በወቅቱ አሜሪካ ምክንያት ያደረገችው ኢራቅ ጅምላ ጨራሽ መሳሪያ አላት የበሚል ነበር። ነገር ግን መሳሪያው አለመኖሩ የታወቀው ኢራቅ ከፈራረሰችና ከዘገዬ በኋላ መሆኑን ታሪክን ያጣቅሳሉ። በተመሳሳይም አፍጋኒስታንን በማንሳት ከቀደመ ስህተት መማርና ማገናዘብ እንደሚገባ ያወሳሉ። "በስሜት የሚደረጉ ነገሮች የሚያሳዝኑ ይሆናሉ። በዚህ ትብብር ወቅት ኢትዮጵያን በግድ አንበረክካታለሁ ብሎ ማሰቡ በተለይም በጣም ካደጉ አገራት የሚጠበቅም አልነበረም። በተለይም የኢትዮጵያና የአሜሪካ ግንኙነት ረዥም ዘመናት ያስቆጠረ ከመሆኑ አንፃር። ይሄንን በድጋሚ ያጤኑታል ብዬ አስባለሁ" ይላሉ። የኢትዮጵያ መንግሥትም በተለይም አሜሪካ ከምታወጣቸው መግለጫዎች ጋር በተያያዘ በአገሪቱ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ ገብተው ጫና ለመሞከር የሚሞክሩ መንግሥታት ተቀባይነት አይኖረውም ሲል መደመጡ ይታወሳል፟። ከዚህም በተጨማሪ በትግራይ ክልል ቀውስና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘ ምዕራባውያን እንዲሁም አሜሪካ ከፍተኛ ጫና እያሳደረች ነው ያሉ ተቃውሟቸውን በአዲስ አበባ እንዲሁም በሌሎች አገራት በበይነ መረብ አሰምተዋል። የኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን የውሃ ሚኒስትሮች እንዲሁም የሕግ እና የውሃ ጉዳይ የቴክኒክ ባለሞያዎች በዋሽንግተን ዲሲ ሲደራደሩ በነበረበት ወቅት፤ በዓመታት የተራዘመ ድርቅ እንዲሁም በተራዘመ ዓመታት አነስተኛ የውሃ ፍሰት ላይም መሰረታዊ መግባባት ተደርሷል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ያለምንም ውጤት መቋረጡ ይታወሳል። ኢትዮጵያ ዋሽንግተን ሲካሄድ የነበረውንም ድርድር ያቋረጠችበት ምክንያት በግብጽ ፍላጎት ታዛቢ እንዲሆኑ የገቡት አሜሪካና የዓለም ባንክ ለግብጽ ከመወገን አልፈው የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን ላይ ጫና ለማሳደር ሞክረዋል በማለት ኢትዮጵያ መውቀሷ የሚታወስ ነው። አሜሪካ፣ የዓለም ባንክ ከግብጽ ጎን ቆመው ነበር በተባለው በዚህ ድርድር ላይ ከመጀመሪያው ሙሌት በኋላ ኢትዮጵያ ለምትጠቀመው ውሃ ለግብጽ የተጠራቀመ የውሃ ጉድለት ማካካሻ እንድትሰጥ የሚያስገድድ እንደሆነም ተገልጾ ነበር። ከዚህም ጋር በተያያዘ የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በሕዳሴ ግድቡ ድርድር ምክንያት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን 100 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደማይሰጥ ገልፀው ነበር። ከዚህም ጋር ተያይዞ የአሜሪካ የአሁኑ ማዕቀብ የትግራይ ግጭት ብቻ አይደለም የሕዳሴ ግድብም ነው የሚሉ አልታጡም። ነገር ግን የአትላንቲክ ካውንስሉ ካሜሩን ሀድሰን በበኩላቸው "የአሜሪካ ዋነኛ ስጋት በትግራይ ያለው ጦርነት እንዲሁም በአገሪቱ ያለው አለመረጋጋት አገሪቷን አንዳይበታትናት የሚል ፍራቻ ነው" ይላሉ። ምንም እንኳን የተጣለው ማዕቀብ አገሪቱን የበለጠ እንዳያዳክማት አሜሪካ ብትሰጋም "በትግራይ ውስት እየተፈፀመ ካለው የመብት ጥሰት ክብደት አንፃር ጠንከር ያለ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ ሆና አግኝታዋለች" ይላሉ። እቀባው ጣልቃ ገብነት ወይስ? ዲፕሎማቱ ጠንከር ያለ እርምጃ ቢሉም ለዶክተር ዮናስ በአገራት ጉዳይ ውስጥ ጣልቃ መግባትና በጉልበት ለመፍታት መሞከር "ጊዜ ያለፈበት የፖለቲካ አካሄድ ነው" ይላሉ። "ሁላችንም እንደ መረብ የተያያዝን ዓለም ላይ ስለምንኖር አንዱ ሌላውን ገፍትሮ፣ አንዱ የሌላው የበላይ፣ አዛዥና ናዛዥ ሆኖ፤ ሌላኛው ታዛዥ ሎሌ ወይም ባርያ ሆኖ ለመኖር ጊዜው አልፏል" የሚሉት ዶክተር ዮናስ "21ኛው ክፍለ ዘመን አገራት ችግሮቻቸውን በአንድነት ተባብረው የሚፈቱበት ዘመን እንጂ አንዱ ሌላኛውን አስፈራርቶ ችግር ሊፈታ አይችልም" ይላሉ። ይህንንም ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዘመናት የቆየው ግንኙነት እንዳይበላሽና ዘላቂው ጥቅም እንዲጠበቅ ውሳኔው መጤን አለበት በማለትም ምክር ይለግሳሉ። "አሜሪካ ለራሷም ጥቅም ለራሷም ክብር ሲባል የወሰደችውን አቋም እንደገና ማጤንና መገምገም አለባት" በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ለመሆኑ አሜሪካ ኢትዮጵያ እቀባውን የጣለችውም ሆነ ምክር ቤቱ ያሳለፈው ውሳኔ አገሪቷ ምን እንድታደርግ የሚጠይቅ ነው? ጥሰቶችን በገለልተኛ አካላት ተጣርተው ጥፋተኞቹ ተጠያቂ እንዲሆኑ፣ ሰላማዊ ዜጎች እንዲጠበቁ፣ የሰብዓዊ ድጋፎች ያለምንም እክል እንዲደርሱ እንዲሁም የኤርትራ መንግሥትም ሠራዊቱን በአስቸኳይ ከክልሉ እንዲያስወጣና ዓለም አቀፍ እውቅና ወዳለው የኤርትራ ግዛት እንዲመለሱ የሚጠይቅ ነው። ግጭቱ እስካልቆመና ሰብዓዊ እርዳታዎችን ማቅረብ ካልተቻለ ያለው የምግብ ደኅንነት ስጋት ወደ ረሃብ ይቀየራል ይላል። የትግራይን ቀውስ ማስቆም የማይችሉ ከሆነ ከአሜሪካም ሆነ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሌሎች እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል የሚለው የአሜሪካ ሐሳብ በኢትዮጵያ ላለው ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ እንዲመጣ አገራቸው እንደምትሰራ ዘርዝሯል። ኢትዮጵያ በበኩሏ በክልሉ ተፈፀሙ የተባሉ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በመመርመር ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራች እንደሆነና በተመሳሳይም የሰብዓዊ እርዳታም ባልተገደበ ሁኔታ እርዳታ እንዲቀርብ እየሰራሁ ነው ብላለች። ነገር ግን ያላት አቅም ውስን መሆኑንም አስታውቃለች። ኢትዮጵያ ባወጣችው በዚሁ መግለጫ ላይ አሜሪካ በዋነኝነት ስለምትጠቅሰው የኤርትራ ሠራዊት መውጣት ጉዳይ የተጠቀሰ የለም። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ መንግሥት የኤርትራ ወታደሮች በቅርቡ እንደሚወጡ አስታውቆ ነበር። አሜሪካ የምታወጣው መግለጫዎችን በውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባት ነው እያለ ሲወቅስ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት እቀባውን ተከትሎ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቃል አቀባዩ በኩል በሰጠው መግለጫ "የኢትዮጵያ ነፃነትና ሉዓላዊነት በገንዘብ የማይቀየር ቀይ መስመር ነው" ብሎታል። በተለይም በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑት ኃይሎች ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው የሚለው ጥረት በመንግሥት በኩል ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው በተደጋጋሚ ተገልጿል። እቀባውንም ተከትሎ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ "ሽብርተኛ ተብሎ ከተሰየመው ህወሓት ጋር ድርድር ማድረግ እንደማይቻል ከግንዛቤ ሊገባ ይገባል" በማለት ቡድኑ መልሶ እንዲያንሰራራ የሚደረግ ማንኛውም ሙከራ አሉታዊ ውጤት የሚኖረውና የማይሳካ መሆኑ ተጠቅሷል። ዶክተር ዮናስም በበኩላቸው ከህወሓት ጋር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት በተለያዩ አካላት ወደ ድርድር ለማምጣት እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ከፍተኛ ጥረት መደረጉን አስታውሰው በወቅቱ አሜሪካም የራሷን ድርሻ መጫወት ትችል ነበር ይላሉ። "የኢትዮጵያ ምክር ቤት ተሰብስቦ ህወሓትን በሽብርተኝነት ከፈረጀው በኋላ እንደገና ህወሓትን ከዚያ ውስጥ ለማውጣትና እንደ መንግሥት ሁለቱን እኩል አድርጎ ለድርድር ግቡ ማለት ቅንነት ያለው አይመስለኝም" ብለዋል። የአሜሪካ መንግሥት በአገሪቱ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት "ሽብርተኛ ቡድን" ተብሎ የተሰየመውን ህወሓት ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በእኩል የመመልከት ዝንባሌ እንዳስቀየመው አስፍሯል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57238327 |
3politics
| ከእስር እንዲለቀቁ ስለተወሰነላቸው ፖለቲከኞች ከምናውቀው በጥቂቱ | በኢትዮጵያ የተከሰቱ ሁለት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ቀውሶችን ተከትሎ ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ላይ የቆዩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዲፈቱ መወሰኑ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል። በገና ዕለት አመሻሽ ላይ የፖለቲከኞቹ የመፈታት ዜና ከመሰማቱ በፊት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይቅርታና ምህረትን በተመለከተ "ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምህረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን" በማለት ፍንጭ የሚሰጥ መግለጫ አውጥተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም "ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትሕ በሽግግር እና በተሃድሶ ፍትህ ዕይታ፣ አገራዊ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን" ብለዋል። በማስከተልም አመሻሽ ላይ መንግሥት በኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤቱ በኩል ስለውሳኔው መግለጫ ቢያወጣም፣ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የተለያየ ምላሽን እያስተናገደ ከመሆኑ በተጨማሪ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል። የምህረት ውሳኔውን በተመለከተ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት "ኢትዮጵያ ለዘላቂ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የትኛውንም መሥዋዕትነት ትከፍላለች" በሚል ባወጣው መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ችግሮችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መፍታት እንደሚገባ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን አመልክቷል። ለዚህም መንግሥት አካታች አገራዊ ምክክር እንዲሳካ ከሚጠበቅበት ሞራላዊ ግዴታዎች አንዱ ምህረት መሆኑን በመጥቀስ "ለተሻለ ፖለቲካዊ ምኅዳር ሲባል የተወሰኑ እሥረኞችን መንግሥት በምህረት ከእሥር ፈትቷል" ብሏል። ይህ ምህረት ከዚህ በፊት በተፈጸመ ጥፋት የታሠሩትንም ሆነ በቅርቡ ከተፈጠረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የታሠሩትን እንደሚጨምርም ጠቅሷል። ጨምሮም የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋትና ለአካታች አገራዊ ምክክር ሲባል በምህረት የተፈቱት ግለሰቦች "ካለፈው የጥፋት መንገድ ተምረው፣ የተሻለ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አስተዋጽኦ በማድረግ፣ አገራቸውንና ሕዝባቸውን ይክሳሉ" ብሎ መንግሥት እንደሚያምን ተገልጿል። መንግሥት ይህንን ውሳኔ የወሰነው "የኢትዮጵያን ችግሮች ሰላማዊ በሆነ፣ ከእልህና ከመጠፋፋት በራቀ ሁኔታ፣ በአገራዊ ምክክር በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል መንገድ ለመክፈት" መሆኑን ጠቅሶ፤ ለዘመናት የቆዩ ፖለቲካዊ ችግሮችን በአካታች ምክክር ለመፍታት እንዲቻል መንግሥት ገለልተኛ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝም አስታውሷል። የፍትሕ ሚኒስቴር በበኩሉ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕገ መንግሥት እና የሽብር ችሎት እየታየ ከነበሩት መካከል በእነጃዋር መሐመድ እና በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን አሳውቋል። ለዚህም ምክንያቱ በቀጣይ የሚደረገውን "አገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ" መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም የጤና እና የዕድሜ ሁኔታቸውን ከግምት በማስገባት በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ የተከሰሱ ስድስት የህወሓት አባላትና አመራሮች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን የፍትሕ ሚኒስቴር ገልጿል። ለመሆኑ እነዚህ ከእስር እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው ግለሰቦች እንማን ናቸው? በአጭሩ እነሆ. . . ጃዋር መሐመድ አቶ ጃዋር መሐመድ በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ከሚጠቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ለበርካታ ዓመታት በውጭ አገር ቆይተው ወደ አገር የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ነበር። በውጭ አገር ቆይታቸው በአገር ውስጥ የሚካሄደውን ተቃውሞ በመምራትና በማስተባበር ጉልህ ሚና የነበራቸው አቶ ጃዋር ኦኤምኤን የተባለውን የሳተላይት ቴሌቪዥን በማቋቋምና በመምራት ጉልህ ሚና ነበራቸው። ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ወደ ፓርቲ ፖለቲካ ለመግባት በመወሰናቸው፣ ከመታሰራቸው ጥቂት ወራት ቀደም ብለው የነበራቸውን የአሜሪካ ዜግነት መመለሳቸው ይታወሳል። በዚህም በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ወደ'ሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በመግባት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምረው የነበረ ሲሆን፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ በነበረው ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ነበር። ምርጫው ከተራዘመ በኋላ በ2012 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። በወቅቱም በአቶ ጃዋር መዝገብ ስር ከ20 በላይ ሰዎች የፀረ ሽብር አዋጅን፣ የቴሌኮም አዋጅን፣ የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን በመተላለፍ ክስ ተመስርቶባቸው፣ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቷል። አቶ ጃዋር በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ የተለያዩ የጤና እክሎች አጋጥሟቸው እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ በአንድ ወቅት ደግሞ እስራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ አድርገው የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰው እንደነበር ይታወሳል። በቀለ ገርባ አቶ በቀለ ገርባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩ ሲሆን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባልና ከፍተኛ አመራር ሲሆኑ በአቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ሥር ተመሳሳይ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው። አቶ በቀለ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ከመምጣቱ በፊት ከሚያደርጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተይዘው ለበርካታ ዓመታት በእስር ቤት ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከእስር የተለቀቁት አቶ በቀለ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በእስር ቆይተው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ጊዜ ነው የተለቀቁት። አቶ በቀለ በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ ከአቶ ጃዋርና ከሌሎች ጋር መታሰራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ አድርገው የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ሆስፒታል እስከ መግባት ደርሰው ነበር። እስክንድር ነጋ አቶ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛና ፖለቲከኛ ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በነበረው አስተዳደር ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በእስር ላይ ቆይተዋል። አቶ እስክንድር የተለያዩ ጋዜጦችን በማዘጋጀትና በማሳተም የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ሲሆን መንግሥትን በመተቸትም ይታወቃሉ። በዚህም ሳቢያ በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ሲሆን ለረጅም ጊዜ በእስር ከቆዩ በኋላ ነበር ከሦስት ዓመት በፊት ነጻ የወጡት። አቶ እስክንድር በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ ተካሂዶ ከእስር እንደወጡ ወደ ጋዜጠኝነት ሥራቸው ተመልሰው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ፣ በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የተባለውን ፓርቲ መስርተው ሲመሩ ቆይተዋል። ሰኔ ወር 2012 ዓ.ም በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ እስክንድር የፀረ ሽብር አዋጅን በመተላለፍና ኃይልን በመጠቀም መንግሥትን ለመቆጣጠር ሙከራ በማድረግ ተከስሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል። አቶ እስክንድርና አብረዋቸው የታሰሩ የፓርቲያቸው አባላት ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ፣ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበው ተቀባይነት አግኝተው ነበር። በዚህም ቀደም ሲል ባልታየ ሁኔታ አቶ እስክንድርን ጨምሮ የባልደራስ ፓርቲ አመራሮች እስር ቤት ሆነው በምርጫው ዕጩ ሆነው በመቅረብ ለመወዳደር ቢችሉም ሳይመረጡ ቀርተዋል። በተጨማሪም አቶ እስክንድር በእስር ቤት ሳሉ በአንድ እስረኛ ጥቃት እንደደረሰባቸው የተነገረ ሲሆን ጉዳዩን ለፍርድ ቤትና ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቅርበው እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀው ነበር። አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ የተባሉ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም ከእስር ተለቅቀዋል። አስቴር ስዩም በኬሚስትሪ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ የሆነችው ወጣቷ ፖለቲከኛ ቀለብ (አስቴር) ስዩም ከዓመታት በፊት የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) የሰሜን ጎንደር ዞን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመሆን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ታደርግ ነበረ። ከለውጡ በፊት በነበረው የኢህአዴግ አስተዳደር የፀጥታ ኃይሎች ተይዛ በሽብር ወንጀል ተከስሳ አራት ዓመታትን በማዕከላዊና በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ተፈርዶባት ቅጣቷን ጨርሳ ወጥታለች። የሁለት ልጆች እናት የሆነችው አስቴር ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሲመሰረት ፓርቲውን ተቀላቅላ በአመራርነት እያገለገለች የነበረ ሲሆን ሌሎቹ የፓርቲው አመራሮች በታሰሩበት ክስ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በላይ በእስር ላይ ቆይታ ነው አሁን የተፈታችው። አስቴር 'ሀገር ስታምጥ' እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሚያጠነጥንና መሪዎችን የሚተች 'የመሪዎች ሴራ በኢትዮጵያ' የሚል መጽሐፍት ለንባብ አብቅታለች። አስቴር በተለያዩ ጊዜያት በፖለቲካዊ ተሳትፎዋ የተነሳ በእስር በቆየችበት ጊዜ በአጋጠማት አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሰቆቃ ምክንያት የተለያዩ የጤና እክሎች እንዳጋጠሟት ይነገራል። ስብሐት ነጋ የህወሓት መስራች የሆኑት እና ኢህአዴግን በመምራት ሥልጣን ከያዘ በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ ባለፈው ዓመት በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ መንግሥት ለግጭቱና ለቀውሱ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው በማለት የእስር ማዘዣ ካወጣባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ይህንንም ተከትሎ የ86 ዓመቱ አዛውንት አቶ ስብሐት ነጋ በኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት ትግራይ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተነገረው የዛሬ ዓመት ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም ነበር። አቶ ስብሐት ህወሓትን ከመመስረት በተጨማሪ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን፣ በኢህአዴግና በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት የነበራቸው ፖለቲከኛ ነበሩ። አቶ ስብሐት ከፖለቲካው ባሻገር የህወሓት የምርትና የአገለግሎት ተቋማትን የሚያስተዳድረውና በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ተቋማትን በስሩ የያዘው ኤፈርትንም መርተዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ተቋምን ጡረታ እስከ ወጡበት ጊዜ ድረስ በዋና ዳይሬክተርነት መርተውት ነበር። በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ሲፈለጉ ከነበሩት የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች መካከል የሚገኙት አቶ ስብሐት፣ ባለፈው ዓመት ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በሆነ ገደላማ አካባቢ ከባለቤታቸውና ከእህታቸው ጋር ተይዘው ነበር ወደ አዲስ አበባ የመጡት። አቶ ስብሐት በአገር ክህደት፣ በትግራይ ይገኝ በነበረው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በማድረስና በመሳሪያ በታገዘ አመጽና ሁከት በማነሳሳት ወንጀሎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው እየታየ ነበር። ቅዱሳን ነጋ የህወሓት ነባር አባልና ከፍተኛ አመራር የነበሩት ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ በትግራይ ክልል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ከወራት በኋላ በመከላከያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር የዋሉት ከወንድማቸው ከአቶ ስብሐት ነጋ ጋር ነበር። ወ/ሮ ቅዱሳን በህወሓት ውስጥ ካላቸው ሚና በተጨማሪ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ሠርተዋል። ባለቤታቸው አቶ ፀጋይ በርሄ የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን ከመሆናቸው በተጨማሪ የክልሉ ፕሬዝዳንት የፌዴራል መንግሥቱ ደኅንነት አማካሪ ነበሩ። ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር የህወሓት አባል ሲሆኑ በፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አባል ከመሆናቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ከአንድ ዓመት በፊት በፌደራሉ ኃይሎች ተይዘው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የነበረ ሲሆን አሁን እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው ግለሰቦች መካከል አንዷ ናቸው። ሌሎች ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ በርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች በፌደራሉ የፀጥታ ኃይሎች መያዛቸው የሚታወቅ ቢሆንም አሁን በምህረት የሚለቀቁት ስድስቱ ብቻ መሆናቸውን ከመንግሥት በኩል የወጣው መግለጫ ያመለክታል። በዚህም መሠረት ከአቶ ስብሐት ነጋ፣ ከወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ ከወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር በተጨማሪ የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አምባሳደርና የክልሉ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ አባዲ ዘሙና አቶ ኪሮስ ሐጎስ ይገኙበታል። | ከእስር እንዲለቀቁ ስለተወሰነላቸው ፖለቲከኞች ከምናውቀው በጥቂቱ በኢትዮጵያ የተከሰቱ ሁለት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ቀውሶችን ተከትሎ ከአንድ ዓመት በላይ በእስር ላይ የቆዩ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት እና አመራሮች እንዲፈቱ መወሰኑ ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም ይፋ ተደርጓል። በገና ዕለት አመሻሽ ላይ የፖለቲከኞቹ የመፈታት ዜና ከመሰማቱ በፊት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይቅርታና ምህረትን በተመለከተ "ድላችን ዘላቂ ለማድረግ እንድንችል በአሸናፊ ምህረት ግጭቱ የፈጠረውን ውጥረት እናረግባለን" በማለት ፍንጭ የሚሰጥ መግለጫ አውጥተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም "ያጠፋ እንዲቀጣ፣ የበደለ እንዲክስ የሚያደርግ ሁሉን አቀፍ ፍትሕ በሽግግር እና በተሃድሶ ፍትህ ዕይታ፣ አገራዊ ባህሎቻችን እና እሴቶቻችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ፍትህ እናሰፍናለን" ብለዋል። በማስከተልም አመሻሽ ላይ መንግሥት በኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤቱ በኩል ስለውሳኔው መግለጫ ቢያወጣም፣ በተለያዩ ወገኖች ዘንድ የተለያየ ምላሽን እያስተናገደ ከመሆኑ በተጨማሪ ጥያቄዎች እንዲነሱ አድርጓል። የምህረት ውሳኔውን በተመለከተ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት "ኢትዮጵያ ለዘላቂ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የትኛውንም መሥዋዕትነት ትከፍላለች" በሚል ባወጣው መግለጫ ላይ የኢትዮጵያ ችግሮችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ መፍታት እንደሚገባ መንግሥት በጽኑ እንደሚያምን አመልክቷል። ለዚህም መንግሥት አካታች አገራዊ ምክክር እንዲሳካ ከሚጠበቅበት ሞራላዊ ግዴታዎች አንዱ ምህረት መሆኑን በመጥቀስ "ለተሻለ ፖለቲካዊ ምኅዳር ሲባል የተወሰኑ እሥረኞችን መንግሥት በምህረት ከእሥር ፈትቷል" ብሏል። ይህ ምህረት ከዚህ በፊት በተፈጸመ ጥፋት የታሠሩትንም ሆነ በቅርቡ ከተፈጠረው ጦርነት ጋር በተያያዘ የታሠሩትን እንደሚጨምርም ጠቅሷል። ጨምሮም የፖለቲካ ምኅዳሩን ለማስፋትና ለአካታች አገራዊ ምክክር ሲባል በምህረት የተፈቱት ግለሰቦች "ካለፈው የጥፋት መንገድ ተምረው፣ የተሻለ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አስተዋጽኦ በማድረግ፣ አገራቸውንና ሕዝባቸውን ይክሳሉ" ብሎ መንግሥት እንደሚያምን ተገልጿል። መንግሥት ይህንን ውሳኔ የወሰነው "የኢትዮጵያን ችግሮች ሰላማዊ በሆነ፣ ከእልህና ከመጠፋፋት በራቀ ሁኔታ፣ በአገራዊ ምክክር በዘላቂነት ለመፍታት እንዲቻል መንገድ ለመክፈት" መሆኑን ጠቅሶ፤ ለዘመናት የቆዩ ፖለቲካዊ ችግሮችን በአካታች ምክክር ለመፍታት እንዲቻል መንግሥት ገለልተኛ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን ለማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝም አስታውሷል። የፍትሕ ሚኒስቴር በበኩሉ ጉዳያቸው በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሕገ መንግሥት እና የሽብር ችሎት እየታየ ከነበሩት መካከል በእነጃዋር መሐመድ እና በእነ እስክንድር ነጋ መዝገብ ያሉ ተከሳሾች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን አሳውቋል። ለዚህም ምክንያቱ በቀጣይ የሚደረገውን "አገራዊ የምክክር መድረክ ሂደት ውጤታማነት እና አካታችነት ከፍ ለማድረግ" መሆኑን አመልክቷል። በተጨማሪም የጤና እና የዕድሜ ሁኔታቸውን ከግምት በማስገባት በእነ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መዝገብ የተከሰሱ ስድስት የህወሓት አባላትና አመራሮች ክሳቸው እንዲነሳ መደረጉን የፍትሕ ሚኒስቴር ገልጿል። ለመሆኑ እነዚህ ከእስር እንዲለቀቁ የተወሰነላቸው ግለሰቦች እንማን ናቸው? በአጭሩ እነሆ. . . ጃዋር መሐመድ አቶ ጃዋር መሐመድ በኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሞ ፖለቲካ ውስጥ ከሚጠቀሱ ተቃዋሚ ፖለቲከኞች መካከል አንዱ ሲሆኑ ለበርካታ ዓመታት በውጭ አገር ቆይተው ወደ አገር የተመለሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ነበር። በውጭ አገር ቆይታቸው በአገር ውስጥ የሚካሄደውን ተቃውሞ በመምራትና በማስተባበር ጉልህ ሚና የነበራቸው አቶ ጃዋር ኦኤምኤን የተባለውን የሳተላይት ቴሌቪዥን በማቋቋምና በመምራት ጉልህ ሚና ነበራቸው። ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ ወደ ፓርቲ ፖለቲካ ለመግባት በመወሰናቸው፣ ከመታሰራቸው ጥቂት ወራት ቀደም ብለው የነበራቸውን የአሜሪካ ዜግነት መመለሳቸው ይታወሳል። በዚህም በፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ወደ'ሚመራው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) በመግባት እንቅስቃሴ ማድረግ ጀምረው የነበረ ሲሆን፣ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተራዝሞ በነበረው ምርጫ ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረጉ ነበር። ምርጫው ከተራዘመ በኋላ በ2012 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ አዲስ አበባ ውስጥ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። በወቅቱም በአቶ ጃዋር መዝገብ ስር ከ20 በላይ ሰዎች የፀረ ሽብር አዋጅን፣ የቴሌኮም አዋጅን፣ የጦር መሳሪያ አስተዳደር እና ቁጥጥር አዋጅን በመተላለፍ ክስ ተመስርቶባቸው፣ ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቷል። አቶ ጃዋር በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ የተለያዩ የጤና እክሎች አጋጥሟቸው እንደነበር የተነገረ ሲሆን፣ በአንድ ወቅት ደግሞ እስራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ አድርገው የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ሆስፒታል እስከመግባት ደርሰው እንደነበር ይታወሳል። በቀለ ገርባ አቶ በቀለ ገርባ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የነበሩ ሲሆን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባልና ከፍተኛ አመራር ሲሆኑ በአቶ ጃዋር መሐመድ መዝገብ ሥር ተመሳሳይ ክስ ከቀረበባቸው ግለሰቦች መካከል አንዱ ናቸው። አቶ በቀለ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ከመምጣቱ በፊት ከሚያደርጉት ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ተይዘው ለበርካታ ዓመታት በእስር ቤት ቆይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ ከእስር የተለቀቁት አቶ በቀለ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከተከሰተው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ በእስር ቆይተው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ጊዜ ነው የተለቀቁት። አቶ በቀለ በእስር ላይ በነበሩበት ጊዜ ከአቶ ጃዋርና ከሌሎች ጋር መታሰራቸውን በመቃወም የረሃብ አድማ አድርገው የጤናቸው ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በመድረሱ ሆስፒታል እስከ መግባት ደርሰው ነበር። እስክንድር ነጋ አቶ እስክንድር ነጋ ጋዜጠኛና ፖለቲከኛ ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በነበረው አስተዳደር ከጋዜጠኝነት ሥራቸው ጋር በተያያዘ በተደጋጋሚ በእስር ላይ ቆይተዋል። አቶ እስክንድር የተለያዩ ጋዜጦችን በማዘጋጀትና በማሳተም የረጅም ጊዜ ልምድ ያላቸው ሲሆን መንግሥትን በመተቸትም ይታወቃሉ። በዚህም ሳቢያ በተደጋጋሚ ለእስርና ለእንግልት የተዳረጉ ሲሆን ለረጅም ጊዜ በእስር ከቆዩ በኋላ ነበር ከሦስት ዓመት በፊት ነጻ የወጡት። አቶ እስክንድር በኢትዮጵያ ውስጥ ፖለቲካዊ ለውጥ ተካሂዶ ከእስር እንደወጡ ወደ ጋዜጠኝነት ሥራቸው ተመልሰው ሲሰሩ ከቆዩ በኋላ፣ በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚያተኩረውን ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ የተባለውን ፓርቲ መስርተው ሲመሩ ቆይተዋል። ሰኔ ወር 2012 ዓ.ም በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ የተፈጸመውን ግድያ ተከትሎ በቁጥጥር ስር የዋሉት አቶ እስክንድር የፀረ ሽብር አዋጅን በመተላለፍና ኃይልን በመጠቀም መንግሥትን ለመቆጣጠር ሙከራ በማድረግ ተከስሰው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቷል። አቶ እስክንድርና አብረዋቸው የታሰሩ የፓርቲያቸው አባላት ባለፈው ዓመት በተካሄደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ፣ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ አቅርበው ተቀባይነት ባለማግኘታቸው ጉዳያቸውን ለፍርድ ቤት አቅርበው ተቀባይነት አግኝተው ነበር። በዚህም ቀደም ሲል ባልታየ ሁኔታ አቶ እስክንድርን ጨምሮ የባልደራስ ፓርቲ አመራሮች እስር ቤት ሆነው በምርጫው ዕጩ ሆነው በመቅረብ ለመወዳደር ቢችሉም ሳይመረጡ ቀርተዋል። በተጨማሪም አቶ እስክንድር በእስር ቤት ሳሉ በአንድ እስረኛ ጥቃት እንደደረሰባቸው የተነገረ ሲሆን ጉዳዩን ለፍርድ ቤትና ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቅርበው እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀው ነበር። አቶ እስክንድር ነጋን ጨምሮ አቶ ስንታየሁ ቸኮል፣ ወ/ሮ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ የተባሉ የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራሮች ታኅሣሥ 29/2014 ዓ.ም ከእስር ተለቅቀዋል። አስቴር ስዩም በኬሚስትሪ የከፍተኛ ማዕረግ ተመራቂ የሆነችው ወጣቷ ፖለቲከኛ ቀለብ (አስቴር) ስዩም ከዓመታት በፊት የአንድነት ለፍትሕና ለዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) የሰሜን ጎንደር ዞን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ በመሆን ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ታደርግ ነበረ። ከለውጡ በፊት በነበረው የኢህአዴግ አስተዳደር የፀጥታ ኃይሎች ተይዛ በሽብር ወንጀል ተከስሳ አራት ዓመታትን በማዕከላዊና በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ተፈርዶባት ቅጣቷን ጨርሳ ወጥታለች። የሁለት ልጆች እናት የሆነችው አስቴር ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሲመሰረት ፓርቲውን ተቀላቅላ በአመራርነት እያገለገለች የነበረ ሲሆን ሌሎቹ የፓርቲው አመራሮች በታሰሩበት ክስ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በላይ በእስር ላይ ቆይታ ነው አሁን የተፈታችው። አስቴር 'ሀገር ስታምጥ' እንዲሁም በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ የሚያጠነጥንና መሪዎችን የሚተች 'የመሪዎች ሴራ በኢትዮጵያ' የሚል መጽሐፍት ለንባብ አብቅታለች። አስቴር በተለያዩ ጊዜያት በፖለቲካዊ ተሳትፎዋ የተነሳ በእስር በቆየችበት ጊዜ በአጋጠማት አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሰቆቃ ምክንያት የተለያዩ የጤና እክሎች እንዳጋጠሟት ይነገራል። ስብሐት ነጋ የህወሓት መስራች የሆኑት እና ኢህአዴግን በመምራት ሥልጣን ከያዘ በኋላ በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ቁልፍ ሰው የነበሩት አቶ ስብሐት ነጋ ባለፈው ዓመት በትግራይ ውስጥ ወታደራዊ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ መንግሥት ለግጭቱና ለቀውሱ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው በማለት የእስር ማዘዣ ካወጣባቸው ሰዎች መካከል አንዱ ነበሩ። ይህንንም ተከትሎ የ86 ዓመቱ አዛውንት አቶ ስብሐት ነጋ በኢትዮጵያ መንግሥት ሠራዊት ትግራይ ውስጥ በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተነገረው የዛሬ ዓመት ታኅሣሥ 30/2013 ዓ.ም ነበር። አቶ ስብሐት ህወሓትን ከመመስረት በተጨማሪ የድርጅቱ ሊቀመንበር የነበሩ ሲሆን፣ በኢህአዴግና በኢትዮጵያ መንግሥት ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት የነበራቸው ፖለቲከኛ ነበሩ። አቶ ስብሐት ከፖለቲካው ባሻገር የህወሓት የምርትና የአገለግሎት ተቋማትን የሚያስተዳድረውና በቢሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የሚያንቀሳቅሱ ተቋማትን በስሩ የያዘው ኤፈርትንም መርተዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂያዊ ጥናት ተቋምን ጡረታ እስከ ወጡበት ጊዜ ድረስ በዋና ዳይሬክተርነት መርተውት ነበር። በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ ሲፈለጉ ከነበሩት የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች መካከል የሚገኙት አቶ ስብሐት፣ ባለፈው ዓመት ለመንቀሳቀስ አስቸጋሪ በሆነ ገደላማ አካባቢ ከባለቤታቸውና ከእህታቸው ጋር ተይዘው ነበር ወደ አዲስ አበባ የመጡት። አቶ ስብሐት በአገር ክህደት፣ በትግራይ ይገኝ በነበረው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በማድረስና በመሳሪያ በታገዘ አመጽና ሁከት በማነሳሳት ወንጀሎች ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው እየታየ ነበር። ቅዱሳን ነጋ የህወሓት ነባር አባልና ከፍተኛ አመራር የነበሩት ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ በትግራይ ክልል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ከወራት በኋላ በመከላከያ ሠራዊት በቁጥጥር ስር የዋሉት ከወንድማቸው ከአቶ ስብሐት ነጋ ጋር ነበር። ወ/ሮ ቅዱሳን በህወሓት ውስጥ ካላቸው ሚና በተጨማሪ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ሠርተዋል። ባለቤታቸው አቶ ፀጋይ በርሄ የህወሓት ከፍተኛ ባለሥልጣን ከመሆናቸው በተጨማሪ የክልሉ ፕሬዝዳንት የፌዴራል መንግሥቱ ደኅንነት አማካሪ ነበሩ። ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር የህወሓት አባል ሲሆኑ በፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ አባል ከመሆናቸው በተጨማሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር። ወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር ከአንድ ዓመት በፊት በፌደራሉ ኃይሎች ተይዘው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የነበረ ሲሆን አሁን እንዲለቀቁ ከተወሰነላቸው ግለሰቦች መካከል አንዷ ናቸው። ሌሎች ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ በርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች በፌደራሉ የፀጥታ ኃይሎች መያዛቸው የሚታወቅ ቢሆንም አሁን በምህረት የሚለቀቁት ስድስቱ ብቻ መሆናቸውን ከመንግሥት በኩል የወጣው መግለጫ ያመለክታል። በዚህም መሠረት ከአቶ ስብሐት ነጋ፣ ከወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ ከወ/ሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔር በተጨማሪ የቀድሞው የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ዓባይ ወልዱ፣ አምባሳደርና የክልሉ ባለሥልጣን የነበሩት አቶ አባዲ ዘሙና አቶ ኪሮስ ሐጎስ ይገኙበታል። | https://www.bbc.com/amharic/news-59920859 |
2health
| ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት | ለበርካቶች ፕሮስቴት ሲባል ሁለቱ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች አካባቢ ወይም የዘር ፍሬ ከረጢቱ ውስጥ ያለ አካል እንደሆነ ነው የሚያስቡት። የኩላሊት፣ የፕሮስቴት፣ የሽንት ፊኛ እና ቧንቧ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፍፁም ሠለሞን ግን ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች ያለ አካል ነው ይላሉ። እንደ ዶ/ሩ ገለጻ ከሆነ ፕሮስቴት በወንድ ልጅ ብልት እና ፊኛ መካከል የሚገኝ እጢ ነው። ፕሮስቴት የዘር ፈሳሽ የማመንጨት ጥቅም አለው። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ወደ ውጪ ሲፈስ ሰባ በመቶ ያህሉን የሚያመነጨው ፕሮስቴት መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ሀዋስ የሚዋኘው እንዲሁም ምግቡን የሚያገኘው ከዚህ ፈሳሽ መሆኑን አክለው ይጠቅሳሉ። ታድያ የፕሮስቴት ችግር ያለበት ወንድ የዘር ፈሳሹ ወደ ውጪ መፍሰሱን ትቶ የሚመለሰው ወደ ፊኛው ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም ፕሮስቴት፣ የዘር ፈሳሹ ወደ ፊኛ እንዳይመለስ እና ወደ ውጪ እንዲወጣ ይረዳል። ፕሮስቴት ልክ እንደ ምራቅ አመንጪ እና ታይሮይድ እጢዎች ሁሉ እጢ (ግላንድ) ነው። የፕሮስቴት እጢ የሚገኘው ወንድ ላይ ብቻ ነው። እንደ ዶ/ር ፍፁም ገለጻ በየትኛውም የሰውነታችን ክልፍ ላይ ካንሰር ሊከሰት ይችላል፣ ስለዚህም ፕሮስቴትም ለካንሰር ይጋለጣል። በዓለም ላይ ከስምንት ወንዶች መካከል አንዱ በሕይወት ዘመኑ በፕሮስቴት ካንሰር ይያዛል። ፕሮስቴት አጥቢ እንስሳት ላይ በሙሉ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስም ካንሰሩ ከሰው ውጪ የታየው ውሾች ላይ ብቻ ነው። 80 በመቶ ያህሉ ፕሮስቴት ካንሰር ቀስ ብሎ የሚያድግ እንዲሁም ህመም ሳያስከትል ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ነው። በብዛት የፕሮስቴት ካንሰር በመጀመሪያ ከፕሮስቴት እጢ ላይ ተወስኖ ይቆይና ከባድ ጉዳት በማያስከትል መልኩ ቀስ እያለ የሚያድግ ችግር ነው። ለፕሮስቴት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ እድሜ ነው። እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑ፣ ጥቁር ወንዶች እንዲሁም በቤተሰባቸው ውስጥ የፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚገኝ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎችም እድሜያቸው 40 የሞላቸው ወንዶች በየዓመቱ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ዶ/ር ፍፁም በበኩላቸው ፕሮስቴት ካንሰር ከ40 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ የመገኘት እድሉ እጅጉን በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። እድሜያቸው ከ20 እስከ 30 የሆነ ወንዶች በፕሮስቴት የመያዝ እድላቸው አንድ በመቶ ብቻ ነው። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የፕሮስቴት ካንሰር የሚከሰተው እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ወንዶች ላይ ነው ይላሉ ዶ/ር ፍፁም። አፍሪካውያን ከነጮች አንጻር ሲታይ በዚህ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው ግለሰቦች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። ወንድም፣ አባት፣ አያት እንዲሁም አጎቱ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘበት ግለሰብ የተጋላጭነት ዕድሉ ሰፊ ነው። ከቅርብ ቤተሰብ መካከልም አባቱ በዚህ ካንሰር የተያዘ እና አያቱ የተያዘ ወንድ እኩል የተጋላጭነት ልክ እንደሌላቸው ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። አባቱ ወይንም ወንድሙ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ወንድ፣ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከሁለት እና ሦስት እጥፍ በላይ ተጋላጭ ነው። ሌላኛው መታየት ያለበት በቤተሰብ ውስጥ ካንሰር የተያዘው ሰው በስንተኛው ዕድሜው ላይ ተገኘበት የሚለው ወሳኝ ነጥብ መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። ይህንንም ሲያብራሩ ከ65 ዓመት በታች የፕሮስቴት ካንሰር የተገኘበት አባት፣ ልጁ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል ሲሉ ያስረዳሉ። ይህም ማለት ልጁ እስከ 5 እጥፍ ድረስ የተጋለጠ ነው። ሌላኛው ደግሞ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም፣ አባቱ እና አያቱ በፕሮስቴት የተጠቁ እና አባቱ ብቻ የተያዘ ልጅን ብናወዳድር፣ ይህ ሁለቱም የቤተሰብ አባላት የተያዙበት ግለሰብ የበለጠ ተጋላጭ ነው ይላሉ። የዘረመል እክል (ጄኔቲክ ሚውቴሽን) ላይ እክል ካለ የበለጠ ለዚህ ካንሰር ያጋልጣል። ካንሰር በአብዛኛው ሲታይ ህዋሱ በተነሳበት አካል ወይንም ስፍራ ከመጠን በላይ ይራባል። ከዚያም በመቀጠል ባለበት አካል ላይ ብቻ ተገድቦ ሳይቀመጥ ወደ ሌላ የአካል ክፍል ይሰራጫል። ፕሮስቴት ካንሰር ተገቢውን ሕክምና በተገቢው ሰዓት ካላገኘ የሽንት ፊኛን ሊያፍን ያችላል። የፕሮስቴት እጢ ከተራባ በኋላ ፕሮስቴት አጠገብ ያሉ የሽንት ቧንቧ እና ፊኛ ላይ ይዛመታል። ከዚያም አልፎ በደም ስር ተሰራጭቶ ወደ ጀርባ ይሄዳል። ፕሮስቴት ካንሰር ብዙ ጊዜ በደም ስር አድርጎ ወደ ጀርባ፣ አከርካሪ አጥንት እና ሆድ ውስጥ ወዳሉ ንፍፊቶች ይሰራጫል። የፕሮስቴት ካንሰርን ለመከላከል አመጋገብን ማስተካከል ዋነኛው መፍትሄ ነው። አትክልት እና ፍራፍሬ የበዛበት፣ ዓሳ፣ የዓሳ ዘይት፣ ኦሊቭ ኦይል ያለው ምግብ መመገብ ለመከላከል ይረዳል። ከእነዚህ በተጨማሪ አረንጓዴ ሻይ እነዲሁም ቫይታሚን ዲ መጠቀም የመከላከል አቅምን ያጎለብታል። የፕሮስቴት ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ ቀስ ብሎ የሚያድግ በመሆኑ፣ ከጀመረበት አንስቶ ለመሰራጨት እና ሕይወትን አደጋ ላይ ለመጣል ረዥም ጊዜ ይወስድበታል። ስለዚህም ቢያንስ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው። በተለይ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው፤ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ። ቅድመ ምርመራ ለመጀመር የተለያዩ አገራት፣ የተለያዩ መመርያዎች እንዳላቸው የሚናገሩት ዶ/ር ፍፁም፣ አንድ ሰው እድሜው ከ50 አስከ 55 ዓመት ሲሆን ቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል። ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያለው ግለሰብ ደግሞ እድሜው ከ40 አስከ 45 ላይ እያለ ምርመራውን ቢጀመር መልካም መሆኑን ገልፀዋል። “ቢያንስ ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ይመከራል” ሲሉ ያክላሉ። ከሁሉ በፊት በቤተሰብ ውስጥ ያለን የፕሮስቴት ካንሰር ታሪክን ማወቅ እንዲሁም ወደ አርባዎቹ የእድሜ ክልል ሲገባም በተወሰ ጊዜው ውስጥ ምርመራ ማድረግ ችግሩ ካለ ስር ሳይሰድ ለማከም ይረዳል። ምርመራው ተደርጎ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ዓይነት ሕክምናዎች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከእነዚህም ውስጥ በቀዶ ሕክምና ካንሰሩን ማውጣት፣ የጨረር ሕክምና ወይንም ደግሞ የወንድ ልጅ ቴስቴስትሮን ካንሰሩን በዋነኛነት ስለሚመግብ በሰውነት ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን መጠንን ለመቀነስ ሕክምና ይሰጣል። | ዕድሜያቸው 40 የሞላ እና ጥቁር ወንዶች ሊያውቁት የሚገባ የካንሰር ዓይነት ለበርካቶች ፕሮስቴት ሲባል ሁለቱ የወንድ ልጅ የዘር ፍሬዎች አካባቢ ወይም የዘር ፍሬ ከረጢቱ ውስጥ ያለ አካል እንደሆነ ነው የሚያስቡት። የኩላሊት፣ የፕሮስቴት፣ የሽንት ፊኛ እና ቧንቧ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ፍፁም ሠለሞን ግን ፕሮስቴት ከሽንት ፊኛ በታች ያለ አካል ነው ይላሉ። እንደ ዶ/ሩ ገለጻ ከሆነ ፕሮስቴት በወንድ ልጅ ብልት እና ፊኛ መካከል የሚገኝ እጢ ነው። ፕሮስቴት የዘር ፈሳሽ የማመንጨት ጥቅም አለው። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ወደ ውጪ ሲፈስ ሰባ በመቶ ያህሉን የሚያመነጨው ፕሮስቴት መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። የወንድ ልጅ የዘር ፈሳሽ ሀዋስ የሚዋኘው እንዲሁም ምግቡን የሚያገኘው ከዚህ ፈሳሽ መሆኑን አክለው ይጠቅሳሉ። ታድያ የፕሮስቴት ችግር ያለበት ወንድ የዘር ፈሳሹ ወደ ውጪ መፍሰሱን ትቶ የሚመለሰው ወደ ፊኛው ነው። ስለዚህ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም ፕሮስቴት፣ የዘር ፈሳሹ ወደ ፊኛ እንዳይመለስ እና ወደ ውጪ እንዲወጣ ይረዳል። ፕሮስቴት ልክ እንደ ምራቅ አመንጪ እና ታይሮይድ እጢዎች ሁሉ እጢ (ግላንድ) ነው። የፕሮስቴት እጢ የሚገኘው ወንድ ላይ ብቻ ነው። እንደ ዶ/ር ፍፁም ገለጻ በየትኛውም የሰውነታችን ክልፍ ላይ ካንሰር ሊከሰት ይችላል፣ ስለዚህም ፕሮስቴትም ለካንሰር ይጋለጣል። በዓለም ላይ ከስምንት ወንዶች መካከል አንዱ በሕይወት ዘመኑ በፕሮስቴት ካንሰር ይያዛል። ፕሮስቴት አጥቢ እንስሳት ላይ በሙሉ የሚገኝ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስም ካንሰሩ ከሰው ውጪ የታየው ውሾች ላይ ብቻ ነው። 80 በመቶ ያህሉ ፕሮስቴት ካንሰር ቀስ ብሎ የሚያድግ እንዲሁም ህመም ሳያስከትል ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ነው። በብዛት የፕሮስቴት ካንሰር በመጀመሪያ ከፕሮስቴት እጢ ላይ ተወስኖ ይቆይና ከባድ ጉዳት በማያስከትል መልኩ ቀስ እያለ የሚያድግ ችግር ነው። ለፕሮስቴት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል አንዱ እድሜ ነው። እድሜያቸው ከ50 በላይ የሆኑ፣ ጥቁር ወንዶች እንዲሁም በቤተሰባቸው ውስጥ የፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ሰው የሚገኝ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። የዩናይትድ ኪንግደም ተመራማሪዎችም እድሜያቸው 40 የሞላቸው ወንዶች በየዓመቱ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመክራሉ። ዶ/ር ፍፁም በበኩላቸው ፕሮስቴት ካንሰር ከ40 ዓመት በታች በሆኑ ሰዎች ላይ የመገኘት እድሉ እጅጉን በጣም አነስተኛ መሆኑን ይናገራሉ። እድሜያቸው ከ20 እስከ 30 የሆነ ወንዶች በፕሮስቴት የመያዝ እድላቸው አንድ በመቶ ብቻ ነው። ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የፕሮስቴት ካንሰር የሚከሰተው እድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ በሆናቸው ወንዶች ላይ ነው ይላሉ ዶ/ር ፍፁም። አፍሪካውያን ከነጮች አንጻር ሲታይ በዚህ ካንሰር የመጋለጥ እድላቸው ከፍ ያለ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው ግለሰቦች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። ወንድም፣ አባት፣ አያት እንዲሁም አጎቱ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘበት ግለሰብ የተጋላጭነት ዕድሉ ሰፊ ነው። ከቅርብ ቤተሰብ መካከልም አባቱ በዚህ ካንሰር የተያዘ እና አያቱ የተያዘ ወንድ እኩል የተጋላጭነት ልክ እንደሌላቸው ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። አባቱ ወይንም ወንድሙ በፕሮስቴት ካንሰር የተያዘ ወንድ፣ ከአጠቃላይ ሕዝቡ ከሁለት እና ሦስት እጥፍ በላይ ተጋላጭ ነው። ሌላኛው መታየት ያለበት በቤተሰብ ውስጥ ካንሰር የተያዘው ሰው በስንተኛው ዕድሜው ላይ ተገኘበት የሚለው ወሳኝ ነጥብ መሆኑን ዶ/ር ፍፁም ያብራራሉ። ይህንንም ሲያብራሩ ከ65 ዓመት በታች የፕሮስቴት ካንሰር የተገኘበት አባት፣ ልጁ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድሉ ከፍተኛ ይሆናል ሲሉ ያስረዳሉ። ይህም ማለት ልጁ እስከ 5 እጥፍ ድረስ የተጋለጠ ነው። ሌላኛው ደግሞ ይላሉ ዶ/ር ፍፁም፣ አባቱ እና አያቱ በፕሮስቴት የተጠቁ እና አባቱ ብቻ የተያዘ ልጅን ብናወዳድር፣ ይህ ሁለቱም የቤተሰብ አባላት የተያዙበት ግለሰብ የበለጠ ተጋላጭ ነው ይላሉ። የዘረመል እክል (ጄኔቲክ ሚውቴሽን) ላይ እክል ካለ የበለጠ ለዚህ ካንሰር ያጋልጣል። ካንሰር በአብዛኛው ሲታይ ህዋሱ በተነሳበት አካል ወይንም ስፍራ ከመጠን በላይ ይራባል። ከዚያም በመቀጠል ባለበት አካል ላይ ብቻ ተገድቦ ሳይቀመጥ ወደ ሌላ የአካል ክፍል ይሰራጫል። ፕሮስቴት ካንሰር ተገቢውን ሕክምና በተገቢው ሰዓት ካላገኘ የሽንት ፊኛን ሊያፍን ያችላል። የፕሮስቴት እጢ ከተራባ በኋላ ፕሮስቴት አጠገብ ያሉ የሽንት ቧንቧ እና ፊኛ ላይ ይዛመታል። ከዚያም አልፎ በደም ስር ተሰራጭቶ ወደ ጀርባ ይሄዳል። ፕሮስቴት ካንሰር ብዙ ጊዜ በደም ስር አድርጎ ወደ ጀርባ፣ አከርካሪ አጥንት እና ሆድ ውስጥ ወዳሉ ንፍፊቶች ይሰራጫል። የፕሮስቴት ካንሰርን ለመከላከል አመጋገብን ማስተካከል ዋነኛው መፍትሄ ነው። አትክልት እና ፍራፍሬ የበዛበት፣ ዓሳ፣ የዓሳ ዘይት፣ ኦሊቭ ኦይል ያለው ምግብ መመገብ ለመከላከል ይረዳል። ከእነዚህ በተጨማሪ አረንጓዴ ሻይ እነዲሁም ቫይታሚን ዲ መጠቀም የመከላከል አቅምን ያጎለብታል። የፕሮስቴት ካንሰር አብዛኛውን ጊዜ ቀስ ብሎ የሚያድግ በመሆኑ፣ ከጀመረበት አንስቶ ለመሰራጨት እና ሕይወትን አደጋ ላይ ለመጣል ረዥም ጊዜ ይወስድበታል። ስለዚህም ቢያንስ በዓመት ወይንም በሁለት ዓመት አንዴ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ነው። በተለይ ለካንሰሩ የመጋለጥ ዕድላቸው የሰፋ የቤተሰብ ታሪክ ያላቸው፤ ቅድመ ምርመራ እንዲያደርጉ ይመከራሉ። ቅድመ ምርመራ ለመጀመር የተለያዩ አገራት፣ የተለያዩ መመርያዎች እንዳላቸው የሚናገሩት ዶ/ር ፍፁም፣ አንድ ሰው እድሜው ከ50 አስከ 55 ዓመት ሲሆን ቅድመ ምርመራ እንዲያደርግ ይመከራል። ተመሳሳይ የቤተሰብ ታሪክ ያለው ግለሰብ ደግሞ እድሜው ከ40 አስከ 45 ላይ እያለ ምርመራውን ቢጀመር መልካም መሆኑን ገልፀዋል። “ቢያንስ ቢያንስ በየሁለት ዓመቱ ቅድመ ምርመራ ማድረግ ይመከራል” ሲሉ ያክላሉ። ከሁሉ በፊት በቤተሰብ ውስጥ ያለን የፕሮስቴት ካንሰር ታሪክን ማወቅ እንዲሁም ወደ አርባዎቹ የእድሜ ክልል ሲገባም በተወሰ ጊዜው ውስጥ ምርመራ ማድረግ ችግሩ ካለ ስር ሳይሰድ ለማከም ይረዳል። ምርመራው ተደርጎ የፕሮስቴት ካንሰር መኖሩ ከተረጋገጠ በኋላ የተለያዩ ዓይነት ሕክምናዎች እንዳሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከእነዚህም ውስጥ በቀዶ ሕክምና ካንሰሩን ማውጣት፣ የጨረር ሕክምና ወይንም ደግሞ የወንድ ልጅ ቴስቴስትሮን ካንሰሩን በዋነኛነት ስለሚመግብ በሰውነት ውስጥ ያለውን የቴስቴስትሮን መጠንን ለመቀነስ ሕክምና ይሰጣል። | https://www.bbc.com/amharic/articles/cndxlne6nk9o |
5sports
| ጣሊያን ስፔንን በመርታት ለፍጻሜ መድረሷን አረጋገጠች | በአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ጣልያን ስፔንን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷን አረጋገጠች። በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘጠና ደቂቃው እና ተጨማሪ ደቂቃ አንድ አቻ በመጠናቀቁ ሁለቱ ቡድኖች በፍጽም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ሆኗል። የስፔኑ የፊት መስመር ተጫዋች አልቫሮ ሞራታ የስፔንን የመጨረሻውን ፍጹም ቅጣት ምት የሳተ ሲሆን የጣልያኑ ጆርጂንዮ ደግሞ ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ግብ መቀየሩን ተከትሎ ጣልያን ዛሬ ምሽት ከእንግሊዝና ዴንማርክ አሸናፊ ጋር ለፍጻሜ በመጪው እሁድ ትጫወታለች። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በፈጣን እንቅስቃሴና በስፔን የተበላይነት የተሞላ ቢሆንም ግብ ግን ሳይቆጠር ነበር የተጠናቀቀው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ የጣልያኑ ፌደሪኮ ኪዬዛ አስገራሚ ግብ አስቆጥሮ ጣልያንን መሪ ማድረግ ችሏል። ነገር ግን ጨዋታው ሊጠናቀቅ እየተቃረበ በነረበት ሰአት የስፔን ተጫዋቾች በጥሩ ጨዋታ ጣልያን የግብ ክልል ውስጥ የተቀባበሏትን ኳስ ተቀይሮ የገባው አልቫሮ ሞራታ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር አገሩን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። የጣልያኑ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ያዋቀሩት ቡድን እስካሁን ድረስ ብዙም ሳይቸገር ነበር ለግማሽ ፍጻሜው መድረስ የቻለው። ነገር ግን ከስፔን ጋር የተደረገው ጨዋታ ጣልያኖችን የፈተነ ነበር። የስፔኑ አሰልጣኝ ሊዊስ ኤነሪኬ የጣልያንን አጨዋወት በሚገባ አጥንተውና ኳስን መሰረት ያደረገ ጨዋታ ላይ አተኩረው ነበር የጀመሩት። በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ እንደ ሞራታ ብዙ ግብ የሚሆኑ እድሎችን ያባከነ የለም በሚል በርካቶች ሲወቅሱት የነበረ ሲሆን ስፔን ውስጥም ቤተሰቦቹ ዛቻ ደርሶባቸዋል። ነገር ግን በግማሽ ፍጻሜው አገሩን አቻ አድርጎ ነገሮችን መለወጥ ቢችልም ፍጹም ቅጣት ምቱን መሳቱ ደግሞ ተመልሶ ጫና ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ጣልያን ከምድብ ድልድል ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ ማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገና ብዙ ግቦችን ማስቆጠር የሚያስችል አጨዋወት ነበር ይዛ የመጣችው። ነገር ግን ከስፔን በነበረው ጨዋታ ወደቀድሞው መከላከልን ማዕከል ያደረገ አጨዋወት ተመልሰው ነበር። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ብሄራዊ ብድኑን ከተረከቡ ወዲህ ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ እንኳን ጣልያንን ማሳለፍ አቅቷቸው የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ግን በደንብ የተደራጀና ውጤታማ ቡድን ሰርተው ለፍጻሜ መድረስ ችለዋል። ዛሬ ምሽት አራት ሰአት ላይ ደግሞ ሌላኞቹ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚዎች ዴንማርክና እንግሊዝ ይገናኛሉ። የዚህ ጨዋታ አሸናፊ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ከጣልያን ጋር ይፋለማል። | ጣሊያን ስፔንን በመርታት ለፍጻሜ መድረሷን አረጋገጠች በአውሮፓ ዋንጫ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ ጣልያን ስፔንን በፍጹም ቅጣት ምት በማሸነፍ ለፍጻሜ መድረሷን አረጋገጠች። በእንግሊዙ ዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዘጠና ደቂቃው እና ተጨማሪ ደቂቃ አንድ አቻ በመጠናቀቁ ሁለቱ ቡድኖች በፍጽም ቅጣት ምት እንዲለያዩ ሆኗል። የስፔኑ የፊት መስመር ተጫዋች አልቫሮ ሞራታ የስፔንን የመጨረሻውን ፍጹም ቅጣት ምት የሳተ ሲሆን የጣልያኑ ጆርጂንዮ ደግሞ ፍጹም ቅጣት ምቱን ወደ ግብ መቀየሩን ተከትሎ ጣልያን ዛሬ ምሽት ከእንግሊዝና ዴንማርክ አሸናፊ ጋር ለፍጻሜ በመጪው እሁድ ትጫወታለች። የጨዋታው የመጀመሪያ አጋማሽ በፈጣን እንቅስቃሴና በስፔን የተበላይነት የተሞላ ቢሆንም ግብ ግን ሳይቆጠር ነበር የተጠናቀቀው። ሁለተኛው አጋማሽ ላይ የጣልያኑ ፌደሪኮ ኪዬዛ አስገራሚ ግብ አስቆጥሮ ጣልያንን መሪ ማድረግ ችሏል። ነገር ግን ጨዋታው ሊጠናቀቅ እየተቃረበ በነረበት ሰአት የስፔን ተጫዋቾች በጥሩ ጨዋታ ጣልያን የግብ ክልል ውስጥ የተቀባበሏትን ኳስ ተቀይሮ የገባው አልቫሮ ሞራታ በግሩም ሁኔታ ወደ ግብነት በመቀየር አገሩን አቻ ማድረግ ችሎ ነበር። የጣልያኑ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ያዋቀሩት ቡድን እስካሁን ድረስ ብዙም ሳይቸገር ነበር ለግማሽ ፍጻሜው መድረስ የቻለው። ነገር ግን ከስፔን ጋር የተደረገው ጨዋታ ጣልያኖችን የፈተነ ነበር። የስፔኑ አሰልጣኝ ሊዊስ ኤነሪኬ የጣልያንን አጨዋወት በሚገባ አጥንተውና ኳስን መሰረት ያደረገ ጨዋታ ላይ አተኩረው ነበር የጀመሩት። በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ እንደ ሞራታ ብዙ ግብ የሚሆኑ እድሎችን ያባከነ የለም በሚል በርካቶች ሲወቅሱት የነበረ ሲሆን ስፔን ውስጥም ቤተሰቦቹ ዛቻ ደርሶባቸዋል። ነገር ግን በግማሽ ፍጻሜው አገሩን አቻ አድርጎ ነገሮችን መለወጥ ቢችልም ፍጹም ቅጣት ምቱን መሳቱ ደግሞ ተመልሶ ጫና ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ጣልያን ከምድብ ድልድል ጀምሮ ባልተለመደ መልኩ ማጥቃት ላይ መሰረት ያደረገና ብዙ ግቦችን ማስቆጠር የሚያስችል አጨዋወት ነበር ይዛ የመጣችው። ነገር ግን ከስፔን በነበረው ጨዋታ ወደቀድሞው መከላከልን ማዕከል ያደረገ አጨዋወት ተመልሰው ነበር። አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማንቺኒ ብሄራዊ ብድኑን ከተረከቡ ወዲህ ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ እንኳን ጣልያንን ማሳለፍ አቅቷቸው የነበረ ቢሆንም በዘንድሮው የአውሮፓ ዋንጫ ግን በደንብ የተደራጀና ውጤታማ ቡድን ሰርተው ለፍጻሜ መድረስ ችለዋል። ዛሬ ምሽት አራት ሰአት ላይ ደግሞ ሌላኞቹ የግማሽ ፍጻሜ ተፋላሚዎች ዴንማርክና እንግሊዝ ይገናኛሉ። የዚህ ጨዋታ አሸናፊ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ከጣልያን ጋር ይፋለማል። | https://www.bbc.com/amharic/news-57737844 |
2health
| የሌሊት ወፍ ሳንድዊች የሚበላ ሰው የሚያሳየው ማስታወቂያ ላይ ምርመራ ተጀመረ | የሌሊት ወፍ ሳንድዊች ሲበላ የሚያሳይ ማስታወቂያ ላይ የአውስትራሊያው የማስታወቂያ ጥበቃ ድርጅት ምርመራ ጀመረ፡፡ ከቤት ውጭ መገልገያ አምራች የሆነው ቦቲንግ ካምፓኒ ፊሺንግ (ቢሲኤፍ) ያሠራው ይህ ማስታወቂያ በዩቲዩብ ከ 250,000 ጊዜ በላይ ታይቷል፡፡ በማስታወቂያው ለላይ ተዋናዩ ወረርሽኙ የተከሰተው አንድ ግለሰብ የሌሊት ወፍ በመብላቱ ነው ብሎ ይቀልዳል። የመጀመሪያዎቹ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች በቻይና ዉሃን ከተማ ከሚገኝ የእንሰሳት ገበያ ቢገኙም፣ ቫይረሱ እንዴት እንደጀመረ እና እንደተሰራጨ ትክክለኛ ማረጋገጫ የለም፡፡ የማስታወቂያ ደረጃዎች ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "የማስታወቂያ ደረጃዎች በቢሲኤፍ የበጋ ዘመቻ ማስታወቂያ ላይ በርካታ ቅሬታዎች የደረሱት ሲሆን እነዚህን ቅሬታዎች በመገምገም ላይ ይገኛል" ብለዋል። የቢሲኤፍ ቃል አቀባይ ቀደም ሲል ለአውስትራሊያ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ቀለል ብሎ በቀረበው ማስታወቂያ ብዙ አውስትራሊያውያን በክረምቱ ቤታቸውን እንዲቆዩ እና የራሳቸውን ጓሮ እንዲመረምሩ ያበረታታል፡፡ "በእርግጥ የተከሰተውን ወረርሽኝ እና ስርጭት ምን ያህል እንደሆነ ተረድተናል። ይህ ግን ማስታወቂያ በተመሳሳይ መንፈስ የተቀረፀ መሆኑ ግልፅ ነው" ብለዋል። ቢሲኤፍ ለአውስትራሊያ የማስታወቂያ ጥበቃ እንግዳ አይደለም- በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 እና 2018 ባሠራቸው ማስታወቂያዎች ብዙ ቅሬታ ቀርቦበት ነበር፡፡ "ባለፉት ዓመታት ቢሲኤፍ ተመሳሳይ ማስታወቂያዎችን የማስነገር ባህል መሥርቷል" ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡ " ማስታወቂያዎቹ ተቺዎች ቢኖራቸውም እኛም ግን ያንን እናውቃለን" ሲሉም ያክላሉ። እንደባለሙያዎች ከሆነ በአውስትራሊያና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ባለፈው ዓመት በአስርተ ዓመታት ውስጥ ከነበረበት ደረጃ ዝቅ ብሏል። ማስታወቂያው ውጥረቱ ይበልጥ እየተለጠጠ ስለመሆኑ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ አውስትራሊያ የኮሮናቫይረስ አመጣጥን ለማወቅ የሚያደረገውን ዓለም አቀፍ ምርመራን ደግፋለች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የቻይና ተማሪዎች እና ቱሪስቶች ዘረኝነትን ፍራቻ ወደ አውስትራሊያ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው የአውስትራሊያ ምርቶች የሚገቡትም በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ትኩረት ነበር፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ቻይና በአውስትራሊያ ወይን ላይ እስከ 212% የሚደርስ ግብር ጥላለች። | የሌሊት ወፍ ሳንድዊች የሚበላ ሰው የሚያሳየው ማስታወቂያ ላይ ምርመራ ተጀመረ የሌሊት ወፍ ሳንድዊች ሲበላ የሚያሳይ ማስታወቂያ ላይ የአውስትራሊያው የማስታወቂያ ጥበቃ ድርጅት ምርመራ ጀመረ፡፡ ከቤት ውጭ መገልገያ አምራች የሆነው ቦቲንግ ካምፓኒ ፊሺንግ (ቢሲኤፍ) ያሠራው ይህ ማስታወቂያ በዩቲዩብ ከ 250,000 ጊዜ በላይ ታይቷል፡፡ በማስታወቂያው ለላይ ተዋናዩ ወረርሽኙ የተከሰተው አንድ ግለሰብ የሌሊት ወፍ በመብላቱ ነው ብሎ ይቀልዳል። የመጀመሪያዎቹ የኮሮናቫይረስ ተጠቂዎች በቻይና ዉሃን ከተማ ከሚገኝ የእንሰሳት ገበያ ቢገኙም፣ ቫይረሱ እንዴት እንደጀመረ እና እንደተሰራጨ ትክክለኛ ማረጋገጫ የለም፡፡ የማስታወቂያ ደረጃዎች ቃል አቀባይ ለቢቢሲ እንደተናገሩት "የማስታወቂያ ደረጃዎች በቢሲኤፍ የበጋ ዘመቻ ማስታወቂያ ላይ በርካታ ቅሬታዎች የደረሱት ሲሆን እነዚህን ቅሬታዎች በመገምገም ላይ ይገኛል" ብለዋል። የቢሲኤፍ ቃል አቀባይ ቀደም ሲል ለአውስትራሊያ መገናኛ ብዙሃን እንደገለጹት ቀለል ብሎ በቀረበው ማስታወቂያ ብዙ አውስትራሊያውያን በክረምቱ ቤታቸውን እንዲቆዩ እና የራሳቸውን ጓሮ እንዲመረምሩ ያበረታታል፡፡ "በእርግጥ የተከሰተውን ወረርሽኝ እና ስርጭት ምን ያህል እንደሆነ ተረድተናል። ይህ ግን ማስታወቂያ በተመሳሳይ መንፈስ የተቀረፀ መሆኑ ግልፅ ነው" ብለዋል። ቢሲኤፍ ለአውስትራሊያ የማስታወቂያ ጥበቃ እንግዳ አይደለም- በጎርጎሮሳዊያኑ 2016 እና 2018 ባሠራቸው ማስታወቂያዎች ብዙ ቅሬታ ቀርቦበት ነበር፡፡ "ባለፉት ዓመታት ቢሲኤፍ ተመሳሳይ ማስታወቂያዎችን የማስነገር ባህል መሥርቷል" ብለዋል ቃል አቀባዩ፡፡ " ማስታወቂያዎቹ ተቺዎች ቢኖራቸውም እኛም ግን ያንን እናውቃለን" ሲሉም ያክላሉ። እንደባለሙያዎች ከሆነ በአውስትራሊያና በቻይና መካከል ያለው ግንኙነት ባለፈው ዓመት በአስርተ ዓመታት ውስጥ ከነበረበት ደረጃ ዝቅ ብሏል። ማስታወቂያው ውጥረቱ ይበልጥ እየተለጠጠ ስለመሆኑ ማሳያ ሊሆን ይችላል፡፡ አውስትራሊያ የኮሮናቫይረስ አመጣጥን ለማወቅ የሚያደረገውን ዓለም አቀፍ ምርመራን ደግፋለች፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የቻይና ተማሪዎች እና ቱሪስቶች ዘረኝነትን ፍራቻ ወደ አውስትራሊያ እንዳይጓዙ ማስጠንቀቂያ ሲሰጣቸው የአውስትራሊያ ምርቶች የሚገቡትም በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ትኩረት ነበር፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት ቻይና በአውስትራሊያ ወይን ላይ እስከ 212% የሚደርስ ግብር ጥላለች። | https://www.bbc.com/amharic/55547003 |
3politics
| መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ለምን የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ አዳገተው? | ከወለጋ ዞን ሆሮ ጉዱሩ ተፈናቅሎ አሁን አዲስ አበባ የሚገኘው የ37 ዓመቱ ግለሰብ፣ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በቃላት መግለጽ ከባድ ነው ይላል። ለደኅንነቱ ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው ይህ ግለሰብ በቅርቡ በአካባቢው የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በአንድ ቦታ ስምንት የቤተሰቡን አባላት እንዳጣ ለቢቢሲ ይናገራል። “ከቤተሰቦቼ ግማሹ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በሕይወት የተረፉት ደግሞ ተበታትነዋል፤ የት እንዳሉ የማይታወቁም አሉ።” በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምዕራባዊው ክፍል የታጠቁ ኃይሎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑ እየጨመረ የሚደርሰውም ጉዳት እየበረታ መጥቷል። ቢቢሲ በተለያዩ ጊዜያት ያናገራቸው ነዋሪዎች ለጥቃቱ ተጠያቂዎች ‘ፋኖ’ የሚሏቸው ኃይሎች እንዲሁም መንግሥት ሽብርተኛ ነው ያለው ኦነግ/ሸኔ እንደሆነ ይናገራሉ። ምንም እንኳ ሁለቱ ኃይሎች ለሚደርሰው ጥቃት ኃላፊነት ወስደው ባያውቁም የፌዴራሉ መንግሥት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጣታቸውን ወደ ታጣቂዎቹ ይቀስራሉ። የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ‘ኦነግ/ሸኔ’ እንዲሁም ‘አክራሪ የአማራ ኃይሎች’ ለፖለቲካ ዓላማቸው ሲሉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ሲሉም ይወቅሳሉ። ላለፉት አራት ዓመታት በመንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ሸኔ) መካከል በተደረጉ ግጭቶች ሳቢያ በርካታ ሰላማዊ ነዋሪዎች ሕይወታቸውንና ንበረታቸውን አጥተዋል፤ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ከመገናኛ ብዙኃን ዕይታ የተሸሸገ ይመስላል፤ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ትኩረት ተነፍጎታል። ይህ የሆነው ለምን ይሆን? መንግሥትስ የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ ለምን ተሳነው? በኦሮሚያ ክልል በተለይም በደቡባዊ እና በምዕራባዊ ክፍሎቹ ውስጥ የሚታየው ቀውስ ላለፉት አራት ዓመታት ዘልቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የፖለቲካ ምሕዳሩ እንዲሰፋ በማለት በውጭ አገራት እና ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ፈቀዱ። በዚህ ወቅት ወደ ፖለቲካው መድረክ ከተመለሱ ፓርቲዎች መካከል ለዘመናት የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አንዱ ነው። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ኦነግ ለሁለት ተከፈለ። አንደኛው ክንፍ የትጥቅ ትግሉን አቁሞ በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ የሚለው ሲሆን፣ ሌላኛው ክንፍ ደግሞ በጠመንጃ አላማውን ለማሳካት የሚታገል ነው። እነዚህ ጉዳዮች በአገር ቤት መገናኛ ብዙኃን ቢዘገቡም በዓለም አቀፍ ሚድያ ግን ችላ የተባሉ ነበሩ ይላሉ የአዲስ ስታንዳርድ መሥራች ፀዳለ ለማ። በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በመቅረብ በኢትዮጵያ ስላሉ ሁኔታዎች ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት ፀዳለ፣ የኦሮሚያ ጉዳይ በተለያዩ ርዕሰ ዜናዎች ምክንያት ተቀብሮ ነበር ይላሉ። ከእነዚህ ምክንያቶች አንደኛው የትግራይ ጦርነት ነው። የትግራይ ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ በትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ ኦነግ/ሸኔ እንዲሁም ህወሓት ሽብርተኛ ቡድኖች ናቸው ሲል ማወጁ ይታወሳል። ይህ የታጠቀ ኃይል በተለያዩ ጊዜያት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል በሚል በተደጋጋሚ ወቀሳ ቢደርስበትም ቡድኑ ለደረሱት ጥቃቶች ኃላፊነት ከመውሰድ ተቆጥቧል። ፀዳለ እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የፖለቲካ ምሕዳሩን ሲከፍቱ፣ እሥረኞችን ሲፈቱ፣ የምጣኔ ሃብት ‘ሪፎርም’ እያካሄዱ ሳለ በኦሮሚያ ክልል ግጭት ነበር። “ምንም እንኳ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የመገናኛ ብዙኃን ችላ ቢሉትም፣ የኦሮሞ ነፃነት ኃይል ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሲገነጠል፤ ግጭቶች ሲጀማምሩ. . . የአገር ቤት ሚድያው ሲዘግብ ነበር።” አክለው እንደሚሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ለኦሮሞ ጥያቄ ምላሽ ናቸው” ብሎ ስለሚያስብ በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ ትኩረት ተነፍጎታል። በሰሜን በኩል መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር ጦርነት ላይ በነበረበት ወቅት ጭምር ከኦሮሚያ ክልል የሚወጡ ዜናዎች መልካም አልነበሩም። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ ኦሮምያ ክልል ያሉ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው መባሉን ተከትሎ ፋኖ የተባለው ኃይል ጥቃት እያደረሰ ነው የሚል ወሬ መሰማት ጀመረ። ተንታኟ እንደሚሉት ይህ ግጭት ከመገናኛ ብዙኃንና ከሰብዓዊ መብት ቡድኖች ዕይታ ውጪ የሆነበት ሌላኛው ምክንያት ጦርነቱ የሚካሄድበት ቦታ በጣም ራቅ ያለ መሆኑ ነው። “ደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ጀምሮ ተስፋፍቶ አሁን ወደ ማዕከል የመቅረብም ነገር አለ። የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት መቋረጡ የሚድያ ሽፋን እንዳይሰጠው አስተዋፅዖ አድርጓል።” ቢቢሲ በተለያየ ጊዜያት ጥቃት ሲደርስ የሚያናግራቸው ሰላማዊ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ሰለባ እንደሆኑ፣ ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንደተፈናቀሉ ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል የ37 ዓመቱ የሆሮ ጉዱሩ ነዋሪ የመንግሥት ኃይሎችን ከደረሰበት ጥቃት ሊያስጥሉት እንዳልቻሉ ይናገራል። በተለይም በምዕራብ ወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በተደጋጋሚ ለሚደርስባቸው ጥቃት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ተወቃሽ በማድረግ፤ መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ አላደረገልንም ይላሉ። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በበኩሉ “ጥቃቱን አልፈፀምንም፤ ተጠያቂው መንግሥት ነው” የሚል ምላሽ በመስጠት ክስተቱ በገለልተኛ አካል ይጣራ ይላል። “አሁን ያለው ሁኔታ ግጭት ከማለት ጦርነት ተብሎ ቢጠራ ይሻላል” ይላሉ በጄምስ ማዲሰን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ታሪክ መምህር እና ተመራማሪው ፕ/ር ኢታና ሃብቴ። ተመራማሪው በተለያዩ ቦታዎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት ሲደርስባቸው መንግሥት ደኅንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነቱን አልተወጣም ብለው ያምናሉ። ምሑሩ፤ መንግሥት ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ሁኔታውን የመቆጣጠር አቅም አለው፤ ነገር ግን ፍላጎት ይኑረው አይኑረው እርግጠኛ አይደሉም። በኦሮሚያ ክልል ግጭት በሚከሰትባቸው ቦታዎች ያሉ ነዋሪዎች የሚያቀርቡትን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንዲሁም የፈደራል ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎትን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ኮሚሽናቸው በቅርቡ የተዘገቡ ጥቃቶችን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ የጠይቅናቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) “መረጃ እየሰበሰብን ነው። ምርመራችን ስናጠናቅቅ ውጤቱን ይፋ እናደርጋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ወደ አካባቢው አቅንተው ጉዳዩን እየመረመሩት እንደሆነ ለማጣራት ያናገርናቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋች “ለጊዜው አስተያየት መስጠት አንችልም” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። ፀዳለ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሌሎች በተሻለ መረጃ የማግኘት ዕድል አለው ብለው ቢያምኑም “ድርጅቱ የሚያወጣው ሪፖርት አከራካሪ መሆኑ ተነሳሽነቱን ጎድቶታል” ብለው ያስባሉ። “ገለልተኛ የሆነ ሪፖርት ቢያወጡ እንኳ አወዛጋቢ ስለሚሆን ይህ ጉዳይ መነሳሳታቸውን የጎዳው ይመስለኛል። ይሄ ሊሆን ባይገባማ አስተዋፅዖ ግን ይኖረዋል።” ተንታኟ፤ ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የኦሮሚያን ግጭት ልክ እንደ ትግራይ ጦርነት ተከታትለው ባይመረምሩትም፣ ከዚህ ቀደም የተወሰኑ ምርምራ ማከናወናቸውን መዘንጋት አይፈልጉም። እርሳቸው እንደሚሉት ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ልክ እንደ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሁሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ጉዳዩን ችላ እንዲሉት አስተዋፅዖ አድርጓል። ፕሮፌሰር ኢታና፤ “ይህን ጥያቄ ከ2018 በፊት ብጠየቅ ቀለል ያለ ምላሽ እሰጥ ነበር” በማለት፣ ጉዳዩ አሁን በጣም ከባድ እና የተወሳሰበ ደረጃ ላይ ስለደረሰ በቀላሉ ምላሽ የሚገኝበት አይመስልም። አዲስ ስታንዳርዷ ፀዳለ ለማ በበኩላቸው፣ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲበጅለት “መንግሥት ዝግጁ አይደለም” የሚል ስጋት አላቸው። ፀዳለ፤ መንግሥት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ሽብርተኛ ተብሎ፤ እውቅና መንፈጉ፣ ጉዳዩ ከቁም ነገር እንዳይወሰድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ይላሉ። “የኦሮሞ ፓርቲዎችን ጨምሮ አንዳንድ ፖለቲከኞች በመንግሥት ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። ይህንን የተቃወሙ ሌሎች ፓርቲዎች ደግሞ ከፖለቲካ ምሕዳሩ ተገፍተዋል።” መንግሥት፤ ለኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እውቅና መስጠት በፍፁም አይሻም የሚሉት ፀዳለ፣ ይህ ካልሆነ ፖለቲካዊ መፍትሔ አይመጣም ብለው ያምናሉ። ፕ/ር ኢታና ደግሞ መጀመሪያ መቅደም ያለበት ጦርነቱ መቆሙ ነው ይላሉ። “ጦርነት ካልቆመ ንግግር ማድረግ አይቻልም።” “የሕዝብ ደኅንነት ተጠብቆ፤ የታጠቀው ኃይል እውቅና ተሰጥቶት፤ ጥያቄዎች ወደ ጠረጴዛ መጥተው ውይይት ሊደርግባቸው ይገባል።” ከዚህ ጋር በተያያዘ የኦሮምያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ መንግሥታቸው በክልሉ ለሚስተዋለው የፀጥታ ችግር መፍትሔ ለማበጀት እየሠራ ነው ሲሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ሰላማዊ ዜጎች በስጋት ውስጥ መኖራቸውን ቀጥለዋል፤ በየትኛዋ ደቂቃ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሊሰደዱ እንደሚችሉ አያውቁም፤ ብዙዎች ለቅሷቸውን ለፈጣሪያቸው ከማሰማት ውጪ አማራጭ ያላቸው አይመስልም። | መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ለምን የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ አዳገተው? ከወለጋ ዞን ሆሮ ጉዱሩ ተፈናቅሎ አሁን አዲስ አበባ የሚገኘው የ37 ዓመቱ ግለሰብ፣ በአካባቢው ያለውን ሁኔታ በቃላት መግለጽ ከባድ ነው ይላል። ለደኅንነቱ ሲል ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገው ይህ ግለሰብ በቅርቡ በአካባቢው የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በአንድ ቦታ ስምንት የቤተሰቡን አባላት እንዳጣ ለቢቢሲ ይናገራል። “ከቤተሰቦቼ ግማሹ ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ በሕይወት የተረፉት ደግሞ ተበታትነዋል፤ የት እንዳሉ የማይታወቁም አሉ።” በኦሮሚያ ክልል በተለይም በምዕራባዊው ክፍል የታጠቁ ኃይሎች ሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጠኑ እየጨመረ የሚደርሰውም ጉዳት እየበረታ መጥቷል። ቢቢሲ በተለያዩ ጊዜያት ያናገራቸው ነዋሪዎች ለጥቃቱ ተጠያቂዎች ‘ፋኖ’ የሚሏቸው ኃይሎች እንዲሁም መንግሥት ሽብርተኛ ነው ያለው ኦነግ/ሸኔ እንደሆነ ይናገራሉ። ምንም እንኳ ሁለቱ ኃይሎች ለሚደርሰው ጥቃት ኃላፊነት ወስደው ባያውቁም የፌዴራሉ መንግሥት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ጣታቸውን ወደ ታጣቂዎቹ ይቀስራሉ። የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ‘ኦነግ/ሸኔ’ እንዲሁም ‘አክራሪ የአማራ ኃይሎች’ ለፖለቲካ ዓላማቸው ሲሉ ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት እያደረሱ ነው ሲሉም ይወቅሳሉ። ላለፉት አራት ዓመታት በመንግሥትና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ሸኔ) መካከል በተደረጉ ግጭቶች ሳቢያ በርካታ ሰላማዊ ነዋሪዎች ሕይወታቸውንና ንበረታቸውን አጥተዋል፤ ቀያቸውን ጥለው ተሰደዋል። በኦሮሚያ ክልል ያለው ግጭት ከመገናኛ ብዙኃን ዕይታ የተሸሸገ ይመስላል፤ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ትኩረት ተነፍጎታል። ይህ የሆነው ለምን ይሆን? መንግሥትስ የሰላማዊ ዜጎችን ደኅንነት መጠበቅ ለምን ተሳነው? በኦሮሚያ ክልል በተለይም በደቡባዊ እና በምዕራባዊ ክፍሎቹ ውስጥ የሚታየው ቀውስ ላለፉት አራት ዓመታት ዘልቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የፖለቲካ ምሕዳሩ እንዲሰፋ በማለት በውጭ አገራት እና ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ ፈቀዱ። በዚህ ወቅት ወደ ፖለቲካው መድረክ ከተመለሱ ፓርቲዎች መካከል ለዘመናት የትጥቅ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አንዱ ነው። ይህንን ውሳኔ ተከትሎ ኦነግ ለሁለት ተከፈለ። አንደኛው ክንፍ የትጥቅ ትግሉን አቁሞ በሰላማዊ መንገድ እታገላለሁ የሚለው ሲሆን፣ ሌላኛው ክንፍ ደግሞ በጠመንጃ አላማውን ለማሳካት የሚታገል ነው። እነዚህ ጉዳዮች በአገር ቤት መገናኛ ብዙኃን ቢዘገቡም በዓለም አቀፍ ሚድያ ግን ችላ የተባሉ ነበሩ ይላሉ የአዲስ ስታንዳርድ መሥራች ፀዳለ ለማ። በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን በመቅረብ በኢትዮጵያ ስላሉ ሁኔታዎች ትንታኔ በመስጠት የሚታወቁት ፀዳለ፣ የኦሮሚያ ጉዳይ በተለያዩ ርዕሰ ዜናዎች ምክንያት ተቀብሮ ነበር ይላሉ። ከእነዚህ ምክንያቶች አንደኛው የትግራይ ጦርነት ነው። የትግራይ ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ በትግራይ ውስጥ ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት፣ ኦነግ/ሸኔ እንዲሁም ህወሓት ሽብርተኛ ቡድኖች ናቸው ሲል ማወጁ ይታወሳል። ይህ የታጠቀ ኃይል በተለያዩ ጊዜያት ሰላማዊ ዜጎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል በሚል በተደጋጋሚ ወቀሳ ቢደርስበትም ቡድኑ ለደረሱት ጥቃቶች ኃላፊነት ከመውሰድ ተቆጥቧል። ፀዳለ እንደሚሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የፖለቲካ ምሕዳሩን ሲከፍቱ፣ እሥረኞችን ሲፈቱ፣ የምጣኔ ሃብት ‘ሪፎርም’ እያካሄዱ ሳለ በኦሮሚያ ክልል ግጭት ነበር። “ምንም እንኳ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እና የመገናኛ ብዙኃን ችላ ቢሉትም፣ የኦሮሞ ነፃነት ኃይል ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር ሲገነጠል፤ ግጭቶች ሲጀማምሩ. . . የአገር ቤት ሚድያው ሲዘግብ ነበር።” አክለው እንደሚሉት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ለኦሮሞ ጥያቄ ምላሽ ናቸው” ብሎ ስለሚያስብ በኦሮሚያ ክልል ያለው ሁኔታ ትኩረት ተነፍጎታል። በሰሜን በኩል መንግሥት ከትግራይ ኃይሎች ጋር ጦርነት ላይ በነበረበት ወቅት ጭምር ከኦሮሚያ ክልል የሚወጡ ዜናዎች መልካም አልነበሩም። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት፣ ኦሮምያ ክልል ያሉ የአማራ ተወላጆች ላይ ጥቃት እያደረሰ ነው መባሉን ተከትሎ ፋኖ የተባለው ኃይል ጥቃት እያደረሰ ነው የሚል ወሬ መሰማት ጀመረ። ተንታኟ እንደሚሉት ይህ ግጭት ከመገናኛ ብዙኃንና ከሰብዓዊ መብት ቡድኖች ዕይታ ውጪ የሆነበት ሌላኛው ምክንያት ጦርነቱ የሚካሄድበት ቦታ በጣም ራቅ ያለ መሆኑ ነው። “ደቡብ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ጀምሮ ተስፋፍቶ አሁን ወደ ማዕከል የመቅረብም ነገር አለ። የኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት መቋረጡ የሚድያ ሽፋን እንዳይሰጠው አስተዋፅዖ አድርጓል።” ቢቢሲ በተለያየ ጊዜያት ጥቃት ሲደርስ የሚያናግራቸው ሰላማዊ ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ሰለባ እንደሆኑ፣ ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንደተፈናቀሉ ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል የ37 ዓመቱ የሆሮ ጉዱሩ ነዋሪ የመንግሥት ኃይሎችን ከደረሰበት ጥቃት ሊያስጥሉት እንዳልቻሉ ይናገራል። በተለይም በምዕራብ ወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በተደጋጋሚ ለሚደርስባቸው ጥቃት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ተወቃሽ በማድረግ፤ መንግሥት ተገቢውን ጥበቃ አላደረገልንም ይላሉ። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በበኩሉ “ጥቃቱን አልፈፀምንም፤ ተጠያቂው መንግሥት ነው” የሚል ምላሽ በመስጠት ክስተቱ በገለልተኛ አካል ይጣራ ይላል። “አሁን ያለው ሁኔታ ግጭት ከማለት ጦርነት ተብሎ ቢጠራ ይሻላል” ይላሉ በጄምስ ማዲሰን ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ታሪክ መምህር እና ተመራማሪው ፕ/ር ኢታና ሃብቴ። ተመራማሪው በተለያዩ ቦታዎች ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ጥቃት ሲደርስባቸው መንግሥት ደኅንነታቸውን የመጠበቅ ኃላፊነቱን አልተወጣም ብለው ያምናሉ። ምሑሩ፤ መንግሥት ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ሁኔታውን የመቆጣጠር አቅም አለው፤ ነገር ግን ፍላጎት ይኑረው አይኑረው እርግጠኛ አይደሉም። በኦሮሚያ ክልል ግጭት በሚከሰትባቸው ቦታዎች ያሉ ነዋሪዎች የሚያቀርቡትን ቅሬታ በተመለከተ ምላሽ እንዲሰጡን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ እንዲሁም የፈደራል ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎትን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም። ኮሚሽናቸው በቅርቡ የተዘገቡ ጥቃቶችን በተመለከተ ምርመራ እያደረገ እንደሆነ የጠይቅናቸው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) “መረጃ እየሰበሰብን ነው። ምርመራችን ስናጠናቅቅ ውጤቱን ይፋ እናደርጋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ምላሽ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ወደ አካባቢው አቅንተው ጉዳዩን እየመረመሩት እንደሆነ ለማጣራት ያናገርናቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዋች “ለጊዜው አስተያየት መስጠት አንችልም” የሚል ምላሽ ሰጥተውናል። ፀዳለ፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከሌሎች በተሻለ መረጃ የማግኘት ዕድል አለው ብለው ቢያምኑም “ድርጅቱ የሚያወጣው ሪፖርት አከራካሪ መሆኑ ተነሳሽነቱን ጎድቶታል” ብለው ያስባሉ። “ገለልተኛ የሆነ ሪፖርት ቢያወጡ እንኳ አወዛጋቢ ስለሚሆን ይህ ጉዳይ መነሳሳታቸውን የጎዳው ይመስለኛል። ይሄ ሊሆን ባይገባማ አስተዋፅዖ ግን ይኖረዋል።” ተንታኟ፤ ሌሎች ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት የኦሮሚያን ግጭት ልክ እንደ ትግራይ ጦርነት ተከታትለው ባይመረምሩትም፣ ከዚህ ቀደም የተወሰኑ ምርምራ ማከናወናቸውን መዘንጋት አይፈልጉም። እርሳቸው እንደሚሉት ከላይ የተጠቀሱት ምክንያቶች ልክ እንደ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ሁሉ የሰብዓዊ መብት ተቋማትም ጉዳዩን ችላ እንዲሉት አስተዋፅዖ አድርጓል። ፕሮፌሰር ኢታና፤ “ይህን ጥያቄ ከ2018 በፊት ብጠየቅ ቀለል ያለ ምላሽ እሰጥ ነበር” በማለት፣ ጉዳዩ አሁን በጣም ከባድ እና የተወሳሰበ ደረጃ ላይ ስለደረሰ በቀላሉ ምላሽ የሚገኝበት አይመስልም። አዲስ ስታንዳርዷ ፀዳለ ለማ በበኩላቸው፣ ለችግሩ ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲበጅለት “መንግሥት ዝግጁ አይደለም” የሚል ስጋት አላቸው። ፀዳለ፤ መንግሥት የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊትን ሽብርተኛ ተብሎ፤ እውቅና መንፈጉ፣ ጉዳዩ ከቁም ነገር እንዳይወሰድ ትልቅ ሚና ተጫውቷል ይላሉ። “የኦሮሞ ፓርቲዎችን ጨምሮ አንዳንድ ፖለቲከኞች በመንግሥት ሥልጣን ተሰጥቷቸዋል። ይህንን የተቃወሙ ሌሎች ፓርቲዎች ደግሞ ከፖለቲካ ምሕዳሩ ተገፍተዋል።” መንግሥት፤ ለኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት እውቅና መስጠት በፍፁም አይሻም የሚሉት ፀዳለ፣ ይህ ካልሆነ ፖለቲካዊ መፍትሔ አይመጣም ብለው ያምናሉ። ፕ/ር ኢታና ደግሞ መጀመሪያ መቅደም ያለበት ጦርነቱ መቆሙ ነው ይላሉ። “ጦርነት ካልቆመ ንግግር ማድረግ አይቻልም።” “የሕዝብ ደኅንነት ተጠብቆ፤ የታጠቀው ኃይል እውቅና ተሰጥቶት፤ ጥያቄዎች ወደ ጠረጴዛ መጥተው ውይይት ሊደርግባቸው ይገባል።” ከዚህ ጋር በተያያዘ የኦሮምያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ መንግሥታቸው በክልሉ ለሚስተዋለው የፀጥታ ችግር መፍትሔ ለማበጀት እየሠራ ነው ሲሉ ለአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል። ነገር ግን አሁንም ሰላማዊ ዜጎች በስጋት ውስጥ መኖራቸውን ቀጥለዋል፤ በየትኛዋ ደቂቃ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ሊሰደዱ እንደሚችሉ አያውቁም፤ ብዙዎች ለቅሷቸውን ለፈጣሪያቸው ከማሰማት ውጪ አማራጭ ያላቸው አይመስልም። | https://www.bbc.com/amharic/articles/czkd948zd7zo |
3politics
| ምዕራባውያን በሩሲያ እና በፑቲን ላይ ምን አይነት ማዕቀቦችን ሊጥሉ ይችላሉ? | ምዕራባውያን አገራት ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ በርካታ ማዕቀቦችን ሊጥሉባት እንደሚችሉ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ኃያላኑ ምዕራባውያን በሩሲያ እና በመሪያዋ ቭላድሚር ፑቲን ላይ ሊጥሉ የሚችሏቸው የማዕቀብ አይቶችን ይፋ ባያደርጉም፤ ተንታኞች ግን የሚከተሉት ማዕቀቦች በሞስኮ እና ፑቲን ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ እያሉ ነው። የገንዘብ ዝውውር ዕቀባዎች በሩሲያ ላይ ሊጣሉ ከሚችሉ ማዕቀቦች መካከል አንዱ ሞስኮን 'ስዊፍት' ከተባለው የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ማገድ ነው። ስዊፍት ከ200 በላይ በሆኑ አገራት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ኩባንያዎች የፋይናንስ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ የሚጠቀሙት የየገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ነው። ሩሲያ ከስዊፍት ታገደች ማለት፤ ባንኮቿ ከአገር ውጪ ካሉ ባንኮች ጋር የገንዘብ ዝውውር ማድረግ በእጅጉን አዳጋች ያደርግባቸዋል። መሰል ማዕቀብ እአአ 2012 ላይ ኢራን ላይ ተጥሎ ነበር። ታዲያ ኢራን በዚህ ማዕቀብ ምክንያት ከነዳጅ ገበያ ማግኘት የነበረባትን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ሳትሰበስብ ቀርታለች። የዶላር ክልከላ ዋሽንግተን ሞስኮ የአሜሪካ ዶላርን ለግብይት እንዳትጠቀም መከልከል ትችላለች። ሩሲያ ዶላርን መጠቀም አትችልም ከተባለች፤ በምዕራባውያን አገራት የሚገኙ ባንኮች ከሩሲያ ባንኮች ጋር በዶላር ልውውጥ ቢያደርጉ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ይህ ደግሞ ሩሲያ ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራት ግብይት እጅጉን የተገደበ ይሆናል። ሩሲያ የጋዝ አቅርቦቷ ለገበያ የሚቀርበው በአሜሪካ ዶላር እንደመሆኑ በምጣኔ ሃብቷ ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተጽእኖ ከፍ ያለ ነው። የባንክ እገዳዎች አሜሪካ በቀላሉ የሩሲያ ባንኮችን ጥቁር መዝገብ ላይ ልታሰፍር ትችላለች። ይህ ማለት ማንኛውም አካል ከሩሲያ ባንኮች ጋር ግብይት መፈጸም ፍጹም እንዳይቻለው እንደማድረግ ይቆጠራል። ይህ በሞስኮ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት እንዲከሰት ያደርጋል። አሜሪካ በሩሲያ ባንኮች ላይ የምትጥለው እገዳ ጉዳቱ ለሞስኮ ብቻ አይተርፍም። ገንዘባቸው በሩሲያ ባንኮች ያስቀመጡ ምዕራባውያን ዲታዎችም የዚህ ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ። የኤክስፖርት ቁጥጥር ገደቦች ምዕራባውያኑ ሩሲያ ምን፤ በምን ያክል መጠን ወደ አገር ውስጥ ታስገባ የሚለውን መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ አሜሪካ ኩባንያዎቿ የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ወይም ሶፍትዌር ውጤት የሆኑ ምርቶች በሩሲያ ገበያዎች ላይ እንዳይሸጡ ልታግድ ትችላለች። የኃይል ሽያጭ ገደብ የሩሲያ ምጣኔ ሃብት መሠረቱን ካደረገባቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የጋዝ እና የነዳጅ ሽያጭ ላይ ነው። ክሬምሊን ለምዕራባውያኑ ጋዝ እየሸጠች ከፍተኛ ገንዘብ ታገኛለች። ምዕራባውያኑ አገራት እና ኩባንያዎች ከሩሲያ ጋዝ እና ነዳጅ መግዛትን መከልከል ይችላሉ። ይህ ውሳኔ በተመሳሳይ በተለይ ለአውሮፓውያኑ አገራት ከባድ ኪሳራን ይዞ ሊመጣ ይችላል። አውሮፓውያኑ በብዛት የሚጠቀሙት ጋዝ ምንጩ ከሩሲያ እንደመሆኑ፤ በሩሲያ የኃይል አቅርቦት ላይ ዕቀባ ቢጣል በአውሮፓ የጋዝ ዋጋ ጣራ ይነካል። ግለሰቦችን ዒላማ ማድረግ አዳዲስ ማዕቀቦች ግለቦች ላይ ሊጣሉ ይችላሉ። ይህ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቅርብ አጋሮቻቸውን ሊጨምር ይችላል። የንብረት እና የጉዞ እገዳ ደግሞ ዋነኛዎቹ ግለሰቦች ላይ ሊጣሉ የሚችሉ ማዕቀቦች ናቸው። በተጽኖ ፈጣሪ ሩሲያውያን ላይ መሰል ማዕቀብ መጠል ምናልባት ንብረታቸውን እና አራሳቸውን ማንቀሳቀስ ያልቻሉ ግለቦች ፕሬዝደንት ፑቲን ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ የሚል ግምት በምዕራባውያን አገራት መንግሥታት ዘንድ ሊፈጠር ይችላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለምዕራባውያኑ በቀላሉ የማይመለሰው ጥያቄ በሩሲያ ላይ መቼ እና ምን አይነት ማዕቀብ መጣል አለበት የሚለው ነው። ምዕራባውያን አገራትም በዚህ ላይ የተለያየ አቋም ሊያንጸባርቁ ይችላሉ። | ምዕራባውያን በሩሲያ እና በፑቲን ላይ ምን አይነት ማዕቀቦችን ሊጥሉ ይችላሉ? ምዕራባውያን አገራት ሩሲያ ዩክሬንን የምትወር ከሆነ በርካታ ማዕቀቦችን ሊጥሉባት እንደሚችሉ እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። ኃያላኑ ምዕራባውያን በሩሲያ እና በመሪያዋ ቭላድሚር ፑቲን ላይ ሊጥሉ የሚችሏቸው የማዕቀብ አይቶችን ይፋ ባያደርጉም፤ ተንታኞች ግን የሚከተሉት ማዕቀቦች በሞስኮ እና ፑቲን ላይ ሊተገበሩ ይችላሉ እያሉ ነው። የገንዘብ ዝውውር ዕቀባዎች በሩሲያ ላይ ሊጣሉ ከሚችሉ ማዕቀቦች መካከል አንዱ ሞስኮን 'ስዊፍት' ከተባለው የገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ማገድ ነው። ስዊፍት ከ200 በላይ በሆኑ አገራት፤ በሺዎች የሚቆጠሩ ኩባንያዎች የፋይናንስ መልዕክቶችን ለመለዋወጥ የሚጠቀሙት የየገንዘብ ዝውውር ሥርዓት ነው። ሩሲያ ከስዊፍት ታገደች ማለት፤ ባንኮቿ ከአገር ውጪ ካሉ ባንኮች ጋር የገንዘብ ዝውውር ማድረግ በእጅጉን አዳጋች ያደርግባቸዋል። መሰል ማዕቀብ እአአ 2012 ላይ ኢራን ላይ ተጥሎ ነበር። ታዲያ ኢራን በዚህ ማዕቀብ ምክንያት ከነዳጅ ገበያ ማግኘት የነበረባትን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ሳትሰበስብ ቀርታለች። የዶላር ክልከላ ዋሽንግተን ሞስኮ የአሜሪካ ዶላርን ለግብይት እንዳትጠቀም መከልከል ትችላለች። ሩሲያ ዶላርን መጠቀም አትችልም ከተባለች፤ በምዕራባውያን አገራት የሚገኙ ባንኮች ከሩሲያ ባንኮች ጋር በዶላር ልውውጥ ቢያደርጉ ቅጣት ይጠብቃቸዋል። ይህ ደግሞ ሩሲያ ከተቀረው ዓለም ጋር የሚኖራት ግብይት እጅጉን የተገደበ ይሆናል። ሩሲያ የጋዝ አቅርቦቷ ለገበያ የሚቀርበው በአሜሪካ ዶላር እንደመሆኑ በምጣኔ ሃብቷ ላይ የሚኖረው አሉታዊ ተጽእኖ ከፍ ያለ ነው። የባንክ እገዳዎች አሜሪካ በቀላሉ የሩሲያ ባንኮችን ጥቁር መዝገብ ላይ ልታሰፍር ትችላለች። ይህ ማለት ማንኛውም አካል ከሩሲያ ባንኮች ጋር ግብይት መፈጸም ፍጹም እንዳይቻለው እንደማድረግ ይቆጠራል። ይህ በሞስኮ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ግሽበት እንዲከሰት ያደርጋል። አሜሪካ በሩሲያ ባንኮች ላይ የምትጥለው እገዳ ጉዳቱ ለሞስኮ ብቻ አይተርፍም። ገንዘባቸው በሩሲያ ባንኮች ያስቀመጡ ምዕራባውያን ዲታዎችም የዚህ ገፈት ቀማሽ ይሆናሉ። የኤክስፖርት ቁጥጥር ገደቦች ምዕራባውያኑ ሩሲያ ምን፤ በምን ያክል መጠን ወደ አገር ውስጥ ታስገባ የሚለውን መቆጣጠር ይችላሉ። ለምሳሌ አሜሪካ ኩባንያዎቿ የአሜሪካ ቴክኖሎጂ ወይም ሶፍትዌር ውጤት የሆኑ ምርቶች በሩሲያ ገበያዎች ላይ እንዳይሸጡ ልታግድ ትችላለች። የኃይል ሽያጭ ገደብ የሩሲያ ምጣኔ ሃብት መሠረቱን ካደረገባቸው ዘርፎች መካከል አንዱ የጋዝ እና የነዳጅ ሽያጭ ላይ ነው። ክሬምሊን ለምዕራባውያኑ ጋዝ እየሸጠች ከፍተኛ ገንዘብ ታገኛለች። ምዕራባውያኑ አገራት እና ኩባንያዎች ከሩሲያ ጋዝ እና ነዳጅ መግዛትን መከልከል ይችላሉ። ይህ ውሳኔ በተመሳሳይ በተለይ ለአውሮፓውያኑ አገራት ከባድ ኪሳራን ይዞ ሊመጣ ይችላል። አውሮፓውያኑ በብዛት የሚጠቀሙት ጋዝ ምንጩ ከሩሲያ እንደመሆኑ፤ በሩሲያ የኃይል አቅርቦት ላይ ዕቀባ ቢጣል በአውሮፓ የጋዝ ዋጋ ጣራ ይነካል። ግለሰቦችን ዒላማ ማድረግ አዳዲስ ማዕቀቦች ግለቦች ላይ ሊጣሉ ይችላሉ። ይህ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የቅርብ አጋሮቻቸውን ሊጨምር ይችላል። የንብረት እና የጉዞ እገዳ ደግሞ ዋነኛዎቹ ግለሰቦች ላይ ሊጣሉ የሚችሉ ማዕቀቦች ናቸው። በተጽኖ ፈጣሪ ሩሲያውያን ላይ መሰል ማዕቀብ መጠል ምናልባት ንብረታቸውን እና አራሳቸውን ማንቀሳቀስ ያልቻሉ ግለቦች ፕሬዝደንት ፑቲን ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ የሚል ግምት በምዕራባውያን አገራት መንግሥታት ዘንድ ሊፈጠር ይችላል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ለምዕራባውያኑ በቀላሉ የማይመለሰው ጥያቄ በሩሲያ ላይ መቼ እና ምን አይነት ማዕቀብ መጣል አለበት የሚለው ነው። ምዕራባውያን አገራትም በዚህ ላይ የተለያየ አቋም ሊያንጸባርቁ ይችላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-60158165 |
0business
| ኢኮኖሚ ፡ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ሙዲስ ጠቆመ | ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫውን ማራዘሟን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በአገሪቱ የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ሙዲስ የተሰኘው የአሜሪካ የቢዝነስና ፋይናንስ ተቋም ጠቆመ። አገራዊው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቢራዘምም ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ምርጫውን “ሕገ ወጥ” ማለታቸው እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት "ምርጫው እንዳልተካሄደ ይቆጠራል" እንደተባለ ይታወሳል። ሙዲስ እንዳለው፤ ባለፉት ዓመታት ፖለቲካዊ ውጥረቶች ያስከተሏቸው ግጭቶች የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ስጋት ከፍተኛ አድርጎታል። ሙዲስ ግንቦት ላይ የኢትዮጵያን ነጥብ ከቢ1 ወደ ቢ2 ዝቅ አድርጎታል። ለዚህም በምክንያትነት የተቀመጠው ከውጪ ምንዛሪ ገቢ ይልቅ እዳ ማመዘኑ ነው። ነሐሴ ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ኢትዮጵያ አሉታዊ ግምት ተሰጥቷታል። ወረርሽኙ በግብርና እና በመስተንግዶ ዘርፍ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት ገቢው ቢቀንስም ወጪው መናሩ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ሳትደርስ ታላቁ ህዳሴ ግድብን መሙላት መጀሯም ተጠቅሷል። በተያያዥም አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች ሳይወሰዱ ሙሌቱ መጀመሩ የውጪ አገራት ኢንቨስትመንቶች እንዲቀንሱ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት መድባ የነበረው እርዳታ ላይ እገዳ መጣሏን ይፋ አድርጋለች። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በጥሩ ሁኔታ ማስቀጠል መቻሏ ወደ አገሪቱ ኢንቨስትመንት እየሳበ መሆኑን ሙዲስ ገልጿል። ለዓመታት በመሠረተ ልማት ዝርጋታው ዘርፍ የውጪ ኢንቨስትመንት ከሳበች በኋላ፤ አይኤምኤፍ በፍጥነት ምጣኔ ሀብታቸው እያደገ ያሉ ካላቸው የአፍሪካ አገሮች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች። ሙዲስ የተባለው ተቋም ዓለም አቀፋዊ በሆኑ በተለያዩ የፋይናንስና ምጣኔ ሃብት እንዲሁም የብድር ጉዳዮች ላይ ምርምሮችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በመነሳትም የአገራትን የብድር አዋጭነት ደረጃ ያወጣል። ሙዲስ በዓለም ላይ ካሉ ከሦስቱ ተሰሚነት ካላቸው ተመሳሳይ ተቋማት አንዱ ሲሆን አገራትና መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ሙዲስን የመሳሰሉ የምጣኔ ሀብትና የፋይናንስ ተቋማት በሚያወጧቸው ትንተናዎችና ደረጃዎች ላይ በመመርኮዝ ቁልፍ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ። | ኢኮኖሚ ፡ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖ ሊኖረው እንደሚችል ሙዲስ ጠቆመ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫውን ማራዘሟን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት በአገሪቱ የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ውሳኔዎች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል ሙዲስ የተሰኘው የአሜሪካ የቢዝነስና ፋይናንስ ተቋም ጠቆመ። አገራዊው ምርጫ በኮሮናቫይረስ ምክንያት ቢራዘምም ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ተካሂዷል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ ምርጫውን “ሕገ ወጥ” ማለታቸው እንዲሁም የፌደሬሽን ምክር ቤት "ምርጫው እንዳልተካሄደ ይቆጠራል" እንደተባለ ይታወሳል። ሙዲስ እንዳለው፤ ባለፉት ዓመታት ፖለቲካዊ ውጥረቶች ያስከተሏቸው ግጭቶች የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ስጋት ከፍተኛ አድርጎታል። ሙዲስ ግንቦት ላይ የኢትዮጵያን ነጥብ ከቢ1 ወደ ቢ2 ዝቅ አድርጎታል። ለዚህም በምክንያትነት የተቀመጠው ከውጪ ምንዛሪ ገቢ ይልቅ እዳ ማመዘኑ ነው። ነሐሴ ላይ በኮቪድ-19 ምክንያት ኢትዮጵያ አሉታዊ ግምት ተሰጥቷታል። ወረርሽኙ በግብርና እና በመስተንግዶ ዘርፍ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት ገቢው ቢቀንስም ወጪው መናሩ እንደ ምክንያት ተጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ ከግብጽና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ሳትደርስ ታላቁ ህዳሴ ግድብን መሙላት መጀሯም ተጠቅሷል። በተያያዥም አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች ሳይወሰዱ ሙሌቱ መጀመሩ የውጪ አገራት ኢንቨስትመንቶች እንዲቀንሱ ሊያደርግ እንደሚችል ተገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ቀደም ሲል አሜሪካ ለኢትዮጵያ ለመስጠት መድባ የነበረው እርዳታ ላይ እገዳ መጣሏን ይፋ አድርጋለች። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን በጥሩ ሁኔታ ማስቀጠል መቻሏ ወደ አገሪቱ ኢንቨስትመንት እየሳበ መሆኑን ሙዲስ ገልጿል። ለዓመታት በመሠረተ ልማት ዝርጋታው ዘርፍ የውጪ ኢንቨስትመንት ከሳበች በኋላ፤ አይኤምኤፍ በፍጥነት ምጣኔ ሀብታቸው እያደገ ያሉ ካላቸው የአፍሪካ አገሮች ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ትገኝበታለች። ሙዲስ የተባለው ተቋም ዓለም አቀፋዊ በሆኑ በተለያዩ የፋይናንስና ምጣኔ ሃብት እንዲሁም የብድር ጉዳዮች ላይ ምርምሮችን በማድረግ የሚታወቅ ሲሆን ከዚህ በመነሳትም የአገራትን የብድር አዋጭነት ደረጃ ያወጣል። ሙዲስ በዓለም ላይ ካሉ ከሦስቱ ተሰሚነት ካላቸው ተመሳሳይ ተቋማት አንዱ ሲሆን አገራትና መዋዕለ ነዋይ አፍሳሾች ሙዲስን የመሳሰሉ የምጣኔ ሀብትና የፋይናንስ ተቋማት በሚያወጧቸው ትንተናዎችና ደረጃዎች ላይ በመመርኮዝ ቁልፍ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-54170608 |
0business
| አማዞን 'ከሂትለር ጋር ይመሳሰላል' የተባለውን የመተግበሪያ አርማውን ቀየረ | አማዞን የመገበያያ መተግበሪያው አርማ አዶልፍ ሂትለር ጋር ይመሳሰላል በሚል በርካቶች አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ አርማውን መቀየሩን አስታውቋል። ኩባንያው ይህንን የመተግበሪያ አርማ በቅርቡ ነው ያስተዋወቀው። ጥር ላይ የተዋወቀው ይህ አርማ የአማዞን የፈገግታ ምልክት ላይ ሰማያዊ የዕቃ ማሸጊያ ፕላስተር የተለጠፈበት ነው። ሆኖም አንዳንዶች የቀድሞውን የናዚ አምባገነን ሂትለር ፂም ጋር ይመሳሰላል በሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የቴክኖሎጂ ኩባንያው ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዚግዛግ መስመር የነበረበትን ሰማያዊ ፕላስተር የታጠፈ እንዲሆን በማድረግ አሻሽሎታል። አማዞን ለቢቢሲ እንዳስታወቀው የመጀመሪያው ዲዛይን ሲቀየር በአንዳንድ አገራት መሞከሩን ነው። ኮሊ ፖርቴል ቤል የተባለው የማስታወቂያ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቪኪ ቡሌን በበኩላቸው "በሚያሳዝን ሁኔታ ለአማዞን በመጀመሪያ አርማቸው ላይ የተለጠፈው ሰማያዊ ፕላስተር ከሂትለር ሪዝ ጋር ተመሳሳይ ሆኗል። ይሄ ቅርፅ በህሊናችን ውስጥ የማይረሳ ሆኗል። በተለይም በየቤቱ ዕቃ ለሚያደርስ ኩባንያ ይህ ጥሩ መመሳሰል አይደለም" ብለዋል። ከዚህ ቀደም በተንቀሳቃሽ ስልኮችና ታብሌቶች ላይ የሚታየው የኩባንያው መተግበሪያ አርማ የዕቃ ጋሪ ነበር። አዲሱ ዲዛይን መነሻ ያደረገው የአማዞን ቡናማ የዕቃ መጠቅለያ ካርቶን፣ የኩባንያው ታዋቂ የፈገግታ ምልክትና ሰማያዊ ፕላስተር ነበር። "አዲሱን አርማ ዲዛንይን ስናደርግ ደንበኞቻችን ዕቃቸው በራቸው በሚደርስበት ወቅት የሚያሳዩትን ደስታ በሚሸምቱበትም ወቅት ያንኑ እንዲያሳዩ ለማድረግ ነው" ብሏል አንድ ደንበኛ እንዳለው "ቤተሰቦቼ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ ነው አማዞንን የሚጠቀሙት። በሚቀጥሉት ቀናትም ግራ የሚጋቡ ይመስለኛል። አማዞን የት ሄደ ሲሉኝ፤ የሂትለርን ምስል እንዲያዩ እነግራቸዋለሁ" ብሏል ሌላ ደንበኛ በበኩሉ " ዚግዛግ ምልክት ያለው ፕላስተር ስለሆነ አይደለም ነገር ግን ቅርፁም ሆነ አጠቃላይ ነገሩ የሚስቅ አዶልፍ ሂትለርን ነው የሚመስለው" ብሏል። የኩባንያዎች ዲዛይንን በመስራት የሚታወቀው ስቱዲዮ ኤልደብልዩ ዲ መስራች ላውራ ዌልደን በበኩላቸው "ኩባንያዎች አርማቸውን በተለያየ ጊዜ ይቀያይራሉ። አማዞን ደንበኞቹን መስማቱ መልካም ነገር ነው። ደንበኞችን ቅድሚያ በመስጠት ይህንን ማድረጋቸው የኩባንያውን ጥሩ አሰራር የሚያሳይ ነው" ብለዋል። | አማዞን 'ከሂትለር ጋር ይመሳሰላል' የተባለውን የመተግበሪያ አርማውን ቀየረ አማዞን የመገበያያ መተግበሪያው አርማ አዶልፍ ሂትለር ጋር ይመሳሰላል በሚል በርካቶች አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ አርማውን መቀየሩን አስታውቋል። ኩባንያው ይህንን የመተግበሪያ አርማ በቅርቡ ነው ያስተዋወቀው። ጥር ላይ የተዋወቀው ይህ አርማ የአማዞን የፈገግታ ምልክት ላይ ሰማያዊ የዕቃ ማሸጊያ ፕላስተር የተለጠፈበት ነው። ሆኖም አንዳንዶች የቀድሞውን የናዚ አምባገነን ሂትለር ፂም ጋር ይመሳሰላል በሚል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። የቴክኖሎጂ ኩባንያው ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ዚግዛግ መስመር የነበረበትን ሰማያዊ ፕላስተር የታጠፈ እንዲሆን በማድረግ አሻሽሎታል። አማዞን ለቢቢሲ እንዳስታወቀው የመጀመሪያው ዲዛይን ሲቀየር በአንዳንድ አገራት መሞከሩን ነው። ኮሊ ፖርቴል ቤል የተባለው የማስታወቂያ ኩባንያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቪኪ ቡሌን በበኩላቸው "በሚያሳዝን ሁኔታ ለአማዞን በመጀመሪያ አርማቸው ላይ የተለጠፈው ሰማያዊ ፕላስተር ከሂትለር ሪዝ ጋር ተመሳሳይ ሆኗል። ይሄ ቅርፅ በህሊናችን ውስጥ የማይረሳ ሆኗል። በተለይም በየቤቱ ዕቃ ለሚያደርስ ኩባንያ ይህ ጥሩ መመሳሰል አይደለም" ብለዋል። ከዚህ ቀደም በተንቀሳቃሽ ስልኮችና ታብሌቶች ላይ የሚታየው የኩባንያው መተግበሪያ አርማ የዕቃ ጋሪ ነበር። አዲሱ ዲዛይን መነሻ ያደረገው የአማዞን ቡናማ የዕቃ መጠቅለያ ካርቶን፣ የኩባንያው ታዋቂ የፈገግታ ምልክትና ሰማያዊ ፕላስተር ነበር። "አዲሱን አርማ ዲዛንይን ስናደርግ ደንበኞቻችን ዕቃቸው በራቸው በሚደርስበት ወቅት የሚያሳዩትን ደስታ በሚሸምቱበትም ወቅት ያንኑ እንዲያሳዩ ለማድረግ ነው" ብሏል አንድ ደንበኛ እንዳለው "ቤተሰቦቼ በየቀኑ በሚባል ሁኔታ ነው አማዞንን የሚጠቀሙት። በሚቀጥሉት ቀናትም ግራ የሚጋቡ ይመስለኛል። አማዞን የት ሄደ ሲሉኝ፤ የሂትለርን ምስል እንዲያዩ እነግራቸዋለሁ" ብሏል ሌላ ደንበኛ በበኩሉ " ዚግዛግ ምልክት ያለው ፕላስተር ስለሆነ አይደለም ነገር ግን ቅርፁም ሆነ አጠቃላይ ነገሩ የሚስቅ አዶልፍ ሂትለርን ነው የሚመስለው" ብሏል። የኩባንያዎች ዲዛይንን በመስራት የሚታወቀው ስቱዲዮ ኤልደብልዩ ዲ መስራች ላውራ ዌልደን በበኩላቸው "ኩባንያዎች አርማቸውን በተለያየ ጊዜ ይቀያይራሉ። አማዞን ደንበኞቹን መስማቱ መልካም ነገር ነው። ደንበኞችን ቅድሚያ በመስጠት ይህንን ማድረጋቸው የኩባንያውን ጥሩ አሰራር የሚያሳይ ነው" ብለዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-56272133 |
2health
| ባለሙያዎች በኮቪድ ምክንያት የጠፋን የማሽተት ስሜት ለመመለስ 'የማሽተት ሥልጠና' ውሰዱ አሉ | በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ የማሽተት ስሜታቸውን በፍጥነት መመለስ ያልቻሉ ሰዎች የማሽተት ሥልጠና እንዲወስዱ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ሰጡ። ባለሙያዎቹ የማሽተት ስሜትን ለመመለስ የስትሮይድስ ህክምና ከመከታተል ይልቅ 'የማሽተት ስልጠና' መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የማሽተት ስልጠና ለወራት የተለያዩ ሽታዎችን በማሽተት አእምሮን እንደገና በማሰልጠን የተለያዩ ሽታዎችን እንዲለይ የማድረግ ሂደት ነው። የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚለው የማሽተት ስልጠና ዋጋው ርካሽ እና ሂደቱም ቀላል ነው። ከስቴሮይድስ ሕክምና ጋር ሲነጻጸርም፤ የማሽተት ስልጠናው የጎንዮሽ ጉዳቶች የሉትም። ከትኩሳት እና ከማያቋርጥ ሳል በተጨማሪ የመሽተት እና የጠዓም ስሜት ማጣት ከኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ማሽተት አለመቻል ብዙውን ጊዜ ሕመሙ ካለፈ በኋላ በፍጥነት ይመለሳል። ሆኖም ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ከህመሙ ከስምንት ሳምንት በኋላም የማሽተት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። የኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ ኖርዊች የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት እንደሚሉት ኮርቲኮስትሮይድስ ማሽተትን የመመለስ አቅሙ በጣም ጥቂት ነው። "የታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ከቫይረሱ በኋላ በሚመጣ የማሽተት ስሜት ማጣትን ለማከም መታዘዝ የለባቸውም ብለን እንመክራለን" ብለዋል። "እንደ ዕድል ሆኖ በኮቪድ-19 የተነሳ ሽታ ማጣት የሚገጥማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች በፍጥነት የማሽተት ስሜታቸውን መልሰው ያገኛሉ" ብለዋል። ከስቴሮይድ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የደም ግፊት እና የስሜት መለዋወጥ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ዓለም አቀፍ የአለርጂ እና ሪህኖሎጂ ኦረም መጽሔት ላይ በወጣው ጽሑፍ መሠረት ተመራማሪዎቹ "የማሽተት ሥልጠና"ን በአማራጭነት አቅርበዋል። ይህም ተለይተው የሚታወቁ እና በቀላሉ የሚለዩ ሽታ ያላቸውን አራት ነገሮችን ማሽተትን ያካትታል። ለምሳሌ ብርቱካን፣ አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቡናን በቀን ሁለት ጊዜ ማሽተት። ፕሮፌሰር ፊልፖት እንዳሉት ጥናቶች 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ከስድስት ወር በኋላ የማሽተት ስሜታቸውን ሙሉ በሙሉ መልሰው ያገኛሉ። በዚህ ጊዜ ካልተመለሰ ግን አእምሮ ሽታ እንዲለይ እና የተለያዩ ሽታዎችን እንደገና እንዲያውቅ "የማሸተት ስልጠና" ይረዳል። | ባለሙያዎች በኮቪድ ምክንያት የጠፋን የማሽተት ስሜት ለመመለስ 'የማሽተት ሥልጠና' ውሰዱ አሉ በኮቪድ-19 መያዛቸውን ተከትሎ የማሽተት ስሜታቸውን በፍጥነት መመለስ ያልቻሉ ሰዎች የማሽተት ሥልጠና እንዲወስዱ ባለሙያዎች ምክረ ሃሳብ ሰጡ። ባለሙያዎቹ የማሽተት ስሜትን ለመመለስ የስትሮይድስ ህክምና ከመከታተል ይልቅ 'የማሽተት ስልጠና' መውሰዱ የተሻለ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህ የማሽተት ስልጠና ለወራት የተለያዩ ሽታዎችን በማሽተት አእምሮን እንደገና በማሰልጠን የተለያዩ ሽታዎችን እንዲለይ የማድረግ ሂደት ነው። የዓለም አቀፉ የባለሙያዎች ቡድን እንደሚለው የማሽተት ስልጠና ዋጋው ርካሽ እና ሂደቱም ቀላል ነው። ከስቴሮይድስ ሕክምና ጋር ሲነጻጸርም፤ የማሽተት ስልጠናው የጎንዮሽ ጉዳቶች የሉትም። ከትኩሳት እና ከማያቋርጥ ሳል በተጨማሪ የመሽተት እና የጠዓም ስሜት ማጣት ከኮሮናቫይረስ ዋና ዋና ምልክቶች መካከል ተጠቃሾች ናቸው። ማሽተት አለመቻል ብዙውን ጊዜ ሕመሙ ካለፈ በኋላ በፍጥነት ይመለሳል። ሆኖም ከአምስት ሰዎች መካከል አንዱ ከህመሙ ከስምንት ሳምንት በኋላም የማሽተት ችግር እያጋጠማቸው መሆኑን ሪፖርት አድርገዋል። የኢስት አንግሊያ ዩኒቨርሲቲ ኖርዊች የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባው ፕሮፌሰር ካርል ፊልፖት እንደሚሉት ኮርቲኮስትሮይድስ ማሽተትን የመመለስ አቅሙ በጣም ጥቂት ነው። "የታወቁ የጎንዮሽ ጉዳቶች ስላሉት ከቫይረሱ በኋላ በሚመጣ የማሽተት ስሜት ማጣትን ለማከም መታዘዝ የለባቸውም ብለን እንመክራለን" ብለዋል። "እንደ ዕድል ሆኖ በኮቪድ-19 የተነሳ ሽታ ማጣት የሚገጥማቸው አብዛኛዎቹ ሰዎች በፍጥነት የማሽተት ስሜታቸውን መልሰው ያገኛሉ" ብለዋል። ከስቴሮይድ የጎንዮሽ ጉዳቶች መካከል የደም ግፊት እና የስሜት መለዋወጥ ተጠቃሽ ችግሮች ናቸው። ዓለም አቀፍ የአለርጂ እና ሪህኖሎጂ ኦረም መጽሔት ላይ በወጣው ጽሑፍ መሠረት ተመራማሪዎቹ "የማሽተት ሥልጠና"ን በአማራጭነት አቅርበዋል። ይህም ተለይተው የሚታወቁ እና በቀላሉ የሚለዩ ሽታ ያላቸውን አራት ነገሮችን ማሽተትን ያካትታል። ለምሳሌ ብርቱካን፣ አዝሙድ፣ ነጭ ሽንኩርት እና ቡናን በቀን ሁለት ጊዜ ማሽተት። ፕሮፌሰር ፊልፖት እንዳሉት ጥናቶች 90 በመቶ የሚሆኑት ሰዎች ከስድስት ወር በኋላ የማሽተት ስሜታቸውን ሙሉ በሙሉ መልሰው ያገኛሉ። በዚህ ጊዜ ካልተመለሰ ግን አእምሮ ሽታ እንዲለይ እና የተለያዩ ሽታዎችን እንደገና እንዲያውቅ "የማሸተት ስልጠና" ይረዳል። | https://www.bbc.com/amharic/56870718 |
5sports
| በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፉ ቡድኖች ከ32 ወደ 36 ያድጋል ተባለ | በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2024/25 የውድድር ዓመት ጀምሮ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ቁጥር ከ34 ወደ 36 ከፍ እንደሚል የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታወቀ። በአዲሱ ሕግ መሰረት ተሳታፊ ቡድኖቹ በ10 የውድድር ሳምንታት ውስጥ ስምንት ጊዜ የሚጫወቱ ይሆናል። ነገር ግን ከየሊጉ ሁለት ተጨማሪ ቡድኖችን በውድድሩ ባላቸው ታሪክ አወዳድሮ ለማስገባት ታስቦ የነበረው እቅድ ተግባራዊ አይሆንም ተብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማሕበር ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሴፍሪን ስለ አዲሱ ሕግ ሲናገሩ ''ሁሉም ክለቦች የመሳተፍ ህልማቸውን ማሳካት ይችላሉ'' ብለዋል። በዚህም ቡድኖች ከዚህ በፊት ለዓመታት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ያላቸውን ታሪክ ከግምት ውስጥ ከማስገባት ይልቅ በየሊጋቸው ያላቸው ነጥብ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚኖራቸው ተሳትፎ እንደሚያስመርጣቸው ተገልጿል። ለምሳሌ ከ2024/25 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አዲሱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና የሆላንድ ኤርዲቪሲ ተጨማሪ ሁለት ክለቦችን ማሳተፍ ይችላሉ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ ከሳምንታት በኋላ በሚጠናቀቀው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ብዙ ክለቦችን ያሳተፉትና ውጤታማ ሆነው መጓዝ የቻሉት ከእንግሊዝ እንዲሁም ከሆላንድ ሊግ የመጡ ክለቦች በመሆናቸው ነው። ስለዚህ አምስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት ክለቦች በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ እድል ይሰጣቸዋል ማለት ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እንደሚለው አምስተኛ ሆነው ጨርሰው በቀጥታ ከሚያልፉት ሁለት ቡድኖች በተጨማሪ ቀሪዎቹ ሁለት ቡድኖች ደግሞ በውድድር ዓመቱ በሁሉም የአውሮፓ ሊጎች አምስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት ተወዳድረው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ አሰራር ይዘረጋል። ማሕበሩ መጀመሪያ ላይ አቅርቦት የነበረውን ቡድኖች ባላቸው ታሪክ ላይ የመመስረት ሀሳብ ትልልቅ ክለቦችን ብቻ ለማካተት የተደረገ ነው በሚል የቀረበበትን ከፍተኛ ተቃውሞና ትችት ተከትሎ ነው ሃሳቡ ውድቅ የሆነው። ይህ ሕግ ተፈጻሚ የሚሆን ቢሆን ኖሮ በአውሮፓ መድረክ ለዓመታት ጎልተው መታየት የቻሉ ትልቅ ክለቦች በሊጋቸው ደካማ አቋም ቢያሳዩ እንኳን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድል ያስገኝላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በምድብ ድልድሉ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ከ6 ወደ 10 ከፍ እንዲል መደረጉን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል። ምንም እንኳን እንደ ሊቨርፑል ያሉ ክለቦች የጨዋታዎች መደራረብ ተጫዋቾችን ለጉዳት እያጋለጠ ነው የሚል ቅሬታ ቢያሰሙም ማህበሩ ግን እንደውም የጨዋታዎችን ቁጥር እንደሚጨምር ገልጿል። አዲስ የቀረበው ሕግ በሁሉም በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ የየአገራቱ ሊጎች እንዲሁም ብሄራዊ የእግር ኳስ ማህበራት በሙሉ ድምጽ ድጋፍ ማግኘቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል። በሌላ በኩል በቀድሞው ሕግ መሰረት ቡድኖች በስምነት ምድቦች ተደልድለው ከየምድቦቹ ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ሁለት ቡዶኖች ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ ነበር የሚደረገው። በአዲሱ ሕግ መሰረት ግን ይህ ይቀራል ተብሏል። በአዲሱ አሰራር ቡድኖች በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ተዘጋጅቶላቸው የሚወዳደሩ ይሆናል። ቡድኖቹ ስምንት ጨዋታዎችን የሚያደርጉ ሲሆን አራት በሜዳቸው አራት ደግሞ ከሜዳቸው ውጪ ማለት ነው። በመጀመሪያው ዙር ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ። በደረጃ ሰንጠረዡ ከዘጠነኛ እስከ 24ኛ ቦታ ይዘው የሚያጠናቅቁት ቡድኖች ደግሞ በደርሶ መልስ ተጫውተው አሸናፊዎቹ 8 ቡድኖች ደግሞ ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላሉ። | በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፉ ቡድኖች ከ32 ወደ 36 ያድጋል ተባለ በፈረንጆቹ አቆጣጠር ከ2024/25 የውድድር ዓመት ጀምሮ በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚሳተፉ ክለቦች ቁጥር ከ34 ወደ 36 ከፍ እንደሚል የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታወቀ። በአዲሱ ሕግ መሰረት ተሳታፊ ቡድኖቹ በ10 የውድድር ሳምንታት ውስጥ ስምንት ጊዜ የሚጫወቱ ይሆናል። ነገር ግን ከየሊጉ ሁለት ተጨማሪ ቡድኖችን በውድድሩ ባላቸው ታሪክ አወዳድሮ ለማስገባት ታስቦ የነበረው እቅድ ተግባራዊ አይሆንም ተብሏል። የአውሮፓ እግር ኳስ ማሕበር ፕሬዝደንት አሌክሳንደር ሴፍሪን ስለ አዲሱ ሕግ ሲናገሩ ''ሁሉም ክለቦች የመሳተፍ ህልማቸውን ማሳካት ይችላሉ'' ብለዋል። በዚህም ቡድኖች ከዚህ በፊት ለዓመታት በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ያላቸውን ታሪክ ከግምት ውስጥ ከማስገባት ይልቅ በየሊጋቸው ያላቸው ነጥብ እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የሚኖራቸው ተሳትፎ እንደሚያስመርጣቸው ተገልጿል። ለምሳሌ ከ2024/25 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አዲሱ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ቢሆን ኖሮ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ እና የሆላንድ ኤርዲቪሲ ተጨማሪ ሁለት ክለቦችን ማሳተፍ ይችላሉ። ይህ የሚሆንበት ምክንያት ደግሞ ከሳምንታት በኋላ በሚጠናቀቀው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ውድድር ብዙ ክለቦችን ያሳተፉትና ውጤታማ ሆነው መጓዝ የቻሉት ከእንግሊዝ እንዲሁም ከሆላንድ ሊግ የመጡ ክለቦች በመሆናቸው ነው። ስለዚህ አምስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት ክለቦች በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ እድል ይሰጣቸዋል ማለት ነው። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር እንደሚለው አምስተኛ ሆነው ጨርሰው በቀጥታ ከሚያልፉት ሁለት ቡድኖች በተጨማሪ ቀሪዎቹ ሁለት ቡድኖች ደግሞ በውድድር ዓመቱ በሁሉም የአውሮፓ ሊጎች አምስተኛ ሆነው የሚያጠናቅቁት ተወዳድረው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግን እንዲቀላቀሉ የሚያደርግ አሰራር ይዘረጋል። ማሕበሩ መጀመሪያ ላይ አቅርቦት የነበረውን ቡድኖች ባላቸው ታሪክ ላይ የመመስረት ሀሳብ ትልልቅ ክለቦችን ብቻ ለማካተት የተደረገ ነው በሚል የቀረበበትን ከፍተኛ ተቃውሞና ትችት ተከትሎ ነው ሃሳቡ ውድቅ የሆነው። ይህ ሕግ ተፈጻሚ የሚሆን ቢሆን ኖሮ በአውሮፓ መድረክ ለዓመታት ጎልተው መታየት የቻሉ ትልቅ ክለቦች በሊጋቸው ደካማ አቋም ቢያሳዩ እንኳን በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የመሳተፍ ዕድል ያስገኝላቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ በምድብ ድልድሉ ቡድኖች የሚያደርጉት ጨዋታ ከ6 ወደ 10 ከፍ እንዲል መደረጉን የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር አስታውቋል። ምንም እንኳን እንደ ሊቨርፑል ያሉ ክለቦች የጨዋታዎች መደራረብ ተጫዋቾችን ለጉዳት እያጋለጠ ነው የሚል ቅሬታ ቢያሰሙም ማህበሩ ግን እንደውም የጨዋታዎችን ቁጥር እንደሚጨምር ገልጿል። አዲስ የቀረበው ሕግ በሁሉም በአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ስራ አስፈጻሚ አባላት፣ የየአገራቱ ሊጎች እንዲሁም ብሄራዊ የእግር ኳስ ማህበራት በሙሉ ድምጽ ድጋፍ ማግኘቱን የማህበሩ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል። በሌላ በኩል በቀድሞው ሕግ መሰረት ቡድኖች በስምነት ምድቦች ተደልድለው ከየምድቦቹ ከፍተኛ ነጥብ ያላቸው ሁለት ቡዶኖች ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ ነበር የሚደረገው። በአዲሱ ሕግ መሰረት ግን ይህ ይቀራል ተብሏል። በአዲሱ አሰራር ቡድኖች በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ተዘጋጅቶላቸው የሚወዳደሩ ይሆናል። ቡድኖቹ ስምንት ጨዋታዎችን የሚያደርጉ ሲሆን አራት በሜዳቸው አራት ደግሞ ከሜዳቸው ውጪ ማለት ነው። በመጀመሪያው ዙር ከአንድ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁት ቡድኖች በቀጥታ ወደ ቀጣዩ ዙር ያልፋሉ። በደረጃ ሰንጠረዡ ከዘጠነኛ እስከ 24ኛ ቦታ ይዘው የሚያጠናቅቁት ቡድኖች ደግሞ በደርሶ መልስ ተጫውተው አሸናፊዎቹ 8 ቡድኖች ደግሞ ቀጣዩን ዙር ይቀላቀላሉ። | https://www.bbc.com/amharic/news-61404524 |
0business
| በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ጀመረ | የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እሁድ የካቲት 13/2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ይህ ግንባታው አስራ አንድ ዓመታት ያህል ባስቆጠረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ትልቅ ምዕራፍ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ ባለሥልጣናት በቤንሻንጉል ጉሙዝ በጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት መጀመሩ ተበስሯል። በባለፉት ሁለት ዓመታት ክረምት ወቅቶች ሙሌቱ የተከናወነውና ለዓመታት በቀጣናው የውዝግብ ምንጭ የሆነው ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በይፋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል አንዱ ተርባይን ነው ከተሳካ ተከላ እና ሙከራ በኋላ የመጀመሪያውን ኃይል የማመንጨት ሥራ የጀመረው። ይህ ሥራ የጀመረው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። የ13ቱም ተርባይኖች ግንባታ ሲጠናቀቅ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የማመንጨት አቅም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት እንደሚደርስ የተገለጸ ሲሆን ይህም በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ አመንጪ ያደርገዋል። በኢትዮጵያውያን የቦንድ ግዥና በመንግሥት በጀት እየተገነባ ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እስካሁንድ ደረስ 163 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበትም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ግድቡ ግንባታ ጅማሮው ላይ በ80 ቢሊዮን ብር ወጪ ይገነባል የሚል ዕቅድም ተይዞ ነበር። ግድቡ 145 ሜትር ከፍታና ወደ ጎን ደግሞ 1 ሺህ 780 ሜትር ርዝመት ሜትር አለው። ግድቡ የሚይዘውን 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ሙሉ በሙሉ ሲይዝም ውሃው የሚተኛበት ስፍራ ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር እንደሚደርስም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኃይል ማመንጨት ጅማሮውን አስመልክቶ ባስተላፉት መልዕክትም "ዛሬ የአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ የሕዳሴ ግድብ ሥራውን ጀምሯል። ይህ ለአህጉራችን እንዲሁም አብረናቸው ሠርተን በጋራ ለመጠቀም ለምንሻ የታችኛው ተፋሰስ አገራት የምሥራች ነው። "አባይ ወንዛችንን አገራችንን አልምቶ ጎረቤቶቻችንን ሊያረሰርስ ጉዞውን ቀጥሏል። ዛሬ ለኢትዮጵያ የብርሀን መባቻ ነውና መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን!" ብለዋል። ለዓመታት ያህል በግብፅ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የሦስትዮሽ ድርድር የተካሄደበት ታላቁ ግድብ ጉዳዩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲፈታ ተመርቶ ነበር። በሦስቱ አገራት መካከል የነበረው የሦስትዮሽ ድርድር አፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ በተለያዩ አሸማጋዮች እልባት እንዲያገኝ ቢሞከርም ሊቋጭ አልቻለም፤ አሁንም በእንጥልጥል ላይ ይገኛል። በተለይም ከሙሌቱ ጋር ተያያይዞ አሳሪ ስምምነት ሳይኖር መከናወን የለበትም በሚል ግብፅና ሱዳን ቢሞግቱም በ2012 እና በ2013 ክረምቶች ሙሌቱ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ ተገልጿል። ለግንባታው ከ4.5 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በ2012 ዓ.ም 4.9 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዙ በወቅቱ ተገልጿል። የግድቡ ቁመትም ከባህር ጠለል በላይ 565 ሜትር ደርሶ ነበር። የሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታው ሂደት ወደ 84 በመቶ መድረሱም ተገልጿል። ግድቡ የውሃ የመያዙ አቅሙ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን ለባለፈው ዓመት ክረምትም 13.5 ቢሊዮን ያህል ውሃ ሙሌት ታቅዶ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ክረምት ላይም የውሃ ሙሌቱን በተመለከተ ግቧን ማሳካቷን አሳውቃለች ፤ ይህም ማለት ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል በቂ ውሃ አለ ማለት ነው። ይህም ውሃ በታችኛው ተፋሰሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያደርስና የመጀመሪያ ደረጃ የግድቡ የውሃ ሙሌት መመሪያም የተወሰደው ሦስቱ አገራት ከተስማሙበት የግድብ ትብብር መግለጫ ስምምነት መሆኑንም በወቅቱ ኢትዮጵያ ጠቅሳለች። ለዓመታት ያህል በግብፅ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ፍሬ ሳያፈራ የቀረ ሲሆን ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌቱን ተከትሎ ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ወደ ተመድ የፀጥታ ጉባኤ ምክር ቤት ወስደውት ነበር። በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ሲደረግ የነበረው ድርድር ምንም ፍሬ አላፈራም ሲሉም ነበር ወደ ምክር ቤቱ ጉዳዩን የወሰዱት። ምክር ቤቱ የሕዳሴ ግድብን ውዝግብ ከተለያዩ ወገኖች ከሰማ በኋላ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ወደ አፍሪካ ሕብረት እንዲመለሱ ምክር ለግሶ ልኳቸዋል። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ግብፅ የቅኝ ግዛት ውሎችን ሙጥኝ እንዳለችና ኢ-ፍትሃዊና አግላይ የሆነውን ስምምነት ተቀባይነት እንዲያገኝ ጫና እያደረገች ነው በማለትም ትወቀሳለች። ባልነበረችበት የተፈረመ ስምምነት ለአባይ ወንዝ 77 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ለምታመነጨው ኢትዮጵያ ምንም ድርሻ የማይሰጥና ተፈጥሯዊም ሆነ ሕጋዊ መብቴን የሚነጥቅ ነው በማለትም ኢትዮጵያ ትከራከራለች። ግብፅ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውና፣ የአብዛኛውን የውሃውን ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት አጥብቃ በመያዝ ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርህ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት አላትም ስትል ኢትዮጵያ ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ደብዳቤ ወቅሳለች። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ያላካተተ ከመሆኑ በተጨማሪ ግብጽ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንዲሁም ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንድታገኝና 86 በመቶ የአባይን ውሃ የምትገብረውን ኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያስቀር አግላይና ኢፍትሃዊ ስምምነት ነው፤ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊነትንም ይጥሳል -ትላለች ኢትዮጵያ። ግብፅ ግድቡ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቴን ይቀንሰዋል እንዲሁም ለእርሻ የሚያስፈልገኝ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በየዓመቱ ይገባኛል ስትል የቆየች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ አሜሪካ በነበረው ድርድር 31 ቢሊዮን ኪዩቡክ ውሃ በዓመት ለመልቀቅ ሃሳብ አቅርባ ነበር። ግብፅ በተጨማሪ ከምታነሳቸው ቅሬታዎች መካከል ኢትዮጵያ ግድቡን ሙሉ አቅም እየተጠቀመች ድርቅ ቢያጋጥም ችግሩ የሦስቱም አገራት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ላይ መድረሷን ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ድርቅ የሚከሰት ከሆነ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጥቅምን ለመጠበቅ ዋስትና ልትሰጠን ይገባል በማለትም ግብፅ ትከራከራለች። ኢትዮጵያ በበኩሏ የግብፅ ሃሳብ በአባይ ወንዝ ላይ ተፈጥሯዊ መብት እንዳይኖራት ወይም ምንም ዓይነት የውሃ ልማት ያልተገነባበት ፍሰት እንዲኖር የሚጠብቅ ነው በማለትም ተችታለች። | በአፍሪካ ግዙፉ የኃይል ማመንጫ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ኤሌክትሪክ ማመንጨት ጀመረ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ እሁድ የካቲት 13/2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀመረ። ይህ ግንባታው አስራ አንድ ዓመታት ያህል ባስቆጠረው የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ትልቅ ምዕራፍ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ የተለያዩ ባለሥልጣናት በቤንሻንጉል ጉሙዝ በጉባ ወረዳ በታደሙበት ዝግጅት ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኃይል ማመንጨት መጀመሩ ተበስሯል። በባለፉት ሁለት ዓመታት ክረምት ወቅቶች ሙሌቱ የተከናወነውና ለዓመታት በቀጣናው የውዝግብ ምንጭ የሆነው ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በይፋ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ጀምሯል። ግድቡ ካሉት 13 ተርባይኖች መካከል አንዱ ተርባይን ነው ከተሳካ ተከላ እና ሙከራ በኋላ የመጀመሪያውን ኃይል የማመንጨት ሥራ የጀመረው። ይህ ሥራ የጀመረው ተርባይን 375 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም እንዳለው ተገልጿል። የ13ቱም ተርባይኖች ግንባታ ሲጠናቀቅ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የማመንጨት አቅም 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት እንደሚደርስ የተገለጸ ሲሆን ይህም በአፍሪካ ውስጥ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ አመንጪ ያደርገዋል። በኢትዮጵያውያን የቦንድ ግዥና በመንግሥት በጀት እየተገነባ ያለው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ እስካሁንድ ደረስ 163 ቢሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበትም የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል። ግድቡ ግንባታ ጅማሮው ላይ በ80 ቢሊዮን ብር ወጪ ይገነባል የሚል ዕቅድም ተይዞ ነበር። ግድቡ 145 ሜትር ከፍታና ወደ ጎን ደግሞ 1 ሺህ 780 ሜትር ርዝመት ሜትር አለው። ግድቡ የሚይዘውን 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ሙሉ በሙሉ ሲይዝም ውሃው የሚተኛበት ስፍራ ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር እንደሚደርስም ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ኃይል ማመንጨት ጅማሮውን አስመልክቶ ባስተላፉት መልዕክትም "ዛሬ የአፍሪካ ትልቁ የኃይል ማመንጫ የሕዳሴ ግድብ ሥራውን ጀምሯል። ይህ ለአህጉራችን እንዲሁም አብረናቸው ሠርተን በጋራ ለመጠቀም ለምንሻ የታችኛው ተፋሰስ አገራት የምሥራች ነው። "አባይ ወንዛችንን አገራችንን አልምቶ ጎረቤቶቻችንን ሊያረሰርስ ጉዞውን ቀጥሏል። ዛሬ ለኢትዮጵያ የብርሀን መባቻ ነውና መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን!" ብለዋል። ለዓመታት ያህል በግብፅ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል የሦስትዮሽ ድርድር የተካሄደበት ታላቁ ግድብ ጉዳዩ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት እንዲፈታ ተመርቶ ነበር። በሦስቱ አገራት መካከል የነበረው የሦስትዮሽ ድርድር አፍሪካ ሕብረትን ጨምሮ በተለያዩ አሸማጋዮች እልባት እንዲያገኝ ቢሞከርም ሊቋጭ አልቻለም፤ አሁንም በእንጥልጥል ላይ ይገኛል። በተለይም ከሙሌቱ ጋር ተያያይዞ አሳሪ ስምምነት ሳይኖር መከናወን የለበትም በሚል ግብፅና ሱዳን ቢሞግቱም በ2012 እና በ2013 ክረምቶች ሙሌቱ በተሳካ ሁኔታ መከናወኑ ተገልጿል። ለግንባታው ከ4.5 ቢሊዮን ዶላር በጀት የተያዘለት ታላቁ ሕዳሴ ግድብ በ2012 ዓ.ም 4.9 ቢሊዮን ሜትር ኪዩቢክ ሜትር ውሃ መያዙ በወቅቱ ተገልጿል። የግድቡ ቁመትም ከባህር ጠለል በላይ 565 ሜትር ደርሶ ነበር። የሕዳሴ ግድብ አጠቃላይ የግንባታው ሂደት ወደ 84 በመቶ መድረሱም ተገልጿል። ግድቡ የውሃ የመያዙ አቅሙ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ሲሆን ለባለፈው ዓመት ክረምትም 13.5 ቢሊዮን ያህል ውሃ ሙሌት ታቅዶ ነበር። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ክረምት ላይም የውሃ ሙሌቱን በተመለከተ ግቧን ማሳካቷን አሳውቃለች ፤ ይህም ማለት ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል በቂ ውሃ አለ ማለት ነው። ይህም ውሃ በታችኛው ተፋሰሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያደርስና የመጀመሪያ ደረጃ የግድቡ የውሃ ሙሌት መመሪያም የተወሰደው ሦስቱ አገራት ከተስማሙበት የግድብ ትብብር መግለጫ ስምምነት መሆኑንም በወቅቱ ኢትዮጵያ ጠቅሳለች። ለዓመታት ያህል በግብፅ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ሲደረግ የነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ፍሬ ሳያፈራ የቀረ ሲሆን ሁለተኛውን ዙር የውሃ ሙሌቱን ተከትሎ ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ወደ ተመድ የፀጥታ ጉባኤ ምክር ቤት ወስደውት ነበር። በአፍሪካ ሕብረት ጥላ ስር ሲደረግ የነበረው ድርድር ምንም ፍሬ አላፈራም ሲሉም ነበር ወደ ምክር ቤቱ ጉዳዩን የወሰዱት። ምክር ቤቱ የሕዳሴ ግድብን ውዝግብ ከተለያዩ ወገኖች ከሰማ በኋላ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ወደ አፍሪካ ሕብረት እንዲመለሱ ምክር ለግሶ ልኳቸዋል። ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ግብፅ የቅኝ ግዛት ውሎችን ሙጥኝ እንዳለችና ኢ-ፍትሃዊና አግላይ የሆነውን ስምምነት ተቀባይነት እንዲያገኝ ጫና እያደረገች ነው በማለትም ትወቀሳለች። ባልነበረችበት የተፈረመ ስምምነት ለአባይ ወንዝ 77 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ለምታመነጨው ኢትዮጵያ ምንም ድርሻ የማይሰጥና ተፈጥሯዊም ሆነ ሕጋዊ መብቴን የሚነጥቅ ነው በማለትም ኢትዮጵያ ትከራከራለች። ግብፅ በጎርጎሳውያኑ 1959 የተፈረመውና፣ የአብዛኛውን የውሃውን ድርሻ የሚሰጣትን የቅኝ ግዛት ስምምነት አጥብቃ በመያዝ ታሪካዊ ተጠቃሚነት በሚል መርህ የወንዙን ውሃ ሙሉ በሙሉ በበላይነት ለብቻዋ የመጠቀም ፍላጎት አላትም ስትል ኢትዮጵያ ለተመድ የጸጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ደብዳቤ ወቅሳለች። ስምምነቱ ኢትዮጵያን ያላካተተ ከመሆኑ በተጨማሪ ግብጽ 55.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንዲሁም ሱዳን 18.5 ቢሊዮን ኪዩቢክ ውሃን እንድታገኝና 86 በመቶ የአባይን ውሃ የምትገብረውን ኢትዮጵያ ያለ ውሃ የሚያስቀር አግላይና ኢፍትሃዊ ስምምነት ነው፤ የኢትዮጵያንም ሉዓላዊነትንም ይጥሳል -ትላለች ኢትዮጵያ። ግብፅ ግድቡ የመጠጥ ውሃ አቅርቦቴን ይቀንሰዋል እንዲሁም ለእርሻ የሚያስፈልገኝ 40 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውሃ በየዓመቱ ይገባኛል ስትል የቆየች ሲሆን፤ ኢትዮጵያ በበኩሏ አሜሪካ በነበረው ድርድር 31 ቢሊዮን ኪዩቡክ ውሃ በዓመት ለመልቀቅ ሃሳብ አቅርባ ነበር። ግብፅ በተጨማሪ ከምታነሳቸው ቅሬታዎች መካከል ኢትዮጵያ ግድቡን ሙሉ አቅም እየተጠቀመች ድርቅ ቢያጋጥም ችግሩ የሦስቱም አገራት ጉዳይ ነው የሚል አቋም ላይ መድረሷን ነው። ረዘም ላለ ጊዜ ድርቅ የሚከሰት ከሆነ ኢትዮጵያ የታችኛው ተፋሰስ አገራት ጥቅምን ለመጠበቅ ዋስትና ልትሰጠን ይገባል በማለትም ግብፅ ትከራከራለች። ኢትዮጵያ በበኩሏ የግብፅ ሃሳብ በአባይ ወንዝ ላይ ተፈጥሯዊ መብት እንዳይኖራት ወይም ምንም ዓይነት የውሃ ልማት ያልተገነባበት ፍሰት እንዲኖር የሚጠብቅ ነው በማለትም ተችታለች። | https://www.bbc.com/amharic/news-60413930 |
3politics
| የአልጄሪያው የቀድሞ መሪ አብደላዚዝ ቡቴፍሊካ አረፉ | የቀድሞው የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡቴፍሊካ ከረጅም ጊዜ ሕመም በኋላ በ84 ዓመታቸው አረፉ። ቡቴፍሊካ ከ20 ዓመት በፊት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ ሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት እንዲያደርጉ ጉልህ ሚና መጫወታቸው ይታወሳል። ቡቴፍሊካ አልጄሪያን ለ20 ዓመታት ገደማ ከመሩ በኋላ ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን ለመወዳደር መቅረባቸው ለከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ዳርጓቸው ነበር። ቡቴፍሊካ ከ1940 እስከ 1950ዎቹ አልጄሪያን ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ለማላቀቅ በተደረገው ጦርነት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። በመቀጠልም በ1991 የ200 ሺህ ያህል ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የእርስ በእርስ ጦርነት መገባደዱን ተከትሎ በመጣው ወታደራዊው ግፊት ለፕሬዝዳንትነት በቅተዋል። ፕሬዝዳንቱ በ2005 በስትሮክ ከተመቱ በኋላ ንግግር እና እንቅስቃሴ ማድረግ ላይ ከፍተኛ እክል ስላጋጠማቸው በአደባባይ እምብዛም አይታዩም ነበር። ቡቴፍሊካ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመሩት አገራቸው አልጄሪያ በ1954 ዓ.ም ነፃ ከወጣች በኋላ ነበር። ገና በ20ዎቹ አጋማሽ ላይ ሳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው በወቅቱ የዓለም ወጣቱ ሚኒስትር ተብለውም ነበር። ለ16 ዓመታት በአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው። በ1966 የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቡቴፍሊካ የፍልስጤም መሪ የነበሩትን ያሲር አራፋት ለተባበሩት መንግሥታት ንግግር እንዲያደርጉ የጋበዙበት ሁኔት ታሪካዊ ነበር። በተጨማሪም ቻይና የተባበሩት መንግሥታት መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ በመሟገታቸው እንዲሁም በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የአፓርታይድ አገዛዝን በይፋ በመቃወማቸውም ቡቴፍሊካ ይታወሳሉ። ለኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠታቸውም ይታወቁ ነበር። ቡተፍሊካ በ1970ዎቹ በቀረበባቸው የሙስና ክሶች ምክንያት በስደት የኖሩ ሲሆን በኋላ ላይ ክሶቹ ውድቅ መደረጋቸውን ተከትሎ በ1980ዎቹ ወደ አገራቸው ተመልሰው ከሦስት አስርተ ዓመታት በኋላ የአልጄሪያ የመጀመሪያው የሲቪል መሪ ሆነው ተሹመዋል። የአገሬው ሰው "ቡቴፍ" እያለ የሚጠራቸው የቀድሞው ፕሬዘዳንት በመከላከያው እና በእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ሰላም በማምጣት የአገሪቷን የእርስ በእርስ ጦርነት በዘላቂነት ለመፍታት ችለዋል። ቡቴፍሊካ በ2000 የፕሬዘዳንትነት ዘመንን ለሁለት ጊዜ የሚገድበውን የአልጄሪያን ሕገ-መንግሥት በማሻሻል ለተጨማሪ ሁለት የሥልጣን ዘመናት ቆይታቸውን አራዝመዋል። በመቀጠልም የአረብ አብዮት በመላው ሰሜን አፍሪካ ሲነሳ ቡተፍሊካ ሕዝባዊ ድጎማዎችን በፍጥነት ያሳደጉ ሲሆን ለረጅም ዓመታት የቆየውን የአልጄሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስተው ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የታዩትም ከአራት ዓመት በፊት በአልጄርስ የተገነባውን የባቡር ጣቢያ እና እድሳት ተድርጎለት የነበረው የኬቼዋ መስጊድን ባስመረቁበት ወቅት ሲሆን ይህም በስትሮክ ከተመቱ ከአራት ዓመት በኋላ ነበር። በወቅቱም ታናሽ ወንድማቸው ሰይድ ቡቴፍሊካ ከጀርባ አገሪቷን ይመራ እንደነበር ይታመን ነበር። በሕመም ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንቱ ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ሲሰማ መላው አልጄሪያ በአመጽ ተቀጣጠለች። ታይቶ በማይታወቅ መልኩም በአገር አቀፍ ደረጃ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጉ ነበር። ይህንን ተከትሎም ምርጫውን ለሌላ ጊዜ በማስተላለፍ ብሎም በአንድ ዓመት ውስጥ ሥልጣን ለመልቀቅ ቃል ከገቡ በኋላ ቡቴፍሊካ ከሥልጣን ወርደዋል። ይህም አልጄሪያዊያን ቡቴፍሊካን ለመጨረሻ ግዜ ያዩበት ጊዜ ነበር። | የአልጄሪያው የቀድሞ መሪ አብደላዚዝ ቡቴፍሊካ አረፉ የቀድሞው የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብደላዚዝ ቡቴፍሊካ ከረጅም ጊዜ ሕመም በኋላ በ84 ዓመታቸው አረፉ። ቡቴፍሊካ ከ20 ዓመት በፊት በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል የተካሄደውን ደም አፋሳሽ ጦርነት ተከትሎ ሁለቱ አገራት የሰላም ስምምነት እንዲያደርጉ ጉልህ ሚና መጫወታቸው ይታወሳል። ቡቴፍሊካ አልጄሪያን ለ20 ዓመታት ገደማ ከመሩ በኋላ ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን ለመወዳደር መቅረባቸው ለከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ዳርጓቸው ነበር። ቡቴፍሊካ ከ1940 እስከ 1950ዎቹ አልጄሪያን ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት ለማላቀቅ በተደረገው ጦርነት ውስጥ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል። በመቀጠልም በ1991 የ200 ሺህ ያህል ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የእርስ በእርስ ጦርነት መገባደዱን ተከትሎ በመጣው ወታደራዊው ግፊት ለፕሬዝዳንትነት በቅተዋል። ፕሬዝዳንቱ በ2005 በስትሮክ ከተመቱ በኋላ ንግግር እና እንቅስቃሴ ማድረግ ላይ ከፍተኛ እክል ስላጋጠማቸው በአደባባይ እምብዛም አይታዩም ነበር። ቡቴፍሊካ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ማድረግ የጀመሩት አገራቸው አልጄሪያ በ1954 ዓ.ም ነፃ ከወጣች በኋላ ነበር። ገና በ20ዎቹ አጋማሽ ላይ ሳሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው በመሾማቸው በወቅቱ የዓለም ወጣቱ ሚኒስትር ተብለውም ነበር። ለ16 ዓመታት በአልጄሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ነበራቸው። በ1966 የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የነበሩት ቡቴፍሊካ የፍልስጤም መሪ የነበሩትን ያሲር አራፋት ለተባበሩት መንግሥታት ንግግር እንዲያደርጉ የጋበዙበት ሁኔት ታሪካዊ ነበር። በተጨማሪም ቻይና የተባበሩት መንግሥታት መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ በመሟገታቸው እንዲሁም በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ የነበረውን የአፓርታይድ አገዛዝን በይፋ በመቃወማቸውም ቡቴፍሊካ ይታወሳሉ። ለኔልሰን ማንዴላ ወታደራዊ ሥልጠና በመስጠታቸውም ይታወቁ ነበር። ቡተፍሊካ በ1970ዎቹ በቀረበባቸው የሙስና ክሶች ምክንያት በስደት የኖሩ ሲሆን በኋላ ላይ ክሶቹ ውድቅ መደረጋቸውን ተከትሎ በ1980ዎቹ ወደ አገራቸው ተመልሰው ከሦስት አስርተ ዓመታት በኋላ የአልጄሪያ የመጀመሪያው የሲቪል መሪ ሆነው ተሹመዋል። የአገሬው ሰው "ቡቴፍ" እያለ የሚጠራቸው የቀድሞው ፕሬዘዳንት በመከላከያው እና በእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች መካከል ሰላም በማምጣት የአገሪቷን የእርስ በእርስ ጦርነት በዘላቂነት ለመፍታት ችለዋል። ቡቴፍሊካ በ2000 የፕሬዘዳንትነት ዘመንን ለሁለት ጊዜ የሚገድበውን የአልጄሪያን ሕገ-መንግሥት በማሻሻል ለተጨማሪ ሁለት የሥልጣን ዘመናት ቆይታቸውን አራዝመዋል። በመቀጠልም የአረብ አብዮት በመላው ሰሜን አፍሪካ ሲነሳ ቡተፍሊካ ሕዝባዊ ድጎማዎችን በፍጥነት ያሳደጉ ሲሆን ለረጅም ዓመታት የቆየውን የአልጄሪያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንስተው ነበር። ለመጨረሻ ጊዜ ለሕዝብ የታዩትም ከአራት ዓመት በፊት በአልጄርስ የተገነባውን የባቡር ጣቢያ እና እድሳት ተድርጎለት የነበረው የኬቼዋ መስጊድን ባስመረቁበት ወቅት ሲሆን ይህም በስትሮክ ከተመቱ ከአራት ዓመት በኋላ ነበር። በወቅቱም ታናሽ ወንድማቸው ሰይድ ቡቴፍሊካ ከጀርባ አገሪቷን ይመራ እንደነበር ይታመን ነበር። በሕመም ላይ የነበሩት ፕሬዝዳንቱ ለአምስተኛ የሥልጣን ዘመን እንደሚወዳደሩ ሲሰማ መላው አልጄሪያ በአመጽ ተቀጣጠለች። ታይቶ በማይታወቅ መልኩም በአገር አቀፍ ደረጃ በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጉ ነበር። ይህንን ተከትሎም ምርጫውን ለሌላ ጊዜ በማስተላለፍ ብሎም በአንድ ዓመት ውስጥ ሥልጣን ለመልቀቅ ቃል ከገቡ በኋላ ቡቴፍሊካ ከሥልጣን ወርደዋል። ይህም አልጄሪያዊያን ቡቴፍሊካን ለመጨረሻ ግዜ ያዩበት ጊዜ ነበር። | https://www.bbc.com/amharic/news-58554996 |
5sports
| ፕሪሚየር ሊግ፡ ማን ዋንጫ ያነሳል? ማንስ ከሊጉ ይወርዳል? | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለዋንጫ ከሚደረገው ፉክክር በተጨማሪ በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ እና ላለመውረድ የሚደረገው ትግል እስከ መጨረሻው ሳምንት ድረስ እንደሚዘልቅ እውን ሆኗል። 15 ጨዋታዎች ቀርተዋል። እሁድ የሊጉ ጨዋታዎች ከመጠናቀቃቸው በፊት ሰኞ (ዛሬ) ፣ ማክሰኞ እና ሐሙስ የሚከናወኑ ተስተካካይ ጨዋታዎች አሉ። የትኛው ቡድን ምን ይፈልጋል? ማክሰኞ፡ ሳውዝሃምፕተን ከሊቨርፑል እሑድ፡ ሊቨርፑል ከዎልቭስ እና ማንቸስተር ሲቲ ከአስቶን ቪላ ማንቸስተር ሲቲ ትላንት እሁድ ከዌስት ሃም ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል። አሁንም ግን ሊጉን በበላይነት ከመምራት አላገደውም። ቀሪ ጨዋታውን ካሸነፈ በአምስት ዓመት ውስጥ አራተኛ የሊግ ዋንጫውን ከፍ አድርጎ ይስማል። ሲቲ እስከ እሁድም ላይጠብቅ ይችላል። ማክሰኞ ሴንት ሜሪ ላይ ሊቨርፑል ከተሸነፈ ዋንጫው ኢትሃድ መድረሱ ይረጋገጣል። ዋንጫውን ለማንሳት ሊቨርፑል ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ይገባዋል። ማንቸስተር ሲቲም በእሁዱ ጨዋታ ከአስቶን ቪላ ጋር ነጥብ መጣሉ መረጋገጥ አለበት። "ሊቨርፑልን የመሰለ ቡድን እያለ አራት ጨዋታዎች እየቀሩ ዋንጫ ማንሳት ከባድ ነው። እስከመጨረሻው ፉክክሩ ይቀጥላል። እኛን የሚጠቅመን በሜዳችን መጫወታችን እና የሚወሰነውም በራሳችን መሆኑ ነው" ያለው የሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ነው። "ማንንም አንመለከትም። ራሳችን ጨዋታውን ለማሸነፍ እንሞክራለን። ኢትሃድ ስታዲም እንደሚሞላ እና ደጋፊው ከጎናችን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ።" ከማክሰኞው ጨዋታ በፊት ለሳውዝሃምፕተን መልዕክት ካለው ሲጠየቅም "ሊቨርፑልን 4 ለ 0 አሸንፉ" ብሏል። በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚደረገው ፉክክር ሰኞ፡ ኒውካስል ከአርሴናል ሐሙስ፡ ቼልሲ ከሌስተር እሑድ፡ አርሴናል ከኤቨርተን፣ ቼልሲ ከዋትፎርድ እና ኖርዊች ከስፐርስ አርሴናል ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ከቻለ ከ2016/17 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ይሆናል። ነጥብ ከጣለ ግን ስፐርስ መውረዱን ያረጋገጠውን ኖርዊችን ማሸነፍ ብቻ የአውሮፓ ትልቁ ውድድር ተሳታፊ ያደርገዋል። "እንግሊዝ ውስጥ የቻምፒዮንስ ሊግ ቦታ በጣም ወሳኝ ነው። በሌላ ሊግ ትልቅ ዋንጫ እንደማንሳት ይቆጠራል" ያለው ስፐርሱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ነው። "አርሴናል ዛሬ ይጫወታል። ለጊዜው በሁለት ነጥብ እንበልጣቸዋለን። ካላሸነፉ ዕጣችንን የምንወስነው ራሳችን ነን። ለጊዜው ግን ኳሱ ያለው በእነሱ እጅ ነው።" "የመጨረሻው ጨዋታ ለእኛ ወሳኝ ነው። እንግሊዝ ውስጥ ቀላል ጨዋታ የለም። ወደ ኖርዊች አቅንተን አሸንፈን ሦስት ነጥብ ማግኘት አለብን።" ቼልሲ የቻምፒዮንስ ሊግ ቦታውን ሊያጣ ይችላል። ከሌስተር እና ከዋትፎርድ በሚቀሩት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ካገኘ በቂው ነው። ለዩሮፓ ሊግ እና ለኮንፈረንስ ሊግ የሚደረገው ፉክክር እሁድ፡ ብራይተን ከዌስት ሃም እና ክሪስታል ፓላስ ከማንቸስተር ዩናይትድ ዌስት ሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ዓመት በአውሮፓ መድረክ እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል። ጥያቄው በየትኛው መድረክ የሚለው ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ በመጨረሻው ጨዋታ ክሪስታል ፓላስን ካሸነፈ የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋግጣል። ዌስት ሃም ደግሞ በኮንፈረንስ ሊግ ይሳተፋል። ዌስት ሃም አሸንፎ ማንቸስተር ዩናይትድ ማሸነፍ ካልቻለ ግን የለንደኑ ክለብ ወደ ዩሮፓ ሊግ ዩናይትድ ደግሞ ኮንፈረንስ ሊግ ያመራሉ። "ስድስተኛ ሆነን ካጠናቀቅን ትልቅ ስኬት ነው። ሰባተኛ መሆንም ትልቅ ነው። ስድስተኛ መሆን ከቻልን ግን የበለጠ ጥሩ ነው። በሚቀጥለው ሳምንት እንደምናሳካው ተስፋ አለኝ። ለማሳካትም እንሞክራለን።" ሐሙስ፡ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ እና አስቶን ቪላ ከበርንሌይ እሁድ፡ አርሴናል ከኤቨርተን፣ በሬንትፎርድ ከሊድስ እና በርንሌይ ከኒውካስል ሐሙስ ዕለት የሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የሚወርዱ ቡድኖችን ዕጣ ይወስናል። ኤቨርተን፣ ሊድስ እና በርንሌይ በሁለት ነጥብ ተለያይተው ተቀምጠዋል። በርንሌይ በወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል። በዚህም የሊድስ ዕጣ ፈንታ በሌሎች ይወሰናል። የፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ትላንት እሁድ ከብሬንትፎርድ ያደረገው ጨዋታ አሸንፎ ቢሆን እንደማይወርድ ያረጋግጥ ነበር። ሐሙስ ፓላስን ካሸነፉም በተመሳሳይ ያረጋግጣሉ። "ሐሙስም ያለንን በሙሉ መስጠት አለብን። እስከመጨረሻው እንታገላለን። ዕጣችን እጃችን ነው" ብሏል። በርንሌይ ሐሙስ ምሽት አስቶን ቪላን ገጥሞ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጠና ይወጣል። "በደጋፊያችን ፊት እንደምንጫወት እናውቃለን። ነጥብ ማግኘት አለብን" ያለው የበርንሌይ ተጠባባቂ አሰልጣኝ የሆነው ማይክ ጃክሰን ነው። "በጣም ግልጽ ነው። መሸፋፈን አያስፈልግም። ቀጣዩን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን።" የሊድስ እና የበርንሌይ ፉክክር እስከ መጨረሻው ሳምነት ይቀጥላል። ሊድስ በሬንትፎርድ ሲጫወት በርንሌይ ደግሞ ኒውካስልንን ያስተናግዳል። ቶፎዎቹ ሐሙስ ማሸነፍ ካልቻሉ በመጨረሻው ሳምንት ከአርሴናል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ከባድ ይሆናል። "በርንሌይ ተስተካካይ ጨዋታ አለው። ትላንት አንድ ነጥብ ማግኘታችን ተጽዕኖውን ወደ እነሱ ያዞረዋል" ያለው የሊድሱ አሰልጣን ጄሲ ማርሽ ነው። "ያለነው የሥነ-ልቦና ጦርነት ውስጥ ነው። በሚቀጥለው ሳምንት ያለንን ሁሉ ማውጣት አለብን። ለዚህም ተዘጋጅተናል። ያለንን በሙሉ ለመጨረሻው ጨዋታ አዘጋጅተናል።" | ፕሪሚየር ሊግ፡ ማን ዋንጫ ያነሳል? ማንስ ከሊጉ ይወርዳል? በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ለዋንጫ ከሚደረገው ፉክክር በተጨማሪ በአውሮፓ መድረክ ለመሳተፍ እና ላለመውረድ የሚደረገው ትግል እስከ መጨረሻው ሳምንት ድረስ እንደሚዘልቅ እውን ሆኗል። 15 ጨዋታዎች ቀርተዋል። እሁድ የሊጉ ጨዋታዎች ከመጠናቀቃቸው በፊት ሰኞ (ዛሬ) ፣ ማክሰኞ እና ሐሙስ የሚከናወኑ ተስተካካይ ጨዋታዎች አሉ። የትኛው ቡድን ምን ይፈልጋል? ማክሰኞ፡ ሳውዝሃምፕተን ከሊቨርፑል እሑድ፡ ሊቨርፑል ከዎልቭስ እና ማንቸስተር ሲቲ ከአስቶን ቪላ ማንቸስተር ሲቲ ትላንት እሁድ ከዌስት ሃም ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል። አሁንም ግን ሊጉን በበላይነት ከመምራት አላገደውም። ቀሪ ጨዋታውን ካሸነፈ በአምስት ዓመት ውስጥ አራተኛ የሊግ ዋንጫውን ከፍ አድርጎ ይስማል። ሲቲ እስከ እሁድም ላይጠብቅ ይችላል። ማክሰኞ ሴንት ሜሪ ላይ ሊቨርፑል ከተሸነፈ ዋንጫው ኢትሃድ መድረሱ ይረጋገጣል። ዋንጫውን ለማንሳት ሊቨርፑል ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ይገባዋል። ማንቸስተር ሲቲም በእሁዱ ጨዋታ ከአስቶን ቪላ ጋር ነጥብ መጣሉ መረጋገጥ አለበት። "ሊቨርፑልን የመሰለ ቡድን እያለ አራት ጨዋታዎች እየቀሩ ዋንጫ ማንሳት ከባድ ነው። እስከመጨረሻው ፉክክሩ ይቀጥላል። እኛን የሚጠቅመን በሜዳችን መጫወታችን እና የሚወሰነውም በራሳችን መሆኑ ነው" ያለው የሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ነው። "ማንንም አንመለከትም። ራሳችን ጨዋታውን ለማሸነፍ እንሞክራለን። ኢትሃድ ስታዲም እንደሚሞላ እና ደጋፊው ከጎናችን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ።" ከማክሰኞው ጨዋታ በፊት ለሳውዝሃምፕተን መልዕክት ካለው ሲጠየቅም "ሊቨርፑልን 4 ለ 0 አሸንፉ" ብሏል። በቻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ የሚደረገው ፉክክር ሰኞ፡ ኒውካስል ከአርሴናል ሐሙስ፡ ቼልሲ ከሌስተር እሑድ፡ አርሴናል ከኤቨርተን፣ ቼልሲ ከዋትፎርድ እና ኖርዊች ከስፐርስ አርሴናል ቀሪዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ከቻለ ከ2016/17 በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳታፊ ይሆናል። ነጥብ ከጣለ ግን ስፐርስ መውረዱን ያረጋገጠውን ኖርዊችን ማሸነፍ ብቻ የአውሮፓ ትልቁ ውድድር ተሳታፊ ያደርገዋል። "እንግሊዝ ውስጥ የቻምፒዮንስ ሊግ ቦታ በጣም ወሳኝ ነው። በሌላ ሊግ ትልቅ ዋንጫ እንደማንሳት ይቆጠራል" ያለው ስፐርሱ አሰልጣኝ አንቶኒዮ ኮንቴ ነው። "አርሴናል ዛሬ ይጫወታል። ለጊዜው በሁለት ነጥብ እንበልጣቸዋለን። ካላሸነፉ ዕጣችንን የምንወስነው ራሳችን ነን። ለጊዜው ግን ኳሱ ያለው በእነሱ እጅ ነው።" "የመጨረሻው ጨዋታ ለእኛ ወሳኝ ነው። እንግሊዝ ውስጥ ቀላል ጨዋታ የለም። ወደ ኖርዊች አቅንተን አሸንፈን ሦስት ነጥብ ማግኘት አለብን።" ቼልሲ የቻምፒዮንስ ሊግ ቦታውን ሊያጣ ይችላል። ከሌስተር እና ከዋትፎርድ በሚቀሩት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ካገኘ በቂው ነው። ለዩሮፓ ሊግ እና ለኮንፈረንስ ሊግ የሚደረገው ፉክክር እሁድ፡ ብራይተን ከዌስት ሃም እና ክሪስታል ፓላስ ከማንቸስተር ዩናይትድ ዌስት ሃም እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሚቀጥለው ዓመት በአውሮፓ መድረክ እንደሚሳተፉ አረጋግጠዋል። ጥያቄው በየትኛው መድረክ የሚለው ነው። ማንቸስተር ዩናይትድ በመጨረሻው ጨዋታ ክሪስታል ፓላስን ካሸነፈ የዩሮፓ ሊግ ተሳታፊነቱን ያረጋግጣል። ዌስት ሃም ደግሞ በኮንፈረንስ ሊግ ይሳተፋል። ዌስት ሃም አሸንፎ ማንቸስተር ዩናይትድ ማሸነፍ ካልቻለ ግን የለንደኑ ክለብ ወደ ዩሮፓ ሊግ ዩናይትድ ደግሞ ኮንፈረንስ ሊግ ያመራሉ። "ስድስተኛ ሆነን ካጠናቀቅን ትልቅ ስኬት ነው። ሰባተኛ መሆንም ትልቅ ነው። ስድስተኛ መሆን ከቻልን ግን የበለጠ ጥሩ ነው። በሚቀጥለው ሳምንት እንደምናሳካው ተስፋ አለኝ። ለማሳካትም እንሞክራለን።" ሐሙስ፡ ኤቨርተን ከክሪስታል ፓላስ እና አስቶን ቪላ ከበርንሌይ እሁድ፡ አርሴናል ከኤቨርተን፣ በሬንትፎርድ ከሊድስ እና በርንሌይ ከኒውካስል ሐሙስ ዕለት የሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች የሚወርዱ ቡድኖችን ዕጣ ይወስናል። ኤቨርተን፣ ሊድስ እና በርንሌይ በሁለት ነጥብ ተለያይተው ተቀምጠዋል። በርንሌይ በወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ተስተካካይ ጨዋታ ይቀረዋል። በዚህም የሊድስ ዕጣ ፈንታ በሌሎች ይወሰናል። የፍራንክ ላምፓርድ ቡድን ትላንት እሁድ ከብሬንትፎርድ ያደረገው ጨዋታ አሸንፎ ቢሆን እንደማይወርድ ያረጋግጥ ነበር። ሐሙስ ፓላስን ካሸነፉም በተመሳሳይ ያረጋግጣሉ። "ሐሙስም ያለንን በሙሉ መስጠት አለብን። እስከመጨረሻው እንታገላለን። ዕጣችን እጃችን ነው" ብሏል። በርንሌይ ሐሙስ ምሽት አስቶን ቪላን ገጥሞ ካሸነፈ ከወራጅ ቀጠና ይወጣል። "በደጋፊያችን ፊት እንደምንጫወት እናውቃለን። ነጥብ ማግኘት አለብን" ያለው የበርንሌይ ተጠባባቂ አሰልጣኝ የሆነው ማይክ ጃክሰን ነው። "በጣም ግልጽ ነው። መሸፋፈን አያስፈልግም። ቀጣዩን ጨዋታ ማሸነፍ አለብን።" የሊድስ እና የበርንሌይ ፉክክር እስከ መጨረሻው ሳምነት ይቀጥላል። ሊድስ በሬንትፎርድ ሲጫወት በርንሌይ ደግሞ ኒውካስልንን ያስተናግዳል። ቶፎዎቹ ሐሙስ ማሸነፍ ካልቻሉ በመጨረሻው ሳምንት ከአርሴናል ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ከባድ ይሆናል። "በርንሌይ ተስተካካይ ጨዋታ አለው። ትላንት አንድ ነጥብ ማግኘታችን ተጽዕኖውን ወደ እነሱ ያዞረዋል" ያለው የሊድሱ አሰልጣን ጄሲ ማርሽ ነው። "ያለነው የሥነ-ልቦና ጦርነት ውስጥ ነው። በሚቀጥለው ሳምንት ያለንን ሁሉ ማውጣት አለብን። ለዚህም ተዘጋጅተናል። ያለንን በሙሉ ለመጨረሻው ጨዋታ አዘጋጅተናል።" | https://www.bbc.com/amharic/news-61462123 |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ ሐሰተኛ ዜና በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ደቡብ እስያውያንን የኮቪድ-19 ክትባት እንዳይወስዱ እያደረገ ነው ተባለ | ሐሰተኛ ዜና በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ የተወሰኑ የደቡብ እስያ ማኅበረሰብ አባላት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ላለመውሰድ እንዲያንገራግሩ እያደረገ ነው ሲሉ ሐኪሞች አስጠነቀቁ። ዶ/ር ሀርፕረት ሱድ በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የጤና አገልግሎት ዘርፍ የተሳሳቱ መረጃዎችን በሚያጣራው ቡድን ውስጥ ኃላፊ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን በሚመለከት የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች "በጣም አሳሳቢ ናቸው" ካሉ በኋላ "ይህንን ለማስተካከል እየሰራን ነው" ብለዋል። ለሐሰተኛ መረጃዎቹ መስፋፋት እንደምክንያት የተጠቀሰው የባህልና የቋንቋ ተግዳሮት መኖሩን ነው። በምዕራብ ሚድላንድስ የምትሰራ አንዲት ዶክተር ለቢቢሲ እንደተናገረችው የተወሰኑ ደቡብ እስያውያን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባቱን አንወስድም ሲሉ አንገራግረዋል። በእንግሊዝ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ውስጥ የሚሰሩት ዶ/ር ሱድ፣ እነዚህን ስለክትባቱ የሚነገሩ ሐሰተኛ መረጃዎች ለማስወገድ ከደቡብ እስያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር እየሰሩ ነው። በርካቶቹ የሐሰተኛ መረጃዎች የሚያጠነጥኑት በክትባቱ ይዘት ዙሪያ ነው ተብሏል። እነዚህ የማኅበረሰብ አባላት የእንስሳት ተዋጽኦ እንደማይመገቡ ስለሚታወቅ "ክትባቱ ከላምና ከአሳማ ሥጋ መሰራቱ" እንደተወራ ዶ/ር ሱድ ያስረዳሉ። "በሁሉም የእምነት አባቶች ክትባቱ ተቀባይነት ማግኘቱንና ተከታዮቻቸውም እንዲወስዱት መፍቀዳቸውን በግልጽ ለማኅበረሰቡ አባላት መንገር አለብን" ብለዋል። አክለውም ለማኅበረሰቡ በሚናገሩት ቋንቋ ተተርጉሞ የሚሰራጨው መረጃ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል መድረሱን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ያስረዳሉ። ስለዚህም በየማኅበረሰቡ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪና አርአያ የሆነ ግለሰብ እየፈለግን፣ አንዳቸው ለሌላኛቸው ትክክለኛውን መረጃ በማስተላለፍ የተሳሳተውን መረጃ እንዲቀለብሱ እየሰራን ነው ብለዋል። ቢቢሲ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ ያያቸው የተወሰኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ሐይማኖትን መሰረት ተደርገው የተሰራጩ ናቸው። እነዚህ መልዕክቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት የእንስሳ ተዋጽኦን ይዟል የሚሉ ሲሆን፣ የአሳማ ሥጋ በማይበሉ ሙስሊሞች እና የበሬ ሥጋ በማይበሉ ሂንዱዎች ረገድ ይህ መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ተቀባይነት አግኝቷል። ዶ/ር ሳማራ አፍዛል በምዕራብ ሚድላንድስ ዱድሊ ሰዎችን ስትከትብ "ሁሉንም ሕሙማን ለክትባት ወረፋ እንዲይዙ እንዲደረግ ለሠራተኞቹ ቢነገርም፣ ነገር ግን የደቡብ እስያ ተወላጅ የሆኑ አንዳንድ ሕሙማን ክትባቱን አንወስድም ማለታቸውን ሰምተናል" "ቤተሰባቸውንና ጓደኞቻቸውን ባነጋገርንበትም ወቅት ያገኘነው መረጃም ተመሳሳይ ነው። እኔ ራሴ ጓደኞች አሉኝ፤ ቤተሰቦቹቼ ወይም አያቶቼ ክትባቱን እንዲወስዱ እንዳሳምንላቸው የሚጠይቁኝ" ስትል የገጠማትን ተናግራለች። በሃምፕሻየር የውበት ባለሙያ የሆነችው ሬና ፑጃራ የሂንዱ እምነት ተከታይ ስትሆን በእንደዚህ አይነት ሐሰተኛ መረጃዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ገጿ መጥለቅለቁን ትናገራለች። "ላልተማረ ሰው ግራ አጋቢ ነው። በዚያ ላይ ክትባቱ ከላም ሥጋ እንደተሰራ ሲገነጽ፤ ላም ደግሞ ለእኛ ቅዱስ በመሆኗ የሚረብሽ ነው" ብላለች። 100 መስጂዶች በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ላይ የሚናፈሱ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመመከትና ማኅበረሰቦቻቸው ክትባቱን እንዲወስዱ ለማሳመን ጥምረት ፈጥረዋል። እነዚህ መስጂዶች የአርብ ፀሎትን ለማስተማሪያነት ለመጠቀም ተስማምተዋል። በቅርቡ በሮያል ሶሳይቲ ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ በተደረገ ጥናት ግማሽ ያህል ጥቁሮች፣ እስያውያን እና ሌሎች በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ሕዝቦች የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለመውሰድ ፈቃደኛ ናቸው ይላል። ከ79 በመቶ ነጮች መካከል ደግሞ 57 በመቶዎቹ ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆናቸውን በጥናቱ ላይ ተመልክቷል። | ኮሮናቫይረስ፡ ሐሰተኛ ዜና በዩናይትድ ኪንግደም ያሉ ደቡብ እስያውያንን የኮቪድ-19 ክትባት እንዳይወስዱ እያደረገ ነው ተባለ ሐሰተኛ ዜና በዩናይትድ ኪንግደም የሚኖሩ የተወሰኑ የደቡብ እስያ ማኅበረሰብ አባላት የኮሮናቫይረስ ክትባትን ላለመውሰድ እንዲያንገራግሩ እያደረገ ነው ሲሉ ሐኪሞች አስጠነቀቁ። ዶ/ር ሀርፕረት ሱድ በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የጤና አገልግሎት ዘርፍ የተሳሳቱ መረጃዎችን በሚያጣራው ቡድን ውስጥ ኃላፊ ናቸው። እርሳቸው እንደሚሉት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን በሚመለከት የሚሰራጩ ሐሰተኛ መረጃዎች "በጣም አሳሳቢ ናቸው" ካሉ በኋላ "ይህንን ለማስተካከል እየሰራን ነው" ብለዋል። ለሐሰተኛ መረጃዎቹ መስፋፋት እንደምክንያት የተጠቀሰው የባህልና የቋንቋ ተግዳሮት መኖሩን ነው። በምዕራብ ሚድላንድስ የምትሰራ አንዲት ዶክተር ለቢቢሲ እንደተናገረችው የተወሰኑ ደቡብ እስያውያን የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባቱን አንወስድም ሲሉ አንገራግረዋል። በእንግሊዝ የብሔራዊ ጤና አገልግሎት ውስጥ የሚሰሩት ዶ/ር ሱድ፣ እነዚህን ስለክትባቱ የሚነገሩ ሐሰተኛ መረጃዎች ለማስወገድ ከደቡብ እስያ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሰዎች፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሐይማኖት አባቶች ጋር እየሰሩ ነው። በርካቶቹ የሐሰተኛ መረጃዎች የሚያጠነጥኑት በክትባቱ ይዘት ዙሪያ ነው ተብሏል። እነዚህ የማኅበረሰብ አባላት የእንስሳት ተዋጽኦ እንደማይመገቡ ስለሚታወቅ "ክትባቱ ከላምና ከአሳማ ሥጋ መሰራቱ" እንደተወራ ዶ/ር ሱድ ያስረዳሉ። "በሁሉም የእምነት አባቶች ክትባቱ ተቀባይነት ማግኘቱንና ተከታዮቻቸውም እንዲወስዱት መፍቀዳቸውን በግልጽ ለማኅበረሰቡ አባላት መንገር አለብን" ብለዋል። አክለውም ለማኅበረሰቡ በሚናገሩት ቋንቋ ተተርጉሞ የሚሰራጨው መረጃ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል መድረሱን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ ያስረዳሉ። ስለዚህም በየማኅበረሰቡ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪና አርአያ የሆነ ግለሰብ እየፈለግን፣ አንዳቸው ለሌላኛቸው ትክክለኛውን መረጃ በማስተላለፍ የተሳሳተውን መረጃ እንዲቀለብሱ እየሰራን ነው ብለዋል። ቢቢሲ በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን ላይ ያያቸው የተወሰኑ የተሳሳቱ መረጃዎች ሐይማኖትን መሰረት ተደርገው የተሰራጩ ናቸው። እነዚህ መልዕክቶች የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት የእንስሳ ተዋጽኦን ይዟል የሚሉ ሲሆን፣ የአሳማ ሥጋ በማይበሉ ሙስሊሞች እና የበሬ ሥጋ በማይበሉ ሂንዱዎች ረገድ ይህ መረጃ በስፋት ተሰራጭቶ ተቀባይነት አግኝቷል። ዶ/ር ሳማራ አፍዛል በምዕራብ ሚድላንድስ ዱድሊ ሰዎችን ስትከትብ "ሁሉንም ሕሙማን ለክትባት ወረፋ እንዲይዙ እንዲደረግ ለሠራተኞቹ ቢነገርም፣ ነገር ግን የደቡብ እስያ ተወላጅ የሆኑ አንዳንድ ሕሙማን ክትባቱን አንወስድም ማለታቸውን ሰምተናል" "ቤተሰባቸውንና ጓደኞቻቸውን ባነጋገርንበትም ወቅት ያገኘነው መረጃም ተመሳሳይ ነው። እኔ ራሴ ጓደኞች አሉኝ፤ ቤተሰቦቹቼ ወይም አያቶቼ ክትባቱን እንዲወስዱ እንዳሳምንላቸው የሚጠይቁኝ" ስትል የገጠማትን ተናግራለች። በሃምፕሻየር የውበት ባለሙያ የሆነችው ሬና ፑጃራ የሂንዱ እምነት ተከታይ ስትሆን በእንደዚህ አይነት ሐሰተኛ መረጃዎች የማኅበራዊ ሚዲያ ገጿ መጥለቅለቁን ትናገራለች። "ላልተማረ ሰው ግራ አጋቢ ነው። በዚያ ላይ ክትባቱ ከላም ሥጋ እንደተሰራ ሲገነጽ፤ ላም ደግሞ ለእኛ ቅዱስ በመሆኗ የሚረብሽ ነው" ብላለች። 100 መስጂዶች በኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ላይ የሚናፈሱ ሐሰተኛ መረጃዎችን ለመመከትና ማኅበረሰቦቻቸው ክትባቱን እንዲወስዱ ለማሳመን ጥምረት ፈጥረዋል። እነዚህ መስጂዶች የአርብ ፀሎትን ለማስተማሪያነት ለመጠቀም ተስማምተዋል። በቅርቡ በሮያል ሶሳይቲ ኦፍ ፐብሊክ ሄልዝ በተደረገ ጥናት ግማሽ ያህል ጥቁሮች፣ እስያውያን እና ሌሎች በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ሕዝቦች የኮሮናቫይረስ ክትባትን ለመውሰድ ፈቃደኛ ናቸው ይላል። ከ79 በመቶ ነጮች መካከል ደግሞ 57 በመቶዎቹ ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆናቸውን በጥናቱ ላይ ተመልክቷል። | https://www.bbc.com/amharic/news-55677502 |
3politics
| ለኬንያው ምርጫ በሕይወት የሌሉ ሩብ ሚሊዮን ድምጽ ሰጪዎች ተመዝግበው ተገኙ | ኬንያ ከሁለት ወራት በኋላ ለምታካሂደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሕይወት የሌሉ ከ250 ሺህ በላይ ድምጽ ሰጪዎች ተመዝግበው መገኘቱ ተገለጸ። ኢንዲፔንደንት ኤሌክቶራል እና ባውንደሪስ ኮሚሽን የተሰኘው የኬንያው ገለልተኛ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋም ባወጣው መግለጫ፤ የመራጮች ምዝገባ ላይ ባደረገው ምርመራ በሕይወት የሌሉ ሩብ ሚሊዮን ሰዎች ተመዝግበው አግኝቻለሁ ብሏል። ከዚህ በተጫማሪም ለፕሬዝደንታዊው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡት መካከል ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉት ከአንድ ጊዜ በላይ ተመዝግበው ተገኝተዋል ብሏል። ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋሙ 226 ሺህ ሰዎች ደግሞ የራሳቸው ባልሆኑ ሰነዶች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል። ድምጽ ለመስጠት ብቁ በማያደርጉ ሰነዶች የተመዘገቡ ድምጽ ሰጪዎች መኖራቸውንም ተቋሙ በመግለጫ አመላክቷል። በጠቅላላው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ድምጽ ሰጪዎች ሕጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ ድምጽ ለመስጠት ተመዝገበው ተገኝተዋል። የተቋሙ ሊቀመንበር ዋፉላ ቼቡካቲ ሕጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ መራጮች ተመዝግበው መገኘታቸው ተከትሎ ተቋማቸው የመጨረሻዎቹን መራጮች አረጋግጦ ይፋ የሚያደርግበትን ቀን ያራዝመዋል ብለዋል። ገለልተኛ የሆነው ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋም የድምጽ ሰጪዎችን ዝርዝር አረጋግጦ ዛሬ ሐሙስ ይፋ ማድረግ ነበረበት። በኬንያ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ማጭበርበሮች፣ ምርጫን ተከትሎ ለሚከሰቱ ሁከቶች አንዱ ምክንያት ነበር። ኬንያ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ለምታካሂደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ እና ሥልጣን ላይ ያሉት ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መካከል ጠንካራ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት አገሪቱን እያስተዳደሩ ያሉት ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁለት የሥልጣን ዘመን በማገልገላቸው በምርጫው ተሳታፊ አይሆኑም። | ለኬንያው ምርጫ በሕይወት የሌሉ ሩብ ሚሊዮን ድምጽ ሰጪዎች ተመዝግበው ተገኙ ኬንያ ከሁለት ወራት በኋላ ለምታካሂደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሕይወት የሌሉ ከ250 ሺህ በላይ ድምጽ ሰጪዎች ተመዝግበው መገኘቱ ተገለጸ። ኢንዲፔንደንት ኤሌክቶራል እና ባውንደሪስ ኮሚሽን የተሰኘው የኬንያው ገለልተኛ ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋም ባወጣው መግለጫ፤ የመራጮች ምዝገባ ላይ ባደረገው ምርመራ በሕይወት የሌሉ ሩብ ሚሊዮን ሰዎች ተመዝግበው አግኝቻለሁ ብሏል። ከዚህ በተጫማሪም ለፕሬዝደንታዊው ምርጫ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገቡት መካከል ወደ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉት ከአንድ ጊዜ በላይ ተመዝግበው ተገኝተዋል ብሏል። ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋሙ 226 ሺህ ሰዎች ደግሞ የራሳቸው ባልሆኑ ሰነዶች ድምጽ ለመስጠት መመዝገባቸውን ደርሼበታለሁ ብሏል። ድምጽ ለመስጠት ብቁ በማያደርጉ ሰነዶች የተመዘገቡ ድምጽ ሰጪዎች መኖራቸውንም ተቋሙ በመግለጫ አመላክቷል። በጠቅላላው ከአንድ ሚሊዮን በላይ ድምጽ ሰጪዎች ሕጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ ድምጽ ለመስጠት ተመዝገበው ተገኝተዋል። የተቋሙ ሊቀመንበር ዋፉላ ቼቡካቲ ሕጋዊ አሰራርን ባልተከተለ መልኩ መራጮች ተመዝግበው መገኘታቸው ተከትሎ ተቋማቸው የመጨረሻዎቹን መራጮች አረጋግጦ ይፋ የሚያደርግበትን ቀን ያራዝመዋል ብለዋል። ገለልተኛ የሆነው ምርጫ እና ሕዝበ ውሳኔ አስፈጻሚ ተቋም የድምጽ ሰጪዎችን ዝርዝር አረጋግጦ ዛሬ ሐሙስ ይፋ ማድረግ ነበረበት። በኬንያ ከዚህ ቀደም በተካሄዱ ምርጫዎች ከምርጫ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥሙ ማጭበርበሮች፣ ምርጫን ተከትሎ ለሚከሰቱ ሁከቶች አንዱ ምክንያት ነበር። ኬንያ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ለምታካሂደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ እና ሥልጣን ላይ ያሉት ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መካከል ጠንካራ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት አገሪቱን እያስተዳደሩ ያሉት ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ ሁለት የሥልጣን ዘመን በማገልገላቸው በምርጫው ተሳታፊ አይሆኑም። | https://www.bbc.com/amharic/articles/clkvg9ek0j3o |
2health
| ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ክትባትን በዓለም ለማሰራጨት 8ሺህ ግዙፍ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ | ይበለውና የኮሮና ክትባት ቢሳካ በነገታው እንወጋዋለን ማለት አይደለም፡፡ በመላው ዓለም ማሰራጨቱ በራሱ ሌላ ትልቅ ፈተና ነው ሲል የአቪየሽን ኢንደስትሪ ማኅበር ተናግሯል፡፡ ምናልባትም በአውሮፕላን የካርጎ ታሪክ እጅግ ከባዱ ፈተና፣ እጅግ ከባዱ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) እንደሚለው ምናልባት ክትባቱ ቢሳካ እያንዳንዳቸው የቦይንግ 747 አውሮፕላኖች አይነት ግዝፈትና ፍጥነት ያላቸው 8ሺህ ግዙፍ የካርጎ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ብሏል፤ ክትባቱን ለማዳረስ፡፡ ምንም እንኳ ለጊዜው ክትባት ባይፈበረክም፣ መሳካቱ አይቀርም በሚል የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ነገሮችን ለማቀናጀት ከወዲሁ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡ ማኅበሩ በጤና ዙርያ ከሚሰሩት በርካታ ድርጅቶች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከመድኃኒት አምራቾች፣ ከመድኃኒት አቀባባዮች፣ አከፋፋዮች፣ ከአውሮፕላን ካርጎ ሥራ ተሳታፊዎች ጋር በጥምረት መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ 8ሺህ ቦይንግ ያስፈልጋል የተባለው ታዲያ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ፣ አንድ ጠብታ ክትባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሚል የተሰላ ሲሆን ይህ ግምት ለምሳሌ በእጥፍ ቢጨምር እጥፍ ካርጎ አውሮፕላን ያሻል ማለት ነው፡፡ የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዴ ጁኒያክ እንዲህ ተናግረዋል፣ ‹‹የኮቪድ 19 ክትባትን በጥንቃቄ ማጓጓዝ የዚህ ክፍለ ዘመን ትልቁ የካርጎ ኢንዱስትሪ ግብ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲሁ በዘፈቀደ የሚጓጓዝ አይደለም፤ ከፍተኛ ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ለዝግጅቱ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው›› በርካታ አየር መንገዶች በወረርሽኙ ጊዜ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ወደ ካርጎ ሥራ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይጠቀሳል፡፡ ነገር ግን ማንም እቃ የሚያጓጉዝ አየር መንገድ ክትባትን ማጓጓዝ ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ክትባት ለማጓጓዝ ካርጎው ከ2 እስከ 8 ሴንትግሬድ የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ክትባቶች ደግሞ እጅግ ቀዝቃዛ (ከዜሮ በታች) የሆነ የሙቀት መጠንን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማሟላት ለብዙ አየር መንገዶች ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ዝግጅት ከወዲሁ የተጀመረውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን ክትባት የማጓጓዙን ፈተና ለመቀነስ አንዱ መንገድ አገራት በየራሳቸው ክትባቱን እንዲያመርቱት ማድረግ ቢሆንም ይህ ለብዙ የዓለም አገራት የሚቻል አይሆንም፡፡ በተለይ በርካታ የካርጎ በረራዎች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ ስለሚገኝና ክትባት የማምረት አቅም ያለው አገርም ባለመኖሩ ነው፡፡ ክትባቱን በቀላሉ ወደ አፍሪካ ለማጓጓዝም የሚቻል አይደለም ብሏል ማኅበሩ፡፡ ይህም በቂ የካርጎ አቅም ስለሌለ፣ አፍሪካ ሰፊ አህጉር በመሆኗና የድንበር ውስብስብነት መኖሩ ነው፡፡ የካርጎ ሥራው ልክ ወታደራዊ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው፤ ከተጓጓዘ በኋላም ቢሆን የሚቀመጥበት ቦታ መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓለም ደረጃ 140 ቤተ ሙከራዎች ክትባት ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለት ጀምረው ነበር፡፡ አሁን 24 የሚሆኑት በሰዎች ላይ ሙከራ ጀምረዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የተሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው የክትባት ሙከራ ነው፡፡. ሩሲያ ክትባቱ በእጄ ገብቷል ብትልም ዓለም በአገሪቱ ላይ እምነት በማጣቱ ይመስላል እምብዛምም የራሺያ ክትባት አይወራም፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሩሲያ ክትባት ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ አይደለም፣ ብሔራዊ ኩራተን ከጤና አስበልጧል ሲሉ ይተቹታል፡፡ | ኮሮናቫይረስ፡ የኮሮና ክትባትን በዓለም ለማሰራጨት 8ሺህ ግዙፍ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ይበለውና የኮሮና ክትባት ቢሳካ በነገታው እንወጋዋለን ማለት አይደለም፡፡ በመላው ዓለም ማሰራጨቱ በራሱ ሌላ ትልቅ ፈተና ነው ሲል የአቪየሽን ኢንደስትሪ ማኅበር ተናግሯል፡፡ ምናልባትም በአውሮፕላን የካርጎ ታሪክ እጅግ ከባዱ ፈተና፣ እጅግ ከባዱ ኃላፊነት ይሆናል ተብሏል፡፡ የዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር (IATA) እንደሚለው ምናልባት ክትባቱ ቢሳካ እያንዳንዳቸው የቦይንግ 747 አውሮፕላኖች አይነት ግዝፈትና ፍጥነት ያላቸው 8ሺህ ግዙፍ የካርጎ አውሮፕላኖች ያስፈልጋሉ ብሏል፤ ክትባቱን ለማዳረስ፡፡ ምንም እንኳ ለጊዜው ክትባት ባይፈበረክም፣ መሳካቱ አይቀርም በሚል የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ነገሮችን ለማቀናጀት ከወዲሁ ተፍ ተፍ እያለ ነው፡፡ ማኅበሩ በጤና ዙርያ ከሚሰሩት በርካታ ድርጅቶች፣ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ከመድኃኒት አምራቾች፣ ከመድኃኒት አቀባባዮች፣ አከፋፋዮች፣ ከአውሮፕላን ካርጎ ሥራ ተሳታፊዎች ጋር በጥምረት መስራት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡ ይህ 8ሺህ ቦይንግ ያስፈልጋል የተባለው ታዲያ አንድ ሰው በሕይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ብቻ፣ አንድ ጠብታ ክትባት ብቻ ነው የሚያስፈልገው በሚል የተሰላ ሲሆን ይህ ግምት ለምሳሌ በእጥፍ ቢጨምር እጥፍ ካርጎ አውሮፕላን ያሻል ማለት ነው፡፡ የአየር ትራንስፖርት ማኅበሩ ሥራ አስፈጻሚ አሌክሳንደር ዴ ጁኒያክ እንዲህ ተናግረዋል፣ ‹‹የኮቪድ 19 ክትባትን በጥንቃቄ ማጓጓዝ የዚህ ክፍለ ዘመን ትልቁ የካርጎ ኢንዱስትሪ ግብ ነው፡፡ ነገር ግን እንዲሁ በዘፈቀደ የሚጓጓዝ አይደለም፤ ከፍተኛ ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ለዝግጅቱ ትክክለኛው ጊዜ ደግሞ አሁን ነው›› በርካታ አየር መንገዶች በወረርሽኙ ጊዜ የሰዎች ከቦታ ቦታ እንቅስቃሴ በመታቀቡ ወደ ካርጎ ሥራ ገብተው ቆይተዋል፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይጠቀሳል፡፡ ነገር ግን ማንም እቃ የሚያጓጉዝ አየር መንገድ ክትባትን ማጓጓዝ ይችላል ማለት አይደለም፡፡ ክትባት ለማጓጓዝ ካርጎው ከ2 እስከ 8 ሴንትግሬድ የሙቀት መጠን ሊኖረው ይገባል፡፡ አንዳንድ ክትባቶች ደግሞ እጅግ ቀዝቃዛ (ከዜሮ በታች) የሆነ የሙቀት መጠንን ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ማሟላት ለብዙ አየር መንገዶች ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ ዝግጅት ከወዲሁ የተጀመረውም ለዚሁ ነው፡፡ ይህንን ክትባት የማጓጓዙን ፈተና ለመቀነስ አንዱ መንገድ አገራት በየራሳቸው ክትባቱን እንዲያመርቱት ማድረግ ቢሆንም ይህ ለብዙ የዓለም አገራት የሚቻል አይሆንም፡፡ በተለይ በርካታ የካርጎ በረራዎች ወደ ደቡብ ምሥራቅ ኢሲያ ይደረጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ ስለሚገኝና ክትባት የማምረት አቅም ያለው አገርም ባለመኖሩ ነው፡፡ ክትባቱን በቀላሉ ወደ አፍሪካ ለማጓጓዝም የሚቻል አይደለም ብሏል ማኅበሩ፡፡ ይህም በቂ የካርጎ አቅም ስለሌለ፣ አፍሪካ ሰፊ አህጉር በመሆኗና የድንበር ውስብስብነት መኖሩ ነው፡፡ የካርጎ ሥራው ልክ ወታደራዊ ጥንቃቄን የሚፈልግ ነው፤ ከተጓጓዘ በኋላም ቢሆን የሚቀመጥበት ቦታ መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚሆን መሆን አለበት፡፡ ይህ ደግሞ ለበርካታ የአፍሪካ አገሮች ፈተና ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በዓለም ደረጃ 140 ቤተ ሙከራዎች ክትባት ለመሥራት ተፍ ተፍ ማለት ጀምረው ነበር፡፡ አሁን 24 የሚሆኑት በሰዎች ላይ ሙከራ ጀምረዋል፡፡ ከነዚህ ሁሉ ትልቅ ተስፋ የተሰጠው የኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲው የክትባት ሙከራ ነው፡፡. ሩሲያ ክትባቱ በእጄ ገብቷል ብትልም ዓለም በአገሪቱ ላይ እምነት በማጣቱ ይመስላል እምብዛምም የራሺያ ክትባት አይወራም፡፡ የጤና ባለሙያዎች የሩሲያ ክትባት ሳይንሳዊ ሂደትን የተከተለ አይደለም፣ ብሔራዊ ኩራተን ከጤና አስበልጧል ሲሉ ይተቹታል፡፡ | https://www.bbc.com/amharic/news-54093179 |
3politics
| ሩዋንዳ "በዩኬ የጥገኝነት ስምምነት ላይ በሰዎች እየነገደች አይደለም" ፕሬዚዳንት ካጋሜ | የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አገራቸው የዩኬ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስመልክቶ የገባችውን ስምምነት አስመልክቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት አስተያየት ሀገራቸው "በሰው ልጅ አትነግድም" ብለዋል። በስምምነቱ መሰረት በትንንሽ ጀልባዎች ወደ እንግሊዝ የተሻገሩ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ በማዛወር ጉዳያቸው በዚያ የሚታይ ይሆናል። በሩዋንዳና በዩናይትድ ኪንግደም ተደርሷል የተባለው አወዛጋቢው የ120 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት በአለም አቀፉ ዘንድ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት ትችት ገጥሟቸዋል። ስምምነቱ ሲፈረም በኮንጎ ብራዛቪል፣ጃማይካ እና ባርባዶስ ጉብኝት ላይ የነበሩት ፕሬዚዳንት ካጋሜ - ሩዋንዳ ስደተኞችን ለመቀበል በምላሹ ገንዘብ እያገኘች ነው ብሎ ማሰብ ስህተት ነው ብለዋል። " እኛ በሰው አንነግድም፣ እባካችሁ እርዳታ እየሰጠን ነው " በማለት ከአሜሪካው ብራውን ዩኒቨርስቲ ጋር በበይነ መረብ በነበረ ሴሚናር ላይ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ካጋሜ እንደሚሉት እንግሊዝ ሩዋንዳን የመረጠችበት ምክንያት በሊቢያ ለነበሩ ስደተኞች መጠለያ በመስጠታቸው መሆኑን ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 የአፍሪካ ህብረትን ሲመሩ በነበረበት ወቅት ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩና በሊቢያ መሄጃ ላጡ ስደተኞች ሃገራቸው መጠለያ እንደምትሰጥ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አስታውሰዋል። ይህንን እርምጃም ተከትሎ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ የተወሰዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 2/3ኛ የሚሆኑት ጉዳያቸው አልቆ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ካናዳ አቅንተዋል። ፕሬዚዳንት ካጋሜ አገራቸው እያደረገችው ያለችው ተግባር "የስደት ችግር ላለባቸው" እንደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የተሳካ ሂደት ነበር ሲሉ አወድሰዋል። ሩዋንዳ ህገወጥ የስደተኞች ዝውውርን ለመግታት እየረዳች ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ካጋሜ ዩኬ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን የምትቀበለውን ወይም የማትቀበላቸውን ግለሰቦች ጉዳይም እልባት እስኪገኝ በሩዋንዳ እንደሚቆዩ ጠቁመዋል። የሩዋንዳ ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስምምነቱን "ከእውነታው የራቀ" ከማለት በተጨማሪ የሩዋንዳ መንግሥት "የበለጸጉ አገሮችን ሸክም" ከመፍታት ይልቅ በአካባቢው ችግሮች ላይ እንዲያተኩር ጠይቀዋል። | ሩዋንዳ "በዩኬ የጥገኝነት ስምምነት ላይ በሰዎች እየነገደች አይደለም" ፕሬዚዳንት ካጋሜ የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ አገራቸው የዩኬ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስመልክቶ የገባችውን ስምምነት አስመልክቶ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት አስተያየት ሀገራቸው "በሰው ልጅ አትነግድም" ብለዋል። በስምምነቱ መሰረት በትንንሽ ጀልባዎች ወደ እንግሊዝ የተሻገሩ የጥገኝነት ጠያቂዎችን ወደ ሩዋንዳ በማዛወር ጉዳያቸው በዚያ የሚታይ ይሆናል። በሩዋንዳና በዩናይትድ ኪንግደም ተደርሷል የተባለው አወዛጋቢው የ120 ሚሊዮን ፓውንድ ስምምነት በአለም አቀፉ ዘንድ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን የሁለቱም ሀገራት ባለስልጣናት ትችት ገጥሟቸዋል። ስምምነቱ ሲፈረም በኮንጎ ብራዛቪል፣ጃማይካ እና ባርባዶስ ጉብኝት ላይ የነበሩት ፕሬዚዳንት ካጋሜ - ሩዋንዳ ስደተኞችን ለመቀበል በምላሹ ገንዘብ እያገኘች ነው ብሎ ማሰብ ስህተት ነው ብለዋል። " እኛ በሰው አንነግድም፣ እባካችሁ እርዳታ እየሰጠን ነው " በማለት ከአሜሪካው ብራውን ዩኒቨርስቲ ጋር በበይነ መረብ በነበረ ሴሚናር ላይ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንት ካጋሜ እንደሚሉት እንግሊዝ ሩዋንዳን የመረጠችበት ምክንያት በሊቢያ ለነበሩ ስደተኞች መጠለያ በመስጠታቸው መሆኑን ነው። በአውሮፓውያኑ 2018 የአፍሪካ ህብረትን ሲመሩ በነበረበት ወቅት ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሚሞክሩና በሊቢያ መሄጃ ላጡ ስደተኞች ሃገራቸው መጠለያ እንደምትሰጥ ውሳኔ ላይ መድረሳቸውን አስታውሰዋል። ይህንን እርምጃም ተከትሎ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ወደ ሩዋንዳ የተወሰዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 2/3ኛ የሚሆኑት ጉዳያቸው አልቆ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ካናዳ አቅንተዋል። ፕሬዚዳንት ካጋሜ አገራቸው እያደረገችው ያለችው ተግባር "የስደት ችግር ላለባቸው" እንደ ዩናይትድ ኪንግደም እና ሌሎች የአውሮፓ ሀገራት የተሳካ ሂደት ነበር ሲሉ አወድሰዋል። ሩዋንዳ ህገወጥ የስደተኞች ዝውውርን ለመግታት እየረዳች ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ካጋሜ ዩኬ የጥገኝነት ጥያቄያቸውን የምትቀበለውን ወይም የማትቀበላቸውን ግለሰቦች ጉዳይም እልባት እስኪገኝ በሩዋንዳ እንደሚቆዩ ጠቁመዋል። የሩዋንዳ ሁለት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስምምነቱን "ከእውነታው የራቀ" ከማለት በተጨማሪ የሩዋንዳ መንግሥት "የበለጸጉ አገሮችን ሸክም" ከመፍታት ይልቅ በአካባቢው ችግሮች ላይ እንዲያተኩር ጠይቀዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-61192479 |
0business
| ባለሀብቱ በአሜሪካ ታሪክ ትልቁ በተባለ የታክስ ስወራ ተከሰሱ | አሜሪካዊው ባለሀብት በአገሪቱ ታሪክ ትልቁ በተባለ የታክስ ስወራ ክስ ተመሰረተባቸው። ሮበርት ብሮክማን፤ ሬይኖልድስ ኤንድ ሬይኖልድ የተሰኘ የኮምፒዩተር ሶፍትዌር አምራች ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲሆኑ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት፤ ያገኙትን 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ከአሜሪካ መንግሥት ደብቀዋል ተብሏል። ሮበርት ብሮክማን ከአሜሪካ መንግሥት 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ የሰወሩት ገንዘቡን በሌሎች አገራት ከሚገኙ ኩባንያዎቻቸው የተገኘ በማስመሰል ነው ተብሏል። ብሮክማን በቴሌኮንፍረስን አማካኝነት በሂውስተን ቴክሳስ በሚገኝ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ለቀረቡባቸውን ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው ተከራክረዋል። ባለሀብቱ በአጠቃላይ 39 ክሶች የተመሰረቱባቸው ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የታክስ ስወራ እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ማስመሰል የሚሉት ይገኙበታል። ብሮክማን ይህን የታክስ ስወራ ወንጀል ስለመፈጸማቸውን ለአሜሪካ መንግሥት ጥቆማ ያደሩት ደግሞ ሮበርት ስሚዝ የሚባሉ ሌላ ሚሊየነር የንግድ ሰው ናቸው። ሮበርት ስሚዝ በተመሳሳይ የገቢ ምንጮቻቸውን በመደበቅ ታክስ ሲያጭበረብሩ እንደነበረ ያመኑ ሲሆን፤ መንግሥት ክስ እንዳይመሰርትባቸው ብሮክማን ላይ ጥቆማ ሰጥተዋል ተብሏል። ሮበርት ስሚዝ ጥቆማውን ለአሜሪካ መንግሥት የሰጡት ለፈጸሙት የታክስ ማጭበርበር ክስ እንደማይሰመረትባቸው ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ሮበርት ስሚዝ 139 ሚሊዮን ዶላር በቅጣት መልክ ለአሜሪካ መንግሥት ክፍያ ለመፈጸም ተስማምተዋል። | ባለሀብቱ በአሜሪካ ታሪክ ትልቁ በተባለ የታክስ ስወራ ተከሰሱ አሜሪካዊው ባለሀብት በአገሪቱ ታሪክ ትልቁ በተባለ የታክስ ስወራ ክስ ተመሰረተባቸው። ሮበርት ብሮክማን፤ ሬይኖልድስ ኤንድ ሬይኖልድ የተሰኘ የኮምፒዩተር ሶፍትዌር አምራች ኩባንያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሲሆኑ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት፤ ያገኙትን 2 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ከአሜሪካ መንግሥት ደብቀዋል ተብሏል። ሮበርት ብሮክማን ከአሜሪካ መንግሥት 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ የሰወሩት ገንዘቡን በሌሎች አገራት ከሚገኙ ኩባንያዎቻቸው የተገኘ በማስመሰል ነው ተብሏል። ብሮክማን በቴሌኮንፍረስን አማካኝነት በሂውስተን ቴክሳስ በሚገኝ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ለቀረቡባቸውን ክሶች ጥፋተኛ አይደለሁም ብለው ተከራክረዋል። ባለሀብቱ በአጠቃላይ 39 ክሶች የተመሰረቱባቸው ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የታክስ ስወራ እና በሕገ ወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ ማስመሰል የሚሉት ይገኙበታል። ብሮክማን ይህን የታክስ ስወራ ወንጀል ስለመፈጸማቸውን ለአሜሪካ መንግሥት ጥቆማ ያደሩት ደግሞ ሮበርት ስሚዝ የሚባሉ ሌላ ሚሊየነር የንግድ ሰው ናቸው። ሮበርት ስሚዝ በተመሳሳይ የገቢ ምንጮቻቸውን በመደበቅ ታክስ ሲያጭበረብሩ እንደነበረ ያመኑ ሲሆን፤ መንግሥት ክስ እንዳይመሰርትባቸው ብሮክማን ላይ ጥቆማ ሰጥተዋል ተብሏል። ሮበርት ስሚዝ ጥቆማውን ለአሜሪካ መንግሥት የሰጡት ለፈጸሙት የታክስ ማጭበርበር ክስ እንደማይሰመረትባቸው ከስምምነት ከደረሱ በኋላ ነው ተብሏል። ይሁን እንጂ ሮበርት ስሚዝ 139 ሚሊዮን ዶላር በቅጣት መልክ ለአሜሪካ መንግሥት ክፍያ ለመፈጸም ተስማምተዋል። | https://www.bbc.com/amharic/news-54565664 |
3politics
| የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት በመላው ኢትዮጵያ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በዛሬው ዕለት የካቲት 08/2014 ዓ.ም በይፋ አነሳ። የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላለፉት ሦስት ወራት ያህል ተግባራዊ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል። በዚህም ስብሰባ ላይ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማንሳት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በ63 ተቃውሞ በ21 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲያጥር ምክንያት የሆነውም ለአገሪቱ ስጋት የነበረው "የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት አደጋ" መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱ መሆኑም ተገልጿል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ህወሓት እና አጋሮቹ የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የደቀኑትን አደጋን ለመከላከል እንዲያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014ን ያወጀ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 መጽደቁ ተገልጾ ነበር። አዋጁ በጸደቀበትም ወቅት በአገሪቱ የተደቀነውን የህልውናና እና የሉዓላዊነት አደጋ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥራ መከላከል የማይቻል ሆኖ በመገኘቱም እንደነበር ተጠቅሷል። በአሁኑ ወቅት ያለውን ስጋት በመደበኛው የሕግ ማስከበር ተግባር መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱም ተገልጿል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች ከተቀየሩ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር ይቻላል ብሎ ካመነ የስድስት ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ሥልጣን እንደተሰጠውም ተጠቅሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ሥራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል። በሰሜን ኢትዮጵያ ይካሄድ የነበረው ጦርነት ከትግራይ ክልል ባሻገር ወደ አማራና አፋር ክልሎች መስፋፋቱን ተከትሎ በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በመንግሥት በአሸባሪነት ከተፈረጁት አማጺያን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ይታወሳል። | የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አነሳ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለስድስት ወራት በመላው ኢትዮጵያ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በዛሬው ዕለት የካቲት 08/2014 ዓ.ም በይፋ አነሳ። የኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ6ኛው ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ላለፉት ሦስት ወራት ያህል ተግባራዊ የሆነውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ በአብላጫ ድምፅ ወስኗል። በዚህም ስብሰባ ላይ በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነውን አደጋ ለመከላከል የወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለማንሳት የቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በ63 ተቃውሞ በ21 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲያጥር ምክንያት የሆነውም ለአገሪቱ ስጋት የነበረው "የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት አደጋ" መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱ መሆኑም ተገልጿል። የሚኒስትሮች ምክር ቤት ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም ህወሓት እና አጋሮቹ የአገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የደቀኑትን አደጋን ለመከላከል እንዲያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር 5/2014ን ያወጀ ሲሆን፣ ይህ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ በአዋጅ ቁጥር 1264/2014 መጽደቁ ተገልጾ ነበር። አዋጁ በጸደቀበትም ወቅት በአገሪቱ የተደቀነውን የህልውናና እና የሉዓላዊነት አደጋ በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥራ መከላከል የማይቻል ሆኖ በመገኘቱም እንደነበር ተጠቅሷል። በአሁኑ ወቅት ያለውን ስጋት በመደበኛው የሕግ ማስከበር ተግባር መከላከልና መቆጣጠር የሚቻልበት ደረጃ ላይ በመደረሱ ለስድስት ወራት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተፈፃሚነት ጊዜ ማሳጠር አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱም ተገልጿል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የስድስት ወራት የጊዜ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መታወጅ ምክንያት የሆኑ ሁኔታዎች ከተቀየሩ እና በመደበኛው የሕግ ማስከበር ሥርዓት ሊከሰቱ የሚችሉ ጉዳዮችን መቆጣጠር ይቻላል ብሎ ካመነ የስድስት ወር ጊዜው ሳይጠናቀቅ ጊዜውን የማሳጠር ሥልጣን እንደተሰጠውም ተጠቅሷል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም ጋር ተያይዞ ያላጠናቀቃቸው ጅምር ሥራዎች ካሉ ይህ ውሳኔ ከተላለፈበት ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠናቆ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት እንዲያደርግ ተወስኗል። በሰሜን ኢትዮጵያ ይካሄድ የነበረው ጦርነት ከትግራይ ክልል ባሻገር ወደ አማራና አፋር ክልሎች መስፋፋቱን ተከትሎ በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ በመንግሥት በአሸባሪነት ከተፈረጁት አማጺያን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ይታወሳል። | https://www.bbc.com/amharic/news-60385017 |
5sports
| ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ | አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቢ ብራያንት ከሴት ልጁ ጋር ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ሲጓዝበት የነበረው ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር ህይወቱ አለፈ። የ41 ዓመቱ ብራያንትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ላይ አደጋው የደረሰው ሲጓዙበት የነበረው የግል ሄሊኮፕተር ከተከሰከሰ በኋላ በእሳት ተያይዞ ነው። የሎስ አንጀለስ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከአደጋ በህይወት የተረፈ ሰው የለም። • የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀትና የልብ ህመም ተጋላጭ ናቸው ተባለ • የትራምፕን የክስ ሂደት በቀላሉ እንዲገነዘቡ የሚረዱ 5 ወሳኝ ጥያቄዎች • የአፍ ጭምብል ማጥለቅ ከቫይረስ ይታደገን ይሆን? ብራያንት ለታዋቂው ሎስ አንጀለስ ሌከርስ የቅርጫት ኳስ ቡድን በመጫወት አምስት ጊዜ ሻምፒዮን ለመሆን በመቻሉ በውድድሩ ታሪክ ውስጥም ታላላቅ ከሚባሉ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ ስፖርተኛ ነበር። በርካቶች በብራያንት ድንገተኛ ሞት ድንጋጤያቸውን እየገለጹ ሲሆን ታዋቂ ግለሰቦችን ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው። የስፖርተኛው ሞት እንደተነገረም በመላው አሜሪካ በሚካሄዱ የቅርጫት ኳስ ውድድሮች ላይ ለብርያንት የህሊና ጸሎት ተደርጎለታል። የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ውድድር የበላይ አካል የሆነው ኤንቢኤ የብራያንትን ሞት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ማህበሩ በስፖርተኛውና በ13 ዓመት ታዳጊ ልጁ ሞት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል። መግለጫው "ላለፉት 20 የውድድር ወቅቶች ኮቤ ተሰጥኦንና ለስፖርቱ ያለውን ሁሉ በማድረግ አሸናፊ መሆን እንደሚቻል አሳይቷል" ሲል ብራያንትን አስታውሶታል። ብራያንት ለ20 ዓመታት በዘለቀው የቅርጫት ኳስ ህይወቱ የተጫወተው ሎስ አንጀለስ ሌከርስ ለተባለው ቡድን ብቻ የነበረ ሲሆን ከአራት ዓመት በፊት መጫወት አቁሟል። በተለያዩ ጊዜያት በቅርጫት ኳስ ውድድር ባሳየው ችሎታው የኮከብነት ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ሁለት ጊዜ በኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ የአሸናፊነትን ክብር ተጋርቷል። ብራያንት ከሁለት ዓመት በፊት 'ዲር ባስኬትቦል' በሚል ለቅርጫት ኳስ ስፖርት ያለውን ፍቅር በሚያሳየውና በእራሱ በተጻፈው አጭር ፊልም የኦስካር ሽልማትን ለማግኘት ችሎ ነበር። ኮቢ ብራያንት በአደጋው አብራው ህይወቷ ካለፈው ሴት ልጁ በተጨማሪ የሌሎች ሦስት ሴት ልጆች አባት ነው። | ታዋቂው አሜሪካዊ ስፖርተኛ ከነልጁ በሄሊኮፕተር አደጋ ሞተ አሜሪካዊው የቅርጫት ኳስ ኮከብ ኮቢ ብራያንት ከሴት ልጁ ጋር ካሊፎርኒያ ግዛት ውስጥ ሲጓዝበት የነበረው ሄሊኮፕተር ተከስክሶ ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር ህይወቱ አለፈ። የ41 ዓመቱ ብራያንትና አብረውት የነበሩት ሰዎች ላይ አደጋው የደረሰው ሲጓዙበት የነበረው የግል ሄሊኮፕተር ከተከሰከሰ በኋላ በእሳት ተያይዞ ነው። የሎስ አንጀለስ ፖሊስ እንዳስታወቀው ከአደጋ በህይወት የተረፈ ሰው የለም። • የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀትና የልብ ህመም ተጋላጭ ናቸው ተባለ • የትራምፕን የክስ ሂደት በቀላሉ እንዲገነዘቡ የሚረዱ 5 ወሳኝ ጥያቄዎች • የአፍ ጭምብል ማጥለቅ ከቫይረስ ይታደገን ይሆን? ብራያንት ለታዋቂው ሎስ አንጀለስ ሌከርስ የቅርጫት ኳስ ቡድን በመጫወት አምስት ጊዜ ሻምፒዮን ለመሆን በመቻሉ በውድድሩ ታሪክ ውስጥም ታላላቅ ከሚባሉ ተጫዋቾች መካከል የሚጠቀስ ስፖርተኛ ነበር። በርካቶች በብራያንት ድንገተኛ ሞት ድንጋጤያቸውን እየገለጹ ሲሆን ታዋቂ ግለሰቦችን ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው። የስፖርተኛው ሞት እንደተነገረም በመላው አሜሪካ በሚካሄዱ የቅርጫት ኳስ ውድድሮች ላይ ለብርያንት የህሊና ጸሎት ተደርጎለታል። የአሜሪካ የቅርጫት ኳስ ውድድር የበላይ አካል የሆነው ኤንቢኤ የብራያንትን ሞት ተከትሎ ባወጣው መግለጫ ማህበሩ በስፖርተኛውና በ13 ዓመት ታዳጊ ልጁ ሞት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል። መግለጫው "ላለፉት 20 የውድድር ወቅቶች ኮቤ ተሰጥኦንና ለስፖርቱ ያለውን ሁሉ በማድረግ አሸናፊ መሆን እንደሚቻል አሳይቷል" ሲል ብራያንትን አስታውሶታል። ብራያንት ለ20 ዓመታት በዘለቀው የቅርጫት ኳስ ህይወቱ የተጫወተው ሎስ አንጀለስ ሌከርስ ለተባለው ቡድን ብቻ የነበረ ሲሆን ከአራት ዓመት በፊት መጫወት አቁሟል። በተለያዩ ጊዜያት በቅርጫት ኳስ ውድድር ባሳየው ችሎታው የኮከብነት ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ሁለት ጊዜ በኦሊምፒክ ላይ ተሳትፎ የአሸናፊነትን ክብር ተጋርቷል። ብራያንት ከሁለት ዓመት በፊት 'ዲር ባስኬትቦል' በሚል ለቅርጫት ኳስ ስፖርት ያለውን ፍቅር በሚያሳየውና በእራሱ በተጻፈው አጭር ፊልም የኦስካር ሽልማትን ለማግኘት ችሎ ነበር። ኮቢ ብራያንት በአደጋው አብራው ህይወቷ ካለፈው ሴት ልጁ በተጨማሪ የሌሎች ሦስት ሴት ልጆች አባት ነው። | https://www.bbc.com/amharic/news-51260529 |