id
stringlengths
8
14
url
stringlengths
36
42
title
stringlengths
8
90
summary
stringlengths
6
505
text
stringlengths
133
19.2k
news-52932157
https://www.bbc.com/amharic/news-52932157
ጊኒ ቢሳው፡ የገዛ ጄኔራሎቿ አደገኛ እጽ የሚነግዱባት አገር
ባለፈው ጥር ወር በአንድ ጀምበር በተደረገ አሰሳ የተገኘው ነገር አስደንጋጭ ነበር።
ሃያ መርሴዲስ ቤንዝ ቅንጡ መኪኖች፣ በባንክ የተደበቀ 3 ሚሊዮን ዶላር፣ 90 ሺህ ዶላር የሚያወጣ ውስኪና ወይን። ነገር ግን ከሁሉ የሚያስደነግጠው ይህ አይደለም። 1 ነጥብ 8 ቶን የሚመዝን ኮኬንይን መገኘቱ ነው አነጋጋሪ የሆነው። ይህ ፍርድ ቤት ይፋ ያደረገው መረጃ ነው። በጊኒ ቢሳው በኩል ወደ አሜሪካና አውሮፓ የሚሾልከው የአደገኛ እጽ መጠን አስደንጋጭ እየሆነ መጥቷል። ማቆሙም ፈተና ሆኗል። ባለፈው ወር በተደረገው ልዩ ዘመቻ የተያዙት 12 አደገኛ የእጽ አስተላላፊዎች የጊኒ ዜጎች ብቻ አልነበሩም። ፖርቹጋሎች፣ የሜክሲኮና ኮሎምቢያ ሰዎችም ነበሩበት። ይህ በዚያች አገር ያለው የእጽ ዝውውር ምን ያህል ዓለም አቀፋዊ ትስስር እንዳለው አመልካች ሆኗል። ከተከሳሾቹ መካከል ሁለቱ በሌሉበት ተፈርዶባቸዋል። ጊኒ ቢሳው በወንጀለኞቹ ላይ የወሰደችው እርምጃ ተደንቆላታል። ሆኖም የዚያች አገር እንጀራ፣ የዚያች ትንሽ አገር ፖለቲካና ምጣኔ ሀብት ኮኬንይን እንዳይሆን ስጋት አለ። 'ጄኔራሎቹ ኮኬይን ይነግዳሉ' አንቶኒ ማዛቶሊ በጊኒ ቢሳዎ የተባበሩት መነግሥታት ድርጅት የአገሪቱን የጸረ አደገኛ እጽ ዘመቻ ይመራሉ። "ይህ ሰሞኑን ይፋ የተደረገው የአደገኛ እጽ መረብን የመበጣጠስ እርምጃ እንደ መጀመሪያ ስኬት ቀላል ግምት የምንሰጠው አይሆንም። ስምንት ዓመት የፈጀ ጉዳይ ነው። ጊኒ ቢሳውን በቀጣይነት ከአደገኛ እጽ የማስተላለፊያ ወደብነት ነጻ ለማድረግ አንድ እርምጃ ነው" ብለዋል። ጊኒ ቢሳው ለማስተላለፊያነት የተመቸ መለክአ ምድራዊ አቀማመጥ ነው ያላት። ከብራዚል፣ ከኮሎምቢያ፣ ከቬንዝዌላ፣ ከኢኳዶርና ከፔሩ ወደ ስፔን፣ ፈረንሳይ እና ጣሊያን መጠኑ ከፍ ያለ ኮኬይን ለማሸጋገር እንደ ጊኒ የሚመች አገር የለም። ይህቺ የቀድሞው የፖርቱጋል ቅኝ ግዛት ጊኒ ቢሳው በአሜሪካና በተባበሩት መንግሥታትም ጭምር የአደገኛ እጽ ወደብ በሚል ተሰይማ ነበር። "ናርኮስቴት" ይሏታል። መዋቅሩ ሁሉ በአደገኛ እጽ ሰንሰለት የተተበተበ አገር እንደማለት ነው። በአፍሪካ እንዲህ ዓይነት ስም የተሰጣት ብቸኛዋ አገር ጊኒ ቢሳው ናት። የጊኒ ቢሳዎ ደሴቶች የእጽ ማስተላለፊያ አመቺ ቦታዎች ናቸው ይባላል ይህ ስም የዛሬ 10 ዓመት ነበር ለጊኒ ከአሜሪካና ከተባበሩት መንግሥታት ጭምር የተሰጣት። አሁን ግን ነገሮችን ለመቆጣጠርና ስሟን ለማደስ የተጀመሩ ሙከራዎች አሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚያች አገር ባለፈው የካቲት በተደረገ አጨቃጫቂ ምርጫ ኡማሩ ሲሶኮ አሸንፈዋል። የእርሳቸው ወደ ሥልጣን መምጣት አደገኛ እጽ ዝውውር ላይ የተከፈተውን ጦርነት ቀዝቃዛ ውሃ እንዳይቸልስበት ተፈርቷል። ፍርሃቱ ያለ ምክንያት አልመጣም። ምንም እንኳ አዲሱ ፕሬዝዳንት በአደገኛ እጽ የዝውውር ሰንሰለት እጃቸው እንዳለበት የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ ባይኖርም ዋና ዋና የጦር ጄኔራሎች ለእርሳቸው ድጋፍ መስጠታቸው ምናልባት በእጽ ዝውውር የሚታሙት እነዚያው የጦር መሪዎች ንግዱን በአዲስ መልክ እንዳያጧጡፉት ተሰግቷል። በተለይ ባለፈው በመፈንቅለ መንግሥት ሥልጣን ይዘው የነበሩት ኢታማዡር ሹሙ አንቶኒዮ ኢንጃይ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ድጋፍ መስጠታቸው አዲስ ጥርጣሬን ፈጥሯል። ኢታማዡር ሹሙ የእጽ ዝውውሩ ላይ እስከ አንገታቸው ተዘፍቀዋል ተብለው ይታማሉ። ጄኔራል ኢንጃይ ግን ክሱን ያስተባብላሉ። ጊኒና ኮኬይን ጊኒ ቢሳዎ ከፖርቱጋል የቅኝ አገዛዝ ቀንበር ነጸ የወጣቸው በ1970ዎቹ መጀመርያ ነበር። ከዚያ በኋላ 9 መፈንቅለ መንግሥት አስተናግዳለች። ይህም በመሆኑ የዚያች አገር ተቋማት ልፍስፍስ ሆነው ቆይተዋል። የተቋማቱ መልፈስፈስ ደግሞ የእጽ ዝውውሩ እንዲሳለጥ የተመቻቸ ሁኔታን ፈጥሯል። ጊኒ ቢሳዎ የምዕራብ አፍሪካ አገር ናት። የሕዝብ ብዛቷ አንድ ሚሊዮን ተኩል ሲሆን ፖርቹጊዝ እና ክሪዮሎ የሚባል ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው። አደገኛ እጽ ሲራራ ነጋዴዎች ጊኒን በጣም ይወዷታል፤ ከደቡብ አሜሪካ ተጭኖ ወደ አውሮፓ ለማድረስ ምቹ ወደብ ሆና ትታያቸዋለችና። ከሕዝቧ 70 ከመቶ የሚሆነው የቀን ገቢው ከ2 ዶላር ያነሰ ነው። "በዚያች አገር ተቋማት ባለመገንባታቸው እጽ አስተላላፊዎች ማንኛውንም ባለሥልጣን በሙስና እንዲያባብሉ አግዟቸዋል" ይላሉ የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢው ጸረ እጽ ግብረ ኃይል መሪ ማዜቴሊ። "በዚህ ሂደት ጥቂት ጄኔራሎች ይበለጽጋሉ። የሚደማው ግን ሰፊው የአገሬው ሕዝብ ነው።" የቀድሞው የባሕር ኃይል አዛዥ ቡቦ ና ቹቶ በአስተላላፊነት ከተጠረጠሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት አንዱ ናቸው። ሰውየው በርካታ መፈንቅለ መንግሥት ሙከራዎችን ያደረጉ ሲሆን ተሳክቶላቸው ግን አያውቅም። አሜሪካ እኚህን ጄኔራል "የእጽ ጌታ" የሚል ቅጽል ሰጥታቸዋለች። 2013 ላይ በወታደሮቻቸው እገዛ በልዩ ጥበብ ነበር በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የተደረጉት። የቀድሞው ኢታማዡር ሹሙ ጄኔራል ኢንጃይን 'የኮኬይን መፈንቅለ መንግሥት' በሚባለው ስልጣን ላይ ወጥተው ነበር ጄኔራሉ ወደ አሜሪካ ለሚዘዋወር እጽ ድጋፍ በመስጠት ክስ ተመስርቶባቸው 4 ዓመት እስር ተበይኖባቸዋል። ለመርማሪዎች ተባባሪ ስለነበሩና መልካም ባህሪን ስላሳዩ በሚል የእስር ዘመናቸው አጭር እንዲሆን ተደርጓል። አሁን ወደ ኑሯቸው ተመልሰው ድምጽ አጥፍተው እዚያው ጊኒ ውስጥ ናቸው። ሰውየው የተያዙበት መንገድ ፊልም የሚመስል ነበር። በቁጥጥር ሥር ለማዋል የተፈለገው ኢታማዡር ሹሙ ጄኔራል ኢንጃይን ነበር። ለኚሁ ኢታማዦር ሹም የእጽ ነጋዴዎች ሊያነጋግሯቸው እንደሚፈልጉና ወደ ወደብ በአስቸኳይ እንዲመጡ መልዕክት ይደረግላቸዋል። ኢታማዦር ሹሙ ነገሩ ጥርጣሬ ይፈጥርባቸውና የባሕር ኃይል አዛዡን ይልኳቸዋል። እኚህ አዛዥ ወደ ድንበር ሄደው የተባሉትን የእጽ ነጋዴዎች ሲጠብቁ የአሜሪካ ሰላዮች ያጠመዱላቸው ወጥመድ ውስጥ ይወድቃሉ። በቁጥጥር ሥር የዋሉትም ያን ጊዜ ነበር። የጊኒ 'እስር ቤቶች' ጊኒ ቢሳው 10 እስር ቤቶች አሏት። ነገር ግን እስር ቤቶቿ እጅግ የተጎሳቆሉ ናቸው። ፖሊሶችም አንድ እስረኛ ሊያመልጥ ቢል ለማስቆም የሚያስችል የጥበቃ መሳሪያ እንኳ በበቂ ሁኔታ የሌላቸው ናቸው። ይህን ያሉት የቀድሞው የፍትሕ ሚኒስትር ሩት ሞንቴሪዮ ናቸው። ለምሳሌ መግቢያው ላይ የተጠቀሰው ወንጀል የተጠርጣሪዎቹ ክስ ሊታይ የነበረው በጊኒ ቢሳዎ ዋና ከተማ ቢሳዎ አልነረበረም። በዚያው በተያዙበት ከተማ ቢሶሮ ውስጥ ነበር። ነገር ግን በቢሶሮ ከተማ ተጠርጣሪን ወደ እስር ቤት የሚወስድ መኪና እንኳ ባለመኖሩ ወደ ዋና ከተማው እንዲመጡ ተደረገዋል። "እስር ቤት የለንም፤ እስረኛ ማጓጓዠ የለንም፣ ተቋማት የሉንም፣ እስረኛ ላምልጥ ቢል እንኳ ማስቆም አንችልም። ይህ ሁሉ ተደማምሮ እኛ ለአደገኛ እጽ ማስተላለፊያነት የተመቸን አድርጎናል" ይላሉ የቀድሞው የአገሪቱ የፍትሕ ሚኒስትር ሩት ሞንቴሪዮ። ከዚህም በተጨማሪ በዚያች አገር ከአደገኛ እጽ ዝውውር የሚገኘው ገንዘብ የአልቃይዳ ርዝራዦችን መደጎሚያነት እየዋለ ነው። መስከረም ላይ ከዋና ከተማዋ አቅራቢያ የተያዘው ኮኬይን ለምሳሌ ባለፈው ወር የተየዘ 900 ኪሎ ግራም የሚመዝን የጭነት መኪና የጫነው ዓሳ እንደሆነ ነበር የሚታወቀው። ሆኖም ውስጡ ኮኬይን ተሞልቶ ነበር። የጭነት መኪናው ሊያመራ የነበረው ሰሜን መግረብ በረሃ ለሚነስቀሳቀሱ አሸባሪ ቡድኖች ነበር። በጊኒ የአደገኛ እጽ ገንዘብ የምርጫ ቅስቀሳ ይደረግበታል። ለምሳሌ ብራይማ ሳይድ ባ አደገኛ እጽ አዘዋዋሪ ነው። እስከዛሬም አልተያዘውም። ሁለት ዜግነት አለው። ፖርቱጋላዊና ጊኒያዊ ነው። በጋምቢያ በጊኒና በማሊ እንደሚዘዋወር ይገመታል። ይህ የሚያሳየው ንግዱ የአካባቢውን አገራት እንደሚያዳርስ ነው። ሌላው ተጠርጣሪ ሪካርዶ ነው። ሪካርዶ የኮሎምቢያም የሜክሲኮም ዜግነት አለው። አልተያዘም። ምናልባት በደቡብ አሜሪካ እንደሚዘዋወር ይገመታል። ተጠርጣሪዎቹ ፖለቲካዉን ጭምር ይዘውሩታል። ከእጽ ዝውውር የሚገኘው ገንዘብ መልሶ ለምርጫ ቅስቀሳ ይውላል። ለፓርላማ ምርጫ የየድርሻቸውን ይቀራመቱታል። በዚያው ሌላ በእጽ የናወዘ፣ በእጽ የሚዘወር ሥርዓት ይመሰረታል። ጊኒን "ናርኮስቴት" ያሰኛትም ሌላ ሳይሆን ይኸው ነው"
54581101
https://www.bbc.com/amharic/54581101
በትግራይ እና በፌደራል መንግሥት መካከል ያለውን ፍጥጫ ለመፍታት ምን መደረግ አለበት?
በትግራይ ክልልና በፌደራል መንግሥቱ መካከል ያለው ግነኙነት ከጊዜ ወደጊዜ እየሻከረ መጥቷል።
(ከግራ ወደ ቀኝ) ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ አቶ አሉላ ሃይሉ፣ አቶ አዳነ ታደሰ፣ አቶ ናትናኤል ፈለቀ በሁለቱ አካላት መካከል ያለው አለመግባባትም አንዳቸው ሌላኛቸውን "ሕገ ወጥ" እስከ ማለት ያደረሰ እና የእርስ በእርስ ግንኙነታቸውንም ማቋረጣቸውን በይፋ እስከ መግለጽ አድርሷቸዋል። ባለፈው ዓመት ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው አገራዊ ምርጫ በኮሮናቫይረስ ወረርሽን ምክንያት ሲራዘም፣ የትግራይ ክልል የራሱን ክልላዊ ምርጫ ማካሄዱ ይታወሳል። የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ምርጫው ከመከናወኔ በፊት ምርጫው ቢካሄድም ሕገ-ወጥ ነው ሲል ቆይቶ፣ ምርጫው ተደርጎ ውጤቱ ይፋ ከሆነ በኋላ ደግሞ ምርጫው እንዳልተደረገ የሚቆጠርና ተፈጻሚነት የማይኖረው ይሆናል ሲል አስታውቋል። በዚህ ብቻ ሳያበቃም የፌደራል መንግሥት የትግራይ ክልል ሕዝብ የልማትና መሠረታዊ አገልግሎቶች ፍላጎት ላይ በማተኮር የከተማ እና የቀበሌ አስተዳደርን ጨምሮ በክልሉ ከሚገኙ ሕጋዊ ተቋማት ጋር ብቻ ግንኙነት እንዲያደረግ ወስኗል። የትግራይ ክልል በበኩሉ ውሳኔውን ቅቡልነት የሌለው በማለት ምክር ቤቱ ሥልጣኑን ከሕገ መንግሥቱ ውጪ፣ የሕገ መንግሥት ትርጉም በመስጠት ያራዘመ ስለሆነ፤ ሕገ መንግሥታዊ መሠረት የለውም ብሏል። ይህ የሁለቱ አካላት ፍጥጫ እንዴት ይፈታ? የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናስ ምን መሆን አለበት ስንል የተለያዩ ፓርቲ አመራሮችን አነጋግረናል። ውይይት ውይይት ውይይት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና "አደገኛ ወደ ሆነ ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል" በማለት ሁሉም አካላት ከገቡበት አለመግባባት ተመልሰው ወደ ድርድር እንዲገቡ እንደሚጠብቁ ይናገራሉ። የፖለቲካ ልዩነቶች በድርድር መፈታት አለባቸው የሚሉት ፕሮፌሰሩ የትግራይ ክልል መንግሥትን እና የፌደራል መንግሥቱን ፍጥጫ ለመፍታትም "መፍትሔው ድርድር ብቻ ነው" ይላሉ። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ ሕወሓትና የፌደራል መንግሥቱ የገቡት እሰጥ አገባ "አደጋ ይጋርጣል" ሲሉ ከፕሮፌሰር መረራ ሃሳብ ጋር ይስማማሉ። አክለውም በኢትዮጵያ ውስጥ የለውጥ ሂደቱ ተጀመረ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ሕወሓት በበላይነት ያስተዳድረው ከነበረው የፌደራል መንግሥት መገለሉን፤ በኋላም ላይ ብልጽግና ሲመሰረት ከፌደራል ሚና ወጥቶ ክልሉን ብቻ ወደ ማስተዳደር መቀየሩን አስታውሰው፤ በጊዜ ሂደት ሕወሓት እየወሰዳቸው የመጣቸው ውሳኔዎች ራሱን የሚነጥልና ከአገራዊ የለውጥ ሂደቱ ራሱን የሚያስወጣ ሂደት ተከትሏል ይላሉ። የኢዜማው አቶ ናትናኤል፣ የፌደራል መንግሥቱንና የትግራይ ክልልን የሚያስተዳድሩት አካላት ያላቸው አለመግባባት የትግራይ ክልል ሕዝብ ላይ አደጋ ሊጋርጥ የሚችል ይመስላል በማለት፣ ጉዳዩን "በውይይት ለመፍታት የሚያስችሉ በሮች እየተዘጉ ከዚያ ውጪ ያሉ አማራጮችን ለማየት የሚያስገድዱ ይመስላሉ" ሲል ይገለፁታል። የፌደራል መንግሥቱን ከማንም በላይ ሊያሳስበው የሚገባው ሕግ የማስከበር፣ የዜጎችን ደህንንት የማስከበር ነው በማለትም ጉዳዩ ከዚህ በላይ ሳይባባስ ወደ ውይይት ሁለቱ ወገኖች የሚመጡበትን ሁኔታ የማመቻቸት የበለጠ ኃላፊነት ያለበት መሆኑን ይገልጻሉ። ኢዜማም የፌደራል መንግሥቱ ያንን ማድረግ አለበት ሲል አንደሚያምን የገለፁት አቶ ናትናኤል፤ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ ሕወሓትን ወደ ጠረጴዛ እንዲመጣ የሚጋብዙ አለበለዚያም የሚያስገድዱ መሆን አለባቸው ይላሉ። የፌደራል መንግሥቱ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የትግራይን ሕዝብ ደህንነት አደጋ ውስጥ የሚጥል መሆን እንደሌለበትም አቶ ናትናኤል ጨምረው ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዚዳንት አቶ አዳነ ታደሰ በበኩላቸው በአገሪቱ ውስጥ የተለያዩ የፖለቲካ ችግሮች ቢኖሩም አገሪቱ ሕልውና ላይ ተጨባጭ አደጋ ጋርጦ ያለው በሕወሓት እና በብልጽግና፣ በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ክልል መንግሥት መካከል ያለው ፍጥጫ ነው ብለው እንደሚያምኑ ይናገራሉ። ፓርቲያቸው ከባለፈው ዓመት ጥር ወር ጀምሮ ይህንን በመገንዘብ አቋሙን ሲገልጽ እንደነበር በማስታወስም፣ ሁለቱን ወገኖች ለማቀራረብ በሚደረግ ማንኛውም ተሳትፎ ውስጥ የፓርቲያቸው ሚና የሚያስፈልግ ከሆነ ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኑንም ማስታወቁን ይገልጻሉ። ከፌደራል መንግሥት ወገን ክልሉን "የመግፋት"፤ ከትግራይ ክልል ወገን ደግሞ "ሆን ተብሎ ችግሮቹን የማስፋት አዝማሚያ" የሚታይ መሆኑንም በመጥቀስ ይህ ለአገር ትልቅ ስጋት መሆኑን ይገልጻሉ። አቶ ታደሰ ሁለቱ አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተቀራርበው ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ አለባቸው ሲሉ ይገልጻሉ። ኃላፊነት ያለባቸው የሃይማኖት አባቶች፣ የአገር ሽማግሌዎችም ቢሆኑ የችግሩን አደገኛነት ተረድተው ለመፍታት ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ያስታውሳሉ። 6ኛው ሃገራዊ ምርጫ መራዘሙ ትክክል እንዳልሆነና ትግራይ ክልላዊ ምርጫ በማካሄድ መንግስት ማቋቋም መቻሏ ህጋዊነት እንዳለው የሚገልጸው የሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ በብልጽግናና ህወሓት መካከል ያለው "አደገኛ አለመግባባት" ግን በአስቸኳይ መፈታት እንዳለበት ያምናል። ፓርቲዎቹ ችግራቸውን በራሳቸው መንገድ መፍታት እንዳለባቸው የሚናገረው አሉላ ይህንን ማድረግ ካልቻሉ ግን በህጋዊ መንገድ መፈታት እንደሚኖርበት የፓርቲያቸው ሳወት አቋም መሆኑን ይገልጻ። የፌደሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ እና የሕወሓት አቋም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሕገመንግሥት አጣሪ ጉባኤ የቀረበለትን ውሳኔ በመንተራስ አገራዊ ምርጫውንም ሆነ የመንግሥትን ስልጣን ለማራዘም መወሰኑ ይታወሳል። ከዚህ በተጨማሪም ምክር ቤቱ የትግራይ ክልል መንግሥት ያካሄደው ምርጫ ተፈጻሚነት የሌለው፣ የማይጸና እና እንደተደረገ የማይቆጠር በማለት፣ ከክልሉ መንግሥት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደማይኖር በማስታወቅ፣ ከታችኛው መዋቅሮች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሚደረግ ወስኗል። ሕውሃትም ተመሳሳይ አቋም አንጸባርቋል። ይህንን በማስመልከትም የኦፌኮው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ፤ የፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልል መንግሥት አንዳቸው አንዳቸውን በመወንጀልና "ሕገ-ወጥ" በማለት ግንኙነት ማቋረጣቸው ተገቢ አለመሆኑን ይገልጻሉ። የፌደራል መንግሥት ከወረዳና ቀበሌ አስተዳደሮች ጋር ግንኙነቱን አደርጋለሁ ማለቱ በምን መልኩ ተግባራዊ ይሆናል የሚለው ለፕሮፌሰሩ መመለስ ያለበት ነጥብ ነው። በእርሳቸው እምነት በበላይነት ክልሉን የሚያስተዳድረው አካል የታችኛው መዋቅሩንም የማደራጀት ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ፣ የፌደራል መንግሥቱ፣ ሕወሓትን አልፎ ከታችኛው መዋቅር ጋር ምን ምን እንደሚሰራ መታወቅ እንዳለበት በማንሳት፣ ወደ ስራ ለመተርጎምም ቀላል ይሆናል የሚል እምነት እንደሌላቸው ገልፀዋል። ሕዝቡን የሚያስተዳድር እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮችን የሚያሟላው አካል የተለያዩ መሆናቸው ለአፈጻጸም አስቸጋሪ እንደሚያደርገውም ያነሳሉ። ፕሮፌሰር መረራ አክለውም እነዚህ ሁለት አካላት ዋነኛ የፖለቲካ ችግራቸውን እስካልፈቱ ድረስ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ አብሮ መጓዝ እንደሚከብዳቸውንም ግምታቸውን ያስቀምጣሉ። የኢዜማ ሕዝብ ግንኙነት የሆኑት አቶ ናትናኤል በበኩላቸው ሕወሓት ቀደም ብሎ ከመስከረም 30 በኋላ መንግሥት የለም የሚል ቅስቀሳ እና ንግግሮች በተደጋጋሚ ሲያደርግ እንደነር በማስታወስ፣ ቅስቀሳውም ሆነ ውሳኔው "አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚከተን ነው የሚሆነው" ብለዋል። "ይህ አደገኛ ቅስቀሳ እንደ አገር አደገኛ ሁኔታ ውስጥ እንደሚከተን አድርገን ነው ያየነው" የሚሉት የኢዜማው አቶ ናትናኤል የፌዴሩሽን ምክር ቤቱ ከትግራይ የክልል መንግሥት በታች ካሉ መዋቅሮች ጋር ግንኙነት ለማድረግ መወሰኑ አግባብነት ያለው ነው ብለን ነው የምንወስደው ብለዋል። ውሳኔው ግን ምን ያህል ሁለቱን ወገኖች የሚያቀራርብና ወደ ውይይት ያመጣል የሚለው ላይ አሁንም ስጋት እንዳላቸው ከመግለጽ አልተቆጠቡም። ስለዚህ ሕወሓትን ወደ ውይይት ጠረጴዛ ለማምጣት ምን መደረግ አለበት የሚለው በሚገባ መታሰብ እንዳለበት ይገልጻሉ። የኢዴፓው አቶ አዳነ በበኩላቸው ሕወሓት ምርጫ አድርጎ ስልጣኑን ያራዘመበት መንገድ ፍፁም ተገቢ ያልሆነ እና ሕገ-መንግስታዊ ነው ብለው እንደማያምኑ ይናገራሉ። በሌላ በኩል ደግሞ የፌደራል መንግሥቱም ሥልጣኑን ያራዘመበት መንገድም ሕገ ወጥና ሕገ መንግሥታዊ ያልሆነ መሆኑን ይገልጻሉ። ከዚህ አንጻር በፌደሬሽን ምክር ቤት እና በትግራይ ክልል መካከል የሚካሄዱ ሕጋዊ የሚመስሉ ምልልሶች ተገቢ አለመሆናቸውን ይጠቅሳሉ። ከዚህ ይልቅ "ሕጉን ወደ ጎን ትቶ፣ በዚያ ሰበብ ሕዝብ ማደናገሩን ትቶ፣ ፖለቲካዊ መፍትሄ መስጠት" እንደሚያሻቸው ይናገራሉ። ብልጽግናና ሕወሓት በጠረጴዛ ዙሪያ ቁጭ ብለው ችግሮቻቸውን መፍታት አለባቸው በማለትም፣ "እነርሱ በያዙት የፖለቲካ ጨዋታ አገር ይፈርሳል" በማለት ፖለቲካዊ ውሳኔ ለመስጠት የሚያስችል ድርድርና ውይይት ማድረግ እነደሚያስፈልግ ይገልጻሉ። የተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚና የሳወት ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉ እንደሚለው ተቃዋሚ ፓርቲዎች ብልጽግናን እና ህወሓትን በማስታረቅ የሚፈለገውን መግባባት ለመፍጠር የሚያስችላቸው ዕድል ሊኖር አይችልም። "የነበረው የኢህወዴግ ስርዓት በወቅቱ ሲፈጠሩ የነበሩት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ደካማ እንዲሆኑ ያደርግ ነበር። አንዳንድ ጠንካራ የሚባሉ ከተፈጠሩም በገዢው ግንባር የሚታፈኑበት ሁኔታ ነው የነበረው። ስለዚህ አሁንም የመሰማት ወይም የመደመጥ ዕድል ያገኛሉ ብዬ አላስብም" በማለት ምክንያቱን ያስቀምጣል። በተጨማሪም በብልጽግናና ህወሐት መካከል "የስልጣን ሽኩቻ" ስላለ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመሃል ገብተው መፍትሔ ሊያመጡ እንደማይችሉና ተሰሚነት እንደማይኖራቸው በትግራይ ውጥስ ያለውን የፖለቲካ ሁኔታ በምሳሌነት በመጥቀስ ያስረዳል። ፕሮፌሰር መረራ ፓርቲያቸው ብሔራዊ እርቅ እና ብሔራዊ መግባባት እንደሚያስፈልግ ላለፉት ሁለት ዓመታት ሲናገር መቆየቱን ያስታውሳሉ። ብሔራዊ እርቁና መግባባቱ በማህበረሰብ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በመንግሥትና ተቃዋሚዎች መካከል እስካልተፈጠረ ድረስ የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ አስቸጋሪ እንደሚሆን ፓርቲያቸው እንደሚያምን ፕሮፌሰሩ ገልፀዋል። አክለውም ለትግራይም ሆነ ለቀሪው ኢትዮጵያ ፍትሃዊ የሆነና በብሔራዊ መግባባት ላይ የተመሰረተ ምርጫ ማካሄድ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ። አቶ ናትናኤል በበኩላቸው ፓርቲዎች በጋራ የፈረሙትን የቃል ኪዳን ሰነድ በማስታወስ የፌደራል መንግሥትን እያስተዳደረው ያለው ፓርቲ እና ትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ፓርቲ ይህንን የቃል ኪዳን ሰነድ እንዲያከብሩ ግፊት ማድረግ ከፓርቲዎች እንደሚጠበቅ ይናገራሉ። በቃል ኪዳን ሰነዱ በአሁኑ ሰዓት በሥራ ላይ ያለውን ሕገመንግሥት ማክበር፣ የሚደረጉ አንቅስቃሴዎች በሙሉ የሰላማዊ የሌሎችን ዜጎች መብት ያከበሩ እንዲሆን መስማማታቸውን ይጠቅሳሉ። ኢዜማ ከዚህ አንጻር ይህ እንዲከበር ምክር ቤቱን እንደሚጎተጉት በመጥቀስ፣ በዚህ ጉዳይ ፓርቲዎች በጋራም ሆነ በግል ሁለቱ ወገኖች በውይይት ጉዳያቸውን እንዲፈቱ መጎትጎት እንደሚያስፈልጋቸው ይጠቅሳሉ። የሁለቱ ወገኖች አለመግባባትም ወደ መሬት ወርዶ ተግባራዊ እንዳይሆን ፓርቲዎች ሚናቸውን መጫወት እንዳለባቸው ያሰምሩበታል። አቶ አዳነ የሕወሓትና የብልጽግና ችግር የሁለቱ ፓርቲዎች ብቻ ሆኖ እንደማይቀር በመግለጽ፣ የተቃዋሚ ፓርቲዎች፣ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ ከመቀስቀስ ይልቅ ወደ ውይይት እንዲመጡ ተሰባስበው ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ይመክራሉ። በፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ውስጥ የሚሳተፉ ከአንድ መቶ በላይ ፓርቲዎች እንዳሉ የሚናገሩት አቶ አዳነ፣ እነዚህ ፓርቲዎች አንድ ልዑክ በማዋቀር የሁለቱ ፓርቲዎች ችግር እንዲፈታ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መጀመር እንዳለባቸው ያስታውሳሉ።
news-53657254
https://www.bbc.com/amharic/news-53657254
“የኑሮ ውድነቱ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መፍትሄ ያስፈልገዋል”
ነዋሪነቱ በአዲስ አበባ ከተማ የሆነውና መካከለኛ ገቢ ካለቸው ሰዎች ሊመደብ የሚችለው ግለሰብ በተለይ የኮቪድ-19 ወረረሽኝ ስጋትን ከመጣበት ከወርሃ ሚያዚያ አንስቶ የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መጨመር ህይወቱ ላይ የሚጨበጥ ተፅዕኖ ማምጣቱን ለቢቢሲ ይገልፃል።
የብር የመግዛት አቅም እየቀነሰ ነው "ሃገር ውስጥ የሚመረቱ እንደ ሽንኩርት፣ ጤፍ፣ ቲማቲም የመሳሰሉት ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል፤ ከዚያ ባሻገር ከውጭ የሚገቡ እንደ መዋቢያ ምርቶች፣ አልባሳት የመሳሰሉትም ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል" የሚለው ይሄው ግለሰብ ምናልባትም ከዓለም አቀፍ ወረርሽኙ ጋር በተያያዘ የንግድ እንቅስቃሴዎች መቀዛቀዛቸው፣ እንደ ወትሮውም በቀላሉ መጓጓዝ ባለመቻሉ የአቅርቦት እጥረት ማጋጠሙ ለዋጋ ጭማሪ ምክንያት ሳይሆን እንደማይቀር ግምቱን ሰንዝሯል። "ሽንኩርት በአስራዎቹ ብር ደረጃ ነበር የምንገዛው፥ አሁን ወደ አርባ ብር ደርሷል፤ ቲማቲምም እንደዚሁ ከፍ ብሏል፤ እንደዚሁ ሃያ ስምንት ብር ሃያ ዘጠኝ ብር [ገደማ] እየተሸጠ ነው ያለው በኪሎ" የሚለው ይህ ሰው ከዚህም የተነሳ እርሱና በማኅበራዊ ከባቢው የሚያውቃቸው ሌሎች ሰዎች አጠቃቀማቸውን ለማስተካከል መገደዳቸውን ይናገራል። የፍቼ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ዘውዲቱ አሰፋም ከአዲስ አበባው ነዋሪ ጋር ተመሳሳይ ሃሳብ ነው ያላት። የኑሮ ውድነቱ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መሆኑን ለቢቢሲ ስትገልጽ፤ "ለምሳሌ ሽንኩርት ከ45 እስከ 50 ብር እየተሸጠ ይገኛል። ሁሉም ነገር ጨምሯል። ጤፍ ከ4300 በላይ እየሆነ ነው። ዘይት ድሮ መንግሥት ያቀርብ ነበር፤ አሁን ግን አያቀርቡም፤ ስለዚህ ከነጋዴ እየገዛን ነው። ዋጋው ጨምሯል። የመንግሥት ሰራተኛ የሆነ፣ ደሞዙ አነስተኛ የሆነ፣ ቤተሰብ ያለው በጣም እየተቸገረ ነው።" ብላለች። የኑሮ ውድነቱ መናር በአኗኗሩ ላይ ያመጣውን ለውጥ የሚገልፀው የአዲስ አበባ ነዋሪ ". . .በምንጠቀማቸው ምግቦች ውስጥ ቲማቲም የምናዘወትር ከሆነ እርሱን እንተዋለን ማለት ነው፤ ሽንኩርትም የምንገዛውን እየቀነስን ሄደናል"፤ ስለዚህ "የምታገኘው ገቢና ለፍጆታዎችህ የምታወጣው ካልተመጣጠነልህ ፍጆታውን ወደ መቀነስ ብሎም ወደ ማቆም ነው የምንሄደው" ብሏል። ይኼው ሰው የኮቪድ-19 ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ መግባቱ እርግጥ የሆነበት ሰሞን በርካታ ሰዎች፣ የተለያዩ ምርቶችን በጅምላ ይሸምቱና ያከማቹ እንደነበር አስታውሶ፣ በወቅቱ አጋጣሚውን ለመጠቀም በፈለጉ አንዳንድ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ መደረጉን ይጠቅሳል። "እኛ አገር የተለመደው ነገር ደግሞ ዋጋ አንድ ጊዜ ከፍ ካለ በኋላ ተመልሶ የመውረድ ዕድሉ በጣም አናሳ ስለሆነ" በዚያው ከፍ ብሎ ቀርቷል ይላል። የአርባምንጭ ነዋሪ የሆኑ ሌላ ግለሰብ ለቢቢሲ ሲናገሩ ገበያው "እሳት ነው" ይላሉ። ዋጋውን ለማነጻጸር ሩቅ መሄድ አልፈለጉም፤ "በቅርቡ እንኳ ቲማቲም እንገዛ የነበረው 20 ብር ነው አሁን ግን 30 ገብቷል" ካሉ በኋላ ሽንኩርት ደግሞ 30 ብር መግባቱን፣ ድንች በኪሎ 15 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት 150 መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል። ነጋዴዎችም እንደ ከዚህ ቀደሙ ደፍረው የሚገዙ ደንበኞቻቸው እየቀነሱ መምጣታውን ለቢቢሰ ተናግረዋል። በላሊበላ የሚኖሩት ሌላው ቢቢሲ ያነጋገራቸው ግለሰብ ኑሯቸው የተመሰረተው ከተማዋን ለመገብኘት በሚመጡ ቱሪስቶች ላይ እንደነበር ተናግረው አሁን ግን በኮቪድ-19 ምክንያት ጎብኚ በመጥፋቱ ኑሯቸው ፈተና ውስጥ መውደቁን ለቢቢሲ አልሸሸጉም። ከዚህ ቀደም 30 እና 40 ብር ይገዙት የነበረውን ሽንኩርት አሁን 120 ብር እንደሚሸጥም አስረጅ በመጥቀስ ተናግረዋል። ከቅርብ ወራት ወዲህ በምግብ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የዋጋ መጨመር ታይቷል "ጤፍ ከ4000 ብር በላይ ገብቷል" በማለትም ኑሮ ከእለት ወደ እልት እየከበደ መምጣቱን ለቢቢሲ በሃዘን ስሜት ውስጥ ሆነው አስረድተዋል። ኮሮናቫይረስና የዋጋ ንረት የምጣኔ ሃብት ባለሙያው ዶ/ር ጉቱ ቲሶ በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም በኮሮናቫይረስ ምክንያት የሸቀጣሸቀጥ ዋጋ መጨመሩን ይገልፃሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያቱ በኮቪድ-19 እና በተጓዳኝ ችግሮች ምክንያት ምርትና አቅርቦት ላይ መስተጓጎል በመፈጠሩ መሆኑን ያስረዳሉ። ምሁሩ አክለውም ከየካቲት ወር ጀምሮ ይህ መከሰቱን እና እስካሁን መቀጠሉን ይናገራሉ። ዶ/ር ጉቱ በተለይ ደግሞ የአለማቸችን የሸቀጣሸቀጥ እቃዎች ዋነኛ አቅራቢ ቻይና በኮሮናቫይረስ ክፉኛ መጎዳቷ ምርቶችን ማስተጓጎሉንና በዚህም የተነሳ የዋጋ ንረት መከሰቱን ገልፀዋል። "አቅርቦት ሲቀንስ ዋጋ ይጨምራል" የሚሉት ባለሙያው፤ በተፈጠረው የአቅርቦት እጥረት ገበያ ውስጥ ያለውን መቀራመት በመፈጠሩ የምርት ዋጋ መናሩን አብራርተዋል። ሌላኛው ምርቶችን ከውጪ አገራት ገዝቶ ለማምጣት የውጭ ምንዛሬ በማስፈለጉ እና በበቂ ሁናቴ የውጪ ምንዛሬ ማግኘት አለመቻል ለዋጋ ግሽበቱ መናር አንዱ አስተዋጽኦ እንደሆነ ያስረዳሉ። በኮሮናቫይረስ ምክንያት አምራቾች የግብአት እጥረት ስለሚገጥማቸው የዋጋ ንረት ይከሰታል የሚሉት ዶ/ር ጉቱ፣ አምራቾች የማምረት ወጪያቸው ሲጨምር አብሮ የምርት ዋጋ ይጨምራል ይላሉ። አምራቹ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ከትራንስፖርትና ከማምረት ጋር የተገናኘ የግብአት አቅርቦት እየተገታና እጥት እየተፈጠረ በመምጣቱ ለምርት እጥረቱ አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልፀዋል። "ግብአት አቅርቦት ቀነሰ ማለት፣ የግብአት ዋጋ ጨመረ ማለት ነው" በማለትም ናገራሉ። የማምረቻ ዋጋ ሲጨምር፣ በተዘዋዋሪ አምራቹ ዋጋውን ወደ ሸማቹ እንደሚያዞር የሚያስረዱት ዶ/ር ጉቱ፤ ዋጋው ወደ ተጠቃሚ ሲዞር ምርቱ ላይ ጭማሪ ያሳያል ሲሉ ይተነትናሉ። ከእነዚህ በተጨማሪ የስርጭት መሰተጓጎል መኖሩን ባለሙያው ጨምረው አስድተዋል። "በአንድ ቦታ የተመረተ ምርት በሚፈለግበት ወቅት ወደ ተለያየ የአገሪቱ ክፍል ማሰራጨት ሲያቅት፣ እጥረት ስለሚፈጠር ለተጨማሪ ወጪ ይዳረጋል፤ የዋጋ ጭማሪ ይከሰታል።" በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት የሰላምና መረጋጋት ጥያቄ ትልቅ ፈተና ውስጥ መውደቁን በማስታወስ፣ ይህ ሁሉ በምርት ሰንሰለት፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በምርት ስርጭቶች ላይ ትልቅ መስተጓጎል መፍጠሩን ይናገራሉ። በሰላም እና መረጋጋት እጦቱ ፋብሪካዎች ምርታቸውን መቀነሳቸውን፣ ምርት ስርጭት ላይ የተሰማሩም መስተጓጎል ገጥሟቸዋል ሲሉ ይገልጻሉ። መኪናዎች ጭነት ጭነው መንገድ ላይ ከአንድ ቀን በላይ ተስተጓጉለው መቅረት፣ ለተጨማሪ ወጪ እና ኪሳራ ሲዳርጋቸው በተዘዋዋሪ ሸማቹ ላይ የምርቱ ዋጋ ከተገቢው በላይ ዋጋ እንዲጫን እንደሚያደርጉ ጨምረው ያስረዳሉ። እነዚህ ነገሮች በጥቅሉ ሲታዩ የሸቀጣ ሸቀጥ ዋጋ ላይ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም አገልግሎቶችና አቅርቦቶች ላይ የዋጋ ንረት እንደሚያሳዩ ዶ/ር ጉቱ ገልፀዋል። የምግብ እህሎች ንረት ለዋና ዋና ከተሞች የምግብ ፍጆታ ምርቶች የሚመጡት በከተሞቹ አቅራብያ ከሚገኙ የክልል ከተሞች መሆኑን በማስታወስ እነዚህ የግብርና ምርቶች ከየትኛውም ጊዜ ይልቅ የዋጋ ንረት ማሳየታቸውን ገልፀዋል። እነዚህ የፍጆታ እቃዎች አሳሳቢ በመባል ደረጃ ዋጋቸው እየጨመረ ነው የሚሉት ምሁሩ፣ ለዋጋ መናር ምክንያቱ ምን እንደሆነ ሲያስረዱም እነዚህ የእለት ፍጆታ ምርቶች ( እንደ ጥራጥሬ ያሉት) ለገበያ የሚቀርቡት ባለፈው አመት የተመረቱ መሆናውን በመጥቀስ ነው። ባለው አመት በተለያየ የአገሪቱ ክፍል አካባቢዎቹ የነበሩበት ሁናቴ የነበረውን ሁኔታም በማስታወስ፣ ለማምረት፣ ለመሰብሰብ፣ ለማሰራጨት አስቸጋሪ በሆነ ሁናቴ ውስጥ ማሳለፋቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ የተነሳ የምርት ማሽቆልቆል ተከስቶ ዘንድሮ ለገበያ ሲደርስ የዋጋ መናር መፈጠሩን ያስረዳሉ። ባለፉት ወራት የተከሰተውንም በተመለከተ ሲያስረዱም፣ ከድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዳሴ ግድያ በኋላም ወደ አዲስ አበባ የሚመጡ ምርቶች ትልቅ መስተጓጎል እንደገጠማቸው ያብራራሉ። በተጨማሪም ነጋዴዎች ባለፈው አመት የገዙት ምርት እንኳ ቢሆን በእንዲህ አይነት ወቅት ዋጋ ከመጠን በላይ ጨምረው እንደሚሸጡ ሸማቾችም በገፍ ገዝው እንደሚያከማቹ ይህም ለዋጋ ንረቱ አስተዋጽኦ እንዳለው ይገልጻሉ። ወደ 80 በመቶ የሚጠጋው አትዮጵያዊ መደበኛ ባልሆነ ስራ ውስጥ ተሰማርቶ፣ ከእጅ ወደአፍ ገቢ እንደሚያገኝ የሚናገሩት ምሁሩ፤ በዚህም ለበርካታው ኢትዮጵያዊ ኑሮን ማክበዱን ይገልፃሉ። ገንዘብ ያለውም ቢሆን የፍጆታ እቃዎች ዋጋ በናረበት ቁጥር ያለውን ገቢው በአጠቃላይ ወደ ሚመገበው ነገር ለማዞር ይገደዳል ይላሉ። ይህም ቁጠባን፣ የወደፊት የማደግ ተስፋውንና ጥረቱን እንደሚያመክን ገልፀው፣ ይህ እንደ ግለሰብ ቢሆንም እንደ አገር ማህበረሳባዊ እድገትንም ፈተና ውስጥ እንደሚጥል ይገልፃሉ። ምን መደረግ አለበት እንደ ዶ/ር ጉቱ ከሆነ ለዋጋ ግሽበቱ መፍትሄ ለመስጠት ችግሩ ከምን መነጨ የሚለውን መለየት አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ጊዜ ለምጣኔ ሃብት ችግር የምጣኔ ሃብት መልስ መስጠት ያስቸግራል የሚሉት ምሁሩ፣ የችግሩ መንስኤ ምጣኔ ሃብታዊ ሳይሆን ማህበራዊ አልያም ፖለቲካዊ ሊሆን ይችላል ይላሉ። ከኮሮናቫይረስ ጋር ተያይዞ የተከሰተን የዋጋ ንረት በፍጥነት በሽታውን በቁጥጥር ስር በማዋል፣ ህብረተሰቡ ወጥቶ ሰርቶ መግባት እንዲችል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ይናገራሉ። ለዚህ ደግሞ የመንግሥት ብቻ ሳይሆን የሁሉም አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል። ይህን በፍጥነት መቆጣጠር ካልተቻለ የምጣኔ ሃብቱን ቀውስ እያባባሰው እንደሚሄድ ይናገራሉ። ሌላው በየዓመቱ ያለው የሰላም መደፍረስ ምክንያቱ ተጠንቶ እውነተኛ፣ አሳታፊ እና ግልጽ የሆነ ውይይት ተደርጎ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ምላሽ ሊሰጠው እንደሚገባ ይመክራሉ። በሶስተኛ ደረጃ እንደ ህዝብ ያሉትን ፖሊካዊ ብሶቶችና ጥያቄዎችን የምንገልፅበት መንገድን ቆም ብሎ መመልከት ተገቢ መሆኑን ይመክራሉ። ሁል ጊዜ የምጣኔ ሃብት ተቋማትን በማውደም፣ ምርትና ምርታማነትን በማስተጓጎል ብቻ ሳይሆን ሌሎች በተዘዋዋሪ ጫና መፍጠር የተፈለገው አካል ላይ ጫና መፍጠር የሚያስችሉ አማራጮችን መመልከትና መፈተሽ ተገቢ መሆኑን ያስታውሳሉ። ካልሆነ ግን አሁን የዋጋ ንረቱ እየሄድንበት ያለው ፍጥነትና መንገድ ከምጣኔ ሃብት አንፃር ሲታሰብ አገሪቷን መጥፎ ደረጃ ላይ እያደረሰ መሆኑን ለቢቢሲ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
41483893
https://www.bbc.com/amharic/41483893
ከሰሞኑ የኢትዮ-ቴሌኮም የተንቀሳቃሽ ስልኮች ምዝገባ ጀርባ
ሰሞኑን ኢትዮ-ቴሌኮም በሃገሪቱ ዉስጥ ያሉ ሁሉም የሞባይል ቀፎዎች እና ሌሎች በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሳሪያዎች እንዲመዘገቡ ባስቀመጠው ቀነ-ገደብ መሰረት ብዙዎች ተመዝግበዋል።ይህንንም ተከትሎ ምዝባው ምንድን ነው? ለምን አስፈለገ? እንዲሁም መንግስት በዜጎች ላይ የሚያደርገውን "የስለላ ስራ ለማጧጧፍ ነው" የሚሉ መረጃዎች ከተለያየ የሕብረተሰቡ ክፍል እየመጣ ነው።
ሰሞኑን ኢትዮ-ቴሌኮም ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ለመመዝገብ የወጣው ጥሪ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከተመረቱ በኋላ አምራቾቹ 15 አሃዝ የያዙ ቁጥሮች ለእያንዳንዱ ስልኮች ይሰጣል፤ ይህም አይኤምኢአይ (IMEI) ቁጥር ይባላል። ይህ ቁጥር አንድን ስልክ ከሌላ የሚለይ እንደሆነ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ደኅንነት ባለሙያው አቶ ተክሊት ኃይላይ የሚናገር ሲሆን ቁጥሩም ለአንድ ስልክ ብቻ የሚሰጥ ነው። ምዝገባው አዲስ እንዳልሆነ የሚናገረው አቶ ተክሊት፤ አሁን የተደረገው ምዝገባ በተጨማሪም ተንቀሳቃሽ ስልኮችን መክፈትና መዝጋት ለማስቻል ኮርፖሬሽኑ አዲስ ሶፍትዌርንም አስገብቷል። ለምን መመዝገብ አስፈለገ? የኢትዮ-ቴሌኮም የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ አቶ አብዱራሂም አህመድ እንደሚሉት የዚህ ምዝገባ ዋና አላማ ተገልጋዩን ደንበኛ ከስርቆት እንዲሁም ደረጃቸውን ያልጠበቁ ስልኮች ከሚያስከትሉት የጤናና የአገልግሎት ጥራት መጓደል ለመከላከል ነው። በሲም ካርድ የሚሰሩ የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች በስርቆትም ሆነ በሌላ ምክንያት ከደንበኞች እጅ ሲጠፉ ደንበኞች በሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት ቀፎው የቴሌኮም አገልግሎት እንዳይሰጥ ለማድረግም ይረዳልም ይላሉ። እነዚህንም ተንቀሳቃሽ ስልኮች በጥቁር መዝገብ ላይ የሚያሰፍሩ ሲሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ሃገር መጠቀም አይቻልም። አቶ አብዱራሂም እንደሚሉት በህጋዊ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ የገቡ እና ኦሪጅናል የቴሌኮም መገልገያ መሣሪያዎች የመኖራቸውን ያህል ቁጥራቸው ጥቂት የማይባል ጥራታቸውንና ደረጃቸውን ያልጠበቁ ተመሳስለው ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መሣሪያዎች አገልግሎት ላይ እየዋሉ ይገኛሉ፡፡ ይህም ሁኔታ አገር ውስጥ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ገጣጥመው የሚሸጡ ነጋዴዎች ቀረጥ ከፍለው በሚያስገቡት ላይ ኢ-ፍትሐዊ የገበያ ውድድር እየፈጠረ መሆኑን የሚናገሩት አቶ አብዱራሂም፤ ይህ ምዝገባ ይህንን ለማስቀረት ይረዳልም ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪ ሃገሪቷ የምታገኘውን ቀረጥ ለማሳደግ፣ በኢትዮ ቴሌኮም የሞባይል ኔትወርክ ውስጥ ያሉ ሁሉንም የሞባይል ተጠቃሚዎችን ባሉበት ለመለየትና በባለቤቱ ወይም በደንበኛው ስም ለመመዝገብ ያስችላል። በአጠቃላይ በሃገሪቷ 58 ሚሊየን ያህል ደንበኞችን ሲስተሙ በቀጥታ እንደመዘገባቸው የሚናገሩት አቶ አብዱራሂም ተጨማሪ ቀፎ እንዲሁም አይ ፓድና ሌሎች ሲም ካርድ የሚወስዱ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ሲም ካርድ በማስገባት መመዝገብ ይችላሉ። ይህ የምዝገባ ሂደት ለኢትዮጵያ የተለየ እንዳልሆነ የሚናገሩት አቶ አብዱራሂም በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘመናዊ የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ባደጉ ሃገራትና በሌሎች የአፍሪካ ሃገራት ጭምር እየተተገበረ ያለ ዘመናዊ አሰራር ነውም ይላሉ። ከምዝገባው ጀርባ? አቶ ተክሊት በበኩሉ የግለሰቦችን ፕራይቬሲ (ግላዊ ምስጢር) በተመለከተ ምንም አይነት ለውጥ እንደማያመጣ ቢናገሩም ቁጥጥርን በተመለከተ ሥራን እንደሚያቀል ጨምረው ይገልፃሉ። "ሌላ ጊዜ አስመስለው በተሰሩ ስልኮች ያመልጡ የነበሩት አሁን በዚህ አሰራር ማምለጥ አይችሉም" ይላሉ። የ አይኤምኢአይ ቁጥር ግለሰቦች አድራሻቸውን ቢቀይሩ እንኳን በቁጥሩ አማካይነት ትክክለኛ አድራሻቸውን ለማወቅ ያስችላል። "የምትከታተለውን ሰው እንዳያመልጥህ ይረዳሃል።" በማለትም ያስረዳል። አቶ ተክሊት እንደሚለው አንድ ሰው ሲምካርዱን ትቶ ሌሎች አይኤምኢአይ ቁጥራቸው የማይታወቁ ስልኮችን በመያዝ በሌላ ሲም ካርድ መጠቀም ይችል ነበር "ሲምካርድ በመቀየር ያመልጥ የነበረ ሰው አሁን አያመልጥም"ይላል። ጦማሪው በፍቃዱ ኃይሉ መንግሥት ምንም እንኳን ስርቆትን ለመከላከልና አስመስለው የተሰሩ ከጥራት በታች ያሉ ስልኮችን አገር ውስጥ እንዳይገቡ ለመከላከል ነው ቢልም ከዚህ ቀደም ስልካቸው ተጠልፎ እንደ መረጃ የቀረበባቸው እንደ በፍቃዱ ኃይሉ ያሉ ጦማሪዎች "አስጨናቂ ጉዳይ ነው" በማለት ይገልፁታል። የሽብር ድርጊት ፈፅማችኋል በሚል ምክንያት ታስረው ከነበሩት የዞን ዘጠኝ ቡድን አባል የሆነው በፍቃዱ "መንግስት በስልክ በኩል ዜጎቹን ይሰልላል የሚባለው ውሸት አይደለም። " ይላል። ከመታሰራቸው በፊት ለአንድ ዓመት ያህል ያለምንም ፍርድ ቤት ፍቃድ ስልካቸው እንደተጠለፈ የሚናገረው በፍቃዱ እንደ መረጃም የተያያዘው ሰነድ የስልክ ንግግሮቻችን ናቸው ይላል። "እኛ በቁጥጥር ስር የዋልነው ሚያዝያ 2006 ዓ.ም ቢሆንም የቀረበብን መረጃ ከግንቦት 2005 ጀምሮ የተቀዳ ነው።" በማለትም ያስረዳል። ምንም እንኳን በፀረ-ሽብርተኝነት ህጉ የሽብርተኝነት ድርጊትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሽብርተኝነት የተጠረጠረን ሰው የስልክ፣ የፋክስ፣ የሬድዮና የኢንተርኔት፣ የኤሌክትሮኒክስና የፖስታ ግንኙነቶችን የመሳሰሉትን ለመጥለፍ ወይም ለመከታታል የፍርድ ቤት ፍቃድ እንደሚያስፈልግ በግልፅ ቢያትትም እንደ በፍቃዱ ላሉ በሽብር ለተፈረጁ ግለሰቦችም ህጉ ተፈፃሚ እንዳልሆነም ጨምሮ ይናገራል። ብዙ የሽብር ክሶችን የተከታተለው በፍቃዱ አብዛኞቹ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች የሚቀርብባቸው መረጃ በስልክ ያደረጉዋቸው ንግግሮች መሆናቸውንም ይጠቅሳል። ከተፈታ በኋላ በነበረው የስልክ ቁጥር መጠቀም ከብዶት የተለያዩ ሲምካርዶችን እየለዋወጠ እንደነበር የሚናገረው በፍቃዱ፤ በድጋሚ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ ከታሰረ በኋላ "ወደ ዱሮው እንደተጠለፈ ወደማውቀው ስልክ ተመልሻለሁ፤ ሲም ካርድ እየቀያየርኩ መሸወድ እችል ነበር። ነገር ግን መንግሥት የማወራውን ሰምቶ ንፁህነቴን ቢረዳልኝ ይሻላል የሚል ነው"በማለትም ይናገራል። ምንም እንኳን በፍቃዱ ወደ ቀድሞ ሲም ካርዱ ቢመለስም ብዙ ታስረው የተፈቱ ተቃዋሚዎችና ጋዜጠኞች ሲም ካርዳቸውን እንደሚቀይሩ በፍቃዱ ይናገራል። "ያለፍርድ ቤት ፍቃድ የስልክ ንግግሮችን የሚሰማ የመንግሥት ፀጥታ ኃይል መኖሩ በራሱ የሚፈጥረው የሚያሸብር ስሜት አለው" ይላል በፍቃዱ። የ አይኤምኢአይ ቁጥር ምዝገባ መምጣት የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የስለላ መረብን በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚያጠናክረውም ጨምሮ ይናገራል። "ፕራይቬሲን ከማጣት በተጨማሪ አሁን ደግም አካላዊ ነፃነታችንም ሊገደብ ነው" በማለት ይናገራል። የሶፍትዌር ባለሙያው ሐፍቶም በርኸ ሌላኛው የሶፍትዌር ባለሙያና የየሓ ቴክኖሎጂስ ሥራ አስኪያጅ የሆነው ሓፍቶም በርኸ የቴሌፎን ጠለፋ በተለያዩ ሃገራት በፍርድ ቤት ትእዛዝ ይደረጋል፤ ይህም ህጋዊ ጠለፋ ይባላል ይላል። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የጠለፋ ተግባር ይፈፀማል። ይህንንም ተግባር ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ተደራጁ ቡድኖች እንዲሁም በመንግሥታት ጭምር እንደሚካሄድም ይናገራል። ከዚህ ቀደም የነበሩ ጠለፋዎች ሂውማን ራይትስ ዎች ከሁለት ዓመት በፊት ባጠናቀረው ሪፖርት ያነጋገራቸው ኢትዮጵያውያን እንደተናገሩ በኬንያ እንዲሁም በአውሮፓ የመኖርያ ፍቃድ አግኝተው ወይም ጥገኝነት ጠይቀው የሚጠባበቁ በርካታ ግለሰቦች ስልካቸውና ኢሜይላቸው በፀጥታ ኃይሎች ተጠልፎ የተናገሩትና የተፃፃፉትን መልሰው ለራሳቸው እንዳሳዩዋቸው ይናገራሉ። ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ መንግስትም በተለያዩ ጊዜያት በሽብር የተጠረጠሩ ሰዎች ያደርጓቸዋል የተባሉ የተጠለፉ የስልክ ንግግሮች በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር መሰማቱ የሚታወስ ነው። ከቻይናና ከጣልያን የተገኙ የጠለፋ ሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች በተለይ በኢትዮጵያ ያለአግባብ የሰዎችን ግለሰባዊ ሚስጢራዊነትን ለመበርበር ተግባር እንደሚውል ሲንትያ ዎንግ የተባሉ በሂውማን ራይትስ ዋች የኢንተርኔት ከፍተኛ ተመራማሪ ይናገራሉ። ይህ ድርጊት መሰረታዊ የሆኑ ሰብአዊ መብትን የሚጥስ ድርጊት እንደሆነ፤ ሃገራቱም እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ለኢትዮጵያ መንግሥት ከመሸጣቸው በፊት ለምን ጥቅም እንደሚዉሉ ማረጋገጥ አለባቸውም ይላሉ ተመራማሪዋ። ምዝገባውን በተመለከተ ብዙዎች መንግሥት ዜጎቹ ላይ ጠለፋ ለማካሄድ እንዲቀለው ነው ሲሉ፤ ሃፍቶምም የሰዉን ጥርጣሬ አያጣጥለውም። የአይኤምኢአይ ቁጥር ምዝገባ ዋናው የመንግሥት ትኩረት ስርቆትን እንዲሁም ኮርፖሬሽኑ የሚያስቀምጣቸውን ጥቅሞች ለመስጠት ቢሆንም ስለላን በተመለከተ ለመንግሥት ቀላል ሥራ እንደሚያደርግለትም ጨምሮ ይጠቅሳል። ይህ አስተያየት ከፍራቻ የመነጨ ነው የሚሉት አብዱራሂም አንድን ሰው ለመከታተል ከአይኤምኢአይ ቁጥር ጋር እንደማይገናኝና ክትትልን በተመለከተ ኤችኤልአር ከሚባል ሶፍትዌር ጋር የተያያዘ አሰራር እንዳለም ይናገራሉ።
news-53080078
https://www.bbc.com/amharic/news-53080078
በጋና ሌቦች ፖሊስ ጣቢያን ዘረፉ
በዛሬዋ ዕለት በጋና መዲና አክራ ዘራፊዎች አንድ የፖሊስ ጣቢያን መስኮት ሰብረው በመግባት ላፕቶፕ፣ ቴሌቪዥንና የፖሊስ መለዮ አልባሳቱን እንደሰረቁ ተገልጿል።
ኒማ በተባለው ፖሊስ ጣቢያ መስኮት ሰብረው በመግባት መዝረፋቸው ተገልጿል። ባለስልጣናቱ ምርመራ ቢጀምሩም እስካሁን በተጠርጣሪነት የያዙት እንደሌለም አሳውቀዋል። ክስተቱ ብዙዎችንም አስደንግጧል፤ መገረምም ፈጥሯል። አንደኛ ሌቦቹ እንዴት ቢደፍሩ ነው ፖሊስ ጣቢያውን ለመዝረፍ የቻሉት የሚለው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ፖሊስ ጣቢያ የተመደቡ ጠባቂዎች አለመኖራቸው መነጋገሪያ ሆኗል። ነገር ግን ባለስልጣናቱ ለቢቢሲ እንዳስታወቁት ዘራፊዎች መስኮት ሰብረው በገቡበት ወቅት ፖሊሶች የጦር መሳሪያዎችን እንዲሁም ሌሎች ተጠርጣሪዎች የተያዙበትን ህንፃ እየጠበቁ ነበር ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም በዘራፊዎቹ የተሰበረው የፖሊስ መስኮትም እየተጠገነ ነው ተብሏል።
news-57222401
https://www.bbc.com/amharic/news-57222401
'ለኤርትራ ነጻነት 30 ዓመት ተዋደቅን፤ ለ30 ዓመት ዲሞክራሲን ጠበቅን፤ አልመጣም' የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ
ኤርትራ ነጻነቷን ካገኘች 30 ዓመት ደፈነች። የቀድሞው የቢቢሲ ትግርኛ አርታኢ የነበረው ሳሙኤል ገብረሕይወት ለነጻነቱ ነፍጥ አንግበው ከተዋደቁ ኤትራዊያን አንዱ ነበረ። ስለ ትግሉ እና እንደ ጉም ስለተነነው ኤርትራዊያን የነጻነትና ዲሞክራሲ ተስፋ እንዲሁም አገሪቱ እንዴት በአምባገነን እጅ ስር እንደወደቀች እንዲህ ይተርካሉ።
በርካታ ወጣቶች በኤርትራ የነጻነት ትግል ውስጥ ተሳትፈዋል ለሰላሳ ዓመታት ነፍጥ አንስተን ለነጻነት ተዋጋን፣ እያንዳንዱ ቀንና ሰዓት በጦርነት የሚያልፍ ነበር። ስቃይንና መስዋዕት መሆንን ለመድነው። አብዛኞቻችን ሁለት ወይም ለሦስት ጊዜ ቆስለናል። ይህ ብርቅ አይደለም። እንደነገሩ ታክመን ወደ ሌላ ጦርነት እንዘምት ነበር። በሰሜን ኤርትራ ቃሮራ ግንባርን እንዴት እንደታደግን ይገርመኛል። በደቡብ ኤርትራ ዱሜራን እንዴት እንደተከላከልን ይደንቀኛል። ምሽግ ለምሽግ እየተሳብን፣ እዚያው እያደርን፣ ተራራ እየቧጠጥን፣ ከሸለቆ ሸለቆ እየዘለልን…። ብቻ እኔ ከዕድለኞቹ እመደባለሁ። 65 ሺህ ጓዶቻችን በጦርነቱ ሞተዋል። የነጻነት ግንባሩን የተቀላቀልኩት በፈረንጆች 1982 ላይ ገና በ16 ዓመቴ ነበር። ስለነጻነት ተዋጊ ኤርትራዊያን ብዙ እሰማ ነበር። ቁምጣቸው፣ ረዥም ጸጉራቸው፣ የሚይዙት ኤኬ 47 ጠመንጃ …፣ ይህ ሁሉ ታሪካቸው ያጓጓኝ ነበር። በአራግ ሸለቆ ለጥቂት ወራት ስልጠና ተሰጠኝ። እንዴት ጥቃት መሰንዘር እንደምንችልና እንዴት ማፈግፈግ እንደሚቻል ተማርን። እንዴት ራሳችንን ከአካባቢው ጋር ማመሳሰል እንደምንችል፣ እንዴት መደበቅ እንደምንችል፣ እንዴት ቦምብ ፈቶ መግጠም፣ ነቅሎ መጣል እንደሚቻል፣ አርፒጂ መሣሪያ አጠቃቀምን ሁሉ ሰለጠንን። ስልጠናችን መጥፎ የሚባል አልነበረም። ጎን ለጎን ደግሞ የፖለቲካ ትምህርት እንደወስድ ነበር። ከዚህ መሀል እንዴት ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ማቋቋም እንደምንችል ጭምር ተምረናል። ከዚህ ስልጠና በኋላ በበርካታ ጦርነቶች ውስጥ ተሳትፊያለሁ። መደምደሚያው የነበረው በ1990 (እአአ) በምጽዋ ወደብ ላይ የተደረገው 'የፈንቅል ዘመቻ' ነበር። ሳሙኤል ገብረሕይወት ያ ድል እጅግ ወሳኝ ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን ከኤርትራ እንዲወጣም ያስገደደ ቁልፍ ወታደራዊ ድል ነበር። ያን ጊዜ ያለማቋረጥ ለ72 ሰዓታት ተዋግተናል። እጅግ ወሳኝ የነበረችውን ምጽዋን ለመያዝ ያልሆነው የለም ማለት ይቻላል። ከዚያ በኋላ ደግሞ ለመከላከል 100 ኪሎ ሜትር ምሽግ ቆፍረን ከአንድ ዓመት በላይ ቆይተናል። በዚህ ውጊያ ጭንቅላቴ ላይ እንዲሁም እጄ ላይ ቆስያለሁ። ከዚያ ሆስፒታል ታክሜ ዳንኩ። ታዲያ ወዲያውኑ ወደ ውጊያ ነበር የተመለስኩት። በ1980ዎቹ መጨረሻ ወደ ኪነትና ባሕል ክፍል ተዛወርኩ። የዚህ ክፍል ዋና ዓላማ ወታደሩን በሙዚቃና ድራማ ሞራሉን ከፍ ማድረግ፣ ማነሳሳት ነበር። በ1991 (እአአ) ከምጽዋ ቅርብ ርቀት በዳሕላክ ደሴት ላይ ነበርን። ዳሕላክ ሳለን ነበር በሕይወታችን እጅግ ጣፋጩን ዜና የሰማነው። ኤርትራ ነጻነቷን እንደተቀዳጀች ተነገረን። የፈንጠዚያ ቀናት በደስታ ሰክረን በጀልባ ወደ ምጽዋ ተጓዝን። እዚያ ስንደርስ ከባድ ተሸከርካሪ ላይ ተጭነን ወደ ዋና ከተማ አሥመራ ጉዞ ጀመርን። ጉዞው ሦስት ሰዓታትን የፈጀ ነበር። የኢትዮጵያ ሠራዊት ደቡባዊ ቀጠናን አለፍነው። ሰው የሚባል አልነበረም። የኢትዮጵያ ወታደሮች ጥለውት ሄደዋል። በአሥመራ ውስጥ ሕልም የሚመስል አውድ ነበር። ነዋሪዎች እኛን የነጻነት ታጋዮችን ለመቀበል ጨርቄን ማቄን ሳይሉ አደባባይ ወጥተው ነበር። በጓይላ ጭፈራ ራሳቸውን ስተው ነበር። ጎዳናው በሙሉ ሕዝብ ፈሶበት አስታውሳለሁ። ይህ በአሥመራ ብቻ ሳይሆን በሌሎች ከተሞችና መንደሮችም የታየ ኩነት ነበር። ይህ ቀን ከመምጣቱ በፊት አሥመራ ሙሉ በሙሉ ጭንቅ ውስጥ ነበረች። አየር ማረፊያው በተከታታይ በተኩስ ሲናጥ ነበር የሰነበተው። ጥብቅ ሰዓት እላፊም ታውጆ ነበር። ልክ በግንቦት 24 (እአአ) ሁሉ ነገር ተለወጠ። እናቶች የጣዱትን ጀበና ትተው፣ የለኮሱትን ሞጎጎ እንጀራ መጋገሪያቸውን ጥለው፣ የቡና ሥነ ሥርዓታቸውን ጣጥለው ግልብጥ ብለው አደባባይ ወጥተው ነበር። ይህም እኛን ታጋዮችን ለመቀበል ነበር። ብዙ ኤርትራውያን የዘንባባ ዝንጣፊ ይዘው ይታዩ ነበር። ወጣቶች እየዘለሉ ታንክ ላይ ይወጡ እንደነበረና የዘንባባ ዝንጣፊ እያውለበለቡ ሲቀበሉንም አስታውሳለሁ። ይህ ፈንጠዝያ ለቀናት ቀጠለ። ምሽቶቹም ደማቅ ነበሩ። በእርግጥ በዚህ ደማቅ ስሜት መሀል ጭንቅም ነበረ። ወላጆች የልጆቻቸውን ፎቶ ይዘው በመውጣት በሕይወት ይኖሩ እንደሁ ይጠይቁ ነበር። ሕዝበ ውሳኔ ከተካሄደ በኋላ እናቶች ደስታቸውን ሲገልጹ "ልጄ ተርፎልኝ ይሆን? ልጄ ሞታ ይሆን?" የሚል የማያባራ ጥያቄ። በኛ ምድብ ገድለና አባየይ የሚባሉ ጓዶች ነበሩ። ሁለቱ ጓዶች ፊት ለፊት በመኪና ላይ ተጭነው ቤተሰባቸውን ባዩ ጊዜ የሆኑት ትዝ ይለኛል፤ ሲጮኹ፣ ሲስቁ፣ የደስታ እንባ ሲያነቡ። የገድለ አባት "ልጄን አገኘሁት! ልጄን አገኘሁት!" እያለ ወደኛ መኪና ሲሮጥ ትዝ ይለኛል። አባየይ ደግሞ ሴት ታጋይ ነበረች። ጋቢና ነበር የተቀመጠችው። የባለቤቷን እናት ስታይ ጊዜ ድንገት እየሄደ ከነበረ መኪና ዘላ ልትወርድና ራሷን ለከፍተኛ አደጋ ልታጋልጥ ስትል ነበር በተአምር የዳነችው። በኋላ ላይ በአዛዦቻችን ፈቃድ ተሰጠን፤ ፈቃዱ ወጥተን ቤተሰባችንን እንድናገኝ ነበር። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ ቤተሰብን ማግኘት ቀልድ አልነበረም። ለእነዚያ ሁሉ ዓመታት የተለዩትን ማግኘት እንዲህ የዋዛ አልነበረም። ሆኖም ብዙዎቻችን ዘመድ አላጣንም። በዚያ ቅጽበት ሁላችንም እናስብ የነበረው ከዚህ ሁሉ በኋላ ኤርትራ በልጽጋ፣ ችግር ከኤርትራ ምድር ጠፍቶ እያንዳንዱ ኤርትራዊ በደስታና በፍሰሐ መኖር ይጀምራል የሚል ነበር። ነገር ግን ይህ ተስፋችን እንደ ጉም ሊተን ብዙ ጊዜ አልወሰደበትም። የነበረንን ሁሉ ሰጠን፣ ለነጻነት ስንል። ወጣትነታችንን፣ ሕይወታችንን…። ብዙዎቻችን ከነጻነት በኋላ ከውትድርና ተሰናብተን ቤተሰባችንን ተቀላቅለን፣ ትምህርታችንን ቀጥለን፣ ወደ ግል ሥራና ኑሮ ለመመለስ ነበር ዕቅዳችን። ሆኖም ሠራዊቱን እንኳ ለመልቀቅ እንደማንችል ስናውቅ ተደነቅን። ወታደራዊ አዛዦቻችን የፖለቲካ መሪዎች ሆኑ። አዲሲቷ አገር በእጇ ምንም ቤሳቤስቲ እንደሌላት ነገሩን። ኤርትራ ያላት ብቸኛ ሀብት የያዝናቸው የጦር መሣሪያዎች እንደሆኑ ተነገረን። ከዚያ ሁሉ የጦርነት ፍዳና መከራ በኋላ የቀድሞ ተዋጊዎች ቀበቷችንን ይበልጥ እንድናጠብቅ በድጋሚ አረዱን። ማንኛውንም ሥራ ያለ ክፍያ እንድንምንሰራ ነገሩን። ምግብ ብቻ ይሰጡናል። በነጻ እናገለግላለን። ይህ ሁኔታ ለሁለት ዓመት ቀጠለ። ከዚያ በኋላ ነው ትንሽ ገንዘብ ማግኘት የጀመርነው። በትግሉ ጊዜ ልክ እንደ አንድ ቤተሰብ ይተሳሰቡ የነበሩ ታጋዮች የመሪዎቹን እውነተኛ ባሕሪ ሲረዱ ተከፉ። ብዙዎቹ ወታደራዊ መሪዎች አገሪቱ ልክ ነጻ ከመውጣቷ አስረሽ ምቺው ውስጥ ገብተው ነበር። በርካታ ታላላቅ አመራሮች በየመሸታ ቤቱ ይታዩ ነበር። ራሳቸውን እስኪስቱ ይጠጡም ነበር። በዚህ ወቅት ታጋዩ ኑሮው አለት ሆኖበት ነበር። የዕዝ ሰንሰለቱ እየላላ፣ መደበኛ ስብሰባዎች እየተረሱ መጡ። መደበኛ ታጋዮች ነገሮች ከዛሬ ነገ ይስተካከላሉ ሲሉ ተስፋ አደረጉ፤ ገፋ ብለው ጠበቁ፣ ጠየቁ። አዲስ ነገር አልነበረም። በርካታ ሴቶች በኤርትራ የነጻነት ትግል ውስጥ ተሳትፈዋል ከጎረቤት ጋር አዲስ ጦርነት እንደ አውሮፓውያኑ በ1993፣ የኤርትራ ነጻነት 2ኛ ዓመት ሊከበር ዋዜማ፣ የቀድሞ ተዋጊዎች አመጹ። መሪዎቻቸው ብሶታቸውን እንዲያዳምጡም ተማጸኑ። መሪዎቻቸው ታላቅ ስብሰባ በአሥመራ ስታዲየም እንዲጠሩ አስገደዷቸው። የተሰጠው ምላሽ ግን፣ "ችግራችሁ ይገባናል፣ የተለደመ ችግር ነው፤ ሁሉንም በቅርብ እንፈታዋለን" የሚል ነበር። ልክ ይህ ስብሰባ እንዳበቃ ታዲያ መሪዎቹ የአመጹን አስተባባሪዎች አፍነው ወሰዱ። አንድ በአንድ። በጥቂት ጊዜ ውስጥ ከአንድ ዓመት እስከ 15 ዓመት እንደተፈረደባቸው ሰማን። የታጋዩን ችግር በይፋ በመናገራቸው ትልቅ ዋጋ ከፈሉ። ብዙ "ሰዎች በቃ መሪዎቻችን ወደ አምባገነንነት ሊለወጡ ነው" ማለት ጀመሩ። ሌሎች ግን ትንሽ መታገስና ማየት እንደሚገባ መከሩ። ኤርትራ እያረቀቀችው ያለው ሕገ መንግሥት ሲጠናቀቅ አገራችን ወደ ዲሞክራሲ እንደምታመራ ተነገረን። ይህ ሁሉ ግን መና ቀረ። ኤርትራ በአንድ ፓርቲ የምትመራ፣ ምርጫ አካሄዳ የማታውቅ አገር ሆና ቀረች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ኤርትራ ከሁሉም ጎረቤቶቿ ጋር ጦርነት ውስጥ ገባች። ከየመን በ1995፣ ከሱዳን በ1996፣ ከኢትዮጵያ በ1998 እና ከጂቡቲ ጋር በ2008። አዲሷ አገራችን ኤርትራ ሌሎች ተጨማሪ 10ሺህ ወጣቶቿን ሕይወት አስቀጠፈች። አሁን የኤርትራ ወታደሮች ከነጻነት በኋላ በ5ኛው ዙር ጦርነት ውስጥ ይገኛሉ። አሁን የኤርትራ ወታደሮች በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ውስጥ ነው። ከህወሓት ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። ህወሓት ኤርትራ ነጻነቷን ባወጀች ጊዜ ሥልጣን ላይ የነበረ ነው። ከ1998 እስከ 2000 ከኢትዮጵያ ጋር በተደረገው ጦርነት ወቅትም የነበረ ነው። ከነጻነት በኋላ በነበረው ጊዜ ከገዢው ፓርቲ የባሕል ክፍል ውስጥ ገባሁ። ለታጋዮች የሚገባቸውን ሞገስ ለማሰጠት ብሎም አገሪቱን ለመገንባት ብዙ ሥራ እሠራለሁ በሚል ነበር። በርካታ ተውኔቶችን፣ ሙዚቃዎችን ደረስኩኝ። ተሳትፌባቸዋለሁም። ተወዳጇ ሔለን መለስ 'ምጽዋ' የሚለውን የኔን ሙዚቃ ተጫወተችው። ሙዚቃው 'ምጽዋ ወድ ልጆችሽ የት ገቡ?' የሚል ነበር። ለውጥ አይቀሬ ነው ትንሽም ቢሆን ጭል ጭል ትል የነበረችው የፖለቲካ ምህዳር ተስፋ የኢትዮጵያ-ኤርትራ ጦርነት ማግስት ከሰመች። መንግሥት ልወረር ነው የሚል ሥነልቦና በሕዝቡ ዘንድ ገዢ ሐሳብ እንዲሆን አደረገ። ይህ ጦርነት በጠረጴዛ ዙርያ ንግግር ብቻ እንዲቀር ማድረግ ይቻል እንደነበር ብዙዎች ያምናሉ። በመስከረም 2001 (እአአ) ደግሞ መንግሥት ያልተጠበቀ እርምጃ እንዲወሰድ አዘዘ። አሥራ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት እና መካከለኛ ካድሬዎች ድንገት ዘብጥያ ወረዱ። ለዚህ የተዳረጉት ታዲያ አንዳንድ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ስለጠየቁ ብቻ ነው። ከዚያች ዕለት ጀምሮ ሰዎቹ የት እንዳሉ ምንም አልተሰማም። እነዚህን መሻሻል እንዲደረግ የጠየቁ ባለሥልጣናትን ያናገሩ፣ ስለነሱ የጻፉ 11 ጋዜጠኞችም ታስረዋል። ከነዚህ መሐል ወዳጄና ጓደኛዬ ስዩም ይገኝበታል። ስዩም ያኔ በድል ስንገባ ፎቶ ሲያነሳ የነበረ ልጅ ነው። እነዚህ ሁሉ እስረኞች አንዳቸውም ፍርድ ቤት አልቀረቡም። አንዳቸውም ያሉበት አይታወቅም። ኤርትራ አሁንም የአንድ ፓርቲ አገር ናት። ከነጻነት ወዲህ ለ30 ዓመት ምርጫ የሚባል ነገር አድርጋ አታውቅም። ነጻ ፕሬስ የለም። ነጻ አደረጃጀት የለም። ሁሉም ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ሆኑ የአገር ውስጥ ሲቪክ ድርጅቶች ታግደዋል። ይፋ የሚደረጉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከነጻነት ወዲህ በአገሪቱ ውስጥ የጤናና የትምህርት አገልግሎት እንደተሻሻሉ ያሳያሉ። ይህን ማመን ግን ከባድ ነው። ካለው ጥቂት የሥራ ዕድል እና አስገዳጅ እንዲሁም ክፍያ አልባ የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ጋር ተያይዞ በርካታ ወጣቶች አገሪቱን እየለቀቁ ነው። በርካታ ወጣቶች በሌሎች የአፍሪካ አገሮችና በአውሮፓ ተጠልለው ይኖራሉ። ይህ ሁሉ ሆኖ ግን አሁንም ብዙዎቻችን ተስፋ አልቆረጥንም። ለውጥ አይቀሬ እንደሆነ በጽኑ እናምናለን። ኤርትራ አንድ ቀን በሰማዕታት ቃል የተገባላትን የዲሞክራሲ ሕልም ትኖረዋለች።
52854628
https://www.bbc.com/amharic/52854628
"ሚዲያው ዛሬ በአግባቡ ካልተገራ ነገ ከባድ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል" ዘነበ በየነ (ዶ/ር)
ባለንበት ዘመን ማኅበራዊው የመገናኛ መድረክን ጨምሮ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ስፍር ቁጥር የሌለውን መረጃ በየደቂቃው ለታዳሚዎቻቸው ያቀርባሉ።
በዚህ ሂደት ውስጥ ጠቃሚና ሐቀኛ መረጃዎች የመቅረባቸውን ያህል አሳሳችና አደገኛ ወሬዎች ተሰራጭተው አለመግባባትና ጉዳትን ያስከትላሉ። በተለይ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቁጥራቸው የበዛ የተለያየ አላማ ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ወደ ሕዝቡ እየደረሱ ባሉበት ጊዜ ስጋት የሚፈጥሩባቸው አጋጣሚዎች ጥቂት የሚባል አይደለም። ከዚህ አንጻር የታዘቡትንና መደረግ አለበት የሚሉትን እንዲያካፍሉን ዘነበ በየነን (ዶ/ር) ጋብዘናል። ዘነበ በየነ (ዶ/ር) አሜሪካ በሚገኘው የሚሲሲፒ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ትምህርት መምህር ናቸው። በአብዛኛው ጥናቶቻቸው መገናኛ ብዙኀን ለሰላምና ለአገር ግንባታ ያላቸውን አስተዋጽኦን ይመለከታል። በቅርቡ ደግሞ፤ 'ሁሉ የሚያወራበት፤ አድማጭ የሌለበት' የሚለው ጥናታቸው በተለይ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ አለ የሚሉትን ነባራዊ ሁኔታን እንደሚገልጽላቸው ይናገራሉ። መገናኛ ብዙኀን የሚጠበቅባቸውን ከወገንተኝነት በራቀ ሁኔታ ሙያዊ በሆነ መልኩ የሚሰሩ ከሆነ በሕዝብ መካከል መግባባትን ለመፍጠር የመቻላቸውን ያህል በተቃራኒው ከሆኑ ደግሞ አለመግባባትና የሠላም መናጋትን ሊያስከትሉ ይችላሉ። ከዚህ አንጻር ቢቢሲ ለ ዘነበ (ዶክተር) የሕዝብን ሰላም ሊያናጉ የሚችሉ ዘገባዎች የሚሉዋቸው የትኞቹ እንደሆኑና ሕዝቡ ሐሰተኛውን ከሐቀኛ ዘገባ እንዴት ነው መለየት ይችላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ በመስጠት ይጀምራሉ፡ ዘነበ (ዶ/ር)፡ ብዙ ነው። ሌላ አካባቢ የተደረጉ ነገሮችን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ተደረገ አድርጎ ማቅረብ ኃላፊነት የጎደለው ነው። ከሁሉ በላይ ለአንድ ሚድያ ትልቁ ዋጋው እምነት ነው። አንድን ነገር ሲፈጸም አንዳንድ ሚድያዎች "የሆነው ነገር ምንድን ነው፤ መረጃ ከየት ነው የምናገኘው? ያገኘነው እንዴት ነው የምንጠቀምበት?" ብለው ሊያስቡበት ይገባል። የሕብረተሰቡን ንቃተ ህሊና መጨመር ያስፈልጋል። ሕዝቡ፣ ውሸት የሚነዙ ሚድያዎችን እርግፍ አድርጎ የሚተዋቸው፤ ንቃተ ህሊናው ከፍ ያለ እንደሆነ ብቻ ነው። የዛሬ ሦስት ዓመት የተደረጉትን ዛሬ እንደተደረጉ አድርጎ ማቅረብ ከማንም በላይ የሚጎዳው ራሱ ሚድያውን ነው። ለጊዜው ሕዝብን ሊያደናግር ይችላል፤ ከሁሉም በላይ ግን ራሱ ሚድያው ነው ተዓማኒነቱን የሚሸረሸረው። መንግሥት፤ እንደዚህ ዓይነት ኃላፊነት የጎደላቸው የሚድያ አውታሮችን ተጠያቂ ሊያደርግ ይገባል። ያ ሚድያ መንግሥታዊ ሊሆን ይችላል የግል ሊሆን ይችላል። ምንም ለውጥ የለውም። ኃላፊነት የጎደለው ሥራ እስከሰራ ድረስ፣ መጠየቅ የመንግሥት ግዴታ ነው። መንግሥት የሕዝብን ደኅንነት የመጠበቅ ግዴታ አለበት። ቢቢሲ፡ ከዚህ በፊት በነበረው የኢህአዴግ ሥርዓት፡ ሚድያው የመንግሥት አፈቀላጤ ሆነ ተብሎ ሲተች ነበርና፣ አሁን በዚህ ሁለትና ሦስት ዓመታት ውስጥ በሚድያው ላይ ምን ለውጥ ተመለከቱ? ዘነበ (ዶ/ር)፡ ይህ ተደጋግሞ ሲነሳ እሰማለሁ። "መንግሥት ተለውጧል፤ ሚድያውስ ለውጧል ወይ?" የሚል። አንድ ደረጃ ወደ ኋላ መሄድ ያለብን ይመስለኛል። ኢትዮጵያ ውስጥ መንግሥት ተቀይሯል ወይ? ሁላችንም ጥያቄ አለን። ምክንያቱም እርግጥ ነው አስተዳደሩ ተቀይሯል። ከአቶ መለስ ወደ አቶ ኃይለማርያም፤ ከአቶ ኃይለማርያም ወደ ዶክተር ዐብይ የስልጣን ሽግግር ተደርጓል። መዘንጋት የሌለብን ግን ሁሉም ኢህአዴጎች መሆናቸውን ነው። በዶ/ር ዐብይ ጊዜ ብዙ ልናስባቸው የማንችላቸው አንዳንድ ለውጦችን እየተመለከትን ነው። እሱ ላይ ጥርጣሬ የለኝም። 'ከዚያው አንጻር ሚድያው ተቀይሯል ወይ?' የሚለው ጥያቄ ግን ልንመረምረው የሚገባ ጉዳይ ይመስለኛል። ምክንያቱም፣ ጋዜጠኞቹ እነዚያው ናቸው፣ መሰረተ ልማቱ ያው ነው። አስተሳሰቡ [ማይንድ ሴቱ] ያው ነው። ከሁሉም በላይ የፖለቲካ ባህል የምንለው ያው ነው። ጋዜጠኛው የኅብረተሰቡ ውጤት ነው። ኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው የፖለቲካ ባህል ተቀይሯል ወይ? ብለን በምናስብበት ሰዓት እንደውም ጥግ የመያዝ ሁኔታ አሁን የባሰ እየጎላ የመጣ ይመስለናል። ምክንያቱም አንዳንድ ሚድያዎች በተለይ ደግሞ ሶሻል ሚድያው ላይ፤ ጥግ ይዞ ድንጋይ መወራወር ላይ ነው ያለው። ያ ድንጋይ የሚወረወረው ግን ሕዝብ ላይ ነው፤ ወገን ላይ ነው። አገር ላይ ነው። አንዳንዴ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን መሆናችን የረሳን ይመስለኛል። ምንድነው እያደረገን ያለነው? እየሄድን ያለነው ወዴት ነው? የሚለውን ነገር በአግባቡ ልንመለከተው ይገባል። ቀደም ሲል እንዳልኩት፤ የመንግሥት አስዳደር ለውጥ የፖለቲካ ባህሉና ባህሪው እስካልቀየረው ድረስ ያ በድሮ 'ማይንድ ሴት' ውስጥ ያለው ሚድያ አዲስ ነገር ያመነጫል ብሎ መጠበቅ በጣም ከባድ ነው። ከሁሉ በላይ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ አስቸጋሪ የሚያደርገው ሁኔታ ሁሉም በየአካባቢው ሶሻል ሚድያ አለው፤ ወይም ደግሞ ጠንካራ የሆነ የራሱ ሚድያ አለው። ስም መጥቀስ አያስፈልግም። ሁላችንም የምናውቃቸው ናቸው። በነገራችን ላይ ሚድያው ዛሬ በአግባቡ ካልተገራ ነገ ዋጋ ያስከፍለናል። ቢቢሲ፡ የመገናኛ ብዙሃን ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ምን ሊያስከትል ይችላል ይላሉ? ዘነበ (ዶ/ር)፡ ምሳሌ ለመጥቀስ ኬንያ በ2007/8 (እኤአ) ከምርጫው በኋላ የተከሰተው ግጭት በአብዛኛው እሳት ያቀጣጥሉ የነበሩት፤ ለግጭቱ ከፍተኛ አስተዋጸኦ ሲያደርጉ የነበሩት የሬድዮ ጣብያዎች ናቸው። ለምሳሌ ሪፍት ቫሊ አካባቢ የነበረው የሬድዮ ጣብያ ትልቁን ሚና ተጫውቷል። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ነባራዊ ሁኔታም መንግሥት አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥቶ ሚድያዎቹን ማስተካከል ካልቻለ ነገ ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍሉናል። ስለዚህ "የመንግሥት ለውጥ ተደርጓል፤ ሃሌ ሉያ ስለዚህ የሚድያ ለውጥ ይኖራል፤ ወደ ተስፋይቱ ምድር እየገሰገስን ነው፤ ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ ሆነዋል" ብለን የምናስብ ከሆነ ራሳችንን እያታለልን ነው። ከሁሉ በላይ ሶሻል ሚድያው እየፈጠረው ያለው አደጋ ቀላል አይደለም። ሚድያው አንዳንድ ጊዜ የሚሰነዝራቸው ነገሮች ለሶሻል ሚድያ መልስ የመስጠት እስከሚመስል ድረስ ነው። ማይንማር [በርማ] የተፈጠረው ከፍተኛ ዘር ተኮር ጥቃት [ዘር ማጥፋት] በማኅበራዊ ሚድያው ዋና መሪነት የተካሄደ መሆኑን ልናውቅ ይገባል። እኛ አካባቢስ ሚድያዎቻችን ምን እየሰሩ ነው ያሉት ብሎ መመርመር ያስፈልጋል። በሌሎች ሚድያዎች የማየው ነገር ችግሩ እንዳለ ነው። አፈቀላጤ የመሆን፣ ኃላፊዎችን የመፍራት፣ በአንድ አቅጣጫ የመሄድ ነገር ይታያል። ከዚያ በዘለለ የሕዝቡ የልቡ ትርታ ማደመጥና ብዙ ሥራ መስራት የሚጠበቅብን ይመስለኛል። ይህንን ስል በፌዴራል ላይ ያሉትንም በክልል ላይ ያሉትንም ይመለከታል። ቢቢሲ፡ አሁን በተጨባጭ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ካነሱዋቸው ችግሮች ኣንጻር ምን ይደርግ ይላሉ? ዘነበ (ዶ/ር)፡ ሚድያው ውስጥ ያሉት ሰዎች መሆናቸው አንዘንጋ። በተለያዩ ምክንያቶች ስህተት ይሰራሉ። 'ኢትዮጵያ ውስጥ እንዴት ብቁ ጋዜጠኛ መፍጠር እንችላለን?' ብለን ማሰብ አለብን። ሕንድ ለምሳሌ ትልቁ የዲሞክራሲ አገር እየተባለች የምትንቆለጳጰሰው ጥሩ የሚባል ሚድያ ስላላት ነው። ጋና፣ ኬንያና ደቡብ አፍሪካ እነዚህ ሚድያዎች ከሌላ ጋር ሲነጻጸር ውጤታማ የሆነ ዲሞክራሲ እንዲፈጠር የራሳቸው ሚና ተጫውተዋል። ኢትዮጵያም ውስጥ የምንፈልገው ዲሞክራሲና የሰብዓዊ መብት አያየዝ እንዲመጣ ከፈለግን የሚድያው ሁኔታው መለወጥ አለብን። ማብቃት አለብን። መጀመሪያ ነገር ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ስልጠናዎች መስጠት ይገባል። ለምሳሌ በእርድ ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው ቢላውን አስር ግዜ መሞረድ አለበት፤ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ መስራት ስለሚያቆም። ብዙ ነገሮች ስለሚለዋወጡ ሚድያውም እንደዚያ ነው። ጋዜጠኞች አቅማቸውን የምንገነባ ከሆነ አስፈላጊውን ግብዓት የምናቀርብላቸው ከሆነ የማይቀየሩበት ምክንያት የለም። ይሄ ሁሉ ተደርጎ የማይቀየሩ ካሉ፤ ኬንያ ውስጥ አንድ የሚታወቁበት ነገር አላቸው። 'ኔሚንግ ኤንድ ሼሚንግ' [መጥፎ ድርጊትን ማጋለጥ] ይሉታል። ጋዜጠኞች ሆኑ ፖለቲከኞች ኃላፊነት የጎደለው ሥራ በሚሰሩበት ጊዜ፣ ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት በሚሞክሩበት ጊዜ እንዲሸፈኑና እንዲደበቁ አይፈቅዱላቸውም። አሜሪካ በምትመጣበት ጊዜ ሲቪክ ማኅበረሰቦች አሉ፤ ዘረኝነትን የሚሰብክ የሚድያ አውታሮችን 'ኔሚንግ ኤንድ ሼሚንግ' የሚለው ዘዴ እየተከተሉ ይሰራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንደዚህ ካልተደረገ በስተቀር፤ የእኔን ፍላጎት ስለአንጸባረቀልኝ ብቻ ይሄኛው ሚድያ ትክክል ነው የምል ከሆነ፤ ልክ አይደለም። ዛሬ ምናልባት ሴቶችን ብቻ ለይቶ የሚያጠቃ ሚድያ ካለ፣ 'እኔ ወንድ ነኝ፤ አይመለከተኝም' ብለን የምናልፈው ከሆነ፤ ነገ እኔጋ ሲመጣ ሊያስቆመው የሚችል ኃይል አይኖርም። ስለዚህ በአንድ ወገናችን ላይ የሚሰራው የሚድያ ጥቃትና ግፍ ሁላችንም ላይ እንደተሰራ አድርገን ልንቆጥረው ይገባል። ስለ እውነትና ስለልጆቻችን ስንል ሚዲያው ዛሬ በአግባቡ ካልተገራ ነገ ከባድ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል።
news-50484487
https://www.bbc.com/amharic/news-50484487
ከብራና ወደ ኮምፒውተር . . .
ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) ያስመዘገበቻቸው የሥነ ጽሑፍ ቅርሶችን ጨምሮ (በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈው አርባዕቱ ወንጌል እና ዳግማዊ አፄ ምኒሊክ ለሞስኮው ንጉሥ ኒኮላር ቄሳር ሁለተኛ የጻፉት ደብዳቤ ይገኙበታል) የበርካታ ጥንታዊ መዛግብት ባለቤት ናት።
በላሊበላ ናኩቶ ለአብ ቤተ ክርስቲያን የሚገኝ ጥንታዊ የጽሑፍ ቅርስ እነዚህ ጽሑፎች የቀደመውን ዘመን ታሪክ ከማንጸባረቅ ባሻገር የማኅበራዊ መስተጋብር፣ የፖለቲካዊ ሥርዓት፣ የህክምና፣ የሥነ ከዋክብት ጥናት እና ሌሎችም መረጃዎችን ይዘዋል። ዲጂታይዜሽን (ጽሑፎችን በካሜራ ቀርጾ በዲጂታል ቅጂ ማስቀመጥ) እነዚህ ጥንታዊ ጽሑፎች ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚሻገሩበት ዘመነኛ መንገድ ነው። ያለንበት የቴክኖሎጂ ዘመን ሰዎች እንደቀድሞው ጽሑፍ የሚያገላብጡበት ሳይሆን በኮምፒውተር መረጃ የሚያገኙበት ነው። ይህንን ከግምት በማስገባትም በርካታ አገሮች ጥንታዊ ጽሑፎችን ዲጂታይዝ ማድረግ ከጀመሩ ዓመታት ተቆጥረዋል። በብራና ላይ በግዕዝና በአረብኛ የሠፈሩ ጥንታዊ ጽሑፎችን በዲጂታል ቅጂ የማስቀመጥ ሂደት ውስጥ ከሚሳተፉት አገራዊ ተቋሞች መካከል ብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር) ይጠቀሳል። ውጪ አገር የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋሞች እና ተመራማሪዎችም ጥንታዊ መዛግብትን ዲጂታይዝ ማድረግ ጀምረዋል። የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች ሰው ሰራሽ ወይም ተፈጥሯዊ አደጋ ቢደርስባቸው፤ ቅጂያቸውን ለማትረፍ በካሜራ ይቀረጻሉ። ቅርሶቹ ባሉበት ቦታና ይዞታ ተጠብቀው፤ ቅጂያቸው ለተመራማሪዎች እንዲሁም መረጃውን ለሚፈልጉ ግለሰቦች በአጠቃላይ ተደራሽ እንዲሆንም ዲጂታይዜሽን ሁነኛ አማራጭ ነው። • ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ • የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን የባህል ጥናት እና ምርምር ማዕከል ተመረቀ በርካታ ጥንታዊ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች ያሏት ኢትዮጵያ ምን ያህሉን መዛግብት ዲጂታይዝ ማድረግ ችላለች? በባለሙያዎች ከሚነሱ ጥያቄዎች አንዱ ነው። ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ አንጻር የጽሑፎቹን ዲጂታል ቅጂ ለተጠቃሚዎች ማድረስ ተችሏል ወይ? ሌላው ጥያቄ ነው። የዘርፉ ባለሙያዎች በዋነኛነት ከሚያነሷቸው ተግዳሮቶች መካከል በቴክኖሎጂ ብቁ አለመሆንና የባለሙያ እጥረት ይገኙበታል። በቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን የቅርስና የታሪክ ከፍተኛ ባለሙያ እንዲሁም የፊሎሎጂ ሦስተኛ ዲግሪ ተማሪ እስራኤል አራጌ በበኩላቸው የቅርሶቹ ባለቤቶች ዲጂታይዜሽንን እንደማይደግፉ ያስረዳሉ። የቅርሶቹ ባለቤት ከሆኑት አንዷ የሆነችው ቤተ ክርስቲያን፤ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶቹ ይሰረቃሉ በሚል ስጋት ዲጂታይዜሽንን እንደማታበረታታ ይናገራሉ። "በተለይም የውጪ አገር ምሁራን ዲጂታይዝ ለማድርግ ሲመጡ፤ ቅርሶቹ ተዘረፉ ስለሚባል በቤተ ክርስቲያን ዘንድ የዲጂታይዜሽን ጥቅም አይታይም። ቤተ ክርስቲያኗ እንኳን ለውጪ ተመራማሪዎች ለቅርስ ጥናትና ጥበቃ ሠራተኞችም በሯን መዝጋት ጀምራለች።" ጥንታዊ ጽሑፎችን ለመቁጠር፣ ያሉበትን ሁኔታ ለማጥናትና ለቱሪስቶች ክፍት የሚሆኑበትን መንገድ ለማመቻቸት ሲሞከርም፤ ቤተ ክህነት እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኖች አስተዳዳሪዎችም ፈቃደኛ እንደማይሆኑ ያስረዳሉ። በእርግጥ ቅርሶች ይሰረቃሉ የሚለው ስጋት መሠረት አልባ አይደለም። ባለፉት ዓመታት በርካታ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች ተዘርፈው ከኢትዮጵያ ወጥተዋል። በተለይም ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ብዙ የብራና መጻሕፍት በተለያየ መንገድ በውጪ አገር ሰዎች መወሰዳቸው ይታወቃል። የቅርስና ታሪክ ባለሙያው እስራኤል፤ ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ የተወሰዱ ብርቅዬና በሌላ አገር የማይገኙ ቅርሶችን እንደምሳሌ ይጠቅሳሉ። "እንደምሳሌ መጽሐፈ ሔኖክ፣ መጽሐፈ ኩፋሌ፣ ገድለ አዳም ወ ሔዋን ይጠቀሳሉ። በሐረርና በደቡብ ወሎ የነበሩ የእስልምና መዛግብትም ተዘርፈዋል። አሁንም በቱሪስቶች፣ በዲፕሎማሲ ሠራተኞችና በሌሎችም ሰዎች የብራና መጻሕፍት እየተሰረቁ እየወጡ ነው።" • በታሪካዊው ቤተ መንግሥት ውስጥ ምን አለ? • ለኢትዮጵያዊያን የንባብ ወዳጆች ምርጡ መጽሐፍ የትኛው ነው? ሆኖም ግን መፍትሔው ስርቆትን መከላከል እንጂ ዲጂታይዜሽንን መግታት አለመሆኑን ባለሙያዎች ይስማሙበታል። የቅርስና ታሪክ ባለሙያው እንደሚሉት፤ በዋነኛነት በሰሜን ኢትዮጵያ ብዙ መጻሕፍት ዲጂታይዝ ቢደረጉም አጥጋቢ ነው ማለት አይቻልም። በተለይም ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአገሪቱ የተስተዋለው አለመጋጋት የፈጠረው ስጋት ሥራው ላይ እንቅፋት መፍጠሩን ያክላሉ። "ከዘመኑ ሥልጣኔ አንጻር ዲጂታይዜሽን አማራጭ የሌለው ዘዴ ነው። የብራና ጽሑፎችን ገልብጦ ማስቀመጥ ጊዜ ይወስዳል፤ በብራና የሚጽፉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥርም እየተመናመነ ነው" ሲሉ ያስረዳሉ። በአክሱም አባ ጴንጤሌዎን ገዳም የሚገኝ ጥንታዊ የጽሑፍ ቅርስ በኢትዮጵያ፤ ዲጂታይዜሽን በ1963 ዓ. ም ገደማ መጀመሩን ሰነዶች ያሳያሉ። በወቅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ የነበሩት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ቲዎፍሎስ፤ ሜኖሶታ ከሚገኝ የቅዱስ ዩሐንስ ዩኒቨርስቲ፣ የሂል ገዳም የብራና ቤተ መጻሕፍት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት በፎቶ ተቀርጸው እንዲቀመጡ ማድረጋቸውን ባለሙያው እስራኤል ይናገራሉ። ይህ እንቅስቃሴ በ1980ዎቹ በአገሪቱ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ በጊዜያዊነት ተቋርጦ ነበር። ባለሙያው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በዲጂታይዜሽን ከሚጠቅሷቸው የውጪ ተቋሞች መካከል፤ የኢትዮጵያ ብራና ማይክሮፊልም ቤተ መጻሕፍት (ኢትዮጵያን ማኑስክሪፕት ማይክሮፊልም ላይብረሪ ወይም ኢኤምኤምኤል) ይገኝበታል። በተቋሙ ወደ 9238 የብራና መጻሕፍት በማይክሮፊልም መቀረጻቸውን ይናገራሉ። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በኢትዮጵያ ጥናትና ተቋም (ኢንስቲትዮት ኦፍ ኢትዮጵያን ስተዲስ ወይም አይኢኤስ) ከተሠራው የፕ/ር ታደሰ ታምራት እና ሥርግው ሀብለሥላሴን እንቅስቃሴ፤ ውጪ አገር መቀመጫቸውን ካደረጉ መካከል ፕ/ር ጌታቸው ኃይሌን ይጠቀሳሉ። የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የብራና መጻሕፍትን ዲጂታይዝ ያደርጋል። የሙዝየም ባለሙያ እና በአሁን ወቅት በአረብኛና ግዕዝ ጽሑፎች ላይ ጥናት እያደረጉ ያሉት ፕሮፌሰር አህመድ ዘካሪያ እንደሚሉት፤ በአገር ውስጥም ይሁን በውጪ አገር ዲጂታይዝ የሚደረጉ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶች ተደራጅተው ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡበት ወጥ አሠራር ያስፈልጋል። "ለሥራው ያለው ተነሳሽነት ጥሩ ቢሆንም ማቀናጀቱ ላይ ክፍተት አለ። አጠቃቀሙ ሕግና ሥርዓት ይፈልጋል" ይላሉ። ኢትዮጵያ ከድንጋይ ጽሑፎችና ከዋሻ ሥዕሎች አንስቶ በብራና ላይ የሰፈሩ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶች ባለቤት እንደመሆኗ፤ በተለያየ ዘመን የነበሩ የሥነ ጽሑፍ ሀብቶችን ዲጂታይዝ አድርጎ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ፕሮፌሰር አህመድ፤ በግዕዝም በአረብኛም በየቦታው የሚገኙ ጽሑፎችን በመሰብሰብ ረገድ የፊሎሎጂ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች እያደረጉ የሚገኙትን ጥረት ያደንቃሉ። • የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ • በኦሮምኛና በትግርኛ አፋቸውን የፈቱ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ባለውለታዎች ሀምቡርግ ዩኒቨርስቲ፤ በአፍሪካ ቀንድ የእስልምና ጽሑፍን የማሰባሰብ ንቅናቄውንም ይጠቅሳሉ። ጥንታዊ ጽሑፎች በተጠቀሱት የአገር ውስጥና የውጪ አካሎች ዲጂታይዝ መደረጋቸው ቢበረታታም፤ ወደ አንድ ማዕከል መምጣት እንዳለባቸው ያስረግጣሉ። ጥቅም ላይ የሚውሉበትን መንገድ የሚመራ ሥርዓት ከተዘጋጀ፤ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተደራሽ እንደሚሆኑም ያክላሉ። "ተመራማሪዎች እንዴት እንደሚጠቀሙበት ደንብ መውጣት አለበት፤ አቀራረቡም ሕጋዊ አካሄድ ያስፈልገዋል።" ጥንታዊ ታሪክን፣ ማኅበራዊ ኑሮን፣ ምጣኔ ሀብትን፣ ፖለቲካን፣ ሀይማኖትን ወዘተ. . . የሚያሳዩትን መዛግብት በመተንተን የዛሬው ትውልድ ጥቅም ላይ እንዲያውለው የሚያደርግ የተማረ የሰው ኃይል እንደሚያስፈልግም ፕ/ር አህመድ አያይዘው ያነሳሉ። "ከሌሎች የአፍሪካ አገራት አንጻር ብዙ የሥነ ጽሑፍ ሀብት አለን። ሚስጥሮቻችን ብዙ ናቸው። የቀደመውን ዘመን እውቀት ማብላላት፣ ወደ ዛሬው ተጨባጭ ሁኔታ መለወጥም ያስፈልጋል። እኒህ የትላንት እውቀቶች ለአገርም፣ ለዓለምም ይበጃሉ" ይላሉ። ጥንታዊ ጽሑፎችን ዲጂታይዝ የማድረግ እንቅስቃሴ በአንድ አካል መመራት እንዳለበት የሚያስረዱት ደግሞ በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ (ወመዘክር) የመረጃ ሀብቶች አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሙሉእመቤት ጌታቸው ናቸው። "በአገር ውስጥም በውጪም እንቅስቃሴ አለ። ሁሉም በየራሱ ዘርፍ መሮጡ ግን ውጤታማ አያደርግም። ሁሉም በየራሱ መንገድ ሲሄድ ክፍተት ይፈጠራል። ሀብቶቹ ሊጠፉም ይችላሉ። ስለዚህም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መሥራት አለባቸው።" ወመዘክር በአዋጅ የተሰጠውን ሥልጣን ተጠቅሞ ጥንታዊ የሥነ ጽሑፍ ቅርሶችን ዲጂታይዝ ያደርጋል፤ የመዛግብቱን ቅጂ አከማችቶም በቤተ መጻሕፍቱ ለተጠቃሚዎች ያቀርባል። መዛግብቱ በድረ ገጽ ተለቀው ማንኛውም ሰው ባለበት ሆኖ መጠቀም እንዲችል ፖሊሲ ቢረቀቅም ገና አልጸደቀም። ዳይሬክተሯ እንደሚሉት፤ ሰዎች ያለውን ክምችት እንዲያውቁ እንዲሁም በሚፈልጓቸው ወቅትም እንዲጠቀሙ የሕግ ማዕቀፍ ያስፈልጋል። "ሙሉ መረጃው በድረ ገጽ የሚለቀቅ፣ የማይለቀቅም ሊኖር ይችላል። ሰው የትኛውን መረጃ፣ እንዴት ይጠቀምበት? በነጻ ይሁን ወይስ በክፍያ? የሚለውም በፖሊሲ የሚወሰን ይሆናል" ሲሉ ያስረዳሉ። ወመዘክር የትኛው የሥነ ጽሑፍ ቅርስ የት ይገኛል፤ የሚለውን በዳሰሳ ጥናት ይለያል። በጥቆማ የሚያገኛቸው መዛግብትም አሉ። ቅርሶቹ እንዴት ተጠብቀው መያዝ እንዳለባቸው ለባለቤቶቹ ሥልጠና ከመስጠት ባሻገር ዲጂታል ቅጂም ይወስዳል። የዲጂታይዜሽን ጅምሩ ቢኖርም ሂደቱ አመርቂ አለመሆኑን ሙሉእመቤት ያስረዳሉ። የባለሙያ እጥረትና የቴክኖሎጂ ውስንነትም በሚፈልጉት መጠን እንዳይሄዱ እንቅፋት ሆነዋል። መዛግብቱ የት እንዳሉ ለማወቅና ለመሰነድ የሚደረገው ጥረት የተጓተተ መሆኑንም ዳይሬክተሯ ያክላሉ። "ወመዘክር እየሞከረ ነው እንጂ እየሠራ ነው ለማለት ያስቸግራል። እየሠራን ነው ለማለት የሚፈለገውን ያህል እየሠራን አይደለም፤ የምንሰበስባቸው መዛግብት ቢኖሩም በቂ አይደሉም።" • የታሪክ መማሪያ መጻሕፍት ለምን ይከለሳሉ? • ፍቅርና ጋብቻ በቀይ ሽብር ዘመን የሥነ ጽሑፍ ቅርሶችን እንዲሰበስቡ በአዋጅ ቢፈቀድላቸውም የመዛግብቱ ባለቤቶች ቅርሱ ዲጂታይዝ እንዲደረግ ፈቃደኛ የማይሆኑበት አጋጣሚ አለ። "ለምሳሌ በቤተ ክህነት ማንም ሰው ዲጂታይዝ እንዳያደርግ መመሪያ ወጥቷል። ከመዛግብቱ ባለቤቶች ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ እየሞከርን ነው። የእስልምና የሥነ ጽሑፍ ቅርሶችና ሌሎችም መዛግብትን ከባሌቤቶቹ ጋር በመነጋገር መሰብሰቡን ግን ቀጥለናል።" ጥንታዊ የኢትዮጵያ መዛግብት ዲጂታይዝ የሚደረጉት አገር ውስጥ ብቻ አይደለም። ከኢትዮጵያ ውጪ ከሚገኙ ተቋሞች የእንግሊዙ ብሪትሽ ላይብረሪ ተጠቃሽ ነው። በቤተ መጻሕፍቱ የእስያና አፍሪካ ስብስብ ክፍል ውስጥ በ 'ኢትዮፒክ ኮሌክሽንስ ኢንጌጅመንት ሰፖርት' የሚሠራው እዮብ ድሪሎ እንደሚናገረው፤ በመላው ዓለም አደጋ ያንዣበበባቸው መዛግብት የሚሰነዱበት 'ኢንዴንጀርድ አርካይቭስ ፕሮግራም' የተሰኘ ክፍል አለ። ይህም ቸል የተባሉ፣ የመጥፋት አደጋ የተጋረጠባቸው ጥንታዊ የጽሑፍ ቅርሶች የሚሰነዱበት ክፍል ሲሆን፤ በየዓመቱ ጥንታዊ መዛግብትን ለይተው ዲጂታይዝ ለሚያደርጉ ተመራማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ ያደርጋል። በዓለም በ90 አገሮች፣ ከ100 በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች፣ ከ400 በላይ ፕሮጀክቶች የነበሯቸው ሲሆን፤ ከ 1000 በላይ የኢትዮጵያ ጥንታዊ መዛግብት ዲጂታይዝ ተደርገዋል። ከነዚህ መካከል ከገዳማት የተገኙ መዛግብት ይጠቀሳሉ። በቤተ መጻሕፍቱ የሚገኙ ጥንታዊ መዛግብት ለሕዝብ እይታ ከመቅረባቸው ባሻገር፤ የ25 መዛግብት ዲጂታል ቅጂም በድረ ገጽ ይገኛል። ባለፈው ዓመት የዘመናት ውጤት የሆኑ ጽሑፎች ዓውደ ርዕይ ተካሂዶም ነበር። "ዘመናትን ያስቆጠሩ የእውቀትና የጥበብ ሥራዎችን አሳይተናል። 'አፍሪካን ስክራይብስ፡ ማኑስክሪፕት ካልቸር ኦፍ ኢትዮጵያ' በሚል የተዘጋጀው ዓውደ ርዕይ ዋነኛ አላማው ላልታወቁ ኢትዮጵያዊያን ጸሐፍትና ጥበበኞች ቦታ መስጠት ነበር" ሲል እዮብ ይገልጻል። በቤተ መጻሕፍቱ ከሚገኙ ስብስቦች መካከል የመቅደላ መዛግብን የመሰሉትን በመጥቀስም "የኢትዮጵያዊያን ጸሐፍት የእውቀትና ጥበባዊ ተሰጥኦ መገለጫ ናቸው" ሲል ያስረዳል። ቤተ መጻሕፍቱ በዚህ ዓመት፤ ወደ 100 የሚደርሱ ጥንታዊ መዛግብትን ለወመዘክር መስጠቱን በመጥቀስ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ተቋሞች ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆናቸውንም ያክላል።
news-47786938
https://www.bbc.com/amharic/news-47786938
የፈረሰው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ ቤት ጠባቂ ምን ይላል?
መጋቢት 17/2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ በቅርስነት ተመዝግቦ የነበረው የደጃዝማች ዐምዴ አበራ መኖሪያ ቤት ከቤቶች ኮርፖሬሽን ታዘን ነው በሚሉ ሰዎች መፍረሱን የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙሐን ዘግበዋል። ድርጊቱ በቤቶች ኮርፖሬሽን፣ በቅርስ ጥበቃ፣ በክፍለ ከተማ እንዲሁም በባህል፣ ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ መካከል ውዝግብ የፈጠረ ነው።
• በአዲስ አበባ ከተማ ሊታዩ የሚገባቸው 5 ታሪካዊ ቤቶች • ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር መረጃዎች እንደሚያሳዩት የደጃዝማች ዐምዴ አበራ መኖሪያ ቤት በ1967 ዓ.ም በደርግ ከተወረሰ በኋላ በኪራይ ቤቶች አስተዳደር ስር ሆኖ ግለሰቦች በኪራይ ኖረውበታል። ከ1977 ዓ.ም ጀምሮ ሕይወታቸው እስካለፈበት 2002 ዓ.ም ድረስ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የኖሩበት ጁሴፔ የተባሉ ጣሊያናዊ ናቸው። ኃይለእየሱስ በክሩ በአጋጣሚ ትውውቅ ከጣሊያናዊው ጋር አንደ አንድ የቤተሰብ አካል ሆኖ ይኖር ነበር። ትውውቁ የጀመረው ጣሊያናዊው ከባለቤቱ ጋር በፍች ተለያይተው ስለነበር በዚሁ ቤት ውስጥ በወር 300 ብር ለኪራይ ቤቶች እየከፈሉ ሁለት ልጆቻቸውን በሞግዚት ያሳድጉ ነበር። የእርሳቸው ልጅ ኤርኔስቶ ኮዜንቲኖ ከኃይለእየሱስ ጋር የአንድ ሠፈር ልጅ በመሆኑ አብረው ኳስ ይጫወታሉ። እርሳቸውም ቢሆን በአካባቢው የእግር ጉዞ ማድረግን ያዘወትሩ ነበር። • የአፄ ቴዎድሮስ ቁንዳላ ሊመለስ ነው በዚህ መካከል ጣሊያናዊው ቤቱን በሚጠብቁላቸው ግለሰቦች እንደተማረሩ የልባቸውን ያጫውቱታል። ለጨዋታ ብቻም ሳይሆን ጭንቀታቸውን እንዲጋራ አስበው ነበርና ከእርሳቸው ጋር እየኖረ ቤቱን እንዲጠብቅ ይጠይቁታል። ኃይለእየሱስ ጥያቄያቸው አይኑን ሳያሽ ተቀበለ። በአባትና ልጅ ግንኙነት ሥራውን ጀመረ -ኃይለየሱስ። በዚህ መካከል "እንደ ልጃቸው አሳድገውኛል" የሚላቸው ጣሊያናዊ በልብ ሕመም ምክንያት በድንገት በሞት ተለዩ። "የጁሴፔ ባለቤት ወደ አገር ውስጥ መጥታ ንብረቶቹን ወሰደች፤ ቤቱን እንድጠብቅና እንድንከባከብ የኪራይ ቤቶች አስተዳደር ቁልፍ ሰጠኝ" የሚለው ኃይለእየሱስ በዚህ መልኩ ቤቱን እየጠበቀ ለ6 ዓመታት እዚያው ግቢ ውስጥ አትክልቶቹን እየተንከባከበና ቤቱን እየጠበቀ ኖረ። ይሁን እንጅ ከአራት ወራት በፊት ቤቱን ለቆ እንዲወጣ መጠየቁን ያስታውሳል። በብዙ ሙግት ከቆየ በኋላ ቤቱን በለቀቀ ማግስት መጋቢት 17/2011ዓ. ም ቤቱን ፈርሶ እንዳገኘው ይናገራል። "ከውስጤ አንድ ነገር እንዳጣሁ ነው የተሰማኝ፤ በማልቀስ ነው የገለፅኩት... ለማየት እንኳን የሚሳሳለት ቤት በዚህ መልኩ መፍረሱ ከልቤ አሳዝኖኛል" ሲል ይገልፃል። ቤቱ ታድሶ ተጠብቆ ይኖራል የሚል እንጂ ይፈርሳል የሚል ቅንጣት ያህል ስጋት እንዳልነበረውም ይናገራል። የደጃዝማች ዐምዴ አበራ መኖሪያ ቤት የቀደመውን ዘመናዊ የቤት አሰራርን የሚገልጥ ጥበብ ያለው ነው የሚለው ኃይለየሱስ ወለሉ በጣውላ፤ የጭስ ማውጫው በእብነ በረድ የተሰራ ሲሆን በቤቱ ውስጥ የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችም ነበሩ። "የጣሪያው ዲዛይን በጣም የተለየ ነው፤ በዘመናዊ ጣውላ የተሰራ ነው፤ አሰራሩ በቃ ለየት ያለ ነው" ይላል። • ያልታበሰው የላሊበላ እንባ በግቢው ውስጥ የዋናውን ቤት ያህል አሰራራቸው የተለየ ባይሆኑም 6 ክፍል ቤቶች የነበሩ ሲሆን፤ ከዚህ ቀደም እንዲፈርሱ እንደተደረገ ያስታውሳል። ከዚህ በተጨማሪም ዓይነተ ብዙ የሆኑ እንደ የሀበሻ ፅድ፣ ወይራና ሌሎች እድሜ ጠገብ ዛፎች ይገኙበታል። "በመኪና ተገጭቶ ፈርሶ ነው እንጂ 'ፋውንቴንም' ነበረው" ይላል። እርሱ እንደሚለው መኝታ ቤት፣ የእንግዳ ማረፊያ፣ ሳሎንና በረንዳው እንዳሉ ፈርሰዋል፤ የሚታየው ፊት ለፊት ገፅታም ጉዳት ደርሶበታል። ደጃዝማች ዐምዴ በደርግ የተገደሉ ሲሆን አባታቸው አበራ ካሣ ደግሞ በጣሊያን በግፍ እንደተገደሉ ታሪክ ያስረዳል፤ ራሳቸውን ለሀገራቸው አሳልፈው ሰጥተዋል። ታዲያ በተወረሰው የእርሳቸው ቤት ጣሊያናዊ መኖራቸው ግጥምጥሞሹ ያስገርማል። እንደው ምን ይሰማቸው ነበር ያልነው ኃይለየሱስ ቤቱ በጣሊያን እጅ እንደተሰራ ከመንገር በዘለለ የነገሩት እንደሌለ ገልፆልናል። ከአገር ውጭ የሚገኙት የጣሊያናዊው ልጆች ለቤቱ ልዩ ፍቅር እንደነበራቸውና አንድ ቀን ተመልሰው ሊኖሩበት እንደሚፈልጉ ያጫውቱት እንደነበርም ነግሮናል። ይሄው ታሪካዊ ቤት ለሙዚቃ ክሊፖችና ፊልሞች የቀረፃ ቦታ ያገለግል ነበር። የአዲስ አበባ ባህል ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ በበኩላቸው ቤቱ ላይ የተፈጸመውን ነገር አውግዘዋል። "አዲስ አበባን ትዝታና ታሪክ ያሳጣታል፣ የአዲስ አበባ አከታተም እንዴት እንደተጀመረ፣ የከተሜነቱን ሁኔታ የሚያሳይ ሲሆን ሥነ ህንፃን ማጥናት ለሚፈልጉ ትልቅ ጠቀሜታ የነበረው ነው፤ ደጃዝማች ዐምዴ ለሀገራቸው ሲሉ ህይወታቸው ያለፈ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ማስታወሻም ነበር" ሲሉ በሆነው ሁሉ ማዘናቸውን ገልፀዋል። መኖሪያ ቤቱ በ1930 ዓ.ም እንደተሰራና ከቀደምቶቹ የአዲስ አበባ መኖሪያ ቤቶች አንዱ እንደሆነ ይናገራሉ - ኃላፊው። ከዚህ ቀደም እንደ ሰፈር የሚቆጠሩ በርካታ ቦታዎች ታሪካቸውን ማጣታቸውንም አውስተዋል። የደጃች ውቤ ሰፈርን፣ አራት ኪሎንና መርካቶን በምሳሌነት ይጠቅሳሉ። ኃላፊው አክለውም የደጅ አዝማች ዐምዴ አበራን ቤት በተመለከተ በህግ መጠየቃቸውን እንደሚቀጥሉ ገልፀው፤ ጥገና እስከሚደረግለት ፍርስራሹ ባለበት ሁኔታ እየተጠበቀ እንደሆነ ነግረውናል። የጉዛራን ቤተ መንግሥት ጥገና እያስታወሱ ቤቱ በቀላሉ መልሶ መጠገን እንደሚቻል ከባለሙያዎች አስተያየት ማግኘታቸውን ጠቅሰው ሥራውን ለማከናወን ጥናት እየተደረገ እንደሆነ ለቢቢሲ ገልፀዋል። በአዲስ አበባ ከተማ 440 ቅርሶች በተለያየ ይዞታ በቅርስነት ተመዝግበው ይገኛሉ።
news-44720966
https://www.bbc.com/amharic/news-44720966
"ከሞቱት አንለይም" የሶማሌ ክልል እስረኞች
በእስር ቤቱ የሚወልዱ እናቶች በሙሉ የህክምና አገልግሎት አያገኙም የምትለው የ31 ዓመቷ የሶማሌ ክልል የቀድሞ ታራሚ አያን "ሴት እስረኞች እርስ በርስ መረዳዳት ያለን ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ባውቅም የመውለጃዬ ጊዜ ሲደርስ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡኝ ጠየቅኩኝ። የክልሉ ልዩ ፖሊሶች ግን የሰጡኝ ምላሽ ግን ልጁ አድጎም ስለማይረባ ሽንት ቤት ጣይው የሚል" እንደሆነ ትናገራለች።
የኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር ደጋፊ ስለሚሆን መሞት እንዳለበት የነገሯት ታራሚም ተስፋ ባለመቁረጥ ሆስፒታል ውሰዱኝ ስትላቸው ምላሻቸው ሳቅ እንደነበር ትናገራለች። "ተጨማሪ ውሀም ሊሰጡኝም አልቻሉም" ትላለች። እዚያው አስር ቤት በአስቸጋሪ ሁኔታ የተገላገለችው አያን የልጁንም እትብት ለመቁረጥ ስለት ያለው ብረት ከአካባቢያቸው መፈለግ ነበረባቸው። ይህ የአያን ታሪክ የተወሰደው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆነው ሂውማን ራይት ዋች "ዊ አር ላይክ ዘ ዴድ" (ከሞቱት አንለይም) በሚል ርዕስ ዛሬ ካወጣው ሪፖርት ሲሆን በሶማሌ ክልል ኦጋዴን እስር ቤት የሚደርሰውን የዘፈቀደ እስራት፣ መደብደብ፣ መደፈርና የሰው ልጅ ማሰብ ከሚችለው በላይ እንግልትን ያጋለጠ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስቸኳይ ምርመራ እንዲጀምሩ የሚጠይቀው ሪፖርቱ የክልሉን የፀጥታ ኃይሎች እንዲቆጣጠሩና ባለሥልጣናቱም ተጠያቂነት ሊኖራቸው የሚያስችል ሥርዓት እንዲዘረጋና እርምጃ እንዲወስዱም አፅንኦት ይሰጣል። በዚህ 88 ገፅ ባለው ሪፖርት እስረኞች የሚደርስባቸውን ስቃይ፣ እንግልት፣ መደፈር በተጨማሪ የህክምና እጦት፣ ረሃብ እንዲሁም ቤተሰብም ሆነ ጠበቃዎቻቸው እንዳያዩዋቸው እንደተደረጉም እስረኞቹ ለድርጅቱ እንደገለፁ ሪፖርቱ ያስረዳል። በሪፖርቱ መሰረት ይህንን ሲፈፅሙ የነበሩት የእስር ቤቱ የሥራ ኃላፊዎችና የፀጥታ ኃይሎች፤ የሶማሌ ክልል ልዩ ፖሊስ ናቸው። እነዚህ ቡድኖች በሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ መሀመድ ኦማር ስር የሚገኙ ሲሆን ብዙዎቹም ከኦጋዴን ነፃ አውጭ ግንባር ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ስቃይ እንደደረሰባቸው ተናግረዋል። ግንባሩ በኢትዮጵያ መንግሥት አሸባሪ ተብለው ከተፈረጁ ቡድኖች መካከል አንዱ መሆኑ የሚታወስ ነው። መንግሥት አድርጎ በማያውቀው ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ በእስረኞች ላይ ስለሚደርሰው እንግልትና ስቃይ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ማስረዳታቸው የሚታወስ ነው። በሶማሌ ክልል እየደረሰ ስላለው እንግልትም ሆነ ተጠያቂነት ስለሚረጋገጥበትም ሆነ ስለተጠቂዎቹ ፍትህ ዝርዝር ጉዳይ ግን አልተናገሩም። ይህ ሪፖርት ሂውማን ራይትስ ዋች በሶማሌ ክልል የሚገኙ 100 የፀጥታ ኃይሎችን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናትንና በባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ ስቃይና እንግልት የደረሰባቸውን 70 ግለሰቦችን መጠይቅ አድርጎ ያጠናቀረው ነው። "ለሦስት ዓመታት በጨለማ ቤት ተዘግቶብኝ ነው የኖርኩት" የሚለው የቀድሞ እስረኛ "በየቀኑ ማታ ማታ እደበደባለሁ። የማረሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ያላደረሱብኝ ነገር የለም የዘር ፍሬዬን በኤሌክትሪክ ማቃጠልና በኤሌክትሪክ ሽቦ መጠፈር፣ በጭንቅላቴም ላይ በርበሬ ጨምረው በፌስታል ያፍኑኛል። እንዳልጮህም በጨርቅ አፌን ይጠቀጥቁት ነበር" ብሏል። ራቁታቸውን በእስረኞች መካከል እንዲረማመዱ ማድረግ፣ እስረኞን ማደባደብና የሚያሸማቅቁ ተግባራትን እንዲያከናውኑ እንደሚያደርጓቸውም ታራሚዎቹ ተናግረዋል። "በአንድ ወቅት በሁሉም እስረኞች መካከል ራቁቴን በጭቃ ላይ እንድንከባለል አዘዙኝና በዱላ ይደበድቡኝ ጀመር" የምትለው የ40 ዓመቷ ሆዳን ስትሆን ያለምንም ክስ አምስት ዓመታትን በእስር አሳልፋለች። "በሌላ ጊዜም እንዲሁ አንድ በእድሜ ሸምገል ያሉ ሰውዬን ከሴት ልጃቸው ጋር ራቁታቸውን እንዲቆሙ አድርገዋቸዋል። በጣም የሚያሳፍር ነገር ነው" ትላለች። እስረኞቹ እንደሚሉት የእስር ቤቶቹ ኃላፊዎች፣ የልዩ ፖሊስ ከፍተኛ ኃላፊዎች እንግልቱን፣ መደፈሩን፣ ምግብ ክልከላውን ከማዘዝ በተጨማሪ ተሳታፊም ነበሩ ይላሉ። በተጨናነቁት በእነዚህ እስር ቤቶች ውስጥ በሚፈጠር ረሃብ፣ በሽታና ስቃይ ምክንያት ብዙዎችም ለሞት እንደተዳረጉ ሪፖርቱ ጨምሮ ያትታል።
news-55526507
https://www.bbc.com/amharic/news-55526507
አሜሪካ፡ ለትራምፕ የጎን ውጋት ሆነው የቆዩት ናንሲ ፔሎሲ ማን ናቸው?
ካፒቶል ሂል የአሜሪካ 4 ኪሎ ማለት ነው። ቦታው የወንዶች የፖለቲካ አውድማ ሆኖ ነው የቆየው።
አሜሪካ "ሴቶች ወደ ማጀት" ማለት ካቆመች መቶ ዓመት ቢሆናት ነው። በዚህ ዘመን የወንዶች ብቻ ተደርጎ የሚታሰበውን የፖለቲካ መድረክ እንደ ፔሎሲ ገብቶ ለማተራስ የበቃ ሴት ፖለቲከኛ የለም። አሁን ፔሎሲ 80 ዓመታቸው ነው። በአፈ ጉባኤነት ለ4ኛ ዘመናቸው ተመርጠው ዜና ሆነዋል። ለማንም የማይመለሱ ብርቱ ሴት ናቸው። የካፒቶል ሂል ፖለቲከኞች ፔሎሲን ሲመለከቱ የሚናወጡት የሴትዮዋን ጥንካሬ አሳምረው ስለሚያውቁ ነው። ሕግን ጠፍጥፎ የሚጋግረውና አብስሎ የሚያወጣው የታችኛው ምክር ቤት የ435 እንደራሴዎች የሙግት ቤት ነው። ይህን የሙግት ምክር ቤት የሚመሩት ደግሞ እኚህ ብርቱ ሴት ናቸው። የሕግ መምሪያው ምክር ቤት የአፈ ጉባኤ የሥልጣን ዘመን 2 ዓመት ነው። ፔሎሲ እንደ አውሮፓዊኑ በ2007 ተመርጠው 2 የሥልጣን ዘመን አገልግለዋል። ከዚያ ወዲያ በ2019 ተመልሰው መጥተው አሁን ለ4ኛ ዙር ተመርጠዋል፤ በትናንትናው ዕለት። ፔሎሲ የዋዛሴት አይደሉም። 50 ዓመታት በአሜሪካ ፖለቲካ የጽኑ ብርቱ ሴት ናቸው። 50 ዓመት ከዲሞክራቲክ ፓርቲ ጋር ተጣምረው ኖረዋል። ካምላ ሐሪስ መጥተው በአሜሪካ ፖለቲካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ከመክፈታቸው፣ የፖለቲካ ሥልጣን ከመቆናጠጣቸው በፊት በአሜሪካ ቁጥር አንድ ኃያሏ ሴት ፖለቲከኛና ተጽዕኖ ፈጣሪ ማን ነበሩ ቢባል መልሱ ናንሲ ፔሎሲ እንጂ ሌላ አይሆንም። አሁን የዲሞክራቶች ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት መግባትን ተከትሎ ናንሲ ፔሎሲ ወሳኝ ኃላፊነት ይጠብቃቸዋል። ለዲሞክራቶቹ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆ እና ምክትላቸው ሐሪስ የሚስማሙ አጀንዳዎችን ወደ ፊት ማምጣት። ማቀበል፣ ማስወሰን፣ ወዘተ ይኖርባቸዋል። የአሜሪካ የታችኛው ምክር ቤት አሁንም ድረስ የዲሞክራት እንደራሴዎች ብልጫ ያለበት ቢሆንም ቁጥሩ ከቀድሞው ተመናምኖ ድንጋጤ ፈጥሯል። ዲሞክራቶች ታችኛውም ሆነ ላይኛው ምክር ቤት አብላጫነት ከእጃቸው ተንሸራቶ ሊወጣ ጫፍ ላይ ነው ያለው። ናንሲ ፔሎሲም ቢሆን ለ4ኛ ጊዜ በአፈ ጉባኤነት ሲመረጡ የተወሰኑ የእኔ የሚሏቸው ዲሞክራቶች ድምጽ ነስተዋቸው ለጥቂት ነው ያሸነፉት፤ እንጂማ ጉድ ሆነው ነበር። በጠባብ ልዩነት ማሸነፋቸው የናንሲ ፔሎሲ መጪዎቹ 2 ዓመታት ፈተና እንዴት ያለ እንደሚሆኑ አመላካች ነው ተብሏል። ከቤት እመቤትነት እስከ ብርቱ ፖለቲከኛነት ፔሎሲ የተገኙት ፖለቲካ የዕለት ተዕለት ቀለቡ ከሆነ ቤተሰብ ነው። ገና የ12 ዓመት አዳጊ እያሉ ፔሎሲ የዲሞክቲክ ፓርቲ ስብሰባ ላይ ተገኝተዋል። ልጅ እያሉ በሪፐብሊካን ባንዲራ ያጌጠ አሻንጉሊት አልቀበልም እንዳሉ በአፈ ታሪክ ይነገርላቸዋል። ጥብቅ ካቶሊክ እንደሆኑ የሚነግርላቸው ፔሎሲ በ20 ዓመታቸው ከጆን ኤፍ ኬኔዲ ጋር ተዋውቀዋል። ብዙ ሰዎች እሳቸውን ከድሀውና ከጭቁኑ አሜሪካዊ የራቁ፣ ግራ ዘመምነት በጭራሽ የማይታይባቸው "የሳንፍራንሲስኮ ለዘብተኛ" እያሉ ይጠሯቸዋል። እውነታው ግን ያ አይደለም። ፔሎሲ 6 ወንዶች ከሚገኙበት ትልቅ ቤተሰብ ውስጥ የመጨረሻ ሴት ልጅ ሆነው ነው ያደጉት። በምሥራቃዊ አሜሪካ ሜሪላንድ፣ ባልቲሞር ነው የተወለዱት። አባቷ ደንበኛ ዲሞክራት ነበሩ። አባቷ ቶማስ ዴ አሌሳንድሮ የባልቲሞር ከተማን ለ12 ዓመታት በከንቲባነት መርተዋል። አባቷ ብቻ ሳይሆን ወንድሟ ቶማስ ዴ አሌሳንድሮም ባልቲሞርን በከንቲባነት መርተዋል። ፖለቲካ ወደ ፒሎሲ የተሸጋገረው በእውቀት ብቻ ሳይሆን በቤተሰብም ነው የሚባለው ለዚህ ነው። ፔሎሲ ከዚያ በኋላ ዋሺንግተን ጆርጅ ታውን ኮሌጅ ገብተው ተማሩ። የአሁን ባላቸውን ፖል ፔሎሲን ያገኙትም እዚያው ኮሌጅ ነበር። መጀመርያ ወደ ማንሐተን ከዚያም ወደ ሳንፍራንሲስኮ ሄደው መኖር ጀመሩ። ያን ጊዜ የቤት እመቤት ነበሩ። አምስት ልጆችን በተከታታይ አፍርተዋል። አራቱ ሴቶች ናቸው። በአንድ አንድ ዓመት ልዩነት ነው ልጆቹን የወለዷቸው። ፔሎሲ በ1976 ነበር ለመጀመርያ ጊዜ ፖለቲካ ውስጥ የገቡት። የካሊፎርኒያው ገዥ ጄሪ ብራውን የምረጡኝ ቅስቀሳ ላይ ነበሩ። እርሳቸውን በማገዝ ፖለቲካን 'ሀ' ብለው ጀመሩ። ከዚያ በኋላ በሜሪላንድ የዲሞክራቲክ ፓርቲ ውስጥ ሊቀመንበር ከዚያም ደግሞ ኮንግረስ ተመራጭ ሆኑ። ይህም በ1988 ነበር የሆነው። በ2011 በታችኛው ምክር ቤት የመንግሥት ተጠሪ ለመሆን ተወዳደሩ። ይህ ሥልጣን በሕግ መምሪያው ምክር ቤት ውስጥ ሁለተኛው ትልቁ ሥልጣን ነበር። በቀጣይ ዓመት ደግሞ በሕግ መምሪያ ምክር ቤት ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ተጠሪ ሆነው ተመረጡ። ይህም ማለት በሕግ መምሪያ ምክር ቤት ውስጥ አነስተኛ መቀመጫ ያለውን ፓርቲ የመምራት ሥልጣን ማለት ነው። ፔሎሲ በ2003 ትንሹ ቡሽ ኢራቅን ለመውረር ሲነሱ አምርረው ወረራውን በመቃወማቸው በይበልጥ ይታወሳሉ። የእርሳቸው የያኔው አቋም በኋላ ላይ ወረራው ባስከተለው ጉዳት ተረጋግጧል። ይህም የማይናወጥ አቋማቸው በ2006 ዲሞክራቶች ወደ ሥልጣን እንዲመጡና የሕግ መምሪያ ምክር ቤቱን ከ12 ዓመታት በኋላ በበላይነት እንዲይዙት ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ከዚያ በኋላ በፓርቲያቸው የሕግ መምሪያው ምክር ቤት ተመራጭ ሆነው ረዥሙን የአፈ ጉባኤነት ሥልጣን ያዙ። በአሜሪካ ታሪክም የመጀመርየዋ ሴት አፈ ጉባኤ በመሆን አዲስ ታሪክ ሠሩ። እሳቸው ሥልጣን በያዙ ከ4 ዓመት በኋላ ዲሞክራቶች የሕግ መምሪያውን ምክር ቤት ቁጥጥር ከእጃቸው ወጣ። ፔሎሲ እጅ አልሰጥ ብለው ብዙ ትግል አደረጉ። ከዚህ ወዲያ ጥረታቸው ፍሬ አፍርቶ በ2018 ዲሞክራቶች በምክር ቤቱ ተመልሰው መጡ። የሕግ መምሪያው ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሥራ ምንድን ነው? የሕግ መምሪያ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ መሆን ማለት በአሜሪካ የሥልጣን እርከን ከምክትል ፕሬዝዳንቱ ቀጥሎ ያለ ትልቅ ኃላፊነት ነው። በካፒቶል ግቢ በተንጣለለው የምክር ቤቱ ሕንጻ የፔሎሲ ቢሮ ስፋት የሥልጣናቸውን ግዝፈት የሚያመላክት ነው ማለት ይቻላል። የራሱ የሆነ ግዙፍ ባልኮኒ ያለውና በረንዳውም ወደ ዋሺንግተን ሐውልት የሚያሳይ ነው። በሕግ ማውጣት ሂደት ውስጥ ዋናው ይህ የታችኛው ምክር ቤት ነው። አፈ ጉባኤዋ እና ምክትላቸው እንዲሁም ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ተማክረው የትኛው ረቂቅ ሕግ ድምጽ ይሰጥበት በሚለው ላይ ይወስናሉ። የመወያያ አጀንዳ የሚቀርጹት እርሳቸው ናቸው። ክርክሮች የሚመሩበትን ሕግ የሚወስኑትም አፈ ጉባኤዋ ናቸው። ምክር ቤቱ ዱላ ቀረሽ ክርክር ሲያደርግ እንደራሴዎችን አደብ የሚያሲዙ እርሳቸው ናቸው። አፈ ጉባኤዋ በሕግ መምሪያው ምክር ቤት ውስጥ የፓርቲያቸውን የበላይነት እስካስጠበቁ ድረስ የመረጧቸው ረቂቆች ሕግ የማድረግ ጋሬጣ ላይጋረጥባቸው ይችላል። አነዚህ ምክር ቤት የሚወስናቸው ውሳኔዎች በአሜሪካ ሕዝብ ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ የመፍጠር አቅም አላቸው። ለምሳሌ ፔሎሲ አፈ ጉባኤ ሳሉ ከ2009 እስከ 2011 ድረስ ብቻ ምክር ቤቱ 840 ቢሊዮን ዶላር የምጣኔ ማነቀቂያ ገንዘብ እንዲረጭ ውሳኔ አሳልፏል። ፔሎሲ ተመጣጣኝ የጤና መድኅን (Affordable Care Act) ተግባራዊ እንዲሆን ታላቅ ተጋድሎ ያደረጉ የኦባማ ቀኝ እጅ የነበሩ ብርቱ ሴት ናቸው። ለትራምፕ ደግሞ የጎን ውጋት። የፔሎሲ የስላቅ ጭብጨባ ፔሎሲ በ2018 ወደ ምክር ቤቱ የአፈ ጉባኤነት መዶሻቸውን ይዘው ሲመለሱ ነገሮች ተቀያይረው ነበር የጠበቋቸው። ፕሬዝዳንት ትራምፕና የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ተጠሪ ሚች ማኮኔል ለፔሎሲ ደንቃራ ሆኑባቸው። በሕግ መምሪያ ምክር ቤት በእርሳቸው አርቃቂነት አብላጫ ድምጽ ተሰጥቶባቸው ወደ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ሲላኩ ውድቅ እየተደረጉ ተቸገሩ። ከሕግ መወሰኛ ሲያልፍ ደግሞ ትራምፕ ጠልፈው ይጥሉት ጀመር። ከዚህ ወዲያ ትራምፕና ፔሎሲ ተቃቃሩ። ይህ መቃቃራቸውም አንዳንድ ጊዜ ግላጭ ከመውጣቱ የተነሳ ለአሜሪካ ሚዲያ መዝናኛ ሆነ። ለምሳሌ #PelosiClap (የፔሎሲ የሹፈት ጭብጨባ) የሚለው የኢንተርኔት የስላቅ ኢሞጂ የተፈጠረው በዚህን ጊዜ ነበር። ፔሎሲ የስላቅ ጭብጨባውን ያደረጉት ዶናልድ ትራምፕ በሁለቱ ምክር ቤቶች የጋራ ስብሰባ ወቅት ተንኳሽ ንግግር ባደረጉበት ቅጽበት ነበር። ፔሎሲ በዚህን ጊዜ ገና ሥልጣኑን ከያዙ አንድ ወራቸው ነበር። ዛሬም ድረስ ይህ የናንሲ ፔሎሲ የስላቅ ጭብጨባ የኢንተርኔት ተወዳጅ የደቂቀ ምሥል ገላጭ (ኢሞጂ) መግባቢያ ሆኖ ቀጥሏል። ያን ቀን ምሽት ደግሞ ሌላ አስደናቂ ድርጊት ፈጸሙ። ፔሎሲ ለትራምፕ እጃቸውን ሲዘረጉ ትራምፕ ሳይጨብጧቸው ቀሩ። ፔሎሲ ደነገጡ። አፈሩም። ትራምፕ የሚያደርጉት ንግግር ግልባጭ ለሁሉም እንደራሴዎች ታድሎ ነበር። በጽሑፍ ለምክር ቤት አባላት የታደለውን የትራምፕን ንግግር ናንሲ ፔሎሲ ካሜራ ፊት እንደ ቆሻሻ ወረቀት ቡጭቅጭቅ አድርገው ቀዳደው ሲጥሉት በቀጥታ በቴሌቪዥን ታየ። ይህ ትልቅ መነጋገርያ ሆኖ ቆየ። ትራምፕና ናንሲ ፔሎሲ ዓይንና ናጫ ሆነው ይኸው ትራምፕ ከነጩ ቤተ መንግሥት ሲወጡ፣ ፔሎሲ ወደ ካፒቶል ሂል ሰተት ብለው በድጋሚ እየገቡ ነው። ፔሎሲ ከትራምፕ ጋር በግንብ አጥር የበጀት ጉዳይ ከፍ ዝቅ ተደራርገው ተሰዳድበዋል። ይህም በብዙ ሰዎች የተጋራ የፖለቲካ ቪዲዮ ሆኖ ነበር። ፔሎሲ በአሜሪካ ታሪክ ሦስተኛው ተከሳሽ ፕሬዝዳንት በነበሩት ትራምፕ ላይ ክሱን ለመምራት አቅማምተው ነበር። በኋላ ላይ ግን ትራምፕ ከዩክሬን ጋር የገቡበትን ቅሌት ሲሰሙ ክሱን ለመምራት ፍቃደኛ ሆኑ። ትራምፕ በሥልጣናቸው ባልገዋል። ይህ ደግሞ ቸል ሊባል አይገባም ብለው መቀነታቸውን አጥብቀው ተነሱ። ትራምፕ በዚህን ጊዜ የዩክሬን ባለሥልጣናት በጆ ባይደንና በልጁ ላይ አንዳች ጥፋት እንዲያፈላልጉና እንዲከሱ፣ አለበለዚያ ግን ለጦር መሣሪያ የሚሰጥ እርዳታ እንደማይለቀቅላቸው እያስፈራሩ ነበር። ትራምፕ ላይ የተነሳው ክስ ገፍቶ ሄዶ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ደርሶ የነበረ ቢሆንም በትራምፕ ወዳጆች የተሞላው የላይኛው ምክር ቤት ክሱን ውደቅ አድርጎታል። ፔሎሲ ለትራምፕ የጎን ውጋት ሆነውባቸው ነው ዘመናቸውን ሁሉ ያሳለፉት። የሜክሲኮን ድንበር በግንብ አጥር እጋርዳለሁ ገንዘብ ስጡኝ ያሉት ትራምፕ፣ ገንዘብ ይፈቀድ አይፈቀድ በሚለው ዙርያ ፔሎሲ ለትራምፕ አስጨናቂ ሆነውባቸው እንደነበር አይዘነጋም። ይህን ተከትሎ ነበር ትራምፕና ፒሎሲ በሚዲያ ፊት መተነኮኳኮስ የጀመሩት። መጪዎቹ የፒሎሲ ዘመናት ያስፈራሉ የባይደንን ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት መጠጋትን ተከትሎና ከዚያ ቀደም በነበሩ የሕዝብ ስሜቶች ተመርኩዘው ፔሎሲ የሚመሩት የሕግ መምሪያ ምክር ቤት የበላይነቱን አጠናክሮ ይቀጥላል የሚል መተማመን ነበር። የሆነው ግን በተቃራኒው ነው። ዲሞክራቶች ከአንድ ደርዘን በላይ እንደራሴ ወንበሮችን ለሪፐብሊካን ለመስጠት ተገደዋል። ከዚህ በኋላ የፔሎሲ የምክር ቤት ወንበር ቀላል አይሆንም። ለግራ ዘመሙ ፓርቲያቸው የሚስማማ አጀንዳዎችን መቅረጽ፣ ከዚያም ረቂቅ አድርጎ ማወያየት፣ አወያይቶም ማጸደቅ እንደ ከዚህ በፊቱ ቀላል ተግባር አይሆንም። የቢቢሲው የአሜሪካ ፖለቲካ ተንታኝ አንተኒ ዘርቸር እንደሚለው የፔሎሲ የ50 ዓመታት ፖለቲካዊ ተጋድሎ ከባዱ ፈተና ከዚህ በኋላ ያለው ነው የሚሆነው። ፈተናውን እንዴት ይወጡት ይሆን? "አንዱ መንገድ ለዘብተኛ የሪፐብሊካን እንደራሴዎችን ወደ እርሳቸው ሐሳብ እያግባቡ ማምጣት ነው። ሁለተኛው ተስፋቸው በሕግ መወሰኛ ምክር (ሴኔት) ቤት ዲሞክራቶች አብላጫ ወንበር ማግኘት ከቻሉ ነው" ይላል አንተኒ። ነገ ለጆርጂያ ግዛት 2 የምክር ቤት አባላት ይወዳደራሉ። ከተሸነፉ የላይኛው ምክር ቤት በሪፐብሊካን የበላይነት ይያዛል። ይህ ደግሞ ለጆ ባይደንና ለሐሪስ አዲስ ራስ ምታት ነው። ነገ የጆርጂያ ውክልና በዲሞክራቶች አሸናፊነት ከሆነ ግን ምክር ቤቱ እኩል የሪፐብሊካንና የዲሞክራቶች ተወካዮች ይኖሩታል። ይህ ከሆነ ደግሞ የሕግ መወሰኛውን ምክር ቤት ሊቀመንበርነት ከማይክ ፔንስ የሚረከቡት ተመራጭዋ ምክትል ፕሬዝዳንት ካምላ ሐሪስ የልዩነት ድምጽ የሚሰጡ ወሳኝ ሰው ይሆናሉ ማለት ነው። ይህ የመሆን ዕድሉ ግን ጠባብ ነው። አምስት ልጆችና ዘጠኝ የልጅ ልጆችን ያፈሩት ፔሎሲ ምናልባትም በፖለቲካ የመጨረሻው ዘመናቸው ፍሬያማ ላይሆን ይችላል።
43151436
https://www.bbc.com/amharic/43151436
እስራኤል ካገር አልወጣም ያሉ ኤርትራውያን ስደተኞችን አሰረች
ወደ ሩዋንዳ አንሄድም ያሉ 16 ኤርትራውያን ስደተኞች ለእስር ተዳረጉ።
የእስራኤል መንግሥት ስደተኞችን ካገር የማስወጣትንም እቅድ ተከትሎም ለእስር የበቁ የመጀመሪያዎቹ ስደተኞች ናቸው። የእስራኤል መንግሥት በሀገሪቷ ተቀማጭነታቸውን ያደረጉ የኤርትራና የሱዳን ስደተኞችን ወደ ሩዋንዳና ኡጋንዳ በመላክ ሙሉ በሙሉ ካገር የማስወጣት እቅድ አላት። እስካሁን ባለው 600 የሚሆኑ ስደተኞች ከሀገር እንዲወጡ ትዕዛዝ የተሰጣቸው ሲሆን ወደ 35 ሺ የሚሆኑ ስደተኞችም ከሀገር የመባረር አደጋ ላይ እንደሆኑ አንድ የእስራኤል የስደተኞች መብት ድርጅት አስታውቋል። ስደተኞቹ ሆሎት ከሚባለው የማቆያ ማዕከል የተወሰዱ ሲሆን በማእከሉም የረሀብ አድማ መነሳቱ ታውቋል። የእስራኤል መንግሥት በጥር ወር አካባቢ ስደተኞቹ ካገር እንዲወጡ ቀነገደብ ያስቀመጠ ሲሆን ካለበለዚያ ግን እስር እንደሚጠብቃቸው ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር። ስደተኞቹ እሰራኤልን በሚቀጥሉት ሦስት ወራት ውስጥ ለቀው ለመውጣት ከተስማሙ 3500 ዶላር ይሰጣቸዋል ተብሏል። በዚህ ወር መጀመሪያም የእስራኤል መንግሥት የቀድሞ የሰራዊት አባላት ኤርትራውያን ስደተኖችን ጥገኝነት እንደሚሰጥ ቃል ገብቶ ነበር።
news-44964862
https://www.bbc.com/amharic/news-44964862
"የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዮጵያን ሊያበራ ነው የሞተው"
ትናንት ባልታወቀ ሁኔታ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ የተገኘው የኢንጂነር ስመኘው ቤተሰቦች መሪር ሃዘን ውስጥ ናቸው። የቢቢሲ ዘጋቢ ትናንት የአስክሬን ምርመራ በሚካሄድበት የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ተገኝታ በጥልቅ ሐዘን ላይ የሚገኙ የቅርብ ቤተሰቦቻቸውን አነጋግራለች።
የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ቤተሰብ አባላት ሐዘናቸውና ቅሬታቸውን በለቅሶ መሐል ሆነውም አጋርተዋታል። የቅርብ ዘመድ ቢኾኑም ስለ ግድያው በሚዲያ መስማታቸውን የገለጹት እኒህ የቤተሰብ አባላት አስክሬኑ መጉላላቱና የሚገባውን ክብር አለማግኘቱ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ተናግረዋል። ሌሎች የቤተሰቡ አባላት ደግሞ አንድም የመንግሥት አካል በአካባቢው አለመኖሩ የፈጠረባቸውን ቅሬታንም አልሸሸጉም። • ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሕይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ • ስለኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን? "ቢሮ ተቀምጦ አይደለም መግለጫ መስጠት" ሲሉ የመንግሥት አካላት ላይ ያነጣጠረ የሚመስል ቅሬታን አሰምተዋል። "እሱ ቤቱን ትቶ በረሀ ላይ ነው የኖረው። ለስመኝ ይሄ አይገባውም። ምን አረጋቸው፣ የበደላቸውን ለምን አይነግሩንም? ምን አደረጋቸው? ይሄ ለሱ አይገባውም" ስትል በመሪር ሐዘን ሆና ስሟን ያልገለፀች አንድ የቤተሰብ አባል ተናግራለች። "ማነው ጀግና፣ ማነው ጎበዝ? ማነው ለአገር አሳቢ። የሚመስል ወይስ የሆነ?" ሲል በምሬት ሐዘኑን የገለጸው ሌላ ወጣት "የእሱ አባት ኩራዝ የላቸውም፤ እሱ ግን ኢትዯጵያን ሊያበራ ነው የሞተው" ሲል ሳግ እየተናነቀው ምሬቱን ገልጿል። ከሐዘንተኞቹ መሐል በቅርብ ቀናት ሟችን በስልክም ይሁን በአካል አግኝተዋቸው ያውቁ እንደሆነ ተጠይቀው ኢንጂነሩ ሥራ ላይ ስለሚያተኩሩ እምብዛም ከቤተሰብ ጋር እንደማይገናኙ የሚያመላክት አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። "እሱ አገሬን ሥራዬን እያለ ሁሉም ሰው ረስቶታል። እሱ ሁሉ ነገሩ ሥራው ላይ ነው። ዘመድ አይልም..." ስትል ስሟን መግለጽ ያልፈለገች የቤተሰብ አባል። "ከሰው ጋር አልኖረም፤ በረሃ ነው የኖረው" ስትል ሟች ማኅበራዊ ሕይወት የሚባል ነገር እንኳ እንዳልነበራቸው ተናግራለች። ኢንጂነር ስመኘው በቀለ
news-48455870
https://www.bbc.com/amharic/news-48455870
ስለአልኮል ማስታወቂያ ክልከላ የሚዲያ ባለሙያዎች ምን ይላሉ?
የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አዲስ የምግብና የመድሃኒት አስተዳዳር አዋጅ የአልኮል መጠጦችን በራዲዮ፣ በቴሌቪዥንና በቢል ቦርድ ማስተዋወቅ የሚከለክለው ደንብ ከትናንት ግንቦት 21፣ 2011 ዓ. ም ጀምሮ ተግባራዊ ሆኗል።
(ከግራ ወደ ቀኝ) ጋዜጠኛ ታምራት ኃይሉ፣ ኤልሳ አሰፋ እና ጥበቡ በለጠ በዚህ መሠረት ማንኛውንም መገናኛ ብዙሃን የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ ሕጉ ከሚፈቅደው ሰዓት ውጭ ማስተላለፍ እንደማይችል ተነግሯል። በኢትዮጵያ በርካታ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች እንዲሁም የሕትመት ውጤቶች በቢራ ፋብሪካዎች ድጋፍ አድራጊነትና ከአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ በሚገኝ ገንዘብ ይደገፋሉ። አንዳንዶቹ እንደውም ዋና የገቢ ምንጭ የሚያገኙበትም መንገድም ነው። ታዲያ አዲሱ ሕግ ምን ዓይነት ተፅእኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል? • ለአንድ ወር ከአልኮል መታቀብ የሚኖረው አስደናቂ ውጤት • ብቻቸውን ወደ መዝናኛ ስፍራ የሚሄዱ ሴቶች ፈተና የቁም ነገር መፅሔት አዘጋጅና ባለቤት ታምራት ኃይሉ "ለመጭው ትውልድ በማሰብ ከሆነ በመልካም ጎኑ ሊወሰድ ይችላል፤ ነገር ግን እኛ አገር የማስታወቂያ ችግር በራዲዮና በቴሌቪዥን መተዋወቁ ሳይሆን አቀራረቡ ነው" ይላል። እሱ እንደሚለው፤ የአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ በሌሎች አገራትም የተለመደ ሲሆን አቀራረቡ ግን የተጠና ነው። ባለው ልምድ፤ የቢራ ማስታወቂያዎቹ የሚተላለፉበት መንገድና ህፃናትን ሊስብ በሚችል መልኩ መቅረባቸው እንጂ ማስታወቂያው ሰዉን ጠጪ አድርጓል? ጠጪስ አለ? የሚለው ጥናት የሚፈልግ ጉዳይ እንደሆነ ይናገራል። ታምራት እንደሚለው፤ ከፍተኛ ማስታወቂያ አስነጋሪዎች ቢራ ፋብሪካዎች በመሆናቸው ሕጉ የመዝናኛ ዘርፉንና ሚዲያውን ይጎዳል። አዋጁ ተግባራዊ ሳይሆን በፊት የቢራ ፋብሪካዎች ማስታወቂያ መስጠት ማቆማቸው ተፅእኖ አሳድሯል የሚለው ታምራት፤ ከመከልከል ይልቅ በአቀራረቡ ላይ መነጋጋር ይሻላል ይላል። ከዚህም ባሻገር የቢራ ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ገንዘብና በርካታ ሠራተኞች የያዙ በመሆናቸው፤ ባለማስተዋወቃቸው ገበያቸውን የሚያጡ ከሆነ የአገሪቱን ኢኮኖሚ ይጎዳል የሚል ስጋትም አለው። "በርካታ ፕሮግራሞች የሚደገፉት የቢራ ፋብሪካዎች በሚያሰሩት ማስታወቂያ ነው" የምትለው በብስራት ኤፍኤም የፋሽንና ውበት ፕሮግራም አዘጋጅና ጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ ጉዳዩን በሦስት መንገድ እንደምታየው ትገልፃለች። የመጀመሪያው በተለይ ከአልኮል መጠጥ ፋብሪካዎች በሚገኝ የድጋፍና የማስታወቂያ ገንዘብ የተቋቋሙና በዚያም ፕሮግራማቸውን የሚያስኬዱ ተቋማትን ገቢ ያሳጣል። በሌላ በኩል እንደአንድ ማኅበረሰብ ማስታዋቂያዎች ከሚሠሩበት መንገድና ከቢራ ፋብሪካዎቹ ስያሜ ታዳጊዎች ምን እየተማሩ ያድጋሉ? የሚለው ጥያቄ ያስነሳል ትላለች። • ወንዶች የማያወሯቸው አምስት አሳሳቢ ነገሮች • እውን ቡና መጠጣት እድሜ ይጨምራል? "ቢራ እንደመድሃኒትና እንደምግብ ነበር ሲተዋወቅ የነበረው" የምትለው ኤልሳ፤ ህፃናትን በማይጎዳ መልኩ ጥናት ተሠርቶ ማስታወቂያዎቹ እንዲተላለፉ ማድረግ ይቻል ነበር ስትል ትሞግታለች። የአሀዱ ኤፍኤም ራዲዮ ጣቢያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጥበቡ በለጠ የተለየ ሃሳብ አላቸው። "ባለፉት ዓመታት በማስታወቂያና በፕሮሞሽን ድጋፍ ጉልህ ቦታ የነበራቸው የቢራ ፋብሪካዎች ነበሩ፤ ራዲዮና ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ለመክፈት ከቢራ ፋብሪካዎች ጋር መነጋጋር የተጀመረበት ወቅትም መጥቷል" ይላሉ። በአብዛኛው ቢራዎች ሚዲያውን የመቆጣጠር ደረጃ ላይ ደርሰዋል የሚሉት አቶ ጥበቡ፤ ማስታወቂያዎቹንም ከኢትዮጵያዊነት፣ ከማንነት፣ ከታላቅነት ጋር በማያያዛቸው ሰዎች ጠጪ እንዲሆኑ የማድረግ ተፅዕኖ ሲያሳድሩ መቆየታቸውን ያምናሉ። ነገሩ ያሳስባቸው እንደነበርም አልሸሸጉም። በመሆኑም የቢራ ማስታወቂያዎቹ መከልከላቸው በአገሪቱ ላይ በጎ አሻራ ያሳርፋል ይላሉ። "ኃላፊነታቸውን አልተወጡም፤ ትውልድ ላይና አገር ላይ የሚሰሩ ጉዳዮችን የቢራ ፋብሪካዎች ሲደግፉ አይታዩም" በማለት ሚዲያው ሊወጣ የሚችለውን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ሚና እንደጎዱት ያብራራሉ። አቶ ጥበቡ እንደሚሉት፤ ከቢራ ፋብሪካዎች ውጭ ከሚዲያ ጋር መሥራት የሚፈልጉ ሌሎች ድርጅቶችም ቢኖሩም የቢራ ፋብሪካዎቹ ከፍተኛ ገንዘብ በመክፈል ሌሎቹ ገፍተው እንዳይመጡ የማድረግ ሚናም ነበራቸው። የሚዲያ ተቋማቱ ጥራት ያለውና ሊደመጥ የሚችል ፕሮግራም ማቅረብ ከቻሉ ድጋፍ የሚያደርግላቸው አያጡም የሚል እምነትም አላቸው። • የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች • ከእግር ኳስ ሜዳ ወደ ኮኛክ ጠመቃ ሕጉ ለሕትመት ሚዲያዎች ተስፋ ይሰጥ ይሆን? አዲሱ የምግብና የመድሃኒት አስተዳዳር ሕግ የአልኮል ማስታወቂያዎችን ማስተላለፍ የሚከለክለው በራዲዮ፣ በቴሌቪዥን እና በቢል ቦርድ ነው። በመሆኑም በህትመት ዋጋ ውድነትና አንባቢ ባለመኖሩ ለሚንገዳገዱት የህትመት ሚዲያዎች ተስፋ ይሰጥ ይሆን? የቁምነገር መፅሔት አዘጋጅና ባለቤት ታምራት በዚህ ረገድ ተስፋ አለው። መፅሔትና ጋዜጣ የሚያነቡት ኃላፊነት የሚሰማቸውና ትልልቅ ሰዎች እንደሆኑ የሚናገረው ታምራት፤ በየጊዜው እየጨመረ የመጣውን የህትመት ዋጋ መቋቋም የሚቻለው በማስታወቂያ ገቢዎች ነው ይላል። በዚህም ጥራቱን ማሻሻል፣ ሥርጭቱን ማሳደግ፣ የንባብ ባህልን መጨመር ይቻላል ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። • የኦነግ ጦር መሪ በትግላችን እንቀጥላለን አለ ይሁን እንጂ አሁንም በሕጉ ላይ ብዥታ በመኖሩ፤ የቢራ ፋብሪካዎችም ሆኑ የአልኮል ማስታወቂያ የሚሰጡ ድርጅቶች ክልከላው ለሁሉም መገናኛ ብዙሀን ነው በማለት እየተንቀሳቀሱ እንዳልሆነ ገልጿል። "በኢትዮጵያ የህትመት ሚዲያው ሥርጭት የተዳከመ ነው፤ ግፋ ቢል ከአምስት ወይም ስድስት ሺህ ቅጂ በላይ አይሸጥም" የሚሉት አቶ ጥበቡ፤ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎች በህትመት ሚዲያዎች ላይ ቢወጡ አቀራረባቸው የተገደበ ስለሚሆን፣ በተለይም ለህጻናት ፊት ለፊት ስለማይታዩ ተፅእኖ አይኖረውም ይላሉ። "ፋብሪካዎቹ ብራንዳቸው እንዳይረሳ ወደህትመት ሚዲያ ሊመጡ ይችላሉ" የምትለው ኤልሳ፤ አሁን በመነቃቃት ላይ ያለውን የህትመት ሚዲያው የበለጠ እንደሚያበረታው እምነት አላት። በሚዲያው ላይ ምን ተፅእኖ አሳረፈ? ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ሚዲያዎች ላይ ጥናት እንዳደረጉ የሚናገሩት አቶ ጥበቡ፤ ወሳኝ የሚባሉት ሰዓቶች ከድጋፍ አድራጊ አካላት ጋር ግንኙነት አላቸው ይላሉ። ከቢራ ፋብሪካዎች ጋር ተፈራርመው ገንዘብ ይዘው የሚመጡ ፕሮግራሞች ቅድሚያ እንደሚሰጣቸውም ያክላሉ። ዋና ዋና የሚባሉት ሰዓቶች 'መዝናኛ' ለሚባሉና በቢራ ፋብሪካዎች ለተደገፉ ፕሮግራሞች ይሰጣሉ። ይህም በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ፋይዳ የሌላቸው ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ሚዲያ ላይ እንዲደረጁ እንዳደረገ ያስረዳሉ። • የተሟላ የወጪ ማስረጃ ሳይቀርብ ከ1.4 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል የታምራት ሀሳብም ተመሳሳይ ነው። የስፖንሰርሺፕ (ድጋፍ) ሃሳብ ተግባራዊ የሚደረገው በተዛባ መልኩ ነው ይላል። "የውጭ አገር ሚዲያዎችና ዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድሮች ላይ የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያዎች ይተላለፋሉ፤ ነገር ግን እንደ እኛ መልክ ያጣ አይደለም" ሲል የማስታወቂያ አሠራር እውቀትና አቅም ችግር እንዳለ ይናገራል። "ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን ማየት የተቸገሩበት ጊዜ ላይ ደርሰን ነበር" ሲልም ያክላል። ኤልሳ በበኩሏ የአልኮል መጠጥ ፋብሪካዎቹ ምርቶቻቸውን ለማስተዋወቅ የራሳቸው ምርጫ ቢኖራቸውም፤ በአብዛኛው አስተማሪና ጠንከር ያሉ ፕሮግራሞችን ተመራጭ ሲያደርጉ አይታይም ስትል ልምዷን አጋርታናለች። "በቤተሰብ ላይ ያተኮረ ተወዳጅ ፕሮግራም ነበረኝ፤ ነገር ግን ዓመቱን ሙሉ አንድም የቢራ ስፖንሰር አልነበረኝም፤ ምክንያቱም ፕሮግራሙ ስለሚያስተምር አያዝናናም የሚል ነው" ስትል በርካታ ቁም ነገር አዘል ፕሮግራሞች ያለድጋፍ ሲሠሩ እንደሚስተዋል አክላለች። የፋብሪካዎቹ የገበያ ዘርፍ ኃላፊዎች (ማርኬቲንግ) የየራሳቸው አድማጭ ሊኖራቸው ቢችልም፤ በተለያዩ መንገዶች ማኅበራዊ ግዴታዎችን መወጣት እንደሚገባቸው አስተያየቷን ሰጥታለች።
43695226
https://www.bbc.com/amharic/43695226
ባባኒ ሲሶኮ፦ 'ዓለም አቀፉ ምትሃተኛ'
ጊዜው በፈረንጆቹ ወርሃ ነሃሴ 1995 ዓ.ም.፤ ፎቱንጋ ባባኒ ሲሶኮ የተባለ ግለሰብ ወደ ዱባይ እስላማዊ ባንክ ጎራ ይልና "መኪና ልገዛ ነው ብድር ስጡኝ" ይላል።
የባንኩ ስራ አስኪያጅ ሞሃመድ አዩብም "ምን ገዶን ዕዳህን በጊዜው ክፈል እንጂ" ይለዋል። በዚህ የተደሰተው ሲሶኮ ስራ አስኪያጁን "ፈቃድህ ሆኖ እራት አብረን እንበላ ዘንድ እንዳው ቤቴ ብቅ ብትል" ሲል ግብዣ ያቀርባል። በዓለማችን ከታዩ አስደናቂ ማታለሎች አንዱ የሆነው ታሪክ የሚጀምረው እንዲህ ነው። የቢቢሲዋ ብሪዢት ሺፈር እንዲህ ታቀርበዋለች። እራት እየበሉ ሳለ ሲሶኮ ለስራ አስኪያጁ አንድ አስደናቂ ታሪክ ያካፍለዋል። "አንድ ኃይል አለኝ" ይለዋል. . .ይህን ኃይል ተጠቅሜም ገንዘብ እጥፍ ማድረግ እችላለሁ። እንደውም በሚቀጥለው ጊዜ የተወሰነ ገንዘብ ይዘህ መጥተህ ለምን አላሳይህም?" ሲል ሲሶኮ ጥያቄ ያቀርባል። ምትሃት በእስልምና የተወገዘ ሲሆን እንደ ትልቅ ኃጥያትም የሚቆጠር ነው። ቢሆንም በርካታ ሰዎች በምትሃት ያምናሉ። ሞሃመድ አዮብ ከአንድ ከከተማ ራቅ ብላ ከምትገኝ የማሊ ገጠራማ ሥፍራ ወደመጣው ሲሶኮ ገንዘቡን ይዞ ተከሰተ። ልክ በሩን ከመርገጡ አንድ ሰው ከውስጥ ወጥቶ "መንፈስ (ጅኒ) መታኝ" ይለዋል። "ወደ ውስጥ ስትገባ ጅኒውን እንዳታበሳጨው ጠንቀቅ በል፤ ያለዚያ ገንዘብህ እጥፍ አይሆንም" ሲል ይነግረዋል። አዩብም ወደውስጥ ከዘለቀ በኋላ ገንዘቡን አስቀምጦ እጥፍ እንዲሆንለት በጥሞና ይጠብቅ ጀመር። "ድንገት ከክፍሉ ውስጥ መብራት እና ጭስ እንዲሁም የመናስፍቱ ድምፅ መውጣት ጀመረ" ይላል አዩብ። ለጥቆም ገንዘቡ እጥፍ ሆነለት፤ አየብም ፊቱ ፈካ። በአውሮፓውያኑ 1995 እስከ 98 ባለው ጊዜ ብቻ አዩብ ለሲሰኮ ምትሃቱን ተጠቅሞ ገንዘቡን እጥፍ እንዲያደርግለት በማለት 83 ጊዜ በባንክ ደብተሩ አማካይነት ገንዘብ አስገብቶለታል፤ ገንዘቡ የባንኩ መሆኑ ሳይረሳ። 98 ላይ የዱባዩ ባንክ እየከሰረ መሆኑ መዘገብ ያዘ። ዜናውን ያነበቡ የባንኩ ደንበኞችም ገንዘባቸውን ለማውጣት በየቅርንጫፉ ተሰለፉ። ቢሆንም የዱባይ ባለሥልጣናት ዘገባው ሃሰት የተሞላ ነው እንጂ ባንኩ የገንዘብ እጥረት አልገጠመውም ሲሉ ተደመጡ። እውነታው ግን ይህ አልነበረም። ኋላ ላይ በጉዳዩ ጣልቃ የገባው የዱባይ መንግሥት ባንኩን በገንዘብ በመደጎም ራሱን ችሎ እንዲቆም አደረገው። ይህ ሁላ ሲሆን ታዲያ ሲሶኮ በጣም ሩቅ ሥፍራ ነበር፤ ምትሃቱን የበለጠ ድንቅ የሚያደርገው ደግሞ ገንዘቡን ለማግኘት ዱባይ መገኘት ግዴታ አለመሆኑ ነው። ጊዜው ጥቅምት 1995...ምትሃቱን በሞሃመድ አዩብ ላይ የተጠቀመው ሲሶኮ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ወደ ኒው ዮርክ በማቅናት ተመሳሳይ ድርጊት ፈፀመ። ሲቲባንክ የተባለ ባንክ በመዝለቅ አንድ የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኛ ተዋወቀ፤ ትንሽ ቆይቶም አገባት። ይህንን ተጠቅሞም ከሲቲባንክ ጋር ያለውን ግኑኝነት ማሳመር ቻለ። ሲሶኮ ከሲቲባንክ ወደ ዱባይ እስላማዊ ባንክ ደብተሩ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ እንዳስተላለፈም ይታመናል፤ ለዚህ የረዳችው ሚስቱን በረብጣ ዶላሮች እንደካሳትም ተነግሯል። ስለሲሶኮ ይህንን መረጃ የሚናገሩት የዱባዩ ባንክ በጉዳዩ ላይ ክስ በከፈተ ጊዜ ጠበቃ አድርገው የቀጠሩት አለን ፋይን ናቸው። ከጊዜ ወደ ጊዜ ምትሃቱን ተጠቅሞ ገንዘብ ማፍራቱን የቀጠለው ሲሶኮ ምኞቱ የነበረውን በምዕራብ አፍሪካ አየር መንገድ መክፈት ያመቸው ዘንድ ቦይንግ አውሮፕላን ገዛ። አየር መንገዱን በትውልድ መንደሩ ስም ዳቢያ ብሎ ሰየመው። ነገር ግን ወርሃ ሐምሌ 1996 ላይ ሲሶኮ አንድ ስህተት ሠራ። ሁለት ከቪየትናም ጦርነት የተረፉ ሄሊኮፕተሮች ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ለመግዛት ሞከረ። ሄሊኮፕተሮቹ ለጦርነት ጥቅም ላይ የዋሉ በመሆናቸው ምክንያት ለመብረር ልዩ ፍቃድ ያሻቸዋል። ይህን ያስተዋሉት የሲሶኮ ሰዎች ፖሊሶችን ለመደለል ሲሞክሩ ለእስር በቁ። ዓለም አቀፉ ኢንተርፖልም ሲሶኮ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ትዕዛዝ አወጣ። ሌላ የባንክ ደብተር ለመክፈት ወደ ጄኔቫ አቅንቶ የነበረው ሲሶኮ በቁጥጥር ሥር ዋለ፤ ለጥቆም ወደ አሜሪካ ተላከ። ምንም አንኳ የአሜሪካ መንግሥት ሲሶኮ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ቢፈልግም በ20 ሚሊዮን ዶላር ዋስ እንዲለቀቅ ሆነ። ሲሶኮ ለዚህ ላበቁት የህግ ሰዎች ውድ የሚባሉ መኪኖችን ሸለመ። አንድ መኪና ሻጭ ሲሶኮ ቢያንስ 53 መኪናዎችን ገዝቶኛል ሲል ይናገራል። ነዋሪነቱን ማያሚ ያደረገው ሲሶኮ በከተማዋ ታዋቂ ሆነ፤ በርካታ ሚስቶችንም አገባ፤ 23 አካባቢ አፓርትማዎችንም ተከራየ። ሲሶኮን የሚያውቁት ግርማ ሞገስ ያለው፣ አለባበሱ ያማረ እና መልከ-መልካም ሰው ነው ሲሉ ይገልፁታል። አልፎም ከገንዘቡ ወደ 413 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ለእርዳታ አዋሏል። ጠበቃዎቹ ከነበሩ በርካታ ግለሰቦች መካከል አንዱ የሆነው ስሚዝ የተባለ ሰው ሲናገር ሲሶኮ ዘወትር ሃሙስ በመኪናው እየዞረ ለቤት አልባ ሰዎች ገንዘብ ያድል ነበር። የጠበቃዎቹን ምክር አልሰማም ያለው ሲሶኮ ጥፋተኛ ነኝ ሲል አመነ። ለ43 ቀናት እሥር እንዲሁም ለ250 ሺህ ዶላር ቅጣትም ተዳረገ። ከተፈረደበት ፍርድ ግማሹን የፈፀመው ሲሶኮ 1 ሚሊዮን ዶላር ለቤት አልባ ሰዎች በመስጠት የተቀረውን ፍርድ በቤት ውስጥ እስር እንዲጨርስ ሆነ። በዚህ ጊዜ ነው ታድያ የዱባዩ እስላማዊ ባንክ ኦዲትሮች የሆነ ነገር ትክክል እንዳልሆነ መጠርጠር የጀመሩት። አዩብም ፀባዩ መለዋወጥ ታየበት፣ ሲሶኮም እንደ ድሮ በተፈለገ ጊዜ ስልክ አላነሳ ማለት ይጀምራል። በስተመጨረሻም አዩብ ለሥራ ባልደረባው ያጋጠመውን ይተነፍሳል። "ምን ያህል ብር ነው የጠፋው?" ሲል ለጠየቀው ጓደኛው በቃላት ምላሽ መስጠት የተሳነው አዩብ በብጣሽ ወረቀት ፅፎ ያቀብለዋል. . .242 ሚሊዮን ዶላር። በዚህ ጉዳይ ጥፋተና ሆኖ የተገኘው አዩብ የሶስት ዓመታት እሥር ይፈረድበታል፤ "በምትሃት አምነሃልና ሸይጣንህን እናስወጣልህ" ተብሎ በኃይማኖቱ መሠረት ሸይጣን ማስወጣት እንደተካሄደለትም ይነገራል። አዩብ በዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ ሲያልፍ ሲሶኮ ግን ዱባይ ሊገኝ ባለመቻሉ ምክንያት በሌለበት የሶስት ዓመታት ፍርድ ይወሰንበታል። ዓለም አቀፉ ፖሊስ 'ኢንተርፖል' ግን "አፈልገዋለሁ" ሲል ማስታወቂያ ይለጥፋል። ሲሶኮ ለ12 ዓመታት ያክል ማለትም በአውሮፓውያኑ ከ2012 እስከ 2014 ባለው ጊዜ በማሊ የሕዝብ እንደራሴ ሆኖ በመሾሙ ምክንያት ያለመከሰስ መብቱ ተጠብቆለት ቆየ። ላለፉት አራት ዓመታት ደግሞ ሃገሩ ማሊ ወንጀለኞች አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ከየትኛውም ሀገር ጋር ስምምነት ባለመፈረሟ ምክንያት ያለ ምንም ስጋት ሕይወቱን እያጣጠመ ኖረ። ከዚያ በኋላ ነው ሲሶኮን ፍለጋ ወደ ማሊ ርዕሰ መዲና ባማኮ ያቀናሁት ትላለች የቢቢሲዋ ብሪዢት። ከዚያም የሲሶኮ ሹፌር የሆነውን ሉካሊ ኢብራሂምን ታገኘዋለች። በትውልድ መንደሩ ዳቢያ ሊኖር እንደሚችልም መረጃው ለብሪዢት ይደርሳታል። ከሰዓታት ጉዞ በኋላ ብሪዢት ሲሶኮ መኖሪያ የተባለው ቤት ትደርሳለች፤ በወታደሮች የሚጠበቅ ሰፋ ያለ ግቢ። በስተመጨረሻም ሰውየውን በአካል ታገኘዋለች. . .የሰባ ዓመቱን 'ምትሃተኛ' ፎቱንጋ ባባኒ ሲሶኮን። ለቃለ-መጠይቅ ፈቃደኛ ሆኖ የተገኘው ሲሶኮ "ስሜ ፎቱንጋ ባባኒ ሲሶኮ ይባላል። የተወለድኩ ዕለት ማሪየቶ ወንድ ልጅ ወለደች በማለት ሰፈሩ ቀለጠ" በማለት ታሪኩን ለብሪዢት መተረክ ይጀምራል። "እንደው ከዱባዩ እስላማዊ ባንክ ጠፋ ስለተባለው 242 ሚሊዮን ዶላር የምታወቀው ነገር ይኖራል?" ለሲሶኮ የተሰነዘረ ጥያቄ ነው። "እመቤት...ይህ 242 ሚሊዮን ዶላር የማይመስል ታሪክ ነው። የባንኩ ሠራተኛ ቢያስረዳሽ ነው የሚሻለው እንጂ ያን ያክል ገንዘብ ሲጠፋ መቼም ዝም ብለው አይቀመጡም። በዚያ ላይ ይህን ያህል ገንዘብ ከባንክ ለመውሰድ በርካታ ቢሮዎች መሄድ አለብሽ።" "አዩብ ግን. . . ?" ብሪዢት የሰነዘረችው ጥያቄ። "አዩብ የባንኩ ሠራተኛ? አዎ እሱን ሰውዬ አንድ ጊዜ አግኝቸዋለሁ። መኪና ለመበደር የሄድኩ ጊዜ። ምርጥ የጃፓን መኪና ነበረች። ዕዳዬንም በጊዜው ከፍዬ ጨረስኩ" የሲሶኮ ምላሽ። ጋዜጠኛዋ በስተመጨረሻም ስለ 'ምትሃት' ጠየቀችው። "እመቤት አንድ ሰው እንዲህ ዓይነት ኃይል ካለው ለምን ይሠራል? ቁጭ ብሎ ባንክ እየዘረፈ መብላት እየቻለ። ቢፈልግ ከአፍሪካ፣ አሜሪካ፣ ፈረንሳይ ያሻውን ባንክ እየዘረፈ መኖር ይቻል አልነበር።" "እና አሁንስ ሃብታም ነህ?" "ኧረ በጭራሽ። እኔ ሃብታም አይደለሁም። እንደውም ደሃ ነኝ።" ምንም እንኳ ዓለም አቀፉ ፖሊስ 'ኢንተርፖል' አሁንም ሲሶኮን ፍለጋውን ቢቀጥልም፣ ምንም እንኳ በርካታ ገንዘብ አፍርቶ ቢያጠፋም ፎቱንጋ ባባኒ ሲሶኮ በሃገሩ ማሊ በጤና ኑሮውን እየገፋ ይገኛል።
news-49069302
https://www.bbc.com/amharic/news-49069302
ሳባ አንግላና፡ "ኢትዮጵያዊትም፣ ጣሊያናዊትም ሶማሊያዊትም ነኝ"
ሳባ አንግላና ከኢትዮጵያዊት እናቷና ከጣሊያናዊ አባቷ የተወለደችው ሞቃዲሾ ውስጥ ነው። የእናቷ ቤተሰቦች በኢትዮ-ሶማሊያ ጦርነት ወቅት ነበር በምርኮኛነት ወደ ሶማሊያ የተወሰዱት። ከዓመታት በኋላ እናቷ አንድ ጣሊያናዊ ሞቃዲሾ ውስጥ ተዋወቀች፤ ትውውቃቸው ወደ ፍቅር፣ ፍቅራቸው ወደ ትዳር አደገ፤ ከዚያም ሳባ ተወለደች።
ሳባ አንግላና ስልጣን ላይ በነበረው በሞሐመድ ዚያድ ባሬ መንግሥት አስተዳደር ወቅት የሳባ እናትና አባት ሞቃዲሾ ውስጥ ተደላድለው መኖርና ልጃቸውንም ማሳደግ የማይታሰብ ሲሆንባቸው ያላቸውን ሸክፈው ወደ አባቷ ሀገር ጣሊያን አመሩ። ሳባ የሦስት ሀገራት ነጸብራቅ በውስጧ በአንድ ላይ ይታይባታል። ስትጠየቅም ይህንኑ ታስረዳለች፤ በእናቷ ኢትዮጵያዊ፣ በአባቷ ጣሊያኒያዊ፣ እትብቷ የተቀበረው ደግሞ ሶማሊያ ውስጥ ቢሆንም ጥርሷን ነቅላ ያደገችው ግን ሮም ከተማ ውስጥ ነው። • "ኢትዮጵያዊነቴን ያገኘሁት ሙዚቃ ውስጥ ነው" አቨቫ ደሴ ሳባ ለጥበብ ጥሪ 'አቤት' ብላ ምላሽ የሰጠችም ናት፤ ትወና ነፍሷ ነው፤ ደራሲና ድምፃዊም ናት። "ሳባ ብለው የሰየሙኝ ንግሥቲቷን በማሰብ ነው ... ለእኔ ግን በስሜ ራሱ አንድ ከባድ ኃላፊነት እንደተጣለበኝ ነው የማስበው" ትላለች። ሳባ የኢትዮጵያ የሃገር ባህል ልብስ ተውባ መድረክ ላይ ስታንጎራጉር ሳባ "ብዙ ጊዜ ከአንድ ወይም ሁለት በላይ በባህል፣ በደምና በማንነት 'የተዳቀሉ' (ክልስ) ሰዎች ለየት ያለ እሳት በውስጣቸው እንደሚነድ አምናለሁ። ሆኖም ግን ነበልባሉ የሚተነፍስበትን ትክክለኛ መውጫ ማግኘት ያስፈልጋል" በማለት በውስጧ ስላለው ራሷን በሙዚቃ ለመግለፅ ስላላት ጽኑ ፍቅር ትናገራለች። ሙዚቃን የሕይወት ጥሪዬ ነው ብላ የተቀበለችውም በዚህ ምክንያት እንደሆነ ስታስረዳ "በውስጤ የነበረውን ነበልባል የማወጣበት የሆነ ነገር ያስፈልገኝ ነበር" በማለት ነው። ከልጅነቷ ጀምሮ እግሯ በረገጠበት ሁሉ ዜግነቷን ትጠየቅ ስለነበር፤ በሙሉ የራስ መተማመን መልስ ለመስጠት እንደትችል ማንነቷን ማወቅና መገንባት ነበረባት። • "ራሴን የምፈርጀው የሀቅ ታጋይ ነኝ ብዬ ነው" አሊ ቢራ "ሙዚቃ፤ ነፃነቴንና ተቃውሞዬን የምገልጽበት ቋንቋ ነው" የምትለው ሳባ ማንነቷን ራሷ እየገነባችው እንደመጣች ታስረዳለች። ሳባ ወደ ሙዚቃው ዓለም የተቀላቀለችው እድሜዋ ሠላሳን ከዘለቀ በኋላ ነው። ለምን? ስትባልም አባቷን ታነሳለች። "...በልጅነቴ ሁል ጊዜ አንጎራጉር ነበር። ነገር ግን ቤተሰቦቼ በተለይ አባቴ ሙዚቃው እንዳይስበኝ ይጥር ነበር" በማለት አባቷ ፊደል ቆጥራ፣ ተምራ፣ ተመራምራ የዕለት እንጀራዋን እንድታበስል ይመክሯት እንደነበር ትናገራለች። አባቷ ካረፉ በኋላ ግን ነገሮች ተቀየሩ፤ "አባቴ ቆንጆ ድምፅ እንዳለኝ ለሰው ሁሉ ይናገር እንደነበር ተነገረኝ። ውስጤ በጣም ደማ፤ ምክንያቱም ለእርሱ ባንጎራጉርለት ኖሮ ደስ ይለኝ ነበር። ምነው ለራሴ በነገረኝ ኖሮ እያልኩ ወደ ሙዚቃው ተሳብኩ" ትላለች። ኢትዮጵያዊት? ጣልያናዊት? ወይስ ሶማሊያዊት? ሶማሊያ ተወልዳ ያደገችው ሳባ ለዚህ ጥያቄ መልሷ "ሦስቱም" የሚል ነው። የልጅነትና የወጣትነት እድሜዋን በሮም ብታሳልፍም በእናቷ በኩል ያለውን የዘር ግንዷን ለማወቅ ወደ አዲስ አበባ መጥታ የአያቶቿን መቃበር ጎብኝታለች። "ሶማሊያዊያን ሶማሊያዊት ነሽ ይሉኛል፣ ኢትዮጵያውያንም ኢትዮጵያዊት ነሽ፤ ዓይኖችሽ ይናገራሉ ይሉኛል። ጣልያኖችም የራሳቸው ያደርጉኛል። እኔ ግን ሦስቱም ነኝ" ትላለች። • “እዚህ ደረጃ የደረስኩት በእርሷ ብርታት ነው” አርቲስት ደመረ ለገሰ "በውስጤ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኘኝን ነገር ለማግኘት በጣም እጓጓ ነበር። አማርኛ አለመቻሌ ትልቅ ቁስል ፈጥሮብኛል ... በተለይ ኢትዮጵያን ስጎበኝ 'ፈረንጅ' እያሉ የሚከተሉኝ ልጆች የኢትዮጵያዊነቴን ስሜት የተገፈፈኩ ያህል እንዲሰማኝ አድርጓል" የምትለው ሳባ የማንነቷን ፍለጋ ጉዞዋ በሙዚቃ በኩል እንደተያያዘችው ታስረዳለች። • ከድምፃዊት ቤቲ ጂ እና ቸሊና ጀርባ ሳባ አንግላና "አበበች" አበበች የሳባ ሙዚቃ አልበም መጠሪያ ነው። ነገር ግን ወ/ሮ አበበች ወደ ሳባ ሕይወት እንዲሁ የተከሰቱ አልፎ ሂያጅ መንገደኛ ሳይሆኑ አያቷ ናቸው። ከኢትዮጵያ ጋር በጥብቅ ገመድ ያስተሳሰሯት፤ የማነሽ? የከየት ነሽ? ጥያቄዎች መልሷ ናቸው። "አያቴ አበበች ነበር ስሟ" ትላለች ሳባ ስለእርሳቸው ማስረዳት ስትጀምር፤ "በእርሷም በኩል ነው የኢትዮጵያዊነቴ ግንድ የተገለጠልኝ" በማለትም የመጨረሻውን የሙዚቃ አልበሟን በእዚሁ ምክንያት በእርሳቸው ስም "አበበች" ብላ እንደሰየመችው ትናገራለች። ወ/ሮ አበበች ለአውሮፓያውያን ወግኖ በነበረ የሶማልያ ወታደር እንደ ምርኮኛ ወደ ሶማልያ ተወስደው እንደነበር ሳባ ትተቅሳለች። "ስለእርሷ በሙዚቃዬ ማውራቴ ደግሞ ስሬ ምን ያህል ኢትዮጵያዊ እንደሆነ የማመላክትበት ነው" ትላለች ሳባ። ሙዚቃዋን በኢትዮጵያ ፔንታቶኒክ ስኬል፣ በአምባሰልና በትዝታ ቅኝት የምትጫወትበትም ምክንያት ይኸው እንደሆነ ታስረዳለች። • አውታር - አዲስ የሙዚቃ መሸጫ አማራጭ በሙዚቃዋም በትዝታ ጎዳና በማንነትን ፍለጋ አቀበት እየተጓዘች፣ የሚያደምጧትንም ጭምር ጉዞዋን ተቀላቅለው አብረው እንዲነጉዱ ታደርጋለች። ሳባ አብዛኞቹ ሥራዎቿ እራስን ከመፈለግ ጋር የተያያዙ ናቸው። ማንነቷ በሙዚቃ ሥራዎቿ በግልጽ የሚንፀባረቀው ሳባ፣ በአራት የተለያዩ ቋንቋዎች ታንጎራጉራለች። ሶማልኛ፣ አማርኛ፣ ጣልያንኛና እንግሊዘኛ ሙዚቃዎቿን ያቀረበችባቸው ቋንቋዎች ናቸው። ይህን በማድረጓም ማንነቷን በደንብ እንደገለፀች ይሰማታል። አራቱንም ቋንቋዎች እንደ ተወላጆቹ እንደልብ አፏ ላይ ባታሾራቸውም መኮላተፏ ግን የመሳሳቷ ሳይሆን የውህድ ማንነቷ ውጤት መሆኑን ትናገራለች። "መኮላተፌም ሆነ መሳሳቴ ...የማንነቴ አካል ስለሆነ አላፍርበትም።" • 'ኢትዮጵያዊነት' ከጄሰን ድሩሎ ጀርባ ያለው ቡድን "የሁሉም ሰው ማንነት አንድ ነገር ብቻ ሊሆን አይችልም" የምትለው ሳባ በምዕራቡ ዓለም እየታዩ ያሉት ስደተኞችን ወደ ሀገራቱ እንዳይገቡ የመከላከል እርምጃን ታወግዛለች። ምክንያቱስ ስትባል "ውበታችን የሚጎላው እንደዚያ ስለሆነ ነው" በማለት "ምንም ልዩነቶች ቢኖሩ የሰው ልጅ አንድ ነው" በማለት ሃሳቧን ታጠናክራለች። መድረክ ላይ በምትሆንበት ጊዜ ፊት ለፊቷ ያለው ታዳሚዎች ኢትዮጵያዊም ሆኑ ጣልያናዊ አልያም ሶማሊያዊ መልዕክቷን ስለሚረዱ በጣም ዕድለኛ እንደሆነች ትገልፃለች። "ምንጊዜም ችግር የሚገጥመኝ አንዱን ባህል ብቻ እንዳንፀባርቅ ሲጠብቁ ነው... ለምን? አንድ ነገር ብቻ አይደለሁም" በማለት በሁሉም የሙዚቃ ሥራዋ ሦስቱንም ቋንቋና ባህልን እያደባለቀች የምትሰራበት ምክንያቷን ታስረዳለች። "ከእኔ በኋላ ለሚመጡት ሙዚቀኞች በር እንደከፈትኩ ያህል ይሰማኛል። ምክንያቱም መንፈሳዊነቴን፣ ባህሎቼንና ማንነቴን በአንድ ላይ በሙዚቃዬ ለመግለፅና ተቀባይነት ለማግኘት ብዙ ውጣ ውረዶችን አይቻለሁ። አሁን ግን የቅይጥነቱን መንፈስና ትርጉም ብዙዎች የተረዱት ይመስለኛል" የምትለው ሳባ የአቅሟን በመሥራት ለመጪው ትውልድ አሻራ ብቻ ሳይሆን መንገድ እንደምትጠርግም ተስፋ ታደርጋለች።
news-53977507
https://www.bbc.com/amharic/news-53977507
የቻይናና አውስትራሊያ ውጥረት፡ አውስትራሊያዊቷ ዜና አንባቢ ቻይና ውስጥ ታገተች
በቻይና እና አውስትራሊያ መካከል ያለው ውጥረት እያየለ መጥቷል።
የቻይና ባለሥልጣናት የአውስትራሊያ ዜግነት ያላትን አንዲት ዜና አንባቢ በቁጥጥር ሥር አውለዋል። የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዳለው ለቻይና መንግሥት ቴሌቪዥን ጣቢያ ሲጂቲኤን የምትሠራው ቼንግ ሌይ በቁጥጥር ሥር የዋለችው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማሪስ ፔይን እንዳሉት በቁጥጥር ሥር ከዋለችው አውስትራሊያዊት ጋዜጠኛ ጋር የቪድዮ ስልክ ልውውጥ ተደርጓል። የአውስትራሊያ መንግሥት ቻይና የሚገኙ ዜጎቹ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያሳሰበው ባለፈው ሐምሌ ነው። አውስትራሊያና ቻይና በተለይ ከቅርብ ወራት ወዲህ ግንኙነታቸው እየሻከረ መጥቷል። አውስትራሊያ የኮሮናቫይረስ መነሾ በይፋ ይጣራ ማለቷን ተከትሎ ነው ቻይና የተቆጣችው። ቻይና ለሁለተኛ ጊዜ ከአውስትራሊያ የሚመጡ ወይኖች ላይ ምርመራ ይካሄድ ብላ አዛለች። ባለፈው ሳምንት የአውስትራሊያ መንግሥት ክልሎች ከውጭ ሃገራት ጋር ያላቸውን ግንኙት ፌዴራል መንግሥቱ ማቋረጥ እንዲችል የሚያዝ ሕግ ለማውጣት እያቀደ መሆኑን ይፋ አድርጓል። ቼንግ በቁጥጥር ሥር የዋለችው 'የሃገር ድህንነትን አደጋ ላይ በመጣል' በሚል ክስ እንደሆነ የአውስትራሊያው ኤቢሲ ዘግቧል። ቻይና ውስጥ በዚህ ክስ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሰው እስከ ስድስት ወራት ድረስ ምርመር ሊደርግለትና ከእሥር ላይወጣ ይችላል። ነግር ግን ቻይና በጉዳዩ ላይ ገና ማብራሪያ አልሰጠችም። የአውስትራሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስለጋዜጠኛዋ በቁጥጥር ሥር መዋል መረጃ የተሰጠው ከሁለት ሳምንታት በፊት ነው። ነባሯ ዜና አንባቢ አውስትራሊያ የሚኖሩ ሁለት ልጀች አሏት። ኤቢሲ ኒውስ እንደዘገበው ቤተበሶቿና ወዳጅ ዘመዶቿ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ ስለ ቼንግ የሰሙት ምንም ነገር የለም። ቤተሰቦቿ ከአውስትራሊያ መንግሥት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ጋር በቅርበት እየተነጋገሩ መሆኑን አሳውቀዋል። ቼንግ ለሲጂቲኤን ለስምንት ዓመታት ያገለገለች ሲሆን 'ግሎባል ቢዝነስ' በተሰኘው የቴሌቪዥን ሥርጭት ላይ አቅራቢ ሆና ትሰራለች። ጋዜጠኛዋ በቻይና መንግሥት ቁጥጥር ሥር ከዋለች ወዲህ ከቴሌቪዥን ጣቢያው ድረ-ገፅ ላይ ስለሷና ሥራዎቿ የሚያትተው ገፅ መጥፋቱ ተነግሯል። ቻይና ባለፈው ዓመት ጥር ላይ የቻይናና አውስትራሊያ ዜግነት ያለው ያንግ ሄንገጁን የተባለ ፀሐፊ ብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ ይጥላል በማለት በቁጥጥር ሥር ማዋሏ አይዘነጋም።
news-49007336
https://www.bbc.com/amharic/news-49007336
ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል፡ 'ከሕግ ውጪ' የተዋሃዱት አምስቱ ክልሎች
ወታደራዊው መንግሥት ከስልጣን ከተወገደ በኋላ የኢትዮጵያ አስተዳደራዊ መዋቅር መሰረታዊ ለውጥ ተደርጎበት በዋናነት ቋንቋን መሰረት ባደረገ ሁኔታ የአስተዳደር ክልሎች ተመስርተዋል።
ከሰማኒያ በላይ የተለያየ ሐይማኖት፣ ቋንቋና ባሕል ያላቸው ሕዝቦችን መብትና ጥቅም ያስከብራል በሚል ዋና ዋና በሚባሉትና በርካታ የሕዝብ ቁጥር ባላቸው ብሔሮች ዙሪያ ውስጣዊ የአስተዳደር ሥርዓቱን ማዋቀር በወቅቱ የሃገሪቱን የመሪነት ሚና የተረከቡት ኃይሎች ዋነኛ ሥራ ነበር። በዚህም ለዘመናት ኤርትራን ጨምሮ በ14 ክፍላተ ሃገራት የተዋቀረው የአስተዳደር ሥርዓት ከ1983 ዓ.ም ወዲህ በአዲሱ ቋንቋን መሰረት ባደረገ የፌደራል አስተዳደራዊ አወቃቀር አንዲተካ ተደርጓል። • በሲዳማ ክልልነት ጉዳይ ህዝበ ውሳኔ እንዲካሄድ የምርጫ ቦርድ ወሰነ • የደቡብ ክልል፡ ውስብስቡ የዐብይ ፈተና ይህም የሆነው ሃገሪቱ የምትተዳደርበት ሕገ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በተቋቋመው ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት አማካይነት ነበር። የወቅቱ አከላለል 14 ክልሎች እንዲፈጠሩ ያደረገ ሲሆን አዲስ አበባም በክልል ደረጃ የተዋቀረች ከተማ ነበረች። በሽግግሩ ወቅት በአዋጅ ቁጥር 7/1984 መሰረት አዲስ የክልል አወቃቀር ሲታወጅ በሂደቱ ውስጥ ተሳታፊ እንደነበሩ የሚናገሩትና በወቅቱ የምክር ቤት አባል የነበሩት ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ከሁለት ዓመታት በኋላ አሁን በደቡብ ክልል ውስጥ የሚገኙ አምስት አካባቢዎች በሕገ ወጥ መንገድ ተዋህደው አንድ ክልል እንዲመሰርቱ መደረጉን ያስታውሳሉ። በሽግግሩ ጊዜ የተዋቀረው አዲሱ የአስተዳደር ሥርዓት በዋናነት በቁጥርና በአሰፋፈር ተለቅ ተለቅ የሚሉትን ማዕከል አድርጎ የተካለለ ቢሆንም የደቡብ ክልል ግን 56 የሚደርሱ ብሔር፣ ብሔረሰቦችን በመያዝ ከሌሎቹ ክልሎች በተለየ የተዋቀረ ነው። በወቅቱ አዲስ አበባም ራሷን የቻለች ክልል በመሆን የፌደራል መንግሥቱ አካል የነበረች ሲሆን በኋላ ላይ ይህ ተቀይሮ በቻርተር የምትተዳደር የከተማ አስተዳደር እንድትሆን ተደርጓል፤ ድሬዳዋም በተመሳሳይ የአስተዳደር ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች። • ለሲዳማ ክልልነት 'ይሁንታ ተሰጠ' በሚል በርካቶች ደስታቸውን እየገለጹ ነው በወቅቱ ክልሎቹ ሲዋቀሩ ቋንቋንና ማንነትን መሰረት አድርገው ሲሆን አሁን ከያዙት ስያሜ በተለየ በቁጥር ነበር የሚታወቁት። ቁጥሩ ከትግራይ ክልል አንድ ብሎ ይጀምርና ደቡብ ተብሎ በአንድ እንዲጠቃለል የሆነው ክልል ከሰባት እስከ 11 የሚደርሱትን ክልሎች በውስጡ እንዲይዝ ተደርጎ አምስት ክልሎችን ነበሩት ይላሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ። እንደእርሳቸው አባባል በአከላሉ ሂደት ወቅት አሁን የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ተብሎ ወደ አንድ የተጠቃለለው በአምስት ዋና ዋና ክልሎች ተዋቅሮ የተለያዩ ሕዝቦች የሚኖሩባቸው ክልሎች እንዲሆኑ ተደርገው ነበር የተደራጁት። በዚህም መሰረት በጊዜያዊው የሽግግሩ መንግሥቱ ዘመን እነዚህ አምስት ክልሎች እንደ ክልል ለሁለት ዓመት ራሳቸውን የቻሉ ክልሎች በመሆን ሲተዳደሩ ቆይተዋል። ብዙም ያልዘለቀው የእነዚህ ክልሎች እድሜ ማዕከላዊው የሽግግር መንግሥት ክልሎቹ የተዋቀሩበትን አዋጅ 7/1984ን በመጣስ አምስቱን ክልሎች በአንድ ላይ እንዲዋሃዱ የሚያደርግ ትዕዛዝ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት እንደወጣና በዚህ መሰረትም ክልሎቹ ከሁለት ዓመት በላይ ህልውና እንዳይኖራቸው ተደርጎ በአንድ ክልል እንዲጠቃለሉ መደረጉን ፕሮፌሰር በየነ ይገልጻሉ። "ለዚህ ምክንያቱ እነዚህ ክልሎችን በአንድ ክልል ስር የማካተቱ እርምጃ ለማዕከላዊው መንግሥት ጥቅምና ቁጥጥር አመቺነት ነው" ይላሉ ፕሮፌሰሩ፤ አክለውም ድርጊቱን ተቃውመው ውዝግብ ውስጥ መግባታቸውንና ከሽግግሩ ምክር ቤት እስከመባረር እንደደረሱ ይናገራሉ። ያስከተለው ጽዕኖ አምስቱን ክልሎች በአንድ ያማከለው የመንግሥት እርምጃ የተለያዩ ቦታዎች የየራሳቸው የሆነ የልማት ማዕከላት እንዳይኖራቸው እንደደረገ ይገላጻሉ ፕሮፌሰር በየነ። ይህም በተለያዩ ስፍራዎች ለሚኖር የሥራ ፈጠራና ለኢኮኖሚያዊ እድገት መፋጠን አስተዋጽኦ ይኖረው እንደነበር ያምናሉ። "ክልሎቹ በነበሩበት መተዳደር ቢችሉ ኖሮ አሁን ሐዋሳ ላይ የተከማቸው ሐብት በተለያዩ ቦታዎች ላይ ጥቅም ይሰጥ ነበር። በዚህም ደቡብ ውስጥ በእድገት ጎላ ብላ የምትታየው የሐዋሳ ከተማ ብቻ ሆናለች" የሚሉት ፕሮፌሰር በየነ፤ ነገር ግን አምስቱ ክልሎች በነበሩበት ቢቀጥሉ ኖሮ በርካታ ሊያድጉ የሚችሉ አካባቢዎችን መፍጠር ይቻል እንደነበር ያምናሉ። ነገር ግን ኢህአዴግ ክልሎቹን ወደ አንድ ለማምጣት በወሰደው የዘፈቀደ እርምጃ በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች የልማት ማዕከሎች እንዳይፈጠሩ እንቅፋት በመሆን ክልሉም ሕዝቡም ተጎድቷል። • ያልተነገረለት የኮንሶ ጥያቄ ከሃብት አንጻር ለተቀሩት የክልሉ አካባቢዎች በፍትሐዊነት ሊከፋፈልና ሊዳረስ የሚገባው ሐብት በሐዋሳ ላይ ብቻ እንዲፈስና እንዲከማች በማድረግ ሌሎቹ አካባቢዎች በተመጣጣኝ ሁኔታ እንዳያድጉ እንቅፋት መሆኑን ይናገራሉ። በደቡብ ክልል ውስጥ የቦታ ይገባኛል እንዲሁም ክልል እና ዞን ለመሆን በርካታ ጥያቄዎች በተለያዩ የክልሉ ማኅበረሰብ አባላት ሲቀርቡና በዚህም ሽኩቻና ውዝግብ የነበረ መሆኑን የሚናገሩት ፕሮፌሰር በየነ፤ የእነዚህ ምክንያቶች ደግሞ የመልካም አስተዳደርና የሕግ የበላይነት መጥፋት ያመጣው እንደሆነ ያምናሉ። ነገር ግን ይህ "ሁሉም ጋር ያለ መናቆር ነው" ደቡብ ውስጥ እነዚህ አምስት ክልሎች በአንድ በመዋቀራቸው ከሌሎች ክልሎች ከታዩት ችግሮች የተለየ ነገር ገጥሞታል ብለው የሚጠቅሱት እንደሌለ ይናገራሉ። ለፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ የቀረቡት ክልል የመሆን ጥያቄዎች ምላሽ ቢያገኙ በሃገሪቱ አንድነት ላይ የሚፈጥሩት ውጤት የለም። እንደ እርሳቸው አተያይ ዋነኛው ተግዳሮት የሚሆነው "በእነዚህ ቦታዎች ላይ ከሚያጋጥመው ኢኮኖሚያዊ ውስንነት ውጪ ክልልም ሆኑ ዞን፣ በኢትዮጵያ ማዕቀፍ ውስጥ እስካሉ ድረስ ከስም ለውጥ ባሻገር የሚኖር ጉልህ ለውጥ የለም።" ከአሉታዊው ውጤት ባሻገር ከተጠቀሱት ክልሉ ውስጥ የሚታዩ ውስጣዊ መሻኮቶችና መገፋፋቶች ባሻገር ከኢትዮጵያዊነትና ከኢትዮጵያ ህልውና አንጻር ሲታይ ሰፊ ቁጥር ያላቸው ሕዝቦች በአንድ ክልል ውስጥ መተዳደር እንደሚችሉ ትልቅ ማሳያ ሊሆን ይችላል ይላሉ ደቡብ ክልልን። "ለዚህም ነው ደቡብ ሲነሳ ዘወትር ትንሿ ኢትዮጵያ እስከመባል የተደረሰው" ሲሉ ሀሳባቸውን ያጠናክራሉ። የክልሎቹ መዋሃድና ውጤቱ ከሁለት አስርት ዓመታት በፊት የተወሰነው ክልሎቹን ያለሕዝቡ ፈቃድ የመቀላቀል ውሳኔ በየጊዜው በተለያዩ ደረጃዎች ራስን የማስተዳደር ጥያቄዎች ደጋግመው እንዲከሰቱ አድርጓል። አሁንም አስር የሚደርሱ የክልሉ አካባቢዎች ክልል እንሁን የሚል ጥያቄን ይዘው ምላሽ እየጠበቁ ነው። ፕሮፌሰር በየነም "ሕግን በመጣስ አምሰቱን ክልሎች ወደ አንድ ሲያጠቃልሏቸው ፖለቲካዊ ውሳኔ ነበር ። ይህም ለዛሬው ጥያቄና ችግር ዋነኛ ምክንያት ነው" በማለት ያምናሉ። ሌሎችም አካባቢዎች ክልል የመሆን ጥያቄ አንስተዋል፤ ይህ ተግባራዊ ቢሆን ትናንሽ ክልሎች ከመመስረት ባሻገር በኢትዮጵያ ሃገራዊ ህልውና ላይ ተጽእኖ ይኖራቸዋል ብለው አያስቡም። በርካቶች ክልል የመሆን ጥያቄን ያቀረቡት አካባቢዎች ሁሉም አወንታዊ ምላሽ ቢያገኙ በሚጠበቅባቸው ደረጃ ኃላፊነታቸውን መወጣት ይችላሉ ወይ የሚል ጥያቄ ይነሳል። ፕሮፌሰር በየነም "እነዚህ አዲስ ክልል የሚሆኑት አካባቢዎች ከውስጣቸው በቂ ሐብትና ገቢ ማመንጨት ይችላሉ ወይ? በራሳቸውስ በቂ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማድረግና መተዳደር ይችላሉ ወይ? የሚሉና ሌሎች ጥያቄዎች በቅድሚያ መመለስ አለባቸው።" ባይ ናቸው። ከሌሎች የሃገሪቱ ክልሎች በተለየ በርካታ የክልል እንሁን ጥያቄዎች የቀረቡለት የደቡብ ክልል ምላሽ ለመስጠት የተቸገረ ይመስላል። የክልሉ ገዢ ፓርቲም ከመቀመጫው ሐዋሳ ርቆ አዲስ አበባ ውስጥ በጥያቄዎቹ ዙሪያ ለቀናት ተወያይቶ ያወጣው መግለጫ ተጨባጭ ነገርን አላቀረበም። • ያልጠገገው የሀዋሳ ቁስል ጥያቄዎቹ አዎንታዊ ምላሽን አግኝተው ቢያንስ አንድ ክልል መመስረቱ እንደማይቀር የበርካቶች እምነት ሲሆን ይህ ውጤትም በደቡብ ክልል ላይ በተለይ በዋና ከተማዋ ሐዋሳ ላይ የራሱ የሆነ ውጤት ሊኖረው እንደሚችል ይሰጋሉ። ከዚህ አንጻርም አዳዲስ የሚከሰቱ የቦታ ይገባኛልና የድንበር ጥያቄዎች በሚፈጠሩትና በነባር ክልሎች መካከል ሊከሰቱ እንደሚችሉ አንዳንዶች ቢሰጉም ፕሮፌሰር በየነ ግን "የሚባሉት ውዝግቦችና ግጭቶች አሁንም ያሉ ናቸው ነገር ግን በሰከነና በተረጋጋ ሁኔታ በሕግ አግባብ መፍታት ብቻ ነው የሚያስፈልገው" በማለት ከአዳዲስ ጥያቄዎች ባሻገርም የነበሩ ጥያቄዎች ወደ ፊት መምጣታቸው አይቀርም ይላሉ።
48284662
https://www.bbc.com/amharic/48284662
የ74 ዓመቱ ኮ/ል ካሳዬ አጭር የመፈንቅለ መንግሥት ማስታወሻ
ኤርትራ የሚገኘው የ102ኛው አየር ወለድ ኢታማዦር ሹም ነበርኩ ያኔ።
መንግሥቱ ኃይለማርያም፣ የካቲት 12/1970 ዓ.ም ሞስኮ ግንቦት 8 ቀን ነው፤ ማክሰኞ 'ለታ ድንገት ጄ/ል ደምሴ ቡልቶ ቢሮ በአስቸኳይ ትፈለጋለህ ተባልኩ። መኪናዬን አስነስቼ እሳቸው ቢሮ ሄድኩ። እኔ ስደርስ ብ/ጄ ካሳዬ ጨመዳ ውስጥ ነበሩ፤ እሳቸው ሲወጡ እኔ ገባሁ። ‹‹አቤት ጌታዬ!›› አልኳቸው። ‹‹አዲስ አበባ ትንሽ ግርግር አለ፤ ሁለት ብርጌድ ጦር ይዘህ ሄደህ በአስቸኳይ አረጋጋ›› አሉኝ። ጄ/ል ቁምላቸው ተጨማሪ ትዕዛዝ ይሰጥኻል ተባልኩ። ጄ/ል ቁምላቸው ቢሮ ስደርስ፣ ‹‹መጣህ ካሳዬ! በል ተከተለኝ›› ብለው መኪናቸውን አስነሱ። ከኋላ ከኋላ ስከተላቸው፣ ስከተላቸው አሥመራ አየር ኃይል ደረስን። ፊት ለፊታችን ራሺያዎች ለመንግሥቱ በሽልማት የሰጧቸው አውሮፕላን ቆማለች። በዚህ አውሮፕላን አዲስ አበባ እንሄዳለን አሉኝ። ‹‹ልብስና ማስታወሻ አልያዝኩም እኮ፣ ጌታዬ›› ስላቸው፣ ‹‹…በል በሚቀጥለው አውሮፕላን ድረስብን›› ብለውኝ ገቡ። ቶሎ ቤት በርሬ ልብስና ማስታወሻ ይዤ ስመለስ አውሮፕላኗ ሳትነሳ ደረስኩ። አውሮፕላኗ ውስጥ 70 የሚሆኑ ሰዎች ተሳፍረዋል። አየር ወለዶች ደግሞ በአራት አንቶኖቭ ተጭነው ተከትለውን ይመጣሉ። አውሮፕላኗ ወደ ምጽዋ አቅጣጫ ያዘችና ከዚያ ወደ ቃሩራ ሄደች። ከዚያም ተመለሰችና ልክ መረብን ስንሻገር ይመስለኛል ጄ/ል ቁምላቸው ብድግ ብለው ተነሱና አንዲት ወረቀት ይዘው ማንበብ ጀመሩ። የትግራይና የኤርትራ ሕዝብ የሚደርስበትን ችግርና መከራ አወሩና ሲያበቁ...መጨረሻ ላይ አስደነገጡን። እኔም በደንብ ትዝ የምትለኝ መጨረሻ ላይ የተናገሯት ነገር ናት…። ‹‹ኮ/ል መንግሥቱ ተገድለው ከሥልጣን ተወግደዋል!›› አሉ። በጣም ነው የደነገጥኩት፤ እኔ ከአሥመራ ስነሳ የማውቀው ነገር አልነበረማ። በአውሮፕላኑ ላይ የነበርነው በአጠቃላይ 73 እንሆናለን። ያ ሁሉ ሰው ሲያጨበጭብ እኔ ግን ፈዝዤ፣ ደንዝዤ ቀረሁ። እንደመባነን ብዬ ነው ማጨብጨብ የጀመርኩት። ኢምፔሪያሊዝምን በመቃወም በአብዮት አደባባይ ሚያዚያ 23/1969 የተደረገ ሰልፍ፣ አዲስ አበባ የሚቀበለን አጣን እኛ 11 ሰዓት ተኩል ላይ ኤርፖርት ደርሰን ስልክ ብንደውል፣ ብንደውል ማን ያንሳ። ሬዲዮ ብናደርግ ማን ያናግረን። መከላከያ ደወልን፤ ማንም ስልክ አያነሳም። ምድር ጦር ደወልን፤ ማንም የለም። ግንኙነቱ ሁሉ ተቋርጧል። ለካንስ እኛ ከመድረሳችን በፊት ነገሩ ሁሉ ተበለሻሽቷል። ለምን በለኝ…፣ በ9፡30 አካባቢ ጄ/ል አበራም ሚኒስትሩን ጄ/ል ኃይለጊዮርጊስን ገድሎ አምልጧል። እኛ ይሄን ሁሉ አናውቅም። እኛ የምናውቀው ኮ/ል መንግሥቱ መገደላቸውን ነው። በዚያ ሰዓት እኛ ይዘነው የመጣነውን ጦር የሚያስተባብር ሰው አልነበረም። እኛ ገና ሳንደርስ ነው ከልዩ ጥበቃ ብርጌድ ታንክ መጥቶ መከላከያን የከበበው። እንደነገርኩህ እኛ ይሄን አናውቅልህም። እኛ የምናውቀው መንግሥቱ መገደሉን ነው። • መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ ብቻ ምናለፋህ…ተከታትሎ የመጣውን አየር ወለድ ግማሹ እዚያ ኤርፖርት ዙርያ ጥበቃ ማድረግ ጀመረ። ሌላው አቃቂ ቃሊቲ ፍተሻ ጣቢያ ላይ ተመድቦ ከውጭም ከውስጥም ሰውም ሆነ ተሸከርካሪ እንዳይገባ እንዳይወጣ አደረገ። የቀረነው ወደ ምድር ጦር አቪየሽን ግቢ ሄድን። ከጦላይ የመጣ 'ስፓርታ' ጦርም እዚያው ተቀላቀለን። የግንቦት 8 አመሻሽ- በጎማ ቁጠባ አካባቢ እየመሸ ሲሄድ ግራ ተጋባን። ጄ/ል ቁምላቸው ጠሩኝና «በቃ ወደ መከላከያ እንሂድ» አሉኝ። ምንም እንኳ ግንኙነታችን ቢቋረጥም አመጣጣችን እዚያ መከላከያ ሚኒስቴር ለሚገኙ የመፈንቅለ መንግሥቱ መሪዎች ከለላ መስጠት ስለነበር ነው ወደዚያው ያመራነው። አንድ ሻለቃ ጦር ይዘን በምድር ጦር መሐንዲስ፣ በባልቻ ሆስፒታል ላይኛው በኩል፣ አድርገን በአምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አልፈን ጤና ጥበቃ ጋ ደረስን። አንድ ሻለቃ ጦር ይዘናል። እዚያው ጎማ ቁጠባ ጋ አስቀመጥናቸውና እኛ ለቅኝት ወደ መከላከያ ተጠጋን። እንደነገርኩህ መሽቷል። እንዲያውም እኩለ ሌሊት አልፏል…። ግን ጨረቃዋ ድምቅ ብላ ወጥታ ነበር። የሚገርምህ ያን ምሽት ሁሉ ነገር ማየት ትችላለህ። በቃ ምን ልበልህ ልክ እንደ ፀሐይ ነበር የምታበራው። ከላይ ከጎማ ቁጠባ መጥቼ ብሔራዊ ቲያትር አደባባዩ ጋ ለቅኝት ስቀርብልህ ከኢትዮጵያ ሆቴል በታች ትራፊክ መብራት አለ አይደል? ወደ ፍልዉሃ መሄጃ…? እዚያ አንድ ታንክ ቱሬቱን እያዘቀዘቀ ወደኔ ጂፕ እያስተካከለ ሲመጣ አየሁት። እኔ መትረየስ ጂፕ ላይ ነው የነበርኩት። ቶሎ ቀኝ ወደኋላ ተጠምዘዝ አልኩት ሾፌሩን። እንደገና በላይ በኩል ዞረን ለማየት ስንል ከፒያሳ በኩል ሌላ አንድ ታንክ ቱሬንቱን ወደኛ እያስተካከለ ሊመታን ተዘጋጀ። ምናልባት አንድ ነገር ቢያጋጥም ለመተኮስ ነውኮ ወደኛ የሚያነጣጥረው። በቃ ተመልሼ ወደ ጎማ ቁጠባ ሄድኩ። እኛ እስከዚህ ሰዓት ድረስ መከላከያ ውስጥ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አናውቅም። መፈንቅለ መንግሥቱ መክሸፉንም አልሰማንም። እነ ጄ/ል መርዕድም በሕይወት ያሉ ነው የመሰለን። መንግሥቱ ኃይለማርያም መወገዱን ብቻ ነው የምናውቀው። ቢቢሲ፡ መሣሪያ ታጥቃችኋል? እኔና ቁምላቸው ይዘነው የመጣነው ሠራዊት ሁለት አሞርካ አለው። አራት አፈሙዝ ያለው አሞርካ። እሱንም ቢሆን ያንኑ ምሽት ከልዩ ጥበቃ ብርጌድ የማረክነው ነው። ቢቢሲ፡ ይቅርታ ግን ኮ/ል፣ አሞርካ ምንድነው? አሞርካ የኮሪያ ባለሁለት አፈሙዝ፣ ሽልካ የመሰለ ሁለት አፈሙዝ ያለው የዙ 23 ጥይት የሚጎርስ ከባድ መሣሪያ ነው። ሁለት ነበሩ ከልዩ ጥበቃ ብርጌድ የመጡ። ምድር ጦር ሲገቡ ወታደሮቹን ማረፊያ ወስደን ማረክናቸውና ሾፌር መድበን፣ ተኳሾቹን ከአየር ወለድ ጨምረን ነው ወደ ጎማ ቁጠባ አካባቢ የሄድነው። ከዚያ ከጄ/ል ቁምላቸው ጋር ወደ አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሄደን ስልክ አግኝተን መደወል ጀመርን። መከላከያ ስልክ የሚያነሳ ሰው የለም። አር-ፒ-ጂ የለ፤ ታንኩን በምን እንምታው? በቃ ጧት መልሶ ማጥቃት እናደርጋለን ብለን ያን ሌሊት ከጎማ ቁጠባ ወደ ምድር ጦር ተመለስን። • የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ እዛ ስንደርስ ጄ/ል ቁምላቸው መጣሁ ብለውኝ ሄዱ። ከዚያ ወዲያ ተያይተን አናውቅም። ብሔራዊ ባንክ አካባቢ፣ አዲስ አበባ፣ 1960ዎቹ «ጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያ እንባቸው መጣ» የታሠርነው ቤተ መንግሥት ነበር። እዚያ ትልቅ አዳራሽ አለ፤ የንግሥት ዘውዲቱ ጠጅ መጥመቂያ የነበረ ነው። የአሥመራ ሞካሪዎችም በአሰቃቂ ሁኔታ የፊጢኝ ታስረው እየጮኹ ሲቀላቀሉን ትዝ ይለኛል። 112 እንሆን ነበር። ታስረን እያለን ጓድ መንግሥቱ ሁለት ጊዜ ጎብኝተውናል። የመጀመርያ ቀን የመጡት አብዮት አደባባይ ለሕዝብ ንግግር ያደረጉ ቀን ነው። ግንቦት 10 ይሁን 11 ብቻ ረሳሁት። ከአብዮት አደባባይ በቀጥታ እኛ ጋ መጡ። እኛ ደግሞ ያኔ ፖሊሶች ተመድበውልን ቃል እንሰጥ ነበር። ያን ቀን መጥተው ዝም ብለው አይተውን ሄዱ። ከዚያ ደግሞ ሰኔ 11፣1981 ቀን ተመልሰው መጡ። ያኔ ወደ 118 መኮንኖች እንሆናለን በንግሥት ዘውዲቱ ጠጅ መጥመቂያ አዳራሹ ውስጥ የታሰርነው። አዳራሹ አንድ በር ብቻ አለችው። ምንም ብርሃን የለውም። የምታየው አንዳች ነገር የለም። እርግጥ ጧትና ማታ ለአንድ ሰዓት ፀሐይ እንሞቃለን። ሰኔ 11 ቀን ለሁለተኛው ጊዜ ሲመጡ ታዲያ ፀሐይ እየሞቅን ነበር። ተሰብሰቡ ተባለ። ግማሹ ጋቢ ለብሷል። ግማሹ ጭንቅላቱ ላይ ጠምጥሟል። ከዚያች ዕለት ትዝ የሚለኝን ልንገርህ…? መንግሥቱ ዞር ዞር ብለው አዩን፤ ከዛ ወደ ጄ/ል አብዱላሂ ዞረው፣ ‹‹አብዱላሂ!» አሉ። የመከላከያ ሚኒስትር አስተዳደር የነበሩት ጄ/ል አብዱላሂ፣ «አቤት ጌታዬ» አሉ፤ "አንተ የአዲስ አበባ ዙርያ ጦር ጥበቃ 6 ወር ደመወዝ እንዳልተከፈለው ታውቅ የለም እንዴ?" አሏቸው። ‹‹አዎን አውቃለሁ ጌታዬ›› ብለው መለሱ። ‹‹ይሄ በኔ ላይ ሴራ ለመጠንሰስ ያደረከው አይደለም?? አይደለም ወይ…?!›› ከዚያ ደግሞ ዞር ሲሉ ሰለሞን በጋሻውን አዩ። ጄ/ል ሰለሞን የአየር ኃይል ኢታማዦር ሹም ነበሩ። "ሰለሞን! እናንተ በሂሊኮፕተር ሽርሽር ስትሄዱ እኔ ፈንጂ ውስጥ በእግሬ እዞር ነበር፤ ይሄን ታውቃለህ...?" አሉ። በዚህን ጊዜ ጄ/ል ሰለሞን ጥያቄ ለመጠየቅ [መልስ ለመስጠት] እጃቸውን አወጡ። ልክ ከመናገራቸው በፊት ግን ጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም እንባቸው ግጥም ሲል ታየኝ። ፊት ለፊታቸው ነበርኩ። እንባቸው የመጣው…እልህ ይዟቸው ይመስለኛል። እንባ ሊቀድማቸው እንደሆነ ሲያውቁ 360 ዲግሪ ዞሩና ወጥተው ሄዱ። በኛ ፊት ሲያለቅሱ መታየት አልፈለጉ ይሆናል። ከዚያ በኋላ ጓድ መንግሥቱን አይተናቸው አናውቅም። ጓድ መንግሥቱ ኃይለማርያም በአፍሪካ አንድነት ድርጅት ጉባኤ ንግግር ሲያደርጉ-ኀዳር 21፣ 1980 ዓ.ም ሞት የሚጠባበቁ ታሳሪዎች ምን ይሉ ነበር? አብረውኝ የታሠሩት ሁሉም መፈንቅለ መንግሥት ሞካሪዎች ናቸው። ከጄ/ል እስከ ሚሊሻ። እኔ እንዳውም ከኮ/ል በታች ላሉት 'ካቦ' ነበርኩ። ደርግ ተገለበጠ ሲባል እልል ብለህ መሬት ስመኻል ተብሎ የታሰረ ሚሊሻም አብሮን ነበር። እነ ጄ/ል ኃይሉ ገ/ሚካኤል (የምድር ጦር አዛዥ)፣ ምክትሉ ሜ/ጄ/ል ዓለማየሁ ደስታ፣ የፖሊስ አዛዡ ሜ/ጄ ወርቁ ዘውዴ ሌሎችም ከአሥመራው አሰቃቂ ግድያ የተረፉት በሙሉ አብረውን አሉ። ጄ/ል ፋንታ በላይ ግን ሦስተኛው ቀን መጡና ወዲያው ደግሞ ማዕከላዊ ሄዱ ተባለ። እዚያ አዳራሽ ውስጥ ቁጭት ነበረ። ሰለሞን በጋሻውና ጄ/ል ተስፉ ለምሳሌ ይቆጩ ነበር። ብርጋዴር ጄኔራል ተስፉ ደስታ የአየር ኃይል የዘመቻ መኮንን ነበር። ብርጋዴር ጄኔራል ሰለሞን በጋሻው ደግሞ የአየር ኃይል ምክትል አዛዥ ነበር። ከእኔ አጠገብ ነበር የሚተኙት። እሰማቸዋለሁ። ማታም ጠዋትም ‹‹ይሄ ሰውዬ አይለቀንም፤ ምናለ በለኝ ይገድለናል›› ይሉኝ ነበር። ያው የፈሩት አልቀረም። ሁለቱም የሚቆጩበት አንድ ነጥብ ምን ነበር መሰለህ? ያኔ ኮ/ል መንግሥቱ [ወደ ምሥራቅ ጀርመን] ለጉብኝት በሚሄዱበት ጊዜ አውሮፕላኑ ሲነሳ ቀይ ባሕር ላይ እንዲመታ ተብሎ ነበር የተዘጋጀው። እና እነሱ ያ አለመደረጉ [ይቆጫቸው ይመስለኛል]። ቢቢሲ፡ ኮ/ል አሁን በ74 ዓመትዎ ሲያስቡት መፈንቅለ መንግሥቱ ተሳክቶ በሆነ ብለው ይቆጫሉ? እኔ ምንም እንደዛ አላስብም። ምክንያቱም እኔ ያለውን ሁኔታ ሳየው መንግሥቱም አጠፋ ብዬ በሱ የምፈርደው ነገር የለም። ምንም አላደረገም። ለኢትዮጵያ ጥሩ ነገር ነው የሠራው። እስር ቤት ሳለንም እነሱ ፊት እከራከር ነበር። የደርግ ደጋፊም ነበርኩ። መንግሥቱ ምን አደረገ? መቼም አገሪቱ ውጊያ ላይ ብትሆንም፣ ጦርነት ቢበዛም፣ እሱም የኢትዮጵያን አንድነት ነው ይዞ የተነሳው። አገር እንዳይቆረስ ነው የታገለው። እኛ መኮንኖቹ ያጠፋነው ጥፋት ነው ለዚህ የዳረገን። አብዛኛውን ውጊያ ቦታ ላይ ለመሸነፍም የበቃነው ከአመራር ስህትት ነው። መረጃ ሾልኮ እየወጣ ነው። ችግሩ ከኛ ነበር እንጂ ከመንግሥቱ አልነበረም። ሚያዚያ 23/1969 ዓ.ም ወታደሮች መስቀል አደባባይ ላይ በተካሄደ ሰልፍ ኢምፔሪያሊዝምን እያወገዙ ከሞት መንጋጋ ስለመትረፍ እስር ቤት ሆነን እነ ጄኔራል ደምሴ ቡልቶ አሥመራ ላይ የደረሰባቸውን ስንሰማ አዘንን፤ እኛ ጋ ታስረው የመጡ መኮንኖች ናቸው የነገሩን። ያው በዚያ መንገድ መሞታቸው አግባብ አልነበረም። በሕግ ነበር መቀጣት የነበረባቸው። ሁላችንም በቡድን በቡድን ተከፋፍለን ቤተ መንግሥት ውስጥ የተቋቋመ ወታደራዊ ፍርድ ቤት ነበር የምንቀርበው። እነሱ ሰኔ 12፣1982 ለውሳኔ ተቀጠሩ። ሰኔ 11 ብርጋዴር ጄነራል ተስፉ ደስታ (የአየር ኃይል ዘመቻ ኃላፊ) ይናገር የነበረው ትዝ ይለኛል። ‹‹ዛሬ የመጨረሻችን ነው። ካሳዬ [ምናለ በለኝ] እኛ አንመለስም›› ይል ነበር። ተሰነባብተን ነው የተለያየነው። እነሱም አንመለስም ይገድለናል ብለው ነው ተሰናብተውን የወጡት። ግንቦት 11 ቀን ነው። አብረን ነው ያደርነው። እነሱ ወደ ችሎተ ሄዱ፤ ምናልባት ይመጣሉ ብለን ስንጠብቅ ቀሩ። ሞትን ቁጭ ብሎ መጠበቅ ምን ይመስላል? እነሱ በተገደሉ በዓመቱ ግንቦት 23 ለውሳኔ ተቀጠርን። ከእኛ በፊት ግንቦት 15፣1983 ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለውሳኔ የሚቀርቡ ጓደኞቻችን ነበሩ። ያው እነሱ ሳይመለሱ ሲቀሩ እኛም ተመሳሳይ ነገር እንደሚመጣ ነው የምንጠብቀው፤ በእውነቱ እንወጣለን እንድናለን ብለን የምንለው ነገር አልነበረም። ያው የሞት ፍርድ ይፈረድብናል ብለን ነበር እንጠብቅ የነበረው። በመሀሉ ግንቦት 13፣ መንግሥቱ ከአገር ወጡ ተባለና በተአምር ተረፍን። ይኸው በሕይወት አለን... የስንብት ጥያቄዎች ለኮ/ል ካሳዬ ታደሰ ቢቢሲ፡- ጄ/ል መርዕድ ንጉሤ እንዴት ራሳቸውን እንዳጠፉ ያውቃሉ? ኮ/ል ካሳዬ፡- አላውቅም ቢቢሲ፡- ጄ/ል አመሃ ደስታ ራሳቸውን እንዴት እንዳጠፉ ያውቃሉ? ኮ/ል ካሳዬ፡- አላውቅም ቢቢሲ፡- ጄ/ል አበራ አበበን በሕይወት መያዝ እየተቻለ ለምን የተገደሉ ይመስልዎታል? ኮ/ል ካሳዬ፡- ጄ/ል አበራን እኔ ሳውቃቸው እጅ የሚሰጡ ሰው አይደሉም። ተታኩሰው ነው የሚሞቱት።
47250955
https://www.bbc.com/amharic/47250955
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ንቅናቄ ትናንት እና ዛሬ
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተቃውሞ ፖለቲካና እንቅስቃሴ በስፋት ተስተውሏል። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተለይም ብሔራቸው በሚመለከቱ ጉዳዮች ድምፃቸውን አሰምተዋል፣ በብሔር እርስ በርስ ተጋጭተዋል፤ በብሔር ተኮር ጥቃትም ሕይወታቸውን እስከማጣት ደርሰዋል።
ዶ/ር ገብሩ ታረቀ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና ዶ/ር የራስወርቅ አድማሴ ዘንድሮም ተማሪዎች ከክልላቸው ውጪ ወደሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች አንሄድም ብለው እንደነበርም አይረሳም። መጻሕፍትን ከሚሸከሙ እጆች ይልቅ በትር በዝቷል። እስክርቢቶን ለመጻፍያ ሳይሆን ሌላ ተማሪን ለመውጋት አገልግሎት ላይ ውሏል። ሲጠቃለል 'ዱላና ድንጋይ የትምህርት መሣሪያ ሆኑ' እየተባለ ነገሩ በምፀት ተነግሯል። • ዩኒቨርሲቲ ብሎ ለመጥራት የሚያስቸግሩ "ዩኒቨርሲቲዎች" ወላጅ ልጆቹን በኩራት ሳይሆን በሥጋት ወደ ዩኒቨርሲቲ የላከበት ጊዜ ላይ እንገኛለን። ሥጋቱ አይሎባቸው ልጆቻቸውን በመጨረሻው ሰዓት ከትምህርት ገበታ ያስቀሩም ጥቂት እንደማይሆኑ መገመት ይቻላል። "ዩኒቨርሲቲ ምኑን ዩኒቨርሲቲ ሆነ?" በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ተሳታፊ የነበሩት ዶ/ር የራስ ወርቅ አድማሴ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ36 ዓመታት በማስተማራቸውም የተማሪዎች ፖለቲካዊ ጥያቄንም ሆነ እሱን ተከትሎ የሚነሱ እንቅስቃሴዎችን ለመረዳት ቅርብ ናቸው። ከሳቸው ጊዜ የ 'መሬት ላራሹ' የተማሪዎች ንቅናቄ አንፃር የቅርብ ዓመታቱም ኾነ የዛሬዎቹ የተማሪዎች ፖለቲካዊ ጥያቄና እንቅስቃሴዎች በብዙ መልኩ የተለዩ ናቸው ይላሉ። ያኔ ተማሪው የሚያምፀው በሥርዓቱ፤ የሚቃወመውም ሥርዓቱን ነበር የሚሉት ዶ/ር የራስ ወርቅ በአንድ ዓላማ በአንድ ላይ መቆም የሳቸው ጊዜ የተማሪዎች ንቅናቄ መገለጫ እንደነበር ያስታውሳሉ። • ከ300 በላይ የሚዛን ቴፒ ተማሪዎች ታመው እንደነበር ተሰማ ያሁኑ ግን "ተማሪው በብሔር ተከፋፍሎ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ክፍፍሉ ከብሔርም ወርዶ ጎጥም ይደርሳል። ሃይማኖትም ሁሉ ይኖራል" በማለት ያነፃፅራሉ። ባለፉት ዐሥርና እንደዚያ ዓመታት በዛሬዎቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄዎች ምክንያት የዩኒቨርሲቲ ቅጥሮች ውስጥ በሚገኙ ንብረቶች ላይ ውድመት ደርሷል። እሳቸውና የሳቸው ጊዜ ተማሪዎች ደጅ ከፖሊስ ጋር ይጋጩ እንጂ የዩኒቨርሲቲ ቅጥር ላይ ጉዳት አያደርሱም ነበር። ዩኒቨርሲቲዎችን መደብደብ በጭራሽ የሚታሰብ ነገር እንዳልነበር የሚናገሩት ዶ/ር የራስ ወርቅ "ይልቅ ዩኒቨርሲቲው የንቅናቄው ካምፕና ምሽግ ነበር" ይላሉ። ተማሪ በተማሪ የተደበደበበትና የተሳደደበትን የቅርብ ጊዜውን የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግጭት በምሳሌነት በማንሳት የአሁን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፖለቲካ ጥያቄ "ፀባዩም፣ ዓላማውም እንደገናም የትግል መሣሪያዎቹም ከኛ የተለዩ ናቸው" ይላሉ። ቤተ መጻሕፍት ተቀምጦ የሚያነብ ተማሪ ከኋላዬ ተመታሁ ብሎ የሚሰጋ ከሆነ፣ በተማሪዎች መኝታ እርስ በርስ ተፈራርተው እንቅልፍ አጥተው የሚያድሩ ከሆነ፣ ሴት ተማሪዎች እንደፈራለን እያሉ የሚሰጉ ከሆነ "ዩኒቨርሲቲ ምኑን ዩኒቨርሲቲ ሆነ?"ይላሉ ዶ/ር የራስወርቅ። • የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የፖለቲካ ጥያቄ እንዴት ይመለስ? ዩኒቨርሲቲ የሚለው ቃል "ዩኒቨርሳል" (ትልቁ ዓለም) ከሚለው ቃል የመጣ፣ የአስተሳሰብ አድማስን የሚያጎለብት፣ ነገሮችን አስፍቶ የሚመለከት ቢሆንም ዛሬ ግን እንደ ብሔርና ሃይማኖት ያሉ ልዩነቶች አይለው የአገሪቱ የዩኒቨርሲቲዎች ነባራዊ እውነታ ከዚህ በተቃራኒው መሆኑ አለመታደል እንደሆነ ይናገራሉ። ከ"ዩኒቨርሳሊስት" ይልቅ ብሔር ብሔር በመባሉ ግን ተማሪው ላይ አይፈርዱም። ምክንያቱ ደግሞ ተማሪው የዛሬው የአገሪቱ ፖለቲካዊ ሥርዓት ነፀብራቅ ነው ብለው ማመናቸው ነው። እሳቸውና የሳቸው ዘመን ተማሪዎች አተያይና የተማሪዎች ንቅናቄም ከጊዜው ዓለም አቀፋዊ ሁኔታ አንፃር የተቃኘ ነበር። "ምናልባት በዚያ ጊዜ ስለዓለም አቀፋዊነት፣ ስለ ሆቺ ሚንና ቼጉቬራ ስናወራ የነበርነው እኛም የዚህ ጊዜ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብንሆን ከዛሬው ተማሪ የምንለይ አንሆንም ነበር" ይላሉ። የተማሪ ጥያቄ ማንሳትም ሆነ ቁጭቱን መግለፅ የሚወገዝ ሳይሆን የሚመሰገን ነው የሚሉት ዶ/ር የራስወርቅ የአሁኑ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጥያቄ አቀራረብና የእንቅስቃሴው ኢላማ ግን መስመር የሳተ በመሆኑ ሊቀየር ይገባል ባይ ናቸው። "የያኔና የአሁኑን የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ማነፃፀር በጣም ይከብዳል" ከዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብዛት፣ ከአገራዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች መለዋወጥ አንጻር ሁለቱን የተማሪ ትውልድ ማወዳደር እጅጉን ከባድ እንደሆነ የሚናገሩት ደግሞ በኢትዮጵያ የተማሪዎች ንቅናቄ ተሳታፊ የነበሩትና ስለ ኢትዮጵያ አብዮት መጽሐፍ የጻፉት ፕሮፌሰር ገብሩ ታረቀ ናቸው። ለእነሱ በቀላሉ መቀራረብና መግባባት ብሎም በአንድ ርዕዮተ ዓለም መሰባሰብ ቀላል ነበር። ተማሪው የሚከተለው ማርክሲዝም ሌኒንዝምን እንደነበርም ፕሮፌሰር ገብሩ ያስታውሳሉ። • "ለሴት ምሁራን የተከለከለ ኃላፊነት?" "ዋናው ዓላማችን በአፋጣኝ የኢትዮጵያን ዕድገት ማየት፣ ገበሬውና ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የነበረው ሰፊው ሕዝብ ከዕድገቱ ተጠቃሚ እንዲሆን ነበር የተሰባሰብነው፣ የታገልነው፣ የቆሰልነውና የሞትነውም" ይላሉ። እንደ እሳቸው እምነት የብሔር ፌደራሊዝሙ ተማሪው ላይ ትልቅ ተፅእኖ አሳድሯል። በዚህም በሳቸው ጊዜ አሰባሳቢና አዋሃጅ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ግን ከፍተኛ ልዩነት የሚንፀባረቅባቸው ሆነዋል። ባለፉት ዓመታት ኢህአዴግ ትምህርት ቤቶች ላይ የሠራው የፖለቲካ ሥራ (በተለይም ተማሪዎችን አባል ማድረግ) ያሳደረውን ተፅእኖም ይጠቅሳሉ። አብዛኞቹ የዩኒቨርሲቲ መምህራንም በዕድሜም ሆነ በብቃት ለእነሱ ዘመን ምሁራን ሳይሆን ለተማሪዎቻቸው የቀረቡ መሆንን ዶ/ር የራስወርቅና ፐሮፌሰር ገብሩ እንደ አንድ ችግር ጠቅሰዋል። ፖለቲከኞችና ፅንፈኛ ብሔርተኞች ዩኒቨርሲቲዎችን የራሳቸው የጨዋታ ሜዳ ማድረጋቸውም ለፕሮፌሰር ገብሩ ከፍተኛ ችግር ነው። • የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ስጋት የትምህርት ዝቅጠት እና የሥነ ሥርዓት ጉድለትም ሌላው እንደ ችግር ያነሱት ጉዳይ ነው። ከጠቀሷቸው ምክንያቶች በመነሳት የሳቸውን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ንቅናቄ ከዚህኛው ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንቅስቃሴ ልዩነቱ የሰማይና የምድር ያህል ነው በማለት ይደመድማሉ። እንደ ዶ/ር የራስወርቅ ሁሉ ፕሮፌሰር ገብሩም ለዛሬው ሁኔታና ምስቅልቅል እሳቸው 'የተበደሉ' በሚሏቸው የአሁኑ ጊዜ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ አይፈርዱም። "ፖለቲካው ንግድ አልሆነም ነበር" የ60ዎቹ ትውልድ ከአሁኑ በሁለት መሠረታዊ ነገሮች እንደሚለይ ይናገራሉ፣ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናም። የመጀመሪያው በሳቸው ጊዜ የነበረው የጋራ አጀንዳና የአንድነት ጉዞ ቀርቶ ጭራሹኑም ተማሪዎችን የሚያስማማ ነገር መጥፋቱ ነው። "መሬት ላራሹና የብሔር እኩልነት የሁሉም አጀንዳ ነበር። ያኔ የብሔር ጥያቄ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ነበረውም" በማለት ያስታውሳሉ። ሁለተኛውና ዋናው ልዩነት የሚሉት በሳቸው ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪው ወደ ድርጅቶች ይሄድ የነበረው ለትግል እንጂ የሆነ ዓይነት ጥቅም ለማግኘት ያልነበር መሆኑን ነው። "ፖለቲካ እንደዛሬው ወደ ንግድነት አልተቀየረም ነበር ። ከመንግሥትም ሆነ ከማንም ለሚገኝ ትርፍ ሳይሆን ለዓላማ ነበር።" በዩኒቨርሲቲዎች ብቻም ሳይሆን በመላ አገሪቱ ፖለቲካን ወደ ንግድ መለወጡ የኢህአዴግ ትልቁ ጥፋት እንደሆነም ይደመድማሉ ፕሮፌሰር መረራ። • የሃምዛ ሃሚድ ገመድ አልባ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የተወሰኑ መመሳሰሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ የሚናገሩት ፕሮፌሰር መረራ "ይነስም ይብዛ ይሄኛውም ተማሪ የራሱ አጀንዳ ይኖረዋል" ይላሉ። እሳቸው እንደሚያስታውሱት የብሔር ጥያቄ በዚያ ጊዜም ተነስቷል። ኢትዮጵያዊ ማን ነው? የሚሉ ዓይነት ጥያቄዎችም መነሳት ጀምረው ነበር። ታዲያ የዛሬው ልዩ ነገር ምንድን ነው? "መከፋፈሉ ያኔ የጀመረ ቢሆንም ዛሬ ብዙ የቻይና ግንቦች በዝተዋል" የሚሉት ፕሮፌሰር መረራ የዛሬውና የሳቸው ጊዜ የብሔር ጥያቄ አረዳድም በጣም መለያየቱን ያስረዳሉ። "ያኔ የተማሪን ልብ የሚስበው ሶሻሊዝም ነበር። ዛሬ ደግሞ የተማሪው ልብ ብሔር ላይ ነው" አፄ ኃይለ ሥላሴ ከሥልጣን ወርደው፣ አብዮቱም አልፎ፣ የተማሪዎች ንቅናቄ ቦታውን በልዩነት ላይ ለተመሠረቱ ድርጅቶች መልቀቀ ሲጀምር የተፈጠረው ነገር ዛሬ ላይ አድርሶናል፤ በዚህም ልዩነቶች እየሰፉ ግጭቶችም እየበዙ መጥተዋል ሲሉ ይደመድማሉ።
47512845
https://www.bbc.com/amharic/47512845
ከአዲስ አበባ ናይሮቢ በመብረር ላይ የነበረው ET302 ተከሰከሰ
ዛሬ እሁድ መጋቢት 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጠዋት ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ ይበር የነበረ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 የበረራ ቁጥር ET302 መከስከሱን ጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በትዊተር ገፁ አስታውቋል።
አውሮፕላኑ 149 ሰዎችን እንዲሁም 8 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ እንደነበርና ከተነሳ ከ ስድስት ደቂቃ በኋላ ግንኙነት መቋረጡን ፋና ዘግቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአንድ ሰዓት በፊት ባወጣው የአደጋ ሪፖርት ጠዋት 2፡38 ከአዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ የተነሳው አውሮፕላን የተከሰከሰው ደብረዘይት አካባቢ እንደሆነ አስታውቋል። ምን ያህል ሰው ሞተ ወይም ተረፈ ስለሚለው የታወቀ ነገር እንደሌለና የተሳፋሪዎችን ማንነት የሚያጣራ የመረጃ ማእከል በመክፈት ላይ መሆኑን አየር መንገዱ አስታውቋል። እስካሁን ስለ አደጋው መንስኤ የተባለ ነገር የለም። ወሎ በነዳጅ 'ልትባረክ' ይሆን?
news-52812267
https://www.bbc.com/amharic/news-52812267
ኮሮናቫይረስ ሲጠፋ እንጨባበጥ ይሆን? ሳይንቲስቶች "በፍጹም!" ይላሉ
በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ብዙ ልማድ መጥቶ ሄዷል። መጨባበጥ ግን እነሆ እንዳለ አለ።
መጨባበጥ ከሰው ልጅ ባሕል ጋር እንደተጨባበጠ እነሆ ስንት ዘመኑ! ሰዎች አዲስ ሰው ሲተዋወቁ ይጨባበጣሉ፤ ከሚያውቁት ሰው ጋር ይጨባበጣሉ። ቢሊየነሮች የንግድ ሥምምነት ተፈጣጥመው ይጨባበጣሉ። አጫራች አሸናፊውን ተጫራች ማሸነፉን የሚያውጅለት እጁን በመጨበጥ ነው። መንግሥታት በጦርነት ከተቋሰሉ በኋላ "ይቅር ለእግዜር" የሚባባሉት በመጨባበጥ ነው። መጨባበጥ እንደ መተንፈስ ያለ ነው። ሕይወታችንን ተቆጣጥሮታል። እንኳንስ እኛ የአሜሪካ ፕሬዝዳንትም የነጩ ቤተ መንግሥት የግዛት ዘመኑን ሩብ የሚያጠፋው በመጨባበጥ ነው። አንድ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በዓመት በአማካይ ስንት ሰው የሚጨብጥ ይመስልዎታል? 65 ሺህ ሰዎችን! ታዲያ ከመጨባበጥ ጋር በቀላሉ የምንፋታ ይመስልዎታል? ለመሆኑ ማን ጀመረው? እንዴት ይታወቃል ይሄ? አይታወቅም። ኾኖም መላምቶች አሉ። ጥንታዊ ግሪኮች መሣሪያ ይሸከሙ ስለነበር አንዱ ሌላውን ለማጥቃት እንዳልመጣ ለማሳየት ይጨባበጡ ነበር። አውሮፓዊያንም ጀምረውት ይሆናል። ድሮ በመካከለኛው ዘመን በነፍስ የሚፈላለጉ የመሳፍንትና የመኳንንት ቤተሰቦች እርስ በርስ የሚጨባበጡበት ዋናው ምክንያት አንዱ ሌላውን ሊጎዳ የሚችል መሣሪያ እንዳልታጠቀ እጁን በማርገፍገፍ ለማጣራት ነበር። መጨባበጥን እንደ የኮይኮር ክርስቲያኖች ያስፋፋው ግን የለም። ኮይኮሮች በ17ኛው ክፍለ ዘመን የነበሩ የክርስቲያን ወንድማችነት ማኅበር አባላት ናቸው። ማንኛውም መልክ ያለው ጦርነትን ይጸየፋሉ። እነርሱ በሰው ልጆች እኩልነት ከማመናቸው ጋር ተያይዞ ይሆናል ከማጎንበስ ይልቅ መጨባበጥ እኩልነትን ይገልጣል ብለው ያስባሉ። እንዲያ በማመናቸው ነው ሰመል መጨባበጥን አጠናክረው ገፉበት። ክርስቲን ላጋር በቴክሳስ ኦስተን ዩኒቨርስቲ የሥነ ልቡና ሳይንስ ፕሮፌሰር ናት። መጨባበጥ የሰው ልጆች ትሁትነት የሚገለጥበት፤ ልብ ለልብ መናበባቸውን በጥቂቱም ቢሆን የሚንጸባረቅበት ጥበብ ነው። "የሰው ልጅ በጊዜ ርዝማኔ እንዴት ማኅበራዊ ፍጡር እየሆነ እንደመጣም ማሳያ ነው" ትላለች ፕሮፌሰር ክሪስቲን። በተለይም ሰው በንክኪ ራሱን የሚገልጽ እንሰሳ ስለመሆኑም ሌላ ማረጋገጫ ነው። መጨባበጥ የብዙ ዓለም ጥግ ረቂቅ ቋንቋ ነው። ለዚያም ነው አቁሙት ስንባል ግራ የገባን። ለዚያም ነው በእግር ተጨባበጡ ሲባል ፌዝ የሆነብን። ለዚያም ነው መሪዎች ስንት ጊዜ መመሪያ እየረሱ ሲጨባበጡ የነበረው። ለዚያም ነው በክርን ተጨባበጡ ሲባል "እረ ወዲያ!" ያልነው። ፕሮፌሰር ላጋር እንደምትለው "መጨባበጥ ብቻም ሳይሆን መነካካት ጠንካራው የስሜታችን ቋንቋ ነው፤ ልናጣው አንፈልግም።" በሳይንስ እኛን ይቀርባሉ የሚባሉት "አጎቶቻችን" እነ ቺምፓዚም ከእኛ የባሱ ናቸው። እጅግ ይተቃቀፋሉ። ሰላምታ ሲሰጣጡ አጠገባቸው ያለውን ዛፍም ቢሆን ያቅፉታል እንጂ የእግዜር ሰላምታን ቸል አይሉም። አንዳንዴ ከመተቃቀፍም አልፈው ይሳሳማሉ። በ1960ዎቹ ምርምሩን ይፋ ያደረገው አሜሪካዊው የሥነ ልቦና ሳይንስ ሊቅ ሃሪ ሀርሎ የዝንጀሮ ልጆች ለዕድገታቸው እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ መነካት አንደሆነ ደርሶበታል። መተሻሸት፣ መታቀፍ። ቀጭኔዎችም እንደኛው ናቸው። ሁለት ሜትር በሚረዝመው መቃ አንገታቸው አንዱ የአንደኛውን አንገት ይጨብጣል። መጨባበጥን ለምን አንተካውም? ይሄ መጨባበጥ የሚሉት ነገር ምንም ያህል ወሳኝ የስሜት መግለጫችን ቢሆንም አማራጭ አልባ አይደለም። ለምሳሌ ሁለት መዳፎቻችንን በማገናኘት እጃችንን ከደረታችን አስደግፈን ከወገብ ሸብረክ ብንልስ? ደስ አይልም? ሕንዶች "ናመስቴ" ይሉታል። ወይም ደግሞ እንደ ሳሞአ ደሴት ነዋሪዎች በዓይን ጥቅሻ ሰላም ብንባባልስ? እነዚህ ከአውስትራሊያ ማዶ በትንሽ ደሴት የሚኖሩ ሕዝቦች ሁነኛ ሰላምታ አሰጣጣቸው ሞቅ ካለ ፈገግታ ጋር የዐይን ሽፋሽፍታቸውን ከፍ ዝቅ በማድረግ ነው። ወይም ደግሞ በሙስሊም አገራት እንደሚዘወተረው አንድ እጅን ወደ ልብ አስጠግቶ በማሳየት በፈገግታ ብቻ ሰላም ብንባባልስ? ወይም ደግሞ እንደ ሃዋይ ሰዎች ሦስቱን የመሐል ጣቶች አጥፎ አውራ ጣትንና ትንሽ ጣትን ዘርግቶ እደውልልኻለው አይነት ምልክት በማሳየት ሰላም መባባልም ይቻላል። ዝርዝሩ ብዙ ነው። አንዳቸውም ግን እንደ መጨባበጥ አርኪ አይመስሉም። የባሕሪና ተያያዥ ጉዳዮች ሳይንቲስት ቫል ከርቲስ እንደምትለው ሰዎችን ስንጨብጥ የጥርጣሬ ግንብን እያፈረስን ነው። መጨባበጥን መርሳት እንችላለን? መጨባበጥ ከኮቪድ-19 ወዲህ ብቻ አይደለም ዘመቻ የተከፈተበት። በ1920ዎቹ በወጡ የጥናት ወረቀቶች መጨባበጥ ክፉ ተህዋሲያንን የምናዛምትበት ሁነኛው መንገድ እንደሆነ ተደርሶበት ነበር። አሜሪካኖች ታዲያ በዚያ ጊዜ መጨባበጥን ትተን እንደ ቻይናዎች የራሳችንን እጆች በማጨባበጥ ሰላምታን እንለዋወጥ የሚል ዘመቻ ተከፍቶ ነበር። በፈረንጆች 2015 በሎሳንጀለስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ አንድም ሰው እንዳይጨባበጥ መመሪያ አውጥቶ ነበር። ይህም የተደረገው በተለይ በጽኑ ሕሙማን ሕክምና ክፍል አካባቢ ነበር። ሆኖም ይህ መመሪያ መቆየት የቻለው ለ6 ወራት ብቻ ነበር። በነገራችሁ ላይ በብዙ የዓለም ክፍል የሚገኙ ሙስሊም ሴቶች በአመዛኙ የቅርብ ቤተሰብ ካልሆነ በስተቀር ወንድ ለመጨበጥ አይፈቅዱም። ይህም ከሐይማኖት መመሪያ ጋር የተያያዘ ምክንያት ያለው ነው። ይህ ሁሉ ሐይማኖታዊና ሳይንሳዊ ጫና የደረሰበት የመጨባበጥ ባሕል ሁሉን አሸንፎ በመላው ዓለም እጅግ ተመራጩ የሰላምታ መንገድ ሆኖ ለኮሮናቫይረስ ዘመን በቅቷል። ሰዎች ለምን ይጨባበጣሉ፤ ስሜታቸውስ ምን ይመስላል ሲሉ የጠየቁና መጨባበጥን ያጠኑ ሳይንቲስቶች፤ የሰው ልጆች አእምሮ ልክ አመርቂ ወሲባዊ ተራክቦ፣ ወይም ጥሩ ምግብ አልያም ጥሩ መጠጥ ሲያገኝ የሚሰማው ስሜት ዓይነት በመጨባበጥም ተመሳሳዩ የአእምሮ ክፍል እንደሚነቃቃ ደርሰውበታል። ወደፊት እንጨባበጣለን? አብዛኛዎቹ የአሜሪካ ግዛቶች በራቸውን እየከፈቱ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴያቸው እየተመለሱ ቢሆንም መጨባበጥ ግን ከዚህ በኋላ ተመልሶ ስለመምጣቱ እርግጠኛ መሆን አልተቻለም። ዶ/ር አንተኒ ፋውቺ የአሜሪካ ተቀዳሚው የኅብረተሰብ ጤና ጉዳዮች መሪ ናቸው። በአሜሪካ ምድር ከትራምፕ በላይ ይታመናሉ፤ ይሰማሉ። ስለ መጨባበጥ ጉዳይ በተጠየቁ ጊዜ እንዲህ ብለዋል። "እውነቱን ተናገር ካላችሁኝ ከዚህ በኋላ መቼም ቢሆን ወደ መጨበጥ የምንመለስ አይመስለኝም። ያ ዘመን ላይመለስ አልፏል።" ዶ/ር ፋውቺ መጨባበጡ ፈጽሞ እንዲቀር የሻቱት ኮሮናቫይረስን ለማቆም ብቻ ሳይሆን በአሜሪካ በርካታ ሰዎች በኢንፍሉዌንዛ ስለሚሞቱም ጭምር ነው። ኢንፍሉዌንዛው በዋናነት ከሰው ወደ ሰው እየተላለፈ ያለው ደግሞ በመጨባበጥ እንደሆነ በዘመናት ልምዳቸው ያውቁታል። ምናልባት በድኅረ-ኮሮና ሁለት ዓይነት ሕዝቦች ሊፈጠሩ ይችላሉ። የሚጨባበጡና የማይጨባበጡ። መነካካት የሚፈልጉና የማይፈልጉ። ይህ ደግሞ የሰው ልጅን በሥነ ልቦና የሚሰባብር ይሆናል። ዶ/ር ስትዋርት ዎልፍ በዚህ ረገድ የሰጡት አስተያየት በተለይ በኮቪድ-19 ዘመን ያደጉ ወጣቶች ምናልባት ያለመጨባበጡን ነገር ሊገፉበት እንደሚችሉ የሚጠቁም ነው። የተቀረው ሕዝብ ግን መነካካት ደሙ ውስጥ የተቀበረ ያህል የተላመደው ስለሆነ በዋዛ እንዲሁ እርግፍ አድርጎ ሊተው አይችልም። መነካካትን ምንም አይተካውም? ፕሮፌሰር ክሪስ ላጋር "የዚህ የኮቪድ-19 ዘመን ምጸት ምን መሰላችሁ?" ትልና ትጠይቃለች። "ምጸቱ አትነካኩ የተባልነው እጅግ መነካካት በምንሻበት ወቅት መሆኑ ነው።" ፕሮፌሰር ላጋር ለዚህ ሐሳቧ ማጠናከሪያ በሐዘን ላይ ያለንን ስሜት እንድንፈትሽ በመጋበዝ ነው። "እስኪ ሐዘን ላይ ባላችሁበት ጊዜ ማን ስሜታችሁን ይበልጥ እንደሚነካው አስታውሱ። ከልቡ እቅፍ የሚያደርገን ሰው ለልባችን በጣም የቀረበው ነው። ወይ ደግሞ አጠገባችን ሆኖ ትከሻችንን የሚያቅፈንን ወዳጃችን ስሜታችንን እጅጉኑ ይነካዋል። ይህ ስለእኛ የሚነግረን አንድ ነገር ቢኖር እኛ የሰው ልጆች በንክኪ የምንግባባ ዳሳሽ እንሳሳት መሆናችንን ነው።" ደሊያና ጋሪሺያ በኅብረተሰብ ጤና ዘርፍ የተሰማራች ስለሆነ በተቻለ መጠን ንክኪን ታስወግዳለች። ነገር ግን ልማድ ክፉ ነውና ሰው እቅፍ በማድረግ ሱስ የተጠመደች ናት። "85 ዓመት የሆነችውን እናቴን ሁልጊዜም ፍቅሬን የምገልጽላት በማቀፍ ነው። እቅፍ ሳደርጋት ነው ደስ የሚለኝ። እቅፍ አድርጋ ነው ያሳደገችኝ። አሁን አትነካኩ ሲባል ከእናቴ ጋር የነጠሉኝ ያህል ነው የተሰማኝ። አሁንም ቢሆን ስትጠጋኝ እቀፊያት እቀፊያት ይለኛል።" ለማንኛውም ከኮሮናቫይረስ በኋላ መጨባበጥ አይጠፋ ይሆናል፤ እጃችንን ስንዘረጋላቸው ግን የሚያሳፍሩን ሰዎች አይጠፉም።
news-52862114
https://www.bbc.com/amharic/news-52862114
የኮሮናቫይረስ፡ ለአሜሪካ ብቁው ፕሬዝዳንት ማን ነው? አንዱሩ ኮሞ ወይስ ዶናልድ ትራምፕ?
የቢቢሲው የሰሜን አሜሪካ አርታኢ ጆን ሶፔል በአሜሪካ የሟቾች ቁጥር 100 ሺህ ማለፉት ተንተርሶ ትራምፕና ኮሮናን፣ ኮሮናን የኒውዮርክ ገዢን አንዱሮ ኮሞን እንዲሁም የዚያችን አገር እጣ ፈንታ የታዘበበት ጽሑፍ እንዲህ ያስነብበናል።
ታላቋ አሜሪካ ባለፉት 44 ዓመታት የዓለም ፖሊስ ነበረች። ጦርነት ያልገጠመችበት አህጉር፣ ያልቧጠጠችው ተራራ፣ ቦምብ ያላዘነበችበት ዋሻ የለም። ቶራቦራ ድረስ ሰምጣ ገብታለች። አገር አፍርሳ አገር ሠርታለች። ለምሳሌ ኢራቅን። ለምሳሌ አፍጋኒስታንን። በአፍጋኒስታን ጦርነት ከ30 ሺህ በላይ የአገሬው ዜጎች ሞተዋል፤ የሞቱት የአሜሪካ ወታደሮች ግን 2 ሺህ ናቸው። በኢራቅ ለ10 ዓመታት ጦር አስቀምጣ ነበር። በዚያ ጦርነት የሞቱ ኢራቃዊያን 50 ሺህ ይጠጋሉ። በዚህ ሁሉ ዘመን አሜሪካ የሞተባት የወታደር ቁጥር 4 ሺህ 500 ብቻ ነው። ለ16 ዓመት በቆየው የቬትናም ጦርነት አሜሪካ 58 ሺህ ወታደር ነው የገበረችው። ለሦስት ዓመት በቆየው የኮሪያ ጦርነትና ኢትዮጵያም የሰላም አስከባሪ ወታደር በላከችበት ውጊያ ላይ አሜሪካ 36 ሺህ ወታደሮችን አጥታለች። ይህ ባለፉት 44 ዓመታት በጦርነት የጠፋውን ሕይወት ያህል በአራት ወራት ይጠፋል ማን አለ? ያውም በደቂቅ ረቂቅ ተህዋስ? ለዚህም ምክንያቱ የፕሬዝዳንቷ እንዝህላልነት ነው የሚሉ አሉ። ትራምፕና ኮሮናቫይረስ ትራምፕ ኮቪድ-19ን መጥፎ የቻይና ስጦታ ሲሉ ነው የሚጠሩት። ስማቸው ከዚህ ተህዋስ ጋር ባይነሳ ይመርጣሉ። ለዚህም ነው ለተህዋሱ መፈጠር ጥፋተኛዋ ቻይና ወይም የዓለም ጤና ድርጅት እንጂ እኔና አሜሪካ የለንበትም የሚሉት። ኮቪድ-19 ከመሪዎች ሁሉ እንደ ትራምፕ አፈር ከድሜ ያስጋጠው ፕሬዝዳንት አለ ለማለት ያስቸግራል። ለምሳሌ ከዚህ ወረርሽኝ በፊት በአሜሪካ የሥራ አጥ ቁጥር መሬት ነክቶ ነበር፤ በኮቪድ-19 ዘመን ግን ሰማይ ነካ። ምጣኔ ሀብቱ ተመንድጎ ነበር፤ በኮቪድ ዘመን ሽባ ሆነ። አሁን ከ30 ሚሊዮን አሜሪካዊያን በላይ ከመንግሥታቸው ድጎማ ጠባቂዎች ናቸው። ይህን የትራምፕን በዋይት ሐውስ ዘመን አንድ ስኬት (ሥራ ፈጣሪነትን) ወረርሽኙ ጠራርጎ ወስዶታል። ከዚህ በኋላ ዶናልድ ትራምፕ ሕዝባቸውን ታላቅ ፕሬዝዳንት እንደሆኑ ለማሳመን ነገሩ አልጋ በአልጋ አይሆንላቸውም። ምን ሊሉ ነው? ታላቅ አድርጊያችሁ ነበር ቫይረሱ ወሰደብኝ? ትራምፕ በዚህ ተህዋስ አሜሪካዊ አይሞትም፣ ቢሞትም ከ20 ወይ ከ30 ሺህ አይበልጥም ብለው ነበር። ቀጥለው ቁጥሩን ወደ 50 ሺህ አሳደጉት። ቀጥለው ወደ 60 እና 70 ሺህ። አሁን ግን መቶ ሺህን አልፏል። የተያዙት ዜጎች ደግሞ ወደ 2 ሚሊዮን እየተጠጉ ነው። ይህ ደግሞ ትምፕን እየገዘገዘ የሚጥል እውነታ ነው። የሚገርመው በዚህ ሁሉ ውጥንቅጥ ውስጥ ትራምፕ ቀን ተሌት የሚያወሩት እርሳቸው ቶሎ እርምጃ ባይወስዱ ኖሮ 2 ሚሊዮን አሜሪካዊያን ሊሞቱ ይችሉ እንደነበረ ነው። ከሞቱባቸው ዜጎቻቸው ይልቅ በእርሳቸው አመራር ያዳኗቸውን ሰዎች እንዲመለከት ሕዝባቸውን ይወተውቱታል። ሌት ተቀን። ትራምፕ አንድ በበጎ የሚነሳላቸው ነገር በጥር ወር መጨረሻ አሜሪካዊ ያልሆኑ ከቻይና ወደ አሜሪካ ምድር እንዳይገቡ ማድረጋቸው ነው። ያ እርምጃ ብዙ አማካሪዎቻቸውን ቸል ብለው ያደረጉት በመሆኑ ይሞገሱበታል። በእርግጥ ትራምፕ ያን ጊዜ የውጭ ዜጎችን ብቻ ሳይሆን የገዛ ዜጎቻቸውን ጭምር ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ማድረግ ነበረባቸው ብለው የሚተቿቸው አሉ። እርሳቸው ግን "እንዴት ዜጎችን ወደ አገራችሁ መግባት አትችሉም" እላለሁ ሲሉ ይከራከራሉ። ትራምፕ ይህን እርምጃ መውሰዳቸው ቢያስመሰግናቸውም በየካቲት ወር ላይ ፈዘው መቀመጣቸው ከሁሉ በላይ ያስተቻቸዋል። የካቲት ወር በአሜሪካ የመመርመሪያ መሣሪያዎች ቢሰሩበት፣ ቬንትሌተር ቢመረትበት ሁሉን አቀፍ ርብርብ ቢካሄድበት ኖሮ አሁን ያለቀው ሕዝብ ግማሹ እንኳ አያልቅም ነበር ይላሉ የማኅበረሰብ ጤና ባለሞያዎች። አንዲት ጋዜጠኛ ትራምፕ ስለሞቱት ሳይሆን ስለዳኑት እያወሩ ሲያስቸግሯት "በየካቲት ወር የት ነበሩ? ምን ሲሰሩ ነበር?" ብላ አፋጠጠቻቸው። እርሳቸው ወደ ጥር ወር መለሷት "በጥር መጨረሻ ድንበር ባልዘጋ ኖሮ…" በማለት። "እኔ እየጠየክዎ ያለሁት ስለ የካቲት ነው…" አለቻቸው። ሰውየው ተመልሰው "ጥር ላይ ማንም ሳይደግፈኝ፣ ዶ/ር ፋውቺ እንኳ እየተቃወመኝ ድንበር እንዲዘጋ የወሰንኩ ድንቅ ሰው ነኝ" ይላሉ። "የተከበሩ ፕሬዝዳንት በድጋሚ እጠይቅዎታለሁ፤ በየካቲት ወር ምን ሰሩ?" "ምን ያልሰራሁት አለ? እንቅልፋሙ ጆ ባይደን ምን ሲሰራ ነበር?…" "እኔ ስለ ጆ ባይደን አልጠየክዎትም ክቡር ፕሬዝዳንት…" "አንቺ ፌክ ነሽ፤ ከፌክ ኒውስ ነሽ! ጨርሰናል!" ዶናልድ ትራምፕ ምን ብለው ነበር? እርግጥ ነው ጋዜጠኛዋ ያነሳችው ጥያቄ መሠረታዊ ነበር። በዚያ ወር ብዙ ሊሠራ ሲችል አልተሰራም። መመርመሪያ መሣሪያ አልተዘጋጀም፤ ቬንትሌተር ማምረት አልተጀመረም፣ መሠረታዊ የሕክምና መሣሪያዎች አልተዘጋጁም፣ የዓለም ጤና ደኅንነት ክፍልን ትራምፕ አፍርሰውት ነበር፣ ለአንዲህ ዓይነት ጊዜ ይጠቅም የነበረ ፈንድ ወደ ሌላ ተዘዋውሯል። እነዚህ ናቸው የሚያስተቿቸው። በአነዚህ ወራት ዶናልድ ትራምፕ ምን ሲናገሩ እንደነበር እናስታውስ… ጥር 22፡ "ከቻይና ቫይረስ ተሸክሞ የገባው አንድ ሰው ነው። ተቆጣጥረነዋል። ሁሉም ነገር ሰላም ነው።" የካቲት 2፡ "ሁሉም ነገር ጥርቅም ተደርጎ ተዘግቷል። ቫይረሱ በየት አድርጎ ይገባል?" የካቲት 10፡ "ያው እንደምታውቁት በሚያዚያ ሙቀት ስለሚሆን ቫይረሱ ብን ብሎ ነው የሚጠፋው፤ ልክ እንደ ተአምር። ይህ እውነት ይሆናል ብዬ እጠብቃለሁ። ከቻይናው አቻዬ ሺ ዢን ፒንግ ጋር በስልክ አውርቻለሁ፤ ጥሩ እየሰራ ነው። ሁሉም ነገር በመልካም ሁኔታ እየሄደ ነው።" የካቲት 11፡ "በአገራችን 12 ሰዎች ብቻ ናቸው በቫይረሱ የተያዙት፤ እነሱም እያገገሙ ናቸው፤ የሚያሳስብ ነገር የለም። ኧረ እንዲያውም 12ትም አይሞሉም!" የካቲት 24፡ "ኮሮናቫይረስን በአሜሪካ በቁጥጥር ሥር አውለነዋል። ከሚመለከታቸው ጋር እየተነጋገርን ነው፡፡ ሲዲሲ እና የዓለም ጤና ድርጅት እጅና ጓንት ሆነው እየሰሩ ነው። የአክስዮን ገበያው ሞቅ ደመቅ ብሏል።" የካቲት 26፡ "አሜሪካንን በሚያህል ትልቅ አገር 15 ታማሚዎች ብቻ ሲኖሩና እነሱም በቀጣይ ቀናት ሲያገግሙ ቁጥሩ ወደ ዜሮ ይወርዳል። እኛ እንዲህ እጹብ ድንቅ ሥራ የምንሠራ ሰዎች ነን።" መጋቢት ወር መጣ። ሁሉም ነገር ወደ ሐዘን ተቀየረ።ሰዎች በቫይረሱ ይያዛሉ፤ ከማን እንደተያዙ ግን አያውቁም። ዜጎች ለሆስፒታሎች ድረሱልን አሉ። ሆስፒታሎች ለመንግሥት ድረስልን አሉ። የጭምብል ያለህ፣ የቬንትሌተር ያለህ፣ የጓንት ያለህ…! ሞት ከነአጀቡ በዋሺንግተን አድርጎ ኒውዮርክ ገባ። በኤልሜርሀስት ሆስፒታል ሬሳ ከመብዛቱ የተነሳ የሬሳ ፍሪጅ ያላቸው የጭነት መኪናዎች ደጅ ላይ በተጠንቀቅ መቆም ጀመሩ። ኒው ዮርክ ውስጥ ሬሳ ማስቀመጫ ቦታ ጠፍቶ ፍሪጅ ያላቸው የጭነት መኪኖች ጥቅም ላይ ውለዋል አሜሪካዊያን መቀበርያ አጥተው የጅምላ መቃብር ተቆፈረላቸው። ነርሶች ተገቢ የሕክምና እቃ የሚያቀርብላቸው አጥተው ጽኑ ሕሙማን ክፍል የሚገቡት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ፌስታል ላስቲክ ለብሰው ነበር። በታላቋ አሜሪካ ይህ ይሆናል ያለ አልነበረም። በሕዝብ አሰፋፈሯ ጥቅጥቅ እጭቅ ያለች ናት። ትራምፕ ያደጉባት ኒውዮርክ፤ የዓለም ደማቋ ከተማ ኒውዮርክ፣ የዓለም ሀብታሟ ከተማ ኒውዮርክ ድንገት የሞት አውድማ ሆነች። መጀመሪያ ሟቾች ስም ነበራቸው፤ ከዚያ ቁጥር ሆኑ። መጀመርያ የሟቾች ቁጥር ያስደነግጥ ነበር፤ ቀጥሎ ቁጥር ቁጥርን እንጂ ሰውን መወከል አቆመ። ስሜት መስጠት ተወ። ሺህዎች ረገፉ። በዚህ እጅግ አስከፊ ወቅት አንድ ጀግና ብቅ አሉ። የኒው ዮርክ ገዢ አንድሩ ኩሞ። ትራምፕ በኒው ዮርክ ኪዊንስ ውስጥ አድገው በማንሃታን ነግደው የናጠጠ ሀብታም ሆነው ይሆናል። እውነተኛ የኒው ዮርክ ልጅ መሆናቸውን ያስመሰከሩት ግን አንድሩ ኩሞ ናቸው። ኩሞ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ሟቾችን አፈር ምሰው ቀብረው በሬሳቸው ላይ የእርሳቸውን ስኬት፣ የእርሳቸውን ዝና አይዘምሩም። ማዘን ሲኖርባቸው ያዝናሉ፤ ማልቀስ ካለባቸው ያለቅሳሉ፤ ሲቆጡም ተቆጡ ነው። በአጭሩ ሰው ናቸው ይሏቸዋል። ከሕዝብ ጋር ናቸው። ኒው ዮርካዊያን በወረርሽኝ እየወደቁ በመሀሉ በእርሳቸው ፍቅር ትንሽ ትንሽ ወደቁ። የኒው ዮርክ ገዢ አንድሩ ኩሞ ልክ እንደ ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ዲጂታል ሰሌዳቸው ላይ ሰንጠረዥ እየዘረጉ አስተዳደራቸው ምን እየሰራ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን፤ ምን እንዳልሰራ፣ የትኛው መድኃኒት፣ የትኛው የሕክምና መሣሪያ እንደጎደለው፤ ነዋሪዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው/እንደሌለባቸው ይተነትናሉ። የእርሳቸውን የቲቪ መግለጫ ሰዎች እንደ ተከታታይ ድራማ ይመለከቱታል። ይህ ትራምፕን አስኮረፈ። ትራምፕም የእራሳቸውን "ሾው" ጀመሩ። ልዩነቱ እርሳቸው ስለእራሳቸው ብቻ ያወራሉ። ኩሞ ግን ስለ ኒው ዮርካዊያን ያወራል። ዶናልድ የሚናገሩት ሁሉ ይተናነቃል። አንድሩ ኩሞ የሚናገሩት ግን ጠብ አይልም። ሁለቱም በኒው ዮርክ የኩዊንስ ሰፈር ልጆች ናቸው። ሆኖም በባህሪም በሥራም አልተገናኝቶም ናቸው። ኩሞ ስለራሳቸው ቁጥብ ናቸው፤ ጊዜያቸውን በአልባሌ ዝባዝንኬ አያጠፉም። ሁልጊዜም እጥር ምጥን ያለና ወደ መሠረታዊ ጉዳይ ያተኮረ መግለጫን ይመርጣሉ። ኩሞ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር አንድ ሁለት ተባብለው ያውቃሉ። ያ ጸብ ግን ኩሞ ትራምፕን ማመሰገን ባለባቸው ጊዜ እንዳያመሰግኗቸው አላደረገም። ትራምፕ በኩሞ መደነቅን እጅግ ይወዳሉ። "ኩሞም አድንቆናል" ብለው በቪዲዮ አቀናብረው፣ ጋዜጠኛ ጠርተው እዩልኝ ብለው ያውቃሉ። አንድሩ ኩሞ የኮሮናቫይረስ ምርመራ ሲደረግላቸው የኒው ዮርኩ ገዢ የሰው ልብ ላይ የገቡበት ጥልቀት አስደናቂ ነው። ከልጅነት እስከ እውቀት ዲሞክራት ሆነው የኖሩት አንድሩ ኩሞ በሪፐብሊካኖች ከዶናልድ ትራምፕ ይልቅ መወደዳቸው የአደባባይ ሚስጢር ነው። ዲሞክራቶችማ ውስጥ ውስጡን ምነው በቀጣይ ምርጫ ጆ ባይደን ቀርቶብን አንድሩ ኩሞ በወከለን ይላሉ። የሚደንቀው የአንድሮ ኩሞ የ45 ደቂቃ ዕለታዊ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደ ጎበዝ የዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር ጥፍጥ ያለች ናት። በተመሳሳይ ዕለታዊ መግለጫ የሚሰጡት ዶናልድ ትራምፕ 'ሲነሽጣቸው' እስከ 2 ሰዓትና ከዚያ በላይ ካሜራ ደቅነው ሊያወሩ ይችላሉ። ሁሉም ጋዜጣዊ መግለጫቸው ሲጨመቅ ግን ከሚከተለው ጭብጥ አያልፍም። • እኔ ብዙ ሚሊዮን አሜሪካዊያንን ከሞት ባልታደግ ኖሮ ይቺ አገር አብቅቶላት ነበር • እኔ አሜሪካንን በኢኮኖሚ በታሪኳ አይታው የማታውቀው ከፍታ ላይ አስቀምጫታለሁ • እንቅልፋሙ ጆ ባይደን እኔን ማሸነፍ አይችልም • እኔ አሜሪካንን በቬንትሌተር እራሷን እንድትችል አድርጊያታለሁ • ናንሲ ፒሎሲ አስቀያሚ ሴት ናት • ብዙ ርዕሳነ መንግሥታት እየደወሉ ያደንቁኛል • ሲኤንኤን ሐሰተኛ ሚዲያ ነው • ዲሞክራቶች በእኔ ላይ እያሴሩ ነው • አገረ አሜሪካንን ዘግተን ልንቀመጥ አንችልም፤ በራችሁን ክፈቱ ዶናልድ ትራምፕ ይህ ተህዋስ ድብርት ውስጥ እንደከተታቸው ግልጽ ነው። ቢያንስ ሁለት እጅግ የሚወዱትን ነገር አሳጥቷቸዋል። አንዱ የጎልፍ ጨዋታ ነው። ሌላው ደግሞ የደጋፊዎቻቸው የፖለቲካ ስብሰባ ጩኸት። ትራምፕ በደጋፊዎቻቸው ተከበው ዲሞክራቶች ላይ መሳለቅ ነፍሳቸው ነው። ደማቸው የሚሞቀው ስማቸው እየተጠራ በደጋፊዎቻቸው ሲዘመርላቸው ነው ይሏቸዋል። ይህ ክፉ ደዌ ከመጣ ወዲህ ግን በየቁኑ ከፊታቸው የሚደቀኑት ደጋፊዎቻቸው ሳይሆኑ እንደ ደመኛ የሚያይዋቸው ጋዜጠኞችና ካሜራዎቻቸው ናቸው። ስለዚህ በየጊዜው ድብርት ተጭኗቸው ነው መግለጫ የሚሰጡት። የአሜሪካ ታማሚ ሕዝብ የኦክሲጂን ቬንትሌተር ይሻል፤ ትራምፕ ለመተንፈስ የደጋፊ ጭብጨባና ጩኸት ይሻሉ። ይህ ክፉ ተህዋስ ይህንን አሳጥቷቸዋል። ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ከፕሬዝዳንት ትራም ጋር የትራምፕ ምክትል "ብልጡ" ማይክ ፔንስ ሌላው በዚህ ወረርሽኝ ቁልፉ ተዋናይ ምክትል ፕሬዝዳንት ማይክ ፔንስ ናቸው። እሳቸው የማይመሩት ግብረ ኃይል የለም። በትራምፕ የሚዋቀር ነገር በሙሉ በበላይነት ፔንስ ይመሩታል። በትራምፕና በተቋማት መሀል ያሉት ድልድይ ፔንስ ናቸው፤ በትራምፕና በ50ዎቹ ግዛት ገዢዎች መሀል ያሉት ድልድይ እሳቸው ናቸው። ቆፍጣና ሰው ናቸው። ምንም ነገር ቢረሱ ሁለት ነገር አይረሱም። አንዱ ትራምፕን ማድነቅ ነው። ለሁሉም ስኬቶች የአለቃቸውን የትራምፕን ስም ይጠራሉ። ውድቀት ካለም የእሳቸው ጥፋት እንጂ የአለቃቸው እንዳልሆነ ይናገራሉ። ማይክ ፔንስ ሌላ የማይረሱት ነገር ለቅሶ መድረስን ነው። ንግግሩን በትራምፕ ስም ከቀደሱ በኋላ ሕይወታቸው ላጡ አሜሪካዊያን ሐዘናቸውን መግለጽ በፍጹም አይረሱም። በዚህ ረገድ አለቃቸው ትራምፕ ደካማ ናቸው። ለፖለቲካ ሲሉ እንኳ ማዘን አይችሉም። ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ከፕሬዝዳንት ትራም ጋር ክቡር ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ሌላው የኮቪድ-19 አለቃ ዶ/ር አንቶኒ ፋውቺ ናቸው። የጤና ግብረ ኃሉን በሞያ የሚመሩ ናቸው። የእርሳቸው ሚና ለትራምፕ ሳይንሳዊ ድጋፍ መስጠት ነው። ሆኖም አልተሳካላቸውም። እርሳቸው የገነቡትን ትራምፕ ያፈርሱታል። የአሜሪካ ሕዝብ ከዶናልድ ትራምፕ ይልቅ ዶ/ር ፋውቺ የሚሉትን ቢሰማ ይመርጣል። ሆኖም ትራምፕ የሚቃረናቸውን ሰው ቀይ ካርድ ነው የሚሰጡት። ለዶ/ር ፋውቺም ተደጋጋሚ ቢጫ ካርድ አሳይተዋቸዋል። ዶናልድ ትራምፕ እንደ ቸርችል የጦር ጊዜ ጀግና መሪ ለመሆን ይሞክራሉ። የቢቢሲ ዘጋቢ ጆን ሶፔል እንደሚለው ግነ "በአብዛኛዎቹ ጋዜጣዊ መግለጫዎቻቸው ላይ ተገኝቻለው። ትራምፕ በጭራሽ የጦርነት ጊዜ መሪ ተክለስብዕና የላቸውም" ይላል። ከመግለጫዎቹ ሁሉ የከፋው ለ2 ሰዓት የቆየው ነው። 45 ደቂቃ የምርጫ ቅስቀሳ አደረጉ። ለሌለ ብዙ ደቂቃ እንዴት ታላቅ መሪ እንደሆኑ ደሰኮሩ፤ ለሌላ ደቂቃዎች የአሜሪካ ሚዲያ እርሳቸው ላይ እንደሚጨክን ተናገሩ፤ ለሌላ ደቂቃ በታሪክ ስኬታማው መሪ እርሳቸው እንደሆኑ ለማሳመን ሞከሩ። በዚህ ዘለግ ባለ መግለጫ ለአንድ ደቂቃ እንኳ ስለሚሞተው ሕዝባቸው ግድ ሰጥቷቸው አንዲት የሐዘን ቃል አልወጣቸውም። ያም ሆኖ ትራምፕ ከአገር መሪነት ይልቅ የመድረክ ሰው ተደርገው ስለሚታሰቡ ይሆናል ሕዝብ አይጨክንባቸውም፤ ሚዲያውም ለፌዝ ካልሆነ አያመርባቸው ይሆናል። እርሳቸው ግን ይናገራሉ። እንደ አሜሪካ አንድም አገር የጅምላ ምርመራ አላደረገም ይላሉ። "It's not even close" (ጭራሽ ከእኛ ጫፍ የሚደርስም የለም) በጣም የሚወዷት ሀረግ ናት። እርሳቸው ግን ይናገራሉ፤ አንድም አገር እንደኛ ቬንትሌተር ያለው የለም ይላሉ። ሁሉም አገር ያለው ቬንትሌተር ቢደመር የእኛን አያህልም ይላሉ፤ "not even close" የሚወዷት ሀረግ ናት። እርሳቸው ግን ይናገራሉ፤ " የሌሎች አገር መሪዎች በእኛ ይቀናሉ፤ ቬንትሌተር አውሰን ይሉኛል፤ አንዳቸውም የእኛን ያህል አላመረቱም።" "not even close." ጀርመኖች ናቸው በአሜሪካ የሚቀኑት? ደቡብ ኮሪያ ትሆን? ነው ታይዋንና ኒውዚላንድ? ትራምፕ እውነታቸውን ይሆናል፤ አሜሪካ አንደኛ ናት! በሟቾች ቁጥርም የሚያህላት የለም። "Not even close."
news-50980153
https://www.bbc.com/amharic/news-50980153
ኢራቃዊያን የጀነራሉን አስክሬን ሲሸኙ ''ሞት ለአሜሪካ'' ሲሉ ተደምጠዋል
በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ የተገደሉት ጀነራል ቃሲም ሱሊይማኒ አስክሬን ከኢራቅ ወደ ኢራን እየተሸኘ ነው።
በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃዊያን የጀነራሉን አስክሬን ለመሸኘት አደባባይ ተገኝተዋል የጀነራሉን አስክሬን ለመሸኘት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃዊያን አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ ''ሞት ለአሜሪካ'' ሲሉም ድምጻቸውን አሰምተዋል። የጀነራሉ አስክሬን ወደ ኢራን ከተሸኘ በኋላ በተወለዱበት ከተማ ገብዓተ መሬታቸው የፊታችን ማክሰኞ ይፈጸማል ተብሏል። ኢራቃዊያኑ አስክሬኑን ለመሸኘት ከንጋት ጀምሮ ነበር ወደ አደባባይ መትመም የጀመሩት። ብዙዎቹም የኢራቅን ሰንደቅ ዓላማ፣ የጀነራል ሱሊማኒን እና የኢራናዊውን የሃይማኖት መሪ አያቶላህ አሊ ካህሜኒን ምስል ይዘው ነበር። የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ፤ ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ የተገደለው ጦርነት ለማስቆም እንጂ ለማስጀመር አይደለም ማለታቸው ይታወሳል። በኢራን እና በመካከለኛው ምስራቅ ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪ የነበሩት ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በፕሬዝደንት ትራምፕ ትዕዛዝ እንዲገደሉ ከተደረገ በኋላ፤ ትራምፕ 'ሦስተኛውን የዓለም ጦርነት አስጀመሩ' ያሉ በርካቶች ነበሩ። ፕሬዝደንት ትራምፕ ግን የሱሊማኒ ''የዓመታት የሽብር አገዛዝ አብቅቶለታል" ብለዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ከፍሎሪዳ ግዛት ሆነው በሰጡት መግለጫ፤ "የአሜሪካ ወታደሮች በቅንጅት ባካሄደው ኦፕሬሽን፤ ቁጥር አንድ የዓለማችንን አሸባሪ ገድለዋል" ብለዋል። "ሱሊማኒ በማንኛውም ሰዓት ሊቃጣ የሚችል የሽብር ሴራ በአሜሪካ ዲፕሎማቶች እና የጦር መኮንኖች ላይ ሲያሴር ነበር። ይህንን ሲፈጽም ያዝነው፤ አስወገድነው" ሲሉም ተደምጠዋል። በሌላ ዜና ጀነራሉ ከተገደሉ ከ24 ሰዓታት በኋላ አሜሪካ ዛሬ ጠዋት ሌላ የአየር ጥቃት በኢራቅ ፈጽማ እንደነበር የኢራቅ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። ምንም እንኳን ይህ ዜና በአሜሪካ በኩል ባይረጋገጥም ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያው ቅዳሜ ንጋት ላይ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ተጨማሪ 6 ሰዎች ተገድለዋል ብሏል። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ፤ የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ኩድስ ኃይል አዛዥ በትራምፕ ትዕዛዝ ከተገደሉ በኋላ በቀጠና አሜሪካ ጠል እንቅስቃሴዎች ተንሰራፍተዋል። ይህንን ተከትሎም የትራምፕ አስተዳደር በቀጠናው ለሚገኙ ዲፕሎማቶች እና አጋሮቿ ደህንነት ሲባል ተጨማሪ 3000 ወታደሮች ወደ መካከለኛው ምስራቅ እንደሚልኩ አስታውቀዋል። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ውስጥ ቁንጮ ከሚባሉ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነበሩ። ፔንታጎን (የአሜሪካ የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤት) ጀነራል ሱሊማኒ "በፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ" ተገድለዋል ሲል ማረጋገጫ ሰጥቷል። ጀነራሉ የተገደሉት አሜሪካ በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ አየር ማረፊያ ላይ በወሰደችው የጦር እርምጃ መሆኑ ታውቋል። ጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ የኢራን ምላሽ ሃይማኖታዊ መሪው አያቶላ አሊ ካሃሜኒ በአሜሪካ ላይ አጸፋዊ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ዝተዋል። የጀነራሉ መገደል በአሜሪካ እና ኢራን መካከል ያለውን ውጥረት ከፍ አድርጎታል። የኢራን የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጃቪድ ዛሪፍ በትዊተር ገጻቸው ላይ አይኤስ፣ አል ኑስራህ፣ አል-ቃይዳ የመሳሰሉ የሽብር ቡድኖችን ሲዋጋ የነበረውን ጀነራል የመግደል እርምጃ እጅግ አደገኛ እና የሞኝ ውሳኔ ነው ብለውታል። አሜሪካ ሙሉ ኃላፊነቱን ትወስዳለችም ተብሏል። አሜሪካ ዜጎች በፍጥነት ኢራቅን ለቀው እንዲወጡ አሳሰበች ጀነራሉ በትራምፕ ትዕዛዝ ከተገደሉ በኋላ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል ውጥረት አይሏል። በባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ፤ ዜጎች በተቻላቸው ፍጥነት ከኢራቅ ለቀው እንዲወጡ አሳስቧል። ኤምባሲው በቅርቡ በተቃዋሚዎች የደረሰበትን ጥቃት ተከትሎ ምንም አይነት አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውሶ፤ የአሜሪካ ዜጎች ወደ ኤምባሲው በፍጹም እንዳይቀርቡ አሳስቧል። ከተቻላቸው በአየር ካልሆነ ደግሞ ወደ ጎረቤት ሃገራት በየብስ ከኢራቅ እንዲወጡ አስጠንቅቋል። ኢራቅ፤ በኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ጆርዳን፣ ሶሪያ እና ቱርክ ትዋሰናለች። ከኢራቅ በአየር መውጣት የማይችሉ አሜሪካዊያን፤ በየብስ ሳዑዲ ሁነኛ አማራጫቸው እንደሆነች ይታመናል። የእስራኤል ጦር በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል የጀነራሉን ግድያ ተከትሎ የእስራኤል ጦር በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል። ኢራን የጀነራሏን ግድያ ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ የአሜሪካ አጋር በሆነችው እስራኤል ላይ በሌሎች ቡድኖች አማካኝነት ጥቃት ልትሰነዝር ትችላለች የሚል ግምት አለ። በሂዝቦላ ወይም ሃማስ አማካኝነት አልያም ደግሞ ኢስላሚክ ጅሃድ በተሰኘው ቡድን በጋዛ በኩል እስራኤል ላይ የአጸፋ እርምጃ ሊወሰድ ይችላል የሚሉት ግምቶች ከፍ ያሉ ናቸው። የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር እና መከላከያ ሚንስትሮች እስራኤል በተጠንቀቅ ላይ እንዳለች ይፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ቤይናሚን ኔታኒያሁ በግሪክ የነበራቸውን ጉብኝት አቋርጠው ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸውም ተነግሯል። ጀነራል ሱሊማኒ በኢራን መንግሥት ውስጥ ሁለተኛው ተጽእኖ ፈጣሪ ሰው ነበሩ። እርሳቸው የሚመሩት ኃይል ተጠሪነቱ በቀጥታ ለሃይማኖታዊ መሪው አያቶላ አሊ ካሃሜኒ ሲሆን ጀነራሉ በኢራናውያን ዘንድ እንደ ጀግና ነው የሚታዩት። አያቶላ የጀነራሉን ግድያ ተከትሎ በኢራን የሦስት ቀናት ብሔራዊ ሃዘን አውጀዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት አስተያየት ሰሳይሰጡ የአሜሪካን ባንዲራን በትዊተር ገጻቸው ላይ ለጥፈው ቆይተው ነበር። የተፈጠረው ምን ነበር? ፔንታጎን ባወጣው የጽሑፍ መግለጫ "በፕሬዝደንቱ ትዕዛዝ፤ ከሃገር ውጪ የሚኖሩ አሜሪካዊያንን ደህንነት ለመጠበቅ የአሜሪካ ጦር በወሰደው የመከላከል እርምጃ ቃሲም ሶሌኢማኒን ገድሏል" ብሏል። "ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው የወደፊት የኢራንን ጥቃት ለማስወገድ ነው። አሜሪካ ዜጎቿን እና ጥቅሞቿን ለማስጠበቅ በማንኛውም አካል ላይ፤ በየትኛውም የዓለማችን ሥፍራ ቢገኙ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዷን ትቀጥላለች" ይላል የፔንታጎን መግለጫ። ፔንታጎን ከዚህ በተጨማሪም፤ ጀነራሉ በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን ለመግደል ሲያሴር ነበር ብሏል። አሜሪካ ይህን ጥቃት የሰነዘረችው አደባባይ በወጡ ሰልፈኞች ባግዳድ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ላይ ጥቃት ከተሰነዘረ በኋላ ነበር። በወቅቱ የኤምባሲው አሜሪካዊያን ጠባቂዎች ከሰልፈኞቹ ጋር ተጋጭተው ነበር። ፔንታጎን እንደሚለው ከሆነ ጀነራል ሱሊማኒ በኤምባሲው ላይ ጥቃቱ እንዲቃጣ ፍቃድ ሰጥተዋል። ባግዳድ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አሜሪካ በአየር ማረፊያው በወሰደችው ጥቃት ከጀነራሉ በተጨማሪ የኢራቅ ሚሊሻ መሪ አቡ ማሃዲ አል-ሙሃንዲስ እንደተገደሉ የኢራን አብዮት ጥበቃ አስታውቋል። የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ፤ ከፍተኛ የጦር ኃላፊዎቹ የተገደሉት የአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች በወሰዱት እርምጃ ነው ብሏል። የጀነራሉን ግድያ ተከትሎ የተሰጡ አስተያየቶች፡ አሜሪካ የጀነራል ሱሊማኒ ግድያ በአሜሪካ ሁለት ጎራዎችን ፈጥሯል። የፕሬዝደንት ትራምፕ የፖለቲካ አጋር የሆኑት ሪፐብሊካኖች 'ሱሊማኒ የአሜሪካ ጠላት ነው' በማለት ግድያውን ደግፈዋል። የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፔዮ፤ ኢራቃዊያን የጀነራሉን ግድያ ተከትሎ ደስታቸውን ሲገልጹ የሚያሳይ ምስል በትዊተር ገጻቸው ላይ አጋርተዋል። በሌላ በኩል ዲሞክራቶች የሱሊማኒን ግድያ አጥብቀው ኮንነዋል። ፕሬዝደንት ትራምፕ ጀነራሉ እንዲገደሉ ትዕዛዝ ከመስጠታቸው በፊት ከአሜሪካ ኮንግረስ ፍቃድ መጠየቅ ነበረባቸው እያሉ ነው። ኢራን ኢራናውያን በጀነራል ሱሊማኒ ግድያ ብስጭታቸውን እየገለጹ ነው። የኢራን ባለሥልጣናት በበኩላቸው ይህ የጦርነት ትንኮሳ ነው ብለውታል። ሄዝቦላ ሄዝቦላ የሺዓ ሙስሊም ፓርቲ እና የሚሊሻ ቡድን ነው። ከኢራን የፍይናንስ፣ የቁስ እና የሥልጠና ድጋፎችን የሚያገኘው ሄዝቦላ መቀመጫውን በሌባኖስ መዲና ቤይሩት አድርጓል። ሳይድ ሃሳን ነስረላህ የሄዝቦላ መሪ ሲሆኑ ጀነራል ሱሊማኒ ቢገደሉም የእርሳቸውን ፈለግ እንደሚከተሉ ገልጸዋል። አሜሪካ ይህን 'ትልቅ ወንጀል' ፈጽማ የፈለገችውን ማሳካት አትችልም ማለታቸውን እና ለግድያው አሜሪካ ሙሉ ኃላፊነቱን እንደምትወስድ ተናግረዋል። ሶሪያ የሶሪያ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር የአሜሪካን እርምጃ ኮንኗል። የሶሪያ ብሔራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሳና፤ የውጪ ጉዳይ ሚንስትርን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሶሪያ ለኢራቅ አለመረጋጋት አሜሪካ ቀጥተኛ ተሳትፎ እንዳላት የሚያረጋግጥ ነው ብላለች። ቃሲም ሱሊማኒ ማን ነበሩ? ከእአአ 1998 ጀምሮ ሜጀር ጀነራል ሱሊማኒ የኢራን ኩድስ ኃይል ሲመሩ ቆይተዋል። ይህ ኃይል ከሃገር ውጪ የሚፈጸሙ ሚስጥራዊ ኦፕሬሽኖችን የሚያከናውን ነው። ጀነራሉ በኢራቅ ውስጥ አይኤስ እና አል-ቃይዳን በመዋጋ ትልቅ አስተዋጽኦ ነበራቸው። ከዚህ በተጨማሪም፤ እኚህ የሽብር ቡድኖች እግራቸውን በኢራን እንዳይተክሉ ተከታትለው ድባቅ የመቷቸው ጀነራል ሱሌይማኒ ነበሩ ተብሏል። ጀነራሉ የሚመሩት ኃይል በሶሪያ ግጭት ውስጥ ተሳትፎ እንዳለው አምኗል። ለፕሬዝደንት በሽር አል-አሳድ ታማኝ ለሆኑ ወታደሮች የጦር ምክር ይሰጣል። እንዲሁም ለበሽር አል-አሳድ ታማኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ሺዓ ሙስሊሞችን አስታጥቋል። በኢራቅ ደግሞ አይኤስን እየታገሉ ለሚገኙ ለሺዓ ሙስሊም ሚሊሻዎች ድጋፍ ያደርጋል። በመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት የተከሰቱት ግጭቶች ጀነራሉ ኢራን ውስጥ እጅግ ዝነኛ ሰው እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። ጀነራል ሱሊማኒ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት የኢራን ከፍተኛ የጦር ሽልማት ተቀብለዋል። አሜሪካ በበኩሏ ጀነራሉ የሚመሩት የኩድስ ኃይል በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ አሜሪካን በጠላትነት በመፈረጅ በሽብር መናጥ ለሚፈልጉ ኃይሎች ፈንድ፣ ሥልጠና እና የጦር መሳሪያን ጨምሮ የቁስ ድጋፍ ያደርጋል ስትል ትወነጅላለች። አሜሪካ እንደምትለው ከሆነ ይህ የኩድስ ኃይል ድጋፍ ከሚያደርግላቸው ኃይሎች መካከል፤ የሌባኖሱ ሄዝቦላ እንዲሁም የፍልስጤሙ እስላማዊ ጅሃድ ተጠቃሽ ናቸው። የቀድሞ የሲአይኤ አለቃ የአሁኑ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፖምፔዮ የኢራንን አብዮታዊ ጥበቃ እና ኩድስ ኃይሉን "የሽብር ቡድን" ሲሉ ከወራት በፊት ፈርጀውት ነበር።
news-47227417
https://www.bbc.com/amharic/news-47227417
"የተገፋሁት በራያነቴ ነው" አቶ ዛዲግ አብርሃ
በሚኒስትር ዲኤታነት እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት የነበሩት አቶ ዛዲግ አብርሃ በቅርቡ ከህወሃት አባልነታቸው በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቃቸውን አሳውቀዋል። የመልቀቃቸው ጉዳይ በብዙዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። ከድርጅታቸው ጋር ስለነበራቸው ቅሬታና ስለ ወደፊቱ የፖለቲካ ህይወታቸው ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል። ቢቢሲ፡ ለንደን ምን እያደረጉ ነው?
አቶ ዛዲግ፡ ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የድህረ ምረቃ ትምህርቴን በመከታተል ላይ ነኝ። በቅርቡም ትምህርቴን ስለማጠናቅቅ ወደ አገር ቤት እመለሳለሁ። ቢቢሲ፡የህወሃት አባልነት መልቀቂያውን ያስገቡት ለንደን ሆነው ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ እያሉ ማስገባት አይቻልም ነበር? አቶ ዛዲግ፡ የመልቀቂያ ደብዳቤየ ላይ እንዳስቀመጥኩት በተለያየ ምክንያት አልቻልኩም ነበር። ከድርጅቱ ጋር ያለኝ ልዩነት መፈጠር ከጀመረ ቆይቷል። ያሻሽሉ ይሆን የሚለውን እያሰላሰልኩና ተስፋም ስለነበረኝ፤ የመጨረሻውን ውሳኔ ለመወሰንና አሟጥጬ ለመጠቀምምጊዜ ያስፈልግ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ መልቀቂያ ማስገባት የራሱ የሆነ አካሄድ አለው። እድልም መስጠት ፈልጌ ስለነበርም ለዛ ነው ጊዜዬን የወሰድኩት። በቅርቡ የሚታዩት ምልክቶች ደግሞ ከናካቴው ከለውጥ ጋር እንደተጣሉ አስረግጦ የሚያስረዱ ነገሮች ስላጋጠሙኝ በዚያ ምክንያት የመጨረሻውን ውሳኔ ለመወሰን ችያለሁ። • አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው" ቢቢሲ፡ በድርጅትዎ ህወሃት ውስጥ ማስፈራሪያ እና ዛቻ ይደርስብዎ እንደነበር በመልቀቂያ ደብዳቤዎ ላይ ገልፀዋል። በግለሰብ ደረጃ ነው ወይስ እንደ ድርጅት ህወሃትን ወክሎ በደብዳቤ ነው? አቶ ዛዲግ፡ተቋም በሰው ነው የሚወከለው፤ ደብዳቤየ ላይ እንዳስቀመጥኩት ትልልቅ ስልጣን ያላቸው መሪዎች፤ በተለይም የፖለቲካ እስረኞችን በተመለከተ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅህፈት ቤት ፌስቡክና ትዊተር ገፅ በቀጥታ ማስተላለፋችን ከታወቀበት ከዚያ ምሽት ጀምሮ ለረዥም ጊዜ ከአንድ አመት በላይ ማስፈራሪያና ዛቻ ይፈፀምብኝ ነበር። ይህንን የሚያደርሱብኝ ትልልቅ ስልጣን ያላቸው መሪዎች ናቸው። አሁን የግለሰብ ስም ማጥፋት ስለማያስፈልግ ስማቸውን መግለፅ አልፈልግም። የእነሱ ድርጊት እንደ ድርጅት ድርጊት ነው የሚቆጠረው፤ ከተሳደቡም፣ መልካም ስራ ከሰሩም ያው ድርጅታቸውን ወክለው ነው። የደረሰብኝን ዛቻና ማስፈራሪያም አውቀው ከጎኔ የቆሙና አይዞህ ያሉኝ በተራ አባልነት ያሉ ሰዎችም ነበሩ። ምንም እንኳን የተፈፀመው በመሪዎች ቢሆንም ይህ ነገር በተቋም ወይስ በግለሰብ ደረጃ ነው የሚለው አከራካሪ ነው። ያው እንግዲህ እንዘንላቸው ከተባለ ይህ በግለሰብ ደረጃ የተፈፀመ ነው ማለት ይቻላል። ሆኖም ግን ደብዳቤየ ላይ በግልፅ እንዳስቀመጥኩት በዛ ወቅት በወሰድኩት አቋም ነው። በግል ይህ ነው የማይባል፤ ተራ ሳይሆን ከበድ ያለ ጥቃት፣ ዛቻ ፣ ወከባና ትንኮሳ ደርሶብኛል። • በአላማጣ ግጭት ቢያንስ 5 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ እነዚህ ሰዎች ደግሞ ተራ ዛቻ ሳይሆን ጥቃት የማድረስ ብቃቱና ከፍተኛ አቅም ያላቸው ናቸው። ያደረጉት ሰዎችም እውነት መሆኑን ያውቁታል። ከዚያም አልፎ በማህበራዊ ሚዲያና በራሳቸው ኔትወርኮች የስም ማጥፋት ዘመቻ ደርሶብኛል። ይሄ ሁሉ የሆነው የህሊና እስረኞች አሉ ብዬ ስላመንኩና ሁለተኛ ያ ደግሞ ለኢትዮጵያ ህዝብ በፍጥነት እንዲታወቅ ስለተደረገ ውሳኔ የማስቀየሪያ ጊዜ አጣን፤ ሁለተኛ የህሊና እስረኛ የሚባል ነገርም እንዳለ ተጋለጠ፤ እንግልትና ስቃይም እንዳለ ተጋለጥን የሚል ስሜት የደረሰባቸው ናቸው። በኔ እምነት ይህንን ማድረጌ ትክክል ነው፤ ለትግራይም ህዝብ እንዲሁ ለህወሃትም ችግሩ ካለ መታረሙ የሚጠቅም እንጂ እንደሆነ አይጎዳም። ሰዎች በመደብደባቸውና በመታሰራቸው ህወሐት የሚያተርፍ አይመስለኝም። ፕሮግራሙም ላይ እንዳስቀመጠው ለዲሞክራሲ የሚታገል ድርጅት ነው። ለዲሞክራሲ የሚታገል ከሆነ እንግልትን መፍቀድ የለበትም፤ በህገ መንግሥቱ መሰረት የህሊና እስረኞች ሊኖሩ አይገባም። ስለዚህ የወሰድኩት አቋም ትክክል ነው። ትክክለኛ አቋም በመውሰዴ ግን የጥፋት አቋም ያራምዱ የነበሩ ኃይሎች ስልጣናቸውን ተገን አድርገው የማይገባ ዛቻና ድርጊት ፈፅመውብኛል። ቢቢሲ፡ ደረሰብኝ የሚሉት ማስፈራሪያና ዛቻ እርስዎ ዛዲግ በመሆንዎ የደረሰብዎት ነው? ወይስ መነሻ አለው? አቶ ዛዲግ፡ በአጠቃላይ ፓርቲውን ከተቀላቀልኩ ጀምሮ የባዳነትና የባይተዋርነት ስሜት እንዲሰማኝ ተደርጓል። እኔ ብቻ ሳልሆን በርካታ ከራያ የመጡ ሰዎች ይህንን ስሜት ይጋራሉ። ተሰባስበንና ተገናኝተን ስናወራ ሁሉም ይህንን ይናገራል፤ ይሄ ጥቃቱና ማግለሉ ነው። በኔ እምነት የወሰድኩት ትክክለኛ አቋም ለጥቃት ዳርጎኛል፤ ያን ነገር ባላደርግ ኖሮ መገለሉ፣ መገፋቱና አድልዎ ይኖራል፤ ነገር ግን ወደዛ ደረጃ አይሸጋገርም ነበር። ያ አምባገነኑ ቡድን የህሊና እስረኞች መፈታት፣ የማዕከላዊ መዘጋትን የመሳሰሉ ውሳኔዎችና እርምጃዎች በሞኖፖሊ (ብቻዬን) ተቆጣጥሬ የነበረውን ስልጣን ያሳጡኛል፤ የማታ ማታ ኢትዮጵያ እውነተኛ ዴሞክራሲ ሊኖራት ነው የሚል ስጋት አድሮበታል። ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለእንደነዚህ አይነት ሰዎች ቦታ አይኖራትም፤ የምትሰጠውም ስልጣን አይኖርም። ቢቢሲ፡ እርስዎ ያሳዩት የፖለቲካ እድገት በሌሎች አጋር ድርጅቶች በርታ ባይነትና ድጋፍ የተገኘ መሆኑን ገልፀው ህወሃት ግን ይህንን ይቃወም እንደነበር ገልፀዋል። ምን ማለት ነው? ምን ተጨባጭ መረጃ አለዎት? አቶ ዛዲግ፡ በአንድ ወቅት ጉባኤ ላይ በቀረበ ግምገማ እኛ ያላፀደቅነው ስልጣን ነው የተሰጠው ተብሎ ቀርቦብኛል። ሌሎች በርካታ በኢህአዴግ ውስጥ የሚገኙ መሪዎች ወጣት ሰው ሲያዩ የስራ ፍላጎት ያለው ታታሪ ሰው ሲያዩ ደስ ይላቸዋል። ከብዙዎች ጋር አብረን ሌት ተቀን ሰርተናል። የማቅረብ ፣ የማገዝን፣ ቀናነትና የመሪነት ባህል አይቻለሁ። ህወሃት ውስጥ ያሉ አንዳንድ ሰዎች ግን መጀመሪያውኑ ወጣት ወጥቶ እንዳይታይ በተለይ ደግሞ ከእኔ አይነት አካባቢ የመጣ ሲሆን የበለጠ ጨክነው ይገፋሉ፤ ለሌላው ትግራይ ወጣትም ቢሆን የሚያቀርቡ ሰዎች አይደሉም፤ እንደ እኔ አይነት ከራያ ለመጣ ሰው ሲሆን ግን ይበረታል። ሌላው ቢቀር የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ የሚዲያና ህዝብ ግንኙነት ዴሊቨሪ ዩኒት ሚንስትር ስሆን በጠቅላይ ሚንስትሩ አቅራቢነት ነው፤ ይሁን እንጂ ለማፅደቅ ከስምንት ወር በላይ ወስዷል፤ ከዛም በላይ አላፀድቅም ብሎ ህወሐት እስከ መጨረሻው ሞግቷል። • "በረከትና ታደሰ በሙስና መጠርጠራቸው አስደንቆኛል" አቶ ጌታቸው ረዳ በየደረጃው ኃላፊነት የተሰጠሁባቸው ቦታዎች ህወሐት ጠይቆ አይደለም የተሰጠሁት፤ የነበርኩባቸው የኃላፊነት ቦታዎችም የፌደራል መንግሥት የተለያዩ ቦታዎች ናቸው፤ ያም ቢሆን ህወሐት ተገፍቶ ተለምኖ ነበር ሲያፀድቅ የነበረው፤ አንዳንዴም አላፀድቅም ብሎ ያሰናክላል። ይህ የሚሆነው በእኔ እምነት አንደኛ ወጣት በመሆኔ፤ ሁለተኛ የራያ ልጅ በመሆኔ ነው። ሁለቱ ህወሐት ውስጥ የሚያስገፉ ናቸው። ቢቢሲ፡ የማንነት ጥያቄን ሙሉ ለሙሉ መልሻለሁ ከሚል ድርጅት ጋር ላለፉት ዓመታት አብረው ሲሰሩ ቆይተው አሁን የራያ ማንነት ጥያቄ አለ ብለው መጥተዋል። ለመሆኑ የራያን የማንነት ጥያቄ እርስዎ በህወሃት ውስጥ እያሉ አንስተው ያውቃሉ? አቶ ዛዲግ፡ ደብዳቤ ላይ በግልፅ እንዳመለከትኩት ህወሐት ውስጥ እያለሁ ማንሳት ብቻ ሳይሆን ታግየባቸዋለሁ። በመታገሌ፣ በመጠየቄ ደግሞ ጥቃት ደርሶብኛል፤ መገለል ደርሶብኛል፤ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶብኛል። አሁንም እተካሄደብኝ ነው። ስለዚህ ሁሉንም ነገሮች አንስቼ የታገልኳቸው ነገሮች ናቸው። የተሰጠኝ ምላሽ ደግሞ አንዳንዶቹ እናየዋለን የሚል ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ ይሄ ክህደት ነው... አንዳንዴ 'ሊበራል' ስለሆንክ ነው... ሌላ ጊዜ የአማራ ልጅ ስለሆንክ ነው፤ ሌላ ጊዜ ትግሬነትህን ስለምትጠላ ነው ይላሉ። እንደየ ግለሰቡና እንደየ ስብሰባው ሁኔታ የተለያየ ምላሽ ነበረው። አንድ አይነት መልስ ያጋጠመበት ሁኔታ አላውቅም፤ለመሬት አልታገልንም ግድ የለም ሕዝቡ ይወስናል የሚሉም ነበሩ። ዞሮ ዞሮ እኔ ታግያለሁ፤ ጥያቄው ይህን ነገር በአዎንታዊ መልክ አይተው የተቀበሉት ሰዎች የሉም ከሆነ ፤አላውቅም። መጨረሻ ላይ እንደማይቀየር ሳውቅ ተስፋ ስቆርጥ ወጥቻለሁ። ቢቢሲ፡ ሌላው ያነሱት ጉዳይ ህወሃት ከለውጡ በተቃራኒ ቆሟል የሚል ነገር ነው። ምን ማለትዎ ነው? አቶ ዛዲግ፡ በእኔ እምነት የሐገራችን ህዝቦች ዲሞክራሲ ያስፈልጋቸዋልም፤ ይገባቸዋልም። ያስፈልጋቸዋል ሲባል አገራችን ውስጥ በአስተሳሰብ በሃይማኖት በብሔር የሚገለፅ ብዝሃነት አለ። ይህንን ደግሞ አቻችሎ ለመሄድ የሚያስችለው የዲሞክራሲ ስርዓት ነው። የአገራችን ህዝብ በተለያየ ጊዜ መራር ትግል እያደረገ፣ ውድ ዋጋ እየከፈለ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማስፈር የሚያስችል በርካታ ድሎችን ለመፍጠር የታገለ ህዝብ ነው። እነዚህ ድሎች ግን በነጣቂዎችና በጥቂት ስልጣን ፈላጊዎች እየተወሰዱ፤ እድሎች እየመከኑ ነበርና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮነን እየተመራ ያለው ለውጥ ይህንን አዙሪት የሚቀጭ ነው። እንደ ከዚህ ቀደሙ ከንፈራችንን እየመጠጥን በሃዘን የምናስታውሳቸው ድሎች ሳይሆን የማይመክን ወደኋላ የማይመለስ እድልን አግኝተናል። ህወሃት ይህንን መደገፍ ነበረበት፤ ነገርግን በተለያየ ወቅት ያወጣቸው መግለጫዎች፣ መሪዎች በሚዲያ የሚያስተላልፉት መልዕክት፣ በአጠቃላይ በኢህአዴግም ሆነ በመንግሥትም እየተንፀባረቀ ያለውን አቋም በቅርበት የመረዳት እድል አለኝ፤ የመወያየት እድል አለኝ። እናም... በእኔ አጠቃላይ ግምገማ ህወሐት ለውጡን አልተቀበለም። • "ወሎዬው" መንዙማ ይህ ለውጥ ደግሞ በእኔ እምነት በጣም ወሳኝ ለውጥ ነው። ከዚህም የተሻለ ዲሞክራሲ ያስፈልገን እንደሆነ እንጂ የሚያንሰን አይደለም። ግን ይህንን ትንሹን ለውጥ እንኳን ካልተቀበለ፣ ሌላው ቢቀር እስረኞች ሲፈቱ የተንፀባረቀው ነገር፣ የነበረው እሰጥ አገባ፣ መሪዎችና ግለሰቦች ያሳዩት ነገር፣ በግሌም የደረሰብኝ ጥቃት፤ አይደለም ሰፊ ዲሞክራሲን የመቀበል፤ ትንሿን ተወላግዶ የበቀለውን የማረም ሂደት እንኳን ያለመቀበልና ለማደናቀፍ መታተር ነበረ። በእኔ አተያይ ህወሐት ለውጡን የተቀበለ አልመሰለኝም። ቢቢሲ፡ ለውጡን በተመለከተ በተሰጠው መግለጫ ወቅት የፖለቲካ እሥረኞች እንደሚፈቱ ተገልፆ ከዚያ በኋላ የተባለው በተደጋጋሚ ተቀይሯል። ምን ነበር የተፈጠረው? አቶ ዛዲግ፡ ከአንዳንድ የህወሐት ፖለቲካ አመራሮች የፖለቲካ እስረኞች ሳይሆን በፖለቲካ ምክንያት የታሰሩ ብየ ይፋ እንዳደርግ የማስፈራሪያ፣ የስድብ፣ የዛቻ ውርጅብኝ ተፈፅሞብኛል። ቢቢሲ፡ ከህወሃት አመራሮች ብቻ ነው ዛቻው የመጣው? አቶ ዛዲግ፡ ይሄ የመጣው ፓርቲው ውስጥ ካሉ ሁለት ግለሰቦች እና ሌላ ቦታ ካሉ ሁለት አመራሮች ነው። ከህወሃትጋር ጋር ቅርበት በዛቻውና በማስፈራራቱ በተዘዋዋሪ ተሳትፈዋል። ሌላው ሰው ግን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝን ጨምሮ ሌሎችም ደስተኛ ነበሩ። ከዚያ በኋላ ሚዲያዎች መግለጫውን እንዲያስተካክሉ ተደርጓል። ቢቢሲ፡ እንዲስተካከል የተደረገው በህወኃት ጫና ነው ማለት ነው? አቶ ዛዲግ፡ ጫናው የመጣው ህወሃት ውስጥ ባሉ አንዳንድ አመራሮች ነው። የደወሉልን ግለሰቦች ቢሆኑም የህወሐት አመራሮች ነበሩ። በወቅቱ አለቃዬ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ነበሩ፤ ሚንስትር ነኝ። ከእኔ በስልጣን ያነሱ የህወኃት አመራርና ከስልጣን የወረዱ ሁሉ ሳይቀሩ ደውለው ማስፈራሪያና ዛቻ አድርሰውብናል። እነዚህ ብቻ ሳይሆኑ በስራ ላይ ያሉ ሰዎችም ማስፈራሪያ አድርሰውብኛል። ከዚያ በኋላ በተደረጉ ስብሰባዎች እና እራሴን መከላከል በማልችልባቸው የማዕከላዊ ስራ አስፈፃሚ መድረኮችም ላይ ይህን ነገር ሆን ብለው አንስተዋል። የቀለም አብዮተኛ ነው፣ ለጥቃት አጋለጠን፣ 'ሊበራል' ነው፤ እያሉ የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም ዛቻና ማብጠልጠል ፈፅመውብኛል። ቢቢሲ፡ በ13 ኛው የህወሃት ጉባዔ ላይ ለማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ታጭተው ሳይመረጡ ቀርተዋል። በዚህ አኩርፈው ነው ፓርቲውን የለቀቁት የሚሉ አስተያቶች ይሰማሉ። ለዚህ ያለዎት ምላሽ ምንድን ነው? አቶ ዛዲግ፡ መጀመሪያ ጉባዔው ላይ ስጠቆም፤ አንድ የማላውቀው ሰው ነበር የጠቆመኝ። ድጋፍም ተቃውሞም ቀረበ፤ በወቅቱም እኔ ራሴ እጄን አውጥቼ እኔ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል መሆን አልፈልግም ብዬ ተናግሬያለሁ። ይህ ጉባኤ 1500 ሰዎች የተሳተፉበት ነው፤ በነዚህ ሁሉ ሰዎች ፊት የተነገረ ነገር ውሸት አይደለም፤ ከእውነት ጋር ካልተጣሉ በስተቀር። የኔ የመልቀቂያ ደብዳቤም መርህ ላይ እንጂ ኩርፊያ አያሳይም። በእኔ እምነት ህወሃት ለእኔ የማይሆን ድርጅት እንደሆነ፤ በተለይ መሪዎቹ ዲሞክራሲያዊ እንዳልሆኑ ከተገነዘብኩ ውዬ አድሬያለሁ። ትክክለኛ ጊዜ እየጠበቅኩ ነበር፤ ስለዚህ ይሄ የሚባለው ነገር ተራ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው። ማንኛውም ሰው ከህወሃት ሲወጣ (ትላልቅ መሪዎች ሳይቀር) ማንኳሰስ፣ ከፍተኛ የሆነ ስም ማጥፋት ዘመቻ፣ በሬ ወለደ ወሬ ማስተላለፍ፣ ስራ እንዳያገኙ፣ የግል ሕይወታቸውን እንዳይመሩ የማድረግ ተግባር በየተለያየ ጊዜ እንዳጋጠመ በ1993 ዓ.ም አይተነዋል። ከዚያም በኋላ እንዲሁ። እኔ በመልቀቂያ ደብዳቤዬ ላይ 'በጥይት እንነጋገራለን" ያለኝን ሰው ስም እንኳን አልጠቀስኩም፤ ምክንያቱም ጥያቄዬ የመርህ ጥያቄ ስለሆነ። ቢቢሲ፡ የእርስዎ ቤተሰቦች የራያ ተወላጅአይደሉም፤ እርስዎም ስለ ራያ አይመለከታቸውም የሚሉ ሰዎች አሉ። ምን ምላሽ አለዎት? አቶ ዛዲግ፡ ወደዚህ ደረጃ መውረድ አልፈልግም፤ መጀመሪያ ማንም የሰው ልጅ የትም ቦታ የሚደርስ ጥቃትና ጉዳት ይመለከተዋል። የነፃነት ታጋዩ ቼጉቬራ አርጀንቲናዊ ቢሆኑም የኩባ ህዝቦች ሲበደሉ ያገባኛል ብለው ታግለዋል። ታጋይ የትም ቦታ ያለ ክፉ ድርጅትን ወይም ነገርን ተቃውሞ መታገል ተገቢ ነው። በመርህ ደረጃ ትግል ድንበር የለውም፤ ደም የለውም ። እኔ ግን የራያ ልጅ ነኝ፤ ኢትዮጵያዊም ነኝ፤ ደብዳቤዬ ላይ የገለፅኩት አያቴ ከራያ የሚወለድ ነው። በዚህ ነጭ ውሸት የራያ ህዝብ እየሳቀ ነው። ስለዚህ በራያ ህዝብ እየደረሰ ያለው ጥቃት ይመለከተኛል። ላልተወለድክበትም አካባቢ መቆርቆር መልካም ነው፤ ትልቅነትን ያሳያል፤ ጠባብ አለመሆንን ያሳያል። ቢቢሲ፡ ከሁለት ዓመት በፊት ኢህአዴግ ከአሜሪካ የተሻለ ዲሞክራሲ ገንብቷል ብለው ነበር፤ አሁን ያቀረቡት ሃሳብ ደግሞ ከዚህ ጋር የሚመሳሰል አይደለም። ይህንን እንዴት ያስታርቁታል? በዚያን ጊዜ ያቀረቡትን ሀሳብ ከልብ አምነውበትስ ነበር? አቶ ዛዲግ ፡ በቀጥታ መወሰድ የለበትም። አንድ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የፖለቲካ ምህዳር እንዴት መለካት እንደሚቻልና መለኪያዎቹ ላይ ሐሳቦችን አቅርቧል። ለምሳሌ ኢትዮጵያ ውስጥ ምርጫ በሚካሄድበት ወቅት በነቂስ ወጥቶ ድምፅ የሚሰጠው የህዝብ ቁጥር ከአሜሪካ ጋር ስናነፃፅረው በጣም የተሻለ ነው። ከዛ አንፃር ስናየው እንጂ ከአሜሪካ የተሻለ እፁብ ድንቅ ስርዓት ነው አላልኩም፤ ሊሆንም አይችልም። ዲሞክራሲን ከጀመርን አጭር ጊዜ ነው። እንደማይሆን አውቃለሁ። እንደዛ ብዬ የምናገር ሰው አይደለሁም። ቢቢሲ፡ መልቀቂያዎ ላይ አሁንም በፖለቲካ ተሳትፎዎ እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል። አዲስ ፓርቲ ሊያቋቁሙ ነው ወይስ ካሉት ፓርቲዎች አንዱን ይቀላቀላሉ? አቶ ዛዲግ፡ ያልኩት ጊዜው ሲደርስ አሳውቃለሁ ነው። በእኔ እምነት ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ፓርቲዎች አሉ። ሌላ ተጨማሪ ፓርቲ የሚያስፈልገን አይመስለኝም። እንዲያውም ያሉት ፓርቲዎች ቢሰባሰቡ ጥሩ ነው። እስካሁን ካሉት ፓርቲዎች አንዱን መቀላቀል እንጂ አዲስ ፓርቲ ማቋቋም አልፈልግም፤ ዞሮ ዞሮ ሊቀየር የማይችል ነገር የለም። ጊዜው ሲደርስ ኣሳውቃለሁ አሁን ጊዜው አይደለም።
news-56305099
https://www.bbc.com/amharic/news-56305099
ኮሮናቫይረስ፡ "በ14 ዓመቴ ትዳር እንድመሰርት ቤተሰቦቼ አዘዙኝ" አበባ
"ቤተሰቦቼ እኔን ለማግባት ለሚቀርብ የትዳር ጥያቄ እምቢ እንዳልል ነገሩኝ፤ ምክንያቱም ሊያገባኝ የሚፈልገው ግለሰብ ከሀብታም ቤተሰብ የተገኘ ስለሆነ" ትላለች የ14 ዓመቷ አበባ።
'አባቴ እንዳገባ ይገፋፋኝ ነበረ' አበባ ከጥቂት ወራት በፊት እናቷ እና ወንድም እህቶቿ የትዳር ጥያቄውን እንድትቀበል ከፍተኛ ጫና ያደርሱባት የነበረ ሲሆን፤ ቶሎ አግብታ በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የገንዘብ እጥረት ያጋጠመውን ቤተሰብ እንድትረዳ ይፈልጉ ነበር። አበባ ዶክተር መሆን ትፈልጋለች። ነገር ግን በትውልድ ከተማዋ ደቡብ ጎንደር የመማር ተስፋዋ የመነመነ ነው። ራቢ ደግሞ የ16 ዓመት ታዳጊ ስትሆን ናይጄሪያ በሚገኘው ጋሳዉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርቷን እየተከታተለች ነው። ነገር ግን በጣም የምትቀርባቸው አራት ጓደኞቿ በኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ወቅት ትዳር መስርተዋል። እናቷ ደግሞ እሷም ማግባት እንዳለባት ታስባለች። "ሁለት የጎረቤቶቻችን ታዳጊ ሴቶች በሚቀጥለው ሳምንት ያገባሉ፤ እንደ ፈጣሪ ፈቃድ። የእኔም ተራ እንዲህ በቶሎ ይደርሳል ብዬ አልጠበኩም ነበር" ትላለች ራቢ ስጋት ውስጥ ሆና። ይህን መሰል በቤተሰብ ግፊት የሚፈጸሙ ጋብቻዎች የተለመዱ ነገሮች ናቸው። በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ተጨማሪ 10 ሚሊየን ታዳጊ ሴቶች ሊዳሩ እንደሚችሉና የኮሮረናቫይረስ ወረርሽኝ ደግሞ ነገሮችን ሊያባብስ እንደሚችል ዩኒሴፍ በቅርቡ የሰራው ጥናት ያሳያል። ዩኒሴፍ እንደሚለው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከመከሰቱ በፊት እንኳን በሚቀጥሉት አስር ዓመታት 100 ሚሊየን ታዳጊ ሴቶች ወደ ትዳር ተገደው ሊገቡ እንደሚችሉ ተገምቷል። ነገር ግን አሁን ይህ ቁጥር ጨምሯል። ከተገመተው በላይ ሆነ 10 በመቶ ጭማሪም አሳይቷል። በመላው ዓለም ወረርሽኙን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው፣ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች በመስተጓጎላቸውና የበርካታ ቤተሰቦች የገቢ ምንጭ በመጎዳቱ ምክንያት ተጨማሪ 10 ሚሊየን ታዳጊ ሴቶች ለአቅመ ሄዋን ሳይደርሱ እስከ 2030 ድረስ ተገደው ትዳር ይመሰርታሉ ይላል የዩኒሴፍ ጥናት። "ይህ መረጃ የሚያሳየው ዓለማችን ምን ያክል ለታዳጊ ሴቶች አስቸጋሪ እየሆነች መምጣቷን ነው" ይላሉ የዩኒሴፍ የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች መከላከል አማካሪ የሆኑት ናንካሊ ማስኩድ። "ወላጆች ትዳር ከማሰባቸው በፊት ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት መላክ ነው ያለባቸው" ትላለች አበባ። ይህች ታዳጊ ኢትዮጵያዊት ከተዘጋጀላት የትዳር መንገድ ማምለጥ ችላለች። ምክንያቱ ደግሞ አባቷን ማሳመን በመቻሏ ነበር። "እናቴና ወንድሞቼ እንዳገባ በጣም ይገፋፉኝ ነበር። መጨረሻ ላይ የአካባቢው ኃላፊዎች ምክር ከሰጧቸው በኋላ ሃሳባቸውን ቀየሩ።" ባንግላዴሽ ውስጥ ያሉ የሴቶች ተቋማት ያለእድሜ ጋብቻን ለማስቀረት ሲጥሩ ቆይተዋል ለራቢ ግን [ትክክለኛ ስሟ አይደለም፤ ምስሏም እንዲታይ አትፈልግም] አደጋው አሁንም እንዳለ ነው። በግብርና በሚታወቅ ጋምባ በሚባል አካባቢ ነው የምትኖረው። በዚህ አካባቢ ታዳጊ ሴቶች ቶሎ እንዲያገቡ ይደረጋል። "ሁሉም ነገር የጀመረው በወረርሽኙ ምክንያት እንቅስቃሴ ሲገሰደብ ነው። ታናናሽ ወንድሞቼ ቃላትን የመጻፍ ጨዋታ ሲጫወቱ አብሬያቸው መጫወት ጀመርኩኝ" ትላለች የ16 ዓመቷ ራቢ። "ጨዋታው ትንሽ ከበደኝ። እናቴ ደግሞ በጣም ተበሳጨች። ይሄን ሁሉ ጊዜ ትምሀርት ቤት ስትሄጂ ጊዜሽን ዝም ብለሽ ነው ያባከንሽው። ታናናሽ ወንድሞችሽ ከአንቺ የተሻሉ ናቸው" አለችኝ። እናቷ በዚህ አላበቁም ነበር። "እስካሁን የአብረውሽ የሚማሩት ሴቶች በሙሉ አግብተዋል። ለሻፊዩ (ራቢን ሊያገባ የሚፈልገው ግለሰብ) ሊያገባሽ እንደሚፈልግ በይፋ በቤተሰቦቹ በኩል ለትዳር መጠየቅ አለበት" አለች። ጓደኞቿ ሀቢባ፣ ማንሱራ፣ አስማው እና ራሊያ ባለፉት ወራት ውስጥ ሁሉም ትዳር መስርተዋል። ዋነኛ ምክንያታቸው ደግሞ በወረርሸኙ ምክንያት ጫና የደረሰበትን ቤተሰባቸውን ለመርዳት ነው። አንዲት የራቢ እናት ጎረቤት ለምን ታዳጊ ሴቶች ቶሎ ማግባት እንደማይፈልጉ አይገባኝም ትላለች። "ወላጆች ምንድነው የሚጠብቁት? ለልጆቼ በሙሉ የትምህርት ወጪ መክፈል አልችልም። ትዳር ደግሞ የተረጋጋ ህይወት ለመምራት ወሳኝ ነው። በተጨማሪ ደግሞ ሴቶቹ አግብተው ሲወጡ በቤተ ውስጥ ትንሽ ሰው ይኖራል" ትላለች። ከአውሮፓውያኑ 2011 ጀምሮ ያለእድሜያቸውና ያለፍላጎታቸው የሚያገቡ ታዳጊ ሴቶች ቁጥር 15 በመቶ መቀነስ አሳይቶ የነበረ ሲሆን የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ግን ይህን መሻሻል ወደኋላ እንዳይመልሰው ስጋት አለኝ ብሏል ዩኒሴፍ። "በዓለም አቀፍ ደረጃ የታዳጊዎች ትዳርን በተመለከተ ብዙ መሻሻሎችን እያየን ነው። ከነጭራሹ ለማጥፋት ካስመጥነው እቅድ አንጻር ብዙ ቢቀረንም በትክክለኛው መንገድ ላይ እንዳለን ግን እናምናለን" ይላሉ ናንካሊ ማስኩድ። "ነገር ግን ኮቪድ-19 ነገሮችን በሙሉ አበለሻሽቶብናል። በመላው ዓለም የሚኖሩ ታዳጊ ሴቶች በሙሉ ህይወታቸው ከባድ ሆኗል።" በዩኒሴፍ ሪፖርት ላይ በጎ የሚባሉ ነገሮችም ተስተውለዋል። ኃላፊዎችና የሚመለከታቸው ሰዎች ጣልቃ የሚገቡ ከሆነ የታዳጊ ሴቶችን ወደ ትዳር መግባት በከፍተኛ ሁኔታ መከላከልና መቀነስ ይቻላል። ምንም እንኳን ያለእድሜ ጋብቻ በአንዳንድ የዓለማችን አካባቢዎች በጣም የተለመደ ነገር ቢሆንም ትክክለኛው እርምጃ በሚወሰድባቸው ቦታዎች ግን ክስተቱ በጣም የቀነሰ ነው። ካለእድሜ ከሚፈጸም ጋብቻ የተረፉት አበባ (ግራ) እና መቅደስ (ከመሃል) ከጓደኛቸው ከውዴ ጋር "ዘጠኝ የትዳር ጥያቄዎች ቀርበውልኛል" "ከ14 ዓመቴ ጀምሮ በተለይ ከወረርሽኙ በኋላ ዘጠኝ የእናግባሽ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ ነበር" ትላለች ማራም። ከጥቂት ዓመታት በፊት ከሶሪያ ተሰዳ ወደ ዮርዳኖስ የመጣች ሲሆን በአሁኑ ጊዜ በዛታሪ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ነው የምትኖረው። ''ከማኅበረሰቡ ከፍተኛ ጫና የነበረ ቢሆንም እናትና አባቴ ግን ሁሌም ከጎኔ ናቸው" ትላለች። "እናቴ በጣም ነው የምትደግፈኝ፤ ሁሌም ቢሆን ገና ልጅ እንደሆንኩኝና ስለትዳር ምንም የማውቀው ነገር እንደሌለ ነው የምትነግረኝ።" ማራም ትምህርት ቤት ሄዳ ለመማርና ኳስ ለመጫወት ችላለች። "ካገቡ በኋላ ትምህርታቸውን ያቋረጡ በርካታ ሴቶችን አውቃለው። ቤተሰቦቻቸውን ጥለው ከባሎቻቸው ጋር ይሄዳሉ። እነዚህ ታዳጊ ሴቶች እንዲህ አይነት ትልቅ ውሳኔ ላይ ለመድረስ ገና ልጆች ናቸው።" የዘርፉ ባለሙያዎች እንደሚሉት በትክክለኛው ጊዜ ማኅበራዊ ግንዛቤ መፍጠር ከተቻለ ያለእድሜ ጋብቻን መቆጣጠር ይቻላል። "ለዚህ ትልቅ ምሳሌ መሆን የምትችለው ሕንድ ነች። ባለፉት 30 ዓመታት የሕንድ መንግሥት በርካታ ቤተሰቦች የገንዘብ ክፍያ ፕሮግራም ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ አድርጓል" ይላሉ ናንካሊ ማክሱድ። በዚህ ምክንያት የሕንድ መንግሥት ለበርካታ ቤተሰቦች ታዳጊ ሴት ልጆቻቸውን እንዳይድሩ ለማድረግ ማበረታቻ ክፍያ ፈጽሟል። በተጨማሪም ጋብቻውን ማስቀረት ካልተቻለ ደግሞ ቢያንስ ለማራዘም ይሞከራል። "ይሄ በጣም ወሳኝ ነገር ነው። ሌላው ቢቀር ታዳጊ ሴቶች ትምህርታቸውን የመጨረስ እድል ይኖራቸዋል። በተጨማሪም ሌሎች እውቀቶችን አዳብረውና በራስ መተማመናቸው ጨምሮ ነው ወደ ትዳር የሚገቡት።" የዩኒሴፍ የጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች አማካሪ የሆኑት ናንካሊ ማክሱድ እንደሚሉት በኮቪድ-19 ምክንያት እየጨመረ የመጣውን የታዳጊዎች ወደ ትዳር መግባት ለመቀነስ ሦስት ወሳኝ ነገሮች አሉ። "በመጀመሪያ ሴቶቹ ደኅንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ማድረግ አልያም እንደ ንግድና የእጅ ጥበብ ሥራዎች አይነት ክህሎታዎችን እንዲያዳብሩ ማድረግ ወሳኝ ነው።" "በተጨማሪ ደግሞ በወረርሽኙ ምክንያት በደሀ ቤተሰቦች ላይ የደረሰውን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጫና ለመቀነስ የተለያዩ ፕሮግራሞችን መቅረጽ። ይህ ሲሆን ቤተሰቦች ለገንዘብ ብለው ልጆቻቸውን መዳር ያቆማሉ" ብለዋል። አክለውም በአስራዎቹ እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ታዳጊዎች ማርገዝ በራሱ በቶሎ ወደ ትዳር እንዲገቡ ከሚያደርጓቸው ነገሮች መካከል አንደኛው ነው ይላሉ። "የማኅበረሰብ ጤና እና የሥነ ተዋልዶ ትምህርት ለታዳጊ ሴቶች በአግባቡ ሊሰጣቸው ይገባል። ትክክለኛው ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ሁሉም መረጃ ሊቀርብላቸው ይገባል።" ወደ ኢትዮጵያ ስንመለስ አበባ ጓደኞቿ በሙሉ ከትዳር በፊት ትምህርታቸውን ጨርሰው እንደሚመረቁ ተስፋ ታደርጋለች። ሌላኛዋ መቅደስ ደግሞ ወደፊት ኢንጂነር የመሆን ሕልም አላት። "የእንቅስቃሴ ገደቡ ታውጆ በቤት ውስጥ እያጠናን እያለ ወላጆቼ ለአንድ ሰው እኔን ስለመዳር ሲያወሩ ሰማኋለቸው። ልጁን ከነጭራሹ አላውቀውም" ስትል ለቢቢሲ ገልጻለች። "ማግባት እንደማልፈልግና ትምህርቴን መጨረስ እንደምፈልግ ስነግራቸው ሊሰሙኝ ፈቃደኝ አልነበሩም።" "ትምህርት ቤታችን እስከሚከፈት ድረስ ጠበኩቅና ለትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ነገርኩት" ትላለች መቅደስ። "ወዲያው አካባቢውን ኃላፊዎች አሳወቀ፤ እነሱም መጥተው ከቤተሰቦቼ ጋር ተነጋገሩ።" አሁን ላይ ቤተሰቦቿ ከ18 ዓመቷ በፊት እንደማይድሯት ቃል ገብተዋል። "የምክር አገልግሎቱ በእኛ ማኅበረሰብ ውስጥ በጣም እየጠቀመን ነው። ሌላው ቀርቶ ወላጆች እምቢ ብለው ልጆቻቸውን ለመዳር የሚያስቡ ከሆነ ጉዳዩ በፖሊስ በኩል እንዲያዝ ይደረጋል።"
48605253
https://www.bbc.com/amharic/48605253
የኢትዮጵያ ዐይን ባንክ፡ የዐይን ብርሃኑን አጥቶ የተመለሰለት ታዳጊ
የመቀሌ ነዋሪ የሆነው አቡበክር ውሃውረቢ እናቱና አባቱ በፍቺ በመለያየታቸው ዕድገቱ ከእናቱ ጋር ነው። ለቤተሰቡ የመጀመሪያ የሆነው አቡበክር የዐይን ህመሙ የጀመረው ገና የሁለት ዓመት ከሰባት ወር ህፃን ሳለ ነበር።
ያጋጠመው የአለርጂ ህመም ዐይኑን በተደጋጋሚ እሸኝ እሸኝ ይለው ነበር። እርሱም ህመሙ እያስገደደው በተደጋጋሚ ዐይኑን ያሸዋል። ከትምህርት ቤትም ሆነ ከጨዋታ ሲመጣ አይኑ ተጨናብሶና ደም ለብሶ መምጣቱ የተለመደ ሆነ። • የወንዶች ያለዕድሜ ጋብቻ ህመሙ የእርሱ ብቻ ሳይሆን የእናቱም የዘወትር ጭንቀት ነበር። "በእኔ ዐይን ምክንያት ዐይኗ እምባ እንዳዘለ፤ እንዳለቀሰች ነው፤ አንተን ከሚያምህ እኔን ለምን አያመኝም? ትለኝ ነበር" ይላል የእናቱን መጠን ያለፈ ጭንቀት ሲያስረዳ። "በዚህ ዐይን ምክንያት እናቴ ሁል ጊዜ ታለቅስ ነበር" የሚለው አቡበክር እርሱን ለማሳከም ያልጎበኘችው የጤና ተቋም እንዳልነበርም ይናገራል። ይሁን እንጂ የተወሰነ የህመም ማስታገሻና 'ዕድሜህ ሲጨምር ይተውሃል' ከሚል ምክር በስተቀር የተሰጠው ዘላቂ መፍትሄ አልነበረም። ትምህርት ቤት በሄደ ቁጥር ከነጭ ሰሌዳና ከብርሃን ጋር እንደተሟገቱ ነው። የልጅነት ዐይኑ ብርሃንን ጠላ። • ከወለደች ከ30 ደቂቃዎች በኋላ ለፈተና የተቀመጠችው እናት ማስታገሻ መድሃኒት እየተሰጠው፤ እየተሻለው፤ እንደገና እያገረሸበት ትምህርቱን ለመከታታል አዳጋች ሆነበት። ቢሆንም ግን ትምህርቱን እያቋረጠና እንደገና እየቀጠለ አስራ ሁለተኛ ክፍል ደረሰ። የ10ኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ብዥ ማለት የጀመረው ዐይኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሳለ ግን የዐይን ዕይታው ጨርሶውኑ ስለቀነሰ ትምህርቱን መማር አልቻለም። ቀስ በቀስም በተለይ የአንደኛው ዐይኑ ዕይታ ሙሉ በሙሉ ጠፋ። "ከዕይታ በላይ ፈጣሪ የሰጠን ፀጋ የለም፤ ማየት መቻል ትልቅ ነገር መሆኑን ነው የተረዳሁት" ይላል -የዐይኑን ብርሃን ያጣበትን አጋጣሚ ሲያስታውስ። "ማታ አሞኝ ሳሸው... ሳሸው ቆይቼ ተኛሁ፤ ከዚያም ጠዋት ስነሳ ... አንዱ ዐይኔ አያይም፤ በቃ አበድኩ፤ ጮህኩ፤ ቤተሰቦቼ ተደናገጡ፤ ፍርሃት ፍርሃት አለኝ፤ አንቀጠቀጠኝ" ሲል ሁሉም ነገር እንደጨለመበትና ሁኔታውም በቃላት እንደማይገለፅ ይናገራል። በዚህ ጊዜ የተደናገጡት ቤተሰቦቹ ደቂቃም ሳያባክኑ ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሄዱ፤ ይሁን እንጂ በከተማው ላለው ሐኪም ቤት ከአቅም በላይ ነበር። ለሕክምናው ወደ ውጭ አገር መሄድ እንዳለበት ታዘዘ። ይህ ትዕዛዝ አቅም ለሌላቸው ቤተሰቦቹ ዱብ ዕዳ ነበር። ጊዜም ሳይወስዱ በነጋታው አዲስ አበባ ወደሚገኘው ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ለተሻለ ሕክምና ወሰዱት። የዐይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደሚደረግለትም የሰማው እዚሁ ነበር። አብዝቶ የሚሰማው ስለ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ስለነበር ፅንሰ ሃሳቡ ራሱ እንግዳ ሆነበት። የዐይን ብሌኑ ሕይወታቸው ካለፉ ሰዎች የተለገሰ እንደሆነ ሲያስበው ደግሞ በጣም ተደናገጠ። ሕክምናው እውነት አልመሰለውም። • በህንድ ህፃኗን ደፍረው የገደሉ በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ 'ታዲያ ከፈራህ እምቢ ለምን አላልክም?' አልነው። "ብርሃን አጥቼ እንዴት አልፈልግም እላለሁ፤ ያለውን አማራጭ መሞከር ነው እንጂ" ሲል ነበር ሳያወላዳ ምላሹን የሰጠን። ሙሉ በሙሉ ብርሃን ያጣው ዐይኑ የዐይን ብሌን ንቅለ ተከላው ተደረገለት። ከቀዶ ሕክምናው እንደወጣ ህመም ቢሰማውም እየቆየ ግን ዐይኑ በትንሹም ቢሆን ማየት ጀመረ። ለመጀመሪያ ጊዜም ያየው ቀዶ ሕክምናውን ያደረገችለትን ሐኪም እንደሆነ ያስታውሳል። ከሰው ያውም ሕይወቱ ካለፈ ሰው በተለገሰ የዐይን ብሌን ማየት መቻሉ በጣም አስገርሞታል። የማያውቃቸውን የለጋሽ ቤተሰቦች "የለጋሹ ቤተሰቦች ባላውቃቸውም ለሰዎች የሚያስቡ፣ ጥሩና የዋህ ሰዎች እንደሆኑ ነው የማስበው" ሲል ያመሰግናቸዋል። በተለገሰ የዐይን ብሌን ማየት ምን ስሜት ይሰጣል? አቡበክር አንዳንዴ ንቅለ-ተከላው በተደረገበት ዐይኑ ሲመለከት በእኔ ነው ወይስ በለጋሹ ሰው ዐይን የማየው? የሚለው የሁል ጊዜም ሃሳቡ ነው። ነገር ግን ከራሱ ጋር በሚያደርገው ንግግር ለራሱ መልስ ይሰጣል። "በለጋሹ ዐይን እኔ የማየውን ነው የማየው" ይላል። አንዳንዴ ጓደኞቹ "ለጋሹ ያየው የነበረውን እኮ ነው የምታየው" እያሉ እንደሚወርፉትና 'ሙድ' እንደሚይዙበት አልሸሸገንም። ኧረ እንዲያውም በሴት ወይስ በወንድ የዐይን ብሌን ነው የምታየው እያሉ እንደሚጠይቁትም ሳቅ ባልተለየው አንደበቱ አጫውቶናል። • የኢትዮጵያ ፊልም ወዲያና ወዲህ "የዐይን ብሌኑን የለገሱኝን ቤተሰቦች እጅግ አመሰግናቸዋለሁ፤ ባላውቃቸውም አላህ ጥሩ ነገር እንዲሰጣቸው እመኝላቸዋለሁ" ሲል የዐይን ብርሃኑን የመለሱለትን ለጋሾች አመስግኖ አይጠግብም። አቡበክር አሁን የአንድ ዐይኑ ብርሃን ሙሉ ለሙሉ የተመለሰለት ሲሆን ለሌላኛው ዐይኑ ሕክምና ለማድረግም እየተጠባበቀ ይገኛል። ትምህርቱን ለመቀጠልና እንደርሱ የተቸገሩ ሰዎችን ለመርዳት ዶክተር መሆን እንደሚፈልግም ነግሮናል። የዐይን ብሌን ንቅለ ተከላ በተለያየ ምክንያት የዐይን ብሌን ላይ የሚከሰት ጠባሳ ለዐይነ ስውርነት ሊዳርግ ይችላል። በተፈጥሮ፣ በአደጋ፣ በኩፍኝ በሽታ ወይም በተለያዩ የዐይን ህመሞች ሊከሰት ይችላል። ይህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ሊድን የሚችል ዐይነ ስውርነት ይባላል። የዐይን ብሌን ጠባሳ መሆኑ በሐኪም ከተረጋገጠ በኋላ በንፁህ የዐይን ብሌን የመቀየር ሂደት የዐይን ብሌን ንቅለ ተከላ እንደሚባል የኢትዮጵያ የዐይን ባንክ ሥራ አስኪያጅ ወ/ሮ ለምለም አየለ ያስረዳሉ። "አንድ ፍሬም ያለው መስታዎት በድንጋይ ተመቶ ቢሰነጣጠቅ ከውስጥ ወደ ውጭም ሆነ ከውጭ ወደ ውስጥ አያሳይም፤ በመሆኑም ፍሬሙን ቀርፆ አውጥቶ በሌላ መተካት ነው። የዐይን ብሌን ንቅለ ተከላም እንደዚያው ነው" ሲሉ ምሳሌ ይመዛሉ። • ስለ ግንቦት 27፤ 1983 የጎተራው ፍንዳታ ምን ያስታውሳሉ? እርሳቸው እንደሚሉት የጣታችንን ጥፍር ልጦ እንደማንሳት ያህል የዐይን ብሌንን ልጦ ማንሳት ይቻላል። በመሆኑም በዚህ ሂደት ከለጋሹ የተነሳውን የዐይን ብሌን ወደ ታካሚውም በተመሳሳይ መልኩ ማስተላለፍ ይቻላል። ሕክምናውን ለማግኘት የእድሜ ገደብ የለውም የሚሉት ወ/ሮ ለምለም ለሕፃናት ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ ስለሚያስልግ ትንሽ መጠበቅ እንደሚያስፈልግ ይህም እንደ ሐኪሙ ውሳኔ ይወሰናል ይላሉ። የኢትዮጵያ የዐይን ባንክም ሰዎች በሕይወት እያሉ የዐይን ብሌናቸውን ለመስጠት ቃል እንዲገቡ በማድረግ የዐይን ብሌን የማሰባሰብ ሂደት ይሰራል። በዚህም ቃል የተገቡ የዐይን ብሌኖችን ከሟች ቤተሰቦች ጋር በመነጋጋር እንዲነሱ ያደርጋሉ። አንድ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት መለየቱ ከተረጋገጠ በኋላ በስምንት ሰዓታት ጊዜ ውስጥ የዐይን ብሌኑ ተነስቶ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ወደ ሚገኘው የኢትዮጵያ ዐይን ባንክ ቢሮ ይመጣል። ከዚያም የደም ናሙና በመውሰድ የዐይን ብሌኑ ጥራት ይረጋገጣል። በባንኩ ውስጥ የዐይን ብሌኑ የሚቀመጠው ለ14 ቀናት ብቻ ነው። ከ14 ቀን በላይ ከቆየ ስለሚበላሽ ጥቅም ላይ አይውልም። • አምስት ጂ ኢንተርኔት ምን አዲስ ነገር አለው? በመሆኑም እነዚህን ሂደቶች ያለፈ የዐይን ብሌን፤ ንቅለ ተከላ በሚካሄድባቸው በአዲስ አበባ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታልና ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፤ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ ኲሓ ሆስፒታል፣ ሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል በጠየቁት ወረፋ መሠረት የዐይን ባንኩ ያዘጋጃቸውን የዐይን ብሌኖች ያሠራጫል። የኢትዮጵያ የዐይን ባንክ ከተመሠረተ 15 ዓመታትን ቢያስቆጥርም እስከ ፈረንጆቹ 2018 መጨረሻ ድረስ የዐይን ብሌን ንቅለ ተከላ የተደረገላቸው 2112 ኢትዮጵያዊያን ብቻ ናቸው። ከሚለገሱት የዐይን ብሌኖችም 80 በመቶ ያህሉን ብቻ እንደሚጠቀሙ የሚናገሩት ሥራ አስኪያጇ ቀሪው 20 በመቶ በተለያየ ችግር ምክንያት ከጥቅም ውጭ የሚሆኑ ናቸው ብለዋል። እስካሁን ድረስ ወደ 3 ሺህ የተጠጋ የዐይን ብሌን መለገሱንም ወ/ሮ ለምለም አክለዋል።
news-55285694
https://www.bbc.com/amharic/news-55285694
ትግራይ ፡ ወደ ሱዳን የተሰደደችው ጋዜጠኛ አጭር ማስታወሻ
የጦርነቱን መጀመር ተከትሎ ወደ ሱዳን የተሰደደችው የድምጸ ወያነ ጋዜጠኛ ታሪኳን ለቢቢሲ ትግርኛ እንዲህ አጋርታለች።
ስሜ ስምረት* ይባላል። ጋዜጠኛ ነኝ። ተወልጄ ያደኩት በምዕራብ ትግራይ፣ በሑመራ ከተማ ነው። እስካለፈው ወር ድረስ የድምጽ ወያነ ራዲዮ ጋዜጠኛ ነበርኩ። ያደኩት እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነው። ባደኩበት ከተማ ሁሉም ዓይነት ሰው ይኖራል። ትግራዋይ፣ ኦሮሞና አማራ ብቻም ሳይሆን የሱዳንና የናይጄሪያ ዜጎችም አብረውን ይኖራሉ፤ ለዚያውም በሰላምና በፍቅር። አንዱ ለሌላኛው አክብሮትና መዋደድ ኖሮት በጋራ ነበር የምንኖረው። ሑመራ የበረሃ ገነት ናት ማለት ይቻላል። ብዙ የተፈጥሮ ሀብቶች አሏት። በተለይ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች። በዚህም የተነሳ በበጋው ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከአማራ ክልልና ከሌሎችም የኢትዮጵያ ክፍሎች ለሥራ ይመጣሉ። ስለዚህ ሁመራ ሁልጊዜም ሕይወት ያላት ውብ ከተማ ነበረች። ጥቅምት 08/2013 ዓ.ም የዓመት ፍቃድ ወስጄ ከምሠራበት መቀለ ወደ ትውልድ አገሬ ሑመራ ተጓዝኩ። ከቤተሰቦቼና ከአብሮ አደጎቼ ጋር ቆንጆ ጊዜን አሳልፌ ወደ ሥራ ለመመለስ ነበር አካሄዴ። እንዳሰብኩትም ቆንጆ ጊዜን በሑመራ በማሳለፍ ላይ ነበርኩ፤ ከቤተሰቤና ከጓደኞቼ ጋር ደስ የሚል ጊዜ ነበረን። ይህ የሆነው ግን ለአጭር ጊዜ ብቻ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን በከተማዋ ድንገት የሆነ ፍርሃት እና ውጥረት ማሽተት ጀመርን። እውነትም በማዕከላዊው መንግሥትና በህወሓት መካከል ውጥረት እየነገሰ ነበር። የሆነ ቀን የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት የነበሩት ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ለጋዜጠኞች መግለጫ እየሰጡ ነበር። መግለጫውን በክልሉ ቴሌቪዥን ተከታተልኩት። "ሁሉም ነገር አብቅቶለታል" ሲሉ ሰማኋቸው። "የትግራይ ሕዝብ ሁሉን አቀፍ ዝግጅት ማድረግ አለበት፤ ጦርነቱ አይቀሬ ነው…" አሉ። ዶ/ር ደብረጺዮን ብዙውን ጊዜ በመግለጫዎቻቸው እንደዚያ ይላሉ። "ለጦርነት ተዘጋጁ" የምትለው ቃል ከአፋቸው አትጠፋም። ሆኖም ግን በዚህ ወቅት የሰጡት መግለጫ ከሌላው ጊዜ ተለየብኝ። ስለዚህ መቀለ የሚገኙ ጓደኞቼ ጋር ደወልኩኝ። "አስፈሪ ነገር እየመጣ ይሆን? ነገ ምን ሊመጣብን ይሆን?" እያልን አወራን። በሚደንቅ ሁኔታ ያንኑ ቀን ሌሊት፣ ተኩስ ተሰማ። አስታውሳለሁ ያን ምሽት በዶ/ር ደብረጺዮን መግለጫ ተደናግጬ ነበር ወደ መኝታ የሄድኩት። ለዚህም ይመስላል ሌሊት 8 ሰዓት ላይ ባንኜ ተነሳሁ። ስልኬን ስበረብር በጣም ብዙ የጽሑፍ መልዕክቶችን አገኘሁ። መቀለ ከሚገኙ ጓደኞቼ የተላኩ ነበሩ። ምንድነው ይሄ ሁሉ መልዕክት ብዬ ለአንዳንዶቹ ለመመለስ ስሞክር ኔትወርክ መቋረጡን ተረዳሁ። ታላቅ ወንድሜን እየሆነ ያለውን ነገር እንዲያስረዳኝ ጠየቅኩት። "አታስቢ፤ የጦር ልምምድ እየተደረገ ይሆናል፤ አሁን አርፈሽ ተኚ" አለኝ። ነገር ግን በቀጣዩ ቀን የተሰማው ነገር ሌላ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህወሓት ላይ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲካሄድ አዘዙ፤ ይህም የህወሓት ኃይሎች በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ ነበር። ጦርነቱ ከተጀመረ ከሳምንት በኋላ አንድ የታመመ ዘመዴን ለመጠየቅ ካህሳይ አበራ ሆስፒታል ሄድኩ። እዚያው እያለሁ ድንገት ከባድ ተኩስ መሰማት ተጀመረ። ተኩሱ ከጎረቤት ኤርትራ ድንበር በኩል የሚሰማ ነበር። ሁሉም ሰው በድንጋጤ ተዋጠ። ነዋሪዎች ቶሎ ብለው መሸሽ ጀመሩ። በየገጠሩ ለመደበቅ ሩጫ ተጀመረ። የእኛ ቤት ከከተማው ራቅ ብሎ የሚገኝና ወደ ኤርትራ ድንበር የተጠጋ ነው። ስለዚህ ወደ እናቴ ቤት መሮጥ ጀመርኩ። ሰዎች ግን እየጮኹ ሊመልሱኝ ሞከሩ። እየሮጥሽ ያለሽው ተኩስ ወደሚሰማበት አቅጣጫ ነው ሲሉ አስጠነቀቁኝ። ሩጫዬን ግን አልገታሁም፡፡ በዚያ ሰዓት ቶሎ ብዬ ከእናቴ ጋር መሆንን ነበር የፈለኩት። ስደርስ እናቴ እንጀራ አቀረበቸልን። ከቤተሰቡ ጋር አብረን በላን። ከዚያም ወላጆቼ "አሁን መሄድ አለብሽ" አሉኝ። ከዚያ ቶሎ ብለን በቅርብ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን ገብተን ተጠለልን። በዚህ ሁሉ ጊዜ የከባድ መሣሪያ ተኩስ ድምጽ ይሰማ ነበር። ምንም አንኳን አልፎ አልፎ መሳሪያዎቹ የከተማዋን እምብርት ቢመቱም ዋንኛ ዒላማቸው ግን በቅርብ የሚገኘው የትግራይ ልዩ ኃይል የነበረበትን ካምፕ ነበር። ያን ቀን እስከ ማታ 4፡00 ሰዓት ድረስ ከቤተክርስቲያን ሳንወጣ ስንጸልይ ቆየን። በሌላ አቅጣጫ ታላቅ ወንድሜ ከብቶቹንና እርሻውን እየጠበቀ ነበር። ማታ ላይ እኛንና ልጆቹን ሊያይ የተጠለልንበት ቤተ ክርስቲያን ድረስ መጣ። ልክ እንደመጣ ግን አዲስ ሐሳብ አመጣ። ተነሺ ወደ ሱዳን እንሂድ አለኝ። ለቤተሰብ እንኳ ሰላም ያገናኘን ሳልላቸው በሞተር አፈናጦ ወደ ድንበር ከተማዋ ዲማ ወሰደን። ምሽቱንም እዚያው ዲማ አሳለፍኩ። ሑመራ፣ ኤርትራና ሱዳን እርስበርስ ሩቅ አይደሉም። ስለዚህ የጦር መሣሪያ ድምጽ አልፎ አልፎ ይሰማን ነበር። በዚህ ጊዜ ስለ ቤተሰቦቼ መጨነቅ ጀመርኩ። ቤተሰቦቼ የሚኖሩበት ቤት ለኤርትራ ድንበር በጣም ቅርብ ነው። ያ ብቻም ሳይሆን የትግራይ ልዩ ኃይል አንዳንዶቹ ካምፖች ከእኛ ቤት ጀርባ ይገኙ ነበር። ስለዚህ የቤተሰቦቼ ሁኔታ አስጨነቀኝ። ነገር ግን ወደ ሱዳን፣ ሐምዳይት ከተማ ከመሸሽ ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለኝ ተረዳሁ። በመጀመርያው ቀን ሐምዳይት እንደገባሁ ያየሁት ነገር ቢኖር በጣም ብዙ ስደተኛ ወደዚህ መምጣቱንና የአስፈላጊ አቅርቦቶች እጥረት መኖሩን ነበር። ሐምዳይት ከሑመራ ብዙም ሩቅ የሚባል አልነበረም። የሑመራና የሐምዳይት ነዋሪ ድንበር የለየው ዘመድ ያህል ነው። እኔ ዛሬም ድረስ በካምፑ ውስጥ ነው የምገኘው። ጋዜጠኞችና ሌሎች ወኪሎች ሲመጡ እነሱን በማገዝ እሠራለሁ። እዚህ የሚገኙት ብዙዎቹ ስደተኞች በጦርነት ምክንያት ሰቆቃ ውስጥ ናቸው። የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጊዜ ገና የ5ዓመት ልጅ ነበርኩ። ነገር ግን ብዙዎቹ የጦርነት ስቃዮች ትዝ ይሉኛል። ወላጆቼ ደግሞ ዕድሜያቸውን በሙሉ ጦርነት ውስጥ ነው ያሳለፉት። ነገር ግን ጦርነት መጣ ብለው ከጦርነት ቀጠና ወጥተው አልጠፉም። ሁልጊዜም የሚሉት እዚሁ ቤታችን ብንሞት እንመርጣለን ነው። ዛሬ ሑመራ በጦርነቱ ምክንያት ሌላ ከተማ መስላለች። ብዙ ሰዎች ተፈናቅለዋል። ቤቶች ፈራርሰዋል። ንብረት ተዘርፏል። ስልክ መሥራት እንደጀመረ ቤተሰቦቼን ደወልኩላቸው። ደህና እንደሆኑ ነገሩኝ። ሁላችንም ስለ ጦርነት መጥፎ ትዝታዎች እንዳሉን አውቃለሁ። በትግራይ ጦርነት የእያንዳንዱን በር አንኳኩቷል። ጦርነት አስቀያሚ ነገር ነው። ራሴን በሐምዳይት መጠለያ ካምፕ ውስጥ አገኘዋለው ብዬ አልሜም አስቤም አላውቅም ነበር። ዘመዶቼ፣ ጓደኞቼ እና ሕዝቤ ሲሞቱ እመለከታለሁ ብዬ እስቤ አላውቅም። ሆኖም ይህን ለማየት በቃሁ። ይህን በዓይኔ የተመለከትኩትን ሰቆቃ እዘነጋዋሁ ብዬ አላስብም። በፊት በፊት በሶሪያ ጦርነት ምክንያት ስለተፈናቀሉ ሰዎች ታሪክ እሰማ ነበር። ይህ በአገሬ ወይም በሌላ በማንኛውም አገር እንዲሆን አልመኝም። በጣም አዝኛለሁ። በዚህ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ብዙዎቹ ሰላም ሆኖ ወደ ትውልድ ቀያቸው ለመመለስ ተስፋ ያደረጉ ናቸው። ከዳንሻ የመጡ አዳዲስ ጓደኞችን እዚህ ካምፕ ውስጥ ተመልክቻለሁ። እነሱ በጦርነቱ ጊዜ በጣም የከፉ የሚሰቀጥጡ ነገሮችን ተመልክተዋል። ጋዜጠኛ እንደመሆኔ መቅረጸ ድምጽ ነበረኝ፤ ማስታወሻ ደብተር ተለይቶኝ አያውቅም ነበር። በሕይወቴ የሚያጋጥሙኝን ነገሮች መሰነድ እወድ ነበር። በዜና ክፍል ነበር የምሠራው። ፎቶ ማንሳት ያስደስተኝ ነበር። ለዚህም ስል ሁልጊዜም ስልኬን ይዤ ነበር የምንቀሳቀሰው። ነገር ግን ያኔ ተኩስ ሲጀመር ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመደበቅ የሮጥን ቀን ስልኬን ቤት ጥዬው ነበር የወጣሁት። ያው እመለሳለሁ በሚል ተስፋ…። ከ10 ቀናት በኋላ ነበር ከወንድሜ ስልክ ያገኘሁት። በመጀመርያዎቹ ቀናት የነበሩትን ሁኔታዎች እንደ ጋዜጠኛ ሰንጄ አለመያዜ ይቆጨኛል። ነገር ግን አእምሮዬ ላይ ተቀርጾ ተቀምጧል። ያኔ ዶ/ር ደብረጺዮን "በሁሉም ረገድ ለሚመጣው ነገር ተዘጋጁ" ሲል ምን ማለቱ እንደነበረ አልገባኝም ነበር። ከባንክ ራሱ ግንዘብ ማውጣት አላሰብኩም ነበር። መቀለ እያለሁ ሁልጊዜ ጠዋት 11፡00 ሰዓት ነበር የምነቃው። ከዚያ ለአንድ ሰዓት ያህል እንቅስቃሴ አደርግ ነበር። በሳምንት ለ6 ቀናት ሥራ እገባ ነበር። እሑድ፣ እሑድ ግን ሁልጊዜም ወደ ተለያዩ የትግራይ ተራሮች እሄድ ነበር። ከጦርነቱ በፊት ሕይወቴ ደስ የሚል ነበር። አሁን እዚህ እንቅስቃሴ ማድረግም አልችልም። አሸዋማ ነው። አየሩም አይመችም። ቀኑን ሙሉ በካምፑ ውስጥ ቁጭ ብዬ አሳልፋለሁ። ቁጭ ስል እጨነቃለሁ፤ ቀኑን ሙሉ ጭንቀቴን እያዳመጥኩ ማስታመም ሆኗል ሥራዬ። ትግራይን ለቅቄ እሄዳለው ብዬ በፍጹም አስቤ አላውቅም። ለዚህም ነው ፓስፖርት እንኳ ኖሮኝ የማያውቀው። ወደ አገሬ ተመልሼ ሕዝቤን ማገልግል ነው ምኞቼ። ወደ አገሬ ተመልሼ ጋዜጠኛነቱን መቀጠል ነው ህልሜ። ከግጭቱ በፊት በርካታ ሕልም ነበረኝ። ሁለተኛ ዲግሪዬን ለመሥራት እያሰብኩ ነበር። ቤት የመሥራት ሐሳቡም ነበረኝ። ሌሎችም አያሌ ህልሞች። ምን ዋጋ አለው ታዲያ…! አሁንም ቢሆን ግን ወጣት ነኝ። ወደፊት ብዙ ተስፋዎች ይጠብቁኛል። ነገ የተስፋ ብርሃን ትፈነጥቅ ይሆናል። ሕልሜንም አሳካለሁ። ማመን የምፈልገው አሁን የደረሰብኝ ነገር ለነገ ይበልጥ እንድዘጋጅ የሚያደርገኝ እንጂ የሚሰብረኝ እንዳልሆ ነው። * ስሟ ለደኅንነቷ ሲባል ተቀይሯል
news-50516076
https://www.bbc.com/amharic/news-50516076
ህወሓት ከኢህአዴግ ለመፋታት ቆርጧል?
ሐሙስ በተካሄደውና ግንባሩ የመዋሃድን ሃሳብ በሙሉ ድምፅ ባፀደቀበት በኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደማይገኝ ቀድሞ ያስታወቀው ህወሓት በተግባርም ጉባኤውን ሳይሳተፍ ቀርቷል።
ባለፉት ጊዜያት መንግሥት/ኢህአዴግ የሚያስተላልፋቸውን ውሳኔዎች በተለያየ ምክንያት እንደማይቀበል በመግለጫዎች ሲያስታውቅ ለቆየው ህወሓት በኢህአዴግ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ አለመገኘት በያዘው የተቃውሞ ጉዞው ጉልህ ሊባል የሚችል ተጨባጭ እርምጃ እንደሆነ ይታመናል። ህወሓት በዚህ አቋሙ ፀንቶ ከኢህአዴግ ጋር ይለያያል? የኢህአዴግና የህወሓት ፍቺ እውን የሚሆን ከሆነ ፖለቲካዊና አገራዊ አንድምታው ምን ሊሆን ይችላል? የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች የብዙዎች መነጋገሪያ ከሆኑ ዋል አደር ብለዋል። • የኢትዮጵያ አየር መንገድ ''አሸባሪ" በተባለ ግለሰብ ችግር ገጠመው • የህወሓት አመራሮች ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ጋር ስለምን ጉዳይ ተወያዩ? የኢህአዴግ ውህደትን የሚደግፉት የግንባሩ አባሎችና አጋር ድርጅቶችም ሆኑ ህወሓት ኢህአዴግ እስከዛሬ በመጣበት መንገድ መቀጠል እንደማይችል ቢያምኑም ከዚህ ወዲህ ድርጅቱ እንዴት ይራመዳል? በሚለው ላይ መስማማት አልቻሉም። ባለፈው ቅዳሜ የተደረገውን የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እሁድ ዕለት ከህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ጋር ያደረጉት ውይይት ፍሬ አልባ መሆን የዚህ ምስክር ነው። ከዚህም በኋላ በነበሩት በቀጣዮቹ ቀናትም የሁለቱ ወገኖች ልዩነትና መካረር እንደቀጠለ ይመስላል። ኢህአዴግና ህወሃት፡ 'አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል' በተቃውሞ ፖለቲካ ውስጥ የቆዩት አቶ ሞሼ ሰሙ "ፖለቲካ እንደ ሒሳብ ይህ ከሆነ ያ ይሆናል የሚባል ስላይደለ ከዚህ ክስተት ውስጥ መጠቀም የሚቻልበት እድል እንዳለ ካመኑበት ሁለቱም ወገኖች ለንግግር ወደ ኋላ ሊመለሱ ይችላሉ" ብለው ያምናሉ። በተቃራኒው በጠላትነት ስሜት ወደ መወነጃጀል የሚሄዱ ከሆነ ለመነጋገር የሚኖረውን እድል ያጠፋሉ ይላሉ። "ከሁለቱም ወገን የሚጠበቀው ከስም መጠራራት፣ ከመወነጃጀልና አስቀያሚ መግለጫ ከማውጣት ሰከን ብለው ሁኔታዎችን መገምገም ነው። ያን ካደረጉ ሁል ጊዜ እድል አለ። እድሉን የሚወስኑት በተለይም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከዚህ በኋላ በሚያራምዱት ፕሮፖጋንዳ ነው" ይላሉ አቶ ሞሼ። ልዩነትና አለመግባባት ተፈጠረ ማለት አከተመለት፤ መነጋገር አይቻልም ማለት አይደለም። ልዩነቱ ደም ያፋሰሰ ሳይሆን የአሰራር፤ የርዕዮተ ዓለም ነው። ነገር ግን ይህንን ተቋቁመው በሰከነ መንገድ ነገሮችን መስመር አለማስያዝ የግንባሩ ፓርቲዎች መጥፊያም ሊሆን ይችላል የሚል ስጋታቸውንም ያስቀምጣሉ አቶ ሞሼ። ይህ ደግሞ ለአገሪቱም ለህዝቡም ከባድ ነው። • የ31 ዓመቱ ኢሕአዴግ ማን ነው? "ህወሓት ውስጥ ሆኖ እንጂ ወጥቶ አልነበርም መታገል የነበረበት" የሚል እምነት ላላቸው አቶ ሞሼ ህወሓት ቆርጦ ከኢህአዴግ የሚለይ ይመስልዎታል? የሚል ጥያቄ አቅርበን ነበር። "ህወሃት ብቻውን ኖሯል ከዚህ ቀደም፣ ከብአዴን፣ ከኦህዴድና ከደኢህዴን ጋር አብሮ ሰርቷል። ሌሎቹ ባልነበሩበት ሁኔታ እነዚህ ፓርቲዎች የአገሪቱን ፖለቲካ ሲያንቀሳቅሱ ኖረዋል። ትልቁ ነገር ራስን ከተጨባጭ ሁኔታ ጋር ማዛመድ ነው። በሌላ በኩል ከህወሓት ውጪ ነገሮች ይሰራሉ ወይ? ብሎ መጠየቅም ያስፈልጋል።" እሳቸው እንደሚሉት ራስን ከተጨባጭ ሁኔታዎች ጋር የማዛመድ ነገር እንዳለ ሆኖ ህወሓት እንደሚለው የትግራይ ህዝብ መቶ በመቶ ከህወሓት ጋር ከሆነ ለኢህአዴግ የትግራይን ሕዝብ ሥነ ልቦና ማግኘት ቀላል አይሆንም። • የብልጽግና ፓርቲ ከአማርኛ በተጨማሪ ኦሮምኛና ሌሎችም ቋንቋዎች የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ወሰነ ከህዝቡ ጋር ተነጋግሮና ተደማምጦ በኢትዮጵያ መፃኢ እድል ላይ ለመወሰን ያለው እድልም በጣም ጠባብ ይሆናል። ቁጥሩ ምንም ይሁን አንድም ክልል ከመንግሥት ጋር በሙሉ ልቡ አብሮ የማይሰራ ከሆነ ብዙ ጉዳቶች አሉት። "ያልተግባቡት ፓርቲዎች ናቸው ስለዚህም የትግራይ ሕዝብ ልቡ መሸፈት የለበትም። የትግራይን ሕዝብ ማጣትም ቀላል ዋጋ አይደለም ብዬ አምናለሁ" ሲሉ አቶ ሙሼ ይጠቅሳሉ። ለአቶ ሞሼ ልዩነቱ ዘላቂና ውስጣዊ አይደለም፤ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የኢህአዴግና የህወሓት ገመድ ተበጥሶ ይቀራል ብለውም አያምኑም። ይህ እምነታቸው የፓርቲ መሪዎቹ በረዥም የትግል ጉዞ ስላለፉ ለምክንያታዊነት ቦታ ይሰጣሉ በሚል እሳቤ ላይ የተመሰረተ ነው። ህወሓትን እንደ ተቃዋሚ? ህወሓት ከኢህአዴግ ከተለየ ቀጣይ እርምጃው ምን ይሆናል በሚለው ላይ የተለያዩ ሃሳቦች የተንፀባረቁ ሲሆን ተቃዋሚ ሆኖ ይቀጥላል የሚለው አንዱ ነው። አቶ ሞሼ ደግሞ "ከኢህአዴግ መውጣት ተቃዋሚ መሆን ነው ወይ?" ሲሉ ይጠይቃሉ። "ያኛውም ወገን ተቃዋሚ ሊሆን ይችላል። ህወሓት ሌሎችን አስተባብሮ መንግሥት ሊሆን የሚችልበት እድል አብቅቷል ማለትም አይደለም" ሲሉ ነገሮች በሌላኛው አቅጣጫ ሊሄዱ የሚችሉበትም እድል እንዳለ ነው ይላሉ። የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የህወሓት ጽህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጌታቸው ረዳ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የፓርቲው ቀጣይ እጣ ፋንታ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም በኢህአዴግ ሳይሆን በህወሓት፣ በደጋፊዎቹና በትግራይ ህዝብ የሚወሰን ነው ማለታቸው ይታወሳል። ትግራይን 'አምሳለ አገር' ማድረግ ባለፈው ሳምንት ትግራይን 'አምሳለ አገር' (Defacto State) የማድረግ ነገርን በተመለከት የህወሓት ልሳን በሆነው 'ወይን' መፅሔት ላይ የወጣው ጽሁፍ የኢህአዴግና የህወሓት ልዩነት መካረር ጥግን አመላክቷል ሊባል ይችላል። ይህም 'የትግራይ መገንጠል' የሚለውን ሃሳብ በአንድም ይሁን በሌላ መንገድ የብዙዎች መነጋገሪያ አጀንዳ አድርጎታል። በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህር የሆኑት አቶ መኮንን ፍስሃ ወይን ላይ የወጣው ጽሁፍ "ሙሉ በሙሉ የህወሃት አቋም ነው፤ አይደለምም ብሎ መደምደም ያስቸግረኛል፤ ነገር ግን የሚያሳየው አንድ ነገር ግን አለ" ይላሉ። ይህ ሃሳብ ወይን ላይ ከመውጣቱ በፊት ጥቂት በማይባሉ የትግራይ አክቲቪስቶች፤ ምሁራንም ጭምር በግልፅ ሲንፀባረቅ ቆይቷል። • ኢሕአዴግ እዋሀዳለሁ ማለቱን የፖለቲካ ተንታኞች እንዴት ያዩታል? አቶ መኮንን እንደሚሉት ህወሃት ትግራይን የመገንጠል ሃሳብ ጨርሶ የለውም ብሎ ማለት አይቻልም። ለእሳቸው ይልቁንም 'ተገድጄ ወደዚህ አማራጭ ፊቴን ላዞር እችላለሁ' የሚል ነገር ይታያቸዋል። ይህም ቢሆን ግን ህወሓት ብቻውን የሚወስነው አይደለም። እንደ አንድ ትግራዋይ በጉዳዩ ላይ የእሳቸው አቋም ምን እንደሆነ የጠየቅናቸው አቶ መኮንን "ታላቂቷን ትግራይ በታላቂቷ ኢትዮጵያ ነው የምፈልገው፤ ታላቅ ሲባል ሕዝብ ነው ታላቅ የሚሆነው" ነበር መልሳቸው። ቢሆንም ግን 'ትግላችን እየተቀለበሰ ነው፤ እየተገፋን ነው' የሚል ስሜት በትግራይ ሕዝብ ዘንድ በስፋት እንዳለ ያስረግጣሉ አቶ መኮንን። በትክክል ምን ያህሉ የትግራይ ሕዝብ መገንጠልን ይደግፋል? የሚለው ጥልቅ ጥናት የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ኢህአዴግ ካልተስማማ ይፈርሳል፤ መፍረስም አለበት ይህ ግን የኢትዮጵያን እጣ መወሰን የለበትም የሚል አቋም ያላቸው አቶ መኮንን "ሞቱ አልታወጀም እንጂ ኢህአዴግ ከሞተ ቆየ እኮ" ይላሉ። አባልም አጋርም ድርጅቶች በውህደቱ እኩል ይወስናሉ በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት የግንባሩን ውህደት ያጠናው ቡድን መሪ የሆኑት ዶ/ር ተመስገን ቡርቃ ከዚህ በፊትም ሲያራምዱ የነበረው የኢህአዴግን ፖሊሲና ስትራቴጂ ስለሆነ አባል ድርጅቶች ብቻ ሳይሆኑ አጋር ድርጅቶችም እራሳቸውን አፍርሰው በእኩል ደረጃ መጥተው ብልፅግና ፓርቲን እንደሚመሰርቱ ለቢቢሲ አብራርተዋል። "ኢህአዴግ ፓርቲውን መስርቶ የሚያመጣቸው ሳይሆን እኩል ተደራድረው የሚመሰርቱት ነው የሚሆነው። የእኛ ጥናት ይሄን ነው የሚያመለክተው እነሱ የሚወስኑትን እናያለን" ይላሉ ዶ/ር ተመስገን። ውህደቱ በይፋ ሊታወጅ ስለሚችልበት ጊዜ በተደረገው ጥናት ላይ የተቀመጠ ነገር መኖሩን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው ዶ/ር ተመስገን "ችግሮችን ለመፍታት እኛ አሁኑኑ ተዋሃዱ ነበር ያልነው፤ ግን ያው ውሳኔው የፖለቲካ ነው" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። ውህደትና የህወሓት ቀጣይ ዕጣ አገሪቱን ለሦስት አስርት ዓመታት ያስተዳደረውን ግንባር ጸንሶ በመውለድ ዋኛውን ድርሻ የሚወስደው ህወሓት በፈጠረው ድርጅት ቀጣይ ውህድ ህላዌ ላይ አብሮ እንደማይሳተፍ አሳውቋል። ቀሪዎቹ የግንባሩ አባላትና አጋር ድርጅቶችም ውህደቱን እውን ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ሂደቶችን በፍጥነት እያከናወኑ ነው። በግንባሩ ሥራ አስፈጻሚ ስብሰባ የጀመረው የውሳኔው ሂደት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በምክር ቤቱ ውሳኔ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ተሸጋግሯል። ከዚህ በኋላም ድርጅቶቹ ከአባሎቻቸው ጋር ወስነው የውህደቱን ጥያቄ ወደ ጠቅላላ ጉባኤው በመውሰድ የመጨረሻውን እልባት ይሸጡታል። ይህም እስካሁን በነበረው ሂደት እምብዛም እንቅፋት የሚገጥመው አይመስልም። • ህወሓት፡ ሃገራዊ ምርጫ የሚራዘም ከሆነ ትግራይ የራሷን ምርጫ ታካሂዳለች ህወሓትም እስካሁን ባለው አቋም ከቀጠለ በውህደቱ ላይ አሉኝ የሚላቸውን የሕግ ጥያቄዎች በማንሳት ሊሞግት ይችላል። ከዚህ ባሻገርም ከዚህ በፊት አንዳንድ አባላቱ እንደጠቆሙት ከሌሎች የፖለቲካ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት አዲሱን ውህድ ፓርቲ የሚገዳደር አገራዊ ግንባር አሊያም ጥምረት በመመስረት በቀጣይ ምርጫ ላይ ሊቀርብ እንደሚችል ይጠበቃል። እስካሁን በወሰዳቸው አቋሞች ግን ህወሓት እራሱን አክስሞ ከቀድሞ የወታደራዊና የፖለቲካ ትግል አጋሮቹ ጋር የብልጽግና ፓርቲ አባል የመሆን እድሉ በጣም የጠበበ ነው። ከዚህ አንጻር ኢህአዴግ በውህደት እርምጃው የሚቀጥል ከሆነ ህወሓት በውህድ ፓርቲው ውስጥ የመኖሩ ነገር እምብዛም የሚታሰብ አይሆንም። ለሁሉም ግን በቀጣይ ቀናት የፖለቲካ ቡድኖቹ የሚደርሱበት ውሳኔ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወሳኝ መስመሮችን የሚያሰምር ይሆናል።
news-45054662
https://www.bbc.com/amharic/news-45054662
የኃይለማርያም እና የመንግሥቱ ፎቶ ለምን በርካቶችን ግራ አጋባ?
የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ብዙዎችን ግራ ያጋባውን ፎቶ ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ አንስተውታል። ከሁለት ቀናት በፊት ከኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ጋር የተነሱትን ፎቶግራፍ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ከለጠፉ በኋላ በርካቶች ፎቶውን ከአስተያየታቸው ጋር በማህበራዊ ድረ ገጾች ላይ ሲቀባበሉት ነበር።
ፎቶው የተነሳው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በዚምባብዌ የተካሄደውን ምርጫ ለመታዘብ የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢ ቡድንን በመምራት ወደ ዚምባብዌ ካቀኑ በኋላ ነበር። ፎቶው በኢትዮጵያ ታሪክ ሁለት የቀድሞ መሪዎች አብረው ፎቶግራፍ ሲነሱ የመጀመሪያ በመሆኑ በበርካቶች ላይ ልዩ ስሜትን ፈጥሯል። • የቀድሞዎቹ መሪዎች ኃይለማርያም ደሳለኝና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ተገናኙ • መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ • ለፍርድ የቀረቡ አፍሪካውያን መሪዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ምን ተባለ? የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለምርያም ደሳለኝ ፎቶግራፉን ከፌስቡክ ገጻቸው ላይ ከማጥፋታቸው ቀደም ብሎ ''ከቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ጋር ተገናኝቻለሁ። ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ከተካሄደ በኋላ የቀድሞ የሃገር መሪዎች ለሃገር እድገት የተቻላቸውን አስተዋጽኦ ሲያበርካቱ ማየት እመኛለው'' ብለው ነበር። ይህ የፌስቡክ ፖስት ከሃይለማርያም ደሳለን የፌስቡክ ገጽ ላይ ተሰርዟል ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከተነበቡ አስተያየቶች መካከል ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኮሎኔል መንግስቱ ኃያለማርያም ጋር ፎቶ መነሳታቸውን የተቃወሙ ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ፎቶውን የተመለከቱ ቀላል የማይባሉ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች መንግሥቱ ወደ አገር ቢገቡ ደስታቸው እንደሆነ ገልጸዋል። ኮሎኔል መንግስቱ 'ስላደረሰው ጥፋት በህግ ሊጠየቅ ሲገባው እንዴት እውቅና ይሰጠዋል?' የሚል ቅሬታቸውን በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩ ነበሩ። አቤል አባተ የተባለ የትዊተር ተጠቃሚ ''በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ይህ ሌላ ለውጥ ነው'' ያለ ሲሆን አወል አሎ ደግሞ፤ ይህ ፎቶግራፍ እጅጉን ግራ ያጋባል። መንግሥታችን ስለ ፍቅር እና መግባባት ማውሳቱ መልካም ሆኖ ሳለ ይቅርታ እና ምህረትን ግን ለሁሉም የሚሰጥ አይደለም ብሏል። አንዲት ኤርትራዊት በትዊተር ገጿ ጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አህመድ ለኤርትራው ፕሬዘዳንት የሞቀ አቀባበል ሲያደርጉ 'እንዴት ከአምባገነን ጋር?' ሲሉ ብዙ ኤርትራውያን መቆጣታቸውን ከኃይለማርያምና ከኮሎኔል መንግስቱ መገናኘት ጋር አነጻጽራ ጽፋለች። የሁለቱን የቀድሞ መሪዎች በጥምርት ፎቶ መነሳት አሳፋሪ፣ ያልተገባ ሲሉ የተቹ እንደሉ ሁሉ ባለፈው ዘመን ብዙ ጥፋት ያጠፉ ሰዎች ይቅር ተብለዋል ለምን የኮሎኔል መንግስቱ በተለየ መንገድ ይታያል ሲሉ የጠየቁም አሉ። ይህ ፎቶግራፍ ለምን በርካቶችን አነጋገረ? ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም የመሩት የቀይ ሽብር ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ቀጥፏል። በዚህም ኮሎኔል መንግሥቱ በሌሉበት በዘር ማጥፋት ወንጀል የሞት ፍርድ እንደተወሰነባቸው ይታወሳል። ስለ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም በርካታ መጽሃፎችን የጻፉት እና በለንደን ሳውዝ ባንክ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ጋይም ክብረአብ ሁለቱ የቀድሞ መሪዎች መገናኘታቸው አስገራሚ ነው ምናልባትም በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር አበረታችንት የተከናወነ ነው ይላሉ። ኃይለማርያም እና መንግሥቱ እንዴት ሊገናኙ ቻሉ? አቶ ኃይለማርያም እና ኮሎኔል መንግሥቱ እንዴት ሊገናኙ እንደቻሉ ወይም የተገናኙበትን ምክንያት በሚመለከት የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም። ይሁን እንጂ በርካቶች የራሳቸውን ግምት ያስተጋባሉ። አቶ ጋይም ኃይለማርያም ዚምባብዌ ሳሉ ኮሎኔል መንግሥቱን እንዲጎበኘ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ሳይጠየቁ አይቀርም ሲሉ ይጠረጥራሉ። ''ያለ ዓብይ ፍቃድ በምንም አይነት ሁኔታ ኃይለማርያም መንግሥቱን ሊያገኙ አይችሉም'' በማለትም ይከራከራሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ በቅርቡ በነበረቸው መድረክ ላይ ለኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ይቅርታ ልናደርግ እንችላለን ስለማለታቸውም ተሰምቶ ነበር። በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ከግምት ውስጥ በማስገባት ''መንግሥቱን ወደ ሃገር እንዲመለስ ቢያደርጉ ብዙም አይደንቀኝም'' ይላሉ አቶ ጋይም። ይሁን እንጂ በርካቶች ለኮሎኔል መንግሥቱ ይቅርታ ማድረግ ''ፍትህን ማጓደል'' ነው ይላሉ። አቶ ጋይም ጨምረውም ''መንግሥቱ ወንጀለኛ ነው'' ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረወዋል። ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ከሃገር ሸሽተው ከወጡ በኋላ ዚምባብዌ ላለፉት ሦስት አስርት ዓመታት ለሚጠጋ ጊዜ መኖሪያቸው ሆና መቆየቷ ይታወቃል።
news-45976660
https://www.bbc.com/amharic/news-45976660
መዝገቡ ተሰማ፡ ተፈጥሮን በብሩሹ የሚመዘግበው ሠዓሊ
ተማሪ እያለ ጠረጴዛ ላይ ሥዕል በመሳሉ በተማሪዎች ፊት ተገርፏል፤ የሒሳብና የአማርኛ ደብተሮቹን ራስጌና ግርጌ በሥዕሎቹ በማሳበዱ ኩርኩም ቀምሷል።
የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን፤ ካርታ፣ የሰው አካል ክፍሎች፣ ሌሎች በሥዕልና በሞዴል የሚገለፁ አጋዥ ቁሳቁሶችን በመሥራትና ማስታወቂያዎችን በድርብ ጽሑፍ በመጻፍ ለትምህርት ቤቱ ውለታ ውሏል። እርሱ ራሱ ለምን እንደሆነ ባያውቀውም ድሮ ድሮ እግር ኳስ የሚጫወት ልጅና ደብተር የያዙ ልጆችን መሣል ያዘወትር ነበር። አድናቂዎችን ማፍራት የጀመረውም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ነው ታዲያ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ስሙ ገኗል፤ ስንቶቹን አስደምሟል፤ ስንቶቹን በማመንና ባለማመን አሟግቷል! መዝገቡ በሥራዎቹ ትንግርት ነው። ተፈጥሮን ይገልጣል፣ ስሜትን ያንጸባርቃል፣ ሥነ ልቦናን ያሳብቃል፣ ቀለሞቹን በብርሹ አጥቅሶ ሸራዎቹ ላይ ያፋቅራል። ሥራዎቹን ያዩት ሁሉ "ኦ! መዝገቡ!" የሚሉት ወደው አይደለም። • ስለኢትዮጵያ የቤተ ክርስቲያን ስዕሎች ምን ያህል ያውቃሉ? ሥዕሎቹ በካሜራ እንጂ በሠዓሊው ጣቶች የተገለጹ አይመስሉም። እርሱ ግን ማነው ካሜራን ከሥዕል ያላቀው? ይላል። "በሥልጣኔ ታሪክ ፎቶግራፍ የመጣው ከሥዕል በኋላ ነው፤ሥዕልን ፎቶግራፍ ይመስላል ማለት ማሳነስ ነው" ሲል የሥነ ሥዕልን ታላቅነት ይሞግታል። "በተለይ የእኛ ማኅበረሰብ ከሥዕል ይልቅ ፎቶግራፍን ነው የሚያውቀው" የሚለው ሠዓሊው "አድናቆትን ለመግለጽ፤ 'እውነተኛ ይመስላል' የምንለውም ለዚሁ ይመስለኛል" ይላል። • ልዑሉ የኻሾግጂን ገዳዮች ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ዛቱ ይህንን ሲል የፎቶግራፍን ጥበብ አንኳሶ አይደለም ታዲያ። አንዳንዴ በሥዕል ለመግለጽ የተፈለገን አካል ወይም ቦታ ሙሉ ለሙሉ ማስታወስ ሊቸግር ስለሚችል በጣም ጥልቅና ዝርዝር ነገሮችን ለመሥራት የግድ ፎቶግራፍ አሊያም ሞዴል መጠቀም ሊያስፈልግ እንደሚችል ያስገነዝባል። የቀለም አወቃቀር፣ ብርሃንና ጥላ ከልምድ የሚመጣ በመሆኑ አይቸገርበትም፤ ነገር ግን ውህደት (Composition) ማዋቀሩ የምንጊዜም ተግዳሮት በመሆኑ ዘወትር መጠበብን ይጠይቀዋል። የገሃዱን ዓለም የማስመሰሉን ጥበብ ከተሻገረው ግን ዓመታት ተቆጥረዋል። የሥዕል አቡጊዳ ገና በልጅነት ዕድሜው አድናቆትንም ግሳጼንም በማስተናገድ ያለፈው መዝገቡ፤ የሥዕል ሥራን 'ሀ...ሁ' ያለው በትምህርት ቤት እንደሆነ ይናገራል። ያኔ ድሮ ከመምህራንና ከተማሪዎችም አድናቆት ይጎርፍለትም ነበር፤ ደብተርህን ለምን ታቆሽሻለህ ከሚል ኩርኩም በላይ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ብትገባ የሚሉት ቁጥራቸው ይበረክት ነበር። በወቅቱ የሚያበላና የማያበላ ሥራ ብሎ የሚያስብ ጭንቅላት አልነበረውም፤ ወላጆቹም ይህንን ከቁብ አልቆጠሩትም፤ አንድም ቀን ሳት ብሏቸው 'ይሄ የምትሞነጫጭረውን ምናምንቴ ተው!' ሲሉ አልገሰጹትም። ያደገው ገጠር አካባቢ በመሆኑ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት ስለመኖሩ ከነ አካቴው አያውቅም ነበር። ሥዕል ሰዎች ባላቸው ተሰጥዖና በልምድ የሚሠሩት እንጂ በትምህርት ያገኙታል ብሎ ስለማሰቡም እንጃ። "አንድ ሰው ልምምድ አድርጎ በትምህርት ሲደገፍ ዐይን የሚይዝ ጥሩ ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል፤ አድናቆትን የሚያስቸር፣ በሰዎች ስብዕና ላይ ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችል፣ ሚዛን የሚደፋ ነገር መሆን አለበት" ይላል። እንዲህ ዓይነት ሥራዎችንም መሥራት የጀመረው የሁለተኛ ዲግሪውን ካገኘ በኋላ እንደሆነ ይናገራል። የመጀመሪያዬ የሚለው ሥራውም "ቤተሰብ" ይሰኛል፤ ሦስት ክፍሎችም አሉት፤ ካደገበት ማኅበረሰብና ቤተሰብ ተቀድቶ የተሣለ ነው። • "የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ "ገጠር ውስጥ ቤተሰብ የሚለው ሐሳብ በራሱ ሰፊ ነው፤ የቤት እንስሳት ሁሉ እንደ ቤተሰብ አባል ይቆጠራሉ፤ የእገሌ ልጅ እንደሚባለው፤ የእገሌ ፍየል፣ የእገሌ በሬ ይባላል" የሚለው ሠዓሊው ይህንን ለማጉላት ሥዕሉን እንደሠራው ያስረዳል። በማኅበረሰቡ ውስጥ ወንድ ሴቶችን የመጠበቅ፣ የቤተሰቡንና የራሱን ክብር የማስጠበቅ እሴት ይሰጠዋል። ይህንንም የሚያጎላ ሐሳብ ተካቶበታል - በበኩር ሥራው። ተፈጥሮን የሚመዘግበው መዝገቡ መዝገቡ እውናዊ (Naturalistic/ Realistic/ Expressionist) የሥዕል አሳሳል ዘዴን ከሚከተሉት ሰዓሊያን በጉልህ ይጠቀሳል። በኢትዮጵያ የሥዕል ታሪክ የትኛው የአሳሳል ዘዴ ተቆናጦ እንደቆየ ለመናገር ቢያስቸግርም ለምሳሌ በደርግ ዘመን የእውናዊ የአሳሳል ዘዴን እንደ አንድ የፕሮፖጋንዳ ጥበብ ለዐሥራ ሰባት ዓመታት ይጠቀሙበት ነበር። በሠዓሊና ሃያሲ ስዩም ወልዴ ግለ ታሪክ መጽሐፍ (ኩርፊያ የሸፈነው ፈገግታ) በደርግ ጊዜ የሌሎች አገራት መሪዎችን ለመቀበል የመሪዎቹን ምሥል በትልቅ ሸራ ላይ ይሥሉ እንደነበር ተጠቅሷል። ይህንንም ለንግግሩ ዋቢ ማድረግ ይቻላል። እርሱ ግን ገበያውንና ጊዜውን አይቶ ሳይሆን የልጅነት ህልሙ እንደሚመራው ይናገራል። ተወልዶ ባደገበት አካባቢ ያለው የመንገዱ ጠመዝማዛነት፣ የምንጮቹ፣ የዳገቱ፣ የመስኩ፣ የዕጽዋቱ፣ የከብቶቹ…በልጅነት አዕምሮው መዝገብ ሰፍረዋል፤ ይህም አሁን ለሚከተለው እውናዊ የሥዕል አሳሳል ዘዴ መነሻ እንደሆነው ይገልጻል። በወቅቱ አካባቢውን እንዲያይ፣ እንዲያደንቅ፣ እንዲመረምር፣ የፈለገበት ቦታ እንዲሄድም ቤተሰቦቹ ይፈቅዱለት ነበር። ይህም ከመልክዓ ምድሩ ጋር ያለውን ትስስር አጠናክሮለታል። ከዚህም ባሻገር የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤቱ እውናዊ ሥራዎች እንዲሠሩ የሚጠይቅ ነበር፤ እርሱን አሟልቶ ያልሠራ ተማሪ መቀጠል አይችልም ነበር፤ ስለሆነም የትምህርት ሥርዓቱ ብርታት ሆኖታል። የሥዕል ሥራዎቹ ረቂቅ ስሜቶችና ሥነ ልቦና ይንጸባረቁበታል። "ይህ ግን በአንድ ጊዜ ተሳክቶ የሚመጣ አይደለም" የሚለው መዝገቡ ሁል ጊዜ በዝርዝር የሚገለፁ ነገሮችን ከመሣል በፊት "ጥናትና ሙከራ አደርጋለሁ፤ የሰው ባህሪ ከነ መልኩ መዋሃዱን በተደጋጋሚ አጤናለሁ፤ ውጤታማ እስከሚሆን መሥራትንም እመርጣለሁ" ብሏል። አውታረ መጠን (3D) ይህን አሳሳል ዘዴ ሠዓሊና ሃያሲ ስዩም ወልዴ አውታረ መጠን ይሉታል። በጥንት ግሪክ ሠዓሊዎች ይተገበር ነበር፤ ከዚያም በህዳሴው ዘመን እንደ ዋና የአሳሳል ዘዴ ይጠቀሙበት ነበር፤ አሁን ባለንበት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ደግሞ ተቀባይነት ከማጣቱም አልፎ ሠዓሊዎች ሥዕል ሁለት አውታረ መጠን ነው፤ በመሆኑም ጠፍጣፋ ሆኖ መቀመጥ አለበት በሚል ሃሳብ እንደሚሟገቱ ያብራራል። ሦስት አውታረ መጠን የሚያስመስል( Illusion) እንዳይኖር ጥረት ያደርጋሉ፤ ነገር ግን ቀለማቱ ብቻ የሚፈጥሩትን የቀለም ክፍተት ማስወገድ አይቻልም ይላል። የሸራ ቅርፅ በራሱ የመስኮትነት ባህሪ አለው። መስኮት ደግሞ የሚያሳየው ከሸራው ቀጥሎ እንጂ ከሸራው ወዲህ አይደለም ሲል ግልጽ ምሳሌ ያጣቅሳል። • ኢትዮጵያዊያን በህጋዊ መንገድ ለሥራ መሄድ የሚችሉባቸው ሃገራት የትኞቹ ናቸው? "የገሃዱ ዓለምም ሦስት አውታረ መጠን እንዲኖረው ተደርጎ ነው የተፈጠረው፤ ቋሚ፣ አግዳሚና ጥልቀት ናቸው። ይህንንም ወደ ሸራ ወስዶ ለማምጣት በሚፈለግበት ጊዜ የጥቁረትና ንጣት ግንኙነት፣ የሞቃትና የቀዝቃዛ ቀለማት ውህደት፣ የመቅላትና ሰማያዊ በማድረግ ወደ እውነታው ዓለም የተጠጋ እንዲሆን አድርጎ መሳል ይቻላል" ሲል ያብራራል። በመሆኑም ይህንን ጥበብ ለማስወገድ ጥረት ከማድረግ ይልቅ ማጉላቱ ወደ እውነታው ያስጠጋል በሚል ለዚህ የአሳሳል ዘዴ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ጀመረ። በጊዜ የነገሰው 'ንግሥ' የንግሥ በዓል በድምቀት የሚከበር ሃይማኖታዊ በዓል ነው፤ ሰዎች አዳዲስ ልብስ ለብሰው፤ አጊጠው ፤ እየጨፈሩ፤ እየዘመሩ ያከብሩታል። ይህ የልጅነት የንግሥ በዓል ትውስታው በሸራው ላይ ያሰፍረው ዘንድ ወትውቶታል። የንግሥ በዓልን ቁልጭ አድርጎ የሚሳየው ሥዕል 10 ስኩየር ሜትር ሸራ ላይ ያረፈ ሲሆን በሥዕሉ ላይ በርካታ ሰዎች ያሉበትና የየራሳቸው የፊት ቅርጽ፣ አለባበስ፣ የስሜት አገላለጽ በዝርዝርና በጥልቀት የተሠራ ነው። የጥናት ጊዜውን ሳይጨምር ቀለሙን ብቻ ሠርቶ ለማጠናቀቅ ሦስት ዓመታትን ወስዷል። የሥዕል ሥራዎቹ ለዕይታ በቀረቡበት አውደ ርዕይ የይደገም ጥያቄን ያስተናገዱ ናቸው፤ በአገር ውስጥ በሚገኙ ቅንጡ ሆቴሎችም ሥራዎቹ ይገኛሉ። "እንደ ንግሥ ዓይነት ትላልቅ ሥራዎችን ሽጬም ሆነ ለመሸጥ አስቤ አላውቅም፤ በዋጋ ተምኛቸው ባላውቅም እንደየ ጊዜውና አንደ ዋጋ ግሽበቱ ተለዋዋጭ መሆኑ አይቀርም" ይላል ሠዓሊ መዝገቡ። ለዚህም በአገር ውስጥ ለጥበብ የሚሰጠው ትኩረትና ለተመልካቾች ቅርብ የሚደረግበት ልምድ እምብዛም አለመሆኑን ያነሳል። "በሌሎች አገራት የሥዕል ሥራዎችን ማሳያ ቦታ አለ፤ ለመሸጥም አስማሚዎች አሉ፤ ዋጋም የሚተመነው በእነርሱ አማካኝነት ነው፤ አገር ውስጥ ግን ጠንካራ የሥዕል ማሳያ 'ጋለሪ' እንኳ የለም፤ ስለዚህ ዋጋው ይሄን ያህል ነው ማለት አልችልም" ሲል ምክንያቶቹን ያስረዳል። ሥዕሎችም እንደ ሰው ዕድል አላቸው ብሎ የሚያምነው መዝገቡ እንደ ልጆቹ የሚሳሳላቸው ሥራዎቹ ከእርሱ ጋር መቆየታቸው ይመርጣል። • የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰ ብሔር- አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ከዚህ ቀደም ባሳያቸው ሁለት የሥዕል አውደ ርዕዮች ሥራዎቹ በሰዎች ላይ የፈጠረው ስሜት እንዳሳሳውና ማበረታቻ እንደሆነውም ይናገራል። አሁን በሚያስተምርበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የርሱን ፈለግ የተከተሉ ተማሪዎችን ማፍራት ችሏል፤ በጎ ተፅዕኖም እንዳደረገ ይናገራል። የመዝገቡ 'ሙድ' በተለይ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ደራሲዎች፣ ሠዓሊዎች ፣ ሙዚቀኞች፤ ሥራዎቻቸውን የሚሠሩበትና ፍላጎት የሚፈጥሩ መልካም አውድ 'ሙድ' ይፈልጋሉ። ገጣሚ፣ ደራሲና የመብት ተሟጋች ማያ አንጀሎ ምንም እንኳን ቤት ቢኖራት ለመጻፍ የሆቴል ክፍል ትከራይ ነበር። ጆርጅ ኦርዌል አልጋ ላይ ወይም ሶፋ ላይ በጀርባው ጋደም ማለትን ሲመርጥ በተቃራኒው ቻርለስ ዲከንስ ቆሞ መጻፍ ይመቸዋል። ቪክቶር ሁጎ ልብሱን አወላልቆ እርቃኑን ካልሆነ የሥነ ጽሑፍ አድባር አትጠራውም። ፈረንሳዊው የልቦለድ ጸሐፊ ባልዛክ በቀን 50 ስኒ ቡና ካልጠጣ የጥበብ አውሊያዎች ዝር አይሉለትም ነበር። መዝገቡስ? "የራሴ ስንፍና፣ የመሥራት ፍላጎት፣ ጥንካሬና ጉድለት ካልሆነ በስተቀር ምንም የሚረብሸኝ ነገር የለም" ይላል። • የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው? ሥዕሎቹን ለመሥራት የትም መሄድ፣ ምንም ማድረግ አይጠበቅበትም። ከቤተሰቦቹ ጋር ተመካክሮ ፈቃድ በማግኘቱ የሥዕል ስቱዲዮውን የመኖሪያ ቤቱ ሳሎን ውስጥ አድርጓል። ልጆች ቢቦርቁ፣ ዘመድ አዝማድ ቢያወራ፣ ቡና አጣጭ ቢያሽካካ ከጀመረው ሥራ አንዳችም የሚያናጥበው ምድራዊ ኃይል የለም።
news-45470149
https://www.bbc.com/amharic/news-45470149
2010 ያልተጠበቁና ተደራራቢ ክስተቶች የታዩበት ዓመት
ተሰናባቹ 2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መልክዓ ምድር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ደረጃ በፋታ አልባ ድርጊቶች የተሞላ እንዲሁም ከፍተኛ ለውጦችን ያግተለተለ እንደነበር መስማማት ይቻላል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቅቀውበታል፣ ሦስት ዓመት ባለሞላ ጊዜ ለሁለተኛ ጊዜ አስቸኳይ ጊዜ ታውጆበታል፣ የቆይታ ጊዜውን ሳያጠናቅቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተነስቶበታል። በኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) ፊታውራሪነት ከቀደሟቸው ሁለት መሪዎች በአቀራረብም በአቋምም እንደሚለዩ የተነገረላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አራት ኪሎ ቤተ መንግሥት ገብተው ተሰይመውበታል። በተለያዩ የስልጣኖች መንበሮች በርካታ ዓመታትን ተቀምጠው የቆዩ ጎምቱ ሹማምንቶች ተሰናብተውበታል፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ እና ከፖለቲካ ተሳትፎ ወይንም አቋማቸው ጋር በተያያዘ እንደታሰሩ የተነገረላቸው ግለሰቦች የወህኒ አጥሮችን ለቀው ወዳጅ ዘመዶቻቸውን ተቀላቅለውበታል፤ ጥቂት በማይባሉ ማረሚያ ቤቶች ሲፈፀሙ የከረሙ የሰብዐዊ መብት ጥሰቶች ወደ ህዝብ ዓይኖች እና ጆሮዎች ደርሰውበታል። • የዓመቱ የቢቢሲ አማርኛ ተነባቢ ዘገባዎች • የ2010 የጥበብ ክራሞት ኢህአዴግ እና በውስጡ ያቀፋቸው አራት ፓርቲዎች ላዕላይ አመራሮች የሚያልቁ በማይመስሉ ተከታታይ ጉባዔዎች ተጠምደውበት ባጅተዋል፤ ክልሎች (ትግራይ፣ የደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ ሶማሌ) እና የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር መራኄ መንግሥታቶቻቸውን ቀይረውበታል፤ የገዥው ፓርቲ የውስጥ ሽኩቻ ማስተባበል የማይቻልበት ደረጃ ደርሶበታል፤ የክልል ፕሬዚዳንት ከስልጣናቸው ወርደው ተወንጅለውበታል። አራቱ ፓርቲዎች ሕዝባዊ ምስላቸውን ለመቀየር ተውተርትረውበታል፤ ገሚሶቹ ሹማምንትን ከመለዋወጥም በዘለለ ስምና አርማቸውን በአዲስ ለመተካት እስከመዳዳት ደርሰዋል። ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን፣ አምደኞች እና ጸሐፍት በቅርብ ዓመታት ከለመዱት መሳደድ እና መታፈን መላቀቅ ይሰማቸው እንደያዘ ብስራት ተናግረውበታል። የተዘጉ ድረ ገፆች ተከፍተውበታል፤ ማንም ዜጋ እንዳይታደማቸው መንግሥታዊ የተዓቅቦ ድንጋጌ ታውጆባቸው የነበሩ የብዙኃን መገናኛዎች ነፃ ተለቅቀውበታል፤ ውጭ የነበሩ ወደ አገር ቤት ተመልሰውበታል፤ ጽሕፈት ቤት ከፍተውበታል። የፖለቲካ መሪዎች፣ የመብት ተሟጋቾች፣ የሕዝባዊ ንቅናቄ አሿሪዎች እና አስተባባሪዎችም እንዲሁ ወደ አገር ቤት ተመልሰውበታል፤ ደጋፊዎቻቸው ወትሮ የሚያስወነጅሉ ሰንደቅ ዓላማዎችን ይዘው ተቀብለዋቸዋል። የተቃውሞ ቡድኖች ከሽብር መዝገብ ላይ ስማቸው ተሰርዞበታል፤ እነርሱም በፋንታቸው የነፍጥ ትግል በቃን ብለው አውጀውበታል፤ የሽብር ሕጉን ጨምሮ ሌሎችም አፋኝ ናቸው የተባሉ ሕግጋት ማሻሻያ ሊደርግባቸው ሽር ጉድ መጀመሩ ተግልፆበታል። ዐብይ አህመድ፡ ያለፉት 100 ቀናት በቁጥር የፖለቲካ ገው ገጭ መብዛት ምጣኔ ኃብቱ ላይ ጫና መፍጠሩ ተነግሮበታል፤ ለግሉ ዘርፍ ተከርችመው የቆዩ መንግስታዊ የልማት ድርጅቶች ለሽያጭ በራቸውን ሊከፍቱ ተሰናድተውበታል፤ በየዘርፉ በርካታ ኮሚቴዎች እና ቦርዶች ተቋቁመውበታል። ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ለሁለት አስርት ዓመታት ፀንቶ የቆየው ጠላትነት ተደምድሞ አዲስ ወዳጅነት ተኮትኩቶበታል፤ ከሌሎችም የቀጠናው አገራት ጋር ትስስር ሲጠነክር ተስተውሎበታል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የግንባታ ሒደት የተሰነቀረበት ቅርቃር ግልጥልጥ ያለ መስሎበታል፤ የግንባታው መሪ በመዲናይቱ ዋና አደባባይ መኪናቸው ውስጥ ሞተው ተገኝተውበታል፤ ፖሊስ በምርመራየ ራሳቸውን እንደገደሉ ተገንዝቤያለሁ ቢልም በዚህ ድምዳሜ ላይ ሕዝባዊ መከፋፈል ጎልቶ ታይቷል። አገሪቱ በተጋነነ ተፈጥሯዊ አደጋ ባትላጋም፤ በዓመቱ ሁለት ሚሊዮን ገደማ ዜጎችን ያፈናቀሉ ብሔር ተኮር ግጭቶች በየስፍራው ተለኩሰዋል፣ ተጋግለዋል፤ ተፈናቃዮቹን የማስፈር እና/ወይንም ወደቀደመ ቀያቸው የመመለስ ፈተና የመንግሥት ጫንቃ ላይ ወድቆበታል። ሁለቱ ትልልቅ የአገሪቱ ኃይማኖቶች የኦርቶዶክስ ክርስትና እና እስልምና በመሪዎቻቸው መካከል የነበሩ ቁርሾዎች ረግበውበታል፤ ወደ እርቅም ተጉዘውበታል። እንዲያም ሆኖ ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች የሰርክ ክስተት እስኪመስሉ ተደጋግመውበታል፤ ብሔረተኛነት ይበልጥ ሥር የሰደደ መስሏል። የፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ፉክክሮች ባንዲራን በመሳሰሉ ትዕምርቶች ላይ ከርረውበታል። • የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አዲስ ምዕራፍ • የዲያስፖራው አንድ ዶላር እነዚህ ሁሉ ክስተቶች የማሰቢያ እልባት እንኳ በማይሰጥ ፍጥነት ተግተልትለው መከወናቸው ቆም ብሎ ተራዛሚ ፋይዳቸውን ለመረዳት፣ አንድምታቸውን ለመገምገም እና አቅጣጫቸውን ለመተንበይ ዕድል የሚነፍግ መሆኑ አልቀረም። ይሁንና 2010 በኢትዮጵያ ፖለቲካዊ መስክ ላይ በልዩነት ከሚጠቀሱ ዐበይት ዓመታት መካከል አንዱ ሆኖ ወደፊት መወሳቱ እንደማይቀር ምክንያታዊ የሆነ ግምት መስጠት ይቻላል። ዓመቱ ጷጉሜ አምስት ቀን የቆይታ ጊዜውን ድምድሞ ለቀጣዩ ዱላውን ሲያቀብል ግን አብሮ የሚያስረክባቸው አንገብጋቢ ጥያቄዎች መኖራቸውም አይታበልም። ኢህአዴግ አለ ወይ? ባለፉት ሦስት ዓመታት ኢትዮጵያ በሕዝባዊ ተቃውሞዎች ስትናጥ እና መንግሥትም እነዚህን ተቃውሞዎች ለመቆጣጠር ሲውተረተር፥ ገዥውን ፓርቲ ባዋቀሩት አራት ብሔር ተኮር የፖለቲካ ቡድኖች መካከል ነፋስ መግባቱ ግልፅ ይሆን ጀምሯል። በተለይም ተቃውሞዎቹን ገንነው የነበሩባቸውን የኦሮሚያ እና አማራ ክልሎችን የሚወክሉት የኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) እና የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) አመራሮች፣ አባላት እና ደጋፊዎች ተቃውሞዎቹን ያፋፍማሉ በሚል ከገዛ ጠቅላይ ፓርቲያቸው እንዲሁም ከኢህአዴግ ጥምረት መስራች ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በይፋም ባይሆን በትችት ሲሸነቆጡ ይደመጥ ነበር። ቆይቶም በተለይ ኦህዴድ ከገዥው ፓርቲ አባልነት ይልቅ ተቃዋሚ ፓርቲ እየመሰለ መጥቷል የሚሉ ተንታኞች አልጠፉም ነበር። የኦህዴዱ ሊቀመንበር ዐብይ አህመድ የኢህአዴግን አውራ ስልጣን የተቆናጠጡበት ሒደት እና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላም ያስጀመሯቸው የለውጥ እና የማሻሻያ እርምጃዎች በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያሉትን ስንጥቃቶች ሲያጠቡ አልተስተዋሉም። አሁን ያለውን የኢህአዴግ አሰላለፍ ለውጥ ደጋፊዎች እና ለውጡን ተቃዋሚዎች በሚል ጅምላ ክፍፍል መድቦ መናገር እየተለመደ ቢሆንም አራቱንም ፓርቲዎች የሚሻገር በአመለካከት ላይ ብቻ የተመሠረተ ምደባ ብቻ ከመምሰሉ ይልቅ ህወሓትን በአንድ ወገን ኦህዴድን፣ ብአዴንን እንዲሁም በርካታ ላዕላይ አመራሮቹን በዚሁ ዓመት የቀየረውን የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ሕዝቦች ንቅናቄን (ደኢህዴን) በሌላ ወገን መለያነቱ የሚያይል ይመስላል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ 100 የሥራ ቀናት በቁጥር ሲቀመጡ ምን ይመስላሉ? በየፓርቲዎቹ ያሉት ነባር አመራሮች መገለላቸው፤ ኢህአዴግ በዐብይ አህመድ መሪነት ከያዛቸው አዳዲስ የአመለካከት መስመሮች ጋር ተዳምረው የወትሮ መልኩ በአያሌው በመቀየሩ የወትሮ ተቃዋሚዎቹ ሙገሳ ሲዘንብለት ትችት የሚሰነዘርበት በአብዛኛው ከቀድሞ አሞጋሾቹ ሆኗል። የአራቱ ፓርቲዎች ግንኙነት ቀጣይ መልኮችን ጊዜ የሚገልጣቸው ቢሆንም ባለፈው መንፈቅ የታየው ኢህአዴግ በቀደሙት ሃያ ሰባት ዓመታት ከነበረው ኢህአዴግ ስሙ እና አርማው ሲቀሩ በብዙ መስፈሪያዎች የተለየ ቀለም እንዳለው መከራከር ይቻላል። ፓርቲው በአንድ ወቅት ሊያደርገው ይችላል ሲባል እንደነበረው ከግንባርነት ወደ ውህደት ይሸጋገራል? ከአባል ፓርቲዎቹ መካከል የሚቀነሱ ይኖራሉ? የሚጨምራቸው ሌሎችስ? በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በአስተዳደራቸው ቃል የተገቡ የተቋማዊ እና ህጋዊ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚሆኑ ከሆነ በፓርቲው ቁመና ላይ ምን ዓይነት ተፅዕኖ ሊፈጥሩ ይችላሉ? ጊዜ የሚመልሳቸው ጥያቄዎች ናቸው። ቅራኔዎች እንዴት ይታረቁ? በአጎራባች ወረዳዎች፣ ዞኖች እና ክልሎች መካከል ግጭቶች እየተከሰቱ ጥቂት የማይባሉ ዜጎች ህይወት ጠፍቷል። በአንዳንድ ግጭቶች ወቅት የታዩ አሰቃቂ ጭካኔዎች የችግሩን አሳሳቢነት አጉልተው አሳይተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም ግጭት በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ተጉዘው ነዋሪዎችን አነጋግረዋል፣ አመራሮችን ወቅሰዋል፣ ይህንን ተከትሎም ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁ እንዲሁም ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የተደረጉ ሹማምንት አሉ። በግጭቶቹ አለንጋ የተሸነቆጡ ብዙኃን ግን ህይወታቸው እንደተናወጠ ነው ዓመቱን የሚሰናበቱት፤ በልዩ ልዩ መስኮች መልካም ትልሞችን እንደመተረ የሚናገረው እና በበርካቶችም የሚመሰከርለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አስተዳደር ላይ ማዲያት የሚያስቀምጥ እውነታም ነው። በዜጎች ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ ነፃነትን የሚቀፈድዱ እና ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶች አዲስ ክስተት ባይሆኑም ከወትሮው በተለየ መደጋገማቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የሰላም እና የአብሮነት መልዕክቶች ጋር በቀጥታ የሚፃረሩ መሆናቸው ግልፅ ነው። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? • ጀዋር እና ዐብይ ምን ተባባሉ? በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል ቁርሾ እየከረረ ሲሄድ የተስተዋል ሲሆን፤ ይህንንም ተግ ለማስባል በክልል መንግሥታቱም ሆነ በዜጎች መካከል የሚያመረቃ ሥራ ሲከናወን ታይቷል ማለት አይቻልም። በሌላ በኩል መዲናዋ አዲስ አበባ ያለፉትን ሦስት ወራት በፈንጠዝያ ውቅያኖስ ተጥለቅልቃ ብታሳልፍም፤ በዚያውም ልክ የተፎካካሪ ፖለቲካዊ አስተሳሰቦችን ፍልሚያ ስታስተናግድ ቆይታለች። ከስያሜዋ እስከሚውለበለቡባት ሰንደቅ ዓላማዎች ድረስ የመፃኢ ሙግቶችን አመላካች ቅድመ ጥቁምታ ሊባሉ የሚችሉ ሙግቶች በነቢብ ብቻም ሳይሆን በገቢር ተስተናግደውባታል። ልዩ ልዩ አቋም ያላቸው፤ በተለያዩ የአደረጃጀት መንገዶች የተዋቀሩ በርካታ ፖለቲካዊ ቡድኖች ወደ አገር ቤት በአካልም በኃሳብም ሲመለሱ ይዘዋቸው የሚመጡ ተፋላሚ ምልከታዎችን ማስታረቅ ቀጣዩ ፈተና የሚሆን ይመስላል። ቀጣዩ ምርጫ በተያዘለት የ2012 ዓ.ም የሚከናወነ ከሆነ ገዥውም ሆነ ተቃዋሚዎቹ ፓርቲዎች ከመጪው ዓመት ቢያንስ የተወሰነውን ክፍል በዘመቻ እንደሚያሳልፉት መገመት ይቻላል። ዘመቻዎቹ እነዚህን ቅራኔዎች ይብሱኑ አራግበዋቸው ውጥንቅጥ እንዳይፈጠር የሚሰጉ አካላት አሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አስተዳደራቸው ይህንን ስጋት መቅረፍ ይችሉ ይሆን? የአገሪቱ ተቋማት እና ፖለቲካዊ ባህል የፍላጎቶችን ግጭት የማስተናገድ አቅም አዳብረዋል? ሌሎች የጊዜን መልስ የሚሽቱ ጥያቄዎች ናቸው።
47797190
https://www.bbc.com/amharic/47797190
በአፋር ክልል በተፈጸመ ጥቃት የሰው ህይወት መጥፋቱ ተሰማ
መጋቢት ሰኞ 16 እና መጋቢት ማክሰኞ 17 በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ከጎረቤት ሀገራት መጡ የተባሉ ታጣቂዎች ጥቃት አደረሱ። ጥቃቱ የተፈፀመው ከሶማሌ ላንድ እና ከጅቡቲ አዋሳኝ አካባቢዎች በኩል በገቡ ኃይሎች መሆኑን የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ አህመድ ኻሌይታ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የሎጊያ ነዋሪ የሆኑት አቶ አብዱ አሊ መሀመድ ይህ ጥቃት ከአሳይታ 80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኝ አዋሳኝ ቀበሌ ላይ እንደተፈፀመ አረጋግጠዋል። አክለውም ጥቃት አድራሾች በተለያየ ጊዜ ገዳማይቱና እንዱፎ በሚባል አካባቢ ገብተው እንደነበር ያስረደሉ። በአካባቢው መከላከያ መኖሩን የሚያስታውሱት አቶ አብዱ ከሁለት ወር በፊት እንዱፎ ላይ የአፋር ባንዲራን አውርደው ማቃጠላቸውን እና በአካባቢው በነበረ የፀጥታ ኃይል ላይ ጥቃት መፈፀማቸውን አስታውሰዋል። • የአዲስ አበባ ባለአደራ ምክርቤት መግለጫ ምን ይላል? ከዚህ በኋላም በተለያዩ የድንበር አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ጥቃት እንደሚፈፀም ተናግረው፤ በአካባቢው በገዳማይቱ እስከ ሀርጌሳ የሚያገናኝ የኮንትሮባንድ መንገድ መኖሩን አንስተው ገዳማይቱ በኮንትሮባንድ ንግድ እንደ ቶጎጫሌ እጅግ በጣም ታዋቂ መሆኗን ይናገራሉ። ይህ የኮንትሮባንድ ንግድ በአደባባይ የሚካሄድ ሲሆን ውስጥ ለውስጥ የሚያገናኙ የኮንትሮባንድ መንገዶች መኖራቸው የአካባቢውን አርብቶ አደር ለጥቃት ማጋለጡን ለቢቢሲ አስረድተዋል። እነዚህ ጥቃት አድራሾች መጋቢት 16 ሰኞ እለት ጀምረው በስፍራው እንደቆዩ መስማታቸውን አስታውሰው ድንገት ግመል የሚፈልጉ ሰዎች ወደ ስፍራው ሲሄዱ ጥቃት መክፈታቸውንና አንድ ሰው መሞቱን እንዲሁም አንድ ሰው ደግሞ መቁሰሉን አረጋግጠዋል። ከዚያ በኋላ በታጣቂዎቹና በአርብቶ አደሮቹ መካከል የተኩስ ልውውጥ መቀጠሉን በነጋታው ማክሰኞም ታጣቂዎቹ ስፍራውን ለቀው መሸሻቸውን ያስረዳሉ። • ብ/ጄኔራል ከማል ገልቹ ከስልጣናቸው ተነሱ የክልሉ የፀጥታና የደህንነት ቢሮ ኃላፊው አቶ አህመድ ሱልጣን የደረሰውን ጥቃትና የጠፋውን የሰው ህይወት አረጋግጠው የተፈጠረውን ሁኔታ ሲያስረዱ፤ በዱብቲ ወረዳ ገዊሊ በሚባል ስፍራ በወቅቱ ፍየል ለመጠበቅ ከአካባቢያቸው ወጣ ብለው የነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩንና በኋላም የአካባቢው ማህበረሰብ ጥቃቱን ለመከላከል ተኩስ መክፈቱን ታጠቂዎቹም መኪናቸውን ይዘው መሸሻቸውን አስረድተዋል። ግጭቱ የተከሰተው በዱብቲና አሳይታ ወረዳ ወደ ውስጥ ገባ ብሎ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው አራት የታጠቂዎቹ ተሽከርካሪዎች ማምለጣቸውን ነገር ግን አንድ የጭነት መኪና መያዙን አስረድተዋል። በአካባቢው የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች የሚጠቀሙበት ከጅቡቲ እንደፎ፣ ገደማይቱና አዳይቱ የሚወስድ መንገድ መኖሩን ያረጋገጡት ኃላፊው በአካባቢው ይህ ጥቃት ሲደርስ መንገድና የስልክ ኔትወርክ ባለመኖሩ ዘግይተው መስማታቸውን ያስረዳሉ። በአካባቢው የጦር መሳሪያን ጨምሮ ከፍተኛ የኮንትሮባንድ ንግድ አንደሚካሄድ መረጃው እንዳላቸውም ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። • የኒፕሲ ሐስል ግድያ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋለ እነዚህ ቡድኖች የአፋር አርብቶ አደሮች ላይ ተዘጋጅተው ጥቃት ለማድረስ የመጡ ይመስላል የሚሉት አቶ አህመድ፤ ጥቃት አድራሾቹ የሚመገቡትን ሩዝና ስኳር፣ የሚጠጡትን ውሃ እንዲሁም ሲሚንቶና ቆርቆሮ ይዘው መምጣታቸውን ገልፀዋል። አክለውም ጥቃት ፈጻሚዎቹ ጥይት ይዘውባቸው የነበሩ ካርቶኖች በስፍራው መያዛቸውንም አረጋግጠዋል። "ታጣቂዎቹ ካምፕ ለመመስረት የመጡ ይመስላሉ" ያሉት የክልሉ የፀጥታና የደህንነት ቢሮ ኃላፊ፤ አሁን በቁጥጥር ስር የዋለው መኪና ሁለት ሰሌዳዎችን መጠቀሙን ያስረዳሉ። ከፊት የለጠፈው ሦስት ቁጥር ኢቲ የሀገራችን ሲሆን በጀርባ በኩል ደግሞ የሶማሌ ላንድ ሰሌዳ እንዳለው ተናግረዋል። የክልሉ ኮሙኑኬሽንም ሆነ የፀጥታ እና ደህንነት ኃላፊዎች እንደሚናገሩት ጥቃቱ በተደራጁ ቡድኖች የተፈመ መሆኑን የሚያሳዩ ሌሎች የተገኙ መረጃዎች አሉ። የአልሸባብ ባንዲራ፣ የፊት መሸፈኛ ጭምብል፣ የሶማሌ ላንድ ሰሌዳ ቁጥር እና የ ጅቡቲ መታወቂያ በማለት ያብራራሉ። • ሕዝብ ስለመሪው ምን እንደሚያስብ እንዴት እንወቅ? የደህንነትና የፀጥታ ኃላፊው አክለውም ከዚህ ጥቃት ጋር ተያይዞ በአሳይታ ከተማ ይኖር የነበረ አንድ የጅቡቲ ዜግነት ያለው ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉንም ተናግረዋል። ይህ በድንበር አካባቢ ባሉ የአርብቶ አደሮች መካከል የሚደረግ የተለመደ ግጭት ላለመሆኑ መረጃ እንዳላቸው የተጠየቁት የክልሉ የደህንነት ኃላፊ፤ አካባቢው ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ ጥቃቶች ማስተናገዱን አስታውሰው በፊት አርብቶ አደሮች በግጦሽና በውሃ ፍለጋ ቢጋጩም በመኪና መጥተው ስንቅ አደራጅተው እንዳልሆነ በማስታወስ "አሁኑ ግን የአልሸባብ ባንዲራ መገኘቱ፣ የሚጠቀሙት መሳሪያ እና የሚፈጽሙት ጥቃት ግጭቱ በአርብቶ አደር መካከል የሚደረግ እንዳልሆነ ያሳያል" ብለዋል። በጉዳዩ ላይ የሃገር መከላከያ ሠራዊት ባለስልጣናትን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
45781660
https://www.bbc.com/amharic/45781660
በገዛ አገሩ ኤምባሲ ውስጥ የተገደለው ጋዜጠኛ
ጀማል ባለፈው ማክሰኞ በቱርክ ኢንስታንቡል የሳዑዲ ቆንስላ ቀጠሮ ነበረው። የጋብቻ ጉዳዮችን ለመጨራረስ፤ የቀድሞው ባለቤቱን የፍቺ ጉዳይ ለመዝጋት አዲሷን ቱርካዊት ባለቤቱን አስከትሎ ወደዚያ ሄደ። "ደጅ ጠብቂኝ መጣሁ" አላት። በዚያው አልተመለሰም።
የመጀመርያው ጥርጣሬ ሳዑዲ አፍና ወደ አገሯ ልካዋለች የሚል ነበር። አሁን እየወጡ ያሉ መረጃዎች ግን እዚያው ቆንስላው ውስጥ በምስጢር እንደተገደለ ፍንጭ የሚሰጡ ናቸው። • የማትተነፍሰው ከተማ: አዲስ አበባ • የጠፉት የኢንተርፖል ሹም ቻይና ውስጥ ተገኙ ሳዑዲያዊው ጀማል ካሹጊ ቀደም ባሉት ዘመናት የንጉሣዊው ቤተሰብን እስከማማከር የደረሰ ሰው ነበር። የኋላ ኋላ ግን የመብት ጥያቄዎችን በማንሳቱ ጥርስ ውስጥ ገባ። ነገሩ አላምር ሲለው ወደ ቱርክ ሸሸ። ላለፉት ዓመታት የሳዑዲን አፋኝ አስተዳደር ሲነቅፍ ቆይቷል። የቱርክ ባለሥልጣናት ከሳዑዲ ጋር ያላቸውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት ላለማቆርፈድ ዝምታን መርጠው የነበረ ሲሆን ትናንት ግን ዝምታውን ሰብረውታል። ጀማል በቆንስላው ሳለ ተገድሏል ብለዋል ለቢቢሲ። ሳዑዲ ግን "ዜጋዬን እየፈለኩት ነውና አፋልጉኝ" ስትል ፌዝ የሚመስል መግለጫን አውጥታለች። አቶ ጀማል ካሹጊ ስመ ጥር ጸሐፊ ሲሆን በተለይም ለዋሺንግተን ፖስት አምደኛ በመሆን ይታወቃል። አብራው ወደ ሳኡዲ ቆንስላ ሄዳ የነበረችውን ባለቤቱ "ምናልባት ካልተመለስኩ በዚህ ስልክ ቁጥር የረሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ረዳት ለሆነ ሰው ደውለሽ ተናገሪ" ብሏት እንደነበር ገልጻለች።
news-49753180
https://www.bbc.com/amharic/news-49753180
ብዙ ነገር ''አንድ'' የሆነባት ሃገር ኤርትራ
ከጥቂት ሳምንታት በፊት የቢቢሲ ጋዜጠኞች በኤርትራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረውን ከ15 ዓመት በታች የሴካፋ ውድድርን እንድንዘግብ ፍቃድ ተሰጥቶን ወደ ኤርትራ እቅንተን ነበር።
በኤርትራ በነበርን ቆይታ ያየነውን እና የሰማነውን በሦስት ክፍሎች አሰናድተናል። ሁለተኛውን ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል። የመጀመሪያውን ክፍል ለማንበብ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። • አሥመራን አየናት፡ እንደነበረች ያለችው አሥመራ ማስታወሻ፡ በኤርትራ በነበረን ቆይታ የዘገባ ርዕሶቻችን እና እንቅስቃሴዎቻችን የተገደቡ ነበሩ። በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት እንደ ጎርጎሪሳውያኑ አቆጣጠር ነው። ብዙ ነገር ''አንድ'' የሆነባት ሃገር ኤርትራ በኤርትራ አንድ ብቻ የሆኑ ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ አይነት ቢራ፣ አንድ አውሮፕላን፣ አንድ ሥርዓት ያለው የባንክ አገልግሎት፣ እንድ የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ፣ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ አንድ የቴሌቪዝን ጣቢያ . . . "ሜሎቲ" ወይም አሥመራ ቢራ ከእአአ 1939 ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። አንድ ቢራ "ሜሎቲ" ወይም አሥመራ ቢራ ከ1939 ጀምሮ በኤርትራ ሲጠመቅ ቆይቷል። ይህ ለኤርትራ ብቸኛ የሆነው ቢራ በበርካቶች ዘንድ ትዝታ እና ተወዳጅነትን ያተረፈ ነው። የቢራ ፈላጊውን እና የአቅርቦት መጠኑ ተመጣጣኝ ስላልነበረ ከቅርብ ዓመታት በፊት አንድ ሰው ሁለት ቢራ ብቻ ገዝቶ እንዲጠጣ ነበር የሚፈቀድለት። • አሥመራ፡ የአዛውንቶች ከተማ ከሁለት በላይ ደጋግሞ መጠጣት የፈለገ፤ ቢራ የማይጠጣ ሰው ወደ መጠጥ ቤት ይዞ በመሄድ የዚያን ሰው ኮታ ይጠጣ እንደነበር ሰምተናል። አሁን ላይ በቢራ ፋብሪካው በተካሄደ ለውጥ የቢራ አቅርቦቱን በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። ከኢትዮጵያ ጋር የሚያዋስኑ የድንበር በሮች በተከፈቱ ጊዜ የኢትዮጵያ ቢራ ምርቶች አሥመራን አጥለቅልቀዋት እንደነበረ በዚህም የአንድ ሜሎቲ ቢራ ዋጋ ከ25 ናቅፋ ከ11-15 እንደወረደ ነዋሪዎች ነግረውናል። ናቅፋ አንድ አይነት የባንክ ሥርዓት በኤርትራ የሚገኙት ባንኮች በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደሩ ናቸው። በቁጥር ሦስት የሆኑት የመንግሥት ባንኮች በአድናቆት አፍ የሚያስከፍት ሕግ አላቸው። ይህም የባንኩ ደንበኞች በባንኩ ካላቸው ገንዘብ በወር ከ5 ሺህ ናቅፋ በላይ እንዲያወጡ አይፈቅድም። መኪና ለመግዛት 100 ሺህ ናቅፋ በጥሬ ገንዘብ ያስፈለገው ወጣት ይህን ያክል ገንዘብ በጥሬ ለማግኘት ወር እየጠበቀ 5000 ናቅፋ ሲያወጣ አንድ ዓመት እንደስቆጠረ ነግሮናል። • ቀነኒሳ 'ከሞት እንደመነሳት' ነው ባለው ሁኔታ ማራቶንን አሸነፈ መንግሥት ይህን መሰል ውሳኔ ማስተላለፍ ለምን እንደፈለገ የጠየቅናቸው ነዋሪዎች፤ ሁለት የተለያየ አተያዮች አሏቸው። የመጀመሪያው መንግሥት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው የዋጋ ግሽበትን ለመቆጣጠር እና የህዝቡን የቁጠባ ባህል ለማዳበር ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ "መንግሥት ምንም አይነት የንግድ እንቅስቃሴ እንዲኖር ስለማይፈልግ የገንዘብ ዝውውር እንዳይኖር አድርጓል" ይላሉ። ኤቲኤም (ገንዘብ መክፈያ ማሽን) በኤርትራ የለም። አሥመራ በነበረን ቆይታ ያገኘነው ወጣት፤ ድንበር ክፍት በተደረገ ጊዜ ወደ መቀሌ አቅንቶ በነበረበት ወቅት ''ሰዎች ከማሽን ብዙ ገንዘብ ወጪ ሲያደርጉ'' ማየቱ በእጅጉ እንዳስደነቀው አጫውቶናል። ኤቲኤም በሌለባት ሃገረ ኤርትራ ሌላው ያስተዋልነው፤ በምግብ እና መጠጦች ላይ ተጨማሪ የእሴት ታክስ አለመጣሉ ነው። ሲም ካርድ በቀላሉ ማግኘት ስለማይቻል አብዛኛው ህብረተሰብ የህዝብ ስልኮችን ይጠቀማል። ቀኝ-አሥመራ ከተማ ልብስ መሸጫ ሱቅ ውስጥ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ስልክ። አንድ የቴሌኮም ኩባንያ ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ በኤርትራ ያለው የቴሌኮም አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት በመንግሥት ባለቤትነት የሚተዳደር ሲሆን ኤሪቴል ይባላል። በኤርትራ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ደካማ ነው። ሲም ካርድ ማግኘት እጅግ አዳጋች ነው። ጎብኚዎች ሲም ካርድ ማግኘት አይችሉም። ነዋሪዎችም ቢሆኑ ሲም ካርድ ማውጣት ቢፈልጉ በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ይሁንታንና ፈቃድን ሲያገኙ ነው የሲም ካርድ ባለቤት የሚሆኑት። 07 ብሎ የሚጀምረው የኤርትራ የሞባይል ስልክ ቁጥር ባለ 8 አሃዝ ብቻ ነው። ለምሳሌ የኤርትራ ሞባይል ቁጥር ይህን ሊመስል ይችላል 07 123 456። አብዛኛው ማህብረሰብ በፈቀደው ወቅት የሲም ካርድ ባለቤት መሆን ስለማይችል አብዝቶ የሚጠቀመው የመንገድ ላይ የሕዝብ ስልኮችን ነው። የተለያዩ ዋጋ ያላቸውን ካርዶች ከኤሪቴል መደብሮች ብቻ በመግዛት ወደ ሃገር ውስጥ እና ከሃገር ውጪ መደወል ይቻላል። • በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል ሲም ካርድ ቢገኝም፤ የሞባይል ዳታ የለም። በስልክዎ ላይ ኢንተርኔት መጠቀም የሚችሉት የዋይፋይ አገልግሎት በሚገኙባቸው ስፍራዎች ብቻ ነው። ዋይፋይ ቢገኝም፤ የኢንተርኔት ፍጥነት እጅግ ቀሰስተኛ ነው። ማህበራዊ ሚዲያዎችን ለመቃኘት ደግሞ ቪፒኤን መጠቀም ግድ ይላል። ዓለም አቀፍ የቴሌኮሚዩኒኬሽን ሕብረት ሪፖርት እንደሚጠቁመው፤ ከኤርትራ ሕዝብ ውስጥ የኢንተርኔት ተጠቃሚው ብዛት ከ2 በመቶ በታች ነው በማለት አገልግሎቱ ምን ያህል ዝቅተኛ መሆኑን ይጠቁማል። አንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ በመንግሥት ባለቤትነት የተያዘው ኤሪ-ቲቪ ከኤርትራ ሆኖ በብቸኝነት የሚያሰራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ ነው። በቅርቡ ኤርትራ በዓለማችን ቁጥር አንድ የመገናኛ ብዙሃን አፈና የሚፈጸምባት ሃገር ናት ተብለ ተፈርጃ ነበር። የጋዜጠኞችን እስር፣ ጋዜጠኞችን ለመሰለል የሚፈቅዱ ሕጎችን እንዲሁም በኢንተርኔት እና በማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ላይ የሚጣለውን ገደብ ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ ኤርትራ ከሰሜን ኮሪያ በላይ ቁጥር አንድ አፈና የሚፈጸምባት ሃገር ናት ይላል። • ኤርትራ በምሽት ድንበር ማቋረጥን ከለከለች ከኤርትራ በመቀጠል ሰሜን ኮሪያ፣ ቱርኬሚስታን፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ቻይና፣ ቬትናም፣ ኢራን፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ቤላሩስ እና ኩባ ከ2ኛ እስከ 10ኛ ደረጃን ይዘው ተቀምጠዋል። በኤርትራ መገናኛ ብዙሃን የመንግሥት ልሳን ሆነው ነው የሚያገለግሉት የሚለው ሲፒጄ፤ ገለልተኛ የሆኑ ጋዜጠኞች ወደ ሃገራቱ ሲያቀኑም ቅርብ ክትትል ይደረግባቸዋል። አንድ የፖለቲካ ፓርቲ ሃገሪቷን የሚያስተዳድረው እና በፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው የሕዝባዊ ግንባር ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ (ሕግዴፍ) በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሰው ብቸኛው የፖለቲካ ፓርቲ ነው። ሦስት አስርት ዓመታትን ሊደፍን የተቃረበው የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አስተዳደር ዘመን በኤርትራ የሚንቀሳቀስ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ታይቶ አታውቅም። ይህ ብቻም አይደለም ሥራ ላይ ውሎ የሚያውቅ ሕገ-መንግሥት የለም። ምርጫ ተካሂዶ አያውቅም። ወደፊትም ስልጣን ላይ የሚገኘው መንግሥት ምርጫ የማካሄድ ሃሳብ የለውም ሲሉ ተቺዎች ይናገራሉ። የኃይማኖት ነጻነት በኤርትራ ፍቃድ ያላቸው እና መንግሥት እውቅና የሰጣቸው ኃይማኖቶች አራት ብቻ ናቸው። የኦርቶዶክስ ክርስትና፣ የሱኒ እስልምና፣ የሮማ ካቶሊክ ቤተ-ክርስቲያን እና የሉተራን ወንጌላዊ ቤተ-ክርስቲያን ናቸው። • ኤርትራ ፖለቲከኞችን እና ጋዜጠኞችን እንድትለቅ ተጠየቀ ሌሎች የእምነት ተቋማት እንደ ሕገ-ወጥ ነው የሚቆጠሩት። መንግሥት የተቀሩትን የእምነት ተቋማትን የውጪ ሃገራት አጀንዳ ማስፈጸሚያ መሳሪያዎች ናቸው ሲል ይገልጻቸዋል። የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የኃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን የ2019 ሪፖርት እንደሚጠቁመው ከሆነ፤ ዛሬ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኤርትራዊያን በእምነታቸው ምክንያት ለእስር እንደተዳረጉ ናቸው። የጆሆቫ ምስክሮች በእምነት ተከታዮች በኃይማኖታቸው ምክንያት በብሔራዊ አገልግሎት ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ዜግነት ይከለከላሉ፣ መታወቂያ ደብተር ማግኘት አይችሉም። የድንበር በሮች መከፈት ሁለቱን ሃገራት የሚያገናኙ አራት የድንበር በሮች ይገኛሉ። አራቱ የድንበር በሮች ዛላምበሳ - ሰርሃ፣ ራማ - ክሳድ ዒቃ፣ ሁመራ - ኦማሃጀር እና ቡሬ - ደባይ ሲማ ናቸው። በሁለቱ ሃገራት የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ክፍት ተደርገው የነበሩት አራቱ የድንበር በሮች አሁን ላይ ሁሉም ተዘግተዋል። ለድንበር በሮቹ መዘጋት በሁለቱም መንግሥታት የተሰጠ ምክንያት ባይኖርም ይፋዊ ያልሆኑ መረጃዎች የድንበር በሮቹ የተዘጉት፤ የቪዛ እና የቀረጥ ጉዳዮችን መልክ ማስያዝ በማስፈለጉ እንደሆነ ይጠቁማሉ። ዛላምበሳ - ሰርሃ፣ ራማ - ክሳድ ዒቃ እና ለሱዳን ቅርብ የሆነው ሁመራ - ኦማሃጀር በትግራይ ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከኤርትራ ጋር የሚያገናኙ የድንበር በሮች ሲሆኑ፣ ቡሬ - ደባይ ሲማ ደግሞ በአፋር ክልል በኩል ኢትዮጵያን ከኤርትራ የሚገናኝ የደንበር በር ነው። የድንበር በሮቹ ክፍት ተደርገው በነበረበት ወቅት ከፍተኛ የሆነ የንግድ እንቅስቃሴ ድንበር እቅራቢያ ተስተውሎ ነበር። በአሥመራም የድንበር በሩ መከፈት በተለያዩ ሸቀጦች ላይ የዋጋ ለውጥ አምጥቶ እንደነበር በቆይታችን ሰምተናል። ለምሳሌ ድንበር ከመከፈቱ በፊት እስከ 10 ሺህ ናቅፋ ይሸጥ የነበረው አንድ ኩንታል ጤፍ ድንበሩ ሲከፈት ዋጋው በሚያስደንቅ ሁኔታ አሽቆልቁሎ እንደነበር ነዋሪዎች ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት በድንበር በሮቹ ላይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በመገደቡ የአንድ ኩንታል ጤፍ አሥመራ ውስጥ የተጋነነ ባይሆንም ጭማሪ አሳይቷል።
news-49161119
https://www.bbc.com/amharic/news-49161119
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን የተተከሉት ከ300 ሚሊዮን በላይ ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ?
ትናንት ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም 'አረንጓዴ አሻራ' በሚል ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ ባለሥልጣናትና የተለያዩ አካባቢ ነዋሪዎች በአገር አቀፍ ደረጃ ችግኝ ተክለዋል። ይህንን ቀን በማስመልከት በአንዳንድ አገራት የሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎችም ባሉበት አሻራቸውን አሳርፈዋል።
• የጠቅላይ ሚኒስትሩ 200 ሚሊዮን ችግኞች • የአየር ንብረት ለውጥ፤ የት ደረስን? የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻው በአንድ ቀን 200 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የዓለምን ክብረ ወሰን መስበር እንዲሁም በአጠቃላይ 4 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል ዓላማ ይዞ የተነሳ ነው። በዚህ የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ በአንድ ጀምበር ከ300 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል በሕንድ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን ኢትዮጵያ መስበሯ ተዘግቧል። ለመሆኑ የተተከሉት ችግኞች እንዴት ተቆጠሩ? ይህንን ሂደት ሲከታተል የነበረው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ሲሆን በሥሩም አንድ ቡድን ተቋቁሟል። ቡድኑ የችግኝ ተከላዎችን አቆጣጠራቸውንና ምዝገባቸውን የሚከታተል ነው። ያነጋገርናቸው የዚህ ቡድን አስተባባሪ አቶ ኢምራን አቡበከር በትክክል መተከላቸውን ለመቆጣጠር ቀድሞ የተሠራ ሶፍት ዌር መኖሩን ይናገራሉ። እርሳቸውም ይህንን ሶፍት ዌር በመስራቱ ረገድ ሚና ነበራቸው። ሶፍት ዌሩ በዛፍ መትከያ ቦታዎች ላይ የተከላውን ሂደት ለመቆጣጠር የተመደቡ ሰዎች ስልክ ላይ ብቻ የሚሠራ ሲሆን በአካል በመገኘት የቆጠሩትን ችግኝ ብዛት የሚያስተላልፉበት ሥርዓት አለው። በዚህም መሠረት በተመደቡበት ቦታ ላይ ምን ያህል ችግኞች እንደተተከሉ ቁጥሩን ሲያስገቡ ሶፍት ዌሩ በተለያዩ ቦታዎች የሚደርሱትን አሃዞች በማጠቃለል እየደመረ ውጤቱን ይሰጣል። በመጨረሻ ላይም በአጠቃላይ በመላዋ ሃገሪቱ የተተከሉትን ችግኞች ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ ያሳውቃል- ሶፍት ዌሩ። ከዚህም ባሻገር ሌሎች የመቆጣጠሪያ መንገዶችን እንደተጠቀሙና ከ300 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን አቶ ኢክራም ገልፀውልናል። • ምድር በአስፈሪ ሁኔታ እየሞቀች ነው ከዚህ ቀደምም የተለያዩ የችግኝ መትከል ዘመቻዎች መከናወናቸው ይታወቃል። ሆኖም ምን ያህሉ ፀደቁ? የሚለው ላይ ባለሙያዎች ጥያቄ ያነሳሉ። የለም ኢትዮጵያ አካባቢ ልማት ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ ወርቁ ችግኝ ከመተከሉ በፊት ጥንቃቄ ያስፈልጋል ሲሉ ይጀምራሉ። "መንግሥት ከዘመቻ ሥራ ወጥቶ የተጠና ሥራ መስራት አለበት" የሚሉት አቶ ሞገስ ሰሞኑን ችግኞች በተተከሉባቸው ቦታዎች ላይ ሰዎች ግንዛቤው ሳይኖራቸው ቁጥር ላይ ብቻ ትኩረት ሲያደርጉ መታዘባቸውን ነግረውናል። "አተካከላቸው ሳይንሱ የሚፈልገው ዓይነት አይደለም፤ አንዳንዱ ተከልኩ ለማለት ያህል ጣል አድርጎ የሚመጣ አለ" ሲሉ በግድ የለሽነት ችግኝ እንደማይተከል ያስረዳሉ። ችግኝ ያልተተከሉባቸው ቦታዎች እያሉ የተተከሉባቸው ቦታዎች ላይ መልሶ መትከልም ጠቃሚ እንዳልሆነ አቶ ሞገስ ያነሳሉ። "በአንድ ጊዜ አገሪቱን በደን መሸፈን ይቻላል ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው" የሚሉት አቶ ሞገስ በደንብ በባለሙያዎች በተጠና መልኩ፣ እቅድ ተይዞ፣ ይህን ያህል እንተክላለን ተብሎ፣ ቦታው ተለይቶ፣ የችግኞቹ ዝርያ ታውቆ፣ ችግኙም በወቅቱ ተዘጋጅቶ ሊካሄድ ይገባል ሲሉም ይመክራሉ። እስካሁን በነበረው ልምድ ችግኞች ሲተከሉ ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ናቸው? አይደሉም? ብሎ ለመወሰን የሚያስቸግር መሆኑን በመግለጽ የተገኘው ሁሉ ነው ሲተከል የቆየው ብለዋል። ይሁን እንጂ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ችግኞች ለመትከል የተደረገውን ይህን እንቅስቃሴና ዘመቻ ሳያደንቁ አላለፉም።
news-50171908
https://www.bbc.com/amharic/news-50171908
ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ
ረቡዕና ሐሙስ ዕለት የተቃውሞ ሠልፍ በተካሄደባቸው የኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች በክልሎችና በአስተዳደሩ ጥያቄ መሰረት የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ለሃገር ውስጥ መገናኛ ብዙኀን በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
መከላከያ ሠራዊት የተሰማራባቸው ከተሞች መካከል አምቦ፣ ቢሾፍቱ፣ ባሌ ሮቤ፣ አዳማ፣ ሞጆ እንዲሁም በድሬዳዋ እና ሐረር መሆናቸውን በመግለጫቸው ወቅት ተናግረዋል። መከላከያ ሠራዊት ወደ ስፍራው የገባው የፌደራል መንግሥቱ ከክልሉ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት መሆኑን ሜጄር ጄኔራል መሀመድ ተሰማ ገልፀዋል። እስካሁን በተሰራው ሥራ ተጨማሪ የሰው ህይወት እና ንብረትን ከጥፋት ማትረፍ የተቻለ ቢሆንም፤ መከላከያ ሠራዊት በፍጥነት ባልደረሰባቸው አካባቢዎች ጉዳት ማጋጠሙን የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽንና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ጠቁመዋል። የመከላከያ ሠራዊት በእነዚህ አካባቢዎች ከአባ ገዳዎች፣ ከሃይማኖት መሪዎች፣ ከወጣቶች እና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የማረጋጋት ሥራ እያከናወነ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው የተዘጉ መንገዶችንና የንግድ ተቋማትን ማስከፈት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ተነግረዋል። የፀጥታ መደፍረስ ያጋጠማቸው አካባቢዎች ወደ ቀደመ ሰላማቸው እስከሚመለሱ ድረስ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አካባቢዎቹን የማረጋጋቱን ሥራ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። በአንዳንድ የኦሮሚያ ከተሞች የሆነው ምን ነበር? በአክቲቪስት ጃዋር ሞሐመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞችና በሌሎች ቦታዎች ረቡዕ እና ሐሙስ ሲካሄዱ ከቆዩት የተቃውሞ ሰልፎች ጋር በተያያዘ እስካሁን በተገኙ ይፋዊ መረጃዎች የሟቾች ቁጥር ቢያንስ 27 ደርሷል። የተቃውሞ ሰልፍ ተደርጎባቸው ሰው ከሞተባቸው አከባቢዎች መካከል አምቦ፣ ድሬዳዋ እና ዶዶላ ይገኙበታል። አምቦ ረቡዕ በአምቦ ከተማ ከተገደሉት ሶስት ሰዎች በተጨማሪ ሐሙስ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። ዛሬ በጥይት ከተገደሉት መካከል የ80 ዓመቱ አዛውንት አቶ ሞሮዳ ሞሳ የሚባሉ ይገኙበታል በማለት ነዋሪዎች ተናግረዋል። አቶ ሞረዳ ልጃቸውን ፍለጋ በወጡበት ከጸጥታ አስከባሪ ኃይል በተተኮሰባቸው ጥይት መገደላቸውን የከተማው ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል። በአምቦ ሐሙስ ከተገደሉት ሁለት ሰዎች በተጨማሪ ሌሎች በርካታ ሰዎቸ በጥይት ተመትተዋል። • "ያለን አማራጭ ውይይት ብቻ ነው" ጀዋር መሐመድ የአምቦ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር አቶ ደበበ ፈጠነ፤ "14 ሰዎች በጥይት ተመተው እኛ ጋር መጥተዋል። ሁለቱ ህይታቸው አልፏል። 9 ሰዎች ደግሞ ተኝተው እየታከሙ ሲሆን የተቀሩት ቀላል ህክምና ተደርጎላቸው ወደየቤታቸው ተመልሰዋል" በማለት ያስረዳሉ። አቶ ደበበ ወደ ሆስፒታላቸው የመጡት ሰዎች በሙሉ ወንዶች መሆናቸውን እና ዕድሜያቸውም ከ17-80 እንደሚገመት ተናግረዋል። በዚህም በአምቦ ረቡዕ 3፤ ሐሙስ 2 በድምሩ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል። ምስራቅ ሐረርጌ በሁለቱ ቀናት በምስራቅ ሃረርጌ በተካሄዱት ሰልፎች የሟቾች ቁጥር 6 መድረሱን ሰምተናል። በዞኑ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ አየለ ዴሬሳ በምስራቅ ሃረርጌ በሚገኙ ከተሞች ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው እንደነበረ ተናግረው፤ በሁለት ከተሞች በተፈጠረው ግጭት የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በተቀሩት ከተሞች ግን የተካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች በሰላም መጠናቀቃቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። • "የተፈጸመው መሆን ያልነበረበት ትልቅ ስህተት ነው" አቶ አየለ፤ ትናንት 5ቱ ሰዎች የተገደሉት ጉሮ ጉቱ በምትባል ከተማ ወደ ብሄር በተቀየር ግጭት ስለመሆኑ ይናገራሉ። "አንድ ባለሃብት የደህንነት ስጋት ተሰምቶት ሁለት ሰዎችን በጥይት መትቶ ገደለ። ከዚያም በቂም በቀል ግለሰቡ እና ሁለት የቤተሰብ አባላቱ ተገደሉ" ሲሉ ሁኔታውን ያስረዳሉ። የአወዳይ ከተማ ነዋሪ የሆነ ወጣት ከመከላከያ ሠራዊት በተተኮሰ ጥይት ስለመገደሉ የአወዳይ ከተማ ከንቲባ ጃፋር ሙሐመድ ለቢቢሲ ተናግረው ነበር። ዶዶላ በምዕራብ አርሲ ዞን ዶዶላ ከተማ ረቡዕና ሐሙስ በነበሩ ግጭቶች በጠቅላላው 6 ሰዎች መገደላቸውን ታውቋል። ሐሙስ በነበረ ግጭት 4 ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ተናግረዋል። ረቡዕ ደግሞ ሁለት ሰዎች ተገድለው ነበር። • ዶዶላ ውስጥ በተቀሰቀሰ ግጭት የ4 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በሌሎች ከተሞችም ተቃውሞው ቀጥሏል በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። ሁኔታው አስፈሪ ስለነበር ለሕይወታቸው የሰጉ ሰዎች በአካባቢው በምትገኘው ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን ተጠልለው አንደሚገኙ ተናግረዋል። ሐረር በሐረር ከተማ ረቡዕ 3 ሰዎች መገደላቸውን ከነዋሪዎች ሰምተናል። ድሬዳዋ በድሬዳዋ ከተማም ረቡዕ 1 ሰው የተገደለ ሲሆን ዛሬ ደግሞ 4 ሰዎች ተገድለዋል። የድል ጮራ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አብዱራሃማን አቡበከር ሐሙስ ሰባት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታላቸው እንደመጡ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ለህክምና ከመጡት ሰዎች መካከል 4ቱ ህይወታቸው ማለፉን ጠቅሰው፤ ዶ/ር አብዱራሃማን "ሰዎቹ በጥይት እና በሌሎች ነገሮች" ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል እንደመጡ አመልክተዋል። አዳማ ረቡዕ በአዳማ ከተማ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደው ነበር። ሰልፎቹ ባህርያቸውን በመቀየር በሁለት ጎራ በተከፈሉ ሰዎች መካከል ግጭት ተከስቶ በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። ለጃዋር መሐመድ ድጋፍ ለማሳየት በወጡ ወጣቶች እና እነሱን በሚቃወሙ መካከል ግጭት እንደተፈጠረ በሥፍራው የነበረው የቢቢሲ ሪፖርተር ዘግቧል። የአዳማ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ራውዳ ሁሴን በበኩላቸው በከተማዋ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ዱቄት ፋብሪካ የጥበቃ ሠራተኛ ጥይት ተኩሶ ሁለት ሰዎችን መግደሉን እና በዚህ የተበሳጩ ሰልፈኞ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ 15 መኪኖችን ማቃጠላቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። በግጭቱ ሁለተኛ ቀን ሐሙስ ዕለትም እዚያው አዳማ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ከ20 በላይ የንግድ ሱቆች በተቃዋሚዎቹ በተፈጸመባቸው ጥቃት በእሳት ተቃጥለው መውደማቸው ተነግሯል። ግጭቶች ባጋጠሙባቸው አካባቢ ያሉ ነዋሪዎችን፣ የሆስፒታል ምንጮችንና የመንግሥት አካላትን በማነጋገር ባገኘው የተረጋገጠ መረጃ መሰረት በሁለት ቀናቱ ግጭት ቢቢሲ 27 ሰዎች መሞታቸውን ለማረጋገጥ የቻለ ይሁን እንጂ ቁጥሩ ከዚህ ሊበልጥ እንደሚችል አንዳንዶች ስጋታቸውን ገልጸዋል።
news-53756124
https://www.bbc.com/amharic/news-53756124
ኮሮናቫይረስ፡ "ከመንግሥት በላይ ለጤናዬ የሚጨነቅ አምላክ ስላለ ጭምብል አላጠልቅም" አሜሪካዊቷ ከመቶ ዓመታት በፊት
ከመንግሥት በላይ ለጤናዋ የሚጨነቅ አምላክ ስላለ ወረርሽኙን ለመከላከል ጭምብል እንደማታጠልቅ አንዲት አሜሪካዊት ሴት ተናገረች።
ይህ አባባል የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የወጣውን ጭምብል ማጥለቅ እምቢተኝነት በማሳየት አሜሪካውያን ለተቃውሞ ከመውጣታቸው አንፃር በቅርቡ የተነሳ ይመስላል። ግን አይደለም ይሄንን የተናገረችው የዴንቨር ነዋሪ ከመቶ ዓመታት በፊት የታላቁ ኢንፍሉዌንዛ፣ ስፓኒሽ ፍሉ ወይም በኢትዮጵያ የኅዳር በሽታ ተብሎ የሚጠራውን ወረርሽኝ ለመከላከል የወጣን መመሪያ በመቃወም ነው። መቶ ዓመታት ወደፊት እንምጣና በአሁኑ ወቅት በኮሮናቫይረስ ክፉኛ በተመታችው አሜሪካ ከአርባ ግዛቶች በላይ ተጠቅተዋል። በየቀኑም አዳዲስ ሞቶችና በወረርሽኙ የሚጠቁ ሰዎችን ታሪክም መስማት የተለመደ ሆኗል። በወረርሽኙ ቀዳሚ በሆነችው አሜሪካ ከአምስት ሚሊዮኖች በላይ ሰዎች ተጠቅተዋል፤ ከ160 ሺዎች በላይ ህይወታቸውን አጥተዋል። የጤና ባለሙያዎችም በተደጋጋሚ የወረርሽኙን ስርጭት ለመግታት እርምጃዎችን ተግባራዊ ልታደርግ ይገባል ካለበለዚያ ግን ወረርሽኙ ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ወደ ኋላ መመለስ ይከብዳልም ይላሉ። የቫይረሱን ስርጭትም ለመቆጣጠር አካላዊ ርቀትን መጠበቅና በሕዝባዊ ቦታዎች ላይ የፊት ጭምብል ማድረግ በአሁኑ ወቅት ዋነኛ መከላከያ መንገዶች ናቸው በሚልም በርካታዎች እየተገበሩት ይገኛሉ። ምንም እንኳን በርካታ አሜሪካውያን ጭምብል ማድረግን በፅንሰ ሃሳብ ደረጃ ቢቀበሉትም፤ በሕዝባዊ ቦታዎች ላይ ጭምብል አናደርግም የሚል እምቢተኝነት ተንፀባርቋል። የተለያዩ ግዛቶችም እነዚህን መመሪያዎች ማስከበር አዳግቷቸዋል። በርካታ ሰልፈኞች በስኮትስዴል፣ አሪዞና፣ ኦስቲን፣ ቴክሳስና ሌሎች ከተሞች ግዛቶች ያወጧቸውን ጭምብል የማጥለቅ መመሪያዎችን በመቃወም በከተሞቹ ከንቲባ ፅህፈት ቤቶች ተቃውሟቸውን አሰምተዋል። ተቃዋሚዎች መብታችን እየተገፋ ነው የሚሉ ድምፆች በመበርታታቸውም ዋሽንግተንና ሰሜን ካሮላይና የመሳሰሉ ግዛቶች መመሪያዎቹን ተግባራዊ አናደርግም የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰዋል። እስቲ በታሪክን ወደኋላ እንጓዝና በጎርጎሳውያኑ 1918 የነበረውን ስፓኒሽ ፍሉ (የኅዳር በሽታ) ወረርሽኝን እንይ። ከመቶ ዓመታት በፊት ክትባትም ሆነ መድኃኒትም በሌለበት ሁኔታ የታላቁ ኢንፍሉዌንዛ ወረርሽኝ እንዳይዛመት የተለያዩ መመሪያዎች መውጣት ነበረባቸው። ትምህርት ቤቶች፣ የንግድ ተቋማት ተዘጉ፤ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ታገዱ፤ በጉንፋኑም የተጠቁት ሰዎች እንዲለዩና ተገልለውም ለብቻቸው እንዲቆዩ ተደረጉ። የዚህን ወረርሽኝ ስርጭት ለመቆጣጠር ዜጎች ጭምብል እንዲያጠልቁ ታዘዙ። ቁጣዎችን የቀሰቀው ለይቶ ማቆያው ሳይሆን ጭምብል አጥልቁ መባሉ ነበር። ስፓኒሽ ፍሉን አስመልክቶ የወጡ የቺካጎ ጋዜጦች ለአገራችሁ ስትሉ እድርጉት ወቅቱ ጥቅምት አጋማሽ 1918 ነበር፤ በሰሜን ምሥራቅ የአሜሪካ ግዛቶች አሰቃቂ የሚባል ወረርሽኝ እየተስፋፋ በመሆኑ የመንግሥት የጤና ኃላፊዎች ሁሉም ዜጎች አፍና አፍንጫቸውን በጭምብል እንዲሸፍኑ ጠየቁ። ቀይ መስቀልም እንዲሁ ዜጎች ጭምብል እንዲያጠልቁና በቀላሉም በቤታቸው ውስጥ ካሉ ጨርቆች፣ ክሮችም ሆነ ፋሻዎች ጭምብል አስራርንም ለማበረታት በጋዜጦች ላይ ማስታወቂያዎችን ያወጣ ነበር። ካሊፎርኒያ፣ ኡታህና ዋሽንግተንን የመሳሰሉ ግዛት ጤና ማዕከላት ደግሞ የራሳቸው ጅምሮች ነበራቸው። በመላው አገሪቷም ጭምብል ማጥለቅ የዜግነት ግዴታ መሆኑን የሚያትቱ ፖስተሮች መለጠፍ ጀመሩ። በተለይም የመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ማብቂያ ከመሆኑም ጋር ተያይዞ በጦርነቱ ወቅት ይለፈፉ የነበሩ ፕሮፓጋንዳዎችም በዚህም ወቅት ማኅበራዊ ኃላፊነትና አርበኝነት ጋር በማያያዝም ቀጠሉ። የሳንፍራንሲስኮ ከንቲባ ጄምስ ሮልፍም "ለአገር ማሰብ፣ አርበኝነት፣ ራስንና ሌሎችን ለመጠበቅ" ጭምብል ማድረግ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ነው አሉ። የኦክላንድ ከንቲባ ጆን ዴቪም እንዲሁ "ምንም እንኳን የተለያዩ እምነቶች ቢኖሩንም አርበኝነትና ሌሎችን ማስቀደም ማለት ዜጎችን መጠበቅ የሚቻለው ጭምብልን ስናደርግ ነው" በማለት መንፈስን የሚያነቃቃ መልዕክታቸውን አስተላለፉ። መንገድ ጠራጊ በኒውዮርክ ጎዳና ላይ ጭምብል አጥልቀው መመሪያዎችን ማፅደቅ ፈታኝ ሲሆን የጤና ኃላፊዎች የሕዝቡ ባህርይ ላይ ስር ነቀል ለውጥ ማምጣት ፈታኝ እንደሆነ ተረድተውታል፤ በተለይም ጭምብል ማጥለቅ ምቾት ይነሳናልም በመባሉ ማሳመን ፈታኝ ሆኖ አግኝተውታል። አርበኝነት፣ አገር፣ ብሔራዊ ኃላፊነት የሚሉ አገራዊ ስሜቶችን ለማነቃቃት የሚተላለፉ መልዕክቶችን ማስተላለፍ ብዙ የሚያስኬዱ አልሆኑም። ለዚያም ነው የካሊፎርኒያው ባለስልጣን "ሰዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲባል መገደድ አለባቸው" ያሉት። ቀይ መስቀልም እንዲሁ "ወንድ፣ ሴት፣ ልጅ፣ ማንኛውም ጭምብል የማያጠልቅ አደገኛና ለሰዎች የማያስቡ ናቸው" በማለት ጭምብል የማያጠልቁ ሰዎችን በግልፅ በማውገዝ አስተላለፈ። በርካታ ግዛቶች በተለይም በአሜሪካ በምዕራብ የሚገኙ ግዛቶች ጭምብል ማጥለቅን አስገዳጅ አድርገውትም ነበር። አንዳንዶች አጠር ላለ ጊዜ እንዲታሰሩ እንዲሁም ከ5 እስከ 200 ዶላርም የገንዘብ ቅጣትም የተቀጡ በርካቶች ናቸው። ሆኖም መመሪያዎቹ በአወዛጋቢነታቸው ቀጠሉ። ለምሳሌ የሳክራሜንቶ የጤና ዳይሬክተር የከተማዋ ኃላፊዎች መመሪያውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ በተደጋጋሚ መጠየቅን ጨምሮ፣ መለማመጥና መማፀን ነበረባቸው። በሎስ አንጀለስ መመሪያው ሊፀድቅ አልቻለም። በፖርትላንድም ረቂቁ ከፍተኛ ክርክርና ውዝግብም አስነስቷል፤ አንደኛው የከተማዋ ምክር ቤት አባልም "ጨቋኝና ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው" ሲሉ ወርፈውታል። "በምንም ተአምር እንደ ውሻ አያስገድዱኘም" አሉ። እንዳሉትም መመሪያው ሳይሳካ ቀረ። የኡታህ የጤና ኃላፊዎችም በጭምብል አስፈላጊነት ከተወያዩ በኋላ አላስፈላጊ ነው በማለት ውድቅ አድርገውታል። ለዚህም ምክንያታቸው ዜጎች ሐሰተኛ ደኅንነት ስለሚሰማቸውና ባዶ ተስፋም ስለሚሰጣቸው ከመጠንቀቅ ችላ ይላሉ ብለው ነው። ወረርሽኙ ሁለተኛ ዙር እንደገና ሲያገረሽም ኦክላንድ ጭምብል ማጥለቅ ላይ ሌላ ክርክር ጀመረች። ከንቲባዋ በሌላ ግዛት ውስጥ ጭምብል ሳያደርጉ ተገኝተው መታሰራቸው በጣም አበሳጭቷቸው የነበረ ሲሆን በኦክላንድም ይህ እንዳይደገም ሽንጣቸውን ገትረው ተከራከሩ። ይሄንን ክርክር ሲታዘቡ የቆዩ አንድ ታዋቂ ዶክተር በወቅቱም "በዋሻ ይኖር የነበረ ግለሰብ ጭምብል ያጠለቁ ሰዎችን ቢያይ እብድ ናቸው ይለናል" ብለዋል። መመሪያዎችን ተግባራዊ የማድግ ፈተና ጭምብል የማጥለቅ መመሪያዎች ከላይ ቢታዘዙም ነዋሪዎች ግን ሕጎቹን አናከብርም በማለት መጣሳቸው አልቀረም። የገበያ መደብሮች ጭምብል ያላጠለቁ ደንበኞችን መልሱ ቢባሉም ከመግባት አላገዷቸውም። ሠራተኞችም ጭምብል አጥልቆ መስራት አይመችም በማለት ቅሬታዎችን ያሰሙ ነበር። የዴንቨር ነዋሪ የሆነች የሽያጭ ሠራተኛም "አፍንጫዋ እየደነዘዘ" በመሆኑ ጭምብል አላጠልቅም ብላ እምቢተኝነቷን አሳየች። ሌላኛዋ ደግሞ "ከዴንቨር የጤና ቢሮ በላይ ስለ ደኅንነቷ የሚጨነቅ አምላክ" ስላለ አፏንም ሆነ አፍንጫዋን እንደማትሸፍን ተናገረች። የወቅቱ ጋዜጦች እንደዘገቡት ምንም እንኳን መመሪያው ቢፀድቅም "ሕዝቡ እምቢተኝነቱን በማሳየት ችላ ብሎታል፤ እንዲያውም ትዕዛዙ ማፌዣና መቀለጃ ሆኗል" ብሏል። እናም ሕጉ ተሻሽሎ ለባቡርና ለአውቶብስ አሽከርካሪዎች ብቻ ጭምብል እንዲያደርጉ ቢታዘዝም እነሱም የሥራ ማቆም አድማ እናካሂዳለን ማለታቸውን ተከትሎ ከተማዋ ጭምብል የማድረግ መመሪያዋን ልታላላ ተገዳለች። ዴንቨር የሕዝቡን ደኅንነትና ጤንነት የሚያስጠብቅ መመሪያዎች ሳይኖሯትም ወረርሽኙን ተጋፈጠችው። በሲያትል ግን የአውቶብስ አሽከርካሪዎች ጭምብል ያላጠለቁ ተጓዦችን አናሳፍርም አሉ። በተለያዩ ግዛቶች መመሪያውን የሚጥሱ ከመብዛታቸው የተነሳ በኦክላንድ የሚገኙ ባለስልጣናት 300 የቀድሞ ወታደሮችን በበጎ ፈቃደኝነት አሰማርተው ነበር። እነዚህ ወታደሮች ሕግ የሚጥሱ ሰዎችን ስምና አድራሻ በመመዝገብ እንዲቀጡ ለባለስልጣናት ይሰጡ ነበር። በሳክራሜንቶ ጭምብል የማጥለቅ መመሪያው ሲፀድቅ የፖሊስ ኃላፊው "ወደየጎዳናዎቹ ውጡና ጭምብል ያላደረጉ ሰዎችን ስታዩ ይዛችኋቸው ኑ" ብለው ቀጭን ትዕዛዝ አስተላለፉ። በሃያ ደቂቃ ውስጥም ፖሊስ ጣቢያው ጥፋተኛ በተባሉት ሰዎች ከአፍ አስከ ገደፉ ተሞላ። በሳንፍራንሲስኮም መመሪያውን በመተላለፍ የታሰሩ ዜጎች በዝተው የፖሊስ ኃላፊው እስር ቤቶቹ ሞልተዋል በማለት ለከተማው አስተዳዳሪዎች ማሳሰቢያ ለመስጠት ተገደው ነበር። ዳኞችና ኃላፊዎችም ከሰዓት እላፊ ውጪ አምሽተው መስራት፣ ቅዳሜና እሁድንም ያለ እረፍት በመስራት መመሪያ የተላለፉ ሰዎች ላይ ብይን ይሰጡ ነበር። ተቃውሞ ጭምብል ሳያጠልቁ የተያዙት በርካቶቹ ሳይነቃብን የእለት ሥራችንን እናከናውናለን ያሉ ናቸው። ሆኖም በሳንፍራንሲስኮ ጭምብል ሳያጠልቁ የሚወጡ ሰዎች ከመበርከታቸው ብዛት የተነሳ ሌላ ዙር ወረርሽኘ ለመከሰቱ መንስኤ ሆነ። የከተማዋ አስተዳዳሪዎች በጎርጎሳውያኑ ጥር 1919 ጭምብል እንዲደረግ ሌላ ትዕዛዝ ለማውጣት ተገደዱ። ሕዝቡም ኢ-ሕገ መንግሥታዊ፣ ነፃነትን የሚጋፋና መብትን የሚጥስ ነው በማለት አወገዘው። በጥር 25/1919 ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የፀረ-ጭምብል ከፍተኛ ተቃውሞን አካሄዱ። በዚህ ተቃውሞ ላይ ከተሳተፉት መካከል ታዋቂ የህክምና ዶክተሮች እንዲሁም የሳንፍራንሲስኮ የጤና ቁጥጥር ቦርድ አባላት ይገኙበታል። ትናንትናና ዛሬ ዋሽንግተን በ1918 በ1918 የነበረውን ጭምብል ውጤታማነት በአሁኑ ወቅት ማወቅ አዳጋች ነው። ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ ጭምብሎች ተሻሽለው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መግታት እንደሚችሉም ማረጋገጥ ተችሏል። ሆኖም የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ሆኖ በቀጠለበት ወቅት አሜሪካውያን የፊት ጭምብል ማድረጋቸው አወዛጋቢነቱ እንደቀጠለ ነው። ለዚህም ስር የሰደደ የግለሰብ ነፃነት፣ በጭምብሎች አደራረግ ላይ ግልፅ ያለ መልዕክት አለመኖር፣ የአመራር ችግር እንዲሁም ስለ ጭምብሎች የሚወሩ መሰረት የሌላቸው መረጃዎች ምክንያት ናቸው ተብሏል። በአሁኑ ወቅትም እየተከሰተ ባለው ቀውስ ጭምብል ማድረግ አስገዳጅ ሊሆን በተገባ ነበር። በ1918ቱም 675 ሺህ አሜሪካውያን ህይወታቸውን አጥተዋል፤ አሁንም ህይወታቸውን እያጡ ነው። ታሪክ ራሱን እየደገመ ይሆን?
news-50058089
https://www.bbc.com/amharic/news-50058089
"አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን"በቤይሩት ነዋሪ ኢትዮጵያውያን
ባለፉት ሰባት ወራት ለሥራ ወደ ሌባኖስ ካቀኑ ኢትዮጵያዊያን መካከል ሰላሳ አራቱ በተለያዩ ምክንያቶች ህይወታቸውን እንዳጡ በሊባኖስ ያሉ የኢትዮጵያዊያንና ሌሎች የበጎ አድራጎት ማህበራት ይፋ አደረጉ።
ለኢትዮጵያዊያኑ ህይወት መጥፋት በአብዛኛው እንደ ምክንያት የሚጠቀሰው በአሰሪዎቻቸው በሚፈጸምባቸው አሰቃቂ ግፍና ጥቃት ሳቢያ ራሳቸውን በማጥፋት እንዲሁም ካሉበት ኢሰብዓዊ የስቃይ ኑሮ ለማምለጥ በሚደርጉት ትግልና ጥረት እንደሆነም ተገልጿል። • መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ ማብቂያ የሌለው የኢትዮጵያውያን የስደት ጉዞ ይህ ይፋ የሆነው በሊባኖስ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እየገጠማቸው ያለውን አስከፊ ችግር በተመለከተ "መንግሥት የኢትዮጵያዊያን ሰራተኞችን ሞትና ስቃይን ለማስቆም" አፋጣኝ የሆነ እርምጃ እንዲወሰድ በጠየቁበት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ላይ ነው። "አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን" "አስከሬን ወደ አገር ቤት መላክ ደከመን" በማለት በደብዳቤያቸው ላይ ያሰፈሩት ኢትዮጵያዊያኑ በአገሪቱ ያለው ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለዜጎቹ ደህንነትና መብት እየሰራ ባለመሆኑ መንግሥት እርምጃ እንዲወስድ በአጽንኦት ጠይቀዋል። "በኢትዮጵያዊያን ላይ እየደረሰ ስላለው ግፍና ሰቆቃ በይገባኛል ስሜት አገርን ወክሎ በመንቀሳቀስ ረገድ በሌባኖስ ያለው የኢትዮጵያ ቆንስላ ሙሉ ኃላፊነትም ሆነ ግዴታ ቢኖረውም፤ እውነታው ግን ፍጹም ከዚህ የራቀ ነው" በማለት በደብዳቤያቸው ላይ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። ለሰባት ዓመታት ሊባኖስ ውስጥ ነዋሪ የነበረችውና ለችግር የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያንን ለመርዳት ከሚጥሩት አንዱን ድርጅት የምታንቀሳቅሰው ባንቺ ይመር ለቢቢሲ እንደተናገረችው "ይህ ነገር የቆንስላውን ስም ለማጥፋት የቀረበ ውንጀላ አይደለም" በማለት በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ማሳወቃቸውን ገልጻለች። ቆንስላው ዜጎቹን ለመርዳት ተገቢውን ጥረት ስለማያደርግ ኢትዮጵያውያን የተለያዩ ማህበራትን በመመስረት የቻሉትን ለማድረግ ጥረት እያደረጉ መሆናቸውን ጠቅሳ፤ እሷም በየቀኑ ከአምስት በላይ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ሆነው እንደሚደውሉላት ትናገራለች። • "ሶስት ጊዜ ለተለያዩ ነጋዴዎች ተሽጫለሁ" "እኛ የምንችለውን ከማድረጋችን በፊት ቆንስላው ያጋጠሙ ችግሮችን እንዲያውቅና ድጋፍ ሲጠየቁ ለመስማት እንኳን ፈቃደኞች አይደሉም" ስትል ታማርራለች። በተለያዩ አጋጣሚዎች ኢትዮጵያዊያን ችግር ውስጥ መሆናቸውን በተመለከተ ሪፖርት ሲደረግላቸውና ሄደው ሲያገኟቸው፣ የሚጠበቅባቸውን ለማድረግ ተባባሪዎች እንዳልሆኑና መረጃ ለማግኘት ስልክ በሚደወልበት ጊዜ ፈጽሞ መልስ እንደማይሰጡ ተናግራለች። ቢቢሲም በቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ላይ በኢትዮጵያውያን ላይ የቀረበውን ክስ አስመልክቶ በአራት መደበኛ ስልኮች ላይ በመደወል ለቀናት ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ሦስቱ ስልኮቹ ቢጠሩም የማይነሱ ሲሆን አንደኛው ደግሞ በደንበኛው ጥያቄ መሠረት እንዲቋረጥ መደረጉን ለማወቅ ችሏል። በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚበረታው በደል ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ከሊባኖስ የሠራተኞች ሚኒስቴር የወጣን መረጃ ጠቅሰው እንደሚሉት ከ150 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በሊባኖስ በተለያየ ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ። አክለውም ይህ አሃዝ በህጋዊ መንገድ ተመዝግበው ያሉትን የሚያመለክት በመሆኑ በተለያዩ ምክንያቶች ህጋዊ ሳይሆኑ በአገሪቱ የሚሰሩ በመኖራቸው ቁጥሩ ከዚህ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር ይገምታሉ። በኢትዮጵያዊያኑ ላይ የሚፈጸመው ግፍ ከሌሎቹ የተለየ እንደሆነ የሚናገሩት እነዚህ ለሰራተኞቹ መብት መከበር የሚጥሩት ቡድኖች ከክፍያ አንስቶ በሊባኖስ የሠራተኞች ህግ ተጠቃሚ አይደሉም። • ኢትዮጵያ ወደ አውሮፓና እስያ ሠራተኞችን ልትልክ ነው ኢትዮጵያዊያኑ በቀጣሪዎቻቸው፣ በአስቀጣሪዎቻቸውና ከሄዱበት መንገድ አንጻር የሌላ ሀገር ዜጎች እምብዛም የማይገጥማቸው ተጽእኖ እንደሚደረግባቸው በሊባኖስ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ሊቀመንበር ሳሙኤል ተስፋዬ ለቢቢሲ ይናገራል። "በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለምሳሌ መከፈል ያለበትን ዝቅተኛ ደሞዝ መጠን፣ አንድ ሰው ሊሰራ የሚገባውን የሥራ ሰዓትና የእረፍት ቀናቶችን የማግኘት መብታቸው ይጣሳል" ሲል ሳሙኤል ጠቅሷል። ያልተገታው ህገወጥ ጉዞ ከሁለት ዓመት በፊት የወጣ አንድ ሪፖርት እንዳመለከተው ከውጪ አገር መጥተው ሊባኖስ ውስጥ በሚሰሩ ሰዎች ላይ ከሚፈጸመው አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሰቆቃ በተጨማሪ በየሳምንቱ ሁለት ሰራተኞች ህይወታቸውን ያጣሉ። ከእነዚህ መካከልም አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ይነገራል። ይህ ሁሉ ስቃይ እየተሰማ አሁንም በርካታ ኢትዮጵያውያን በአብዛኛው ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ወደ ሌባኖስ እየመጡ እንደሆነ ባንቺ ትናገራለች። "ከሁሉ የሚያስደነግጠው ግን የሚፈጸመውን ግፍ ሳይሆን የሥራውን ጫና ለመሸከም የማይችሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መምጣታቸው ነው" በማለት ፓስፖርታቸው ግን ከ20 ዓመት በላይ እንደሆናቸው እንደሚያሳይ ትናገራለች። • ''ኢትዮጵያዊያንን የባሕር ላይ አደጋ መሞከሪያ ያደርጉ ነበር'' ለዚህ ደግሞ የቀበሌ መታወቂያን በሐሰተኛ መንገድ ለማውጣት መቻላቸው ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ሳሙኤል አንስቶ ቤተሰቦችንንና በዚህ ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉትን ይኮንናል። "ምንም እንኳን ወደዚህ የሚገፋቸው ችግር ቢሆንም፤ ቤተሰብ ልጆቹን ሲልክ በምን ሁኔታ ወደየት እንደሚሄዱና ምን ሊገጥማቸው እንደሚችል መረዳት አለበት" በማለት "ብዙዎች እዚህ ከመጡ በኋላ በሚገጥማቸው መከራና ጭካኔ እንኳን ለቤተሰባቸው ለራሳቸውም እንዳይሆኑ የሚያደርጉ ችግሮች ይገጥማቸዋል።" ወደሊባኖስ በመሄድ የራሳቸውንና የቤተሰባቸውን ኑሮ ለመለወጥ የወጡ በርካታ ኢትዮጵያዊን የሚገጥማቸው መከራ እንዳለ ሆኖ አንዳንዶች ደግሞ ደብዛቸው እንደሚጠፋ ባንቺ ትናገራለች። "የሰሚ ያለህ" "የት እንዳሉ ሳይታወቅ ከአስር እስከ አስራ አምስት ዓመታት በባርነት ያሉ፣ ድብደባ የሚፈጸምባቸው፣ የሚደፈሩ ሴቶችና ያለፍርድ እስር ቤት ያሉ አማራጭን ሲያጡ ራሳቸውን ለማጥፋት ይሞክራሉ" በማለት የግፍና ሰቆቃውን መጠን ትጠቅሳለች። ከዚህ ባሻገር በሚፈጸምባቸው በደልና በሚያልፉበት ግፍና ሰቆቃ ሳቢያ ሥነ ልቦናዊ መረበሽ እየገጠማቸው ለሌላ የከፋ ጉዳት እንደሚዳረጉና ለዚህም በርካታ ምሳሌዎች እንዳሉ ሳሙኤልና ባንቺ ይናገራሉ። ኢትዮጵያውያኑ በጻፉት ደብዳቤ ላይ እንዳሰፈሩት በሊባኖስ የሚደርስባቸውን መከራ ጉዳዬ ብሎ የሚከታተልና የሚረዳቸው የቆንስላ ጽህፈት ቤት እንዲኖራቸው እንደሚፈልጉ አመልክተዋል። "በሊባኖስ ያለውን የኢትዮጵያ ቆንስላ የዜጎች ህመም የማይታየው በሚሰጠው መረጃ ፍጹም የማይታመን፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ ዜጎች እንግልትና ስቃይ በሚደርስባቸው ግዜ የድረሱልን ጥሪ ሲያስተላልፉ ምንም እንዳልሰማ ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ የዜጎች ስቃይ ችላ የሚል ነው" ሲሉ አስፍረዋል። ባንቺ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ለቢቢሲ እንደተናገረችው "በሊባኖስ ያሉ ኢትዮጵያውያን ችግር በገጠማቸው ጊዜ ቆንስላው ይደርስልኛል ብሎ መጠበቅ ይቅርና አሉ ብሎ ማሰብም አይፈልጉም። ተጠሪ እንደሌለን ነው የምንቆጥረው" ትላለች። የማይሰማው ጽህፈት ቤት በአንዳንድ አጋጣሚዎች ቆንስላው ጣልቃ የሚገባበት ጊዜ ሲኖር ለዜጎቻቸው መብትና ደህንነት ከመቆም ይልቅ በአሰሪዎች ፊት ኢትዮጵያውያንን በማመናጨቅና በማዋረድ ወደነበሩበት የስቃይ ህይወት እንዲመለሱ እስከማስገደድ እንደሚደርሱ ባንቺ ትናገራለች። በዚህ ሁኔታ ወደ አሰሪዎቻቸው የተመለሱ ሴቶች ሊገጥማቸው የሚችለው መከራና ጥብቅ ቁጥጥር ምን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ቀላል ነው የምትለው ባንቺ ከነዚህ ውስጥ ለባሰ ችግር የተዳረጉ ኢትዮጵያዊያንን እንደምታውቅ ትናገራለች። "ቆንስላው በኢትዮጵያዊያን ላይ የሚፈጸሙ ግፎችን በተመለከተ አንዳንድ መረጃዎችን ከመሸፈን አልፎ፣ ጥቃት ስለተፈጸመባቸው እንዲሁም ስለተገደሉ ሰዎች በግልጽ የሚቀርቡ መረጃዎችን ማጣራትና መከታተል አይፈልግም። ማንም የሚጠይቃቸው የለም። ብዙ ጊዜ የሚገኙት የሞቱ ኢትዮጵያዊያንን ለመላክ ነው" በማለት ባንቺ በምሬት ትናገራለች። ኢትዮጵያዊያኑ በደብዳቤያቸው በሊባኖስ ከሚገኘው ቆንስላ ማግኘት ሲገባቸው ስላላገኙት አገልግሎትና ተፈጸሙ ስለሚሏቸው በደሎች አስፍረዋል። በዚህ ሁሉ መከራና ግፍ ውስጥ አሁንም በርካታ ኢትዮጵያውያን በህገ ወጥ መንገድ ወደሊባኖስ እየገቡ መሆኑን የሚናገረው ሳሙኤል፤ "በየዕለቱ የሚፈጸመው ሰቆቃና የምንሰማው ግፍ እየተባባሰ ነው። ከቆንጽላው በኩል የሚሰጠው መልስም ተስፋ አስቆራጭ ነው። ምንም መተማመኛ የለንም" ሲል የችግሩን መጠን መጨመር ጠቅሷል። በተጨማሪም በሊባኖስ የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግሥት ቆንጽላውን ወደ ኤምባሲ ከፍ እንዲያደርግና ለወገኖቻቸው የሚቆረቆሩና ኃላፊነት የሚሰማቸው ባለሙያዎችን መድቦ ለመብታቸውና ለደህንነታቸው ዋስትና እንዲሆናቸው በመጠየቅ በደብዳቤያቸው ላይ መደረግ ያሉባቸውን ነገሮች ጠቁመዋል። በሊባኖስ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን ቤይሩት በሚገኘው የቆንስላ ጽህፈት ቤት ላይ ስላነሷቸው ጉዳዮች በስልክ ምላሽ ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደዚያው ብንደውልም ስልኮቹ አይነሱም፤ በተጨማሪም አዲስ አበባ ከሚገኘው የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቆንስላው ውስጥ ኃላፊ የሆኑ ግለሰብን ስልክ አግኝተን መልስ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
news-53870296
https://www.bbc.com/amharic/news-53870296
ምርጫ ፡ የትግራይ ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ይጥላል?
በትግራይ ክልል የሚካሄደው ምርጫ ቀን ተቆርጦለታል። ክልላዊ ምርጫው ጳጉሜ 4 እንደሚካሄድ የክልሉ ምርጫ ኮሚሽን ይፋ አድርጓል። መራጮችም ከአርብ ጀምሮ የድምጽ መስጫ ካርድ መውሰድ ጀምረዋል።
በቅርቡም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክልላዊ ምርጫው መካሄድ እንደሌለበትና ምርጫውን ለማስቆም የፌደራል መንግሥት ጣልቃ ገብነትን እንደሚጠይቅ ለትግራይ ክልል ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል። የኢፌድሪ ሕገ-መንግሥት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባርን በሚደነግግበት አንቀጽ 62.9 ላይ "ማንኛውም ክልል ይህን ሕገ-መንግሥት በመጣስ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌደራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል" ይላል። ለመሆኑ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወደቀ ማለት ምን ማለት ነው? ይህ የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ ተፈጻሚ የሚሆነው እንዴት ነው? በትግራይ ክልላዊ ምርጫ በመካሄዱ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ይወድቃል? በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ የቀድሞ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛና ምክትል ፕሬዝደንት አቶ በሪሁ ተወልደብርሃን፣ በኔዘርላንድስ የአስተዳደርና ዲሞክራሲ አማካሪ አደም ካሴ (ዶ/ር) እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌደራሊዝምና የሰብዓዊ መብቶች መምህር ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወደቀ ማለት ምን ማለት ነው? በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 62.9 መሠረት የፌዴሬሽን ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት በአንድ ክልል ጉዳይ ጣልቃ እንዲገባ የሚያዘው ክልሉ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ጥሏል ብሎ ሲያምን ነው። አቶ በሪሁ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወደቀ የሚባለው፤ "ከመደበኛው ሥርዓት ኢ-መደበኛው ሥርዓት ገዢ በሚሆንበት ጊዜ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ነው" ቢባል በርካቶችን ሊያስማማ እንደሚችል ይናገራሉ። ሲሳይ መንግሥቴም (ዶ/ር) በመደበኛው የሕግ አስከባሪ አካል ሕግና ሥርዓትን ማስከበርና መቆጣጠር የማይቻልበት ሁኔታ ሲፈጠር፣ የአገር ሉዓላዊነት አደጋ ላይ ሲወድቅ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወድቋል ሊያስብል ይችላል ብለዋል። አደም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የሕገ-መንግሥቱ መሰሶ የሚባሉ ነጥቦችን የሚያዛባ ሁኔታ ከተፈጠረ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ተከሰተ ሊባል እንደሚችል ያስረዳሉ። አክለውም "ሁሉም የሕገ-መንግሥት ጥሰቶች ግን ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ይጥላሉ ማለት ግን አይደለም" ይላሉ። አቶ በሪሁ 'ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ ተጣሰ' እና 'ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወደቀ' በሚሉት አገላለጾች መካከል ልዩነት መኖሩን ይጠቁማሉ። "ሕገ-መንግሥታዊ ጥሰት ማለት ማናቸውም የጸረ-ሕገ መንግሥት ሂደቶችና ተግባራት ሲሆኑ፤ ሕገ-መንግሥቱ አደጋ ላይ ወድቋል የሚባለው ግን ሕገ-መንግሥታዊ ተቋማት በራሳቸው ውድቀት ሲያጋጥማቸው ነው" ይላሉ። እንደምሳሌም ሕግ አውጪ፣ አስፈጻሚው እና የዳኝነት አካላት በአንዳች ምክንያት ከተልዕኮ ውጪ ከሆኑ ሕገ-ምንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወድቋል ያስብላል ሲሉ አቶ በሪሁ ያስረዳሉ። የትግራይ ክልል፤ ምርጫ በማድረጉ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ይጥላል? አቶ በሪሁ ለዚህ ጥያቄ ምላሻቸው "አይጥልም" የሚል ነው። በዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የመንግሥት ሰልጣን የሚመነጨው በምርጫ ከመሆኑ አንጻር፤ "ምርጫ አደርጋለሁ ማለት ሕገ-መንግሥቱን ማክበር ነው። ስለዚህ ምርጫ ማካሄድ ለሕገ-መንግሥቱ አደጋ ሳይሆን ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እንዲከበርና ስር እንዲሰድ የሚያደርግ ተግባር ነው" ይላሉ አቶ በሪሁ። "በእኔ እምነት ምርጫ ማካሄድ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ማክበርና ማስከበር ከመሆኑ በስተቀር፤ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል አይደለም።" የፌዴሬሽን ምክር ቤት ክልሉ የሚያደርገው ክልላዊ ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ይጥላል ማለቱ ስህተት ነው ሲሉም ይሞግታሉ። "በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 13 ላይ በማንኛው ደረጃ የሚገኙ የፌደራል እና የክልል የሕግ አውጭ፣ ሕግ አስፈጻሚ እና የዳኝነት አካሎች ድንጋጌዎችን የማክበርና የማስከበር ኃላፊነት ግዴታ አለባቸው ይላል። የትግራይ ክልልም እያደረገ ያለው ይሄን ነው። ስለዚህ ለትግራይ ክልል ምርጫ ማካሄድ ግዴታው እንጂ ውዴታ አይደለም" ይላሉ አቶ በሪሁ። 'ክልላዊ ምርጫው መካሄዱ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ይጥላል' ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) በአቶ በሪሁ ሃሳብ አይስማሙም። ዶ/ር ሲሳይ የትግራይ ክልል የሚያካሂደው ምርጫ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ይጥላል ይላሉ። የክልሎች ሥልጣን የሚመነጫው ከሕገ-መንግሥቱ እንደሆነ የሚያስረዱት ሲሳይ (ዶ/ር)፤ አንቀጽ 50.8 የፌደራል መንግሥትና የክልሎች ሥልጣን በሕገ-መንግሥቱ መወሰኑንና ሕገ-መንግሥቱ የፌደራል መንግሥትና ክልሎች አንዳቸው የአንዳቸውን ሥልጣን ያከብራሉ ማለቱን ያስታውሳሉ። ከዚያም ሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 102ን ጨምሮ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ሕጎችን የማውጣትና የማስተዳደር እንዲሁም የምርጫ ቦርድ አባላት ሹመትን በተመለከተ ስልጣን የሰጠው ለፌደራል መንግሥቱ ነው ይላሉ። የክልል ሥልጣንና ተግባር የተደነገገበትን አንቀጽ 52 ስንመለከትም ምርጫ ለማካሄድ ወይም የምርጫ አካል ለማቋቋም ለክልሎች የተሰጠ ስልጣን አለመኖሩን እንረዳለን ይላሉ ሲሳይ (ዶ/ር)። "ስለዚህ የፌደራሉን መንግሥት ስልጣን የሚጋፋ የትኛውም እንቅስቃሴ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ውስጥ ይከታል" የሚሉት ሲሳይ (ዶ/ር)፤ "ክልሎች የፌደራሉን መንግሥት ስልጣን ከተጋፉ በክልሎች መካከል የሚኖረውን ግነኙነት አደጋ ውስጥ ይከታል። ከዚያም አልፎ የሕዝቦችን አንድነት የሚያላላና የግዛት አንድነትን ጥያቄ ውስጥ ይከታል። ስለዚህ የትግራይ ክልል ከምርጫ ጋር ተያይዞ እየወሰደ ያለው እርምጃ ሕገ-ወጥና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ነው" ሲሉ ሲሳይ (ዶ/ር) ይሞግታሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በተመሳሳይ ከሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) ሃሳብ ጋር ይስማማሉ። አደም (ዶ/ር) የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ሥርዓት በምርጫ የተወሰነ ነው ይላሉ። ከሕገ-መንግሥቱ ዋና ምሶሶዎች መካከል አንዱ ከምርጫ ጋር የተያያዙ ነጥቦች እንደመሆናቸው መጠን የፌደራል መንግሥቱን የምርጫ ሥርዓትን ወደጎን የሚተው ከሆነ ፌደራላዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ሊጥል ይቻላል ይላሉ። አደም (ዶ/ር) በዚህ ጉዳይ ላይ ትልቁ ምስል ምርጫ የማካሄድና ያለማካሄድ ጉዳይ ሳይሆን፤ "ክልሎችና የፌደራል መንግሥት አንዳቸው የአንዳቸውን ሥልጣን አክብረዋል ወይ የሚለው ነው።" "ከሞራላዊ እሳቤ አንጻር የትግራይ ክልል እኮ ኃላፊነቴን መወጣት አለብኝ በማለት ነው ምርጫ እካሂዳለሁ የሚሉት። ይሁን እንጂ መመልከት ያለብን ይህ እርምጃ በፌደራልና በክልል መካከል ያለውን የስልጣን ክፍፍል ይጥሳል ወይስ አይጥስም? የሚለው ነው። ስልጣኑ የፌደራል መንግሥት ነው እየተባለ ክልሉ ይህን ስልጣን መጠቀሙ ነው አደጋው" ይላሉ። ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወድቋል ብሎ የሚወስነው ማነው? ሲሳይ (ዶ/ር) ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወድቋል ብሎ የሚወስነው "የሕገ-መንግሥቱ የበላይ ጠባቂ የሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ነው" ይላሉ። በተመሳሳይ አደም (ዶ/ር) በሕገ-መንግሥቱ መሠረት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ አደጋ ላይ ወድቋል ብሎ የሚወስነውም ሆነ የፌደራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ የሚያዛው የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን ይናገራሉ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔር ብሔረሰቦች ጭምቅ ስብስብ በመሆኑ የብሔር ብሔረሰቦች መብት ያንጸባርቃል በመባሉ ይህ ኃላፊነት እንደተሰጠው አደም ካሴ (ዶ/ር) ይናገራሉ። የፌዴሬሽን ምክር ቤት አንድ ክልል ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ጥሷል ብሎ ወስኖ፤ እራሱ መልሶ የፌደራል መንግሥት በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገባ መወሰኑ ፍትሃዊ ያደርገዋል ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "አሁን ያለው የሕገ-መንግሥት ሥርዓት እንደ አገር ያዋጣናል አያዋጣንም የሚለው ሌላ ክርክር የሚያስነሳ ነው። አሁን ያለውን ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት እንቀበላለን እስከተባለ ድረስ ግን ይህን ብቻ ነጥሎ አንቀበልም ማለት አይቻልም" ይላሉ። "እውነት ነው የሚተረጉመውም የሚያዘውም አንድ አካል ነው። አቤት ማለት አይቻልም። ይህ መሠረታዊ የሆነ የአወቃቀር ችግር ነው። ይህን መለወጥ ሊኖርብን ይችላል። እስካልተለወጠና በሥርዓቱ እስካመንን ድረስ ግን ለሕገ-ምንግሥቱ ከመገዛት ውጪ ሌላ አማራጭ የለም" ይላሉ አደም (ዶ/ር)። ጣልቃ ይገባል ማለት ምን ማለት ? የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር በተደነገገበት የሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 62.9 ላይ ማንኛውም ክልል ይህን ሕገ-መንግሥት በመጣስ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለ እንደሆነ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ያዛል ይላል። ለመሆኑ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ ይገባል ሲባል ምን ማለት ነው? ሲሳይ መንግሥቴ (ዶ/ር) የፌደራል መንግሥት በክልል ጉዳይ ጣልቃ የሚገባው "እንደየ ችግሩ መጠን እና ስፋት ይለያያል" ይላሉ። የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጣልቃ ሊገባ የሚችልበትን መንገድ ሲያስረዱም፤ "ሕገ-መንግሥዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶችን ሊያስቆም በሚችል መልኩ ከድርድር እስከ የኃይል እርምጃ ሊደርስ ይችላል" ይላሉ። እንደምሳሌም የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝደንት አብዲ ሞሐመድ በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሌሎች ወንጀሎች በተጠርጠሩበት ጊዜ የፌደራሉ መንግሥቱ ከጅግጅጋ በቁጥጥር ሥር ያዋለበትን ሁኔታ ያነሳሉ። አደም ካሴ (ዶ/ር) በፌደሬሽን ምክር ቤት ትዕዛዝ መሠረት የፌደራል መንግሥት በክልል ጉዳይ በተለያየ መልኩ ጣልቃ ሊገባ እንደሚችል ይጠቁማሉ። የፌደራሉ መንግሥት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠውን ትዕዛዝ የመፈጸም ሕገ-መንግሥታዊ ግዴታ እንዳለበትም ያስታውሳሉ። ይሁን እንጂ ይላሉ አደም (ዶ/ር)፤ "ይሁን እንጂ አንድ ማስታወስ ያለብን ጉዳይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ስልጣን አለው ማለት የግድ ስልጣኑን መጠቀም አለበት ማለት አይደለም።" አደም (ዶ/ር) እንደሚሉት በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሥርዓት የዳበረ ቢሆን ኖሮ መሰል በክልልና በፌደራል መንግሥት መካከል የስልጣን ግጭት በተደጋጋሚ ባጋጠመ ነበር። ነገር ግን ይህ አለመግባባት ወደ ኃይል የሚያመራ አይሆንም ነበር ይላል። ለቀድሞ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛና ምክትል ፕሬዝደንት አቶ በሪሁ ተወልደብርሃን ግን "የፌዴሬሽን ምክር ቤት በምርጫው ጉዳይ የፌደራል መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ አዛለሁ ማለቱ ትክክል አይደለም፤ ስልጣኑም የለውም" ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪም አቶ በሪሁ አዋጅ ቁጥር 359/1995 የፌደራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሕጋዊ ሥርዓት ተክሏል ይላሉ። ሕገ-መንግሥቱም ቢሆን የፌደራል መንግሥት በክልሎች ጉዳይ ጣልቃ ሊገባ የሚችለው በሁለት ምክንያቶች እንሆነ አስቀምጧል ይላሉ። እነሱም፡ አንቀጽ 51.14 ከክልል አቅም በላይ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ሲያጋጥም በክልሉ መስተዳድር ጥያቄ የፌደራል መንግሥት የመከላከያ ሠራዊትን ያሰማራል ይላል። 55.16 ደግሞ በማንኛውም ክልል ሰብዓዊ መብቶች ሲጣሱና ክልሉ ድርጊቱን ማስቆም ሳይችል ሲቀር፤ በራሱ አነሳሽነትን ያለ ክልሉ ፍቃድ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ ለፌዴሬረሽን ምክር ቤትና ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ ጥያቄ ያቀርባል፤ በተደረሰበት ውሳኔ መሠረት ለክልሉ ምክር ቤት መመሪያ ይሰጣል ይላል። ከዚህ ቀደም ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ክስተት አጋጥሞ ነበር? ሲሳይ (ዶ/ር) ከዚህ ቀደም አንድ ክልል ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ጣለ የተባለበትን አጋጣሚ እንደማያስታውሱ ተናግረው፤ ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አህመድን ወደ ስልጣን የመጣው የሕዝብ ተቃውሞ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ ጥሏል ተብሎ በአገሪቱ በተደጋጋሚ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጆ እንደነበረ አስታውሰዋል።
45493518
https://www.bbc.com/amharic/45493518
'ልጅ ብወልድ ብዬ እመኛለሁ' አፈንዲ ሙተቂ
በከፍተኛ ቁጥር የተወደ ደልህ 'ፖስት'
እ... ትንሽ ቆይቷል… 'ኢትኖግራፊ' ስጽፍ በርካታ ተከታዮቼ ይወዷቸዋል፤ በአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት ዙርያ የጻፍኩት እስከ 8ሺህ የሚሆኑ ውዴታዎችን አግኝቷል። በዝቅተኛ ደረጃ የተወደደ ኸረ ብዙ ነው! በተለይ እንደ ጀመርኩ ሰሞን 10 ሰው ብቻ የሚወደው 'ፖስት' ነበር፤ ጽሑፉን በመጥላት ሳይሆን ብዙ ተጠቃሚ ባለመኖሩ። እጅግ አስቂኙ አስተያየት ባለፈው 'አዳል' የሚል የታሪክ መጽሐፍ ጽፌ ነበር፤ አንዱ 'ኮሜንት' ላይ እንዲህ አለ፣ "አሕመድ ግራኝ ከትግራይ ወደ ሐረር ተሰደው የመጡ መሆናቸውን ገልጸኻል፤ ስለዚህ የመጽሐፍህን ርዕስ በዶክተር ፍቅሬ ቶሎሳ ስታይል 'የትግሬና የአደሬ እውነተኛ የዘር ምንጭ' ማለት ነበረብህ' ያለኝ በጣም አስቆኛል። የምትወደው 'ፌስቡከር' ብዙ ናቸው፤ ዶ/ር እንዳላማው አበራን ግን የሚያህልብኝ የለም። አወዛጋቢ 'ፖስት' የሚያወዛግቡ ጽሑፎችን አልጽፍም፤የኔ ስታይልም አይደለም፤ የኔ ዓላማ ሰዎች እንዲቀራረቡ ስለሆነ የሚያወዛግብ ጉዳይ ቢኖርም ከመጻፍ ራሴን አቅባለሁ። እጅግ ያልተጠበቀ የውስጥ መስመር መልዕክት (ሳቅ)... የሚሳደበውን ትተን 'እስኪ ይህችን የሞባይል ካርድ ሙላት ከሚል ጀምሮ 10 ሺህ ብርና ላፕቶፕም የሸለመኝ አለ። ፌስቡክ ሳታይ የቆየህበት ረጅም ጊዜና ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለሁለተኛ ጊዜ ሲታወጅ ኢንተርኔት ተቋርጦ ስለነበር ለአንድ ወር ተኩል ያህል ጠፍቼ ነበር። ከመረጃ መራቁ ቢከብድም፤ ወደ ንባቡ በጣም አተኩር ነበር። ከማኅበራዊ ሚዲያው ምን አተረፍክ? እንደሚታወቀው ፌስቡክ የሚጠቀሙት አፍላ ወጣቶች ናቸው፤ ስሜታዊነት ይንፀባረቅበታል፤ ብዙም ሐሳብ የሚሰጥ ነገር የለውም፤ ግን ከሰው ጋር አስተዋውቆኛል። ከፌስቡክ ጡረታ የምትወጣበት ዘመን እ....ፈጣሪ ነዋ የሚያውቀው! ግን መውጣቴ አይቀርም፤ ሙሉ በሙሉ ባይሆንም አጠቃቀሙን መቀየር አስባለሁ፤ የጊዜ ገደብ ግን አላስቀመጥኩም። በ70 ዓመትዎ ፖስት ሊያደርጉት የሚችሉት ሐሳብ ከዛሬ 30 ዓመት በኋላ? አሁን እኮ 40 ዓመቴ ነው! እ... አይ መኖሬንም እንጃ! (ረዘም ያለ ፋታ) ወይ እንደ ዶናልድ ትራምፕ... (ሳቅ) በጣም ከባድ ጥያቄ ነው... እኔንጃ እንግዲህ.... ፌስቡክን የሚመለከቱበት ፍጥነት በአማካይ በቀን አራት ጊዜ ያህል አያላሁ ፤ፖስትም አደርጋለሁ። ማኅበራዊ ሚዲያ በመጠቀም ምን አጣህ? ጊዜ ይገድላል፤ በፊት መጽሐፍ ንባብ ላይ ነበር የማተኩረው፤ አሁን እሱም እየቀረ ነው። ትኩረትን ይሰርቃል፤ የሰውን ሐሳብ ይሰርቃል፤ እንደውም አንዳንዴ ሱስ ይሆናል። አይንም ይጎዳል ፤ አሁን የርቀት ዕይታዬ እየቀነሰ ነው። 2010ን በአንድ መስመር ቱርክን መጎብኘቴ አስደስቶኛል። የመንግሥት ለውጡም አስደስቶኛል። ለተሻለ ሕይወትና ነጻነት ሲታገሉ ዜጎች መሞታቸው ልቤን ነክቶታል። የ2011 ምኞት በአንድ መስመር ልጅ ብወልድ ብዬ እመኛለሁ።
50598835
https://www.bbc.com/amharic/50598835
ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት የሆነችው ረድኤት አበበ
የ28 ዓመቷ ረድኤት አበበ ተወልዳ ያደገችው አዲስ አበባ ነው። ኮምፒውተር ሳይንቲስቷ ረድኤት፤ በአልጎሪዝም እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) ዙርያ ትሠራለች። ረድኤት ከኮርኔል ዩኒቨርስቲ በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ በማግኘት የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ስትሆን፤ የመጀመሪያ ዲግሪዋን የያዘችው ከሀርቫርድ ዩኒቨርስቲ በሒሳብ ነው።
ረድኤት አበበ ሁለተኛ ዲግሪዋን በአፕላይድ ማቲማቲክስ የሠራች ሲሆን፤ ጥናቶቿ ኤአይን ጨምሮ ሌሎችም የቴክኖሎጂ ውጤቶች ያለ ጾታና የቆዳ ቀለም መድልዎ፣ ፍትሐዊ በሆነ መንገድ አብዛኛውን ማኅበረሰብ መጥቀም የሚችሉበት መንገድ ላይ ያተኩራሉ። ረድኤት፤ ፍትሐዊ የቴክኖሎጂ ተደራሽነት ላይ የሚያተኩሩ 'ሜካኒዝም ዲዛይን ፎር ሶሻል ጉድ' እንዲሁም 'ብላክ ኢን ኤአይ' የተሰኙ ተቋሞችን ከሙያ አጋሮቿ ጋር መስርታለች። በሥራዎቿ ዙርያ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርጋለች። ቢቢሲ፡ በታህሳስ ከኮርኔል በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ ትይዣለሽ። በዘርፉ ከዩኒቨርስቲው በፒኤችዲ የምትመረቂ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ነሽ፤ እንኳን ደስ አለሽ። ረድኤት አበበ፡ አመሰግናለሁ! በርካታ ጥቁር ሴቶች እንደ ኮርኔል ካሉ ትልቅ ዩኒቨርስቲዎች ለምን በዘርፉ አልተመረቁም? ችግሩ የኮርኔል ብቻ አይደለም። አሜሪካ ውስጥ ሲአርኤ የሚባል ተቋም አለ። በየዓመቱ በፒኤችዲ ተመራቂዎች 'ሰርቬይ' [ጥናት] ይሠራል። ወላጆችሽ የኮሌጅ ተማሪ ነበሩ? ዲግሪሽን በምን ጨረስሽ እና ሌሎችም ጥያቄዎች ይጠይቃሉ። ጾታና የቆዳ ቀለምም ይጠይቃሉ። ከዛ ውጤቱን በድረ ገጽ ይለጥፋሉ። ውጤቱን ሳይ. . . በየዓመቱ በመላው አሜሪካ በኮምፒውተር ሳይንስ ፒኤችዲ የሚመረቀው ጥቁር ሴት አምስት ብቻ ነው። በዓመት በኮምፒውተር ሳይንስ በፒኤችዲ የሚመረቀው ሰው ባጠቃላይ ወደ 3,000 ይሆናል። ከዛ ሁሉ አምስቱ ብቻ ጥቁር ናቸው። ሌላው ችግር ፕሮፌሰሮች ናቸው። አሜሪካ ውስጥ ቢያንስ ከ 5,000 በላይ የኮምፒውተር ሳይንስ ፕሮፌሰር አለ። ከነዚህ ጥቁሮች 75 ብቻ ናቸው። ከነዚህ ጥቁር ሴቶች 20ም አይሆኑም። ብዙ እንደኔ አይነት ሰው ወደ ፒኤችዲ መግባት ሲፈልግና የኮርኔልን፣ የፕሪንስተንን፣ የሀርቫርድን ፕሮግራሞችን ሲያይ፤ አንድ ጥቁር ፕሮፌሰር ቢኖራቸው ነው። በአብዛኛው ግን ዜሮ ነው። ስለዚህ 'ሮል ሞዴል' [አርአያ] የለም ማለት ነው። ስታመለክቺም መድልዎ አለ። ሰው የራሱን አይነት ሰው ነው መመዘን የሚችለው። ሰው ራሱን የሚመስል ሰው ይወዳል። ማመልከቻውን የሚያነቡት ሰዎች በሙሉ ጥቁር ካልሆኑ፤ ጥቁር ሰው ላይ መድልዎ ይኖራል ማለት ነው። ዩኒቨርስቲ ከገባሽ በኋላም ብዙ ድጋፍ ላታገኚ ትችያለሽ። ስለዚህ ይከብዳል። ብዙ ጥቁር ሴት ላያመለክት ይችላል። ካመለከቱም ላይገቡ ይችላሉ። ከገቡም ላይጨርሱ ይችላሉ። ለመጨረስም ብዙ ጊዜ ሊፈጅባቸው ይችላል። ኮርኔል ለመጨረስ የሚፈጀው አምስት ዓመት ነው። ግን ጥቁር ከሆንሽና ድጋፍ የማይሰጡሽ ከሆነ እስከ ስምንት ዓመትም ሊፈጅ ይችላል። • በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት • አምስቱ የአፍሪካ ቴክኖሎጂ ጎዳናዎች በ2018 የነገርሽኝን መሰናክሎች በሙሉ አልፈሽ ልትመረቂ ነው። እንደ አንድ ጥቁር ሴት ያለሽበት ቦታ መድረስ ምን ስሜት ይሰጥሻል? መመረቂያ ጽሑፌን ሳቀርብ ስለዚህ ጉዳይ ተናግሬያለሁ። በአንድ በኩል ሳስበው ለኔ ትልቅ ነገር ነው። ለፒኤችዲ ብዙ ዓመት ነው የሠራሁት። ስለዚህ ደስ ብሎኝ ነበር። ጓደኞቼ ኮርኔል ውስጥ በሌላ ትምህርት ክፍል ያሉትን ጨምሮ ጥቁር ተማሪዎችን ጠርተው ነበር። የኔ አድማጭ ግማሹ ጥቁር ነበር። ቀኑን ማክበር ፈልገው ነበር። ፕሮፌሰሮችም ነበሩ። አብዛኞቹ ፕሮፌሰሮች ከዛ ትምህርት ክፍል የምመረቀው የመጀመሪያ ጥቁር ሴት እኔ እንደሆንኩ አላወቁም ነበር። ምክንያቱም ስለዚህ ጉዳይ አያስቡም። እኔን ይሄ ነገር እንደሚረብሸኝ አይረብሻቸውም። ነገሩ [ከዛ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት መመረቋ] የሚያስደስት ነገር ሊመስል ይችላል። እኔ ሳስበው ግን ጥሩ ነገር አይደለም። እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ጨረስኩ፤ ግን ስንት ጥቁር ሴት ለዚ ትምህርት አመልክታ አልገባችም? ስንት ጥቁር ሴት ጀምራ አልጨረሰችም? ይሄን ሳስብ በጣም ያሳዝናል። በ2019 [እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር] የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት መመረቋ ጥሩ አይደለም። መመረቂያ ጽሑፌን ሳቀርብ "አያቶቼ እንኳን ኮሌጅ አንደኛ ደረጃም አልተማሩም" ብዬ ተናገርኩ። እኔ ግን ሁለቱንም እንደ ሳይንቲስት ነበር የማስባቸው። የአባቴ እናት መሶብ ትሠራ ነበር። ተሰጥኦ ነበራት። መሶቦቹን ጂኦሜትሪክ ዲዛይን ነበር የምታደርገው። በጣም ያምራል። አንድ ቀንም ይህንን ዲዛይን ስትጽፍ አላየሁም። ቁጭ ብላ መሥራት ትጀምራለች፤ ትጨርሳለች። በመደበኛ [ትምህርት ቤት] ሳይንስ ባታጠናም እንደ ሂሳብ ባለሙያ ነበር የምታስበው። የአባቴ አባት ደግሞ አርሶ አደር ነበር። ትልቅ እርሻ ነበረው። የሚያርሰው ራሱ በሠራው መሣሪያ ነበር። ትራክተር የገዛው በጣም ካረጀ በኋላ ነበር። አያቶቼ ባይማሩም እንደ ሳይንቲስት ያስቡ ነበር። አዲስ አበባ ሳድግ፤ እናትና አባቴን ሳይም ራሴን እንደ ሳይንቲስት አይ ነበር። አሜሪካ ስመጣ ግን የተነገረኝ ጥቁር ሰው ሳይንስ አይችልም፤ ሴት ሳይንስ አትችልም ተብሎ ነበር። ኢትዮጵያ ሳድግ ግን ሴት፣ ወንድ፤ አማራ፣ ኦሮሞ ተብሎ ሳይከፋፈል ሁሉም ሳይንስ መሥራት እንደሚችል ነበር የማስበው። መመረቂያ ጽሑፌን ሳቀርብም የነገርኳቸው ይህንኑ ነው። "ሳድግ ሳይንቲስት ለመሆን አስብ ነበር። አሜሪካ መጥቼ 'አንቺ ሳይንስ አትችይም' ስባል በጣም ገረመኝ፤ አሳዘነኝም። ይሄንን ነገር መለወጥ አለባችሁ። ምክንያቱም እናንተ እንደ ሳይንቲስት ባታዩኝ እንኳን ራሴን እንደ ሳይንቲስት ነው የማየው" አልኳቸው። ረድኤት አበበ አርቴፍሻል ኢንተለጀንስን (ኤአይ) ጨምሮ ዘመነኛ ቴክኖሎጂዎች አካታች እንዳልሆኑ (በተለይ ጥቁሮችና ሴቶችን)፣ ኢ-ፍትሐዊነት እንደሚስተዋልባቸውም የሚናገሩ ባለሙያዎች አሉ። ቴክኖሎጂው አካታች መሆን ያልቻለው ለምንድን ነው? ጉዳዩ ብዙ ችግር አለበት። ኤአይ በዳታ ላይ የተመረኮዘ ነው። አልጎሪዝም ስትሰጪ ዳታውን ይወስድና ከዳታ ውስጥ ፓተርን ያያል። እሱን ይዞ ክሬዲት ያደርጋል። ለምሳሌ አሜሪካ ውስጥ ወደ 15 በመቶው ጥቁር ሰው ነው። ዳታውን ስታይ በጣም ትንሽ ጥቁር ሰው ነው የምታይው። ዳታው ብዙ ጥቁር ሰው አካታች አይደለም። ማሽን ለርኒንግ አልጎሪዝም 'ትሬን' ስታደርጊ [ሲሠራ]፤ የማያየውን ሰው ጉዳይ በደንብ አያጠናም። በዚህ ተመርኩዞ 'ፕሪዲክት' ሲያደርግ [ሲገምት] ጥሩ አይሆንም። ለምሳሌ ትምኒት ገብሩ ፌሻል ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ ላይ አንድ ሥራ አላት። ፌሻል ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂው ያጠናው በአብዛኛው ነጭ ወንዶችን ነው። ስለዚህ ጥቁር ሴት ስትሰጪው ትክክለኛ አይሆንም። እንደዚህ አይነት ቴክኖሎጂን የሚሠሩ ሰዎች ጥቁሮች አይደሉም፤ ሴቶች አይደሉም። ስለዚህ ቴክኖሎጂዎቹ አካታች አይደሉም። ለምሳሌ አማዞን አንድ መሣሪያ ሠርቶ ነበር። ጾታን መሰረት ያደረገ መድልዎ እንዳይፈጠር ተብሎ ጾታና ስም [ከመሣሪያው] ጠፋ። ግን የኮሌጅ ስም አልጠፋም ነበር። አንዳንድ ኮሌጆች ደግሞ የሴቶች ብቻ ናቸው። ስምና ጾታ ቢጠፋም የኮሌጁ ስም ፕሮክሲ ይፈጥራል። ይህንን ሳያውቁ ይጠቀሙበት ነበር። ከዛ ሴቶችን ማግለል ሲጀምር [ክፍተቱ] ታወቀና ጠፋ። ግን ይህ ቴክኖሎጂ ሲሠራ ሴት ብትኖር፣ መናገር ብትችል ይሄንን ጉዳይ ትይዘው ነበር። ከዚህ ጋር በተያያዘ "ሂውማን ሴንተርድ ኤአይ" [ሰውን ያማከለ ኤአይ] የሚለው ሀሳብ በተደጋጋሚ ይነሳል። አሁን ባለንበት ዘመን ቴክኖሎጂ ሰዎችን እንዲጠቅም የሚደረገው በምን መንገድ ነው? "ሂውማን ሴንተርድ ኤአይ" የመጣው ለዚህ [አካታች ላልሆነ ቴክኖሎጂ] እንደ መልስ ነው። ድሮ ቴክኖሎጂ 'ዴቨሎፕ' ስናደርግ መጀመሪያ የምናስበው ቴክኖሎጂ ምን ይሠራል? ምን ያህል ሳይንሱን ማሳደግ ይቻላል? ብለን ነበር። አሁን የፈለግነው ግን ከሰው መጀመር ነው። ሰው ምንድን ነው የሚያስፈልገው? ምን ሰውን የሚጠቅም ነገር መሥራት እንችላለን? መጀመሪያ የምታስቢው ነገር ስለ ሰው ነው ወይስ ስለ ቴክኖሎጂ ነው? ይሄ ለመጀመር ጥሩ ቦታ ነው። ግን ማሰብ ያለብን ስለየትኛው ሰው እንደምንነጋገር ነው። "ሂውማን ሴንተርድ ኤአይ" ብለሽ መጀመሪያ የምታስቢው ለወንዶች ከሆነ ካለንበት ቦታ ብዙም አይለወጥም። የምናስበው ከመጀመሪያውም የተገለሉ ሰዎችን ከሆነ ግን ሊለወጥ ይችላል። • የሰዎችን ማንነት የሚለየው ቴክኖሎጂ እያከራከረ ነው • ቻይናዊው ቢሊየነር በአዲስ አበባ ሁለት ዓለሞችን በምናብ እንድትስይልኝ አፈልጋለሁ። አንደኛው ኤአይ በቀዳሚነት ሰዎችን የሚጠቅምበት ዓለም፤ ሁለተኛው ደግሞ ኤአይ አካታች ያልሆነበትና በመድልዎ የተሞላ ዓለም። ሁለተኛው ዓለም አሁን ያለንበት ነው። በአብዛኛው ፓወር የሚደረገው ዳታ፣ አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ፣ በጣም የተራቀቀው ቴክኖሎጂ ያላቸው እነ ጉግል እና ፌስቡክ ናቸው። ካምብሪጅ የሚኖር ጥቁር ልጅ የቴክኖሎጂው 'አክሰስ' [ተደራሽነት] የለውም። ጉግል የሰው ዳታ ወስዶ እየተጠቀመበት፤ አልፈልግም ማለት አይችልም። ድንጋጌም የለም። ለምሳሌ እዚ አገር ቤት ፈልገሽ ስታመለክቺ አከራዩ የኤአይ ድርጅት መጠቀም ይችላል። ድርጅቱ አልሰጥሽም ማለት ይችላል። አልጎሪዝማችሁ ምንድን ነው የሚለው? ብለሽ መጠየቅ አትችይም። 'አክሰሱ' ያላቸው ጉልበት ያላቸው ተቋሞች ናቸው። በተለይ የተገለሉ ሰዎች (ሴቶች፣ ጥቁሮች፣ ስደተኞች) 'አክሰስ' የላቸውም። የመጀመሪያው አይነት ዓለም ላይ መድረስ የምንችል ይመስለኛል። ትምህርትና ልማት ላይ ሁሉንም ሰው ካካተትን መለወጥ እንችላለን። ኢትዮጵያዊ ስለሆንኩ የኢትዮጵያና የአፍሪካ ነገር ያሳስበኛል። አንድ ኢትዮጵያዊ አርሶ አደር በሚቀጥለው ወር ይዘንባል ወይስ አይዘንብም?፣ ከዘነበስ ምን ያህል ይዘንባል?፣ የገበያው ሁኔታስ ምን ይመስላል? የሚለውን ማወቅ ይፈልጋል። እኔ የማስበው. . . የኤአይ ቴክኖሎጂን ዴሞክራሲያዊ አድርገን፤ ሁሉም ሰው 'አክሰስ' እንዲኖረው ካደረግን፤ እንኳን ትልቅ ድርጅት አንድ አርሶ አደርም መርዳት ይቻላል። እስኪ አንድ አርሶ አደር 'ዌብሳይት' [ድረ ገጽ] የሚጠቀምበት 'አክሰስ' ሲኖረው አስቢው። "መሬቱ ይህን ያህል ነው፤ ይሄ [ቦታ] ሰብል ይዟል ስትይው" በጣም ይረዳዋል። እኔ ለሁሉም ሰው 'አክሰስ' መስጠት የምንችልበት ዓለምን ነው የምፈልገው። በመላው ዓለም ማለት በሚቻልበት ደረጃ የቴክኖሎጂ ፍርሀት እየተስፋፋ ይመስላል። ሥራችንን ልንነጠቅ ነው፣ ቴክኖሎጂ ከመጠን በላይ በሕይወታችን ገብቶ እያመሰቃቀለው ነው ወዘተ. . . በተደጋጋሚ የሚስተጋቡ ስጋቶች ናቸው። በእርግጥ ታሪክን እንደ ማሳያ ብንወስድ፤ ሰዎች ለውጥ ሲፈሩ ተስተውሏል። ፈጠራዎችን እንዲሁም አዲስ ነገሮችን ባጠቃላይ ለመልመድም ጊዜ ይወስዳል። አሁን እየታየ ያለው ግን ለውጥን መፍራት ሳይሆን መሰረት ያለው ስጋት ነው የሚሉ ባለሙያዎች አሉ። እና በርካቶች ዘመኑን መፍራታቸው ልክ ነው? አንቺስ ያለንበት ወቅት እንዲሁም የወደፊቱ ዓለም ያስፈራሻል? መፍራታቸው ልክ ነው። እውነት ነው ሰው ለውጥ አይፈልግም። አይወድም። እንኳን ኤአይ ሌላ ቴክኖሎጂም ሲተዋወቅ እንደዛ ነው። አሁን በኤአይ ከላይ ወደታች ማለትም የሆነ ድርጅት 'ዴቨሎፕ' [አምርቶ] አድርጎ ይሰጠናል። እምቢ ማለት አንችልም። ግን ቴክኖሎጂውን 'ዴቨሎፕ' አድርገን ሰው ላይ በግዴታ ከመጫን ትምህርቱን አስፍተን፣ ሰው የሚፈልገውን ነገር ራሱ ቢሠራ፤ ያኔ ለውጡን ይወደዋል። ምክንያቱም ራሱ የሠራው ለውጥ ነው። ለምሳሌ አንድ ትልቅ ድርጅት፤ ይህንን መሣሪያ ሠርተናል ውሰዱት ብሎ ለአርሶ አደሮች ሲሰጥ ሊያስፈራቸው ይችላል። ልክም ናቸው። ምንድን ነው የምትፈልጉት? ምን እንሥራላችሁ? ብለን አነጋግረናቸው፣ የነሱን ሀሳብ ወስደን፤ ሠርተን ተደራሽነቱን ብናሰፋ ወይም ራሳቸው 'ዴቨሎፕ' እንዲያደርጉት ብናደርግ ችግር አይኖርም። ድሮ 'ታይፕ ራይተሮች' ነበሩን። አሁን ሁላችንም መጻፍ ስለምንችል አያስፈልገንም። እንደዚህ ሥራ ሲለወጥ ችግር የለውም። ሥራዎች ሲለወጡ ግን ሌላ ሥራዎች እየተፈጠሩ [መሆን አለበት]። ብዙ ቦታዎች የሶፍትዌር ኢንጂነር ሥራዎች ያስፈልጋቸዋል። ጉግል ብቻ ሳይሆን ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶችም ሶፍትዌር ኢንጂነር ያስፈልጋቸዋል። ግን ለነዚህ ሥራዎች 'አክሰስ' ያለው ማነው? ሁሉም ሰው ነው ወይስ ትንሽ ሰው? ስለዚህ አንዳንድ ሥራዎችን 'አውቶሜት' ስናደርግ ሁሉም ሰው 'አክሰስ' እንዲኖረው [አስበን] መጠንቀቅ አለብን። አሁን ግን እየተጠነቀቅን አይደለም። ሰው የሚፈራውም ለዚህ ነው። መፍራታቸውም ልክ ነው። ግን መለወጥ እንችላለን። አልረፈደም። ኤአይ በየዘርፉ እየገባ ነው። የወደፊቱን ዓለም ስናስብም በብዙ መስኮች ማዕከላዊ ቦታ ይኖረዋል። ህክምናን እንደ ምሳሌ ብናነሳ፤ ኤአይ አፍሪካ ውስጥ በህክምና ዘርፍ ምን አይነት ሚና ሊኖረው ይገባል ትያለሽ? በዚህ ጉዳይ ላይ አንድ ጽሑፍ አለኝ። 'ኦንላየን' [በድረ ገጽ] ሰዎችን በመጠየቅ ሰርች ዳታ ነበረን። ከ54 የአፍሪካ አገሮች እሱን ዳታ ወሰድንና ሰው ስለ ህክምና ምን አይነት ጥያቄ እየጠየቀ ነው? 'ኦንላየን' መረጃስ እንዴት ነው የሚያገኘው? ብለን አጠናን። አፍሪካ ኅብረት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና ሌሎችም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ሪፖርት አላቸው። እና አፍሪካ ላይ ዳታ የለም ይላሉ። ለምሳሌ ኤችአይቪ ኤድስን ብትወስጂ፤ እንኳን ዝርዝር ዳታ አይደለም፤ በአንድ አገር በየዓመቱ ስንት ሰው በኤድስ ሞተ? ብለሽ ብትጠይቂ መረጃውን ማግኘት በጣም ይከብዳል። ከተገኘም ስህተት ይኖረዋል። እና እንደዚህ አይነት ጉዳዮች ላይ ብዙ ዳታ ቢኖረን ጥሩ ነው። ያኔ ያለንን 'ሪሶርስ' [ሀብት] መጠቀም እንችላለን። እኛ [ጥናቱን የሠሩት ባለሙያዎች] ማየት የፈለግነው፤ ስለ ኤችአይቪ ኤድስ ሰው ምን አይነት መረጃ እየጠየቀ ነው? እንዴት አይነት መረጃ እየተሰጠው ነው? የሚለውን ነው። ስለ አፍሪካ የህክምና ጉዳይ ሳስብ መረጃ የለም። ቴክኖሎጂ የለም። ቴክኖሎጂ ካለ ደግሞ ላይሠራ ይችላል። ለምሳሌ ኢትዮጵያ መብራት ይጠፋል። [ስለዚህ] በባትሪ የሚሠራ ነገር ሊሠራ ይችላል። ኢንተርኔት ከጠፋ 'ኮኔክሽን' የማያስፈልገው ነገር መሥራት ትችያለሽ ወይ?. . . ብዙ 'ዴቨሎፕ' ማድረግ የምንችለው ነገር አለ። አፍሪካዊ ሰዎችን ማሳተፍ እንችላለን። ብላክ ኢን ኤአይ፣ ዳታ ሳይንስ አፍሪካ እና ሌሎችም ተቋሞች አፍሪካ ላይ ይሠራሉ። ሁላችንም የምናስበው ለአፍሪካ ጉዳይ መልሱ የሚመጣው ከአፍሪካዊ እንደሆነ ነው። ከውጪ አይመጣም። መድልዎን ማቆም፣ አፍሪካን መጠበቅ እንችላለን። ትምህርቱን አስፍተን፤ ተሰጥኦው እንዲወጣና በዓለም እንዲታይ ማድረግ አለብን። ረድኤት አበበ የነገርሽኝ "ዩዚንግ ሰርች ክዌሪስ ቱ አንደርስታንግ ኸልዝ ኢንፎርሜሽን ኒድስ ኢን አፍሪካ" የተሰኘው ጥናት ሲሠራ ናሙና ከተወሰደባቸው አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ናት። በኢትዮጵያ፤ በጤና ዘርፍ ከመረጃ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያገኛችሁት ክፍተት ምንድን ነው? እንደ ምክረ ሀሳብ ያቀረባችሁትስ? በኢትዮጵያ ምን አይተናል መሰለሽ. . . ሰዎች ነጭ ሽንኩርት፣ ማር ወይም ሎሚ ከኤችአይቪ ይፈውሳል? ከተጸለየልኝ ኤችአይቪ ይጠፋል? እነዚህ አይነት ጥያቄዎች ሲጠየቁ 'ዌብሳይት' ላይ "አዎ፤ ነጭ ሽንኩርት ኤችአይቪን ያጠፋል" ተብሎ ይጻፋል። በዚህ ጉዳይ ላይ የጤና ጥበቃ ሚንስትር ሊያስብብበት ይገባል። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም አገሮች [በአፍሪካ] እንደዛ ነው። ሌላው ጥያቄ ስለ መገለል ነው። ኤችአይቪ በደሜ በመኖሩ ከሥራ ልባረር እችላለሁ? ሰው ያገለኛል? ብለው ይጠይቃሉ። ኢትዮጵያ እያለሁ ሰዎች እንዳይገለሉ [አስተማሪ] ድራማ ይታይ ነበር። በጤና ጥበቃ [መረጃ የሚሰጡ] ንቅናቄዎች በጣም ይረዳሉ። ኢትዮጵያ ግን ብዙ ይቀራታል። ብዙ መሻሻል ያለባቸው ነገሮች አሉ። • ካንሰር እንዴት እንደተፈጠረ ማወቁ ለምን አስፈለገ? • ማይክሮሶፍት ጽሁፍን የሚያቀል አሠራር ፈጠረ
news-42114518
https://www.bbc.com/amharic/news-42114518
በግብጽ መስጊድ በደረሰ ፍንዳታ ቢያንስ 235 ሰዎች ሞቱ
ተጠርጣሪ ታጣቂዎች በግብጽ ሰሜናዊ ሲናይ ክልል የቦምብና የተኩስ ጥቃት በመሰንዘር 235 ሰዎች መግደላቸውን የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
ታጣቂዎቹ በአል-አሪሽ አቅራቢያ የሚገኝን መስጊድ ኢላማ አድርገዋል የዓይን እማኞችም በአል-አሪሽ አቅራቢያ በቢር አል-ኣቤድ ከተማ የሚገኘው አል-ራውዳ በአርብ ጸሎት ጊዜ ኢላማ መደረጉን አረጋግጠዋል። አሶሺየትድ ፕሬስ በበኩሉ የአካባቢውን ፖሊስ በመጥቀስ ታጣቂዎቹ በአራት መኪኖች በመምጣት በምዕመናኑ ላይ ተኩስ መክፈታቸውን ገልጿል። ግብጽ ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ የእስላማዊ ሰርጎ ገቦችን ጥቃት ለመመከት እየሰራች ነው። እስካሁን በሲናይ በታጣቂዎች ተደጋጋሚ ጥቃቶች ቢፈጸሙም በደም አፋሳሽነቱ ግን ይህ ከፍተኛ ነው። በጥቃቱ ሌሎች 100 ሰዎችም ተጎድተዋል።
news-55717279
https://www.bbc.com/amharic/news-55717279
አሜሪካ ፡ በዛሬው የጆ ባይደን በዓለ ሲመት ላይ ምን ሊከሰት ይችላል?
የአሜሪካ ምርጫ ተመዞ አያልቅም። ወገብ ይቆርጣል።
ባይደን እና ሃሪስ ይህን ምርጫ ተከትሎ የሚመጣው ፕሬዝዳንት ታዲያ ደማቅ አቀባበል ቢደረግለት ቢያንስ እንጂ አይበዛበትም። አሜሪካ አዲስ ፕሬዝዳንቶቿን ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት የምታስገባበት የራሷ ወግና ሥርዓት አላት። ዘንድሮ ግን በኮቪድ-19 እና በነውጠኞቹ የትራምፕ ደጋፊዎች ምክንያት በታሪክ ደብዛዛው በዓለ ሲመት ነው የሚሆነው ተብሏል። 46ኛው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዚህ ረገድ ዕድለኛ አይደሉም። ለማንኛውም ስለዚህ ሥነ ሥርዓት የሚከተሉትን ነጥቦች ማወቁ አይከፋም። ፕሬዝዳንታዊ በዓለ ሲመት ምንድነው? የበዓለ ሲመቱ መደበኛ ቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓቱ የሚካሄደው የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ በሆነችው በዋሺንግተን ዲሲ ነው። ዕለቱ የፕሬዝዳንቱ ይፋዊ የሥራ መጀመሪያ ቀን ተደርጎ ይታሰባል። በዚህ ቀን ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሐላ ይፈጽማል። ቃለ መሐላው ይዘቱ የሚከተለው ነው፡- "በሐቅና በታማኝነት የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆኜ ለማገልገል ቃል እገባለሁ፤ ባለኝ አቅም ሁሉ፣ የአሜሪካንን ሕገ መንግሥት ለመጠበቅ፣ ለማክበርና ለማስከበር እተጋለሁ!" ልክ ይህን ቃል መሐላ እንደፈጸሙ ነው ጆ ባይደን 46ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳት መሆናቸው በይፋ የሚበሰረው። ሥነ ሥርዓቱ በዚሁ ያበቃል። ፈንጠዚያው ግን ይቀጥላል። ምክትል ካመላ ሐሪስም በዚሁ ዕለት ነው ቃል መሐላ የሚፈጽሙት ብዙውን ጊዜ ፕሬዝዳንቱ ቃለ መሐላ ከመፈጸማቸው በፊት ምክትላቸው ይህንኑ እንዲያደርጉ ይደረጋል። መቼ ነው በዓለ ሲመቱ? ዛሬ ረቡዕ ነው ኩነቱ ሁሉ የሚከወነው። በሕግ የአሜሪካ ፕሬዝዳታዊ በዓለ ሲመት በጃንዋሪ 20 (ጥር 12) ነው የሚሆነው። ሥነ ሥርዓቱ ብዙውን ጊዜ በዋሺግተን ሰዓት ከረፋዱ 5፡30 ነው የሚጀመረው። እኩለ ቀን ላይ ባይደንና ሐሪስ ቃለ መሐላ ይፈጽማሉ። ጆ ባይደን ያንኑ ቀን ከሰዓት በኋላ [ማለትም ወደ 9 ሰዓት ግድም] ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ይገባሉ። ይሄ ቤት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት የጆ ባይደን መኖሪያም መሥሪያ ቤትም ይሆናል። ዕድሜ ከሰጣቸው። የቤቱን ጠቅላላ መንፈስ ከትራምፕ ፖለቲካና ግለሰባዊ ጠረን ለየት ለማድረግ መጠነኛ እድሳትና የዲዛይን ለውጥ አይደረግም አይባልም። አንድ ፕሬዝዳንት ጨርሶ ሌላው ሲገባ ይህን ማድረግ የተለመደ ነው። ነውጠኛ የፕሬዝዳንት ትራምፕ ደጋፊዎች ካፒቶል ሒልን ጥሰው ከገቡ በኋላ ለበዓለ ሲመቱ የሚደረገው የጸጥታ ጥበቃ ተጠናክሯል ረብሻ ሊቀሰቀስ ይችላል? ወትሮም ይህ በዓለ ሲመት በየአራት ዓመቱ በመጣ ቁጥር ብዙ የደኅንነት ከለላና ጥበቃ አይለየውም። በግላጭም በኅቡዕም። ምክንያቱ ደግሞ በርካታ ሕዝብ የሚገኝበት ኩነት ስለሆነ ነው። ከሕዝብም እጅግ ቁልፍ የሚባሉ ኃያላን ባለሥልጣናት የሚገኙበት ነው። ለጠላትም ጥቃት ለመፈጸም ምቹ ጊዜና ቦታ መሆኑም ይታወቃል። የዘንድሮ ደግሞ ከዚህም በላይ ጥበቃ የሚሻ ሆኗል። የትራምፕ ነውጠኛ ደጋፊዎች አደጋ ለመጣል ስለዛቱና ይህም በፌዴራል የምርመራ ቢሮ ስለተደረሰበት 15 ሺህ የአሜሪካ ብሔራዊ ጥበቃ ወታደሮች እዚያም እዚህም ተሰማርተዋል። እነዚህ የጸጥታ አባላት ለዋሺንግተን ዲሲና አካባቢው ብቻ የተመደቡ ናቸው። ልብ አድርጉ፣ ዋሺንግተን ዲሲ አሁንም በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥር ናት። ይህን የጸጥታ ጥበቃ 'ሲክሬት ሰርቪስን' [ምስጢራዊው የደኅንነት አገልግሎት] ተክተው የሚመሩት ማት ሚለር፣ ለዛሬው ቀን ጸጥታ ከአንድ ዓመት በላይ ዝግጅት እንደተደረገ ተናግረዋል። በትራምፕ ሲመተ በዓል ላይ ባራክ ኦባማ ተገኝተው ነበር ዶናልድ ትራምፕ ይገኛሉ? እርግጥ ነው አንድ ፕሬዝዳንት ሲሸነፍም ሆነ የተገደበውን የሥልጣን ዘመኑን ሲጨርስ ለቀጣዩ ፕሬዝዳንት ሥልጣኑን በይፋ የሚያስረክበው በዚህ ሥነ ሥርዓት ላይ ነው። ትራምፕ ግን ለደንብና ሥርዓት የሚገዙ ሰው አይደሉም። ትራምፕ በበዓለ ሲመቱ ላይ ተገኝተው ዓለምን ያስገርማሉ ሲባል ነበር በአንዳንድ ሚዲያዎች። ከሁለት ሳምነት በፊት ገደማ ግን ለሕዝባቸው ቁርጡን ተናግረዋል። በትዊተር በጻፉት አጭር ጽሑፍ እንዲህ በማለት፡- "ትመጣለህ ወይ እያላችሁ ለምትጠይቁኝ ሁሉ! አልመጣም።" በዚህ ዕለት ትራምፕ የት ይሄዱ ይሆን? ምናልባት ከጎልፍ መጫወቻ መስኮቻቸው በአንዱ ውስኪ ይዘው ይሸጎጡ ይሆን? በምርጫ የተሸነፉ ቀን ጎልፍ ላይ ነበሩ። ደጋፊዎቻቸው ግን አሁንም "መሄድክን አላምንም" እያሏቸው ነው። ለዚህም ያሸነፉት ትራምፕ ናቸው ብለው ከልባቸው ስለሚያምኑ በኦንላይን [በኢንተርኔት] የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓት አዘጋጅተናል ብለዋል። 70 ሺህ ሰዎች በዚህ ሐሳዊ የትራምፕ የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓት ላይ ለብሰን አጊጠን እንገኛለን ብለዋል። ትራምፕ የዛሬ 4 ዓመት ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ ተሸናፊዋ ሒላሪ ከባለቤታቸው ቢል ክሊንተን ጋር ተገኝተው ነበር። ከዚያ ሁሉ እልህ አስጨራሽ ክርክርና የሚያስቆጭ ሽንፈት በኋላ ነው የተገኙት። ደግሞም ያኔ ብዙ ሰው የመረጠው ሒላሪን እንጂ ትራምፕን አልነበረም። በግዛት ውክልና ቆጠራ አሰራር ነው ለሽኝት የተዳረጉት። ቢሆንም ሒላሪ ሽንፈታቸውን ዋጥ አድርገው ፈገግ ብለው ሥነ ሥርዓቱን ታድመዋል። ዶናልድ ትራምፕ ግን የዲሞክራቶችን ውለታ የሚመልሱ አይደሉም። ከዚህ በፊት በአሜሪካ ታሪክ 3 ፕሬዝዳንቶች ብቻ በተቀናቃኛቸው በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ቀርተዋል። እነሱም ጆን አዳምስ፣ ጆን ኩንሲ አዳምስ እና አንድሩ ጆንሰን ናቸው። ሆኖም ባለፈው መቶ ዓመት ይህ ሆኖ አያውቅም። ትራምፕ ናቸው የመጀመርያው ሰው። ማይክ ፔንስ ግን የጆ ባይደንን በዓለ ሲመት እታደማለሁ ብለዋል። በባራክ ኦባማ የመጀመሪያ ሲመተ በዓል ላይ ሁለት ሚሊዮን ሕዝብ በሥነ ሥርዓት ላይ ታድመው ነበር ምን ያህል ሕዝብ ይገኛል? ከዚህ ቀደም ሚሊዮነች ይጎርፉ ነበር። ለምሳሌ ባራክ ኦባማ በ2009 ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ 2 ሚሊዮን ሕዝብ ዲሲን አጨናንቋት ነበር። ሆቴል አልጋ የሚባል ጠፍቶ፣ ጎዳናዎች በሕዝብ ተሞልተው፣ እንደው ነገሩ ሁሉ ትልቅ ብሔራዊ በዓል ነበር የሚመስለው። የሥነ ሥርዓቱ ታዳሚ በሚሰባሰብበት በናሽናል ሞል ሰፊ መስክ ላይ ጠጠር ቢጣል መሬት አይወድቅም ነበር። ዘንድሮ ግን ኮቪድና የትራምፕ ደጋፊዎች ነገሩን አደብዝዘውታል። ሥነ ሥርዓቱ ላይ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ነው የሚገኙት። ጆ ባይደንም "አሜሪካዊያን እኔን ብላችሁ ወደ ዲሲ ድርሽ እንዳትሉ" ብለዋል። እሳቸው ጤናን የሚያስቀድሙ ጤነኛ መሪ ናቸው እያሉ አሞግሰዋቸዋል፣ አንዳንዶች። ሆኖም ሐሪስና ባይደን እንደተለመደው ከካፒቶል ሒል ፊት ለፊት ባለው ቦታ ነው ቃለ መሐላ የሚፈጽሙት። እንጂ አዳራሽ ተቆልፎባቸው አይደለም ሥርዓቱን የሚታደሙት። ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ተራርቀው መድረክ ላይ ይቀመጣሉ ተብሏል። በቦታው የሚገኙት ሰዎች በሙሉ ከሳምንት ጀምሮ በየሁለት ቀኑ የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ሁሉም የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማጥለቅ አለባቸው። ባይደንም ቃለ መሐላ ሲፈጽሙ ብቻ ጭምብላቸውን ያወልቃሉ። ከዚህ ቀደም ይህን ልዩ በዓለ ሲመት ለመታደም ሁለት መቶ ሺህ የግብዣ መጥሪያዎች ታድለው ያልቁ ነበር። ዘንድሮ ግን 1ሺህ የግብዣ ካርዶች ብቻ ናቸው የተዘጋጁት። ሥነ ሥርዓቱ ካለቀ በኋላ ጆ ባይደን ከሚስታቸው ጋር፣ ካመላ ሐሪስ ደግሞ ከባላቸው ጋር በወታደራዊ አጀብና በልዩ የማርሽ ሙዚቃ ታጅበው ወደ ነጩ ቤተ መንግሥት ይወሰዳሉ። ከካፒቶል ሒል ፊት ለፊት ለጆ ባይደን ሲመተ በዓል ዝግጅት ሲደረግ የግብዣ ካርዱ የት ይገኛል? ከዚህ በፊት በነበረው ሥርዓት ከፊት መቀመጫ ለማግኘት ወይም በቅርብ ቆሞ ለማየት የግብዣ ካርድ መያዝ የግድ ነበር። የተቀረው የናሽናል ሞል ቦታ ግን ለሕዝብ ክፍት ነው የሚሆነው። ስለዚህ አንድ ሰው ይህን ሥነ ሥርዓት በቅርብ ተገኝቶ ለመከታተል የግብዣ ካርዱን ከአካባቢው አስተዳዳሪዎች ማግኘት ይኖርበታል። ከዚህ የቃለ መሐላ ሥነ ሥርዓት በኋላ ለሚኖሩ የፈንጠዚያ መርሐ ግብሮች የግብዣ ካርዶች የሚገኙት ከአዘጋጆቹ ነው። የሕግ መምሪያውና የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት አባላት በርከት ያሉ የግብዣ ካርድ ይታደላቸዋል። እነሱ ለፈለጉት ሰው ካርዱን ያድላሉ። ሌዲ ጋጋ ትዘፍናለች? በቅርብ ዓመታት በዚህ በዓለ ሲመት እውቅ ሙዚቀኞች እንዲያቀነቅኑ ይጋበዛሉ። ዘንድሮም ይህ ነገር አልቀረም ተብሏል። የጆ ባይደንና የሐሪስ ደጋፊ እንደሆነች የሚነገርላት ሌዲ ጋጋ ዕለቱን በደማቅና ወጣ ባለ አለባበሷና በውብ ሙዚቃዎቿ ታደምቀዋለች ተብሎ ይጠበቃል። ጄኔፈር ሎፔዝም ታዜማለች ተብሎ መድረክ ተሰናድቶላታል። በባራክ ኦባማ ሲመተ በዓል ላይ ያቀነቀኑ ታዋቂ ድምጻዊያን መካከል ታላቅ ክብር የሚሰጣት አሪታ ፍራንክሊን እና ቢዮንሴ ነበሩ። ኦባማ እምባ እየተናነቃቸው ለአሪታ ፍራንክሊን ቆመው አጨብጭበዋል። በኦባማ ጊዜ ጭንቀቱ የትኛው ዘፋኝ ዕድሉን ያግኝ የሚል ነበር። ምክንያቱም ለእሳቸው ሁሉም መዝፈን ይፈልግ ነበርና። የዛሬ 4 ዓመት ደግሞ ዶናልድ ትራምፕ የበዓለ ሲመታቸውን መድረክ የሚያደምቅላቸው ዘፋኝ ለማግኘት ብዙ ለፍተዋል። በደላላ ሁሉ ማግባባት ይዘው ነበር። ከየት ይምጣ? ሰር ኤልተን ጆን እንዲዘፍን ትራምፕ ጠይቀውት "ይለፈኝ" ብሏቸው ነበር። ሴሊን ዲዮንም እንዲሁ ትራምፕ ጠይቀዋት "እምቢኝ" ብላ ነበር ብለዋል ውስጥ አዋቂዎች። የትራምፕን ከነጩ ቤተ መንግሥት መሰናበት እንደ እፎይታ የሚቆጥሩ ዘፋኞች ኮቪድ-19 አቆማቸው እንጂ የባይደንን በዓለ ሲመት በአያሌው ባደመቁላቸው ነበር። ለዚያውም በደስታ! ምናልባት የዛሬ 4 ዓመት ኮቪድ-19ኝም ባይደንም ታሪክ ይሆኑ ይሆናል። ወይም ደግሞ አይሆኑ ይሆናል። ማን ያውቃል? ቢዮንሴ በሁለቱም የኦባማ ሲመተ በዓል ላይ ቀርባ ነበር
news-47520890
https://www.bbc.com/amharic/news-47520890
በአዲስ አበባ ህዝባዊ ውይይት የታሰሩ ተለቀቁ
ትናንትና በአዲስ አበባ ባልደራስ አካባቢ ተደርጎ የነበረውን ሕዝባው ውይይት ተከትሎ ቢያንስ ሃያ ሰዎች ታስረው እንደነበር ነገር ግን አሁን መለቀቃቸውን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጄነራል እንደሻው ጣሰው ለቢቢ አረጋግጠዋል።
ኮሚሽነር ጄኔራሉ እንዳሉት አንድ ሺህ ሰዎች ይሳተፉበታል በሚል ፈቃድ ያገኘው ስብሰባ ላይ ስምንት ሺህ ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን፥ ስብሰባው ግን በሰላም ተጠናቅቋል። ይሁንና የስብሰባውን መጠናቀቅ ተከትሎ ወደየቤታቸው የሚያመሩ አንዳንድ ወጣቶች በተለይ ፒያሳ አካባቢ ወዳሉ የንግድ ተቋማት የመግባት ፍላጎት ስላሳዩ ፖሊስ ኅብረተሰቡን ከጉዳት ለመከላከል ያለበትን ኃላፊነት ለመወጣት እንዲሁም ወጣቶቹ ራሳቸውንም ከጥፋት ለመከላከል ሲል ከሃያ እስከ ሰላሳ የሚሆኑትን በቁጥጥሩ ስር አውሏል ብለዋል። • ስለ አደጋው እስካሁን የምናውቀው • ቻይና በቦይንግ 737 ማክስ 8 የሚደረጉ በረራዎችን አገደች አብዛኞቹ ተሳታፊዎች ጭፈራ እያሰሙ ወደየቤታቸው መግባታቸው ታውቋል። በህዝባዊ ውይይቱ ጋዜጠኛ የመብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ንግግረ ካደረጉ ሰዎች መካከል ነበር።
news-49765472
https://www.bbc.com/amharic/news-49765472
ሳራህ ቶማስ፡ ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ ያለማቋረጥ የዋኘችው የጡት ካንሰር ታማሚ
የጡት ካንሰር የሕክምና ክትትሏን ባለፈው ዓመት ያጠናቀቀችው ሳራህ ቶማስ፤ የእንግሊዝን የውሃ ሰርጥ ያለምንም እረፍት አራት ጊዜ በዋና ያቋረጠች የመጀመሪያዋ ሴት ሆናለች። 'ኢንግሊሽ ቻነል' የአትላንቲክ ውቅያኖስ አነስተኛ ክፍል ሲሆን፤ ደቡባዊ እንግሊዝን ከሰሜን ፈረንሳይ ጋር የሚለያይ የውሃ አካል ነው።
ሳራህ ቶማስ • የኦሎምፒክ ተወዳዳሪው በመስጠም ላይ የነበረን ሙሽራ ታደገ • የባርሳ ሴቶች ከወገብ በላይ ራቁት ለመሆን ድምጽ ሰጡ የ37 ዓመቷ ሳራህ ይህን እልህ አስጨራሽ የሆነ ውድድር ያደረገችው ባሳለፍነው እሁድ ሲሆን ለ54 ሰዓታትን ከዋኘች በኋላ ልታጠናቅቅ ችላለች። ሳራህ የጡት ካንሰር ሕክምናዋን ያጠናቀቀችው ባለፈው ዓመት ሲሆን፤ ይህንን ገድሏን "እንደ እኔ ከሞት ለተረፉት መታሰቢያ ይሁን" ብላች። ዋናው 128.7 ኪሎ ሜትር (በ80 ማይል) የሚያስጉዝ ቢሆንም ሳራህ ባጋጠማት ከፍተኛ ማዕበል ምክንያት 209.2 ኪሎ ሜትር (130 ማይል) ርቀት ለማዋኘት ተገዳለች። የአሜሪካ ኮሎራዶዋ ሳራህ፤ ዋናዋን ያጠናቀቀችው ባሳለፍነው ማክሰኞ ነበር። የማራቶን ዋናተኛዋ "በድል ማጠናቀቄን በፍፁም ማመን አልቻልኩም፤ በጣም ደስ ብሎኛል" ስትል ዋናውን አጠናቅቃ በዶቨር የባህር ዳርቻ ላይ እንዳረፈች ለቢቢሲ ተናግራለች። "በጣም በርካታ ሰዎች እኔን ለማግኘትና መልካም ለመመኘት በውሃው ዳርቻ ላይ ተገኝተው ነበር። እነርሱ በጣም ደስ ብሏቸዋል፤ እኔ ግን ባለማመን ደንግጬ ነበር" ብላለች ሳራህ። ሰውነቷ በድካም እንደዛለ የተናገረችዋ ሳራህ ለቀናት መተኛት እንደምትፈልግም ገልፃለች። የሳራህን ገድል አስመልክቶም ዋናተኛው ለዊስ ፐግህ በትዊተር ገፁ ላይ "የሰውን ልጅ የአቅም ልክ አሳይተናል ስንል፤ አንዳንዶች ያንን ክብረ ወሰን ይበጣጥሱታል" ሲል አሞካሽቷታል። እንኳን ደስ ያለሽ ሲልም መልካም ምኞቱን ገልጾላታል። የሳራህ እናት ቤኪ ባክስተር በበኩላቸው፤ "በሕይወት ጉዞዎቿ ሁሉ አብሬያት አለሁ፤ የአሁኑ ግን እጅግ አስፈሪው ነው" ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ልጃቸው የተፈጥሮ አድናቂ ብትሆንም በዚሀ ጉዞዋ በርካታ ተግዳሮቶችና የሆድ ህመም እንዳጋጠማት አልሸሸጉም። ባለፈው ዓመት የጡት ካንሰር ሕክምናዋን ያጠናቀቀችው ሳራህ፤ መዋኘትን እንደ አንድ ሕክምና አድርጋ ትጠቀምበት ነበር። የሳራህ ደጋፊ ቡድን አባል የሆነችው ኤሌን ሆውሌይም፤ "የጓደኛየ ስኬት እጅግ አስደናቂ፣ ያልታሰበ እና የተለየ ነው" ስትል ገልጻዋለች። የዋና ማራቶንን ድንበር ያለፈች ብላታለች። ማራቶን ለማዋኘት ምን አነሳሳት? የዋና ልምድ ያላት ሳራህ በውሃ ላይ የምታደርገውን ዝግጅት ያጠናቀቀችው በአውሮፓዊያኑ 2007 ነበር። የእንግሊዙን 'ቻነል'ን በዋና ለመጀመሪያ ጊዜ ያቋረጠችው በ2012 ሲሆን፤ በድጋሚ በ2016 በዋና አቋርጠዋለች። • የጡት ካንሰር የያዛት የጡት ካንሰር ሀኪም • "ዛሚ አልተሸጠም፤ በትብብር እየሠራን ነው" ጋዜጠኛ ሚሚ ስብሃቱ ለፊልም ሠሪው ጆን ዋሸር፤ "32 ኪሎ ሜትር (20 ማይል) ርቀት ስዋኝ፤ ከዚህ በላይ መዋኘት እንደምችል ይሰማኝ ነበር፤ በመሆኑም ምን ያህል ልጓዝ እንደምችል ማየት ፈለግኩ" ስትል የተነሳሳችበትን ምክንያት አስረድተዋለች። ከዚያም በ2017 ነሐሴ ወር ላይ በአሜሪካና በካናዳ ድንበር በሚገኘው ቻምፕሌን ሐይቅ 168.3 ኪሎ ሜትር (104.6 ማይል) ዋኘች። ከዚያ በኋላ ነበር የጡት ካንሰር ሕመም አጋጥሟት ሕክምና መከታተል ጀመረች። ሳራህ የጡት ካንሰር ሕክምናዋን ባለፈው ዓመት ነበር ያጠናቀቀችው። አሁን የእንግሊዙን 'ቻነል' በመዋኘት የሰበረችውን ክብረ ወሰን፤ ለሌሎች ከሞት ለተረፉት የእሷ ቢጤ ታማሚዎች መታሰቢያ ይሁንልኝ ብላለች።
news-53733422
https://www.bbc.com/amharic/news-53733422
ወላይታ ፡ በወላይታ ሰልፈኞች ላይ የተወሰደው የኃይል እርምጃ "ተመጣጣኝነት አጠያያቂ ነው" ኢሰማኮ
በወላይታ ዞን አንዳንድ ከተሞች በነበሩ ተቃውሞዎች የፀጥታ ኃይሎች እርምጃ "ተመጣጣኝነት አጠያያቂ" መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
ኮሚሽኑ በወላይታ ዞን የተለያዩ ከተሞች ነሐሴ 4/2012 ዓ.ም ሰኞ እለት ተቃውሞ መካሄዱን ጠቅሶ "የፀጥታ ኃይሎች ሰላማዊ ሰልፈኞችን በሚቆጣጠሩበት ወቅት የሞት አደጋን የሚያስከትል የኃይል እርምጃ ከመውሰድ ሊቆጠቡ ይገባል" ብሏል። እንዲህ ዓይነት እርምጃዎች ቀድሞውንም የነበሩ ውጥረቶችን እንደሚያባብሱ የገለፀው ኮሚሽኑ፣ በግጭቱ ወቅት የተከሰተው የስድስት ሰልፈኞች አሟሟትን እና የፀጥታ ኃይሎች የኃይል አጠቃቀምን አስመልክቶ "ፈጣን ምርመራ" እንደሚያስፈልግ ገልጿል። በወላይታ የተቃውሞ ሰልፉ የተቀሰቀሰው እሁድ እለት ከፍተኛ የዞኑ ባለስልጣናት፣ አክቲቪስቶች፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የአገር ሽማግሌዎች መታሰራቸውን ተከትሎ ነው። ግለሰቦቹና ባለስልጣናቱ የታሰሩት ዞኑን በክልልነት ለማደራጀት የተቋቋመው ሴክሬተርያት የህግ ኮሚቴ ባዘጋጀው የሕገመንግሥት ረቂቅ ላይ ለመወያየት ተሰብስበው ሳሉ ነው። እንደ ኮሚሽኑ መግለጫ ከሆነ እስካሁን ድረስ 178 ሰዎች በቁጥጥር ስር ሲውሉ ከእነዚህ መካከል 28 የዞኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት ናቸው። ግለሰቦቹ ታስረው የሚገኙት በወላይታ ሶዶ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ውስጥ መሆኑን መግለጫው አክሎ ገልጿል። በወላይታ ዞን በተቀሰቀሰው ግጭት የተከሰተው ምንድን ነው? ባለፈው እሁድ ከወላይታ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በጸጥታ ኃይሎች በተያዙ ሰዎች ሰበብ በተከሰተ አለመረጋጋት ቢያንስ የአስር ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተነገረ። ዞኑን በክልልነት ለማደራጀት ከተቋቋመው ሴክሬታሪያት ስብሰባ ተሳታፊ የነበሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የህግ ባለሙያዎችና የአገር ሽማግሌዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ነው ችግሩ የተከሰተው። በተለይ አለመረጋጋቱ ከፍተኛ ነበር በተባለባትና ከሶዶ ከተማ 18 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ቦዲቲ ከተማ የሟቾች ቁጥር ከሰባት በላይ እንደሆነና በሶዶም ሰዎች መገደላቸውን ከሆስፒታሎችና ከአካባቢው ነዋሪዎች አገኘሁት ያሉት መረጃን ጠቅሰው የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ የሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ማቴዎስ ባልቻ ለቢቢሲ ተናግረዋል። በሶዶ ሦስት ሰዎች እንደሞቱና በቦዲቲም ሌሎቹ እንደተገደሉ አቶ ማቴዎስ አስረድተዋል። ከሰበሰቧቸው መረጃዎች ተረዳሁት ያሉት አቶ ማቴዎስ ብዙዎቹ በእድሜ ታዳጊ እንደሆኑና "መንግሥት ያለ አግባብ ኃይል ተጠቅሟል" ሲሉም ወንጅለዋል። "የሚያሳዝነው እነዚህ ልጆች ጠንከር ያለ አርጩሜ ይበቃቸው ነበር። አስለቃሽ ጋዝም መርጨት ይቻል ነበር። አንዳንዶቹ እየሮጡ አሳዶ መተኮስ በጣም የሚያሳዝን ነው" ብለዋል። የክልሉ ምክትል ፖሊስ ኮሚሽነር የግለሰቦቹ ሕይወት የጠፋው መሳሪያ ለመንጠቅ ባደረጉት ትንቅንቅ ነው ማለታቸውን ጠቅሰው ይሄ ትክክል እንዳልሆነ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ስለግለሰቦቹ ሞት ቢቢሲ ባደረገው ማጣራት በሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል ውስጥ ከትናንት በስቲያ በጥይት ተመትቶ የመጣ አንድ ግለሰብ ሕይወቱ አልፏል። ግለሰቡ የ30 ዓመት እድሜ እንደሆነ የሚናገሩት ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያ ሦስት ግለሰቦችም በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኙ ተናግረዋል። የ22 ዓመት እድሜ ያለው አንደኛው ግለሰብ በጥይት አንገቱ ላይ ተመትቶ በፅኑ ህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በከፋ ደረጃ ላይ እንደሚገኝም እኚሁ የጤና ባለሙያ ለቢቢሲ አስረድተዋል። ሌላኛው የ25 ዓመት ጎልማሳ ሲሆን እግሩ ላይ በጥይት ተመትቶ ደም ስሩም በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል። በተጨማሪም ሌላኛው ህመምተኛ በጥይት ሳይሆን በዱላ ከፍተኛ ድብደባም ደርሶበታል ብለዋል። ከፅኑ ማቆያ ህሙማን ክፍል በተጨማሪም ሦስት ግለሰቦችም በጥይት ተመትተው የአጥንት ህክምና ክፍል ውስጥ ተኝተው እየታከሙ ነውም ብለዋል። ከዚህም በተጨማሪ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸው ህክምና አድርገው የተመለሱ ወደ አምስት ሰዎች መኖራቸውንም እኚሁ ባለሙያ ገልፀዋል። ምንም እንኳን ሆስፒታል ውስጥ መጥቶ ህይወቱ ያለፈ ባይኖርም በቦዲቲ አምስት ሰዎች መሞታቸውን መረጃ ማግኘታቸውን እንዲሁም በሶዶ ከተማም ውስጥ ሆስፒታል ሳይመጡ በጥይት የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውንም ተናግረዋል። በአሁኑ ሰዓት የንግድ እንቅስቃሴዎችም ሆነ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች መቆማቸውን ገልፀው ሶዶ ብትረጋጋም በቦዲቲ መጠነኛ ውጥረት እንዳለ አስረድተዋል። የሶዶ ከተማ ፀጥ ረጭ እንዳለችና ከመከላከያና የፀጥታ ኃይሎች ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ በስተቀር ምንም እንደሌለ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪ አስረድተዋል። ምንም እንኳን ከትናንትናው ጋር ሲነፃፀር አንፃራዊ ሰላም ቢኖርም ስጋቶች እንደነገሱ ይኸው ነዋሪ ይናገራሉ። እሳቸው ሰማሁ ባሉት መረጃ በቦዲት ሰባት ሰዎች መገደላቸውን በሶዶ ደግሞ የሶስት ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል። በዛሬው ዕለት በሶዶ እንዲሁም በቦዲት ከተሞች የቀብር ስነ ስርአቶች እየተካሄዱና ነዋሪው ለሃዘን ተቀምጠዋልም ብለዋል። ባለው የመንገድ መዘጋት የተነሳ ከአዲስ አበባ ወደ ቦዲቲ ለመሄድ ያልቻለው ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የቦዲቲ ከተማ ነዋሪም አንድ አክሊሉ የተባለ ጓደኛው በጥይት መገደሉን ተናግሯል። አክሊሉ በሃያዎቹ እድሜ ላይ የሚገኝ እንደሆነም ለቢቢሲ አስረድቷል። ከትናንት ጀምሮ ለደቡብ ክልል ፖሊስና ለሰላም ፀጥታ ቢሮ በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡን ደጋግመን በመደወል ቀጠሮ ቢሰጡንም ምላሻቸውን ማግኘት አልቻልንም። የደቡብ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ አለማየሁ ባውዲ በወላይታ ዞን የተከሰተውን አለመረጋጋት በተመለከተ በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች 10 መሆናቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ትናንት ገልጸው እነሱም "የክልል እንሁን ጥያቄ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እንዳይፈታ ለማድረግ ሲጥሩ የነበሩ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች" መሆናቸውን ተናግረዋል። የጸጥታ ኃይል እነዚህን ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ተከትሎ "መንገድ የመዝጋትና ግርግር የመፍጠር አዝማሚያ መታየቱን" ገልጸው። ከዚህ ጋር ተያይዞም የአንድ ሰው ህይወት ማለፉንና ሌሎች ደግሞ መቁሰላቸውንም ኃላፊው አቶ አለማየሁ ትናንት ተናግረው ነበር። ለግጭቱ መነሻ ምክንያት የሆነው በዞኑ የተቋቋመው የክልል ምስረታ ሴክሬታሪያት ካውንስል አማካሪ ቦርድ አባላት፣ በሕግ ኮሚቴው የተዘጋጀውን የሕገ መንግሥት ረቂቅ ላይ እንዲወያዩ ስብሰባ ላይ የተጠሩ ሰዎች መታሰራቸውን ተከትሎ ነው። ከታሰሩትም ውስጥ የዞኑ አስተዳዳሪ ዳጋቶ ኩምቤ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ አቶ ጥበቡ ዮሃንስ፣ የዞኑ ከፍተኛ አመራር ወ/ሮ እቴነሽ ኤልያስ፣ የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ ሥራ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎበዜ አበራ፣ የወላይታ ዲሞክራሲያዊ ግንባር ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት ኤልያስ ይገኙበታል። ከዚህም በተጨማሪ ከአገር ሽማግሌዎች አቶ ሰይፉ ለታና አቶ ዳንኤል ደሳለኝ፤ የንግድ ምክር ቤት ዋናና ምክትሉ አቶ በተላ ቦረናና አቶ አክሊሉ ደስታ፤ የመብት ተሟጋቾችና ከሕግ ባለሙያዎች መካከል አቶ አሸናፊ ከበደ፣ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ፣ አቶ ተከተል ለቤና በአጠቃላይ 26 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላችውን አቶ ማቴዎስ ተናግረዋል። እሳቸውም አባል የሆኑበት የዚህ ሴክሬታሪያት አባላት መታሰር እንዳሳዘናቸው ጠቅሰው ግለሰቦቹን ከመፍታት በተጨማሪ፣ የሞቱ ግለሰቦችንም አሟሟት ነፃና ገልልተኛ የሆነ አካል ሊያጣራ ይገባል ብለዋል። የወላይታ ዞን ምክር ቤት ሰኔ 15/2012 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የወላይታ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት እንዲቋቋም ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል። የክልሉን መንግሥት ለማደራጀት የሚያስችል ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤትም እንዲቋቋም እና የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እንዲከናወኑም በዚሁ ወቅት ወስኖ ነበር።
news-50001896
https://www.bbc.com/amharic/news-50001896
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ለዚህ ሽልማት የበቁት ወደ ስልጣን ከመጡበት ጊዜ ጀምሮ በአገራቸው ውስጥ ለውጥ ለማምጣት መውሰድ በጀመሯቸው እርምጃዎችና በተለይ ከኤርትራ ጋር ሠላም ለማውረድ ባደረጉት ጥረት እንደሆነ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኖቤል ሰላም ሽልማት 100ኛው አሸናፊ ናቸው። የአየር ለውጥ መብት ተሟጋች የሆነችው ስዊድናዊቷ የ16 ዓመት ታዳጊ ግሬታ ተንበርግ ከፍተኛ ግምት ከተሰጣቸው መካከል ነበረች። የኖቤል የሰላም ሽልማትን የሚያሸንፉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች 900 ሺ ዶላር የሚሰጣቸው ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በመጪው ታህሳስ ወር በኦስሎ ሽልማታቸውን ይወስዳሉ። በአጠቃላይ 301 እጩዎች ለዚህ ታላቅ ክብር ታጭተው የነበረ ሲሆን ከነዚህ መካከል 223 ግለሰቦችና 78 ድርጅቶች ይገኙበታል። የኖቤል ሽልማት በየዓመቱ በፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ሕክምና፣ ሥነጽሑፍና ሰላም ዘርፎች በየዓመቱ ይሰጣል። ሽልማቱ የሚሰጠው ባለፉት 12 ወራት "ለሰው ልጅ የበለጠ አበርክቶ" የሚያደርጉ ነገሮችን ላከናወኑ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ነው። ኖቤል የሚለው ስያሜ የተወሰደው ከሲውዲናዊ ነጋዴ እና የድማሚት ፈጣሪ አልፍሬድ ኖቤል ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሽልማቱ መሰጠት የጀመረው እኤአ በ1901 ግለሰቡ በለገሰው ገንዘብ ነው ። ከዚህ በፊት የኖቤል ሰላም ሽልማት እነማን ታጩ? የዘንድሮው የኖቤል የሠላም ሽልማት እጩ የሆኑት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከአጼ ኃይለሥላሴ ቀጥሎ ለሽልማቱ በመታጨት ሁለተኛው የኢትዮጵያ መሪ ለመሆን ችለዋል። በስፋት እንደሚነገረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዐብይ ዘንድሮ ለሽልማቱ በመታጨት ከቀረቡት ተፎካካሪዎች መካከል ለአሸናፊነት ተስፋ አላቸው ተብሎ ከሚጠበቁት ጥቂት እጩዎች አንዱ እንደሆኑም ተነግሯል። ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ለኖቤል ሽልማት ታጭተው የነበሩት ከዛሬ 80 ዓመት በፊት እንደ አውሮፓዊያኑ በ1938 እንደነበር የሽልማት ድርጅቱ መረጃ ያመለክታል። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለኖቤል ሽልማት በመታጨት ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ መሪ ናቸው። • ዐብይ አሕመድ ለኖቤል ሽልማት ታጭተዋል? • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ግምቶች አሉ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በኖቤል የሠላም ሽልማት ታሪክ ውስጥ በዕጩነት ከቀረቡ ስድስት ንጉሣዊያን መካከል አንዱ ሲሆኑ፤ ከእርሳቸው ቀደም ብለው የሩሲያው ንጉሥ ዳግማዊ ኒኮላስ፣ የስዊዲኑ ልዑል ካርልና የቤልጂየሙ ንጉሥ ቀዳማዊ አልበርት ታጭተው የነበሩ ሲሆን ከእሳቸው በኋላ ደግሞ የግሪኩ ንጉሥ ቀዳማዊ ፖልና የኔዘርላንድስ ልዕልት ዊልሄልሚና ታጭተው ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ የሆኑበት የዚህ ውድድር አሸናፊ ዛሬ አርብ ኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ውስጥ በሚካሄድ ሥነ ሥርዓት ላይ ይፋ ይደረጋል። የሌሎቹ የኖቤል ሽልማቶች ግን የሚሰጡት ስዊዲን ስቶክሆልም ውስጥ ነው። በዚህ ዓመት በተለያዩ የኖቤል ሽልማት በእያንዳንዱ ዘርፍ አሸናፊ የሚሆኑ ግለሰቦች ዘጠኝ ሚሊዮን የስዊዲን ክሮነር ወይም ከ900 ሺህ የአሜሪካ ዶላር በላይ የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል። አንዳንድ እውነታዎች ስለኖቤል የሠላም ሽልማት በተለያዩ መስኮች ፍር ቀዳጅ ተግባራትን ያከናወኑ ግለሰቦችንን ተቋማት በየዓመቱ የሚሸለሙበት የኖቤል ሽልማት በዓለማችን ከሚሰጡ ዕውቅናዎች መካከል በቀዳሚነት ይጠቀሳል። አልፍሬድ ኖቤል ኅዳር 18/1888 ዓ.ም በፈረመው ኑዛዜ ያለውን አብዛኛውን ሃብቱን የኖቤል ሽልማት ተብለው ለሚሰጡ ሽልማቶች እንዲውል ተናዟል። በኑዛዜው ላይ እንደተገለጸው ከዚህም መካከል አንዱ የሠላም ሽልማት ሲሆን፤ ሽልማቱም "በመንግሥታት መካከል ወንድማማችነት እንዲሰፍን አብዝተው ወይም የተሻለ ሥራን ላከናወኑ፣ የጦር ሠራዊቶች ቅነሳና ለሠላም መስፋፋት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ይሰጥ" ይላል። እስካሁን የተሰጡ የኖቤል የሰላም ሽልማቶች ከአውሮፓዊያኑ 1901 ጀምሮ 99 የኖቤል የሠላም ሽልማቶች ተበርክተዋል። ሽልማቱ ከተጀመረ በኋላ ሁለቱ የዓለም ጦርነቶች በተካሄዱባቸው ዓመታትና በሌሎችም ምክንያቶች ለ19 ጊዜያት ሳይሰጥ ቀርቷል። የኖቤል የሽልማት ድርጅት እንደሚለው በመጀመሪያውና በሁለተኛው የዓለም ጦርነቶች ወቅት ጥቂት የሠላም ሽልማቶች የተሰጡ ሲሆን በሌላ ጊዜ ደግሞ በእጩነት የቀረቡት ተቋማትም ሆነ ግለሰቦች ለሽልማቱ የሚጠበቀውን ያህል አስተዋጽኦቸው የጎላ ነው ተብሎ ካልታሰበ ነው። በዚህም የሽልማቱ ገንዘብ በድርጅቱ እጅ ስር እንዲቆይ ይደረጋል። ሽልማቱ በግልና በጋራ ይሰጣል 67 የሚሆኑ የኖቤል የሠላም ሽልማቶች በተናጠል ላሸነፉ ግለሰቦች የተሰጡ ሲሆኑ፤ 30ዎቹ ደግሞ ሁለት ግለሰቦች በጋራ የተሸለሟቸው ናቸው። 2 የሠላም ሽልማቶችን ሦስት ሦስት ሰዎች በቡድን አሸንፈዋል። • "አካል ጉዳተኛ መሆኔ ጥሩ ደረጃ እንድደርስ አድርጎኛል" • የዘንድሮ የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊዎች ለሦስት ሰዎች የተሰጡት ሽልማቶች በአውሮፓዊያኑ 1994 እና በ2011 ሲሆን የመጀመሪያውን የፍልስጥኤሙ መሪ ያሲር አራፋት እንዲሁም እስራኤላዊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሺሞን ፔሬዝና ይትዛክ ራቢን በጋራ ወስደዋል። ሁለተኛውን ደግሞ አፍሪካዊቷ የላይቤሪያ ፕሬዝዳንት ኤለን ሰርሊፍ ጆንሰን፣ ላይቤሪያዊቷ የመብቶች ተሟጋች ሌይማህ ቦዊና የመናዊቷ ጋዜጠኛና የመብት ተከራካሪ ታዋኮል ካርማን ሽልማቱን ተጋርተውታል። ሽልማቱ ከአንድ በላይ ለሆነ አሸናፊ የሚሰጥ ከሆነ የገንዘቡም መጠን ለአሸናፊዎቹ ይከፋፈላል። ሸላሚው ድርጅት ለአንድ ሽልማት ከሦስት በላይ አሸናፊዎች እንዳይኖሩ ይገድባል። አጼ ኃይለ ሥላሴ እና ንግሥት ኤልሳቤት ሁለተኛ ለንደን ውስጥ የኖቤል የሠላም ሽልማት ለምን ያህል ጊዜ ተሰጠ? የኖቤል የሠላም ሽልማት ለ133 ግለሰቦችና ተቋማት ተሰጥቷል። ከእነዚህ ውስጥም 106 ግለሰቦች ሲሆኑ 27ቱ ድርጅቶች ናቸው። ከተቋማቱ ውስጥ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ ሦስት ጊዜ ሽልማቱን የወሰደ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ደግሞ የኖቤል ሠላም ሽልማትን ሁለት ጊዜ ለማግኘት ችሏል። በእድሜ ትንሿ የኖቤል ሠላም ሽልማት አሸናፊ ሴቶች የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ የምትጥረው ፓኪስታናዊቷ ማላላ ዩሳፍዛይ እንደ አውሮፓዊያኑ 2014 የተሰጠውን የኖቤል የሠላም ሽልማትን በ17 ዓመቷ በማግኘት በዕድሜ ትንሿ የሽልማቱ አሸናፊ ሆናለች። አዛውንቱ የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ በትውልድ ፖላንዳዊ በዜግነት እንግሊዛዊ የሆኑት ጆሴፍ ሮትብላት የኑክሌር ጦር መሳሪያ በዓለም ፖለቲካ ውስጥ ያለውን ተጽእኖ ለመቀነስ ባበረከቱት አስተዋጽኦ እንደ አውሮፓዊያኑ በ1995 የኖቤል የሠላም ሽልማትን ሲያገኙ እድሜያቸው 87 ነበረ። በዚህም በእድሜ የገፉ የሽልማቱ አሸናፊ ናቸው። ሴት የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ እስካሁን በግለሰብ ደረጃ ከተሰጡት 106 የኖቤል የሰላም ሽልማቶች ውስጥ ሴቶች ያገኙት 17ቱን ብቻ ነው። ለመጀመሪያ ጊዜ ሽልማቱ የተሰጠው የኖቤል ሽልማት በተጀመረ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ነበር። ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ 1905 የመጀመሪያዋ ሴት የሽልማቱ አሸናፊ የሆነችው በርታ ቮን ሰትነር ናት። ኦስትሪያዊቷ ሰትነር የረጅም ልቦለድ ጸሐፊና ስለ ሠላም ተከራካሪ ነበረች። ከአንድ ጊዜ በላይ የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ በዓለም ዙሪያ የሚያከናውናቸው ሥራዎች ከየትኛው ተቋም በላይ በኖቤል ሠላም ሽልማት ዘርፍ እውቅናን አግኝቷል። ቀይ መስቀል ሦስት ጊዜ ሽልማቱን በመውሰድ ቀዳሚ ሲሆን መስራቹ ሄንሪ ዱና ደግሞ የመጀመሪያውን የኖቤል የሠላም ሽልማትን በመውሰድ ይታወቃል። የሠላም ሽልማቱን አልቀበልም ያለው ግለሰብ ቬትናማዊው ፖለቲከኛ ሊ ዱች ቶ በአውሮፓዊያኑ 1973 ከአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር በጋራ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ቢያሸንፉም ሽልማቱን አልቀበልም በማለት የመጀመሪያው ለመሆን በቅተዋል። ሁለቱ ግለሰቦች ለሽልማቱ የተመረጡት የቬትናም የሠላም ስምምነት እንዲደረስ ጉልህ ሚና በመጫወታቸው ነው። ሊ ዱች ቶ የኖቤል የሠላም ሽልማቱን አልቀበልም ያሉት በወቅቱ ቬትናም ውስጥ የነበረውን ሁኔታ እንደምክንያት ጠቅሰው ነው። በእስር ላይ እያሉ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ያሸነፉ ሦስት ሰዎች እስር ቤት እያሉ የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ይፋ ተደርጓል። እነርሱም ጀርመናዊው የሠላም ተሟጋችና ጋዜጠኛ ካርል ቮን ኦሲትዝኪ፣ የበርማ ፖለቲከኛዋ አንግ ሳን ሱ ኪ እና ቻይናዊው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ሊዩ ዢኦቦ ናቸው። ከሞቱ በኋላ የኖቤል የሠላም ሽልማትን ያገኙ አንድ ግለሰብ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላ የኖቤል የሠላም ሽልማትን አግኝተዋል። ይህም እንደ አውሮፓዊያኑ 1961 የተሰጠ ሲሆን ተሸላሚውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሊቀመንበር የነበሩት ዳግ ሐመርሾልድ ናቸው። ከ1974 በኋላ የሽልማቱ ድርጅት ተሸላሚው ህይወቱ ያለፈው አሸናፊ መሆኑ ይፋ ከተደረገ በኋላ ካልሆነ በስተቀር በሞት ለተለዩ ሰዎች ሽልማቱ እንዳይበረከት ወስኗል።
news-54475040
https://www.bbc.com/amharic/news-54475040
አፍሪካ ቀንድ፡ አሜሪካ ሱዳን ላይ የጣለችውን ማዕቀብ የማታነሳው ለምንድን ነው?
ሱዳን ምጣኔ ሀብታዊ 'ነፍስ ውጪ-ነፍስ ግቢ' ላይ ናት። የዋጋ ግሽበት ኢኮኖሚዋን አገርጅፎታል። ገንዘቧ የዚምባብዌ ዕጣ እንዳይገጥመው ተሰግቷል።
አባይ ካርቱም ከተማን እስከ ወገቧ ነክሯታል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቤት እንኳን አልተረፈም። ደግ ነው የሚባለው የሱዳን ሕዝብ ዕለታዊ ዳቦ ቅንጦት ሆኖበታል። ይሄኔ ነው አሜሪካና እስራኤል ፈገግ ያሉት። አንድ ቁልፍ ነገር ለማሳካት ትክክለኛው ጊዜ እንደመጣ ገብቷቸዋል። በጣላቶቿ የተከበበችው እስራኤል ከአረብ አገራት የምትፈልገው ብዙ ነገር አይደለም። እውቅና ማግኘት ብቻ። ሌላው ትርፍ ነው። የአየር ክልል መከፈት፣ ንግድና ኢንቨስትመንት ይህን ተከትለው የሚመጡ ናቸው። ከዕውቅናው በኋላ አረቦቹ የቴክኖሎጂና የጦር መሣሪያ ደንበኞቿ ይሆናሉ። የትራምፕ አስተዳደር ከአረቦቹ ጋር በምንም ነገር ሊደራደር ይችላል። በእስራኤል የመጣ ግን በዐይኑ መጣ ማለት ነው ይባላል። ሱዳን ፈተና የገጠማትም ለዚሁ ነው። ዕድልም ገጥሟታል። ማይክ ፖምፔዮ በቅርቡ ወደ ካርቱም ብቅ ብለው ነበር። "እኔ ምለው፤ ብንተጋገዝ አይሻልም?" አሉ። "እንዴት አድርገን?" አለች ሱዳን። እዚህ ጋ ነው ፍጥጫው የተጀመረው። ከወራት በፊት ማይክ ፖምፔዬ ወደ ካርቱም ብቅ ብለው ነበር ማዕቀቡ ያን ያህል ከባድ ነው? ሱዳን ላይ የተጣለባት የማዕቀብ አለት የዋዛ አይደለም። ሽብርን በአገር ደረጃ ከሚደግፉ አገራት ተርታ ነው ጥቁር መዝገብ ላይ ወስዳ የጻፈቻት፤ አሜሪካ ሱዳንን። ይህ ማዕቀብ ለሱዳን ቢነሳላት የዐይን ሞራዋ ተገፈፈ ማለት ነው። ዶላርን ማየት ቻለች ማለት ነው። ለሕዝቧ ዳቦ አደለች ማለት ነው። ሱዳን እዚህ ቅርቃር ውስጥ ከገባች 30 ዓመት ሊሆናት ነው። አምባገነኑ አልበሽር ናቸው ከዚህ ማጥ ውስጥ የዶሏት። ነገሩ ውስብስብ ይመስላል። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1989 አልበሽር መፈንቅለ መንግሥት አደረጉ። ካርቱምን የአሸባሪዎች መናኽሪያ ለማድረግ ወራት እንኳን አልወሰደባቸውም። ጂሐዲስቶች ነጻ አገር አገኙ። በአሜካና በምዕራቡ ላይ ለመዝመት እንቅስቃሴያቸውን ከዚያ ማድረግ እንደጀመሩ ይነገራል። አልቃኢዳና ሌሎች የሽብር ቡድኖች ሱዳንን የጦር ቀጠናቸው አደረጓት። በአሜሪካ፣ በሳዑዲ አረቢያ፣ በግብጽ፣ በኢትዮጵያ፣ በዩጋንዳና በኬንያና በታንዛኒያ እንዲሁም በየመን ለተፈጸሙ ጥቃቶች ግንኙነት ሲካሄድ የነበረው ከሱዳን እንደነበር የደኅንነት መረጃዎች አመላክተዋል። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1993 በኒውዮርክ መንትያ የንግድ ማዕከላት ሕንጻዎች የተፈጸመው የመጀመሪያው የቦንብ ጥቃት ነበር። ያን ጊዜ አሜሪካ ሱዳንን በደማቅ ብዕር በጥቁሩ የአሸባሪ አገራት ዝርዝር መዝገብ ላይ አሰፈረቻት። እነሆ ከ30 ዓመታት በኋላም የዚያ ጥቁር የቀይ ቀለም አልደረቀም። ጥቁር መዝገቡም እንዳለ ነው። ሱዳን አሁን ሕልሟ ከዚህ ክፉ መዝገብ ስሟን መፋቅ ብቻ ነው። ሱዳንና ሲአይኤ የኒውዮርኩን ጥቃት ተከትሎ አሜሪካ ከጀርባ የምትዘውራቸው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሱዳንን ፊት ነሷት። አሜሪካ ስታዝን ቀድመው የሚያነቡ አንዳንድ የሱዳን አረብ ጎረቤት አገራት ከሱዳን ጋር ተኳረፉ። ጎረቤቶቿ ከኩርፍያም አልፈው የሱዳን መንግሥትን የሚገዳደሩ ሽምቅ ተዋጊዎችን ማስጠለል ጀመሩ። ሱዳን ጫናው ሲበረታባት እ.አ.አ በ1996 ከኒውዮርኩ የመጀመሪያ የቦንብ ጥቃት ሦስት ዓመት በኋላ፤ ኦሳማ ቢን ላደንና ወዳጆቹን "ከይቅርታ ጋር ከግዛቴ ውጡልኝ" ብላ አሰናበተቻቸው። ከዚህ በኋላ ትልቁ ክስተት 9/11 ተብሎ የሚታወቀው ከሃያ ዓመታት በፊት የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ነው። በዚህ የዓለምን ፖለቲካ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በለወጠው ጥቃት አሜሪካ ሱዳንን ተጫነች። ሱዳንም ነገሩ ሳያስደነግጣት አልቀረም። ጥቁር እንግዳዋ የነበረው ኦሳማ ቢን ላደን ይህን ያህል ጉዳት ያደርሳል ብለው አላሰቡ ይሆናል። ሱዳኖች ለሲአይኤ ፍጹም ተባባሪ ሆነው ቆዩ። በአልበሽር ዘመን የሱዳን የደኅንነት መሥሪያ ቤት ከሲአይኤ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ሠርቷል። ቢን ላደን ግን ያን ጊዜ ቶራ ቦራ መሽጎ ነበር። ሱዳን ከዚያ ጥቃት ማግስት ጀምሮ ለአሜሪካ ያሳየችው ተባባሪነትና መሽቆጥቆጥ ከሽብር አገራት ተርታ ሊያወጣት ይገባ ነበር። ያ ግን አልሆነም። አንዱ ምክንያት የአሜሪካ የላይኛው ምክር ቤት አባላት (ሴናተሮች) ለሱዳን በጎ አመለካከት ማሳደር ስላልቻሉ ነበር። ሴናተሮቹ የአልበሽር አስተዳደር በዳርፉር የሰው ልጆች ላይ የፈጸመውን ግፍ ቸል ብለው ማለፍ አልፈለጉም። ስለዚህ ሱዳን በዚህ ጥቁር መዝገብ ስሟ እንዲቆይ ተወሰነባት። የአልበሽበር መንግሥት ማዕቀቡ እንደማይነሳለት ሲረዳ በድብቅ ከኢራን እና ከሐማስ ጋር መተባበር ጀመረ። ለምሳሌ የእስራኤል አውሮፕላኖች መዳረሻቸውን ወደ ሐማስ ያደረጉ የመሣሪያ ክምችት የጫኑ ከባድ ተሸከርካሪዎችን በሱዳን የቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ አግኝተው ከጥቅም ውጭ አድርገዋል፤ ከአንዴም ሁለት ሦስቴ። አልበሽር ከሳዑዲና ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ በደረሰባት ከባድ ጫና ከኢራን ጋር መሥርታው የነበረውን ግንኙነት በ2016 ቆርጣዋለች። ይህ ውሳኔዋ ግን ማዕቀቡን እንዲላላላት አላደረገም። ምናልባት ከሳዑዲና ከኢምሬትስ የተወሰነ የኪስ ገንዘብ አግኝታበት ይሆናል ብለው የሚገምቱ አሉ። እንዲህ እንዲያ እያለ ነው ባለፈው ዓመት በሱዳን ድንገቴ የሕዝብ አብዮት የተቀሰቀሰው። በአብዮቱ የገዛ ጄኔራሎቻቸው በአልበሽር ላይ ፊታቸውን አዞሩና ሱዳን ሌላ መልክ ያዘች። ይወድቃሉ ተብለው ያልታሰቡት አልበሽር ወደቁ። ለሦስት ዐሥርታት ከተጫኑባት አምባገነን ገዢም ተገላገለች። ከዚህ በኋላ ነገሮች አልጋ በአልጋ ይሆናሉ ተብሎ ነበር የታሰበው። ዋሺንግተን ግን እጅግ የማትወዳቸው መሪ ዞር ብለውላትም እምብዛምም ለመተባበር አልፈቀደችም። የነገሮች ሁሉ ቁልፍ ያለው በአሜሪካ እጅ ነው። አሜሪካ ማዕቀቡን ስታነሳ ሱዳን ንግድ ይደራላታል። ግሽበት እየገዘገዘው የሚገኘው ኢኮኖሚዋም ያንሰራራል። አሜሪካ ግን ይህ እንዲሆን ለጊዜው የፈቀደች አትመስልም። ለምን? አሜሪካ ለምን እምቢ አለች? ሱዳን ችግር ላይ ናት ሲባል ቀልድ ይመስላል። በጣም ከባድ ችግር ላይ ነው ያለችው። ቶሎ ማዕቀቡ ካልተነሳላት ያ ሁሉ የሕዝብ አብዮት ተስፋ አፈር ይበላል። የዲሞክራሲ ሽግግሩም እክል ይገጥመዋል። እርግጥ ነው አሜሪካ ይህ እንዲሆን አትፈልግም። ለአሜሪካ መልካም የሚሆነው በሱዳን የምዕራቡን የዲሞክራሲ እሴቶች የሚያከብር መንግሥት እንዲፈጠር ነው። ሱዳን ሽግግሩ ካልተሳካላት በድጋሚ የአሸባሪዎች መናኸሪያ እንዳትሆን ስጋት አለ። ሱዳን የዓለም የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ 72 ቢሊዮን ዶላር እዳ አለባት። ይህ ካልተቃለለ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ብሎ ነገር አይኖርም። የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ከሌለ ደግሞ ንግድ አይነቃቃም። ሥራ ፈጣሪ አይኖርም። ሕዝብ በልቶ ማደር አይችልም። ሱዳናዊያን በጣም ተቸግረዋል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሱዳን 10 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ ረሐብ እያንዣበበበት ነው የሚል አስደንጋጭ ሪፖርት አውጥቷል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ የሆነው ደግሞ ኮቪድ-19 ነው። ሌላ ጆሮ ደግፍ ደግሞ ጎርፉ ነው። የሱዳን ችግር ከዚህ በኋላ በዳቦ እደላ የሚፈታ አይደለም። በቢሊዮን ዶላሮች ብድር ማግኘት አለባት። ቢሊዮን ዶላር እዳ ሊሰረዝላት ይገባል። ኢንቨስተሮች በስፋት ወደ ሱዳን ሊገቡ ይገባል። ከቅርብ ወራት ወዲህ ሱዳንን ከአሸባሪ አገራት ተርታ ካስቀመጣት ጥቁር መዝገብ ለመፋቅ አዝጋሚ ሂደት ተጀምሮ ነበር። በአሜሪካ ሴኔት ውስጥ እክል ገጠመው። ለዚህ የመጀመሪያው እርምጃ የሆነው አልቃኢዳ በምሥራቅ አፍሪካ አገራት በተለይም በየመን ላደረሰው ጉዳት ለሟችና ተጎጂ ቤተሰቦች ሞቅ ያለ ካሳ መክፈል ነበር። ሱዳን ይህን ለማድረግ ዓይኗን አላሸችም። ገንዘብ ባይኖራትም ከዚያም ከዚህም ብላ የካሳ ብር አዘጋጀች፤ 335 ሚሊዮን ዶላር አሁኑኑ እሰጣለሁ አለች። ነገር ግን ባለፈው ወር መስከረም የአሜሪካ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሴናተር ቸክ ሹመር እና ቦብ ሜናንዴዝ ሂደቱን አስቁመውታል። ምክንያታቸው ደግሞ የመስከረም 11ዱ ጥቃት ሰለባዎችም በዚህ ካሳ ውስጥ መግባት አለባቸው የሚል ሐሳብ በመጠንሰሱ ነው። ሱዳን ይህ አዝጋሚ ሂደት እያቆሰላት ይገኛል። ሱዳን ጊዜ የላትም። ጥምር መንግሥቱ ሊፈርስ፣ ሕዝቡም አደባባይ ተመልሶ ሊወጣ ይችላል። ነገሮች በፍጥነት መሻሻል አለባቸው። አሜሪካ ይህንን የሱዳንን መጨነቅና መጠበብ ለራሷ ፍላጎት ማዋል ትፈልጋለች። ነሐሴ መጨረሻ ሱዳንን የጎበኙት ማይክ ፖምፔዎ አንድ ሐሳብ ይዘው ነበር የሄዱት፤ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላ ሐምዶክ። "ከዚህ ሁሉ ጣጣ ብትወጡ አይሻልም?" "መንገዱን ያመላክቱን ክቡር ሚኒስትር" "እናንተ እስራኤልን እውቅና ስጧት፣ ትራምፕ ኮንግረሱ ያስቆመውን የማዕቀብ መነሳት ሂደት በፍጹማዊ ሥልጣኑ ይቀልብሰው።" የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ ባለፈው ወር ለእስራኤል እውቅና መስጠቷን ተከትሎ ሱዳን ተመሳሳይ እርምጃ ከወሰደች 4ኛዋ የአረብ ሊግ አባል አገር ትሆናለች ማለት ነው። ፖምፒዮ ይህ እንዲሆን የሚፈልጉት ትራምፕ ለምርጫ ከመቅረባቸው በፊት ነው። ጄኔራሎቹ ምን አሉ? ከእስራኤል ጋር ዓይንና ናጫ ሆነው መቆየት የሚፈልጉት ኢስላሚስቶች አሁን ከአልበሽር ጋር ወይ ዘብጥያ ወርደዋል ወይ ከፖለቲካው ገሸሽ ብለዋል። አሁን በሱዳን ያለው የአደራ አስተዳደር ነው። የወታደሩና የሲቪሉ ጥምረት ይህን ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን ሥልጣኑ አለው ወይ? ጠቅላይ ሚኒስትር ሐመዶክ ይህን ውሳኔ ቢወስኑ ብዙ ቀውስ ውስጥ ይገባሉ። የጊዜያዊ የሽግግር አስተዳደሩም የመፍረስ አደጋ ይገጥመዋል። ለፖምፒዮም በግልጽ የነገሯቸው ይህንኑ ነው። ይህንን ውሳኔ እልባት መስጠት የሚችለው ሕዝብ የሚመርጠው ቀጣዩ የሱዳን መንግሥት ብቻ ነው። እርግጥ ነው አሁን የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክና ሲቪል አስተዳደሩ ቢሮ ቢውልም ዋናው ሥልጣን ያለው አሁንም በወታደሮቹ እጅ ነው። ሳዑዲ፣ ግብጽና ኢምሬቶች የሚደግፏቸው የሽግግር ካውንስሉ ሊቀመንበር ሌተናል ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን እና ምክትላቸው ሌተናል ጄኔራል መሐመድ ሐምዳን ዳጎሎ ወይም በቅጽል ስማቸው ሐሜቲ ወታደሩን ብቻ ሳይሆን በሱዳን ካዝና የሚያዙ ቁልፍ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ጄኔራሎች ናቸው አሁን ከእስራኤል ጋር መነጋገር የጀመሩት። ጄኔራል ቡርሃን የእስራኤልን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ናታንያሁን በየካቲት አግኝተዋቸው ነበር። ናታንያሁን ለማግኘት ሲሄዱ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዱክ እንኳ አላሳወቋቸውም ነበር። ጄኔራሉ ከናታኒያሁ ጋር በድጋሚ ለመገናኘትም ቀጠሮ ይዘዋል። ጄኔራል ቡርሃን ጄኔራል ቡርሃንና ለጄኔራል ሐሜቲ ለእስራኤል እውቅና መስጠትና ከማዕቀቡ መገላገል ምርጫቸው ነው። ሁለቱ ጄኔራሎች ይህ እንዲሆን የሚፈልጉበት ሌላ ቁልፍ ምክንያት አላቸው። ባለፈው ዓመት ሚያዝያ የሕዝብ አመጽ አልበሽርን በትረ መንግሥት ሲነቀንቅ ሁለቱ ጄኔራሎች ናቸው አገሪቱን የተቆጣጠሩት። ከሁለት ወራት በኋላ ወታደሮቻቸው ሰልፈኞችን ገድለዋል። ይህንን ግድያ የፈጸሙ እንዲጠየቁ ሕዝብ ከፍተኛ ፍላጎት ነበረው። ከሲቪል አስተዳደር ጋር ሥልጣን ለመጋራት እምቢታን ይመርጣሉ ተብሎ ተሰግቶ ነበር። አሜሪካ፣ ታላቋ ብሪታኒያ፣ ሳዑዲና ኤምሬትስ ጫና ፈጥረው ነገሩ እውን አደረጉት እንጂ ሱዳን ከአንድ አምባገነን ወደ ሌላ ልትሸጋገር ጫፍ ደርሳ ነበር። አሁን ጄኔራሎቹና የሲቪል አስተዳደሩ ሥልጣን ይጋራል። ጄኔራሎቹ በአልበሽር ጊዜ ለተፈጸሙ የጦር ወንጀሎች ጥያቄ ውስጥ መግባት አይፈልጉም። ይህ እንዲሆንላቸው ግን ቶሎ ለእስራኤል እውቅና መስጠት ይኖርባቸዋል። በሌላ ቋንቋ አሁን ወታደሩ የሲቪል አስተዳደሩን እየታገሰ ያለው በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ እውቅና እንዳይነፈገው ስለሰጋ ብቻ ነው። እንጂ ሙሉ ሥልጣኑን ቢቆናጠጥ ይመርጣል። ሕዝቡ ወታደሮቹ ያደረሱበትን በደል ግን አልረሳላቸውም። ተጠያቂ የማያደርጋቸው ሁሉም ሥልጣን በእጃቸው ስላለ ብቻ በአቅም ማጣት ነው። ይህ ማለት ለጄኔራሎቹ ከሥልጣን መራቅ ማለት ዘብጥያ ከመውረድ ብዙ አይለይም። በሱዳን እድሜያቸው የገፉት የዚያኛው ትውልድ አባላት ኦፕሬሽን ሙሴን አይረሱም። በዚያ ዘመን ከእስራኤል ጋር የነበራቸውን ግንኙነት ያስታውሳቸዋል። እንደ አውሮፓዊያኑ በ1984 በወቅቱ የነበሩት ፕሬዝዳንት ጃፋር ኒሜሪ የእስራኤል ልዩ ኃይልና ሞሳድ ሱዳን መጠለያ ካምፕ ውስጥ የነበሩትን ከኢትዮጰያ የሄዱ ቤተ እስራኤላዊያንን በምስጢር እንዲወስዱ ፈቅደው ነበር። ኒሜሪ በኋላ ላይ ከእስራኤሉ ሞሳድ ለዚህ ተግባራቸው ጠቀም ያሉ ሚሊዮን ዶላሮችን ለዚህ ትብብራቸው እንደተቀበሉ ይነገር ነበር። አሁንም ቢሆን በሱዳን ትልቁን ቢዝነስ ከጀርባ ሆነው የሚያንቀሳቅሱት የቀድሞ መኮንኖች እንደሆኑ ይታወቃል። በአልበሽር ጊዜ የጦር መኮንን የነበሩት ሁሉ ወደ ንግድ ገብተዋል። ገንዘቡ የሚዘወረው በእነርሱ ነው። ማዕከላዊ ባንኩ ብር ሲቸግረው፣ መንግሥት ደመወዝ የሚከፍለው ሲያጣ እነዚህን የቀድሞ ጄኔራሎች ለምኖ ነው የሚበደራቸው። ይህ ሁኔታ ሱዳን ወደፊትም በፖለቲካና ወታደራዊ ኃይል የአገሪቱን ሃብት በተቆጣጠሩ ኃያላን [ክሊፕቶክራሲ] የምትዘወር አገር እንደምትሆን የሚጠቁም ነው። እስራኤል ከአረብ አገራት ጋር ግንኙነቷን ማለሳለስ ትፈልጋለች። እውቅ ማግኘት ደግሞ ቀዳሚው ፍላጎቷ ነው። አሜሪካ ይህ የእስራኤል ህልም እንዲሳካ ትሰራለች። ትራምፕ ይህን አሳክተው ሳምንታት ብቻ በቀሩት ምርጫ ሞገስን ማግኘት ይሻሉ። ሳዑዲና ኢምሬትስ ሱዳን ከእነሱ ፍላጎት እንዳትርቅ ፍላቶታቸው ነው። ሱዳኖች የዳቦ ጥያቄ በቶሎ እንዲመለስላቸው ይሻሉ። የሲቪል አስተዳደሩ ግን ለእነዚህ ሁሉ ፍላጎቶች ተገዢ መሆን ፈተና ሆኖበታል። ወጣት እስራኤላዊያንና አሜሪካዊያን መንግሥታቸው ከነጄኔራል ቡርሃን ጋር አዲስ ፍቅር ለመጀመር መፈለጉ ልባቸውን ይሰብረዋል። ምክንያቱም ጄኔራሎቹና ወታደራዊ መኮንኖቹ በአልበሽር ዘመን ለተፈጸሙ ዘግናኝ እልቂቶች በአንድም ሆነ በሌላ ተጠያቂ ናቸው። በተለይም የዛሬ 15 ዓመት በዳርፉር ለሆነው ጭካኔ የሚጠየቅ አለመኖሩ ያሳዝናቸዋል። በዳርፉር ያኔ የሞተው ሰው ከሩብ ሚሊዮን በላይ ነው። በዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ስሜት የሚሰጥ አመክንዮ እየተናገሩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዶክ ናቸው። ለእስራኤል እውቅና መስጠትና ሱዳንን ከጥቁሩ የአሸባሪ አገራት መዝገብ መፋቅ ሁለት የተለያዩ ነገሮች ናቸው ይላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ሁለቱን ለምን እናገናኛቸዋለን? ሐምዶክ እያሉ ያሉት ሱዳን አሸባሪዎችን ጠራርጋ አባራለች። ሱዳን ለተጎጂ ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ገንዘብ መድባለች። ሱዳን አሁን የዲሞክራሲ ጭላንጭል እያየች ያለች አገር ናት። ይቺን አገር ለእስራኤል እውቅና ካልሰጠሽ ብሎ ማስጨነቅ ዲሞክራሲን ማዳፈን ነው ይላሉ። ሐምዶክ ይቀጥላሉ፣ "የእስራኤልን የዕውቅና ጉዳይ በዲሞክራሲ ምርጫ የሚመጣው መንግሥት ይጨነቅበት። አሁን ዳቧችንንና ዲሞክራሲያችንን አትንፈጉን።" አሜሪካኖች ለጊዜው ሐምዶክን የሚሰሙበት ጊዜ ላይ አይደሉም። ሱዳን የአሜሪካንን ምርጫ ውጤት ከአገሬውም በላይ በጭንቀት የምትከታተለው ወ'ዳ አይደለም።
45094422
https://www.bbc.com/amharic/45094422
የ"ይቻላል" መንፈስ የሰፈነበት የአዲስ አበባው ቴድኤክስ የንግግር መድረክ
ልጅ ሳለ ሰዎች በስልክ ሲነጋገሩ ያያል። 'እንዴት ድምጽ በቀጭን ሽቦ ይተላለፋል?' ሲል በጠያቂ አእምሮው ያሰላስላል። አውጥቶ አውርዶም ስልክ ለመፈልሰፍ ይወስናል።
ያስፈልጉኛል ያላቸውን እቃዎች ከአካባቢው መሰብሰብ ጀመረ። ጣሳን ለድምጽ መሳቢያነት ተጠቅሞ ከጭቃ የተሰራ የስልክ እጀታ ሠራ። ስልክ የመጀመሪያ የፈጠራ ሙከራው አይደለም። ዘወትር አዳዲስ ነገር ስለመፈልሰፍ ከማሰብ ወደ ኋላ አይልም። እስራኤል ቤለማ ይህ ባህሪው የኢንጂነርነት ሙያን ለመቀላለል እንዳበቃው የተናገረው ከቴድኤክስ አዲስ መድረኮች በአንዱ ነበር። ቴድኤክስ አዲስ እንደ እስራኤል ያሉ በንግግር ሰዎችን ማነሳሳት የሚችሉ ግለሰቦች ሀሳባቸውን የሚያካፍሉበት መድረክ ነው። ተናጋሪዎች ወደ 20 ደቂቃ ገደማ ይሰጣቸዋል። ስለ ሙያዊ ህይወታቸው ያወሳሉ። እንዴት ውጣ ውረድን አልፈው ከስኬት ማማ እንደደረሱ ይናገራሉ። ተሞክሯችውን በማካፈል አድማጮችን ለማነሳሳትም ይሞክራሉ። • የኬንያ ዳኞችን አለባበስ የቀየረች ኢትዮጵያዊት • ኢትዮጵያዊቷ ኮከብ ‘የ2017 የምስራቅ አፍሪካ ምርጥ ዲዛይነር’ ሆነች • የታኘከ ማስቲካ ዳግም ነብስ ሲዘራ የእስራኤል ኢላማም ንግግሩን የሚሰሙትን ማጀገን ነበር። እሱ በመረጠው የሙያ መስክ የደረሰበትን መነሻ በማድረግ፤ ግብን ማወቅ ያላሰለሰ ጥርት ሲጨመርበት ውጤታማ እንደሚያደርግ ያመለክታል። "ከቴድኤክስ አዲስ ተናጋሪዎች መሀከል ዩኒቨርስቲ እንኳን ሳይገባ ስልክ የሠራውን እስራኤል አልረሳውም" የሚለው የቴድኤክስ አዲስ ዋና አዘጋጅ ስንታየሁ ሰይፉ ነው። የንግግር መድረኩን የጀመረው ማህበረሰቡ የስኬታማ ሰዎችን የህይወት ተሞክሮ በመስማት የ"ይቻላል" መንፈስ እንዲሰፍንበት መሆኑን ይናገራል። የቴድቶክስ ታናሽ እህት ቴድኤክስ አዲስ ስንታየሁ የቴድኤክስ አዲስ ሀሳብን የጠነሰሰው ከዘጠኝ ዓመት በፊት አየርላንድ ሳለ ነው። አዳዲስ ሀሳብ የሚቀርብበትን የቴድቶክስ የንግግር መድረክ እንዲታደም በጓደኛው ይጋበዛል። ሳይንስን ለብዙሀኑ ተደራሽ የማድረግ ጽንሰ ሀሳብ የተስተጋባበት ንግግርም ያዳምጣል። በንግግሩ ስለተደመመ የቴድ መድረኮችን መከታተል ቀጠለ። ቴድቶክስ ዓለም አቀፍ የንግግር መድረክ ነው። የቴክኖሎጂ፣ የመዝናኛና የዲዛይን ልሒቃን ወደ 20 ደቂቃ ገደማ ንግግር ያደርጋሉ። ቴድቶክስ በተለያዩ ሀገሮች እህት ቅርንጫፍ ያለው ሲሆን የአዲስ አበባው ቴድኤክስ አዲስም ይገኝበታል። "ብዙዎቻችን ውጪ ሀገር ጥሩ ነገር ስናይ ወደ ኢትዮጰያ መውሰድ እንፈልጋለን" የሚለው ስንታየሁ ቴድንም ወደ ኢትዯጰያ ለማሻገር የወሰነበትን ወቅት ይገልጻል። ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት 45 ሰዎች ንግግር አድርገዋል። በሚታወቁበት የሙያ መስክ ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል። ከሙያዊ ትንታኔ ባሻገር የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮችን በማንሳት ምልከታቸውን አስደምጠዋል። ቴድኤክስ አዲስ፤ በቴድቶክስ ህግጋት ለመተዳደር ተስማምቶ ፍቃድ ተሰጥቶቷል። ስምምነቱ በየዓመቱ የሚታደስ ሲሆን ታዳሚዎች የሚሰነዝሩት አስተያየት ከግምት ይገባል። በመድረኩ የማስታወቂያ፣ የፖለቲካና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች አይስተናገዱም። ተናጋሪዎቹ እነማን ናቸው? ሰዎች በአንድ ንግግር ተአምራዊ ለውጥ ያመጣሉ ባይባልም የስኬት ታሪኮችን ማድመጥ አንዳች ብርታት እንደሚሰጥ እሙን ነው። "ማህበረሰቡን ማነሳሳት የሚችሉ የቴክኖሎጂ፣ የመዝናኛና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ይቀርባሉ" ይላል ስንታየሁ። ስኬታማ የሆኑ እንዲሁም መልካም ነገርን ማበርከት የሚችሉ ይጋበዛሉ። መድረክ ይሰጠን ብለው የሚጠይቁም አሉ። በታዳሚዎች የሚጠቆሙ ተናጋሪዎችም ይካተታሉ። "ተናጋሪ ማግኘት ከባድ ነው። መጠነኛ ጉዳይን አግዝፈው መሸጥ የሚችሉ ተናጋሪዎች አሉ። ትልቅ ነገር ሰርተው ምንም መናገር የማይችሉም እንዲሁ" ሲል ተቃርኖውን ያስረዳል። ከሀገር ውስጥ ባሻገር ከውጪ ያስመጧቸው ተናጋሪዎችን ይጠቅሳል። በእርግጥ የአቅም ውስንነት ስላለ አዘውትረው ከውጪ ለማስመጣት አይደፍሩም። ስንታየሁ እንደሚለው በመድረኩ የሚጋበዙት ሰዎች ሀሳባቸውን በየትኛውም የህይወት ደረጃ ያለ ሰው እንዲገነዘበው ከሽነው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ስለቴድኤክስ የሚያውቁ ሰዎች በአዲስ አበባው መድረክ የመናገር እድል ሲያገኙ በደስታ ይቀበላሉ። እንዲከፈላቸው የሚጠይቁም አልታጡም። በቴድ ህግ መሰረት ለንግግር ገንዘብ መክፈል እንደማይፈቀድ የሚያወሳው ዋና አዘጋጁ፤ ባይከፈላቸውም ለመናገር የሚፈቅዱ ቢኖሩም ያለ ክፍያ አንዳችም ቃል አንተነፍስም ብለው ጥሪውን የማይቀበሉም እንዳሉ ያስረዳል። የአካባቢ ጥበቃ ተሟጋቹ ንጉሡ አክሊሉ በቴድኤክስ አዲስ ንግግር ካደረጉ መካከል አንዱ ነው። የአካባቢ ጥበቃ ትኩረት ባይቸረውም ባገኘው መድረክ ሀሳቡን ከማካፈል አይቦዝንም። ቴድቶክስ አንጋፋ የንግግር መድረክ እንደመሆኑ በእህት ድርጅቱ ቴድኤክስ አዲስ ሀሳቡን እንዲያካፍል ሲጠየቅ እንደተደሰተ ያስታውሳል። "አረንጓዴ ኢትዮጵያን መፍጠር ይቻላል?" የንግግሩ መነሻ ጥያቄ ነበር። በተሰጠው አጭር ደቂቃ ሀሳቡን እያዋዛ ስለሚያቀርብበት መንገድ በቴድኤክስ አዲስ መምህራን ስልጠና ከወሰደ በኋላ ንግግሩን አቅርቧል። "የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ እንደ ቅንጦት ይቆጠራል። የምዕራባዊያን ጉዳይ እንደሆነም ይታሰባል። ስለዚህ በተገኘው አጋጣሚ ስለ አካባቢጥበቃ እናገራለሁ" ይላል። ንግግሩን ብዙዎች በማህበራዊ ድረ ገጾች ስለተጋሩት መወያያ ሆኖ ነበር። ማህበራዊ ድረ ገጽ ላይ መገኘቱ የሀሳቡን ተደራሽነት ያሰፋዋል። በሌላ በኩል በማህበራዊ ድረ ገጾች መነጋገሪያ የሚሆኑ ሀሳቦች ከአውድ የሚወጡበት ጊዜ እንዳለም ንጉሡ ሳይጠቅስ አላለፈም። ንግግር ወዲህ እኛ ወዲያ? ሀሳቦች የሚስተናገዱባቸው በቂ መድረኮች አሉ ወይ? የብዙዎች ጥያቄ ነው። በአደባባይ ሀሳብን የመግለጽ ተነሳሽነት ወይም ሀሳብ የሚንሸራሸርባቸው መድረኮችን የመታደም ፍላጎትስ አለ? ለስንታየሁና ንጉሡ መልሱ "የለም!" ነው። በተለይም የአደባባይ ንግግር በጣም አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ አይሞከርም። ከሌሎች ሀገሮች ተሞክሮ ጋር ሲነጻጸር ኢትዮጵያው ውስጥ ንግግር ቦታ መነፈጉ ጥያቄ ያጭራል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እንደ 'ቶስትማስተርስ' ያሉ ንግግርን የሚያበረታቱ መርሀ ግብሮች ብቅ ብቅ እያሉ ነው። ተስፋ ፈንጣቂ ቢሆኑም ከአዲስ አበባ ማለፍ ግን አልቻሉም። ዘመኑ ተናግረው ማሳመን የሚችሉ ሰዎች ነው። ስለዚህም የንግግር ችሎታን ማስረጽ የግድ ይላል። በስንታየሁ ገለጻ "የንግግር ባህል አልሰረጸም። ሀሳባችንን በመሸጥ ረገድም ክፍተት አለ። የአደባባይ ንግግር እንዲለመድ የውይይት መድረኮች መበራከት አለባቸው። መሰናዶዎቹም በዓመት አንዴና ሁለቴ ከመሆን ሊያልፉ ይገባል።" ሀሳቡን የምትጋራው ቴድቶክስን ከሀገር ውጪ፤ ቴድኤክስ አዲስን ደግሞ በሀገሯ የታደመችው ቤተልሔም ናት። "ሀሳባችንን እንዴት መሸጥ እንዳለብን አናውቅም። ጥሩ ነገር ቢሰሩም በአግባቡ ማብራራት ባለመቻል ብዙ እድል የሚያመልጣቸው በርካቶች ናቸው" ትላለች። ቤተልሔም የታደመችው ኢትዮጵያዊ የደም ሀረግ ያለው እንግሊዛዊ ጸሀፊ ለምን ሲሳይ ንግግርን ነበር። ንግግር ካደረገ በኋላ ብዙዎች ጥያቄ በመሰንዘር መሳተፋቸው አስደስቷታል። "ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው ሰዎችን ልምድ መስማት ይጠቅማል። በአንድ ቀን ንግግር ለውጥ ባይመጣም አስተሳሰብን ለመፈተሽና ሌላ ዕይታ ለመቃኘት ያግዛል። ከምንም ተነስቶ ትልቅ ደረጃ የደረሰ ሰው ተሞክሮ አነሳሽና ተስፋ ሰጪም ነው" ስትል የቴድ መድረኮች ምልከታዋን ታካፍላለች። በተያያዥም መሰል መድረኮች የጥቂቶች መሆናቸውን በመጠቆም፤ ተደራሽነታቸውን የማስፋት ጉዳይን አዘጋጆቹ ያስቡበት ትላለች። በቴድኤክስ አዲስ ከ250 እስከ 300 ሰው ይታደማል። ተሳታፊዎች ሲመረጡ የፆታ፣ የእድሜና የሙያ ስብጥርን ለመጠበቅ እንደሚሞከር ስንታየሁ ይገልጻል። ንጉሡ በበኩሉ የንግግር መድረኮች አለመኖር ብዙሀኑን ለፅንፈኛነት እንዳጋለጠ ያምናል። "በሀገራችን ንግግር እንደ ሀጢያት ይቆጠራል። ሁላችንም ተገናኝተን ብንነጋገር ግን ከፅንፈኝነት ወደ መግባባት እንሸጋገራለን" ይላል። ሀሳብና ሀሳብ መካከል ፍጭት ካልተደረገ ሁሉም በየፅንፉ የከረረ አቋም ይይዛል። የሀሳብ ልዩነትን ለማክበርም መነጋገሪያ መድረክ ያስፈልጋል።
news-54213710
https://www.bbc.com/amharic/news-54213710
ክትባት፡ ተመራማሪዎች ያልደረሱበት አነጋጋሪው የክትባት ምስጢር
ክትባት ባይኖር ኖሮ ምን ይውጠን ነበር? ምናልባት የዓለም ሕዝብ 4 ቢሊዮን ብቻ ይሆን ነበር። ወይም ከዚያ በታች።
ማን ስለ ክትባት ይጨነቅ ነበር? እድሜ ለኮሮናቫይረስ። በእርግጥ ኮቪድ-19 ብዙ ስለ ክትባት እንድናስብ አድርጎናል። ይህ ትውልድ በጉጉት የሚጠብቀው ክትባት የኮሮናቫይረስን ነው። ቻይና ክትባቱን አግኝቼዋለሁ ማለት ጀምራለች። አንዳንዶች 'አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው' ሲሉም ቀልደዋል። ሩሲያም ክትባቱ በእጄ ነው ካለች ሰንብታለች። አንዳንድ የምዕራቡ አገራት 'ሩሲያን ማን ያምናል' ብለዋታል። ክትባት የዓለምን ሕዝብ ለሁለት ከፍሎታል። ፀረ-ክትባት የሆኑ ቡድኖች ከወዲሁ ክትባት ይቅርባችሁ እያሉ ነው። ለምን ሲባሉ፣ ቢልጌትስን ከማበልጸግ ያለፈ ትርፍ የለውም ይላሉ። ለመሆኑ ክትባት በጥቅሉ መጥፎ ነገር ነው? ይህ ዘገባ ስለክትባት በረከቶች ያሉ እውነታዎችን በሳይንስ አስደግፎ ያቀርብልናል። እንደ ጠብታ ክትባት ይቺንም ጽሑፍ ዋጥ ማድረግ ነው እንግዲህ። በጊኒ ቢሳው አስደናቂ ነገር ተከሰተ። ከጊኒው ቢሳው ሆኖ ለቢቢሲ በስካይፕ ቃለ ምልልስ የሰጠው ዴንማርካዊ ተመራማሪ ፒተር ኤቢ፤ ከ40 ዓመታት ውስጥ ብዙ ዘመኑን ያሳለፈው በጊኒ ቢሳው ነው። ለመጀመርያ ጊዜ ጊኒ ቢሳው የሄደው በ1978 ዓ.ም ነበር። ድሮ! በአፍሪካዊቷ ድሀ አገር ውስጥ ለዚህን ያህል ዘመን ይሄ ዴንማርካዊ ምን ይሠራል? እየተመራመረ ነበር። ክትባት በዚያች አገር አንድ አስደናቂ ውጤት ካመላከተው በኋላ እዚያው በምርምር ሰምጦ ቀረ። ፒተር ጊኒ ቢሳው በሄደ ጊዜ ገዳይ የኩፍኝ ወረርሽኝ ነበረ። ብዙ ልጆችን ቀጥፏል። ህጻናቱ በበሽታው እንደ ቅጠል ረገፉ። ከዚያ እነ ፒተር የክትባት ዘመቻ ጀመሩ። ልክ ይህን ዘመቻ ባደረጉ በዓመቱ አስደናቂ ነገር ታየ። ክትባት ከወሰዱት 50 ከመቶዎቹ የመሞት ዕድላቸው ክትባት ካልወሰዱት ይልቅ በግማሽ አንሶ ተገኘ። ይህን ስታነቡ "ልጆቹ ክትባት ወስደው ሊሞቱ ነበር እንዴ፣ታዲያ?" ትሉ ይሆናል። ነገሩ ወዲህ ነው። እናንተ ልጆቹ በኩፍኝ ሳይሞቱ የቀሩ ነው የመሰላችሁ። አይደለም። አስደናቂው ነገር ይህ ነው። ክትባት የወሰዱ ልጆች በሌላ በሽታም የመሞት እድላቸው በግማሽ ቀንሶ ነው የተገኘው። ከክትባቱ በኋላ እንዴት በጊኒ ልጆች ዘንድ ሞት በዚያ ደረጃ ሊቀንስ ቻለ ብለው መመራመር ጀመሩ፤ እነ ፒተር። ለካንስ የኩፍኝ ክትባቱ ሳይታሰብ ልጆቹን በሌሎች የማይታወቁ በሽታዎችም እንዳይሞቱ አድርጓል። ክትባቱ ለዚያ ዓላማ ባይሰራም ሰውነታቸው ውስጥ ሲገባ ግን የሆነ ያሻሻለው ነገር ነበረ። ሳይንቲስቶቹን ያስደነቀውም ይኸው ነው። ሰውነታችን እንዴት ነው የሚሰራው? ለዘመናት ክትባቶች ለአንድ በሽታ መከላከያ ብቻ ነበር ሲሰጡ የነበሩት። ነገር ግን ሰውነታችን ክትባቶችን እንደዚያ አይደለም የሚረዳቸው። ባልታሰበ ሁኔታ አንድ ክትባት በርካታ በሽታዎችን ሊከላከል ይችላል። ካልታሰበ በሽታ ይከላከላል። ይህ የተደረሰበት ግን ዘግይቶ ነው። በጊኒ ቢሳው የተደረገ ሌላ ምርምር ለፈንጣጣ በሽታ ክትባት የወሰዱ ልጆች 80 ከመቶ በሕይወት የመኖር ዕድል ጨምሮላቸዋል። የምናወራው በፈንጣጣ ምክንያት ሳይሞቱ የቀሩትን አይደለም። ያ ሲጀመርም የክትባቱ ዓላማ በመሆኑ አይደንቅም። በሌላ በሽታም የመሞት እድላቸው መቀነሱ ነው አስደናቀው። በዴንማርክ ሳይንቲስቶች የሳንባ ነቀርሳ ክትባት የወሰዱ ልጆች በሌላ ተፈጥሯዊ በሽታ የመሞት እድላቸው በ42 ከመቶ ያህል ቀንሶ አግኝተውታል፡፡ ይህም ልጆቹ ክትባቱን ወስደው እስከ 45 ዓመታቸው ክትትል ተደርጎላቸው የተገኘ አስደናቂ ውጤት ነው። በደቡብ አፍሪካ ደግሞ ውሾች ላይ የተሰራ ጥናት ተመሳሳይ ውጤትን አሳይቷል። ከእብድ ውሻ በሽታ (ሬቢስ) ክትባት የተወጉት ውሾች በሌላ የውሻ በሽታ ጭምር የመሞት ዕድላቸው ቀንሶ ተገኝቷል። ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት አንቀጾች አንድ ነው ነጥባቸው። ክትባት ከታሰበለት ዓላማ ውጭም ይሰራል። ያልታሰቡ፣ የማይታወቁ፣ ያልተደረሰባቸውን በሽታዎችንም ይከላከልልናል። እንዴት? ለሚለው ግን ሳይንቲስቶቹም መልስ የላቸውም። መገመት ብቻ ነው የቻሉት። የአንድ በሽታ ክትባት እንዴት ሌላ በሽታን ሊከላከል ቻለ? አንድ ሰው አንድ ክትባት ወስዶ ካልታሰበ አለርጂ (ብግነት)፣ ካልታሰበ ካንሰር፣ ካልተጠበቀ አልዛሚር ሊፈወስ ይችላል ማለት ነው። ለዚህም ነው የሳምባ በሽታው [ቲቢ] ክትባት ምናልባት ኮቪድንም ሊከላከል ይችል ይሆን እየተባለ ሙከራው የቀጠለው። ነገር ግን በቲቢና በኮቪድ-19 ደቃቃ አካላት (ማይክሮኦርጋዝምስ) መካከል ምንም የሚያመሳስላቸው ነገር የለም። ኧረ እንዲያውም አይገናኙም። አንዱ በባክቴሪያ ሌላው በቫይረስ ነው የሚመጣው። ሆኖም ግን ክትባቱ የሆነ ተአምር ሰውነታችን ላይ እንዲፈጠር ሲያደርግ ታይቷል። ጭላንጭል ነው ለጊዜው የታየው። ለዚያም ነው ሳይንቲስቶች ተስፋ ያልቆረጡት። ይሁን እንጂ ሁለቱን በሽታዎች የሚያስከትሉት ደቂቀ አካላት ባክቴሪያና ቫይረስ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን፤ በዝግመተ ለውጥ ራሱ በአፈጣጠራቸው 3 ቢሊዮን ተኩል ዓመታት ይለያያሉ። አንዱ የሌላው ታላቅ ነው። አንዱ ለሌላው ታናሽ ነው። አሁን ትልቁ ጥያቄ የሆነው እንዴት ለአንድ በሽታ የታሰበ ክትባት ሌሎች ያልታሰቡ ውጤቶችን አውንታዊ ውጤትን ያስከትላል የሚለው ነው። ሳምባ በሽታን [ቲቢ] እንውሰድ፤ ይህ በሽታ ለዘመናት የሰው ልጅ ጠላት ሆኖ የቆየ ነው። በአንድ ዘመን ይሄ የፈረንሳይ የባክቴሪያ ሳይንስ ተመራማሪ አልበርት ካልሜት እና ካሚል ጉሪን ክትባት አገኙለትና የሰው ልጅን ከፍጅት ታደጉት። እንጂ ይሄን ጊዜ 1 ቢሊዮን ሕዝብ እንኳን በምድር ላይ አይቀርም ነበር። ይሄ ጠምዛዛ ባክቴሪያ ከሰው ልጅ ጋር ለ40ሺህ ዓመታት አብሮ ነበረ። ሰው በሳምባ በሽታ ሲለከፍ የሞት ፍርድ ማለት ነበር። የጥንት የግብጽ ሕዝቦች ባደረቋቸው ሬሳዎች ውስጥ በአንድ ሦስተኛው አስከሬኖች ላይ ይህ የሳምባ በሽታ ባክቴሪያ ተገኝቶበታል። በዚያ ዘመን ሕዝቡን የፈጀው ይኸው በሽታ ነው። ከምድረ ገጽ ሊያጠፋን የደረሰ ባክቴሪያ ነበር። ምን ያኔ ብቻ! በ20ኛው ክፍለ ዘመን ራሱ የሳምባ በሽታ ባክቴሪያ ያልፈጀው የሰው ዘር አለ እንዴ? የፖለቲካ አዋቂውን ኤሊኖር ሩዝቬልትን ማን ገደለው? ገራሚውን ደራሲ ጆርጅ ኦርዌልን ማን ነጠቀን? ወጣ ያለ የምንግዴ ሕይወት የኖረውን ፍራንዝ ካፍካን ማን ወሰደው? የሳምባ በሽታ አይደለምን? እነዚህ ሁለት ፈረንሳያውያን ነፍሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑርልንና ቢሲጂ (BCG) የተባለውን ክትባትን ፈጠሩ። ይኸው ምድር ላይ ቢሊዮኖች ከቲቢ እልቂት ተረፉ። እነ አልበርት ካልሜትና ካሚሎ ጓሪን ክትባቱን እንዴት አገኙ? እንዴት ክትባቱን ደረሱበት? ቲቢ ያን ጊዜ ልክ የኤችአይቪ ወይም የኮሮናቫይረስ ክትባት ከማግኘትም በላይ ነበር። አሁን ክትባቱ እጃችን ላይ ስላለ ነው የማይደንቀን። ክትባቱን ያገኙት ከላም ነው። ድሮም ላም የዋህ ናት። ላም ውስጥ ያገኙትን ክትባት ቀስ በቀስ እየቀየሩ ነው ፈውስ ያገኙት። በ1921 ዓ. ም ላይ በአንድ ልጅ ተሞከረና በ1950ዎቹ ታሪክ ተለወጠ። ክትባቱ ከ70-80 በመቶ ፈውስ የሚሰጥ ነበር። ችግር ተቀረፈ። ብዙዎች ዳኑ። ለቲቢ መከላከያ ተበጀለት። እስካሁን ያወራነው የክትባት ታሪክ ነው። ምኑም አስደናቂ ላይሆን ይችላል። አሁን አስደናቂው ሳይንቲስቶች ለሳምባ ነቀርሳ ሲሰጥ የነበረው ቢሲጂ የተባለው ክትባት ስንትና ስንት በሽታን ሲከላከል እንደነበረ ስለደረሱበት ነው። ደግና ቀና ክትባት ነበር። ልጆች እንደተወለዱ በጥቂት ወራት ውስጥ በበሸታው ይቀጠፉ ነበር። ከክትባቱ በኋላ ግን ይህ ቀረ። ለካንስ ይህ ክትባት በሳምባ እንዳይሞቱ ብቻ አልነበረም የሚያደርገው። ከዚህ ክትባት በኋላ በሌላ በሽታም የሚሞቱት ህጻናት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ቀነሰ። በቁጥር ማስቀመጥ ካስፈለገ የልጆች ሞት በ70 ከመቶ ቀነሰ። በዚህ ክትባት ምክንያት ብቻ። በኋላ እንደተደረሰበት የሳምባ በሽታ ክትባት ከጉንፋን፣ ሴፕቲሴሜያና ከሄርፒስ በሽታዎች ይከላከላል። ይህ ተጠንቶ የተደረሰበት ብቻ ነው። ያልተደረሰበት ስንት ይሆን? ያልተመለሰው ጥያቄ እንዴት ነው አንድ ክትባት ከታሰበለት በሽታ ውጪ ላሉ በሽታዎች ፈውስ ሊሆን የሚችለው? ይህ የአንባቢ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሳይንቲስቶችም ጥያቄ ነው። አንዱ ትንታኔ ደቂቀ ህዋሳት (ማይክሮኦርጋዝምስ) ቢለያዩም የሆነ አይነት አንቲጂን ይጋሩ ይሆናል የሚለው ነው። አንቲጂንስ ማለት ሞሎኪዮሎች ናቸው። ሞሎኪዮሎቹን የተፈጥሮ የበሽታ መከላከያ ሠራዊታችን በሰላይነት ይጠቀማቸዋል። ባዕድ አካል ወደ ሰውነታችን ስለመግባቱ የሚጠቁሙት እነሱ ናቸው፤ አንቲጂኖች። ለምሳሌ አንድ ህጻን የፀረ ሳምባ በሽታ ቢሲጂ ክትባት ብንወጋው መጀመርያ ያለቅሳል። ከዚያ ክትባቱ ሰውነቱ ውስጥ ይገባል። ከዚያ ሰውነቱ ከሆነ አንዳች አዲስ ዓይነት ፕሮቲን ጋር እውቂያ ይፈጥራል፤ እዚህ ጋ ነው ጨዋታው። ሰውነት ያንን በዚያ ክትባት ውስጥ ያለን ፕሮቲን ሲያውቅ በሰበቡ ሌሎችንም ያውቃል? አንዴት ከተባለ ተመሳሳይ ፕሮቲኖቹ በሌሎች በማይታወቁና ባልታሰቡ የተህዋስም ሆነ የባክቴሪያ ቅንጣት ውስጥ መገኘታቸው ነው። በዚህ የተነሳ አንድ ክትባት በፍጹም ላልታሰበ ቫይረስም ሆነ ባክቴሪያ መከላከያ በመሆን ሊሰራ ይችላል። ሁለተኛው መላምት ደግሞ የሚከተለው ነው። ሰውነታችን ክትባት ሲገባበት በጥቅሉ ተከላካይ ሠራዊቱ ይነቃቃል። በተጠንቀቅ ይሆናል። ልዩ ኃይልም፣ ተለዋጭ ሠራዊትም፣ ሁሉም በተጠንቀቅ ይሆናሉ። በዚህ የተነሳ ሌሎች ቫይረሶችና ባክቴሪያዎች ወደ ሰውነት ሲመጡ ከባድ ምት ስለሚያጋጥማቸው ይወገዳሉ። ይህን ለማረጋገጥም የቢሲጂ ክትባት ለሆኑ ልጆች ተሰጣቸው። ከዚያ ለተለያዩ በሽታ አምጪ አቸንፍር (ፓቶጂኖች) እንዲጋለጡ ተደረገ። ከሳምባ በሽታ ብቻ አይደለም የተጠበቁት። ሰውነታቸው ሌሎችንም አቸንፍሮችን በጥንካሬ ሲዋጋ ተገኘ። ሁለት ዓይነት በሽታን የመከላከያ ሠራዊት አለ። አንደኛው ለባዕድ ተንበርካኪ ነው። ባዕዱን ኃይል ተዋግቶ ሲረታ ይላመዳል። ከዚያ በኋላ ሺህ ክትባት ቢሰጥም አይዋጋም። ይለግማል። እንዳይላመድ በሚል ነው ክትባት ሲሰራ ራሱ በሽታውን አዳክመው የሚሰጡት። ደንብሮ እንዲነሳ። አለበለዚያ ይላመድና ይለግማል። እንዲያውም ከጠላት ጋር አብሮ ተስማምቶ ሊኖር ይችላል። ሁለተኛው የበሽታን መከላከያ ሠራዊታችን ግን የተፈጥሮ ነው። ከእኛው ጋር የተፈጠረ (innate immune system) ነው። ይሄኛው አይዋጋም፤ ከተዋጋ ግን ድል አድራጊ ነው። አሁን ክትባቶች የሚያነቃቁት ክፍል ይህኛውን መሆኑ ነው ሌላው ሳይንቲስቶችን ያስደነቀው። ዴንማርካዊው ሳይንቲስት እንደሚለው ቢሲጄ ክትባት ለምሳሌ የዲኤንኤ ጥልፍልፍን በአዲስ መልክ ነው የሚያዋቅረው። ይህም ማለት ቲቢን የሚከላከል ሠራዊትን ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን አዲስ በሽታ የመከላከል ዘዴን የተማረ ውቅር ሠራዊት ሰውነታችን ይፈጥራል። "ይህ በመሆኑ ነው አንድ ተራ ክትባት አንዳንድ ሰዎችን ከካንሰርና ከእርጅና ጋር የሚመጣ የአንጎል ችግር [ዲሜንሺያ] ጭምር ሲከላከላቸው የምናየው።" በሚደንቅ ሁኔታ የቲቢ ክትባት አሁን አሁን ለፊኛ ካንሰር እጅግ ወሳኝ መድኃኒት እየሆነ መጥቷል። ሁለቱን ምን አገናኛቸው?ነው ጥያቄው። የፊኛ ካንሰር ታማሚዎች ደግሞ በዚህ መድኃኒት ከዳኑ በኋላ አልዛሚር ድርሽ አይልባቸውም። ይህም ሌላ አስደናቂ ነገር ነው። አንድ አስደናቂ ውጤት እንጨምርና ይህን ነገር እንዝጋው። ዴንማርካዊው ሳይንቲስት ፒተር እንደሚለው አንድ ጠብታ ክትባት በቂ ቢሆንም አንዳንድ ክትባቶች በርከት ተደርገው ሲወሰዱ ውጤታቸው በዚያ መጠን ሲያድግ ተስተውሏል። ይህ ግን ክትባቱ ስለሚያስከትለው አሉታዊ ጎኑ የተጠኑ ጥናቶችን ሳያነሳ ነው። አንድ ክትባት ተደጋግሞ መወሰዱ ለሆኑ በሽታዎች ጠንቅ ሊሆንባቸው ይችላል። የሰውነት መከላከያ ሠራዊቱ አባላት ጡንቻ እንዲያወጡና እንዲጠነክሩ ያደርጋቸዋል። በእርግጥ ይህ በክትባት ብቻ የሚመጣ ውጤት አይደለም። አንዳንድ ሰዎች በተፈጥሮ ከአንድ በሽታ ከዳኑ በኋላ መከላከያ ሠራዊታቸው ፈርጥሞ ይገኛል። በኩፍኝ ተይዞ የዳነ ሰው ኩፍኝ ጭራሽ ካልያዘው ሰው ይልቅ ሌሎች በሽታዎችን ሊከላከል ይችላል። ይህ በትክክል ለምን እንደሚሆን ባይታወቅም የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ተከላካይ ሠራዊት ጠላት አይቶ አንድ ጊዜ ከበረገገ በኋላ ያን ጠላቱን ታግሎ በመጣል ብርታቱን ስለሚያገኝ ነው የሚሉ ሳይንቲስቶች አሉ። የመጨረሻው አስደናቂ የክትባቶች ትሩፋት በ1980ዎቹ የዓለም ጤና ድርጅት ፈንጣጣ ከዓለም ጠፋ ብሎ አወጀ። ከዚያም ክትባቱ ራሱ ጠፋ። ስለዚህ ልጆች ይህን ክትባት መወጋት ቀረ ማለት ነው። የሚደንቀው ይላል ሳይንቲስቱ ፒተር፤ በጊኒ ቢሳውም ሆነ በዴንማርክ የፈንጣጣ ክትባት ብዙ ትሩፋቶች እንዳሉት ይታወቅ ነበር። ስናቆመው ግን ፈንጣጣን ብቻ እያሰብን ስለ ሌሎች ትሩፋቶቹ ቸል ብለን ነበር። አሁንም ተመሳሳይ ስህተት እየተሰራ ይመስላል። ፖሊዮ ከምድረ ገጽ ጠፍቷል ተብሎ ታውጇል። አፍሪካም ባለፈው ወር ጠራርጌ አጥፍቼዋለሁ ብላ አውጃለች። አሁን ምናልባት ፖሊዮ በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን ገጠሮች አልፎ አልፎ ሊያጋጥም ይችላል እንጂ ጠፍቷል። ፖሊዮ ክትባት ሲሰጥ ግን ክትባቱ ሌሎች ያልታሰቡ በሽታዎችንም ይከላከል እንደነበር አልተጠናም። የፖሊዮ ክትባት በጊኒ ከፖሊዮ ሌላ ሞትን በ67 ከመቶ መቀነሱን አንድ ጥናት ደርሶበታል። ያን ጊዜ ፖሊዮ በጊኒ ጠፍቷል በሚባልበት ደረጃ ነው ታዲያ ይህ ውጤት የተመዘገበው። ክትባቱ ምስጢራዊ ትሩፋት ነበረው ማለት ነው። "አንድን በሽታ ከምድረ ገጽ ስናጠፋ ክትባቱን አብረን አሽቀንጥረን ስንጥለው ትልቅ ነገር ያሳካን ይመስለናል። ነገር ግን አንድን ክትባት ከድል በኋላ ስንጥለው ሞትን እየጨመርን እንደሆነ አናውቅም" ይላሉ ሳይንቲስቱ። አዲስ የሚመጣልን የኮቪድ-19 ክትባት ምን ትሩፋት ይዞልን ይመጣ ይሆን?
news-42249770
https://www.bbc.com/amharic/news-42249770
ፌስቡክን ለልጆች?
ማህበራዊ ድረ-ገጾችን ለመጠቀም ትንሹ ዕድሜ ስንት መሆን አለበት?
ልጆች ከጓደኞቻቸውና ፍቃድ ካላቸው ትልቅ ሰዎች ጋር የቪድዮ መልዕክት መቀያየር ይችላሉ በእርግጥ ፌስቡክን ዕድሜያቸው 13ና ከዚያ በላይ የሆኑት ብቻ ነው እንዲጠቀሙ የሚፈቀደው። ሆኖም ይህንንም ለመቆጣጠር ከባድ በመሆኑ ዕድሜያቸው ከ13 ዓመት በታች የሆኑ ከ20 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት ይጠቀሙበታል። ለዚህም ነው ባለፈው ሰኞ ፌስቡክ ለልጆች ታሰቦ የተሠራን መተግበሪያ (አፕሊኬሽን) ያቀረበው። የወላጆችንን ፈቃድ የሚጠይቁ ከባድ የዕድሜ መቆጣጠሪያ መንገዶችንም ዘርግቷል። ይህ 'ሜሴንጀር ኪድስ' የተሰኘው መተግበሪያ ዕድሜያቸው ከ13 በላይ ለሆኑት ከቀረበው ይልቅ ለአጠቃቀም ቀለል ያለ ነው። ''ወላጆች ልጆቻቸው ዘመናዊ ስልኮችንና የተለያዩ ዘመናዊ መሣሪያዎችን እንዲጠቀሙ በይበልጥ እየፈቀዱላቸው ይገኛሉ'' ይላሉ የ'ሜሴንጀር ኪድስ' ሥራ አስኪያጅ ሎረን ቼንግ። ''እናም እንደዚህ አይነት መተግበሪያዎች ለልጆቻቸው ታስበው እንዲሠሩ በውይይቶችና በጥናት ከወላጆች ጥያቄ ሲቀርብልን መሥራት እንደነበረብን እርግጠኛ ሆንን'' ብለዋል። ፈቃድ ያሏቸው ጓደኞች ሁለት ልጆች በ'ሜሴንጀር ኪድስ' ጓደኛሞች መሆን ቢፈልጉ የሁለቱም ወላጆች ፈቃድ መስጠት ይኖርባቸዋል። ከጥቃትና ከችግር ነፃ መሆናቸውንም ሲያረጋግጡ ልጆቹ ከጓደኞቻቸው ጋር በቀጥታ በቪድዮ መነጋገርና ፎቶግራፎችና የጽሑፍ መልዕክቶችን መቀባበል ይችላሉ። የወላጆች ፈቃድ ማስፈለጉ የልጆቹን ደህንነት ይጠብቃል መልዕክቶቻቸውንም በሚላላኩበት ጊዜ ከማንነታቸው ጋር የሚሄዱና በፈለጉት ሥዕላዊ መግለጫዎች እንዲገዙ ለልጆች ታስበው የተዘጋጁ 'ጂፍ'ና'ሰቲከር' የተሰኙ ይዘቶችን ይዟል። ፈቃድ ያገኙ አዋቂዎችም ቢሆኑ ከልጆቹ ጋር መልዕክት መለዋወጥ ይችላሉ። እነሱ ግን መልዕክቱን በነባር የፌስቡክ መልዕክት ሳጥን ነው የሚያገኙት። ቀጣዩ ትውልድ ፌስቡክ ይህን አዲስ መተግበሪያ ለዋናው ማህበራዊ ድረ-ገጽ የመረጃ ምንጭ እንደማይሆን ቃል ገብቷል። ፌስቡክ ሊያገኝ የሚችለው ጥቅም ለወላጆች የታሰቡ ማስተዋወቂያዎችን በዚህ መተግበሪያ በመላክ ነው። ካለበለዚያ ደግሞ ወጣቶችን ዒላማ ያደረጉ ማስተዋቂያዎችን በመልቀቅ ልጆቹ 13 ሲሞላቸው ወደ ዋነኛው ፌስቡክ እንዲሸጋገሩ ያደርግ ይሆናል። ፌስቡክ ግን የተፈሩት ነገሮች እንደማይፈጠሩ ተናግሯል። መተገበሪያው የልጆቹን ዕድሜ እንደማያውቅና ሲያድጉ ወደ ዋነኛው ፌስቡክ እንደማይገፋቸው ገልጿል። ልጆቹ ግን ዕድሜያችው ሲደርስ የፌስቡክ ማህበራዊ ገጽ መክፈት ቢፈልጉ እንኳ ከ'ሜሴንጀር ኪድስ' ጋር የማይያያዝ አዲስና እራሱን የቻለ እንደሚሆን ተናግረዋል። ፌስቡክ ያካተታቸው ሥዕላዊ ይዘቶች ለልጆች አዝናኝ እንደሚሆኑ ይገመታል መውደድ እራሳችንን መጠየቅ ያለብን ልጆች ከህፃንነታቸው አንስቶ ማህበራዊ ድረ-ገጾችን መጠቀም አለባቸው ወይ የሚለው ነው? የፌስቡክ ቀዳሚ ኢንቨስተርና የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ሻን ፓርከር ለማቋቋም ስላገዙት አገልግሎት አፍራሽ ሃሳቦችን አቅርበዋል። ''በልጆቻችን አዕምሮ ምን እንደሚመላስ የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው'' በማለት በፌስቡክ ላይ የምናጋራቸውን ይዘቶች ሌሎች መውደዳቸውን 'ላይክ' በማድረግ በሚያሳውቁበት ጊዜ በአዕምሮአችን ምን አይነት ስሜቶችን እንደሚፈጥርብን አስታውሰዋል። ይህ የመውደድ ወይንም 'ላይክ' የማድረግ መሣሪያ የ'ሜሴንጀር ኪድስ' ዋናው አካል ነው። ለዚህም ነው ዕድሜያቸው ከ6 ዓመት ጀምሮ ያሉ ልጆችን በዚህ መልኩ የአቻዎቻቸውን ተቀባይነት መለኪያ ማድረጉን እንደ ሕብረተሰብ ልናስብበት ይገባል ብለዋል። 'መልካሙ ሃሳብ --በፊት ላይ ' ለፌስቡክ ሥራም ጊዜያዊ የሆነ ተቀባይነት አለ። የብዙሃን ስሜትም ልጆች በድብቅ እነዚህን ማህበራዊ ድረ-ገጾች እየተጠቀሙ ስለሆነ ይህን መቆጣጠር በሚቻልበት መንገድና በማይጎዱበት ሁኔታ መመቻቸቱ ተገቢ ነው ብለዋል። ኮመን ሴንስ ሚድያ የተሰኘው የልጆችንና የቤተሰብን ሕይወት የማሻሻል ዓላማ የያዘና ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት በልጆች የሚዘወተሩ የማህበራዊ ድረ-ገጽ አጠቃቅም ላይ ጥናት አካሂዷል። ''ላይ ላዩን ወላጆች ብቻ መመዝገብ የሚችሉበት ለ13 ዓመት በታች ላሉ ልጆች ታስቦ የተዘጋጀ ጥሩ ድረ-ገጽ ነው'' በማለት የድርጅቱ ዋና አስተዳዳሪ ጄምስ ስቴየር ተናረግዋል። በመቀጠልም ''ግልጽ የሆነ የመረጃ መሰብሰቢያ ህግ ከሌለ ግን ልጆቹ የሚያጋሯቸው ይዘቶች ምን እንደሚደረጉ ስለማይታወቅ ሙሉ በሙሉ ለማመን ከባድ ይሆናል'' ብለዋል። ''ለጊዜው ይህን ገጽታውን እንወደዋለን ምክንያቱም ማስተዋወቂያ የለውም በዚያ ላይ ቁጥጥሩ ሙሉ በሙሉ በወላጆች እጅ ነው። ሆኖም ወላጆች ፌስቡክ ለልጆቻቸው በማሰብ ብቻ እንደሠራው እንዴት ማወቅ ይችላሉ?'' በማለት ይጠይቃሉ። ፌስቡክም ቢሆን አዲሱ አገልግሎት ልጆችን ተጋላጭ ስለሚያደርግ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልገው ከመግለጽ አልተቆጠበም። ለልጆች ጎጂ የሆነ ማንኛውም ይዘት በ'ሜሴንጀር ኪድስ' ላይ ቢገኝ ለፌስቡክ ትልቅ ችግር እንደሚያስከትልም ያውቃል። ዩቲየብም ለልጆች ታስቦ በተዘጋጀው 'ዩቲዩብ ኪድስ' ገጻቸው ላይ ለልጆች ጎጂ የሆኑ ይዘቶች በማምለጣቸው መቆጣጠሩ ከባድ እንደሆነ በልምድም ታይቷል። ይህ መተግበሪያ ለጊዜው በአሜሪካ ያውም የአይኦኤስ ሲስተም ላላቸው ተገልጋዮች ላይ ብቻ የቀረበው ነው።
news-51993422
https://www.bbc.com/amharic/news-51993422
የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በመቆጣጠር ረገድ አፍሪካ ከእስያ አገራት ምን ትማራለች?
በአውሮፓና በአሜሪካ በኮሮናቫይረስ የሚያዙና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ይህንንም ተከትሎ አገራት የበረራ እገዳ፣ የትምህርት ቤት መዘጋትና የእንቅስቃሴ ገደብ አስተላልፈዋል።
ከበርካታ ሳምንታት በፊት ግን ወረርሽኙ በርካታ የእስያ አገራትን አጥቅቶ ነበር። አንዳንዶቹ አገራት በቀላሉ ቫይረሱን በቁጥጥር ሥር ማዋል በመቻላቸው ተደንቀዋል። ከእነዚህም አገራት መካከል ሲንጋፖር፣ ሆንግ ኮንግ እና ታይዋን የሚገኙበት ሲሆን በአንጻራዊነት ለቻይና ካላቸው ቅርበት አንጻር ሲታይ በእነዚህ አገራት በቫይረሱ የተያዙና የሞቱ ሰዎች ቁጥር በጣም ትንሽ ነው። እነዚህ አገራት ምን የተለየ ነገር ቢያከናውኑ ነው የቫይረሱን ስርጭት በቀላሉ መቆጣጠር የቻሉት? አፍሪካ ከእነዚህ አገራትስ የምትማረው ይኖር ይሆን? ትምህርት አንድ፡ ወረርሽኙን የምር መውሰድና በፍጥነት ወደተግባር መግባት የጤና ባለሙያዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር በአንድ ድምጽ የሚስማሙበት ነገር አለ። ይኸውም በሰፊው መመርመር፣ በቫይረሱ የተያዙትን ለይቶ ማቆያ ማስገባት፣ እና ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ የሚሉት ናቸው እነዚህ ተግባራት በምዕራቡ አለም በተለያየ መጠን ተግባራዊ እየተደረጉ ቢሆንም አገራቱ ግን በፍጥነት ወደተግባር ባለመግባታቸው ይመሳሰላሉ። ለዚህም ዩናይትድ ኪንግደምንና አሜሪካን የሚጠቀሱ ሲሆን በቻይና ወረርሽኙ ከተከሰተ ሁለት ድፍን ወራት አልፎ ምንም አይነት ዝግጅት አላደረጉም ነበር ተብሏል። ሁለቱ አገራት፣ ቻይና ሩቅ መስላቸውና ቫይረሱን ሩቅ አድርገው ገምተው መዘናጋታቸው ዛሬ ለገቡበት አጣብቂኝ ዳርጓቸዋል። ቻይና የመጀመሪያው ስለበሽታው ለዓለም ጤና ድርጅት ያስታወቀችው ከፈረንጆቹ አዲስ አመት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ነበር። በዚህ ወቅት በሽታው ከሰው ወደ ሰው ስለመተላለፉ ምንም ማረጋገጫ አልተሰጠም አልተሰማምም። ነገር ግን በሶስት ቀናት ውስጥ ሲንጋፖር፣ ታይዋን፣ ሆንክ ኮንግ በድንበሮቻቸው ቫይረሱን ለመለየት የሚያስችላቸውን ምርመራ ጀመሩ። ታይዋን በአውሮፕላን ከዉሃን ወደ አገሯ የሚመጡ መንገደኞችን ከአውሮፕላን ሳይወርዱ መመርመር ጀምራ ነበር። ቀናት በጨመሩ ቁጥር ተመራማሪዎች ሰዎች የቫይረሱን ምልክት ሳያሳዩ ረዥም ጊዜ ሊቆዩ እንደሚችሉ ደረሱበት። ያም ቢሆን እነዚህ አገራት ወረርሽኙን በአጭር ቀጩት። ትምህርት ሁለት፡ ምርመራውን በርካታ ሰዎች ላይ ማካሄድና ተደራሽ ማድረግ በደቡብ ኮሪያ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች በብዛት መገኘት የጀመሩት በአንድ ጊዜ ነበር። ነገር ግን ወዲያውኑ ደቡብ ኮሪያ ምርመራ ማድረግ ጀምራለች። እስካሁን ድረስም ከ290ሺህ በላይ ሰዎችን መመርመር ችላለች። በየቀኑ በነፃ 10ሺህ ሰዎችን ትመረምራለች። ይህ የደቡብ ኮሪያ ተግባር ከተመራማሪዎችና ከባለስልጣናት አድናቆትን ተችሮታል። በተነፃፃሪ በአሜሪካ ምርመራው እጅጉን ዘግይቷል። መጀመሪያ አካባቢ የመመርመሪያ ኪቶቹ ስህተት ነበረባቸው። በርካታ ሰዎች ለመመርመር ተቸግረው ነበር። ምንም እንኳ ነፃ ምርመራ በሕግ የተደነገገ ቢሆንም ለመመርመር ግን ውድ ዋጋ ይጠየቅ ነበር። በዩናይትድ ኪንግደምም ቢሆን ሆስፒታል ታመው የመጡት ብቻ ምርመራ ይደረግላቸው ነበር። መለስተኛ ምልክት ያሳዩ የነበሩ ሕሙማን ምርመራ ለማግኘት ፈተና ሆኖባቸው ቆይቷል። በርግጥ በአንዳንድ አገራት የመመርመሪያ ኪት አልተሟላም። ቢሆንም ግን በርካታ ሰዎችን መመርመር ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን የዓለም ጤና ድርጅትም ሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች ያሰምሩበታል። አክለውም ወደ ሆስፒታል የሚመጡትን ብቻ ሳይሆን ምልክቱ የሚታይባቸውንና ለሌሎች ሊያሰራጩ የሚችሉ ሰዎችን መመርመር እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል። ትምህርት ሦስት፡ ንክኪዎችን መፈለግና ለይቶ ማቆያ ማስገባት መመርመር ብቻ በቂ አይደለም ይላሉ የጤና ባለሙያዎች። ተመርምረው ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከእነማን ጋር ንክኪ እንደነበረባቸው መለየት ወሳኝ ነው። በሲንጋፖር የወንጀል ምርመራ ባለሙያዎች የመንገድ ላይ ደህንነት ካሜራን በመጠቀም ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ከማን ጋር ግንኙነት ወይንም ንክኪ እንደነበረባቸው በመለየት ስራ ውስጥ ተሳትፈው 6ሺህ ሰዎችን አግኝተዋል። ከዚያም ምርመራ እንዲያደርጉ፣ ውጤታቸው ነፃ እስኪሆን ድረስ ራሳቸውን ነጥለው እንዲቀመጡ አድርገዋል። በሆንክኮንግ ንክኪዎችን የመለየት ተግባሩ ግለሰቡ የበሽታውን ምልክት ማሳየት ሳይጀምር ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ነው የሚካሄደው። በሆንክ ኮንግ ከሌላ አገራት የሚመጡ መንገደኞች እግራቸው ላይ እንቅስቃሴያቸውን የሚያሳይ እግረ ሙቅ እንዲያደርጉ ሲደረግ፣ በሲንጋፖር ደግሞ ራሳቸውን ነጥለው በቤት የሚቀመጡ ሰዎች በቀን ለበርካታ ጊዜያት ይደወልላቸው ነበር፣ የት እንዳሉ የሚያሳይም ፎቶ ተነስተው እንዲልኩም ይደረግ ነበር። በሲንጋፖር ቤት ራሱን ነጥሎ መቀመጥ ሲኖርበት ያላደረገ ጠበቅ ያለ ቅጣት ይጠብቀዋል። በምዕራቡ ዓለም ግን ከግለሰቦች ነፃነትና ከቆዳ ስፋታቸው አንጻር እንዲህ አይነት እርምጃን ለመተግበር አስቸጋሪ ነው። ትምህርት አራት፡ አስቀድሞ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅን ተግባራዊ ማድረግ ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር ምርጡ መላ ተድረጎ ይወሰዳል። ነገር ግን ተግባራዊ ለማድረግ በዘገዩ ቁጥር ተፈፃሚነቱን ለማረጋገጥ እጅጉን መልፋት ይጠይቃል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መነሻ ናት ተብላ የምትጠራዋ የቻይናዋ ዉሃን ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ከመጣሏ በፊት አምስት ሚሊዮን ሰዎች ከተማዋን ለቅቀው ወጥተው ነበር። ይህም መንግሥትን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቁ የተባለውን የእንቅስቃሴ ገደብ ለመጣል አስገድዶታል። ጣሊያንም ሆኑ ስፔን ከተሞቻቸውን ከእንቅስቃሴ በማቀብ ዜጎቻቸው ከቤታቸው ውልፊት እንዳይሉ ያዘዙት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በሺዎች ሲቆጠር ነው። በተቃራኒው ግን ሲንጋፖር ትምህርት ቤቶች አልተዘጉም ነበር። በርግጥ ሕዝባዊ ስብሰባዎች ተከልክለው ነበር። ሆንግ ኮንግ ትምህርት ቤቶችን የዘጋች ሲሆን ሠራተኞችም ከቤታቸው እንዲሰሩ ብታደርግም ምግብ ቤቶችና መጠጥ ቤቶች ክፍት ነበሩ። ይህ ለምን ሆነ ብለው የሚጠይቁ ቢኖሩ፣ ባለሙያዎች መልሳቸው ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅን በፍጥነት ተግባራዊ ማድረጋቸው ለዚህ ረድቷቸዋል በማለት ምላሻቸውን ይሰጣሉ። አሁን እንቅስቀሴ የገደቡ አገራት፣ ትምህርት ቤት፣ ሕዝባዊ ስብሰባ የከለከሉ መንግሥታት ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከጨመረ በኋላ በመሆኑ ከባድ እርምጃ የሚሉትን እንዲወስዱ አስገድዷቸዋል። ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ በመንግሥታት ውሳኔ ላይ የተመሰረተ ቢሆንም ዜጎች ትዕዛዙን ተቀብለው ተግባራዊ ማድረግ አለማድረጋቸውም አስተዋጽኦው የጎላ ያደርገዋል። ለዚህም ነው የሚተላለፉ መልዕክቶችና የግለሰቦች አመለካከት ወሳኝ የሚሆኑት። ትምሀርት አምስት፡ ሕዝቡ በቂ መረጃ እንዲኖረው እንዲሁም ከመንግሥት ጎን እንዲሰለፍ ማድረግ እንደ ኮሮናቫይረስ ያሉ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና በቁጥጥር ሥር ለማዋል ሕዝብን ከጎን ማሰለፍ ካልተቻለ የመንግሥት እርምጃና ፖሊሲ ከንቱ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ይላሉ የጤና ባለሙያዎች መንግሥት ፖሊሲዎች በሳይንሳዊ ማስረጃዎች ላይ የተደገፉ መሆናቸውን ማሳየት ይጠበቅበታል። ለዚህም አስረጅ አድርገው የሚያቀርቧት ቻይናን ነው። ቻይና በዉሃን የተፈጠረውን ለመሸፋፈን ሞክራ ነበር። ስለወረርሽኙ ለመናገር የሞከሩ የሕክምና ባለሙያዎችንም ቀጥታለች። በዚህ መካከል በዉሃን ትልልቅ ስብሰባዎች ተካሂደዋል። በኋላም ቫይረሱን ለመቆጣጠር ከተማዋን በሙሉ ከእንቅስቃሴ ውጪ ወደማድረግና የሕክማና ተቋማትን አቅም በፍጥነት ወደማሳደግ በመግባቷ ወረርሽኙን ልትቆጣጠር ችላለች። ይህ ሁሉ የሆነው ግን መጀመሪያ ላይ ለቫይረሱ የሰጠችው ምላሽ ዘገምተኛ በመሆኑ ነው ይላሉ። በአሜሪካም ቢሆን ስለኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ፕሬዝደንት ትራምፕ ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር በሃሳብ ይለያዩ ነበር። እንደ ሆንክ ኮንግ ባሉ የእስያ አገራት ግን ማህበረሰቡን ስለወረርሽኙ ለማንቃት ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀሙ ነበር። ደቡብ ኮሪያ ዜጎች በአካባቢያቸው በቫይረሱ የተያዘ መኖር አለመኖሩን በሞባይል አጭር መልዕክት ታሳውቅ ነበር። በሲንጋፖርም ቢሆን መረጃዎች በፍጥነት ይደርሱ ነበር። ትምህርት ስድስት፡ የግለሰቦች አመለካከት ወሳኝ ነው እሲያውያን ከመንግሥታቸው የሚመጣን ውሳኔና ትዕዛዝ ተግባራዊ ለማድረግ አያመነቱም። በሆንክ ኮንግ ዜጎች መንግሥታቸው ላይ ተቃውሞ ቢያሰሙም በአገራቸው ግን ይኮራሉ። እናም ሁሉም ወረርሽኙን እንደ ብሔራዊ አደጋ ቆጥረውት ነበር ተብሏል። ሌላው ሆንግ ኮንጋውያን በግለሰብ ደረጃ ሃላፊነት እንዳለባቸው የሚያምኑ ዜጎች መሆናቸውን የሚናገሩ ባለሙያዎች አሉ። ለዚህ ደግሞ ምክንያታቸው ከዚህ ቀደም የሳርስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ የጎዳቸው መሆኑ አንዱ ነው። በዓለም ላይ እጅን በተደገጋጋሚ በሳሙናና በውሃ መታጠብ የሚጠይቁ ወረርሽኞች ተከስተው ያውቃሉ የሚሉት ባለሙያዎቹ በቅርብ ጊዜ የተከሰተው ኢቦላን በመጥቀስ ትልቁ ፈተና የነበረው ዜጎች እጃቸውን በተደጋጋሚ እንዲታጠቡ ማድረግ እንደነበር ያስታውሳሉ። ግለሰቦች የሚወስኑት ውሳኔ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን አብረዋቸው የሚኖሩና ለሌሎችም የሞት የሽረት ጉዳይ ይሆናል ሲል የዓለም ጤና ድርጀት ማስጠንቀቁ ይታወሳል። ይህ ሁሉ እርምጃ ተወስዶም ቢሆን ግን የዓለም ዜጎች ልባቸው እርፍ የሚለው ክትባት ሲገኝ ብቻ ይመስላል። ለእርሱ ደግሞ 18 ወራት መጠበቅ ግድ ነው። ለረዥም ጊዜ ከተሞችን እንቅስቀሴ አልባ አድርጎ መቀመጥ ዜጎች እንዲሰላቹ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የአገራትንም ምጣኔ ሀብት ያሽመደምዳል። ስለዚህ ከእስያ አገራት በመማር የባህሪ ለውጥ ማምጣትና በሕክምና ባለሙያዎችና በዓለምጤና ድርጅት የሚሰጡ ምክሮችን ተግባራዊ ማድረግ ራስን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል ወሳኝ ነው።
news-48878891
https://www.bbc.com/amharic/news-48878891
ማክስ 737፡ «ቤተሰቦቼን በኢትዮጵያው አውሮፕላን አደጋ አጥቻለሁ»
«ባለቤቴ ካሮልን አጥቻለሁ፤ ሦስት ልጆቼ ራያን፣ ኬሊንና ሩቢንን አጥቻለሁ። እንዲሁም የባለቤቴን እናትም አጥቻለሁ፤ ብቸኝነት ይሰማኛል። በተለይ ሰዎችን ሳይ. . . ከልጆቻቸው ጋር የሚጫወቱ ወላጆችን ሳይ. . . እኔ ከልጆቼ ጋር መሆን አለመቻሌን ሳስብ። ድምፃቸውን መስማት፤ ፊታቸውን ማየት አለመቻሌን ሳስብ።»
ፖል ንጆሮጌ፤ ሙሉ ቤተሰቡን ያጣው በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር 302 ማክስ 737 አውሮፕላን መከስከስ ሳቢያ ነው። አደጋው በአጠቃላይ የ157 ሰዎችን ሕይወት ቀጥፏል። • የኢቲ 302 የመጨረሻዎቹ ስድስት ደቂቃዎች ፖል አሁን ከጓደኛ ጓደኛ ቤት እየተዟዟረ ይኖራል፤ ወደ ቤቱ መመለስ አልቻለምና። የልጆቹን ጫማ እንኳ ማየት እንደተሳነው ይናገራል። «እግሮቻቸው ይታዩኛል። እኔ ተመልሼ ወደዚያ መሄድ አልችልም» ይላል ዘመዶቹ ቁሳቁሶቹን ሰብስበው እስኪወስዱለት የሚጠብቀው ፖል። • ቦይንግ "ችግሩ ተፈቷል" እያለ ነው ሰበበኛው ቦይንግ ማክስ 737 በአምስት ወር ጊዜ ውስጥ ነው ሁለት ጊዜ ነው የተከሰከሰው። የመጀመሪያው ኢንዶኔዥያ ውስጥ፤ ጥቅምት 2011 ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ቢሾፍቱ አቅራቢያ መጋቢት 2011 ነው። የሁለቱም አደጋዎች የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት የአደጋው መንስዔ ተመሳሳይ እንደሆነ ያሳያል። አሁን የአደጋው ተጎጂ ቤተሰቦችም ሆኑ ሌሎች አንድ ጥያቄ ሰቅዞ ይዟቸዋል። ለምንድነው አውሮፕላኑ ችግር እንዳለበት ከታወቀ በረራ እንዳያደርግ ያልታገደው? የሚል። የፖል ንጆሮጌ ሶሰት ልጆች፣ ባለቤቱና እናቷ ክሪስ እና ክላሪስ ሙርም ልጃቸው ዳንኤሌን ያጡት በኢትዮጵያ አየር መንገዱ አውሮፕላን አደጋ ነው። ቶሮንቶ በሚገኘው ቤታቸው አንድ ክፍል ውስጥ የልጃቸው ፎቶ በአበባ ተከብቦ ይታያል። ልጃቸው ዳንኤሌ ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ስትበር የነበረው ናይሮቢ በሚካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ጥበቃ ጉባኤ 'ኢንቫይሮንመንት ኮንፈረንስ' ላይ ለመሳተፍ ነበር። የዳንኤሌ ቤተሰቦች ይናገራሉ፤ «ይህ ሊሆን ባልተገባ ነበር። ኢንዶኔዥያ ላይ ከደረሰው አደጋ አምስት ሙሉ ወር እንኳ ሳይሞላው. . . ደግሞ በጣም ደህንነቱ የተጠበቀ ይሉናል። በፍፁም አይደለም። የምንወዳቸውን ሰዎች ሕይወት የቀጠፈ ነው። ምንም ይበሉ ምንም ሕይወታችን እንደ ቀደመው ጊዜ ሊሆን አይችልም። • ''አብራሪዎቹ ትክክለኛው መመሪያ ተከትለዋል'' ምንም እንኳ የሁለቱም አደጋዎች መንስዔ ከአውሮፕላኑ ጋር የተያያዘ መሆኑ ቢጠቆምም የአሜሪካ ምክር ቤት አባል የሆኑት ሳም ግሬቭስ «ፓይለቶቹ አሜሪካ ቢሠለጥኑ ኖሮ. . .» ሲሉ ጣታቸውን ኢትዮጵያውያን አብራሪዎች ላይ ቀስረዋል። «ቤተሰቦቼን ያጣሁት በቦይንግ ቸልተኝነት፣ እብሪተኝነት እና አስተዳደራዊ ዝቅጠት ነው። የአሜሪካ አቪዬሽን አስተዳደርም [ኤፍኤኤ] ቢሆን አወሮፕላኑን በሥርዓቱ መፈተሽ ነበረበት» ይላል ፖል። «ምክንያቱም ዕድሉ ነበራቸው። የኢንዶኔዥያው አደጋ ሲደርስ አውሮፕላኑን ከበረራ ማገድ ነበረባቸው። የእኔን ቤተሰቦች ጨምሮ 157 ሰዎች በእነርሱ ደካማ አሰራር ሳቢያ ሞቱ። ሰው በእነዚህ አውሮፕላኖች እየበረረ ሳለ ነው ችግሩን ለመቅረፍ የሞከሩት። ግን ምን ዋጋ አለው የመጋቢቱ አደጋ ደረሰ።» ናዲያ ሚሌሮን እና ባለቤቷ ሚካኤል ስቱሞ በአሜሪካዋ ማሳቹሴትስ ግዛት ነዋሪ ናቸው፤ ሥፍራው ሰላም የተመላ ነው፤ አረንጓዴ ቦታ። የ24 ዓመቷ ልጃቸው ሳምያ ሮዝ መጋቢት 1/2011 ዕሁድ ጠዋት 3፡00 ገደማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በረራ ቁጥር ኢቲ 302ን ተሳፈረች። • ቦይንግ ተከሰሰ፤ ሰለአደጋው ተጨማሪ መረጃዎች እየወጡ ነው «በጣም አስፈሪ ህልም ይመስላል. . . ትላለች እናቷ ናድያ፤ ሁሌም አንድ ቀን ከህልሜ እንደምነቃ አስባለሁ።» ናድያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን መክሰከስን ዜና የሰማችው ከቢቢሲ ራድዮ ጣብያ ነበር። ልጇ ሳሚያ በዚያ አውሮፕላን ውስጥ እንዳለችም ታውቃለች። ልጇ ከመሳፈሯ አንድ ሰዓት ቀደም ብላ ስለ አውሮፕላኑ ዓይነት በዋትስአፕ ነግራታለች። «ዜናውን ስሰማ ያንቀጠቅጠኝ ጀመር። ሰወነቴ ሲንቀጠቀጥ ይሰማኛል ቢሆንም ልቆጣጠረው ተሳነኝ። ዜናውን ቤት ውስጥ ለነበሩ ሰዎች መናገር ተሳነኝ።» ናዲያ ሚሌሮን እና ባለቤቷ ሚካዔል ስቱሞ ልጃቸውን በኢትዮጵያ አየር መንገዱ አውሮፕላን አደጋ አጥተዋል። ቦይንግ ትርፍን ማስቀደሙ ነው ለዚህ የዳረገን ሲሉም ይወቅሳሉ ናዲያ ሚሌሮን እና ባለቤቷ ሚካኤል ስቱሞ የአሜሪካ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት አባላትን እያገኙ "ለምን ይሆን ከመጀመሪያው አደጋ በኋላ ማክስ 737 ከበረራ ሊታገድ ያልተፈለገው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ተቺዎች ማክስ 737 የተሰኘው የቦይንግ አውሮፕላንን ወደ ገበያ ለማውጣት ጥድፊያ ነበረ ሲሉ ይወቅሳሉ። ኤርባስን ከመሳሰሉ የአውሮፕላን አምራች ኩባንያዎች ጋር ለመፎካከር ሲል ነው ጥድፍያ ያበዛው፤ የባለሙያዎች ትችት ነው። ቢቢሲ ቦይንግ እየደረሰበት ስላለው ወቀሳ ምላሽ አለው ብሎ ቢጠይቅም ድርጅቱ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥቧል። • 'መጥፎ ዕድል' አውሮፕላኑ የወደቀበት ስፍራ ስያሜ እንደሆነ ያውቃሉ? ቦይንግ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች 100 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ ያለውም በዚህ ሳምንት ነበር። ቢቢሲ ያነጋገራቸው የተጎጂ ቤተሰቦች የቦይንግን ልገሳ እንደማይቀበሉ ነው የሚናገሩት። ክሪስ ሙር ቦይንግ በወንጀል ሊከሰስ ይገባል ይላሉ፤ ፖል ንጆሮጌ የቢሺፍቱውን አደጋ ሊከላከሉት የሚገባ ነበር ይላል። ሰሚ ያላገኙ እና ቤታቸውን ዘግተው በማዘን ላይ ያሉትን ጨምሮ፤ የተጎጂ ቤተሰቦች አሁንም ጥያቄ እንዳዘሉ ናቸው።
news-47975295
https://www.bbc.com/amharic/news-47975295
ሻሚማ ቤገም፡ ሴቶች የሽብር ምስጢራዊ መሳሪያ ለምን ሆኑ?
ከሽብርተኝነት ጋር በተገናኘ ሴቶች የዜና አካል ሲሆኑ በአብዛኛው የዜናው ትኩረት የሚሆነው ሴቶች ተጎጂዎች አሊያም ተባባሪዎች እንደሆኑ ተደርጎ ነው። በአንፃሩ ሽብርተኝነትን የሚደግፉ አሊያም እጃቸው ያለበት ሴቶች ጎልተው አይወጡም።
ሻሚማ ቤገም እ.አ.አ 2015 እንግሊዝን ለቃ ስትወጣ የ15 ዓመት ታዳጊ ነበረች ነገርግን በአስራዎቹ የእድሜ ክልል የምትገኘው ሻሚማ ቤገም የእስላማዊ ታጣቂ ቡድኖች ምልክት ሆና መውጣት ከጀመረች አንስቶ ይህ እየተለወጠ መጥቷል። • “ኢትዮጵያ አዲስ የጥላቻ ንግግር ህግ አያስፈልጋትም” አቶ አብዱ አሊ ሂጂራ ሻሚማ ከሁለት ጓደኞቿ ጋር በመሆን የእስላማዊ ቡድኑን ( አይ ኤስ) የተቀላቀለችው ከአራት ዓመታት በፊት ነበር። እርሷ እንደምትለው በወቅቱ የቤት እመቤት ነበረች። ቢሆንም ግን የእንግሊዝ ባለስልጣናት "ተመልሰሽ ከመጣሽ፤ አደጋ ሊገጥምሽ ይችላል" ሲሉ የእንግሊዝ ዜግነቷን እንደተነጠቀች ከተናገሩ በኋላ ውሳኔውን ለማስቀየር የህግ ድጋፍ ለማግኘት አቤቱታዋን አሰምታለች። ሴቶችና ሽብርተኝነት የሻሚማ ቤገም ጉዳይ ሴቶች በሽብርተኝነትና በእስላማዊ ታጣቂ ቡድን ውስጥ በንቃት መሳተፋቸውን በተመለከተ በርካታ ጥያቄዎችን አስነስቷል። የጥናት ተቋሙ ሩሲ ያካሄደው ጥናት እንደሚያመላክተው 17 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች የሚመለመሉት ከአፍሪካ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ የእስላማዊ ታጣቂ ቡድን በኢራቅና በሶሪያ በሚያካሂዳቸው የውጪ ምልመላወቹ 13 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸው በሌላ ጥናት ተገልጿል። ሌሎች የሚወጡ በርካታ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ጉዳዩ የተወሳሰበና ቁጥሩም ከዚህም ሊልቅ ይችላል። ከአራት ዓመታት በፊት ሻሚማ ቤገም (በቀኝ በኩል) ከሁለት ጓደኞቿ አሚራ አባሴ እና ካዲዛ ሱልታና በጋትዊክ አየር መንገድ የጥናት ማዕከሉ ሩሲ የቀደሙ ጥናቶች እና ሌሎች ምርምሮች በአፍሪካ ለበርካቶች ሕይወት መጥፋት ተጠያቂ በሆኑት በአል ሻባብ እና በእስላማዊው ቡድን (አይ ኤስ) ውስጥ ሴቶች ያላቸውን ሚና መርምረዋል። በአል ሻባብ እንቅስቃሴዎች በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፈችን አንዲት ሴት ቃለ መጠይቅ ያደረጉት አጥኝዎች፤ ሴቶቹ እንዴት እንደሚመለመሉና ጥቃቶች ላይ መሳተፋቸው በሴቶቹ በራሳቸው ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ መለየት ችለዋል። • ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ? ጥናቱ የተሰራው በኬንያ በሚገኝ የትምህርት ተቋም ሲሆን ድርጅቱ የእነርሱን ልምድና ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን ትስስር በማየት ለእንደዚህ አይነት አደጋዎች የሚያጋልጡ ምክንያቶችን ለመለየትና ለመቀነስ ይሰራል። አይ ኤስ እና አል ሻባብ በሁለቱ የሽብር ቡድኖች የሴቶች ሚና የተለያየ ነው። በአል ሻባብ ውስጥ ያሉ ሴቶች በአብዛኛው በተለመደና ባህላዊ በሆነ መንገድ ሚስት በመሆን፣ አጥፍቶ ጠፊ አሊያም በቤት ውስጥ ሥራ በመስራት የሚሳተፉ ሲሆን አንዳንዴም የወሲብ ባሪያ ይደረጋሉ። እነዚህ ሴቶች ሌሎች አዳዲስ አባላትን ለመሳብ ይረዳሉ። በኬንያ የተሰራ አንድ የጥናት ግኝት እንዳመለከተው ሴቶች በሌሎች ይሳቡ የነበሩት የሥራ እድል እንደሚያገኙላቸው ቃል ስለሚገቡላቸው፣ በገንዘብ እርዳታና በሚሰጧቸው የምክር አገልግሎት ነበር። ለምሳሌ ሂዳያ (እውነተኛ ስሟ አይደለም) ልብስ ሰፊ ስትሆን የንግድ ሥራዋን እንደሚያስፋፋላት ቃል በገባላት አንድ ጓደኛዋ አማካይነት ነበር የሽብር ቡድኑን የተቀላቀለችው። ከዚያም ከምትኖርበት ቦታ ወደ ሶማሊያ አመራች። በኤይ ኤስ በኩል ግን ብዙ ጊዜ ሴቶች የሚመለመሉት በአብዛኛው በኢንተርኔት (ኦን ላይን) ሲሆን የቡድኑን እምነትና አቋም በማንፀባረቅ በእንቅስቃሴያቸው ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋሉ። • የተነጠቀ ልጅነት እዚህ ላይ የሻሚማን ጉዳይ ማንሳት ይቻላል። የእርሷ መመልመል በአይ ኤስ በኩል የፕሮፓጋንዳቸው አንድ ድል ተደርጎ ይቆጠራል። በአንዳንድ ቅድመ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ቢሆንም በአይ ኤስ ውስጥ ያሉ ሴቶች እንደ ዶክተርና የጤና ባለሙያዎች ሆነው ያገልግላሉ። ለቡድኑ በጠቅላላ የሞራል ድጋፍ የሚሰጡ ኃይል ሆነውም ይሰራሉ። በቅርቡ ቡድኑ በኢራቅና በሶሪያ ያለውን ግዛት ሲያጣ ሴቶችን በግምባር ቀደምትነት አሰልፎ ነበር። ቡድኑ 'አል ናባ' በሚለው ጋዜጣውም ለሴቶቹ የጅሃድ ጥሪን አቅርቦላቸዋል። ባለፈው ዓመትም በሶሪያ ይህንኑ ሲያደርጉ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስልም ተለቋል። ምንም እንኳን በቡድኑ ውስጥ የሚታዩ ልዩነቶች የድርጅቱን ገፅታ ቢያጠለሹትም አንዳቸው ባንዳቸው እየተበረታቱ ቀጥለዋል። አል ሻባብ በሸሪዓ የሚተዳደር እስላማዊ መንግሥት ለመመስረት በሚሞክርበት ሶማሊያ፤ ሴቶች ፊት አውራሪ ሆነው ሲታገሉና በአጥፍቶ መጥፋት ሲሳተፉ ታይተዋል። • አይ ኤስን ተቀላቅላ የነበረችው እንግሊዛዊት ዜግነቷን ልትነጠቅ ነው በአል ሻባብ የተፈጸሙ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ላይ የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው ከአውሮፓውያኑ 2007 እስከ 2016 ድረስ ከተፈጸሙ ጥቃቶች መካከል 5 በመቶ የሚሆኑት የደረሱት በሴቶች ነው። የቦኮ ሃራም እስላማዊ ቡድን ተንሰራፍቶ ባለባቸው እንደ ናይጀሪያ ያሉ ሌሎች የአፍሪካ አገራትም የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃቶች ለማድረስ ሴቶችን ይጠቀሙባቸዋል። ሴቶች የጂሃዳዊ ቡድኖችን ለምን ይቀላቀላሉ? ጥናቶች እንደሚያስረዱት ሴቶቹ ለእነዚህን ቡድኖች እንዲመለመሉ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች አሉ። ወንዶች የቡድኖቹ አባል ለመሆን የሚያነሳሳቸው ፅንፍ ያለው ርዕዮተ ዓለምና የገንዘብ ማግኛ ምንጭ የመሆኑ ምክንያት ለሴቶችም ይሰራል። ይሁን እንጂ በተለየ መልኩ ሴቶች ቡድኑን እንዲቀላቀሉ የሚያደርጉ ምክንያቶች አሉ፤ ከእነዚህም መካከል ሴቶች ፆታን መሰረት ባደረጉ ሚናዎች መታለላቸው ነው። • በአንድ ቤተሰብ አባላት የተቀነባበረው የሽብር ጥቃት አንድ ጥናት እንዳመለከተው አል ሻባብ ወጣት ሙስሊም ሴቶች በትምህርታቸው እየገፉ ሲሄዱ የጋብቻ ሁኔታቸውን እንደሚያጓትትባቸው በመንገር ያግባቧቸዋል። "የሚያገባኝ፣ የሚጠብቀኝና የሚንከባከበኝ ባል ካገባሁ ለምን ራሴን በትምህርት አጨናንቃለሁ?" ስትል የናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነች አንዲት ሴት አጥኝዎቹን ጠይቃቸው እንደነበር በምሳሌነት ቀርቧል። ሌሎቹ ደግሞ ሥራ፣ ገንዘብና ሌሎች እድሎችን ለማግኘት ሲሉ ወደ ቡድኑ ይሳባሉ። ምንም እንኳን ቡድኑን መቀላቀላቸው አደገኛ መሆኑን ቢያውቁም አንዳንዶቹ ካለፈቃዳቸው ይመለመላሉ። ልክ እንደ ሻሚማ ቤገም ሁሉ በቡድኖቹ ውስጥ በንቃት እንደማይሳተፉ ቢናገሩም ያለፈቃዳቸው የሚያደርጓቸው ነገሮች ነበሩ፤ በመሆኑም አንዳንዶቹ ራሳቸውን እንደ ተጠቂ እንጂ እንደ ሽብርተኛ ቡድን አባል አድርገው አይቆጥሩም። አንዳንዶቹ ደግሞ በአንዳንድ ጉዳዮች ፈቃደኛ እንዳልነበሩ በመግለፅና የነበራቸውን ኃላፊነት በመካድ ከማህበረሰቡ ጋር ዳግም ለመቀላቀል ምክንያት አድርገው ይጠቀሙበታል። የተሃድሶ መንገዶች ከዚህ ቀደም አባል የነበሩትም ሆኑ አሁን የተመለሱ ጥቃት አድራሾች ከድርጊታቸው ሊመለሱ የሚችሉባቸው የተሃድሶ ዘዴዎች አሉ። አብዛኞቹ በሴቶች ላይ ትኩረት ያደርጋሉ። የህግ እንዲሁም የፀጥታና ደህንነት አካላት ቀድሞ ለመከላከል፣ ለተሃድሶና፣ መልሶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመቀላቀል የሚያስችሉ ህጎችን ሲያረቁ ሴቶች የሽብር ቡድኖችን ጥለው የወጡበትን ምክንያት በውል ሊረዱ ይገባል። • "ኢትዮጵያ የከሸፈች ሀገር እየሆነች ነው" ሻለቃ ዳዊት ለምሳሌ፣ አንዳንዶቹ የት እንዳሉ የማይታወቁ አሊያም የሞቱ ልጆች አሏቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በደረሰባቸው የመደፈር ጥቃትና ወሲባዊ ትንኮሳ የአዕምሮ ጤና ችግር ስላጋጠማቸው የምክር አገልግሎት ያስፈልጋቸዋል። ሴቶች አፍራሽ በሆነው የሽብርተኛ ቡድን ያላቸውን ሚና አስመልክቶ መንግሥታት በትኩረት ሊከታተሉት ይገባል። ይህ የሚጀምረውም የሥርዓተ ፆታ ልዩነትን በመረዳትና በሽብር ቡድኖች ውስጥ ሴቶች ያላቸው ተሳትፎና በራሳቸው ላይ ለሚመጣው ጉዳት ነዳጅ ሆኖ እያገለገለ እንደሆነ መረዳት ያስፈልጋል። ይህ ደግሞ አደጋዎችን ለመከላከልና የሽብር ቡድኑን የሚቀላቀሉ ሴቶችን ቁጥር ለመቀነስ ይረዳል።
43130780
https://www.bbc.com/amharic/43130780
ለጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ቦታ ዓይኖች በእነዚህ ሰዎች ላይ ናቸው
ያሳለፍናቸው ሁለት ወራት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታን ይዘው አልፈዋል። በኦሮሚያ ክልል ውስጥ ጠንካራ የሚባል የቤት ውስጥ መቀመጥ አድማ ተከናወነ። በቀጣዮቹ ቀናት በሽብር ወንጀል የተከሰሱና ተፈርዶባቸው የነበሩ ፖለቲከኞች እንዲሁም ጋዜጠኞችም ተፈቱ፤ ለጥቆም ጠቅላይ ሚንስትሩ የስልጣን ልልቀቅ ጥያቄያቸውን አቀረቡ፤ ተከትሎም አነጋጋሪ የሆነው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታወጀ።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ተሰናባቹን ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝን ማን ይተካቸዋል የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪነቱ እንደቀጠለ ነው። በርካቶችም በማህበራዊ የትስስር ዘፌዎች እና መገናኛ ብዙሃን ላይ ጠቅላይ ሚንስትሩን ሊተኳቸው ይችላሉ የሚሏቸውን ሰዎች ሲጠቅሱ ቆይተዋል። ማዕከላዊ ስብሰባውን አጠናቆ ወደ ምክር ቤት ስብሰባ የዘለቀው ኢህአዴግ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ከባድ የሚባሉ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል። 180 አባላት ያሉት ይህ ምክር ቤት ከሚወያይባቸው አበይት አጀንዳዎች አንዱ የፓርቲውን ሊቀ-መንበርና ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያምን የሚተካ መሪ መምረጥ ነው። የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 73 ንዑስ አንቀጽ 1 ስለ ጠቅላይ ሚንስትሩ አሰያየም በግልጽ እንደሚያትተው፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት መካከል ይመረጣል። ሊመረጥ የታሰበው ግለሰብ ግን የምክር ቤቱ አባል ካልሆነ፤ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ቦርድ ሟሟያ ምርጫ እንዲያካሂድ ከጠየቀ በኋላ፤ ዕጩውን ግለሰብ በሟሟያ ምርጫው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ሆኖ መመረጥ አለበት። ተሻሽሎ በወጣው የኢትዮጵያ የምርጫ ህግ አዋጅ ቁጥር 532/1999 ዓ.ም መሰረት የሟሟያ ምርጫ የሚካሄደው፤ በየደረጃው ያሉ የምክር ቤቶች በተለያየ ምክንያት የተጓደሉባቸውን አባላት እንዲሟሉላቸው ለምርጫ ቦርዱ ጥያቄ ሲያቀርቡ ወይም በሕጉ መሰረት የቀረበ የይውረድልን ጥያቄ ተቀባይነት ሲያገኝ ነው። ቦርዱም ጥያቄው በደረሰው በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ የሟሟያ ምርጫ ያካሂዳል። ማሟያ ምርጫ ማለት በይውረድልን ወይም በማንኛውም ምክንያት በየደረጃው የሚገኙ የተጓደሉ የምክር ቤት አባላት መቀመጫዎችን ለማሟላት የሚካሄድ ምርጫ ማለት ነው። ጠቅላይ ሚንስትሩን ለመተካት የሚታጨው ግለሰብ ግን የምክር ቤት አባል ከሆነ በተለመደው የኢህአዴግ አሰራር መሰረት፤ የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሂዶ ሊቀመንበሩን ከመረጠ በኋላ፤ ሊቀመንበሩን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በማቅረብ በጠቅላይ ሚንስትርነት እንዲሰየም ይደረጋል። ሰሞኑን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገፆች ላይ በተደጋጋሚ ስማቸው እየተጠቀሰ የሚገኙት ሰዎች የሚከተሉት ናቸው። እነዚህ ግለሰቦች እነማን ናቸው? አጭር የሕይወት ታሪካቸውን እንደሚከተለው ቀርቧል። ስማቸው የተዘረዘረው በእንግሊዝኛ የፊደላት ቅደም ተከተል መሰረት ነው። ዶክተር አብይ አህመድ ዶክተር አብይ አህመድ በአጋሮ ከተማ የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ አግኝተዋል። ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ ሰርተዋል። በግሪንዊች ዩኒቨርሲቲ እና በሊደርሺፕ ተቋም ደግሞ የሥራ አመራር ሳይንስ አጥንተዋል። እንዲሁም አሽላንድ ዩኒቨርሲቲ በንግድ አስተዳደር ሁለተኛ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሰላም እና ደህንነት ጥናት ፒኤችዲ አላቸው። በመጀመሪያ 40ዎቹ የሚገኙት ዶክተር አብይ ኦህዴድን የተቀላቀሉት በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ነው። ከፖለቲካ ተሳትፏቸው በተጨማሪ በወታደራዊ ጉዳዮች ሰፊ ተሳትፎ የነበራቸው ሲሆን የሌተናል ኮሎኔል ማዕረግ አላቸው። በተባበሩት መንግሥታት የስላም ማስከበር ተልዕኮን ለማስፈጸም ሩዋንዳ ዘምተዋል። ከ2000 እሰከ 2003 የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ መስራች እና ዳይሬክተር በመሆነ አገልግለዋል። ከዚያም የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚንስትር በመሆን ሰርተዋል። ከ2002 ጀምሮ የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩ ሲሆን፤ ከ2007 ጀምሮ ደግሞ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪ ላለፉት ሦስት ዓመታት የኢህአዴግ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ። የኦህዴድ ሊቀ-መንበር ሆነው በቅርቡ የተመረጡት ዶክተር አብይ በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው። ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በትግራይ ሽረ ወረዳ ነው የተወለዱት። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከተቀላቀሉ በኋላ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ትጥቅ ትግል ገብተዋል። በትጥቅ ትግል ወቅት ወደ ጣልያን አገር በመሄድ በመገናኛ ቴክኖሎጂ ስልጠና የወሰዱ ሲሆን፤ በ1972 ዓ.ም የህወሓት ሬድዮ ጣብያ ድምፂ ወያነን አቋቁመዋል። ኢህአዴግ ስልጣን ላይ ሲወጣ የደህንነት መ/ቤቱን ይመሩ የነበሩት የአቶ ክንፈ ገብረ መድህን ምክትል ሆነውም አገልግለዋል። ቀደም ሲል ያቋረጡትን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ተከታትለው የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ ተቀብለዋል። እንዲሁም ደግሞ የዶክትሬት ድግሪያቸውን ከዩኒቨርሲቲ ኦፍ ለንደን አግኝተዋል። ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የኢንፎርሜሽንና ኮምዩኒኬሽን ልማት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን፤ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ማዕረግ የክላስተር አስተባባሪ ሆነውም ሰርተዋል። በአሁን ሰዓት የህወሓት ሊቀመንበር፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደርነት የትግራይ ክልልን እንዲሁም የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ሚንስትር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ። ዶክተር ደብረፅዮን በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው። ደመቀ መኮንን በ1980 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በባዮሎጂ ትምህርት ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ተቀብለዋል። ከዚያም ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በግጭት አፈታት አጠናቀዋል። በ1980ዎቹ መጀመሪያ ኢህአዴግን የተቀላቀሉት አቶ ደመቀ፤ ከጥቂት ዓመታት በኋላ የአማራ ክልል ምክር ቤት ተመራጭ ሆነው ነበር። በ1997 የአማራ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የተመረጡ ሲሆን፤ በቀጣዩም ዓመት የብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ሆነው ተመርጠዋል። አቶ ደመቀ መኮንን የብአዴን ሊቀመንበር ሲሆኑ በኀዳር 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ምክትል ሊቀምንበር ሆነው ከተመረጡበት ጊዜ ጀምሮ በምክትል ጠቅላይ ሚንስትርነት እያገለገሉ ይገኛሉ። የቀድሞው መምህር ወደዚህ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት የትምህርት ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል። አቶ ደመቀ መኮንን በአሁኑ ጊዜ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ናቸው። አቶ ለማ መገርሳ አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ሊቀመንበር በመሆን አገልግለዋል፤ አሁን ደግሞ ምክትል ሊቀ-መንበር እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ናቸው። በአርባዎቹ መጨረሻ ላይ እንደሚገኙ የሚነገርላቸው አቶ ለማ፤ ትውልድ እና እድገታቸው ምስራቅ ወለጋ ነው። ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካል ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመጀመሪያ ዲግሪ ያገኙ ሲሆን በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ ሁለተኛ ዲግሪያቸውንም ከዚያው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት በኦሮሚያ ህዝባዊ ተቃውሞ በበረታበት ወቅት ነበር የኦህዴድ ሊቀመንበር እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሆነው የተመረጡት። አቶ ለማ በ1980ዎቹ መጀመሪያ ላይ ኦህዴድን የተቀላቀሉ ሲሆን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ከመሆናቸው በፊት የክልሉ ምክር ቤት - የጨፌ አፈጉባኤ ነበሩ። አቶ ለማ መገርሳ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት-ጨፌ አባል ሲሆኑ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ግን አይደሉም። ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የኦህዴድ ምክትል ሊቀመንበር እና የኢፌዴሪ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ናቸው። የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን በፖለቲካል ሳይንስ እና በውጪ ግንኙነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አጠናቀዋል። ከሁለት ዓመታት በፊት ከደቡብ አፍሪካ ዩኒቨርሲቲ በፖሊስ ሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪን አግኝተዋል። 1960ዎቹ መጀመሪያ ላይ የተወለዱት ዶክተር ወርቅነህ ለረጅም ዓመታት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሸነር በመሆን አገልግለዋል። ከ2004 ጀምሮ የትራንስፖርት ሚንስትር በመሆን ለአራት ዓመታት ሰርተዋል። ከ1980ዎቹ መጀመሪያ አንስቶ የኦህዴድ አባል የነበሩት ዶክተር ወርቅነህ፤ ከ2004 ጀምሮ የኦህዴድ እና የኢህዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው። ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት አባል እንጂ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አይደሉም። ተጨማሪ ምንጮች፡ ቢቢሲ ሞኒተሪንግ፣ Historical Archives
news-47819867
https://www.bbc.com/amharic/news-47819867
የ737-8 ማክስ መከስከስ ለቦይንግ ምን ማለት ነው?
በአቪዬሽን ዓለም ሃያል የሆነው ቦይንግ ከባድ ቀውስ ውስጥ ይገኛል።
ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኑ ላይ ያሻሻለው ሲስተም ለኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኑ አደጋ ምክንያት መሆኑን የሚያሳየው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት በመርማሪዎች ከተረጋገጠ ነገሩ ለቦይንግ ትልቅ ፈተና ይሆናል። • ጄፍ ቤዞስ በ35 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ትዳሩን ለማፍረስ ተስማማ የዚህኛው አውሮፕላን አደጋ መንስኤ ከአምስት ወራት በፊት ከተከሰከሰው ከላየን አየር መንገዱ ማክስ አውሮፕላን ጋር እየተመሳሰለ መሆኑ ደግሞ በቦይንግ ላይ ነገሮችን ይበልጥ ያከብዳል። የሁለቱ ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ ምርመራ ሳይጠናቀቅ ገና የቦይንግ ችግሮች አንድ አንድ እያሉ እተደራረቡ ነው። ችግሩ ያለው የት ነው? የአውሮፕላኑን አፍንጫ ወደ ታች በመድፋት የአደጋው ምክንያት ሆኗል እየተባለ ያለው ቦይንግ በአውሮፕላኑ ላይ ያሻሻለው ስርዓት ነው። ይህ ስርዓት የሚሰራው በማክስ አውሮፕላኖች ከፊት ለፊት በአንድ በኩል ከሚገኝ ምልክት ሰጭ (ሴንሰር) በሚያገኘው መረጃ ላይ ተመስርቶ ነው። የላየኑ አየር መንገድ አውሮፕላንም በዚህ መልኩ በሄደ የተሳሳተ መረጃ አፍንጫው ወደ ታች እየተደፋ በተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች መከስከሱ ተገልጿል። ጥቁሩ ሳጥን፤ በአውሮፕላኖች ላይ የሚደርስ አደጋን ለሚደረግ ምርመራ ጠቃሚ መረጃን የሚይዝ ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ነው። እስከ አሁን ማስረጃዎች እንደሚያሳዩት የኢትዮጵያ አየር መንገዱ አውሮፕላን አደጋም በተመሳሳይ ምክንያት የደረሰ ነው። በተነሱ በደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሱት የላየንና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች አፍንጫ በተደጋጋሚ ከቁጥጥር ውጭ ወደ ታች ሲል እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። የሁለቱም አውሮፕላኖች አብራሪዎች አውሮፕላኑን ቀና ለማድረግ ቦይንግ ያስቀመጠውን መመሪያ ቢተገብሩም አውሮፕላኖቹን መታደግ አልቻሉም። የቦይንግ 737 የቴክኒክ መመሪያ አዘጋጅ የሆኑት ካፒቴን ብራዲ በሁለቱ አውሮፕላኖች አደጋ ዙሪያ እያጠነጠነ ያለው ነገርና ውዝግብ ሊታዩ የሚገባቸው ዝርዝር ጉዳዮች መኖራቸውን ያመለክታል ይላሉ። ዝርዝር ጉዳዮች የሚሏቸው የአውሮፕላኑ የበረራ ብቃት፣ የአደጋ ተጋላጭነት፣ ቁጥጥር፣ አጠቃለይ ስልጠና፣ የፓይለቶች ማሰልጠኛ መመሪያ የመሰሉትን ያካትታል። የቦይንግ ቀጣይ የህግ ፈተናዎች? በአሁኑ ወቅት ቦይንግ ላይ የተለያዩ ምርመራዎች እየተካሄዱ ሲሆን ሁለት ክሶችም ተመስርተውበታል። ሌሎች ክሶችም ይቀጥላሉ ተብሎ ይገመታል። የመጀመሪያው ክስ የተመሰረተው በተደጋጋሚ ለአሜሪካ ፕሬዘዳንትነት በተወዳደሩትና በአደጋው የ24 ዓመት የቅርብ ዘመዳቸውን ባጡት ራልፍ ናደር ነው። • ኬንያውያን የኢትዮጵያ አየር መንገድንና ቦይንግን ሊከሱ ነው ባለፈው ሳምንት ደግሞ ከመንገደኞች ውስጥ አንዱ የነበረው ሩዋንዳዊ ጃክሰን ሙሶኑ ቤተሰቦች በችካጎ ቦይንግ ላይ ክስ መስርተዋል። የክሱ ጭብጥም ቦይንግ ያሻሻለው ስርዓት እንከን ያለው መሆኑን ያስቀምጣል። ቦይንግ ምን እያደረገ ነው? ቦይንግ መጀመሪያ ለማክስ አውሮፕላን እንዲሁም አውሮፕላኑ ላይ ላደረገው ማሻሻያ ያገኘው ሰርተፍኬት ላይ ምርመራ ይከፈታል። የቀድሞ የቦይንግ የሙከራ አብራሪ በሺህ የሚቆጠሩ የሙከራ የበረራ ሰዓታትን የሚመለከቱ መረጃዎች ዳግም እንደሚመረመሩ ተናግሯል። አደጋውን ተከትሎ ቦይንግ 737-8 ማክስ አውሮፕላኑ ላይ ተጨማሪ አደጋ አስጠንቃቂ ስርዓቶችን እንደሚጨምርና የፓይለቶች ስልጠና መመሪያውንም እንደሚያሻሽል አስታውቋል። ነገር ግን ይህኛው የቦይንግ ማሻሻያ የሚመለከታቸውን የአቪዬሽን ተቆጣጣሪ አካላት ይሁንታ በቀላሉ የሚያገኝ አይሆንም። እንደ አውሮፓ አቪዬሽን ደህንነት ኤጀንሲ ያሉ ከአሜሪካ ውጭ ያሉ ተቆጣጣሪ አካላትም ነገሩን በንቃት የሚከታተሉት ሲሆን በነገሮች እርግጠኛ ሳይሆኑ ማክስ ዳግም በአውሮፓ የአየር ክልል እንዲበር ሊፈቅዱ አይችሉም። ቦይንግ ምን ያህል ይከስራል? በመቶዎች የሚቆጠሩ ማክስ አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ የታገዱበት፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ማክስ አውሮፕላኖቹ ግዥ ውሎቹ ውሃ የበላቸው ቦይንግ ያጋጠመው የገበያ ቀውስ ገና ተጀመረ እንጂ አላለቀም። ማክስ አውሮፕላኖቻቸው እንዳይበሩ የታገዱባቸው አየር መንገዶች ከቦይንግ ካሳ መፈለጋቸው አይቀሬ ነው። • አውሮፕላኑ 'ከቁጥጥር ውጪ ሆኖ ነበር' እገዳው ፀንቶ የሚቆይ ከሆነ የቦይንግ እዳ እየናረ መሄዱንም ይቀጥላል። ቢሆንም ግን ቦይንግ የገንዘብ ሃያል ነው። የቀድሞ የቦይንግ በረራ ኢንጅነር ፒተር ሊሜ አሁን ከፊቱ የተጋረጠው ኪሳራ ቦይንግን ክፉኛ በሚባል ደረጃ የሚጎዳው እንዳልሆነ ይናገራሉ። የኩባንያውን መልካም ስም እንደሚያበላሸው ግን ያምናሉ። ዳግም ማክስ አውሮፕላንን አየር ላይ መመለስም ቀላል እንደማይሆን ይገልፃሉ። በአቪዬሽን አለም ቁልፉ ነገር ደህንነት በመሆኑ "አሁን ተቆጣጣሪዎቹን በእርግጠኝነት ምን እንደሚያሳምናቸው አይታወቅም" ብለዋል። ቦይንግም ደህንነት ሁሌም ትኩረት የሚያደርግበት ቀዳሚ ነገር እንደሆነ በተደጋጋሚ ተናግሯል።
news-55485498
https://www.bbc.com/amharic/news-55485498
"መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር"፡ በሰብአዊነት ላይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል-ኢሰመኮ
የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች የተፈጸሙ ጥቃቶች በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ናቸው ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ዛሬ ባወጣው ሪፖርት አመለከተ።
ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተ ሁከት ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከተከሰተባቸው ስፍራዎች መካከል ሻሸመኔ ከተማ አንዷ ነች ኮሚሽኑ እንዳለው ለወራት ክስተቱን በተመለከተ ባደረገው ምርመራ መሰረት ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በኋላ "በጥቃቱ በተሳተፉ ሰዎችና ቡድኖች በሲቪል ሰዎች ላይ የተፈጸሙት ጥቃቶች በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል ባሕርያትን የሚያሟሉ ናቸው" ብሏል። ለዚህም ሪፖርቱ እንደማሳያነት ከጠቀሳቸው መካከል ለተከታታይ ጊዜያት ቢያንስ በ40 የተለያዩ ቦታዎች በአብዛኛው በቡድን የተደራጁ ሰዎች ከቦታ ቦታ እየተንቀሳቀሱ በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን በአሰቃቂ ሁኔታ መግደላቸው፣ የአካልና የሥነ ልቦና ጉዳት ማድረሳቸው፣ ንብረት ማውደማቸውና ነዋሪዎችን ማፈናቀላቸው ይገኙበታል። በተጨማሪም ጥቃቱ ያነጣጠረው በከፊል በብሔርና በሐይማኖታቸው ተለይተው የተመረጡ ሰዎችን ከየቤታቸው ለይቶ በማሳደድና በማጥቃት፣ በከፊል ብሔርና ሐይማኖት ሳይለይ ሰላማዊ ነዋሪዎችን ወይም ሲቪል ሰዎችን ሆነ ብሎ በማጥቃት የተፈጸመ የወንጀል ድርጊት መሆኑ ገልጿል። የሦስት ልጆች አባት ሆነው ታዋቂው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኞ ሠኔ 22/2012 ዓ.ም ምሽት አዲስ አበባ ውስጥ ገላን ኮንዶሚኒየም ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ በተተኮሰበት ጥይት ለህልፈት መዳረጉ ይታወሳል። ኢሰመኮ በሪፖርቱ በወንጀል ድርጊቱ ሲሳተፉ የነበሩት ሰዎች፤ ተግባራቸው ስልታዊና የተቀናጀ ወይም የሰፊ ጥቃት አካል መሆኑን በማወቅ የተሳተፉበት እንደነበር ጠቅሶ፤ እነዚህ በቡድን የተፈፀሙት ጥቃቶች ጠቅላላ ድርጊቶቹና ውጤታቸው በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ የግፍና ጭካኔ ወንጀል መሆኑን ሪፖርቱ አመልክቷል። መንግሥታዊው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጨምሮም ምርመራ ባደረገባቸው 40 የኦሮሚያ አካባቢዎች፣ የአርቲስቱን ሞት ተከትሎ በነበሩት 3 ተከታታይ ቀናት በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ፣ የ123 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ ቢያንስ በ500 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ደርሷል ብሏል። ሕይወታቸው ካለፈ ሰዎች ውስጥ 35ቱ በሁከቱ በተሳተፉ ግለሰቦችና ቡድኖች የተገደሉ መሆኑን ኢሰመኮ ጠቅሶ፤ በተጨማሪም ጥቃት ፈጻሚዎቹ በ306 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት አድርሰዋል ብሏል። በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በተወሰደ እርምጃ ቢያንስ 76 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ከ190 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቶ፤ በፀጥታ መደፍረስ ወቅት በተከሰተ ፍንዳታ፣ ቃጠሎና መሰል አደጋዎች 12 ሰዎች ሕይወታቸውን ማጣታቸውን ሪፖርቱ ገልጿል። በሁከቱ በህይወትና በሰዎች አካል ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከመኖሪያቸው መፈናቀላቸው፣ በግለሰቦች፣ በንግድ ድርጅቶች እንዲሁም በመንግሥት ንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመትና ዘረፋ መፈጸሙን የኮሚሽኑ ሪፖርት አመልክቷል። ከሃጫሉ ግድያ በኋላ በተከሰተ ሁከት ከፍተኛ የንብረት ውድመት ከተከሰተባቸው ስፍራዎች መካከል ሻሸመኔ ከተማ አንዷ ነች አሰቃቂ ድርጊቶች ባለ 64 ገጹ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባወጣው በዚህ ዝርዝር ሪፖርት ላይ በጥቃቶቹ ብዙ ቁጥር ያላቸው ከቦታ ቦታ በቡድን ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ሰዎች እንደተሳተፉበት ገልጾ ለድርጊቱም የተለያዩ ነገሮችን መጠቀማቸውን ገልጿል። ጥቃት አድራሾቹ በሰዎች ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን፣ የአካል ጉዳት ማድረሳቸውንና "ፍጹም ግፍና ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በማሰቃየት ወይም በማረድ ጭምር ሰዎችን ገድለዋል" ሲል ድርጊቱ በሰለባዎቹ ቤት ውስጥና በመንገድ ላይ ጭምር የተፈጸመ እና አሰቃቂ እንደነበር ገልጿል። አክሎም አጥቂዎቹ ከፈጸሙት ድብደባ፣ ግድያና ንብረት ማውደም በተጨማሪ ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን "ብሔርን መሰረት ያደረጉ ስድቦች ሲሳደቡ፣ ሲያንቋሽሹ፣ ሲያስፈራሩና ሲዝቱባቸው" እንደነበር ሪፖርቱ ጠቅሶ ይህም ሰላማዊ ነዋሪዎች በብሔር ወይም በሐይማኖታቸው ምክንያት ለጥቃት የመጋለጥ ከፍተኛ ስጋትና የሥነ-ልቦና ጭንቀት እንደፈጠረባቸው ኢሰመኮ መገንዘቡን ጠቅሷል። ይህ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ይፋ የተደረገው ሪፖርት እንደሚለው የጥቃቱ ባሕሪና መጠን እንደ የአካባቢው ሁኔታ የሚለያይ ቢሆንም "በአመዛኙ የክርስቲያን እምነት ተከታዮች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ጥቃቱ በአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች በብዛት በሚኖሩባቸው አካባቢዎች ደግሞ በኦርቶዶክስ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች ላይ ያነጣጠረ ነበር" ብሏል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ጊዜ ቀድሞ ከመከላከልና ከማስቆም አንጻር የፀጥታ ኃይሎች የነበራቸው ሚና ከቦታ ቦታ የተለያየ መሆኑን ያመለከተው ሪፖርቱ "በተወሰኑ አካባቢዎች የፀጥታ ኃይሉ ቅድመ ዝግጅት በማድረጉ ጉዳቱን ለመከላከል፣ ለማስቆም ወይም ለመቀነስ ተችሏል" ሲል ገልጿል። በአንጻሩ በተለይ ከፍተኛ ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የነዋሪዎችና ተጎጂዎች ለየአካባቢው አስተዳደርና ለፀጥታ አካላት በተደጋጋሚ እርዳታ ቢጠይቁም አዎንታዊ ምላሽ አለማግኘታቸውን አመልክቷል። ይልቁንም "በበላይ አካል አልታዘዝንም፣ የግለሰብ ንብረት ጠብቁ አልተባልንም፣ የምንጠብቀው የመንግሥትን የልማት ተቋማትን፣ ባንኮችን እና የሐይማኖት ተቋማትን ነው" የሚል ምላሽ ሲሰጣቸው እንደነበር ኮሚሽኑ መረዳቱን ገልጾ፤ በተወሰኑ ቦታዎች ፖሊስ ጥቃቱን እያየ በዝምታ ማለፉን በመጥቀስ የዓይን እማኞች በምሬት "መንግሥት ያለ አይመስልም ነበር" ማለታቸውን አመልክቷል። የየአካባቢዎቹ የፀጥታ አካላትና የመንግሥት ኃላፊዎች ጥቃቱ ድንገተኛና በብዙ ስፍራዎች ብዙ ቁጥር ያላችው ሰዎች የተሳተፉበት ስለነበር በሚፈለገው መጠንና ፍጥነት ለማስቆም አስቸጋሪ እንደነበር መናገራቸውን የጠቀሰው ሪፖርቱ፤ ነዋሪዎችን ከዚህ አይነት ጥቃት አስቀድሞ ለመከላከል "በክልሉ መንግሥት የተደረገ በቂ ዝግጅት አለመኖሩ፣ በተለይ ቀደም ሲል መሰል ብሔርንና ሐይማኖትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በተፈጸሙባቸው ቦታዎች አንዳችም ዝግጁነት አለመኖሩ ዜጎችን በአሳዛኝ ሁኔታ ለተደጋጋሚ ጥቃትና በደል አጋልጧል" ብሏል። የፀጥታ አካላት ኃይል አጠቃቀም በየቦታው የተከሰተውን የፀጥታ መደፍረስ ለፀጥታ ኃይሉ ኃላፊነቱን ለመወጣት እጅግ ፈታኝ የነበረ መሆኑን የገለጸው ሪፖርቱ፤ ነገር ግን በተወሰኑ ቦታዎች የነበረው "የኃይል አጠቃቀም ተመጣጣኝነት ከፍተኛ ጥያቄ የሚያስነሳ ነው" ብሏል። የፀጥታ አካላት ኃይል አጠቃቀምን በተመለከተ በሪፖርቱ ላይ እንደተጠቀሰው ሁከት ባጋጠመባቸው በተለያዩ ስፍራዎች "በመንግሥት የፀጥታ አካላት ጭንቅላታቸው፣ ግንባራቸው፣ ደረታቸውና ጀርባቸው ላይ በጥይት ተመትተው የተገደሉ ሰዎች" እንደሚገኙ ጠቅሶ፤ ከተጎጂዎች መካከል ምንም ተሳትፎ ያልነበራቸው ሰዎች በመንገድ ወይም በቤታቸው በር ላይ የተገደሉ፣ የአገር ሽማግሌዎችን ጨምሮ የአዕምሮ ህመምተኛና ሕፃናት ይገኙበታል ብሏል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በሪፖርቱ ላይ ጨምሮም በተወሰኑ አካባቢዎች በተፈጠረው ሁከት ውስጥ መሳሪያ የያዙ፣ ጥይት የተኮሱ፣ ቦምብ የወረወሩ መኖራቸውንና በዚህም የተነሳ የፀጥታ ኃይል አባላት መቁሰላቸውንና መገደላቸውን ጠቅሶ፤ ይህም የፀጥታ ኃይል አባላት የጦር መሳሪያ እንዲጠቀሙ ያስገደደ ሁኔታ እንደነበር መገመት ይቻላል ብሏል። በዚህም በአብዛኞቹ አካባቢዎች የፀጥታ ኃይል አባላት መለስተኛ ጉዳት በሚያስከትሉ መሳሪያዎች ሳይሆን፣ ሕይወት ሊያጠፋ የሚችል መሳሪያዎች መጠቀማቸው ለሰልፈኞቹ፣ በአካባቢው ለነበሩ ሰዎችና ለየፀጥታ ኃይል አባላቱ ጭምር የሕይወትና የአካል ደኅንነት አደጋን መፈጠሩን ገልጿል። ይህንንም ተከትሎ ኮሚሽኑ ምርመራውን ባደረገባቸውና የፀጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሰው ሕይወት በጠፋባቸው አካባቢዎች "በፌዴራል ወይም በክልል መንግሥት አካላት የደረሰውን የሕይወት መጥፋት ምርመራ በማድረግና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ የተጀመረ ሥራ መኖሩን ለማረጋገጥ አልቻለም" በማለት የተወሰደ እርምጃ አለመኖሩን ገልጿል። ምክረ ሐሳብ በዝርዝር ሪፖርቱ ላይ ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ በኋላ በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች የተፈጸመውን ጥቃት "በሰብአዊነት ላይ የተፈጸመ ወንጀል" በማለት የገለጸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የፌደራል መንግሥቱና የክልሉ መንግሥት መውሰድ ያለባቸውን እርምጃዎችን ጠቁሟል። በዚህም መሠረት በኮሚሽኑ የቀረቡ መረጃዎችን በመመርኮዝ የወንጀል ምርመራ በማድረግ በጥቃቶቹ የተጠረጠሩ ሰዎች ተለይተው ተጠያቂ እንዲሆኑና በኦሮሚያም ሆነ በሌሎችም ክልሎች ተመሳሳይ "የግፍና የጭካኔ ወንጀል ሊከሰት እንደሚችል በመገንዘብ" መከላከል የሚያስችል የተቀናጀ የቅድመ ማስጠንቀቂያና የመከላከያ ሥርዓት እንዲዘረጋ አሳስቧል። በተጨማሪም ሪፖርቱ በአገሪቱ ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንጻር "የዘር ማጥፋት ወንጀልን ጨምሮ የዚህ አይነት የግፍና ጭካኔ ወንጀሎች ስጋት መኖሩን የሚያመላክት ስለሆነ" መንግሥት ከባለድርሻ አካላትጋር በመተባበር እንዲህ አይነት የግፍና የጭካኔ ወንጀል መከላከያ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ሥራ ላይ እንዲያውል ጠይቋል። በተጨማሪም ኮሚሽኑ ካወጣው ሪፖርት አንጻር የአገሪቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ጨፌ ኦሮሚያ እንዲሁም መገናኛ ብዙሃንና የማኅበረሰብ አንቂዎች ከዚህ በፊት ስለተፈጸመው ጥቃትና ወደፊት ሊያጋጥም ከሚችለው ተመሳሳይ ክስተት አንጻር ማድረግ የሚጠበቅባቸውን በዝርዝር በሪፖርቱ ላይ አመልክቷል። የሃጫሉ ግድያ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በጥይት ከተመታ በኋላ በኋላ የህክምና እርዳታ እንዲያገኝ ወደሚገኘው ሆስፒታል ቢወሰድም ህይወቱ ሊተርፍ እንዳልቻለ ፖሊስ በወቅቱ አስታውቆ ነበር። ግድያውን ተከትሎ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በድምጻዊው ሞት የተሰማቸውን ሀዘን "ውድ ህይወት አጥተናል" በማለት ድንጋጤና ሐዘናቸውን የገለጹ ሲሆን ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናትም ሐዘናቸውን በወቅቱ ገልጸው ነበር። ሃጫሉ በኦሮሚኛ ሙዚቃዎቹ ታዋቂነትና ተወዳጅነትን አትርፎ የነበረው ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ በተለይ በኦሮሚኛ ተናጋሪው ዘንድ በሥራዎቹ ከፍ ያለ ተወዳጅነትን ለማግኘት ችሎ ነበር ስለነበር የሞቱ ዜና እንደተሰማ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ቁጣና ሐዘን ተፈጥሮ ነበር። በዚህም ሳቢያ በተለያዩ ቦታዎች ከጸጥታ ኃይሎች ጋር ከተከሰተ ግጭትና በነዋሪዎች ላይ ከተፈጸሙ ጥቃቶች ጋር በተያያዘ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላትን ጨምሮ አስር ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በተለያዩ አካባቢዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው በወቅቱ መገለጹ ይታወሳል። ከግድያው ጋር ተያይዞ አለመረጋጋቱ በተከሰተበት ጊዜ በአገሪቱ የኢንተርኔት አገልግሎት ለሳምንታት ተቋርጦ ነበረ። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ከቀናት በኋላ ወንጀሉን ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ሦስት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑ ይታወቃል። አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ሰኔ 22/2012 ዓ.ም መገደልን ተከትሎ በአዲስ አበባና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች ለቀናት በተከሰተው ሁከትና አለመረጋጋት የበርካታ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ከፍተኛ መጠን ያለው ንብረት ለውደመትና ለዝርፊያ መዳረጉን ቀደም ሲል የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።
news-54463752
https://www.bbc.com/amharic/news-54463752
ኮሮናቫይረስ፡ በአፍሪካ በኮቪድ-19 የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ የሆነበት 5 ምክንያቶች
በርካታ የአፍሪካ አገራት ምንም እንኳን ደካማ የጤና ሥርዓት ቢኖራቸውም የበሽታውን ሥርጭት ለመግታት ባካሄዱት ዘመቻ ተወድሰዋል።
እንደ ጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ መሰረት ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሕዝብ ብዛት ባላት አህጉር አፍሪካ፤ እስካሁን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 1.5 ሚሊዮን ገደማ ነው። የሟቾቹ አጠቃላይ ቁጥር ደግሞ 37 ሺህ። ይህም በአሜሪካ ከተመዘገበው 580 ሺህ ፣ በአውሮፓ 230 ሺህ እና በእስያ 205 ሺህ የሟቾች ቁጥር ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው። በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥርም በአፍሪካ እየቀነሰ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ። በሽታውም ከሌሎች አህጉራት ጋር ሲታይ በአፍሪካ ያን ያህል የከፋ እንዳልሆነ የግልና የሕዝብ ድርጅቶችን መረጃ በማጠናቀር የተሰራ አህጉራዊ ጥናት አመልክቷል። ይሁን እንጅ በአህጉሪቷ እየተደረገ ያለው ምርመራ አነስተኛ መሆኑ በሽታውን ለመቆጣጠር የሰጠችውን ምላሽ አጥልቶበታል። ቢሆንም ግን በአፍሪካ ሳይመዘገብ የቀረ የሞት ቁጥር መኖሩን የሚያመላክት መረጃ አለመኖሩን የአፍሪካ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል ዳሬክተር ዶክተር ጆን ኬንጋሶንግ ተናግረዋል። ታዲያ በአፍሪካ ከሌላው አህጉር በተለየ በበሽታው አነስተኛ የሞት ቁጥር የተመዘገበበት ምክንያት ምንድን ነው? 1: ፈጣን እርምጃ በሌጎስ የሚገኝ ቤተ ክርስቲያን በአህጉሯ ለመጀመሪያ ጊዜ ቫይረሱ መገኘቱ የተረጋገጠው እአአ. የካቲት 14 በግብፅ ነበር። ወረርሽኙ ደካማ የጤና ሥርዓት ባላት አህጉር በስፋት እና በፍጥነት ይዛመታል የሚል ከፍተኛ ስጋትም ነበር። በመሆኑም ከመጀመሪያው ጀምሮ በርካታ የአፍሪካ መንግሥታት የቫይረሱን ሥርጭት ለመቆጣጠር አፋጣን እርምጃ ወሰዱ። በእጅ የመጨባበጥ ሰላምታን ማስቀረት፣ በተደጋጋሚ እጅን መታጠብ፣ አካላዊ ርቀትን መጠበቅ ፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን ወዲያው ነበር ያስተዋወቁት። እንደ ሌሴቶ ያሉ አንዳንድ አገራትም በአገራቸው ቫይረሱ መግባቱ ሳይረጋገጥ ነበር እርምጃ መውሰድ የጀመሩት። ሌሴቶ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ መጋቢት ወር ላይ ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ አድርጋለች። ከዚያም ለሦስት ሳምንታት የዘለቀ የእንቅስቃሴ ገደብ ጣለች። በተመሳሳይ ሌሎች የደቡባዊ አፍሪካ አገራትም ይህንኑ ተገበሩ። ይሁን እንጅ በግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ የእንቅስቃሴ ገደቡ ከተነሳ ከቀናት በኋላ ሌሴቶ የመጀመሪያውን በቫይረሱ የተያዘ ሰው አገኘች። ከ2 ሚሊዮን በላይ የሕዝብ ብዛት ያላት ሌሴቶ እስካሁን 1 ሺህ 700 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን የመዘገበች ሲሆን፤ የ40 ሰዎች ሕይወትም በቫይረሱ ሳቢያ አልፎባታል። 2: የሕዝብ ድጋፍ ፒኢአርሲ የተባለ ድርጅት ነሐሴ ወር ላይ በ18 አፍሪካ አገራት ላይ በሰራው የዳሰሳ ጥናት፤ ለጥንቃቄ መመሪያዎቹ የነበረው የሕዝብ ድጋፍ ከፍተኛ እንደነበር 85 በመቶ የጥናቱ ተሳታፊዎች ተናግረዋል። የጥናቱ ተሳታፊዎች ቀደም ብለው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ያደርጉ እንደነበር አክለዋል። ሪፖርቱ " የሕብረተሰብ ጤና እና ማህበራዊ የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመተግበር የአፍሪካ ሕብረት አባል አገራት ከመጋቢት እስከ ግንቦት ድረስ የቫይረሱን ስርጭት መቆጣጠር ችለው ነበር " ብሏል። ይሁን እንጅ ሰኔ ወር ላይ የተጣሉት ገደቦች እየላሉ በመምጣታቸው፤ ሐምሌ ወር ላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ጭማሬ እንዳሳየ ሪፖርቱ ጨምሮ ገልጿል። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወዲህ ግን ግማሽ በሚሆነው የአህጉሪቱ ክፍል በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች እና በበሽታው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ መጥቷል። ይህም ምን አልባት በደቡብ ንፍቀ ክበብ ካለው የክረምት የአየር ጠባይ ጋር ሊያያዝ እንደሚችል ተነግሯል። በአገራቱ በሽታውን ለመቆጣጠር የተጣሉ ገደቦችም ዋጋ ሳያስከፍሉ አልቀሩም ታዲያ። በኢኮኖሚው ፣ በማህበራዊው፣ በፖለቲካዊ ዘርፉ ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል። በርካታ የሥራ እድሎችም ታጥፈዋል። በዓለማችን ጥብቅ የእንቅስቃሴ ገደብ ከጣሉ አገራት መካከል አንዷ የሆነችው ደቡብ አፍሪካ በዓመቱ የመጀመሪያው አጋማሽ 2.2 ሚሊዮን ሠራተኞች ሥራ አጥተዋል። በዚህም ምክንያት ምንም እንኳ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ቢጨምርም በርካታ አገራት ኢኮኖሚያቸውን እንደገና ለመክፈት ተገደዋል። እንደ ፒኢአርሲ ሪፖርት ከሆነ፤ ኢኮኖሚው እንደገና ለመከፈቱ የተሰጠው የሕዝብ አስተያየት የተቀላቀለ ነው። አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ የበሽታውን ሥርጭት መቀነስ የሚቻል በመሆኑ እንቅስቃሴው መከፈት አለበት ያሉ ቢኖሩም፤ ሌሎች ደግሞ ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ መመለሱ ያዘናጋል ብለዋል። መረጃው እንደሚያመለክተው በአፍሪካ ያሉ ሕዝቦች ኮቪድ-19 አደገኛ በሽታ እንደሆነ ቢመለከቱትም፤ በርካቶች ግን ለራሳቸው ከሚያደርጉት ጥንቃቄ በላይ የኢኮኖሚውና ማህበራዊ ጫናው አይሎባቸዋል። ይህም ለበሽታው እንዲጋለጡ አድርጓቸዋል ሲል ሪፖርቱ ድምዳሜውን አስቀምጧል። 3: ወጣት የሕዝብ ብዛት እና አነስተኛ የአረጋውያን የእንክብካቤ ማዕከላት በአፍሪካ አብዛኛው ሕዝብ ወጣት በመሆኑ በሽታውን ለመቆጣጠር ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ በበሽታው የሞቱት አብዛኞቹ ከ80 ዓመት በላይ ያሉ ናቸው። እንደ የተባበሩት መንግሥታት መረጃ ከሆነ አፍሪካ በአማካይ 19 ዓመት እድሜ ያላቸው የዓለማችን ከፍተኛ የወጣቶች ቁጥር የሚገኝባት አህጉር ናት። እንደ የዓለም ጤና ድርጅት ከሆነ በሽታው በአብዛኛው በወጣቶቹ ውስጥ ነው ያለው፤ ነገር ግን ከሰሃራ በታች ባሉ አገራት 91 በመቶ የሚሆኑት በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ከ60 ዓመት በታች ናቸው፤ ከ80 ዓመት በላይ የሆኑትም ምልክት የማያሳዩ ናቸው። በናይሮቢ ህፃናት እጃቸውን ሲታጠቡ "በአፍሪካ ደግሞ ከ65 ዓመት በላይ የሆነው ሕዝብ 3 በመቶ ብቻ ነው። በአውሮፓ፣ ሰሜን አሜሪካ እና ሃብታም የእስያ አገራት ግን በእድሜ የገፋ ሕዝብ ነው ያላቸው።" ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሞቲ ተናግረዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም በምዕራብ አገራት አረጋውያን የሚኖሩት በእንክብካቤ ማዕከላት መሆኑን በመጥቀስ እነዚህም የበሽታው ሥርጭት ጠንከር ያለባቸው ቦታዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል። በአፍሪካ አገራት አብዛኞቹ በእድሜ የገፉ ሰዎች በሚኖሩባቸው የገጠር አካባቢዎች እንደዚህ ዓይነት ማቆያዎች የተለመዱ አይደሉም። በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገራትም ሰዎች በከተማ ሲሰሩ ቆይተው ጡረታ ሲወጡ ወደ ገጠር የመሄድ ልማድ አለ። ይህ ደግሞ በገጠር አካባቢም ያለው የሕዝብ ብዛት አነስተኛ በመሆኑ አካላዊ ርቀትን ለመጠበቅ ቀላል ነው። ከዚህም በተጨማሪ በአገር ውስጥም ሆነ በአገራቱ መካከል ባለው ያልዳበረው የትራንስፖርት ሥርዓት ከበሽታው መሸሸጊያ ምክንያት ሆኗል። አፍሪካዊያን ባደጉ አገራት እንዳሉ ሕዝቦች ጉዞ አያደርጉም። ይህም ከሰዎች ጋር ያላቸውን ንክኪ እንዲቀንስ አድርጎታል። 4: ምቹ የአየር ንብረት በአሜሪካ የሜሪላንድ ዩንቨርሲቲ አጥኝዎች የሙቀት መጠን፣ የወበቅ እና ኬክሮስ [ከምድር ወገብ በላይና በታች ያለው ርቀት]እና በኮሮናቫይረስ ሥርጭትን በተመለከተ አንድ ጥናት አካሂዷል። የጥናቱ ቡድን መሪ ሞሃመድ ሳጃዲ "በመጀመሪያ በዓለማችን 50 ከተሞች ያለውን የቫይረሱን ሥርጭት ተመለከትን። ቫይረሱ ዝቅተኛ የሙቀት መጠንና ወበቅ ውስጥ ለመሰራጨት ጊዜ አልወሰደበትም" ሲሉ ተናግረዋል። "ይህ ማለት ግን በሌላ አየር ጠባይ ውስጥ ቫይረሱ አይሰራጭም ማለት አይደለም" ያሉት አጥኝው፤ የሙቀት እና ወበቅ መጠን ሲቀንስ ግን ቫይረሱ በተሻለ የመሰራጨት እድል አለው ብለዋል። በመሆኑም ከትሮፒካል [ከምድር ወገብ አካባቢ ርቀው የሚገኙ] የአፍሪካ አገራት ከሌሎቹ የባሰ ችግር ገጥሟቸዋል። 5: ጥሩ የማህበረሰብ ጤና ሥርዓት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የተከሰተው የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝን ለመዋጋት እየታገለች ባለበት ወቅት ነበር። ጎረቤት አገራትም በተጠንቀቅ ላይ ነበሩ። በመሆኑም ለተጓዦች የሚደረግ የኢቦላ ምርመራ የኮቪድ-19 ምርመራን እንዲያካትት ተደርጓል። አስከፊውን የኢቦላ ወረርሽኝ እአአ ከ2013-2016 ሲታገሉ የቆዩት በርካታ የምዕራብ አፍሪካ አገራትም በሕብረተሰብ ጤና እርምጃዎች ላይ ጥሩ ልምድ አካብተው ነበር። ታማሚዎችን ለይቶ ማቆያ ማስገባትን፣ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች መለየትን፣ እነርሱን መፈለግና መርምሮ ለይቶ ማቆያ ማስገባትን ጨምሮ የሚወሰዱ ሌሎች እርምጃዎች ኮቪድ-19ንም ለመከላከል ተጠቅመውበታል። በናይጄሪያ የፖሊዮ ክትባት ከዚህም በተጨማሪ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት ያላት አፍሪካዊቷ አገር ናይጀሪያ፤ የፖሊዮ መከላከያ ክትባት ለመስጠት በየመንደሩ የሚሄደውን የጤና ቡድን፤ ስለ አዲሱ ወረርሽኝ [ኮቪድ-19] ለሕብረተሰቡ ግንዛቤ ለመፍጠር በአፋጣኝ እንዲሰማራ አድርጋለች። ይህ በፖሊዮ መከላከል ፕሮግራም ላይ ይሰሩ የነበሩት ዶክተር ሮስመሪ ኦንይቤ ሚያዚያ ላይ ያቀረቡት ሃሳብ ነበር። ዶክተር ሮስመሪ " ዜናውን እንደሰማሁ ሕብረተሰቤን ለመጠበቅ የእኔ ሙያ እና እርዳታ እንደሚያስፈልግ አሰብኩ። በመሆኑም ፖሊዮ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎችን በማንቀሳቀስ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች እንዲለዩ እና እንዲከታተሉ አደረግን" ብለዋል። ከሌሎች ዓለማት ጋር ሲነፃፀር በአብዛኛው የአፍሪካ አገራት ሆስፒታሎች መሰረተ ልማት ያልተሟላና ያልዘመነ ነው። የአህጉሪቷ ጥንካሬም በተፈተነው የሕብረተሰብ ጤና ሥርዓት ውስጥ ይገኛል። ይህ ማለት ግን የአፍሪካ ሕዝብ መዘናጋት አለበት ማለት አይደለም። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳሬክተር ዶክተር ሞቲ " በቀጠናው ያለው የቫይረሱ ስርጭት አዝጋሚ ነው ማለት ወረርሽኙ ለተወሰነ ጊዜ ይቆያል ማለት ነው። ሥርጭቱ ሊጨምር እንደሚችልም ይጠበቃል" በማለት አሳስበዋል።
news-46183220
https://www.bbc.com/amharic/news-46183220
ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ጠበቃ ራሳቸው እንዲያቆሙ ተወሰነ
ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ዳኘውና ሌሎችም ተጠርጣሪዎች በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበዋል።
በትናንትናው የፍርድ ቤት ውሎ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ፤ ''ደሞዜ አነስተኛ ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ'' በማለታቸው ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ከሰዓት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል። በትላንትናው የፍርድ ቤት ውሎ፤ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ከጡረታ የማገኘው ገንዘብ 4000 ብር ስለሆነ ፍርድ ቤቱ ጠበቃ እንዲያቆምልኝ እጠይቃለሁ ሲሉ ለዳኞች አስታውቀዋል። ዛሬ ፖሊስ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ አለኝ ብሏል። ፖሊስ እንደሚለው፤ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ በጸረ ሙስና ኮሚሽን ያስመዘገቡት የሃብት መጠን እና በአንድ ባንክ ውስጥ ያላቸው ተቀማጭ ሂሳብ ጠበቃ የማቆም አቅም እንዳላቸው ያመላክታል። ፖሊስ ከ15 ቀን በፊት አንድ መቶ ሺህ ብር ከባንክ ሂሳባቸው ወጪ መደረጉን እና በስማቸው ቤት እንዲሁም 80 ሺህ ብር የሚያወጣ መኪና ተመዝግቦ እንደሚገኝ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል። ሜጀር ጄኔራል ክንፈ በበኩላቸው ፖሊስ የጠቀሰው ንብረት እና ገንዘብ ''የእኔ አይደለም'' ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ምላሽ የሰጡ ሲሆን፤ ''ቤት የለኝም፣ መኪና የለኝም፣ ንብረት የለኝም። ያለኝ ሰውነቴ ብቻ ነው'' በማለት ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ሆኖም ፍርድ ቤቱ ሜጄር ጄኔራል ክንፈ የራሳቸውን ጠበቃ እንዲያቆሙ ውሳኔ አስተላልፏል። ሜጄር ጄኔራሉ እና ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘው ለህዳር 10፣ 2010 ዓ. ም ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ከሜጄር ጄኔራሉ ጋር የቀድሞ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋዤጠኛ ፍጹም የሺጥላ፣ ሳጅን ኪዳኔ አሰፋ፣ ትዕግስት ታደሰ እና አቶ ቸርነት ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ወ/ሮ ፍጹም የሺጥላ ወ/ሮ ፍጹም የሺጥላ ከሜቴክ የስራ ኃላፊዎች ጋር ያልተገባ የጥቅም ግንኙነት በመፍጠር ፍጹም ኪነ ጥበባት በሚሰኝ የንግድ ስም ህጋዊ ባልሆነ መንገድ የ900 ሺህ ብር የስራ ስምምነት ከሜቴክ ጋር ተዋውለዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል። ወ/ሮ ፍጹም የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን እና ከሕግ ለማምለጥ ሙከራ አለማድረጋቸውን በመጥቀስ የዋስትና መብት እንዲከበርላቸው ቢጠይቁም ፍርድ ቤቱ ግን የዋስትና መብት ከልክሏል። ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ ዛሬ ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የሜጄር ጀነራል ክንፈ ዳኘው ወንድም ኢሳያስ ዳኘው ይገኙበታል። እንደ ሜጀር ጀነራል ክንፈ ወንድማቸው አቶ ኢሳያስ ዳኘውም ገንዘብ ከፍለው ጠበቃ ማቆም እንደማይችሉ በመጥቀስ፤ መንግሥት ጠበቃ እንዲያቆምላቸው መጠየቃቸው ይታወሳል። የኢትዮቴሌኮም ሰራተኛ ሳሉ የግዢ ስርዓቱ በማይፈቅድ መልኩ ሜቴክ ጨረታ እንዲያሸንፍ በማድረግ ወንጀል ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡት አቶ ኢሳያስ ወራሃዊ ደሞዜ 8 ሺህ ብር በመሆኑ ጠበቃ ማቆም አልችልም ብለው ነበር። ሜጀር ጄነራል ክንፈ ዳኘው ማክሰኞ እለት በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ይታወሳል። ፋና ብሮድካስቲንግ፤ ሜጀር ጄነራል ክንፈ ወደ ሱዳን ለመውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ ብሎ የዘገበ ሲሆን፤ ኢቢሲ ደግሞ በትግራይ ክልል ባካር ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በኩል ለማምለጥ ሲሞክሩ በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ውለዋል ሲል ዘግቧል። በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና የተጠረጠሩት 63 ግለሰቦች ሰኞ ዕለት ከፍተኛ ፍርድ ቤት 10ኛ የወንጀል ችሎት ቀርበው ነበር። ፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል 36ቱ በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን፤ 16ቱ ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት፣ ስድስቱ ከፌዴራል ፓሊስ ምርመራ ቢሮ፣ ሁለቱ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን፣ ስምንቱ ከፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ሲሆኑ፤ ሶስቱ ግለሰቦች ደግሞ ተጠርጣሪን በማስመለጥና ሰነድ በማጥፋት የተጠረጠሩ ናቸው። ብርጋዲየር ጄኔራል ጠና ኩርዲንን ጨምሮ 28 የሜቴክ ሰራተኞችም በሙስና ተጠርጥረው ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ የስኳር ገንዘብን ያለአግባብ በመጠቀም፣ የህዳሴ ግድብና የያዩ ማዳበሪያ ፕሮጀክቶች ላይ ህግን ያልተከተለ ግዢ በመፈፀም ተከሰዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሁለት መርከቦችን ለህገወጥ ንግድ በመገልገል ክስ የተወነጀሉ ሲሆን፤ የግራ ቀኙን ክርክር ያዳመጠው ፍርድ ቤትም የተጠርጣሪዎችን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀን ጊዜ የፈቀደ ሲሆን፤ ለህዳር 14 ቀን ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አቶ ብርሀኑ ጸጋዬ፤ የቀድሞ የብሄራዊ ደህንነት እና መረጃ ኤጀንሲ አመራሮች እና አባላት በሽብር እና ከሽብር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የተያዙ ግለሰቦች ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጽሙ ነበር ብለዋል። ከሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከሙስና ጋር በተያያዘ የተሰሩ ወንጀሎችን በተመለከተ ባለፉት አምስት ወራት ጠቅላይ አቃቤ ሕግ ሲያከናውን የነበረውን የምርመራ ውጤት ሕዳር 3 ቀን 2011 ዓ. ም ይፋ አድርጓል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በመግለጫቸው፤ በግለሰቦችና በተቋማት ደረጃ ተፈጽመዋል ያሏቸውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የሙስና ወንጀሎች ዘርዝረዋል። ''የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹ ሲፈጸሙ የነበረው በኃላፊዎች ነው። የሙስና ወንጀሉ ሰፊና ውስብስብ ስለሆነ የምርመራ ሂደቱ ቀላል አልነበረም'' ብለዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ''ሰዎቹን ሳናስራቸው በፊት ከሕግና ከአሰራር አንጻር መረጃና ማሰረጃ ለማደራጀት ሰፊ ጊዜ ወስዶብናል'' በማለት እስካሁን ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ያልዋሉበትን ምክንያት አስረድተዋል። • ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቅ ለምን አስፈለጋት? • "የቅማንትን ሕዝብ እንወክላለን የሚሉ ፅንፈኞች ከሌሎች ጋር በቅንጅት እየሰሩ ነው" ጄኔራል አሳምነው • ኦነግ እና መንግሥትን ለማግባባት የሃገር ሽማግሌዎች እየጣሩ ነው የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሽብርና ከሽብር ጋር በተያያዘ ክስ በቁጥጥር ሥር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ላይ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተፈጸሙ ተናግረዋል። በሽብር ተጠርጥረው የሚያዙ ግለሰቦች በብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት አመራሮች እና አባላት አማካኝነት ወደ መደበኛ እስር ቤቶች ከመወሰዳቸው በፊት በማይታወቁ፣ ስውር እስር ቤት ውስጥ እንዲቆዩ ይደረጉ እንደነበር ተናግረዋል። ስውር እስር ቤቶቹ በይፋ በሕግ የማይታወቁ፤ በሃገሪቱ የተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ እንደሆኑ ገልጸው፤ ከነዚህም መካከል "አዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ሰባት እና ከዚያ በላይ እስር ቤቶች አሉ" ብለዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ ተጠርጣሪዎች አብዛኛውን ጊዜ በአምቡላንስ በቁጥጥር ሥር እንደሚውሉ እና በድብደባ የተጠረጠሩበትን ወንጀል እንዲያምኑ ይደረጉ እንደነበረ አክለዋል። ተጠርጣሪዎች የራሳቸው ያልሆኑ የጦር መሳሪያዎችን 'የኔ ነው' ብለው እንዲፈርሙ ይገደዱ እንደነበር ገልጸዋል። ዛፍ ላይ ሰቅሎ መግረፍ፣ በኮሬንቲ ማስያዝ (በኤሌክትሪክ መጥበስ)፣ በፒንሳ የብልትን ቆዳ መሳብ፣ በአፍንጫ እስክሪብቶ ማስገባት፣ በአፍ እና አፍንጫ እርጠብ ፎጣ መወተፍ፣ ሙቀታማ ስፍራዎች ላይ ለረዥም ጊዜ ጸሃይ ላይ ማስቀመጥ፣ ብልት ላይ የውሃ ኮዳ ማንጠልጠል እና ጥፍር መንቀልን የመሳሰሉ የማሰቃያ መንገዶች ይጠቀሙ እንደነበረም ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪም በተጠርጣሪዎቹ ላይ የአስግድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሟል ብለዋል። በምረመራው ወቅት የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን እንዲሁም አሁን ድረስ ያሉበት የማይታወቅ ግለሰቦች እንዳሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። ''የተፈጸሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በብሔራዊ የመረጃ እና ደህንነት ኤጀንሲ አመራሮች ዘንድ እንደ አሰራር ጥቅም ላይ ሲውሉ ነበረ፤ ግምገማ እየተካሄደባቸው አቅጣጫ ይሰጥባቸው ነበረ'' ብለዋል። የሰኔ 16 የቦንብ ፍንዳታ የሰኔ 16ቱ የቦንብ ፍንዳታን በማስመልከትም፤ በዋናነት ወንጀሉን የመሩትና በገንዘብ የደገፉት የብሄራዊ ደህንነት እና መረጃ ኤጀንሲ የቀድሞው ኃላፊ ናቸው ብለዋል። ወንጀሉ ኬንያ ሃገር ከምትገኘው ገነት ወይም ቶለሺ ተብላ ከምትጠራ ግለሰብ ጋር በመተባበር እንደተፈጸመ አስረድተዋል። ''ከብሄራቸው አንጻር ስንመለከት ወንጀሉን የፈጸሙት ኦሮሞዎች ናቸው። ጠቅላይ ሚንስትሩ ኦሮሞ ሆነው ሳለ፤ ተግባሩ በኦሮሞ መፈጸሙ፤ ጠቅላይ ሚንስትሩ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም የሚል ተልዕኮ ይዞ እንደተቀነባበረ እጃችን ላይ ያለው መረጃ ያሳያል'' ሲሉ ተናግረዋል። ሙስና ሙስናን በተመለከት፤ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ባለፉት ስድስት ዓመታት 37 ቢሊየን ብር የውጪ ሃገር ግዢ መፈጸሙን ተናግረው "ሁሉም ግዢዎች ያለ ምንም አይነት ጨረታ ተከናውነዋል" ብለዋል። የውጪ ሃገር ግዢ ሲደረግ፤ ከኮርፖሬሽኑ ኃላፊዎች ጋር የስጋ ዝምድና ወይም የጥቅም ትስስር ያላቸው በግዢዎቹ ላይ እስከ 400 በመቶ ድረስ የተጋነነ ወጪ ያደርጉ ነበር ብለዋል። ለአብነትም በአንድ ድርጅት የ205 ቢሊዮን ብር ግዢ ያለ ጨረታ መፈጸሙን ተናግረዋል። ሁለት መርከቦች እና አምስት አውሮፕላኖች የአሁኑ የባህር ትራንዚት እና ሎጂስቲክ አገልግሎት ድርጅት ወይም በቀድሞ ስሙ የኢትዮጵያ መርከብ ድርጅት 'አንድነት' እና 'አባይ' የተሰኙ መርከቦች ነበሩት። እነዚህ መርከቦች ከ28 ዓመታት በላይ አገልግሎት በመስጠታቸው በባለሙያዎች ጥናት መሰረት አገልግሎት ላይ መዋል እንደሌለባቸው ስለተረጋገጠ ድርጅቱ ሁለቱ መርከቦች አንዲሸጡ ይወስናል። በውሳኔው መሰረት አንድ የውጪ ድርጅት ለመርከቦቹ 3.3 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ይሰጣል። ሜቴክ መርከቦቹ ለውጪ ድርጅት ከሚሸጡ ለሽያጭ በቀረቡበት ዋጋ መርከቦቹን ገዝቶ ብረቱን አቅልጦ መጠቀም አንደሚሻ ለመርከብ ድርጅት ያስታውቃል። መርከብ ድርጅትም የሜቴክን ጥያቄ በመቀበል ሜቴክ ለመርከብ ድርጅት 3.2 ሚሊየን ብር ለመከፈል ተስማምቶ መርከቦቹን ይረከባል። ይሁን እንጂ ሜቴክ መርከቦቹን ከማቅለጥ ይለቅ ወደ ዱባይ በመላክ 513 ሚሊዮን ብር ወጪ በማድረግ መርከቦቹን አስጠግኖ ወደ ንግድ ሥራ አስገብቷል ይላሉ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ። መርከቦቹ የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እያውለበለቡ መንቀሳቀስ ስለማይችሉ፤ ለጥገና ተብሎ የተሰጣቸውን ፍቃድ በመጠቀም ወደ ንግድ ሥራ ተሰማርተው ከኢራን-ሶማሊያ መስመር ጭምር በመንቀሳቀስ እስከ 500ሺህ ዶላር ድረስ ገቢ ቢያስገኙም፤ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ግን ለሜቴክ ገቢ ሳይደረግ ቀርቷል። በመጨረሻም መርከቦቹ 2.6 ሚሊዮን ዶላር መሸጣቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። ከመርከቦቹ በተጨማሪ ሃገራዊ ፕሮጀክቶችን ለመቃኘት አውሮፕላን ያስፈልጋል በማለት ከአንድ የእስራኤል ኩባንያ የአውሮፕላን ግዢ በሜቴክ መፈጸሙን ተናግረዋል። ከ50 ዓመታት በላይ ያገለገሉ፣ የነዳጅ ፍጆታቸው ከፍተኛ የሆነ እና የቴክኒክ ችግር ያለባቸውን አውሮፕላኖች ከታሰበላቸው ዓላማ ውጪ ለንግድ አገልግሎት ውለዋል ያሉት ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ ባለቤትነታቸው የሜቴክ ከሆኑ አምስት አውሮፕላኖች መካከል አራቱ አገልግሎት መስጠት ማቆማቸውንና አንዱ እስካሁን የት እንዳለ እንደማይታወቅ ጨምረው ተናግረዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ እስካሁን ድረስ በሰብዓዊ መብት ጥሰትና በሙስና የተጠረጠሩ 63 ግለሰቦች በቁጥጥር መዋላቸውን የተናገሩ ሲሆን፤ አሁንም በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ግለሰቦች መኖራቸውን ተናግረዋል። "ከሃገር ውጪ ያሉት ተጠርጣሪዎች የሚኖሩባቸው ሃገራት አሳልፈው እንደሚሰጡን ቃል ገብተውልናል" ብለዋል። • የዓመቱ ሐሰተኛ ዜናዎች በአፍሪካ • «በቋንቋው ሳያስተምር ያደገ ሃገር እኔ አላውቅም» ፕሮፌሰር አለማየሁ ገዳ ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ፤ አሁንም በስልጣን ላይ ያሉ በቁጥጥር ስር ያልዋሉ ተጠርጣሪዎች አሉ፤ ይህ እንዴት ይታያል? ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ "የአንድ ክልል የጸጥታ ቢሮ ኃላፊ አይደለም፤ የሃገር መሪም ቢሆን ከህግ በታች ነው። ወንጀል የፈጸሙ በሙሉ ለህግ ይቀርባሉ" ብለዋል። የተጠርጣሪዎች ፎቶግራፎች ዛሬ ወይም ነገ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም አክለዋል። የምርመራው ሥራ ሕግ እና ስርዓትን የተከተለ ነበረ? የሚል ጥያቄ የተነሳላቸው ሲሆን፤ "የትናንቱን አንደግምም፤ ምርመራዎቹ በሙሉ ሕግ እና ስርዓትን የተከተሉ ነበሩ፤ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎችም በስልክ ተጠርተው ነው ለፖሊስ ሪፖርት ያደረጉት" ብለዋል። ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጨምረው አስረድተዋል።
news-45812229
https://www.bbc.com/amharic/news-45812229
ስለ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ- ትህዴን ምን ያህል ያውቃሉ?
በቅርቡ በኢትዮጵያ የተካሄውን ፖለቲካዊ ለውጥ ተከትሎ ከሃገር ውጪ ነፍጥ አንግበው የኢትዮጵያን መንግሥት ሲወጉ የነበሩ ቡድኖች ወደ ሃገር እየተመለሱ ነው። ከእነዚህም መካከል ትናንት 2000 የንቅናቄውን ሰራዊት ይዞ ዛላምበሳ የደረሰው የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ይገኘበታል።
የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) መሃከሉ ላይ የአክሱም ሃውልት ያለበት አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ ዓላማ ያውለበልባል። ድርጅቱ ባለፈው ነሀሴ ወር ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በአሥመራ በተደረሰው ስምምነት መሰረት ወደ አገር ቤት ገብቶ ትግሉን በሰላማዊ መንገድ ለማካሄድ መስማማቱን የሚታወስ ነው። • ኢትዮጵያዊቷ ሰው አልባ አውሮፕላን • ቤተልሄም ታፈሰ፡ ''በሥራዬ እቀጥላለሁ'' • እንግሊዝ ሳዑዲን አስጠነቀቀች ለመሆኑ ትህዴን መቼ ተመሰረተ ? የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) በ1993 ዓ.ም በአሥመራ ተመስርቶ ላለፉት 17 ዓመታት በኤርትራ መንግሥት ወታደራዊና የትጥቅ ድጋፍ ሲደረግለት እንደቆየ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራና ሶማልያ አጣሪ ቡድን የተጠናቀረ ሪፖርት ያሳያል። የኤርትራ መንግሥት በተለይ የድርጅቱ ደንብ ቁጥር 1907 (2009) በመጣስ ለታጣቂ ኃይሉ ድጋፍ ያደርጋል የሚል ክስም አቅርቦ ነበር። በትግራይና በኤርትራ ድንበር አከባቢ የሚንቀሳቀሰው ትህዴን፤ በአከባቢው ደምሒት የሚል መጠሪያው ስሙ ይበልጥ ይታወቃል። ቡድኑ ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) 1993 ዓ.ም ላይ ባለመግባባት የተነጠሉ የቀድሞ ታጋዮች የመሰረቱት ሲሆን፤ ከመስራቾቹ አንዱ የሆነውና የድርጅቱ ከፍተኛ መሪ የነበረው አቶ ፍሰሃ ሃይለማርያም በ1997 ዓ.ም ላይ ተገድሎ ተገኝቷል። ገዳዮቹም ሆነ አሟሟቱን የሚመለከት ምንም አይነት ይፋዊ መረጃ የለም። ትህዴን ሊታገልለት የተነሳው ዓላማ ምን ነበር? የትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) መሃከሉ ላይ የአክሱም ሃውልት ያለበት አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ ዓላማ አለው። ትህዴን በድረ-ገፁ እንዳሰፈረው የሚታገልለት ዓላማ፤ በኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች መብት ሙሉ ለሙሉ የሚከበርበት ዴሞክራሲያዊ መንግሥትና ስርዓት ለመመስረት ነው ይላል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2014፤ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራና ሶማልያ አጣሪ ቡድን አገኘሁት ባለው መረጃ መሰረት፤ ትህዴን በምስራቃዊ የኤርትራ ክፍል ሓሬና በተባለው ደሴትና በኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ ሌላ አነስተኛ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እንደነበረው ቡድኑ ይገልፃል። መርማሪ ቡድኑ የቀድሞ ጄነራሎችን ዋቢ በማድረግ፤ ቡድኑ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ነፍጥ ካነሱ ድርጅቶች መካከል ከፍተኛ ወታደራዊ ኃይል የነበረው ነው ይላል። እስከ 20 ሺህ ወታደሮች እንደበሩት በመጥቀስ። "የኤርትራ መንግሥት ለሌሎች የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ከሚያደርገው ድጋፍ ሁሉ ለዚህ ቡድን የሚሰጠው ድጋፍ የላቀና የተደራጀ ነበር" ይላል የአጣሪ ቡድኑ ሪፖርት። አጣሪ ቡድኑ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ አልፎ አልፎ ወደ ኢትዮጵያ በተለይ ወደ ትግራይ እየዘለቀ ከሚያደርሰው ወታደራዊ ጥቃት በተጨማሪ ሌላ ተልዕኮም ነበረው ይላል። የድርጅቱ አባላት ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ይበልጥ ታማኝ ስለነበሩ በአሥመራና በቤተ መንግሥት አከባቢ የፀጥታና ደህንንት ጉዳዮች ዙሪያ እስከማማከር ደርሰው እንደነበር የአጣሪ ቡድኑ ሪፖርት ይጠቁማል። ይህንን ውንጀላ የኤርትራ መንግሥት እንደማይቀበለው በወቅቱ የፕሬዚዳንቱ ልዩ አማካሪ የማነ ገብረአብ ኣሳውቀው ነበር። የትህዴን ጣልቃ ገብነት በኤርትራ ህዝብ ዘንድ ቅሬታ አስነስቶ እንደነበርም ይነገራል።
news-45219224
https://www.bbc.com/amharic/news-45219224
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ባህርዳር ሊያቀኑ ነው ተባለ
የአማራ ክልል ኮምንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት፤ በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ አስመራ እንዲጓዝ እና ፕሬዚዳንት ኢሳያስ የሚመሩት የልዑካን ቡድን ወደ አማራ ክልል እንዲያቀና ተስማምተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ እና ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን የሚመራ የልዑካን ቡድን በአስመራ ይገኛል። የልዑካን ቡድኑ በቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ልዩ አማካሪ አቶ የማነ ገብረአብ ጋር የተወያዩ ሲሆን፤ የኤርትራውያንንና የኢትዮጵያውያንን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መነጋገራቸውን ገልጸዋል። በስምምነቱ መሰረትም በአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሚመራ የልዑካን ቡድን ወደ አስመራ የሚጓዝ ሲሆን፤ በኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራ የልዑካን ቡድን ደግሞ ወደ አማራ ክልል እንዲያቀና መስማማታቸውን አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታውቀዋል። • ስለ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ምን ያህል ያውቃሉ? • በኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት ሦስተኛ ወገን አልተሳተፈበትም ተባለ • ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች ኃላፊው የልዑካን ቡድኑ በኤርትራ ቆይታው፤ መቀመጫውን ኤርትራ ያደረገው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ ወደ አማራ ክልል ገብቶ በሰላማዊ ትግል የሚሳተፍበት ሁኔታ ላይ በመወያየት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውንም አስታውቀዋል። ከአመራሮቹ ጋር በተደረገው ውይይት፤ የአማራ ህዝብን መብትና ጥቅም በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በሰላማዊ ሁኔታ ለመታገል የሚያስችል ሀገራዊ እና ክልላዊ ሁኔታ መፈጠሩን በመገንዘብ፤ በሰላማዊ መድረክ ለመታገል ስምምነት ላይ መደረሱን ጨምረው ተናግረዋል።
53104054
https://www.bbc.com/amharic/53104054
“ከአሁን በኋላ ስለወላይታ የሚመለከተው የዞኑ ምክር ቤት ብቻ ነው የሚል እምነት አለኝ”
በደቡብ ክልል ምክር ቤት እኣካሄደው ባለው ጉባዔ ላይ የወላይታ ዞን ተወካዮች አለመሳተፋቸው ተሰምቷል።
ከስብሰባው ቀደም ብሎም በልዩ ስብሰባ ላይ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን የወላይታ ዞን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አበበች እራሾ ለመገናኛ ብዙሃን ገልፀው ነበር። የወላይታ ዞን በደቡብ ክልል 39 መቀመጫዎች እንዳሉት የሚታወቅ ሲሆን የዞኑ ተወካይ የምክር ቤት አባላት ትናንት በተጀመረው የክልሉ ጉባኤ ላይ እንዳልተሳተፉ ገልፈዋል። በበምክር ቤቱ ጉባኤ ላይ የዞኑ ተወካዮች ላለመሳተፍ የደረሱበትን ውሳኔ ምከንያት ሲያስዱም የዞኑ ሕዝብ ለምክር ቤቱ ያቀረበው በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ "ተደማጭነት አላገኘም" በሚል መሆኑን ገልፀዋል። የወላይታ ዞን ለደቡብ ክልል ምክር ቤት በራሱ ክልል ሆኖ ለመደራጀት ጥያቄውን ቢያቀርብም ሳይታይ በመቅረቱ የተነሳ ለፌሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ ማለታቸውን ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ወቅት አስረድተዋል። አፈ ጉባዔዋ ወ/ሮ አበበች እራሾ የወላይታ ሕዝብ ጥያቄውን በተገቢው መልኩ ለክልሉ ምክር ቤትም ሆነ ለፌደሬሽን ምክር ቤት ማቅረቡን አስረድተው፤ ከአሁን በኋላ የወላይታ ብሔን የሚመለከቱ አጀንዳዎች ቢኖሩ በብሔሩ ምክር ቤት ካልሆነ በፌደራል መስተናገድ አለባቸው እንጂ እኛ በሌለንበት በክልሉ ምክር ቤት መሆን የለበትም ብለዋል። ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ያደረጉትን ቆይታ እነሆ፡ በክልሉ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ ላለመሳተፍ የወሰናችሁበትን ምክንያት እስቲ አስረዱኝ? የወላይታ ብሔርን በክልል የመደራጀት ጥያቄ በተመለከተ ከአንድ ዓመት በፊት ነው ለደቡብ ክልል ምክር ቤት ያቀረብነው። ያንን ጥያቄ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በሕገ መንግሥቱ መሰረት መመለስ ነበረበት፤ ሥልጣኑ እስከዚያ ድረስ ነው። ሪፍረንደም ማደራጀት ነው። አላደራጀም። ከዚህ የተነሳ በዞኑ ላይ በርካታ ውጥረቶች ነበሩ። ይመለሳል በሚል እምነትም ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎች በሕጋዊ መንገድ ይመለሳሉ የሚል ተስፋ ተጥሎ ስንከታተል እስከ ታህሳስ 10/2012 ድረስ አንድ ዓመት እስኪሆነው ጠብቀናል። እስከዚያ ድረስ የተመለሰ ምንም ምላሽ የለም። ስለዚህ እኛ የብሔሩ ተወካዮች በክልሉ ምክር ቤት ወደ 39 መቀመጫ ነው ያለው። ስለዘህ በተለያዩ ጊዜ በተገኙ አጋጣሚዎች፣ በተደረጉ መደበኛ ያልሆኑ ጉባኤዎች አስፈላጊ ጉዳዮች በሚካሄዱበት ሁሉ አጀንዳው እንዲቀርብ በጽሁፍ የአሰራር ደንቡ በሚፈቅደው መሰረት ጠይቀናል። አባላት ደግሞ በየጊዜው በጉባዔ ላይ ተገኝተን በሚሰጠው እድል ለመጠየቅ ተሞክሯል። የሕዝባችንን ድምጽ ለመስማት ፍላጎት የለም። ስለዚህ ከዚህ የተነሳ እኛ ቀጣይ ምንድን ነው ማድረግ ያለብን የሚለውን የብሔሩ ምክር ቤት አስተዳደር አስቸኳይ ጉባኤ ተጠርቶ ነው ይግባኝ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እንዲሄድ ያደረገው። ስለዚህ ደቡብ ክልል ምክር ቤት ከአሁን በኋላ ለእኛ ምንም የሚሰጠው ምላሽ እንደሌለ ታምኖበት አባላት ቀጣይ በሚኖሩ ጉባዔዎች አንገባም የሚል አቋም ተይዞ ነው ያልገባነው። ይህ ማለት ዞኑ ከአሁን በኋላ በደቡብ ክልል ምክር ቤት ውስጥ ወካይ የለውም ማለት ነው? ተወካይ ቢኖር ባይኖር የሚተላለፉ ውሳኔዎች በአብላጫ ድምጽ ነው። የእኛ ጉዳይ የብሔሩ ፍላጎት እየታየ አይደለም። የውክልና ተግባር ሕዝብን እንጂ ግለሰብ እዚያ መቀመጫ ኖሮት፣ ቢገባም ባይገባም ያለው የአብላጫ ድምጽ ነው። ብሔሩ የራሱ ፍላጎት እየተጠበቀለት ስላይደለ የሌላው ፍላጎት ላይ ብቻ ውሳኔ እያስተላለፈ የሚመለስበት አሰራር ነው እስካሁን ድረስ ያየነው፤ ስለዚህ ይህ ለእኛ የሕዝቡን ክብር ማስጠበቅ ካልቻልን እዚያ ለሚቀጥሉት ጊዜያት መገኘት አስፈላጊ አይደለም። አሁን የተያዘው የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሕዝቡን ጥያቄ መመለስ አለበት የሚለውን የእኛን ጥያቄ ትኩረት እንዲያገኝ ለማድረግ ነው። የአባላቱ ቀጣይ እርምጃዎች ምንድን ነው የሚሆነው? ቀጣይ እምጃ የሚሆነው እኛ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ይግባኝ አስገብተናል። አሁን ከደቡብ ክልል ተከታትለን የምናገኘው ምላሽ የሚኖር አይመስለኝም። ስለዘህ ቀጣይ እርምጃው ፌዴሬሽን ምክር ቤት በአፋጣኝ ከምርጫ ቦርድ ጋር ተነጋግሮ የብሔሩን ሪፍረንደም እንዲያደራጅ የመከታተል ሥራ ነው የምንሠራው። • መንግሥት አደገኛ የሆነውን የትግራይን መገለል መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል- ክራይስስ ግሩፕ በቅርቡ በተደረገ ስብሰባ የደቡብ ክልል እንደ አዲስ እንደሚራጅ ተሰምቷል። ይህ ውሳኔን እስከ መጨረሻው ታግሳችሁ ለመከታተል አላሰባችሁም ነበር? አንደኛ እሱ ጉዳይ የእኛ ጥያቄ አይደለም። በዚህ መልኩ የደቡብ ክልል እንዲደራጅ የእኛ ጥያቄ እዚያ ውስጥ የለበትም። የጠየቅነው ራሱን ችሎ በክልል የመደራጀት ጥያቄ እና ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ ነው። ከዚያ ውጪ ያሉ ጥያቄዎች እና የሚወከሉ አካላትም ሕዝብ ተመራጮች ስላይደሉ በእርሱ ጉዳይ ውስጥ ብዙም ተሳትፊ አይደለንም። ለመሳተፍም አንፈልግም። እኛ ሕዝቡ የብሔሩ ጥያቄ እንዲመለስ ሕጋዊና ሕገመንግሥታዊ ጥያቄዎችን ነው ያቀረብነው። አሁን የተጀመረው ነገር የአገሪቱ መንግሥት በራሱ ተነሳሽነት የሚያድጋቸው ካልሆኑ በስተቀር ወደ ሕዝብ ቀርበው ሕዝብ ተችቶ ይመቸኛል ብሎ ሕዝብ የተቀበለው ነገር አይደለም። ስለዚህ አልተወያየንበትም እያሉኝ ነው? እኛ አልተወያየንም። አዲስ አበባ ላይ በነበረው ስብሰባ ላይ ተገኝታችሁ የነበራችሁን ቅሬታ አስረድታችሁ ነበር? እኛ ልንገኝም አንችልም። እኛ እኮ የሕዝቡን ጥያቄ፣ እኔ አሁን እንደ አፈ ጉባኤ የሕዝቡን ጥያቄ ነው የማስተባብረው እንጂ በዚያ ጉባኤ ላይ ልገኝም አልችልም። መገኘትም አልፈልግም። ምክንያቱን እርሱ አይደለም ጥያቄያችን። ስለዚህ በዚያ መልኩ ሊመለስ ከሆነ ራሱ አጀንዳውን አምጥቶ፣ ሕዝብ ሰብስቦ ማወያየት ያለበት ራሱ ነው። የኛ ጥያቄ በሕገ መንግሥቱ መሰረት እንዲመለስ ብቻ ነው የምንፈልገው። ወላይታ ዞንን ወክሎ በስብሰባው ላይ እንዲገኝ የተጋበዘ ነበር? የተጋበዙ አካላት ይኖራሉ። ግን እርሱ ላይ እኔ አስተያየት መስጠት አልፈልግም። ኮሮናቫይረስ በተስፋፋበት በዚህ ወቅት የእናንተን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ እድል ይኖራል ብለው ያምናሉ? እኔ እንግዲህ ኮሮናቫይረስ በአገራችን ላይ ከተከሰተ ወራት አስቆጥሯል። አሁን የምናነሳው ጥያቄ የአንድ ዓመት እድል የነበረው ነው። ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሄደም ስድስት ወር ያስቆጠረው ነው። በፍጥነት ከምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን ሪፍረንደም እንዲካሄድ የመስራት ጉዳዮች መስራት ከተቻለ እኮ የሁለት የሦስት ቀን ሥራ ነበር። ግን አልተሰራም። ይኼ ነገር አሁን በዚህ ወቅት ይመልሳሉ ወይ? አላውቅም። የራሳቸው የተሰጣቸው ስልጣን ስለሆነ በራሳቸው ስልጣን ገደብ ውስጥ ሆነው የሚሰጡትን ምላሽ እየተጠባበቅን ነው። አገሪቱ የኮሮናቫይረስ ወረረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በሚል የጣለችው የተለያዩ ገደቦች አሉ። በዚህ ገደብ ውስጥ ሆነው የፌዴሬሽን ምክር ቤትም ሆነ የምርጫ ቦርድ የወላይታን ጥያቄ መመለስ ይቻላሉ ብለው ያምናሉ? የሚቻልባው መንገዶች አሉ። ካልተቻለም እኮ ለሕዝቡ መነገር አለበት። አልችልም ብሎ መንገር አለበት እንጂ ሰበቡ አሁን ስለመጣ፤ በሰበብ ውስጥ ሆኖ የሕዝቡን ጥያቄ ማፈን አይቻልም። እናንተ ሁላችሁም ከደቡብ ክልል ምክር ቤት ወጥታችኋል እንደነገሩኝ፤ በደቡብ ክልል የሚተላለፉ ውሳኔዎች ቢኖሩ ጥያቄዎች ተቃውሞዎች ቢኖሩ የወላይታ ሕዝብን ወክሎ የሚናገረው በምክር ቤት ውስጥ አሁን ማነው? የሚቀርቡ አጀንዳዎች ናቸው የሚወስኑት። በብሔሩ ጉዳይ ከአሁን በኋላ መወሰን የሚችለው የብሔሩ ምክር ቤት ነው የሚል እምነት አለኝ። በብሔሩ ጉዳይ ማንም ከእዚያ ወላይታ እንዲህ ይሁን ብሎ አንስቶ ሊናገርም፣ ሊወስንም አይችልም። ስለዚህ ብሔሩን የሚመለከቱ አጀንዳዎች ቢኖሩ በብሔሩ ምክር ቤት መመራት አለባቸው። ካልሆነ በፌደራል መስተናገድ አለባቸው እንጂ እኛ እዚያ ባልተገኘንበት እና በሌለንበት ሁኔታ ስለእኛ አንስቶ ማንም ሊያወራ አይችልም። አጀንዳው ያድር ይሆናል እንጂ የሚል እምነት ነው ያለኝ። በሕዝቡ ጉዳይ ላይ ማንም ሌላ አካል ሊወስን አይችልም። ግን በራሳው አጀንዳዎች፣ ብሔርን በማይመለከቱ፣ አገርን ለመምራት ሕዝብን ለመምራት የሚሆኑ አጀንዳዎች በሚኖሩበት ጊዜ በአብላጫ ድምጽ እየሰሩ መቆየት ይችላሉ። ስለዚህ ከአሁን በኋላ ስለወላይታ የሚመለከተው የብሔሩ ምክር ቤት እንጂ የደቡብ ምክር ቤት አይደለም እያሉኝ ነው? አዎ!
news-44601780
https://www.bbc.com/amharic/news-44601780
የአሜሪካው ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርምራ ላይ መሰማራቱ ተገለፀ
በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን በሀገሪቱ ላይ እያከናወኗቸው ላሉ በጎ አስተዋፅኦዎች ለመደገፍ በወጡበት ሰልፍ በደረሰ የቦምብ ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲሞቱ፣ ከመቶ በላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የጥቃት አድራሾቹን ማንነት ለማወቅ ምርመራ እንደተጀመረ ፖሊስ ገልፆ የአሜሪካው ኤፍቢአይም በምርመራው ስራ ላይ እንደተሰማራ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ዘይኑ ጀማል ለቢቢሲ ገልፀዋል። በሀገር ውስጥም አደጋውን ለማጣራት ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ ተቋማትና ግለሰቦች የተውጣጣ አንድ ቡድን የተቋቋመ መሆኑንም ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል ጨምረው ተናግረዋል። "ምርመራው በጅምር ላይ ሲሆን እስካሁን ያለው ሂደት ጥሩ ነው" ብለዋል። የዚህን ቡድን ስራ ለመደገፍ ደግሞ የተሻለ ልምድ እና የተሻለ ቴክኖሎጂ ያላቸው የሌሎች ሃገራት የፖሊስ ተቋማት ቡድኑን በማገዝ ስራ ላይ ለማሳተፍ እቅድ መያዙንም ተናግረዋል። ለጊዜው በፈቃዳቸው የመጡት የአሜሪካው ኤፍ ቢ አይ መሆናቸውንምና ከቡድኑ ጋር በስራ ላይ መሰማራታቸውንም ገልፀዋል። እስካሁን ባለው ሂደትም 28 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጨምረው ተናግረዋል።
news-55421934
https://www.bbc.com/amharic/news-55421934
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ማብቂያ ያላገኘው ጥቃት
ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን፣ ቡለን ወረዳ፣ በኩጂ ቀበሌ ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት አካባቢ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ከ100 በላይ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይፋ አድርገዋል።
ቢቢሲ ያነጋገራቸው የቡለን መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች በበኩላቸው በዚህ ጥቃት ብቻ ከ30 በላይ ሰዎች በጥይትና በቀስት ተመትተው፣ በስለት ተወግተው የሕክምና እርዳታ ለማግኘት መጥተዋል። የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ የሆኑት አቶ መለሰ በየነ የሟቾችን ቁጥር "እጅግ በጣም ከፍተኛ" ከማለት ውጪ ትክክለኛውን ቁጥር ከመግለጽ ተቆጥበዋል። አክለውም በዞኑ የሰላም መደፍረስ እጃቸው አለበት የተባሉና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ የክልሉ ሰባት አመራሮች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተናግረዋል። ረቡዕ ማለዳ ጥቃት ከተፈፀመባት በኩጂ ቀበሌ አቅራብያ በምትገኝ ዶቢ ቀበሌ ማምሻውን በነበረ ጥቃትም አምስት ሰዎች መገደላቸውን ቢቢሲ ከነዋሪዎች መረጃ ያገኘ ሲሆን፤ የክልሉ ኮሙኑኬሽን ኃላፊ ስለጥቃቱ "መስማታቸውን ነገር ግን የተጣራ መረጃ እንደሌላቸው" ገልፀዋል። የመተከል ዞን አራት ወረዳዎች የፀጥታ ኃላፊነት ከመስከረም 14 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በኮማንድ ፖስት ስር እንዲሆን በተሰጠ ውሳኔ መሰረት የጸጥታ ማስከበሩን ሥራ የፌደራሉ መንግሥት ተረክቧል። በኮማንድ ፖስቱ ስር የሆኑት የዳንጉር፣ የወምበራ፣ ቡለን እና ጉባ ወረዳዎች ናቸው። የታኅሣስ 13 ጥቃት የተፈፀመባት በኩጂ በኩጂ ቀበሌ ከወረዳው መቀመጫ ከሆነችው ቡለን ከተማ 90 ኪሎ ሜትር ርቃ የምትገኝ ሲሆን የሺናሻ፣ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች ይኖሩባታል። በቀበሌዋ ይህ ጥቃት የደረሰው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድና ከፍተኛ የፌደራል መንግሥቱ እንዲሁም የክልሉ ባለስልጣናት ወደ አካባቢው ሄደው ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር በመገናኘት በክልሉ ስላለው የሰላም መደፍረስ ከተወያዩና የመፍትሔ አቅጣጫዎች ካስቀመጡ በኋላ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ መተከል ያመሩት ታኅሣስ 13/2013 ማለዳ ሲሆን ጥቃቱ የተፈፀመው ደግሞ የዛኑ ዕለት ምሽት ላይ ነበር። እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ከሆነ እንዲህ አይነት ጥቃት መድረስ የጀመረው ካለፈው ዓመት ጳጉሜን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን እስካሁን ድረስ በእነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ ሦስት ትላልቅ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በዚህም የበርካታ ንፁሃን ዜጎች ሕይወት አልፏል። ንብረት ወድሟል። እንዲሁም ቤት ንብረታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ምክንያት ሆኗል። በተለያየ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የፀጥታ መደፍረሶችን ተከትሎ ያጋጠሙ ክስተቶች እጅግ እንዳሳሰቡት ሲገልጽ ነበር። ኮሚሽኑ በጳጉሜ 1/2012 ዓ.ም እንዲሁም ከጳጉሜ 2 አስከ መስከረም 3/2013 ዓ.ም መካከል ቢያንስ ሁለት ጥቃቶች ማጋጠማቸውን ከክልሉ መንግሥት ማረጋገጡን ገልጾ ነበር። መስከረም 15 ቀን 2013 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ሰዓት ገደማ በመተከል ዞን፣ ዳንጉር ወረዳ፣ ማንቡክ ከተማ በንገዝ ወንዝ አካባቢ በሚገኝ መንደር ላይ በታጠቁ ሰዎች በተከፈተ ተኩስ የ15 ሰዎች ሕይወት ማለፉን በወቅቱ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣው መግለጫ ያሳያል። ኅዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም ደግሞ ሌሊት፣ በደባጤ ወረዳ ከወንበራ ወደ ቻግኒ በመጓዝ ላይ በነበረ የሕዝብ ማመላሻ አውቶብስ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከ30 በላይ ሰዎች መሞታቸው በወቅቱ በክልሉና በሰብዓዊ በብቶች ኮሚሽን ተገልጾ ነበር። በወቅቱ የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ "ይህ ጥቃት ሁላችንም በጋራ የተሸከምነውን የሰው ሕይወት ክፍያ ዛሬም በአሳዛኝ ሁኔታ የሚያሻቅብ ነው። የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች በፍጥነት ጥቃቱ የበለጠ እንዳይባባስ እርምጃ መውሰዳቸው አበረታች ነው" ብለው ነበር። ሦስተኛው ጥቃት ታኅሣስ 13 የተፈፀመውና ቢቢሲ ከነዋሪዎችና ከአይን እማኞች ባደረገው ማጣራት 120 ሰዎች ሕይታቸውን ያጡበት የአሁኑ ጥቃት ነው። ከዚህ ውጪ ግን ቢቢሲ ባደረጋቸው የተለያዩ ማጣራቶች በክልሉ ከመስከረም ወር ወዲህ ተለያየ መጠን ያላቸውን ጉዳቶች ያስከተሉ ወደ 20 የሚጠጉ ጥቃቶች ተፈፅመዋል። በመተከል ዘላቂ ሰላም ማምጣት ለምን አልተቻለም? የክልሉ መንግሥት በመተከል ዞን ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ አመራሮችን በሕግ ቁጥጥር ሥር እያዋለ መሆኑን ተናግሯል። የክልሉ የኮሙኑኬሽን ኃላፊ አቶ መለሰ በየነ እስካሁን ድረስ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል። በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው ያለበትን፣ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አመራሮችን በሚል በቁጥጥር ሥር ከዋሉት ውስጥ መካከል አቶ ቶማስ ኩዊ የኢፌዴሪ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የማኅበራዊ ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ፣ አቶ አድጎ አምሳያ የቀድሞው የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር፣ አቶ ሽፈራው ጨሊቦ የቀድሞ የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ዳይሬክተር፣ አቶ ባንዲንግ ማራ የመተከል ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ አቶ አረጋ ባልቢድ የመተከል ዞን የቀድሞ አመራር የነበሩ ይገኙበታል። ዛሬ በተጨማሪ ሁለት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እጃቸው አለበት በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አቶ መለስ በየነ ለቢቢሲ ተናግረዋል። እነዚህ ግለሰቦች አቶ ገመቹ አመንቲ፣ የክልሉ የግዢና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እንዲሁም አቶ አድማሱ መልካ የገጠር መንገድና ትራንስፖርት ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር መሆናቸውን ገልፀዋል። እነዚህ አመራሮች ከመተከል ዞን የጸጥታ ችግር ጋር እጃቸው እንዳለበት በመረጋገጡ በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል ይባል እንጂ ከዚህ ቀደምም በዚሁ ዞን ኅዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም በተከሰተ የጸጥታ ችግር ውስጥ እጃቸው አለበት የተባሉና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣት የተጠረጠሩ ከክልል እስከ ወረዳ ያሉ አመራሮች ላይ ፖለቲካዊ እርምጃ መወሰዱን የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ይስሃቅ አብዱልቃድር ለቢቢሲ ተናገረው ነበር። እነዚህ በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች አመራር የነበሩ 45 ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጉን በወቅቱ አቶ ይስሐቅ ገልፀዋል። በዚያ ጊዜ ከኃላፊነታቸው ከተነሱ የክልል አመራሮች መካከል የክልሉን ፖሊስ በምክትል ኮሚሽነርነት እየመሩ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች እንደሚገኙበት የክልሉ የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተናግረዋል። በዞን ደረጃ ስድስት አመራሮች፣ የዳንጉር፣ ቡለን፣ ወንበራ ወረዳ ዋና እና ምክትል አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ቁልፍ አመራሮችም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው የተነሳ ከቦታቸው መነሳታቸውን ጨምረው ተናግረው ነበር። በመተከል ዞን በተለያየ ወቅት በደረሱ ጥቃቶች እጃቸው አለበት ወይንም ኃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል ኃላፊዎችና ታጣቂዎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ሲውሉ አዲስ አለመሆኑን ያነሱት አቶ ይስሃቅ፤ አሁንም በዞኑ ማረሚያ ቤት የሚገኙና ሁለት ዓመት ሙሉ ክስ ያልተመሰረተባቸው ግለሰቦች እንደሚገኙ አስረድተዋል። ይህም ቅሬታን ፈጥሯል የሚሉት አቶ ይስሃቅ ይህ የሆነበት ምክንያትን ሲያስረዱ የእነዚህ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ የተያዘው በፌደራል መርማሪ ቡድን በመሆኑ እንደሆነ ይገልፃሉ። የፌደራል መርማሪ ቡድኑ በየጊዜው በተዘዋዋሪ ችሎት በመምጣት ጉዳዩን እንደሚመለከት የተናገሩት ኃላፊው የተፋጠነ ፍትህ አለማግኘት ቅሬታዎችን መፍጠሩን ይናገራሉ። ይህ በመተከል ዞን ብቻ የሚታይ ሳይሆን ካማሼ ዞንም አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙ ተጠርጣሪዎች መኖራቸውንም ገልፀዋል። እነዚህ ሰዎች የተፋጠነ ፍርድ እንዲያገኙ ክልሉ ከዐቃቤ ሕግ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ጨምረው ገልፀው ነበር። ጥቃቶቹ ለምን ይፈጸማሉ? ጥቃቱን እያደረሱ የሚገኙት ታጣቂዎች ከሌላ ቦታ የመጡ አለመሆናቸውን የሚገልፁት አቶ ይስሃቅ፣ በአብዛኛው ባለፈው ዓመት ጃዊ አካባቢ በነበረው ጥቃት "መንግሥት ሊከላከለን አልቻለም" በሚል ቅሬታ የገባቸው ወጣቶች ሸፍተው ጫካ መግባታቸውን ተናግረው ነበር። በወቅቱ ጥቃቱ ሲደርስ በአመራርነት ቦታ ላይ የነበሩ ግለሰቦች አልተጠየቁም የሚል ቅሬታ በወጣቶቹ ዘንድ መፈጠሩን ያነሱት አቶ ይስሃቅ፣ ነገር ግን የክልሉንና የአገሪቱን ሰላም የማይፈልጉ ኃይሎች በተለይ "ከሕዳሴ ግድቡ ጋር በተያያዘ" ወጣቶቹን በሱዳን ጠረፍ አካባቢ አስታጥቀው አሰልጥነው ወደ አካባቢው እንዲገቡ ማድረጋቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል። በማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃንም "መተከል የኛ ነው" የሚል ቅስቀሳ መኖሩ እና ይህም የአካባቢዎቹን ወጣቶች ላይ 'የእኛ እጣ ፈንታ ምንድን ነው?' የሚል ስጋት መፈጠሩን ተናግረዋል። ይህ ግን የአማራ ክልልም ሆነ የሕዝቡ አቋም አለመሆኑን የሚገልፁት አቶ መለስ "ጥቂት ኃይሎች የሚያራምዱት ሃሳብ" መሆኑን ይናገራሉ። ክልሉ መሬት ወስደው ሳያለሙ በተቀመጡ ባለሃብቶች ላይ በወሰደው እርምጃ ቅሬታ የገባቸው የተለያዩ ኃይሎችም የሚነሱትን ግጭቶች በመደገፍ ተሳትፎ ማድረጋቸውን አቶ ይስሐቅ ለቢቢሲ ገልፀው ነበር። ጥቃቱን ከፈፀሙ እና በተወሰደው እርምጃ በቁጥጥር ስር ከዋሉት በተገኘው መረጃ መሰረት በክልሉ የሚንቀሳቀስ አንድ ተፎካካሪ ፓርቲ ተልዕኮ እንደሰጣቸው የተናገሩ ወጣቶች መኖራቸውንም ጨምረው ተናግርዋል። ይህ አቶ ይስሃቅ በስም የሚጠቅሱት ተቃዋሚ ፓርቲ፣ ግልጽ ቅስቀሳ የሚያደርግ እንደነበር አንስተው፣ በተጨማሪ ደግሞ የአካባቢው መልከአምድር፣ እንዲሁም መሰረተ ልማቶች አለመሟላታቸው ለታጣቂ ኃይሎች እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን ገልፀዋል።
51009969
https://www.bbc.com/amharic/51009969
"አገር ትፈረካከሳለች ብዬ እፈራ ነበር" ጀዋር መሐመድ
ጀዋር መሐመድ በይፋ የተቀላቀለው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ብሔራዊ ፓርቲ (አብፓ) ጋር በጥምረት ለመሥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸው የተሰማው ባለፈው ሳምንት ነበር። ለመሆኑ ይህ ስምምነት ምን ይዞ ይመጣል ተብሎ ይጠበቃል? በቀጣዩ ምርጫ እንደሚሳተፍ ያሳወቀው ጀዋርስ ስለ ምርጫው ምን ያስባል? ቢቢሲ በነዚህ ጥያቄዎችና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ከጀዋር ጋር ቆይታ አድርጓል። ኦነግ፣ ኦፌኮና ኦ ብ ፓ በጥምረት ለ መ ሥ ራት መስማማታችሁን በቅርቡ ይፋ አድርጋችኋል። ይህ ጥምረት በምርጫ ወቅት ሕ ዝቡ ለእናንተ ለሚሰጠው ድምጽ ምን ያ ህ ል አስተዋጽኦ ይኖረዋል?
ጀዋር፡ እንግዲህ የዚህ ትብበር ዓላማና ይዘቱን በተመለከተ የፓርቲው አመራሮች በቅርቡ መግለጫ ስለሚሰጡ ከዛ በስፋት መረዳት የሚቻል ይሆናል። የፓርቲዎች ትብብርና አንድ ግንባር መፍጠር በተለይ ለዚህ የሽግግር ወቅት ምርጫ ሁለት ዋና ዋና ጥቅሞች ይኖሩታል የሚል እምነት አለኝ። አንደኛው የፓርቲዎቹ መተባባር ለፉክክር አዲስ ለሆነች አገርና ለመራጭ እንዲሁም ለፓርቲው አባላት ከምርጫው በፊት በቅድመ ምርጫ ቅስቀሳዎችና ማደራጀቶች ውስጥ ግጭት እንዳይቀሰቀስ ዕድል ይፈጥራል፤ መቀራረብን ይፈጥራል እንዲሁም ሰላማዊ የሆነ የምርጫ ቅስቀሳ እንዲካሄድ ዕድልን ይፈጥራል። ሁለተኛው ደግሞ በአንድ አይነት አካባቢ የሚወዳደሩ ፓርቲዎች አብረው ለመሥራት መቀናጀትና መስማማታቸው ድምጽ እንዳይባክንና የማሸነፍ ዕድላቸው ከፍ ማድረግ እንዲችሉ ይረዳቸዋል። እናም እነዚህ ሁለቱ ናቸው የትብብሩ ዋና ጥቅሞች። ከዚህ ቀደም የብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክንፍ ከአንተ ጋር አብሮ የመሥራት ጥያቄ አቅርቦልህ ነበር? ጀዋር፡ አሁን አይደለም፤ እንግዲህ እንደሚታወቀው ትግሉን በምናካሂድበት ወቅት እኛም ከውጪ ሆነን እነሱ ደግሞ ከውስጥ ትግሉን ያካሂዱ ነበር። አሁን ያሉትም ባይሆኑ ከነባርና አንጋፋዎቹ አመራሮች ጋር ሁለቱን ትግሎች አቀናጅተን ለአስርት ዓመታት የቆየ የትግል አጋርነት ነበረን። ይሄ ለውጥም አነስ ባለ ዋጋ በፍጥነት እንዲመጣ ከእነሱ ሰፊ የሆነ ትብብር ነበረን። ለዚህም ነው መንግሥት ሳይወድቅ ሥርዓት ሳይገረሰስ ወደዚህ ሽግግር ልንገባ የቻልነው። ግን አንድም ቀን አባላቸው ሆኜ አላውቅም፤ አብረንም ስንሠራ ነበር። የነበረንም ግንኙነት በዚህ መሰረት ነበር። በፓርቲ ደረጃ ግን አንድ ላይ ሆኖ አብሮ ለመሄድ የሚያስችለን ነገር የለም። ሰፊ የሆነ የአመለካካት ልዩነት አለን። ከዛ ባለፈ ግን ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅና ምርጫው የዚህ ትግል ውጤት ስለሆነ እንዲሁም የትግሉ ሌላ ምዕራፍ ስለሆነ እነሱ እንደ ገዢ ፓርቲ፣ እኔ ደግሞ እስከ ቅርብ ጊዜ እንደ አክቲቪስትና በአገሪቱ ፖለቲካ ጫና እንዳለው ሰው ተቀራርበን ስንሠራ ነበር። ወደፊትም እንሠራለን። የኦሮሞ አመራር ካውንስል አለ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው የሚመሩት። እኔም እንደ አንድ አስተባባሪ ስሠራ ነበረ። ከዚህ አንጻር ምርጫው በተሳካ መልኩ ችግር ሳይፈጠር እንዲካሄድ ወደፊትም አብረን መሥራት እንቀጥላለን። ከዛ ባለፈ ግን አንድ ወገን ሆነን ወደ ምርጫ የምንገባበት ዕድል አይታየኝም። የቀጣዩ ምርጫውጤት ይፋ ከተደረገ በኋላ አገሪቱ ወደምን አይነት ሁኔታ የምታመራ ይመስልሃል? ጀዋር፡ መረጋጋትም አለመረጋጋትም መኖሩን የሚወስነው የአገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን የሚያደርጉት ሥራ ነው። በተለይ የገዢው ፓርቲ የተሰጠው አደራ አለ፤ የአደራ መንግሥት ነው። ይሄ አደራ ለ27 ዓመት ሲጨቁነው፣ ሲበዘብዘው የነበረውን አምባገነናዊ ስርዓት ሕዝቡ ከፍተኛ ትግል አድርጎ አስገድዶ ወደ ለውጥ እንዲመጣ አድርጎታል። ለእነ ዐብይ [ጠቅላይ ሚንስትር] ደግሞ አደራ ሰጥቷል። አምባገነኑን ስርዓት አዳክመናል፤ ጥለነዋል፤ ስለዚህ ወደ ዴሞክራሲ አሸጋግረን የሚል ኃላፊነት ተሰጥቶታል። ከእነዚህ ኃላፊነቶች አንዱ ፍትሃዊ፣ ነጻ እንዲሁም ፉክክር የሚታይበት የምርጫ ስነ ስርዓት ማካሄድ ነው። ይህ ማለት የመንግሥት አካላት ከአላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት፣ ለገዢው ፓርቲ አለማዳላት፣ ግጭት እንዲቀሰቀሱ የሚያደርጉ ነገሮችን አለማድረግ ኃላፊነት አለባቸው። ኃላፊነታቸውንም መወጣት አለባቸው። የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ቢሆኑ ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸው። ምክንያቱም ይህ ምርጫ ሕዝባችን፣ ምናልባት ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ለሁለተኛ ጊዜ ሊሆን ይችላል ከ97ቱ ምርጫ ወዲህ የሚፈልገውን ፓርቲ፣ እጩ ወይም የሚፈልገውን መሪ የሚመርጥበት ስለሆነ ተቃዋሚዎችም ለግጭት በማይጋብዝና በተረጋጋ መልኩ ሕዝብ ሲቀሰቅሱና ሲያደራጁ፤ ውጥረት በማይፈጥር፣ ለዘብ ባለ መልኩ መሄድ ይጠበቅባቸዋል። • ኃይሌ ገብረሥላሴ ለ78 ሰዎች ሞት ፌስቡክን ወቀሰ ይሄን ደግሞ ለማድረግ መተማማን ይጠይቃል። የተቃዋሚውም አመራር በመሀከሉ ሰብሰብ ማለት አለበት። እንዲሁም ደግሞ ከገዢው ፓርቲ አመራሮች ጋር በመቀራረብ የግድ በሁሉ ነገር ባንስማማ እንኳን፣ ሌላው ቢቀር ሰላማዊ የምርጫ ቅስቀሳ፣ ሰላማዊ የድምጽ አሰጣጥ፣ ተዓማኒነት ያለው የድምጽ አሰጣጥና ቆጠራ እንዲካሄድ፤ ከዚያ በኋላ አሸናፊውም ተሸናፊውም ውጤቱን በጸጋ እንዲቀበል የሚያስችል ስምምነት ያስፈልጋል። ይሄን መገንባት ላይ ከሠራን ለሃምሳ፣ ስልሳ ዓመታት ብዙ ወጣቶች የተዋደቁለት ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፌደራላዊ ስርዓት ለመገንባት የሚያስችለንን ጅማሮ ላይ መድረስ እንችላለን። ያ ካልሆነ ግን ገዢው ፓርቲም እንደለመደውና 27 ዓመት ሲያደርገው እንደነበረው ወደ ማፈን፣ የመንግሥትን ሀብትና ተቋማት ለራሱ መጠቀምና ሌሎችን ለማግለል የሚሄድ ከሆነ፣ የተቃዋሚውም ኃይልም በቁጭትና በንዴት ብቻ እየተመራ የሚሄድ ከሆነ፣ ከምርጫ በኋላ ከፍተኛ አደጋ ሊመጣ ይችላል። ደጋግሜ እንደምለው ይሄ ምርጫ በአግባቡ ከተጠቀምንበት የአገራችን ትንሳኤ ሊሆን ይችላል፤ ያለአግባብ የምንሄድበት ከሆነ ግን የአገር መውደቅ፣ ወደ አገር መፈረካከስና እርስ በርስ ጦርነት ሊወስደን ይችላል። እውነቱን ለመናገር ሁሉም ነገር ምናልባት ከመቶ በሚያንሱ ሰዎች እጅ ነው ያለው ካልን ብዙም ማጋነን አይሆንም። ያሉት የፖለቲካ አመራሮች በተቃዋሚውም ደረጃ ያሉት፣ በገዢውም ፓርቲ ያሉት ከፍተኛ ኃላፊነት በሚሰማው መልኩ መንቀሳቀስ አለባቸው። አንዱም ወደዚህ የገባሁት ባለኝ እውቀትና ልምድ በዚን ያህል ለመርዳት ነው። እንግዲህ ፈጣሪ ብልሀቱን ከሰጠንና ትዕግስቱን ከሰጠን ጥሩ ነገር እንሰራለን የሚል ተስፋ አለኝ። ከምርጫው በኋላ አለመረጋጋቶች ሊኖሩ ይችላሉ የሚል የግል ስጋት አለህ? ጀዋር፡ አዎ አለኝ፤ ምክንያቱም እኔ የፖለቲካ ተመራማሪ ነኝ፤ ብዙ ለውጦችን አጥንቻለሁ። ብዙ ሽግግሮችን በአካል ሄጄ፤ የተሳኩትንም የተጨናገፉትንም አይቻቸዋለሁ። ሲከናወኑም ከተከናወኑም በኋላ በአረብ ሀገራት፣ በእስያ፣ በምሥራቅ አውሮፓ፣ በደቡብ አሜሪካ እንደ ታዛቢም እንደ ባለሙያም በቅርበት ሳያቸው ስለነበረ ስህተቶች እንዴት ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ስለምገነዘብ ስጋቶች አሉኝ፤ ፍርሀቶችም አሉኝ። ሁሌም ስናገር የነበረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን እንደያዙ በማግስቱ ማድረግ የነበረባቸው ከተቃዋሚው ጋር ቁጭ ብለው የሰፋውን የፖለቲካ ምህዳር እንዴት በአግባቡ እንጠቀምበት፤ እንዴት በኃላፊነት እንጠቀምበት፤ በተለይ ደግሞ ከዛሬ አንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ምርጫው ሩቅ በሚመስልበት ወቅት በምርጫ ቀነ ገድብ ላይ፣ በምርጫ አካሄድ ላይ፣ በምርጫ ሕግጋቶች ላይ ጠለቅ ያለ ውይይትና ስምምነት ያስፈልግ ነበር። • የኃይማኖት መፃዒ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? • በሙስሊሞች የሚጠበቀው የአይሁዶች ቤተ መቅደስ ያ ባለመሠራቱና በቂ ዝግጅት ስላልተደረገ ስጋት አለኝ፤ ትልቅ ስጋት አለኝ። የተስፋ ጭላንጭሎችም ይታዩኛል። በተለይ ሕዝቡ ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል ያሳየው አይነት ትጋት፣ የመንግሥት ንህዝላልነትና ድክመት፣ የፖለቲካ አመራሩ ስህተት የታየበት ሆኖ ሳለ በአገራችን ውስጥ የምንፈራው ግጭትና ቀውስ ባለመፈጠሩ ወደፊትም ሕዝቡ ከዚህ የበለጠ ሥራ ይሠራል፣ ከዚህ የበለጠ ትዕግስትና ብስለት ያሳያል የሚል እምነቱ አለኝ። አመራሩም ምርጫ በቀረበ ቁጥር እየተቀራረበ ይሄዳል የሚል ግምትና ተስፋ አለኝ። ወደ ምርጫው የገባህበት ዋነኛ ምክንያትህ ይኼ ስጋትህ ነው? ጀዋር፡ አዎ ይኼ ስጋት ነው። ለረዥም ጊዜ ስለውም ሳስበውም የነበረው እንደኔ ዓይነት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ በወጣቱ ላይ ተጽዕኖ ያለን፣ ዕውቀቱም ታዋቂነቱም ያለን ሰዎች ወደ ምርጫ ከምንገባ ይልቅ ባለን ተጽዕኖ በተቃዋሚውም፣ በገዢውም ፓርቲ ላይ ጫና እየፈጠርን ሽግግሩን ማካሄድ ነው የተሻለው የሚል ግምት ነበረኝ። ባለፈው አንድ ዓመትም ይህንን ነበር ስሞክር የነበረው። በተለይ ደግሞ የትጥቅ ትግል ባሉባቸው አካባቢዎች፣ በኦነግና በመንግሥት መካከል እርቅ እንዲፈጠር፣ ወታደሮች በሰላም ወደ ቀያቸው እንዲገቡ፣ ብዙ ሙከራ አድርገናል። የሕብረተሰብ ግጭቶች በነበሩባቸው በኦሮሞና ሶማሌ፣ በቤንሻንጉልና ኦሮሞ እንዲሁም በአማራና ኦሮሞ መካከልም ያሉ ግጭቶች እንዳይባባሱ ብዙ ጥረት ሳደርግ ነበር። በሂደት ግን ያየሁት፣ በተለይ ደግሞ በገዢው ፓርቲ አመራር ላይ ብዙ፣ የሽግግር ፖለቲካን ባለመረዳት፣ በአምባገነናዊ ሥርዓት ውስጥ ያደጉ ግለሰቦች ስለሆኑ፣ ሁሉንም ነገር በዚያ በተካኑበትና በለመዱት አምባገነናዊ አካሄድ፤ ማለትም ለፖለቲካ ችግር ፖለቲካዊ መፍትኼ ከመስጠት ይልቅ የሴኪዩሪቲ [ኃይል የመጠቀም] መፍትሄ ወደ መሻት ማዘንበሉ እያየለ ከመምጣቱ የተነሳ ምናልባት እንደኔ ተጽዕኖ ያለን፣ ልምዱም ያለን ሰዎች ወደ ተቃዋሚ ጎራ ከገባን ለመገሰፅም ጫና ለመፍጠርም የኃይል ሚዛኑንም ለማስጠበቅ፣ ይረዳል ወደሚለው እያዘነበልኩ መጣሁ። በሂደትም ካሉ አመራሮች፣ ምሁራን፣ ከተለያዩ ሽግግሮችን ከመሩ አመራሮች [ከኛ አገር ውጪ ካሉትም] ጋር ስንወያይ የኔ ወደተቃዋሞው መግባቱ የተሻለ አማራጭ ይሆናል ወደሚለው እያዘነበልኩ መጣሁ። ይህንንም ላሉት አመራሮች፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም፣ ለተቃዋሚውም፣ ለሁሉም አብራርቼ ነው ወደዚህ የገባሁት። ያለንን ዕውቀትና ተሰሚነት በመጠቀም ይህ ምርጫ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ሕዝባችን የሚፈልገውን ዓይነት በሕዝብ የተመረጠ መንግሥት እንዲያቋቁም እንዲረዳ ያለንን እውቀት ለመጠቀም፣ ያለኝን ጫና ለመጠቀም ነው ወደዚህ ለመግባት የወሰንኩት። በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የአሜሪካ ፓስፖርትህን የመመለስ ሂደት ላይ እንዳለህ ተናግረህ ነበር እርሱ ሂደት ምን ደረሰ? ጀዋር፡ ፓስፖርቴን መልሼያለሁ። በኔ በኩል የሚጠበቀውን ጨርሼያለሁ። ምንም የሚያግደን ነገር የለም። ሌላ በምርጫ ላይ ለመሳተፍ እንቅፋት ይሆኑብኛል ብለህ የምትጠብቃቸው ነገሮች አሉ? ጀዋር፡ ምንም የሉም። ምንም አልጠብቅም። በዚህ ምርጫ ውስጥ እንደማንኛውም የአገራችን ዜጋ፣ እንደ ማንኛውም የፖለቲካ አመራር፣ ኃላፊነቴን እወጣለሁ። መብቴንም እጠቀማለሁ የሚል ግምት ነው ያለኝ። ምንም የምጠብቀው ነገር የለም። ምርጫው የቀረው ጥቂት ወራት ነው። ከምርጫው በፊት የፖለቲካ ፓርቲዎች አጀንዳቸውንና ፖሊሲያቸውንለሕዝቡ ሲያስተዋውቁ አይታይም።ይህንን እንደ ችግር ታየዋለህ? ጀዋር፡ በጣም፤ በጣም እንደ ትልቅ ችግር ነው የማየው። የሽግግር ጊዜ ምርጫ የምንለው ከፍተኛ ዝግጅት፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣ ከፍተኛ ብልሃትና ብስለትን የሚጠይቅ ነው። የምርጫ ሕጉን ከማርቀቅ፣ የምርጫ ጊዜን ከመወሰን ጀምሮ ገዢው ፓርቲ ነው ብቻውን እየወሰነ የመጣው። በቂ ውይይት አልተካሄደም። በርግጥ ገዢው ፓርቲን ብቻ መኮነን አንችልም። የተቃዋሚ ፓርቲዎችም በጣም ኮስተር ብለው፣ ተባብረው፣ ተስማምተው ጫና አልፈጠሩምና በቁም ነገር አልተወሰደም። ምናልባት እዚህ አገር [የሽግግሩ] የመጀመሪያው ዘጠኝ ስምንት ወር የባከነ ጊዜ ነው የምለው። እና አሁን የፖለቲካ አመራሮቻችን በምርጫ ሕግጋትና አካሄድ ላይ ጥያቄ የሚያነሱበትን ሁኔታ ነው የምናየው። ይኼ ያሳዝናል። ከዚህ በፊት የዛሬ አንድ ዓመት፣ የዛሬ ሁለት ዓመት መነሳት፣ መፈፀም የነበረበት ነው። አሁን ደግሞ ምርጫው እንደታሰበው በሕጉ መሰረት ግንቦት ላይ የሚካሄድ ከሆነ የመራጮች ምዝገባ የሚጠናቀቅበትና ቅስቀሳ የሚጦፍበት ጊዜ ነበር። ያ አልተካሄደም። • "አባ ሳሙዔል አልታገዱም" አባ አማረ ካሳዬ በተለያየ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ የተለያዩ የፖለቲካ አመራሮች ባሉበት፣ በተለይ አቶ ሌንጮ ለታ ደጋግመው ጥያቄ አቅርበው ነበር። የዚህ ምርጫ መካሄድ አለመካሄድን በደንብ እንገምግመው፤ እንስማማበት የሚሉ የተለያዩ ሀሳቦች ሲነሱ ነበር። አድማጭ አልተገኘም። አቶ ሌንጮ ብቻ አይደሉም፤ አቶ ልደቱም የተለያዩ ሰዎችም ሲያነሱ እሰማለሁ። ግን በትኩረት አልተወሰደም። ስለዚህ ይህ ያሳስበኛል። ያም ሆነ ይህ ግን በኛ በኩል፣ እንደኔም ግምት ዝግጅት ቢኖር ጥሩ ነበር። ዝግጅት አለመኖሩ እንደሚታየን ገዢው ፓርቲ ዝግጅት ከተካሄደ የተቃዋሚው ፓርቲ አድቫንቴጅ [እድል] ይኖረዋል። ሊያሸንፍ ይችላል። ስለዚህ እኛ የመንግሥት አቅምና ቢሮክራሲ ስላለን መጨረሻ ላይም ብንገባ የተሻለ እድል አለን ወደሚለው መደምደሚያ የገቡ ነው የሚመስለኝ። ያ ስለሆነ ተቃዋሚው ጊዜ ማባከን የለበትም። ራሱን ማደራጀት፣ ማዘጋጀት ሕዝቡም ይህንን እድል ለመጠቀም ዝግጁ መሆን መቻል አለበት። በቂ ዝግጅት የለም፤ ግን ዝግጅት የለም ብለን ይህን ምርጫ፣ ይህንን በደም፣ በከፍተኛ መስዋዕትነት የመጣ ዕድል እንዲባክን መጠበቅ የለብንም። ሠርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ ቢባል ይሻላል፤ ያለበርበሬ ወጡን ከመብላት ሠርገኛ እየመጣም ቢሆን መቀንጠሱ ይሻላል። ስለዚህ አሁን መቀንጠሱን ማጣደፍ ነው። እዚህ ውስጥ እንግዲህ ሌላው ተዋናይ ምርጫ ቦርድ ነው። ምርጫ ቦርድ የሚጠበቅበትን እያደረገ ነው? ጀዋር፡ ምርጫ ቦርድ ካለው ነባራዊ ሁኔታ ብዙ ነገር እየሞከሩ ነው። እንግዲህ እስካሁን የፈተናቸው ወሳኙ የሲዳማ ሪፍረንደም ነው። መጀመሪያ ላይ በጣም ከፍተኛ ስህተት በመስራት የብዙ ሰዎች ሕይወት እንዲቀጠፍ ከፍተኛውን ሚና የተጫወተው ምርጫ ቦርድ ነው። ከዚያ በኋላ ግን ሪፍረንደሙን [ሕዝበ ውሳኔውን] በተሳካ ሁኔታ በማካሄዳቸው ሊመሰገኑ ይገባል። ከዚያ ወዲህ አንዳንድ የምናስተውላቸው ግድፈቶች አሉ። ለምሳሌ የገዢው ፓርቲን ውህደት ሙሉ በሙሉ ስርዓትን በጠበቀ መልኩ አይደለም ያካሄዱት። ለምሳሌ ጉባኤዎችን በሙሉ ሄደው ማየት ነበረባቸው፤ በተቃዋሚው ላይ የሚያደርጉትን አይነት ጠለቅ ያለ ምርመራ ሳያከናውኑ ነው ያደረጉት [ውህደቱን ያጸደቁት]። ትንሽ መድልዎ የሚመስል ነገር እየታየኝ ነው። አሁንም ግልጽነት የለም። የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ መቼ እንደሚወጣ የታወቀ ነገር የለም። ሕጉ ግን ውህደቶችና የትብብር ስምምነቶች ሁለቱ አስቀድመው መግባት አለባቸው ይላል። ግን መቼ እንደሚያስታውቁ የምናውቀው የለም። ግልፅነት ይቀረዋል። ከዚህ አንጻር አንዳንድ የሚያጠራጥሩ ነገሮች እየተፈጠሩ ነው። ሆኖም ግን አመራሮቹን አውቃቸዋለሁ። በተለይ ወ/ት ብርቱካን እዚህ አገር ዲሞክራሲ እንዲመጣ፣ ፍትህ እንዲመጣ በግንባር ቀደምትነት የታገሉ መስዋዕትነት ጭምር የከፈሉ ናቸው። በቅርብም የማውቃቸው ሰው ናቸው። እዚህ አገር ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ከሁላችን የበለጠ እንጂ ባነሰ መልኩ ቁርጠኝነት ያላቸው ሰው ናቸው ብዬ አላስብም። ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት መወጣት አለባቸው። ይህንን ታሪካዊ ኃላፊነት እንዳይወጡ ሊያግዷቸው የሚችሉ አንዳንድ ነገሮች እንዳሉ እናያለን። ለምሳሌ የምርጫ ወረቀቶች የሚታተሙት ዱባይ አገር ባለ ኩባንያ ነው ተብሏል። • "ከ[እኛ] የተለየን ጦር 5 በመቶ እንኳ አይሆንም" መሮ የኦነግ ጦር አዛዥ ይህ ኩባንያ ከዚህ በፊት በኡጋንዳ፣ በኬኒያና በተለያዩ አካባቢዎች የፈጸማቸው ግድፈቶች የምርጫ መዛባትን በመፍጠር፣ በፍርድ ቤትም የተከሰሰ፣ ሕዝብን ያጫረሰ ድርጅት ነው። እንዲህ አይነት ፊርማ ወስጥ ከመግባታቸው በፊት ወ/ት ብርቱካንም ሆኑ ሌሎቹ መመርመር ነበረባቸው። እንዲህ ዓይነት ነገ ለቁጭት፣ ለግጭት፣ ምርጫ ቦርድንም ለተጠያቂነት ሊያጋልጥ የሚችሉ ነገሮችን በጣም በጥንቃቄ መሄድ አለባቸው። ተስፋ አለኝ፤ ሕዝቡም በፀሎትም በሁሉም አብሯቸው እንደሚቆም። እኔም እንደ አንድ የፖለቲካ አመራር በተቻለ መጠን ላምናቸው እወዳለሁ። ስህተት ቢሰሩም አውቀው ሳይሆን ካለው ነባራዊ ሁኔታ ነው የሚል ግምት ውስጥ ነው የምገባው። ግን የሚቀጥሉት ወራት በጣም በጣም ወሳኝ ናቸው። በተለይ ደግሞ የገዢው ፓርቲና ተቃዋሚውን እኩል ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የማገልገል ሥራ በጣም በጣም ወሳኝ ነው። ውስብስብ የሆነው የአገራችን ፖለቲካ በእነዚህ ሰዎች እጅ ነው ያለው። አንዳንዴ ሳያውቁም ሊያዳሉ ይችላሉ። ከእንደዚህ ዓይነት ነገሮች ራሳቸውን እየቆጠቡ ሚዛናዊ በሆነ መልኩ እንዲሄዱ እማፀናለሁ። የተለያዩ ፓርቲዎች አብረው ለመሥራት የሚያስችሏቸው እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። አሁን አንተ ኦፌኮን ተቀላቅለሀል። ሕወሓት ከእናንተ ጋር አብሮ የመሥራት ጥያቄ ቢያቀረብ ትቀበላላችሁ? ጀዋር፡ በሕወሓትና በእነ ዐብይ መካከል የተፈጠረው በአንድ ቤተሰብ ውስጥ፣ በአንድ ፓርቲ ውስጥ የተከሰተ ግጭት ነው። ይህ ግጭት እንግዲህ ሕወሓት በበላይነት ኢሕአዴግን ሲመራ የነበረ ነው። አብረው አገር ሲዘርፉ ሲጎዱና ሕዝብን ሲያሰቃዩ ነበር። አሁን ይኼ ለውጥ ምስቅልቅላቸውን አውጥቷቸዋል። በመካከላቸው ያለው ግጭት ፖለቲካዊ ብቻ ሳይሆን የደህንነትም ጭምር ነው። ከሁለቱ አንዱን በማቅረብ የዚህ ውስብስብ፣ ብዙ ቆሻሻ ያለበት ግጭት አካል መሆን አንፈልግም። ሕወሓትም ሕገ መንግስቱንና ሕጉን በጠበቀ መልኩ ክልሉን እንደሚያስተዳድር ፓርቲ መብትና ግዴታውን እንደሚወጣ እንጠብቃለን። የፌደራል መንግሥቱም ሆነ የፌደራል መንግሥቱን እየመሩ ያሉት የቀድሞ ኢሕአዴጎችም ግጭትን ባረገበ መልኩ ከሕወሓት ጋር አላስፈላጊ እሰጥ አገባ ውስጥ ገብተው ትግራይንና የፌደራል መንግሥቱን አላስፈላጊ ግጭት ውስጥ ከማስገባት እንዲቆጠቡ በተደጋጋሚ ስንመክር ነበር። አሁንም የምንመክረው እርሱኑ ነው። ግን እንደኔ ግምትም ሆነ ምክር ሕወሓትን አሁን ወደ ተቃዋሚው በማምጣት በኢሕአዴግ መካከል የተፈጠረውን ግጭት ወደ ራሳችን መጋበዝ የለብንም። ሕወሓትም ራሱን ችሎ ከኢሕአዴግ ጋር የጀመረውን፣ ከቀድሞ ባልደረቦቻቸው ጋር የጀመሩትን፣ በሰላማዊና ሕጋዊ መልኩ እንዲጨርሱ [ነው የምንመክረው]። [ቀሪው ነገር] ወደፊት በሂደት ምናልባት ከምርጫው በኋላ አሸንፈው የሚመጡ ከሆነ የሚታይ ይሆናል። ከዚያ ወዲህ ግን የኢህአዴግን የበሰበሰና የተበለሻሸ፣ ብዙ ግለሰባዊ ሽኩቻዎች ያሉበት፣ የአገር ደህንነትን አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ሽኩቻዎችና ግጭቶችን፣ ወደ ተቃዋሚው በማምጣት ተቃዋሚውን የዚያ ሰለባ ማድረግ ትክክል ነው ብዬ አላምንም። እኔ ያለሁበትም ሆነ ሌሎቹ ፓርቲዎች እዚህ ውስጥ አይሳተፉም። የመከላከያ ሚኒስትሩ አቶ ለማ መገርሳ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ የመደመር ፍልስፍና እንደማያምኑ፣ የተቻኮለ መሆኑንም መግለጻቸውን ይታወሳል። በኋላ ደግሞ ተመልሰው አብረው ለመሥራት ተስማምተዋል። እንደዚህ አይነት ልዩነቶች ሲፈጠሩ ይህ የመጀመሪያው አይደለምና እነዚህ መንገራገጮች ያሰጉሀል? ጀዋር፡ ለማ መገርሳ የዚህ አገር ታላቅ ባለውለታ ነው። ይህ ትግል እየጦፈ በመጣ ወቅት፣ ሥርዓት ሳይፈርስ አገር ለአደጋ ሳይጋለጥ፣ በድርድር የሚካሄድ ሽግግር እንዲካሄድ፣ የእርሱ ቁርጠኛ አቋም፣ አመራር በጣም በጣም ወሳኝ ነበር። የአገራችን ከፍተኛ ባለውለታ ነው። ያም ብቻ ሳይሆን ዐብይ አሕመድን ወደ ሥልጣን ያመጣው ራሱ ለማ ነው። ከዚያ በኋላ ዐብይንም አገርንም በከፍተኛ ትዕግሥት አገልግሏል። ልዩነቶች መፈጠር ከጀመሩ ቆይተዋል። ግለሰባዊ አይደሉም። ሽግግሩ የተመራበት አካሄድ ትክክል አይደለም የሚል አቋም ወስዷል። ይህንን በውስጥ የምናውቀው ነው። ሆኖም ግን ሁለቱ ካላቸው ከፍተኛ ሚና አንጻር ሽግግሩ ላይ የሚኖረውን አደጋ ለማ በደንብ አድርጎ የሚረዳ ሰው በመሆኑ የተነሳ ረዥም ጊዜ በውስጥ ብቻ በተወሰኑ ሰዎች መካከል ይዞት ነው የቆየው። መጨረሻ ላይም ተቃውሞ ውህደቱን በአቋም ማክሸፍ ይችል ነበር። ያን ማድረግ ሊያመጣ የሚችለውን ግጭትና አለመረጋጋት በመገንዘብ ውህደቱ ከተፈፀመ በኋላ አቋሙን ለሕዝብ ግልጽ አድርጓል። ከዚያ በኋላም ነገሮች እየተባባሱ እንዳይሄዱ፣ በኦሮሚያ ውስጥ ሰፊ የሆነ በቢሮክራሲው ችግር መፈጠር ስለጀመረ ነገሮችን በውይይት እንፈታለን በሚል ነገሮችን ወደ መረጋጋት መመለስ ችሏል። • ወደ ኦሮሚያ፣ ሐረርና ድሬዳዋ ከተሞች የመከላከያ ሠራዊት መሰማራቱ ተገለፀ ከዚህ አንጻር ለማ አገርን ለአደጋ የሚያደርስ፣ ክልሉንም ፌዴሬሹኑንም ለአደጋ የሚጥል እርምጃ ይሠራል ብዬ አላምንም። ዐብይም ቢሆን ይህንን የሚረዳ ይመስለኛል። ወደፊትም እንግዲህ እየተወያየን፣ እየተረዳዳን ወደፊት የምንሄድ ነው የሚሆነው። ለማ ቀላል ሰው አይደለም። አሁን ብቻ ሳይሆን፣ ወደፊትም አገሪቱ ለምትወስደው እርምጃ ከፍተኛ ሚና የሚኖረው ሰው ነው። ከፍተኛ እውቀት፣ ተሰሚነት፣ ያለው ግለሰብ ነው። ወደፊትም ከተስማሙና ፓርቲውን ማሻሻል ሊያቀራርባቸው የሚችል ከሆነ በዚያ፣ ካልሆነ ግን ከተቃዋሚው ጋር በመሆን በግለሰብ ደረጃም ቢሆን ለአገር የሚጠቅም፣ ይህንን ሽግግር የሚያሳካ ሥራዎችን ይሠራል ብዬ ነው የማስበው። ለማ እንግዲህ የፖለቲካ መሪ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ አዋቂና እንደአገር ሽማግሌም የሚያረጋጋ ሰው ነው። ወደፊትም ለማ ብዙ ነገር ይሠራል የሚል እምነት አለኝ። አሜሪካ ሳለህ በአሜሪካ የደህንንት ወይም የመንግሥት መዋቅር ውስጥ ያለና ከአንተ ጋር በቅርብ በመነጋገር ወይም በሌላ መንገድ ታደርግ የነበረውን ትግል የሚደግፍ አካል ነበር? ጀዋር፡ትግሉን ስናካሂድ በነበርኩበትም አገርም ሆነ በተለያዩ አገራት ውስጥ ካሉ ምሁራን፣ የፖለቲካ አመራሮች ጋር ግንኙነት ነበረን። የሀሳብ ልውውጥም ሆነ ትችትም ምክርም ስወስድ ነበር። ከብዙዎች ጋር የተቀራረበ ሥራ ነበረኝ። ምክንያቱም እዚህ አገር ስናደርግ የነበረው እንቅስቃሴ አገራችንን ብቻ ሳይሆን በአገራችን ላይ ብሔራዊ ጥቅም አለን ብለው የሚያስቡ የተለያዩ አካላቶች ተጽዕኖ መፍጠር ይፈልጉ ነበር። ሊረዱ ይፈልጉ ነበር። እንግዲህ ከ [ትግሉ] ፀባይ አንጻር ከሁሉም ድርጅቶች፣ ከሁሉም ግለሰቦች፣ ከሁሉም አገር መንግሥታት ጋር የቀረበ ውይይት አደርግ ነበር። የሚጠቅም ሃሳብ ሲያመጡ የመውሰድ፤ የማይጠቅም ሃሳብ ሲያቀርቡና አገር ሊጎዳ ይችላል ብዬ ሳስብ ሃሳባቸውን ውድቅ ሳደርግ ነበር። ይኼ ነው ብዬ የምለው ግለሰብ የለም፤ ግን ከብዙ አገሮች፣ ከብዙ አመራሮች፣ ድርጅቶች፣ ተቋማት፣ ምሁራን ጋር የቀረበ ግንኙነት እንደነበረን አስታውሳለሁ። እነዚህ ግለሰቦች ቁልፍ የሚባል ሚና ያላቸው ግለሰቦች ናቸው? ጀዋር፡እንግዲህ የተለያዩ ምሁራኖች፣ የተለያዩ የመንግሥት አካላት የተለያዩ መንግሥታዊ ያልሆኑ የ'ቲንክ ታንክ' አመራሮች ጋር ስሠራ ነበር። ቁልፍ ይሁኑ አይሁኑ ብዙ ስለሆኑ አላስብም። ግን ብዙ ወሳኝ የሆኑ ምሁራኖች በተለይ ደግሞ በዲሞክራታይዜሽን ላይ በሽግግር ላይ የሚሠሩ ምሁራንና ተቋማት ጋር አብሬ ስሠራ ነበር። በግለሰብ ደረጃ ግን እከሌ የምለው አሁን የማስታውሰው የለም። ከወራት በፊት መንግሥት የመደበልህ ጥበቃዎች ሊነሱ መሆናቸውን በፌስቡክ ላይ ከጻፍክና በሌላ የጸጥታ አካላት የምትኖርበት አካባቢ መከበቡን በፌስቡክ ገጽህ ላይ ካሰፈርክ በኋላ በማግሥቱ ግጭት ተቀስቅሶ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል። እነዚህ ሕይወታቸው ያለፈ ሰዎችን ስታስብ ምንድን ነው የሚሰማህ? ጀዋር፡ይህንን የፈፀመው የመንግሥት አካል ነው። ሕግን፣ ሥርዓትን፣ ባህልን ባልተከተለ መልኩ ያንን እርምጃ ወስደዋል። በኋላ ላይ እንደተረዳሁት እኔን ብቻ ሳይሆን አገርንና ሽግግሩን አደጋ ላይ ሊጥል የሚችል እርምጃ ነው የወሰዱት። በጣም የሚያሳዝን የሚያሳፍር ክስተት ነበር። ይህ ስህተት፣ ይህ ወንጀል ለፈጠረው አደጋ ተጠያቂው የመንግሥት አካላት ናቸው። ይህንን ደግሞ የመንግሥት አካላት አምኖ የተቀበለው ሁኔታ ነው። በውስጥ አሠራራቸው አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ከሁሉም ጋር የተነጋገርንበት ሁኔታ ነው ያለው። በጣም ነው የማዝነው። ፈጽሞ ሊሆን አይገባም። ትናንትና አምባገነናዊ ሥርዓቱን ስንታገል ለመስዋዕትነት ዝግጁ ነበርን። ሕዝባችን ለመስዋዕትነት እንዲዘጋጅ ስንመክር ስንንቀሳቀስ ነበር። ዛሬ ግን ያ አስከፊ ስርዓት ሄዶ ወደ ዲሞክራሲ ለመሸጋገር ተስፋ ባለን ወቅት በማንኛውም ሁኔታ ሕዝባችን አይደለም ሕይወቱ ፍላጎቱ ራሱ እንዲጓደልበት አንፈልግም። በጣም ነው የማዝነው። ከዚህ ስህተት አገራችን አመራሮቻችን፣ ተምረው እንዲህ አይነት አደጋ ፈጽሞ እንዳይፈጸም እንዳንደግመው ቁርጠኛ ሆነን መቀጠል እንዳለብን ነው የምገልጸው። ከመነጋገር ባለፈ ጥፋቱን ፈጽመዋል የተባሉ ሰዎች ላይ የተወሰደ እርምጃ ስለመኖሩ የምታውቀው ነገር አለ? ጀዋር፡እኔ እስከማውቀው ድረስ በአንድም ሰው ላይ እርምጃ አልተወሰደም። ይህንን ያደረጉ ሰዎች በግልጽ ይታወቃሉ። የተካደ አይደለም። በዚያን ጊዜ ነገሮች እንዲረግቡ ነው የፈለግነው። ጉዳዩ በሕዝቡ ውስጥ ቁጣ ስለፈጠረ፣ ቁጣ እንዲረግብ ስለፈለግን አጀንዳ መሆን አልፈለግንም፤ ግን ከጠቅላይ ሚኒስትሩም ጋር በግልም በቡድንም ስንወያይ አጥብቀን ተናግረናል። በወቅቱ የመንግሥት አመራሮችም ደጋግመው እንደተናገሩት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም በሐረርጌ በአምቦ ባደረጉት ንግግር ጠንካራ የእርምት እርምጃ በአጥፊዎቹ ላይ ይወሰዳል ብለው ቃል ገብተው ነበር። እኔ እስከማውቀው ድረስ ግን እስካሁን ድረስ አንድም የተወሰደ እርምጃ የለም። • በኦሮሚያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት ሶስቱ ፓርቲዎች ጥምረት ለብልጽግና ስጋት? ይህ ደግሞ በጣም ያሳዝነኛል። እዚህ አገር እንዲህ አይነት ክስተቶች ብዙ እየተፈፀሙ፣ ሰዎች እየተገደሉ፣ እርምጃ እንወስዳለን ለሕግ ይቀርባሉ ይባላል። ለሕግ ሳይቀርቡ የቀጠሉበት ሁኔታ ነው ያለው። እና ያሳስባል። ምናልባት ምርመራቸውን ሲጨርሱ እርምጃ ይወስዳሉ የሚል እምነት አለኝ። የዛሬ አራት፣ አምስት ዓመት ወደኋላ ልውሰድህና ትግሉ በተጋጋለበት ወቅት ኢትዮጵያ የነበረችበትን ሁኔታ አይተህ ዛሬ ኢትዮጵያ ያለችበትሁኔታ እንደሚመጣ፣ አንተም ምርጫ እንደምትወዳደር አስበኸው፣ አልመኸው ታውቃለህ? ጀዋር፡በጣም ነው የፈጠነው። ትዝ ይለኛል እኤአ በ2005 ወደ አሜሪካ እንደሄድኩ በዚያ ላለው የኦሮሞ አመራር፣ በ2020 የኢህአዴግን ሥርዓት በመጣል ወደ ዲሞክራሲ መሸጋገር አለብን ብዬ ሳቀርብ [ፈገግታ] በጣም ነው የተቆጡኝ። 15 ዓመት ይህ አምባገነናዊ ሥርዓት እንዲቆይ ትፈልጋለህ እንዴ በሚል፤ እንደውም እነርሱ ናቸው የላኩት የሚል ማጣጣል ነበር የደረሰብኝ። ከዚያ በኋላ በስፋት አጠናሁ። በተለይ ሰላማዊ ትግልን በሕንድ አገር፣ በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ፣ በተለያዩ አገራት በመሄድ በስፋት ካጠናሁ በኋላ ይመስለኛል ከ2007 በኋላ ዕቅድ ነደፍን። በ2020 እኤአ ይህንን ሥርዓት መጣል አለብን የሚል አቅደን ነው ወደ እንቅስቃሴ የገባነው። ነገሮች በጣም በጣም ፈጠኑ። ሁለት ዓመት ቀድሞ ያ ያሰብነው በመሳካቱ ፍጥነቱ ስኬት ብቻ ሳይሆን ጉዳትም አምጥቷል። • "ያለን አማራጭ ውይይት ብቻ ነው" ጀዋር መሐመድ አንዳንድ ያሰብናቸው ነገሮች ነበሩ። ለምሳሌ ፓርቲዎችን የማደራጀት፣ አቅም የመገንባት ሥራዎች ወደኋላ ቀሩብን። አንዳንዴ ቁጭ ብዬ ሳሰላስል ምናልባት አሁን የምናያቸው ችግሮች፣ ስህተቶች፣ በአግባቡ ያልተመራ ለውጥ ሽግግር ሳይ በአግባቡ ልንመራው እንችል ነበር የሚል ግምት አለኝ። አንዳንድ የፈራኋቸው ነገሮች አሉ። ስለሽግግር መናገር መጻፍ የጀመርኩት 2016 አካባቢ ነው። ከእሬቻው ክስተት በኋላ። ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ሊገባ ይችላል በሚል በጣም ሰግቼ ነበር፤ አንዱ ኢሕአዴግ እንዳይወድቅና በውስጡ ለውጥ እንዲመጣ በጣም የገፋሁበት ምክንያት ኢሕአዴግና መንግሥት፣ መንግሥትና አገር አንድ ስለሆኑ መፈረካከስ ይመጣል ብዬ እፈራ ነበር። ያ በፈራሁት ደረጃ ባለመምጣቱ ደስተኛ ነኝ። ሆኖም ግን የነበረኝ ተስፋ እነ ዐብይ መጀመሪያ እንደመጡ አካባቢ፣ ገዱና ለማ ሊሰጡ ይችሉ የነበረው አመራር፣ ሁለቱ ከቦታቸው በመነሳታቸውና በመገፋታቸው የተፈጠረው ክፍተት አደጋ ጋርጦብናል። ዛሬ ለምርጫ አምስት ወር ቀርቶን የምናያቸው መልፈስፈሶች፣ የምናያቸው ብልሃት የጎደላቸው ንግግሮችና እርምጃዎችን ሳይ ደግሞ ያሳዝነናል። ሆኖም ግን አምስት ዓመት ወደኋላ ሄጄ ሳስብ ፍጥነቱ በጣም ይገርመኛል። የደረስንበት ሁኔታ ደግሞ ተስፋ ይሰጠናል። ቅድም እንዳልኩት በተስፋ፣ በስጋት፣ በቁጭት መካከል ነው ያለሁት። ግን ለምርጫ እወዳደራለሁ የሚል ግምትም እቅድም አልነበረኝም። እኔ አላማዬ አምባገነን የነበረውን ሥርዓት አምበርክከን፣ ሽግግር ጀምረን ከዚያ ኮምፒውተሬን ሰቅዬ ወደ ዩኒቨርሰቲ መመለስ ነበር። ያ አልሆነም። አሁንም ተገድጄ በትግል ውስጥ እንድቆይ የሆንኩበት ሁኔታ ደግሞ ትንሽ ይቆጨኛል።
news-48812473
https://www.bbc.com/amharic/news-48812473
ኢትዮጵያ ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር እንዴት ትውጣ?
የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ እንደሆነ በመንግሥት የሚገለጸው የባህር ዳሩ አመራሮችና የአዲስ አበባ ጄነራሎች ግድያ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስተዳደርን ፈተና ውስጥ ከከተቱ ጉዳዮች መካከል ቀዳሚው ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም። ይህ ክስተት ከሚኖረው ዘላቂ አንደምታ አንጻር በርካታ ትርጓሜ እየተሰጠው ነው።
አቶ የሱፍ ያሲን፣ ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ እና ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮል በርካቶች ያልተጠበቀ ነገር እንደሆነ የሚገልጹት ይህ ሁኔታ የቀድሞው ዲፕሎማትና የፖለቲካ ተንታኝ አቶ የሱፍ ያሲንና በአሜሪካ ኤንዲኮት ኮሌጅ የሰብዓዊ መብትና ዓለም አቀፍ ህግ መምህር የሆኑት ዶ/ር ሰማኸኝ ጋሹ በሃገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ እንደዚህ ያለ አደጋ ሊፈጠር እንደሚችል የሚያሳዩ ምልክቶች እንደነበሩ ይናገራሉ። • "ሌሎችንም ከፍተኛ ባለስልጣናት የመግደል ዕቅድ ነበረ" "ክስተቱ ያስደነግጣል ነገር ግን ያልተጠበቀ አይደለም" የሚሉት አቶ የሱፍ ከባድ ችግር ሊከሰት እንደሚችል የሚያመላክቱ በርካታ አስጊ ሁኔታዎች በአማራም ይሁን በሌሎች ክልሎች ውስጥ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ እንደታዩ ጠቅሰው "ነገር ግን በዚህ መልክ ወደ መጠፋፋት ይደርሳል የሚል ግምት አልነበረኝም" ይላሉ። ዶ/ር ሰማኸኝም የሃገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ከፈት ባለበት የለውጥ ጊዜ ውስጥ ብሔርተኛ ኃይሎች ጉልበት አግኝተው መውጣታቸው እየተከሰቱ ላሉት ችግሮች ምክንያት እንደሆነ ያነሳሉ። ይህ ደግሞ "በሚሊሻ፣ በቄሮ ወይም በፋኖ መልክ፤ ሁሉም ግን የራሱን መብት ለማስጠበቅ፣ ሌላውን እንደ ስጋትና እንደ ጠላት የሚያይበት ሁኔታ ተፈጥሯል" በማለት ሰኔ 15 2011 ዓ.ም የተፈጠረው ዓይነት ትልቅ አደጋ ሊያስከትል እንደሚችል ያስታውቅ እንደነበር ያስረዳሉ። ከአንድ ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በአስቸጋሪና በመስቀለኛ መንገድ ላይ ናት እየተባለ ሲነገር ቆይቶ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ "በኢትዮጵያ ውስጥ የነበረው ስጋት እየቀነሰ፣ ተስፋ እየገዘፈ እየመጣ ነበር" የሚሉት አቶ የሱፍ በቦታው የሚታዩት ይህን መሰል ግጭቶች፣ መፈናቀሎችና መጠራጠሮች የተጀመሩትን የለውጥ እርምጃዎች የሚያደናቅፍና የታየውን ተስፋ ሊያጨልም ይችላል ይላሉ። • የሥራ ኃላፊነታቸውን "ከባድና የሚያስጨንቅ... ነው" ያሉት ዶ/ር አምባቸው ማን ነበሩ? ለዚህ ደግሞ ብሔርን መሰረት ያደረገው ፌደራሊዝም አለመተማመንና አንዱ ሌላውን እንደ ጠላት እንዲያይ ክፍተት የሚተው ነው የሚሉት ዶ/ር ሰማኽኝ፤ ባለፉት 27 ዓመታት በአማራ ሕዝብ ላይ ደረሱ በተባሉት በደሎች ምክንያትነት የተለያዩ ሃሳቦች ተነስተዋል ሲሉ ያስረዳሉ። የሰሞኑ ክስተትም ከዚህ ጋር እንደሚያያዝ የሚያምኑት ዶ/ር ሰማኸኝ "ምን ዓይነት ብሔርተኝነት የተሻለ የአማራን ሕዝብን ጥቅም ያስከብራል በሚለው ላይ በአማራ ልሂቃን መካከል ያለመግባባት ውጤት ነው።" ባለፉት 27 ዓመታት ሃገሪቱን በፍጹም የበላይነት ሲያስተዳድር የነበረው ኢህአዴግ በጠንካራ ክንድ አሁን በየቦታው የሚከሰቱትን አሳሳቢ ችግሮች በአስተዳደራዊ፣ በፖለቲካዊ እንዲሁም በወታደራዊና በደኅንነት ተቋሞቹ በኃይል ተቆጣጥሮ ቢቆይም ለውጡ ያመጣው ነጻነት ችግሮቹ በየቦታው እንዲከሰቱ እንዳደረገ ይነገራል። አንዳንዶች እንዲያውም የሚታዩት አሳሳቢ ነገሮች የቀድሞው ጠንካራ ገዢ ፓርቲን መዳከም አመላካች እንደሆነ ይጠቅሳሉ። የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቅርብ የሚከታተሉት ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮል እንደሚሉት "የኢሕአዴግ ማዕከላዊ ጥንካሬ መፍረክረክ የጀመረው ከዚህ ክስተት ቀደም ብሎ ህወሐት ከማዕከሉ ገሸሽ ከተደረገ ጀምሮ ነው" ይላሉ። አክለውም ሃገሪቱ ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት በተለይ የገዢው ፓርቲ ትልልቆቹ አባላት ኦዴፓና አዴፓ በአንድነት መስራት እንዳለባቸው ይመክራሉ። "ኦዴፓ ከፍተኛ ጥንቃቄ ካላደረገ የአዴፓን ድጋፍ ሊያጣ ይችላል። የአማራና የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጥምረት ከተዳከመ ማዕከላዊ መንግሥቱን ማዳከሙ አይቀርም" ይላሉ። • "በዚህ መንገድ መገደላቸው ከፍተኛ የፀጥታ ችግር መኖሩን ያሳያል" ጄነራል ፃድቃን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አስተዳደር ሕግና ሥርዓትን በመላው ሃገሪቱ በማስከበር በኩል መውሰድ ያለባቸውን ያህል እርምጃ አለመውሰዳቸው መንግሥታቸውን በደካማነት እንዲታይና ይህም ወቀሳ እንዲሰነዘርባቸው አድርጓል። አቶ የሱፍ ያሲንም "ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጡ በኋላ መንግሥት እንደ መንግሥት ግርማ ሞገሡንና ሉዓላዊነቱን አላስከበረም በዚህም ምክንያት በመላው ሃገሪቱ ከሥርዓትና ከሕግ ውጪ ብዙ ነገሮች ሲደረጉ ቆይተዋል" ይላሉ። "ጠንካራና ኃያል ገዢ እንጂ መሪ የሚባለው በብዙ መልኩ አይወጣልንም ወይም አይዋጥልንም" የሚሉት አቶ የሱፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተከሰቱ ያሉ ሁኔታዎችን "ለማስተካከልም ሆነ ጠንካራ አመራር ለመስጠት ፈርጠም ያሉ እርምጃዎችን ወደ መውሰድ መገፋፋታቸው አይቀርም" በማለት ይህ ደግሞ ቀድሞ ወደነበረው ሁኔታ ሊመልስ እንደሚችል ይሰጋሉ። የሰሞኑ ክስተት ከፖለቲካው ባሻገር የደህንነት መዋቅሩ ያለበትን ክፍተት የሚያሳይ ነው የሚሉት ደግሞ ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮል ናቸው። "ድርጊቱ የተፈጸመው በአማራ ክልል ልዩ ኃይል ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን እነሱም አጠቃላይ የሃገሪቱ የጸጥታ አካል ናቸው። የጸጥታ መዋቅሩ በዚህ ደረጃ መዳከሙ አሳሳቢ ነው። መንግሥት የጸጥታ መዋቅሩን ሊፈትሸው ይገባል" ይላሉ። ፈታኙን ጊዜ ለማለፍ ባለፈው አንድ ዓመት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ያጋጠሙት አሳሳቢ ሁኔታዎች ከጊዜ ጋር እየሰከኑና መፍትሄ እያገኙ እንደሚሄዱ ሲነገር ቆይቷል። ነገር ግን ባህር ዳርና አዲስ አበባ ውስጥ ያጋጠመው ችግር ገና ብዙ መደረግ ያለባቸው ጉዳዮች እንዳሉ የሚያመለክት ከባድ ፈተና እንደሆነ እየተነገረ ነው። አሁን እየታዩ ያሉት ችግሮች ወደፊት ሊከሰቱ ለሚችሉ የከፉ ችግሮች የማስጠንቀቂያ ምልክቶች ናቸው፤ አቶ የሱፍ ያሲን "ሁሉም ይረጋጋ፤ ያረጋጋ የሚለውን ሃሳብ ተግባራዊ ማድረግ አለበት። ሃሳብ ከሚሰጠው ጀምሮ ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች በሙሉ መረጋጋትና ከስሜታዊነት በመራቅ እየተከሰቱ ያሉት ነገሮች ሃገሪቱንና ሕዝቧን ወዴት ሊወስዱት እንደሚችሉ በኃላፊነት ስሜት ለመረዳት መሞከር አለባቸው" ይላሉ። ከዚህ በተጨማሪ ዶ/ር ሰማኽኝ ጋሹ የታሪክ ተቃርኖዎች በሚሏቸው ጉዳዮች ላይ በመነጋጋር እንደ አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብና እንደ አንድ ሃገር እንዴት እንቀጥል ብሎ ተነጋግሮ ብሔራዊ እርቅ ላይ የመድረስ አስፈላጊነት ላይ አጽንኦት ይሰጣሉ። ለዚህም የገዢነትና የጭቆና ትርክቶች እንዲሁም በሥራ ላይ ያለውን ሕገ መንግሥት ጨምሮ ባሉ ጉዳዮች ላይ በግልጽ በመነጋገር የጋራ መግባባት ላይ የመድረስን አስፈላጊት ይናገራሉ። ስለዚህ እነዚህ ተቃርኖዎች እንዴት ይታረቁ? ሲሉ ይጠይቃሉ ዶ/ር ሰማኸኝ፣ ጠ/ሚ ዐብይ በንግግር ደረጃ ኢትዮጵያዊነትን በማስቀደምና እርቅን በማድረግ እነዚህ ተቃርኖዎች ለማስታረቅ ሞክረዋል። በተግባር ግን መፍትሄ ተብለው የቀረቡ ነገሮች መሰረታዊውን ችግር የሚፈቱ እንዳልሆኑ ይናገራሉ። አሁን ጠ/ሚ ዐብይ ሲፈልጉ እንደሚጋብዙት ዓይነት ሳይሆን ሁሉንም የፖለቲካ ሃይል የሚያሳትፍ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ሂደት አገሪቱ የተጋረጠባትን ፈተና የምታልፍበት ሁነኛ መንገድ ነው ይላሉ። • "ከፍተኛ ችግር ውስጥ ገብተናል. . . ግን እናሸንፋለን" አቶ የሱፍም በቀዳሚነት በየክልሉ የሚታዩ ግጭቶችና መፈናቀሎችን ማስቆም እንደሚያስፈልግ በማንሳት "በፖለቲካ ልሂቃኑ መካከል ባሉ የሚቃረኑ ፍላጎቶችና መጠራጠሮች ላይ በመነጋገር ሰጥቶ በመቀበል መርህ ስምምነት ላይ መደረስ አለበት።" ሁሉንም ነገር በአንድ ጀንበር መቀየር ሃገሪቱን ለከፋ ምስቅልቅል የሚዳርጋት ስለሆነ፤ ያለምንም ጥድፊያ በረጅም ጊዜ ሂደት መደረግ ያለባውን ጉዳዮች በመለየት ማንም ሳይገለል ይመለከተኛል የሚሉ ሁሉም ወገኖች ተሳታፊ ሆነው የጋራ መግባባትና ስምምነት ላይ መድረስ ወቅቱ የሚጠይቀው ነገር እንደሆነ አቶ የሱፍ ይገልጻሉ። ሰሞኑን ከተከሰተው ጉዳይ ጋር በተያያዘ በርካታ ጥርጣሬን የሚያጭሩ ነገሮች እየተከሰቱ በመሆናቸው "የተፈጠረውን ነገር በማጣራትና በመመርመር ረገድ ገለልተኛ አካላትን ማሳተፍ ተአማኒነት እንዲኖር ያደርጋል ብለው እንደሚያስቡ የሚናገሩት ዶ/ር ሰማኸኝ አክለውም መንግሥት "በአሁኑ ወቅት የአማራ ክልል ዋናውን ሥራ እንዲሰራ በማድረግ፤ የፌደራል ፖሊስም ሆነ ሌላ የፌደራል የፀጥታ ኃይል በክልሉ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የተቆጠቡ መሆን አለባቸው" ይላሉ። • "ብ/ጄነራል አሳምነው በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው የተገደሉት'' በርካቶች ሃገሪቱ አሳሳቢ ሁኔታ እንደገጠማት ይስማማሉ፤ ቀጣይ አቅጣጫዋ ወደ የት ሊያመራ እንደሚችል ማወቅ የበርካቶች ፍላጎት ነው። ፕሮፌሰር ሼትል ትሮንቮል እንደሚሉት "ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አጭር ጊዜያት አንገብጋቢና ጊዜ የማይሰጡ ጥያቄዎችን መፍትሄ ልታገኝላቸው ይገባል" ይላሉ። ከእነዚህም ውስጥ በሚቀጥለው ዓመት ግንቦት ወር ይደረጋል ላይ የሚባለው ምርጫ ዋነኛው ጉዳይ ነው። እየተከሰቱ ካሉ ሁኔታዎች አንጻር ሃገሪቱ እንዴት ነው ሰላማዊ ምርጫ የምታደርገው? የሚለው አሳሳቢ ነገር እንደሆነ ጠቅሰው "ምርጫውንም አለማድረግም ሌላ ፈተና" እንደሆነ ፕሮፌሰር ሼትል ያመለክታሉ። ኢትዮጵያ ከገጠማት ፈተና አንጻር ከችግር ለመውጣት በፖለቲካ ልሂቁ መካከል ሃቀኛ ንግግር ማድረግና ሰጥቶ በመቀበል ስምምነት ላይ መድረስ ወሳኝ እንደሆነ በርካቶች ያምናሉ።
50078477
https://www.bbc.com/amharic/50078477
"በማዕከላዊና ምዕራብ ጎንደር የጥምር ኃይል ሊሰማራ ነው" የአማራ ክልል ደኀንነትና ጸጥታ ካውንስል
በማዕከላዊና በምዕራብ ጎንደር ዞኖች፣ በጎንደር ከተማ እንዲሁም በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር "ማንነትን ሽፋን" በማድረግ ባለፉት አምስት ዓመታት የጸጥታ መደፍረስ፣ የሰው ህይወትና ንብረት መጥፋት መከሰቱን የአማራ ክልል ደኀንነትና ጸጥታ ካውንስል ትናንትና አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ ላይ በመግለፅ፤ ዘላቂ ሰላም ለማምጣት ይሆናሉ ያላቸውን መመሪያዎች አስተላልፏል።
በክልሉ የማንነት ጥያቄዎችን ላነሱ ወገኖች ምላሽ መስጠቱን ያስታወሰው ይህ መግለጫ ቅሬታ ያላቸው አካላት ጥያቄያቸውን አቅርበው መስተናገድ "የሚችሉበት ዕድል እያለ" በኃይል ፍላጎታቸውን ለማስፈፀም መሞከራቸውን "ጸረ ህገ መንግስትና የለየለት ጸረ ሰላም ተግባር" ሲል ኮንኖታል። መግለጫው አክሎም "የቅማንት የራስ አሥተዳደር ኮሚቴ የተከተለው አቅጣጫም ፍላጎትን በኃይል በብሔረሰቡና በክልሉ መንግስት ላይ የመጫን "ኢ ህገ መንግስታዊ እንቅስቃሴ" መሆኑን በመግለጫው ላይ አትቷል። • "መንገደኞች የሚጓዙት በመከላከያ ታጅበው ነው" የማዕከላዊ ጎንደር ኮሙኒኬሽን • "የሰለጠነና በሙሉ አቅም የሚዋጋ ኃይል ነው ችግሩን የሚፈጥረው" የማዕከላዊ ጎንደር ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ካውንስሉ በመግለጫው ላይ እንደጠቀሰው "ኢ ሕገመንግሰታዊ እርምጃ ለመቀልበስ በተወሰደው እርምጃ" ግጭት መከሰቱንና ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አንስቶ ክልሉና የፌደራል መንግሥት "በትዕግስትና በአርቆ አስተዋይነት" ችግሩን ለመፍታት ቢጥሩም ውጤት ሊመጣ አለመቻሉን ገልጿል። በአካባቢው የተከሰተው ግጭት "አካባቢውን ወደ ተሟላ ትርምስ የሚያስገባና ለክልሉ ብሎም ለመላው ሃገሪቱ የጸጥታ ስጋት" መሆኑንም የካውንስሉ መግለጫ አመልክቷል። መግለጫው አክሎም የአካባቢው ሠላም መደፍረስ የገቢና የወጪ ንግድ ላይም ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ጠቅሷል። በዚህም የተነሳ የፌዴራል የፀጥታ ኃይል መከላከያን ጨምሮ ማንኛውም ህጋዊ እርምጃ ወስዶ ቀጠናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት እንዲያሸጋግር መመሪያ መተላለፉ ተገልጿል። የተላለፈውን መመሪያ በመከተል የክልሉ የፀጥታና ደኅንነት ካውንስል በማዕከላዊ፣ በምዕራብ ጎንደር፣ በቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር እና በጎንደር ከተማ ክልከላዎችና ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዲደረጉ መመሪያ መሰጠቱን አስፍሯል። ከመመሪያዎቹ መካከል ማንኛውም የኃይል እንቅስቃሴን የኃይል እርምጃ በመውሰድ መቆጣጠር የሚል የሚገኝበት ሲሆን ጥፋተኞችን ለመቆጣጠር ተመጣጣኝ የኃይል እርምጃን በመውሰድ የኃይል ተግባርን ፍፁም እንዳይቀጥል ማድረግ የሚል ይገኝበታል። ካውንስሉ የሠላም አማራጮችን ለማስፋት በሚል በአካባቢው በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ግጭት የገቡ ቡድኖችና ግለሰቦች በአስቸኳይ ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ በመመለስ ያሏቸውን ልዩነቶች እንዲፈቱ ጥሪም አስተላልፏል። • እውን ድህነትን እየቀነስን ነው? • ህወሓት: "እሳትና ጭድ የሆኑ ፓርቲዎች ሊዋሃዱ አይችሉም" በግልፅ በታወቁ የፀጥታ ኃይሎች ከተያዙት ትጥቅና መሳሪያ ውጪ በተጠቀሱት የክልሉ ዞኖች ላልተወሰነ ጊዜ ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ሲንቀሳቀስ ይዞ የተገኘ ግለሰብ የሚወረስበት መሆኑ ተገልጿል። የቅማንት ብሔረሰብ አስተዳድር ከዚህ ቀደም በተወሰነው ህጋዊ ውሳኔ መሠረት በአፋጣኝ በሕዝብ ይሁንታ የሚደራጅ የራስ አስተዳድርን በማቋቋም ሁሉም አገልግሎት እንዲጀምር እንደሚያደርግም በመመሪያው ላይ ተካትቷል። በአካባቢው ውስጥ በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ገብተው የነበሩ ኃይሎች፣ ግለሰቦችና ቡድኖች እስከ ጥቅምት 20/2012 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ወደ ሰላማዊ ሁኔታ እንዲመለሱ የክልሉ መንግሥት በድጋሜ ይቅርታ ማድረጉም ተገልጿል። ነገር ግን በሰው ግድያ ቀጥተኛ ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ጉዳያቸው በህግ አግባብ የሚታይ መሆኑ በመመሪያው ላይ ተካትቷል። በየአካባቢው ለሚፈጠሩ "ወንጀሎች ፀረ-ሰላም ድርጊቶችና እንቅስቃሴዎች" ሁሉም አካላት የመቆጣጠር፣ የማሳወቅ፣ እርምጃ እንዲወስድ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው ያለው መመሪያው፤ ይህ ካልሆነ ግን ተጠያቂነትን ከማስከተልም በተጨማሪ በአካባቢው የሚገኘው ትጥቅ ሙሉ በሙሉ ተራግፎ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል ሲል አስጠንቅቋል። • ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ረቂቅ ህግ የሞት ቅጣት ተካቶበታል በኢ- መደበኛ አደረጃጀትና ባልተሠጠ ኃላፊነት ህግን ለማስከበር በሚል ሰበብ የሚደረግ ማንኛውም እንቅስቃሴ መከልከሉን ያስቀመጠው መመሪያው ተጠያቂነትም እንደሚያስከትል ገልጿል። ከጎንደር ወደ መተማ፣ ሁመራ፣ ባሕር ዳር፣ደባርቅ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚወስዱ መንገዶች በማንኛውም ጊዜ ነፃ ይሆናሉ ያለው መግለጫው፣ የሕዝብ በነፃነት የመንቀሳቀስን መብት ለማደናቀፍ የሚደረግ እንቅስቃሴ ላይ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ ይሆናል ሲል አስቀምጧል። በአካባቢው ሠላምና መረጋጋት ለማምጣት የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ ክልል የፀጥታ ኃይል፣ በየደረጃው ያለው የክልሉ መስተዳድር፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት በጥምረት እንደሚሰሩ መመሪያው አስቀምጧል።
news-49931774
https://www.bbc.com/amharic/news-49931774
"ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች
በዚህ ዓመት ለማካሄድ የታቀደው አጠቃላይ ምርጫ ስምንት ወራት ያህል ነው የቀሩት። ምንም እንኳን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀሩ ምርጫው እንደሚካሄድ በተደጋጋሚ ቢያረጋግጡም፤ በዚህ ወቅት ግን ሁሉም ለማለት በሚያስደፍር ሁኔታ ፓርቲዎች በውድድሩ እንደሚሳተፍ ወገን የሚያደርጉት የጎላ እንቅስቃሴ አይስተዋልም። ምን እየጠበቁ ይሆን? " ምርጫውን ከማካሄድ የተሻለ አማራጭ ያለ አይመስለኝም" ፕ/ር መረራ ጉዲና
ፕ/ር መረራ፣ ዶ/ር ደሳለኝ፣ አቶ የሺዋስ፣ ፕ/ር በየነ፣ አቶ አንዶምና አቶ ቶሌራ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀ መንበር ፕ/ር መረራ ጉዲና አገሪቱ ባልተረጋጋችበት ሁኔታ ምርጫ መካሄድ የለበትም የሚሉ ሰዎችን መረዳት ይከብደኛል ይላሉ። እንዲያውም አገሪቱ መስቀለኛ መንገድ ላይ በመሆኗ ምንም ዓይነት ይሁን ምን ምርጫ አካሂዶ ወደ ህዝብ መቅረብ እንደሚያስፈልግ ያምናሉ። አገሪቷን ዛሬ ያለችበት ሁኔታ ውስጥ የከተተው ኢህአዴግ ራሱ ሆኖ እያለ ይሄንኑ ኢህአዴግ ለምርጫ ሁኔታዎችን ያመቻች ብሎ መጠበቅ ቀልድ ነው ይላሉ። • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ቀጣዩ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ እንደሚሆን ተናገሩ "ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ሆነም አልሆነ፣ በፈለግነው መንገድ ሄደ አልሄደም ምርጫውን ከማካሄድ የተሻለ አማራጭ ያለ አይመስለኝም" ሲሉም ይደመድማሉ። እሳቸው እንደሚሉት ኢህአዴግ መሄድ እንዳለበት እየሄደ አይደለም፤ ሰላምና መረጋጋትም እንደሚጠበቀው እየመጣ ባለመሆኑ ምርጫውን አካሄዶ ወደ አንድ አቅጣጫ መሄድ አስፈላጊ ነው። የምርጫ መዋቅሩንም በፍጥነት መዘርጋት ይቻላል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። በተቃራኒው ይህ ካልሆነ ምርጫ መካሄድ የለበት ወይም ወደ ምርጫ አንገባም ማለት አገሪቱን የከፋ ነገር ውስጥ ይከታታል የሚል ስጋት እንዳላቸው ይገልፃሉ። ነገሮች ካልተስተካከሉ ወደ ምርጫ በመግባት ምን ይገኛል? "ምርጫውን ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ወደ ሆነ ነገር መውሰድ ይሻላል። ከሁለት መጥፎ አማራጮች ህዝቡን ይዞ ወደ ምርጫ፣ ሰላምና መረጋጋት መግባቱ ይመረጣል" የሚል መልስ የሰጡት ፕ/ር መረራ ሌሎች ጥያቄዎች እንዳላቸው ይጠቅሳሉ። • "መንግሥት አይወክለኝም ለሚሉ ወገኖች ምርጫ ምላሽ ይሰጣል" ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ከእነዚህም መካከል በአዲሱ የምርጫ ህግ መሰረት እንደ አዲስ አስር ሺህ የአባላት ፊርማ ሰብስቡ መባላቸውን በመቃወም ለምርጫ ቦርድ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። ለዚህም አባሎች ስለሌሏቸው ሳይሆን የአስር ሺህ ሰዎች ፊርማ ማሰባሰብ እስከ አንድ ሚሊዮን ብር ሊጠይቃቸው እንደሚችል በማንሳት "ተወዳዳሪዎች አንድ ሺህ፣ ሁለት ሺህ ፊርማ ይሰብሰቡ የሚለውን እኮ ከነመለስና በረከት ጋር ሰፊ ድርድር አድርገን እንዲነሳ አድርገናል። ለምን መልሰው እንደሚያመጡብን አላውቅም" ይላሉ። "የመንግሥት ሰራተኞች በምርጫ የሚወዳደሩ ከሆነ ስራ ይለቃሉ የሚለው የአዋጁን አንቀፅ እጅግ ነውር ነውም" ይላሉ። "ምርጫ ቦርድን እስከ መክሰስ ልንሄድ እንችላለን" ፕ/ርበየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀ መንበር የሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ምርጫው በ2012 ዓ.ም ቢካሄድ የጊዜ ጥያቄ እንደሌለባቸው ይናገራሉ። እሳቸው እንደሚሉት ይልቁንም ለእነሱ ትልቁ ችግር የፖለቲካ ሜዳው ለምርጫ ውድድር የተመቻቸ አለመሆኑ ነው። "በተጨባጭ እንደምናውቀው አምስት የምርጫ ቦርድ አባላት ከመሾማቸው በስተቀር ህዝብ ድምፅ እስከሚሰጥባቸው የታችኞቹ ማዕከሎች ድረስ ያለው የምርጫ ቦርድ መዋቅር ያው የድሮው ኢህአዴጋዊ ነው" ይላሉ። "ምርጫ የሚያስፈጽመው እኮ ከአዲስ አበባው ወደታች የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ የምርጫ ጣቢያ እየተባለ በመቶ ሺህዎች የሚመለመሉ ምርጫ አስፈፃሚዎች እስካሁንም የኢህአዴግ ካድሬዎች ናቸው። እዚህ [አዲስ አበባ ላይ] ጎፈሬ ቢያበጥሩ የሚመጣ ለውጥ የለም" ይላሉ። ፕ/ር በየነ ለዚህ ድምዳሜያቸው እንደማስረጃ የሚጠቅሱት የተሳተፉባቸውን ያለፉት አምስት ምርጫዎችን ነው። • "ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አይደለም" ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ "መሬት ላይ ያለውን እውነት እናውቀዋለን። ምን ማስረጃ ያስፈልገዋል" በማለት ከጥቂት ቀናት በፊት ግን ለክልል ምርጫ አስፈፃሚ የሚሆኑ ሰዎችን ጠቁሙ የሚል ደብዳቤ እንደደረሳቸው ይናገራሉ። "ምናልባትም ይህ አንድ አዎንታዊ እርምጃ ሊሆን ይችላል" ይላሉ። ስለዚህም እሳቸው ችግር የሚሏቸውን ነገሮች ለማስተካከል መንግሥት ከተቃዋሚ ፖለቲከኞችና ባለድርሻዎች ጋር ካልሰራ ስለ ምርጫ ማሰብ የዋህነት ነው ሲሉ ይደመድማሉ። እንደ ችግር የሚያነሱት ሌላው ነገር ደግሞ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያፀደቀው አዲሱ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የሥነ ምግባር አዋጅን ነው። "ከዚህ በፊት ከእነ አቶ መለስና አቶ በረከት ጋር ተደራድረን ያመጣነውን፤ ምርጫ ውስጥ ገብቶ መሳተፍ ቀላል እንዲሆን ማድረግን በተመለከተ ይህኛው ለውጥ አመጣሁ የሚለው አካል ወደ ኋላ መልሶታል" ሲሉ ፕ/ር መረራ ያሉትን ያጠናክራሉ። ፓርቲዎች እገሌ እገሌ የእኔ ተወዳዳሪ ነው ብለው እጩዎቻቸውን ያቀረቡበትን የ1997 ዓ.ም ምርጫን በማስታወስ፤ አዲሱ ህግ አንድ ተወዳዳሪ እጩ ለመሆን ቢያንስ ሁለት ሺህ ፊርማ ያሰባስብ ማለቱን ይኮንናሉ ፕ/ር በየነ። "የድሮው አንድ ሺህ ፊርማ ይል ነበር አሁን ሁለት ሺህ አድርገው መልሰውታል።" • በአከራካሪው የ3ሺህ ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያ በታሪኳ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ አገኘች በአዲሱ አዋጅ መሰረት ባለፉት ሁለት አስርታት በምርጫ ውስጥ የተሳተፈ እንደእሳቸው አይነት ፓርቲ "እንደ አዲስ አስር ሺህ የአባል ፊርማ እንዲሰበስብ መጠየቁ ትክክል አደለም" በማለት ምርጫ ቦርድን እየጠየቁ መሆኑን ገልፀዋል። "ይህ እስከ ፍርድ ቤትም ሊወስደን፤ ምርጫ ቦርድን ልንከስ እንችላለን። ጠበቃም እያነጋገርን ነው"ይላሉ። ምርጫ ቦርድን መክሰስ አዋጪ መንገድ ይሆናል ወይ? ተብለው የተጠየቁት ፕ/ር በየነ "የበፊቱ ሥርዓት ተሻሽሏል፤ አዲስ አሰራር ነው ያለው ይሉ የለ?" በማለት እርምጃው ለውጡን ለመፈተሽም እንደሚጠቅም ይገልጻሉ። ፓርቲዎች አስር ሺህ ፊርማ አሰባስበው ይመዝገቡ ማለት ጊዜ የሚጠይቅና ፓርቲዎች ላይ የገንዘብ ጫና የሚፈጥር እንደሆነም ያስረዳሉ። "በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል አብን 'እንደሽብርተኛ' እየተቆጠረ ነው" ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጡ በገቧቸው የለውጥ ቃሎች ተስፋን ሰንቀው የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በፖለቲካ ሜዳው ላይ በሚመለከቷቸው ነገሮች ቀጣዩ ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ይሆናል የሚል እምነታቸው መሸርሸሩን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ይናገራሉ። "ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ብዙ ጥፋቶችን አልፏል" የሚሉት ዶ/ር ደሳለኝ በተለይም ከሰኔ 15ቱ ሁኔታ በኋላ የፖለቲካ ምህዳሩ እየጠበበና እየተዘጋ ነው ይላሉ። በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ክልሎች መንቀሳቀስ አዳጋች እየሆነባቸው መሆኑን በመጥቀስ "አብን በኦዲፒና ቤጉዴፓ የዞን አስተዳዳሪዎችና በወረዳ ካድሬዎች እንደ ሽብርተኛ ፓርቲ እየታየ ነው" ሲሉም የገጠማቸውን ይናገራሉ። "ወለንጪቲ ቦሰት የሚባል ወረዳ ከሁለት ወር በፊት የፓርቲው ጽ/ቤት በጥይት ተደብድቧል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከአምስት መቶ በላይ የሚደርሱ አባላት፣ በተለያየ ደረጃ ያሉ አመራሮችና ደጋፊዎቻችን ኦሮሚያ ላይ ታስረው ነበር" ብለዋል። ጉዳዩንም በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስቴርና ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት እንዲሁም ለምርጫ ቦርድ ጭምር ሪፖርት ማድረጋቸውንም ይናግራሉ ዶ/ር ደሳለኝ ። በችግሩ ላይ ለመወያየትና መፍትሄ ለመፈልግ የኦዲፒ የፓርቲ ጉዳይ ሃላፊ አቶ አለሙ ስሜን አናግረው እንደነበር፤ ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳን ለማነጋገር ያደረጉት ተደጋጋሚ ሙከራም አለመሳካቱን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል በአማራ ክልል ቀላል ከሚባሉ አጋጣሚዎች በስተቀር ያለችግር በነፃነት እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን ይናገራሉ። • ኔታኒያሁ ከጠ/ሚ ዐብይ ጋር ስለኤርትራዊያን ስደተኞች መወያየታቸውን ተናገሩ ከዚህ ባሻገር ግን እስርና አፈና ትልቅ እንቅፋት እንደሆነባቸው፤ የፓርቲያቸው ሕዝብ ግንኙነት እንዲሁም የጽህፈት ቤት ሃላፊና የሌሎችም እስር ለዚህ ምስክር መሆኑን ይጠቅሳሉ። በቀጣይ ምርጫ እየቀረበና ሰፊ የቅስቀሳ ሥራዎችን መስራት ሲጀምሩ ደግሞ የመንግሥት እጅ ይበልጥ ይከብድብናል የሚል ስጋት እንዳላቸውም ይገልፃሉ። አዲሱን የምርጫ አዋጅ በሚመለከት በተለይም በአገር አቀፍ ደረጃ አንደ ፓርቲ አስር ሺህ፤ በተወዳዳሪ ሁለት ሺህ ፊርማ ማሰባሰብን እንደ ችግር የሚያዩ ፓርቲዎች ቢኖሩም አብን በዚህ ረገድ ምንም ችግር እንደሌለበት ዶ/ር ደሳለኝ ያስረግጣሉ። ዶ/ር ደሳለኝ የሚያስፈልገው የፊርማ ቁጥር ላይ ባይሆንም እዚሁ ጉዳይ ላይ የሚያነሱት ጥያቄ ግን አለ። "በፓርቲዎችና በአርቃቂ ቡድኑ መካከል ስምምነት ተደርሶበት የነበረው ቁጥር አራት ሺህ የሚል ሆኖ ሳለ ማን እንደቀየረው አይታወቅም" የሚሉት ዶ/ር ደሳለኝ ረቂቁ መጨረሻ ላይ ለፓርቲዎች ውይይት አስር ሺህ ሆኖ መምጣቱን ያስታውሳሉ። በተጨማሪም የመንግሥት ሰራተኞች ለምርጫ እጩ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ሥራቸውን መልቀቅ አለባቸው የሚለውን የአዋጁን አንቀጽ አብን ይቃወመዋል። ገዢው ፓርቲ በምርጫው ጊዜ ሊያሳይ የሚችለው ባሕሪ ላይ ስጋት ያላቸው ዶ/ር ደሳለኝ "ባለፉት ዓመታት የህዝብን ድምፅ ሲሰርቅ የኖረው ገዥው ፓርቲ አሁንስ ከዚህ አመሉ ምን ያህል ይፀዳል የሚል ጥያቄና ስጋት አለብን። ለውጦች ቢኖሩም፤ ትናንትም፣ ዛሬም ነገም ምርጫ ውስጥ ለውድድር የሚገባው ኢህአዴግ ነው። ኢህአዴግ ደግሞ መሰረታዊ በሚባል ሁኔታ ባህሪው ተቀይሯል ብለን አናስብም።" ይላሉ። አብን ከምርጫ ጋር በተያያዘ የጊዜ ጥያቄ የለበትም። አሁን ባለው ሁኔታም ለምርጫ በሙሉ አቅሙ እየሰራ እንደሆነ የሚናገሩት ዶ/ር ደሳለኝ ከቻሉ አሸንፎ ለብቻው የክልልና የፌደራል መቀመጫዎችን መያዝን፤ ይህ ካልሆነም አብላጫ ወንበሮችን አግኝቶ ከሌሎች ጋር ጥምር መንግሥት መመስረትን እንደሚያስቡ ያስረዳሉ። "ሚሊሽያም ሚዲያም ያላቸው ፓርቲዎች አሉ" አቶ የሺዋስ አሰፋ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ ) ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ "የጊዜ ጥያቄ የለብንም ነገር ግን መታየት ያለባቸው ብለን ለመንግሥት ያቀረብናቸው ጉዳዮች አሉ" ይላሉ። ምርጫ ቦርድ፣ ፍርድ ቤት እና ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በበቂ ሁኔታ ዝግጁ ናቸው ወይ? የሚለው አሁንም ጥያቄያቸው እንደሆነ በመጥቀስ፤ ከዚህ ባሻገር ደግሞ በገዢ ፓርቲም ሆነ በተቃዋሚው በኩል በምርጫ ቢሸነፉ አሜን ብለው የማይቀበሉ ፓርቲዎች ይኖራሉ የሚል ስጋትም እንዳላቸው ይናገራሉ። • አሜሪካ የአባይ ወንዝ አጠቃቀምን በተመለከተ መግለጫ አወጣች "የራሳቸው ሚሊሺያና ሚዲያም ያላቸው ፓርቲዎች አሉ። ገንዘብም አላቸው ምርጫውን ቢሸነፉ ስልጣን የማስረከብ አዝማሚያ አይታይባቸውም" በማለት ልማደኞች ናቸው ያሏቸው የገዥው ፓርቲ አባላትን በስም ይጠቅሳሉ። በሌላ በኩል ኢዜማ በምርጫ ቢሸነፍ ውጤቱን የመቀበል ችግር እንደሌለበት ይናገራሉ። በፓርቲና በተወዳዳሪዎች መሰባሰብ አለበት ስለሚባለው የፊርማ ብዛትን በተመለከተ ኢዜማ ከሌሎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለየ መልኩ ሃሳቡን እንደሚደግፈውና "ሁለትም ሦስትም እየሆኑ ፓርቲ ነን ማለትን ቅርፅ መያዝ አስፈላጊ ነው። አስር ሺህ ፊርማ እንዲያውም ያንሳል " ይላሉ አቶ የሺዋስ። ኢዜማ ከምርጫው የሚጠብቀው "በፖለቲካ ሜዳው ያለው የተዥጎረገረ ሃሳብ ፓርላማ እንዲገባ። ምርጫው የዲሞክራሲ መሰረትን የሚጥል እንዲሆን እንፈልጋለን። ትኩረታችንም ውጤቱ ላይ ብቻ ሳይሆን ሂደቱም ነው፤ የኛ ትኩረትእንፈልጋለን" ሲሉ ያጠቃልላሉ። "ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እናካሂዳለን ተብሎ የተገባው ቃል መፈፀም አለበት" አቶ ቶሌራ አደባ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ አቶ ቶሌራ አደባ በአዲሱ የምርጫ ህግ ሳይሆን በቀደመው ለመመዝገብ የተጠየቁትን ነገሮች በሙሉ አሟልተው የምርጫ ቦርድን ምላሽ በመጠበቅ ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ። ምንም እንኳ የጊዜ እጥረት ውጥረት ሊያስከትል ቢችልም በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ተንቀሳቅሰው በምርጫ እንደሚያሸንፉ እምነት አላቸው። ለዚህም ከሰላምና መረጋጋት አንፃር ሁኔታዎች አስቸጋሪ ባልሆኑባቸው አካባቢዎች የምርጫ ዝግጅት እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ እንደሆነም ይጠቁማሉ። በዚህ ሂደት ውስጥ ስለገጠሟቸው ችግሮችም ሲያነሱ "አንዳንድ ክልሎች ላይ ለመንቀሳቀስ አላስፈላጊ ቁጥጥሮች አሉ። ሌሎች ላይ ደግሞ የፀጥታ ችግር አለ። የተዘጉብን ጽ/ቤቶች አሉ፤ ሰዎች የኦነግ ደጋፊዎች ናችሁ እየተባሉ ይታሰራሉ" በማለት እነዚህ ነገሮችን መንግሥት ሊያስተካክል ግድ ነው ይላሉ። ከዚህ ውጪ ግን በምርጫው የሚገኝን ውጤት ለመቀበል ዝግጁ መሆናቸውን "ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እናከሂዳለን ተብሎ የተገባው ቃል መፈፀም አለበት እንላለን። እኛ ግን በምርጫው የምንፈራው ምንም ነገር የለም። ማሸነፍንም መሸነፍንም እንቀበላለን" ሲሉ ይናገራሉ። "ህወሓትን ለስልጣኑ ስለምናሰጋው ነው ድብደባ፣ እስር እና ዛቻ እያደረሰብን ያለው" አቶ አንዶም ገብረ ሥላሤ ትግራይ ውስጥ ዋነኛው ተቃዋሚ ፓርቲ የሆነው የአረና አባል የሆኑት አቶ አንዶም ገብረ ሥላሴ ቀጣዩን ምርጫ ዲሞክራሲያዊ ለማድረግ በመንግሥት በኩል እንቅፋት የሆኑ ነገሮች አሉ ይላል። "በተለይም በትግራይ የፖለቲካ ምህዳሩ በጣም አስቸጋሪ ነው። የአረና አባላት ይታሰራሉ፣ ይደበደባሉ ንብረታቸው ይቀማል የሚዲያ ተጠቃሚነትም የለም። በአጠቃላይ በአገሪቱ የሚስተዋለው አለመረጋጋትና በገዥው ፓርቲ ውስጥ ያለው ሽኩቻም ለምርጫው አስቸጋሪ ነው" ይላሉ የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አንዶም ገ/ሥላሤ። ቢሆንም ግን ፓርቲያቸው አሁንም ለምርጫው ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠው በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ "የቆየና የተደራጀ ፓርቲ ስለሆነ በትግራይና በአዲስ አበባ ለመወዳደር አስፈላጊ ዝግጅቶችን እያደረገ ነው።"ሲሉም ያክላሉ። • "ቤተ መንግሥቱን ለማስዋብ ለሙያችን የሚከፈለን ገንዘብ የለም" መስከረም አሰግድ እንደ ሌሎቹ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ሁሉ አቶ አንዶምም የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነትን ለማረጋገጥ የተሰራው ሥራ ገና ወደ ታች አለመውረዱን ያነሳሉ። በአዲሱ የምርጫ አዋጅ መሰረት የመንግሥት ሰራተኞች በምርጫ ለመወዳደር እጩ ከሆኑበት ጊዜ ጀምሮ ሥራቸውን ይልቀቁ መባሉን አረናም ይቃወመዋል። በፓርቲ ደረጃ አስር ሺህ የአባላት ፊርማ ማሰባሰብን በተመለከተ ሲናገሩ "እንደ አረና በርካታ ዓመታትን ሲታገል ለቆየ ፓርቲ ይህ ችግር ሊሆን አይችልም" ሲሉ ይህን እንደማይቃወሙት አቶ አንዶም ይናገራሉ። ከአንዳንድ ወገኖች አረና ትግራይ ውስጥ ድጋፉን እያጣ መሆኑን በሚመለከት የሚባለውን በተመለከተ የተጠየቁት አቶ አንዶም "ይህ ቢሆን ኖሮ አረና ህወሓትን አያሰጋውም ነበር። ህወሓትን ለስልጣኑ ስለምናሰጋው ነው ድብደባ፣ እስርና ዛቻ እያደረሰብን ያለው" ሲሉ ይመልሳሉ። አቶ አንዶም የሚያሳስባቸው የክልሉ ገዢ ፓርቲ የሆነው ህወሓት በመጪው ምርጫ ስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያስችለውን ድምጽ ቢያጣ ስልጣን አይሰጥ ይሆናል የሚለው ሳይሆን "በመጀመሪያ ምርጫውን በትክክል ያካሂደዋል ወይ?" የሚለው ነው።
news-48173947
https://www.bbc.com/amharic/news-48173947
ናዝራዊት አበራ፡ የጓደኛዋ ስምረት ካህሳይ ቤተሰቦች ምን ይላሉ?
ናዝራዊት አበራ በቻይና ዕፅ በማዘዋወር ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር መዋሏ ከተሰማ አራት ወራቶች ተቆጥረዋል። አንድ ሰው እፅ ሲያዘዋውር ከተገኘ የሞት ፍርድ እንዲበየንበት የሚያዘው የቻይና ህግ በናዝራዊት ላይ ተግባራዊ ይሆናል በሚል በቤተሰቦቿ፣ በቅርብ ዘመዶቿ እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ስጋት ተፈጥሮም ቆይቷል።
ዕፁን ይዛ ተገኝታለች የተባለችው ናዝራዊት በጉዋንዡ እስር ቤት የምትገኝ ሲሆን ይህንን አደንዛዥ ዕፅ ለናዝራዊት አበራ ሰጥታታለች የተባለችው ጓደኛዋና አብሮ አደጓ ስምረት ካህሳይም አዲስ አበባ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ተይዟል። • “ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ ከደወሉልን በኋላ ተረጋግተናል” የናዝራዊት አበራ እህት የተጠርጣሪዋ ስምረት ካህሳይ ቤተሰቦች ለቢቢሲ እንደገለፁት ስምረትና ናዝራዊት ጓደኛማቾች ነበሩ፤ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጀምሮም አብረው ተምረዋል። የእህትማማችነት ያክል የጠነከረ ጓደኝነት ነበራቸውም ይላሉ። "አንዳቸው ከአንዳቸው ቤት እየሄዱም አብረው ጊዜ ያሳልፉ ነበር፤ በጣም ነበር የሚዋደዱት" የሚሉት አክስቷ ሰብለወንጌል ከፍያለው ናቸው። ወይዘሮ ሰብለወንጌል እንደሚሉት ስምረት ጫማና ልብስ ከቻይና እያመጣች ትሸጣለች፤ ናዝራዊትም ከቻይና ልብስ ማምጣት እፈልጋለሁ እያለች ትነግራት ስለነበር አብረው ለመሄድ እንደወሰኑ ይናገራሉ። ቻይና ለመሄድ አብረው ነበር ትኬት የቆረጡት፤ ይሁን እንጂ በበረራቸው ቀን ጠዋት የስምረት አባት በድንገት ሕይወታቸው ማለፉን ያስታውሳሉ፤ ለዚህም ማስረጃ አለን ይላሉ። በዚህም ጊዜ ናዝራዊት ከቤተሰቦቿ ጋር ለቅሶ እንደመጣችና ጉዞውን እንድታስተላልፈው ስምረት ብትጠይቃትም 'እኔ ደርሼ እመጣለሁ፤ ጉዞውን አላስተላልፍም' ብላት እንደሄደች ይናገራሉ። • በቻይና የተደረሱት ስምምነቶች የትኞቹ ናቸው? "ዕፁን ማን ይስጥ፤ ማን ይቀበል የሚለው በፍርድ ቤት የተያዘ በመሆኑ እዚህ ላይ የምለው የለኝም" የሚሉት የስምረት አክስትና አሳዳጊዋ ሰብለወንጌል በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎችና በሌሎችም መገናኛ ብዙሃን ከአንድ ወገን ብቻ ሲዘገብ መቆየቱ ስምረትን በጣም ጎድቷታል ሲሉ ይወቅሳሉ። እንደ ቤተሰብም ስምረት ካህሳይ ጓደኛዋን አሳልፋ እንደሰጠችት ተደርጎ በድምዳሜ መወራቱ በጣም አሳዝኖናል ብለዋል። ስምረት ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የነበረች ሲሆን በኩላሊት ህመም ምክንያት ሥራውን እንዳቆመችም ገልፀውልናል። ከጉዞው በኋላ ናዝራዊት በቻይና በዕፅ ዝውውር መያዟ ይሰማል፤ ያኔ የናዝራዊት ቤተሰቦች ወደ ቤታቸው እንደመጡ የናዝራዊት ታናሽ እህት ዶ/ር ማርነት ካህሳይ ትናገራለች። "ናዝራዊት ከሄደች ድምጿ አልተሰማም፤ ምን እንደሆነች አናውቅም፤ ነገርግን ቻይና አየር ማረፊያ ስትደርስ በቁጥጥር ስር ውላለች" ሲሉ የናዝራዊት ቤተሰቦች እንደገለፁላቸው ታስታውሳለች። እርሷ እንደምትለው እነርሱም ለጉዳዩ እንግዳ ነበሩ። "ምን ይዛ ነው? ብለን ጠየቅናቸው" ትላለች። እነርሱም ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ምላሽ የሰጧቸው ሲሆን በወቅቱ ስምረት ቤት ውስጥ አልነበረችም። " እኔና እናቴ ነበርን ለስምረት የነገርናት፤ በጣም ደነገጠች፤ ምን እንደተፈጠረ ማወቅ አልቻለችም፤ ከዚያም የናዝራዊትን ወንድም ለማነጋገር ሞከረች። ይሁን እንጂ መልሰው እነሱም እርሷን ነበር ሲጠይቋት የነበረው" የምትለው ዶ/ር ማርነት በተደጋጋሚ ስልክ እየደወሉ 'ምንድን ነው ያደረግሻት? የት ነው ያደረሻት?' እያሉ ሲያናግሯት ነበር ትላለች። • "ናዝራዊት አበራ ላይ ክስ አልተመሰረተም" የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የስምረት አክስት ወ/ሮ ሰብለወንጌል በበኩላቸው በዚህ ጊዜ ስምረት ለናዝራዊት ሲደረግ የነበረውን የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ እንደተቀላቀለችና ሌሎች ሰዎችንም ስታነሳሳ ነበር ይላሉ። "ከታላቅ እህቷም ጋር 'ተገናኝተን እናውራ፤ እንረዳዳ፤ እኔም ተሰምቶኛል' ስትል ከዚህ በኋላ ፍርድ ቤት የያዘው ጉዳይ ስለሆነ ሂጂና ለአቃቤ ህጉ ንገሪው የሚል ምላሽ ነው የተሰጣት" ሲሉ ይገልፃሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ናዝራዊት በቁጥጥር ሥር መዋሏ ከተሰማ በኋላ ባሉት አስር ቀናት ውስጥ ስምረት ኬንያ ደርሳ የተመለሰች ሲሆን ድጋሜ ወደ ታይላንድ ለመሄድ አየር መንገድ ውስጥ ሆና በፖሊስ ቁጥጥር ሥር እንደዋለች ታናሽ እህቷ ዶ/ር ማርነት ታስረዳለች። በረራዋ ማታ ነበር የምትለው እህቷ እርሷን ወደ ጣቢያ ከወሰዷት በኋላ ፖሊሶች ቤታቸውን እንደፈተሹ ትናገራለች። • ዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ናይጄሪያዊት ከእስር ተለቀቀች እርሷ እንደምትለው በቀጣዩ ቀን ስምረት ፍርድ ቤት የቀረበች ሲሆን በቂ ማስረጃ ስላልነበራቸው የዋስ መብቷ እንዲጠበቅላት፤ ጉዳዩ እስከሚጣራም ድረስ ፓስፖርቷ እንዲያዝ ብለው በ20 ሺህ ብር ዋስ እንደተለቀቀች ትናገራለች። ከዚህም በኋላ ስምረት እንደማንኛውም ሰው በሰላም ስትንቀሳቀስ እንደቆየች፤ ነገር ግን ቀኑን በትክክል ባታስታውስም በተለቀቀች በወር ከአራት ቀን ውስጥ በድጋሜ ቤት ውስጥ እያለች በቁጥጥር ሥር እንደዋለች ታስረዳለች- ዶ/ር ማርነት። ስምረት በመጀመሪያ ዕፅ ለናዝራዊት አበራ ሰጥታለች በሚል ክስ ተጠርጥራ የተያዘች ሲሆን በድጋሜ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለችው ያለአግባብ የተገኘ ገንዘብን መጠቀምና ሰዎችን ያለአግባብ ማዘዋወር በሚል ክስ ተጠርጥራ ነው ስትልም አክላለች። ቀድሞ የተያዘ ፕሮግራም ስለሆነ ስምረት የቻይና ጉዞዋን ለምን አላደረገችም? ለምን ታይላንድ ሄደች? ያልናቸው የስምረት አክስት ሰብለወንጌል በበኩላቸው "ከእጮኛዋ ጋር ነበር ወደ ታይላንድ ልትሄድ የነበረው፤ ፕሮግራም ነበራቸው፤ ሰርፕራይዝ ሊያደርጋት ነበር፤ ልንነግርሽ የማንፈልገው ግላዊ ጉዳይ ነበራቸው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል። እጮኛዋም አብሮ በቁጥጥር ሥር የዋለ ሲሆን፣ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ እንደሆነ የስምረት እህት ነግራናለች፤ ይሁን እንጂ ጉዳዩን ህግ ስለያዘው የሚነግሩን ዝርዝር መረጃ የለም ብላናለች። ስምረት በሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የምትገኝ ሲሆን የፍርድ ሂደቱን እየተከታተሉ እንደሆነም ገልፀውልናል። "በጥሩ ጤንነት ላይ አይደለችም" ታናሽ እህቷ ዶ/ር ማርነት "መጀመሪያ በቁጥጥር ሥር ውላ በዋስ ከወጣች በኋላ ሚዲያ ላይ የሚናፈሰውን ስናይ እንደ ቤተሰብ፤ የቤተሰብሽን ክብር ነው ያዋረድሽው ብለን ገለልተኛ አደረግናት" ትላለች የሆነውን ስታስታውስ። • ከአምቦ ከተማ ነዋሪ ለዶ/ር አምባቸው የቀረቡ 4 ጥያቄዎች ሚዲያ ላይ እንድትወጣና እንድትናገር የገፋፏት ቢሆንም 'እህቴ ናት፤ የእርሷ ጉዳት የእኔም ጉዳት ነው፤ እኔ ሚዲያ ላይ ከወጣሁ የፊርማ ማሰባሰቡን ዘመቻ ሊገታው ይችላል' በማለት ሚዲያ እንደሸሸች ትናገራለች። "እኔ ተጎድቼ፤ እርሷ ነፃ ትውጣ" ስትልም ነበር፤ ነገር ግን የናዝራዊትን ቤተሰቦች ለማነጋገርና ለማገዝ ብትፈልግም ፈቃደኛ እንዳልነበሩ ትገልፃለች። ይህ ሁሉ ነቀፌታም ሲደራረብባት ጨጓራዋን ታመመች፤ ትርፍ አንጀትም አጋጥሟት ቀዶ ህክምና አድርጋለች። ሰውነቷም በጣም እንደተጎሳቆለና የቀደመው መልኳ እንደሌለ በሃዘኔታ ይገልፃሉ። ቤተሰቡም እርሷን ይዘው ሐኪም ቤት ለሐኪም ቤት እየተንከራተቱ እንዳሉም ያስረዳሉ። ስምረት ግን በዚህ ሁኔታ ውስጥም ሆና የናዝራዊትን መፈታት ዜና እንደምትጠባበቅና አዘውትራ እንደምትጠይቃቸውም ይናገራሉ። ስምረት ናዝራዊት ተፈትታ፤ እውነቱን ተናግራ እርሷንም ነፃ እንደምታወጣት ተስፋ አድርጋለች። የስምረት አክስትና እህት እንደ ቤተሰብ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተሉ ሲሆን ለናዝራዊትም ፍትህ እንደሚመኙ ነግረውናል። የስምረት ቀጣይ ቀጠሮ ሚያዚያ 29/2011 ዓ.ም እንደሆነም ለቢቢሲ ገልፀዋል።
news-54087512
https://www.bbc.com/amharic/news-54087512
ጾታዊ ጥቃት፡ ለሴቶች ከለላ መሆን የምታስበው "ከለላ"
ከዛሬ ሦስት ዓመት በፊት ሰላም ሙሴና ሁለት ጓደኞቿ አንድ የእረፍት ቀናቸውን ቡና እየጠጡ ለማሳለፍ ተገናኙ። ቀጠሯቸው ሁሌም በሚያዘወትሩት ካፌ ውስጥ ነበር።
ወሬን ወሬ እያነሳው ስለፍቅር ሕይወታቸው መነጋገር ጀመሩ። አንድ ጓደኛዋ ከልጅነቷ ጀምሮ በግቢያቸው ውስጥ የሚኖሩ ወንዶች የተለያዩ ጾታዊ ትንኮሳዎች ያደርሱባት እንደነበር ድንገት በወሬያቸው መካከል ጣል አደረገች። ከዚህ በኋላ ግን የወሬው ርዕሰ ጉዳይ ተለወጠ። ወሬው የነበረው ግለትም ውሃ ተቸለሰበት። በሳቅና በወዳጅነት ስሜት ታጅቦ የነበረው ጨዋታ ውስጥ የሃፍረትና የመሸማቀቅ ነፋስ ገባ። ይህንን ማየት ለሰላም ግርምታን ፈጥሯል። ዘወትር ስለሴቶች ጥቃት፣ እኩልነት የምታወራዋ ጓደኛዋ በእርሷ ላይ ስለደረሰው ትንኮሳ ማውራት ማፈሯ ትኩረቷን ሳበው። ከጓደኞቿ ጋር ተለያይታ ወደ ቤቷ ካመራች በኋላ ከሌላኛዋ ጓደኛዋ መልዕክት በስልኳ ደረሳት። ጓደኛዋ በአጎቷ/በአክስቷ ልጅ በተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን አስተናግዳለች። ቅርብ ላለችው የቤተሰቧ አባል ብትናገርም እርሷን ከሃፍረትና ከመሸማቀቅ የሚያድናት አልሆነም። ለሰላም ይህንን መስማቷ በርካታ ጥያቄዎችን እንድታስተናግድ አደረጋት። ምን ያህል ሴቶች በልጅነታቸው ትንኮሳን፣ ጥቃትን አስተናግደዋል? ምን ያህል ሰዎች ጥቃት ወይንም ትንኮሳ መድረሱን ሰምተው ምንም ሳያደርጉ ቀርተዋል? ይህንን የጓደኞቿን ታሪክ አስፈቅዳ በፌስቡክ ሰሌዳዋ ላይ ካጋራች በኋላ በርካቶች በግሏ መልዕክት ላኩላት። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ እርሷና ጓደኞቿ አንድ ነገር ለማድረግ ተሰባሰቡ። ጾታዊ ጥቃት ለሚደርስባቸው ከለላ ለመሆን በማሰባቸው ለቡድናው 'ከለላ' በማለት ስም አወጡለት። እነሆ ከለላ ለልጆች፤ ከሦስት ዓመት በኋላ ለተጠቃሚዎች በማህበራዊ ድረ ገጾችና፣ በድረ ገጽ በኩል ደረሰ። ጥቃት ከሩቅ አይመጣም ኅብረተሰቡ ብዙ ጊዜ ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎች ከሩቅ የሚመጡ እንደሆኑ ያስባል ትላለች ሰላም ሙሴ። በቴሌቪዥን በሬዲዮ በሚታዩ ድራማዎች፣ በመጽሐፍት ተደርሰው የምናነባቸው ታሪኮችም ላይ የምናስተውለው ጥቃት አድራሾች ከውጪ መጥተው እንደሆነ ነው። ከዚህ እንኳ ቢያልፍ በማኅበረሰቡ ውስጥ ቅቡልነት በሌላቸው፣ እንደ ክፉ በሚታዩና በሚቆጠሩ ሰዎች ጥቃት እንደሚደርስ ተስለው እናነባለን፤ እናያለን። እውነታው ግን ከዚያ የራቀ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ጾታዊ እንዲሁም የወሲብ ጥቃት በልጆች እንዲሁም በአዋቂዎች ላይ የሚፈፀመው በሚታወቁና ቅርብ በሆኑ ሰዎች መሆኑን ሰላም ትናገራለች። በተለይ ሕጻናት ለጥቃት የሚጋለጡት በተከራዮች፣ በቤተሰብ አባላት፣ በዘመዶች መሆኑን በማንሳት ይህ ጉዳይ ጥቃቶች ተዳፍነው እንዲቀሩ እንደሚያደርግ ታነሳለች። "በይበልጥ ደግሞ አለመወራቱ፣ ችግሩ እንደሌለ አድርጎ እንዲሰማን ያደርጋል" ስትል ታብራራለች። በልጅነት እድሜ እንዲህ ዓይነት ነገር ሲፈጠር፣ ጥቃት አድራሾች የሚያደርሱት ማስፈራሪያ፣ ለሌላ ሰው እንዳይናገሩ የሚፈጥሩት ማሳመኛ፣ ጥቃቶቹ ሳይነገሩ እንዲቀሩ መሆናቸው ትገልጻለች። "በባህላችንም እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች የማውራት ነጻነቱ ስለሌለ፣ ልጆች ለእንዲህ አይነት ጥቃቶች ቋንቋ የላቸውም" የምትለው ሰላም፤ "እከሌ እኮ እንደዚህ አደረገኝ፤ እንደዚህ ዓይነት ቦታ ላይ እንዲህ አደረገኝ፤ እንደዚህ ነካኝ" ለማለት ቋንቋ እንደሚቸግራቸው ታስረዳለች። ወላጆች አሳዳጊዎች እንዲሁም መምህራንም እነዚህን ጥቃቶች አብራርተው ለማስረዳት የሚያስችላቸው ቋንቋ አለመጎልበቱን ታነሳለች። ይህ ብቻም ሳይሆን በምን መልኩ እናስተምራቸው ለሚለው የሚረዳ መሳሪያ፣ መምሪያ አለመኖሩን ሰላም ትጠቅሳለች። እነዚህ ክፍተቶች መኖራቸው ልጆቹ ጥቃት በደረሰባቸው ወቅት ሄደው እንዳይናገሩ እንደሚያደርጋቸው፣ የልጆች ነገር ያሳስበኛል የሚሉ አካላት፣ ወላጆች አሳዳጊዎችና መምህራን እነዚህን ጉዳዮች ለማስተማር ጥቃቱን ለመካከል ቀድሞ ለማስተማር የሚያስችላቸው መንገድ ያጣሉ። ብዙ ጊዜ ጥቃቱ ሲፈፀም ልጆች የሚያሳይዋቸው ምልክቶች ይኖራሉ የምትለው ሰላም፣ ነገር ግን ስለ ምልክቶቹ የቀደመ እውቀት የሌለው ሰው ልጆቹ ላይ ስለደረሰው ነገር ተረድቶ ለመደገፍና እርምጃ ለመውሰድ ይቸገራል ትላለች። ስለዚህ ይህንን ክፍተት ለመሙላት በማለት "ከለላ" መዘጋጀቱን ለቢቢሲ ገልፃለች። "ከለላ የበይነ መረብ መድረክ ነች" የሚለው ሃሳብ የሰፈረው በማኅበራዊ ድረ ገፁ ሰሌዳ ላይ ነው። 'ከለላ' ለዚህ መልስ አለው? በ2010 ዓ.ም በተለያየ የሙያ መስክ የተሰማሩ ባለሙያዎች ተሰባስበው፣ ስር የሰደዱ ማኅበረሰባዊ ችግሮችን ለመዋጋት የሚረዱ ሃሳቦችና መሳሪያዎች በበይነ መድረክ ለማዘጋጀት በአንድ ሃሳብ ፀኑ። እነዚህ በጎ ፈቃደኞች የመጀመሪያ የሆነችውን ስራቸውን፣ ከለላ ለልጆች፣ በቀላል ቋንቋ፣ ለቤተሰቦች፣ ለሕግ ባለሙያዎች፣ ለአሳዳጊዎችና መምህራን በሚሆን መልኩ ለማዘጋጀት ስራ ጀመሩ። በጎ ፈቃደኞቹ የሥነ አእምሮ፣ የሥነልቦና፣ የሕግ ባለሙያዎች በጋራ በመሆን መምርያውን መጻፋቸውን ሰላም ትገልጻለች።። ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተው እነዚህ ሙያዎችን ነው የምትለው ሰላም፤ ሥራው ሁለት ዓመት የፈጀውም የበጎ ፈቃደኝነት ሥራ በመሆኑ ነው። "ከለላ" ለልጆች መምሪያን በከለላ ድረገጽ፣ በቴሌግራም፣ ፌስቡክና ትዊተር ማግኘት እንደሚቻል የምትናገረው ሰላም እስካሁን ታትሞ መሰራጨት አለመጀመሩን ነግራናለች። መምሪያው በማኅበራዊ ድረገጾችና በድረገጽ ላይ እንዲሰራጭ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን አሳትሞ ለማሰራጨት ለሚፈልጉ ዝግጁ ነው። ከለላ ዓላማ አድርጋ የተነሳችው በማኅበረሰቡ ውስጥ ስር የሰደዱ ማኅበረሰባዊ ችግሮችን ለመዋጋትና፣ እነዚህን ችግሮች የሚያስቀጥሉና የሚያባብሱ ሥርዓቶችን ማስወገድ ነው። በዚያውም ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃትን እንዲሁም የሴቶች እኩልነት ጨምሮ ግንዛቤ ለመፍጠር እና መዋቅራዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመስራት መሰባሰባቸውን ሰላም ትናገራለች። ከለላ ለልጆች፤ ከለላ ካዘጋጃቸው መሳሪያዎች መካከል ልጆች ላይ ከሚደርስ ጥቃት ጋር በተያያዘ መምሪያ ሆኖ የቀረበ እና የመጀመሪያ ሥራቸው መሆኑን የምትጠቅሰው ሰላም፤ ከዚህ በኋላ ደግሞ ሌሎች መምሪያዎችም ሆኑ በራሪ ወረቀቶች ሊያዘጋጁ አንደሚችሉ ገልጻለች። ከለላ በትግርኛ፣ በኦሮምኛና በእንግሊዘኛ የወጣ ሲሆን፤ ከዚህ በኋላም በአፋርኛ እና ሶማልኛ ቋንቋዎች የተዘጋጁት መምሪያዎች እንደሚወጡ ሰላም ለቢቢሲ ተናግራለች። እነዚህ በአገር ውስጥ ቋንቋ የተዘጋጁ መምሪያዎች ማንበብ ለሚችሉ የተዘጋጁ ናቸው። ማንበብ ለማይችሉ ደግሞ በሚደመጥ መልኩ ለማዳረስ እየተዘጋጁ ናቸው ተብሏል። ከለላ ለልጆችን በተለያየ ይዘት እና መልክ ተዘጋጅታ ለተለያየ ሕብረተሰብ አካላት ለማዳረስ አቅደው እየሰሩ ከመሆናቸው በተጨማሪ፤ ለወደፊት ከሴቶች እኩልነት፣ ከጾታዊ ጥቃት ጋር የተገናኙ ይዘቶችን አደራጅቶ ለማቅረብ እቅድ እንዳላቸው ለቢቢሲ ገልጻለች። ከለላ ለልጆች ከኢትዮጵያ ቋንቋዎች በተጨማሪ በእንግሊዘኛ ማዘጋጀት ያስፈለገበትን ምክንያት ሰላም ስታስረዳ፤ በኬንያ፣ አንጎላ እና ደቡብ አፍሪካ ላይ መምሪያውን ለመጠቀም ፍላጎት በመኖሩ መሆኑን ታነሳለች። ከለላ ለልጆችን በየአገራቱ አውድ ተርጉሞ ለማቅረብ ፍላጎት በመኖሩ በእንግሊዘኛ ለማዘጋጀታቸው ምክንያት እንደሆነ ጠቅሳለች። ከለላ በውስጧ ምን ይዛለች? ከለላ በአጠቃላይ ስለልጆች ወሲባዊ ጥቃት ምንነት፣ አጥቂዎች እነማን ሊሆኑ እንደሚችሉና፣ ልጆች ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ሊያሳይዋቸው ስለሚችሏቸው ምልክቶች ዝርዝር ጉዳዮችን ይዛለች። እንዲሁም ጥቃትን እንዴት መከላከል እንደሚቻል በመግለጽ፣ ጥቃት ከደረሰ በኋላ ደግሞ ምን መደረግ አለበት የሚለውን በሰፊው ታብራራለች። ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃት በደረሰም ወቅት ሕክምና እና የሕግ አገልግሎት የሚገኝባቸውን አድራሻዎችን አካትታለች። ከለላ በተሰኘው መምሪያ ላይ የሕግ ክፍሎቹን በመጻፍ የተሳተፈችው የሕግ ባለሙያዋ አክሊል ሰለሞን በበኩሏ መምሪያው የያዘው የሕግ ጉዳይ በዋናነት እንዲያተኩር የፈለጉት ተጠቂዎች ማወቅ የሚገባቸውን የሕግ አካሄድ ነጥቦች ለማሳወቅ መሆኑን ትናገራለች። በመምሪያው ላይ ጥቃት ከደረሰባቸው ሰዎች ሕክምና መረጃ የሚወሰደው እንዴት ነው? ማን ነው የሚወስደው፣ የት ነው የሚወሰደው የሚሉት ጉዳዮች በዚህ ክፍል መዳሰሳቸውን ትገልጻለች። አንድ ጥቃት ሲፈፀም የወንጀል ሥርዓቱ ላይ ምን ይመስላል የሚለውን ከምርመራ አንስቶ እስከ የፍርድ ውሳኔ አስኪሰጥ ድረስ ያለው ሂደት በሰነዱ ውስጥ ማካተታቸውን ትናገራለች። ጥቃት ከደረሰባቸው ሕጻናት መረጃ ሲሰበሰብ ምን መደረግ አለበት፣ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ምን ማድረግ አለባቸው፣ የሚለው በመምሪያው ላይ መካተቱን የገለፀችው የሕግ ባለሙያዋ፣ ከአጥቂው ጋር መገናኘት እንደሌለባቸው፣ የሥነልቦና ድጋፍ ማግኘት መብታቸው መሆኑንና እንዲሁም ሌሎች ጉዳዮች መጠቀሳቸውን ገልጻለች። የሕግ ባለሙያዋ አክላም ጥቃት ደርሶ ጥቆማ በሚሰጥበት ወቅት ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች አብረው እንዲሆኑ፣ የሥነልቦና ባለሙያ አብሯቸው እንዲገኝ፤ እንዲሁም የጥያቄው አካሄድ የማይመቻቸው አልያም ለበለጠ ጭንቀትና መረበሽ የሚያጋልጣቸው ከሆነ ማስቆም እንደሚችሉ በመመሪያው ላይ ተቀምጧል ስትል ታብራራለች። አክላም ጥቃት አድራሹ ወላጅ ወይንም አሳዳጊ ከሆነ ደግሞ ምን ዓይነት እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው መካተቱን ታስረዳለች። ተጠቃሚዎች በሕግ ሥርዓቱ ላይ ግራ የሚያጋባቸው ነገር ካለ በከለላ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ላይ ጥያቄያቸውን ማቅረብ እንደሚችሉ፣ በዚያም ምላሽ እንደሚሰጡ ገልፃለች። "በሀገራችን ከሶስት ሴቶች አንዷ ላይ ጾታዊ ጥቃት ይደርሳል"
news-55631983
https://www.bbc.com/amharic/news-55631983
ትግራይ ፡ በመንግሥት ከተያዙት የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አምስቱ
በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በአገርና በመንግሥት ተቋማት ላይ ከባድ ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይታወሳል።
አቶ አባይ ወልዱ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ፣ አብረሃም ተከስተ (ዶ/ር)፣ ሰለሞን ኪዳነ (ዶ/ር) እና አቶ ስብሐት ነጋ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ለወጣው የመያዣ ትዕዛዝ እንደ ዋነኛ ምክንያት የተጠቀሱት ህወሓትን በበላይነት በመምራት በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈጸም፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ በማድረግ በሚሉ ወንጀሎች ተጠርጥረው ነው። ፌደራል መንግሥቱ ኃይሎች ከሦስት ሳምንታት ወታደራዊ ዘመቻ በኋላ የክልሉን መዲና ከተቋጣጠረ በኋላ መንግሥት ለግጭቱና ለተፈጠረው ለቀውስ ዋነኛ ተጠያቂ ናቸው ያላቸውን የህወሓት ፖለቲካዊና ወታደራዊ አመራሮች በቁጥጥር ስር እያዋለ ነው። እስካሁን በመንግሥት መያዛቸው ይፋ ከተደረጉት ግለሰቦች መካከል አምስቱን እነሆ፡ አቶ ኣባይ ወልዱ አቶ አባይ በ1969 ዓ.ም መጨረሻዎቹ ነበር ወደ ህወሓት የትጥቅ ትግል የተቀላቀሉት። ታላቅ ወንድማቸው አቶ አውዓሎም ወልዱ ከህወሓት 11ዱ የትጥቅ ትግል መስራቾች አንዱ ሲሆኑ፤ የድንበር ጦርነቱ እስከተጀመረ ድረስ በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩ ናቸው። ሆኖም በ1993 በድርጅቱ ውስጥ በተፈጠረ መከፋፈል ሁለቱም ወንድማሞቹ ለሁለት ተለይተው ከሁለቱ አንጃዎች አንጻር ቆመው ነበር። አቶ አውዓሎም ከድርጅቱ ከተባረሩት መካከል ነበሩ። አቶ አባይ ወልዱ ለረዥም ግዜ የትግራይ ክልል ምክትል መስተዳደር ሆነው ከቆዩ በኋላ በ2002 ዓ.ም የክልሉ ርዕሰ መስተዳደርነትን ከአቶ ጸጋይ በርሀ ተረክበው እስከ 2011 ዓ.ም አገልግለዋል። እንዲሁም ደግሞ ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ የመሩት ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ በ2004 መጨረሻ ድንገተኛ ሕልፈት ተከትሎ እስከ 2009 የህወሓት ሊቀመንበር ሆነው አገልግለዋል። አቶ አባይ ወልዱ የኢህአዴግ ሥራ ፈጻሚ አባልም የነበሩ ያገለገሉ ሲሆን ኋላ ላይ በህወሓት 13ኛ ጉባኤ ላይ ተገምግመው ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ከመመረጣቸው ቀደም ብለው የክልሉ ማዕከላዊ ዞን አስተዳደር ከዚያም የክልሉ የግብርና ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሰርተዋል። አቶ ኣባይ ሁለተኛ ድግሪ ያላቸው ሲሆን ኢሮብኛ፣ አፋርኛ፣ ትግርኛ፣ አማርኛና እንግሊዝኛ ቋንቋዎችን አቀላጥፈው እንደሚናገሩ ይነገራል። አቶ አባይ ከድርጅቱ ሊቀ መንበርነትና ከክልሉ ርዕሰ መስዳደርነት ተነስተው በደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ነበር የተተኩት። ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ የአቦይ ስብሐት ነጋ ታናሽ እህት ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ በ1970 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ህወሓትን ከተቀላቀሉት ቀደምት ሴት ታጋዮች መካከል አንዷ ናቸው። በትጥቅ ትግል ወቅት ብዙ ጊዜ 'ክፍለ ሕዝብ' ተብሎ በሚጠራው የድርጅቱ የሕዝብ ቅስቀሳ ክፍል የሰሩ ሲሆን በተጨማሪም የታጋይ ሴቶች ማኅበር ሊቀመንበርም ሆነው ለረዥም ግዜ እንደሰሩ ይነገራል። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው የተመረጡት ከደርግ ውድቀት በኋላ በ1987 ዓ.ም ነው። ወይዘሮ ቅዱሳን የመቀለ ከንቲባ ሆነው የሰሩ ሲሆን ቀጥለው የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ሆነው ለበርካታ ዓመታት አገልግለዋል። ወይዘሮ ቅዱሳን ነጋ ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር በክብር ከኃላፊነታቸው የተሰናበቱት። በ1993 ዓ.ም በህወሓት ውስጥ በተፈጠረው መከፋፈል ወቅት ከባለቤታቸው አቶ ጸጋይ በርሀ ጋር አቋማቸውን ቀይረው ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ከወገኑት መካከል ናቸው። አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) ህወሓት/ኢህአዴግን ከተቀላቀሉት አዲሱ ትውልድ አመራሮች መካከል የሚመደቡ ሲሆን፤ የአገሪቱ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው አገልግለዋል። እንዲሆም ደግሞ ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢህአዴግና በአገሪቱ ውስጥ ለውጥ ከተደረገ በኋላ ወደ ትግራይ ሄደው ምክትል ርዕሰ መስተዳደርና የፋይናንስና ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆኖው ሰርተዋል። አብርሃም ተከስተ (ዶ/ር) የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴና ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ናቸው። ኢንጂነር ሰለሞን ኪዳነ (ዶ/ር) በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ኢንጂነር ሰለሞን ኪዳነ (ዶ/ር) ባለፈው ዓመት በተደረገ ሹም ሽር ወቅት ከፌዴራል መንግሥት የኃላፊነት ቦታዎች ከተነሱ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ ነበሩ። ሰለሞን (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከተማ ከነበራቸው ኃለፊነት ከተነሱ በኋላ የትግራይ ክልል ከተማ ልማትና የፋይናንስ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ኢንጂነር ሰለሞን በህወሓት ውስጥ ካሉ ጥቂት ወጣት አመራሮች መካል አንዱ ሲሆኑ የድርጅቱ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ናቸው። አቶ ስብሐት ነጋ ከቀደምት የህወሓት ታጋዮች መካከል አንዱና ድርጅቱ በትግል ላይና በመንግሥት ሥልጣን ላይ በቆየበት ጊዜ ከፍተኛ ተጽእኖና ተደማጭነት የነበራቸው አመራር ነበሩ። ከድርጅቱ ባሻገር ኤፈርት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን የሠሩ ሲሆን የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራተጂያዊ ጥናት ተቋምን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሰርተዋል። ከባላባት ቤተሰብ የወጡት የ86 ዓመቱ አዛውንት አቦይ ስብሐት ነጋ መምህር፣ የመንግሥት ሠራተኛ፣ ታጋይ፣ ህወሓትን ለአስር ዓመታት በሊቀመንበርነት የመሩ መስራች ናቸው።
news-42622638
https://www.bbc.com/amharic/news-42622638
ሱዳን የዳቦ ዋጋ በመጨመርን በተቃወሙ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ አስጠነቀቀች
የዱቄት ዋጋ መወደድን ተከትሎ በሱዳን የዳቦ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል። የሱዳን ባለስልጣናትም የዳቦ ዋጋ መጨመርን በማስመልከት የሚደረጉ ተቃውሞዎችን ለመበተን መንግሥት ኃይል እንደሚጠቀም በመግለፅ እያስጠነቀቁ ነው።
ባለፈው አርብ የሱዳን ዳቦ ቤቶች የዳቦ ዋጋን በእጥፍ ከፍ ማድረጋቸውን ተከትሎ በመዲናዋ ካርቱምና በሌሎችም ከተሞች ተቃውሞ ተቀስቅሷል። እስካሁን በተደረገው የአራት ቀናት ተቃውሞ ቢያንስ አንድ ሰው ሲገደል ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። ተቃውሞውን ተከትሎ የሱዳን መንግሥት ለተቃውሞ የሚወጡትን የማሰር ዘመቻ ላይ ነው። ጉዳዩን በሚመለከት የሚዘግቡ መገናኛ ብዙሃን ላይም እርምጃ እየወሰደ ነው። በተቃውሞ ምክንያት አንድ ተማሪ ሲሞት ሌሎች በመቁሰላቸው በምዕራብ ዳርፉር ትምህርት ተቋርጧል። የሱዳን አገር ውስጥ ሚኒስትር ባቢኪር ዲግና ንብረት በማውደም ተቃውሟቸውን ለመግለፅ የሚሞክሩት ላይ የኃይል እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል። ቢሆንም ግን ተቃውሞዎቹ ከዳቦ ዋጋ ጭማሪ ጋር የተያያዙ መሆናቸውን ክደዋል። የዳቦ ዋጋ ጭማሪ ያሳየው ከሰባት የአሜሪካ ሳንቲም ወደ 14 ሳንቲም ነው። የዚህ ምክንያት ደግሞ መንግሥት የዱቄት ዋጋ ላይ የሦስት እጥፍ ጭማሪ ማድረጉን ተከትሎ ነው። ተቃዋሚዎችም ህዝቡ ይህን ድንገተኛ የሆነ ጭማሪና የኑሮ ውድነትን በመቃወም ወደ ጎዳና እንዲወጣ እየወተወቱ ነው። በርካታ ተቃዋሚዎችም መታሰራቸው እየተነገረ ነው።
news-54748697
https://www.bbc.com/amharic/news-54748697
ቦይንግ 20 በመቶ ሰራተኞቹን ለመቀነስ ማቀዱን አስታወቀ
ቦይንግ በቅርቡ 7 ሺህ የሚሆኑ ሰራተኞቹን እንደሚቀንስ ይፋ አድርጓል።
በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የተጎዳው የአሜሪካኑ አውሮፕላን አምራች ቦይንግ በከፍተኛ ሁኔታ የሰራተኞቹን ቁጥር ለመቀነስ እንዳሰበ ያሳወቀ ሲሆን በመጪው አውሮፓውያኑ አመት መጨረሻም 20 በመቶ የሚሆኑትን ወደ 30 ሺህ ሰራተኞቹን እንደሚቀንስ አስታውቋል። ከቀውሱ በፊት ኩባንያው የነበሩት የሰራተኞች ቁጥር 160 ሺህ ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በተጨማሪ ከ337 ማክስ የደህንነት ስጋቶች ጋር ተደራርቦ ኩባንያውን ለኪሳራ ዳርገውታል። እስከ መስከረም አጋማሽ ባለውም ሶስት ወራት ውስጥ 466 ሚሊዮን ዶላር ከስሬያለሁ ብሏል። ይህም ሁኔታ ለአመት ያህልም ቀጥሏል። ከበረራ ውጭ ሆነው የነበሩት 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ በረራ ሊጀምሩ ይችላሉ መባሉም ጋር ተያይዞም ኩባንያው በእነዚህ አውሮፕላኖች ሽያጭ እንደሚያገግም ተስፋ አድርጓል። 737 ማክስ ሁለት አውሮፕላኖች ተከስክሰው የ346 ሰዎች ህይወት ከጠፋ በኋላ ከበረራ ከታገደ ከአንድ አመት በላይ ሆኖታል። አውሮፕላኑ ሙሉ ሙሉ ከበረራ የታገደው በጎርጎሳውያኑ መጋቢት ወር 2019 ዓ.ም ነበር። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በአየር ጉዞ ኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ቀውስን ያስከተለ ሲሆን በርካታ አየር መንገዶችንም ኪሳራ ውስጥ ጥሏል። በዚህም ምክንያት በርካታ አየር መንገዶች ሰራተኞቻቸውን አባረዋል እንዲሁም አዳዲስ ሊገዟቸው ያሰቧቸውን አውሮፕላኖች በይዋል ይደር ትተውታል። ቦይንግም ሰራተኞችን ከመቀነስ በተጨማሪ ምርቱንም ዝቅ ለማድረግ ተገዷል። ከዚህ ቀደም 10 በመቶ ሰራተኞቹን የቀነሰው ቦይንግ እስከ 2023 ባለው ወቅትም ካለበት ቀውስ እንደማይወጣ ግምቱን አስቀምጧል። ገቢውም በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉ የተነገረለት ቦይንግ በዘጠኝ ወራትም 30 በመቶ ዝቅ ብሏል። የቦይንግ ፕሬዚዳንትና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴብ ካልሁን እንዳሉት የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ በከፍተኛ ሁኔታ ኢንዲስትሪው ላይ ጉዳት ማድረሱን ነው።
news-49246185
https://www.bbc.com/amharic/news-49246185
ኤርትራ በሳዋ ባደረገችው ወታደራዊ ትዕይንት ምን እያለች ይሆን?
ባለፈው ሳምንት የኤርትራ መንግሥት ብሔራዊ አገልግሎት የተጀመረበትን 25ኛ ዓመት ክብረ በዓል በደማቅ ሁኔታ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሮታል።
ዕለቱን አስመልክቶ የሃገሪቱን ርዕሰ ብሔር ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ባለስልጣናት በመገናኛ ብዙኃን ብቅ ብለው ንግግር አድርገዋል። ክብረ በዓሉ ከሙዚቃ፣ ድራማና ሌሎች የአደባባይ ትርዒቶች ባሻገር ወታደራዊ ትዕይንቶችም የቀረቡበት ነበር። •የ "ጥርስ አልባው" ማዕቀብ መነሳት ፖለቲካ? •ኤርትራ፡ ''እናቶች ከህጻናት ልጆቻቸው ጋር ታስረዋል'' ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ በበኩላቸው ኤርትራ የብሔራዊ አገልግሎት ከጀመረችበት አንስቶ ባለፉት 25 ዓመታት የተገኘውን ተሞክሮ በመገምገም ብሄራዊ አገልግሎቱ ለአገር እድገትና ብልጽግና ያደረገው አስተዋፅኦ ከፍተኛ እንደሆነ ተናግረዋል። የኤርትራ ብሔራዊ አዋጅ አገልግሎት ከጤና እክል፤ የቀድሞ ታጋዮች፣ ያገቡና ከወለዱ ሴቶች ውጭ ሁሉም ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆነ ኤርትራዊ ለ18 ወራት ብሔራዊ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል። ነገር ግን አዋጁ እንደሚያዘው ሳይሆን ብዙ ኤርትራውያን ለአስርት ዓመታትም በውትድርና አገልግሎት ተሰማርተው ቆይተዋል። ለዚህም እንደ ምክንያትነት የተሰጠው ኤርትራ ከኢትዮጰያ ጋር ጦርነት ላይ በመሆኗ ነው የሚል ነው። በሁለቱ ሃገራትም መካከል ሰላም ቢሰፍንም የብሔራዊ አገልግሎቱ እጣ ፈንታ ግን እስካሁን አልለየም። የኤርትራ መንግሥት በበኩሉ ኢትዮጵያ ከኤርትራ መሬት ስላልወጣች ወታደሮቹ አሁንም ባሉበት እንደሚቀጥሉ ተናግሯል። ሁለቱ ሃገራት የሰላም ስምምነቶችን ሲፈርሙ ኤርትራ የኔ ናቸው የምትላቸው መሬቶች ጉዳይ ለምን ውል አልያዘም ብለው የሚጠይቁ ጥቂቶች አይደሉም። በዚሀም ክብረ በዓል ላይ የሃገሪቱ ፕሬዚዳንትም ሆነ ሌሎቹ የሃገሪቱ ባለስልጣናት ብሔራዊ አገልግሎቱ አዋጁ ባስቀመጠው መሰረት (ለአስራ ስምንት ወራት) ለማከናወን እቅድ ስለመያዙ የተናገሩት የለም፤ በሁለቱ ሃገራትም መካከል ስለተደረሱ ስምምነቶችም ምንም ጉዳይ አልተነሳም። ከፍተኛ ወታደራዊ ትእይንት ለምን? በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ሲከበር የሰነበተው ይሄው ክብረ በዓል ባለፈው ሐሙስ በባህላዊ ስፖርትና በከፍተኛ የጦር መሳርያ በታጀበ ወታደራዊ ሰልፍ በሳዋ ተጠናቋል። በዚህም ወታደራዊ ትእይንት ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው ታንኮች፣ የጦር ሄሊኮፕተሮችና ተዋጊ አውሮፕላኖች እንዲሁም መሳሪያ እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ መኪኖች ተሳትፈዋል። ከፍተኛ ወታደራዊ ትዕይንት በነበረበት በዚህ ስፍራ ላይም ወታደሮች ከጦር ሄሊኮፕተሮች ላይ በፓራሹት ሲወርዱ እንዲሁም ተዋጊ አውሮፕላኖቹ በሰማይ ላይ ሲያንዣብቡ ታይተዋል። ይህ ወታደራዊ ትእይንት ለዓመታት ኤርትራ የገነባችው የብሔራዊ አገልግሎት ውጤት ማሳያ መሆኑንም መድረኩን ይመሩ የነበሩት ግለሰቦች በተደጋጋሚ ሲገልፁ ነበር። ይህ ትእይንት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላም ባልነበረችበት ወቅት ብዙ አስገራሚ ባይሆንም በሁለቱ ሃገራት መካከል ሰላም መስፈን ተከትሎ እንዲህ አይነት ከፍተኛ ወታደራዊ የጦር ትዕይንት ማሳየቷ የአፍሪካ ቀንድን የፖለቲካ ሂደት ለሚከታተሉ ጥያቄን አጭሯል። •ኤርትራ የሃይማኖት እሥረኞችን ፈታች ወታደራዊ ትይንቱ እንግዳ ከሆነባቸው መካከል የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኙና የወርልድ ፒስ ፋውንዴሽን ዳይሬክተር ዶክተር አሌክስ ድቫል ዋነኛው ናቸው። በአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ግጭቶች፣ የሰላምና ግንባታ እንዲሁም የከሸፉ አገራትን በተመለከተ በርካታ ጥናታዊ ስራዎችና ፅሁፎች ያቀረቡት አሌክስ ድቫል "የታየው ሰልፍና ወታደራዊ ትርዒት በተለይ ሰላም በሰፈነበትና ሀገራቱ ተረጋግተው ባለበት ሁኔታ የተካሄደ በመሆኑ እንግዳ ነገር (odd) ሊባል የሚችል ነው።" ይላሉ። ለዚህም እንደምክንያት የሚጠቅሱት ከኢትዮጵያ ጋር የተጀመረው የሰላም ሂደት በአሁኑም ወቅት ቀጣይ በመሆኑ እንዲሁም ለዓመታት ከሱዳን ጋር ተፋጣ የነበረችው ኤርትራ ሰላም መፍጠሯ እንዲሁም ለሶስት አስርት አመታት በስልጣን ላይ የነበሩት ኦማር አልበሽር መውደቅን ተከትሎ በሱዳን የሲቪል አስተዳደር እየተመሰረተ መሆኑ ኤርትራ ከአካባቢው አገራት ጋር ያላት ግንኙነት በአዲስ መልኩ እንደሚታይ ይናገራሉ። ከሺል ትሮንቮል፣ አሌክስ ድቫል፣ከርት ሊንዲየር፣ ሚከላ ሮንግና ዳን ኮኔል ከዚህም በተጨማሪ ከጎረቤቶቿ ጋር ብቻ ሳይሆን ኤርትራ ከመካከለኛ ምስራቅ አገሮች በተለይ ደግሞ ከሳዑዲ ዓረቢያና ከኢሚሬትስ ጋር ያላት ግንኙነት በተሻሻለበት ወቅት እንዲህ ዓይነት ወታደራዊ ትርኢት ማሳየት አስፈላጊ አልነበረም የሚል አቋም አላቸው። ዶክተር አሌክስ አሁን ኤርትራ እያደረገችው ያለውን "አትኩሮት ፍለጋ" ባለፉት ከነበረው አስርት አመታት የሃገሪቴ ስትራቴጂ (አካሄድ) አንፃር መታየት እንዳለበት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። "ባለፉት 20 ዓመታት የፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ስትራተጂ (አካሄድ) በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ትኩረት እንዲያገኙ መስራት ነበር። ይህ አኳኋን ደግሞ የሚረብሽና ሰላምን የሚያደፈርስ አካሄድ ነበር። "ይላሉ በዚህ ጥቂት አመታት ግን በአካባቢው የነበረው ግጭት መቀነስ፤ እንዲሁም የአረብ ኤምሬትስ በአከባቢው ያላቸው ተጽዕኖ እየቀነሰ መምጣትን የአሰብን አስፈላጊነት እየቀነሰ ስለሚመጣ ይህ ደግሞ የኤርትራን ወይም የመሪዋን "እዩኝ" ማለት ተፅእኖ ሊፈጥርበት ይችላል ይላሉ። አሰብ በየመን ሲካሄድ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት መናሃርያ ነበረች። ምሁሩ አክለውም "ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ከወዳጆቹ ጋር ብቻ ሳይሆን በተዘዋዋወሪ ኤርትራን ከሚፈልጓት ሃገራት ከሳውዲዓረብያ ኣጋሮች (ማለትም ከአሜሪካ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ቻይና) ተፈላጊነትም ዝቅ ሊል ይችላል" ይላሉ። በአጠቃላይ ወታደራዊ ትዕይንቴ ፕሬዚዳንቱ እንዳይዘነጉ ወይም ኤርትራ ያላትን ስፍራ ቀልብ የመሳብ ጉዳይ ነው በማለት ያስቀምጡታል። ባለፈው ዓመት ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር የተለያዩ የሰላም ስምምነቶችን ቢፈራረሙም አሁንም ቢሆን ፕሬዚዳንቱ ከህወሐት ጋር ያላቸው መካረር መፍትሄ እንዳላገኘ ዶክተር አሌክስ ይናገራሉ። •በኢትዮ-ኤርትራ ድንበር ንግድ ተጧጡፏል "ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር ሰላም ሲፈጥሩ ኤርትራን በፅኑ ወጥረዋት የነበሩትን የህወሐት መሪዎች ቅርቃር ውስጥ የሚያስገቡ (የሚጨፈልቁ) መስሏቸው ነበር። በእርግጥ ለውጡን ተከትሎ ህወሐት በማዕከላዊ መንግሥት የነበረው ሚና ተዳክሟል። ሆኖም እንደታሰበው አይደለም። የትግራይ ህዝብ ደግሞ ከወንድሙ የኤርትራ ህዝብ ጋር የተደረገው የሰላም ስምምነት በጸጋ ነው የተቀበለው።" በማለት የተጠበቀውና የሆነውን ሁኔታ ይገልፁታል። ምሁሩ ጨምረውም ከህወሐት ጋር ያለው ሁኔታ ሰላምም ጦርነትም ባለመሆኑ ፕሬዚዳንቱ ኃያልነታቸውን ማሳየት መፈለጋቸው የትዕይንቱ ዋነኛ ትኩረት ይላሉ። "ሰላም ለፕሬዚደንት ኢሳይያስ ስልጣን ከጦርነት በላይ ከባድ ፈተና ነው። ህዝቡ በጦርነት ተሸብሮ ከሚኖር ሰላም ሲያገኝ ነው ዓይኑን የሚገልጠው። በዚህ ምክንያት ነው ፕሬዚደንት ኢሳይያስ 'አሁንም ኃይሌ እንዳለ ነው' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ የሞከሩት የሚመስለኝ" ብለዋል። መቀመጫውን ኬንያ ያደረገውና ዘ አፍሪካኒስት ኢንፎ የተሰኘ ድረ ገፅ ያለው ሆላንዳዊው ጋዜጠኛ ከርት ሊንዲየር በበኩሉ ባለፈው ዓመት የተገኘው ሰላም ከብዙ ውጣውረድ በኋላ የመጣ መሆኑን በማስታወስ "በእንደዚህ ሁኔታ ሰላምን የሚያደናቅፍ ትርኢት ማካሄድ አስፈላጊ አልነበረም። እኔ እንደሚመስለኝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው የስልጣን ሽምያ ወዴት እንደሚያዘነብል የሚጠባበቁ ይመስለኛል" ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል። ሳዋ የታለመለትን ግብ ከመምታቴ አንፃር ከዚህ በኋላ ሊቆም ይገባል የምትለው ደግሞ በኤርትራ ላይ በሚያጠነጥነው መፅሀፏ"I Didn't Do It For You: How the World Used and Abused a small African Nation" በሚል የምትታወቀው ሚከላ ሮንግ ናት። "በአፍሪካ ቀንድ አዲስ የሰላም አየር እየነፈሰ ስለሆነ ኤርትራ በተጠንቀቅ መኖር የለባትም። የኤርትራ ወጣቶች ማብቅያ በሌለው የወታደራዊ አገልግሎት ምክንያት ሀገራቸውን ጥለው በመሰደድ ላይ እንደሆኑ ዓለም እየታዘበ ነው" ትላለች። ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር ሰላምን መፍጠሯ ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የሚናገሩት ተንታኟ ለኤርትራ ህዝብም አዲስ አይነት አስተዳደር ማምጣት ነበረባቸው ይላሉ። "የሁለቱ ሃገራት መሪዎች ከተጨባበጡ ጀምሮ ኤርትራውያን ልጆቻቸው ከወታደራዊ አገልግሎት ነጻ የሚወጡበት ፖሊሲ እንዲተገበር በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ" የምትለው ሚከላ ሮንግ "ባለፈው ሳምንት በሳዋ የተመለከትነው በከባድ የጦር መሳርያዎች የታጀበ ትዕይንት ግን 'የተለወጠ ነገር የለም ሁሉም እንደነበረበት ይቀጥላል' የሚል አንድምታ አለው" ትላለች። አሜሪካዊው የፖለቲካ ተንተኝ ዳን ኮኔልም የሚከላን ሀሳብ ይጋራል። •የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት ጦስ በሶማሊያ? "ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ የኢትዮ ኤርትራ ዕርቀ ሰላም ከተፈረመበት ከአንድ አመት በኋላ ህዝቡን አሰባስቦ ወደ ሌላ የፖለቲካ ምዕራፍ ሊያሻግራቸው በተገባ ነበር" ይላል። ነገር ግን የፕሬዚዳንቱ ፖለቲካ ወደየትም ፈቅ እንዳላለ ማሳያው ደግሞ ጦርነት በሌለበት ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ወታደራዊ ትእይንት በቅርቡ ማሳየቷ ነው። "በድሮ ፖለቲካው ተቸክለው የቀሩ ይመስለኛል" በማለት "በከባድ መሳርያ የታገዘ የጦር ትዕይንት የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ሊያስጨንቅ ስለሚችል ሊታሰብበት ይገባ ነበር" ሲል አስተያየቱን ያጠናክራል። "የጦር ትዕይንቱ የኤርትራ ወጣቶች ምን ያክል አቅም እንዳለቸው ያሳየ ቢሆንም የከባድ መሳርያ ትዕይንቱ ግን ይረብሻል" በማለትም ሀሳቡን ያጠናቅቃል። ሌላኛው የሰላም እና ግጭት ጥናት ምሁር ፕሮፌሰር ጀትል ትሮንቮል በበኩላቸው ወታደራዊ አገልግሎት የሀገር አንድነት በመገንባት ረገድ ትልቅ ፋይዳ ያለው ቢሆንም ዓለማውን እንዳይስት በተጣያቂነት አሰራር ሊተገበር እንደሚገባ ምክራቸውን ይለግሳሉ። "የተካሄዱት ጥናቶች እንደሚያመላክቱት ኤርትራውያን ከሀገራቸው የሚሰደዱበት ዋነኛው ምክንያት መጨረሻ የሌለው ብሔራዊ አገልግሎት ነው። ብሔራዊ አገልግሎቱ ወጣቶቹ መጪ ህይወታቸውን ስለሚያጨልምባቸው ሀገራቸው ከመገንባት ይልቅ ወደ ውጪ ሀገራት በመሰደድ ላይ ናቸው" ይላሉ። በአጠቃላይ ይላሉ ምሁሩ የሰሞኑ የጦር መሳርያዎች ትዕይንት ኃይልን ለማሳየትና ፕሬዚደንት ኢሳይያስ "ከእነ አቅሜ ነኝ ለማለት የፈለጉ ይመስለኛል" ይላሉ።
news-56616309
https://www.bbc.com/amharic/news-56616309
'የሐዘን መግለጫ ማውጣት ሰልችቶናል' አቶ አገኘሁ ተሻገር
በተለያዩ ስፍራዎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች በሚገደሉ የአማራ ተወላጆች የሐዘን መግለጫ መውጣት የክልሉ መንግሥት እንደሰለቸው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ተናገሩ።
በምዕራብ ወለጋ ውስጥ የተገደሉ ሰላማዊ ሰዎችን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ ላይ ርዕሰ መስተዳደሩ እንደተናገሩት በተደጋጋሚ በሚፈጸሙ ጥቃቶች ሐዘናቸው እንደበረታና ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ ጠይቀዋል። "የፖለቲካ ልዩነት ሊኖር ይችላል ህፃናትና እናቶች ግን መሞት የለባቸውም" ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ፤ "የሐዘን መግለጫ ማውጣት ሰልችቶናል፣ በጉዳዩ ላይ እልባት እንዲሰጥ እንፈልጋለን" ሲሉ ችግሩ በቶሎ መፍትሄ እንዲበጅለት ጥሪ አቅርበዋል። የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘሁ ተሻገር ክስተቱን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ላይ በአማራ ብሔር አባላት ላይ የሚፈጸመውን ግድያ የፌደራል መንግሥት በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጥ ክልላቸው እንደሚፈልግ ተናግረዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በአማራ ላይ የሚፈጸመው ግድያ እንዲቆም የክልሉ መንግሥት በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ውይይት እንደሚፈልግም አስታውቀዋል። በተለያዩ ጊዜያት በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በሚፈጸሙ ጥቃቶች "በተለይም ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን አማራን ነጥሎ በማጥቃት የሚታወቅ ነው። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ነፃ አውጭ ነኝ የሚል ቡድንም በአማራ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት እያደረሰ ነው" ሲሉ ጥቃቱ በማን እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ችግር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የገለጹት አቶ አገኘሁ፤ ከሰሞኑ በተፈጸመው ግድያም የክልሉ መንግሥት ማዘኑንና "ይህ ጉዳይ ካልተሻሻለ የአገሪቱን ዜጎች ተቻችለው የመኖር ሁኔታን አደጋ ላይ የሚጥል ነው" በማለት ችግሩ የአማራ ክልልን እንዳሳሰበው ገልጸዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በምዕራብ ኦሮሚያ ጥቃቱ ፈጽሟል ያሉት ኦነግ-ሸኔ "ከኦሮሚያ ክልል አልፎ በክልላችን ገብቷል" በማለት፣ "አንዳንዶች ኦነግ-ሸኔ ስለመኖሩና ስላለመኖሩ ሊነግሩን ይፈልጋሉ፤ ምን አይነት መግለጫ ማውጣት እንዳለብን ሊነግሩን የሚፈልጉም አሉ። ይህ ተገቢ አይደለም" ማለታቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የምዕራብ ወለጋ ጥቃት በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የበርካታ ሰዎችን መገደል ተከትሎ ድርጊቱ ከተለያዩ ወገኖች ውግዘት ገጥሞታል። ማክሰኞ መጋቢት 21/2013 ዓ.ም በምዕራብ ወለጋ ዞን ባቦ ገንቤል በተባለው ወረዳ በቦኔ ቀበሌ የነዋሪዎችን ማንነት በለየ ሁኔታ የተፈጸመውን ጥቃት በቀዳሚነት ይፋ ያደረገው የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ነበር። መስተዳደሩ ስለተፈጸመው ጥቃት ባወጣው መግለጫ ላይ "አሰቃቂና ዘግናኝ" ያለውን ጥቃት የፈጸመው ኦነግ-ሸኔ እንደሆነ ጠቅሶ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ እርምጃ መወሰዱንና ይህም እንደሚቀጥል ገልጾ ነበር። በማስከተልም የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል አራርሳ መርዳሳ ኦነግ-ሸኔ የተባለው ቡድን በጥቃቱ "ጭፍጨፋ ፈፅሟል" በማለት ቡድኑን ተጠያቂ አድርገዋል። ኮሚሽነሩ ጨምረውም በጥቃቱ የተገደሉት 28 ሰዎች ሲሆኑ ከመካከላቸውም 16ቱ ወንዶችና 12ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ገልጸው ሌሎች 12 ሰዎችም ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል። ጥቃቱ መፈጸሙ ከተሰማ በኋላ የተለያዩ ወገኖች በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ በማውገዝ መግለጫ በማውጣት ሐዘናቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሰውን ጥቃት እንደሚያወግዙና የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ለሟች ቤተሰቦችና ለኢትዮጵያውያን ገልጸዋል። ጨምረውም በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ የክልልና የፈዴራል መንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በቅንጅት የአጸፋ እርምጃ እየወሰዱ መሆናቸውን አመልክተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም "ጠላቶቻችን በውስጥና በውጭ ተደራጅተው ንጽሐን ዜጎቻችንን በመግደል የጀመርነውን ጉዞ ለማሸማቀቅና ከመንገዳችን ለማስወጣት ጥረት እያደረጉ ነው። መሥዋዕትነት እየከፈልንም ቢሆን የኢትዮጵያን አንድነት አጠናክረን ጉዟችንን እንቀጥላለን" ብለዋል። ሕዝቡም በጥፋት ኃይሎች ወጥመድ ላይ ላለመግባት በማስተዋል እንዲጓዝ ጠይቀው፤ በእንደዚህ ዓይነት ጉዳዮች ከመንግሥት ጋር ተባበሮ ጥፋተኞችን ወደ ሕግ ለማቅረብና ግድያዎች እንዲቆሙ በትብብር ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽኑ በምዕራብ ወለጋ በነዋሪዎች ላይ የተፈፀመው ጥቃት በአካባቢው ያለው የፀጥታ ሁኔታ አለመሻሻሉንና ይልቁንም በክልሉና በአዋሳኝ አካባቢዎች እየተስፋፋና ተያያዥ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እያስከተለ መሄዱን ያሳያል ብሏል። ጨምሮም የፌዴራል መንግሥት አካባቢውን ለማረጋጋት በጊዜያዊነት ከሚወስዳቸው እርምጃዎች በተጨማሪ ነዋሪዎች በየትኛውም ክልል በሰላም የመኖር መብታቸውን በሚያረጋግጥ መልኩ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር መጠነ ሰፊና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፈ እቅድ መንደፍ እንደሚኖርበት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል። የአሜሪካ ኤምባሲ ኤምባሲው በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ሰሞኑን በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ክልሎች የተፈጸሙ ጥቃቶችን በሚመለከት ባሰፈረው መልዕክት ላይ ድርጊቶቹን አውግዟል። "በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ውስጥ የተፈጸሙትን የሰላማዊ ሰዎች ግድያን አጥብቀን እናወግዛለን" ብሏል። ለሟቾች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የተሰማውን ሐዘን የገለጸው ኤምባሲው፤ "እንዲህ አይነት ግድያዎችን ተቃውመን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጎን እንቆማለን" ሲል ጥቃቶቹን አውግዟል። ኢዜማ ተፎካካሪ ፓርቲ የሆነው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ-ኢዜማ ሰሞኑን የተፈጸመውን ጥቃት መሠረት አድርጎ "አገሪቱ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለውን ማንነት ላይ ያተኮረ ግድያን" በተመለከተ መግለጫ ውጥቷል። ኢዜማ በመግለጫው ባለፉት ሦስት ዓመታት በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በተለይም በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ በአሰቃቂ ሁኔታ በተደጋጋሚ ጥቃት ሲደርስባቸው መቆየቱን ጠቅሶ፤ በዚህ ሳምንት በምዕራብ ወለጋ የተፈጸመውን ግድያ በማውገዝ ሐዘኑን ገልጿል። በዚህ ሳምንት ከተፈጸመው ጥቃት ከተረፉ ሰዎች ሰማሁ ያለው ኢዜማ "ጥቃቱ ከመፈፀሙ በፊት አካባቢውን ለቅቀው እንዲወጡ አካባቢውን እንዲያስተዳድሩ ኃላፊነት ከተሰጣቸው የቀበሌና ወረዳ ኃላፊዎች ማስፈራሪያ ደርሷቸው ነበር" ብሏል። በተደጋጋሚ የተፈጸሙት ጥቃቶችና ወንጀሎች በታወቁና ውስን በሆኑ ቦታዎች መሆኑን የገለጸው ኢዜማ፤ ይህም "በክልልም ሆነ በፌደራል መንግሥት በኩል ችግሩን የሚመጥን ትኩረት ላለማግኘቱ አመላካች ነው" ብሏል። የአገሪቱን ሰላም ለማናጋት በአገሪቱ ውስጥ ባሉ ከፍተኛ ቁጥር ባላቸው ማኅበረሰቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት ሊያስነሱ የሚችሉ ጥቃቶች ሆን ተብሎ በተቀነባበረ መንገድ እየፈፀሙ መሆናቸውን ፓርቲው ይገልጻል። ፓርቲው በጥቃቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች መደረግ ስላለበት ድጋፍና በዘላቂነት እንዲህ አይነቶቹን ጥቃቶች ለማስቆም ሊወሰዱ ይገባል ያላቸውን እርምጃዎች በመግለጫው ላይ አስፍሯል። ኦነግ-ሸኔ ሰሞኑን የተከሰተውና ቢያንስ ለ28 ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን ጥቃት ፈጽሟል ተብሎ የተከሰሰው መንግሥት ኦነግ-ሸኔ የሚለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን በምዕራብ ኦሮሚያ እንደሚንቀሳቀስ ይነገራል። ቡድኑ ከሁለት ዓመት በፊት የትጥቅ ትግልን ትቶ ወደ አገሪቱ የፖለቲካ መድረክ ከተመለሰው ከኦሮሞ ነጻነት ግንባር ተለይቶ የወጣ ሲሆን ከበርካታ ጥቃቶችና ግድያዎች ጋር ስሙ በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ነው። ታጣቂው ይንቀሳቀስባቸዋል በሚባሉት የምዕራብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች በተለያዩ ጊዜያት በተፈጸሙ ጥቃቶች በርካታ ሠላማዊ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ተዘግቧል። በተጨማሪም በአካባቢው ባሉ የመንግሥት መዋቅሮች ውስጥ የሚሰሩ ሰዎችን፣ የጸጥታ አካላትንና አመራሮችን በተለያዩ ጊዜያት በቡድኑ በተፈጸሙባቸው ጥቃቶች ሰለባ ሆነዋል። ለእነዚህ ጥቃቶችም መንግሥት ተጠያቂ የሚያደርገው በኩምሳ ድሪባ (ጃል መሮ) ይመራል የሚባለው ኦነግ-ሸኔን ሲሆን ቡድኑ ግድያዎቹን አለመፈጸሙንና በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ እንደሚፈልግ ሰሞኑን መሪው ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ተናግሯል። መንግሥት ታጣቂ ቡድኑን ከአካባቢው ለማስወገድ በተለያዩ ጊዜያት በወሰዳቸው እርምጃዎች በርካታ የቡድኑን አባላት መግደሉንና መማረኩን ሲገልጽ መቆየቱ ይታወሳል። የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር እንዳሉት ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የጸጥታ አካላት በኦነግ-ሸኔ ላይ በተወሰዱት እርምጃ 1947 አባላቱ ሲገደሉ 489ቱ ደግሞ መማረካቸውን ተናግረዋል።
44249353
https://www.bbc.com/amharic/44249353
''አፈረሱት አሉ ውቤ በረሃን...'' ትንቢት ነበር?
ወንዶቹ በ1950ዎቹ የዘመኑ ፋሽን የነበረውን ኮሌታው ረዘም ባለ በሚያብረቀርቅ ሸሚዝ ደምቀው፣ አፍሯቸውን ከፍክፈው፤ ሴቶቹም በጊዜው ገትር በሚባለው ጉርድ ቀሚስ ሸሚዛቸውን ሻጥ አድርገው፣ ታኮ ጫማቸውን ተጫምተው፣ አፍሯቸውን አበጥረው ወደ ደጃች ውቤ (ውቤ በረሃ) አሰገደች አላምረው ቤት ጎራ ይሉ እንደነበር ፀሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ ያስታውሳሉ።
"ከዚያማ የምሽቱ ህይወት ይጀመራል። ሙዚቃው ያለማቋረጥ ይንቆረቆራል። እኛም በምናውቀው ሩምባ፣ ቡጊውን ለመደነስ እንወናጨፋለን" ይላሉ። ቯልስ ለመደነስ ሙከራ ቢያደርጉም መጠጋጋትን ስለሚሻ በጊዜው የነበሩ ሴቶች ይመርጡት እንዳልነበር ሲያስታውሱ ይስቃሉ። የዱሮ አራዳ የሚባሉት የውቤ በረሃ አድማቂዎች እንደነበሩ አያልነህ ትውስ ሲላቸው በተለይ በጊዜው "ጀብደኛ" ይባል የነበረውና በቅፅል ስሙ ማሞ ካቻ ተብሎ ይጠራይ የነበረው ግለሰብ ስም ከአዕምሯቸው አይጠፋም። ወደ ውቤ በረሃ መዝለቅ የጀመሩት ገና ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪና የ16 ዓመት አፍላ ጎረምሳ እያሉ ነበር። በዚያን ጊዜ 1 ብር ይሸጥ የነበረውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ቢራ መጠጣት አቅማቸው ስለማይፈቅድ በ25 ሳንቲም ጠጃቸውን ጠጥተው ማስቲካ እንደሚያኝኩ እየሳቁ ይናገራሉ። ይሄ ትዝታ እድሜ በጠገቡት ሰዎች ብቻ ሳይሆን በእድሜ ባልገፉት እንደ ታዋቂው ሙዚቀኛ ፍሬው ኃይሉ ልጅ ባሉትም የሚታወስ ነው። ዳዊት ፍሬውም ከትውልድ ትውልድ ተላልፎ በእሱ እድሜ በኮንጎ ነፃነት ታጋይ ስም ፓትሪስ ሉሙምባ የተሰየመውን የውቤ በረሃ ክለብን ያስታውሳዋል። ከኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ጋር ተያይዞ ደጃች ውቤ ብዙ አስተዋፅኦ እንዳደረገ የሚናገረው ዳዊት "በከተሜነት" ዙሪያም ፈር ቀዳጅ ከሆኑ አካባቢዎች አንዱ እንደሆነ ይናገራል። በኢትዮጵያ የዘመናዊነት ታሪክ ትልቅ ስፍራ ያለውና በ1960ዎቹ የሥነ-ፅሁፍ፣ ሙዚቃና ጥበብ ትልቅ ቦታ ያለው ውቤ በረሀ ታሪካዊው አሻራው ላይመለስ ፍርስራሽ ሞልቶታል። የአካባቢው የመፍረስ ዜና ሲሰማ ብዙዎችን እንዳስደነገጠ የሚናገረው ዳዊት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘንም የገለፀው ለውቤ በረሃ በማዜም ነው። የሚኖረው ሰሚት አካባቢ ቢሆንም ዘወትር ወደ የደጃች ውቤ ያቀናል። የደጃች ውቤ ትዝታ አይለቅምና። "ስምህ በወጭ ወራጁ የሚታወቅበትና ሁሉም እጁን ዘርግቶ የሚቀበልህ ቦታ ነው" ይላል። በተለይም የአኮርድዮን ሙዚቃ መሳሪያን በመጫወት የሚታወቀውን አባቱን በማስታወስም ሲያልፍ፣ ሲያገድምም "ያባቱ ልጅ ውቤን ገዛሽው" ይሉት እንደነበር ያስታውሳል። ዳዊት የውቤ በረሃ መፈራረስን ሲመለከት ደርግ ስልጣን በተቆጣጠረበት ወቅት ከተማ መኮንን የዘፈነው "አፈረሱት አሉ ዉቤ በረሃን" ለአሁኑ የውቤ በረሃ መፈራረስ ትንቢት እንደሆነ ይሰማዋል። በጊዜው በሰዓት እላፊ ምክንያት በደጃች ውቤ አካባቢ ዘፈን እንዳይዘፈን በመደረጉ "አፈረሱት አሉ" እንደተዘፈነ ይናገራል። ደጃች ውቤ ሰፈር ከፈረሰ በኋላም ብዙዎች ይህን ዘፈን የስልክ መጥሪያ እንዳደረጉ በሀዘን ይገልፃል። ከአዲስ አበባ መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ጋር ተያይዞ ጥንታዊው ደጃች ውቤ ሰፈር (ውቤ በረሃ) የመፍረስ ዜና ሲሰማ ብዙዎችን አስደንግጧል። በዚህም ታሪካዊ የሚባሉ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ እንደ አድዋ ሆቴል፣ የታዋቂው ሙዚቀኛ ፍሬው ሀይሉ ቤት፣ በአፄ ምኒልክ ዘመነ-መንግሥት ከቱርክ መሳሪያ ያመጣ የነበረው አርመናዊው ቴርዚያን ቤትና የአፈ-ንጉሥ ተክሌ ቤት ይገኙበታል። ሰፈሩ አሁን የሚገኝበትን ሁኔታ በማየት ምን ያህል የደመቀ ስፍራ እንደነበር መገመት ይከብዳል። "ምሽቱ አይነጋም" የተባለለት የዚህ ሰፈርን ዝና በጊዜው ያልነበሩት የሚናፍቁትና ሁሉም የእኔ የሚለው ዓይነት እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክራሉ። ቦታው ባንድም ይሁን በሌላ ከብዙ ሙዚቀኞች ትዝታ ጋርም የተቆራኘ ነው። ሙዚቀኞች ብቻም ሳይሆኑ አንቱታን ያገኙ የኢትዮጵያ ፀሀፊዎችና ገጣሚዎች ይህን ቦታ በሥራዎቻቸው ገልፀውታል። ከእነዚህም አንዱ የስብሃት ገብረ-እግዚአብሔር በ"ሌቱም አይነጋልኝ" መፀሃፉ በሰፈሩ ያለውን የሴተኛ አዳሪ ህይወትና ሰቀቀኑን፣ ድህነትን፣ ሙዚቃውን እንዲሁም የማህበራዊ ህይወት ትስስሩን ቃኝቷል። የውቤ በርሃ ውልደት? ሙዚቃና ፖለቲካ በ21ኛው ክፍለ-ዘመን (Music and Politics in Twentieth Century Ethiopia: Empire, Modernization and Revolution) በሚለው የስሜነህ ገብረ-ዮሀንስ የድህረ-ምረቃ የጥናት ፅሁፍ ምንም እንኳን የአዝማሪ ሙዚቃ በዚያን ጊዜ ታዋቂ ቢሆንም በጣልያን አምስት ዓመት ቆይታ ክለቦች ብዙ እንደተስፋፉ ያትታል። በዚያን ጊዜ ታዋቂ የነበሩት ቤላ ፖፑላ፣ ቪላ ቨርዲና ላ ማስኮቴ የሚጠቀሱ ናቸው። የክለቦች ሀሳብ የተጠነሰሰው በልጅ ኢያሱ ጊዜ እንደሆነ የሚናገረው ስሜነህ ማዕከሉም ቤታቸውን በዛ አካባቢ ባደረጉት በንግሥት ዘውዲቱ ሁለተኛ ባል ደጃች ውቤ የሚል መጠሪያ እንደተሰጠው ይገልፃል። የደጃች ውቤ ቤት አሁን አዲስ አበባ ሬስቶራንት የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን አካባቢውም ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያንን ይዞ አፍንጮ በር ይደርሳል። በኋላም ብዙዎች በምሽትና በመጠጥ ህይወት ሰጥመው የሚቀሩበት በመሆኑ ውቤ በረሃ የሚል መጠሪያ እንደተሰጠው የስሜነህ ፅሁፍ ያትታል። ደጃች ውቤም የኮሪያ ዘማች ወታደሮች ብዙ ገንዘባቸውን የሚያጠፉበት ቦታ እንደነበረም ይነገራል። በጊዜውም ሬድዮ ድንቅ ስለነበር ዳጃች ውቤ አካባቢ በሚገኙ ክለቦች ብዙዎች መምጣት ጀመሩ። እነዚህ መጠጥ ቤቶች (ክለቦች) የዚያኔ አዝማሪዎችን እንደተኳቸውና በተለይም የአሰገደች አላምረው እንዲሁም ከሶሪያ የመጡት ኮሪንፊሊ ታዋቂነትን ማትረፍ ችለዋል። እነዚህ ክለቦች ታዋቂነታቸው እየቀነሰ ሲመጣ ሰዎች ዶሮ ማነቂያ አካባቢ ይገኝ ወደነበረው ሜሪ አርምዴ ክለብ ማምራት እንደ ጀመሩ የስሜነህ ፅሁፍ ያስረዳል። የኮንጎ ዘማቾች መበራከት፣ የ1953 መፈንቅለ-መንግሥትን እንዲሁም የ1960ዎቹ የተማሪዎች እንቅስቃሴን ተከትሎ ፈጥኖ ደራሾች ፖሊሶች በከተማው ውስጥ መንሰራፋታቸው የክለቦችን ቁጥር እንደጨመረው ፅሁፉ ያትታል። ምንም እንኳን የክለቦች ቁጥር እየጨመረ ቢመጣም የደጃች ውቤ ማዕከልነት እየቀነሰ መጥቶ ትልልቅ ቪላዎች ወደ ክለብነት ተቀይረው ብዙዎች ንፋስ ስልክ አካባቢን ማዘውተር ጀመሩ። ማፍረስ የመጨረሻው አማራጭ ነበር? በአሁኑ ወቅት ደጃች ውቤ በፍርስራሾች ተሞልታለች። ምንም እንኳን መንግሥት ለልማት ነው ቢልም እነዚህ ታሪካዊ ሰፈሮች ከመጥፋታቸው በፊት የከተማዋ እቅድ ውስጥ ሊካተቱ እንደሚገባ የታሪክ አጥኚዎች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ። በአዲስ አበባ መሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ የኮሚኒኬሽን አስተባባሪ አቶ ንጉሡ ተሾመ ሰፈሮቹ የተጎሳቆሉና የደቀቁ በመሆናቸው ምክንያት ለመልሶ ማልማት እንደሚፈርሱ ይናገራሉ። ለመልሶ ማልማት ተግባር ከመዋላቸው በፊት ብዙ ጥናቶች እንደሚደረጉባቸው የሚናገሩት አቶ ንጉሡ እነዚህ ሰፈሮች መሰረተ-ልማታቸው ያልተሟላ እንዲሁም አደጋ ቢከሰት መውጫ የሌላቸው እንደሆኑ ይጠቁማሉ። "ስያሜዎቹ አልተቀየሩም። አካባቢዎቹ ግን የተጎሳቆሉ ናቸው። ለመኖር ቀርቶ ለማለፍ የሚዘገንኑ ሰፈሮች ናቸው። ያንንስ ይዘን እስከመቼ እንዘልቃለን? ይህ ጥናት ደግሞ የህብረተሰቡን የተሻለ ኢኮኖሚያዊ አቅም መፍጠርን ታሳቢ ያደረገ ነው" ይላሉ። ዳዊት በአቶ ንጉሡ ሀሳብ ይስማማል። በአካባቢው አስር አባወራ በአንድ መፀዳጃ ብቻ ይገለገልበት የነበረበት ሁኔታ መኖሩን ጠቅሶ የነዋሪው ህይወት መሻሻል እንዳለበትም ያስረዳል። የእሱ ቅሬታ መፍረስ የሌለባቸው ቤቶች መፍረሳቸውና ነዋሪው መበተኑ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ቦታው ከፈረሰ በኋላ ምንም ሳይሰራበት መፀዳጃ መሆኑ ያሳዝነዋል። "የፈራረሰው ቤቴ ወደ መፀዳጃነት ተቀይሮ ሳየው በጣም ያሳፍረኛል" ይላል። መልሶ ማልማቱ ታሪካዊ ቤቶችን፣ ሀውልቶችንና ቅርስ ተብለው የተመዘገቡትን ከባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር ከግምት ውስጥ ቢያስገባም በአጠቃላይ ሰፈሮችን አሳቢ እንዳላደረገ ብዙዎች ይናገራሉ። "የደቀቁ ቤቶች አድሶ ሰፈሮቹን መጠበቅና ነዋሪዎቹን መመለስ አይቻልም ወይ? አዳዲስ ግንባታዎችን አሁን በሚመሰረቱት አዳዲስ ሰፈሮች ማካሄድ አይቻልም? የነበረው ታድሶ እንደ ህንድ የመሳሰሉ ሀገራት ለሁለት የድሮና አዲስ በሚል መከፋፈል ይቻል አልነበረም?" አቶ ንጉሡ ጥያቄው ተገቢ መሆኑን ቢያምኑም ከተማዋ በማስተር ፕላን እንደምትመራና የንግድ ማዕከላት፣ ትልልቅ ፎቆች፣ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን ተለይተው በዚሁም መሰረት ግንባታዎች እንደሚከናወኑ ይገልፃሉ። "ይህ ከተማ በአጠቃላይ ሲገነባ ነዋሪውን ሊያስወግድ በሚችል መልኩ አይደለም። አቅም ያለው እዚያው ላይ እንዲሰራ እድል ፈጥሯል። አቅም የሌለው ደግሞ መንግሥት ባስቀመጠው መሰረት" እንደሚስተናገድ ይናገራሉ። ጠቅላላ የልማት ተነሽውን መንግሥት ቤት ሰርቶ በዚያ ሰፈር ያኑር ቢባል የማያስኬድ እንደሆነም ይገልፃሉ። ከውቤ በረሃ በተጨማሪ ብዙ ታሪካዊ የሚባሉ ሰፈሮች የፈራረሱ ሲሆን በዚህ ዓመትም የመልሶ ማልማት ሥራዎች ይቀጥላሉ። በዚሀም መሰረት በአራዳ ክፍለ ከተማ ገዳም ሰፈርና አሜሪካን ግቢ ቁጥር ሁለት፣ ልደታ ጌጃ ሰፈር፣ ካዛንችስ ዕቅድ ውስጥ ገብተዋል። ይህም በአጠቃላይም 78 ሄክታር የሚሸፍን አካባቢ ነው።
news-55186208
https://www.bbc.com/amharic/news-55186208
ቴክኖሎጂ ፡ ከተኙ በኋላ ስልክዎን ሳይንቲስቶች እንዲጠቀሙበት ይፈቅዳሉ?
ሀና ላውሰን-ዌስት የምትኖረው ለንደን ነው።
ዘወትር ከመተኛቷ በፊት ፊቷን ትታጠባለች፣ ጥርሷን ትቦርሻለች። ከዚያም ስልኳ ላይ ዜና ትመለከታለች፣ የኢንስታግራም ገጿን ትጎበኛለች። መጨረሻ ላይ ስልኳ ቻርጅ እንዲያደርግ ሰክታ ትተኛለች። የ31 ዓመቷ ሀና ለስምንት ሰዓታት ስትተኛ ስልኳ ግን ይነቃል። ሳይንቲስቶች ባሉበት ሆነውም ይጠቀሙበታል። ሀና ስልኳ ከአጠገቧ ሳይርቅ ኮሮናቫይረስ ላይ ምርምር የሚሠሩ ሰዎች እንዲጠቀሙበት የሚያስችል አሠራር ተከታይ ናት። የዚህ አሠራር ተከታይ ከሆነች ዓመት ተቆጥሯል። ሳይንቲስቶች ስልኳን ተጠቅመው እስካሁን 2,500 የኮምፒውተር ስሌት ሠርተዋል። የዚህ አሠራር አመንጪ ‘ድሪምላብ’ መተግበሪያ ነው። ሰዎች ከተኙ በኋላ ሳይንቲስቶች ስልካቸውን የሚጠቀሙበት መንገድ ዘርግቷል። በመላው ዓለም 100,000 ሰዎች ስልካቸውን በፈቃደኝነት ለአገልግሎቱ ሰጥተዋል። መተግበሪያው ያተኮረው የኮሮናቫይረስ መድኃኒት ላይ ነው። ሰዎች ምን አይነት ንጥረ ነገር ያለው ምግብ ቢመገቡ ለኮቪድ-19 ሕክምና አጋዥ ይሆናል? የሚለው ላይ ጥናት እየሠሩ ነው። ጥናቱ በተለይም በሽታው ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይባቸው ሰዎች ላይ ያተኩራል። ምግብ ከበሽታው ስለመከላከሉ ወይም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መመገብ ስላለባቸው ነገር እስካሁን ተጨባጭ መረጃ አልተገኘም። እየተሠራ ያለውን ጥናት የሚመሩት የለንደኑ ኢምፔሪያል ኮሌጅ እና ቮዳፎን ፋውንዴሽን ናቸው። ‘ድሪምላብ’ ከተባለው መተግበሪያ በተጨማሪ ‘ኢቭኦንላየን’ እና ሌሎችም መተግበሪያዎች ለኮቪድ-19 ምርምር በጎ ፈቃደኞችን ያሰባስባሉ። ለሳይንቲስቶች ስልክ ‘ማዋስ’ ሂደቱ ‘ቮሉንተር ኮምፒውቲንግ’ ይባላል። የስልኮች አቅም አንድ ላይ ሲሰባሰብ የተከማቸ መረጃን በሦስት ወር ማስላት ይቻላል። ይህ ሥራ ለአንድ መደበኛ ኮምፒውተር 300 ቀን ይወስድበታል። ሀና መተግበሪያውን የጫነችው አባቷ የደም ካንሰር ሲገኝባቸው ነበር። መጀመሪያ የተሳተፈችበት ፕሮጀክት የካንሰር መድኃኒት ላይ ያተኮረ ነው። አሁን ደግሞ በኮቪድ-19 ፕሮጀክት ላይ ትሳተፋለች። “ተኝቼ ውጤታማ ነገር ማድረጌ ሁሌም ይደንቀኛል። ብዙ ሰዎች መሳተፍ አለባቸው” ትላለች። እንደ ሀና ባሉ በጎ ፍቃደኞች አማካይነት 53 ሚሊዮን ስሌቶች ማከናወን ተችሏል። ዓለም አቀፉ መተግበሪያ በደቡብ አፍሪካ፣ ጋና፣ ጀርመን፣ ግሪክ፣ ፖርቹጋል፣ ዩናይትድ ኪንግደምና ሌሎችም አገሮች ተጠቃሚዎች አሉት። ሌላዋ በጎ ፍቃደኛ አንጅሊካ አዝቬዶ የምትሮረው ሊዝበን ነው። “እናቴ በወረርሽኙ ወቅት በደም ካንሰር ሳቢያ ነው የሞተችው። ከሕክምና ጋር የተያያዙ ጥናቶችን ለመደገፍ የወሰንኩትም ለዚህ ነው። ለኮቪድ-19 መድኃኒት እንዲገኝ እንደማግዝ አምናለሁ” ትላለች። የ28 ዓመቷ አንጅሊካ ዘወትር ከእንቅልፏ ስትነሳ መጀመሪያ የምታደርገው ነበር መተግበሪያውን መመልከት ነው። እሷ ተኝታ ሳለ በስልኳ ምን ያህል የኮምፒውተር ስሌት እንደተሠራ ማየት ቀኗን ብሩህ እንደሚያደርገው ትናገራለች። ሳይንቲስቶች ምን ይላሉ? ፕ/ር ኪሪል ቨልስኮቭ የበጎ ፍቃደኖች ድጋፍ ኮቪድ-19 ላይ የሚደረገውን ምርምር እንዳፋጠነ ያስረዳሉ። “100,000 ተንቀሳቃሽ ስልኮች ከፈጣን ኮምፒውተሮች ሁለትና ሦስት እጥፍ የተሻሉ ናቸው” ይላሉ። በእያንዳንዱ ስልክ ላይ የሚሠሩት ስሌት የትኛው ንጥረ ነገር ያለው ምግብ ለኮሮናቫይረስ ታማሚ እንደሚረዳ ይፈትሻል። ጥናቱ ከ50 በላይ ሞለኪውሎች ኮቪድ-19ኝን የመከላከል አቅም እንዳላቸው የሚጠቁም ግኝት ላይ ደርሷል። ዶ/ር ሳይመን ክላርክ ተንቀሳቃሽ ስልክን በመጠቀም አጥኚዎች ምርምር ማካሄድ መቻላቸው ያስደንቃቸዋል። የበጎ ፍቃደኖችን ስልክ ሳይንቲስቶች የሚጠቀሙበት ሂደት እአአ በ1990ዎቹ ነው የተጀመረው። ሲጀመር ከ100,000 በላይ በጎ ፍቃደኞች ነበሩት። ያኔ የተካሄደው ምርምር ከምድር ውጪ ሕይወት ያላቸው አካሎች ይኖሩ እንደሆነ የሚፈትሽ ነበር። ከጥናቱ መስራቾች አንዱ ዶ/ር ዴቪድ አንደርሰን ፕሮጀክታቸውን ሌሎችም ሳይንቲስቶች እንዲጠቀሙበት ክፍት አድርገዋል። “አብዛኛው የኮምፒውተር ስሌት ያለው በፈጣን ኮምፒውተር ማዕከሎች ወይም በክላውድ ሳይሆን በሰዎች ቤት ነው” ይላሉ ተመራማሪው። ዴስክቶፕ፣ ስልክ፣ መኪናና ሌሎችም ቁሳቁሶች ከፍተኛ አቅም እንዳላቸው ያስረዳሉ። “በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ስልኮች፣ ዴስክቶፖች ወዘተ አሉ። እነዚህ ሳይንሳዊ ምርምርን ያፋጥናሉ” የሚሉት ዶ/ር ሳይመን በጎ ፍቃደኞችን ያመሰግናሉ።
53180024
https://www.bbc.com/amharic/53180024
የኢትዮጵያዊው የአምቡላንስ ሹፌር ትዝብት የኮሮናቫይረስ ሕሙማንና ሕክምና ላይ
ታሪኩ አትረጋ እባላለሁ። የአምቡላንስ ሹፌር ነኝ። የአምቡላንስ ሹፌር ከሆንኩ አጭር ጊዜው ነው። ገና ሦስት ወራት። ለሹፌርነት ግን አዲስ አይደለሁም። በምዕራብ ጎንደር ዞን የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ሹፌር ሆኜ አገልግያለሁ።
ለከተማው አዲስ አምቡላንስ ተሰጠ። አዲስ ሥራዬን በአዲስ መኪና ጀመረኩኝ። መጀመሪያ ወደ ሃገር የሚገቡ ሰዎችን ወደ ኳራንቲን ማዕከላት ማመላለስ ነበር ሥራዬ። ኢትዮጵያዊያኑ በተለያየ መንገድ ወደ ሃገር ውስጥ ይገባሉ። አድራሻቸው እና ሙቀታቸው ተለክቶ ወደ ለይቶ ማቆያ ይገባሉ። ኮኪት፣ ገንደ ውሃ ወይም ወደ ሌሎች የለይቶ ማቆያ ማዕከላት። እነዚህ ተጠርጣሪዎች ናቸው። አምቡላንስ ቢሆንም የማሽከረክረው አንድ ላይ የመጡትን እስከ ስድስት ሰባት ሰው ነው የምጭነው። ወደ ለይቶ ማቆያ የምወስዳቸው በተለያየ ቡድን በመክፈል ነው። ከተለያየ ቦታ የመጡትን ለየብቻ እንለያቸዋለን። ከበረሃ የመጡትን ለብቻ። ከካርቱም የመጡት ለብቻ. . . ንክኪ ይኖራል በሚል የተደረገ ነው። ለሁለት ሳምንት በለይቶ ማቆያ ከቆዩ በኋላ ናሙና ይወሰድላቸውና ይመረመራሉ። • «የሕዳሴው ግድብ ለግብፅና ሱዳንም ይጠቅማል» ጥቁር አሜሪካውያን ፖለቲከኞች • ኮቪድ-19 ያስተጓጎለው የኢትዮጵያ የካንሰር ህክምና • "ልባችንም ቤታችንም ጨልሟል" የጀነራል ሰዓረ እና ሜ/ጀነራል ገዛኢ ቤተሰቦች ከዚያ በኋላ ነው ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ወደ ህክምና ማዕከል ማመላለስ የጀመርኩት። ብዙ ጊዜ ኮሮና እንዳለባቸው የተረጋገጠባቸውን ሰዎች አመላልሻለሁ። በቁጥር ብዙ ነው። ባህር ዳር 2 ጊዜ ወስጃለሁ። ጎንደር ደግሞ ወደ 12 ወይም 13 ጊዜ ወስጃለሁ። ከሳምንታት በፊት ዞኑ የተቀበላቸውን አዳዲስ አምቡላንሶች በመጨመር 4 ወይም 5 አምቡላንስ ተመድቦ ነበር ይዘን የምንሄደው። ከመተማ ጎንደር 190 ኪሜ ይርቃል። ከጎንደር ባህር ዳር ደግሞ 180 ኪሜ ነው። ስለዚህ ከመተማ ባህር ዳር 370 ኪሜ ይርቃል ማለት ነው። ኮቪድ-19 ባለሙያዎች አንኳን ገና ተጠንቶ ያላለቀ የሚሉት ቫይረስ ነው። ህብረተሰቡም መጀመሪያ ላይ ወዲያው ይገላል የሚል እምነት ነበረው። በዚህ ወቅት ነው በአካባቢው ሁለት ሰዎች ቫይረሱ እንዳለባቸው የታወቀው። ምልክት አልነበረባቸውም። አንዱ ሱዳን በረሃ የዕለት ሠራተኛ ሌላው ደግሞ የካርቱም ነዋሪ። እነዚህን ነው ከጤና ባለሙያ እና ከጸጥታ ሃይል ጋር በመሆን ወደ ጤና ተቋማት መጀመሪያ የወሰድኳቸው እኔ ነኝ። ከካርቱም የመጣው ግለሰብ '[ቫይረሱ] ቢኖርብኝም ማገገም እችላለሁ። ግን የለብኝም። ምንም ዓይነት ምልከት ሳይኖረኝ እንዴት አለብህ ትሉኛላችሁ? ይሄ ስህተት ነው። ወደ ቤተሰቦቼ እንዳልሄድ እያደረገቻሁኝ ነው' በሚል ቅሬታ አሰምቷል። ወደ አምቡላንሱ እንዲገባም የጤና ባለሙያ ምክር አስፈለጎ ነበር። ጥንቃቄን በተመለከተ አምቡላንሶቹ ከኋላ ሙሉ ዝግ ናቸው። አቀማመጣቸውም የተወሰነ [ከእኛ] ርቀት አለው። ቫይረሱ አለባችሁ ሲባሉ የሚረብሹ ስላሉ። የግንዛቤ ማስጨበጫ እንሰጣቸዋለን። [ቫይረሱ] አለባችሁ ሲባሉ 'የለብንም ስህተት ነው። ውሸት ነው' ብለው የሚረብሹ፤ መስኮት ለመክፈትም ሆነ ለመስበርም የሚታገል አለ። 'አልሄድም' ብሎ የሚገላገልም አለ። • ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ? • ኢትዮጵያ መሰረታቸውን ግብጽ ባደረጉ ቡድኖች የመረጃ መረብ ጥቃት ተሞከረብኝ አለች • በአፍሪካ የመጀመሪያው የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ ሊደረግ ነው እኛ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል እና የእጅ ጓንት እንጠቀማለን። ባህር ዳር የሚገኘው የህክምና ማዕከል ስንደርስ ጸረ-ተዋሲያን ርጭት ያደርጋሉ። ጎንደር ላይ ግን ለማድረግ ራሱ ዝግጁ ሆነው አይጠብቁም። ባህር ዳር ይዤ ስሄድ በአግባቡ መድኃኒት ይረጫል። እኔ ራሱ መሬት ላይ አልወርድም። ጎንደር ግን 'ተቀበሉን አንቀበልም' በሚል አንደ ሰዓትም ብዙ ጊዜ 30 ደቂቃ እቆማለሁ። ሕሙማንና የተለየየ ባህሪያቸው አንዳንዴ ኬዝ [ቫይረሱ ያለበት ሰው] ጭነን ስንቆም 'በግድ ነው ያመጣችሁን። እነሱ ራሱ አንፈልጋችሁም እያሉን ነው ይሄን ያህል ያቆሙን። የት ነው የምትወስዱን?' እያሉ ብዙ ጊዜ እንደዚህ ዓይነት አሰጣ አገባዎች አሉ። የመተማ ልጅ ስለሆንኩ የአካባቢውን ህብረተሰብ ባህሪ ስለምረዳ ሳናግራቸው ይረዳሉ። ቁጣ ምናምን ከቀላቀልክ አይሆንም። በኋላ በኋላ ከኳራንቲን ቫይረሱ አለባችሁ ተብለው ወደ ህክምና ማዕከላት የሚሄዱ ሰዎች [የሚሄዱበትን ማዕከል] ማማረጥ ጀመሩ። በህክምና ማዕከላት እና በለይቶ ማቆያ ያሉት ስልክ ተደዋውለው መረጃ ይለዋወጣሉ። [ባህር ዳር የተሻለ ነው ስለሚሏቸው] ቫይረሱ ተገኘባችሁ ሲባሉ 'ባህር ዳር ከሆነ ውሰዱን ጎንደር ግን አንሄድም' የሚል ባህሪ እያመጡ ነው። የመጀመሪያ ሁለት ኬዝ ይዤ ስሄድ አንዱ የሲጋራ ሱስ አለበት። ለካ ሲጋራ ይዞ ነበር። ልክ ጎንደር እንደገባን 'ሲጋራ ልለኩስ ነው' አለ። ሲገባ ፍተሻ ስላልተደረገበት ሲጋራ ይዟል። 'ልለኩስ?' ሲል ለሁላችንም መጥፎ ነው እንዳትለኩስ አልነው። ቆይቶ 'እሺ በቃ ሽንቴን ልሸና ነው በቃ አውርዱኝ' አለ። በወቅቱ ቫይረሱ አዲስ እና በእኛም አይታወቅም ነበር። አንዴ ጉዞ ከጀመራችሁ በኋላ ባህር ዳር ነው የምትቆሙት ተብለናል። መንገድ ላይ ማውረድ አንችልም ማለት ነው። እንደተባለው አደረግን። ባህር ዳር ማታ አካባቢ ነበር የገባነው። ወደ 4 ሰዓት ገደማ ነበር የገባነው። ልክ ከተማ ከገባን በኋላ 'አልቻልኩም ከፈለጋችሁ አውርዳችሁ ግደሉኝ እንጂ' ብሎ ሲጋራውን አውጥቶ ለኮሰ። አብሮኝ ጋቢና ያለው የህክምና ባለሙያ ነው። የጸጥታ አባሉ በሌላ መኪና ነበር። አይዞህ እያልን እያበረታታን ሲጋራውን አስጥለን ወደ ህክምና ማዕከል አስገባነው። አንድ ጊዜ ደግሞ ስምንት ኬዝ ተገኘ። ለህክምና ጎንደር ነበር የሚሄዱት። • ከሰኔ 16ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ? • "የቻይናና የአሜሪካ ቀዝቃዛው ጦርነት ከኮሮናቫይረስ በላይ ለዓለም ያሰጋል" • "ልባችንም ቤታችንም ጨልሟል" የጀነራል ሰዓረ እና ሜ/ጀነራል ገዛኢ ቤተሰቦች ከህክምና ማዕከሎች ጋር መተዋወቅ ሲመጣ እየደወሉ አምጣ ሲሉኝ በቀጥታ ይዤ እሄዳለሁ። በወቅቱ ከሱዳን ወደ ሃገር ውስጥ በጫካ በኩል አዲስ የሚመጡትን በቁጥጥር ሥር ለማዋል እና የሙቀት ልኬታ ስላለ የጸጥታ መዋቅሩም ሥራ በዝቶበት ነበር። ስምንቱን ይዤ እንድሄድ የጸጥታ አካል አብሮኝ መሳፈር ያስፈልግ ነበር። ከጤና ባለሙያ ወደ ህክምና ማዕከል የማስገባበት ወረቀት ተሰጥቶኛል። የቀረው የጸጥታ መዋቅር አባሉ ከእኔ ጋር ጋቢና ሆኖ ማድረስ ነው። ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች አምቡላንሱ ውስጥ ጫንኩኝ። አባሉ ወጥቻለሁ ቢለንም ስንጠብቀው የለም። ዝም ብዬ ነዳሁት። ግማሽ መንገድ ከደረስን በኋላ 'ሽንታችን ስለመጣ አውርደን' አሉ። 'እንዴት አደርጋለሁ?' የሚል ጭንቀት ያዘኝ። 'ችግር የለም ግን ከተማ ላይ ማቆም አይቻልም። ጫካም ለእናንተ [ደህንነት] ጥሩ ስላልሆነ ከተማ ላይ አንድ የጤና ማዕከል ገብተን ሸንታችሁ ተጣጥባችሁ ትሄዳላችሁ' አልኳቸው። አሁን አሁን እያልኩ እያዋራሁ እያሳሳቅኩኝ ጎንደር ከተማ ገባን። መንገድ ላይ እንደፈለጉ መሆን ይፈልጋሉ፤ ሲጋራ ማጨስ ሽንታቸውን በተለያየ ሰዓት መሽናት ይፈልጋሉ። ከዚያ ውጭ ብዙም ችግር የለባቸውም። አብዛኛዎቹ በሚዲያ የሚተላለፈውን ይሰማሉ። 'ለምን አንድ በአንድ አትወስዱንም?' ሲሉ ይጠይቃሉ። 'መቼም በሃገሪቱ ሁኔታ ለስምንት ሰው ስምንት አምቡላንስ አይመደብም' እንላቸዋለን። 'አንድ ላይ የተገኛችሁ ስለሆናችሁ አንድ ላይ ትሄዳላችሁ። አንድ ሰው ከተገኘበት ለብቻው ነው የሚሄደው ነው' የምላቸው። [ለይቶ ማቆያ ያሉት] ተደጋጋሚ ጊዜ ቫይረሱ ያለባቸውን እንደማመላልስ ሰለሚያውቁ ናሙና ሰጥተው ቫይረሱ ተገኝቶባቸው ወደ ህክምና ማዕከል ለመውሰድ ስጭናቸው 'ታሬ ታሬ የት ነው የምትወስደን? ባህር ዳር ነው ጎንደር?' ይሉኛል። "እናንተ እንደምርጫችሁ ባህር ዳር ያለ ባህር ዳር፤ ጎንደር ያለ ጎንደር እላለሁ።" ምክንያቱም እንዲህ ካልካቸው ነው ተስማምተህ ልትነዳ የምትችለው። እንዲህ ካላልካቸው አትስማማም። እኛ ጎንደር እና ባህር ዳር የህክምና ማዕከላት ይዘን እንሄድ ስለነበር ሁሌም ያጠናሉ። 'የተሻለ ምግብ የሚያቀርቡልን የት ነው ጎንደር ነው ወይስ ባህር ዳር ነው?' ይላሉ። የምትፈልጉት ማዕከል አስገባችኋለሁ እላለሁ። ያው እኔ የጤና ባለሙያው በሚለኝ ነው የምሄደው። ጎንደር ካለኝ ጎንደር እሄዳለሁ። ግን የምትፈልጉት ቦታ እወስዳችኋለሁ ስላቸው 'ባህር ዳር፣ ባህር ዳር' ይሉኛል። ኮቪድ-19 እና የሕሙማን ግንዛቤ በኮቪድ ጉዳይ ጥቂቶች ናቸው በሽታው ስለመኖሩን የሚያውቁት። ከዚያ ውጭ ግን እንደ አሜሪካ፣ ቻይና፣ ብራዚል፣ ስፔን እና ጣሊያን ሞት ካላየ የማያምን ህብረተሰብ ነው ያለው እኛ አካባቢ። እኛ አካባቢ ውሸት ነው የተባለበት ጊዜም አለ። ምክንያቱም 'አላሳለኝ፣ ሙቀት አልተሰማኝ፣ ሙቀቴ አልጨመረ። ጤነኛ ሰው ነኝ። እንዴት አለብህ ትሉኛላችሁ?' ይላሉ። ብዙዎች አለባችሁ የሚባሉትም አልተዋጠላቸውም። በትክክል ተገኝቶብኛል ብሎ ራሱን ያሳመነ አካል የለም። ቫይረሱ ያለባቸውን እና ተጠርጣሪዎችን ሳመላልስ ሙሉ ከተማው ይጠቋቆምብኝ ነበር። ምክንያቱም ኮኪትም ገንደ ውሃ [ከተሞች] ላይ ሳልፍ በጣም እሯሯጥ ነበር። 'ኮቪድ የሚያመላለስው ማነው?' ሲባል 'የመተማው ሹፌር- የመተማው ሹፌር ታሪኩ የሚባል ነው' ይላሉ። እኔ ራሱ ቫይረሱ ያለባቸውን ባህር ዳር ወስጄ ስመለስ ሌላ ቦታ ወርጄ ሻይ መጠጣት ተሳቀቅኩኝ። ሻይ መጠጣት እፈልጋለሁ ግን ተሳቀቅኩኝ። ማህበረሰቡ 'ከኮቪድ ጋር በተያያዘ የሚሠራ ሰው ራሱን አግልሎ ማግለያ ውስጥ መቀመጥ አለበት ነው' የሚለው። • ኮሮናቫይረስ በአሜሪካ በአስደንጋጭ ሁኔታ ሊያንሰራራ ይችላል ተብሎ ተሰግቷል እኔ ሹፌር ሆኜ ከኮቪድ ጋር በተያያዘ ስሠራ ጀምሮ ከቤተሰብ ጋር ከሚስቴ ጋር መቀላቀል የለበኝም። ተመቻችቶ ለብቻዬ ኳራንቲን ሆኜ ከማህበረሰቡ፣ ከእናቴ እና ከባለቤቴ ጋር መቀላቀል አልነበረብኝም። አድርሼ ስመለስ ጓደኞቼ አትቀላቀልም በሚል ከአንገት በላይ ነበር ሠላም የሚሉኝ። አሁን ግን ለውጥ አለው። 'ችግር የለም ሰላም በለን' የሚልም አለ። አሁን ተለምዷል። መጀመሪያ ግን 'መተማ ላይ [ቫይረሱ] ከገባ እሱ ነው የሚያስገባብን' በሚል እኔ ላይ ያነጣጠረ ጥሩ ያልሆነ ሁኔታ ነው የነበረው። ከጊዜ ወደ ጊዜ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ስለጨመረ ከአምቡላንስ አቅም በላይ ሆነ። ጎንደር ዩኒቨርሰቲ አውቶብስ ስለሰጠን እሱን እየተጠቀምን ነው። አንዴ ኬዝ ሲመጣ ከ20 በላይ ስለሚሆን አምቡላንስ ስለማይበቃ ዩኒቨርሲቲው በሰጠን አውቶብስ እየተመላላሱ ነው። አሁን ከጸጥታ እና ህክምና ባለሙያዎች ጋር በመሆን በጫካ በኩል ወደ ማህበረሰቡ የገቡ ስለሚኖሩ እነሱን እየሄድኩ ከጸጥታ መዋቅር ጋር ወደ ገንደ ውሃ እና መተማ ኳራንቲን ነው የማስገባው። ቫይረሱ ያለባቸውን ወደ ህክምና ማዕከል አላመላልስም። በመተማ ድንበር የሚመጡ የበረሃ ሠራተኞች የተለያየ የሱስ ሁኔታዎች ያለባቸው አሉ። ሲጋራ፣ ሺሻም ጫትም ሱስ ያለባቸው አሉ። ለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ ሁሉን ያጣሉ። ለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ 'የምንበላው አይመቸንም' በማለት የሚጠፉ አሉ። ለይቶ ማቆያ ከገቡ በኋላ ሁለት ሳምንት ሞልቷቸውም 12 ወይም 13 ቀን የቆየ ሌላ ሰው ናሙናው ሲወሰድ እኛ 14 ቀን ሞልቶን ለምን አይወሰድልንም በሚል 14 ወይም 15 ቀን ሞልቷቸዋው ለሊት ላይ ከፀጥታ መዋቅሩ በመሸሸግ ከተለያዩ ማዕከላት ያመልጣሉ። በህዝብ ክትትል እና ጥቆማ ይያዛሉ። መጀመሪያ ከቢቢሲ ሲደወልልኝ '14 ቀን ሞልቶኛል። ናሙና መወሰድ ነበረበት። ካልተወሰደ ለምን እቀመጣለሁ?' በማለት ወደ መንደር 7 ከተማ የጠፋ ግለሰብ ለመያዝ እያቀናሁ ነበር። እንደጠፋ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ መንደር ሰባት ላይ ተያዘ። ከቦታው ድረስ ሄጄ አምጥተነው ናሙና እንዲሰጥ አድርገናል። እስካሁን ባለው ሁኔታ ምንም ዓይነት ስሜት የለኝም። መሥራት ከጀመርኩ ራሴንም አሞኝ አያውቅም። ሙሉ ጤነኛ ነኝ። ግን ስጋት ነበረኝ። ቫይረሱ ያለባቸውን ሰዎች ሳይ ምንም ምልክት የለባቸውም። በወቅቱ ሳመላልሳቸው ንጹህ ሰዎች ናቸው። አንዱን አውርጄ ሌላ ለመጫን መኪናውን ጸረ-ተዋህሲያን የሚረጨው ጠፍቶ ለመርጨት የምገደደበት ጊዜ አለ። ሥራው የህሊና ሥራ ስለሆነ ራሴ በጸረ-ተህዋሲያን መኪናውን አጸዳለሁ። አጣዳፊ ሲሆን የእጅ ጓንትም ሲያልቀብኝ አልኮል ያለው ማጽጃ (ሳንታይዘር) እጄን ረጭቼ በር እከፍት ነበር። ራሴን እጠራጠር ነበር። ከሳምንት በፊት ተመረመርኩኝ። ነጻ ሆኜ ተገኘሁ። ከዚህ በኋላ ግን በደንብ እንደምጠነቀቅ ነው የተማርኩበት። ኢትዮጵያ ውስጥ ኮቪድ አስጊ ከሆነባቸው ቦታዎች አንዱ ምዕራብ ጎንደር ነው። ከሱዳኖች ጋር ፊት ለፊት እየተያየን እየተጨባበጥን ነው የምንኖረው። የ10 ሜትር ልዩነት ናት። ዋናው ቦታ ደግሞ መተማ ዮሃንስ ላይ ነው። ኬላውን ሲከፍቱ ምናምን እንተያያለን። እንደሃገር ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ አይደለም። ብዙ በሮች እና ፍሰት ያለበት ቦታ ነው። የሱዳን ኬዝ ሲጨምር ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ፍልሰት ይጨመራል። በረሃ ውስጥ ከሚሠሩት በተጨማሪ ከተማ ላይ የሚኖሩም እየመጡ ነው። መንግስት ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት። ባለው የበጀት ምክንያት ጸረ-ተዋህሲያን በአግባቡ አያመጡልንም። የእጅ ጓንት እና የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አይመጣልንም። በነበረው ነው የምንጠቀመው። ከኮሮና ኬዝ በኋላ የገባልን ነገር የለም። ኮታው እየጨመረ ነው። ግን የደረሰ ነገር የለም። የጸጥታ መዋቅሩም ንክኪ አለው ማለት ይቻላል። እየተጋለጠ ነው። [ተጠርጣሪዎችም ሆኑ ቫይረሱ ያለባቸው] አንሄድም ሲሉ ገፍተው ያስገቧቸዋል። ለምርመራ ጎንደር እና ባህር ዳር መኬድ የለበትም። ለምን ገንደ ውሃ አይሆንም። በሽታው እንደ ሃገር እየተስፋፋ ነው። እየተከላከለን አይደለም። ብቻ ያስቡበት።
news-47702785
https://www.bbc.com/amharic/news-47702785
የአሜሪካው ኩባንያ በኬንያ ካናቢስ ለማብቀል ፍቃድ አገኘ ተባለ
አንድ የአሜሪካ ኩባንያ በኬንያ እጸፋርስ (ማሪዋና) አብቅዬ ለመሸጥ ፍቃድ አግኝቻለሁ አለ። "ማሪዋና ሕገወጥ በሆነባት ኬንያ ይህ እንዴት ሊሆን እንደሚችል እያነጋገረ ነው" ሲል ቢዝነስ ዴይሊ የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል።
ይህ እርምጃ ኩባንያችንን ወደላቀ ደረጃ የሚወስድና በየዕለቱ እያበበ ያለውን የካናቢስ (እጸፋርስ) ቢዝነስ የሚያሳድግ ነው ብሏል ኩባንያው። የዚህ ኩባንያ የዓለም አቀፍ ንግድ ተጠሪ ሚስተር ሱቶን የኬንያ ባለሥልጣናትን አግኝተን በጉዳዩ ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውንም ጨምረው ገልጸዋል። • "ጫትን ማገድ ፈፅሞ የሚቻል አይደለም" ዶ/ር ዘሪሁን መሃመድ • የሰሞኑ የአዲስ አበባ እስርና ሕጋዊ ጥያቄዎች የኬንያ ባለሥልጣናት ግን በጭራሽ በዚህ ጉዳይ ላይ የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል። የኩባንያው ተጠሪ እንደሚሉት የሊዝ ስምምነቱ ለ25 ዓመታት የሚጸና ሲሆን ኬንያ በምድር ወገብ አካባቢ በመገኘቷ የአየር ሁኔታዋ ካናቢስ ለማብቀል እጅግ ምቹ ነው፤ ዓመቱን ሙሉ ምርት ይኖራል ብለዋል። በአንዳንድ አሜሪካ ግዛቶችና በአውሮፓ ካናቢስን ሕጋዊ የማድረግ ሁኔታ የታየ ቢሆንም በአፍሪካ አገሮች ግን ይህ ሂደት አዝጋሚ ነው። ደቡብ አፍሪካ ሕጓን በተወሰነ ደረጃ ያላላች ሲሆን ካናቢስን አዋቂዎች ገለል ባሉ ቦታዎች ቢጠቀሙ ችግር የለውም በሚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።
news-54022841
https://www.bbc.com/amharic/news-54022841
"ልደቱ እዚሁ ጣቢያ ነው መታሰር ያለብኝ ብሎ ለምኖ ነው [ቢሾፍቱ] የቀረው"፡ የኢዴፓ ፕሬዝደንት አቶ አዳነ ታደሰ
የሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቢሾፍቱ ከተማ የተፈጠረውን ሁከት በማነሳሳት፣ መምራትና በገንዘብ መደገፍ ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ልደቱ አያሌው "ህገ መንግሥታዊ ስርአቱን በኃይል ለመናድ" ሞክረዋል በሚል አዲስ ውንጀላ እንደቀረባባቸው ጠበቃቸው አቶ አብዱልጀባር ሁሴን ገመዳ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) የብሔራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው የዋስትና መብታቸውን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ በትናንትናው ዕለት ውሳኔ ለማስተላለፍ በዋለው ችሎት ላይ ነው አቃቤ ህግና ፖሊስ አዲስ ክስ ያቀረቡባቸው። የቢሾፍቱ ወረዳ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌው በተጠረጠሩበት ወንጀል ፖሊስ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የፖሊስን ጥያቄ የህግ አግባብነት እንደሌለው ጠቅሶ ሳይቀበለው የቀረው ነሐሴ 25፣ 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት ነበር። ፖሊስ አልለቅም የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው እንደገና ማመልከቻ ያስገቡ የሚል ጥያቄም አንስቷል። ፍርድ ቤቱም የፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ዘግቶ አቶ ልደቱ በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲቀርብ ውሳኔ አስተላልፎ ነበር። በትናንትናው ዕለት በዋለውም ችሎት የዋስትና ጥያቄ መልስ ለመስጠት ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም አቃቤ ህግና ፖሊስ በግድያ ከመጠርጠር በተጨማሪ "ህገ መንግሥታዊ ስርአቱን በኃይል የመናድ" ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ የሚሉ ውንጀላዎች ቀርበዋል። ለዚህም መሰረት የሆነው የሽግግር መንግሥትን ምስረታን ለመንግሥት እንደ አማራጭነት ያቀረቡት ሰነድ ሲሆን ይህም ጠበቃው እንደሚሉት ጥር ወር ገደማ የተፃፈ ሲሆን ሁከቱ ግን ከአርቲስቱ ሞት በኋላ የተከሰተ ነው። በተጨማሪም አቶ ልደቱ እየፃፉት ነው የተባለውና ቤታቸው ውስጥ የተገኘው የመፅሃፍ ረቂቅ በአባሪነት የቀረበ ሲሆን በይዘቱ "ለውጡን የሚተችና ህገ መንግሥቱን ለመናድ ዝግጅት" የሚሉ አዳዲስ ውንጀላዎች ቀርበውባቸዋል ብለዋል። "እነዚህ ምክንያቶች አቃቤ ህግ ዋስትና ለማስከልከል ያቀረባቸው ናቸው። የምርመራ መዝገቡን መሰረት ያደረጉ አይደሉም" የሚል ክርክር ማቅረባቸውንም ያስረዳሉ። ከዚህም በተጨማሪ አቶ ልደቱ ገና በረቂቅ እንዳለና ለህዝብ ይፋ ያልሆነ ያልታተመ መፅሃፍ እንደሆነም ነግረዋቸዋል። "ይሄ እንግዲህ በሃሳብ ደረጃ ያለ ስለሆነ፤ ማንኛውም ግለሰብ በሃሳቡ አይቀጣም። ሃሳብ ወንጀል አይደለም። እንዳያስብ ሁሉ ሊከለከል ነው ማለት ነው የሚል ነገር ነው አቶ ልደቱም ያነሱት" ብለዋል ጠበቃቸው በበኩላቸው ዋስትና በኢትዮጵያ ህገ መንግሥትም ሆነ ኢትዮጵያ ካፀደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች መስረት መብት እንደሆነ ጠቅሰው ዋስትና የሚከለከልበት በአንዳንድ አጋጣሚ እንደሆነ ጠቅሰው ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። ከዚህም በተጨማሪ ደንበኛቸው የተጠረጠሩበት ወንጀል ግድያ የሌለበትና ከአስራ አምስት አመት በላይም ሊያስቀጣ ስለማይችል የዋስትና መብታቸው እንዲከበር መከራከሪያ ሃሳብ እንዳቀረቡም ለቢቢሲ ገልጸዋል። ፍርድ ቤቱ በጥዋት ቀጠሮው አቃቤ ህግና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ያቀረቡትን ውንጀላ የሚያስረዳ የምርመራ መዝገብ ማምጣት የሚለውን ጉዳይ ውሳኔ ለመስጠትም ከሰዓት ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። ትናንት ከሰዓት በዋለው ችሎትም አቃቤ ህግና ፖሊሶች የፖሊስ ምርመራ መዝገብ ማምጣት አንችልም በሚልም ብዙ እንዳንገራገሩ የገለፁት ጠበቃው የፖሊስ የምርመራ መዝገብ ለዞን አቃቤ ህግ ተልኳል በማለት ምክንያት ሰጥተዋል። ግራ ቀኙን ያየው ፍርድ ቤቱ የምርመራ መዝገቡን ማምጣት አለባችሁ የሚል ውሳኔን አስተላልፏል። ፍርድ ቤቱ፣ ፖሊስ የምርመራ መዝገብና ማስረጃውን እንዲያቀርብ በማዘዝ ለዛሬ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ የሰጠ ሲሆን የምርመራ መዝገቡ ክስ ለመመስረት በቂ ነው ወይስ አይደለም የሚለውንም ሁኔታ የሚወስን እንደሆነ ጠበቃቸው ጠቁመዋል። በዛሬው ዕለት አካልን ነፃ የማውጣት ክስን ለመመስረት ከደንበኛቸው ጋር መነጋገራቸውንም በተጨማሪ አስረድተዋል። ዋስትናን በሚመለከት ደግሞ በዛሬው እለት ፍርድ ቤቱ ውሳኔን እንደሚሰጥ ተናግረዋል። "የዋስትና መብት ይከበር በሚል እኛ የምንከራከረው የነፃነትን መብት ለማስጠበቅ ነው" የሚሉት ጠበቃው አቶ ልደቱ፣ ከዚያም ባለፈ በህይወት የመቆየት ሁኔታቸውን ሊፈታተን የሚችል የሃኪም ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ ቀርቧል። ከዚህ ቀደም የልብ ቀዶ ህክምና አድርገው አርቲፊሻል ነገር ልባቸው ላይ እንዳለ ሐምሌ 30፣ 2012 ዓ.ም አሜሪካን ሃገር የምርመራ ቀጠሮ ቢኖራቸውም እሱንም መሄድ እንዳልቻሉ በተደጋጋሚ በቀጠሮዎቹ ሲጠቀስ እንደነበርም አቶ አብዱልጀባር ያስረዳሉ ። ከዚህም በተጨማሪ ደንበኛቸው የአስም ህመምተኛ ሲሆኑ ከልብ ህመማቸው ጋር ተያይዞ ለኮቪድ-19 ተጋላጭነታቸው በጣም ከፍተኛ እንደሚያደርገውና በአዲስ አበባ የሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል የተያያዘው የሃኪም ማስረጃንም ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል። "በሕይወት የመኖር መብትና በነፃነት መካከል የመብት መበላለጥ ባይኖርም ሰው በህይወት ሲኖር ነው የነፃነት መብቱ የሚጠይቀው የእርሳቸው ትንሽ አስከፊ የሚያደርገው በህመም ላይ መሆናቸው ነው" ብለዋል አቶ አብዱልጀባር። አቶ ልደቱ በመጀመሪያ የተጠረጠሩበት ወንጀል በቢሾፍቱ ከተማ ሁከት በማስነሳት መምራትና በገንዘብ መደገፍ የሚል ነበር። በጊዜ ቀጠሮ በቆዩባቸው ወቅት ቤታቸው ሲበረበር በተገኙት ፅሁፎችና ሰነዶች የምርመራ ሂደቱ መልኩን ቀይሮ ወደ ሌላ ሁኔታ እያጋደለ የመጣበት ሁኔታ እንደነበር ይጠቅሳሉ። "ህገ መንግሥታዊውን ስርዓት በኃይል የመናድ፣" አንቀፅ 238ን በመጥቀስ አቶ ልደቱ በተለያዩ ሚዲያዎች ላይ ለዚች አገር የሽግግር መንግሥት ነው የሚበጃትና ሌሎች አማራጮችን ሲናገሩ ከነበሩት አንዳንድ ነገሮች ተገኝተዋል በሚል መልኩንም የቀየረው ቀድሞም እንደነበር ነው ጠበቃቸው ገልጸዋል። በ25/12/12 ዓ.ም የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ ሲዘጋ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቄያለሁ ብሎ እንደነበርና ሁለተኛ ደግሞ የምርመራ መዝገቡ ውስጥ ከዚህ በፊት መርማሪ ፖሊሶች ሶስት ምስክር ተሰምተው ነበር። በኋላ ላይ ግን ፍርድ ቤት ሲያጣራ ግን በቢሾፍቱ አቶ ልደቱ ብጥብጥ አስነስተዋል፣ መርተዋል፣ ገንዘብ ደግፈዋል በሚል በቀረበባቸው ክስ ሶስት ምስክር የተባሉት የአቶ ልደቱ ቤት ሲበረበር በምርመራ እንዲገኙ በታዛቢነት የቆሙ ግለሰቦች መሆናቸውን ደርሶበታል ይላሉ። በአጠቃላይ "እሳቸውን አስሮ ምርመራ ማድረግ ሳይሆን እንዲያውም ወንጀል የማፈላለግ ሁኔታ ነው ሲደረግ የነበረው" ይላሉ። ፓርቲያቸው ምን ይላል? የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዘዳንት አቶ አዳነ ታደሰ፤ "አሁን ባለው ሂደት መፍትሔ ማግኘት እንደማይቻል ተማምነን አካልን ነጻ የማውጣት ክስ ለመመስረት ወስነናል" ብለዋል። ፖሊስ አቶ ልደቱ ከቢሾፍቱ ወደ አዳማ ማረሚያ ቤት መሄድ አለባቸው ብሎ እንደነበረ ገልጸውም፤ "ልደቱ እዚሁ ጣቢያ ነው መታሰር ያለብኝ ብሎ ለምኖ ነው [ቢሾፍቱ] የቀረው" ሲሉ አስረድተዋል። አቶ አዳነ የዛሬው ፍርድ ቤት ውሎ የተቋጨው "በአሳዛኝ ሁኔታ" ነው ብለው፤ "አስፈጻሚው ከሕግ አውጪው በላይ ጡንቻ አለው ብለን ስለምናምን ሰኞ አዲስ አበባ ላይ አካልን ነጻ የማውጣት ክስ እንመሰርታለን" ሲሉ ውሳኔያቸውን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
55745364
https://www.bbc.com/amharic/55745364
"ማንኪያ ሳይቀር ነው የዘረፉኝ" በመቀለ የሚገኙ ተፈናቃይ
"ልጆቼንና ባለቤቴን ይዠ የ80 አመት ሽማግሌ አባቴን ለብቻው ጥዬ ነው የመጣሁት፤ ያየሁትን ነገር ለመናገር አቅም የለኝም። ከባድ መሳሪያ ከላያችን ላይ እየተተኮሰብን ነፍሰ ጡር ሴቶች በየመንገዱ እየወለዱ አንዱን አንስተን አንዱን ጥለን ነው መቀለ የደረስነው" በማለት በመቀለ በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የምትገኘው ፈረይ በሳግና በለቅሶ በተቆራረጠ ድምፅ ትናገራለች።
ፈረይ በትግራይ ክልል የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ነፍሳቸውን ለማትረፍ ከሸሹት መካከል አንዷ ናት። ፈረይ ጦርነቱን ሸሽታ ከሽረ ከተማ ወደ መቀለ ገብታለች። በመቀለ ከተማ ውስጥ ባሉና በጊዜያዊነት በተለያዩ የትግራይ ክፍሎች ተፈናቅለው ለመጡ በመጠለያነት በተቀየሩት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በአንዱ ትገኛለች። ተፈናቃዮቹ ያሉበትን ችግር ለመናገር እንባ የሚተናነቃት ፈረይ "እዚህም የሚበሉትን ያጡ አራስ እናቶች አሉ ሁሉም ችግር ነው" በማለት ለቢቢሲ በስልክ ተናግራለች። ከምግብ እጥረት በተጨማሪ የልብስና የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እጥረት በመጠለያው ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን ህይወት አክብዶታል። ይህንን ችግር የተረዱ የመቀለ ነዋሪዎችም የሴቶች ንፅህና መጠበቂያና አንሶላ ቢለግሷቸውም ለሁሉም መከፋፈል አልቻለም። "የሚቀይሩት ልብስና የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ አጥተው ከቤት የማይወጡ ወጣት ሴቶችና እናቶች አሉ። እኛም ልብስም ሆነ ጫማ የለንም ብዙ የሚጎድለን አለ" ትላለች በኃዘን በተሰበረ ድምጿ ይህ የፈረይ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በርካታ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎች እያለፉበት ያለ መከራ ነው። ከሽራሮ ከተማ ተፈናቅለው በመቀለ ትምህርት ቤት ውስጥ ተጠልለው የሚገኙት አቶ ተስፋይም ሲፈናቀሉ የመጀመሪያቸው አይደለም፤ ለሁለተኛ ጊዜም ተጎጅ ናቸው። ከሁለት አመት በፊት ከጎንደር ተፈናቅለው ከመጡ በኋላ ያላቸውንም ገንዘብ ሰብስበው በ500 ሺህ ብር ባድመ ከተማ ላይ የወርቅ ማንጠሪያ ድርጅት ከፈቱ። ሽራሮ ከተማ ላይ ደግሞ ጋራዥ ከፍተው የመካኒክ ስራ እየሰሩ እንደነበሩ ይናገራሉ። በአሁኑ ወቅት ግን በግጭቱ ምክንያት ቤሳ ቤስቲን የላቸውም። ያለ የሌለ ንብረታቸው ተዘርፏል። "ሁሉንም አጥቻለሁ ማንኪያ ሳይቀር ነው የዘረፉኝ እኔ የሶስት ልጆች አባት ነኝ። ልጆቼ ምን ሆነህ ነው የነበረህን ያጣኸው? ቢሉኝ ምን ብዬ እመልስላቸዋለሁ። የቱን ታሪክ ነው የምነግራቸው? ይህንን ሳስብ መመለስ ይከብደኛል። እዚህ መቀመጥ ደግሞ ጥዋት ተነስቶ እንጀራ ወይም ዳቦ መጣ ወይ እያሉ ተመፅዋች መሆን ከባድ ነው" ይላሉ። በቅርቡም የአውሮፓ ሕብረት በከፍተኛ ዲፕሎማቱ ጆሴፕ ቦሬል በኩል ባወጣው መግለጫ "ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች፣ ግድያዎች፣ ዘረፋዎች፣ አስገድዶ የመድፈር ድርጊቶችና ስደተኞችን በግዴታ ወደ አገራቸው መመለስና የጦር ወንጀል ድርጊቶች ሊሆኑ የሚችሉ ክስተቶችን በተመለከተ በተከታታይ መረጃ ይደርሰናል" ብለዋል። በሽራሮ ከተማ በነበረው ግጭት ንብረታቸውን ያጡት ሌላኛዋ ወ/ሮ አወጣሽም በመቀለ በሚገኘው ጊዜያዊ የትምህርት ቤት መጠለያ ውስጥ ያሉ ሲሆን ህይወት እንዴት እየፈተነቻቸውም እንደሆነ ለቢቢሲ ትግርኛ በስልክ ተናግረዋል። "አንዳንድ ቀን ፆማችንን እናድራለን። አንዳንዴም እንበላለን። ለአንድ ሰው በተሰጠ ፍራሽ ላይ የአንዱን ሽታና በሽታ ችለን ተጠጋግተን እናድራለን። እዚህ ከባድ ህይወት እያሳለፍን ነው።" የሚሉት ወ/ሮ አወጣሽ ቀይ መስቀል ወደመጡበት እንውሰዳችሁ የሚል ጥያቄ ቢያቀርብም "ወደመጣንበት መመለስ ስናስብ ግን ወታደር ስላለ ስጋት አለን። እዚህ ለአንድ ወር ብለው ከሰጡን እርዳታ ውጭ ህዝቡ ነው የሚደግፈን" ይላሉ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙት ተፈናቃዮች ወደቀደመ ህይወታቸውም ለመመለስ የሚታሰብ እንዳልሆነና ከፍተኛ ፍራቻ እንዳላቸውም ይገልፃሉ። በክልሉ ውስጥ ያለው ሁኔታ አስከፊ እንደሆነና "በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ምክንያት ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ" አንድ የመንግሥት ባለስልጣን መናገራቸውን ከእርዳታ ሠራተኞች ጋር ከተደረገ ስብሰባ ላይ ሾልኮ የወጣ ማስታወሻ ላይ የሰፈረ ጽሁፍ ማመልከቱ የሚታወስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ጦርነት በተካሄደባቸው የትግራይ ክልልና አዋሳኝ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ደኅንነትና ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሰብአዊ ቀውስን ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ገልጿል። በትምህርት ቤቶቹ ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ ከሚያደርጉ በጎ አድራጊ ድርጅት መሪዎች መካከል አቶ ሙሉ ኃይለሥላሴ አንዱ ናቸው። አቶ ሙሉ ለተፈናቃዮች የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም ከፍተኛ የሆነ የመድኃኒት እጥረት መኖሩን ያስረዳሉ። ተፈናቃዮቹ መድኃኒት ሲፈልጉ በነፃ የሚሰጡ ፋርማሲዎች እንዳሉና የተወሰኑ ሆስፒታሎችም ባለው አቅም አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን ቢገልፁም የመድኃኒት አቅርቦት ችግር እንዳለ ያስረዳሉ። ነዋሪዎች ከጤና አገልግሎት እጥረት ጋር በተያያዘ እየሞቱ እንደሆነና በምግብና ውሃ እጥረትም በከፍተኛ ሁኔታም መጎዳታቸውን ሮይተርስ ክልሉን ከጎበኙ የእርዳታ ድርጅቶች ያገኘውን መረጃ ዋቢ አድርጎ ዘግቧል። ነዋሪዎች አሁንም በድንጋጤ ላይ መሆናቸውንም ዘገባው አስነብቧል። ከመቀለ ከተማ ውጭ ባሉ አካባቢዎች በተለይ የጤና አገልግሎት እንደሌለና በሳንባ ምችና በወሊድ ምክንያትም የሚሞቱ እንዳሉም ሮይተርስ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን (MSF) ድንገተኛ ፕሮግራም ኃላፊ ማሪ ካርመን ቪኖሌስን ዋቢ በማድረግ ዘግቧል። በአዲግራትና አክሱም አካባቢ የሚገኙ የገጠር አካባቢዎችን የጎበኙት የእርዳታ ድርጅቱ አባላት በአዲግራት የሚገኙ ዶክተሮችና ነርሶች "የተራቡ ህመምተኞችን" በህይወት ለማቆየት ሲታገሉ ማየታቸውንና ዋነኛው የከተማይቱ ሆስፒታል አምቡላንሶችም ተሰርቋል ማለታቸውን ሮይተርስ በዘገባው አስነብቧል። በጎበኙባቸውም አካባቢዎች የምግብ እጥረት፣ ውሃ፣ የጤና አገልግሎት ችግርና በፍራቻ የተዋጡ ሰዎችን ያገኙ ሲሆን "ሁሉም ምግብ ነው" የሚጠይቁት ብለዋል ኃላፊዋ ማሪ ካርመን። የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ በዚህ ሳምንት ሰኞ እለት ባወጣው መግለጫ በሽረ ባሉ ክሊኒኮች በርካቶችን እየገደለ ያለው የምግብ እጥረት እንዳለ ያሳወቀ ሲሆን ሁኔታውንም የከፋ ነው ብሎታል። ከግጭቱም በፊት በርካታ ሰዎች በምግብ ዕጦት ሲሰቃዩ የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ በግጭቱ ሁኔታ እንደተባባሰና በተለይም ጦርነቱን ፈርተው በተራራዎች ላይ የተደበቁ ሰዎችም በምግብና በህክምና አቅርቦት እጥረትም መቸገራቸውንና መድረስ እንዳልተቻለ ተገልጿል። ሮይተርስ በተጨማሪ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳሪ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙሉ ነጋን (ዶ/ር) ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ባለስልጣኑ ተራራማ የሆኑ ገጠራማ ቦታዎች እርዳታ ለማድረስ የመጓጓዣ እጥረት የነበረ ቢሆንም፣ እርዳታ ማድረስ መጀመራቸውን አስታውቀዋል። ከሰሞኑም እንዲሁ በክልሉ ምግብ፣ ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችና የሕክም አቅርቦቶች የሰብዓዊ ድጋፍ ለ1.8 ሚሊዮን ሰዎች መድረሱን የሠላም ሚኒስቴር ገልጿል። ሚኒስቴሩ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሰዎች እየቀረበ ያለውን እርዳታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ ላይ ከተጠቀሱት ሰዎች በተጨማሪ በክልሉ 2.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል። ከዚህም በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ የስደተኞች ሁኔታ አሳሳቢ እንደሆነም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን፣ ዩኤንኤች ሲ አር አስታውቋል። በስደተኞቹ ሁለት ጣቢያዎች ድርጅቱ መገኘት እንደቻለና መሰረታዊ በሚባሉ አቅርቦት እጦትም እየተሰቃዩ እንደሆነ አስታውቋል። የኮሚሽኑ የኢትዮጵያ ተወካይ ክሪስ ሜልዘር ለቢቢሲ እንደተናገሩት ኤጀንሲው በስደተኞች ካምፑ አካባቢም አገልግሎት መስጠት ይቻል ዘንድም ጊዜያዊ መጠለያ እያቋቋመ ይገኛል። በቅድሚያም ምግብና ንፁህ ውሃ አቅርቦት ቅድሚያ የሚሰጠው ስራ ነው ያሉት ተወካዩ "ለባለፉት ሁለት ወራት በስደተኞች መጠለያ ካምፕ አቅራቢያ ከሚገኝ ወንዝን በመጠቀም ነው ምግብ ለማብሰል፣ ለመጠጥም ሆነ ለመታጠቢያነት ሲጠቀሙ የነበሩት። ለዚያም ነው ተቅማጥ በከፍተኛ ሁኔታ የተባባሰበው" ብለዋል። በምዕራብ ትግራይ በሚገኙት ማይ አይኒና አዲ ሃሩሽ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ 25 ሺህ የኤርትራ ስደተኞች የሚገኙ ሲሆን ቁጥራቸውም በግጭቱ ምክንያት ቀንሷል ተብሏል። ግጭቱንም ፍራቻ በርካታ ስደተኞች መሰደዳቸውም ተነግሯል። የስደተኞቹ መጠለያ ቤቶቹም ሆነ ትምህርት ቤቱ ጉዳት እንዳልደረሰበት የጠቀሱት ክሪስ ሆኖም " የህክምና ባለሙያዎች፣ መምህራን የሉም። የውሃ አገልግሎትም ተቋርጧል" ብለዋል። ዩኤንኤችሲአር እንዲጎበኛቸው የተፈቀደላቸው እነዚህ ሁለት ካምፖች ከባድ ውጊያ የተካሄደባቸው አይደሉም። ከኤርትራ ጋር በሚያዋስነው ድንበር በኩል በሰሜን ትግራይ የሚገኙት የሺመልባና ህፃፅ ካምፖችን ለመጎብኘት ዩኤንኤችሲአር በተደጋጋሚ ለኢትዮጵያ ያደረገው ጥሪ ሊሳካ አልቻለም። ከግጭቱ በፊት በኤርትራ ያለውን ፖለቲካዊ ጭቆና በመፍራትም የተሰደዱና በትግራይ አራቱ ካምፖች ውስጥ የተጠለሉ ስደተኞች ቁጥር ወደ መቶ ሺህ ይጠጋ ነበር። በትግራይ ክልል ግጭት የተቀሰቀሰው ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በወቅቱ ክልሉን ያስተዳድር የነበረው ሕወሓት የሰሜን ዕዝን ማጥቃቱ ከተገለፀ በኋላ ነበር። የፌደራል መንግሥቱ ሠራዊት በኅዳር ወር አጋማሽ ላይ መቀለን ከተቆጣጠረ በኋላ በትግራይ ያካሄደው ወታደራዊ ዘመቻ መጠናቀቁን መግለጹ ይታወሳል። ነገር ግን አልፎ አልፎ ውጊያ እንደሚካሄድ የተነገረ ሲሆን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በክልሉ ያለውን የሰብአዊ ሁኔታ "የከፋ" ሲል ገልጾታል። ጨምሮም "ምግብ አለመኖር ወይም በገበያዎች ላይ ያለው አቅርቦት ውስን መሆን እየባሰ የሚሄድ የምግብ እጥረት አደጋን እየፈጠረ መሆኑን ሪፖርቶች እያመለከቱ ነው" ብሏል። በተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት ላይ እንደተጠቀሰውና የአስቸኳይ ጊዜ ማስተባበሪያ ማዕከል እንደሚለው በትግራይ ክልል 4.5 ሚሊዮን ሕዝብ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል። የተባበሩት መንግሥታትም ሆነ የተለያዩ የእርዳታ ድርጅቶች ህዝቡን መደረስ እንዳልቻሉም ሲናገሩና መንግሥት እንዲያመቻች ሲጠይቁም ተሰምተዋል።
news-47169409
https://www.bbc.com/amharic/news-47169409
ከተማ ይፍሩ፡ ያልተነገረላቸው የአፍሪካ አንድነት ባለ ራዕይ
በፊውዳሉ ስርዓት ሹመት በደም ትስስር፤ በዘርና አጥንት ተቆጥሮ በሚሰጥበት ወቅት ስሟ ብዙ ከማትታወቀው የሐረርጌ ግዛቷ ጋራ ሙለታ ከደሃ ገበሬዎች ቤተሰብ የተገኘውና በ30ዎቹ ዕድሜ የነበረው ወጣት ከተማ ይፍሩ የአገሪቷ የውጭ ጉዳይ ግንኙት አድራጊ፣ ፈጣሪ እንዲሁም የአፄ ኃይለሥላሴ ዋና ልዩ አማካሪ (ቺፍ ኦፍ ስታፍ) ይሆናል ብሎ ያለመ አልነበረም።
ነገር ግን የማይታሰበው እውን ሆኖ ከተማ ከዚህም አልፎ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ ላይ አሻራውን መጣል ችሏል። የታሪክ መዛግብትም ሆነ በቅርብ የሚያውቋቸው ተራማጅ ብለው የሚጠሯቸው ከተማ ኢትዮጵያ ቅኝ ባለመገዛቷ ከአህጉሩ የተለየችና ኢትዮጵያውያንም ልዩ ነን የሚል እሳቤ በአብዛኛው ዘንድ ቢንሸራሸርም ለሳቸው ግን የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ከሌሎች አፍሪካውያን የተለየ አይደለም ፤ መተባበር ካለባትም ከአፍሪካውያን ጋር ነው የሚል ቁርጠኛ አቋም ነበራቸው። •መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ ገና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያሉ ሊግ ኦፍ ኔሽን ኢትዮጵያን አንቅሮ የተፋበት ሁኔታ ቁጭት እንደፈጠረባቸው በአሁኑ ሰዓት የህይወት ታሪካቸውን እየፃፈ ያለው ልጃቸው መኮንን ከተማ ይናገራል። የጥቁር ህዝቦች ነፃነት ተምሳሌት የሆነችው ኢትዮጵያ በጣልያን ስትወረር አባል የሆነችበት የሊግ ኦፍ ኔሽን ይተባበረኛል የሚል እምነት ነበራት ። ነገር ግን ያልተጠበቀው ሆኖ አፄ ኃይለሥላሴ ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት በመዘባበት፣ በጩኸትና በፉጨት ንግግራቸው ተቋረጠ። • የቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ትውስታዎች በኢትዮጵያውያን ዓይን ይህም ሁኔታ ታዳጊው ከተማን ከማስከፋት አልፎ ለተጨቆኑ ህዝቦች እንዲቆም ፤ ለፍትህና ለእኩልነት እንዲታገል መሰረት እንደሆነው የቅርብ ጓደኞቻቸው ምስክር ናቸው። በአንድ ወቅት የቀድሞው የጣልያንና ጂቡቲ አምባሳደር ዶ/ር ፍትጉ ታደሰ ስለ ከተማ ተጠይቀው ሲመልሱ በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ የአፍሪካውያን ሁኔታ ስለሚያሳስባቸውም "እኛ ነፃነት አግኝተን፤ እነርሱ በባርነት ቀንበር እንዴት ይሰቃያሉ" የሚል አስተሳሰብ ነበራቸው ብለዋል። ለዚያም ነበር ኢትዮጵያ ከጣልያን ጋር በነበራት ትግል የረዳቻት እንግሊዝን እንኳ ለመተቸት ቅንጣት ወደ ኋላ ያላሉት። እንግሊዝ በአፓርታይድ ጭቆና ስር ለነበረችው ደቡብ አፍሪካ የጦር መሳሪያ መሸጧንም በከፍተኛ ሁኔታ ተችተዋል። ማንዴላ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅት ከኪሳቸው የከተማ ፎቶ ተገኝቶ ነበር ከመተቸት ባለፈም ነፃ ያልወጡ የአፍሪካ ሀገራት ነፃ እንዲወጡ ከፍተኛ ርብርብና ለነፃ አውጭዎቿም ድጋፍ አድርገዋል። ከዚህም ውስጥ የሚጠቀሰው ለማንዴላ በኢትዮጵያ ፓስፖርት እንዲዘዋወሩ ማድረጋቸው ነው። ማንዴላ በአፓርታይድ መንግሥት በቁጥጥር ስር ሲውሉ የከተማ ፎቶ በኪሳቸው ውስጥ እንደተገኘ የከተማ ልጅ መኮንን ይናገራል። ፎቶው ላይ ለነፃነት ታጋዩ የሚል ፅሁፍ የነበረበት ሲሆን ፎቶው በማንዴላ እስር ወቅት እንደ ማስረጃ ሰነድ ቀርቦ እንደነበር በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ቪትዝ ዩኒቨርስቲ ሙዝየም ማስረጃ ተቀምጧል። •"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች ከተማና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ምስረታ 1950ዎቹ ለአፍሪካውያን የተለየ ተስፋ ይዞ የመጣ ጊዜ ነበር። የነበሩበት የቅኝ ግዛት፣ ጭቆና፣ ባርነትን በመሰባበር ነፃነት የተፈነጠቀበት ጊዜ ነበር። በዛን ጊዜም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከዚህ ቀደም ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ ወጣቱ ፓን አፍሪካኒስት ከተማ የአፍሪካ አህጉራዊ ድርጅት መፈጠር አለበት የሚል ንግግር ተናገሩ። ነፃ በወጡት አፍሪካ ሀገራት መካከል የአህጉሯ ህብረት ቢፈለግም ድርጅትን ሳይሆን ሀገራቱ ተዋህደው አፍሪካ አንድ ልትሆን ይገባል የሚል እሳቤዎች የጎሉበት ጊዜ ነበር። በአንድ ወገን ዋናና ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው ሀገራቱ በፍጥነት ተዋህደው አፍሪካ አንድ ልትሆን ይገባል የሚለው የካዛብላንካ ቡድን፤እንዲሁም አንድ ከመሆን በፊት ሌሎች ትብብሮች ሊቀድሙ ይገባል የሚለው የሞኖሮቪያ ቡድኖች ነበሩ። ኢትዮጵያም በወቅቱ የሞኖሮቪያን ቡድን ተቀላቅላ ነበር። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከተማ ኢትዮጵያ ሁለቱን አንጃዎች የማስማማት ስራ መስራት እንዳለባት ለንጉሱ አጥብቆ ተናገሩ። ምንም እንኳን በወቅቱ ወግ አጥባቂ የነበሩት ሹማምንቱና መኳንንቱ "እንምከርበት" የሚል ኃሳብ ቢያነሱም አፄ ኃይለሥላሴ ግን "ታምንበታለህ" የሚል ጥያቄ ብቻ እንዳቀረቡላቸውና ሂደቱን ብቻ እንዲያሳውቃቸው እንደነገራቸው መኮንን ይናገራል። ሁለቱም ቡድኖች ስብሰባቸው ላይ እንዲገኙ ጥሪ ሲያቀርቡ ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ እንደሆነ በማሰብ አጀንዳቸውን ይዘው ሄዱ። የሚኒስትሩ ዋነኛ አጀንዳ የነበረው ከ20 በላይ አባላት የነበሩትን የሞኖሮቪያን ቡድንና ስድስት ብቻ አባላት የነበሩትን የካዛብላንካን አንጃ አሳምኖ አዲስ አበባ ጉባኤ ማካሄድ ነበር። ከተማ ይፍሩ ትምህርት የጀመሩት ኬንያ ነበር ኢትዮጵያ ሁለቱን ቡድኖች አንድ ላይ ለማምጣት የመሪነት ቦታውን በመያዝ የሞኖሮቪያን ቡድን ስብሰባ ለመሳተፍ አቶ ከተማ ወደ ሌጎስ አመሩ። አመራሮቹን አዲስ አበባ በሚካሄደው ጉባኤ እንዲመጡ ፤ በኋላም ንጉሱንም አሳምነው ለመሪዎቹ ምስጋና እንዲያቀርቡ ያደረጉ ሲሆን ንጉሱም " እኛ ከሞኖሮቪያም ሆነ ከካዛብላንካ አይደለንም። ከአፍሪካ ጋር ነን የሚል" ታሪካዊ ንግግራቸውን አደረጉ። በተለይም በወቅቱ የሀሳቡ አመንጪና ከረር ያለ አቋም የነበራቸውን የ ጋናውን መሪ የነንክሩማህን ቡድን ማምጣት ቀላል እንዳልነበር ከተማ ይናገሩ እንደነበር መኮንን ይገልፃል ። በተለይም ጉዳዩን አወዛጋቢ ያደረገው በወቅቱ የሞኖሮቪያ አባል የነበሩት የቶጎው መሪ መገደል ያኛውን ቡድን መወንጀልና ሁኔታዎችም መካረር ጀመረ። ነገሮችንም ለማለሳለስ ብዙ ጥረት ተደረገ። ከዚህም ውስጥ ሌላኛውን የካዛብላንካ ቡድን አባል የነበሩትንም የጊኒውን መሪ ፕሬዚዳንት ሴኩቱሬንም ወደ አስመራ በመጋበዝ ከንጉሱ ጋር እንዲነጋገሩ ተደረገ። ኢትዮጵያና ጊኒ በመከፋፈል አያምኑም የሚል መግለጫም በጋራ አወጡ። መሪዎቹን አስማምቶ ማምጣት በጣም የከበደ ስራ እንደነበር የሚናገረው መኮንን በብዙ አጋጣሚዎችም አባቱ ከተማ የዲፕሎማሲ ክህሎታቸውን በመጠቀም ነገሮችን እንዳሳኩ ይናገራል። አቶ ከተማ ይፍሩ ከወቅቱ የታንዛንያው ፕሬዚዳንት ጁልየስ ኔሬሬ ጋር ከተማ በየሃገራቱ ሲዞሩ "ሀገር አልለቅም፤ ንጉሱ አያስገቡኝም" የሚሉ ማባበያዎችን ይጠቀሙ እንደነበር የሚናገረው መኮንን ከተማ የቱኒዝያውን ፕሬዚዳንት ያግባቡበትን መንገድ ለይቶ ይጠቅሳል። ፕሬዚዳንቱ የሁለቱ ቡድኖች የጋራ አቋም ሳይኖር እንዴት አንድ ላይ እንሰበሰባለን የሚል የእምቢታ ምላሽ ሲሰጧቸው በምላሹም "አፄ ኃይለሥላሴ ያለርሰዎ ይህ ስብሰባ አይካሄድም" እንዳሏቸው መኮንን ይናገራል። በወቅቱ አፄ ኃይለሥላሴ የነበራቸው ቦታ ከፍተኛ ስለነበርም የቱኒዚያው ፕሬዝዳንት እሺ ብለው መጡ። ያ ታሪካዊ ስብሰባ ሊደረግም በቃ፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅትም ተበሰረ። ነገር ግን ሁሉ ቀላል አልነበረም። ሁለት የተለያዩ እሳቤዎችን ይዘው የመጡ ቡድኖችን አንድ ላይ መምጣት ቀላል አልነበረም፤ የተወሰኑ ግጭቶች ቢፈጠሩም የነበረው የስሜት ድባብ በጣም የተለየ እንደነበር አቶ ከተማ ለልጃቸው ለመኮንን ነግረውታል። "እንዲህ አይነት ስሜት አፍሪካ ውስጥ ተፈጥሮ አያውቅም" ብለው አባቱ አጋጣሚውን ገልፀውለታል። አዲስ አበባን የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፅህፈት ቤት የማድረግ ትግል በመቀጠልም የአፍሪካ ፖሊሲዎችን ማርቀቅ፣ የድርጅቱ ፀሐፊ እንዲሁም ዋና ፅህፈት ቤት የት ይሁኑ የሚሉ አንገብጋቢ ጥያቄዎች ነበሩ። በከተማ አመራርነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሁለቱን አንጃዎች ፖሊሲና ሌሎች ሀሳቦችን ጨምረው አቀረቡ፤ ፖሊሲዎቹ ላይ አንዳንድ አለመስማማቶች ቢፈጠሩም ሰነዱ ተፈረመ። ከተማ ስራቸው አላለቀም ለኢትዮጵያ የነበረው ጥሩ ስሜት እያለ ኢትዮጵያ የድርጅቱ ፅህፈት ቤት መቀመጫ ትሁን የሚል ሀሳብ አቀረቡ። በፍጥነት ከአመራሩ "አይቻልም" የሚል ምላሽ ተሰጣቸው። ምክንያቱ ደግሞ "ከተማ የራሱን ስም ለማበልፀግ" እየሰራ ነው ብለው ንጉሱን የሚመክሩ ስለነበሩ እንደሆነ መኮንን ይናገራል። የተፈራው አልቀረም ትንሽ ቆይቶም ፈረንሳይኛ ተናጋሪ ሀገራት የድርጅቱ መቀመጫ ዳካር እንድትሆን መስማማታቸው ተሰማ። ኢትዮጵያ ድርጅቱን ለመመስረት ይህንን ያህል ለፍታ አመድ አፋሽ መሆኗ ንጉሱን አስደነገጣቸው። ከሴኔጋል ሌላም ናይጀሪያ ያላትን ትልቅነት ተጠቅማ እዚህ መሆን አለበት የሚል ክርክርም ጀምራ ነበር። የሃገራቱ እሰጣገባ ብቻ ሳይሆን "ኢትዮጵያን አትምረጡ" የሚል ቴሌግራም እንደተሰራጨም እንደነበር የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለከተማ አሳዩዋቸው። "ኢትዮጵያና ሶማሊያ መካከል ግጭት እያለ ሚኒስትሩ ያንን ማድረጋቸው ለአባቴ በህይወቱ ሙሉ የሚያስደንቀው ጉዳይ ነበር። ቢጋጩም የሶማሊያ ድጋፏ ለኢትዮጵያ ነበር" ይላል መኮንን በመቀጠልም ኢትዮጵያ እንድትመረጥ የማግባባቱ ስራ/ ዘመቻ/ ተጀመረ። በተለይም ለጊኒ እናንተ ኢትዮጵያን መቀመጫ ካደረጋችሁ የፀሀፊውን ቦታ እንሰጣችኋለን የሚል ሃሳብን እንዳቀረበ መኮንን ይናገራል። በመጨረሻም ከናይጀሪያ በስተቀር ኢትዮጵያ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ዋና ፅህፈት ቤት መቀመጫ እንድትሆን አገራቱ ድምፃቸውን ሰጡ። "ብዙዎች እንደሚሉት አፄ ኃይለሥላሴ ስለነበሩ አዲስ አበባ ተመረጠች የሚለው ሳይሆን ከብዙ ማግባባት፣ ክርክርና ፍጭቶች በኋላ ነው የድርጅቱ ፅህፈት ቤት አዲስ አበባ ሊሆን የቻለችው።" በማለት መኮንን ያስረዳል። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ቀደምት ጉባኤዎች ከጋራ ሙለታ ቦስተን ዩኒቨርስቲ ለዘመናት በተለያዩ መድረኮች ላይ ኢትዮጵያን የወከሉት አቶ ከተማ የተባበሩት መንግሥታትን ጨምሮ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከመሆናቸው በፊት በተለያዩ ኃላፊነት አገልግለዋል። የትምህርት ጉዟቸው ሀ ብሎ የተጀመረው ኬንያ ነበር። ምክንያቱም ጣልያን ኢትዮጵያን ሲቆጣጣር በሰባት አመታቸው ወደ ጂቡቲ ለመሰደድ ተገደዱ። ትንሽ ጊዜ ጅቡቲ ቆይተውም ጉዟቸውን ከአጎታቸው ጋር ወደ ኬንያ አደረጉ። በእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ስር በነበረችው ኬንያም ስደተኞች ከአገሬው ተማሪ ጋር አብሮ መማር ስለማይቻል ለኢትዮጵያውያን ስደተኞች ተብሎ በተከፈተውና በቢትወደድ ዘውዴ ገብረ ህይወት ኃላፊነት በሚመራው ትምህርት ቤት ጀመሩ። ኢትዮጵያ ነፃነቷን ስትቀዳጅ ደግሞ ወደ ጋራ ሙለታ ተመለሱ። ያኔም ትምህርታቸውን የመቀጠል ፅኑ ፍላጎት እንደነበራቸው መኮንን ይናገራል። ለዚህ ደግሞ የአጋጣሚ በር ተከፈተላቸው። ንጉሱ የተለያዩ አካባቢዎችን በሚጎበኙበት ወቅት ጋራ ሙለታን ሲጎበኙ በአካባቤው ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ልጆች አሉ ምን ይደረግ? ብለው ሲጠየቁ አዲስ አበባ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምጣት እንደሚችሉ ምላሽ ተሰጣቸው። መኮንን እንደሚናገረው አዲስ አበባ ሄደው ወዲያው ትምህርት ቤት የሚገቡ መስሏቸው የነበረ ቢሆንም ሲደርሱ አናስገባም የሚል ምላሽ ተሰጣቸው። የሚያድሩበትም ሆነ የሚበሉት አልነበራቸውም፤ በጊዜው "ሰው ለሰው አዛኝ በመሆኑ" ይላል በአካባቢው የነበሩ ወታደሮች መጠጊያ ሆኗቸው። ስራም እየሰሩ ትንሽ ከቆዩ በኋላ ነገሩ በወቅቱ የጦር ሰራዊት ኃላፊ ለነበሩት ጄኔራል መርዕድ መንገሻ በመነገሩ በሳቸው ምክንያት ትምህርታቸውን ሊጀምር እንደቻሉ ይናገራል። የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች የመኳንንትና የሹማምንት ልጆች በመሆናቸው ከፍተኛ ልዩነት ይታይበት የነበረ ሲሆን አባቱ የነገሩትንም መኮንን እንዲህ ያስታውሰዋል። "ንጉሱ በየጊዜው እየመጡ ተማሪዎቹን ይጎበኛሉ። መምህሩም ስም በሚጠራበት ወቅት ከስማቸው ፊት ደጃዝማች፣ ልዑል እንዲሁም ሌሎች ሹመቶች ነበሩ። ጃንሆይም ልጆቹ በእኩልነትና ያለምንም ተፅእኖ ትምህርታቸውን እንዲማሩ ቅጥያው እንዲሰረዝ አዘዙ" ይላል። በመቀጠልም ለከፍተኛ ትምህርት ወደ አሜሪካ ሚቺጋን ሆፕ ኮሌጅ ፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት ለማጥናት ያቀኑ ሲሆን፤ የማስተርስ ዲግሪያቸውንም በቦስተን ዩኒቨርስቲ በተመሳሳይ ትምህርት ተመርቀዋል። አሜሪካ ሲደርሱ ከፍተኛ ዘረኝነት ያጋጠማቸው ሲሆን፤ "ውሾችና ጥቁሮች አይፈቀድም" የሚሉ መልእክቶች እንዲሁም የነበረው የዘረኝነት ሁኔታ አፍሪካዊነታቸውን ብቻ ሳይሆን የፓን አፍሪካዊነት ፅንሰ ሀሳባቸውንም በከፍተኛ ሁኔታ ያሳደገው ነገር እንደሆነ መኮንን ይናገራል። ምንም እንኳን የፒኤችዲ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ቢጠየቁም ቤተሰቤን እረዳለሁ ብለው ተመለሱ። ትልቅ ህልም የነበራቸው አቶ ከተማ በውጭ ጉዳይ በተለያዩ ዘርፎች በኃላፊነት ቢያገለግሉም ከደሃ ቤተሰብ ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ ሹመቶች ያመለጧቸው ነበር። የሹማምንት ልጆች በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ሲቀመጡ እሳቸው ዝም ተባሉ። ይህንንም ጉዳይ በጊዜው ውጭ ጉዳይ ለነበሩት ለፀሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ኃብተወልድ አጫወቷቸው ነበር። ሚኒስትሩም ጉዳያቸውን ለንጉሱ እንዲያቀርብ መከሯቸው። "ደፋርና በግልፅ ተናጋሪ ነበር" የሚለው መኮንን ለንጉሱ የጠየቀበትን መንገድ ይገልፃል " እኔ ወደ ኋላ የቀረሁት በማንነቴ ነው" ብሎ በመናገሩ ንጉሱ ተቆጥተው ውጣ አሉት። አቶ ከተማ ይፍሩ ከታንዛኒያው ዲፕሎማት ሳሊም አህመድ ሳሊም ጋር ቢሆንም የደመወዝ ጭማሪ ተደረገላቸው፤ ከጥቂት ጊዜ በኋላም ቢሆን ደግሞ ሹመቱ ተሰጣቸው። ለሹመቱም ጄኔራል መርዕድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሲሆን ብዙ ተቃውሞም ገጥሟቸዋል። የውጭ ጉዳይ ኃላፊ መሆን ግን አልጋ ባልጋ አልሆነላቸውም። "ይህ ሁኔታ በጣም አስደንጋጭ ነበር። ብዙዎች በመቃወም ተከራክረዋል። ምንም እንኳን ሹመቱ ጥሩ ቢሆንም። ብዙ ጠላቶችንም ማፍራት ቻለ" በማለት መኮንን ይናገራል። ንጉሱን በድፍረት በመናገር ታሪክ የሚያስታውሳቸው ከተማ የንጉሱም ዋና ልዩ ፀሀፊም ለመሆን ችለው ነበር። ምንም እንኳን ከአፍሪካውያን ጋር ህብረት መመስረትና ሌሎች አማራጮችን በድፍረት መናገሩ ብዙዎችን ቢያስደንቅም ለመኮንን "ንጉሱ እሱን መስማታቸውና የሚመክራቸውንም ጉዳይ ተግባራዊ ማድረጋቸውን ያደንቃል" ሌላው ሰው የማይጠይቃቸውን ነገሮች ከተማ በድፍረት ይጠይቁ እንደነበርም መኮንን ይናገራል። ለምሳሌ አባቱ ካጨወቱት መካከል አፄ ኃይለስላሴን ንጉስ ባይሆኑ ምን ይሆኑ ነበር? ብለው ጠይቀው ነበር። እርሳቸውም በምላሹ "ዶክተር" ብለው መልሰውለታል። ተራማጁ በንጉሳዊ አገዛዝ ስርአት ውስጥ ብዙ እሳቤዎቻቸው ከጊዜው የቀደመ ነው የሚባልላቸው ከተማ አፍሪካ አንድነት ድርጅትን መሰረት ከማስያዝ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ገለልተኛ አቋም እንዲኖረው ብዙ ጥረዋል። ከዚያም በተጨማሪ ንጉሱን ስልጣን ለልጃቸው እንዲያጋሩ፤ ህገ መንግሥታዊ የዘውዳዊ ስርዓት እንዲመሰረት የሚሉና ሌሎች ኃሳቦችን አካተው ምክር አዘል ደብዳቤም ፅፈውላቸው ነበር። ከተማ ይፍሩ ለአፄ ኃይለሥላሴ የፃፉት ደብዳቤ የአፄ ኃይለሥላሴን እጣ የተነበየው የአቶ ከተማ ደብዳቤ "በዚች አነስተኛ ማስታወሻ ላሳስብ የምወደው ግርማዊነትዎ ከፈለጉ የመሸጋገሪያውን ድልድይ ለመዘርጋትና የኢትዮጵያ ህዝብ ወደፊት ከሞግዚትነት ወጥቶ የራሱን እድል በራሱ ለመወሰን የሚያስችለውን ለማድረግ ስለሚችሉ ሳይውል ሳያድር አስበውበት አንድ የተፋጠነና የተወሰነ እርምጃ እንዲወስዱ ነው" ከደብዳቤው የተቀነጨበ በድፍረት የመናገሩ ጉዳይ ገደብ እንዳለው ያልተረዱት አቶ ከተማ በተለይም በስልጣናቸው ላይ መምጣቱ በንጉሱ ዘንድ ቅሬታን አሳደረ። ደብዳቤውን በፃፉ በማግስቱ ከውጭ ጉዳይ አውጥተው ወደ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ቱሪዝም ሚኒስትር ቀየሯቸው። አባቱ በሁኔታው ብዙ ደስተኛ እንዳልነበሩና እንደከፋቸውም መኮንን ይናገራል። ከሶስት አመታት በኋላም ከተማ የተነበዩት አልቀረም ንጉሱ ከስልጣን ወረዱ። "ምክሩን ሰምተው ቢሆን ኖሮ ያ መጥፎ ስርአት ላይመጣ ይችል ነበር፤ ይስተካከልም ነበር" ይላል መኮንን የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ፅንሰ ሃሳብ ከመመስረት ጀምሮ፣ የአፍሪካ ፖሊሲዎችን ማርቀቅ፣ ካዛብላንካንና ሞኖሮቪያን አስማምቶ አንድ ላይ ማምጣትና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ፅህፈት ቤት አዲስ አበባ እንዲሆን ማድረግ ከሚጠቀሱ ስራዎቻቸው የተወሰኑት ቢሆንም ታሪክም ሆነ ታሪክ ፀሀፊዎች ዘንግተዋቸዋል። በስማቸውም የተቀመጠ ሀውልት ወይም ሌላ ማስታወሻ የላቸውም። ለምን? መኮንን መልስ አለው "አንድ ህዝብ ታሪኩን ሳያውቅ ሲቀር ይህ ነው የሚሆነው፤ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እንዴት ተመሰረተ የሚለውን በአንድ አረፍተ ነገር መናገር እንችላለን፤ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ሁለቱን ቡድኖች አስታረቁ ማለት እንችላለን። ዝርዝሩን ግን ምን ያህል እናውቃለን፥ መንግሥት በተለወጠ ቁጥር ታሪክ የሚጀምረው በእኔ ነው ይልና ያኛውን ያፈርሰዋል። የሚያውቁት ደግሞ እኔ ለሳቸው ተገዢ ነኝ የሚል አስተሳሰብ አለ። የአቶ ከተማ ይፍሩ ስም ከተነሳ ድንገት የሳቸውን ሊሸፍነው ይችላል የሚልም ነገር ይኖራል። አይሸፍንም እሳቸው መሪ ናቸው ተገቢውን ክብር ማግኘት አለባቸው። ነገር ግን ገና ለገና የሳቸውን ስም ይሸፍናል በሚል የግለሰቦች አስተዋፅኦ ሊደበቅ አይገባም። በዛ ላይ ከእንደዚህ አይነት ደሃ ቤተሰብ ከመጣ ሰው ይህንን ሁሉ ታሪክ ከሰራ በኋላ፤ ላገሩ ካበረከተ በኋላ ለሌሎች ምሳሌ ይሆናል እንጂ ይሄንንማ መደበቅ አንችልም" ያ ተስፋን የሰነቀ ድርጅት ብዙም አልቀጠለም በአባላቱ ሃገራት መፈንቅለ መንግሥቶች፣ ግድያዎች ቀጠሉ። በተለይም ከተማ በደርግ ጊዜ ከዘጠኝ አመት የእስር ቆይታ በኋላ ምሬታቸውና ኃዘናቸው ከፍተኛ እንደነበር መኮንን ይናገራል። የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በተመሰረተበት በመጀመሪያዎቹ ሶስት አመታት ችግሮቻቸውን በአህጉራዊ ድርጅቱ ይፈቱ ነበር እንደ ምሳሌም የሚነሱት አልጀሪያና ሞሮኮ ሲዋጉ ኢትዮጵያ አንዷ አሸማጋይ ነበረች። እሳቸውም በአንድ ወቅት በአሜሪካ ድምፅ ተጠይቀው እንደተናገሩት "ሀገራቱ ስልጣን የሚተካኩበት ስርዓት ማምጣት ስላልቻሉ መፈንቅለ መንግሥቶች መከታተል ጀመሩ" ብለዋል። አፍሪካውያን በአንድነት አህጉሯ በአለም አቀፍ ደረጃ የመደራደር አቅምን እንዲሁም ተሰሚነት እንድታገኝ የተጀመረው ጉዞ ወደ ኋሊት ሆኖ ወታደሮች በተለያዩ ቦታዎች ስልጣንን መያዝ ጀመሩ። ይህም ሁኔታ በጣም ያሳዝናቸው ነበር ቢልም እሳቸው ካበረከቱት አንፃር ከአንድ ሰው ከሚጠበቀው በላይ እንዳደረጉ የሰሯቸው ስራዎች ምስክር ናቸው ይላል። ከባለቤታቸው ራሔል ስነ ጊዮርጊስ አራት ልጆች አፍርተዋል። ከእስር ሲፈቱ የአስራ አምስት አመት ልጅ የነበረው መኮንን ደግ፣ ቀላልና የሰው ሃሳብ የሚሰሙ ሰው እንደነበሩ ይናገራል። አቶ ከተማ ራሳቸውንስ እንዴት ይገልፁ ይሆን መኮንን እንደሚለው ወጣ ያለ አስተሳሰብ (ሬብል) ነኝ ይሉ ነበር ብሏል።
50619672
https://www.bbc.com/amharic/50619672
መመሳሰላቸው እጅጉን የበዛ መንትዮች
የመንትዮች በተለይም ከአንድ የዘር እንቁላል የተፈጠሩ፤ በፆታም በመልክም ፍፁም አንድ ዓይነት የሆኑ መንትዮች በብዙ ነገር መመሳሰል የሚያስገርም አይደለም። የናይጄሪያዎቹ መንትዮች ፍሎረንስ ኦላዎይን እና ኢኑስ ኪሂንዴ አድሪናን መመሳሰል ግን ከተለመደው ውጭ እጅግ የበዛ ይመስላል።
የ55 ዓመቶቹ መንትዮች ያገቡት የወለዱትም በአንድ ቀን ነው። አንድ ላይ ሆነው ቤተ ክርስትያን አቋቁመዋል፤ እነሱም ባሎቻቸውም ፓስተሮች ናቸው። መንትዮቹ እድሜያቸውን ሙሉ አብረው ነው የኖሩት። በአሁኑ ወቅትም በደቡብ ምእራብ ናይጄሪያዋ አይባዳን ከተማ አንድ ግቢ ውስጥ ከየቤተሰቦቻቸው ጋር እየኖሩ ነው። "ልጆች እያለን በተለይም በቤት ውስጥ ሥራ እንጣላ ነበር ግን ማንም፤ ወላጆቻችን እንኳ አያስታርቁንም ነበር። እራሳችን ነበርን የምንታረቀው" ትላለች ኦላዎይን። በናይጄሪያ ዮሩባ ባህል መንትዮች ሁሉ በአንድ ዓይነት ስም ይሰየማሉ። ከማህፀን መጀመሪያ የወጣው 'ታይዮ' ሲባል ትርጓሜው የመጀመሪያ ማለት ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ኪህንዴ' ሁለተኛ ይባላል። የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሳሉ በመተሳሰብ የአንዳቸውን ቅጣት ሌላኛቸው ተቀብለዋል። አስተማሪዎቻቸው ሳያውቁት አንዳቸው ለሌላኛቸው ፈተና ተፈትነዋል። በእቅድ ይሁን ግጥምጥሞሽ ሁለቱም በአንድ ቀን በአንድ ሆስፒታል ወልደዋል። ልጆቻቸውን በአንድ ቀን አስጠምቀዋል። አንዳቸው እቤት ውስጥ ከሌሉ ቤት ያለ የሁለቱንም ህፃናት ልጆች ያጠባም ነበር። ልጆቻቸው አሁን ትልልቅ ሲሆኑ በተለይም በስልክ እናቶቻቸውን በድምፅ መለየት እንደሚቸግራቸው ይናገራሉ። • በከፊል አንድ አይነት ስለሆኑ መንትያዎች ሰምተው ያውቃሉ? • ከተለያየ አባት የተወለዱት መንትዮች • መገረዝ የቀጠፈው ህይወት
45834328
https://www.bbc.com/amharic/45834328
ሙሽሪት እጮኛዋ መቃብር ላይ ድል ባለ ሠርግ ተሞሸረች
ነገሩ ፊልም እንጂ በእውን የኾነ አይመስልም።
ጄሲካ ሐዘን ቢሰብራትም እጅግ ለምታፈቅረው እጮኛዋ ፍቅር ስትል ሠርጓን በመቃብሩ ላይ ደግሳለች ኬንዳል መርፊ ይባላል። በበጎ ፈቃድ የእሳት አደጋ ተከላካይ ሠራተኛ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ለሥራ ሲሰማራ አንድ ጠጥቶ የሚያሽከረክር ሰው ገጭቶት ገደለው። ይህ ምን አዲስ ነገር አለው ታዲያ? ሰው እንደሁ በተለያየ መንገድ ይሞታል። የመርፊን ታሪክ ልዩ የሚያደርገው ጄሲካን ጥሎ መሞቱ ነው። የሞተው እጅግ ለሚወዳት እጮኛው ጄሲካ ቀለበት አድርጎላት፤ ቬሎ ተከራይተው፤ የሠርጉ ቀን ተቆርጦ፣ ለፎቶ አንሺ ተከፍሎ፣ ሊሙዚን ተከራይተው መሆኑ ነው ልዩ የሚያደርገው። የ25 ዓመቷ ጄሲካ በሐዘን ተኮራምታ ቀረች። ደግሞ እንደሚባለው ፍቅራቸው ለጉድ ነበር። ከዐይን ያውጣችሁ የሚባሉ በአንድ ላባ የሚበሩ ወፎች። አንድ ሰፈር ቢያድጉም የተገናኙት የኮሌጅ ተማሪ ሳሉ ነበር። ሁለቱም የለየላቸው የአሜሪካን እግር ኳስ ቲፎዞዎች ነበሩ። አንድ ቀን ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት ኬንዴል ኖተርዳም ስቴዲየም ውስጥ መሐል ሜዳ ላይ ተንበረከከ። የ"ታገቢኛለሽ" ጥያቄን ለጄሲካ አቀረበላት። አለቀሰች። በደስታ አለቀሰች ጄሲካ። ጄሲካ ከእጮኛዋ የ 'ታገቢኛለሽ' ጥያቄ ሲቀርብላት ከዚያ በኋላ ለሠርጋቸው ቀን ተፍ ተፍ ማለት ጀመሩ። በዚህ መሐል ነበር ሙሽራው ኬንዳል ድንገተኛው የመኪና አደጋ ደርሶበት እስከወዲያኛው ያሸለበው። ጄሲካ የርሱን ደግነት ተናግራ አትጠግብም። "እጅግ አፍቃሪ፣ እጅግ አዛኝ፣ ድንቅ ሰው...ነበር" ትላለች በእንባ። ሐዘን ከልቧ ሳይወጣ የሠርጉ ቀን ደረሰ። ለካንስ ሊጋቡ ነበር። ጄሲካ ይህን ልዩ ቀን እንዲሁ በእንባ እየተንፋረቀች ማሳለፍ አልፈለገችም። የሠርጉ ዝግጅት እንዲቀጥል ወሰነች። ሚዜዎቿ "አብደሻል?' አሏት። አልሰማቻቸውም። አንዲትም ነገር ሳትጓደል የሠርጉ ዝግጅት ቀጠለ። ሴፕቴምበር 29 ቬሎዋን ለብሳ፣ አምራና ተውባ ብቅ አለች። ፎቶ አንሺው ሙሽሪትን ከተለያየ ማዕዘን ፎቶ ማንሳቱን ቀጠለ። ሠርገኛው ጉድ ለማየት ብሎ ይሆን እርሷን ላለማስቀየም ብቻ ብዙዎቹ ተገኝተው ነበር። በቬሎ እንደደመቀች ወደታዳሚው ዞረች፣ ወደ መድረኩ ወጣች። ለሟች እጮኛዋ ያላትን ፍቅር ተናገረች። ሰዎችም እየተነሱ ስለርሱ ደስ ደስ የሚሉ ወሬዎችን እያወሩ ሳቁ፣ አለቀሱ፣ ተጫወቱ። መደነስ ያለበትም ደነሰ፣ በላ፣ ጠጣ። ጄሲካም ከአባቷ ጋር ዋልዝ ደነሰች። ለምን ይህን እንዳደረገች ስትጠየቅ "መቼም ባሌ ከሞት ይነሳል ብዬ አይደለም። ጥንካሬዬን ለኔም ለሌሎችም ለማሳየት፣ ፍቅሩም ህያው መሆኑንም ለመመስከር" ብላለች። ሠርግ ማድረጓ ሕመሟን እንዳቀለለላትም ትናገራለች። ከሠርገኞቹ መሀል የሙሽራውን/ የባሏን/የእጮኛዋን ባልደረቦች፣ በእሳት አደጋ ብርጌድ ውስጥ አብረውት ይሠሩ የነበሩትን ጓደኞቹን ጠርታቸው ነበር። "ግዴለም ተጣድፋቹ አትምጡ፤ ወንዶች ስትባሉ ሠርግ ላይ ማርፈድ ባሕላችሁ ነው መቼም። " ስትል ቀልዳባቸዋለች። ታዲያ አንዳቸውም ሠርጉ ላይ አልቀሩም። ግልብጥ ብለው መጡ። ፎቶ አንሺው ከርሷ ጋር የሚያነሳውን ሰው ፍለጋ ባተተ። የሟች ሙሽራውን ጫማ አጠገቧ አድርጎ ፎቶ አነሳ። ጄሲካ የሙሽራው መቃብር ጋር ፎቶ አንሺ ይዛ በመሄድ ሌላ ፎቶ ተነሳች። ፎቶው የግሏ ሆኖ እንዲቀር ፈልጋ ነበር። ኢንተርኔት ላይ ያዩት ሰዎች ሲቀባበሉት ግን ዓለምን አዳረሰ። ብዙ ሰዎች ስልክ ደወሉላት። በታሪኩ የተነኩ ሰዎች እያለቀሱ አበረታቷት። ከነዚህ መሀል ተመሳሳይ ታሪክ ያላቸው ይገኙበታል። "ፎቶዎቹን ስመለከት እጮኛዬ አጠገቤ ቆሞ ፈገግ ብሎ በፍቅር ሲመለከተኝ ይታየኝ ነበር።" ብላለች፤ ጄሲካ።
news-55273576
https://www.bbc.com/amharic/news-55273576
ኮሮናቫይረስ፡ ስንት የኮቪድ-19 ክትባቶች አሉ? ለኢትዮጵያስ የትኛው ይደርሳታል?
ኮሮናቫይረስ ተከስቶ የዓለምን አጠቃላይ ገጽታ መቀየር ከጀመረ እንሆ አንድ ዓመት ሊሞላው ተቃርቧል። በዚህ ጊዜም ከ71 ሚሊዮን በላይ የምድራችን ነዋሪ በበሽታው መያዙ የተረጋገጠ ሲሆን ከ1.6 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በወረርሽኙ ሰበብ ህይወታቸውን አጥተዋል።
በሽታው ያላዳረሰው የዓለም ክፍል የሌለ ሲሆን እንደተሰጋው የከፋ ጉዳትን ባያደርስም በአፍሪካ አገራት ውስጥም ከ2.3 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ ከ56 ሺህ በላይ ድግሞ ለሞት ተዳርገዋል። ከዚህ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ከ116 ሺህ ሰዎች በላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን ከ1 ሺህ 880 በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። ከዓለም ዙሪያ የተሰባሰቡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በበሽታው መያዛቸው ከተረጋገጡ ሰዎች መካከል አብዛኞቹ ከበሽታው ያገገሙ ቢሆንም አስካሁን ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ መድኃኒት ለቫይረሱ አልተገኘም። በሽታው ቻይና ውስጥ መከሰቱ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ የተለያዩ አገራት ለበሽታው መከላከያ የሚሆን ክትባት እንዲሁም የተያዙ ሰዎችን ለማከም የሚያገለግል መድኃኒት ለማግኘት ሊቃውንት ቀን ከሌት እየጣሩ ይገኛሉ። እስካሁን በተደረጉ ምርምሮችና ሙከራዎች በርካታ ተስፋ ሰጪ የክትባት ውጤቶች መገኘታቸው ከመነገሩ ባሻገር፤ በሽታውን ለመከላከል ያስችላሉ የተባሉ ጥቂት ክትባቶችም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለበሽታው ተጋላጭ ናቸው ለተባሉ ሰዎች መሰጠት ተጀምሯል። በዚህ ረገድ ቀዳሚውን የተጠቃሚነት ዕድል ያገኙት ባለጸጋ አገራት ሲሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት ደግሞ ክትባቶቹ ለሁሉም እንዲዳረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን አመልክቷል። አገራትም ለዜጎቻቸው ክትባቱን ለማቅረብ ባላቸው አማራጮች ሁሉ እየሞከሩ ነው። ኢትዮጵያም እንዲሁ ኮቫክስ ከተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ድጋፍ ሰጪና እቅራቢ በኩል ለአገልግሎት ከሚቀርቡት የኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ጥያቄ እንዳቀረበች የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል። ሚኒስትሯ ጨምረውም ለአገልግሎት ብቁ ከሆኑ የክትባት አይነቶች መካከል ኢትዮጵያም እንድታገኝ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረው፤ በኮቫክስ በኩል ክትባቱን በፍጥነት ለማግኘትና በቅድሚያ መከተብ ለሚገባቸው ወገኖች እንዲደርስ እንደሚደረግ ገልጸዋል። ለመሆኑ የትኞቹ ክትባቶች ጥቅም ላይ ውለዋል? በአሁኑ ጊዜ በርካታ መድኃኒት አምራች ኩባንያዎችና አገራት ለኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሚሆን ክትባት በማበልጸግ ላይ ሲሆኑ ጥቂቶቹም በስራ ላይ መዋል ጀምረዋል። ፋይዘር/ባዮንቴክ ኮሮናቫይረስን በመከላከል 90 በመቶ ውጤታማ ነው የተባለው ይህ የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ይፋ የሆነው በፈረንጆቹ ሕዳር 9/2020 ላይ ነበር። በወቅቱ ክትባቱን ይፋ ያደረጉት ፋይዘር እና ባዮኤንቴክ ኩባንያዎች ግኝቱ ለሳይንስና ለሰው ልጅ ትልቅ እድል ነው ብለዋል። የአሜሪካ እና የጀርመን ኩባንያ የሆኑት ፋይዘር እና ባዮንቴክ በስድስት የተለያዩ ሃገራት 43 ሺህ 500 ሰዎች ላይ መሞከራቸውን የገለፁ ሲሆን አንድም ጊዜ አሳሳቢ የጤና ችግር አልታየም ብለዋል። ፋይዘርና ባዮንቴክ ክትባቱን በፈረንጆቹ የህዳር ወር መጨረሻ ጥቅም ላይ ለማዋል ጥያቄ ማቅረባቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ይህን ተከትሎም ዩናይትድ ኪንግደም ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል በመፍቀድ ከዓለማችን ቀዳሚዋ አገር ሆናለች። ዩናይትድ ኪንግደም ለመጀመሪያ ጊዜ የኮሮናቫይረስ ክትባትን ማክሰኞ ዕለት ለዜጎቿ መስጠት የጀመረች ሲሆን የዘጠና ዓመቷ አዛውንት የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባትን በመውሰድ በዓለም የመጀመሪያዋ ሰው ሆነዋል። በመላው ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) የሚገኙ ከ70 በላይ የሚሆኑ ሆስፒታሎች እድሜያቸው ከ80 ዓመት በላይ ለሆኑ አዛውንቶች እና ለጤና ባለሙያዎች ክትባቱን ለመስጠት መዘጋጀታቸው ተገልጿል። የአሜሪካ የምግብና መድኃኒት አስተዳደር መስሪያ ቤትን (ኤፍዲኤ) የሚያማክሩ ባለሙያዎች በፋይዘር/ባዮንቴክ የበለጸገው የኮሮናቫይረስ ክትባት ጥቅም ላይ እንዲውል ሀሳብ ማቅረባቸውም ተገልጿል። ባለሙያዎቹ ይህን ምክረ ሃሳብ የሰጡት 23 አባላት ያሉት የባለሙያዎች ቡድን ክትባቱ ሊፈጥረው የሚችለው ስጋት ከሚሰጠው ጥቅም አንጻር ምን ሊመስል እንደሚችል ምክክር ካደረጉ በኋላ ነው ተብሏል። የአሜሪካ የጤና ሚንስትር አሌክስ ረቡዕ ዕለት ''በሚቀጥሉት ቀናት ክትባቱ በእጃችን ሊገባ ይችላል፤ በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ እጅግ ተጋላጭ የሆኑትን ዜጎች መከተብ ልንጀምር እንችላል'' ብለዋል። የፋይዘር/ባዮንቴክ ክትባት እስካሁን በዩናይትድ ኪንግደም፣ ካናዳ፣ ባህሬን እና ሳኡዲ አረቢያ ጥቅም ላይ ለመዋል ፍቃድ አግኝቷል። ሞደርና የዩናይትድ ስቴትስ መድኃኒት አምራች ኩባንያ የሆነው 'ሞደርና' ከኮሮናቫይረስ 95 በመቶ የሚከላከል አዲስ ክትባት ማግኘቱን ይፋ ካደረገ ሰነባብቷል። በአሁኑ ሰአትም ከአውሮፓና አሜሪካ ፈቃድ ሰጪዎች ክትባቱን ለመጠቀም የሚያስችል ፈቃድ ጠይቆ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል። ሞደርና የምርምር ውጤቱን ይፋ ያደረገበትን ዕለት 'ታላቅ ቀን' በማለት ሐሴቱን የገለፀ ሲሆን፤ በቅርብ ሳምንታትም ክትባቱን ለመጠቀም ፈቃድ እንደሚያገኝ አስታውቋል። የቤተ ሙከራ ሂደቶች እንደሚያሳዩት ኤምአርኤንኤ የተሰኘው ክትባት 94 በመቶ ውጤታማና ሰዎችን ከኮሮናቫይረስ የሚያድን ነው። የክትባቱ ሙከራ አሜሪካ ውስጥ ያሉ 30 ሺህ ሰዎችን ያሳተፈ ሲሆን፤ ግማሾቹ በየአራት ሳምንቱ ክትባቱ ሲሰጣቸው ግማሾቹ ደግሞ ጥቅምና ጉዳት የሌለው መርፌ ተወግተው ውጤቱን ለመለየት ተሞክሯል። ከዚህ ሙከራ በተገኘ ውጤት መሠረት 94.5 በመቶ ሰዎች በክትባቱ ምክንያት ለኮሮናቫይረስ ሳይጋለጡ ቀርተዋል ተብሏል። ስለ ክትባቱ ውጤቱ የቀረበው ዘገባ ጨምሮም፤ ሙከራ ከተደረገባቸው መካከል 11 በኮቪድ-19 ክፉኛ የታመሙ ሰዎች የመከላከል አቅም አዳብረዋል ይላል። ስፑትኒክ 5 ይህ ሩሲያ ሰራሽ ክትባት ይፋ በተደረገ ጊዜ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአገር ውስጥ በተደረገ ምርምር አገር በቀል ክትባት አግኝተናል፤ ለሰዎች አገልግሎት እንዲውልም ይፋዊና ብሔራዊ ፍቃድ ሰጥተናል ብለው ነበር። በዓለም የመጀመርያው የተባለው ይህ ስፑትኒክ-5 ክትባት ሞስኮ የሚገኘው ጋማሊያ ኢንስቲትዩት ነው ያመረተው። ክትባቱ ይፋ የተደረገውም ነሀሴ ወር ላይ ነበር። ኢንስቲትዩቱ እንደሚለው ክትባቱ አስተማማኝ የመከላከል አቅም ይሰጣል። ፑቲን በበኩላቸው ገና ቀደም ብሎ "ይህ ክትባት አስተማማኝ እንደነበር አውቅ ነበር" ብለዋል። "ሁሉንም ሳይንሳዊ ሂደቶችን በአስተማማኝ ሁኔታ ማለፍ ችሏል" ሲሉም አስረግጠው ተናግረዋል። ፑቲን ከልጆቻቸው ለአንዷ ክትባቱ ተሰጥቷት ትንሽ አተኮሳት እንጂ ምንም አልሆነችም ብለዋል። ፑቲን የትኛዋ ልጃቸው ክትባቱን ወስዳ እንዳተኮሳት ግን በስም አልገለጹም። የሩሲያ ሳይንቲስቶች የመጀመሪያ ዙር ሙከራዎች ተደርገው ሁሉም ድንቅ ውጤት አስመዝግበዋል ብለዋል። ሳንቲስቶቹ ሰዎች ላይ ጉንፋንን የሚያመጣው አዲኖቫይረስ የተሰኘውን የተላመደ የተህዋስ ቅንጣት ተጠቅመው ነው ክትባት ሰራን ያሉት። ይህን ለማዳ ተህዋሲ አዳክመው ወደ ሰውነት በማስገባት ሕዋስ በማቀበል ክትባቱ ሰውነት ኮቪድ-19 ተህዋሲ ሲገባ ነቅቶ እንዲዋጋ ያደርገዋል ብለዋል። በአውሮፓውያኑ ታሕሳስ 5/2020 ላይ ደግሞ ይሄው ክትባት በሩሲያዋ መዲና ሞስኮ መሰጠት ተጀምሯል። በመጀመሪያው ዙር ክትባቱን ለመውሰድ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተመዝግበዋል። ሩሲያ ምን ያህል ክትባት ማምረት እንደምትችል ግልጽ ባይሆንም፤ አምራቾች እስከ ዓመቱ መገባደጃ ሁለት ሚሊዮን ጠብታ እንዲያዘጋጁ ይጠበቃል። 13 ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት የሞስኮ ከተማ ከንቲባ ሰርጌ ሶቢያን እንዳሉት፤ ክትባቱ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ለጤና ባለሙያዎች እና ለትምህርት ቤት ሠራተኞች ይሰጣል። ተጨማሪ ክትባቶች ሲመረቱ ለተቀረው ማኅበረሰብ እንደሚዳረስ ከንቲባው ጠቁመዋል። ከላይ በተዘረዘሩት የሙያ መስኮች የተሰማሩና እድሜያቸው ከ18 እስከ 60 የሆኑ ዜጎች በድረ ገጽ ተመዝግበዋል። በሞስኮ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የክትባቱን አገልግሎት የሚሠጡ 70 ማዕከሎች ተከፍተዋል። ክትባቱ የተሰጣቸው ባለፉት 30 ቀናት የመተንፈሻ አካል ህመም የገጠማቸው፣ የከፋ የጤና እክል ያለባቸው፣ ነፍሰ ጡር እና የሚያጠቡ እናቶች እንደሚለዩ ተገልጿል። ሲኖቫክ መላው ዓለም ለኮሮናቫይረስ ክትባት ለማግኘት ደፋ ቀና ሲል ቻይናም እጇን አጣጥፋ አልተቀመጠችም። ሲኖቫክ የተባለ ክትባት መስራት ከጀመረች ሰነባብታለች። እንደውም በጎ ፈቃደⶉችን መከተብ ከጀመረች ቆየት ብላለች። በቻይና በሙከራ ላይ የሚገኘው የኮቪድ-19 ክትባት አመርቂ የሚባል ውጤት እያስገኘ ነውም ተብሏል። ሆኖም ክትባቱ አመርቂ ውጤት ያስገኘው በረዥም የሙከራ ሂደት ውስጥ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ ሳይሆን፣ መካከለኛ ምዕራፍ በሚባለው ክፍል ነው። ተመራማሪዎች እንዳረጋገጡት ከቻይና ሰራሽ ክትባቶች አንዱና ታዋቂ እየሆነ የመጣው በሲኖቫክ ባዮቴክ የተመረተው ሲኖቫክ ክትባት በ700 ሰዎች ላይ ተሞክሮ ይበል የሚያሰኝ ውጤት አስገኝቷል። ክትባቱ የተሞከረባቸው ሰዎች በሽታን የመከላከያ ህዋሳቸውን አንቅቶ ቫይረሱን መመከት እንደቻለ ተደርሶበታል። ላንሴት በሚባለው ሥመ ጥር የሳይንስ ጆርናል ላይ ይህንን ክትባት በተመለከተ የተዘገበው፤ ክትባቱ ለጊዜው በምዕራፍ አንድና ሁለት ያስመዘገበው ውጤት እንጂ አሁን ያለበትን ደረጃ አይገልጽም። በተጨማሪም የስኬት ምጣኔው ምን ያህል እንደሆነ ይፋ አልተደረገም። በዚህ ጆርናል ላይ ስለዚህ ቻይና ሰራሹ ክትባት ከጻፉት ተመራማሪዎች አንዱ የሆኑት ዙ ፋንቻይ እንደሚሉት፤ በምዕራፍ አንድ እና በምዕራፍ 2 ሙከራዎች 600 ሰዎች ላይ ጥናት ተደርጎ ክትባቱ ለአስቸኳይ ሕክምና አገልግሎት ላይ መዋል ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ ተደርሷል። ነገር ግን ወሳኝ በሚባው በምዕራፍ ሦስት ሙከራ ላይ ይህ የቻይና ክትባት ስላስገኘው ውጤት በተጨባጭ ተአማኒ ሳይንሳዊ ጆርናል ላይ የተጻፈ ዘገባ የለም። በቻይና በአሁን ሰዓት ሙሉ በሙሉ ሊባል በተቃረበ ደረጃ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በቁጥጥር ሥር የዋለበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ሆኖም ቻይና ለዜጎቿ ይህንን ክትባት መስጠቷን ቀጥላበታለች። በአሁኑ ሰአት ደግሞ መቀመጫውን ቤዢንግ ያደረገው የክትባት አምራቹ ኩባንያ ያዘዛቸው በርካታ የህክምና ቁሳቁሶች ከኢንዶኔዢያ መግባት ጀምረዋል። ይህ ደግሞ አገሪቱ በቅርቡ ዜጎቿን በይፋ መከተብ ልትጀምር እንደሆነ ማሳያ ነው ተብሏል። በዓለም ላይ ኮቪድ-19 ከፍተኛ ጉዳት ካደረሰባቸው አገራት ተርታ የምትመደው የደቡብ አሜሪካዋ ትልቅ አገር ብራዚል በበኩሏ ቻይና ሰራሽ ክትባት ለሕዝቤ አድላለሁ ማለቷ የሚታወስ ነው። የሳኦ ፖሎ ገዥ ጃዎ ዶሪያ እንዳሉት የፌዴራል መንግሥት 46 ሚሊዮን ጠብታዎችን ለመግዛት ስምምነት ላይ ደርሷል። የክትባት ዘመቻው መቼ ይጀመራል በሚል የተጠየቁት የሳኦ ፖሎ ገዥ በፈረንጆች አዲሱ ዓመት የመጀመርያ ወር ላይ ሊሆን ይችላል ብለዋል። አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ አስትራዜኒካ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ እያበለፀጉ ያሉት ክትባት ከፍተኛ ተስፋ ከተጣለባቸው ክትባቶች መካከል ነው። ይሄው ክትባት በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በሙከራ መልክ ተሰጥቷል። ደቡብ አፍሪካ ለዚህ የክትባት ሙከራ የተመረጠችው በዘርፉ ባሏት ባለሙያዎች ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ በርካታ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ያሉባትና ወረርሽኙም በፍጥነት እየተስፋፋባት በመሆኑ ነው። ይህ የክትባት ሙከራ ኦኤክስ1ኮቪድ-19 ክትባት የሚባል ሲሆን፤ ኮሮናቫይረስን የሚያስከትለው ሳርስ-ኮቪ-2 በተባለው ቫይረስ ሰዎች እንዳይያዙ ለመከላከል የታለመ ነው። በደቡብ አፍሪካ የሚደረገው የክትባት ሙከራ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ጥልቅ ፍተሻ ተደርጎበት በደቡብ አፍሪካ መንግሥት የጤና ምርቶች ተቆጣጣሪ ተቋምና በዊትስ ዩኒቨርስቲ ፈቃድ ተሰጥቶታል ተብሏል። ይህ ክትባት ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ከአራት ሺህ ሰዎች በላይ የተሳተፉበት ክሊኒካል ሙከራ የተደረገበት ሲሆን፤ በደቡብ አፍሪካ ከሚደረገው ሙከራ ጋር ተመሳሳይና ተዛማጅ የሆነ ሙከራ ብራዚል ውስጥ ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል። ከዚህ በተጨማሪም ከሁሉም የላቀ ቁጥር ያላቸው ሰዎች የሚሳተፉበት የዚህ ክትባት ሙከራ አሜሪካ ውስጥ በ30 ሺህ ሰዎች ላይ ለማካሄድ ዕቅድ ተይዟል። በሌሎች ድርጅቶች የሚሠሩ እና በሦስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክትባቶች ሙከራ ተጨማሪ ውጤቶች በሚቀጥሉት ሳምንታት እና ወራቶች ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአሁኑ ሰአትም የመጨረሻው የሙከራ ደረጃ ላይ የሚገኙ በርካታ ተጨማሪ ክትባቶች አሉ። ከነዚህም መካከል ከታች የተዘረዘሩት የሚጠቀሱ ናቸው። የክትባቶቹ ደኅንነትስ? ክትባቱ እስካሁን በደኅንነት ጉዳይ ይህ ነው የሚባል ነገር አልተነሳበትም። ነገር ግን የትኛውም መድኃኒት መቶ በመቶ እንከን አልባ ሊሆን አይችልም። አንዳንድ ተሳታፊዎች ክትባቱን የወሰዱ ሰሞን መጠነኛ ድካም፣ ራስ ምታትና ሕመም እንደተሰማቸው አስታውቀዋል። የሞደርና እና የፋይዘር ክትባት ከ90 በመቶ በላይ ውጤታማ መሆናቸው ተነግሯል። ነገር ግን የሁለቱም ድርጅቶች ውጤት የመጨረሻ ደረጃ ላይ አልደረሰም። ውጤታማነቱም ሊቀየር ይችላል ተብሏል። ቢሆንም የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ ለማስቀመጥ ከሌሎቹ ክትባቶች በተለየ ቀላል እንደሆነ ተነግሯል። የሞደርና ክትባት ማቀዝቀዣ ውስጥ እስከ አንድ ወር መቆየት ሲችል የፋይዘር ግን ለአምስት ቀናት ብቻ ነው የሚቆየው። ሩስያ የለቀቀችው ስፑትኒክ 5 የተሰኘው ክትባትም 92 በመቶ የመከላከል አቅም እንዳለው ተነግሯል።
49644888
https://www.bbc.com/amharic/49644888
ከነፍስ የተጠለሉ የድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ዜማዎች
ዘሪቱ ከበደ 'አርተፊሻል' በተሰኘው ነጠላ ዜማ ውስጥ ስሜታችን አርተፊሻል [ሰው ሰራሽ]፣ ምኞታችን አርተፊሻል፣ ውበታችን አርተፊሻል፣ ሕይወታችን አርተፊሻል ስትል ማኅበራዊ ትዝብቷን ታጋራለች። ድንዛዜ፣ አልበዛም ወይ መፋዘዙ ነቃ በሉ ፣ አልበዛም ወይ ማንቀላፋት ኃ ላፊነትን መዘንጋት
ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ በመድረክ ላይ ሥራዋን ስታቀርብ ስትል ትጠይቃለች፤ ዘሪቱ በዚሁ ሥራዋ ውስጥ. . . ድንዛዜ በወሬ፣ ያለጥቅም ያለ ፍሬ ድንዛዜ በጭፈራ፣ ያለ ዓላማ ያለ ሥራ ድንዛዜ በከተማ፣ ሰው የሰው ብቻ እየሰማ ስትል የሰላ ትችቷን ታቀርባለች። ዘሪቱ በሊቢያ አንገታቸውን በተቀሉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የተሰማትን ቁጣ በገለፀችበት ነጠላ ዜማዋ ላይ 'ሠይፍህን አንሳ' ስትል አቀንቅናለች። ሠይፍህን አንሳ፣ ያበራልሃል ለጠላት መልሱን ያስተምርሃል ሠይፍህን አንሳ፣ ትረፍ ከበቀል ኃይል ይሆንሃል እንድትል ይቅር፤ ስትል ለበደሉ ይቅርታ ማድረግን ትሰብካለች። ዘሪቱ የምንኖርበትን ዓለም 'አሁን በብርሃን አይቼሻለሁ' ብላ መጠየፏን በገለፀችበት ሥራዋ፤ የነበረችበትበን የሕይወት መልክና ልክ ስትገልፅ. . . "ማለለ፣ ልቤ ማለለ፣ ታለለ፣ ልቤ ታለለ ሳተ ከቆመበት ተንከባለለ. . ." እያለች ታንጎራጉራለች። • "ለመጨረሻ ጊዜ ያየሁት በትንሳኤ በዓል ነበር" የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌ እናት ድምፃዊት ዘሪቱ በተለያየ ጊዜ በሠራቻቸው እነዚህ ነጠላ ዜማዎች ማኅበራዊ ትችቷን፣ የሕይወት አቋማን ገልጻለች። 'አርተፊሻል' የተሰኘውና ለአካባቢ ጥበቃ እንደተሠራ የምትናገረው ሙዚቃ፣ 'ሠይፍህን አንሳ' የተሰኘውና በሊቢያ አንገታቸውን በአክራሪ ኃይሎች ለተቀሉት ኢትዮጵያውያን ያቀነቀነችው እንዱሁም 'ውሸታም' የተሰኘ ሙዚቃዋ ውስጥ ዓለምን መጠየፍ ይታያል። ዘሪቱ ከእኛ ጋር ለመጨዋወት ፈቅዳ ስትቀመጥ ያቀረብንላት ጥያቄዎችም እነዚሁ ሥራዎቿን የተመለከቱ ናቸው። ቃለ መጠይቁን ከመጀመራችን በፊት ዘሪቱ ጠቆር ያለ ማኪያቶ አዛ እንዲህ አወጋን. . . ቢቢሲ፡ እነዚህ ሦስት ሥራዎች ('አርተፊሻል'፣ 'ሠይፍህን አንሳ'፣ እንዲሁም 'ውሸታም') እርስ በእርሳቸው ግንኙነት አላቸው? ዘሪቱ፡ የእርስ በእርስ ግንኙነታቸው የኔ መሆናቸው ነው። [ሳቅ] ከዚያ ውጪ ግን ያው እኔ የትኛውንም ሥራ ስሠራ ወይ ከሕይወቴ ነው፤ ወይ ከማየው ነገር፣ ከተነካሁበት ነገር ተነስቼ ነው የምደርሰው። ስለዚህ ከእኔ ጋር ግንኙነት አለው። መጀመሪያ 'አርተፊሻል' የሚለው ነጠላ ዜማ ሲወጣ ለአካባቢ ጥበቃ ተብሎ አንደተሠራ ተነግሮ ነበር። ነገር ግን ሥራውን ልብ ብሎ ላደመጠው፤ የአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚያተኩር አይመስልም። ዘሪቱ፡ ልክ ነው! መነሻው እንደዛ ነው። በዚያ ሰዓት 'ብሪቲሽ ካውንስል' የክላይሜት [የአየር ጠባይ ለውጥ] አምባሳደር ብሎ ከመረጣቸው አርቲስቶች ውስጥ ድምፃዊ እኔ ነበርኩ። በዚያ ሰዓት 'ኢትዮጵያ አረንጓዴ' የሚባል 'ኢኒሼቲቭ' ከሚካኤል በላይነህና ከመሐመድ ካሳ ጋር ጀምረን ለመንቀሳቀስ እንሞክር ነበር። እና በሆነ መንገድ ግንኙነት አለው [አርተፊሻል የተሰኘው ስራ ከአካባቢ ጥበቃ ጋር]። • በአንድ የጦር አውድማ ላይ ከወላጅ አባቷ ጋር የተፋለመችው ታጋይ ግን 'አርት ፕሮሰሱ' ውስጥ የምትረካበትን ነገር ትፈልጋለህ። ስለዚህ 'ብሪቲሽ ካውንስል' ከአካባቢ ጥበቃ ጋር ተያይዞ አንድ ሙዚቃ ይሠራ ብለው 'ኢንቨስት' [ገንዘብ ያወጡበት] ያደረጉበት ፕሮጀክት ነው። ግን ምንድን ነው፤ 'ዳይሬክትሊ' [በቀጥታ] ያንን ጉዳይ ብቻ የሚወክል ሥራ ለመሥራት ተሞክሮ የሚያረካ አልሆን አለ። እና በአጋጣሚ እዚያው 'ፕሮሰሱ' ውስጥ እያለሁ 'አርተፊሻል' የሚለውን ሙዚቃ ፃፍኩት፤ በአጠቃላይ የአካባቢ ጥበቃንም ይመለከታል። ከሁሉም በላይ ግን ተፈጥሮ ውስጥ ሰውም አለ። ስለዚህ ሰውን ጥበቃ [ሳቅ] ላይ የበለጠ የሚያተኩር ሥራ ሊወለድ ችሏል ማለት ነው። ወደ አውሮጳ ለመሻገር በስደት ላይ እያሉ በሊቢያ አንገታቸው ስለተቀሉ ወጣቶች የሠራሽውደግሞ 'ሠይፍህን አንሳ' ይሰኛል። ለዚያ ሥራ መወለድ አንቺ ውስጥ የነበረው የወቅቱ ስሜት ምን ይመስል እንደነበር እስቲ አስታውሺኝ። ዘሪቱ፡ ኡ. . . ሠይፍህን አንሳ ከከባድ ስሜት ውስጥ ነው የተወለደው። በዚያ ሰዓት በእነዚያ ወጣቶች ላይ የደረሰው ነገር በጣም ያስፈራ ነበር። በጣም ያስቆጭ ነበር። እልህ ያሲይዝ ነበር። ቁጣ. . . እንዴት ብለህ ነው የምትገልፀው. . . ቁጣ. . . ወገን ናቸው፤ የሰው ልጅም ናቸው። በጣም ተገቢ አይደለም። ስለዚህ በጣም ቁጣ ተሰማኝ፤ በውስጤ። ከዚያ ቁጣ በኋላ ግን የትም ልሄድ አልችልም። ምንም ላደርግ አልችልም። ያ ተስፋ መቁረጥ ደግሞ ሌላ የድባቴ መንፈስ፤ ስሜት አስከተለ። ያ ደግሞ የኔ ብቻ ሳይሆን አካባቢዬንም ሳይ ብዙዎቻችን ላይ ያየሁት፣ ሀገሪቱም ላይ፣ አየሩም ላይ የነበረው መንፈስ እንዴት ጨፍጋጋ እንደነበር አስታውሳለሁ። እና. . . [በረዥሙ ተንፍሳ] የሆነ ነገር ማበርከት እንዳለብኝ ተሰማኝ። በአካባቢዬም በዚያ ስሜት ውስጥ አብረውኝ የነበሩ ወንድም እህቶቼ የሆነ ነገር ማካፈል እንዳለብን ተማመንና በዚያ ጉዳይ መፀለይ ጀመርኩ፤ ማሰብ ጀመርኩ። ስቱዲዮ ውስጥ፣ በዚያ ሰዓት ሳነበው የነበረው መጽሐፍ አለ፤ የሪክ ጆነር 'ዘ ቶርች ኤንድ ዘ ሶርድ'፣ የሚል መጽሐፍ፤ እዚያ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ያለውን የሠይፍ ምስል ሳየው መልዕክቱ እንደመጣልኝ ተሰማኝ፤ ገባኝ። ከዚያ ስቱዲዮ ውስጥ ነው 'ዴቬሎፕ' [ስራው የዳበረው] መደረግ የጀመረው። • በዓመቱ አነጋጋሪ ከነበሩ ጉዳዮች ጥቂቱ ከዚያ ዳዊት ጌታቸው [የሙዚቃ መምህር፣ አቀናባሪና ዘማሪ] ጋር ሄድኩኝ። ዳዊት ጌታቸው ሌላ ጊዜ መዝሙር ነው የሚሠራው፤ የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ ይህንን ለመሥራት ፈቃደኛ ሆነ። እናም አብረን ልነሠራው ቻልን። እኔም ሆንኩ ምድሪቱ ከነበርንበት ከዚያ ስሜት ውስጥ ተስፋ ይሆናል፤ መፅናኛ ይሆናል መልስ ይሆናል ብዬ ያሰብኩበትንና የተቀበልኩትን መልዕክት ለማድረስ ነው የተሠራው። ሙዚቀኛ ዳዊትን ስትጠቅሺው ከዚህ በፊት መዝሙር ነው ይሠራ የነበረው አልሽኝ። ይህ ሥራ መዝሙር አይደለም ብለሽ ነው የምታምኚው? ዘሪቱ፡ [ሳቅ] ነው፤ መንፈሳዊ ነው። የምልህ መነሻው መንፈሳዊ ነው። መነሻ የሆነኝም መጽሐፍ መንፈሳዊ ነው። 'ሠይፍ' የሚለውም ቃል የእግዚአብሔርን ቃል፣ የእግዚአብሔርን ኃይል፣ የእግዚአብሔርን ምላሽ መወከሉ መንፈሳዊ ነው። ሃይማኖታዊ ግን አይደለም። ያ ነው ልዩነቱ እንጂ መንፈሳዊ ነው። ከእነዚህ ሥራዎችሽ በኋላ ደግሞ 'ውሸታም' የሚለውን ሥራሽን ስታቀርቢ ዘሪቱ ዓለምን እየተጠየፈች ይሆን አልኩኝ? እውነት ዓለምን እየተጠየፍሽ ነው? ዘሪቱ፡ 'አርተፊሻል'፣ ከሁለቱ ዘፈኖች በተለየ በቀጥታ መንፈሳዊ አይደለም። ለምን? መነሻው ማኅበራዊ ትዝብት ነው እንጂ ከመንፈሳዊነት የመነጨ አይደለም። መንፈሳዊ አይደልም ማለት ግን አይቻልም። ለምን? እንድንሆን የሚመክረው፣ ወይም አልሆንም ብሎ የሚወቅሰው ማንነት፣ እንግዲህ እኔ የማምነው አምላክ፣ እንድንሆንለት ሽቶ በአምሳሉ ከፈጠረው ማንነት ውጪ ሆነናል ነው። ለምን? በዚያ ማንነት ውስጥ ያለ ሰው አካባቢውን ይጠብቃል፤ ከሰዎች ጋር አብሮ ይሆናል። በስስት የተያዘ አይሆንም፤ ስለዚህ ሆነናል የተባሉት ነገሮች ሁሉ ሰው ስንሆን ከታለመልን፣ እንድንሆን ከታሰበልን ውጪ ሆነናል፤ ስለሆነም እንደ መንፈሳዊ መልዕክት 'ኳሊፋይ' [ያሟላል] ያደርጋል ብዬ አስባለሁ። መነሻው ግን አይደለም። ሠይፍህን አንሳና ውሸታም ግን ከመንፈሳዊ ሕይወትና በቀጥታ ከመንፈሳዊ ማንነት ጋር የተገናኙ ናቸው ለእኔ። እና ዓለምን እየሸሽ ነው? ዘሪቱ፡ [ፈገግታ] ያው ከዓለም ወዴት ይኬዳል [ሳቅ] ዓለማዊ አለመሆን ግን ይቻላል። የዓለም ውሸት፣ የዓለም ሽንገላ፣ ባታለለኝ ወቅት የጻፍኩት ነው። ባለማወቅ የምንሆናቸው ነገሮች አሉ። ካወቅን በኋላ ደግሞ ከእኛ የተሻለ ሲጠበቅ፣ መንገድ አሳይ መሆን ሲጠበቅብን፣ በተላላነት ተይዘን [ፈገግታ] እንደተሞኘን ሲገባን [ፈገግታ] ተመልሰን የማውቀውን! ይሄንን? ምን ነካኝ? ብለን የዓለምንና የገዢዋን ሽንገላ ለማጋለጥና ከዚህ በኋላ አንስትም የሚለውን [ሳቅ] መልዕክት ለማስተላለፍ ነው። • በፕሮቴስታንት እምነት ተከታይነቱ ለእስር ተዳርጎ የነበረው ኤርትራዊ ህይወቱ አለፈ [ያዘዘችው ጠቆር ያለ ማኪያቶ መጥቶ ጭውውታችንን ለአፍታ አቋረጥን. . . ] በስምሽ ከተሰየመው አልበምሽ ሌላ ባሉት ከእነዚህ ሦስት ስራዎችሽ ውጪ፣ 'አዝማሪ ነኝ' የሚውም ሥራሽን ስንመለከት በሥራዎችሽ የሕይወት አቋምሽን እየተናገርሽና እያስቀመጥሽ ነው የምትሄጂው ማለት እንችላለን? ዘሪቱ፡ ልክ ነው፤ እንደዚያ ነው። የመጀመሪያው ሥራዬ [ዘሪቱ አልበም] በወቅቱ የነበረኝ ማንነት ነው። በማንነቴ ሳድግ፣ መንፈሳዊነት በውስጤ ማደግ ሲጀምር፣ በዚያ መንገድ እያደግሁ ስመጣ ወይንም ደግሞ በዚያ መንገድ መጓዝ ስጀምር፤ ያው ያንኑ የሚመስል ነገር ነው የሚወጣኝ። ስለዚህ ከአሁን በኋላም ሕይወቴን የሚመስል፣ ያለሁበትን ቦታ የሚመስል ሥራ ነው ከእኔ የሚወጣው። ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ስለዚህ ከአሁን በኋላ እየሠራሽ የምትቀጥይው የሕይወቴ መርሆዎች ናቸው የምትያቸውን ብቻ ነው ማለት ነው? ዘሪቱ፡ በፊትም እንደዛ ነው። [ሳቅ] ምንም አዲስ ነገር አይደለም። ለምን? እውነት ለኔ፣ ከመጀመሪያውም ቢሆን ጽሁፍም ሆነ ሙዚቃ፣ እውነትና ራሴን፣ ሕይወቴን፣ ታሪኬንና 'ኤክስፒሪያንሴን' [ልምምዴን] ከማካፈል ጋር የተገናኘ ነው። ስለዚህ ማንነቴ በሚሄድበት አቅጣጫ፣ ሥራዬም እየተከተለ ይሄዳል። ለምን? የሙዚቃ ስራን በሌላ መንገድ አላውቀውም። ወይንም በሌላ መንገድ ላበረክት የምችለውን፤ በጽሑፍም ሆነ በፊልም ሥራም ይሁን የማምንበትንና የሚመስለኝን፣ ለሰው ይጠቅማል ብዬ የማስበውን ወይንም መወከል አለበት ብዬ የማስበውን ማኅበረሰብ፤ ሆን ብዬና መርጬ ነው የማደርገው። እንጂ በዚህ አቅጣጫ የሆነ ነገር ቢፃፍ ገበያ ላይ የሆነ ነገር ያመጣል፣ ወይም ለኔ የሆነ ክብር ይጨምራል በሚል አይደለም። ስለዚህ ከሕይወቴ በማካፈል ነው የምቀጥለው። መርሄንም ይሁን፣ 'ኤክስፒሪያንሴንም' ይሁን፣ አስቂኝ ገጠመኝም ይሁን፣ ጥበብ ስለሆነ ሁሉንም ሳጥን ሰርተን አናስቀምጠውም። አንዳንዱ ሥራ በማንጠብቀው ሁኔታ ይመጣል። አልበምሽ ውስጥ የማይረሱ አገላለጾች እና የቋንቋ አጠቃቀሞች አያለሁ። አሁን የምናወራባቸው ሥራዎች ላይ ግጥሞቹን ብንመለከት ጠንካራ ናቸው። ግጥምና ዜማ ላይ በጎ ተጽዕኖያሳረፈብሽ ባለሙያ አለ? ዘሪቱ፡ እ. . . ማንንም ሳላይ ነው መጻፍ የጀመርኩት። መጻፍ የጀመርኩት ከልጅነቴ ስለሆነ። በልጅነት ውስጥ ዝም ብዬ በዜማም ይሁን በግጥም ራሴን መግለጽ የጀመርኩት በተገኙ ርዕሰ ጉዳዮች ሁሉ ነው። በመጀመሪያ ወደ ሙዚቃ ለመሳቤ እነሴሊንዲዮን፣ ማሪያ ኬሪ፣ ዊትኒ ሂውስተን ምክንያት ናቸው። ወደ የሙዚቃ ግጥም አጻጻፍ ስንመጣ ትሬሲ ቻፕማን፣ ቦብ ማርሌና አላኒስ ሞርሴት መነሻዎቼ ናቸው። እነዚህ ሦስት አርቲስቶች ለዘፈን ጽሁፍ ወይም ደግሞ በዘፈን ውስጥ ለሚነገሩ መልእክቶች መነሻዬ ናቸው። አንድን ሰው፣ አንድን አርቲስት ያገኘሁት ያህል፤ 'አይደንቲቲውን' [ማንነቱን]፣ መልዕክቱን፣ ጉዞውን፣ ከለሩን፣ ከልጅነቴ ጀምሮ እንዳጣጥም እና እንዲገባኝ አድርገዋል። በተለይ አላኒስ ሞርሴት እኔ የምሞክራቸው ነገሮች 'ሴንስ' [ትርጉም] እንዲሰጡ ያደረገች አርቲስት ናት። እና እነዚህ ናቸው የመጀመሪያዎቹ [ተጽዕኗቸውን ያሳረፉብኝ]! ከዚያ በኋላስ? ዘሪቱ፡ ከዚያ በኋላ በራሴ መንገድ ነው የሄድኩት። ግጥሞችሽን አይተው 'እነዚህ ለዘፈን አይሆንም' ያሉ ነበሩ? ዘሪቱ፡ እ. . . [ትንሽ አሰብ አድርጋ] አይ እንደዚያ ሳይሆን፣ እንደውም በመጀመሪያዎቹ ስቱዲዮ ውስጥ በነበርኩባቸው ጊዜያት . . . በጣም ቀላል ናቸው። ጠንከር ያለ የአማርኛ ግጥም መልክ የላቸውምና አይሆኑም ወይም አያስኬዱም የሚሉኝ ብዙ ሰዎች ነበሩ። ስላልሰሟኋቸው እግዚአብሔር ይመስገን ። [ረዥም ሳቅ]። ግን ኤሊያስ በተለየ መልኩ 'ኢንካሬጅ' [ያበረታኝ] ያደርገኝ ነበር። አቀናባሪ ኤሊያስ መልካ? ዘሪቱ፡ አዎ ኤሊያስ መልካ። እንደውም እንደዚህም ይቻላል ለካ። እንደዚህ ነው መሆን ያለበት። ቀላል ሆኖ፣ ከዜማ ጋር ተዋህዶ፣ ሰው 'ኢንጆይ' እንዲያደርገው [ዘና እንዲልበት] ብሎ 'ኢንከሬጅ' አድርጎኛል [አበረታቶኛል]። በመጀመሪያዎቹ ጊዜያት። ኤሊያስን ካነሳን አይቀር፣ ኤሊያስ አለ፣ በሕይወት የሌለው እዮብ አለ፤ ሌሎችም አሁን ስማቸውን ያልጠቀስኳቸው [በእናንተ ክበብ ውስጥ ያሉ] የሙዚቃ ባለሙያዎች አሉ። እነዚህን የሙዚቃ ሙያተኞች ስናይ፤ የዘመንሽን ሙዚቀኞች በሥራዎቼ በሚገባ ወክያለሁ፣ ገልጫቸዋለሁ ብለሽ ታስቢያለሽ? ዘሪቱ፡ [በረዥሙ ተንፍሳ] እ. . . እኔ በጣም ግለሰባዊ ነኝ መሰለኝ። [ሳቅ] የሆነን ወገን መወከሌ አይቀርም። ግን ከምንም በላይ እውነትን እና የራሴን ጉዞ እንደወከልኩ፤ በዚያ ውስጥ ደግሞ ብዙዎች የሚወዱህ ሰዎች በሆነ ያህል እንደተወከሉ የሚያስቡ ይመስለኛል። ስለዚህ እነርሱንም የወከልኩና ያሰማሁ ይመስለኛል። ለምንድን ነው እንደዚያ ያልኩት፤ በወንጌላውያን አማኝ ሙዚቀኞች ዘንድ የጦፈ ክርክር ነበር። ሙዚቃና ሙዚቀኝነትን፣ዓለማዊነትንና መንፈሳዊነትን በተመለከተ። በኋላም የዮናስ ጎርፌ 'ቤት ያጣው ቤተኛ' የተሰኘ መጽሐፍ ታትሞ ተነቧል። ይህ የሚያሳየን ከወንጌላዊያን አማኞች የተገኙ ሙዚቀኞች፣ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ያላቸውን ስፍራ ለማፅናት፣ እዚህ ጋር ነው ስፍራችን ማለትን ያየሁ ስለመሰለኝ ነው። በዚያ ወቅት ደግሞ አንቺ ሥራዎችሽን በዚህ መልክ ስታቀርቢ እነዚህን ወገኖች ወክላ ይሆን የሚል ጥያቄ አድሮብኝ ነው? ዘሪቱ፡ [ከረዥም ዝምታ እና ማሰብ በኋላ]. . . ብዬ አምናለሁ። ተወክለው ከሆነ እነርሱ ያውቃሉ ይመስለኛል። የአንድ መንፈሳዊ ሰው ሕይወት እኮ አይከፋፈልም። አንድ ሰው መንፈሳዊ ነኝ ካለ በማንኛውም ጊዜ በዚያ ማንነት ውስጥ ነው ሊሆን የሚገባው። በጨዋታም ጊዜ፣ በሥራም ጊዜ፣ በፀሎትም ጊዜ፣ በሁሉም ጊዜ በመንፈሳዊ ማንነት ውስጥ ነው መቆየት ያለበት። ያ መንፈሳዊ ማንነት ደግሞ የሆነ ኃይማኖታዊ መልክ አይደለም። መልካምነት፣ ፍቅር፣ ርህራሄ፣ ሰላም፣ በጎ የሆነ ነገር ሁሉ መንፈሳዊ ነው ብሎ መደምደም ባይሆንም፤ ምክንያቱም ማስመሰልም ስላለ። ግን ሥራዬ መንፈሳዊ ካልሆነ፣ ወይ ከመንፈሳዊነት የሚያጎለኝ ከሆነ፣ ከመንፈሳዊነት የሚጋጭ ከሆነ፣ ባላደርገው ነው የሚመረጠው። ስለዚህ እንደማይጋጭ እያመንኩ ነው እያደረኩት ያለሁት። ዘሪቱ ራሷን ከሙዚቃ ውጪ በምን በምን ትገልፃለች? ዘሪቱ፡ ፋሽን ደስ ይለኛል። 'ስታይል' መቀየር ያዝናናኛል። ልንዝናናም ደግሞ ይገባናል። ቁም ነገር የሆኑት ነገሮች እንዳሉ ሆነው፣ በምድር ላይ እስካለን ድረስ የሚያዝናኑን ነገሮች አሉ። ጉዳት የለውም። ስለዚህ በእርሱም ራሴን 'ኤክስፕረስ' አደርጋለሁ [እገልጻለሁ]። በተሰማኝ ጊዜ። ሙሉ በሙሉ በእዚያ ማንነት ውስጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። ዝም ብዬ ስዘንጥ የምኖር ሰው አይደለሁም። [ሳቅ] ዘናጭ አይደለሁም። የሙሉ ጊዜ ዘናጭ [ረዥም ሳቅ]. . . ልክ አሁን ስንገናኝ እንደለበስሽው ቀለል ያለ አለባበስ፣ ጅንስ ሱሪ፣ በሸራ ጫማ በጃኬት? ዘሪቱ፡ አዎ . . . ብዙ መታየትም አልወድም። ግን አንዳንዴ ደግሞ ያኛውም ጎን አለኝ። ለወጥ ብሎ፣ ተጫውቶ. . . እንደጨዋታ ነው የማየው። መለስ ብሎ ደግሞ ወደ ተረጋጋው የዘወትር መልኬ [ሳቅ] በእሱ እጫወታለሁ። ባለኝ በሚያስደስተኝ ሁሉ ራሴን 'ኤክስፕረስ' አድርጌ [ገልጬ] ሰዎችን ፈገግ አድርጌ፣ አዝናንቼ፣ አካፍዬ ማለፍ ነው የምፈልገው። ትርፍጊዜሽን በምን ማሳለፍ ነው ደስ የሚልሽ? ዘሪቱ፡ የሚያስደስተኝ ነገር ወይ ከሥራዬ ጋር የተያያዘ ነው ወይ ከቤተሰቤ ጋር የተያያዘ ነው። ስለዚህ ትርፍ ጊዜ ቢኖረኝም ያንኑ የሚያስደስተኝን ነገር አደርጋለሁ። ወይ አነባለሁ፣ ወይ አጠናለሁ፣ ወይ ከልጆቼ ጋር እሆናለሁ። ፊልም እመለከታለሁ። በሙዚቃ እዝናናለሁ። ትርፍ ጊዜዬም ሥራዬም ተመሳሳይ ነው። ይዘቱ ከቤተሰቤ ራቅ ያለ ነገር አይደለም። በአጠቃላይ ትርፍ ጊዜ ነው ያለኝ ማለት ነው። [ሳቅ] ድምጻዊት ዘሪቱ ከበደ ከሦስት ልጆቿ ጋር ለሁለተኛአልበምሽመዘግየት ምክንያት የሆነውእናት መሆንሽ ነው? ዘሪቱ፡ አይደለም። በፍፁም ምንም ግንኙነት የለውም። እንዲሁ የሕይወት ጉዞ፣ ዝግጁ አለመሆን፣ ከራስ ማንነት መሠራት፣ መስተካከል፣ ከዚያ ያንን መፈለግ፤ ከዚያ ትክክለኛው ለጥበብ ምቹ የሆነ 'ኢነርጂ' [ኃይል]፣ 'ፓርትነርሺፕ' [አጋር] አለመመቻቸት፣ ወይ ጊዜው አለመሆን፣ ያ ያ ነው። አብዛኛው ጊዜዬ በስራ ነው የሚያልፈው። ብዙ ሥራም እሠራለሁ። በፊልምም ብዙ ሠርቻለሁ። እናትነት በጣም 'ቢዚ' [ባተሌ] አድርጎኝ አይደለም። [እናትነት] ጊዜ ቢወስድም ሙዚቃን ለመሥራት ይኼን ሁሉ ዓመት የሚያስቸግር አልነበረም። ምክንያቱ እርሱ አይደለም። ስንት ፊልሞች ላይ ተሳተፍሽ? ዘሪቱ፡ ከ'ቀሚስ የለበስኩለት' በኋላ [ይህ የራሷ ድርሰት ነው]፣ የቅድስት ይልማ ሥራ የሆኑት 'መባ' እና 'ታዛ' ላይ በትወና ተሳትፌያለሁ። ከዚያ አሁን በቅርቡ የወጣ 'ወጣት በ97' የሚል ፊልም አለ። አሁን ደግሞ በቅርቡ የሚወጣ 'ስዊትነስ ኢን ዘ ቤሊ' የሚል የዘረሰናይ ብርሃኔ መሀሪ ፊልም አለ። እስካሁን እነዚህ ናቸው። ልክ እንደ ሙዚቃሽ በፊልሙም እኔ የምወክላት እንዲህ አይነት ገጸ ባህሪ መሆን አለባት ትያለሽ? ዘሪቱ፡ አዎ። እንደዚያ ባይሆን መሳተፌ አስፈላጊ አይደለም። የምትመስለኝን፣ ልትወከል ይገባታል ብዬ የማምነውን፣ ብትታይ ይገባታል ብዬ የማምነውን ገፀ ባህሪ ወይም ላውቃት፣ መስያት ወይም ሆኛት፣ እርሷና አካባቢዋን ልወቅ ብዬ የመረጥኳትን ገፀ ባህሪ ወይንም ደግሞ ሊተላለፍ ይገባዋል የምለው መልእክት ካልሆነ በስተቀር ተሳትፎዬ ምንም ጥቅም የለውም። ስለዚህ እስካሁንም የተሠሩት ሁሉ እንደዚያ ናቸው። ከአሁን በኋላ ያንቺ ድርሰት የሆነ ፊልምእንጠብቅ ወይስ የሌሎች ሥራዎች ላይ ብቻ ነው የምትሳተፊው? ዘሪቱ፡ አስባለሁ። ግን ያው በመጀመሪያ የፊልም ሙከራዬ በጣም ብዙ ነገር ውስጥ ስለተሳተፍኩ ደከመኝ [ሳቅ]። ጥንካሬዬ በነበሩት ነገሮች በጣም ጠንካራ ነገር ባመጣም፤ ገና ያልተማርኳቸውና ያላወቅኳቸው 'ኤክስፒሪያንስ' [ልምድ] የሚያስፈልጉኝ ነገሮች ነበሩ። ስለዚህ እነርሱን ለማግኘትና ለመለማመድ ስል ነው በተለያዩ ሰዎች ፊልም ውስጥ ተሳታፊ የሆንኩት። ጥሩ ልምድ እንዳለኝ አምናለሁ። ሀሳቦች አሉኝ። እንደውም ከዚህ በኋላ የማስበው የራሴን 'አይዲያ' [ሀሳብ]፣ የራሴን መልዕክት ብሠራ ነው። ግን መልካም ሆኖ የሚያስደስትና የሚጠቅም ሥራ ከመጣ የሌሎችን ሰዎችም እሠራለሁ። 'ዘሪቱ' የተሰኘ አልበምሽ እንደወጣከነ ሄኖክ መሀሪ ጋርትልልቅየሙዚቃ ድግሶች አዘጋጃችሁ፤ 'ጉዞ ዘሪቱ' የተሰኘ።እንደዚህ አይነት ቋሚ የሆነ የሙዚቃ ኮንሰርት የማዘጋጀት ሀሳብ የለም? ዘሪቱ፡ አለ። ከአዲስ አበባ ወጥቶ በክልል ከተሞች ሥራዎችን ማቅረብ በጣም ነው የሚያስደስተኝ። ናፍቆት ስላለ ምላሹ በጣም አርኪ ነው። በመጀመሪያም ያደረግነው እርሱን ነው። መቼም የማይረሳን ጊዜና ታሪካዊ ልምድ ነው የሆነው። ከዚህ በኋላም ልናደርግ እናስባለን። ግን እንደሱ አይነቱን ነገር በሰፊው ለማድረግ ከአዲስ አልበም በኋላ ቢሆን የተሻለ እንደሚሆን በማመን [ሳቅ] ነው ያላደረግነው። ግን ባለንበት አካባቢ፣ በተመቻቸ ጊዜ ሁሉ እንጫወታለን። አዲስ አልበምሽ መቼ ይወጣል? ዘሪቱ፡ ፀልይልኝ። [ረዥም ሳቅ] እየተሰራ ነው ባለቀ ጊዜ. . . አልበምሽ ወጥቶ አንቺ ሥራዎችሽን በምታቀርቢበት ወቅት 'ያምቡሌ' በጣም ዝነኛ ነበር። ዝግጅትሽን በምታቀርቢበት ስፍራ ላይ በተፈጠረ ጉዳይ ስምሽ በተደጋጋሚ ተብጠልጥሎ ነበር። ያኔ የተፈጠረውምን ነበር? ዘሪቱ፡ ምንድነው የሆነው? ከተወራው የተለየ ነገር የሆነ አይመስለኝም። አሁን በደንብ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ውስጥ 'ዶሚኔት' [የተቆጣጠረው] ያደረገው 'ሳውንድ' [ድምፅ] ሲመጣ 'ያምቡሌ' ቀዳሚው ሥራ ነበረ። በሙዚቀኞች አካባቢ እንደ ጨዋታ እያደረግን ብዙ እናነሳው ነበረ። እኔ ደግሞ በዚያን ሰዓት ልሠራበት እየተዘጋጀሁ በነበረበት የፕላቲኒየም ክለብ፣ እየተዘጋጀሁበት የነበረው ሥራ 'ያምቡሌ'ን የማይመስል ወይንም ከኔም ሥራ ወጣ ያለ፣ ከ'ፖፑላር' ም ሥራ ወጣ ያለ፣ እንደ ጥበብ ሥራ ብቻ ልታጣጥመው የምትችል፣ ብዙ የተደከመበት፣ በጣም የተዋበ፣ አሁን ባለንበት ወቅት የተሻለ ተቀባይነት ያገኝ ነበር። እርሱን የሚመስሉ ብዙ ነገሮች አሉ። ሰው 'ኢንጆይ' ያደረጋቸው። ያኔ ግን እሱ ቅንጦትና ቅብጠት ነበር የሚመስለው እንጂ . . . • በፈረንጅ "ናይት ክለብ" ጉራግኛ ሲደለቅ በፒያኖ የታጀበ ማለትሽ ነው? ዘሪቱ፡ በፒያኖ ብቻ አይደለም። ፒያኖ፣ አፕ ራይት ቤዝም አለ። ፒያኖም አፕራይት ቤዝም ከሆነ ከዓመታት በኋላ ነው መድረክ ላይ የወጡት። በኢትዮጵያ 'ፖፑላር' ሙዚቃ ውስጥ ብዙ ጊዜ የማንሰማቸው መሣሪያዎች፣ ለስለስ ያለ፣ 'ሴትአፑ'ም ምኑም ወጣ ያለ ነበር። ያሰብነው ነገር በጣም እንደሚያምር ስላወቅን ምላሹን ለመቀበል ከበደን መሰለኝ። ያው በልጅነትና ባለማወቅ ውስጥ የተመልካቹ ጥፋት እንዳልሆነ [ለመረዳት አልቻልኩም ነበር]። በእርግጥ በትክክል 'ፕሮሞት' እንዳልተደረገ [እንዳልተዋወቀ] የተረዳሁት ቆይቼ ነው። ስለዚህ የመጡት ሰዎች ጥፋት አይደለም። በወቅቱ 'እንዴት ይሄ አይገባቸውም' በሚል ነው እንጂ፤ ቢያውቁና ቢጠብቁ የሚፈልጉት ሰዎች ይመጡ ነበር። እና በአንድ መንገድ ለጥበብ የተደረገ ትግል ስለሆነ ያቺን ልጅ እኮራባታለሁ። በሌላ ወገን ደግሞ ያለመብሰልና ያለማስተዋል ውጤት ነው። ለዛ ነው እንግዲህ 'ይሄ ካልገባችሁ እንግዲህ ያው 'ያምቡሌ' ይሁንላችሁ' ብላ ያለፈችው። 'ያቺኛዋ' ስትይኝ አሁን ያቺ የድሮዋ ዘሪቱ የለችም እያልሽኝ ነው? ዘሪቱ፡ መስዋዕትነት ነው እና ያቺኛዋን ዘሪቱም ነኝ። ግን [አሁን] እንደዛ የማደርግ አይመስለኝም። ማንን መቆጣት እንዳለብኝ የማውቅ ይመስለኛል። ሰሞኑን እያነበብሽ ያለሽው መጽሐፍ አለ? ካለ ምንድን ነው? ዘሪቱ፡ ኦ መጽሐፍ ነው፤ ይገርምሀል አንድ ጓደኛዬ ይህንን መጽሐፍ ሰጠኝና [በቀኟ በኩል ካስቀመጠችው ቦርሳዋን ከፍታ ከመጽሐፍ ቅዱስና ማስታወሻ ደብተሯ ጋር አብሮ ተቀምጦ የነበረ መጽሐፍ በማውጣት] 'ዘ ግሬተስት ፖወር ኢን ዘ ወርልድ' ይላል። የካትሪን ኩልማን መጽሐፍ ነው። እርሱን ነው እያነበበብኩ ያለሁት። አሁን እየተነበበ ያለው ይህ ነው። [ሳቅ] ሰሞኑን የምታደምጪውስ ሙዚቃ ምንድን ነው? ዘሪቱ፡ ሰሞኑን ምንድን ነው የማዳምጠው? [እንደማሰብ አለችና]. . . ብዙ መዝሙር እየሰማሁ ነው። ታሻ ኮምስ የምትባል ዘማሪ አለች። እርሷን በጣም [እየሰማሁ ነው]። ኢሊቬሸን ወርሺፕ እነርሱንም በጣም እሰማለሁ። አሁን የዘሩባቤል አልበም ወጥቷል። እርሱንም እየሰማሁ ነው። [ሳቅ]. . . ለአንቺ አዲስ ዓመት የሚሰጠው ስሜት ምንድን ነው? ዘሪቱ፡ አዲስ ዓመት ደስ ይለኛል። 'ኢንከሬጅመንት' [ማበረታታት]፣ ተስፋ፣ መለስ ብሎ 'ሪፍሌክት' አድርጎ [መለስ ብሎ መቃኘት]፣ ያለፈውን ዓመት ጉዞ፣ 'ፕሮግረስ' [ለውጥ]. . . ያው ሁሉም ነገር በዓመት ባይከፋፈልም፤ የሕይወት ጉዞን እንዲሁ ለማየት ግን ደስ ይላል። በአዲስ ተስፋ በደስታ የምቀበለው ጊዜ ነው። አንዳንዴ በዓመት ውስጥ ብዙ አዲስ ዓመቶች እናሳልፋለን። [ሳቅ] ሁሌ ዓመት አንጠብቅም። ግን 'ኢንጆይ' አደርገዋለሁ። ለአድናቂዎችሽ የአዲስ አመት መልዕክት አለሽ? ዘሪቱ፡ ሰላም ይሁኑ! ሰላም ይሁንላቸው! ይብዛላቸው! ከራሳቸው ጋር መሆን፣ ለሰው መሆን ይሁንላቸው! ደስታ ይብዛላቸው! ፍቅር ይብዛላቸው! የምትወጂው ጥቅስ የቱ ነው? ዘሪቱ፡ የምወደው ጥቅስ የቱ ነው? [አሰብ አድርጋ]. . . በሕይወቴ ውስጥ በጣም ብዙ ጥቅስ ከማስተናገዴ የተነሳ [ረዥም ሳቅ] አሁን አልከሰት አለኝ።
45192821
https://www.bbc.com/amharic/45192821
ሞ ሳላህ እያሽከረከረ ሞባይል ሲጠቀም የሚያሳየው ቪዲዮ ፖሊስ ጋር ደረሰ
የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ሞሃመድ ሳላህ ሞባይል ስልክ እየተጠቀመ ሲያሽከረክር የሚያሳይ ቪዲዮ ሊቨርፑል እጅ ከደረሰ በኋላ ክለቡ ለፖሊስ ጥቆማ አድርሷል።
የሊቨርፑል ፖሊስም በትዊተር ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ተንቀሳቃሽ ምስሉን መመልከቱንና የሚመለከተው ክፍል ጉዳዩን እያጣራ መሆኑን ገልጿል። የሊቨርፑል ክለብ ቃል አቀባይ እንዳሉት ክለቡ ለፖሊስ ጥቆማውን ከማድረሱ በፊት ከተጫዋቹ ጋር መነጋገሩን አሳውቋል። ቃል አቀባዩ ጨምረውም ተጫዋቹም ሆነ ክለቡ በዚህ ጉዳይ ላይ ተጨማሪ ነገር ማለት አይፈልጉም። • «ሳሸንፍ ጀርመናዊ ስሸነፍ ስደተኛ» ኦዚል • የሳምንቱ ምርጥ 11! በሳምንቱ የጋሬት ክሩክስ ቡድን ውስጥ እነማን ተካተዋል? • አፍሪካውያን በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት የተሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ ግብጻዊው ተጫዋች እያሽከረከረ ስልኩን ሲጠቀም ያሳያል።
news-55868492
https://www.bbc.com/amharic/news-55868492
ካሥማሰ፡ "ቅር የሚያሰኙ ጉዳዮች ስለነበሩ ክብር ለማስመለስ ነው የሠራሁት"
ካሥማሰ የመድረክ ስሙ ነው። እናት አባቱ ያወጡለት፣ መዝገብ የያዘው ስሙ ደግሙ ፍቅሩ ሰማ ይሰኛል። አዲስ 'ግማሽ አልበም' ለሙዚቃ አድማጮች አቅርቧል። ይህ ግማሽ የሙዚቃ ሰንዱቅ፣ ወይንም አልበም፣ ሰባት ሥራዎችን ይዟል። ካሥማሰ ሥራውን ያቀረበው በሂፕ ሆፕ የሙዚቃ ስልት ሲሆን በርከት ያሉት ሥራዎቹን ከቀደሙ ሥመ ጥር ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች ስራ ጋር አዋህዶ ሰርቷቸዋል።
ድምጻዊ ካሥማሰ እነዚህ ስራዎቹን በአንድ ያሰናዳበትን ሰንዱቅ፣ ማለዳ ብሎ የጠራው ሲሆን በነጻ ለአድማጮች እንዲደርስ መደረጉን ይናገራል። ማለዳ፣ ቀና ልብ፣ አንደኛ፣ ውበት፣ አመለወርቅ፣ ነገን ለትዝታ፣ ትናንቷን የተሰኙ ስራዎችን የያዘው ይህ አልበም ስለ አገር፣ ስለ አዲስ አበባ እንዲሁም ሌሎች ግዘፍ ሃሳቦችን አንስቶባቸዋል። ካሥማሰ በአገርኛ አንደበት ስላቀነቀናቸው ስራዎች ከቢቢሲ ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ! ቢቢሲ- ውልደትህና እድገትህ የት ነው? ካሥማሰ- የተወለድኩት አዲስ አበባ ውስጥ ነው። መገናኛ አካባቢ ነው ተወልጄ ያደግኩት። ከዚያም ቅዱስ ዮሴፍ ትምህርት ቤት ነው የተማርኩት። ከዚያም ወደ ንግድ ሥራ ኮሌጅ፣ ኮሜርስ ገባሁ። ማርኬቲንግ ነው የተማርኩት። ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ ጊዜዬን የሰጠሁት ለሙዚቃ ነው። ከኔ ጋር ሙዚቃውን ከሰራው፣ ካቀናበረው ይኩኖአምላክ ጋር አብረን ጥሩ ጊዜ አሳለፍን። ያው አብረውኝ የሚሰሩ ጓደኞችም ነበሩኝ በሰዓቱ። ውበት ላይ የተሳተፈ ልጅ አለ፤ ሰምተኸው ከሆነ። ለሶስት ነው የዘፈንነው ውበትን። ይኩኖ አምላክም ተሳትፎበታል፣ ሙዚቃውን ያቀናበረው ልጅ። ቢቢሲ- ተወልጄ ያደግኩት አዲስ አበባ ነው ብትለኝም ሥራዎችህ ላይ ግን ቤተ ክህነት ውስጥ ያደገ ሰው ድምጽ ይሰማል። ይህንን ያደረግከው ሆን ብለህ ነው? ካሥማሰ - የበፊት የሙዚቃ ሥራዎችን፤ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ሙዚቀኞች የሰሯቸውን ሙዚቃዎችን ነው የማዳምጠው። ከፕሮዲውሰሩም ጋር አብረን ስንሆን እንደዚህ አይነት የድሮ ሙዚቃዎችን ነው የምንሰማው። ከዚያ ውጪ ደግሞ አዲስ አበባ ስናድግ ከተለያየ ክፍለ ሃገር ብዙ ሰዎች ይመጣሉ እና የሁሉንም አንደበት መጋራት ችለናል ብዬ አስባለሁ። ከዚያም ደግሞ ቤተሰቦቼ በሚያወሩት በእነዚህ ሁሉ የተቃኘ ነው ብዬ የማስበው። ቢቢሲ- ስለዚህ ሆን ብለህ ሳይሆን ያደመጥካቸው ሙዚቃዎች ተጽዕኖ ሊሆን ይችላል ማለት ነው? ካሥማሰ- እንደዚያም ማለት እንችላለን። ሆን ብዬ ላደርገውም አስቤ አውቃለሁ። ሁሉም ሥራ ላይ ወጥ እንዲሆን ያደረግኩበት ምክንያት ወደ ነበረው ማንነት ለመመለስ ስለሆነ፤ ጥረቱ የኛንም አንደበት የእነርሱንም አንደበት በአንድ ላይ ብሌንድ በማድረግ፣ በማዋሃድ ነው የመጣሁት። ቢቢሲ- በአገራችን የሂፕ ሆፕ ሙዚቃ ባለመድነው መልኩ በግጥም ፍሰትም በመልዕክትም ደረጃ ጠንከር ያሉ ግጥሞች ስራዎችህ ውስጥ ይሰማል። ማን ነው የጻፋቸው? ካሥማሰ- ግጥሞቹን እኔው ነኝ የጻፍኳቸው ዜማዎቹን ጭምር። ሥራውን ከዛሬ አምስት ዓመት በፊት፣ ኮሜርስ ትምህርት ቤት እያለሁ ነው የጀመርኩት። የመጀመሪያ ዓመት ትምህርቴን ከጨረስኩ በኋላ ነው ወደዚህ ዓይነት ነገር ማዘንበል የጀመርኩት። ሃሳቦቹም የብዙ ዓመት ሃሳቦች ናቸው። በአንድ ላይ ጠርቀምቀም አድርጌ፣ ስለ አስተዳደጌም የነበረውን ለራሴ እንደ ቴራፒ ነበር የምሰራው። ከትምህርት ቤት ከወጣሁ በኋላ ግን ያው ሃሳቡ መተላለፍ አለበት፣ በእኛ በወጣቶች ሁኔታ ቅር የሚያሰኙ ጉዳዮች ስለነበሩ ክብር ለማስመለስ ነው የሰራሁት። እና ከእኛ ከወጣቶች የማይጠበቅ ሊመስል ይችላል ግን እንደምንችል ለማሳየት ነው። አንድ ሰው ይህንን ማድረግ ከቻለ ሌሎችስ ምን ይላሉ እንዲባል ነው። ቢቢሲ- ሥራዎቹን የሰራሃቸው ለራሴ እንደ ቴራፒ ነው ብለሀኛል፤ ከየትኛው ነገር ውስጥ ለመውጣት ነው እንደ ቴራፒ የተጠቀምክበት? ካሥማሰ- ቴራፒ ልል የቻልኩበት ምክንያት በልጅነቴ የሥዕል ፍላጎት ነበረኝ። በዚያን ጊዜ ግድግዳ ላይ የሚሳሉ ሥዕሎች ይስቡኝ ነበር። እናም ብዙ ጊዜዬን የማጠፋው ቃላቶችን በመሳል ነበር። ስለዚህ እነዚያን ስዕሎች አንድ ቃል ያለውን ትልቅ ሃሳብ በማየት፣ የፊደሎቹን ቅርጽ ሁኔታ በመገንዘብ፣ እያንዳንዶቹን ቃላት በምስልበት ጊዜ አንዱ ቃል ከሚገልፀው በላይ ሃሳብ አሉት። የእኛ አገር ቃላት ሲጠብቁ ሲላሉ፣ ስትበትናቸውም የተለያዩ ሃሳቦች ይይዛሉ። አንዱ ቃል ብቻ ከአንድ በላይ ሃሳብ የመጣ ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እነርሱን በማሰብ ለማጠናከር ሲባል፣ የምስላቸውንም ስዕሎች በደንብ ለመረዳት ስል ሃሳቦችን በመጨመር ቀስ እያልኩ ወደ ግጥሙ ገባሁኝ። ከሥራዬ ጋር ከአርቱ ጋር በአግባቡ ለመቀራረብ ስል ነው ይህንን የደረግኩት። ቴራፒም ያልኩት ለዚያ ነው። ቢቢሲ- ክብርን ማስመለስ የሚል ነገር አንስተሃል። ከማን ነው ክብርን የምታስመልሰው? ካሥማሰ- ክብር ማስመለስ ስል ደግሞ ሁልጊዜም ስለ ኢትዮጵያኖች ሲነገር፣ ሲዘከር፣ በድሮ በድሮ ነው። ስለ ድሮው እየተነሳ ነው ሃሳብ የሚሰጠው። ስለ ድሮው እየተነሳ ነው ይህች አገር ክብር የሚሰጣት። እኛስ የለንላትም እንዴ? እኛ አለን አይደል እንዴ? ሲባል ነው። ስለ ስምንተኛው ሺህ እና ስለ ወጣቶችብዙ ይባላል። ተስፋም ወኔም ለመቀስቀስ ብዬ ያደረኩት ነገር ነው። ወጣት ስለሆንኩኝ። ቢቢሲ -በቅንብር ውስጥ እነማን ተሳተፉ? ካሥማሰ- ሙዚቃውን ያቀናበረው ይኩኖአምላክ የሚባል ጓደኛዬ ነው። ሚክስና ማስተር ያደረገው ደግሞ ኬኒ አለን ነው። በርካታ ስራዎች ነበሩን፣ ግን ሃሳቡ ራሳችንን እንዴት እናስተዋውቅ በሚል ስለ ነበር በዚህ ዓመት ነው እንቅስቃሴውን የጀመርነው። ከመስከረም ጀምሮ አሁን እስካለንበት ጊዜ እስኪለቀቅ ድረስ ይህን ያህል ጊዜ ፈጅቷል። ቢቢሲ -ቅድም ግጥሙን ስትጽፍ ዜማውን ስታደራጅ አምስት ዓመት ፈጅቷል አልከኝ። ካሥማሰ- አይ እንደዚያ ማለቴ ሳይሆን ባለፉት አምስት ዓመታት ውስጥ ሥራው ውስጥ ስለነበርኩኝ ካሉት ለመምረጥ ነው ይኸኛው ጊዜ የፈጀው። ራስን ለማስተዋወቅ የትኛው ስራ ይቅደም በሚል። ቢቢሲ- ሰባት ሥራዎችን በአንድ ጊዜ ለአድማጮች አድርሰሃል፤ በነጻ። ካሥማሰ- አዎ ቢቢሲ- ለምን በነጻ መሥጠት ፈለግህ? ካሥማሰ- የሙዚቃ ስልቱ አዲስ ስለሆነ፣ እኛም በቶሎ አድማጮች ሃሳቡን እንዲይዙት ስለፈለግን፣ እንዲሁ ለማስተዋወቅ እንዲቻል፣ የተለያየ ሃሳብ ገልፀን ለእያንዳንዱ ሃሳብ ያለንን ምልከታ እንዲያዩት ስለፈለግን ነው። አንድ ሃሳብ ብቻ እንዳንሰጣቸው፤ ስለተለያዩ ሃሳቦች ጠቅለል አድርገን ማለዳ ነው፣ ጅማሬ ነው፣ በዚህ መልኩ ነው የጀመርነው ለማለት ነው። ቢቢሲ- ለዚያ ነው የሥብስቡን መጠሪያ ማለዳ ለማለት የወሰንከው? ካሥማሰ- ትክክል፤ እንዲሁም እንዳልኩህ ክብር ከማስመለስ ጋር፤ ማነው ባለእዳ አንደማለት ነው በሌላ አነጋገር። ማን ነው ለእዳ፣ ማለዳ፣ እዳው ለማን ነው ለማለት ነው። ቢቢሲ- ስለዚህ የክብር ማስመለሱ ጥያቄም እዚህ ተመልሶ ይመጣል? ካሥማሰ- አዎ ቢቢሲ- ባለ እዳ ነን ብለህ ታስባለህ? እናንተ ወጣቶች? ካሥማሰ- አዎ በደንብ አስባለሁ። ቢቢሲ- ማን ነው ማንን ባለ ዕዳ ያደረገው? ካሥማሰ- የድሮዎቹ ኢትዮጵያውያንን እንቀናባቸዋለን። እናደንቃቸዋለን። ሁሌም የተለየ ክብር ነው ያለን ለእነርሱ። ራሳችንን ከእነዚህ ከቀደምት ኢትዮጵያውያን ጋር ስናነጻጽር አንደራረስም ብለን ነው የምናስበው። እነርሱ ብቻ ናቸው ኢትዮጵያዊ የሚመስሉት። እኛ ከብዙ ከብዙ የተዳቀልን ነው የሚመስለው። እርሱ ነው አንዱ ሃሳብ። ቢቢሲ- ስለዚህ እኛም ኢትዮጵያዊ ነን ነው? ካሥማሰ- በትክክል ለማለት ነው። እንደውም አዲሶቹ ነን ለማለት ነው። ቢቢሲ- ሙሉ ስምህ ፍቅሩ ሰማ መሆኑን ሰምቻለሁ አንድ ቪዲዮህ ላይ። ካሥማሰ የሚለውን የመድረክ ስም የመረጥክበትን ምክንያት ምንድን ነው? ካሥማሰ- ካሥማሰ የተመረጠው ሁሉም ሰው የመድረክ ስም ቢኖረው ይሻላል፣ በመድረክ ስሙ ቢታወቅና ስራውንና የመደበኛ ሕይወቱን ለመለየት ያስችላል ብዬ ስላሰብኩነው። የመድረክ ስሜ ደግሞ ካሥፈለገ ነው፣ አዲስ ነገር ስለሆነ ካስፈለገ ይህንን አቅርበንላችኋል። የኛን ምልከታ የኛን አስተያየት ለማለት ነው። ካሥማሰ ማለት ካስፈለገ ማለት ነው። ቢቢሲ- ማለዳ የሙዚቃ ቪዲዮው እንደ ለመድናቸው የሙዚቃ ቪዲዮዎች ዓይነት አይደለም። የዚህ የሙዚቃ ቪዲዮ ሃሳብ አሁን በቀረበበት መልኩ እንዲደራጅ ያደረገው ማን ነው? ካሥማሰ፡ የሙዚቃ ቪዲዮውን ዳይሬክት ያደረገው ማራናታ ነው። አብረን ነው የምንሰራው። ሁለቱንም ሥራዎቼን የሰራቸው እርሱ ነው። ወደፊትም ከእርሱ ጋር አብሬ ነው የምሰራው ብዬ አስባለሁ። ከማራናታ ጋር ተመካክረን ነው ቀለል ብሎ ህዝብ ጋር እንዲደርስ፣ ጫና ሳይፈጥር ያለንበትን ሁኔታ ለማስረዳት ስለሆነ፣ ቀለል ብሎ እንዲቀርብ፣ ለዓይን እንዳይከብድ ብለን ስላሰብን ነው። ቢቢሲ- እንዲህ ዓይነት በርከት የሙዚቃ ቪዲዮዎች በብዛት የሉንም፤ ግርግር ያልበዛባቸው። ካሥማሰ- ይኖሩናል ግን ቢቢሲ፤ ባንተ በኩል ነው ወይስ በሌሎችም ማለትህ ነው? ካሥማሰ - እንግዲህ እየተመሳሰልን እንሄዳለን ብዬ ነው የማስበው። አዲስ ሃሳብ ሲመጣ ሁሉም ይጋራዋል ብዬ ነው የማስበው። ሃሳቦችን እየተጋራን ስለሆነ የምንሄደው እነርሱም አቋማችንን ይጋራሉ። እኛም ወይ የእነርሱንም አቋም እንጋራ ይሆናል። ቢቢሲ- ሳምፕል ስላደረግካቸው ስራዎች ደግሞ እናውራ። "Under African skies" ከሚለው የቢቢሲ ዶክመንተሪ ላይ ሳምፕል ወስደህ በሙዚቃህ ያካተትከው ለምንድን ነው? ካሥማሰ- ቪዲዮውን እኛ ስናየው በጣም የተለየ ስሜት ነው የሚሰጠን። እና ይኼ ሳምፕል ያደረግነው ንግግር የምሁራኖቹ ክርክር ነበር። እኛ በእነርሱ ዘመን ብንሆን ምን ልንል እንችላለን? ወይም ምን እናድርግ እንላለን? ብለን ነው ያሰብነው እና ከእነርሱ ንግግር ጀምረን ነው ማጣራት የጀመርነው። ንግግሩን ከሰማኸው በሰዓቱ ለዓለም ሙዚቃ ምን እናድርግ? ምን አስተዋጽኦ እናበርክት? የሚል ውይይት ነው የነበረው። ስለዚህ ያልተቋጨ ውይይት ነው ብለን ነው ያመንነው። ከዚያ በኋላ ውይይቱ በዚያው ነው የተቋጨው፤ ወደ ውሳኔ የተገባ አመልመሰለኝም። እኔ አይመስለኝም በግሌ። ስለዚህ እኛ የግላችንን ሃሳብ እንጨምርበት በሚል ነው። ሲያልቅ ከሰማኸው ስለ ብሬክ ዳንሲንግ እያወራ ነበር የጨረሰው። እና ብሬክ ዳንሲንግ እኛ ጋር የለም እንግዲህ በዚያን ጊዜ ስለ ብሬክ ዳንስ ማወራት ከቻሉ እኛስ አሁን ስለ ብሬክ ዳንስ እንዴት አላወራንም በሚል ነው መጀመሪያ ሃሳቡ የተጠነሰሰው። ስለዚህ እዚያ ላይ ሀሳብ ለማከል ብለን ነው። ቢቢሲ- 'ወርቃማው ዘመን' የሚባለው ዘመን ሙዚቀኞች፤ አለማየሁ እሸቴ፣ አስቴር አወቀ ለምን በሥራዎችህ ተካተቱ? በቀደመውና በአሁኑ ዘመን ድልድይ እየፈጠርኩ ነው ብለህ ታስባለህ? ካስማሰ- በትክክል ይህ ነው ሃሳቡ፤ አሁን ካሉት ሙዚቃዎች የበፊቱ ስራ የነበረው ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ከፍተኛ ነው ብለን ነው የምናስበው። እና እኛ እነዚህን ስራዎች ምን ያህል እንደምናከብራቸው እንዴት እንደምናያቸው እንዲመለከቱት ብለን ነው። እኛ እነርሱን እያየን ነው። ይህንን ሁሉ ብንሰራ ሃሳባችን እንዲደርሳቸው በማሰብ ነው። ቢቢሲ -ማለዳ የተሰኘው ስራህ ስለ አገር ነው። ውበት ደግሞ ስለአዲስ አበባ። ስለ አገር አንድነት፣ አንድ ሆኖ ወደፊት ስለመጓዝ በሙዚቃዎችህ ታነሳለህ፤ ለመሆኑ ኢትዮጵያን እንዴት ትገልጻታለህ? ስለ አንድነት ስታወራ ማየት የምትፈልገውስ ምን አይነት አገር ነው? ካሥማሰ- ቅድም እንዳልከው ድልድይ ለመሆን ነው። ድልድዩ መሰራት የሚችለው ደግሞ ትክክለኛ የሆነ የእውቀት ሽግግር ሲኖር ነው ብዬ አስባለሁ። ስለዚህ እኛ ከታላላቆቻችን ምርቃት መቀበል አለብን። ይኹን ሊሉን ይገባል። እነርሱም ሃሳባቸው፣ ሲመኙት የነበረው ያልተቋጨ ነገር ካላቸው ለእኛ ነግረውን እኛ የምናሳካው ይሆናል ማለት ነው። ልጆች ደግሞ እንዲወዱትና ለነገ ጥሩ ተስፋ እንዲይዙ ነው። ወደ ሌላ እንዳይሄዱ ወደራሳቸው እንዲመለሱ ለመተባበር ነው። ስለዚህ እኔ ድሮ እንደነበረው ስሟ እንዲገን፣ እንዲመለስ ነው የምፈልገው። ያኔ እኔም አብሬ ክብር ይሰጠኛል ብዬ ስለማስብ። ለአገራችን ክብር ሲሰጥ ለእኛም ክብር ይሰጣል ብዬ አስባለሁ። ቢቢሲ- ሂፕ ሆፕን ከኢትዮጵያ ሙዚቃ (በዋነኛነት እንተ ከመረጥከው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ስልት) ጋር የሚያስተሳስረው ነገር አለ? ካሥማሰ- ሂፕ ሆፕ እኛ አስተዳደግ ላይ የተሻለ ተጽዕኖ አድርጎ ነበር። ስለዚህ ብዙዎች ወጣቶች ከዚሁ ጨዋታ ጋር ስለሆነ የተያያዙት፣ እኛም እዚሁ ጨዋታ ላይ ስለሆነ ያለነው እኛ ለየት እናድርገው እስቲ፣ እኛ ወደ ራሳችን እንመለስ በግላችን እንሞክረው የሚል ነገር ነው ያለኝ። ቢቢሲ- የማን ተጽዕኖ አለብህ ከአገር ውስጥና ከውጪ? ካሥማሰ- ከባድ ጥያቄ ነው. . . አንድ ስራ ልጥራ ብል ከውጪ ቦብ ማርሌ ከአገር ውስጥ ደግሞ የሙላቱ አስታጥቄን ሰራዎች በጣም ነው የምሰማቸው። ቢቢሲ- ግማሽ አልበም ማለት በእንጀራ ቢታሰብ እንጎቻ እንደማለት ነው። ሙሉውን መቼ እንጠብቅ? ካሥማሰ- (ሳቅ) በዚህ ቀን ማለት ባልችልም ከወራቶች በኋላ ይደርሳል ብዬ አስባለሁ።
42800322
https://www.bbc.com/amharic/42800322
ኬንያ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው
በናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ኢንጂነሮች ከአንድ የጃፓን የምርምር ተቋም ባገኙት ድጋፍ ከአንድ ሚሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ወጪ ሳተላይት ገንብተዋል።
ይህ ሳተላይት የግብርና ሥራን ለመከታተልና የኬንያን የባህር ጠረፍ ለመቆጣጠር ተግባር ጥቅም ላይ ይውላል ተብሏል። ጃፓን ለሳተላይቱ ግንባታ የሚያስፈልገውን ወጪ የሰፈነች ቢሆንም ግንባታውን ያከናወኑት ኬንያዊያን ባለሙያዎች ናቸው። ሳተላይቱ በመጪው መጋቢት ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ የሚመጥቅ ሲሆን ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ ሥራውን እንዲጀምር ይደረጋል። ይህም በአፍሪካ ሳተላይት ወደ ህዋ ካመጠቁ ስድስት ሃገራት መካከል ኬንያን ያሰልፋታል። ይህን ሳተላይት የገነባው የናይሮቢ ዩኒቨርሲቲቀወ ቡድን፤ በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት የሚገኙ የትምህርት ተቋማት የራሳቸውን ሳተላይት እንዲገነቡ ለማገዝ በተባበሩት መንግሥታትና በጃፓን መንግሥት ከተጀመረው ፕሮጀክት ተጠቃሚ ለመሆን የመጀመሪያው ነው።
news-56622887
https://www.bbc.com/amharic/news-56622887
የምርጫ ቦርድ ውሳኔን በመቃወም ክስ የመሰረቱ ፓርቲዎች ምን ተወሰነላቸው?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተገቢውን መስፈርት አላሟሉም በማለት ከሰረዛቸው ፓርቲዎች መካከል በሁለቱ ላይ የተላለፈው ውሳኔ እንዲነሳ ፍርድ ቤት ወሰነ።
ቦርዱን ውሳኔን በመቃወም ጉዳዩን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ካመለከቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት እና የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር ምርጫ ቦርድ እንዲሰረዙ ያስተላለፈውን ውሳኔ መሻሩን ገልፀዋል። ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 13 ቀን 2013 ዓ.ም ከ35 በመቶ በታች የሆኑ ትክክለኛ ፊርማ ያመጡ እና የተለያዩ በቦርዱ የተጠየቁትን መስፈርት ያላሟሉ ፓርቲዎች በማለት ከሰረዛቸው 26 ፓርቲዎች መካከል የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት እና የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር ይገኙበታል። እነዚህ ፓርቲዎች ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳይ ችሎት ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት፣ ችሎቱ ፓርቲዎቹ እንዲሰረዙ ተወስኖ የነበረው በፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ምርጫ ሥነ ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 9 (4) መሰረት መሻሩን አስታውቋል። ችሎቱ አክሎም ምርጫ ቦርድ ፓርቲዎቹን ለመሰረዝ ምክንያት ባደረገው ጉዳይ ላይ ፓርቲዎቹ መከላከያቸውን አቅርበው ምርጫ ቦርድ የመጨረሻ ውሳኔውን እንደሚያሳውቅ ገልጿል። በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልተው የተመዘገቡ እና ፈቃዳቸው የታደሰላቸው 33 ክልላዊ ፓርቲዎችና 20 አገር አቀፍ ፓርቲዎች ናቸው። ከእነዚህ መካከል በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የምርጫ ጉዳይ ሁለተኛ ችሎት ጥር 16/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት መሰረት የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር እንዲሰረዝ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ ውድቅ ከማድረጉ በተጨማሪ፤ ፓርቲው መጀመሪያ የተሰረዘበት የመስራች አባላት ፊርማ አለማሟላት ጉዳይ ላይ መከላከያውን ካቀረበ በኋላ ቦርዱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ሰጥቷል። በተመሳሳይ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ለፍርድ ቤት ያቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አግኝቶ የምርጫ ቦርድ ውሳኔን እየጠበቀ መሆኑን ፓርቲው ለቢቢሲ ተናግሯል። የኦሮሞ ነፃነት አንድነት ግንባር - የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 4 በመቶ ያገኘ መሆኑ በወቅቱ በምርጫ ቦርድ የተገለፀ ሲሆን፤ የመስራች ፊርማ ናሙና ማረጋገጫ ከ35 በመቶ በታች በመሆኑ እና የ1,142 መሥራች አባላት የነዋሪነት ማረጋገጫ አይነት ስላልተሟላ መሰረዙ ተገልፆ ነበር። የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ሕብረት ደግሞ የመሥራች አባላት ናሙናን አስመልክቶ በተደረገው ማጣሪያ 18 በመቶ ማግኘቱ በወቅቱ ይፋ የሆነው መረጃ ያሳያል። የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ምን ነበር? የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ታኅሣሥ 13/2013 ዓ.ም የመስራቾችን ፊርማ ማጣራት አካሂዶ 26 የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሰረዙን አስታውቆ ነበር። ከተሰረዙት የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል አንዱ የሆነው እና ዘንድሮ በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ በኦሮሚያ ክልል ለመወዳደር በዝግጅት ላይ የነበረው የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር ፓርቲ ይገኝበታል። የፓርቲው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ኡመር መሐመድ ለቢቢሲ "ከ400 ሺህ በላይ ሰዎችን ፊርማ በማሰባሰብ በተባለው ጊዜ አስገብተን ነበር" ሲሉ ተናግረዋል። "ከዚያም በኋላ በምርጫ ላይ ለመሳተፍ በዝግጅት ላይ እያለን ድርጅታችሁ ተሰርዟል ተባልን" በማለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ውሳኔን ገልፀዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ላይ ታኅሣሥ 13/2013 ዓ.ም ባሰፈረው መግለጫ መሰረት በፓርቲው አባላት የፊርማ ናሙና ላይ ባደረገው ማጣራት 4 በመቶው ብቻ ትክክል መሆኑን ገልጾ ነበር። አቶ ኡመር በበኩላቸው "ምርጫ ቦርድ ይህን ውሳኔ ዳግም እንዲያየው ብንጠይቅም መልስ አላገኘንም" ያሉት ሊቀመንበሩ "ግልባጭ እንዲሰጠን ብንጠይቅ አልተሰጠንም፤ ከዚያ በኋላ በተጻፈልን ደብዳቤ ብቻ ነው ፍርድ ቤት ጥያቄያችንን ያቀረብነው" ብለዋል። የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ሕብረት ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ሱልጣን ቃሲም በበኩላቸው "በጋራ በመሆን አቤቱታ አቅርበን [ለፍርድ ቤቱ] የነበርን የኦሮሞ ፓርቲዎች ስድስት ነበርን፤ ይሁን እንጂ ለብቻ ለብቻ አቅርቡ ስለተባልን በግል አቅርበናል" ይላሉ። በፓለቲካ ፓርቲ ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ ሥርዓት ድንጋጌ 1162/2011 አንቀጽ 94/4 ላይ በተቀመጠው መሰረት አንድ የፖለቲካ ፓርቲ በተለያየ ምክንያቶች በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተሰረዘ እና በመሰረዙ ላይ ቅሬታ ካለው የቦርዱ ውሳኔ ፓርቲው ከደረሰው በኋላ በ30 ቀናት ውስጥ አቤቱታውን ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ማቅረብ ይችላል ሲል ይገልጻል። ከዚህም በተጨማሪ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ከመሰረዙ በፊት ፓርቲዎች እንዲከላከሉ እድል መስጠት እንዳለበትም ይደነግጋል። ይኹን እንጂ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲከላከሉ እድል ሳይሰጣቸው መሰረዙን የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ኡመር መሐመድ ይገልጻሉ። የምርጫ ቦርድ ውሳኔን አስመልከተው ሲናገሩ፣ ፓርቲያቸው የሕግ ሂደትን አላሟላም መባሉን በተለይም፣ "የመስራች አባላት ፊርማ አላሟላም፤ አጣርተን ይህንኑ ስላረጋገጥን ከምዝገባ ሂደት ላይ ሰርዘናችኋል የሚል ውሳኔ ተላልፏል" መባላቸውን ይገልጻሉ። "ይህ ውሳኔ መስተካከል አለበት ብለን ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ ብናቀርብም መልስ አልተሰጠንም። ከዚያ በኋላ ነው ወደ ፍርድ ቤት የሄድነው" የሚሉት ደግሞ የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ሕብረት ሊቀመንበር አቶ ሱልጣን ቃሲም ናቸው። እነዚህ ሁለቱ ፓርቲዎች ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባስተላለፈው ውሳኔ ላይ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ፓርቲዎቹ እንዲሰረዙ ቦርዱ ያስተላለፈው ውሳኔ ውድቅ እንዲሆን ተደርጓል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ የምርጫ ጉዳይ ችሎት ጥር 16/2013 ዓ.ም በዋለው ችሎት መሰረት የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር እንዲሰረዝ ምርጫ ቦርድ ያስተላለፈውን ውሳኔ ውድቅ ከማድረጉ በተጨማሪ ፓርቲው መጀመሪያ የተሰረዘበት ምክንያት የመስራች አባላት ፊርማ ጉዳይ ላይ መከላከያውን ካቀረበ በኋላ ቦርዱ ውሳኔ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ሰጥቷል። ፓርቲዎቹ በምርጫ ይሳተፉ ይሆን? ፓርቲያቸው ላይ "ከሕግ ውጪ ተፅዕኖ ገጥሞናል" የሚሉት የኦሮሞ ነጻነት አንድነት ግንባር መሪ አቶ ዑመር መሐመድ ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ በቀሩት ሁለት ወራት ውስጥ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል። "ለምርጫ ቦርድ የፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭና ማመልከቻ አስገብተናል፤ ከምርጫ ሂደት ወደ ኋላ ስለቀረን ሁኔታዎችን አመቻችተውልን ወደ ምርጫ ለመግባት ፍላጎት ስላለን በፍጥነት ውሳኔ እንዲሰጡን አቤቱታ አቅርበናል" በማለት የምርጫ ቦርድ ውሳኔን እየተጠባበቁ መሆኑን ይናገራሉ። አቤቱታቸውንም ለምርጫ ቦርድ ካስገቡ አንድ ሳምነት እንደሆናቸውም ጨምረው ተናግረዋል። በሌላ በኩል የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ሕብረት ሊቀመንበር አቶ ሱልጣን ቃሲም የምዝገባቸው ሂደት እንዲጠናቀቅ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ይናገራሉ። "በአሁኑ ሰዓት እንደ ቁልፍ ነገር አድርገን እየሰራን ያለነው ፈቃዳችንን ማግኘት ነው፤ ተመዝግበን ሕጋዊነታችን ከተረጋገጠ በኋላ ምርጫ ላይ መሳተፍ እና አለመሳተፋችንን ከአባላቶቻችን ጋር ተነጋግረን የምንወስነው ይሆናል" ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ተኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ዕጩዎችን መዝግቦ ማጠናቀቁን መግለፁ ይታወሳል። በዚህም መሰረት 47 ፓርቲዎች ዕጩዎቻቸውን ሲያስመዘግቡ፣ በግል ለመወዳደር ደግሞ 125 ዕጩዎች መመዝገባቸውን ቦርዱ ይፋ ያደረገው መረጃ ኣሳያል። ዕጩዎቻቸውን ካስመዘገቡ ፓርቲዎች መካከል አርባ አንዱ ፌደራልና ለክልል ምክር ቤቶች የሚወዳደሩ ሲሆን አራቱ ለክልል ምክር ቤት እንዲሁም የቀሩት ሁለት ፓርቲዎች ደግሞ ለተወካዮች ምክር ቤት ብቻ የሚወዳደሩ ናቸው።
news-45418415
https://www.bbc.com/amharic/news-45418415
አምሳለ ዋካንዳ በጢስ አባይ ይገነባ ይሆን?
በብላክ ፓንተር ፊልም ላይ በምናብ የተሳለው ዋካንዳ ከተማ በኢትዮጵያ በዕውን ሊሰራ መሆኑ ከተገለፀ አንስቶ የበርካቶች መነጋጋሪያ ሆኗል።
በብላክ ፓንተር ፊልም ላይ በምናብ የተሳለው ከተማ ገፅታ ከተማው በአንድ በኩል የአፍሪካውያን የባህልና የታሪክ ማንነት መገለጫዎች የሚሰባበሰቡበት ፣ በሌላ በኩል በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምርምር የሚካሔድበት፣ ሮቦቶች የሚርመሰመሱበት፣ ሮኬት የሚመጥቅበት ፣ በሌላኛው ገፅ የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት እና የሚከናወንበት የኢንዱስትሪ ክፍለ ከተማ፤ የሚገማሸረውን የአባይ ፏፏቴንና ሸንተረሮቹን ጠዋት ማታ አሻግሮ ለማየት በሚያመች መልኩ ይገነባል ተብሏል። ይሁን እንጂ ዕቅዱን ቅዠት ነው፤የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያላጋናዘበ ነው ሲሉ ያጣጣሉትም አልታጡም። ፕሮጀክቱ ሀብ ሲቲ ላይቭ በሚባል ፕሮጀክት ስም በፊልሙ ላይ የሚታየውን የምናብ ከተማ በእውነት ለመገንባት ታቅዷል። "ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች መኖሪያ፣ የቀደመ ስልጣኔ ምንጭና መገኛ ቦታ ነች፤ ስለዚህ ምንጩ ላይ በአጠቃላይ በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች የሚጋሩትንና በቴክኖሎጂም በባህልም የበለፀገ ከተማ እንገንባ የሚል ሃሳብ ያለው ነው" ይላሉ በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን። ሀብ ሲቲ ላይቭ የቴክኖሎጂ ከተማውን ዋካንዳን ካሊፎርኒያ ውስጥ ለመገንባት የቀደመ ሃሳብ ቢኖረውም፤ እውነተኛ ዋካንዳ ግን አፍሪካ ለዚያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው መሆን ያለበት በሚል በደቡብ ፣ በኦሮሚያ እንዲሁም በባህርዳር የሚገኙ ቦታዎችን ሲያስስ መቆየቱን የሚናገሩት ደግሞ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ የሆኑት ዶክተር ሹመቴ ግዛው ናቸው። በመጨረሻም በአማራ ክልል የሚገኘው ጢስ አባይ በፊልሙ በምናብ ከተሳለው የቴክኖሎጂ ከተማው (ዋካንዳ) ጋር ተመሳስሎ በማግኘታቸው የክልሉን መንግስት ጋር ንግግር እንደተጀመረ ይገልፃሉ። ከክልሉ መንግስት ይሁንታ ከተገኘ በኋላ ሃሳቡ የቴክኖሎጂ ከተማን መገንባት በመሆኑ ድርጅቱ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር መወያየት እንደጀመረ ዶክተር ሹመቴ ይናገራሉ። ጢስ ዓባይ ላይ ይገነባል የተባለው የቴክኖሎጂ ከተማ ገፅታ ፕሮጀክቱ ቴክኖሎጂን ከማሳደግ፣ቱሪዝምን ከማስፋፋት፣ ኢንቨስትመንትን ከማበረታታቱ የሚኖረውን አስተዋጽኦ በማለም ሃሳቡን ወደዱት፤ የመጀመሪያው የምክክር መድረክም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተካሄደ። በቅርቡ በባህር ዳር ከተማ ሁለተኛው ውይይት ይደረጋልም ብለዋል። ተፈጥሮውን ከመጠበቅ ጋር የሚጋጭ ነገር እንደሌለ የሚናገሩት ኮሚሽነር ጌታሁን መኮንን "ሌሎች የሐይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ በመዘየድ የጢስ አባይ ፏፏቴ ወደ ቀድሞው ግርማው መመለሱ የፕሮጀክቱ አካል ነው" ሲሉ ይገልፃሉ። የፕሮጀክቱ ጥናት በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን ሁብ ሲቲ ላይቭ ይዞ የመጣው ሃሳብ ዱብ እዳ ሳይሆን ላለፉት 7 ዓመታት ጥናት እንደተደረገበት ያስረዳሉ። "የጥናቱ ውጤትም በተለያየ ጊዜ ይገለጽልን ነበር" ብለዋል። ብላክ ፓንተር ፊልም ለዕይታ የበቃው በአውሮፓውያኑ ጥር 2018 ነው፡፡ በእርሳቸው ንግግር ፊልሙ የጥናቱ የልጅ ልጅ ቢሆን ነው። ሁለቱን የሚቃረኑ ሃሳቦች አድምጠን በጥናቱ ላይ የተሳተፉት እነማን ናቸው ስንል የጠየቅናቸው ኮሚሽነሩ፤ "በጥናቱ ባለቤትነት ደረጃ ተሳትፈናል ማለት የሚቻል አይመስለኝም" ሲሉ መልሰዋል፤ ይሁን እንጂ ለከተማው ግንባታ ወደተመረጠው ቦታ በመሄድ የተመለከቱ ባለሙያዎች እንዳሉ ተናግረዋል። ይህንኑ ጥያቄ የሰነዘርንላቸው በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ ዶክተር ሹመቴ ግዛው "ባለኝ መረጃ መሰረት ፊልሙን ለመስራት የተሰራ ጥናት ካልሆነ በስተቀር፤ ከተማውን ኢትዮጵያ ውስጥ ለመገንባት የታሰበው ፊልሙ ከወጣ በኋላ ነው" ይላሉ። የፕሮጀክቱ ሃሳብ ወደ መስሪያ ቤታቸው ከመጣ በጣም አጭር ጊዜ እንደሆነ ባይክዱም፤ "ፊልሙን ለመስራት ሲታሰብ ብዙ የተሰራ ጥናት ሳይኖር አይቀርም" ሲሉም የምናልባት ምላሻቸውን ሰጥተውናል። በሃሳብ ደረጃ ያለው ሌላኛው ገፅታ በ20 ቢሊየን ዶላር የሚገነባን ትልቅ የፕሮጀክት ሃሳብ ጋር በዚህ አጭር ጊዜ መዋሃድ ያስችላል ወይ ስንል የጠየቅናቸው ዶ/ር ሹመቴ፤ "አንድን ነገር ለመረዳት አንድ ቀን፣ አንድ ወር አሊያም አስር ዓመት ሊወስድ ይችላል፤ነገር ግን አስር ዓመት የሚፈጀውን በአንድ ቀን ተገንዝቦ መጨረስ ከተቻለ በቂ ነው" ሲሉ ይሞግታሉ። ሊያሳስበን የሚገባው ከጊዜው ይልቅ ጠቀሜታው ነው ይላሉ። ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው? ሀብ ሲቲ ላይቭ ይህ ፕሮጀክት ሲነሳ ተደጋግሞ የሚነሳ ስም ነው፤ በአሜሪካ አገር የሚገኝ ድርጅትና የፕሮጀክቱ ሃሳብ አፍላቂም ተደርጎ ይነገራል። ሀብ ሲቲ ላይቭ ማነው? በእኛ በኩል ስለ ድርጅቱ ለማወቅ ጥረት ብናደርግም ጥቂት ሰዎች ከወደዱት የፌስቡክ ገፅና በቅርቡ አገልግሎት እንደሚሰጥ ከሚገልፅ ድረ -ገፅ (www.hubcitylive.com) በስተቀር በቂና የተደራጀ መረጃ ማግኘት አልቻልንም። ይህንኑ አስመልክተን የጠየቅናቸው ሚኒስትር ዲዔታው የቴክኖሎጂ ከተማ የመገንባቱን ሃሳብ በምክክር መድረኩ ወቅት ያቀረበው ሚካኤል ካሚል የተባለ ጥቁር አሜሪካዊ እንደሆነና በመስሪያ ቤቱም በተደጋጋሚ ሲመላለስ ያዩት እርሱን እንደሆነ ገልጸውልናል። ድርጅቱ ከኢትዮጵያ አሊያም ከመስሪያ ቤቱ ጋር የቀደመ የስራ ግንኙነት ስለመኖር አለመኖሩም ዕውቅናው እንደሌላቸው ተናግረዋል። "ያገኙትን አፍሰው ቢበሉት፣ ያስቸግር የለም ወይ ሲውጡት" እንዳለችው ድምጻዊቷ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ እንዴት ስምምነት ላይ መድረስ ተቻለ ያልናቸው ሚንስትር ዲዔታው፤ የአንድን ፕሮጀክት ተግባራዊነት ደረጃ የማወቂያ ጥናት (Feasibility study) ሃሳባዊ፣ ቅድመ ትግበራና ትግበራ በሚባሉ ሶስት ደረጃዎች ማለፍ እንደሚገባው ያብራራሉ። በመሆኑም "ፕሮጀክቱ በሃሳባዊ ደረጃ ያለ በመሆኑ፤ ግንዛቤ የመፍጠርና ፕሮጀክቱን የማስተዋወቅ ስራ ነው የሚሰራው፤ እኛም እሱ ላይ ነን" ሲሉ ይናገራሉ። • ከኢትዮ- ቻይና ወዳጅነት ጀርባ • ሶፊያ ከአብይ አሕመድ ጋር የራት ቀጠሮ ይዛለች • ጤፍ ሃገሩ የት ነው? ደቡብ አፍሪካ? አውስትራሊያ? . . . በዚህም መሰረት ጥቅምና ጉዳቱን፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ ተግዳሮቶችና ሌሎች ጥናቶች ይደረጋል፤ የጥናቱ ውጤት ታይቶ ፕሮጀክቱ ሊቀር ይችላል፤ በከፊል ሊስተካከል ይችላል፤ አሊያም እንዳለ ሊቀጥል ይችላል። ይህ ፕሮጀክትም ከሶስቱ የአንዱ እጣፈንታ ሊገጥመው ይችላል ይላሉ። ቴክኖ ቱሪዝምን፣ ፈጠራንና ኢንዱስትሪን ያስፋፋል ብለው በማመናቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፕሮጀክቱን በሃሳብ ደረጃ እንደተቀበለው ደጋግመው ያስረዳሉ። የገንዘብ ምንጩ 20 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚፈጅ የተገመተለት ይህ ፕሮጀክት ምንጩ ምንድን ነው? አቅም ያላቸውና በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች ተባብረው ይገነቡታል፤ ዋናኛው የገንዘብ ምንጭም በተለያየ ሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ጥቁር አሜሪካውያን ባለሃብቶች እንደሚሆኑም ይታመናል። ሌላኛው የከተማው ከፊል ገፅታ ሃሳቡን የሚደግፉ ሁሉ ከተማዋን እንዲገነቡ ይደረጋል፤ በተለይ በአገር ውስጥ ያሉ ባለሃብቶች ድርሻ ከፍ እንዲል ጥረት እንደሚደረግ ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን ይገልፃሉ። "ድርጅቱ ሃሳቡን ይዞ የመጣው፤ ገንዘብ ማሰባሰብ እንደሚቻል አምኖ ነው" የሚሉት ደግሞ ዶ/ር ሹመቴ ናቸው። • ከዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለዎት? • ከአንታርክቲካ በስተቀር ስድስቱን አህጉሮች ያዳረሰችው ኢትዮጵያዊት ከዚህ ቀደም ከድርጅቱ ጋር በነበራቸው ውይይትም እውነተኛውን የቴክኖሎጂ ከተማ ለማየት ፍላጎት ያላቸው በርካታ ግለሰቦች እንዳሉ ተገልጾላቸዋል። በመሆኑም የሚጠቅም ሆኖ እስከተገኘ ድረስ እጃቸውን አጣጥፈው የሚቀመጡበት ምክንያት እንደሌለና እንደ መስሪያ ቤት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ያረጋግጣሉ። "ይህ የሚሆነው ግን ጥናቱ ተጠናቆ መተማመኛ ሲገኝ ነው" ይላሉ። ከፈረሱ ጋሪው? የተሟላ ጤና ጣቢያ፣ ትምህርት ቤት፣ የተስተካካለ መንገድ፣ በክህሎትና በዕውቀት የዳበረ የሰው ኃይል ባልተበራከተበትና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ልማቶች ባልተሰሩበት ስለ ፕሮጀክቱ ማሰብ ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ የሚሉት ጥቂት አይደሉም። የኢትዯጵያ መንግስት 20 ቢሊየን ዶላር አወጣለሁ ብሎ ቢነሳ፤ ከፈረሱ ጋሪው ቀደመ ያስብላል የሚሉት ዶ/ር ሹመቴ "ጥቅም ያለውና በጀቱ ከሌላ ቦታ ሊገኝ የሚችል ፕሮጀክት ሲመጣ፤ እኛ አንፈልግም እዚህ ደረጃ ላይ አልደረስንም ማለት ግን አንችልም" ብለዋል። አቶ ጌታሁን መኮንን በበኩላቸው "ስራው በአገር ውስጥ ያለውን ዝግጁነት የሚጠይቅ አይደለም፤ ይህም በአገር ውስጥ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች የሚያጓድል አይደለም፤ ለከተማው ያስፈልጋል የሚባሉት መሰረተ ልማቶች አብረው የሚከናወኑ በመሆናቸው የመንግስትን በጀት የሚነካ አይደለም ይላሉ። • ማንዴላን ውትድርና ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ • አቶ በረከት ስምኦን ሥልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ በአገራችን ተጀምረው መቋጫው የተጣፋባቸው ፕሮጀክቶች ለዚህኛውስ የስጋት ማሳያ አይሆኑም ወይ ያልናቸው ዶ/ር ሹመቴ ተጀምረው የቀሩ እንዳሉ በማመን አሁንም መቶ በመቶ እርግጠኛ መሆን እንደማይቻል፤ ነገር ግን ለተግባራዊነቱ ተባብሮና አስተሳስሮ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል። "ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ አዲስ ሃሳብ ያላቸውና ስጋት የገባቸው ወደኛ ይዘው ቢያቀርቧቸው እንደ ግብዓት እንጠቀምበታለን" ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል። በበላይነት የሚቆጣጠረው ማነው? ዶ/ር ሹመቴ "እንደነዚህ ዓይነት ትላልቅ ፕሮጀክቶችን የሚመራው ማነው? የሚለውን ለመወሰን ጊዜው አሁን አይደለም" ይላሉ። ገዳዩ ከቴክኖሎጂ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ሚኒስቴር መስርያ ቤቱ ጋር ግንኙነት የተጀመረ ቢሆንም አሁን ባለበት ደረጃ በስም፣ በሀብት፣ በሃላፊነት እገሌ ነው ብሎ መጥቀስ እንደማይቻል ይናገራሉ። የሚገነባው ከተማ ሰፊ በመሆኑ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ሃላፊነት ይኖራቸዋል፤ በየ ዘርፋቸው ተሳትፎ ያደርጉበታል ያሉን ደግሞ የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን ናቸው። ፕሮጀክቱ በአስር ዓመታት ይጠናቀቃል ተብሎም እንደተገመተ ተገልጿል።
news-54597785
https://www.bbc.com/amharic/news-54597785
ደቡብ አፍሪካ፡ "የአባቴን ገዳይ አቅፌው አለቀስኩ"
ካንዲስ ማማ ትባላለች፡፡ ደቡብ አፍሪካዊት ናት፡፡
9 ዓመቷ ላይ ሳለች አንድ ጥፋት አጠፋች፡፡ እናቷ ገበያ ስትሄድ ቀስ ብላ የእናቷ መኝታ ቤት ገባች፡፡ እዚያ ቁምሳጥን አለ፡፡ ቁምሳጥኑ ላይ መጽሐፍ አለ፡፡ ልትደርስበት አልቻለችም፡፡ ትንሽ ልጅ ነበረች፡፡ ወንበር ላይ ተንጠለጠለች፡፡ ከዚያም ለዓመታት ተደብቆ የሚቀመጠውን መጽሐፍ ከቁምሳጥኑ አናት ላይ አወረደችው፡፡ ከዚያም ቶሎ ቶሎ ማንበብ ጀመረች፡፡ ሕይወቷ ያን ቀን ፈረሰ፡፡ ባየችው ነገር ተረበሸች፡፡ ጤና ራቃት፡፡ ምናለ ያን ቀን ያን መጽሐፍ ባልገለጠች ኖሮ? ያባቷን ገዳይና የአባቷን ሬሳ ነበር መጽሐፉ ውስጥ የተመለከተችው፡፡ ካንዲስ ማማ ከዚያን ቀን ጀምሮ እያደገች እያደገች አሁን ትልቅ ሰው ሆናለች፡፡ ጸጸት ግን እየገዘገዛት ነው የኖረችው፡፡ ምናለ ያን መጽሐፍ ያን ዕለት ባልገለጠችው ኖሮ! ምስጢራዊው መጽሐፍ ካንዲስ ማማ ገና 8 ወሯ ሳለች ነበር አባቷ የሞተው፡፡ ስለዚህ በቅጡ አባቷን አታውቀውም፡፡ ሰዎች ስለአባቷ ሲያወሩ ግን ትሰማለች፡፡ አባቷ ሕይወትን ቀለል አድርጎ የሚመለከት፣ መደነስና መጫወት የሚወድ፣ ሙዚቃ ሲሰማ ዘሎ ወደ መድረክ የሚወጣ ዓይነት ሰው ነበር፡፡ ይሳቅ ይጫወት እንጂ በመብት ጉዳይ ቀልድ አያውቅም ነበር፡፡ የፓን አፍሪካን ኮንግረስ አባል የሆነውም ለዚሁ ነበር፡፡ በምህጻረ ቃል ፓክ የሚባለው ይህ የፖለቲካ ፓርቲ ከነ ማንዴላ፣ ከነ ሲሱሉ፣ ከነ ኦሊቫር ታምቦ ተገንጥሎ የወጣ ነበር፡፡ ይህ ፓርቲ ለጥቁሮች የቆመ ቢሆንም እነ ማንዴላ እኩልነት ቅብርጥሶ የሚሉት ነገር አይመቸውም፡፡ ‹‹ደቡብ አፍሪካ የጥቁሮች መሬት ናት፤ ኻላስ፡፡ ነጮች ከአገራችን ይውጡ፣ በቃ›› ይላል፡፡ የካዲስ አባት ጥቁሮች ከአፓርታይድ ጭቆና ነጻ እንዲሆኑ የሚመኝበት መንገድ ከነማንዴላ ጋር ቢቃረንም ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ደግሞ እጅና ጓንት ሆኖ ሲታገል ኖሯል፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ግን እርጉሙ፣ ነፍሰበላው፣ ጭራቁ በሚሉ ቅጽሎት በሚታወቀው የአፓርታይዱ ጌታ ዩ ጂን ዲኮክ እጅ ወደቀ፡፡ ዩ ጂን ዲኮክ ማን ነው? ዩ ጂን ዲኮክ በደቡብ አፍሪካ አሁንም ድረስ ስሙን ሲሰሙ የሚንዘረዘሩ አሉ፡፡ ገራፊ ብቻ ሳይሆን የገራፊዎች አለቃ ነበር፡፡ ለጭካኔው ልክ የለውም፡፡ በአፓርታይድ ምድር ማንም እንደ ዩ ጂን ዲኮክ ያለ ክፉ የለም ይላሉ፡፡ የወንድ ብልት ላይ ድንጋይ አንጠልጥሎ፣ የውስጥ እግር ገልብጦ የሚተለትል የስቃይ ቡድን መሪ ነበር ዲኮክ፡፡ የካንዲስ ማማ አባት በዚህ ነፍሰ በላ እጅ ነበር የወደቀው፡፡ ካንዲስ ከልጅነቷ ጀምሮ አባቷ በሆነ ሰው እንደተገደለ ትጠራጠር ነበር፡፡ የአባቷ ገዳይ ግን ዩ ጂን ዲኮክ ነው ብላ በጭራሽ አላሰበችም፡፡ የፈረንጅና የጥቁር ቅልቅል የሆነችው እናቷም ይህን ጉድ ነግራት አታውቅም፡፡ በደቡብ አፍሪካ ክልሶች ከለርድ ይባላሉ፡፡ እናቷ ከለርድ ነበረች፡፡ ልጅ እያለች ግን አንድ ነገር ትዝ ይላታል፡፡ ሁልጊዜም ዘመድ አዝማድ ቤት ከመጣ በኋላ ያቺ ከኮሞዲኖው ጀርባ የምትደበቀው መጽሐፍ ትወጣለች፡፡ ከዚያ ያቺን መጽሐፍ ሰዎች ገልጠው ከተመለከቱ በኋላ ያለቅሳሉ፡፡ ይህ ነገር ሲደጋገም በጣም እየገረማት መጣ፡፡ ለምንድነው ሰዎች ይህን መጽሐፍ ገልጠው የሚያነቡት(የሚያለቅሱት)? ለምን መጽሐፉን ሳይገልጡ አያለቅሱም ግን? ይህ አእምሮዋን እረፍት የነሳውን ጥያቄ ለመመለስ ነበር ልክ 9 ዓመት ሲሞላት የእናቷን ገበያ መሄድ አስታካ ቶሎ ብላ ያን መጽሐፍ የገለጠችው፡፡ መጽሐፉ በውስጡ የያዘው የገራፊዎችንና የገዳዮችን ኑዛዜ በፎቶ አስደግፎ ነበር፡፡ መጽሐፉ ‹‹ኢንቱ ዘ ሀርት ኦፍ ዳርክነስ፤ ኮንፌሽን ኦፍ አፓርታይድ አዛዚንስ›› (Into the Heart of Darkness - Confessions of Apartheid's Assassins) የሚል ርእስ ያለው ነው፡፡ በዚህ ርእስ የአባቷን ገዳይና ሬሳ ብቻ አልነበረም ያየችው፡፡ አገዳደሉንም ጭምር እንጂ፡፡ አባቷ የመኪናውን መሪ እንደተደገፈ በጥይት ተደብድቦ ሰውነቱ ተቃጥሎ ነበር በዚያ ፎቶ ላይ የሚታየው፡፡ ይህ ምሥል እድሜ ዘመኗን ሲያንዘፈዝፋት ኖረ፡፡ ከ9 ዓመቷ ጀምሮ፡፡ የሆነ ዕድሜ ላይ ስትደርስ ራስን ስለማጥፋት ማሰብ ጀመረች፡፡ የሆነ ቀን ልቧ መምታት ያቆመ መሰላት፡፡ የልብ ሕመም ስለመሰላት ሐኪም ቤት ሄደች፡፡ የሆነ ቀን ምሽት 16 ዓመቷ ላይ ራሷን ሳተች፡፡ ሆስፒታል ሐኪሟ ነገሩ እንግዳ ሆኖበት አገኘችው፡፡ በሷ እድሜ ሰዎች የልብ ድካም ሊያጋጥማቸው የሚችልበት እድል ጠባብ ነው፡፡ ምናልባት የሚያስጨንቅሽ ነገር ይኖር ይሆን ተባለች፡፡ ሐኪሙ ‹‹እኔ ባለፉት 20 ዓመታት እንዲህ ዓይነት ነገር ገጥሞኝ አያውቅም፤ ሕይወትሽን በገዛ ጭንቀት አፍነሽ ልታጠፍያት ተቃርበሻል›› አላት፡፡ በዚህን ጊዜ ነበር ስለ አባቷ ገዳይ ላለፉት በርካታ አመታት የተብሰለሰለችውን ነገር ልጓም ትታበጅለት እንደሚገባ የወሰነችው፡፡ ገዳይን አቅፎ ማልቀስ በ1995 ማንዴላ ሥልጣን ሲይዙ የእርቅና እውነት አፈላላጊ ኮሚሽን ተቋቁሞ ነበር፡፡ ይህ ኮሚሽን በአፓርታይድ ዘመን ግፍ የተፈጸመባቸውን ሰዎች መረጃ ማሰባሰብ፣ ፈጻሚዎችንም ለሕግና ለእርቅ ማቅረብ ነበር ዓላማው፡፡ የአባቷን ገዳይ ዲኮክን ማፈላለግ ጀመረች፡፡ ስለሱ ብዙ አነበበች፡፡ የተናዘዛቸውን ግድያዎች በብዙ አግበስብሳ አነበበች፡፡ እያነባች፡፡ ከዚያ አንድ አዲስ ስሜት ተሰማት፡፡ እሷ መኖር የምትችለው ይህንን ነፍሰ በላ ስትገድለው ነው፡፡ ሌላው ለመኖር ያላት አማራጭ ደግሞ ከልቧ ይቅር ስትለው ነው፡፡ ‹‹ይቅር የምለው ለኔም ለሱም ብዬ ነው፡፡ እየተበቀልኩትም ሊሆን ይችላል፡፡ አባቴን ባሰብኩ ቁጥር ይህንን ነፍሰ በላ አስበዋለው፡፡ እሱን ባሰብኩ ቁጥር ስሜቴን እሱ ይቆጣጠረዋል፡፡ በዚህን ጊዜ እታመማለው፡፡ እኔ በሱ ቁጥጥር ስር ነው ያለሁት፡፡ አባቴን ገደለ፡፡ አሁን ደግሞ ቀስ ብሎ እኔን ሊገድለኝ ነው›› ትላለች፡፡ ‹‹ለዚህም ነው ለኔ እሱን ይቅር ማለት አማራጭ ያልነበረው፡፡›› ካንዲስ ሰውየውን ይቅር ማለት ትልቅ ነጻነት ሰጣት፡፡ ስሜቱ ልዩ ነበር፡፡ የይቅር ባይነት ስሜቱ የእውነት ሲሆን እጅግ ነጻ አወጣኝ፡፡ ገና ሰውየውን ሳላገኘው ራሴን መቆጣጠር ቻልኩ፤ መሳቅ መጫወትና የሆነውን መቀበል ጀመርኩ፡፡ ጤንነቴም ተመለሰ›› ልክ በ2014 የካንዲስ እናት ደብዳቤ ደረሳቸው፡፡ ከአቃቢ ሕግ ነበር ደብዳቤው፡፡ ቤተሰቡ በባሏ ግድያ ጉዳይ ከአጥፊው ጋር መነጋገር ከፈለጉ በአካል መገናኘት እንደሚችሉ ተነገራቸው፡፡ በሌላ ቋንቋ ነፍሰ በላውን ዩጂን ዲኮክን ፊት ለፊት በአካል የማግኘት እድል/እርግማን ማለት ነው፡፡ በዚህ ጊዜ ካንዲስ 23 ዓመቷ ነበር፡፡ እናትየው የደብዳቤውን ይዘት ነገሯት፡፡ መልሷ ፈጣን ነበር፡፡ ‹‹በዚያ ቅጽበት ቶሎ እሺ ባልል ዕድሜ ዘመኔን እንደ እስረኛ በራሴው ስሜት ስሰቃይ እንደምኖር አውቀው ነበር›› ትላለች፡፡ የአባትን ገዳይ ማቀፍ የአባቷን ገዳይ ለማግኘት ቀጠሮ ተያዘ፡፡ ለባበሰች፡፡ ከእናቷ ጋር ተያይዘው ሄዱ፡፡ ነፍሰ ገዳዩን ዲኮክን የማገኝበት ክፍል ውስጥ ስገባ ከፍተኛ የስሜት መረባበሽ ተከሰተብኝ ትላለች፡፡ ነፍሰ በላው በሚል በመላው ደቡብ አፍሪካ የሚፈራው ሰው ቁጭ ብሏል፡፡ በቃ ሰው ነው፡፡ የ65 ዓመት ጎልማሳ ሰው፡፡ ሰይጣንን የመገናኘት ያህል ነበር የፈራቸው፡፡ ነገር ግን በቃ ኖርማል ሰው ቁጭ ብሏል፡፡ በፎቶ ላለፉት 20 ምናምን ዓመታት የምታውቀው፡፡ በሕልሟም በእውኗም እየመጣ የሚያሰቃያት ሰው፡፡ እንደ ማንኛውም ጤነኛ ሰው ቁጭ ብሏል፡፡ ‹‹እርቁን የሚመሩት ቄስ ከእናቴ ባል ገዳይ፣ ከአባቴ ገዳይ አስተዋወቁኝ፡፡› ይህ ነፍሰ ገዳይ እኔና እናቴን ሲጨብጥ፣ ስላገኘኋችሁ ደስ ብሎኛል ("Pleasure to meet you.") ይል ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ እናቷ በመጋቢት 26፣ 1992 በትክክል ባሏን እንዴት እንደገደለው እንዲነግራት ጠየቀችው፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡ ዝርዝሩ ምን ይፈይዳል? ተናግሮ ሲጨርስ ግን አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ አልኩት፡፡ የፈለግሽውን አለኝ፡፡ ራስህን ግን ይቅር ትለዋለህ? ዲኮክ ደነገጠ፡፡ ‹‹እስከዛሬ ቤተሰባቸውን የገደልኩባቸውን ሰዎች ለማግኘት ስመጣ እንዳልጠየቅ የምፈረው አንድ ጥያቄ ቢኖር ይህንን ጥያቄ ነበር፡፡ በመጨረሻ አንቺ ጠየቅሽኝ›› ብሎ አቀረቀረ፡፡ ከዚያም ማንባት ጀመረ፡፡ ‹‹እኔ ቦታ ብትሆኚ ግን አንቺ ራስሽን ይቅር ትይው ነበር?›› ብሎ በጸጸት አነባ፡፡ ቄሱን ይቅርታ ጠይቄ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ የአባቴን ገዳይ አቀፍኩት፡፡ ተቃቅፈን አለቀስን፡፡ እስኪወጣልን ድረስ…፡፡
47250956
https://www.bbc.com/amharic/47250956
"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ"
መገናኛ አካባቢ የሚገኝ ፀጥ ያለ መንደር ነው። ሰባት ወይም ስምንት የሚሆኑ ልጅ ያቀፉ አፍላ ታዳጊዎች እየተሳሳቁ ከአንድ ትልቅ ግቢ በመውጣት ላይ ነበሩ። ሁሉም ልጅ የያዙና በእድሜም ለእናትነት ገና መምሰላቸው ትኩረት ይስባል። ምን እየተባባሉ እንደሆነ ለመስማትም ያጓጓል።
እነሱን አልፈን ወደ ውስጥ ዘለቅን። የ23 ዓመት ወጣት ነች። ከገፅታዋ ምንም ነገር ማንበብ አይቻልም። ገፅታዋም ሆነ ሁለንተናዋ ፀጥ ያለ ነው። ከዓመታት በፊት ወደ እዚህ ግቢ ስትመጣ የሥራ ማመልከቻ ለማስገባት ወይም ሥራ ለመጀመር አልነበረም። ይልቁንም በእናቷ ልጅ በወንድሟ ተደፍራ ከደረሰባት ከባድ አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጉዳት ለማገገምና መጠለያ ለመሻት ነበር። የደረሰባት ነገር ሰው እንድትፈራ አድርጓት ነበርና በሙሉ አይኗ ሰው ማየት ያስፈራት፤ ቃላት አውጥቶ መናገርም ይከብዳት እንደነበር ታስታውሳለች። • ሃምሳ በመቶ የሚኒስትሮች ሹመት ለሴቶች "ከባድና እጅግ አሳዛኝ ህይወት አሳልፌአለው" ትላለች ጊዜውን በማስታወስ። የጉዳቷ መጣን በህይወት እየኖርኩ ነው የማያስብል ቢሆንም ያን ቀን አልፋ ዛሬ ቀና ብላ መራመድ ችላለች። ዛሬ የምትፈልግበት መድረስና ህልሟን መኖር እንደምትችልም በእርግጠኝነት ትናገራለች። ዛሬ ያኔ ተደፍራ የተጠለለችበትና ለተደፈሩ ሴቶች ድጋፍ የሚያደርገው 'የሴቶችና የህፃናት ማረፊያ' ውስጥ ለመሥራት ችላለች። ምንም እንኳ ያን ጊዜ ማስታወስ ቢያማትም ያለፈችበት መንገድ ሴቶች ለፆታዊ ጥቃት እንዳይጋለጡ አስተማሪ ይሆናል የሚል ፅኑ እምነት ስላላት የሆነችውን ትናገራለች። ሊያስተምራት አዲስ አበባ ያመጣት ትልቅ ወንድሟ ፖሊስ ነበር። ያኔ እሷ የ16 ዓመት ታዳጊ ነበረች። የሚኖሩት ወንድሟ በተከራየው ቤት ነበር። "ልጅ ስለነበርኩ ብዙ ነገር አላውቅም፤ መናገርም አልችልም ነበር። ሰው ሳይ ተመሳሳይ ጥቃት ያደርሱብኛል ብዬ ፍራቻ ነበረብኝ" በማለት የነበረችበትን የሥነ ልቦና ስብራት ታስታውሳለች። ሰው አይቷት ሚስጥሯን የሚያውቅ ይመስላት ስለነበር ትምህርት ቤት መሄድና መመለስ፤ ክፍል ውስጥ መቀመጥም እጅግ ስለከበዳት ትምህርት ቤት መሄድ አቆመች። • ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የሃገር መከላከያ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ ወንድሟ ለአምስት ዓመታት አብረው ሲኖሩ ደፍሯታል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ሦስት ጊዜም ፅንስ እንድታቋርጥም እንዳደረጋት ትገልፃለች። ልጅነትና የሥነ ልቦና ቀውስ እንዲሁም የወንደሟ ማስፈራራት ለማንም ምንም ትንፍስ ሳትል እንድትቆይ አድርጓት ነበር። ይኖሩ ከነበሩበት ቤት ለቅቀው ሌላ የኪራይ ቤት የገቡበት አጋጣሚ ግን ጉዳቷን አውጥቶ ለመናገር እድል ሰጣት። በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁኔታዋን ያስተዋሉት አዲሷ የቤት አከራያቸው አንድ ቀን "ለምንድነው ሰው የማትቀርቢው? ዘመዱ ነሽ ወይ?" ሲሉ ድንገት ጠየቋት። ሁለቱም ጥያቄዎች ለእሷ እጅግ ከባድ ነበሩ። ከምትኖርበት ስቃይ መውጣት ትሻ ነበርና አለባብሶ እንደነገሩ መልስ መስጠት አልፈለገችም። በሌላ በኩል እውነቱን መናገርም መከራ ሆነባት። እንደምንም ከራሷ ጋር ታግላ የሆነችውን ለአከራይዋ ተናገረች። በነገሩ በጣም የደነገጡት አከራይ ይዘዋት በአቅራቢያ ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ለመሄድ ምንም አላመነቱም። ከፖሊስ ጣቢያ በኋላ ነበር የተደፈሩ ሴቶችን ወደሚያስጠልለውና የሕግ አገልግሎት ድጋፍ ወደሚያደርገው የሴቶች ማረፊያ ልማት ማኅበር የተወሰደችው። ከሰልጣኝ ሴቶች መካከል አንዷ "ቤተሰብ በእኔ ፈረደ" ነገሩ ወደ ሕግ ከሄደ በኋላ ጉዳዩን የሰሙ ቤተሰቦቿ 'እሱ እንዲህ አያደርግም፤ ልጅ ስለሆነች ነው እንዲህ ያለ ነገር የምታወራው' በማለት በፍፁም ሊያምኗት አልቻሉም። በተለይም ትልቅ እህቷ ካለማመን አልፋ የወንድማቸውን ስም ለማጥፋት 'ያልሆነውን ሆነ እያለሽ ነው' በሚል ብዙ ሞግታታለች ዝታባታለችም። "ከእናቴ ውጪ ቤተሰብ ሁሉ እንደ ቆሻሻ ተፀየፈኝ" በማለት ተበዳይ ሆና እንዴት የበዳይ እዳ ተሸካሚ እንደተደረገች ትናገራለች። በሌላ በኩል ፖሊስ ጣቢያ በሄደችበት ወቅት ያየችው አቀባበል እንደሷ ያሉ የተደፈሩ ሴቶች ይብስ ፈርተው እንዳይናገሩ የሚያደርግ እንደነበር ታስታውሳለች። ሃዘኔታ በሌለው አንደበት 'ነይ እዚህ ጋር' 'እዛጋ' 'እስከዛሬ ምን ትሰሪ ነበር?' ተብላለች። • የተነጠቀ ልጅነት ይህ የእሷ ብቻ ሳይሆን የብዙ ሴቶች አስከፊ እጣ ነው። በማህበረሰቡ እንዲህ ስላደረግሽ ነው፣ እንደዛ ባታደርጊ ኖሮ በሚሉ የምክንያት ድርደራዎች ለመደፈራቸው ራሳቸው ጥፋተኛ ተደርገው አንገታቸውን እንዲደፉ የተደረጉ ሴቶችን ቤት ይቁጠራቸው። በቀድሞ መጠለያዋ በዛሬው የሥራ ቦታዋ በወንድም፣ በአባት፣ በአያቶቻቸውም ጭምር የተደፈሩና የወለዱ ሴቶችም ጭምር አጋጥመዋታል። ሁሉም በቤተሰባቸውና በማኅበረሰባቸው ለመደፈራቸው ጥፋተኛ የተደረጉና የተወገዙ መሆናቸውን ትናገራለች። "እኔ ስለ ሕግ ብዙ አላውቅም፤ ግን ካለፍኩበትና ካየሁት በሕግ በኩል ያለው ነገርም ደስ አይልም።" በተለያዩ ምክንያቶች ደፋሪዎች ነፃ ሆነው የመሄድ እድል ያገኛሉ። በተመሳሳይ በእሷ ጉዳይም ክስ ተመስርቶ የነበረ ቢሆንም ክሱ የትም ሳይደርስ፤ ወንድሟም ሳይጠየቅ መቅረቱን ትናገራለች። "ህመሜን ተቋቁሜ ችሎት ላይ ብቆምም መጨረሻው አላማረም። እዚህ ላይ ብዙ ማለት አልፈልግም" ትላለች። "ለመረዳት ፍቃደኛ መሆን አለብን" ባደረገችው ተደጋጋሚ የፅንስ ማቋረጥ የማህፀን ጉዳት ደርሶባት ለረዥም ጊዜ ህክምና ስትከታተል ቆይታለች። በዚሁ ምክንያት ዛሬም ከባድ የወገብ ህመም ስላለባት ለቃለ መጠይቅ ባገኘናት ወቅትም በሃኪም የታዘዘ የወገብ መደገፊያ ቀበቶ አድርጋ ነበር። ይህ ሁሉ ቢሆንም ግን "በጣም የተጎዳሁት በሥነ ልቦና ነው። በተለይም የቤተሰቦቼ ነገር በእጅጉ ጎድቶኛል ዛሬም አልወጣልኝም" ትላለች። ወደ ማረፊያው ከገባች በኋላም ምግብ መብላት፣ ሰው እንዲቀርባትና እንዲያናግራትም አትፈልግም ነበር። ፍላጎቷ አንድና አንድ ነበር። ይቺን ዓለም ለመተው ራሷን ለማጥፋትም ሞክራ ነበር። በመጨረሻ ከዚህ ያወጣት የተደረገላት የሥነ ልቦና ድጋፍ እንደሆነ ትናገራለች። • ሴቶች ዝቅ ብለው እንዲኖሩ የሚያስተምረው ትምህርት ቤት ደህና ሆና ወደ ራሷ ከተመለሰች በኋላ ደግሞ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን ወስዳለች። የሴቶች ማረፊያ ልማት ማኅበር ከሙያ ስልጠና በተጨማሪ ለተደፈሩ ሴቶች ራሳቸውን ከጥቃት መከላከል ይችሉ ዘንድ የቴኳንዶ ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን እሷም ይህን ስልጠና ወስዳለች። ሰዎች በጣም ሲጎዱ ብዙ ነገር አይፈልጉም። ምንም ነገር መስማትም መረዳትም ላይፈልጉ ይችላሉ። "ቢሆንም ግን ሰውን መርዳት የሚፈልጉ ብዙ ሰዎች ስላሉ መጀመሪያ እኛ ለመረዳትና ወደፊት ለመራመድ ፍቃደኛ መሆን አለብን" ትላለች። ካጋጠማት አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃትና ሰቆቃ ለመውጣትና ከባዱን ቀን ለማለፍ ብርታት ያገኘችው ከእራሷ ነበር። "ራሴን ማመኔ፣ የተበላሸ ህይወቴን ማስተካክል እንደምችል ማመኔ ረድቶኛል" ትላለች። ባይናገሩም ከእሷ የበለጠ ከባድ ነገር ያሳለፉ ሴቶች ይኖራሉ ብላ ታስባለች። ማህበረሰቡ የእንደዚህ ያሉ ሴቶችን ታሪክ ሰምቶ መጠቋቆሚያ እያደረገ እንደገና ቁስላቸውን ባያደማ በታሪካቸው ብዙዎች እንዲማሩና የተሰበሩትም ቀና እንዲሉ ማድረግ ይቻል ነበር የሚል እምነት አላት። "ሻርፕ ጠምጥመው ስብር ብለው የሚሄዱ ሴቶች ሳይ ሁሌም የእኔ ታሪክ ይመስለኛል" የምትለው ወጣቷ በእንደዚህ ያለ አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሴቶች ምንም ባታደርግላቸው እንኳ ገፍታ እንደምታናግራቸውና እንደምትሰማቸው ትናገራለች። ማኅበረሰቡ የሴቶች ጉዳይ ግድ እንደሚለው ከተማረና ካመነ በብዙ መልኩ እንደ እሷ የተደፈሩ ሴቶችን ሊያግዝ የሚችልበት መንገድ እንዳለ ታምናለች። ከሁሉም በላይ ደግሞ በዚህ ጥቃትን መከላከልም እንደሚቻል ይሰማታል። • በአለም ላይ በየቀኑ 137 ሴቶች በህይወት አጋሮቻቸውና በቤተሰቦቻቸው ይገደላሉ ህፃናትም ይሁኑ ታዳጊዎች ያሉት ቤተሰብ በሉ፣ ጠጡ፣ ለበሱ እና ትምህርት ቤት ሄደው መጡ፤ ከሚለው ባሻገር ቤት ውስጥም ሆነ ውጪ ልጆቹ ላይ ጥቃት ሊፈፀም እንደሚችል ማወቅ አለበት። ይህም ልጆችን ለመጠበቅ ያስችላል ትላለች። "ማን ይፈልገኛል?" የቀድሞው ፆታዊ ጥቃት ተከላካይ ማኅበር የአሁኑ የሴቶች ማረፊያ ልማት ማህበር በደረሰባቸው ጥቃት የተጎዱ፣ የተሰበሩና 'ማን ይፈልገኛል?' ብለው ራሳቸውን ማጥፋት የፈለጉ በርካታ ሴቶችን ለመደገፍ ጥረት ያደርጋል። ለተደፈሩ ሴቶች የሕግ ድጋፍና የሙያ ስልጠና በመስጠት ከ15 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል። የድርጅቱ መስራች ወ/ሮ ማርያ ሙኒር ማን ይፈልገናል? በሚል ራሳቸውን ለማጥፋት ሞክረው የነበሩ ሴቶች ከፍተኛ ትምህርታቸውን ተከታትለው ህይወታቸው ተቀይሮ ማየት ለሳቸው ትልቅ ነገር እንደሆነ በየጊዜው ምሳሌ የሚሆኑ ሴቶችን ታሪክ ለሚያወጣው 'ተምሳሌት ገፅ' ተናግረዋል። ማኅበሩ በአዲስ አበባ፣ በደሴና በሌሎች ቅርንጫፎቹ እያገለገሉ የሚገኙ ኢንጅነሪንግ፣ ማኔጅመንትና ሌላ ሌላም ያጠኑ ወጣት ሴቶችን አቅፏል። ታሪኳን የነገረችን ወጣትም አዲስ አበባ ውስጥ በሙያ አሰልጣኝነትና በሃላፊነት እያገለገለች ነው።
news-52699603
https://www.bbc.com/amharic/news-52699603
የኮሮናቫይረስ ዘመኗ እመጫት ኢትዮጵያዊት የአራስ ቤት ማስታወሻ
የኮሮናቫይረስ የዓለም ጤና ስጋት በሆነባቸው ባለፉት ወራት ወረርሽኙን በመፍራት በርካቶች በጣም አስፈላጊ ለሆኑ የጤና አገልግሎቶች ወደ ህክምና ተቋማት ከመሄድ እተቆጠቡ መሆናቸው የጤና ባለሙያዎችን እያሳሰበ ነው።
ከእነዚህም መካከል የእርግዝና ክትትል ለማግኘትና ለወሊድ ወደ ሐኪም ቤቶች መሄድ ያለባቸው እናቶች ስጋት ይጠቀሳል። ከእነዚህ ውስጥም ወ/ሮ መሠረት* ተመሳሳይ ስጋት ነበራት፤ ነገር ግን የሚጠበቅባትን ጥንቃቄ አድርጋ ከሳምንታት በፊት ሐኪም ቤት ውስጥ ወልዳለች። ነገር ግን ቀደም ሲል የምታውቃቸው ነገሮች በወረርሽኙ ምክንያት ተቀይሯል ስትል የገጠማትን ነገሮች ያሰፈረችበትን የግል ማስታወሻ ለቢቢሲ አጋርታለች። በእርግዝናዬ ማገባደጃ ሰለሳ ሰባተኛ ሳምንት ላይ ክትትል የማደርግበት ሆስፒታል ስደርስ ግራ የመጋባት ስሜት ውስጥ ነበርኩ። ገና ከሆስፒታሉ መግቢያ ጀምሮ አንዲት ሴት እያንዳንዱን የሚገባውን ሰው የሙቀት መጠን ትለካለች። እኔም ተለክቼ ወደ ውስጥ ስዘልቅ ደግሞ ሆሰፒታሉ ውስጥ ያለው ሰው ሁሉ ጭምብል (ማስክ) አድርጓል። ሳያደርጉ ለሚመጡትም በሆስፒታሉ ከጨርቅ የተዘጋጀ ማስክ እየታደለ ስለነበረ ያላደረገ ሰው አልነበረም፤ የታካሚ ተቀባዮቹም ሆነ የነርሶቹ ቢሮ ፊት ለፊት ወለሎቹ ላይ መስመሮች ተሰምረው ከዚህ ማለፍ አይቻልም የሚል ጽሁፍ ሰፍሮባቸዋል። የእጅ ማጽጃ (ሳኒታይዘርም) ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሏል፤ ከሰዓታት ጥበቃ በኋላ ተራዬ ደርሶ ወደ ሐኪሜ ስገባ የታካሚ መቀመጫ ወንበሩ ከሌላው ጊዜ በተለየ ራቅ ብሎ ግድግዳ ተጠግቶ ነበር የተቀመጠው። በአንድ በኩል ጥንቃቄያቸው የደኅንነት ስሜት ቢያሳድርብኝም በዚያው ልክ ጭንቀት ለቀቀብኝ። የኮሮናቫይረስ ሁሉም ቦታ በሰዉ ልክ የሚርመሰመስ ሲመስለኝ ምነው ዝም ብዬ ቤቴ ሆኜ ምጤን ብጠባበቅስ የሚል ስሜት ተሰምቶኝ ነበር። ግን አላደረግኩትም። በተለይም በመጨረሻዎቼ የእርግዝናዬ ሳምንታት የሐኪም የቅርብ ክትትል እንደሚያስፈልግ ያለፉት ሁለት እርግዝናዎች ስላስተማሩኝ ከባለቤቴ ጋር የራሳችንን ጥንቃቄ እያደረግን ለመቀጠል ተስማማን። ከቤት ለመውጣት በማደርገው ዝግጅት አፌን ስለመሸፈንማ የእጅ ማጽጃ ስለመጠቀም ማሰብ የሚፈጅብኝ ጊዜ ቀላል አይደለም። ጭንቀቴን የሚያባባሰው ደግሞ በጤና ባለሙያዎች ነፍሰጡሮች ለቫይረሱ ይበልጥ ተጋላጭ ናቸው የሚለው ሀሳብ ነው። "እንደው የልጆቼ አምላክ አደራህን" እያልኩ እስከመጨረሻው የቻልኩትን ያህል እየተጠነቀቅኩኝ ለክትትሌ ተመላለስኩኝ። ተደብቆ መውለድ ከባለቤቴ ጋር ለመውለድ ሆሰፒታል ከገባሁ በኋላ በሠላም እስክገላገል ድረስ ለማንም ሰው እንዳይናገር ተስማማን፤ ምክንያታቻን ደግሞ ከዚህ በፊት ሁለቱ ልጆቻችን ሲወለዱ የነበረው የቤተሰባችን ልምድ ነው። ገና ሆሰፒታል መግባቴን ሲሰሙ ብዙዎቹ የቤተሰባችን አባላት ወደ ሆሰፒታል መጥተው ከውጪ ተሰብስበው በጭንቀት ይጠባበቁ ነበር። እናም በዚህ ጊዜ ይህን ላለማድረግ ወሰንን። በእርግጥ እኛ ባናስበውም በሆስፒታሉ ግድግዳ ላይ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ለጊዜው ለእንድ ታካሚ የሚፈቀደው አንድ አስታማሚ ብቻ ነው የሚል መልዕክት በየቦታው ተለጥፎ ነበር። ይህ እንደማያቆማቸው ግን እርግጠኛ ነበርኩኝ። እንዳይደርስ የለም የመውለጃዬ ቀን ደረሰ። አሁንም ከምጥ የሚስተካከል ሌላ ጭንቀት። ከዚህ በፊት በነበረኝ ልምድ በሆሰፒታሉ የምጥ ክፍል እንደእኔ በምጥ የተያዙ ሴቶች እና የሚንከባከቧቸው አዋላጅ ነርሶች ይበዙ ነበር። ታዲያ አሁንስ እንዲህ ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ስሄድ ቫይረሱ ቢይዘኝስ? ቫይረሱ የያዛት ሴት በቅርብ እዚህ ወልዳ ቢሆንስ? በምጥ ላይ ሆኜ ራሴን አንዴት መጠበቅ እችላለሁ?. . . ብቻ ብዙ ጥያቄዎች ቢመላላሱብኝም መልስ ሳጣላቸው ፈጣሪዬን ብቻ ለመንኩ። "እባክህን ጌታዬ ከልጆቼ እንዳትነጥለኝ፤ አዲስ ልጅ ትሰጠኛለህ ብዬ ያሉት እንዳይበተኑብኝ፣ ቤተሰቤን አደራህን በምህረትህ ጎብኘን" እላለሁ። ነገር ግን ወደ ሆስፒታሉ ስገባ በአጋጣሚ ያለሁት ወላድ እኔ ብቻ መሆኔንን ሳውቅ ትንሽ ቀለል አለኝ። አልጋዎቹም ቢሆኑ ከወትሮው ዘርዘር ብለዋል። የማይቀረው የጭንቁ ጊዜ ሲደርስና ምጡ እየተፋፋመ፣ ጭንቀቴም እያየለ ሲመጣ አጠገቤ ያለውን የአልጋ መደገፊያ ብረት ብርታት እንዲሰጡኝ ቁንጥጥ አድርጌ እይዝና ፋታ ሳገኝ የኮሮናቫይረስ እስከ አራት ቀን ይቆይበታል ሲባል የሰማሁትን ብረት መጨበጤ ታውሶኝ ሌላ ጭንቀት ሰውነቴን ይወረዋል። አዋላጅ ነርሷ ደግሞ አጠገቤ ቁጭ ብላ በስልኳ ደቂቃ እየያዘች የቁርጠቴን ጥንካሬና የደም ግፊቴን እየለካች ትንፋሽ በረጅሙ እየሳብኩኝ እንድተነፍስ ስትነግረኝ በጣም እሳቀቅ ነበር። ምክንያቱም ትንፋሼ በቀጥታ ወደእርሷ እንደሆነ ሳስተውል ለእርሷም መጠንቀቅ እንዳለብኝ እያሰብኩ ትንፋሼን ዋጥ አደርግና ሲከብደኝ ደግሞ ፊቴን ዞር አድርጌ በብርድ ልብሱ እየሸፈንኩ እተነፍሳሁ። ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ምጤ ሲታገስልኝ አልጋዬ ጎን ያስቀመጥኩትን ማጽጃ (ሳኒታይዘር) ከህመሜ ፋታ ባጋኘሁበት ቅጽበት ሁሉ እጄን ለማጽዳት መጠቀሜን አላቆምኩም። የመጨረሻው የጭንቅ ጊዜ ሲደርስ ግን የሆንኩትም የጨበጥኩትም ምን እንደሆን አላስታውስም፤ ብቻ ያ ሁሉ ጭንቀት አልፎ ሁለቱን ልጆቼን ስወለድ ከነበረኝ ከምጥ ጊዜ እጅግ ባነሰ ሰዓት ሆስፒታል በገባሁ በሦስት ሰዓታት ውስጥ በሰላም ተገላገልኩኝ። የአራስነት ጊዜ ለብቻ ያን ጊዜ ምንም የማያውቁት ቤተሰቦቼም የምሥራቹን በስልክ ሰሙ፤ ከዚህ በፊት ወደቤት ስንመለስ እናቴ ነበረች ጨቅላውን አቅፋ እልልልልል እያለች የምትገባው፤ ጎረቤትም ተከትሎ እልልታውን ያቀልጠዋል፤ እቅፍ አድርጎ እየሳመ "እሰይ፣ እሰይ እንኳን ደስ ያለሽ! ያሳድግልሽ! ለቁም ነገር ያብቃልሽ!" እያለ መልካም ምኞቱን ያጎርፈዋል። አሁን ግን የእናቴና የጎረቤቶቼ እልልታም ሆነ አነርሱም አልነበሩም። እኔ እና ባለቤቴ ብቻ ልጃችንን ይዘን ሹልክ ብለን እንደወጣን አዲሷን ልጃችንን ይዘን ቤታችን ገባን። በአራስነቴ የመጀመሪያዎቹ ቀናት ልክ እንደ መጀመሪያ ጊዜ እንዴት እንደማደርግ ራሱ ግራ ተጋብቼ ነበር። እናቴ የአራስ ወግ ነው ጭንቅላትሽ ይደርቃል እያለች በግድ የምትቀባኝ ቅቤ ናፈቀኝ፤ ስዎች ተሰብስበው ገንፎ በትልቅ ድስት ተገንፎቶ ሲበላ ቤቱም በምርቃትና በጨዋታ ሲደምቅ ማየት ተመኘሁ። የእኛ ቤተሰብ ደግሞ ብዙ ስለሆነ እኛ ብቻችንን እንኳን ስንሰባሰብ ቤቱ ይሞላ ነበር። በተለይ ደግሞ በወለድኩ በሰባተኛ ቀኔ ጎረቤትና ዘመድ አዝማድ ተስብስቦ የሚደረገው የገንፎ ዝግጅት በጣም ደስ ይለኝ ነበር፤ ሥነ ሥርዓቱን የወዳጆቼ መሰባሰቢያ እና የልጄ የምርቃት መቀበያ መሆኑን እንደጥሩ ዕድል እቆጥረዋለሁ። አሁን ግን ይሄ ሁሉ ነገር በምናብ ብቻ ነው፤ ሁሉም ነገር በስልክ ብቻ ሆኗል። ያውም ደስታቸውን ገልጸው ሳይጨርሱ ወሬው ወደኮሮናቫይረስ ጉዳይ ይለወጣል። 'ይሄ መጥፎ ወረርሽኝ' የሚለው 'ከእንኳን ማሪያም ማረችሽ' ቀድሞ ዋነኛ ጉዳይ ሆኗል። እናቴ እንጀቷ አልችል ቢላት "ግድ የለሽም ለአምስት ደቂቃ ልይሽና አመለሳለሁ" ትላለች፤ አንዳንዴ እንደማልቀስ ሲዳዳኝ ቶሎ ብዬ ስልኩን እዘጋባታለሁ። መቼስ በእናት መታረስ ዓለም ነው ብዙ ሸክም ያቀላል፤ ግን ደግሞ በሽታ የመቋቋም አቅሟ የተዳከመው አረጋዊቷ እናቴ ወይም ጨቅላዋ ልጄ ቢታመሙብኝስ ብዬ ፈራሁ። በተለይ ደግሞ በሽታው እስክ 14 ቀን ምልክት ላያሳይ ይችላል ሲባል ስለነበር እነዚያ ቀናት በጭንቀት ነበር ያለፉት። ይኽው አሁን አንድም ሰው በአካል መጥቶ የተለመደውን የአራስ ጥየቃና ምርቃት ሳላገኝ አንድ ወር ሆኖኝ፤ መጪዎቹ ቀናትም እንዲሁ አልፈው የተሻለ ቀን እስኪመጣ ለሁላችንም ጤና ስል አራስነቴን በብቸኝነት አየገፋሁ ነው። [* ስሟ ለዚህ ታሪክ ሲባል ተቀይሯል]
news-55663241
https://www.bbc.com/amharic/news-55663241
ሂጃብ የምትለብሰው ታዋቂዋ ሞዴል ሀሊማ አደን ለምን ሥራዋን ተወች?
ሀሊማ አደን ሂጃብ ለብሳ የዓለም ምርጧ ሞዴል መባሏ ከእስልምና ሐይማኖቷ ጋር የማይስማማ በመሆኑ ከፋሽን ኢንዱስትሪውን ራሷን አግልላለች፡፡ ከቢቢሲ ግሎባል የሃይማኖት ጉዳዮች ዘጋቢ ጋር በነበራት ቆይታ - እንዴት ሞዴል ሆና መሥራት እንደጀመረች እና ለማቆም እንዴት እንደወሰነች ትናገራለች፡፡
የ23 ዓመቷ ሀሊማ በበርካታ ሶማሌዎች ተከብባ በሚኔሶታ በሴንት ክላውድ ነው ያደገችው፡፡ ተራ ልብሶችን ለብሳ እና ያለ ምንም መዋቢያ ከውሻዋ ኮኮን ጋር ነው በደስታ ያሳለፈችው፡፡ የተወለደችበትንና ኬንያ የሚገኘው የስደተኞች መጠለያን በመጠቆም "እኔ ከካኩማ የመጣሁ ሀሊማ ነኝ" ትላለች፡፡ ሌሎች ሂጃብ የምትለብሰው ሱፐር ሞዴል ወይንም በቮግ መጽሔት ሽፋን ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣች፣ የመጀመሪያዋ የሂጃቢ ለባሽ ሞዴል እያሉ ቢገልጿትም እርሷ ግን የፋሽን ኢንዱስትሪው ከእምነቴ ጋር የሚጋጭ ነው በማለት ትታዋለች። "እንደዚህ በቃለ-መጠይቅ ምቾት ተሰምቶኝ አያውቅም" ስትል ሳቀች፡፡ "ምክንያቱም የራሴ ባልሆነ ልብስ ለመዘጋጀት 10 ሰዓት ስላላጠፋሁ" ብላለች። ሂጃማ እንደምትለብስ ሞዴል ሀሊማ ልብሷን ትመርጣለች። በሥራዋ የመጀመሪያ ዓመታት የራሷን ሂጃብ እና በረዣዥም ቀሚሶች የተሞሉ ሻንጣዎችን ወደ እያንዳንዱ ቀረፃ ትወስድ ነበር፡፡ ለሪሃና ፌንቲ ቢውቲ የራሷን ቀላል ጥቁር ሂጃብ ለብሳለች፡፡ ምንም ለብሳ ቢሆን ለእያንዳንዱ ቀረፃ ሂጃቧን ማድረጓ ለድርድር የማይቀርብ ነበር፡፡ በጎርጎሮሳውያኑ 2017 በዓለም ላይ ካሉ ትልልቅ የሞዴሊንግ ኤጄንሲዎች አንዱ ከሆነው ከአይ ጂ ኤም ጋር ስትፈራረም መቼም ቢሆን ሂጃብ እንደማታወልቅ የሚገልጽ አንቀጽ ውሏ ውስጥ ጨምራለች፡፡ ሂጃብዋ ለእሷ ዓለሟ ማለት ነው፡፡ "የሞዴሊንግ ውል ለማግኘት መሞት የሚፈልጉ ሴቶች ቢኖሩም ተቀባይነት ባላገኝ ላለመሥራት ተዘጋጅቼ ነበር" ትላለች፡፡ ምክንያቱም በዚያ ወቅት ማንም ስለ እርሷ ስለማያውቅ "ማንም ነበረች።" በሞዴሊንግ ስራ ውስጥ እየቆየች ስትመጣ፣ በምትለብሳቸው ልብሶች ላይ ቁጥጥሯ አነስተኛ ነበር። በሙያዋ የመጨረሻ ጊዜያት ሂጃቧ እያነሰ እና እየቀነሰ ሄደ። አንዳንድ ጊዜ አንገቷን እና ደረቷን ያሳይ ነበር። አንዳንድ ጊዜም በሂጃብ ምትክ ጂንስ ወይም ሌሎች ልብሶችን እና ጨርቆችን ጭንቅላቷ ላይ ታደርግ ነበር፡፡ ሌላኛው የሀሊማ የስራ ውል ውስጥ የተካተተው አንቀጽ በራሷ የግል ቦታ መልበስ እንድትችል አድርጓል፡፡ ሆኖም እሷን ተከትሎ ወደ ኢንዱስትሪው የገቡ ሌሎች ሂጃብ የሚለብሱ ሞዴሎች ተመሳሳይ አክብሮት እንደሌላቸው ወዲያው ተገነዘበች፡፡ ልብስ የሚለውጡበት መጸዳጃ ቤት ፈልጉ ሲባሉ ሰምታለች፡፡ "እነዚህ ሴቶች የእኔን ፈለግ እየተከተሉ ቢሆንም የተከፈተከላቸው በር የአንበሳው አፍ ነው" አልኩኝ፡፡ ተተኪዎቿ ከእርሷ እኩል እንዲሆኑ ትጠብቅ የነበረ ሲሆን ለእነሱ ያላት የመከላከያ ስሜትንም አጠናከረ፡፡ "ብዙዎቹ በጣም ወጣት ሲሆኑ ዘግናኝ ኢንዱስትሪ ሊሆንባቸው ይችላል። በተካፈልንባቸው መዝናኛ ቦታዎች እንኳን አንዷን ሂጃብ የምትለብስ ሞዴል ከሚወሯት ወንዶች ለመከላከል እንደምትጥር ትልቅ እህት ሆኜ ራሴን አገኛለሁ። 'ይህ ትክክል አይመስልም ፣ ልጅ ነች' የሚል ስሜት ውስጥ ነበርኩ፡፡ ወደ ውጭ አውጥቼ ከማን ጋር እንደሆነች እጠይቃታለሁ" ትላለች። የሃሊማ የኃላፊነት ስሜት እና ማህበራዊ ህይወት በተወሰነ ደረጃ የመጣው የሶማሌ ተወላጅ ከመሆኗ ነው፡፡ በሰሜን ምዕራብ ኬንያ በሚገኘው ካኩማ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ልጅ ሆኖ ጠንክሮ መሥራት እና ሌሎችን መርዳትን ከእናቷ ተማረች፡፡ ይህም ተግባሯ ሀሊማ የሰባት ዓመት ልጅ ሳለች አሜሪካ ውስጥ ብዙ የሶማሊያ ማህበረሰብ በሚኖሩባት ሚኔሶታ ከተዛወሩ በኋላም ቀጠለ፡፡ ሃሊማ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆና የመጀመሪያዋ ሂጃብ የምትለብስ ንግስት ስትሆን ችግር ተፈጠረ፡፡ ጥሩ ውጤት ላይ ያተኮረችው እናቷ እንደማይወዱት ታውቅ ነበር፡፡ "በጣም አፍሬ ነበር ምክንያቱም ልጆቹ ወደ ቤትዋ ይመጡና እናቴ ያዘጋጀችውን 'ይህንን አታድርጊ' ይላሉ'' ብላለች። ፍርሃቷ ትክክል ነበር፡፡ የሃሊማ እናት ዘውዱን ሰበረችው፡፡ "በጣም ስለጓደኞችሽ እና በውበት ውድድሮች ላይ እያተኮርሽ ነው" አሏት። ሃሊማ በወይዘሪት ሚኒሶታ አሜሪካ የ2016 ውድድር ላይ ተሳተፈች። የመጀመሪያዋ ሂጃብ የለበሰች ተወዳዳሪ ስትሆን ግማሽ ፍፃሜ ለመድረስም በቃች፡፡ ከእናቷ በተጻራሪ ሃሊማ በሞዴልነት ሙያ ለመሰማራት መረጠች። እናቷ ሙያው ሃሊማ ጥቁር፣ ሙስሊም እና ስደተኛ ከመሆኗ ጋር አብሮ አይሄድም ብለው ያስባሉ፡፡ በዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ስትሳተፍም ሆነ በወይዘሪት ዩ ኤስ ኤ ላይ ዳኛ ስትሆን እናቷ "ትክክለኛ ሥራ እንድታገኝ" ያበረታቷት ነበር፡፡ የሃሊማ የበጎ አድራጎት ሥራ ነው እናቷን ለማሳመን በተወሰነ መልኩ የረዳት፡፡ ለተሻለ ኑሮ ከሶማሊያ ወደ ኬንያ ለ12 ቀናት በእግር የተጓዘች ስደተኛ በመሆኗ የተቸገሩትን መርዳት ያለውን ፋይዳ ታውቃለች፡፡ "እርሷም 'ለሰው መልሶ መርዳት ባይኖረው ሞዴሊንግን የምትቀጥይበት ምንም መንገድ የለም' አለች፡፡ ከኤም ጂ አይ ጋር ባደረግሁት የመጀመሪያ ስብሰባ ወደ ዩኒሴፍ እንዲወስዱኝ ነግሬያቸዋለሁ ትላለች ሀሊማ። አይ ኤም ጂ ደገፋት እና በ2018 ሃሊማ የዩኒሴፍ አምባሳደር ሆነች፡፡ ልጅነቷን በስደተኞች ካምፕ በማሳለፍዋ ሥራዋ በህፃናት መብት ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ "እናቴ እንደ ሞዴል በጭራሽ አላየችኝም፡፡ የወጣት ሴቶች የተስፋ ብርሃን እንደሆንኩ ትመለከተኛለች። ለእነሱም ጥሩ አርአያ እንደምሆን ሁልጊዜ ያስታውሰኛል" ብላለች። ሃሊማ ለተፈናቀሉ ሕፃናት ግንዛቤን ከፍ ለማድረግ እንዲሁም እሷ ያለመችበት እንደደረሰች ሁሉ እነሱም አንድ ቀን እንደዚያው እንደሚያደርጉ ተስፋ እንዲያደርጉ ለማሳየት ፈለገች፡፡ ዩኒሴፍ ግን እንደጠበቀችው አልሆነላትም፡፡ በ 2018 የዩኒስፍ አምባሳደር ሆና ብዙም ሳይቆይ ቴድ ቶክ ላይ ለመቅረብ የካኩማ ካምፕን ጎብኝታለች፡፡ "ልጆቹን አግኝቼ 'አሁንም ነገሮች እንደነበሩ እየተከናወኑ ነው? አሁንም በአዳዲስ መጤዎች ፊት መደነስ እና መዘመር አለባችሁ?' ስላቸው 'አዎ ግን አሁን እኛ ወደ ካምፕ ለሚመጡ ሌሎች ታዋቂ ሰዎች አናደርግም። አሁን 'ላንቺ እናደርጋለን' ብለዋል፡፡" ሀሊማ የጥፋተኝነት ስሜት ተሰማት ተናደደች፡፡ እሷ እና ሌሎች ልጆች ዝነኛ ሰዎች ለመጎብኘት ሲሄዱ ሲዘምሩ እና ሲጨፍሩ እንደነበር አሁንም ድረስ እንደምታስታውስ ትናገራለች፡፡ ድርጅቱ በልጆች ትምህርት ላይ ከማተኮር ይልቅ በስሙ ላይ ያተኮረ መስሎ ታያት፡፡ "የራሴን ስም መፃፍ በማልችልበት ጊዜ እንኳን 'ዩኒሴፍ' ብዬ መጻፍ እችል ነበር ትላለች፡፡ ሚኔሶታ የመጀመሪያውን መጽሐፌን፣ የመጀመሪያ እርሳሴን እና የመጀመሪያዬን ቦርሳዬን ሰጠኝ፡፡ ዩኒሴፍ ግን ይህን አላደረገልኝም፡፡" ጥላ ከሄደች በኋላ ያ ሁሉ እንደተለወጠ ትገምታለች፡፡ ለዓለም የህፃናት ቀን በካኩማ የሚገኙትን ልጆች በቪዲዮ ስታነጋግራቸው መቀጠል እንደማትችል ወሰነች፡፡ በዚህ በኮሮና ወረርሽኝ ወቅት እና በክረምቱ እነሱን ማየት ከባድ ነበር፡፡ "ከልጆቹ ጋር ከተነጋገርኩ በኋላ ወሰንኩ" ትላለች ፡፡ ዩኒሴፍ ዩ ኤስ ኤ ለቢቢሲ እንደተናገረው "ለሃሊማ የሶስት ዓመት ተኩል አጋርነትና ድጋፍ እናመሰግናለን፡፡ አስደናቂ የመቋቋም እና የተስፋ ታሪኳ የእያንዳንዱን ልጅ መብት ወደሚያስከብር ራዕያዋ መርቷታል፡፡ ዩኒሴፍ ከሃሊማ ጋር አብሮ በመሥራቱ ዕድለኛ ሲሆን ለወደፊት ሥራዋ መልካሙ እንዲገጥማት እንመኛለን።" ሃሊማ ሞዴሊንግ ሞያዋ ያላት ጥርጣሬም እየባዛ ነበር፡፡ በፋሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ ፍላጎቷ እየጨመረ በሄደ ቁጥር፣ ከቤተሰቦቿ ጋር የምታሳልፈው ጊዜ አነስተኛ ሆነ። በሙስሊም ሃይማኖታዊ በዓላትም ከቤት ውጭ ታሳልፍ ጀመር፡፡ "በሙያዬ የመጀመሪያ ዓመት ለዒድ እና ለረመዳን ቤት ማሳለፍ ችያለሁ። ባለፉት ሦስት ዓመታት ግን እየተጓዝኩ ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ በሳምንት ከስድስት እስከ ሰባት በረራዎች ይኖረኛል፡፡ በቃ ማቆሚያ የለውም' ትላለች፡፡ በመስከረም 2019 በ 'ኪንግ ኮንግ' መጽሔት የፊት ሽፋን ላይ ደማቅ ቀይ እና አረንጓዴ የአይን ማስዋቢያ እና በፊቷ ላይ ትልቅ ጌጥ አድርጋ ታየች፡፡ ጭምብል የሚመስል እና ከአፍንጫዋ እና ከአፍዋ በቀር ሁሉንም ነገር ይሸፍናል፡፡ "ዘይቤው እና ሜካፑ በጣም የሚያስፈራ ነበር። እኔን የሚመስል ነጭ ሰው ነበር የምመስለው" ትላለች። አስደንጋጭ በሆነ መልኩ በተመሳሳይ ዕትም ውስጥ አንድ እርቃኑን የሆነ ወንድ ፎቶ አገኘች፡፡ "ሂጃብ የለበሰች ሴት ባለችበት መጽሔት ላይ እርቃኑን የሆነ ሰው በሚቀጥለው ገጽ ላይ መኖሩን መጽሔቱ እንዴት ተቀባይነት አለው ብሎ ያስባል? ብላ ትጠይቃለች፡፡ ካመነችበት ሁሉ ጋር ተቃራኒ ሆነ፡፡ ኪንግ ኮንግ ለቢቢሲ "አብረን የምንሠራቸው አርቲስቶች፣ ፎቶግራፍ አንሺዎች እና አስተዋፅዖ አድራጊዎች አንዳንዶቹን ሊማርኩ እና ሌሎችንም ቀስቃሽ ሊመስሉ በሚችሉ መንገዶች ራሳቸውን ይገልጻሉ። ነገር ግን የሚፈልጓቸው ታሪኮች ሁሌም ርዕሰ ጉዳዩን እና ሞዴሉን ያከብራሉ' ብሏል፡፡ "ሃሊማ ከእኛ ጋር በሠራችው ሥራ፤ በግሏ ያልወደደቻቸው እና የእሷ ባህሪ ጋር በምንም መልኩ የማይገናኙ ምስሎች በመኖራቸው እናዝናለን፡፡" ሃሊማ በአውሮፕላን ማረፊያዎች ሆና በመጽሔቶች ሽፋን ላይ ያሉትን ፎቶግራፍዋን ስትመለከት ብዙውን ጊዜ ራሷን መለየት እንደሚያቅታት ትናገራለች፡፡ "እራሴን ማየት ስለማልችል ደስታዬ ዜሮ ነው። ሌላ ሰው መሆን ምን ያህል የአዕምሮ ጉዳት ሊኖረው እንደሚችል ያውቃሉ? ደስተኛ እና አመስጋኝ መሆን ሲገባኝ እና መገናኘት ሲኖርብኝ፣ ያ እኔ ነኝ? የራሴን ስዕል ግን ከእኔ በጣም ሩቅ ነበር፡፡" "የሙያ ሥራዬ ከፍተኛ መስሎ ቢታይም በአዕምሮዬ ደስተኛ አልነበርኩም፡፡ " ሌሎች ችግሮችም ነበሩ። ስለሂጃብ ያላት ሕግ እስኪበጠስ ድረስ እየከረረ መጣ፤ እንዲሁም ሌሎች ሂጃብ የሚለብሱ ሞዴሎችም የሚስተናገዱበት መንገድም እንደዛው። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሁሉንም ነገር ቀያየረ፡፡ በኮቪድ -19 የፋሽን ሥራዎችን ሲቆሙ ከምትቀርባት እናቷ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ "2021ን እያሰብኩ በጭንቀት ውስጥ ነበርኩ፤ ምክንያቱም ከቤተሰቦቼ ጋር ቤት መቆየት እና ጓደኞቼን እንደገና ማየት እፈልግ ነበር" ትላለች። በዚህም ባለፈው ጥቅምት የሞዴሊንግን እና የዩኒሴፍ ሚናዋን ለመተው ወሰነች፡፡ "ኮቪድ ለሰጠኝ አዲስ ዕድል አመስጋኝ ነኝ። ሁላችንም ስለ ሙያ መንገዳችን እያሰላሰልን 'እውነተኛ ደስታን ያመጣልኛል ፣ ደስታ ያስገኛል?' ብለን እንጠይቃለን" ትላለች። የእናቷ ጸሎቶች በመጨረሻ ደረሰ፡፡ "ሞዴል በነበርኩበት ጊዜ እናቴ እያንዳንዱን ፎቶ መነሳት አልተቀበለችም። የእናት እና የልጅ ፎቶ መነሳትን እንኳን አታከናውንም ነበር" ትላለች ፡፡ "እርሷ በእውነት የእኔ ቁጥር አንድ አርዐያዬ ነች። ፈጣሪ የእሷ ልጅ እንድሆን ስለመረጠኝ በጣም አመስጋኝ ነኝ። በእውነቱ አስደናቂ እና ጠንካራ ሴት ነች፡፡" ሃሊማ የምትደሰተው በፎቶግራፉ ብቻ አይደለም፡፡ በአፍጋኒስታን ውስጥ ያለውን ጦርነትን እና ዓመፅን በመሸሽ ላይ በተመሠረተ የእውነተኛ ታሪክ ፊልም ዋና አጋጅ ሆና አጠናቃለች፡፡ 'አይ አም ዩ' በመጋቢት ወር በአፕል ቴሌቪዥን ሊለቀቅ ተዘጋጅቷል። "ለኦስካር እጩ መሆናችንን ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን" ትላለች። ዩኒሴፍን መተው ማለት ሃሊማ የበጎ አድራጎት ሥራ መስራቷን ትታለች ማለት አይደለም፡፡ "ፈቃደኛነቴን አላቆምም" ትላለች፡፡ ዓለም እንደ ሞዴል ወይም እንደ ዝነኛ ሰው የምትፈልገኝ አይመስለኝም። የምትፈልገኝ የአንድ ሳንቲምን እና የማህበረሰብን ጥቅም እንደምታውቅ የካኩማዋ ሃሊማ ትፈልጋለች፡፡" መጀመሪያ ግን እረፍት ልታደርግ አስባለች ፡፡ "ታውቃላችሁ ተገቢ እረፍት በጭራሽ አላውቅም፡፡ የአእምሮ ጤንነቴን እና ቤተሰቦቼን ቅድሚያ እሰጣለሁ። የአዕምሮ ጤንነቴ እየታየሁ እና ሕክምና በማግኘት ላይ ነኝ። "
news-47906549
https://www.bbc.com/amharic/news-47906549
በአዲስ አበባ ሊፈጸም የነበረ የሽብር ጥቃት መክሸፉ ተነገረ
የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በተለያዩ ርዕስ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል። ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ ሊፈጸም ታስቦ ሳይሳካ ስለቀረ የሽብር ጥቃት፣ በሃገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች ስለተከሰቱት ግጭቶች፣ ትናንት እና ዛሬ በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ግለሰቦች በመግለጫው የተነሱ ጉዳዮች ናቸው።
ከአልሸባብ ጋር ግነኙነት አላቸው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ የሽብር ጥቃት ሊፈጽሙ ሲሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ተናግረዋል። አቶ ብርሃኑ ጨምረውም ከፍተኛ የሽብር ጥቃት በሀገሪቱ ለመፈፀም ሲዘጋጁ የነበሩ ቁጥራቸው ያልተጠቀሱ ተጠርጣሪዎች መያዛቸውንና ተጠርጣሪዎቹ ከሌሎች ዓለም አቀፍ የሽብር ቡድኖች ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ሽብር የሚፈፅሙበትን ስልት በመቀየስ እና ቦታ በመለየት ላይ እንደነበሩ ጠቁመዋል። • የፀረ ሙስና ዘመቻው አንድምታዎች የሽብር ጥቃቱን ለመፈጸም በዝግጅት ላይ የነበሩትን ተጠርጣሪዎች ከብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ጋር በመተባባር አደጋ ከማድረሳቸው በፊት በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን ገልጸዋል። አቃቤ ሕጉ እንዳሉት የሽብር ጥቃቱን ሊፈጽሙ ነበር ከተባሉት ተጠርጣሪዎች ላይ ተገኙ በተባሉት ሰነዶች መሰረት የሽብር ጥቃቱን ቢፈፀሙ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ ይችል እንደነበር አመልክተዋል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ጥቃቶቹ ህዝብ በስፋት በሚሰበሰብባቸው ስፍራዎች ሊፈጸሙ ታቅደው እንደነበረ ተናግረዋል። ታስበው ስለነበሩት የሽብር ጥቃቶች ዝርዝር መረጃ ይፋ እንደሚሆንም አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ተናግረዋል። መግለጫውን የሰጡት ዋና አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ጸጋዬ ከግንቦት 2010 ዓ.ም እስከ መጋቢት 2011 ዓ.ም ድረስ 21 መትረየሶች፣ 270 በላይ ኤኬ47 ክላሽንኮቮች፣ 33ሺህ ሽጉጦች እና ወደ 300ሺህ የሚጠጉ ጥይቶች መያዛቸውንም ተናግረዋል። በምዕራብ ኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልል መስቃን፣ በወሎ እና በቅማንት አካባቢዎች በተከሰቱት ግጭቶች ዙሪያ ምርመራዎች እየተካሄዱ መሆኑን ጠቅላይ ቃቤ ሕጉ ጨምረው ተናግረዋል። • የሜቴክ ሰራተኞች እስር ብሔር ላይ ያነጣጠረ እንዳልሆነ ተገለፀ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስለዋሉት ግለሰቦች ተጨማሪ መረጃ የሰጡት ዋና አቃቤ ሕጉ የመንግሥት ንብረት ግዢና ማስወገድ አገልግሎት ኤጀንሲ እና የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አመልክተዋል። ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ በሰጡት መግለጫ እንደጠቆሙት፤ በሦስት የተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ከተፈፀሙ የሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ ባለስልጣናትና ባለሀብቶች ጨምሮ 59 ሰዎች በፖሊስ መያዛቸውን ገልጸዋል። ባለፉት ሦስት ወራት የተደረገን ምርመራን ተከትሎ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ያመለከቱት አቶ ብርሃኑ ምርመራው የወንጀል ድርጊቶቹና ያስከተሉት ጉዳት ከእያንዳንዱ ተጠርጣሪ አንጻር መረጃ መሰብሰቡን ተናግረዋል። በመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዳደር አገልግሎት ተቋም ላይ በተካሄደው የምርመራ ከ400 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ ጋር በተያያዘ 24 ሚሊዮን ዶላር ከመመዝበሩ በተጨማሪ ተጠርጣሪዎቹ የዳቦ እጥረት እንዲከሰት በማድረግ በህዝብና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ማድረሳቸው ተጠቁሟል። ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ በተጨማሪም በውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ውስጥ በመመሳጠር ከ55 ሚሊዮን ብር በላይ ከሕግ ውጪ በተፈፀመ ግዢ የሙስና ወንጀል መፈጸሙን ጠቅሰዋል። እንዲሁም የመድሃኒት ፈንድ ኤጀንሲም ከሕግ ውጪ የ79 ሚሊዮን ብር ግዥ መፈጸሙን አመልክተዋል። አቶ ብርሃኑ ጸጋዬ ሊፈጸም ስለነበረው ጥቃትና ሌሎቹም ጉዳዮች በምርመራ ሂደት ላይ በመሆናቸው ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ከመስጠት ተቆጥበዋል። • የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማስጠንቀቂያ ምን ያህል ተጨባጭ ነው? ቀደም ሲል በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር፣ በምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን፣ የመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ እና ከኢትዮጵያ የውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ውስጥ የሚገኙ ስድሳ አንድ ሰዎች በሙስና ተጠርጥረው በፖሊስ መያዛቸው መዘገቡ ይታወሳል። ከተያዙት ሰዎች መካከል እስካሁን ማንነታቸው የተጠቀሰው የመንግሥት ግዢና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይገዙ ዳባ እና የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ኃላፊ ሲሆኑ ቀሪዎቹ በተለያዩ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ በኅላፊነት የሚሰሩ ሌሎች 59 ሰዎች ናቸው። በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በመንግሥት ሃብት ምዝበራ፣ በሙስናና በኢኮኖሚያዊ ሻጥር ተጠርጥረው መሆኑንም የተለያዩ ምንጮች ገልጸዋል። ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት ጠቅላይ አቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በጋራ በመሩት ዘመቻ ትናንት ሲሆን በተጠረጠሩበት ወንጀል ላይ አስፈላጊው መረጃ መሰብሰቡም ተጠቅሷል።
news-48957925
https://www.bbc.com/amharic/news-48957925
"አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ህወሓት ተጠያቂ ነው" አዴፓ
ትናንት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ማካሄዱን ተከትሎ፤ ከትናንት በስትያ ህወሓት ለሰጠው መግለጫ ምላሽ ሰጥቷል። በመግለጫው አገሪቷ አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት ህወሓትን ተጠያቂ ያደረገ ሲሆን፤ የሕወሐትን መግለጫም የአማራን ሕዝብ ህልውናና ክብር የማይመጥን ብሎታል።
በተጨማሪም፤ ህወሓት በፀረ-ለውጥ እንቅስቃሴው አገራዊና ክልላዊ ለውጡ በጥርጣሬ እንዲታይ ከጥፋት ኃይሎች ጀርባ መሽጐ አመራር እየሰጠ ባለበት ሁኔታ፣ ሕዝብና አገር በድፍረት የዘረፉ ሌቦችን፣ በብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ልጆች ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን አቅፎና ደብቆ በያዘበት ሁኔታ የትህነግ/ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ፤ የዘመናት አስመሳይነቱን ያጋለጠ፣ ራሱን ብቸኛ የኢትዮጵያ ጠበቃ አስመስሎ መቅረቡ የሞራል እና የተግባር ብቃት የሌለው ድርጅት መሆኑ እንዲታወቅም በማለት ወንጅሎታል። •አዴፓ እነ ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ፅጌን "የእናት ጡት ነካሾች" አለ •የህወሐት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሙሉ መግለጫ ምን ይላል? ከዚህም በተጨማሪ አዴፓ በከፍተኛ አመራሮቻችን ላይ በተፈፀመው የግፍ ግድያ ሐዘን ላይ ባለበት ሰዓት ሕወሐት ይህንን መግለጫ ማውጣቱ ከ'እህት' ፓርቲ እንደማይጠበቅና ሕወሐትም አዴፓን ይቅርታ መጠየቅ አለበት ብሏል። የአዴፓስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ያወጣው ሙሉ መግለጫ የሚከተለው ነው የድርጅታችን አዴፓ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ሰኔ 15፣ 2011 ዓ.ም በክልላችን መንግስት ላይ ተሞክሮ ሙሉ በሙሉ በከሸፈው መፈንቅለ-መንግሥት እና በከፍተኛ አመራሮቻችን ላይ በተፈፀመው የግፍ ግድያ ምክንያት የማዕከላዊ ኮሚቴያችን ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ባስቀመጣቸው አቅጣጫዎች ላይ ተመስርቶ በወቅታዊ ጉዳይ እና ቀጣይ የትግል አቅጣጫዎች ግምገማ ለማድረግ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም እየመከረ ባለበት፣ የአማራ ህዝብና የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ከጥልቅ ሃዘናችን ባልተላቀቅንበት በዚህ ነባራዊና ህሊናዊ ሁኔታ ውስጥ ሆነን "በሰው ቁስል እንጨት ቢሰዱበት" እንዲሉ፣ የትህነግ/ህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ሐምሌ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ የትህነግ/ህወሓትን የነበረና እየቀጠለ ያለ አሳፋሪ የሴራ ፖለቲካ እርቃኑን በአደባባይ ያጋለጠ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ "ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል እንዲሉ" አገራችን አሁን ለምትገኝበት የፖለቲካ ብልሽት እራሱ ዋና ተጠያቂ ሆኖ ሳለ፣ የአማራን ህዝብ ህልውናና ክብር የማይመጥን መግለጫ አውጥቷል፡፡ ምንም እንኳን የድርጅታችን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ለስብሰባ የተቀመጠው ካጋጠመን ወቅታዊ ችግር በፍጥነት እንዴት መውጣት እንዳለብን እና የለውጡን ቀጣይነት ጠብቀን መዝለቅ እንደሚገባን ለመምከር ቢሆንም፣ የትህነግ/ሕወሓት መግለጫ ከሐዘን ባልወጣንበት ሁኔታ ከአንድ እህት ፓርቲ የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት በመሆኑ፣ ድርጊቱን ለማውገዝና ለአብሮነትና ለትግራይ ህዝብ ባለን ክብር እያየን እንዳለየን የታገስነውና እና ያለፍነውን ነገር ሁሉ፣ ትህነግ/ሕወሓት በመግለጫው "እራሱ ነካሽ፣ እራሱ ከሳሽ" ሆኖ በመቅረቡ ይህ የአዴፓ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መግለጫ አስፈላጊና ወቅታዊ ሆኖ አገኝተነዋል፡፡ የትህነግ/ሕወሓትን መሠሪ እና አሻጥር የተሞላበት የዘመናት ባህሪውን በማጋለጥ፣ የአማራ ህዝብን ጨምሮ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ባደረጉት ቆራጥ ትግል የተገኘውን ህዝባዊ ድል ደግሞ ደጋግሞ በማንኳሰስ እና ፈፅሞ አክብሮት የማያውቀውንና እራሱ ሲጥሰው የነበረውን ህገ-መንግስታዊና የፌዴራል ስርዓት ጠበቃ በመምሰል፣ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ጭቁን ህዝቦችን በማደናገር ለዳግም ሰቆቃ እንዲዳረጉ እያደረገ ባለበት፣ በፀረ-ለውጥ እንቅስቃሴው አገራዊና ክልላዊ ለውጡ በጥርጣሬ እንዲታይ ከጥፋት ሃይሎች ጀርባ መሽጐ አመራር እየሰጠ ባለበት ሁኔታ፣ ለኢትዮጵያ ህዝቦች የለውጥ ፍላጐት መነሻ ተደርገው የተወሰዱ አሳሪና ደብዳቢ ፀረ-ዴሞክራቶችን፣ ህዝብና አገር በድፍረት የዘረፉ ሌቦችን፣ በብሄር፣ ብሄረሰቦች ህዝቦች ልጆቹ ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት የፈፀሙ ተጠርጣሪ ወንጀለኞችን አቅፎና ደብቆ በያዘበት ሁኔታ የትህነግ/ሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ያወጣው መግለጫ የዘመናት አስመሳይነቱን ያጋለጠ፣ እራሱን ብቸኛ የኢትዮጵያ ጠበቃ አስመስሎ መቅረቡ የሞራል እና የተግባር ብቃት የሌለው ድርጅት መሆኑ የሚታወቅ ነው፡፡ ትህነግ/ሕወሓት ከምስረታው ጀምሮ በ1968 ማኒፌስቶው የአማራን ህዝብ በጠላትነት የፈረጀ፣ ከሌሎች ወንድምና እህት ህዝቦች ጋር ተከባብሮና ተሰናስሎ በፍቅር እንዳይኖር "ትምክህተኛና ሌሎች አግላይ ስያሜዎችን እየሰጠ ለዘመናት የፈፀመው ግፍና በደል ሳያንሰው ዛሬም ከለውጥ ማግስት በአደባባይ ተሸንፎ ህዝባዊ እርቃኑ በተጋለጠበት በዚህ ሰዓት፣ አጠቃላይ ትግሉ የኢትዮጵያ ህዝቦች የትህነግ/ህወሓትንና የጥፋት ኃይሎችን እኩይ ድርጊት መፋለም ሆኖ ሳለ ትግሉ በትህነግ/ህወሓትና በአዴፓ መካከል የሚካሄድ በማስመሰል፣ ወቅታዊ ጉዳታችንን እንደ ዘላቂ ሽንፈትና ውድቀት በመቁጠር፣ ዛሬም የአማራን ህዝብ አንገት ለማስደፋት "የተቀበረውን የትምክህት ትርክቱን ዳግም ይዞ ብቅ ማለቱ ድርጅቱ መቼም ቢሆን መፈወስ የማይችል በሽታ ያለበት መሆኑን ያጋለጠ ተግባር ነው፡፡ •"የለውጥ አመራሩን ሳይረፍድ ከጥፋት መመለስ ይቻላል" እስክንድር ነጋ በእርግጥም ትህነግ/ሕወሓት በዚህ ባህሪው ይታወቃል፡፡ በፅናት የሚታገሉትንና ከኔ ጎን አይሰለፉም የሚላቸውን ኃይሎች ሲሻው ትምክህተኛ፣ ሲሻው ጠባብና አሸባሪ በማለት ታርጋ እየለጠፈ የሚያሸማቅቅ ፀረ-ዴሞክራሲያዊ ድርጅት መሆኑ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ያውቀዋል፡፡ በመሆኑም የትህነግ/ሕወሓት መግለጫ አዲስ ነገር ይዞ የመጣ ሣይሆን የተለመደ ፖለቲካዊ ሴራ ማሳያ ነው፡፡ ትህነግ/ህወሓት ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የሁለት አገረ-መንግስት እይታ ያለው፣ አንድም ቀን ለህዝቦች አንድነት የማይጨነቅ፣ በስልጣን ላይ እስከቆየና ዕላፊ ጥቅም እስካገኘ ድረስ ብቻ አስመሳይ የአንድነት ኃይል ሆኖ መቀጠል የሚፈልግ፣ ነገር ግን እንደዛሬው በስልጣን ላይ ሆኖ በአድራጊ ፈጣሪነት ሁሉንም ማሳካት ሳይችል ሲቀር፣ በቁም ቅዥትና ከትግራይ ህዝብ ስነ-ልቦና ባፋነገጠ መልኩ "የዥዋዥዌ ፖለቲካን" የሙጥኝ ያለ እምነት የማይጣልበት ድርጅት ነው፡፡ •"ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ" ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ የአማራ ህዝብና መሪ ድርጅታችን አዴፓ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣ ለሐቀኛ የፌዴራሊዝም ስርዓት፣ ለእውነተኛ ህገ-መንግስታዊ ስርዓትና ለእውነተኛ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣ ለጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት ፅኑ እምነት ይዞ የሚታገል ህዝብና ድርጅት እንጂ ትህነግ/ሕወሓት ደጋግሞ እንደሚከሰው ሳይሆን ለአገር አንድነት የሚተጋ፣፣ በሌሎች ጉዳት ላይ የተመሠረተ ተናጠላዊ ጥቅምን ማረጋገጥ የማይፈልግ፣ ሐቀኛና ህዝባዊ ድርጅት ነው፡፡ አሁን በምንገኝበት የለውጥ መድረክም የአማራ ህዝብና ድርጅታችን አዴፓ ሆን ተብሎ የተበላሸውን አገራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታችን እንዲታረም፣ ከሌሎች የለውጥ ሃይሎች ጋር ሆኖ ፊት ለፊት የተፋለመና የለውጡን ውጤቶች ጠብቆ ለመዝለቅ ሌት ከቀን የሚታትር ድርጅት እንጂ እንደ ትህነግ/ሕወሓት በከፋፋይት በሽታ የተጠመደ ድርጅት አይደለም፡፡ ሰኔ 15/2011 ዓ.ም በክልላችን ከፍተኛ አመራሮች እና የኢትዮጵያን አንድነት መስዋዕትነት እየከፈለ ለማስቀጠል በሚተጋው የመከላከያ ሀይላችን የጦር ጄኔራሎች ላይ ያነጣጠረው ግድያ እና የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ በድርጅታችን አዴፓ፣ በአማራ ህዝብና በኢትዮጵያ ህዝቦች ላይ የተፈጸመ ጥቃትና የለውጣችን ከፍተኛ ተግዳሮት መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ በመሆኑም የጥፋት ድርጊቱን ከህዝባችንና ከፀጥታ መዋቅራችን ጐን ተሰልፈን በፅናት የተፋለምነውና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለንበት ነው ብለን እናምናለን፡፡ በሂደቱም ለኢትዮጵያ አንድነት ያለንን ቁርጠኝነት ዳግም ያሣየንበትን ታሪካዊ ወቅትና የትግላችን አንድ አካል የሆነውን ጥረታችንን እንደሌሎች ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች መሪ ድርጅቶች መደገፍና ማገዝ ሲገባ ትህነግ/ሕወሓት ድርጊቱን ለራሱ በሚጠቅመው መንገድ በመረዳት ይቅርታ እንድንጠይቅበት መግለጫ ማውጣቱ ተደማሪ ታሪካዊ ስህተት ከመሆኑም በላይ የተከበረውን የትግራይ ህዝብ ባህልና እሴት የማይመጥን መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ያሣዘነ መግለጫ ነው ብለን እናምናለን፡፡ •"እስሩ አብንን ለማዳከም ያለመ ነው" ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) በእርግጥም ትህነግ/ሕወሓት ይህንን ወቅታዊ ሁኔታ የራሱን የዘመናት ወንጀሎች ለመሸፋፈን ተጠቅሞበታል፡፡ እውነትና ፍትህ ቢኖር ኖሮ ባለፉት ዘመናት በትህነግ/ሕወሓት የሴራ ፖለቲካ ምክንያት ለተለያየ ጥፋት እና እንግልት በተዳረገው መላው የኢትዮጵያ ህዝብና ቅርቃር ውስጥ በወደቀው አገራዊ አንድነታችን ምክንያት ከወገቡ ዝቅ ብሎና ከልቡ ተፀፅቶ የተበደለውን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት ዋነኛው ተጠያቂ ትህነግ/ህወሓት መሆኑን እንረዳለን፡፡ በተጨማሪም ትህነግ/ህወሓት ድርጅታችን አዴፓን በዚህ ደረጃ ጥርስ ውስጥ ያስገባበት መሰረታዊ መነሻ ለዘመናት ሲሰራው የነበረውን ጸረ - ህዝብና ጸረ - ዴሞክራሲያዊ ተግባር ከሌሎች የለውጥ ኃይሎች ጋር ሆነን በግንባር - ቀደምትነት አምርረን በመታገላችንና ጥፋቱ በኢትዮጵያ ህዝቦች ፊት በመጋለጡ ነው፡፡ ይህም ሆኖ ድርጅታችን አዴፓ በኢህአዴግ ግንባር ውስጥ ከትህነግ/ህወሓት ጋር አብሮ እየታገለ መቆየቱን የመረጠው ለትግራይ ህዝብ ካለን ክብር እንዲሁም ትህነግ/ሕወሓትም እራሱ ተፀፅቶ እራሱን ያርማል በሚል ተስፋ ቢሆንም ትህነግ/ሕወሓት በነበረበት ተቸክሎ የሚዳክር ድርጅት በመሆኑ ድርጅታችን አዴፓን ይቅርታ እንዲጠይቅና ከአዴፓ ጋር አብሮ ለመሥራትም የሚቸገር እንደሆነ አድርጐ መቅረቡ "ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ" የድርጅቱ የሴራ ፖለቲካ መገለጫ ነው፡፡ ትህነግ/ሕወሓት መቼም ቢሆን ከብልሹ ፖለቲካ የማይፈወስ ድርጅት በመሆኑ በተደጋጋሚ የህዝባችን የጐን ውጋት ሆኖ በተለያዩ የክልላችን አካባቢዎች እና አጐራባች ክልሎች ከግጭቶች ጀርባ መሽጐ እንደሚያዋጋ እያወቅንም፣ ለዚህም በርካታ ማስረጃዎች በእጃችን ላይ እያሉ ለህዝቦች የእርስ በእርስ ግንኙነትና ለኢትዮጵያ አንድነት ስንል በሆደ-ሰፊነት ብንመለከተውም፣ ዛሬም እንደ ትላንቱ የትግራይ ህዝብ እንደሌሎች ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ከችግር እና ሰቆቃ ባልተላቀቁበት ነባራዊ ሁኔታ ፣ የራሱን እኩይ ወንጀል ለመሸፋፈን፣ በትግራይ ህዝብ ሲምልና ሲገዘት የሚውል ህዝቡን ለጥቃት በሚያጋልጡ ተንኮሎች የተጠመደ የማይማር እና የማይድን ድርጅት ነው፡፡ •አብን ከ100 በላይ አባላቶቼ ታስረዋል አለ በመሆኑም ትህነግ/ሕወሓት ጥርሱን ነቅሎ ባደገበት የሴራ ፖለቲካ እየተመራ፣ ከልክ በላይ በእብሪተኝነት ተወጥሮ በየአካባቢው ጦር እየሰበቀ እና በበሬ ወለደ አሉባልታ ወንድም የሆነውን የትግራይ ህዝብ በተለይም ወጣቱን ለጥፋት እያነሳሳ ለተለያዩ አደጋዎች ተጋላጭ እንዲሆን እየገፋፋው ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ ድርጅታችን አዴፓ እና የአማራ ህዝብ እንደወትሮው ሁሉ ለኢትዮጵያ አንድነት እና ለህዝቦች እኩልነት እንዲሁም ለእውነተኛ ዴሞክራሲ፣ ለእውነተኛ የፌዴራሊዝም ስርዓትና ለእውነተኛ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት በፅናት የሚታገል እንጂ ተንኳሽ እና ጦር ሰባቂ እንዳልሆነ እየታወቀ በተሣሣተ መረጃ ጭቁኑን የትግራይ ህዝብ እና የኢትዮጵያን ብሄር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሌለ ስጋት በመፍጠር አዴፓንና የአማራን ህዝብ ተጠርጣሪ ለማድረግ የሚያደርገው ተከታታይ ቅስቀሳ መወገዝ ያለበት መሆኑን በፅኑ በማመን የሚከተሉትን የአብሮነትና የአጋርነት ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡ •“የመከላከያው በአደባባይ ሚዲዎችን እከሳለሁ ማለት አስፈሪ ነው” ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ 1. ለመላው የድርጅታችን አዴፓ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች፣ አዴፓ ህዝባዊነቱን እንደያዘ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እና ለብሔር፣ ብሔረሰቦች እኩልነት የታገለና የሚታገል የዛሬና የነገ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ነው፡፡ በመሆኑም ለዓላማዎቹ ግብ መሣካት መስዋዕትነት የከፈሉትን ጓዶች ዓላማ ዳር ለማድረስ በፅናት የሚታገል የአማራ ህዝብ ፓርቲ እንጂ እንደ ትህነግ/ሕወሓት ላሉ የሴራ ሃይሎች የሚያጐበድድ ፓርቲ አይደለም፡፡ እንደሚታወቀው በሰኔ 15/2011 ዓ.ም በደረሰብን አደጋ ጉዳታችን ጥልቅ ቢሆንም መላ መዋቅራችንን፣ ህዝቡንና የፀጥታ ሀይሉን ከጐናችን አሠልፈን እኩይ ሴራውን መቆጣጠራችንና እና ማክሸፋችን የሚታወቅ ነው፡፡ •“በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ ክልላችን ከደረሰብን አደጋና ችግር ፈጥኖ እንዲወጣ ሰፊ የማረጋጋት ሥራ በመስራት አሁን ከመቸውም ጊዜ በላይ ወደ-ላቀ ጥንካሬያችን እየተመለስን ሲሆን፣ በወንጀል ድርጊቱ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የተሳተፉ አካላትን ለህግ በማቅረብ ላይ ስንሆን፣ የምርመራ ሥራውም በጥብቅ ዲሲፕሊንና በተቀናጀ አግባብ እየተመራ ይገኛል፡፡ በመሆኑም አጠቃላይ የምርመራ ሥራውንና የህግ ተጠያቂነትን የማረጋገጡን ተግባር በቁርጠኝነት ዳር የምናደርሰው ሲሆን በዚህ ወቅት አደጋውን ለመቀልበስ ከጎናችን ተሰልፎ ሊታገል የሚገባው እህት ድርጅት ትህነግ/ሕወሓት በድርጅታችን እና በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የጥፋት ዘመቻ በፅናት በመመከት ለአማራ ክልል ህዝቦች እኩል ተጠቃሚነትና ለጠንካራ ኢትዮጵያዊ አንድነት የጀመርነውን አገራዊ ለውጥ አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ 2. ለክልላችን ህዝቦች እንዲሁም በኢትዮጵያና በመላው አለም የምትገኙ የአማራ ተወላጆች አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን ጠብቀንና ህብረታችንን አጠናክረን፣ የቀደመ ታሪካችንን ሣንሸራርፍ ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነትና ለብሔር፣ ብሔረሰቦች እኩልነት፣ በአብሮነት መንፈስ በፅናት የምንታገልበት ታሪካዊ ወቅት ላይ መሆናችን፣ የበለጠ የሚያስተሳስረንና የሚያዋህደን እንጂ ከውስጥም ሆነ ከውጭ በሚሸረብ ሴራ የማንለያይና የማንነጣጠል በመሆናችን፣ የትላንት እኩይ ሴራቸውን ዛሬም ሣይረሱ ወቅታዊ ችግሮቻችን እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም አንገት ሊያስደፉን ከሚፈልጉ ትህነግ/ሕወሓትና መሰል የጥፋት ሃይሎች የማንበገር መሆናችንን በፅናት እየገለፅን ከድርጅታችን አዴፓ ጐን ተሰልፋችሁ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም፣ ቀጣይነት ለሚኖረው ልማትና ዋስትና ላለው ዴሞክራሲ በአንድነት እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ 3. ለተከበራችሁ የኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች፣ ድርጅታችን አዴፓ እና የአማራ ህዝብ ባጋጠመው ፈተና ሁሉ ከጐናችን በመሰለፍ አጋርነታችሁን ስላረጋገጣችሁልን በዚህ አጋጣሚ ምስጋናችንን እያቀረብን ዛሬም እንደትላንቱ ለኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች እኩልነት፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚነት፣ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የፌዴራሊዝም ስርዓት፣ እንዲሁም ለሃቀኛ ህገ-መንግስታዊ ስርዓት ከጐናችሁ ሆነን በፅናት የምንታገል መሆኑን እያረጋገጥን፣ ትህነግ/ሕወሓት የዘመናት ወንጀሎቹን ለመሸፈን እና ድርጅታችን አዴፓና የአማራ ህዝብን የሌሎች ህዝቦች ጠላት በሚያደርግ የተሳሳተ አስተምህሮ ዛሬም በጥርጣሬ እንድንተያይ የሚነዛውን የማደናገሪያ ትርክት መሰረተ ቢስ መሆኑን እንደምትገነዘቡ ጽኑ እምነት ያለን ሲሆን ይህን ጸረ ዴሞክራሲና አስመሳይነት ከጐናችን ተሰልፋችሁ በፅናት እንድትታገሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ •የጥላቻ ንግግርን የሚያሠራጩ ዳያስፖራዎች እንዴት በሕግ ሊጠየቁ ይችላሉ? 4. ለተከበርከው የትግራይ ህዝብ የአማራና የትግራይ ህዝቦች ታሪካዊ አንድነትና ውህደት ያላቸው፣ ባህላዊና ጥንታዊ ሃይማኖታዊ እሴቶችን የሚጋሩ፣ በጋብቻና በደም የተሳሰሩ፣ በፀረ-ጭቆና ትግል ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሆነው በአንድ ጉድጓድ ክቡር መስዋዕትነት እየከፈሉ አሁን ላለንበት የአገረ-መንግስት ምስረታ ጉልህ አሻራ ያሳረፉ ህዝቦች ናቸው፡፡ ሆኖም ትህነግ/ሕወሓትና መሠል እኩይ ድርጅቶች በህዝብ ስም እየማሉና እየተገዘቱ፣ በትግራይ ህዝብ ስም እየነገዱ ከሦስት ሺህ ዓመታት በላይ የዘለቀውን የአብሮነት ታሪካችንን በአራት አስርት አመታት የበሬ ወለደ ትርክቶች ለመሸርሸርና ህዝባዊ አንድነታችንን አደጋ ላይ ለመጣል የሚያደርጉት ሴራ መሆኑን አውቃችሁ ከአማራ ህዝብ ጋር ያላችሁ ወንድማዊና ቤተሰባዊ ግንኙነታችሁ ሳይቋረጥ ሁለቱን ህዝቦች የሚያለያዩ ሙከራዎችን በፅናት እንድትታገሉ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርብላችኋለን፡፡ 5. ለእህትና ለአጋር የፖለቲካ ድርጅቶች እንደሚታወቀው ሁሉ አገራችን ኢትዮጵያ ካሏት ዘርፈ ብዙ ጸጋዎችና እሴቶች መካከል ብዝሀነታችን የምንደምቅበት ጌጣችን መሆኑ ለአፍታም ቢሆን አይዘነጋም፡፡ ይሁን እንጂ ትህነግ/ህወሓት ይህን የብዝሀነት ጸጋ ጠብቆ ለማስቀጠል ብቸኛ ተቆርቋሪ በመምሰል ሲያሻው ደግሞ በህዝቦች መካከል የጥርጣሬ አጥር በመፍጠር ህዝባዊ አንድታችንን ለማላላት የከፋፋይነት ፖለቲካውን ሲያራምድበት በመቆየቱ ምክንያት በለውጥ መድረካችን በአንድነት የረገምነው መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ዛሬም እንደትላንቱ ለብሄር ብሄረሰቦች ጥያቄ የተለየ ትኩረት የሰጠ በመምሰል ይህንኑ የአስመሳይነት ድራማውን በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ሲተውን የሚስተዋል ስለሆነ ይህን መሰል እኩይ ተግባር በአንድነትና በጽናት በመፋለም ህዝባዊና አገራዊ አንድነታችንን ጠብቀን የተጀመረውን ለውጥ አጠናክረን እንድናስቀጥል ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ 6. ለኢፌዴሪ የአገር-መከላከያ ሠራዊትና ለክልላችን የፀጥታ ሃይሎች ድርጅታችን አዴፓ እና የአማራ ህዝብ የአገር መከላከያ ሠራዊታችንና የክልላችን የፀጥታ ሃይሎች ህዝባዊነታችሁን ጠብቃችሁ ለአንዲት ሉአላዊት አገር መከበርና ቀጣይነት ክቡር መስዋዕትነት በመክፈል ላይ መሆናችሁን እንገነዘባለን፡፡ ጥንትም ቢሆን ኢትዮጵያ የተመሰረተችውና ጸንታ የቆየችው በጀግኖች አርበኞቻችን ተጋድሎና መስዋዕትነት በመሆኑ፣ በቅርቡም አጋጥሞን በነበረው አደጋ ፈጥኖ ደራሽነታችሁን በማረጋገጥ ክልላችንና አገራችንን ከጥፋት በመታደጋችሁ ምስጋናችንን እያቀረብን ወደፊትም የአገራችንን ሉአላዊነትና የክልላችንን ሁለንተናዊ ደህንነት በማስጠበቅ ሂደት የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ሁሉ በፅናት በማለፍ ህዝባዊነታችሁን እንድታረጋግጡ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡ በመጨረሻም በክልላችንም ሆነ ከክልላችን ውጪ በአማራና በክልሉ ህዝቦች ስም የምትንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ኃይሎች እየሰፋና እየጠነከረ በመጣው የፖለቲካ ምህዳር አዎንታዊ ሚና እድትጫወቱ ጥሪያችንን እያቀረብን በሌላ በኩል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የትህነግ/ሕወሓትን የፖለቲካ ደባ የምታስፈፅሙ ተላላኪ የፖለቲካ ሃይሎችና ቡድኖች ከዕኩይ ድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ በጥብቅ እያሳሰብን ድርጅታችን አዴፓም ሆነ የአማራ ህዝብ ከሌላው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔሰቦች ጋር ሆነን ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እና ለብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት የሚደረገውን ትግል አጠናክረን የምንቀጥል መሆኑን በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡
news-48284663
https://www.bbc.com/amharic/news-48284663
በኮ/ል መንግሥቱ ላይ በተሞከረው በመፈንቅለ መንግሥት ዙርያ ያልተመለሱት 5ቱ ጥያቄዎች
የ81ዱ መፈንቅለ መንግሥትን በተመለከተ ፊልሞች ተደርሠዋል፣ መጻሕፍት ተጽፈዋል፣ የጥናት ወረቀቶች ቀርበዋል...፡፡ አንዳቸውም ግን ለአንኳር ጥያቄዎች ከመላምት ያለፈ ምላሽ አልሰጡም፡፡
ካፒቴን እዮብ አባተ ምናልባትም በጉዳዩ ዙርያ እንደ አቶ ደረጀ ደምሴ የተጋ ተመራማሪ የለ ይሆናል፡፡ አቶ ደረጀ ከሌሎች አጥኚዎች የተለየ ቦታ የሚያሰጣቸው ሁለት አበይት ምክንያቶች አሉ፡፡ አንደኛ ጄ/ል ቁምላቸው በሕይወት ሳሉ አግኝተው ገጽ ለገጽ ማውጋታቸው ነው፡፡ በዚያ ላይ የሟቹ የጄ/ል ደምሴ ቡልቶ 4ኛ ልጅ ናቸው፡፡ • የዛሬ 30 ዓመት... የኮ/ል መንግሥቱ አውሮፕላን ለምን አልጋየም? ‹‹የተሟላ መረጃ ማግኘት አስቸጋሪ ያደረገው ዋናዎቹ ተዋናዮች በሙሉ በመሞታቸው ነው፤ ከዚህ በኋላ በአውዳዊ መረጃ (circumstantial evidence) ነው መናገር የምንችለው›› ይላሉ የሕግ አዋቂው አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ፡፡ ‹‹ሴራው ሲሸረብ በነበረበት የመከላከያ አዳራሽ ቀኑን ሙሉ ምን ሲደረግ እንደነበር መናገር የሚችል ሰው በሕይወት የቀረ የለም" ይላሉ ሌላኛው የጉዳዩ አጥኚ ሻምበል እዮብ አባተ፡፡ ሻምበል እዮብ ቀድሞ የመከላከያ ደኅንነት መኮንን ነበሩ፡፡ በመፈንቅለ መንግሥቱ ዙርያ የሚያጠነጥን ‹‹ጄኔራሎቹ›› የሚል በርከታ ላለ ጊዜ የታተመ መጽሐፍ ደራሲ ናቸው፡፡ ቢቢሲ የመፈንቅለ መንግሥቱን አምስት ያልተመለሱ ጥያቄዎች ለነዚህ ሁለት ሰዎች አንስቶላቸዋል፡፡ 1. የኮ/ል መንግሥቱን አውሮፕላን እንዳይመታ ያዘዘው ማን ነው? መፈንቅለ መንግሥት አድራጊዎቹ የርዕሰ ብሔሩ አውሮፕላን በሚሳይል እንዲመታ አልያም አሥመራ ተገዶ እንዲያርፍ ስምምነት ደርሰው ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ ግን በመጨረሻ ሰዓት ይህ ውጥን ተቀለበሰ፡፡ ለምን? በማን? አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡- "ለማወቅ ፈልጌ ማወቅ ያልቻልኩት ነገር ምንድነው መሰለህ? ይሄ አሁን አንተ የጠየቅከኝን ጥያቄ ነው፡፡ የአውሮፕላኑን ሁኔታ ፕላኑ እንዲቀየር ያደረገው ማን ነው? በምን ሁኔታ ሊቀየር ቻለ? ደግሞስ የመንግሥቱ አውሮፕላን ወድቋል፤ እሱም ተገድሏል የሚለው መልእክት እንዴት ወደ አሥመራ ተላለፈ?... • ጓድ መንግሥቱ እንባ የተናነቃቸው 'ለት ግምትህን ንገረኝ ካልከኝ…ጄ/ል አመሃ ይመስሉኛል አይመታ ያሉት፡፡ ምክንያቱም እርሳቸው ገና ያን ቀን ነው ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ የተነገራቸው፡፡ወደ ደብረዘይት እየሄዱ ነው ከመንገድ ተጠርተው ወደ መከላከያ ሚኒስቴር የገቡት፡፡..." ሻምበል እዮብ አባተ የመጀመርያው ዕቅድ ሰውየው እንዲመቱ ነው። ይሄን የሚደግፉት እነ ጄ/ል አበራ ናቸው። ፕሬዝዳንቱ ካልተገደሉ ነገሩ አይሳካም ብለው ያምናሉ። በአመጽ ውስጥ ያሉት 'ኤርፎርሶች' ደግሞ ይሄን አልደገፉም። በሄደበት ካስቀረነው በቂ ነው ብለው የሚያምኑ ናቸው። አሁን ምንድነው የሆነው... መጨረሻ አካባቢ ውዝግብ ሲሆን ዝርዝር መመሪያ ይወጣል፤ ምን ማድረግ እንዳለባቸው የሚገልጽ። መንግሥቱ ሊወጣ ሲል ይመታል፤ ከዚያ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይታወጃል፣ መከላከያ ዘመቻ መምሪያ አገሪቱን ይመራል። መግለጫው በዚህ ይነበባል የሚል ዝርዝር ነገር አዘጋጅተው ጠበቁ። አመቺ ጊዜ ነበር የሚጠበቀው። ድንገት ግንቦት 8 ፕሬዝዳንቱ ከአገር እንደሚወጡ ተሰማ። ይሄ የተሰማው ግን ግንቦት 7 ነው። በዚህ ምክንያት በቂ ጊዜ አልነበረም። ጥድፊያ ሆነ። • መንግሥቱ እና የኮሎኔል አጥናፉ ኑዛዜ ጊዜ አጠረ። አመቺ ጊዜ ሲጠብቅ ተኝቶ ተኝቶ ድንገት ሆነ። ከዚያ በኋላ ነው እንቅስቃሴው ሁሉ የተጀመረው። አሁን ከጊዜ በኋላ አውሮፕላኑ ከተመታ በውጭ ኃይሎች ዘንድ ተቀባይነት ያሳጣል፣ እንኳን አውሮፕላን ተመትቶ ኩዴታ ራሱ ተቀባይነት ያሳጣል፣ ብዙ ንጹሐን ይጎዳሉ፣ ከዚህ ሁሉ ለምን በስደት አናስቀረውም ብለው በተለይ 'ኤርፎርሶች' ናቸው የተቃወሙት። በኋላ ስብሰባ ላይ አይመታ ሲባል ጄ/ል አበራ ተበሳጭተዋል። ሰውየው ካልተገደለ መፈንቅለ መንግሥት የለም ብለው ነበር። ሌላው አማራጭ አሥመራ ማሳረፍ ነበር፣ "ለጄ/ል ደምሴ እንስጠውና እዚያው ትጥቅ ያስፈታው" የሚል ነበር። እዛ ደግሞ ችግሩ 2ኛው አብዮተዊ ሠራዊት የመንግሥቱ ወዳጅ ነው። በደጋፊዎቻቸው መሀል ይህን ማድረግ ከባድ አደጋ አለው ተባለ። ስብሰባ ላይ ሲወዛገቡ ቆይተው ኋላ ላይ ጄ/ል ፋንታ "አበራ! አሁን ልንመታው አንችልም፥ ከኢትዮጵያ አየር ክልል ወጥቷል። ቀይ ባሕርን እያቋረጠነው" ብለው ነገሩን ደመደሙት። 2. ጄ/ል ቁምላቸው ደጀኔ በምን ተአምር ከአገር ሊወጡ ቻሉ? በጄ/ል ደምሴ ቡልቶ ትእዛዝ ከአሥመራ የአየር ወለድ ጦር በአንቶኖቭ ወደ አዲስ አበባ ጭነው የመጡት ጄ/ል ቁምላቸው ነበሩ፡፡ እስከ ምሽት አምስት ሰዓት ድረስ ጦራቸውን ይዘው አርሚ አቪየሽን ግቢ ቆዩ፡፡ እነ ጄ/ር መርዕድ ራሳቸውን አጥፍተው ኩዴታው መክሸፉ በሬዲዮ ተነግሮ እንኳን እሳቸው በመከላከያ ቅርብ ርቀት ጎማ ቁጠባና ጤና ጥበቃ አካባቢ ቅኝት ሲያደርጉ ነበር፡፡ ድንገት ግን ሌሊት ላይ ተሰወሩ፡፡ በኋላ አሜሪካ ተገኙ፤ ጄ/ል ቁምላቸው እንዴት ከአገር ወጡ? እንደሚባለው የሲአይኤ እጅ አለበት? አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡- እዚህ አሜሪካን አገር አግኝቻቸው ነበር፡፡ ካንሰር ታመው ነበር፡፡እኔ ያለሁበት ቦስተንም መጥተው መጨረሻ ሰዓት አስተምሚያቸዋለሁ፡፡ ብዙ ነገሮችን አጫውተውኛል፡፡ ስለአወጣጣቸው ግን ብዙም ለመናገር ስለማይሹ አልተጫንኳቸውም፡፡ ከሞቱ በኋላ ግን አንድ የአሜሪካ ዜጋ የፌዴራል መረጃ ቋት ላይ የሚገኝን ሰነድ እንዲሰጠው ከጠየቀ እንዲሰጠው በሚያስገድደው ሕግ ተጠቅሜ (*Freedom of Information Act) ይባላል፤ አዲስ አበባ ከሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አንድ መረጃ አገኘሁ፡፡ ሰነዱ አንድ ሰው በዚያ ወቀት በእሳቸው ስም ኤምባሲውን ጥገኝነት እንደጠየቀ ይገልጻል፡፡ እሳቸው ግን ያንን አልገለጹልኝም፡፡ ‹‹የአገሬው ሰው እያቀባበለ ሸኘኝ›› ነው ያሉኝ፡፡ ሻምበል እዮብ አባተ፦ ጄ/ል ቁምላቸውን ያገዛቸው የመንግሥት ባለሥልጣን የሆነ አካል ነው። ያን ሌሊት አንድ ዘመዳቸው የሆነ ፖሊስ ቤት ነው የሄዱት። ሁኔታውን አመቻቸና ወደ ጉራጌ አገር እንድብር እንዲሄዱ አደረገ። በአጋጣሚ ያን ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የኮንግረስማን ሚኪሊላንድ አውሮፕላን የተከሰከሰበት ጊዜ ነበር። የሚኪሊላንድን አስክሬን ለመፈለግ ከአሜሪካ ብዙ መሣሪያዎች መጥተዋል ያኔ። ይሄን ሽፋን አድርገው የአሜሪካ አየር ኃይል ሰዎች ናቸው በዚያው የወሰዷቸው። እንዴት? ያልክ እንደሆነ አንድ ቀን ፍለጋ ላይ የተሰማሩ ሁለት የአሜሪካ ሄሊኮፕተሮች እንድብር ያርፋሉ። ምንድነው ሲባል ነሐሴ ወር ስለነበር ዝናብ ነው፤ አየር ጠባዩ አስቸገረን አሉ፤ እዚያ አረፉ። ሄሊኮፕተሮቹ እዛው ቆሙ፥ አደሩ። • የከሸፈው መፈንቅለ መንግሥት ሥዕላዊ መግለጫ በድብቅ ጄ/ል ቁምላቸውን ወደ ሄሊኮፕተርሳያስገቧቸው አልቀሩም። በማግሥቱ አዲስ አበባ አመጧቸው። ቡድኑ ሥራው ጨርሶ ወደ አሜሪካ ሲመለስ ጄ/ል ቁምላቸውን አሾለኳቸው። ዋሺንግተን ፖስት ጋዜጣ ኦገስት 15 ፥ 1889 ሄሊኮፕተሮቹ እንድብር ማረፋቸውን ይገልጻል። እነሱ የሚሉት የአየር ጠባዩ አስቸገረን ነው። በኋላ የኢትዮጵያ ደኅንነት የደረሰበት ግን ቁምላቸውን ለማሾለክ ነበር እዚያ ያረፉት። 3. ጄ/ል ፋንታ በላይን ማን 'አስገደላቸው'? መፈንቅለ መንግሥቱ ሲከሽፍ እንደ ኮንቴይነር በተቀለሰች አንዲት የቆርቆሮ ዛኒጋባ ውስጥ እዚያው መከላከያ ሚኒስቴር ተደብቀው ሦስት ቀን ከሌሊት ጋር ያሳለፉት ጄኔራሉ በመጨረሻ እጅ ሰጡ፡፡ ከዚያም ማዕከላዊ ተወሰዱ፡፡ ከተወሰኑ ወራት በኋላ ድንገት ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ ተባለ፡፡ እውነት ሊያመልጡ ሲሉ ነው የተገደሉት? አቶ ደረጀ ደምሴ ቡልቶ፦ ስለእርሳቸው ይሄ ነው የሚባል መረጃ የለም፡፡ ከታሰሩ በኋላ ስለ መፈንቅለ መንግሥቱ ዓላማ አንድ ቃለ ምልልስ ሰጥተው ነበር፤ ከኢቴቪ ጋር፡፡ ‹‹መፈንቅለ መንግሥቱን የሞከርነው ማብቂያ የሌለውን ጦርነት ለማቆም ነው›› ነበር ያሉት፡፡ ያኔ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሊያስተላልፈው ባይፈቅድም በኋላ የመንግሥት ለውጥን ተከትሎ ቪዲዮው ወጥቷል፡፡ ምናልባት ያኔ ለጋዜጠኞች ‹‹ይሄን በል፣ ያንን በል›› ተብለው ይሆናል ለቃለ መጠይቅ የቀረቡት፡፡ እርሳቸው ግን ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርተው እውነቱን ስለተናገሩ ይሆናል ያን ጊዜ ያልተላለፈው፡፡ ስላሟሟታቸው ግን ምንም መረጃ የለም፡፡ አንድ ሰው እንደዚህ ሆነው እንደዚያ ተደርገው ተገደሉ ሲል መረጃውን ከየት እንዳመጣው መናገር አለበት፡፡ ጠባቂያቸውን መትተው ሽጉጥ ነጥቀው ሊያመልጡ ሲሉ ተገደሉ የሚሉ አሉ፡፡ መረጃ አለኝ የሚል ግን የለም፡፡በጣም ብዙ ዓይነት ነገር ነው የሚጻፈው፤ ያለበቂ መረጃ፡፡ ሻምበል እዮብ አባተ፦ ግልጽ አይደለም። መላምቶቹ ሁለት ናቸው። አንደኛው መላምት የደኅንነት ሚኒስትሩ አስገድለዋቸዋል ነው የሚባለው። ብዙ ምሥጢሮችን ከማውጣታቸው በፊት። ጄ/ል ፋንታ እዛ ከኮንቴይነሩ ውስጥ በተያዙበት ጊዜ ኮ/ል ተስፋዬ ወ/ሥላሴን ፊትለፊት ሲያይዋቿው «ተስፋዬ አከሸፍከው አደል? ተሳካልህ አይደል?» ብለዋቸዋል። ይሄ በቀጥታ ለኮ/ል መንግሥቱ ተነግሯቸዋል። ሌላው ደግሞ አብዛኛዎቹ የተያዙት ጄኔራሎች የታሰሩት ቤተመንግሥት ነው። እሳቸው ግን ከመከላከያ እንደተያዙ ወደ ማዕከላዊ ነው የተወሰዱት። ለምን ወደዚያ እንዲሄዱ ተፈለገ? ይሄን የሚነግረኝ አላገኘሁም። 4. የደኅንነቱ ሹም ተስፋዬ ወ/ሥላሴ ሴራው ላይ ነበሩበት? አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡- በእኔ አመለካከት ያውቁ ነበር ባይ ነኝ፡፡ ይህንን የምልህ ብልህ ከሆነ ግምት (Educated guess) በመነሳት ነው፡፡ ነገር ግን ልክ አውሮፕላኑ በሰላም ከኢትዮጵያ አየር ክልል መውጣቱን ሲያውቁ አሰላለፋቸውን የቀየሩ ይመስለኛል፡፡ በዚያን ወቅት ሦስት አሰላለፍ ነበር፡፡ በመጀመርያው ረድፍ ወይ እሞታለሁ ወይ መፈንቅለ መንግሥቱን አሳካለሁ የሚሉ ናቸው፡፡ ሁለተኛው የኮ/ል መንግሥቱ ታማኝ ሆኜ እጸናለሁ የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው የኮ/ል መንግሥቱ መውረድ መቶ በመቶ ከተረጋገጠ መፈንቅለ መንግሥቱን እደግፋለሁ፤ እስከዚያው ግን ለማንም ሳልወግን እቆያለሁ የሚል ቡድን ነው፡፡ የደኅንነት ሹሙ በዚህ ጎራ የተሰለፉ ነበሩ ብዬ አምናለሁ፡፡ አባቴ ግን ሰውዬውን ድሮም አያምነውም ነበር፡፡ አንድ ጊዜ አባቴ ታሞ ደኅንነቱ ተስፋዬ ሊጠይቀው መጥቶ ኮ/ል መንግሥቱን ያማለታል፡፡ ‹‹…ሰውዬው አብዷል፤ ምን ማድረግ እንደሚቻል ግራ ገብቶናል፡፡ የምንሰጠውን ምክር ሁሉ አይቀበልም…›› እያለ ስለ ኮ/ል መንግሥቱ አስቸጋሪነት ይተርክለታል፡፡ አባቴ ለምን እሱ ፊት እንደዛ እንደሚናገር ተደንቆ ሲያወራ ሰምቼዋለሁ፡፡ ‹‹ እንዴ! እሱ ሰላይ ነው፡፡ እንደዛ ሊቀመንበሩን ሲያማልኝ እኔ ምን እንድለው ፈልጎ ነው?›› እያለ ሲገረምበት ነበር፡፡ ይህ አጋጣሚ ከመፈንቅለ መንግሥቱ አንድ ዓመት በፊት የሆነ ነው፡፡ ሻምበል እዮብ አባተ፦ ኬጂቢ ስለ መፈቅለ መንግሥቱመረጃ ነበረው። ነገር ግን መረጃውን እንዴት እንዳገኘ ማንም አያውቅም። ለኬጂቢ የሚሠሩ ኢትዮጵያዊያን እንዳሉ ግምት ተሰጥቷል። በወታደራዊ ደህንነት ውስጥ ዋናው ሥራ ጄኔራሎችን መከታተል ነው። ሴራው ሲጎነጎን ኮ/ል ተስፋዬ አያውቁም ማለት ይከብዳል። ጄኔራሎቹም ቢሆን አንዳንድ ጊዜ በመዝናኛ ቦታ ዘብረቅ ማድረጋቸው አልቀረም። የቢሮና የቤት ስልካቸውን ያዳምጣሉ። ፕሬዝዳንቱ ደግሞ ቁጡ ናቸው። ጄኔራሎቹን በሚቆጡበት መጠን ኮ/ል ተስፋዬንም ይቆጧቸዋል። ተስፋዬ ወ/ሥላሴ ከሚችሉት በላይ ጫና ነበረባቸው። ተሰላችተዋል። ጄኔራሎቹም እያለሳለሱ ዕቅዳቸውን ጠቆም ሳያደርጓቸው አልቀረም። "ፕሬዝዳንቱ ሊያምነን አልቻለም፣ ውደቀት ይመጣል። ብስለት የሌላቸውን የካድሬዎችሪፖርት እያዳመጠ እኛን ጠላን" እያሉ አሳማኝ ማስረጃ ይነግሯቸው ነበር። ደኅንነቱ ተስፋዬ ሐሳባቸውን አላጣጣሉም። እንደ ደኀንነት ሰው በአንድ ጊዜ አልተቃወሙም። "እስኪ ነገሩን እናጥናው፥ እናንተም እስኪ አስቡበት" እያሉ ቀርበዋቸዋል። ደኅንነቱ ኮ/ል ተስፋዬ በበኩላቸው"ፕሬዝዳንቱ ከሥልጣን እንዲወገዱ ፍላጎት ነበረኝ። ነገር ግን በእነዚህ ጄኔራሎች አገሪቱ እንድትመራ አልፈልግም ነበር ብለው ተናግረዋል" ከለውጥ በኋላ እስር ቤት ሳሉ። እንደምገምተው ተስፋዬ ለጄኔራሎቹ ትንሽ 'ግሪን ላይት'(ይሁንታ) ሰጥተዋቸዋል። ያንን ይዘው ይመስለኛል ጄኔራሎቹ ሙከራ ያደረጉት። በኋላ ላይ ግን እየራቁ የመጡ ይመስለኛል። 5. ጄ/ል አበራ አበበ መከላከያ ሚኒስትሩን ለምን ገድለው ጠፉ? የመፈንቅለ መንግሥቱን አቅጣጫ ከቀየሩት ኩነቶች አንዱና ዋንኛው ጄኔራል አበራ የመከላከያ ሚኒስትሩን ጄኔራል ኃይለጊዮርጊስን እዚያው መከላከያ ሚኒስቴር ውስጥ ገድለው መሰወራቸው ነው፡፡ የ‹‹ነበር›› መጽሐፍ ደራሲ ዘነበ ፈለቀ "ጄ/ል አበራ ‹‹አብዮት›› እያካሄዱ መሆናቸውን ዘንግተው እንደ ተራ ነፍሰ ገዳይ እግሬ አውጪኝ ማለታቸው የሚያስገርም ነው" ይላል፡፡ ተገቢ ትዝብት ይመስላል። መጀመሪያውንስ መከላከያ ሚኒስትሩን ለምን ገደሏቸው? ምን ለማትረፍ? ጄኔራል አበራ መፈንቅለ መንግሥቱን የማስተባበር በርካታ ኃላፊነቶች እያሉባቸው እንዴት ይህን ድርጊት ፈጽመው ሸሹ? አቶ ደረጄ ደምሴ ቡልቶ፡- ጄኔራል አበራ የኩዴታው ዘመቻ ኃላፊ ናቸው፡፡ ከፍተኛ የጦር መሪ ናቸው፡፡ ብዙ ጀብዱ የፈጸሙ ናቸው፡፡ ለምን ያን እንዳደረጉ ግልጽ አይደለም። ይሄን የሚመልስ ሰው የለም፡፡ አሁን ብዙ የደርግ ካድሬዎች ዝም ብለው ቁንጽል ነገር ይዘው በመሰለኝ መጽሐፍ ይጽፋሉ፡፡ ሀቁ ግን ይህን የሚነግረን አንድም ወሬ ነጋሪ አለመቅረቱ ነው፡፡ የግል ግምቴን ከሆነ የጠየቅከኝ ያን ልነገርህ እችላለሁ፡፡ እንደሚመስለኝ ጄኔራል አበራ ይመጣል የተባለው ጦር እንደማይመጣ ሲያውቁ፣ ሊከበቡ እንደሚችሉ ሲያውቁ፣ የሚደግፋቸው ጦር እንደሌለ ሲያውቁ መሰለኝ የወጡት። የእርሳቸው መውጣት ደግሞ ሁሉንም ነገር አመሰቃቀለ። ምክንያቱም ጄኔራል ቁምላቸው ያን ጦር ይዘው ተነጋገር የተባሉት ከጄኔራል አበራ ጋር ነበር። ጄ/ል አበራ ደግሞ ምናልባት ያ ጦር ካልመጣ ነገሩ ተበላሽቷል ብለው ያሰቡ ይመስላል፡፡ ሻምበል እዮብ አባተ፡ ጄ/ል አበራ መፈንቅለ መንግሥቱ ሂደት ላይ እያለ «ጊዜ ያስፈልገናል፤ ጥናት እናድርግ» ይሉ ነበር። ቶሎ እናድርግ በሚለው ቡድን ተረቱ። መፈንቅለ መንግሥቱ ቶሎ እናድርግ የሚለው ቡድን ጦርነቱን ከተሸነፍን [ከሻዕቢያ ጋር]የመደራደር አቅማችን ይቀንሳል የሚል መከራከሪያን ይዟል። ስብሰባው እየተካሄደም ቢሆን ገባ ወጣ ይሉ ነበር። በዚህ ጊዜ የመከላከያ ሚኒስትሩ ጄ/ል ኃይለጊዮርጊስ ይመጣሉ። የእሳቸው ልዩ ረዳት በር ላይ ያገኟቸዋል። «ጌታዬ አይግቡ፤ ለእርሶ ጥሩ አይደለም። ይመለሱ» ይላቸዋል፤ ስለሚወዳቸው። በመደናገጥ ተመልሰው ይሄዳሉ። ወጣ ገባ የሚሉት ጄ/ል አበራ ኃይለጊዮርጊስ መጥቶ ሄደ ሲባሉ አበዱ፤እራሳቸውን እስከመሳት ደረሱ። አሁን እሱ ሄዶ እዚህ የሚሆነውን ካወቀ ቀጥሎ በታንክ መከበባችን ነው አሉ። አሁን መደናገጥ መጣ። ጸረ መፈንቅለ መንግሥቱን የሚመሩት ደግሞ ሌላ ትልቅ ስህተት ሠሩ። በድጋሚ ሚኒስትሩን ወደ መከላከያ ግቢ ይልኳቸዋል። ስብሰባውን ይበትኑ ተብለውበድጋሚ መጡ። ሲመጡ ከጄ/ል አበራ ጋር ይገጣጠማሉ። ልክ እሳቸው ደረጃውን ሲወጡ፣ አበራ ደረጃውን ሲወርድ ተገናኙ። በሁለት ጥይት መቷቸው። ጄ/ል አበራ የታንክ ድምጽ ሰምተዋል። በልዩ ጥበቃ ብርጌድ ከተከበቡ በኋላ ምንም ማድረግ እንደማይችሉ አውቀዋል። ስለዚህ ተስፋ መቁረጥ አለ። ያ ይመስለኛል ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው። አየር ወለድ ስለነበሩ የመከላከያ አጥርን ዘለው ሲቪል ሰዎች የሚኖሩበት ግቢ ገብተው ካፖርት ቢጤ ለብሰው ነው ያመለጡት። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ጉለሌ በተደበቁበት ተከበው ሊያመልጡ ሲሉ ግንባራቸውን ተመተው ተገደሉ። ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ሁለት ነገር ቆጭቷቸዋል፤ አንዱ የቁምላቸው ማምለጥ ሲሆን አንዱ ደግሞ የጄ/ል አበራ በሕይወት አለመያዝ ነው።
55789371
https://www.bbc.com/amharic/55789371
"ባለቤቴ ጫካ ውስጥ መንታ ተገላግላ አረፈች" የትግራዩ ተፈናቃይ በሱዳን
በትግራይ ክልል ባለው ግጭት ምክንያት በቤቷ ልጆቿን መገላገል ያልቻለችው ነፍሰ ጡር፤ ግጭቱን ሽሽት በጫካ ውስጥ ተደብቃ ሳለ መንታ ልጆቿን ብትገላገልም፤ በህይወት የቆየችው ለጥቂት ቀናት ብቻ ነበር።
የአብርሃ መንታ ልጆች እናቲቱ ይህችን አለም ላታያት ለመጨረሻ ጊዜ መሰናበቷን ባለቤቷ ይናገራል። ልጆቿን ማየት የቻለችው ለአስር ቀናት ብቻ ነበር። ባለቤቷም ልጆቹን በቅርጫት አድርጎ የእርሱ እና የልጆቹን ነፍስ ለማዳን ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደደ። ከመንታ ጨቅላዎቹ በተጨማሪ፣ የአምስት ዓመት ወንድ ልጁን፣ የ14 ዓመቱን የባለቤቱን ወንድም ይዞ ሱዳን ገብቷል፤ በአሁኑ ወቅት በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ይገኛል። መንታ ህፃናቱን አንዲት አሜሪካዊት ዶክተር ለመርዳት እየሞከረች ነው። በትግራይ ክልል የተቀሰቀሰው ግጭት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ነዋሪን አፈናቅሏል። 60 ሺህ የሚሆኑት ጨርቄን፣ ማቄን ሳይሉ ወደ ሱዳን ሸሽተዋል። እያንዳንዱ ተፈናቃይ የሚናገረው ታሪክ አለው፤ መጀመሪያ ጥይት ሲተኮስ የተሰማቸው ስሜት፣ በአየር ድብደባው ወቅት ዋሾች ውስጥ መደበቅ፣ ጥይት የተተኮሰባቸው፣ የተደፈሩ እንዲሁም ሌሎች ታሪኮችን በውስጣቸው አምቀው ይዘዋል። በርካቶቹ ለቀናት ያህል ያለ ምግብና ውሃ በእግራቸው ተጉዘው በፅናት የደረሱበትንም ያወሳሉ። ባለቤቱን ያጣው አብርሃ ክንፈ ዕድሜየ አርባ ነው። የቀድሞ ባለቤቴ ደግሞ 29። ከባለቤቴ ጋር የተጋባነው ከ13 አመታት በፊት ነው፤ በትዳራችን ሶስት ልጆች አፍርተናል። መኖሪያችን በምዕራብ ትግራይ ማይካድራ ከተማ አቅራቢያ አካባቢ ባለ የእርሻ መሬት ነው። በግጭቱ ክፉኛ የተጎዳው የምዕራብ ትግራይ አካባቢ እለቱ ማክሰኞ ህዳር 1፣ 2013 ዓ.ም ነበር፤ የፌደራሉ ሠራዊት በአካባቢያችን የመጡበት እለት። ወታደሮቹን የኛን ቤት አለፉት። አላዩንም ነበር። ትልቅ እፎይታ ተሰማን። በዚህ አጋጣሚ ከቤታችን ወጥተን በቤታችን አካባቢ በሚገኝ ጫካ ውስጥ ከአራት ጎረቤቶቻችን ጋር ተደበቅን። ባለቤቴ በምጥ ተያዘች፤ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ከፍተኛ ህመም ይሰማት ጀመር። ማይካድራ የሚገኘው ክሊኒክ ለመውሰድ ፈራሁ። አምላክ የተመሰገነ ይሁንና ባለቤቴ አብራን ተደብቃ በነበረች ሴትዮ እርዳታ መንታ ሴት ልጆችን ተገላለለች። በዚያኑ ቀን ወደ ቤት ተመለስን። ያለመታደል ሆኖ ባለቤቴ ለታይ፤ ከወሊድ በኋላ ህክምና ማግኘት አልቻለችም። የሚፈሳትን ደም ለማስቆም የሚያስፈልጋትን መርፌም ባለመወጋቷ ሁኔታዋ እየከፋ መጣ። ከአስር ቀናት ስቃይ በኋላ አረፈች። ኃዘኑ ልቤን እንዴት እንደሰበረው በቃላት መግለፅ አልችልም። በአራት ጎረቤቶቼ እርዳታ እዛው እርሻ ቦታችን ላይ ቀበርናት። ክሊኒክ ምነው በወሰድኳት ብዬ እመኛለሁ ነገር ግን በወቅቱ ከተማዋ ግልብጥብጧ የወጣበት ነዋሪዎች ነፍሳቸውን ለማትረፍ እግሬ አውጭኝ የሚሉበት ወቅት ነበር። እስካሁን ድረስ ከተማዋ ምድረ በዳ እንደሆነች ነው። ከአምስት አመታት በፊት ከቤተሰቦቼ ጋር ከአማራ ክልል፣ መተማ ከተማ በብሔር ግጭት ምክንያት ነው ተፈናቅለን ወደ ማይካድራ የመጣነው። ማይካድራ ከመጣን በኋላ ህይወትን ከዜሮ ጀመርን። በአካባቢው መስተዳድር ለእርሻ የሚሆን መሬት ተሰጠን። በመሬታችን ላይ አነስ ያለች የጭቃ ቤት ገነባን። ለኔም ለባለቤቴም ምቹ ነበር። ህይወትን መምራት ጀመርን። ወንድ ልጃችን እዚሁ ተወልዶ ነው ያደገው። መንታ ልጆቼ ቢሆኑ እዚህ ነው የተወለዱት፤ ምንም እንኳን የኖሩባት ለሃያ ቀናት ነው እንጂ ባለቤቴ ስትሞት ሰማይና ምድሩ ተገለባበጠብኝ። አቅፌያት አነባሁ፤ አለቀስኩ። ይሄንን ደም አፋሳሽ ጦርነት ጠላሁት፤ ረገምኩት፤ ይህ ነው የማይባል ስቃይ ነው ያመጣብን። የምወዳት ባለቤቴ፣ የልጆቼ እናት የሞተችው ህክምና በማጣቷ ነው። የአማራ ክልል ሚሊሻ ባማይካድራ ሁኔታው አደገኛ ስለነበር፤ ጎረቤቶቼ ወደ ሱዳን ቀድመውኝ ሸሹ። እኔ ከልጆቼና ከባለቤቴ ወንድም ጋር ወደ ኋላ ቀረሁ። ወታደሮቹን ባየናቸው ቁጥር ጫካ ውስጥ እንደበቃለን። ያለ ጎረቤቶቼ እርዳታ መንታዎቹን መንከባከብ ፈተና ሆነብኝ። አራሶች ደግሞ የእናታቸው የጡት ወተት ያስፈልጋቸዋል። በቻልኩት መጠን ውሃ፣ ስኳር በጥብጬ በእጄ እየነከርኩ እንዲጠቡት አደርጋለሁ። እንዲሁ ሾርባ ሲኖር በዚያው መንገድ እየነከርኩ እንዲጠቡት እያደረግኩ በህይወት ለማቆየት ቻልኩኝ። በጣም ሲከብደኝ ከሃያ ቀናት በኋላ በአካባቢው ወደሚገኝ የፌደራል ሰራዊቱ ወደሰፈረበት ቦታ አቀናሁ። ልጆቼን ወደ አቅራቢያው ከተማ ሁመራ ወደሚገኝ ክሊኒክ መውሰድ እችል እንደሆነ ጠየቅኳቸው። ስደተኞች ሱዳን ለመግባት የሚሻገሩት የተከዜ ወንዝ እንደ እድል ሆኖ እንዳልፍ ፈቀዱልኝ፤ ነገር ግን ወደ መተማ ክሊኒክ አልሄድኩም። በእግሬ ወደ ተከዜ ወንዝ ተጓዝኩኝ፤ ከተከዜ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ሱዳኗ ሃምዳይት ተሻገርኩ። መንታዎቹን በቅርጫት ውስጥ ይዤ ነበር። አንደኛው ልጄና የባለቤቴ ወንድም አብሮኝ ነበር። በሃምዳያት የስደተኞች ካምፕ ውስጥ መጠለያ አግኝተናል። በቀይ መስቀል ውስጥ የምትሰራ አንዲት አሜሪካዊት ዶክተር መንታዎቹን እየተንከባከበቻቸው ነው። የሚያስፈልጋቸውን ነገር ሁሉ ታደርጋለች፤ ዕድገታቸውን በየሶስት ቀኑ ትከታተላለች። መቼም ለኔም ሆነ ለሌሎች ስደተኞች ለሰጠችን ድጋፍና ላሳየችን ደግነት አምላክ ይባርካት። የመንታዎቹ ክርስትና አሁን መንታዎቹ ሁለት ወር ሆኗቸዋል። አሁን ስጋ ለበስ እያደረጉ ነው። ነገር ግን የአምስት አመት ልጄ እናቱን በጣም ነው የሚናፍቃት፤ በተደጋጋሚ የት ናት እያለ ይጠይቃል። ልብ ይሰብራል። መዋሸቴን ብጠላውም አንድ ቀን አብራን ትሆናለች እለዋለሁ። ለታይ አብራን እንዴት እንዳልሆነች መረዳት ይከብደኛል፤ ይጨልምብኛል። እውነት ነው ህይወት ጨካኝ ናት። እውነቱን ተናገር ከተባልኩ መንታዎቹ ልጆቼ በእቅፌ የሞተችው ባለቤቴን በየጊዜው ያስታውሱኛል። አብረውኝ ያሉት ስደተኞች ሁኔታየን ስለሚያሳዝናቸው ሊያፅናኑኝ ይሞክራሉ። ለመንታዎቹ ልጆቼም ስም አውጥተውላቸዋል። አንደኛዋን ኤደን ብለዋታል፤ ያው የመፅሃፍ ቅዱስን ታሪክ በማጣቀስ እንዴት አዳምና ሔዋን ከኤደን እንደተባረሩ ለማሳየት። ሌላኛዋን ደግሞ ትረፊ ብለዋታል። መትረፏ ያው የአምላክ ተአምር ነው። በትግርኛ ደግሞ ቆይ (ኑሪ) እንደማለት ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት መሰረት ሴት ልጆች በ80 ቀናቸው ክርስትና ይነሳሉ። አሁን የክርስትና ቀናቸው እየተቃረበ ነው። በስደተኞቹ ካምፕ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የለም። ሃዘኔ፣ ህመሜ ጥልቅ ነው። ለአምላኬ በየጊዜው የምፀልየው ዋነኛ ጉዳይ ጥንካሬ ሰጥቶኝ ልጆቼን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ እንዳሳድግ ነው። ይሄ አሰቃቂ ጦርነት ባለቀና ህይወትን ካቆምንበት ብንቀጥል እያልኩ ተስፋ አደርጋለሁ። ለምንድን ነው ሰላምና ደህንነታችን እንዲህ የተነጠቅነው እያልኩ ከራሴ ጋር እታገላለሁ። ለምንስ እንዲህ እንሰቃያለን? ሃዘኑና ስቃዩን ያስከተሉብን ሰዎች በምቾትና ተረጋግተው እየኖሩ እኛ ለምን በደህና እንዳንኖር ተፈረደብን? ለምን ተካድን? እነሱ ያለምንም ችግርና ውጣ ውረድ ልጆቻቸውን እያሳደጉ ነው። ልጆቻቸው በሞቀ ቤታቸው እየተደሰቱ ነው። ቤተሰቦቻቸው ይንከባከቧቸዋል፤ ትምህርት ቤት ይሄዳሉ፤ ሰፈር ይጫወታሉ። ጥልቅ ኃዘን ነው የሚሰማኝ ከመተማ ተፈናቅዬ ወደ ማይካድራ የመጣሁበትን በሃሳብ አምስት አመት ወደ ኋላ እሄዳለሁ። በማህበረሰቡ ውስጥ ተቀባይነትን ለማግኘት፤ ኑሮን ለማሸነፍ ከጥዋት እስከ ማታ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳልል ነበር የጣርኩት። ይሄ ሁሉ ቤተሰቦቼን ለመደገፍ ነው። የተሰጠኝን የእርሻ መሬት ብቻ ሳይሆን የበለጠ ጉርስ ለማግኘት ሌሎች መሬቶች ተከራይቼ አርስ ነበር። ጥሩ ሰሊጥና ማሽላ አመርት ነበር። በስደት ይኸው አለው ምንም የምሰራው ነገር ሳይኖር፤ ያለ መሬት፣ ያለ ባለቤቴ፣ ያለ ማህበረሰቤ እንዲሁም የምሄድበት ቤተ ክርስቲያን በሌለበት፤ ተነቅዬ አለሁ። በትግራይ ግጭት ወደ ሱዳን ከተሰደዱ ተፈናቃዮች መካከል ስለ ምርቴ፤ እሰበስበው ስለነበረው እህል አስባለሁ። ምርቴን የመሰብሰቢያ ወቅት ነበር። ምን ማድረግ እችላለሁ? በትዝታና በሃሳብ መኖር እንጂ፤ የነበረንን ንብረት፣ ህይወት እንዴት እንደነበር፣ልጆቼ እንዴት በደስታ ይቦርቁና ይጫወቱ እንደነበር አስብና ከስደተኝነት ህይወቴ ለመላመድ እታገላለሁ። ኃዘኔ ጥልቅ ነው፤ ልጆቼ ይኸ አይገባቸውም። የነበረኝ ሁሉ ተወሰደብኝ፤ አጣሁ! ትርጉም በሌለው የብሔር ግጭት ምክንያት። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በሱዳን ካምፖች ይገኛሉ፤ ሁላችንም ከትግራይ ነን። በግጭቱ ምን ያህል ክፉኛ እንደተጎዳን ማሳያ ነው። ተስፋዬ ጦርነቱ በቅርቡ እንዲጠናቀቅና ሰላም እንዲሰፍን ነው። ቤታችን ለመመለስ እንናፍቃለን። ወደቀደመ ህይወታችን፤ ወደ አባት፣ አያቶቻችንና ዘሮቻችን መሬት መመለስን እንሻለን። በፌደራል መንግሥቱ እና የትግራይ ክልልን ሲያስተዳድር በነበረው ህወሓት መካከል ለረዥም ጊዜ የዘለቀው አለመግባባት ተካሮ የህወሓት ኃይሎች የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በማለት ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ የፌደራሉን ጦር ወደ ትግራይ ማዝመታቸው ይታወሳል። መንግሥት ሕግ የማስከበር በሚለው ወታደራዊ ዘመቻ ቁጥሩ በትክክል ባይታወቅም በርካቶች ህይወታቸው አልፏል። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ወደ ጎረቤት አገር ሱዳን ተሰደዋል። የትግራይ መዲና የሆነችው መቀለ በፌደራል መንግሥት ሠራዊት ቁጥጥር ስር ከዋለች በኋላ ወታደራዊ ዘመቻው መጠናቀቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ተናግረው ነበር።